You are on page 1of 18

PARTNERsHIP MOU

Between

Kombolcha Agricultural College and CAMS Engineering PLC/Ethiopia (With XSyn Company/USA)

በኮምቦልቻ የግብርና ኮሌጅ እና በ ካምስ ኢንጂነሪንግ ኢትዮጵያ ኩባንያ መካከል፡


አብሮ ለመስራት የተፈረመ የትብብር ስምምነት ሰነድ

የኢትዮጵያን የባህላዊ ግብርና ስራን (እና የቆዳ ምርት ስራን) በተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችና ግብአቶች ለማሳደግ፤ አያይዞም ለበርካታ
የከተማና የገጠር ወጣት (ወንዶችና ሴቶች) ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር፤ የሃገራችንን ልማት ቀጣይነት ባለው መልኩ ለማገዝ የሚያስችሉ
ፕሮጀክቶችን በጋራ ነድፎ በትብብር ለመስራት የተፈረመ የስምምነት ውል ሰነድ

የካቲት/…/2013 ዓ.ም.
አድስ አበባ. ኢትዮጵያ

አንቀጽ አንድ
የተስማሚዎቹ አካላት አጠቃላይ መግለጫ

1
1. የካምስ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ መገለጫ

1.1. Introduction (መግቢያ)

የካምስ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ (CAMS Engineering PLC) - በኢንጂነሪንግ፣ ግብአቶችን በማምረትና አገልግሎት በመስጠት ዘርፍ
ለመሰማራት እ.ኤ.አ. በ 2016 በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ የግል ድርጅት ሲሆን፤ ግቡም- ለገራችን የግብርናና የቆዳ ምርት
ስራዎች- የእሴት ሰንሰለትን ማዕከል ያደረጉ የምርትና የንግድ (Businesses) በሀገራችን ለማስተዋወቅና ለማስፋፋት ያለመ ነው፡፡

ኩባንያው - ከግብርና ሜካናይዜሽን ፕሮጅክቶቹ ባሻገር የተለያዩ የገቢ ማስገኛ ቢዝነሶች በሃገራችን ውስጥ ያሉት ሲሆን ለአብነትም-
እ.ኤ.አ. በ 2017 በአዲስ አበባ ውስጥ በከፈተው ማምረቻ ማዕከል ውስጥ ከአሚሪካ ሃገር (USA) ባስመጣው ኮምፒውተራይዝድ (cutting
and scanning machine/CNC) የመቁረጫ ማሽን በመጠቀም - እጅግ ጠራቱን የጠበቀ የቆዳ መቁረጥና ለተለያዩ ተሸከርካሪዎችና
የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች ግብአትነት የሚያገለግሉ ጋስኬቶችን (high quality gaskets) የማምረትና ለገበያ የማቅረብ ስራውን የጀመረ
ሲሆን፤ ለእንዚህም ስራዎች ለመስራት ያስመጣው ይህ ማሽን በአሜሪካና በጣሊያን ሃገራት ደረጃቸውን የጠበቁ የቆዳ ምርቶችን
ለመስራት የሚገለገሉበት አይነት ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት ተቀዳሚ ፕሮጅክት አድርጎ የያዘውን - የሀገራችንን ባህላዊ የሰብል መፈልፈል ስራና ከዚያም ጋር በተያያዘ የሚከሰተውን
ከፍተኛ የሰብል ብክነት ለመቅረፍ ከአፍተኛ ወጪ ዘመናዊና በርካታ ሰብሎችን የሚፈለፍል “Multi-Crop-Thresher” “Missouri-State
University& USAID” ጋር በመሆን በሃገር ውስጥ ወጣቶቸ ሞዲሉን በማሻሻል በሰፊው ለማምረትና ለመገጣጠም ሂደት ላይ ይገኛል፡፡
ከዚህ ቀደምም- አንድ ለሃገራችን አዲስ የሆነን “Versatile Tractor” የተባለ አነስተኛና ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነን የእርሻ ትራክተር
ከኢልፎራ/ኢትጵያ/ ካምፓኒ ጋር በጋራ ወደሃገራችን አምጥቶና አስፈትሾ ለግልጋሎት አብቅቷል፡፡ ለቀጣይም- በርካታ ቀላልና አዋጪ የሆኑ
የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎችን ወደሃገራችን ለማምጣትና የሃገራችንን ባህላዊ የግብርና ስራ በቲክኖሎጂ ለማዘመን የተቻለውን
ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

1.2. የካምስ ኢንጂነሪንግ ኩባንያ ህጋዊ ይዘት ዝርዝር

- አድራሻ- አዲስ አበባ፤ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ …. ልዩ ስሙ….. የቤት ቁጥር… ስ.ቁ. …
- የስራ አስኪያጅ/ተወካይ ስም- አቶ ዮናስ ሐይሉ ስ.ቁ…..
- የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምዝገባ አይነት- ……….
- የህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ምዝገባ ቁጥር- ……….
- የተሰማራበት የስራ መስክ- ……….
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር- ……….
- የንግድ ምዝገባ ቁጥር- ……….
- የንግድ ፈቃድ ቁጥር- ……….

2
-…

1.3. Vision (ራዕይ)

የካምስ ኢንጂነሪንግ ራዕይ - በሃገራችን በስፋት እየታየ ያለውን የወጣት ወንዶችና ሴቶች የስራ አጥነትን ችግር - ለመቅረፍ የበኩሉን
አስተዋጾ ማበርከት ሲሆን፤ ይህንንም ራእይ ለማሳካት አምራች መሆን ለሚችለው የሃገራችን ወጣት የቴክኖሎጂ ሽግግር የማድረግና
የሀገራችንን ባህላዊ የግብርና ስራዎች በማዘመን አያይዞም ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር የሚል ነው፡፡

1.4. Mission (ተልዕኮ)

 በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ የወጣት የስራ እድል ፈጠራና የንግድ ስራ (Business) ፕሮጅክቶችን የመተግበር
 የሃገራችንን ባህላዊ ግብርና ለማዘመን- በቴክኖሎጂ በታገዙ የግብርና የእሴት ሰንሰለት ፕሮጅቸቶች ላይ ማተኮር
 የሃገራችንን የግብርና ምርት በብዛትና ጥራት በማሳደግ የምግብ ፍላጎትን ማርካትና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን ማገዝ
 የሃገራችንን ሴቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያሳድጉና የጾታ እኩልነትን ያማከሉ ፕሮጅክቶች ላይ ማተኮር
 የአካባቢ ጥበቃን የሚደግፉና በተለይም የምርት ብክነትን የሚቀርፉ ስራዎችንና በየፕሮጅቸቶቹ ማካተት

1.5. Goal/Objectives/ (ግብና አላማ)

 የስራ ዕድል ፈጠራ- በቀጣዩ 5 አመታት ውስጥ በሺዎች ለሚቆጠሩ የከተማና የገጠር ወጣቶች ስራ መፍጠር
 የሃገራችንን ግብርና ማዘመን- በቀጣዩ 5-10 አመታት ውስጥ- እስከ ግማሽ ሚሊዮን ዘመናዊ ገበሬዎችን መፍጠር
 የግብርና ምርት ብክነትን መቀነስ- ተዛማጅ ፕሮጅክቶቹ ተፈጻሚ በሚሆኑባቸው ቦታዎች በባህላዊ የእህል ውቂያ
በማስቀረት- በዛ የተነሳ የሚያጋጥምን የምርት ብክነትን ከ 75% በላይ መቀነስ፤እና ከምርት ብክነት መከላከል ባሻገር
ለተዛማጅ አካባቢ ጥበቃ ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል
 የሴቶች እኩልነትን በተመለከተ- ፕሮጅክቶቹ በሚተገበሩባቸው ቦታዎች ሁሉ የሴቶችን 50% ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
 ከገጠር-እስከ-ከተማ ያለን ረዥም የገበያ ሰንሰለት በገበያ ትስስር ቴክኖሎጂ አሳጥሮ- አምራቹን ቀጥተኛ ተጠቃሚ ማድረግ

1.6. Partners (አጋር ድርጅቶች)

ሀ- ከሃገር ውጪ

3
1. XSyn Corporation, a USA based company for technology transfer, engineering consulting, supply chain
management and identifying strategic alliances and partnerships required for growth.

