You are on page 1of 30

See discussions, stats, and author profiles for this publication at: https://www.researchgate.

net/publication/334591336

Method · January 2009

CITATIONS READS
0 1,593

1 author:

Baye Ayalew
Amhara Regional Agricultural Research Institute
9 PUBLICATIONS   26 CITATIONS   

SEE PROFILE

Some of the authors of this publication are also working on these related projects:

Effects of Inoculation by Bradyrhizobium japonicum Strains on Nodulation, Nitrogen Fixation, and Yield of Soybean (Glycine max L. Merill) Varieties in West Gondar
zone at Metema District, Ethiopia View project

All content following this page was uploaded by Baye Ayalew on 20 July 2019.

The user has requested enhancement of the downloaded file.


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ጎ/ዙሪያ ወረዳ የአካባቢ ዘር የማሽላ ሰብል የማዳበሪያ ሙከራ (2005/6)

የዕቅድ ዝግጅት ቡድን አባላት

1. ባዬ አያሌው ከጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል


2. ዳንኤል ለምለም ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ
3. ሰሎሞን ቁምላቸው ከክልል ግብርና ቢሮ
4. ሙሉጌታ ማሞ ከስሪንቃ ግብርና ምርምር ማዕከል

ጥር- 2009 ዓ.ም


ባህር ዳር

1
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ርዕስ ገጽ

1.ማጠቃለያ ................................................................................................................................ 3

2.መግቢያ ................................................................................................................................... 7

3. መነሻ ሁኔታዎች .................................................................................................................... 8

3.1. የማሽላ ልማት አጠቃላይ ገጽታ ........................................................................................ 8

3.2. በአካባቢው ማሽላን ለማምረት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ................................................ 9

3.3. የማሽላ ልማት ዋናዋና ችግሮች....................................................................................... 10

3.3.1. አካባቢያዊና ስነ-ሕይዎታዊ የምርት ማነቆዎች ........................................................... 10

ሀ. ያልተስተካከለ የዝናብ ስትጭት .......................................................................................... 10

ለ. የአፈር ለምነት መቀነስ ...................................................................................................... 11

ሐ. የማሽላ በሽታና ተባይ ቁጥጥር .......................................................................................... 11

3.3.2 የማሽላ ቴክኖሎጅ ማስተዋወቅና ማስፋት ውስንነቶች .................................................. 12

3.3.3 የአመራርና ባለሙያ ተነሳሽነትና ክህሎት ችግር.......................................................... 12

3.3.4 የአርሶ-አደሩ ቴክኖሎጅን የመቀበል ፍላጎት አናሳ መሆን ............................................. 12

3.3.5 የቅንጅት ችግር ......................................................................................................... 12

3.3.6 የተሻሻሉ ቀላል የእርሻ መሳሪያዎች እጥረት ............................................................... 12

4. የተሻሻሉ የማሽላ ቴክኖሎዎችን የማስተዋወቅና የማስፋት ልምድ ............................................. 13

5. የ2009/10 ምርት ዘመን የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማት ዕቅድ ዓላማ እና ግብ ................... 13

6. ቁልፍ ተግባራት.................................................................................................................... 14

6.1 ዋና ዋና የማሽላ አብቃይ ቀበሌዎችን መለየት ................................................................... 14

6.2. የማሽላ ቴክኖሎጅዎችን ማስተዋወቅና ማስፋት................................................................. 16

6.3 የማሽላ ልማት ፓኬጅ ስልጠና መስጠት ........................................................................... 16

7. ዓብይ ተግባራት .................................................................................................................... 17

2
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

7.1 በዝግጅት ምዕራፍ ........................................................................................................... 17

7.2. በተግባር ምዕራፍ ........................................................................................................... 17

7.3 የማጠቃለያ ምዕራፍ ........................................................................................................ 18

8. የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት .................................................................................... 18

8.1 ግብርና ቢሮ .................................................................................................................... 19

8.5 የምርምር ማዕከላትና ዩንቨርሲቲዎች ................................................................................ 21

8.6 ዘር አባዥ ድርጅቶች ....................................................................................................... 22

8.7 የዕጽዋትና የሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ..................................... 22

8.8 የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጄንሲ ................................................................................... 22

8.9 በየደረጃው የሚገኙ የህብረት ስራ ማ/ማ/ጽ/ቤቶች .............................................................. 23

8.10 በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት ................................................................................ 23

8.11 የገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒዬኖችና የህብረት ስራ ማህበራት ............................................. 23

8.12 አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም .......................................................................................... 24

9. የሚያስፈልግ ግብዓት ............................................................................................................ 24

11. የሚያስፈልግ በጀት ............................................................................................................. 26

11.1. ለግብዓት መግዣ የሚያስፈልግ በጀት ............................................................................ 26

11.2. ለስልጠና፤ ክትትልና ድጋፍ የሚያስፈልግ በጀት ............................................................ 27

13. የማሽላ ልማት ዕቅድ የጊዜ ሰሌዳ ......................................................................................... 29

ሠንጠረዥ ማውጫ

ሠንጠረዥ-1፡ የተመረጡ ዋናዋና የማሽላ አብቃይ ቀበሌዎች ብዛትና የማሽላ ልማት ዕቅድ ............. 16

ሠንጠረዥ-2፡ በ2009/2010 ምርት ዘመን በማሽላ ልማት ፓኬጅ የሚሳተፉ ሰልጣኞች .................. 17

ሠንጠረዥ-3፡ በ2009/2010 የምርት ዘመን ለታቀዱ የማሽላ ልማት ስራዎች የሚያስፈልግ የግብዓት
ዓይነትና መጠን ......................................................................................................................... 24

ሠንጠረዥ-4፡- በ2009/2010 የምርት ዘመን የታቀደ የማሸላ ልማት የበጀት መጠን ....................... 26

3
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ሠንጠረዥ-5፡- በማሽላ ሰብል ልማት ፓኬጅ ለስልጠናው የሚያስፈልግ በጀት (በብር) ..................... 27

ሠንጠረዥ-6፡ የ2009/2010 የማሽላ ልማት ዕቅድ የሚያሰፈልግ ጠቅላላ በጀት .............................. 28

10. አዲሱ የዓፈር ንጥረ-ነገር እጥረት አመላካች ሰንጠረዥ......................................................... 25

ምስል ማውጫ

ምስል-1 በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በተመሳሳይ ጊዜ የተዘራ የማሽላ ማሳ በልማዳዊ አሰራርና የተሻሻለ
አሰራር መካከል ያለው የመድረሻ ጊዜ ልዩነት ሲታይ ..................................................................... 9

ምስል-2 ማሽላ የሚመረትባቸው ወረዳዎች .................................................................................. 15

ግራፍ ማውጫ
የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የዝናብ ስረጭትና መጠን የሚያሳይ ግራፍ ................................................... 11

