You are on page 1of 30

በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት

የሳሙና፣ ቀለምና ተዛማጅ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት

በሳሙና እና ተዛማጅ ውጤቶች አምራች ኢንዱስትሪዎች የሁለተኛ


መደብ /ሀ/ ታሪፍ ተጠቃሚነት ላይ የተደረገ ጥናት

ሚያዚያ፣ 2010 ዓ.ም

i
ምስጋና

የሳሙና ቀለምና ተዛማጅውጤቶችአምራችኢንዱስትሪዎችንየሁለተኛመደብ/ሀ/ ታሪፍተጠቃሚነት ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ


ለመስጠትና መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪው የሰጠውን ማበረታቻ ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገው ጥናት
ላይመረጃ በመስጠት ለተባበሩን ድርጅቶች እና ለኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች አምራቾች የዘርፍ ማህበር እንዲሁም
ከሙያ አንጻር በእርማት ለተባበሩን ለአቶ ሰለሞን ዮሃንስ ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን፡፡
ዋና አዘጋጆች፡-
1. አቶ መቂ ከበደ
2. አቶ ፍቃዱ አሸኔ
3. አቶ ስለሺ አያሌው
ረዳት አዘጋጆች ፡-
1. አቶ ታጋይ አሰፋ (ከቤካስ ኬሚካልስ)
2. ወ/ሪት ናኦሚ መሀመድ (ከበየዳ ሰስቴነብል ማኑፋክቸሪንግ)

ii
ይዘት

1. መግቢያ................................................................................................................................................................ 1
1.1. የጥናቱ መነሻ ሀሳብ / statement of the problem/...................................................................................................2
1.2. የጥናቱ ዓላማ (objective of the study)............................................................................................................2
1.2.1. የጥናቱ ዝርዝር ዓለማዎች (Specific objctives)...............................................................................................2
1.3. የጥናቱ አስፈላጊነት /Significance of the study/፡-.............................................................................................2
1.4. የጥናቱ መዳረሻ (scope of the study)...............................................................................................................3
1.5. የጥናቱ ዘዴ /Methodology/..........................................................................................................................3
1.6. የጥናቱ ውስንነት /Limitation of the study/......................................................................................................3
2. የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ኢንዱስትሪዎች.................................................................................................................4
2.1. የንዑስ ዘርፉ አጠቃላይ ሁኔታ.............................................................................................................................5
2.1.1. የንዑስ ዘርፉ አቅም አጠቃቀም........................................................................................................................6
2.1.2. ንዑስ ዘርፉ ከኤክስፖርት እንቅስቃሴ አንጻር.......................................................................................................6
2.1.3. የሳሙናና ዲተርጀንት ገቢ ምርት ሁኔታ.............................................................................................................7
2.1.4. የንዑስ ዘርፉ የገበያ ፍላጎት.............................................................................................................................9
2.2. የንዑስ ዘርፉ እሴት ጭማሪ..............................................................................................................................10
2.3. የንዑስ ዘርፉጥሬ ዕቃዎች (Basic Raw Materials)............................................................................................14
2.3.1. አገር ውስጥ የማይገኙ የሳሙናና ዲተርጀንት ጥሬ ዕቃዎች.....................................................................................14
2.3.2. አገር ውስጥ የሚገኙ የሳሙናና ዲተርጀንት ጥሬ ዕቃዎች.......................................................................................26
2.3.3 የሶፕ ኑድልስ አምራች ኢንዱስትሪ.....................................................................................................................29
3. ማጠቃለያ /Conclusion/....................................................................................................................................32
4. አስተያየት /Recommendation/.............................................................................................................................33

iii
1. መግቢያ

አገራችንን በ 2017 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለማሰለፍ፣ ከ 40 እስከ 50 ዓመታት ባሉት
ጊዜያት ውስጥ ደግሞ በኢንዱስትሪ የዳበረች፣ በኢኮኖሚ የበለጸገችና ለዜጎቿ ከፍተኛ ገቢ የምታስገኝበት ደረጃ
ላይ ለማድረስ የሚያስችሉ የረጅምና የመካከለኛ ጊዜ ዕቅዶችታቅደው በትግበራላይ ይገኛሉ፡፡ ይህን የልማት ጉዞ
በስኬት ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችም ተነድፈው ለልማትና ዕድገት አመቺ
የሆኑ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ የተደረገ ሲሆን የኢኮኖሚውን ዕድገትና ነባራዊ ሁኔታ መሰረት ያደረጉ የአምስት
ዓመታት እቅዶችና ማስፈጸሚያ መርሀ-ግብሮችም ተዘጋጅተው ተግባራዊ እየተደረጉ ነው፡፡ በዚህም በአገራችን
ቀደም ሲል ያልታዩ የኢኮኖሚ ዕድገቶች እየተመዘገቡ የመጡ ሲሆን በተለይ ባለፉት 12 ዓመታት የተመዘገበው
ተከታታይነት ያለው ባለሁለት አሃዝ እድገት የአገራችንን ገጽታ በመሰረታዊነት የቀየረ ነው፡፡ የተመዘገቡት
የልማት ዕድገቶች ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ያካተቱና መሰረተ-ሰፊ በመሆናቸው ቀጣይነት ላለው ዕድገት
መሰረት የጣሉ ናቸው፡፡ ለኢኮኖሚው እድገት ወሳኝና የመሪነት ሚና የነበረው የግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ
እንደሆነ የሚታወቅ ቢሆንም የኢንዱስትሪው ዘርፍም የበኩሉን አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

በአገራችን ለኬሚካልና ኮንስትራሽን ግብዓት ኢንዱስትሪው ዘርፍ ይሰጥ የነበረው ትኩረት ዝቅተኛ ስለነበር
ኢንዱስትሪዎቹ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እድገታቸው የተገደበ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢንዱስትሪው
ያለበትን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመፍታት መንግስት ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት የሚደግፍ የኬሚካልና
የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በማቋቋም የዘርፉን ችግር ለመፍታት ጥረት
በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብአቶች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከሚደግፋቸው ውስጥ ሳሙና ተዛማጅ
ኢንዱስትሪ ልማት አንዱ ሲሆን የንዑስ ዘርፉ ዋነኛ ዓላማ ለኬሚካል ውጤት ኢንዱስትሪዎች
(ሳሙናናዲተርጀንት) የሚያስፈልጋቸውን ግብዓቶች በአገርውስጥ በማምረት ገቢ ምርትን መተካት እና
የኬሚካል ኢንዱስትሪው ለግብዓትነት የሚጠቀማቸውን ጥሬ እቃዎች በአገር ውስጥ ማምረት የሚችል ባለሃብትን
በማበረታታት ኢንዱስትሪውን ማስፋፋት ነው፡፡ ገቢ ምርቶችን ከመተካት በተጨማሪም የዘርፉን ኤክስፖርት ድርሻ ማሳደግ
ይገኝበታል፡፡

መንግስት የአምራች ዘርፉን ልማታዊነት ለማረጋገጥ በአገሪቱ የሚመረቱትን ምርቶች


በዋጋና በጥራት ተወዳዳሪነት ለማጎልበት ሲባል የታሪፍ ከለላ ለማድረግ መመሪያ አውጥቷል፡፡
በዚህ መመሪያ መሰረትም በሚያመርቱት ምርት ላይ እሴት እንዲጨምሩና የሚጨመረውም
እሴት ለ አ ገ ር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲጨመር የማዕከላዊ ስታትስቲክ ኤጄንሲ
ለየዘርፎቹ መነሻ በማስቀመጥ ይህን አካሄድ ያሟሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንደየዘርፎቹ
ነባራዊ ሁኔታ የምርት ፍላጎት እቅዳቸውን ብክነትና የግብዓት ምርት ጥምርታ ጋር ያለው
ነባራዊ ሁኔታ ተገምግሞ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር
ተዘርግቷል፡፡ ከነዚህ አምራች ኢንዱስትሪዎች መካካል የሳሙናና ተዛማጅ ምርት ን ዑ ስ
ዘርፍ አንዱ ነዉ፡፡ በተለይ ን ዑ ስ ዘርፉ በአሁኑ ሰዓት ባለሃብቶችን በከፍተኛ ሁኔታ እየሳበ
ያለና ይህም ሆኖ ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነፃፃር ገና ያልተሰራበት እንደሆነ እና በተለይም
ሃገሪቱ በቀጣይ ወደ ዉጭ ለምትልካቸዉ ምርቶች ዕሴት ጨምራ ለመላክ ካላት ፍላጎትና

1
የማኑፋክቸሪንጉን ዘርፍ እድገት ለማፋጠን ለተቀመጠዉ ግብ መሳካት የዚህ ንዑስ ዘርፍ
መሰፋፋት በጣም አስፈላጊና ድጋፍን የሚሻ ሆኖ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ መንግስት
ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማመበረታታት ሲባል ያወጣዉ የሁለተኛ መደብ(ሀ) ታሪፍ የሳሙናና
ቀለም ኢንደስትሪ ዘርፍን በአብዛኛው ተጠቃሚ ያደረገ አይደለም፡፡ ስለሆነም የሳሙናና
ዲተርጀንት አምራች ፋብሪካዎች የሚጠቀሟቸዉ ጥሬ ዕቃዎች ለሌሎች ዘርፎች
ተፈቅደው ሳለ አብዛኞቹ ለዚህ ንዑስ ዘርፍ ያልተፈቀዱ በመሆናቸው ይህንን ጥናት ማጥናት
አስፈልጎዋል፡፡

1.1. የጥናቱ መነሻ ሀሳብ / statement of the problem/


ለዚህ ጥናት እንደ መነሻ ሃሳብ የሆኑት፡-
ለሌሎች ዘርፎች በሁለተኛ መደብ /ሀ/ታሪፍ የተፈቀዱ ጥሬ ዕቃዎች ለሳሙና፣ ዲተርጀንት አምራች
ኢንዱስትሪዎች አለመፈቀዳቸው፡፡
የሳሙና ኖድል ለማምረት የሚውሉ ግብዓቶች የተጣለው ታክስ እና በሳሙና ኖድል የተጣለው ታክስ ተመሳሳይ
በመሆኑ ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር ንዑስ ዘርፉን የማያበረታታ በመሆኑና
የሳሙና ምርት ጥሬ ዕቃ የሆነውን የሳሙና ኖድል በአገር ውስጥ እንዲመረት ባለኃብቱን ለማበረታታት ናቸው፡፡

1.2. የጥናቱ ዓላማ (objective of the study)


የዚህ ጥናት ዓላማ መንግስት በአገር ውስጥ በማኑፋክቸሪንግ ንኡስ ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች (የሳሙናና
ዲቲርጅንት) ገቢ ምርት መተካት እንዲችሉና ከውጭ ከሚገባው ተመሳሳይ ምርት ጋር በገበያ መወዳደር እንዲችሉ ከውጭ
በሚገቡ ግብዓቶች ላይ በሰጠው የታክስ ከለላ መሰረት የጉምሩክ ሁለተኛ መደብ (ሀ)ታሪፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል
ንዑስ ዘርፉን በስፋት በመዳሰስ እንደገና በማየት ሊሻሻል የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡

1.2.1. የጥናቱ ዝርዝር ዓለማዎች (Specific objctives)


ይህ ጥናት የንዑስ ዘርፉ አምራች ድርጅቶች ግብአቶቻቸው
 በአንደኛ መደብ ታርፍ/ሀ/ የተመደቡ ጥሬ ዕቃዎች በ 2 ኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ ተመድበው ለንዑስ ዘርፉ
የሚፈቀዱበትን ሁኔታ ማመላከት፣
 ለሌሎች ዘርፎች በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታርፍ የተፈቅዱ ጥሬ ዕቃዎችለንዑስ ዘርፉአምራቾችም የሚፈቀድበትን
ሁኔታ ማመላከትእና፣

1.3. የጥናቱ አስፈላጊነት /Significance of the study/፡-


 መንግስት ለአምራች ድርጅቶች የሰጠውን ትኩረትና ማበረታቻ ከታለመለት ዓላማ አንጻር ግቡን እንዲመታ
ለማድረግ፣
 የንዑስ ዘርፉኢንዱስትሪዎች በቂ ግብዓት አግኝተው ጥራት ያለውን ምርት በማምረት ከአገር ውስጥ ገበያ በተጨማሪ በውጭ
ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል፣
 የንዑስ ዘርፉን ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታ ለይቶ በማወቅ በቀጣይ ምን ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ለማመላከት፣
 በንዑስ ዘርፉ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች እየተጠቀሙበት ያለውን ጥሬ እቃ ለይቶ ለማሳወቅና ለኢንዱስትሪዎቹ ምቹ ሁኔዎችን
ለማመቻቸት፣
 በሳሙናና ተዛማጅ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ፋብሪካዎች መንግስት በሰጣቸው የሁለተኛ መደብ
ታሪፍ /ሀ/ ተጠቃሚነት ላይ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት፣
 ባጠቃላይ በሳሙናና ተዛማጅ ውጤቶች ዘርፍ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ለሀገሪቱ እድገት የበኩላቸዉን እንዲወጡ ለማስቻል
ይህ ጥናት ተደርጓል፡፡

2
1.4. የጥናቱ መዳረሻ (scope of the study)
ይህ ጥናት የሳሙና እና ዲተርጀንት አምራች ድርጅቶችን የሚመለከት ሲሆን በጥናቱ የሳሙናናዲተርጀንት
አምራች ድርጅቶችን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም በዝቅተኛ፣ በመካከለኛና በከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ
ኢንዱስትሪዎች የጥናቱ አካል የሚደረጉ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም ለምርት ሂደታቸው የሚጠቀሟቸውን ሁሉንም
ግብአቶች በመዳስስ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው ለሚመለከተው ክፍል የሚቀርብ ይሆናል፡፡

1.5. የጥናቱ ዘዴ /Methodology/


 ጥናቱን ለማካሄድ የሳሙናናየዲተርጀንትፋብሪካዎችን በመጎብኘትና መረጃበማሰባሰብ
 የኢትዮጵያ ኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ዘርፍ ማህበርንበማወያየት
 ከተመረጡ ፋብሪካዎች ባለሙያዎችን በማሳተፍ፣
 የተለያዩ ድረ-ገጾችን በመጠቀም፣
 የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጄንሲን መረጃ በመጠቀም እና
 የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መረጃዎችን በግብአትነት በመጠቀምና

1.6. የጥናቱ ውስንነት /Limitation of the study/


 ከውጭ በኮንትሮባንድ መልክ የሚገባው ተመሳሳይ ምርት ትክክለኛ መረጃ አለመገኘት
 በየመንደሩ እየተመረተ ስለሚገኘው የፈሳሽም ሆነ የደረቅ ሳሙና መረጃን ለማግኘት የሚመለከታቸው አካላት
ተባባሪ አለመሆን፤
 በንዑስ ዘርፉ ስር ያሉት አንዳንድ ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡት መረጃ ሙሉ በሙሉ ማግኘት አለመቻልና የተዛባ
መሆን የጥናቱ ውስንነት ተደርገው ሊወሰዱ ይቻላል፡፡

ክፍል ሁለት
የንዑስ ዘርፉ አጠቃላይ ዳሰሳ
2. የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ኢንዱስትሪዎች
ከሁሉም ኢኮኖሚያዊ ተግባራት አንጻር አለም ዓቀፋዊ የኢንዱስትሪዎችን ክፍፍል ደረጃ (International
Standard Industrial Classification) በሰንጠረዥ 2.1 ማየት ይቻላል፡፡

ሰንጠረዥ-2.1፡ አለም-ዓቀፋዊ የኢንዱስትሪዎች ክፍፍል ደረጃ


Group Class Subclass Description

2023 manufacture of soap and detergents, cleaning and polishing


preparations, perfumes and toilet preparations
This class excludes:
- manufacture of separate, chemically defined compounds,
- manufacture of glycerol, synthesized from petroleum products,
- extraction and refining of natural essential oils.
3
And Includes:
20231 - Manufacture of soap all forms
20232 - Manufacture of cleaning and polishing products (preparations for
perfuming or deodorizing rooms; artificial waxes and prepared waxes;
polishes and creams for leather, wood, glass, metal etc.; scouring
pastes and powders, including paper, wadding etc. coated or covered
with these)
20233 -Manufacture of detergent and similar washing agents excluding soap
20234 - Manufacture of perfumes and cologne de-eau
20235 - Manufacture of preparations for oral or dental hygiene (includes
manufacture of toothpastes, toothpowder, mouthwash, oral, perfumes,
20236 dental fixative pastes and powders etc.)
- Manufacture of hair oil, shampoo, hair dye etc. (includes manufacture
of shampoos, hair sprays, hair fixers, hair oils, hair creams, hair dyes
and bleaches and preparations for permanent waving or straightening
20237 of the hair etc.)
- Manufacture of cosmetics and toileteries (includes manufacture of
preshave, shaving or after shave preparations; personal deodorants and
antirespirants; perfumed bath salts and other bath preparations; beauty
or make-up preparations and preparations for the care of the skin, other
20238 than medicaments; manicure and pedicure preparations etc.)
- Manufacture of “agarbatti” and other preparations which operate by
20239 burning
- Manufacture of other perfumes and toilet preparations n.e.c.
Source: - Cental statistical organization Ministry of Statistics and programme Implementation
Government of India, New Delhi, (NIC, 2008).

ሀገራችንም ይህንን አለማቀፋዊ ክፍፍል መሰረት በማድረግ በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱስትሪ
ልማት ኢንስቲትዩት ስር በሚገኘው የሳሙና ቀለምና ተዛማጅ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት
አማካኝነት ከላይ የተገለጹት ማኑፋክቸሪንግ ንኡስ ዘርፎች ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

2.1. የንዑስ ዘርፉ አጠቃላይ ሁኔታ


በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሳሙና ፋብሪካ በ 1952 ዓ.ም የተቋቋመው ጉለሌ ሳሙና ፋብሪካ ሲሆን ለረጅም ዓመታት
የሀገራችን የሳሙና ፍላጎት በገቢ ምርት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ጥገኛ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን መንግስት
በቀረፀው ምቹ የኢንቨስትመንት ፖሊሲ እንደ ሳሙና፣ ተዛማጅ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት መረጃ
በአሁኑ ወቅት በዚህ ንዑስ ዘርፍ የተሰማሩ 88 የሚሆኑ አምራች ፋብሪካዎች እንዳሉ ያሳያል፡፡ በመሆኑም
የሀገራችን የሳሙናና ዲተርጀንት ፍላጎት በዋናነት በነዚሁ አምራች ድርጅቶች እየተሟላ ቢገኝም ከገቢዎችና
ጉምሩክ ባለሰልጣን፣ ከኢንስቲትዩቱ እና ከፋብሪካዎች የሚገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አሁንም የምርት ፍላጎትና
አቅርቦት ባለመመጣጠኑና ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶች ባለመመረ ታቸው ከውጭ የሚገባውን ምርት ሙሉ በሙሉ
መተካት አልተቻለም፡፡

በሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ፋብሪካዎች በአሁኑ ወቅት የፈጠሩት የስራ ዕድል፣ ለሰራተኞቻቸው የከፈሉት ዓመታዊ
ደሞዝ፣ አመታዊ የምርት መጠን በቶን፣ አመታዊ የምርት ሽያጭ በብር፣ ያላቸዉ ቋሚ ንብረት የንዑስ ዘርፉን ገጽታ
እንደማሳያነት በሰንጠረዥ-2.2 ቀርቧል፡፡

4
ሰንጠረዥ-2.2፡ የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ፋብሪካዎች ገጽታ
ተ. የተፈጠረ የስራ ዕድል የሴቶች የተከፈለ ዓመታዊ ዓመታዊ የምርት የምርት ዋጋ /በብር/ ቋሚ ንብረት
ቁ ድርሻ ደመወዝ /በብር/ መጠን /በቶን/
ወ ሴ ድ በመቶኛ
1 2933 2323 5256 44.2 135,184,962 94,542.28 2,134,342,258 459,448,622

2.1.1. የንዑስ ዘርፉ አቅም አጠቃቀም


በሳሙናና ዲተርጀንት አምራችነት የተሰማሩ ድርጅቶች ደረቅ ሳሙናን ብቻ የሚያመርቱ፣ ፈሳሽ ሳሙናን ብቻ የሚያመርቱ እና
ሁለቱንም ዓይነት ምርቶች የሚያመርቱ ናቸው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የንዑስ ዘርፉ የማምረት አቅም እና
አጠቃላይ የንዑስ ዘርፉ አፈፃፀም በሰንጠረዥ 2.3 ላይ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ-2.3፡የንዑስ ዘርፉ የምርት አፈጻጸም


ገጽታዎች የበጀት አመት
2005 ዓ.ም 2006 ዓ.ም 2007 ዓ.ም 2008 ዓ.ም
የፋብሪካ ብዛት 12 12 12 12
የሰው ኃይል 4908 5031 5122 5256
የማምረት አቅም 153126.9 153126.9 145658.2 164135.9
የምርት መጠን በቶን /Actual 68294.6 72117.51 80456.69 94542.28
production/
የምርት ዋጋ በብር 1396854939 1475046030 1858392505 2134342258
አቅም አጠቃቀም በመቶኛ 44.6 47.1 52 57.6

በሰንጠረዥ-2.3 እንደተመለከተው እንደ ማሳያነት በተወሰዱ 12 ፋብሪካዎች የተመዘገበው የማምረት


አቅም በ 2 ተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከታቀደው 80 በመቶ አንጻር ከሚፈለገው ደረጃ
በታች ይገኛል፡፡ ለዚህም እንደ ችግር የሚነሱት የሚከተሉት ናቸው፡፡