2. XSyn has several partners for project implementation and technology transfer arrangements, here are
the few:
a. Zanotti - Manufacturer of a complete suite of cold-chain solutions
b. Marel Poultry- Manufacturer of poultry processing equipment
c. Mavitec - Manufacturer of rendering equipment
d. Cleber LLC- XSyn has a licensing agreement to manufacture Oggun tractor in Ethiopia. XSyn is
extending that right to CAMS. Therefore the partnership can plan to produce this tractor in Ethiopia.
e. Pas Reform – Manufacturer of hatchery equipment
f. Soybean Innovation Lab – A USAID funded organization focused on adopting approraiete scale
mechazation and soybean production
g. Slowtools – A non-profit engaged in small scale farm integration and design/manufacturing of
apporpriate farm equipment

ለ- ከሃገር ውስጥ

1. EBTI (Ethiopian Biotech Institute)


2. ሃንድ-ቤል ኢንጂንሪንግ
3. ለበርካታ የመንግስት ቢሮዎች፤ የሃገር ውስጥ ድርጅቶች፤ ባለሃብቶችና ግለሰቦች |የራዕይ ማካፈል ስራ እየተሰራና አብሮ
የመስራት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ጥረት እየተደረገ በመሆኑ፤ ዝርዝሩን እንዳስፈላጊነቱ በቀጣይ የምናሳውቅ ይሆናል፡|፡

1.7. Activities (ተግባራት/ ስራዎች)

1.7.1. ደረጃውን የጠበቀና በዘመናዊ ማሽን የሚሰራ የቆዳ መቁረጥ ስራን በማምረቻ ማዕከሉ በመስራት
የስራ ዕድልን ለአምራችና ለግብአት ተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል

1.7.2. ላገርውስጥና ለውጪ ገበያ በሚውል መልኩ ደረጃውን በጠበቀ ጥሬ ዕቃና በዘመናዊ ማሽን የሚሰራ
የጋስኬት እና የድርጅቶች ምልክቶችን (signage) ማምረት ስራን በመስራት ለበርካታ ተጠቃሚዎች
በማቅረብ ላይ ይገኛል

1.7.3. ዘመናዊ የሆነ የቀለም ቅብ ማሽንን በመጠቀም (ለተሸከርካሪዎችና ለማሽነሪዎች) ግልጋሎት


በመስጠት ላይ ይገኛል

1.7.4. ከዋና አጋር ኩባንያው ከ XSyn Corporation ጋር በመሆን እ.ኤ.አ. ከ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ሊበላሹ
ለሚችሉ የግብርና ምርቶች መጠበቂያ የማቀዝቀዣ ጎተራ (Cold-Storage installation and
maintenance services) ግንባታ/ገጠማ/ እና የጥገና ስራዎችን ለሃገራችን ያመጣና
ለአምራቾች፤ለሱፐርማርኬቶችና አከፋፋዮች እየተገበረ ይገኛል

1.7.5. ከ XSyn Corporation እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የምግብ ማሽጊያ ፋብሪካ
(Canning Factory) የመግጠም

4
1.7.6. ከ XSyn Corporation እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን የስጋ ውጤቶች ማቀነባበሪያ (Meat
Processing Factory) የመግጠም

1.7.7. እ.ኤ.አ. ከ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የምርትና የአገልግሎት መስጠት አድማሱን ወደግብርና ሜካናይዜሽን
ዘርፍም በማስፋት የበርካታ-ሰብል መፈልፈያ ማሽንን (Multi-Crop-Thresher) የተባለ

ቴክኖሎጂን ከውጪ በመቅዳትና የማምረቻ ግብአቶቹንና መሳሪዎቹን ከአሜሪካና ከቻይና


በማስመጣት፤ ሞዴሎቹን አሻሽሎ በመስራት በቴክኖሎጂ ሽግግር

የስራዕድል ለመፍጠርና የምርት ጥራትን አሳድጎ ብክነትን (post harvest loss) ለመቀነስ ሂደት ላይ
ይገኛል

- ከዋና አጋሩ- ጋር ለሙከራ የምረት ሂደትላይ ላለው 100 መፈልፈያዎች በማህበር ለሚደራጁ የገጠር ወጣት
(ወንዶችና ሴቶች) የስራ ዕድል የሚፈጥርበትንና አዲስ የቢዝነስ ሞዴል (to provide threshing service to any
farmer who needs it) በማጥናትና ላይ ይገኛል፤ ያንንም ሞዴል ለወደፊት በርካታ የመፈልፈያ የስራ ዕድል ፈጠራ
በሰፊው ለመጠቀም እቅድ ይዟል

1.7.8. የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ስራዎችን በተመለከተ- የወተት ማጠራቀሚያና ማቀነባበረ፤ የአትክልትና
ፍራፍሬ ማቀነባበር እንዲሁም የቀዝቃዛ ማጠራቀሚያዎችን የእሴት ሰንሰለት ያማከሉ ስራዎችን
በዋና አጋሩ በኩል በተያዙት ሰፊ ፕሮጅክቶች በኩልና በጋራ ለመስራት በሂደት ላይ ይገኛል

- ከዋና አጋሩ- ጋር፡- ለነዚህ ምርቶች በተለይም ለውጪ ገበያ በጥራት የበቁ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትን ለማቅረብ
በ Digital-technology የገበያ ትስስር (e-commerce) እና የክትትል ስርአት የተዘረጋለትና በዘመናዊ የማቀዝቀዣ
ማጠራቀሚና ማጓጓዣ ቴክኖሎጂዎች የታገዘ ሰፊ ፕሮጀክት ለማከናወን ሂደት ላይ ይገኛል

1.7.9. የእርሻ ልማትን በተመለከተ- ቀላልና ከውጪ መጥተተው እዚህ የሚገጣጠሙ- ትራክተሮችን (ማረሻና
መዝሪያ) መሳሪያዎችን እንዲሁም የመስኖ ስራ ቴክኖሎጂዎችን- ለግብርናው ለማበርከት- ከዋና አጋሩ
ጋር በሂደት ላይ ይገኛል

1.7.10. የዶሮ እርባታን በተመለከተ- ከዋና አጋሩ ጋር ሰፋፊ የዶሮ እርባታና እርድ ፕሮጅቸቶችን (Integrated
Poultry Project) በማስፈጸም ላይ ሲሆን፤