4
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

1.ማጠቃለያ

ማሽላ ምርታማ ከሚባሉ የብርዕና አገዳ ሰብሎች መካከል አንዱ ሲሆን ከአጠቃይ ከሃገሪቱ የሰብል
ሽፋን ሲታይ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታቲስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት በመጀመሪያው አምስት
ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መጨረሻ በሆነው 2008/2009 የምርት ዘመን
በሃገሪቱ በሰብል ከተሸፈነው 12.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ የአማራ ክልል 4.4 ሚሊዮን
ሄክታር (35.35%) ድርሻ አለው፡፡ በሰብል ምርት ረገድ በሃገሪቱ ከተመረተው 288 ሚሊዮን ኩንታል
ውስጥ በአማራ ክልል 93 ሚሊዮን ኩንታል (32.2%) ተመርቷል።በሃገራችን የማሽላ ምርት መጠን
በዓመት እስከ 47 ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ ሲሆን በአማራ ክልል እስከ 15 ሚሊዮን ኩንታል
ይመረታል፡፡ማሽላ የአየር ለውጥን የሚቋቋም፤ ከፍተኛ ምርት ከሚሰጡ የብርዕና የአገዳ ሰብሎች፤
ከ400 እስከ 2,500 ሜትር ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ሊመረት የሚችል ሰብል ሲሆን ሌሎች የብርዕና
የአገዳ ሰብሎች መብቀል በማይችሉበት ዝቅተኛ የእርጥበትና ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመብቀልና
ምርት በመስጠት ተወዳዳሪ የሌለው ሰብል በመሆኑ የምግብ ዋስትና ሰብል በመባልም ይታወቃል፡፡
ማሽላ በሰ/ጎንደር ዞን ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በስፋት የሚመረት ቢሆንም ምርታማነቱ
ከሰብሉ የምርታማነት አቅም ጋር ሲነፃፀር በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ማሽላ ከፍተኛ ምርታማ
ከሚባሉ የአገዳ ሰብሎች አንዱ ቢሆንም የማሽላን ምርታማነት ሊጨምሩ የሚችሉ አዳዲስ አሰራሮችና
የአመራረት ምክረ-ሃሳቦች ወደ አርሶ-አደሩ በሚፈለገው መጠንና ፍጥነት ሊገቡ አልቻሉም፡፡
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የክልሉን የሰብል ምርትና ምርታማነት በማሻሻል የአርሶ-አደሩን የምግብ
ዋስትና ለማረጋገጥ ሰፊ የቴክኖሎጂ የማስተዋወቅና የማስፋት ሥራ ቢሰራም የስርፀት ደረጃው
የሚፈለገውን ያህል አይደለም፡፡ ለዚህም የነበረው የሰብል ልማት አሰራር በጥቅል ዕቅድ ላይ
የተመሠረተ መሆኑ ለዋናዋና ሰብሎች የተሰጠው ትኩረት አናሳ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በአንድ
አካባቢ በሚበቅሉ ሰብሎች ላይ የኤክስቴንሽን ሥራ መስራት ከሃብት አጠቃቀምና ውጤታማነት
አንፃር ምርታማ ሊያደርግ ስለማይችል በዋና ዋና ሰብሎች ላይ ሰብል-ተኮር የኤክስቴንሽን ስራ
መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህ የማሽላን ልማትን ለማሻሻል ከጥቅል ዕቅድ ወጥተን
ለየአካባቢው ተስማሚ የሆኑ አሰራሮችን በመቀመር የማሽላን ምርትና ምርታማነት መጨመር
ያስፈልጋል፡፡

በክልሉ በሰ/ጎንደር ዞን በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ ማሽላ አብቃይ ቀበሌዎችን
በመለየት የማሽላን ምርትና ምርታማነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ በምርምር የተሰሩ ምክረ-ሃሳቦችና

5
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ቴክኖሎጂዎችን በመቀመርና በማስተዋወቅ ማሽላን በስፋትና በጥራት ማምረት ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ
በ2009/2010 የምርት ዘመን በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ 52 ዋና ዋና የማሽላ
አብቃይ ቀበሌዎች በመለየት ሃይልን አሟጦ የአካባቢ ዝርያን ከሙሉ የአሰራር ማዕቀፉ ጋር

በማቀናጀት 35022 አርሶ-አደሮችን በማሳተፍና በማሰልጠን በ8755 ሄክታር መሬት ላይ ሰፊ

የኤክስቴንሽን ስራ ይሰራል፡፡እንዲሁም ሌሎች 9 የማሽላ አብቃይ ወረዳዎች በመደበኛ የኤክስቴንሽን

ማዕቀፍ ይሸፈናሉ፡፡ ዕቅዱን ለማከናወን ለግብዓት፤ስልጠና፤ክትትልና ግምገማ 36,198,330ብር

በጀት ያስፈልጋል፡፡

6
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

2.መግቢያ

ማሽላ ምርታማ ከሚባሉ የብርዕና አገዳ ሰብሎች መካከል አንዱ ሲሆን ከአጠቃይ ከሃገሪቱ የሰብል
ሽፋን ሲታይ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ የስታቲስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ መሠረት በመጀመሪያው አምስት
ዓመታት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን መጨረሻ በሆነው 2008/2009 የምርት ዘመን
በሃገሪቱ በሰብል ከተሸፈነው 12.6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ውስጥ የአማራ ክልል 4.4 ሚሊዮን
ሄክታር (35.35%) ድርሻ አለው፡፡ በሰብል ምርት ረገድ በሃገሪቱ ከተመረተው 288 ሚሊዮን ኩንታል
ውስጥ በአማራ ክልል 93 ሚሊዮን ኩንታል (32.2%) ተመርቷል።
በሃገራችን የማሽላ ምርት መጠን በዓመት እስከ 47 ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ ሲሆን በአማራ ክልል
እስከ 15 ሚሊዮን ኩንታል ይመረታል፡፡
ማሽላ የአየር ለውጥን የሚቋቋም፤ ከፍተኛ ምርት ከሚሰጡ የብርዕና የአገዳ ሰብሎች፤ ከ400 እስከ
2,500 ሜትር ከፍታ ከባህር ወለል በላይ ሊመረት የሚችል ሰብል ሲሆን ሌሎች የብርዕና የአገዳ
ሰብሎች መብቀል በማይችሉበት ዝቅተኛ የእርጥበትና ከፍተኛ የሙቀት መጠን በመብቀልና ምርት
በመስጠት ተወዳዳሪ የሌለው ሰብል በመሆኑ የምግብ ዋስትና ሰብል በመባልም ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ማሽላ ለምግብ ፍጆታ (እንጀራና ንፍሮ)፤ ለባህላዊና ዘመናዊ መጠጥ (ጠላ፣ አረቂና ቢራ)
ለእንስሳት መኖና ማገዶ አገልግሎት ይውላል፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የክልሉን የሰብል ምርትና ምርታማነት በማሻሻል የአርሶ-አደሩን የምግብ
ዋስትና ለማረጋገጥ ሰፊ የቴክኖሎጂ የማስተዋወቅና የማስፋት ሥራ ቢሰራም የስርፀት ደረጃው
የሚፈለገውን ያህል አይደለም፡፡ ለዚህም የነበረው የሰብል ልማት አሰራር በጥቅል ዕቅድ ላይ
የተመሠረተ መሆኑ ለዋናዋና ሰብሎች የተሰጠው ትኩረት አናሳ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በአንድ
አካባቢ በሚበቅሉ ሰብሎች ላይ የኤክስቴንሽን ሥራ መስራት ከሃብት አጠቃቀምና ውጤታማነት
አንፃር ምርታማ ሊያደርግ ስለማይችል በዋና ዋና ሰብሎች ላይ ሰብል-ተኮር የኤክስቴንሽን ስራ
መስራት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህ የማሽላን ልማትን ለማሻሻል ከጥቅል ዕቅድ ወጥተን
ለየአካባቢው ተስማሚ የሆኑ አሰራሮችን በመቀመር የማሽላን ምርትና ምርታማነት መጨመር
ያስፈልጋል፡፡

የዚህ ሰነድ ዋና ዓላማም በክልሉ በሰ/ጎንደር ዞን በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ ማሽላ
አብቃይ ቀበሌዎችን በመለየት የማሽላን ምርትና ምርታማነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ በምርምር የተሰሩ
ምክረ-ሃሳቦችና ቴክኖሎጂዎችን በመቀመርና በማስተዋወቅ ማሽላን በስፋትና በጥራት ማምረት ነው፡፡
7
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ስለዚህ በ2009/2010 የምርት ዘመን በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ 52 ዋና ዋና የማሽላ
አብቃይ ቀበሌዎች በመለየት ሃይልን አሟጦ የአካባቢ ዝርያን ከሙሉ የአሰራር ማዕቀፉ ጋር