 የጥሬ እቃ እጥረት (ጥሬ እቃን ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ በወቅቱ ያለማግኘት)


 የኃይል መቆራረጥ
 አሮጌ ማሽነሪዎችን መጠቀም
 ዘመናዊ የአመራረት ስርዓትን አለመዘርጋት
 የማኔጅመንት ችግርና በዘርፉ የሰለጠነ ባለሙያ እጥረት
 የመስሪያ ካፒታል ችግር
 የሎጂስቲክ አገልግሎት አቅርቦት ውሱንነት
 ከውጭ ከሚገቡት ምርቶች ጋር በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ አለመሆን ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

2.1.2. ንዑስ ዘርፉ ከኤክስፖርት እንቅስቃሴ አንጻር


በሳሙናና ዲተርጀንት አምራችነት ከተሰማሩ ፋብሪካዎች አብዛኛዎቹ ምርቶቻቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ
ብቻ የሚያቀርቡ ናቸው፡፡ ሸሙ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር የተባለ የሳሙናና ዲተርጀንት ፋብሪካ የኤክስፖርት
ዕቅዱን ለኢንስቲትዩታችን አስገብቶ በቋሚነት ምርቱን ወደ ሶማሌ ላንድ በመላክ ላይ ሲሆን ኢ.ኤን.ዲ
ግሎባል ፉድ ኮምፕሌክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ቤካስ ኬሚካልስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባሉ ድርጅቶች
የኤክስፖርት ዕቅድ ያላቸው ቢሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ኤክስፖርት ማድረግ አልጀመሩም፡፡
5
በሌላ በኩል ደግሞ አካይ ኮንሰልታንሲና ኢንዱስትሪሰ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ የዲተርጀንት አምራች
ምንም እንኳን የኤክስፖርት ዕቅድ ባይኖረውም ምርቱን በተለያየ ጊዜ ወደ ሱዳን በመላክ በኤክስፖርት
እንቅስቃሴው ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

2.1.3. የሳሙናና ዲተርጀንት ገቢ ምርት ሁኔታ


ሳሙናና ዲተርጀንት ከሰው ልጅ የእለት ተዕለት ኑሮ ጋር ከፍተኛ መስተጋብርና ፍጆታ ያለው የኢንዱስትሪ ምርት ነው፡፡
በአሁኑ ስዓት በሀገራችን ያለው የሳሙናና ዲተርጀንት ፍላጎትና አቅርቦት ባለመመጣጠኑና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የሳሙናና
ዲተርጀንት ምርቶች ማምረት ባለመቻሉ አሁንም ገቢ ምርት እንዳለ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ሰንጠረዥ-2.4፡የፈሳሽ ሳሙና ገቢ ምርት


የምርትዓይነት ዘመን Net wt (tone) CIF value CIFvalue Total tax (ETB)
(ETB) (USD)
2010 523.16 8,133,926.98 558,476.23 5,120,206.81
2011 282.49 6,502,250.54 381,035.15 3,555,844.33
2012 293.54 6,939,062.71 388,403.56 4,325,144.43
ፈሳሽ ሳሙና
2013 311.99 11,401,848.9 606,478.10 7,620,816.39
(liquid
2014 339.68 13,436,540.15 667,037.68 6,890,249.21
detergents)
2015 466.30 21,254,170.5 1,022,720.17 11,349,396.41
2016 469.48 14,435,104.96 657,839.5 8,556,179.14
2017 1,150.14 27,428,488.34 1,162,608.33 15,687,596.21
አማካይ 479.59 13,691,424.14 680,574.84 7,888,179.12

በሰንጠረዥ-2.4 ለማየት እንደሚቻለው ከ 2010 እስከ 2017 ድረስ በአማካይ 479.59 ቶን ፈሳሽ ሳሙና
በ 13,691,424.14 ብር ወደ ሀገራችን ገብቷል፡፡ ከ 2011 ዓ.ም ወዲህ የገቢ ፈሳሽ ሳሙና ምርት መጠን ከዓመት
ዓመት እየጨመረ መጥቷል፡፡ የዚህ ምርት አምራቾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም የማህበረሰቡ
በፈሳሽ ሳሙና የመጠቀም ልምድ እያደገ በመምጣቱ የገቢ ምርቱ መጠን ሊጨምር እንደቻለ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ሰንጠረዥ-2.5፡ ደርቅ የልብስ ሳሙና ገቢ ምርት


የምርትዓይነት ዘመን Net wt (tone) CIF value (ETB) CIFvalue(USD) Total tax (ETB)
2010 11,783.22 151,204,388.1 10,448,995.92 79,890,637.7
2011 11,342.91 204,538,337.2 11,986,049.4 105,848,618
2012 8,560.04 160,908,372.91 9,006,603.36 83,309,389.8
ደረቅ የልብስ 2013 7,138.10 152,069,388.7 8,088,754.248 79,382,635.7
ሳሙና
2014 6,598.72 155,932,638.5 7,741,051.178 81,814,860.7
(laundery bar
2015 2,883.47 66,909,687.19 3,219,598.075 35,012,273.3
soap )
2016 2,910.3 69,221,292.84 3,154,566.92 36,158,481.59
2017 2,148.49 57,220,913.19 2,425,416.586 29,725,429.77
አማካይ 6,670.66 127,250,627.33 7,008,879.46 66,392,790.82

6
በሰንጠረዥ-2.5 ማየት እንደሚቻለው ከተለያዩ ሀገራት በውጭ ምንዛሬ ተገዝቶ ከ 2010 አስከ 2017 የገባው
ደረቅ የልብስ ሳሙና ምርት በአማካይ 6,670.66 ቶን ሲሆን ለዚህም 127,250,627.4 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡
ምንም እንኳን በነዚህ ስምንት አመታት ውስጥ ቀላል የማይባል ደረቅ የልብስ ሳሙና ገቢ ቢደረግም ከዓመት
ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ ገቢ ምርቱ እየቀነሰ መምጣቱን ከሰንጠረዥ 2.5 መረዳት ይቻላል፡፡ ይህም በሀገራችን
የሚገኙ አምራች ፋብሪካዎች ገቢ ምርትን እየተኩ ለመምጣታቸው ማሳያ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጥራትም ሆነ
ሙሉ ለሙሉ ገቢ ምርትን ለማስቀረት እንዲሁም ደንበኞች በየመንደሩ እየተመረቱ ያሉትን ሳሙናዎች ከጤና
ጋር ያለውን ችግር ወደ ጎን በመተው በዋጋ ቅናሽ በመሆናቸው ብቻ እየገዙ ያሉትን ለማስቀረትና ደረጃ
አሟልተው በኢንዱስትሪ እየተመረቱ ያሉትን በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት እንዲችሉ አምራቾች የመንግስትን
ድጋፍ ይፈልጋሉ፡፡
ሰንጠረዥ-2.6፡ ደረቅ የገላ ሳሙና ገቢ ምርት
የምርትዓይነት ዘመን Net wt CIF value (ETB) CIFvalue Total tax (ETB)
(tone) (USD)
2010 2,603.72 56,262,064.57 3,862,958.877 37,814,361.9

2011 3,563.76 85,679,286.88 5,020,849.29 56,850,077.06


ደረቅየገላሳሙና
(toilet bar 2012 3,723.61 117,311,967.31 6,566,360.34 78,164,315.38
soap )
2013 2,435.18 82,679,761.03 4,397,836.237 55,620,732.88

2014 3,031.48 117,878,522.3 5,851,909.403 79,282,643.72

2015 2,829.08 108,673,910.8 5,229,232.549 73,270,596.08

2016
2,450.89 99,293,077.8 4,525,004.457 66,904,888.61
2017
2,415.11 67,646,033.24 2,867,305.009 44,603,118.01
አማካይ
2,881.60 91,928,077.99 4,790,182.02 61,563,841.71

ሰንጠረዥ 2.6 እንደሚያመላክተው ከተለያዩ ሀገራት በውጭ ምንዛሬ ተገዝቶ ከ 2010 አስከ 2017 በአማካይ
የገባው ደረቅ የገላ ሳሙና ምርት 2,881.60 ቶን ሲሆን ለዚህም 91,928,077.99 ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

ሰንጠረዥ-2.7፡የዱቄት ሳሙና ገቢ ምርት


የምርትዓይነት ዘመን Net wt CIF value (ETB) CIFvalue Total tax (ETB)
(tone) (USD)
2010 4,515.14 56,283,060.29 3,864,400.45 29,150,778.34

2011 5,568.73 95,363,382.97 5,588,342.19 48,080,840.74


ዱቄትሳሙና
(soap in 2012 5,009.16 99,342,084.26 5,560,523.25 49,609,979.47

7
powder form)
2013 4,771.31 114,516,604.6 6,091,276.35 56,514,394.45

2014 5,795.14 160,322,374.7 7,958,973.31 79,293,738.64

2015 5,414.50 141,150,302.6 6,791,949.89 69,196,417.69

2016
5,629.85 128,931,151.5 5,875,676.8 64,463,547.23
2017
7,594.12 177,765,771.5 7,534,938.31 88,249,374.81
አማካይ
5,537.24 121,709,341.55 6,158,260.07 60,569,883.92

ሰንጠረዥ-2.7 እንደሚያመላክተው ከተለያዩ ሀገራት በውጭ ምንዛሬ ተገዝቶ ከ 2010 አስከ 2017
በአማካይ 5,537.24 ቶን የዱቄት ሳሙና ወደ ኢትዮጵያ የገባ ሲሆን ለዚህም 121,709,341.55 ብር ወጪ
ተደርጓል፡፡

2.1.4. የንዑስ ዘርፉ የገበያ ፍላጎት


ሳሙናና ዲተርጀንት ከሰው ልጅ የእለት ተዕለት ኑሮ ጋር ከፍተኛ መስተጋብርና ፍጆታ ያለው የኢንዱስትሪ ምርት ነው፡፡
እንደሚታወቀው ሀገራችን ሁሉን አቀፍ የሆነ እድገትና ለውጥ በማምጣት ላይ ስለሆነች ህዝቦቿም በዚያው ልክ
ፍላጎታቸውንና የኑሮ ዘያቸውን ከጊዜው ጋር ለማራመድ በአመለካከት፣ በአቅም፣ በአስተሳሰብ የተለወጡበት ጊዜ ላይ
ተደርሷል፡፡ ይህ ሲባል በሁሉም የሀገራችን አካባቢ በተለይም በገጠሪቱ ኢትዮጵያ በሚፈለገው ደረጃ ይህ ሁኔታ ተፈጥሯል
ማለት አይደለም፡፡ በመሆኑም ከጤና አጠባበቅና ከማህበራዊ ህይዎት አንጻር በአመለካከት ላይ ከተሰራ፤ የሀገራችን የህዝብ
ቁጥር እየጨመረ ከመመምጣቱ ጋር ተያይዞ ለዚህ ንዑስ ዘርፍ ከፍተኛ የገበያ እድል መፍጠሩ አይቀሬ ነው፡፡