- እነዚህ እርባታዎች የሚፈጠሩት በርካታ የሆኑ በተደራጁ ወታቶች የሚተገበሩ ለትልቁ እርድ ፕሮጅቸት ግብአት
የሚያቀርቡ ትናንሽ የዶሮ እርባታና ለእርባታዎቹ ቀለብ ግብአት የሚያመርቱ የእሴት ሰንሰለት ፕሮጅክቶች- ሰፊ የስራ
እድልና ለማህበረሰቡም ተመጣጣኝ የሆነ የዶሮ ስጋ ምርት የማቅረብ አቅምን የሚፈጥሩ ከገጠር እስከ ከተማ የተዘረጉ
የገበያ ትስስሮችንም ጭምር ይሆናል፡፡

5
1.8. Opportunities, Challenges Faced and Solution Measures/Suggestions (ያሉ ዕድሎች፣የታዩ
ችግሮችና የመፍትሄ አቅታጫዎች/እቅዶች)

1.8.1. ያሉ ዕድሎች (Opportunities)

- ሀገራችን ኢትዮጵያ - ለበርካታና በዚህም ፕሮጅክት ለካተቱት የግብርና ምርቶች የተመቸ የአየር ንብረትና አፈር እንዲሁም
የውሃ ሃብት ያላት መሆኑ
- በሃገራችን ከ 80% በላይ ህዝቧ በግብርና (በባህላዊ ግብርና) የሚተዳደር መሆኑና ያንንም የማዘመን እቅድ የመንግስታችን
ተቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑ
- በሃገራችን የሚመረቱ የግብርና ምርቶች በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ ገበያ ተፈላጊ መሆናቸው እና ያንንም ለማሳካት
በቴክኖሎጂ መታገዝና የባለሃብቱን ተሳትፎ የግድ ሚፈልጉ በመሆናቸው
- በሃገራችን ግብርናና ማኑፋችቸሪንግ ተያይዘው የሚሄዱና ሰፊ ፍላጎት ያላቸው የልማት አቅጣጫዎች መሆናቸው
- በሃገራችን ግብርናና ማኑፋችቸሪንግ ለወጣቱ ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር ትልቅ አቅም ያላቸው በመሆኑ
- በሃገራችን ለወጣቱ ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጥሩ ብቃትና ዝግጁነት ያላቸው በመሆኑ
- በርካታ የውጪ ድርጅቶች፤ ዳያስፖራዎችና የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችና ባለሙያዎች የሃገራችንን ግብርና በማዘመን ለሃገር
ውስጥና ለውጪ ገበያ ተወዳዳሪ ምርቶችን ለማቅረብ የቢዝነስ ተሳትፎ ለማድረግ ፍላጎት ያላቸው መሆኑ፡፡

1.8.2. የታዩ ችግሮች (Challenges Faced)

- ለአምራች የግል ሴክተሮች የቀረጥ ነጻ ግልጋሎቶች በአንዳንድ ህጎች ውስጥ ክፍተት መኖሩ
- የአንዳንድ የሃገራችን የስራ ዕድል ፈጠራ ተቋማት ለግሉ የስራ ፈጣሪ ሴክተር የተለየ ትኩረት፤ክትትልና ድጋፍ ማነስ
- አንዳንድ የሃገራችን የከተማና የገጠር ልማት ፖሊሲ አስፈጻሚ አካላት የአፈጻጸም ሂደት ፍጥነት ችግር
- የሃገራችን የግልና የመንግስትን ተቋማት አጣምሮ ለልማት ለማሰለፍ በግልጽ የተቀመጠ የፖሊሲ ዝርዝር አለመኖር ወይም
የአፈጻጸም መመሪዎች በሚተገበር መልኩ በዝርዝር አለመቀመጥ ወይም እንዳስፈላጊነቱ ለተገቢ የአፈጸጸም ማሻሻያዎች
ዕድል አለመስጠት
- የሃገራችን የገጠርና የከተማ ልማት ሴክተር መ/ቤቶች ተናቦና ተሰናስሎ - ተመጋጋቢ ፕሮጅክቶችን የማስኬድ ችግር

- በሚመከታቸው የመንግስት አካላት የግልና-የመንግስት አካላት ትብብርን በተመለከተ የአፋጣኝ ውሳኔ የመስጠት ችግርና
በግሉም ሴክተር የቢዝነስ አደጋን ለመጋፈጥ (Risk Taker) ለመሆን ያለመድፈር

6
- የብድር አገልግሎትና የብድር/የሊዝ እቃዎች ብድር አመላለስ ላይ ለግሉ ሴክተር የተመቻቸና አስተማማኝ አሰራር ሰፊና
በቅርበት እየተሰራበት አለመሆኑ
- ገበያ ተኮር ትምህርትና ስልጠናዎች የመስጠት ልምድ ከሚጠበቀው መጠን ማነስ ወይንም ሰፊ ጥናትና የረዥም አመታት
ራዕይ የሰነቀ የትምህርት ፖሊሲ ያለመኖር
- በመንግስት በኩል የግሉን ሴክተር የሚያበረታታ የተጨማሪ ግልጋሎቶች ማነስ፤ ለምሳሌ የመስሪያ ቦታ እንዳስፈላጊነቱ
በአግባቡና በአፋጣኝ ያለማግኘት
1.8.3. የመፍትሄ አቅታጫዎች/እቅዶች (Solution Measures/Suggestions)

- ከተለያዩ ተዛማጅ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት ጋር ስልታዊ አጋርነት መፍጠር


- በጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች ላይ ጥናት ማድረግና፤ ግኝቶቹንም ለሚመለከተው አካል መጠቆምና መፍትሄ መሻት
- ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ከተመሳሳይ (የሃገር ውስጥም ሆኑ የውጪ) ተቋማትና ኩባንያዎች ልምድ መቅሰም
- ስራዎችንና ፕሮጅክቶችን ከቀላል ጀምሮ ወደ ከባዱ የመሄድ ልምድና ስልትን መቀየስና ማጎልበት
- የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ የጋራ ዕቅድና የአፈጻጸም መመሪዎችን በጋራ ማዘጋጀትና ማስፈጸም

1.8.4. Requests (ጥያቄዎች/ፍላጎቶች፤ በተለይም የ ኮሌጁንና አጋሮቹን ድጋፍና ትብብር በተመለከተ)

1.8.4.1. ለታቀዱና በሂደት ላይ ላሉ የምርትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች የሚሆን ቦታን ድጋፍ
ማግኘትን በተመለከተ

1.8.4.2. የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችና ተዛማጅ ስልጠናዎችን በተመለከተ- የማሰልጠኛ ሾፕና


የባለሙያን ድጋፍ በተመለከተ

1.8.4.3. የቢዝነስ ጥናት ሴንተር ወይም የሰርቶ ማሳያ ማዕከል የሚሆን ቦታ (አዳራሽንና የመገኛ
ቢሮን) ድጋፍ በተመለከተ

1.8.4.4. የሰልጣኝ-የተግባሪዎችን፡- በታቀዱ ፕሮጅክቶች አይነትና ልክ ወጣቶችን ማሰልጠንና


ማደራጀትን ሂደት በተመለከተ

1.8.4.5. የሰለጠኑ ተግባሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊውን የህግ ማዕቀፍ፤ የመስሪያ ቦታ፤


የመነሻ ብድር ወዘተ ድጋፍን ግልጋሎቶችን የማግኘት ሂደትን ከሚመለከተው አካል ጋር
በመተባበር ስለ ማሳለጥ በተመለከተ

2. የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ መግለጫ

7
2.1. መግቢያ/ Introduction/
የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ በ 197 ዐ ዓ.ም በዓለም ባንክና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር የተቋቋመ ኮሌጅ ነው፡፡ኮሌጁ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በ
376 ኪ.ሜ፣ እንዲሁም ከደሴ ደቡብ ምስራቅ በ 23 ኪ.ሜ ላይ በምትገኘውና በፊዴራል ደረጃ በኢንዱስትሪ ከተማነት ከተመረጠችው ኮምቦልቻ ከተማ የሚገኝ
አንጋፋ ኮሌጅ ነው፡፡