በማቀናጀት 35022 አርሶ-አደሮችን በማሳተፍና በማሰልጠን በ8755 ሄክታር መሬት ላይ ሰፊ

የኤክስቴንሽን ስራ ይሰራል፡፡

3. መነሻ ሁኔታዎች
3.1. የማሽላ ልማት አጠቃላይ ገጽታ

በአማራ ክልል ማሽላ አምራች ከሆኑ ወይናደጋ አካባቢዎች በዋናነት ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች
ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህም አካባቢዎች በአብዛኛው በቂ የዝናብ መጠን ስለሚያገኙ ለዳግም ሰብል ልማትና
ለሌሎች ሰብሎችም ማለትም ጤፍ፤ ሽምብራ፤ ስንዴ፤ በቆሎ፤ ገብስና ባቄላ ተስማሚ ናቸው፡፡ ምንም
እንኳን ማሽላ በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ቢኖረውም የአካባቢው አርሶ-አደር ማሽላን
የጉልበትና ግብዓት ወጭን ቆጣቢ ሰብል አድርጎ በማሰብ ማሳ ዝግጅት አረምና ኩትኳቶ እንዲሁም
ግብዓት አጠቃቀም ላይ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ ነው፡፡ የአካባቢን ማሽላ ዝርያ ለማምረት በልማዳዊ
አሰራር በአማካኝ ከ270 ቀናት በላይ ይወስዳል ፡፡ የአካባቢውን የማሽላ ዝርያ ምርትና ምርታማነት
ለማሳደግ የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የማዳበሪያ መጠንና አሰራርን በማሻሻል የሰብሉን
የመድረሻ ጊዜ በአማካይ ከ270 ቀናት ወደ 180 ቀን በመቀነስ ምርታማነቱ በልማዳዊ አሰራር ከ18-22
ኩንታል በሄክታር የነበረውን በተሻሻለ አሰራር ከ40-47 ኩንታል በሄክታር ማድረስ ተችሏል፡፡

8
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

1 ምስል-1 በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በተመሳሳይ ጊዜ የተዘራ የማሽላ ማሳ በልማዳዊ አሰራርና የተሻሻለ
አሰራር መካከል ያለው የመድረሻ ጊዜ ልዩነት ሲታይ
የአካባቢ ዘር የማሽላ ሰብል በልማዳዊ የአካባቢ ዘር የማሽላ ሰብል
አሰራር (2015) በተሻሻል አሰራር(2015)

3.2. በአካባቢው ማሽላን ለማምረት የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች


ማሽላን በስፋት ለማምረትና ምርታማነቱን አሁን ካለበት የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ ምቹ
ሁኔታዎች

o አካባቢው ለማሽላ ልማት ምቹ የሆነ ስነ-ምህዳር ያለው መሆኑ፤

o ከክልል እስከ ቀበሌ ድረስ የማሽላ አመራረትን በተመለከተ የኤክስቴሽን ምክር አግልግሎት
ሊሰጡ የሚችሉ ተቋማትና ባለሙያዎች መኖራቸው፤

o የማሽላን ምርታማነት ሊያሻሽሉ የሚችሉ አዳዲስ አሰራሮች ያሉ መሆኑ፣

o ለግብዓት መግዣ የሚውል ብድር የሚሰጡ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት መኖራቸውና

o የክልሉ መንግስት ማሽላን በስፋትና በጥራት ለማምረት የሰጠው ትልቅ ትኩረት ዋና ዋናዎቹ
ናቸው፡፡

9
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ማሽላ በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በስፋት የሚመረት ቢሆንም ምርታማነቱ ከሰብሉ
የምርታማነት አቅም ጋር ሲነፃፀር በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ማሽላ ከፍተኛ ምርታማ ከሚባሉ
የአገዳ ሰብሎች አንዱ ቢሆንም የማሽላን ምርታማነት ሊጨምሩ የሚችሉ አዳዲስ አሰራሮችና
የአመራረት ምክረ-ሃሳቦች ወደ አርሶ-አደሩ በሚፈለገው መጠንና ፍጥነት ሊገቡ አልቻሉም፡፡

3.3. የማሽላ ልማት ዋናዋና ችግሮች

3.3.1. አካባቢያዊና ስነ-ሕይዎታዊ የምርት ማነቆዎች


ሀ. ያልተስተካከለ የዝናብ ስትጭት
ለማሽላ እደገትና ምርት ከ400ሚ.ሜ-800ሚ.ሜ የተስተካለ የዝናብ ስርጭት እንደሚያስፈልግ የተለያዩ
የምርምር ሪፖርቶች ያስረዳሉ፡፡ የደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የዝናብ መጠን በአማካይ
1052ሚ.ሜ የሚደርስ ቢሆንም የዝናብ ስርጭቱ በአንድ ወቅት በዝቶ ሌላ ጊዜ የሚያንስበት ሁኔታ
ይስተዋላል፡፡ ለዚህም ሐምሌና ነሃሴ ከፍተኛ የሆነ ዝናብና እርጥበት ያለ መሆኑና በሌላ በኩል
ከመስከረም እስከ ጥቅምት አጋማሽ የዝናብ እጥረት መኖሩን ለረጅም ጊዜ የተሰበሰበ የሜትሮሎጅ
መረጃ ያሳያል፤፤

በመሆኑም ማሽላ እርጥበት በሚበዛበትና በሚያንስበት ወቅት እድገቱ የሚገታ ሲሆን ለፍሬ
በሚደርስበት ወቅት የእርጥበት እጥረት ከተከሰተ የማሽላው ራስና የዘር መጠንን በመቀነስ ምርትና
ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይፈጥራል፡፡

ለዚህም ከፍተኛ ዝናብ በሚኖርበት ወቅት ትርፍ ውሃን ማስወገድና ዕጥረት ይኖራል ተብሎ
በሚታሰብበት ጊዜ ቀድሞ ታይ ማድረግ የማሽላን ምርትና ምርታማነት ሊጨምር እንደሚቻል
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የተሰራ ጥናት ሪፖርት ያስረዳል፡፡ በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል የተሰራ
የአፈር እርጥበት ቁጥጥረ ጥናት እንደሚያመለክተው ማሽላ በተዘራ በ3ኛው ሳምንት ሪጅ መስራትና
በ6ኛው ሳምንት ታይ በማድረግ የማሽላን ምርት 49 ኩንታል በሄክታር ማድረስ ተችሏል፡፡

10
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ የዝናብ ስረጭትና መጠን የሚያሳይ ግራፍ

R.F
mm

ለ. የአፈር ለምነት መቀነስ


አካባቢው ለረጅም ጊዜ መታረሱና የልቅ-ግጦሽ መዘውተር ለአፈር ለምነት መቀነስ ዋና ምክንያት
ሆኗል፡፡ በመሆኑም በአፈር ለምነት መቀነስ ምክንያት የማሽላ ምርታማነት ዝቅተኛ መሆን የራሱ
የሆነ አስተዋፅዖ ያለው ሲሆን የተሻሻሉ ምክረ-ሃሳቦችን በመጠቀም የማሽላን ምርትና ምርታማነት
ማሻሻል ይቻላል፡፡ ለዚህም በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል በማሽላ ላይ የተሰራውን የማዳበሪያ
መጠን ምክረ-ሃሳብን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡

ሐ. የማሽላ በሽታና ተባይ ቁጥጥር


ማሽላ በተለያየ በሽታና ተባይ የሚጠቃ ሲሆን የማሽላ ምርታማነትና ጥራትን ሊቀንሱ የሚችሉ
በሽታና ተባዮችን በተቀናጀ የተባይ መከላከል ስልት መቆጣጠር የማሽላን ምርታማነትና ጥራት
ሊያሻሽል እንደሚችል የምርምር ውጤቶች ያስረዳሉ፡፡ የማሽላ ሰብልን በተለያዩ የዕድገት ደረጃዎች
የሚያጠቁ ነፍሳት ተባዮች ያሉ ሲሆን ዋናዋናዎቹ አገዳ-ቆርቁር፤ የማሽላ ጥንዚዛና ወፍ ናቸው፡፡
የመጋዘን ተባዮች ምርት ከተሰበሰበ በኋላ የሚከሰቱ ሲሆን ዋናዋናዎቹ የመጋዘን ተባዮች ነቀዝ፣
አይጥና ሻጋታ ናቸው፡፡