እንደማሳያነት በ 2008 ዓ.ም በአስራ ሁለት ፋብሪካዎች የተመረተ የሳሙናና ዲተርጀንት የምርት መጠን 103,127.68
ቶንየነበረ ሲሆን ከዚህም በዓመቱ የ 1,942,264,316 ብር ከሽያጭ የተገኘ ገቢ አስመዝግበዋል፡፡ በ 2009 ዓ.ም በአስራ
አምስት የሳሙናና ዲተርጅንት ፋብሪካዎች የተመረተ የሳሙናና ዲተርጀንት የምርት መጠን 123,471.79 ቶን ሲሆን ከምርቱ
ሽያጭ የተገኘ ገቢ 2,399,937,737.99 ነው፡፡ በነዚህ ሁለት ተከታታይ ዓመታት የምርትም ይሁን የገበያ እድገት የታየ ሲሆን
ከምርት አንጻር የ 20, 344.1 ቶን እድገት ሲኖረው ከምርት ሺያጭ አንጻር ደግሞ የ 457,673,422 ብር እድገት አሳይቷል፡፡

2.2. የንዑስ ዘርፉ እሴት ጭማሪ


መንግስት አምራች ኢንዱሰትሪውን ለማነቃቃትና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ሁለተኛ መደብ
(ሀ) አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 45/2008 ማውጣቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በመሆኑም የዚህ መመሪያ ተጠቃሚ
እንዲሆኑ በዚህ ንዑስ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች መመሪያውን በመስጠት አስፈላጊውን መረጃና ቅጽ
ሞልተው እንዲያቀርቡ የተጠየቁ መሆናቸው ይታወሳል፡፡ በዚሁ መሰረት ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች
ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ማመልከቻቸውን ያስገቡ ድርጅቶችና አፈጻጸሙን በሰንጠረዥ 2.8 ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ-2.8፡ የፋብሪካዎች የእሴት ጭማሪ አፈጻጸም

ተ.ቁ የፋብሪካው ሁኔታ ብዛት የምስክር ወረቀቱን የምስክር ወረቀቱን አማካይ የእሴት
ያገኙ ያላገኙ ጭማሪ(%)
1 ሳሙናና ዲተርጀንት 19 12 7 23.06
8
አምራች

እንደሚታወቀው የጉምሩክ ታሪፍ ደንብ ሁለተኛ መደብ (ሀ) አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 45/2008 ሲወጣ
የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲን መረጃ መነሻ በማድረግ በሳሙናና ዲተርጀንት ንዑስ ዘርፍ ላይ 26 በመቶ
የእሴት ጭማሪ ምጣኔ መቀመጡ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በሰንጠረዥ-2.8 እንደምንረዳው የንዑስ ዘርፉ የእሴት
ጭማሪ (value addition) ከተወሰነው ምጣኔ በታች መሆኑን ነው፡፡ የእሴት ምጣኔያቸውን ማግኘት ከተቻለው
17 ፋብሪካዎች የተገኘ አማካይ የእሴት ጭማሬ (value addition) 23.09 በመቶ ሲሆን 12 ቱ ድርጅቶች
በመስፈርቱ መሰረት ከ 2009 በጀት ዓመት ጀምሮ እስከ 2010 በጀት ዓመት የምስክር ወረቀቱን ሲያገኙ 6 ቱ
የምስክር ወረቀቱን ያላገኙ ናቸው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ለ 2009 በጀት ዓመት የምስክር ወረቀቱን ካገኙ 11
ፋብሪካዎች ለ 2010 በጀት ዓመት የምስክር ወረቀቱን ያሳደሱት 3 ቱ ሲሆኑ አዲስ በበጀት ዓመቱ የምስክር
ወረቀት ያገኘ ፋብሪካ አንድ(1) ብቻ ነው፡፡

የንዑስ ዘርፉ እሴት ጭማሪ ከአምራቾች አቅም አንጻር

ከላይ በክፍል 2.2 ለማሳየት እንደተሞከረው የንዑስ ዘርፉ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ በከፍተኛ ሁኔታ የተራራቀ ነው፡፡ የዚህን
ንዑስ ዘርፍ አንቀሳቃሾች በሶስት ደረጃ ከፍሎ ለማየት ያስችለን ዘንድ የዚህ ጥናት አካል የተደረጉ ሳሙናና ዲተርጀንት
አምራችድርጅቶች አጠቃላይ ገጽታ በሰንጠረዥ-2.9 ቀርቧል፡፡

በጥናቱ በከፍተኛ ደረጃ የተፈረጁ አምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ (24.49%)፣ በመካከለኛ ደረጃ
የተፈረጁ አምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ (12.67%) እና አንድ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ አምራች
ኢንዱስትሪ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ (37%) ነው፡፡

37% የእሴት ጭማሪ ምጣኔ ያስመዘገበው አንድ ድርጅት ሲሆን ይህም ፈሳሽ ሳሙናን እያመረተ ያለና ከሌሎች ለየት ሊል
ችሏል፡፡ ለዚህ ከፍተኛ ምጣኔ መመዝገብ ምክንያት ተጨማሪ መረጃ የሚያስፈልግ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በኢንዱስትሪዎች መካከል
ሰፊ የሆነ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ ልዩነት መታየት እንደ ዋና ምክንያት ከሆኑ ምክንያቶች መካከል የመረጃ አያያዝ ችግር፣
በማምረት አቅምና በምርት ዕቅድ መካከል ሰፊ ልዩነት መኖሩ፣ የዕቅድ አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን፣ የምርት ሽያጭ ላይ ህግና
ስርዓትን ተከትሎ አለማከናዎን ከፋብሪካዎቹ ሁኔታ እንደምንረዳው የፈሳሽ ሳሙናን በከፍተኛ መጠን የሚያመርቱ አምራቾች
ደረቅ ሳሙናን ከሚያመርቱ ፋብሪካዎች የተሻለ እሴት ጭማሪ ማስመዝገባቸው እና ከውጭ በከፊል ያለቀለት ሶፕ
ኑድልስበራሳቸው ማምረት እየቻሉበማስመጣታቸው የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ከሳሙና እና ዲተርጀንት አምራቾች እስካሁን የሁለተኛ መደብ ታሪፍ ተጠቃሚ የሆኑት ሳፖኒፊኬሽን ፕላንት ያላቸው ወይም
ሶፕ ኑድል ጭምር እያመረቱ ያሉትናቸው፡፡ ፊኒሺንግ ላይን ብቻ ያላቸው በሁለተኛ መደብ ታሪፍ የተፈቀዱ ጥሬ ዕቃዎች
አነስተኛ በመሆናቸውና በብዛት ተፈላጊውን የዕሴት ምጣኔ ማሟላት ባለመቻላቸው ተጠቃሚ አይደሉም፡፡ የሶፕ ኑድሉን ብቻ
ኮስት ፐሮሰስ መስራ ያልተቻለው የሶፕ ኑድል አምራቾች ፊኒሺንግ ላይን ጭምር ያላቸው በመሆኑና የሚጠቀሙትን ጥሬ ዕቃ
እና ምርት ከሶፕ ኑድል ብቻ ነጥሎ የሚያሳይ መረጃ ማግኘት ባለመቻሉ ነው፡፡

9
ሰንጠረዥ-2.9፡ የሳሙናና ዲተርጀንት አምራቾች ከአቅም አንጻር ሲታዩ

ተ. የፋብሪካው ስም የሰው የምርትዓይነት የማምረት የምርትዕቅድ የምርትሂደት ካፒታል (በብር) ዓመታዊሽያጭ አአእሴት ደረጃ
ቁ ኃይል አቅም (በቶን) (በብር) ጭማ
(በቶን) ሪ
1 ቲቲኬ 269 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 56,800 13,465 -Saponfication 79,333,659.1 188,781,915. 21 ከፍተኛ
ኢንዱስትሪስኃ/የተ/የግ/ - የልብስፈሳሽሳሙና -Mixing 12

2 ኢሰትአፍሪካ ታይገር 1002 - ደረቅየልብስሳሙና 29,891.15 29,891.5 -Saponification 686,209,698 610,640,742 25.08 ከፍተኛ
ብራንድስ ኃ/የተ/የግ/ማ - የዱቄትሳሙና -Mixing
3 አህመድ ኑረዲን ሳሙና 191 - ደረቅየልብስሳሙና 16,200 12,150 -Saponfication 53,881,119 86,197,915.9 26 ከፍተኛ
ፋብሪካ 5
4 ጉለሌ ሳሙና ፋብሪካ 275 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 21,120 8,239 -Saponfcation 88,982,362.3 45,166,329 - ከፍተኛ
አ.ማ - ፈሳሽየልብስሳሙና -Mixing
5 ቶሪአ ሳሙናና 252 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 17,226 13,091.76 -Saponification 101,011,446 122,516,098 26.09 ከፍተኛ
ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ
6 እንዣት ኢንዱሰተሪያል 40 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 36,000 12,672 -Saponfication 47,661,997 118,390,781 32 ከፍተኛ
እና ኮመርሻል
ኃ/የተ/የግ/ማ
7 ክሬን ኃ/የተ/የግ/ማ 85 - ደረቅየገላናየልብስሳሙና 94,136 69,334 -Finishing line 18,916,232.4 24,567,199.7 16 መካከለ
cartons cartons ኛ
8 ኢታብ ሳሙና ፋብሪካ 477 - ደረቅየገላናየልብስሳሙና 70,500 35,394.92 -Saponfication 130,064,828 218,636,402 27.24 ከፍተኛ
ኃ/የተ/የግ/ማ
9 ቤካስ ኬሚካልስ 381 - ደረቅየገላናየልብስሳሙና 26,900 13,920.59 -Finishing line 116,609,293 157,719,540 34.5 ከፍተኛ
ኃ/የተ/የግ/ማ - የተለያዩፈሳሽሳሙናዎች -Mixing
10 ስታር ሳሙናና 254 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 29,080 8,325 -Saponfication 181,720,894 139,666,137 14 ከፍተኛ
ዲተርጀንት - ፈሳሽየልብስሳሙና -Mixing
- የዱቄትሳሙና
11 ታዛ ኃ/የተ/የግ/ማ 34 - የተለያዩፈሳሽሳሙናዎች 1,440 445 -Mixing 37,378,682.5 8,917,837.76 37 ዝቅተኛ
12 ረጲሳሙናናዲተርጀነትአ. 635 - ደረቅየእቃሳሙና 104,000 61,000 -Finising line 853,248,829 446,233,563 17 ከፍተኛ
ማ - ፈሳሽሳሙና -Mixing
- የልብስደረቅሳሙና
- የዱቄትሳሙና
13 ሸሙኃ/የተ/የግ/ማ 531 - በከፊልያለቀለትሳሙና 44,100 30,870 -Saponfication 244,490,286 የለም አዲስ ከፍተኛ
(ሶፕኑድልስ)
14 ታደሰ ፍላቴ ኃ/የተ/የግ/ማ 400 -ደረቅየልብስናየገላሳሙና 56,940 56,940 -Saponfication 59,980,000 154,808,755 33 ከፍተኛ