የቀድሞው የግብርና ማሰልጠኛ ማዕከል፣ የአሁኑ ግብርና ኮሌጅ ከደቡብ ወሎ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች አርሶ አደሮችን በኑሮ ዘዴና በተለያዩ የግብርና ሙያዎች ከ 15 -21
ቀናት ስልጠና በመስጠት ስራውን የጀመረ ሲሆን ከ 1985 ዓ.ም ጀምሮ መንግስት ለግብርናው ክፍለ ኢኮናሚ በሰጠው ልዩ ትኩረት ደረጃውን በማሳደግ በተለያዩ
የግብርና ሙያዎች 12 ኛ ክፍልን የጨረሱ ተማሪዎችን ለ 9 ወራት በማሰልጠን ወደ አርሶ አደሩ ቀዬ እየሄዱ እንዲያስተምሩ አድርጎአል፡፡

ተቋሙ ከ 1994 ዓ.ም ጀምሮ የውሰጥ አቅሙን በማሳደግ ወደ ኮሌጅ ደረጃ ከፍ ብሎ ከልማት ጣቢያዎች ተመልምለው በሚላኩ ሰልጣኞች በ 3 የትምህርት መስኮች
ማለትም በ እንስሳት ሳይንስ፣ በዕፅዋት ሳይንስ እና ተፈጥሮ ሃብት ሰልጣኞችን ተቀብሎ በመካከለኛ ደረጃ ባለሙያነት በዲፕሎማ መርሐ -ግብር በማሰልጠን 2 ዐ 7 ዐ
ወንዶችን 337 ሴቶችን በጥቅሉ 24 ዐ 7 ተማሪዎችን በዲኘሎማ ደረጃ አሰልጥኖ በስራ ላይ እንዲሰማሩ አድርጓል፡፡

በዚህ መልኩ እስከ 2000 ዓ.ም ድረስ በዲፕሎማ መርሐ-ግብር አሰልጥኖ ሲያስመርቅ ቢቆይም በሂደት የልማት ጣቢያ ሰራተኞችን የመፈጸም ዓቅም የበለጠ የማጎልበት
አስፈላጊነት በክልሉ ግብርና ቢሮ ስለታመነበት ትምህርትና ስልጠናው ወደ ዲግሪ ደረጃ እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ ለዚህም ተፈጻሚነት የክልሉ ግብርና ቢሮ፣ የኮምቦልቻ
ግብርና ኮሌጅ እና ወሎ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት የ ሦስትዮሽ ስምምነት ትምህርትና ስልጠናው በ ጥምረት /አፊሌሽን/ እንዲሰጥ ተወስኖ ከ 2001 ዓ.ም ጀምሮ ወደ
ትግበራ ተገብቷል፡፡ በዚሁ መሰረትም በግብርናዉ ዘርፍ ያካበታቸዉን ተሞክሮዎች ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገርና ተቋማዊና የሰው ሃይሉን በመገንባት በ 2002 ዓ.ም በ 5
የትምህርት ዘርፎች ማለትም በእንስሳት ሳይንስ፣በእንስሳትጤና፣ተፈጥሮሀብት፣እጽዋት ሳይንስ ፣ተፈጥሮ ሃብት እና ህብረት ስራ የትምህርት ዘርፎች በዲግሪ ደረጃ
በማሰልጠን በመጀመሪያ ዙር በ 2004 ዓ.ም 427 ወንዶች 67 494 ሰልጣኞችን፣በሁለተኛ ዙር በ 2005 ዓ.ም ወንድ 399 ሴት 136 በድምሩ
ሴቶች በድምሩ
535 ሰልጣኖችን፣በሶስተኛ ዙር በ 2008 ዓ.ም ወንድ 454 ሴት 59 ድምር 513 የግብርና ባለሙያዎችን፣ በ 2009 ዓ.ም ለ 4 ኛ ጊዜ ወንድ 403 ሴት 52 ድምር
455 ሰልጣኞችን በ 5 ቱ የስልጠና ዘርፎች በማስመረቅ ለዘርፉ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረግ ችሏል ::

ኮሌጁ በአሁኑ ሰአት በስድስት የትም/ዘርፎች ማለትም በእንስሳት ሳይንስ ፣በእንስሳት ጤና፣ በእጽዋት ሳይንስ ፣ በህብረት ስራ፣ በዉሃ ሀብት እና መስኖ ምህንድስና እና
ተፈጥሮ ሃብት የትም/መስኮች ተማሪዎችን በመደበኛ መርሃግብር በደረጃና በዲግሪ እንዲሁም በተከታታይ ት/ርት በደረጃ በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡

ከመማር ማስተማር ስራዉ ባሻገርም ኮሌጁ ከጊዜ ወደ ጊዜ የውስጥ አደረጃጀቱን በማጠናከር በኮምቦልቻ መድሀኒ አለም 3.5 ሄክታር እና ቃሉ ወረዳ ሀርቡ ላይ ባገኘው
25.1 ሄክታር ማሳ ላይ የሰርቶ ማሳያና የተለያዩ ቴክኖሎጀዎችን በመሞከርና በማሻሻል እንዲሁም የምርምር ስራዎችን በማካሄድ ለአካባቢያችን ብሎም ለክልላችን
ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለማሸጋገር በሎም የውስጥ ገቢውን ለመደጎም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ወደ ኢንዱትሪ ከተማችን ለሚመጡ
በአግሮ ኘሮሰሲንግ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች በሰለጠነ የሰው ኃይልና የተሻሻሉ አሰራሮችን በተመለከተ የማማከር ስራዎችን በመስራት ላይ ሲሆን እንደ አጠቃላይም
የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነዉን የግብርናዉን ዘርፍ በማገዝ ረገድ ሚናዉን እየተወጣ የሚገኝ አንጋፋ ኮሌጅ ነዉ፡፡

2.2. Vision (ራዕይ)


Kombolcha Agricultural College aims to be seen one of the leading agricultural colleges in Ethiopia and well-
known in the world by 2030.
የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅን በ 2030 ዓ.ም. በአለምአቀፍደረጃ መሪ የግብርና ኮሌጅ ሆኖ ማየት፡፡

2.3. Mission (ተልዕኮ)

8
Kombolcha Agricultural College’s mission is committed to train high competence regional, national and
international professionals in agriculture and related disciplines, conducting problem solving research and
serving the community through its esteemed and innovative community based education.
የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ በእዉቀት፤ክህሎትና አመለካከት ከፍተኛ ብቃት ያላቸዉን የግብርና ባለሙያዎች በተለያዩ የግብርና
ሙያዎች ለማሰልጠን፤ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ለማከናወን፤የማህበረሰብ አገልግሎት በቁርጠኛነት ማከናወን፡፡

2.4. እሴቶች /Core Values/


1. Excellence and quality in teaching, research and community service.
2. Equity and access in teaching, research and public services.
3. Gender sensitivity to rectify the prevailing gender inequality and imbalance.
4. Honesty and integrity in carrying out intellectual endeavors.
5. Transparency and accountability in decision making.
6. Community involvement and empowerment.
8. Networking for collaboration and partnership.
9. Mutual respect, collegiality and team spirit in transforming the college.
10. Respect intellectual freedom to conduct research, teach, speak and publish, subject to the norms and
standards of scholarly inquiry.
11. Encouraging innovativeness to inculcate competitiveness and improvement in service delivery.