11
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

3.3.2 የማሽላ ቴክኖሎጅ ማስተዋወቅና ማስፋት ውስንነቶች


በርካታ የማሽላ አመራረት አግሮኖሚዊ ምክረ-ሃሳቦች (ማሳ ዝግጅት፣ በመስመር መዝራት፣ ማዳበሪያ
አጠቃቀም፣ ታይሪጅንግ፣ አረምና ኩትኳቶ) ቢኖሩም በወቅቱና በአግባቡ ጥቅም ላይ ባለመዋላቸው
አርሶ-አደሩ ከልማዳዊ አሰራር ሊላቀቅ አልቻለም፡፡ ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው የግብርና
ኤክስቴንሽኑ አዳዲስ አሰራሮችን በአርሶ-አደር ማሳና ሰርቶ ማሳያ ጣቢያዎች በመሞከር
ስለቴክኖሎጅው አጠቃቀምና ጠቀሜታ የማስተዋወቅና የማስፋት ስራ ውስንነት አለበት፡፡

3.3.3 የአመራርና ባለሙያ ተነሳሽነትና ክህሎት ችግር


በየደረጃው ያለ አመራር የማሽላ እቅድን ትኩረት በመስጠት በአግባቡ እንዲተገበር አለማድረግና
ሂደቱን በጊዜው አለመከታተል፤ እንዲሁም ስለማሽላ አመራረት ቴክኖሎጅ ውስን የሆነ ክህሎት
መኖርና ልማዳዊ አሰራር መከተል ይስተዋላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በየደረጃው ያለ የግብርና ባለሙያ
የታቀደውን የማሽላ ልማት እቅድ አርሶ-አደሩ በአግባቡ እንዲፈፅም ድጋፍና ክትትል አለማድረግና
የተወሰነውም ባለሙያ የክህሎት ችግር በመኖሩ የአርሶ-አደሩ አመለካከት ሊለወጥ አልቻለም፡፡

3.3.4 የአርሶ-አደሩ ቴክኖሎጅን የመቀበል ፍላጎት አናሳ መሆን


የአካባቢው አርሶ-አደር ማሽላን የጉልበትና ግብዓት ወጭን ቆጣቢ ሰብል አድርጎ በማሰብ ማሳ ዝግጅት
አረምና ኩትኳቶ እንዲሁም ግብዓት አጠቃቀም ላይ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ ነው፡፡ በመሆኑም
የአካባቢን ማሽላ ዝርያ በልማዳዊ አሰራር ማለትም ያልተዘጋጀ ማሳ መጠቀም፣ በብተና መዝራት፣
በወቅቱ አለማረምና ታይሬጅ አለመጠቀም፡፡በተጨማሪም በግብርና ኤክስቴንሽንና በአርሶ-አደሩ መካከል
ያለው የቴክኖሎጅ ቅብብሎሽ የተቀላጠፈ አለመሆኑና የአርሶ-አደሩ በቴክኖሎጅዎች ጠቀሜታ ላይ
መጠራጠርና ታካችነት ነው፡፡ ስለዚህ የተገኙ የምርምር ውጤቶችን በተቀናጀ መልኩ ለአርሶ-አደሩ
ማስተዋወቅና አርሶ-አደሩም ቴክኖሎጅውን በመጠቀም ምርትና ምርታማነቱን ማሻሻል ይኖርበታል፡፡

3.3.5 የቅንጅት ችግር


የማሽላ ልማት የሚመለከታቸው ተቋማት በተናጠል ማቀድ መፈፀምና መገምገም እንዲሁም የግብርና
ኤክስቴንሽኑ ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ያለው ግንኙነት ጠንካራ አለመሆንና አለመናበብ የማሽላ
ቴክኖሎጅዎችን በሚፈለገው መጠንና ፍጥነት ለተጠቃሚ አርሶ-አደሮች የማድረስ ውስንነት ይታያል፡፡

3.3.6 የተሻሻሉ ቀላል የእርሻ መሳሪያዎች እጥረት


በብሔራዊና ክልል ግብርና ሜካናይዜሽን ምርምር ማዕከላት የተወሰኑ ቀላል የእርሻ መሣሪያዎች
ለምርት አገልግሎት እንዲውሉ የተመከረ ቢሆንም በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፤ ማኅበራዊና ቴክኒካዊ
ችግሮች ምክንያት በስፋት ወደተጠቃሚ አርሶ-አደር ሊደርስ አልቻለም፡፡ የማሽላ ምርትና
12
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ምርታማነትን ለማሻሻል በመስመርና በተክል መካከል ያለውን ርቀት ጠብቆ መዘራት አስፈላጊ ቢሆንም
አርሶ-አደሩ ማሽላን በብተና ሲዘራ ይታያል፡፡

4. የተሻሻሉ የማሽላ ቴክኖሎዎችን የማስተዋወቅና የማስፋት ልምድ


በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል በ2005/2006 እና 2006/2007 የምርት ዘመን በአርሶ-አደር ማሳ
በተሞከረ የማዳበሪያ መጠንና የአፈር እርጥበት ቁጥጥር ስራ የአካባቢን የማሽላ ዝርያ ምርታማነት 47
ኩንታል በሄክታር ማድረስ ተችሏል፡፡ ከላይ በሙከራ የተገኘውን ውጤት ለማስፋት በ2008/2009
የምርት ዘመን በጎንደር ዙሪያ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ 30 አርሶ-አደሮች በማሳተፍ በ10
ሄክታር መሬት ላይ ተሞክሮ የተሻሻለው አሰራር በአማካይ 40 ኩንታል በሄክታር የተገኘ ሲሆን
በልማዳዊ አሰራር 20 ኩንታል በሄክታር ተመርቷል፡፡ ተሞክሮውን በወረዳና አግሮኢኮሎጅ ደረጃ
ለማስፋት የሚመለከታቸው የዞንና ወረዳ አመራርና ባለሙያዎች፣ ማሽላ አምራች ቀበሌዎች
አመራር፣ ባለሙያዎችና ግንባር ቀደም አርሶ-አደሮች በተገኙበት የመስክ በዓል ቀን ተዘጋጅቷል፡፡
ስለዚህ ይህንን ልምድ በመቀመርና በላቀ ሁኔታ በመፈፀም የማሽላን ምርትና ምርታማነት መጨመር
ያስፈልጋል፡፡

5. የ2009/10 ምርት ዘመን የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማት ዕቅድ ዓላማ እና ግብ


በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ ማሽላ አምራች አርሶ-አደሮች

በምርምር የተገኘውን ምክረ-ሃሳብ ተጠቅመው ማሽላን በስፋትና በጥራት

እንዲያመርቱና ዘላቂ የሆነ የግብይት ስርዓት በመዘርጋት ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ

ግብ 1፡

በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የሚገኙ ማሽላ አምራች አርሶ- አደሮች የአካባቢ ዝርያን
ከሙሉ የአመራረት ማዕቀፉ ጋር በመጠቀም የማሽላን ምርታማነት በአማካይ ወደ 40 ኩንታል
በሄ/ር ማድረስ፡፡

13
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ግብ 2፡

በምርት ዘመኑ በሁለቱም ወረዳዎች ከሚመረተው 332,690 ኩ/ል በክላስተር 68,863 ኩ.ል
በመደበኛ የማሽላ ምርት ውስጥ 53,217 ኩ/ል (13%) የሚሆነውን ለገበያ በማቅረብ ዋና የማሽላ
ምርት ገዥ ድርጅቶች እንዲገዙት በማድረግ አምራች አ/አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ፣

6. ቁልፍ ተግባራት
6.1 ዋና ዋና የማሽላ አብቃይ ቀበሌዎችን መለየት
በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በርካታ ቀበሌዎች ማሽላን የሚያበቅሉ ቢሆንም ከአጠቃላይ 75
ቀበሌዎች ውስጥ የተሻለ የማምረት አቅም ያላቸው 52 ቀበሌዎች የተለዩ ሲሆን የኤክስቴንሽን
አደረጃጀቱን በመጠቀም የማሽላ ልማትን በተሻሻል አሰራር በስፋትና በጥራት እንዲያመርቱ ይደረጋል፡፡

14
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ምስል-2 ማሽላ የሚመረትባቸው ወረዳዎች

15
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ሠንጠረዥ-1፡ የተመረጡ ዋናዋና የማሽላ አብቃይ ቀበሌዎች ብዛትና የማሽላ ልማት ዕቅድ