10
- ፈሳሽሳሙና
- ደረቅየእቃሳሙና
15 ጂአይቪ ሳሙና 218 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 2,654 2,654 -Finishing line 25,055,603.5 48,781,313.4 7 መካከለ
ማኑፋክቸራል - ፈሳሽየልብስሳሙና -Mixing 7 ኛ
ኃ/የተ/የግ/ማ - የዱቄትሳሙና
16 ኢ.ኤን.ዲ ግሎባል ፉድ 163 - በከፊልያለቀለትሳሙና 19,820 11,880 -Saponfication 75,183,934.3 የለም አዲስ ከፍተኛ
ኮምፕሌክስ ኃ/የተ/የግ/ማ /soap noodles/
17 አምደሁን ጠቅላላ ንግድ 190 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 13,877.25 8,297.44 -Finishing line 67,056,037.7 100,622,210 12 ከፍተኛ
ስራ ኃ/የተ/የግ/ማ - ፈሳሽየልብስሳሙና - saponification

18 ኢትዮ-ኤዥያ ሳሙና 248 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 26,292 7,920.34 Finishing line 13,028,000 15 መካከለ
ፋብሪካ ኛ
19 ናዝሬትና አርሲ ሳሙናና 126 -ደረቅየገላናየልብስሳሙና 6,936 5,600 Finishing line 54,947,810 58,515,169 26 ከፍተኛ
ዘይት ፋብሪካ - ፈሳሽየልብስሳሙና - saponification
ኃ/የተ/የግ/ማ

11
2.3. የንዑስ ዘርፉ ጥሬ ዕቃዎች(Basic Raw Materials)
የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ፋብሪካዎች ለምርት ሂደታቸው እንደግብዓትነት የሚጠቀሟቸውን ጥሬ ዕቃዎች ከሀገር
ውስጥ እና ከውጭ ሀገር ብቻ ተገዝተው የሚመጡ ግብዓቶችን እንደሚጠቀሙ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዚህ ክፍል
የኢንዱስትሪውን የጥሬ ዕቃ ሁኔታ በሰፊው ለማየት ተሞክሯል፡፡

2.3.1. አገር ውስጥ የማይገኙ የሳሙናና ዲተርጀንት ጥሬ ዕቃዎች


ከሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ አጠቃቀም አንጻር አገር ውስጥ የማይገኙ ግብዓቶች በ 3 የተከፈሉ ሲሆን 1 ኛ ለዘርፉ
በሁለተኛ መደብ/ሀ/ የተፈቀዱ 2 ኛ በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ የተመደቡ ሆነው ነገር ግን ለዘርፉ ያልተፈቀዱ 3 ኛ
በአንደኛ መደብ ታሪፍ የተመደቡ በሚል የተለዩ ሲሆን የነዚህ ጥሬ ዕቃዎች ለሳሙናና ዲተርጀንት ምርት ያላቸውን ጥቅም፣
የቀረጥ መጠን እና ኤች.ኤስ ኮድ (HS Code) በማካተት ከሰንጠረዥ 2.10 እስከ 2.13 ቀርበዋል፡፡

12
3.3.1.1. ለንዑስ ዘርፉ በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ የተፈቀዱ ጥሬ ዕቃዎች

የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ፋብሪካዎች በምርት ሂደታቸው እንደአስፈላጊነታቸው ጥራታቸውን የጠበቁና ተወዳዳሪ ምርቶችን ለማምረት ከውጭ ሀገር ብቻ ተገዝተው ሊመጡ
የሚችሉ ጥሬ እቃዎች በሰንጠረዥ 2.10 እንደምንመለከተው አስራ አራት /14/ የሚሆኑትና በስምንት /8/ የተለያዩ የታሪፍ ቁጥሮች የተወከሉትን ጥሬ እቃዎች በሁለተኛ መደብ ታሪፍ
/ሀ/ እንዲያስገቡ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

ሰንጠረዥ-2.10፡ለሳሙናና ድተርጀንት አምራቾች በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ የተፈቀዱ ጥሬ ዕቃዎች


ተ.ቁ የታሪፍቁጥር ቀረጥ
ከውጭሀገርብቻየሚገቡጥሬእቃዎች /HS code/ /duty/ የጥሬዕቃውምንነት /raw material application description/
1 Palm fatty Acid Distilled (PFAD) 38231900 10 It is one of the main raw material ingredients for toilet and laundry bar soap
production.
It is converted in to soap after being reacted with alkali hydroxides.
2 Distillate palm fatty acid (DPFA) 38231900 10 It is one of the main raw material ingredients for toilet and laundry bar soap
production.
It is converted in to soap after being reacted with alkali hydroxides.
3 Refined Bleached deodorized 38231900 10 It is one of the main raw material ingredients for toilet and laundry bar soap
palm stearin (RBD palm sterin) production.
It is converted in to soap after being reacted with alkali hydroxides.
4 Pigment (color) 32041700 05 Coloring agent for soaps and detergents, i.e, for liquid, powder, paste, and bar
detergents and soaps.
5 Lauric acid oil 38231900 10 It is one of the main raw material ingredients for toilet and laundry bar soap
production.
It is converted in to soap after being reacted with alkali hydroxides.
6 Optical brightener 32042000 05 Usually incorporated in to soap and detergents to enhance the color brightening
effect of the cleaned fabrics especially white clothes.
7 Crude palm kernel oil 38231900 05 It is one of the main raw material ingredients for toilet and laundry bar soap
production.
It is converted in to soap after being reacted with alkali hydroxides.

13
8 Coconut oil 38231900 05 One of the main raw material in soap production through saponification
processes. When hydrolysed by chemical reaction, it gives soap. It will also
process further to produce better quality synthetic surfactants.
9 Savinase 8.0 T, Medley Brilliant 35079000 10 An enzyme incorporated in detergents to remove strong stains in safer
(Enzymes) condition from fabrics.
10 Tri ethanol amine 29221310 10 Organic pH neutralizing agents during detergents production. It is an important
ingredient in some detergent formulas because of its mildness and dirt cleaning
property.
It also increases the viscosity of liquid detergents.
11 Ester solvents 38249090 05 Cleaning solvents:- removing paints , dirt and oils from surface
(other chemical products & They are relatively unreactive and as a result they are useful as a solvent for
residuals) extraction and chemical reactions
12 Zeolite 38249090 05 Water hardness removing ingredient usually used in powder detergents.

13 Sodium hydroxide 28151100 10 Used to prepare soap from their fatty raw materials and also used to adjust the
(Caustic soda) PH value of soaps and detergents to required standard value. It has also a
cleaning role in some industrial and institutional cleaners
14 HCl 28061000 05 One of the ingredients used in acidic detergent especially in marble cleaning
products for construction industry

3.3.1.2. በሁለተኛመደብ /ሀ/ ታሪፍ የተመደቡ ነገር ግን ለሳሙናና ዲተርጀንት አምራቾች ያልተፈቀዱ ጥሬ ዕቃዎች

በሰንጠረዥ 2.11 የተዘረዘሩት 42 የሚሆኑትና በአስራ ዘጠኝ /19/ የተለያዩ የታሪፍ ቁጥሮች የተወከሉት ግብዓቶች ምንም እንኳን በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ ቢመደቡም ለሌሎች
ዘርፎች (ለቆዳ ውጤቶች አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ለብረታ ብረት ፋብሪካዎች፣ ለመስታወት አምራች ፋብሪካዎች፣ ለመድሀኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች አምራች
ፋብሪካዎች፣ ለጎማ ፋብሪካዎች፣ ለምግብ ፋብሪካዎች) የተፈቀዱ ሲሆኑ ለሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ፋብሪካዎች አልተፈቀዱም፡፡ በመሆኑም ከታች በሰንጠረዥ 2.11 ከተዘረዘሩት
42 ጥሬ እቃዎች መካከል 18 ቱ አስተያየት በሚለው ኮለመን ስር የተጠቀሱት ጥሬ ዕቃዎች ለዘርፉ መፈቀድ አለባቸው ብለን ያመንባቸው ናቸው፡፡

ሰንጠረዥ-2.11፡ በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ የተመደቡ ነገር ግን ለሳሙናና ዲተርጀንት አምራቾች ያልተፈቀዱ ጥሬ ዕቃዎች

14
ተ. ከውጭሀገርብቻየሚገቡጥሬእ የታሪፍቁጥር ቀረጥ አስተያየት
ቁ ቃዎች /HS code/ /duty/ የጥሬዕቃውምንነት /raw material application description/

1 Sodium lauryl sulfate 34021190 10 Raw material for liquid, bar and powder detergents. It has cleaning, foaming ለዘርፉቢፈቀድ
and wetting property.
2 Sodium carboxy methyl 39123100 05 Soil anti re-deposition agent used in soap and detergents. It disperses the soils ለዘርፉቢፈቀድ
cellulose (CMC) removed from the clothes by detergent in to the wash liquor.
3 SLES, TEA-LES 34021190 10 It is a good cleaning, wetting and foaming agent used in detergents. It is also ለዘርፉቢፈቀድ
used in cosmetic products such as shampoos.
4 Alfa Olefine sulfonate 34021190 10 One of anionic surfactant to produce detergents. It has cleaning, wetting and ለዘርፉቢፈቀድ
(AOS) foaming power.
5 CDE, CAPB, Lauryl alkyl 34021390 10 Mild surface active agents which are used along with other surface agents in -
polyglucoside different amounts in different detergent products such as liquid dish wash,
liquid hand washes, etc.
6 Cellosize HEC QP100 M-H 39123900 05 Poly acrylic polymer used as dispersing agent and viscosity improving ለዘርፉቢፈቀድ
ingredients in liquid detergents.
7 Cetrimonium chloride 34021290 10 Cationic surfactant used in hair conditioners and shampoos. It is a ለዘርፉቢፈቀድ
conditioning agent.
8 Betadet THC-2 34021390 10 Cleaning surfactant used in shampoos and others preparation. -
9 Amidet N 34021390 10 Viscosity adjusting and emollient surfactant used in liquid detergents and ለዘርፉቢፈቀድ
shampoos.
10 Akypo RLM-45 CA 34021190 10 Non ionic surfactant used in shampoos and other liquid cleaners. -
11 Levenal H&B 34021390 10 A cleaning agent used in shampoos and others liquid cleaner’s preparation. -
12 Glucopn 215 UP 34021390 10 Non ionic surfactant used for hard surface cleaning products. It is also used to -
prepare industrial application cleaners.
13 Tetranyl U , Tetranyl 7590 34021290 10 Cationic Surfactant used as a softening agent in textile softener products. -
14 Polyoxy ethylated sorbitan 34021390 10 Emulsifying and emollient agent used in shampoos, hand cleaners and others. -
15 Ethylene glycol di stearate 34021390 10 Pearly appearance giving agent to liquid detergents and shampoos. -
(EGD)
16 Polyquartanium -10 34021290 10 Hair and skin conditioning agent used in shampoos and conditioners. -
17 Sodium benzoate 29163100 05 Mild preservative or germ killing agent preserving detergent and cosmetic ለዘርፉቢፈቀድ
products.