1. የመማር ማስተማሩን፤ የጥናትና ምርምሩንና ማህበረሰብ አገልግሎትን በጥራትና በከፍኛ ደረጃ ማከናወን፤
2. የመማር ማስተማሩን፤ የጥናትና ምርምሩንና ማህበረሰብ አገልግሎትን በፍትሃዊነት ለሁሉም ማዳረስ፤
3. አሁን በሃገራችን በጾታ ኢፍትሃዊነትና አለመመጣጠን ላይ ያለዉን ተግዳሮት ለመቅረፍ ጾታ ተኮር የመማር ማስተማር
ተግባር ማከናወን፤
4. ታማኝነትና ቡድናዊ ስሜትን ማዳበር፤
5. ግልፀኝነትና ተጠያቂነትን ማስፈን፤
6. የማህበረሰብ ተሳትፎአዊነትንና ዉሳኔ ሰጭነትን ማሳደግ፤
7. የአብሮነት አሰራርን ማስፈን፤
8. የመከባበር፤ የጓደኝነትና ቡድናዊ ስሜትን ማዳበር፤
9. የምሁራዊ አካዳሚክ ነፃነትን ማረጋገጥ፤
10. የፈጠራ ተግባርን ማበረታታት፡፡

9
2.5. ግብና አላማ (Goal/Objectives)
Provide a challenging and supportive learning environment that fosters achievement and intellectual
interaction among students and department members and promotes excellence in research, scholarship
and artistic creativity,

በክትትልና ድጋፍ ፤በጥረት ታገዘ እንዲሁም በመልካም ግንኙነት ላይ የተመሰረተ የመማር ማስተማር፤ ጥናትና ምርምር፤
የፈጠራ ስራ በማከናወን የዘርፉን ዉጠየታማነት ማሳደግ፤

Learning is what the college is all about. Consistent and effective learning will take place only in a nurturing
environment. The college must take those steps necessary to build a proper foundation for learning so that
teaching, research and service will flourish. Further, the college believes that the quality of life is enhanced by
diversity and that the whole community benefits from educational experiences which promote understanding
and appreciation of gender issues, diverse cultures and ethnic heritages. In a multicultural society such as ours, a
lack of understanding results in stereotypes, misconceptions, prejudicial attitudes and a general lack of
knowledge about the realities and significance of differences among people. Thus it is our intent to offer a
variety of programs that will provide our students with the education they will need to function in our diverse
society.

2. Recruit and retain outstanding students, department and staffs


ከፍተኛ ብቃትና ልምድ ያላቸዉን ተማሪዎች፤መምህራንና ሰራተኞች መቅጠር

Great college becomes great through their outstanding students, faculty and staff, drawn from the whole world.
The college must recruit and enroll Level based and undergraduate professional and continuing education
students who show outstanding academic potential.

3. Create a physical environment that reflects our expectation of excellence and encourages interaction
among a diverse population.
ምቹ የስራ አካባቢን በመፍጠር የኮሌጁን ራእይና ተልዕኮ ማሳካትና በኮሌጁ ማህበረሰብ መካከል ጥሩ ተግባቦትን ማስፈን

The college cannot achieve its goals without sound, functional and attractive physical facilities and a modern,
technologically advanced infrastructure. Despite significant progress in recent years, our facilities and
infrastructure at Storrs and the regional campuses are far below the level required to be a truly outstanding
institution. Classrooms and laboratories, residence halls and support space must be upgraded. The library,
computer center and networking of the campuses must be advanced to the cutting edge as information and
communication resources. Traffic flow, parking and pedestrian problems must be addressed. Recognizing these
needs, the reality of limited resources must be acknowledged in establishing priorities and long-term
approaches.

4. Enhance our sense of community by increasing and valuing interaction while developing a strong
sense of pride and ownership.

10
ለአካባቢዉ ማህበረሰብ የያገባኛል፤ተቆርቋሪነትና የባለቤት ስሜትን ማዳበር

As stated in the vision statement, the college will approach issues of diversity, multiculturalism and
globalization through the establishment of a community with shared values and goals. Effective communication
is essential to this endeavor. Our success shall be measured not only in the representation of many cultures and
our relationships, but also in the infusion of cultural and global concepts in our curricula and attitudes.

Objectives for goal 1

1. Enhance undergraduate education and provide a cohesive, supportive experience through development
of a Center for Undergraduate Education.
2. Prepare students for participation in and adaptation to a rapidly changing world.
3. Emphasize an academic experience in which students develop a method of thinking that allows them to
adapt readily to a rapidly changing environment.
4. Enhance the quality of teaching.
5. Require that all teaching assistants receive training before they teach a course or a significant segment of
a course.
6. Encourage outreach activities that enhance college goals of education and service.
1. የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትን ማሳለጥ፤
2. ተማሪዎች ከተለዋዋጩ አለም ጋር አብረዉ መጓዝ እንዲችሉ ንቁ ተሳትፎና የቴክኖሎጂ አቀባበል
እንዲኖራቸዉ ማዘጋጀት፤
3. የመማር ማስተማር ጥራትን ማሳደግ፤
4. ዘመናዊ የመማር ማስተማር ልምዶችን ማግኘት፤መቀመርና መጠቀም፤
5. ለጀማሪ መምህራን የስራ ማስጀመሪያ ስልጠና መስጠት
6. የማህበረሰብ አገልግሎትና ማዳበር
Objectives for goal 2

1. Specifically define the indicators of potentially outstanding students for recruiting purposes and
establish enrollment targets
2. Aggressively recruit students meeting our qualifications from both within and outside the state in order
to build applicant pools of sufficient size and diversity to assure stable enrollments.

11
3. Increase the availability of all types of financial assistance. Specifically define the criteria for student
merit award candidates, significantly increasing the number of merit-based scholarships and fellowships
as a percentage of total financial aid.
4. Create an environment that is attractive to outstanding graduate students and supports their intellectual
efforts.
5. Attract and retain outstanding professionals staff members.

1. ለመምህራን ቅጥር የሚሆን ደረጃዉን የጠበቀ የመመልመያና ማወዳደሪያ መስፈርት ማዘጋጀት፤


2. ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች መምህራንን በመቅጠር የተረጋጋ የቅጥር ሁኔታን መፍጠር፤
3. ለመምህራንና ሰራተኞች ከኮሌጁ በጀት ነፃ የትምህርት እድልን ማመቻቸት፤
4. ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሁለንተናዊ የድጋፍ ስርዓት መዘርጋት፤
5. የተሻለ ልምድና ብቃት ያላቸዉን ዜጎች የመሳቢያ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፡፡

Objectives for goal 3

1. Improve classroom, laboratory and support facilities for learning


2. Improve residence halls, dining facilities, and student study areas.
3. Improve public gathering places, open space, parking facilities and campus appearance to facilitate
campus and student interaction.
4. Improve the utilities infrastructure.
1. ለመማር ማስተማሩ አስፈላጊ የሆኑትን መማሪያ ክፍል፤ ቤተ-ሙከራ እና ደጋፊ ቁሳቁሶችን ማሻሻል፤
2. የመኖሪያ ህንፃዎችን፤ የመመገቢያ አዳራሾችን እና ቤተ-መፃህፍትን ማሻሻል፤
3. የመዝናኛ ፓርኮችን፤ የመኪና ማቆሚያቸዉን ማሻሻል፤
4. አገልግሎት ሰጪ መሰረተልማቶችን ማሻሻል፤

Objectives for goal 4

1. Build a sense of community.


2. Create a sense of ownership through shared responsibility and recognition
3. Facilitate internal communication and community participation.