ዞን ወረዳ ቀበሌ በአካባቢ ዝርያና ተሳታፊ አርሶአደሮች ብዛት


ብዛት በተሻሻለ አሰራር
የሚሸፈን ጥቅል ወንድ ሴት ድምር
የመሬት ስፋት
(ሄ/ር)
ሰ/ጎንደር ጎንደርዙሪያ 25 4294 12710 4466 17176

ደንቢያ 27 4461 13206 4640 17846

ድምር 52 8755 25916 9106 35022

6.2. የማሽላ ቴክኖሎጅዎችን ማስተዋወቅና ማስፋት


ምንም እንኳን የአካባቢ የማሽላ ዝርያዎች ምርት ለመስጠት ረጅም ጊዜ የሚወስዱ ቢሆንም አርሶ-
አደሮች የአካባቢ የማሽላ ዝርያዎችን እያመረቱ ይገኛሉ፡፡ የአካባቢ የማሽላ ዝርያዎችን ምርታማነት
ለማሻሻል የተሻሻሉ አግሮኖሚያዊ ማዕቀፎችን (ማዳበሪያ መጠቀም፤ በመስመር መዝራት፤ እርጥበት
ዕቀባ መጠቀም፤ የተባይ መከላከል ስራ) መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል
ለወይናደጋ አካባቢዎች በተለይ ለጎንደር ዙሪያና ደምቢያ ወረዳዎች የአካባቢ የማሽላ ዝርያን
ምርታማነት ለመጨመር በተደረገው የምርምር ስራ የተሻሻሉ አሰራሮች (አግሮኖሚያዊ ማዕቀፎች)
ተመክረዋል፡፡ ስለዚህ በተመረጡ ዋናዋና የማሽላ አብቃይ ቀበሌዎች 8755 ሄክታር መሬት
(ሠንጠረዥ- 1) 35022 አርሶ-አደሮችን በማሳተፍ በአካባቢ የማሽላ ዝርያና የተሻሻለ አሰራር
ይሸፈናል፡፡

6.3 የማሽላ ልማት ፓኬጅ ስልጠና መስጠት


ማሽላን በዋናነት የሚያለሙ አርሶ-አደሮች ካለባቸው የእውቀትና ክህሎት ውሱንነት የተነሳ የተሻሻሉ
የማሽላ ቴክኖሎጅዎችን በአብዛኛው አይጠቀሙም፤ ለምርት ለመድረስ መስክ ላይ ከስምንት ወር በላይ
የሚቆይና ለተለያዩ የምርት ማነቆዎች የተጋለጠ የአካባቢ ዝርያ በልማዳዊ አሰራር ሲጠቀሙ
ይስተዋላል፡፡ በዚህም ምክንያት የማሽላ ምርታማነት ዝቅተኛ ሊሆን ችሏል፡፡ አርሶ-አደሩ ያለበትን
የአቅም ችግር በተከታታይ ስልጠና አዳዲስ አሰራሮችን የመጠቀም ፍላጎቱን መጨመር ይኖርብናል፡፡
የማሽላ ልማትን በላቀ ሁኔታ ለማካሄድና የአርሶ-አደሮችን ዕውቀትና ክህሎት ለማዳበር በተመረጡ
በደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በሚገኙ 52 ዋናዋና የማሽላ አብቃይ ቀበሌዎች ያሉ 35022
ግንባር ቀደም አርሶ-አደሮች በማሽላ ልማት ፓኬጅ ስልጠና ይሰጣቸዋል፤ እንዲሁም በተለያየ ደረጃ
ያሉ ፈፃሚና አስፈፃሚ አካላትን ክህሎትና እውቀት ለማሻሻል በንድፈ-ሃሳብና ተግባር-ነክ ስልጠናዎች

16
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ማሳተፍና ብቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ በ2009/2010 ምርት ዘመን የማሽላ ልማት ፓኬጅ
ሰፊ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን የተሳታፊ ስብጥርን ስንመለከት 6 የዞን 12 የወረዳና 123 የቀበሌ
ባለሙያዎች ይሳተፋሉ (ሠንጠረዥ-2)፡፡

ሠንጠረዥ-2፡ በ2009/2010 ምርት ዘመን በማሽላ ልማት ፓኬጅ የሚሳተፉ ሰልጣኞች


ተ.ቁ የሰልጣኞች ስብጥር የተሳታፊ ብዛት

1 የዞን ባለሙያዎች 6

2 ወረዳ ባለሙያዎች 12

3 የቀበሌ ባለሙያዎች 123

4 አርሶ-አደሮች 35022

7. ዓብይ ተግባራት
7.1 በዝግጅት ምዕራፍ
o በክልሉ የተዘጋጀውን ዕቅድ በየደረጃው ለሚምለከታቸው አካላት ግንዛቤ መፍጠር፣
o ለዞን፤ ወረዳና ቀበሌ ባለሙያዎች እንዲሁም ለተመረጡ ግንባር ቀደም አርሶ-አደሮች
በማሽላ አመራረት ላይ ያተኮረ ስልጠና መስጠት፣
o ማሽላ የሚመረትበትን ማሳ መምረጥ፣
o ፍቃደኛ የሆኑ አርሶ-አደሮችን መመልመልና በኤክስቴንሽን አደረጃጀቱ (በልማት ቡድንና
1ለ5) መሰረት በማሳ በማደራጀት ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ማድረግ፣
o በወረዳ ደረጃ የሰብል አመራረት የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት፣
o በግብዓት አቅርቦትና ምርት ግብይት ላይ ለሚሳተፉ ባለድርሻ አካላት (ማህበራት፣
ዩንየኖች፣ አብቁተ ወዘተ) ስልጠና መስጠት፣
o ለተመረጡ ቀበሌዎች በዕቅዱ መሰረት የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች እንደ ማዳበሪያ፤
የተበጠረ የአካባቢ ዘርና ፀረ-ተባይ ኬሚካል ማዘጋጀት፣
o ለግብዓት አገልግሎት የሚውል ብድር ማመቻቸት ያስፈልጋል፡፡
7.2. በተግባር ምዕራፍ

o ማሽላ የሚመረትበትን ማሳ በምክረ-ሃሳቡ መሰረት ማዘጋጀት፣


o ለተሳታፊ አርሶ-አደሮች ስልጠና መስጠት፣
17
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

o የሰብል እንክብካቤ ስራዎችን በወቅቱ ማከናወን (አረም፤ ነፍሳት፤ ተባይና በሽታ ቁጥጥር፤
ሁለተኛ ዙር ዩሪያ መጨመር)፣
o የምርት ጥራትን የሚቀንሱ በዕድ ተክሎች የነቀሳ ስራ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ማከናወን፣
o የምርት ብክነትንና የጥራት ጉድለትን በማያስከትል መልኩ በወቅቱ ሰብሉን መሰብሰብና
መውቃት፣
o በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ ወቅታዊ የመስክ የሙያ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንዲሁም
ተሞክሮ መቀመር፤
o የተግባራትን አፈፃፀም በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በክላስተር በልማት ቡድንና በ1ለ5
እንዲገመገም ማድረግ፣
o የተግበራትን አፈፃፀም በሚመለከት በተለይ በዋና የስራ ወቅት ቀበሌ ለወረዳ ወረዳ ለዞን
እንዲሁም ዞን ለክልል ሪፖርት ማድረግ፣
o በየጊዜው የተግባራትን አፈፃፀም በመስክና በሪፖርት በመገምገም ግብረ መልስ በየደረጃው
መስጠት፣
o የተሻለ ተሞክሮ ካላቸው አካባቢዎች የልምድ ልውውጥ ማድረግ
o በዕቅድ የተያዙ የግብይት ተግባራትን በሚፈለገው ደረጃ ማከናወን ይቻል ዘንድ በማሽላ
ምርት ግብይት ዙሪያ ተዋንያንና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ወቅታዊ ሥራዎችን እና
ያጋጠሙ ችግሮችን የሚገመግምና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ሊጠቁም የሚችል
በዓመት 3 ጊዜ የሚካሄድ የምክክር መድረክ በዕቅድ ተይዟል፡፡ በተመሳሳይም በበጀት
ዓመቱ ሁለተኛ ሩብ ዓመት የመጀመሪያ ወር የማሽላ ምርት አቅራቢ ዩኒዬኖችንና
ነጋዴዎችን ከገዥ አካላት ጋር ሊያገናኝ የሚችል የትስስር መድረክ እንደሚዘጋጅና
በማሽላ ምርት ግብይት ዙሪያም የተሻለ አፈፃፀም ባስመዘገቡ አካባቢዎች በወርሃ የካቲት
የልምድ ልዉዉጥ እንደሚካሄድ በዕቅድ ተይዟል፡፡
7.3 የማጠቃለያ ምዕራፍ
o የዕቅድ አፈፃፀም ማጠቃለያ ሪፖርት ማዘጋጀትና ዓመታዊ የባለድርሻ አከላት ግምገማ
ማካሄድ፡፡
8. የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት

በክልሉ የማሸላ ልማትን በሚፈለገው መጠንና ጥራት በማምረት የምግብ ፍላጎት ማሟላትና
የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚቻለው በየደረጃው ያሉ ፈጻሚና አስፈጻሚ አካላት በጋራ

18
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ተቀናጅተውና በየድርሻቸው ሊያከናውኑ የሚገባቸውን ተግባራት ሲያከናውኑ ብቻ ነው። ስለዚህ


የባለድርሻ አካላት ተግባርና ኃላፊነት እንደሚከተለው ቀርቧል።

8.1 ግብርና ቢሮ
o በማሸላ አመራረት ለዞን አመራሮችና ባለሙያዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ማመቻቸት፣
o የማሸላ ልማት የቴክኖሎጂ ፓኬጅ ማዘጋጀትና እስከ ቀበሌ እንዲደርስ ማድረግ፣
o በማሸላ አመራረት ለዞንና ለወረዳ ባለሙያዎች በቂ የንድፈ-ሃሳብና የክህሎት ስልጠና
መስጠት፣
o የግብዓት አቅርቦትን (ማዳበሪያ፣ ምርጥዘር፣ ኬሚካል ናየመሳሰሉትን) እንዲቀርብ ማመቻቸትና
አፈፃፀሙን መከታተል፣
o የብድር አቅርቦትን ማመቻቸት፣
o ተከታታይነት ያለው የመስክ ድጋፍ መስጠት፣
o የመስክ ጉብኝቶችን መሰረት ያደረገ ግብረ-መልስ መስጠት
o ወቅታዊ የአየር ትንበያ (ሜትዮሮሎጂ) መረጃ ለዞኖች ማስተላለፍ፣ ክትትልና ግምገማ
ማካሄድ፣ የአሰራር አቅጣጫ ማስቀመጥ፣
o በክልል ደረጃ በሚቋቋመው የማሸላ እሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ግብረ-ሃይልና የቴክኒክ ኮሚቴ
አባል በመሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ዋናዋናዎቹ ናቸው።
8.2 ዞን ግብርና መምሪያ

o ለወረዳና ቀበሌ ሙያተኞች የሚሰጠውን የማሸላ አመራረት ስልጠና ማስተባበር፣


o ለወረዳ አመራሮች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ማመቻቸት፣
o አርሶአደሮች ስለ ማሸላ አመራረት ዘዴ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
o የግብዓትና የብድር አቅርቦትን ማሣለጥ፣
o ከወረዳ-ወረዳ ጥቅም ላይ የማይውል ወይም በትርፍነት የሚገኝ ግብዓት ማዟዟር፣
o ወረዳንና ቀበሌን በመስክ ተገኝቶ መደገፍ፣ግ ብረ-መልስ መስጠት፣
o ከወረዳ ወረዳ የመልካም ተሞክሮ ልውውጥ ማካሄድ፣
o ከክልል የሚተላለፍለትን ግብረ-መልስ፣ የአየርሁኔታ መረጃ ወ.ዘ.ተ ለወረዳዎች ማስተላለፍ፣
o ተከታታነትና ተአማኒነትያለው ሪፖርት ለክልል ማስተላለፍ፣

19
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

8.3 ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

o ለቀበሌ ሙያተኞች ስለማሸላ አመራረት ስልጠና መስጠት፣


o ለቀበሌ አመራሮች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ማመቻቸት፣
o በማሽላ ልማት ፓኬጅ የሚሰጠውን የአርሶአደር ስልጠና ማስተባበር፣
o አርሶ-አደሮች ስለ ማሸላ አመራረት ዘዴ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
o ለአርሶአደሩ ግብዓትና ብድር በወቅቱ ማሰራጨት፣
o ወቅታዊ የእርሻ ስራን ለመደገፍ ህብረተሰቡን ማነቃነቅ፣
o ከማሣ ዝግጅት እስከ ሰብል ስብሰባና ክምችት ድረስ ያሉ የማሸላ ቴክኖሎጅ ጥንቅሮችን
(ማሣዝግጅት፣ የዘርወቅት፣ ዘርና የማዳበሪያ መጠን፣ የአረም፣ ነፍሳት ተባይና በሽታ ቁጥጥር፣
ሰብል በወቅቱ መሰብሰብና መውቃት እና ሌሎችንም) አርሶአደሮች ሙሉበሙሉ በወቅቱተ
ግባራዊ እንዲያደርጉት ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
o በምርምር የተለቀቁ አዳዲስ ዝርያዎችን የአርሶ-አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትንና የአርሶአደር
ማሳን በመጠቀም ሰርቶማሳያ በመስራት ማስተዋወቅ፣
o ከዞን የሚተላለፍለትን ግብረ-መልስ፣ የአየር ሁኔታ መረጃና የመሳሰሉትን ለቀበሌዎች
ማስተላለፍ፣
o ተከታታይነትና ተአማኒነትያለው ሪፖርት ለዞን ማስተላለፍ፣
o ክትትልና ግምገማ ማካሄድ፣
o በወረዳ ደረጃ በሚቋቋመው የማሸላ እሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ግብረ-ሃይልና የቴክኒክ ኮሚቴ
አባል በመሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት ዋናዋናዎቹ ናቸው።

8.4 ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት

o ሰብሉ ሊለማባቸው የሚችሉ ተስማሚ አካባቢዎችንና ማሣዎችን መለየት፣ አርሶ አደሮችን


በክላስተር ማደራጀት፣
o ለአርሶአደሩ ስለማሸላ አመራረት በተግባር የተደገፈ የክህሎት ስልጠና መስጠት፣
o ለአርሶአደሮች በወቅቱ ዘርና ማዳበሪያ እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ ፀረ-ተባይ ኬሚካል
እንዲቀርብ ማድረግ፣ ሰብሉን ለማልማት ዘር የወሰዱ አርሶ አደሮችን ዝርዝር መረጃ
መያዝ ለወረዳ ማስተላለፍ፣