15
18 Ablutex OK-44, ablunol 34021390 10 Non ionic surfactants used for preparation of liquid detergents and industrial ለዘርፉቢፈቀድ
AEO-9, etc… surfactants.
19 Antifoam, Dimethicone 39100000 05 Silicone based polymers used as defoaming and also lubricating agent. ለዘርፉቢፈቀድ
20 Korantin LUb 34021390 10 Anionic surfactant used for industrial purpose cleaner’s production. -
21 Lutensol FA12 34021290 10 Non ionic surfactant used to impart degreasing, lubrication, and wetting effect -
to detergents especially to industrial cleaners.
22 Diethanol amine 34021390 10 A reactant input to produce locally a non ionic surfactant called diethanol ለዘርፉቢፈቀድ
amide (CDE) which is the common viscosity improver in liquid detergents.
23 Boric Acid 28100000 05 Incorporated in enzymatic liquid detergent mainly with a function of ለዘርፉቢፈቀድ
stabilizing effect of the enzyme in the detergent formula.
24 Cetearyl alcohol, Cetyl 38237000 05 Used to modify viscosity and function as an emollient lubricant in hair -
alcohol conditioner products and others personal care products.
25 Isopropanol 29051200 05 Solvent :- it removes oils and paints from surfaces ለዘርፉቢፈቀድ
Deodorizing agent:- by disinfecting the bacterial and other germs it gives
certain fresh smell.
Disinfectant:-Used as a cleaning solvent in hard surface cleaners and as a
sanitizing agent in hand sanitizer products.
26 Phosphate ester 34021190 10 Corrosion inhibitor:- it prevents corrosion from happening -
other organic surface-active
agents(other than soap)
27 Anionic surfactants 34021190 10 They are widely used for laundry and dishwashing detergents. ለዘርፉቢፈቀድ
They are particularly good in keeping the dirt, once dislodged away from
fabrics
28 Cationic surfactant 34021290 10 Usually used as a disinfecting, cleaning and conditioning agent in different ለዘርፉቢፈቀድ
types of detergents.
29 Nonionic surfactants 34021390 10 Most advantage is that they do not interact with calcium and magnesium ions ለዘርፉቢፈቀድ
in hard water
30 Trimethoxy benzoic acid 29163100 10 It is one of the main compounds That are used as an anti-oxidant and an ለዘርፉቢፈቀድ
oxygen bleacher.
31 Ether solvent ( bb1) 34021210 05 They are relatively unreactive and as a result they are useful as a solvent for -
extraction and chemical reactions

16
One of the surface active ingredients used as an input detergent disinfectant
32 Ether solvent ( bb2) 34021210 05 Cleaning solvents:- removing paints , dirt and oils from surface. ለዘርፉቢፈቀድ
They are relatively unreactive and as a result they are useful as a solvent for
extraction and chemical reactions.
One of the surface active ingredients used as an input in laundry detergent,
hand soap, dish wash and antiseptic disinfectant
33 Pine solvent ( bb4) 34021210 05 It helps to disinfect germs and clean up by solublising stains in sanitizer -
disinfectants.
34 Buster 34021190 10 Buffering agent:- keep the PH at the appropriate value -
It is also a foaming agent
35 Metocell 39123100 10 It provides in the moisturizing process where in the terms of usage helps in -
keep preventing irritation on the hands
36 Oleic acid 38231200 Emollient:- function asemollients or moisturizers chemical agents specially -
05 designated to make the external layers of the skin softer and more pliable
37 Citric acid 29181400 05 It is an excellent chelating agent. -
It is an active ingredient in some bathrooms and kitchen cleaning solutions.
Used to adjust the PH value of soaps and detergents and other personal care
products to standard PH value. It has also preservation effects.
38 Ternaryl co40 34021290 10 One of the cationic surfactant incorporated in to shampoos and hair -
conditioners for its softening capacity.
39 Glycerol 29054500 10 Used in toilet soaps and liquid hand cleaner detergents mainly as a -
moisturizing agent.
40 Methanol 29051100 10 Used to produce locally a biodiesel product methyl ester of fats and oils and -
also glycerin. The methyl ester may in turn used to produce vegetable oil
derived non ionic surfactants through chemical reaction.
41 Sodium xylenesulfonate 29041000 10 Surfactants for soli suspension:- they hold soli dirt in suspension and so -
allow their removal
42 Titanium dioxide 32061900 05 It gives white color to toilet and laundry bar soaps -

17
3.3.1.3. በአንደኛ መደብ ታሪፍ የተመደቡ ጥሬ ዕቃዎች

ለሳሙናና ዲተርጀንት ምርት ከሚያስፈልጉ ከውጭ ሀገር ብቻ የሚገቡ ጥሬ ዕቃዎች መካከል 19 የሚሆኑትና
በ 13 የተለያዩ የታሪፍ ቁጥር የተወከሉት ግብዓቶች በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ ያልተመደቡ ሲሆን ጥሬ ዕቃዎቹ
ለኢንዱስትሪዎቹ ያላቸውን ጥቅምና አስፈላጊነት በሰንጠረዥ 2.12 ተዘርዝረዋል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለልማትና እድገቷ የሚያስፈልጋትን ሀብት ከምታገኝበት መንገድ አንዱ የቀረጥ ስርዓቷ
ነው፡፡ በመሆኑም ከላይ በሰንጠረዥ 2.11 የተቀመጡት ጥሬ ዕቃዎች ከአንደኛ መደብ ታሪፍ ወደ ሁለተኛ መደብ
/ሀ/ ታሪፍ ቢመደቡና ኢንዱስትሪዎቹ የሚፈጥሩት የስራ ዕድል፣ የሚያስገኙት የግብር ገቢ፣ የሚያስቀሩት
የውጭ ምንዛሬ፣ የሚያስገቡት የውጭ ምንዛሬ ወዘተ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ በታሪፍ ማሻሻያው ምክንያት
ሀገራችን ልታጣው የምትችለውን የቀረጥ ገቢና አጠቃላይ ህግና ስርዓቱን በማነጻጸር በሚመለከተው የመንግስት
አካል ውሳኔ ቢሰጠው እንላለን፡፡ በመሆኑም ከታች በሰንጠረዥ 2.12 ከተዘረዘሩት 19 ጥሬ እቃዎች መካከል 4 ቱ አስተያየት
በሚለው ኮለመን ስር የተጠቀሱት ጥሬ ዕቃዎች ከአንደኛ መደብ ወደ ሁለተኛ መደብ ታሪፍ /ሀ/ ተመድበው ለዘርፉ መፈቀድ
አለባቸው ብለን ያመንባቸው ናቸው፡፡

18
ሰንጠረዥ-2.12፡ በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ ያልተመደቡ ነገር ግን ለሳሙናና ዲተርጀንት አምራቾች ግብዓት የሚሆኑ ጥሬ ዕቃዎች
ተ.ቁ ከውጭሀገርብቻየሚገቡጥሬ የታሪፍቁጥር ቀረጥ አስተያየት
እቃዎች /HS code/ /duty/ የጥሬዕቃውምንነት /raw material application description/
1 Essential oils 33019090 30 Essential oils render soaps and detergents pleasant and appealing odor.
2 Filler 25182000 05 Used to fill the formula of soaps mainly as diluting agent and imparts ለዘርፉቢፈ
some physical properties such as shape, firmness, and flow to the ቀድ
finished soap and detergent products.
3 Coconut Diethanol 34021130 05 Used to enhance skin safety of detergents acting as emollient and also
Amide(CDEA) used to increase viscosity of liquid detergents to required level.
4 Base MK, betadest S-20 34021900 10 Base MK is used as a softening agent in a softener product used in
textile industry as a process aid.
5 Sodium Metasilicate 28391100 20 An alkaline builder used as sequestering agent by removing water
hardness ion causing metallic cations which otherwise interfere with
the detergent activity during application. It also acts as anticorrosion
agent to protect metallic equipments treated with the detergents.
6 Aluminum sulphate 28332200 20 One of the important chemical used in glass window sealant putty ለዘርፉቢፈ
production. It makes the product to have elastic property and adhesive ቀድ
quality.
7 Linseed oil 23062000 10 Fatty matter source imparting the putty product elastic and consistent
physical property.
8 Cotton oil 23061000 10 Oil used to for production of different lubricant products through
chemical modifications.
9 Avocado oil 15100090 20 Nutritive and lubricating ingredient in cosmetic products such as
shampoos and conditioners and other hair and skin care products.
10 Vitamin 29362800 05 A nutrient ingredient in skin and hair care products.
11 Sodium di silicate (CDS) 28391100 20 Silicate polymer used as a builder usually substituting partially sodium ለዘርፉቢፈ
tripoly phosphate(STPP) ቀድ
12 Alkyl amine oxide 34021900 10 Long chain alkyl oxide surface active agent with special properties

19
such as anticorrosion, acid and alkali stability so incorporated in to
different special products formula.
13 ACR-4500 39061000 05 Poly acrylic product used as dispersing and viscosity improving
ingredient in liquid detergents.
14 Ammonium chloride 25010090 05 Bleaching agent:-bleaches stains. ለዘርፉቢፈ
Deodorizing agent: - by disinfecting the bacterial and other germs it ቀድ
gives certain fresh smell.
Cleaning and furnishing agent
15 Sodium meta silicate, 28391100 20 Cleaning agent:- contributes to the cleaning process
pent hydrate Degreasing agent:- helps on removing grease from surfaces
Builders:- remove calcium and magnesium ions and prevent loss of
surfactants through scum formation
16 Amphoteric surfactants 34021900 10 Surface active materials:-hold dirt and oils in suspension and so allow
their removal.
play a certain role in shower jells in helping protecting the skin from
irritation
17 Blends of surfactants 34021900 10 Are combinations of two or more of the anionic, non ionic , cationic
and amphoteric surfactants to be used as cleaning agent
18 Industrial fragrance 33030000 35 Provides a good smell to the products.
Used to give soap and detergents as well as other personal care
products to have attractive characteristic odor
19 Ether solvent ( bb3) 34021130 05 Cleaning solvents:- removing paints , dirt and oils from surface.
They are relatively unreactive and as a result they are useful as a
solvent for extraction and chemical reactions
They also are helpful in the thickening process of the liquid cleaners.
They are one of the ingredients in the production of laundry hand and
dish wash detergent