12
4. Ensure that cultural diversity is nurtured at the college.
1. ለማህበረሰብ ተኮር አገልግሎትን መገንባት፤
2. የጋራ ኃላፊነትና የእዉቅና ስርዓትን በመዘርጋት የባለቤትነት ስሜትን
መፍጠር፤
3. ዉስጣዊ ተግባቦትንና የማህበረሰብ ተሳትፎን ማሳደግ፤

4. የባህል ብዝሃነትን መበልፀጉን ማረጋገጥ

2.6. Partners (አጋር ድርጅቶች)


ኮሌጁ ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር፤ ከቃሉ ወረዳ አስተዳደር እና
ከኮምቦልቻ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በትብብር እየሰራ ይገኛል፡፡
2.7. Activities (ተግባራት/ ስራዎች)
 ኮሌጁ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን ለአርሶአደሩ የማስተዋወቅ፤
የማላመድ፤የማስረፅ፤ ክትትልና ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ፤
 የአነስተኛና ጥቃቅን ጽ/ቤት ስራ አጥ ወጣቶችን መልምሎ
የማደራጀትና የስራ ፈጠራ የማንቂያ ስልጠና መስጠት፤
 የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወደ ስራ ለሚገቡ ለተደራጁ
ወጣቶች የብድር አገልግሎት የማመቻቸት፤
 የኮምቦልቻ ከተማ አገልግሎትና የቃሉ ወረዳ መሬት አስተዳደር
ለወጣቶቹ ከሶስተኛ ወገን የጸዳ የመስሪያ ቦታ አመቻትዉ
ይሰጣሉ እንዲሁም፤
 የመንግስት መደበኛ ባንኮች የብድር ስርዓትን የመዘርጋት፤
የማማከርና ቴክኒካል ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡
2.8. Opportunities, Challenges Faced and Solution Measures/Suggestions
(ያሉ ዕድሎች፣የታዩ ችግሮችና የመፍትሄ አቅታጫዎች/እቅዶች)

13
2.8.1. መልካም አጋጣሚዎች/ Opportunities/
 ከአጋር አካላቶቻችን ጋር ጠናካራና ጥሩ የስራ ግንኙነት ያለን መሆኑ፤
 በአካባቢያችን የሚሰጠዉን ስልጠናና ቴክኖሎጂን መቀበል የሚችል በርካታ ስራ አጥ ወጣት መኖሩ፤
 ምስራቅ አማራ በዚህ ፕሮጅክት ለካተቱት በርካታ የሰብል ምርቶችና የእንስሳት እርባታ የተመቸ የአየር ንብረትና አፈር
እንዲሁም የውሃ ሃብት ያላት መሆኑ፤
 በምስራቅ አማራ ከ 80% በላይ የሚሆነዉ የህብረተሰብ ክፍል በባህላዊ ግብርና የሚተዳደር በመሆኑ መንግስት
ግብርናዉን ለማዘመን የአምስት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሚሽን እቅድ አዘጋጅቶ አጋር አካላቶችን በማስተባበርና
ስትራቴጂ በመቀየስ በትኩረት እየሰራ መሆኑ፤
 ምስራቅ አማራ በተለይም በእንስሳት እርባታ ቁልፍ የልማት ኮሪደር ተደርጎ በመንግስት የተመረጠ መሆኑ፤

 የወጣቶቹንና የአርሶ አደሩን ምርት እንዲሁም ከፕሮጀክቱ የሚመጡ ማሽኖችንና የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ፕሮጀክቱ
ወደ አቋቋማቸዉ ኢንዱስትሪዎች ለማጓጓዝ የተመቸ የመኪና መንገድ፤ የባቡር መንገድና የአየር ትራንስፖርት የተዘረጋ
መሆኑ፤
 ፕሮጀክቱ ከዉጭ አገር የሚያስመጣቸዉን ማሽኖች ከከተማችን በቅርብ ርቀት ከሚገኛዉ የጅቡቲ ወደብን መጠቀም
የሚችሉ መሆኑ፤

 ዉጤታማ የ“TVET Policy”ና የመንግስት ቁርጠኝነት ያለ መሆኑ፤

2.8.2. ያጋጠሙ ችግሮች /Challenges Faced/


 የአስፈጻሚ አካላት የአፈፃፀም ብቃት ማነስ፤
 ስራ የፈጠሩ ወጣቶች ብድር አመላለስ ላይ ተግዳሮት መታየቱ፤
 የከተማ አስተዳደሩ ከሶስተኛ ወገን የፀዳ የመስሪያ ቦታ በሚፈለገዉ ፍጥነት አለማቅረብ፤
 የክልሉ ግብርና ቢሮ ለኮሌጁ በቂ በጀት ያለመመደብ፤
 የግብርና ጽ/ቤት የአርሶአደሩን ፍላጎት የሚመጥንና ነባራዊ የግብርና የአሰራር ችግሮችን የሚፈቱ፤ ጉልበት የሚቆጥቡ፤
ምርታማነትን የሚጨምሩ በቂና ዉጤታማ የግብርና ግብአቶችና ቴክኖሎጂዎችን በተከታታይነት ያለማቅረብ እና፤
 ለአርሲአደሮችና በግብርና ስራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ዉጤታማ የገባያ ትስስር ያለመፈጠሩ፡፡

2.8.3. Requests (ጥያቄዎች/ፍላጎቶች)

14
 ከካምፓኒዉ ጋር ጠንካራ የስራ ግንኙነት ካላቸዉ የአገር ዉስጥና የዉጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የስልጠና፤ የምርምርና የበጎ
ፈቃድ አገልግሎት የሁለትዮሽ ትብብር መመስረትን በተመለከተ፤
 ለተመረጡ የኮሌጃችን መምህራኖች፤ተመራማሪዎችና አመራሮች የአጭርና የረዥም ጊዜ ስኮላርሽፕ እንዲሁም የዉጭ አገር
የልምድ ልዉዉጥን በተመለከተ፤
 የኮሌጃችንን ሰርቶ ማሳያ ፋርም ማዘመንንና የ “Agro-Processing Plant” ማቋቋም፤ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ የ “Technology
Display Center” ማቋቋምን በተመለከተ
 ኮሌጁ ያለበትን የበጀት እጥረት መደጎምን በተመለከተ፤
 በኮሌጁ የ “Research & Development Unit” ማቋቋምን በተመለከተ::