20
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

o የማሸላ ዘር እጥረትን ለማቃለል ባለፈው ዓመት የተመሰከረለት ዘር የተጠቀሙ


አርሶአደሮችን ለይቶ በመመዝገብ ያመረቱትን ሁለተኛ ትውልድ ዘር ለሌሎች
አርሶአደሮች በግዥ ወይም በዘር ልውውጥ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ፣
o አርሶአደሮች ስለኮንትራት አመራረት ዘዴ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ፣
o ከማሣ ዝግጅት እስከ ሰብል ስብሰባና ክምችት ድረስ ያሉ የማሸላ ቴክኖሎጅ ጥንቅሮችን
(ማሣዝግጅት፣ የዘርወቅት፣ የዘርና የማዳበሪያ መጠን፣ የአረም፣ ነፍሳት ተባይና በሽታ
ቁጥጥር፣ ሰብል በወቅቱ መሰብሰብና መውቃት እና ሌሎችንም) አርሶአደሮች ሙሉ
በሙሉ በወቅቱ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
o ግንባር ቀደም አርሶአደሮችን በመጠቀም የመልካም ተሞክሮዎችንና አዳዲስ
ቴክኖሎጂዎችን ማስፋት፣
o የአየርትን በያመረጃዎችን፣ ከወረዳ የሚተላለፉ ተሞክሮዎችንና ግብረ-መልሶችን ለልማት
ቡድኖች ማድረስ፣
o የልማት ቡድኖች በቋሚነት በየዕለቱ ስራዎችን መገምገማቸውን መከታተል፣
o ተከታታይነትና ተአማኒነት ያለው ሪፖርት ለወረዳ መላክ፣
o ክትትልና ግምገማ ማካሄድ፣
o በምርምር የተለቀቁ አዳዲስ ዝርያዎችን የአርሶአደር ማሰልጠኛ ማዕከላትንና የአርሶአደር
ማሳን በመጠቀም ሰርቶ ማሳያ በመስራት ማስተዋወቅ፣
8.5 የምርምር ማዕከላትና ዩንቨርሲቲዎች
o ችግር-ፈች ምርምሮችን በማካሄድ የማሽላ ዝርያዎችን የማፍለቅ፣ በሌሎች ክልሎችና አገሮች
ተሞክረው ውጤታማ የሆኑ ዝርያዎችን በተመሳሳይ ስነ-ምህዳር የማላመድና የማስተዋወቅ
ስራ መስራት፣
o ጥራቱን የጠበቀና በቂ የሆነ መነሻ ዘር ለዘር አባዥ ድርጅቶች ማቅረብ፣
o ለማሸላ አመራረት ተስማሚ የሆኑ የሜካናይዜሽን ቴክኖሎጅዎችን (የዘር
መዝሪያ፣ማጨጃ፣መውቂያወዘተ) መለየትና ለአርሶ-አደሮች ማስተዋወቅ፣
o ማሸላን በተሻለ ሁኔታ ለማምረት የሚቻልባቸውን ስነ-ምህዳሮች የመለየትና የአፈርን
ለምነትን መሠረትያደረገ የማዳበሪያ አጠቃቀም ምክረ-ሃሳብ ማውጣት፣
o የማሸላን ምርታማነት ሊያሳድጉ የሚችሉ የአመራረት ስርዓት ማፍለቅና ማስተዋወቅ፣
o የተለያዩ የማሸላ ነፍሳት ተባዮችንና በሽታዎችን ለመከላከል የሚያስችል የተቀናጀ ተባይ
መከላከል ዘዴን መለየትና ማስተዋወቅ፣

21
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

o የምርምር ኢንስቲትዩቱ ከሌሎቸ አጋር አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት፣


o በማሸላ እሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልነት በመሣተፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት

8.6 ዘር አባዥ ድርጅቶች


o መንግስታዊ በሆኑ ማህበራት ዘር አባዥ ድርጅቶች ከምርምር ማዕከላት የሚቀርብላቸውን
መነሻ ዘር በመውሰድ ደረጃውን የጠበቀ ዘር ማባዛት፣ ማዘጋጀትና ማቅረብ፣
o ስለኮንትራት አመራረት ዘዴ ለባለድርሻ አካላት በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው
ማድረግ፣
o ውስጣዊ የጥራት ቁጥጥር ስራን በወቅቱና በተሟላ መልኩ መፈጸም፣
o ከድርጅቱ ጋር የዘር ብዜት ለመስራት ውል ለያዙ ማህበራትና አርሶ-አደሮች ድጋፍ
መስጠት፣
o በማሸላ እሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልነት በመሣተፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት

8.7 የዕጽዋትና የሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን


o የማሸላ ዘር በሚባዛባቸው የክላስተር ወረዳዎች ወቅቱን የጠበቀ የኢንስፔክሽን ስራ መስራት፣
o በየወረዳው ላሉ የዘር ብዜትና የሰብል ልማትና ጥበቃ ባለሙያዎች ስለ ማሸላ አመራረትና
የጥራት ቁጥጥር ስራዎች የንድፈ-ሃሳብና የክህሎት ስልጠና መስጠት፣
o የዘርጥራት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት በወቅቱ መስጠት፣
o ከሌላ አካባቢዎች የሚገባን ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶችን ጥራትና ደረጃ ያሟሉ
መሆናቸውን መቆጣጠር
o በማሸላ ዕሴት ሠንሠለት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልነት በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት።

8.8 የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጄንሲ


o ለግብርና ባለሙያዎች የማሸላ አመራረትና ግብይትን በተመለከተ ስልጠና መስጠት፣
o በማሸላ አመራረትና በግብይት በኩል ያጋጠሙ አንኳርች ግሮችና መፍትሄዎችን በመለየት
ለውሳኔ ሰጭ አካላት ማቅረብ፣
o በማሸላ የክላስተር ወረዳዎች የሚከናወኑ ተግባራትን ከግብርና ቢሮ ጋር በመቀናጀት
መከታተል፣
o የኮንትራት አመራረት ስርዓት እንዲስፋፋ የበኩሉን ድርሻ መወጣት፣

22
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

o በአምራቹ፣ በመሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት፣ በዩንየኖች፣ መካከል ያለው ትስስር እጅግ


የጠነከረና ዘላቂ እንዲሆን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
o በማሽላ እሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልነት በመሣተፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት።

8.9 በየደረጃው የሚገኙ የህብረት ስራ ማ/ማ/ጽ/ቤቶች

o ማህበራት የማሸላ ጥራትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ የዘር ማበጠሪያዎች፣ መጋዘኖችንና


ሌሎችንም ቁሳቁሶች እንዲያሟሉ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
o የማሽላ ምርጥ ዘር የሚያባዙ አርሶአደሮችን በማህበር በማደራጀት ቢያንስ ለአካባቢው
የሚያስፈልግ ዘር እንዲያመርቱ ማድረግ፣
o ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የማሽላ አመራረትና ግብይት የሚመራበትን
ስርዓት ማዘጋጀት፣ ማስጸደቅ እና ለተግባራዊነቱ ምክትትል ማድረግ፣
o የህብረት ስራ ማህበራትንም ሆነ የዩንየኖችን አቅም ሊያስደጉ የሚችሉ ተግባራትን
ማከናወን፣
o በወረዳ ደረጃ በሚቋቋመው የማሽላ ገበያ ጥናት ላይ በኮሚቴ አባልነት መሳተፍ፣
o በየደረጃው በሚቋቋመው የማሽላ የእሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ግብረ-ሃይልና የቴክኒክ
ኮሚቴ አባል በመሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት።

8.10 በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት


o በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር አካላት ክልሉ በማሽላ ልማት ላይ የሚያከናውናቸውን
ተግባራት በመሪነት በመምራትና በመደገፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት። በተለይ የወረዳ
አስተዳደር ከወረዳ ግብርና ጽ/ቤቶች ጋር በጋራ በመሆን ማሽላ በሚመረትባቸው
ቀበሌዎች አርሶ አደሮች በክላስተር ተደራጅተው ሰብሉን በስፋት እንደያመርቱ
የህዝብንቅናቄ መፍጠር፣
o የወረዳው የማሽላ ዕሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ግብረ-ሃይል ተግባርና ኃላፊነቱን እንዲወጣ
የመሪነት ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል።

8.11 የገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩኒዬኖችና የህብረት ስራ ማህበራት


o የማሽላ ልማት እንዲመረትባቸው በክላስተር ለተደራጁ ወረዳዎች ከዘር ወቅት ቀደም
ብሎጥራቱን የጠበቀ ማዳበሪያ፣ ምርጥ ዘር፣ ፀረ-ተባይ ኬሚካልና ሌሎችንም ግብዓቶች
ማቅረብ፣

23
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

o ለማሽላ አመራረት ጠቃሚ የሆኑ የእርሻ መሣሪያዎችን (የዘር መዝሪያ፣ ታይርጅር አይባር
ቢቢኤም፣ ማጨጃና መውቂያ ወዘተ) ማቅረብ፣
o በማሸላ እሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልነት በመሣተፍ የበኩሉን ድርሻ መወጣት።
o በማሸላ ግብይት ላይ ከመሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት ጋር የውል ስምምነት መያዝ፣
o ለምርት ግዥ የሚሆን ገንዘብ ለመሠረታዊ ማህበራት በወቅቱ መልቀቅ፣
o የመሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት አመራርን አቅም ማሳደግ፣
8.12 አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም
o የማሽላ ልማትን ለመደገፍ ለዩንየኖች፣ ዩንየኖች ደግሞ ለመሠረታዊ ማህበራት እንዲሁም
መሠረታዊ ማህበራት ለአርሶአደሮች በወቅቱ ክፍያ እንዲፈጽሙ የብድር አገልግሎት
መስጠት፣
o በማሸላ እሴት ሰንሰለት አስተባባሪ ኮሚቴ አባልነት በመሣተፍ ጉዳዩ የሚመለከታቸው
አካላትጋር በመሆን የበኩሉን ድርሻ መወጣት።