20
2.3.2. አገር ውስጥ የሚገኙ የሳሙናና ዲተርጀንት ጥሬ ዕቃዎች

በሰንጠረዥ 2.13 የተዘረዘሩት ጥሬ ዕቃዎች ከላይ በሰንጠረዥ (2.10-2.12) ከተዘረዘሩት ግብዓቶች


በተጨማሪ የሳሙናና ዲተርጀንት ምርቶችን ለማምረት የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ግብዓቶች ናቸው፡፡
ከሰባቱ /7/ ጥሬ ዕቃዎች መካከል ሁለቱ /2/ ለዘርፉ የተፈቀዱ፣ ሶስቱ /3/ በሁለተኛ መደብ ተመድበው
ለዘርፉ ያልተፈቀዱ እና ሁለቱ /2/ በአንደኛ መደብ የተመደቡ ቢሆኑም በሀገር በቀል አምራች
ድርጅቶች የሚመረቱ በመሆናቸው በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ መመደብና መፍቀድ ለአገር ውስጥ
አምራቾች ተወዳዳሪነታቸውንና ተስፋፊነታቸውን ያቀጭጫል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ለማፋጠን
መንግስት በሁሉም ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራቾችን በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እነዚህን
ጥሬ እቃዎች የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች ውስንነት ቢኖርባቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻሉ
የሚመጡበትን አቅም እንዲፈጥሩ መንግስትና ባለ ሀብቱ የድርሻቸውን መወጣት አለባቸው፡፡
በአሁኑ ወቅት ሀገር ውስጥ የሚመረቱ አንዳንድ ጥሬ ዕቃዎች ላይ የሚታዩ ችግሮች

1. የጥራታቸው ሁኔታ
2. የፍላጎትን ያህል አቅርቦት አለመኖር
3. ከዋጋ አንጻር ተመጣጣኝ ያለመሆን ችግር ሲሆኑ

ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት የቤት ስራቸውን ከተወጡ እነዚህ ችግሮች መፈታት የሚችሉ ስለሆኑ
በሚፈለገው ጥራትና ፍላጎት መጠን በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ለደንበኞቻቸው ማቅረብ
የሚችሉበት አቅም መፈጠር አለበት፡፡ ይህ ከሆነ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት የስራ መቆራረጥን
ማስቀረት ይቻላል፤ የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት ይቻላል፤ እያንዳንዱ ኢንዱስትሪ አንዱ ለአንዱ
ተመጋጋቢ የሚሆኑበትን ሁኔታ በመፍጠር የኢንደስትሪውን የትስስርሥርዓትመፍጠር ያስችላል

21
ሰንጠረዥ-2.13 ሀገር ውስጥ የሚገኙ የሳሙናና ዲተርጀንት ምርት ግብዓቶች

ተ በሀገርውስጥየሚገኙጥሬ የታሪፍቁጥር ቀረጥ በሁለተኛመ በሁለተኛመደብ (ሀ)


.ቁ እቃዎች /HS code/ /duty/ ደብ (ሀ) የተመደቡ የጥሬዕቃውምንነት /raw material application description/
ያልተመደቡ ለዘርፉየተ ለዘርፉያል
ፈቀዱ ተፈቀዱ
1 Hydrogen peroxide 28470000 10  Bleaching agent to whiten up soap produced through
saponification process. It is also used as disinfecting
and stain removing agent in detergents formula.
2 Ethanol 22071000 35  A solvent and stain remover used in hard surface
cleaners and main ingredient in hand sanitizer products.
3 Soda ash (sodium 28362000 05  Alkaline powder used to neutralize acidic surfactant
carbonate) ingredients in powder detergents and plays as a pH
buffering agent and hardness removing agent in powder
detergents.
4 Sodium chloride 25010010 10  Usually used to increase viscosity of liquid detergents
to required level
5 Alkaline silicate 28391900 20  It is a builder ingredient used as pH buffering and
water hardness removing agent in soaps and detergents
6 Soap noodles 34012010 10  It is a semi finished soap in to a shape of noodle
granules so that it can be simply used to produce
required soap products. It makes the soap product to
have a cleaning, wetting and foaming ability
7 Labsa 34021110 05  Primary surface active agent used in detergents
production for its cleaning and foaming ability

22
የሳሙ ና ቀለም ና ተዛማ ጅ ው ጤ ቶች ኢ/ል ዳይሬክቶሬት

2.3.3 የሶፕ ኑድልስ አምራች ኢንዱስትሪ


ከዚህ በፊት በአገራችን የሚገኙ ሁሉም የሳሙና ኢንደስትሪዎች ለሳሙና መሥሪያ ግብዓት የሆነውን ሶፕ
ኑድልስ የተባለ በከፊል ያለቀለት ሳሙና ከአገር ውስጥ ከሚገኝ ሞራ እና ከውጭ በሚገባ ፓልም ኦይል
በመጠቀም ለራሳቸው ያመርቱ ነበር፡፡ ይሁንና ይህንን ሶፕ ኑድልስ ለማምረት ከውጭ የሚገባው ጥሬ ዕቃ
ቀረጥ እና በከፊል የተጠናቀቀ ሳሙና(ሶፕ ኑድልስ) የሚጣልበት ቀረጥ ተመሳሳይ በመሆኑ በራሳቸው ሶፕ
ኑድልስ የሚያመርቱ ድርጅቶችአብዛኛዎቹ በማቆም ሶፕ ኑድልስ ከውጭ በማስመጣታቸው የንዑስ ዘርፉን
እሴት ሰንሰለት ከማሳነሱም በላይ ለአገሪቱና ለንዑስ ዘርፉ የምታወጣው የውጭ ምንዛሪ ኢንዲንር
አድርጎታል፡፡ ለማሳየት ያህል ባለፉት አምስት ዓመታት ከውጭ የገባውን የሶፕ ኑድልስ ምርት በሰንጠረዥ 2.15
መመልከት ይቻላል፡፡

በሰንጠረዥ 2.15 ከ 2013-2017 በከፊል የተጠናቀቀ ሳሙና (ሶፕ ኑድል) ገቢ ምርት ዳታ


Year of import Gross wt. Net wt. per CIF value ETB CIF value USD
(ton) (ton)
2013 11,697.90 11,522.47 19,6438,054.5 10,448,777.11
2014 21,633.46 21,499.981 409,583,393.6 20,333,177.46
2015 32,205.72 31,998.4 582,099,418.32 28,009,788.2
2016 45,039.24 44,468.65 831,617,346.7 37,898,635.87
2017 30,446.44 30,223.55 648,286,839.7 27,478,863.34
አማካይ 28,204.552 27,942.61 533,605,010.56 24,833,848.39

በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ የሳሙና ፋብሪካዎች ውስጥ ሶፕ ኑድልስ (በከፊል ያለቀለት ሳሙና) በማምረት
ላይ የሚገኙ ፋብሪካዎችና የማምረት አቅማቸው በሰንጠረዥ 2.16 የቀረበውን ይመስላል፡፡

ሰንጠረዥ 2.16 የሀገር ውስጥ የሶፕ ኑድል አምራች ፋብሪካዎች የማምረትዓቅም

ተ. የፋብሪካው ስም የምርቱ ዓይነት የማምረት ዓቅም የማምረት ዓቅም


ቁ (ቶን በስዓት) (ቶን በዓመት)
1 ቲቲኬኢንዱስትሪስ ኃ/የተ/የግ/ማ ሶፕ ኑድልስ 2 8,640

23
የሳሙ ና ቀለም ና ተዛማ ጅ ው ጤ ቶች ኢ/ል ዳይሬክቶሬት

2 ኢሰት አፍሪካ ታይገር ብራንድስ ሶፕ ኑድልስ 4.5 19,440


ኃ/የተ/የግ/ማ
3 አህመድ ኑረድን አብደላ ሳሙና ፋብሪካ ሶፕ ኑድልስ 2.5 10,800
4 ጉለሌ ሳሙና ፋብሪካ አ.ማ ሶፕ ኑድልስ 1.5 6,480
5 ቶሪአ ሳሙናና ዲተርጀንት ኃ/የተ/የግ/ማ ሶፕ ኑድልስ 6 25,920
6 እንዣት ኢንዱሰተሪያል እና ኮመርሻል ሶፕ ኑድልስ 6 25,920
ኃ/የተ/የግ/ማ
7 ኢታብ ሳሙና ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ሶፕ ኑድልስ 5 21,600
8 ስታር ሳሙናና ዲተርጀንት ሶፕ ኑድልስ 3 12,960
9 ሸሙ ኃ/የተ/የግ/ማ ሶፕ ኑድልስ 6.5 28,080
10 ታደሰ ፍላቴ ኃ/የተ/የግ/ማ ሶፕ ኑድልስ 4 17,280
11 ኢ.ኤን.ዲ ግሎባል ፉድ ኮምፕሌክስ ሶፕ ኑድልስ 3 12,960
ኃ/የተ/የግ/ማ
12 አምደሁን ጠቅላላ ንግድ ስራ ሶፕ ኑድልስ 1.5 6,480
ኃ/የተ/የግ/ማ
13 ናዝሬት እና አርሲ የሳሙናና የዘይት ሶፕ ኑድልስ 2 8,640
ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ
14 ፓልም ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ ሶፕ ኑድልስ 4 17280
15 ፓስፊክ ሳሙና ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ሶፕ ኑድልስ 1.5 6480
ድምር 53 228,960

የሳሙና፣ ቀለምና ተዛማጅ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክቶሬት ባለው መረጃ መሰረት ከላይ
ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሌሎች የሳፖንፊኬሽን ላይን ያላቸው (ለምሳሌ ዛክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ፣ ኢትዮ-
ኤዥያ ኃ/የተ/የግ/ማ) ነገር ግን በተለያየ ምክንያት የማያመርቱ ፋብሪካዎች በመኖራቸው የእነዚህን
ፋብሪካዎች ችግር በመፍታት ወደ ምርት በማስገባት የማምረት አቅሙን ከፍ ማድረግ የሚቻል ሲሆን
ዳይሬክቶሬቱ ያልደረሰባቸው ተጨማሪ ፋብሪካዎች ሊኖሩ እንደሚችሉም ግምት ውስጥ ማስገባት ተገቢ
ነው፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት ከውጭ የገባ አማካይ የሶፕ ኑድል ምርት (Gross weight) 28,204.552 ቶን ሲሆን
በሃገር ውስጥ የማምረት ዓቅም (Design Capacity) የዛክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ኢትዮ-ኤዥያ
ኃ/የተ/የግ/ማ የሶፕ ኑድል ምርትን ሳይጨምር 228,960 ቶን ነው፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው በሀገር ውስጥ
ከበቂ በላይ ግብዓት ማምረት መቻሉን ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በንዑስ ዘርፉ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የታክስ ምጣኔው እንደሚስተካከል ተስፋ በማድረግ
ሶፕ ኑድልስ የተባለውን የሳሙና ጥሬ ዕቃ ከራሳቸው አልፈው ለንዑስ ዘርፉ ለማቅረብ ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡
ሌሎችም እንዱስትሪዎች በፕሮጀክት ትግበራ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሀገር ውስጥ ሳሙና አምራቾችን
ለማበረታታትናሌሎችም ወደ ማምረት ሂደቱ ለማምጣት ያለቀለት የሳሙና ምርት ከውጭ የሚገባው በ
30% ታክስ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ለሳሙና ግብዓት የሆነው ሶፕ ኑድልስ ላይምየንዑስ ዘርፉን እሴት
ሰንሰለት ለመጨመር፣ ሀገራችን ለንዑስ ዘርፉ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ መጠን ለመቀነስ፣ የሶፕ
ኑድልሱከ 13-25 በመቶ ውሀ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለዚህ ይወጣ የነበረውን የትራንስፖርት ወጪን ለመቀነስ