አንቀጽ ሁለት
የስምምነት ውሉ ዓላማ

የዚህ ውል አላማ- የግብርና ኮሌጁ ከተቋቋመበት- በስሩ ለሚሰለጥኑ ወጣቶችና ለሌሎች የከተማውና የገጠር ወጣቶች የስራ እድል
የመፍጠርና ለሃገር ልማት የሚያግዙ ፕሮጅክቶችን የማገዝና የመደገፍ አላማና ራዕዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካለው የካምስ ኢንጂነሪንግ
ከተሰኘው ካምፓኒ ጋር እና በኮምቦልቻና በአካባቢው አለፍ ሲልም በክልሉ ከሚገኙ ከአላማው ጋር ተዛማጅነት ካላቸው ሌሎች ተቋማት
(ለምሳሌ- የኮምቦልቻ ከተማ መስተዳድር/የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ/፤ የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የኮምቦልቻ/ቃሉ የግብርና ቢሮ፤
የመንግስት ባንኮችና አበዳሪ ተቋማት እና መሰል ሌሎች ተቋማትን በማስተባበር) የካምፓኒውና የኮሌጁ የጋር አላማና ፕሮጀክት የሆነውን
የግብርና ስራውን በቴክኖሎጂ የማዘመንና አያይዞም የወጣቶች የስራ እድልን በቴክኖሎጂ አምራችነትና በአገልግሎት ሰጪነት
(የቴክኖሎጂ/ማሽነሪ/ ሰርቪስ ለገበሬው በመስጠት) ዘርፍ አደራጅቶ (ማለትም - ለኮሌጁ ሰልጣኞች፤ ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጁ ሰልጣኞች፤
በከተማውና በገጠር ለሚገኙ ወጣት ሴቶችና ወንዶች ) አማራጭና ቀጣይነት ያለው የስራ እድልን ለመፍጠር አልሞ - ከሚመለከታቸው
አካላት ጋር በጋራና በትብብር ለመስራትና የጋራ ትልማቸውንም ለማሳካት ይቻል ዘንድ - በሙያ፤ በቁሳቁስ፤ በኢንቨስትመንት፤ በቦታና
በሰው ሃይል ወዘተ ስለመተባበር የተሰኘውን ይህን የስምምነት ውል ሰነድ በጋራ አዘጋጅቶ ለመፈራረም ያቀደ ነው፡፡

አንቀጽ ሶስት
የተዋዋዮቹ ሃላፊነቶች- መግለጫ በጥቅሉ

3.1. - ኮሌጁ (እና ከላይ በአንቀጽ ሁለት ላይ የተጠቀሱት ባለድርሻ አካላት በትብብር)፡- ከካምፓኒው ጋር በጋራ ለሚያለሟቸው
ፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉትን ቀጥለው የሚዘረዘሩትን ድጋፎች ያቀርባል፡፡ በዋነኛነትም ከሚያቀርባቸው ድጋፎች መካከል-
 የመስሪያ/የማምረቻ ወይም የመገጣጠሚያና የማከማቻ እንዲሁም የሰርቶ ማሳያ /የሚያገለግሉ ወርክሾፖችንና ለቢሮ ስራዎች
እና ለጥናትና ስልጠናዎች (Research and Development and Seminar) የሚሆኑ ቢሮዎችንና አዳራሾችን ወይም
ክፍሎችን እና መሰል ግብአቶችን ለፕሮጅክቶቹ ተስማሚ በሚሆን መልኩ- አስፈላጊውን መሰረተ ልማት አማልቶ ያመቻቻል፡፡
 ለ የጋራ ፕሮጅክቱ ንብረቶችም አስፈላጊውን ጥበቃና ዋስትናም ይሰጣል፡፡ የፕሮጅክቱ አካል የሚሆኑ አጋሮችን፤
ሰልጣኝ/ተሳታፊ ወጣቶችን ለስልጠናና ለስራ ይመለምላል፤ ከሚመለከታቸው አካላትና ከካምፓኒው ጋር በጋራ ያሰለጥናል፤
ያደራጃል፤
 የፕሮጅክቱ ንብረት የነበሩትን ማሽኖች ለወጣቶቹ መገልገያ/ቢዝነስ መስሪያ እንዲሆኑ በካምፓኒውና በወጣቶቹ መሃከል በመሆን
(በብድር አሊያም በክፍያ) ያስተላልፋል፤ የማሽኖቹን የረዥም ጊዜ ብድር አመላለስ ይከታተላል፡
 ወጣቶቹ በማሽኖቹ በሚሰጡት አገልግሎት/ቢዝነስ ሞዴል/ የተነሳ በገበሬውና በግብርና ስራው ላይ የመጣውን ለውጥ (Impact
assessment/research) ጥናት በበላይነት ይመራል- ለካምፓኒውና ለአጋር ድርጅቶቹ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

15
 ለወጣቶቹ ምርቶች ለአገልግሎት ሰጪ ወጣቶች ብሎም ለፕሮጅክቶቹ ከመንግስትና ከግል ባለሃብቶች ጋር በመተባበር የገበያ
ማፈላለግ ስራን በበላይነት ይመራል፡፡

 የኮሌጁ ንብረት 30 ሄክታር በሆነው መሬት ላይ በጋራ የማልማት ፕሮጅክቶችን ይቀርጻሉ ያከናውናሉ ማሽኖቹንም የመሞከሪያና
የሰርቶ ማሳያ ግብአትነትም ጭምር ይጠቀሙባቸዋል፡፡

3.2. - ካምፓኒው በበኩሉ፡-


 ለታቀዱት ፕሮጅክቶች የሚሆኑ የመስሪያ መሳሪዎችን (አላቂና ቋሚ ግብአቶችን በተለይም የሚገጣጠሙ የቴክኖሎጂውን
አካላት ለ-assembly) ያሟላል፡
 ለፕሮጅክቶቹም የስልጠናና የማምረቻ ማኑዋሎችንና ዲዛኖችን በስራ ቋንቋ ያዘጋጃል፤አሰልጣኞችንም በራሱና ከአጋር የቴክኒክና
ሙያ ኮሌጁ ጋር በቅንጅት ያዘጋጃል፡፡
 ለምርትና ለምርምር ስራዎቹ የስራ ማስኬጃና የጥናት በጀት ይመድባል፡፡
 ለምርትና ሽያጭና ለጥናት እና ተያያዥ ስራዎች የሰው ሃይል ከኮሌጁና ከቴክኒክና ሙያ ተቋሙ የሚመደቡ ግለሰቦችን በዋነኛነት
ይቀጥራል (የስራ እድል ይፈጥራል)፡፡
 በተያያዘም- ከኮሌጁና ከአጋሮቹ አካላት ለፕሮጅክቱ ተበርክተው ለሚገለገልባቸው አቅርቦቶች ተገቢውን ጥንቃቄ ያደርጋል
ብልሽቶችንም በጋራ ይጠግናል፡፡
 የፕሮጅክቶቹ ስራዎች በሚጠናቀቁበት ጊዜ ወይም የውሉ ጊዜ በሚጠናቀቅበት ወቅት አንዳንድ የማምረቻ ማሽኖቹን
እንደየአስፈላጊነቱ ለኮሌጁና ለአጋር የማሰልጠኛ ተቋማት ለሚማሩ ተማሪዎች መገልገያነት በስጦታ ሊያበረክት ይችላል፡፡
 ኮሌጁን ከሌሎች የካምፓኒው (የሃገር ውስጥና የውጪ) አጋር ድርጅቶችና ኮርፖሬሽኖች፤ ዩኒቨረስቲዎችና የበጎ ፍቃድ ወዘተ…
ድርጃቶች ጋር የማገናኘት፤
 በተጨማሪም ከፕሮጅክቱ ተዛማጅ የሆኑ የጥናት ጽሁፎችን በአለማቀፍ አጋር ተቋማቱ በኩል የማሳተምና የማስተዋወቅ ስራ
ይሰራል፤ በጋራ የገቢ (Fund) ማፈላለግ ስራዎችን የመስራት፡ ኮሌጁን ከአለማቀፍ ተቋማቱና አጋሮቹ በኩል የማስተሳሰር ስራን
ይሰራል፡
 ለኮሌጁ መምህራን (በተለይም ከፕሮጅክቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላላቸው) ተሳታፊዎች በተቻለው መጠን በአጋር አለማቀፍ
ዩኒቨርስቲዎች/ኮሌጆች በኩል የሚወጡ የስኮላርሽፕ ወዘተ ተጠቃሚ ለማድረግ የግንኙነትና የድጋፍ ደብዳቤ የመስጠትና መሰል
እገዛዎችን ያደርጋል፡፡