9. የሚያስፈልግ ግብዓት
o ለ2009/2010 ምርት ዘመን ለደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች ማሽላ ልማት 8755 ኩንታል
NPSB/NPSZNB 8755 ኩንታል ፖታሽ 4377.5 ኩንታል ዩሪያ ማዳበሪያና 438 ኪሎ
ግራም /ሊትር ፀረ-ተባይ ኬሚካል ያስፈልጋል (ሠንጠረዥ-3)፡፡ እነዚህ ግብዓቶች የማሽላ
ልማት ለሚከናወንባቸው ቀበሌዎች በዝግጅት ምዕራፍ ወቅት መሰራጨት ይኖርባቸዋል፡፡

ሠንጠረዥ-3፡ በ2009/2010 የምርት ዘመን ለታቀዱ የማሽላ ልማት ስራዎች የሚያስፈልግ


የግብዓት ዓይነትና መጠን
ዞን ወረዳ በአካባቢዝርያ ናበተሻሻለ አሰራር የሚሸፈን ፀረ-
ተባይኬሚካል
መሬት(ሄ/ር) ዘር(ኩ.ል) NPSB/NPS ዩሪያ(ኩ.ል) ፖታሽ(ኩ.ል) (ኪግ/ሊትር)
ZnB(ኩ.ል)

ሰ/ጎንደር ጎንደርዙሪያ 4294 429.4 4294 6441 4294 215

ደንቢያ 4461 446.1 4461 6691.5 4461 223

ድምር 8755 875.5 8755 13132.5 8755 438

24
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

10. አዲሱ የዓፈር ንጥረ-ነገር እጥረት አመላካች ሰንጠረዥ


ጎንደር
ሰሜን ዙሪያ o NPSB 0 NPSZnB 0 0 38
ጎንደር ደንቢያ 0 NPSB 0 NPSZnB 0 0 44
መግለጫ

Fertilizer NPS NPSB NPSZn NPSZnB NPSBCu NPSZnBCu Potassium


Map
Clour

25
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

11. የሚያስፈልግ በጀት


ለ2009/2010 ምርት ዘመን ለማሽላ ልማት ግብዓት መግዣ፣ ለስልጠናና ክትትል የሚያስፈልግ በጀት
(ሠንጠረዥ-4)

11.1. ለግብዓት መግዣ የሚያስፈልግ በጀት


ሠንጠረዥ-4፡- በ2009/2010 የምርት ዘመን የታቀደ የማሸላ ልማት የበጀት መጠን

ተቁ የግብዓት ዓይነት ብዛት (ኩ/ል) የአንድ ዋጋ ድምር


1 NPSB/NPSZNB 8755 1800 15,759,000
ፖታሽ 8755 1000 8,755,000
2 ዩሪያ 13132.5 1800 23,638,500

3 Chemical (pesticide) kg/lit 438 500 219,000


ድምር
34,188,400
መጠባበቂያ (5%)
1,709,420
ጠቅላላ ድምር
35,897,820

26
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

11.2. ለስልጠና፤ ክትትልና ድጋፍ የሚያስፈልግ በጀት


ሠንጠረዥ-5፡- በማሽላ ሰብል ልማት ፓኬጅ ለስልጠናው የሚያስፈልግ በጀት (በብር)
ተ.ቁ የተሳታፊዎች የተሳታፊ የስልጠና የጉዞ የቀናት የቀን የወሎ የትራንስ ለነዳጅ ድምር
ስብጥር ብዛት ቀን ብዛት ቀናት ድምር አበል አበል ፖርት ና (ብር)
(ብር) ክፋያ ወጭ ቅባት
(ብር) (ብር) (ብር)
I የስልጠናው
ተሳታፊዎች
1 የዞን ባለሙያዎች 6 3 2 5 300 9000 900 0 9900
2 ወረዳ ባለሙያዎች 12 3 2 5 300 18000 1800 0 19800

3 የቀበሌ ባላሙያዎች 123 3 2 5 300 184500 24600 0 209100

5 አ/አደሮች 35022 3 0 3 0 0 0 0
6 አሰልጣኝ 7 3 2 5 300 10500 0 0 10500

7 ሹፌር 3 3 2 5 300 4500 0 3000 7500

ንዑስ ድምር-1 321660 27300 3000 351960


II ሌሎች ወጭዎች
1 የጽሕፈት 14100 14100
መሳሪያዎች
2 መስተንግዶ 15300 15300
ንዑስ ድምር-2 29400 29400
ድምር (ንዑስ 1፤2) 286200
መጠባበቂያ በጀት 14310
(5%)
ጠቅላላ ድምር 300510

27
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

ሠንጠረዥ-6፡ የ2009/2010 የማሽላ ልማት ዕቅድ የሚያሰፈልግ ጠቅላላ በጀት


ተ.ቁ ዝርዝር ብር መጠን
1 ግብዓት 35,897,820
2 ስልጠና፤ ክትትልና ግምገማ 300510

ጠቅላላ ድምር 36,198,330

12. አዋጭነት

ማሽላ አመራረት የሚገኝ የሽያጭ የሚገኝ ማምረቻ ከወጭ ቀሪ


ምርት(ኩ.ል) ዋጋ(ኩ/ል) ብር ወጭ

ሙሉ ፓኬጅ በመተግበር 40 500 20000 6500 13500

በመደበኛ በመተግበር 23 500 11500 2500 9000

o በ 1 ሂ/ር በሙሉ ፓኬጅ በመተግበር የሚገኘዉ ትርፍ 13500 ሲሆን በመደበኛ ከተሰራ ግን
9000 ብር ነዉ፡፡ በዚህም መሰረት ሙሉ ፓኬጅ በመተግበር የሚገኝ ምርት ከመደበኛ
አመራረት ጋር ሲነጻጸር 269 % ብልጫ ያሳያል::
o በዘህም መሰረት በሙሉ ፓኬጅ መስራት በጣም አዋጭ ነዉ፡፡

28
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የሰ/ጎንደር ዞን 2009/2010
ደምቢያና ጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች የማሽላ ኮሞዲቲ ክላስተር ልማትና ምርት ዘመን
ግብይት ዕቅድ

13. የማሽላ ልማት ዕቅድ የጊዜ ሰሌዳ


ሠንጠረዥ-7፡ የ2009/2010 ምርት ዘመን የማሽላ ልማት ዕቅድ የጊዜ ሰሌዳ

ተ.ቁ የስራ ዝርዝር

መስከረም
መጋቢት

ጥቅምት

ምልከታ
ሚያዚያ
የካቲት

ግንቦት

ተህሳስ
ሃምሌ

ህዳር
ነሃሴ

ጥር
ሰኔ
1 በክልሉ የተዘጋጀውን ዕቅድ በየደረጃው
ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ
መፈጠር
2 ለዞንና ወረዳ ባለሙያዎች የማሽላ ልማት
ፓኬጅ ስልጠና መስጠት
3 ለቀበሌ ባለሙዎች በማሽላ ልማት
ፓኬጅ ስልጠና መስጠትና ለቀበሌ
አመራሩ ግንዛቤ መፍጠር
4 በማሽላ ልማት ፓኬጅ ተሳታፊ አርሶ-
አደሮች ስልጠና መስጠት
5 የግብዓትና ምርጥ ዘር አቅርቦት

6 የማሳ ዝግጅትና የዘር ወቅት

7 ክትትልና ድጋፍ

8 የመስክ ጉብኝት ማካሄድ

9 የማጠቃለያ ግምገማ

29

View publication stats

You might also like