24
የሳሙ ና ቀለም ና ተዛማ ጅ ው ጤ ቶች ኢ/ል ዳይሬክቶሬት

ሲባል እና የንዑስ ዘርፉን አጠቃላይ ምርት ለመጨመር ሶፕ ኑድልስ ላይናሶፕ ኑድልስ ለማምረት የሚውሉ
ግብዓቶች ላይ የታሪፍ ማስተካከያ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

25
የሳሙ ና ቀለም ና ተዛማ ጅ ው ጤ ቶች ኢ/ል ዳይሬክቶሬት

3. ማጠቃለያ /Conclusion/
 የዚህ ጥናት ዓላማ መንግስት በአገር ውስጥ በማኑፋክቸሪንግ ንኡስ ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች
(የሳሙናና ዲቲርጅንት) ገቢ ምርት መተካት እንዲችሉና ከውጭ ከሚገባው ተመሳሳይ ምርት ጋር በገበያ
መወዳደር እንዲችሉ ከውጭ በሚገቡ ግብዓቶች ላይ በሰጠው የታክስ ከለላ መሰረት የጉምሩክ ሁለተኛ መደብ
(ሀ) ታሪፍ ተጠቃሚ በማድረግ የሳሙናና ዲተርጅንት ኢንዱስትሪዎች በቂ ግብዓት አግኝተው ጥራት ያለውን
ምርት በማምረት ከአገር ውስጥ ገበያ በተጨማሪ በውጭ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ዘርፉን በስፋት
በመዳሰስ እንደገና በማየት ሊሻሻል የሚችልበትን ሁኔታ መፍጠር ነው፡፡
 የሳሙናና የዲተርጀንትፋብሪካዎችን መረጃ ማሰባሰብ፣ የኢትዮጵያ ኬሚካልና የኬሚካል ውጤቶች ዘርፍ ማህበርን
ማወያየት፣ ከተመረጡ ፋብሪካዎች ባለሙያዎችን ማሳተፍ፣ የተለያዩ ድረ-ገጾችን መጠቀም፣ የማዕከላዊ
ስታትስቲክስ ኤጄንሲን መረጃ መጠቀም እና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መረጃዎችን በግብአትነት
መጠቀም የዚህ ጥናት ዘዴ/ methodology/ ነበሩ፡፡
 ለሌሎች ዘርፎች በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታርፍ የተፈቀዱ ጥሬ ዕቃዎች ለንዑስ ዘርፉ አምራቾችም የሚፈቀድበትን
ሁኔታ በማመላከትና እንዲሁም የተጣለውን የተጨማሪ እሴት ምጣኔ (value addition) ከነባራዊ ሁኔታ
በመነሳት እንደገና በማየት ሊሻሻል የሚችልበትን ሁኔታ በማሳየት የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ኢንዱስትሪዎች
ለሀገሪቱ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ይህ ጥናት ተደርጓል፡፡
 እንደናሙና በተወሰዱ የሳሙናና ዲተርጀንት ፋብሪካዎች 5,256 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር
94,542.28 ቶን የሳሙናና ዲተርጀንት ምርት በማምረት የገቢ ምርትን በመተካት ላይ ናቸው፡፡
 በሳሙናና ዲተርጀንት፣ ንዑስ ዘርፍ የተመዘገበው የማምረት አቅም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ቢሆንም ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተሻሻለ መምጣቱን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 የጥናቱ አካል ከተደረጉ 12 የሳሙናና ዲተርጀንት ፋብሪካዎች የተገኘ አማካይ የእሴት ጭማሬ (value
addition) 24.49 በመቶ ሲሆን በጥናቱ በከፍተኛ ደረጃ የተፈረጁ አምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የእሴት
ጭማሪ ምጣኔ (18.85%)፣ በመካከለኛ ደረጃ የተፈረጁ አምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ
(12.67%) እና አንድ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ አምራች ኢንዱስትሪ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ (37%) ነው፡፡
 ከዚህ በመነሳት ይህ ንዑስ ዘርፍ መንግስት የሰጠውን ማበረታቻ ተጠቅሞ ለሀገራችን እድገትና ብልጽግና የራሱን
ሚና ለመወጣት ያለው ነባራዊ ሁኔታ ከአፈጻጸሙ አንጻር ሲታይ ክፍተት ስላለው የታለመለትን ዓላማ አሳክቷል
ለማለት አያስደፍርም፡፡
 የሳሙናና ዲተርጀንት አምራች ፋብሪካዎች በምርት ሂደታቸው እንደአስፈላጊነታቸው ጥራታቸውን የጠበቁና
ተወዳዳሪ ምርቶችን ለማማረት ከውጭ ሀገር ብቻ ተገዝተው ሊመጡ የሚችሉ 104 ግብዓቶች የተለዩ ሲሆን
አስራ አራት /14/ የሚሆኑት ጥሬ እቃዎች በሁለተኛ መደብ ታሪፍ /ሀ/ እንዲያስገቡ የተፈቀዱ፣ 42 የሚሆኑት ጥሬ
ዕቃዎች በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ ቢመደቡም ለሌሎች ዘርፎች የተፈቀዱ ሲሆኑ ለሳሙናና ዲተርጀንት
አምራች ፋብሪካዎች ያልተፈቀዱ በመሆናቸው ከነዚህ ውስጥ 18 ቱ ለዘርፉ እንዲፈቀዱና 19 የሚሆኑት ግብዓቶች
በአንደኛ መደብ ታሪፍ የተመደቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 4 ቱ ወደ ሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ ተመድበው ለዘርፉ
ቢመደቡ የሚል አስተያየት በጥናቱ ተመላክቷል፡፡
 በሀገር በቀል አምራች ድርጅቶች የሚመረቱ የሳሙናናዲተርጀንት ግብዓቶችን በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ
መመደብና መፍቀድ ለአገር ውስጥ አምራቾች ተወዳዳሪነታቸውንና ተስፋፊነታቸውን ያቀጭጫል፡፡
 ባለፉት አምስት ዓመታት ከውጭ የገባ አማካይ የሶፕ ኑድል ምርት 28,204.552 ቶን (Gross weight) ሲሆን
በሃገር ውስጥ የማምረት ዓቅም (Design Capacity) የዛክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማ እና ኢትዮ-ኤዥያ
ኃ/የተ/የግ/ማ የሶፕ ኑድልስ ምርትን ሳይጨምር 228,960 ቶን ነው፡፡ ከዚህ መረዳት የሚቻለው በሀገር ውስጥ
ከበቂ በላይ ግብዓት ማምረት መቻሉን ነው፡፡

26
የሳሙ ና ቀለም ና ተዛማ ጅ ው ጤ ቶች ኢ/ል ዳይሬክቶሬት

4. አስተያየት /Recommendation/

 በሰንጠረዥ 2.9 ላይ እንደተገለጸው በጥናቱ በከፍተኛ ደረጃ የተፈረጁ አምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የእሴት
ጭማሪ ምጣኔ (24.49%)፣ በመካከለኛ ደረጃ የተፈረጁ አምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ
(12.67%) እና አንድ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝአምራች ኢንዱስትሪ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ (37%) ሲሆን
አምራች ኢንዱስትሪው የማበረታቻው ተጠቃሚ የሚሆኑበትሁኔታ እንዲፈጠር የእሴት ጭማሪ ምጣኔ (21%)
ለንዑስ ዘርፉ የእሴት ጭማሪ ምጣኔ መነሻ ቢሆን የንዑስ ዘርፉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ይሆናል፡፡
 በሰንጠረዥ 2.11 የተመለከቱት በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ የተመደቡና ለሌሎች ዘርፎች የተፈቀዱ ግብዓቶች
በሰንጠረዡ የተመላከቱት 18 ቱ ጥሬ ዕቃዎች ለሳሙናና ዲተርጀንት ኢንዱስትሪዎችም መፈቀድ አለባቸው፡፡
ምክንያቱም ፋብሪካዎቹ በቂ ግብዓት አግኝተው ጥራት ያለውን ምርት በማምረት ከአገር ውስጥ ገበያ በተጨማሪ
በውጭ ገበያ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑና መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪው የሰጠው ትኩረትና ማበረታቻ
የታለመለትን ዓላማ ለማሳካት ያስችላል፡፡
 በሰንጠረዥ 2.12 ከተዘረዘሩት አስራ ዘጠኝ ዓይነት በአንደኛ መደብ ታሪፍ የተመደቡ ጥሬ ዕቃዎች መካከል 4 ቱ
በሁለተኛ መደብ ታሪፍ ተመድበው ለሳሙናና ዲተርጀንትአምራቾች ቢፈቀዱ፡፡
 በሀገር በቀል አምራች ድርጅቶች የሚመረቱ የሳሙናናዲተርጀንት ግብዓቶችን በሁለተኛ መደብ
/ሀ/ ታሪፍ መመደብና መፍቀድ ለአገር ውስጥ አምራቾች ተወዳዳሪነታቸውንና ተስፋፊነታቸውን
ከማቀጨጩም በተጨማሪ ያላቸው ሀገራዊ ጥቅሞች ከፍተኛ በመሆኑ እነዚህ ጥሬ ዕቃዎች
በሁለተኛ መደብ /ሀ/ ታሪፍ መመደብም ሆነ መፈቀድ የለበትም፡፡
 በሀገር ውስጥ ያሉ የሶፕ ኑድል አምራቾችን ለማበረታታትና ሌሎችም ወደ ማምረት ሂደቱ ለማምጣት እንዲሁም
የንዑስ ዘርፉን እሴት ሰንሰለት ለመጨመርና ሀገራችን ለንዑስ ዘርፉ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሪ መጠን
ለመቀነስና የሶፕ ኑድሉ ከ 20-25 በመቶ ውሀ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለዚህ ይወጣ የነበረውን የትራንስፖርት ወጪን
ለመቀነስ ሲባል ከውጪ በ 10 % ታክስ በሚገባው የሶፕ ኑድል ምርት ላይ አሁን ያለውን ዓቅም ባገናዘበ መልኩ
ወደ 20% ከፍ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
 የሶፕ ኑድል አምራቾች በገበያው ላይ ጫና እንዳያሳድሩ ማድረግ ይቻል ዘንድ በደብዳቤ ውል እንዲገቡ ቢደረግ
ተገቢ ነው እንላለን፡፡

27

You might also like