አንቀጽ አራት

16
ስለ ትርፍና ኪሳራ አከፋፈል በተመለከተ

ኮሌጁ የመንግስት ተቋም እንደመሆኑ መጠን እና ካምፓኒው (አትራፊ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን) ፤ በጋራ የቢዝነስ ስራዎችን ለመስራት
(የህጉ ማዕቀፍ በሚፈቅድላቸው መጠንና ሁኔታና ልክ) በጋራ ተነጋግረው ቢዝነሶችን የማቀድና- በተጨማሪ ዝርዝር የሆኑ የውስጥ
መመሪያዎችና ደንቦች በኩል በማጽደቅ መተግበር የሚችሉ ይሆናል፡፡ ይሁንና- አሁን በዚህ ስምምነት ላይ በዋነኛነት ስለቀረበው (የ ሰብል
መፈልፈያ ማሽን የቢዝነስ ሞዴል ማስጠኛና ማስገምገሚያ) ፕሮጅክት በተመለከተ ግን- በካምፓኒው አስቀድሞ ወጪ የተደረገው ከፍተኛ
ኢንቨስትመንትና በጉዳዩ ላይ ተያያዥ በሆኑ አካላት ተጨማሪ የውሳኔ ተሳትፎ ማስፈለግ የተነሳ፤ የዚህ ብቸኛ ፕሮጀክት ትርፍ
የካምፓኒውና የተጠቃሚ/የተሳታፊ/ ወጣቶቹ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን (ከላይ በአንቀጽ ሶስት) ላይ እንደተገለጸው በኮሌጁና በካምፓኒው የጋራ
ተሳትፎ በቀጣይነት ሊሰሩ የሚችሉት (የተጨማሪ ቴክኖሎጂዎች ማምረትና ማከፋፈል፤ የኮሌጁን ሰፋፊ የመሬት ሃብት በጋራ የማልማት፤
የተጨማሪ ገቢ/Fund/ ወዘተ ላይ የሚመሰረቱ የወደፊት ሰፋፊ ፕሮጅክቶችና ቢዝነሶች…ወዘተ… ውጤቶች- በኮሌጁና በካምፓኒው
(እንዲሁም በማንኛውም ሌላ አጋር/ተሳታፊ/ አካል) በኩል በጋራ ተሰርተውና ለምተው- ትርፍና ኪሳራቸውም በጋራ ተሰልቶ
እንደየድርሻቸው መጠን የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

አንቀጽ አምስት
የውሉ ተቀባይ (የኩባንያው) ወርሃዊ የኪራይ ክፍያን (መክፈል ወይም አለመክፈል) በተመለከተ

ይህ በኮሌጁ እና በካምስ ኢንጂነሪንገ ካምፓኒ መካከል - የካምፓኒውን ፕሮጅክቶች በጋራ ለመስራት ወይም ለመደጋገፍ የተፈረመው
ስምምነት፤ ኮሌጁ የመንግስት ተቋም በመሆኑ ምክንያትና ራዕዩን ለሚደግፉና ለሚያስተገብሩ አካላት ድጋፍ ማድረግ የተቋቋመበት አንዱ
አላማው በመሆኑ- ኮሌጁ (እና አጋሮቹ) ለፕሮጀክቶቹ መሳካት ለካምፓኒው ለሚያቀርባቸው የመስሪያ ቦታዎችና ቢሮዎች ወዘተ ወርሃዊ
ክፍያን ከካምፓኒው የማይጠይቁ ይሆናል፡፡ በምላሹም ካምፓኒው በኮሌጁ (እና በአጋሮቹ) ለሚሰጡ ማህበራዊና የአካባቢ ጥበቃና መሰል
አገልግሎቶች የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ በአመት ወዘተ የሚያገኘውን የተጣራ ትርፉ ላይ አስልቶ በራሱ ውሳኔ ሊደጉም ይችላል፡፡

አንቀጽ ስድስት
ውሉ የሚሻሻልባቸው ወይም የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

ውሉ በማንኛውም ጊዜ ከተዋዋዮቹ በአንዱ ወይም በሁለቱም በሚነሱ ጥያቄዎች ወይም ሃሳቦች፤ ወይንም ፕሮጅክቶቹን በተሸለ
አማራጭ ማስፋትንና ማሳደግን ወይም መቀየርን ከመሻት አንጻር፤ ወይም ተዋዋዮች በዚህ ሰነድ መሰረት የገቧቸውን ግዴታዎች
ባለሟሟላታቸው፤ አሊያም የመንግስትን ተያያዥ የህግ ለውጦች ተከትሎ ሊሻሻል አሊያም ሊቋረጥ ሲችል፤ ሂደቱም የስምምነቱን ሰነድ
ክፍሎችና እንዳስፈላጊነቱም የተጨማሪ የስምምነት መመሪያን በመቅረጽ ያንን ተከትሎ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ይህንንም የተጨማሪ
የስምምነት መመሪያን መቅረጽን በተመለከተ- ተዋዋዮቹ ከዚህ ውል መፈራረም ቀጥሎ እንደ የውስጥ ስምምነት መመሪያ ወይም
መተዳደሪያ ደንብ አድርገው ሰነዱን በጋራ ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡

አንቀጽ ሰባት
አለመግባባትን ስለመፍታት

በዚህ ውል አተረጓጎም ወይም አፈጻጸም የተነሳ በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች መካከል አለመግባባት የተፈጠረ እንደሆነ በግልግል ስምምነት
አሊያም ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት በማቅረብ ሊፈታ ይችላል፡፡
አንቀጽ ስምንት
የውል ዘመን

ይህ አብሮ የመስራት የስምምነት ውል በኮሌጁና በካምፓኒው መካከል ሊሰሩ ከታሰቡት ሰፊና ጊዜን የሚጠይቁ ሃገራዊ ፕሮጅክቶች
ከመሆናቸው አንፃር እና ሊፈጥሩ ካሰቡት በርካታ የከተማና የገጠር ወጣት (ሴትና ወንዶችን) ያማከለ የስራ ዕድልን ውጤታማ ለማድረግ

17
ከማሰብ አንጻር፤ ፕሮጅክቶቹ አመርቂና ዘላቂ ውጤት እንደታሰበው ያመጡ ዘንድ በማሰብ ይህ ውል ለቀጣዮቹ ያልተወሰኑ አመታት
የሚያገለግል ይሆናል፡፡

አንቀጽ ዘጠኝ
ውሉ ስለሚጸናበት ጊዜ

ይህ ውል ከተፈረመበት ከዛሬ……. ወር….. ቀን …. ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆና፡፡

ውሉን የተፈራረሙ አካላት ስምና ፊርማ

በኮሌጁ (ወይም ተወካይ) በኩል በካምስ ኢንጂነሪንግ ካምፓኒ (ወይም ተወካይ) በኩል

ስም- ……. ስም- …….


ፊርማ ……. ፊርማ …….
ቀን - ………. ቀን- ……….

ምስክሮች

ስም ፊርማ ቀን
1…….. ………………. ……………
2……. ………………. ……………
3…… ………………. ……………

18

You might also like