You are on page 1of 68

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት

ልማት ሚኒስቴር

የለውጥ ሰራዊት ግንባታ የአደረጃጀትና የአሰራር


ማኑዋል

ለአሰልጣኞች ስልጠና የተዘጋጀ


መስከረም /2010 ዓ/ም
ቢሾፍቱ

1
የስልጠናው
የትኩረት
ነጥቦች

2
ሰልጣኞች ፡-
በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ምንነት
፣አስፈላጊነት፣ መርሆዎች፣ ማነቆዎችና
የስልጠናው ዋና የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀት አሰራርና
ዓላማ የግንባታ አቅጣጫዎች ዙሪያ በቂ ግልጽነት
ፈጥረው በቀጣይ ሌሎችን ማሰልጠን
እንዲችሉ ማስቻል ነው፡፡

3
1 መግቢያ
 ባለፉት አስራ አምስት ዓመታት ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት
እየተመዘገበና የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታም እየጎለበተ
ነው፣
 ይህንን ቀጣይ ለማድረግ ኪራይ ሰብሳቢነት ከምንጩ ማድረቅና
ልማታዊነት የበላይነቱን እየጨበጠ ማድረግ ያስፈልጋል፣
 በገጠር የልማት ሠራዊት ግንባታ አቅጣጫ ተነድፎና ተግባራዊ
ተደርጎ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር ውጤታማነት
እየተመዘገበ ነው፣
 በመንግሥት መዋቅር ውስጥም የተሟሟቀና የተደራጀ
የልማትና የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ትግል በሕዝቡ የተደራጀ
ተሳትፎ የማቀጣጠልና የማስቀጠል ተግባር እጅግ ወሳኝ ነው፣
1 …መግቢያ
 ጠንካራ የመፈፀም አቅም ያለውና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ
ፐብሊክ ሰርቪስ ለመፍጠር በ2012 ያስቀመጥነውን ራዕይ
ለማሳካት በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ክንፎች
በተጨባጭ የሚታዩትን ማነቆዎች በአግባቡ ለይቶ፣ ፈትሾና
ተገቢውን መፍትሔ አስቀምጦ ስራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል፣
 ይህ ሊሳካ የሚችለው ደግሞ በሁሉም የመንግስት ተቋማት
የተግባርና የአመለካከት አንድነትን በመፍጠር ነው፣
2. የለውጥ ሰራዊት ምንነት፣ አስፈላጊነት፣
መርሆዎችና ባህሪያት
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት

 የሰራዊት ግንባታ ዋነኛ ይዘት በአመለካከት፣ በአሰራርና


አደረጃጀት እንዲሁም በክህሎትና በዕውቀት ደረጃ
ተቀራራቢነትና ከሞላ ጎደል ወጥነት ያለው የለውጥ ሰራዊት
ኃይል መፍጠርን የሚመለከት ነው፣
 የአመለካከት መዘበራረቅ ከኖረ የለውጥ ሰራዊት ተፈጥሯል
ሊባል አይችልም፣
 የአሰራርና የአደረጃጀት መዝረክረክ ባለበት ሁኔታም የሀሳብና
የተግባር አንድነቱ የተረጋገጠ የለውጥ ሰራዊት ኃይል ይኖራል
ተብሎ አይታሰብም፣
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት

 የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አመለካከት ልዕልናን ያዳበረ፣


በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ በክህሎቱና በዕውቀቱ ተቀራራቢና
ውጤታማ የሆነ የለውጥ ሰራዊት የመገንባት ጉዳይ ሲነሳ
አብሮ መታወስ ያለበት ሌላው ጉዳይ የለውጥ ሰራዊቱ በአንድ
ተግባርና በአንድ ንዑስ ምዕራፍ ወይም አብይ ምዕራፍ
ተግባራት ብቻ አይገነባም፣
 አንድ መደበኛ ሰራዊት በአንድ ታክቲካዊ ግጥሚያ ብቻ
እንደማይገነባ ሁሉ የለውጥ ሰራዊት ግንባታም በተለያዩ
ወቅቶች የሚፈጸሙ ተከታታይነት ያላቸው ተግባራትን
በታቀደ አኳኋን በማዘጋጀትና በመፈጸም ብቻ ይፈጠራል፣
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት

• ምንም እንኳን የመጀመሪያው ተግባር በከፍተኛ ውጤታማነት


እስከተሰራ ድረስ የለውጥ ሰራዊት ለመፍጠር የሚያስችል
መሰረት መጣል ቢቻልም አንድና ያለቀለት የሰራዊት መገንቢያ
ተግባር አይሆንም፣
• ሰራዊቱ በአንድ ወይም በጥቂት ተግባራት አፈጻጸም ሂደት
ተፈጥሮ ግንባታው ግን በተከታታይ ተግባራት እየጎለበተና
ቀጣይነቱ እየተረጋገጠ የሚሄድ ነው፣
•  ሰራዊት በመገንባት አኳያ ወሳኙ ጉዳይ የአመለካከትና የተግባር
አንድነትን መፍጠር ነው፣
• የለውጥ ሰራዊት ከሀሳብና ከተግባር አንድነት ውጭ ፈጽሞ
ሊኖር አይችልም፣
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት

 የለውጥ ሰራዊት ከሀሳብና ከተግባር አንድነት ውጭ ፈጽሞ


ሊኖር አይችልም፣
 በአመለካከት ደረጃ ኪራይ ሰብሳቢነትና ልማታዊነት
በተደበላለቁበት ሁኔታ የለውጥ ሰራዊት ብሎ ነገር ሊኖር
አይችልም፣
 ስለሆነም በእያንዳንዱ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ ሁሉም ፈጻሚ
ኃይሎች አንድ ዓይነት የጋራ አስተሳሰብ መያዝ አለባቸው፣
 ኪራይ ሰብሳቢነት በየወቅቱ መልኩን እያቀያየረ
የሚያመጣቸውን የተሳሳቱ አስተሳሰቦች መጸየፍ፣ አምርሮ
መታገልና ማጋለጥም ይጠበቃል፣
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት

 የለውጥ ሰራዊት የሚኖረው በተመሳሳይ የተግባር ስምሪት


ነው፣
 አንዱ ቁልፍና አበይት ተግባራትን ለመፈፀም ሲረባረብ፣
ሌላው በሚያደናቅፍበት ወይም ግዴለሽ በሆነበት ሁኔታ
የለውጥ ሰራዊት ሊኖር አይችልም፣
 በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት እንዲገነባ ሁሉም
የሰራዊቱ አካላት በወቅቱ በተያዙት ቁልፍና አበይት ተግባራት
ላይ ድርሻ ድርሻቸውን ይዘው በውጤታማነት የሚረባረቡበት
ሁኔታ ሊኖር ይገባል፣
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት

ሲጠቃለል
 በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት የመገንባት ጉዳይ በሁሉም
ፈጻሚዎች ዘንድ የአስተሳሰብ፣ የተግባር፣ የአሰራር፣
የአደረጃጀትና እንደየአካሉ የክህሎት ተቀራራቢነትን አዳብሮ
በድህነት ላይ በጋራ የሚዘምት ኃይል የመፍጠር ጉዳይ ነው፣
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት

መከበርን ከፈለግን የውርደት ምክንያት የሆነውን


ድህነትን እናጥፋ!

ተኩሰን መግደል ከቻልን ከሁሉም በፊት መግደል


የሚገባን ድህነትን ነው!
2.2 የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊነትና
ፋይዳው

 የተቋማዊ ለውጥ ትግበራውን የበለጠ ለማጎልበት በመተግበር


ላይ ያሉትን የለውጥ መሳሪያዎች ተጠቅሞ ውጤት
እያስመዘገበ፣ በታዩ ውጤቶችና የወደፊት ተስፋ ህዝቡን
እየነሸጠና እየኮረኮረ ወደ ጸረ ድህነት ትግል የሚያስገባና
በገባበትም ትግል ጸንቶ እንዲቀጥል የሚያስችል ትግልን አጀንዳ
አድርጎ የሚጓዝ የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት
ማደራጀትና ወደ ስራ ማስገባት አስፈላጊ ነው፣
2.2 የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊነት…

 በሌሎች ሴክተሮች የልማት ሰራዊትን በማደራጀት በተገኙ


መልካም ውጤቶች መነሻነት የመንግስት ፖሊሲዎችና
ስትራቴጂዎች አስፈጻሚና ዋነኛ መሳሪያ በሆነው በፐብሊክ
ስርቪሱ ውስጥም ተግባራዊ በማድረግ የተጀማመሩትን ተስፋ
ሰጪ ውጤቶች እያሰፉ መሄድ ተገቢ ነው፣
መንግስት እና ዜጋው በመተባበር፣ በመቀናጀትና ለውጡን
መሰረት በማድረግ የልማት፣ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና
የመልካም አስተዳደር እቅዶችን በቅልጥፍናና በውጤታማነት
ለመፈጸምና የህዝብን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ
የሚያስችል የፐብሊክ ስርቪስ የለውጥ ሰራዊት መገንባት
አስፈላጊ ነው፣
2.1 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት…

 በተቋማዊ ለውጡ አማካኝነት የተፈጠረውን አደረጃጀትና


አሰራር በመጠቀም ውጤት እንዲያመጣ የሚፈለገው የሰው
ኃይል ድህነት ዋነኛ የጋራ ጠላት እንደሆነና በጋራ ሊዘመትበት
እንደሚገባ ተረድቶ በአመለካከቱ አዎንታዊ ለውጥ በማምጣት
ፈጣን ልማታችን ቀጣይነት እንዲኖረው እንደሰራዊት
በመዝመት ተኪ የለሽ ድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ፣
 መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ውስጥ
ህዝቡን ወይም ተገልጋዩን ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም
ባለው ሂደት ውስጥ ድርሻውን በባለቤትነት እንዲወጣ
በማነቃነቅና በማሳተፍ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ፣
2.2 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ምንነት…

 በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊትን መገንባት የኪራይ


ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር መንስዔ የሆኑና ከዕርሱ
የሚመነጩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማዳከም ብሎም
በማክሰም በምትኩ የልማታዊ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ አስተሳሰብ
እንዲጎለብት ማድረግ፣

 በየደረጃው በሚገኙት የሰራዊት ክንፎችና አካላት መካከል


የአመለካከትና የተግባር አንድነት እንዲፈጠር ለማድረግ፣ የቡድን
መንፈስን ለማዳበር፣ የሰራዊቱን አቅም ለማመጣጠን፣ ምርጥ
ተሞክሮዎችን በፍጥነት ለማስፋትና የፐብሊክ ሰርቪሱን የእርስ
በርስ መማማር ቀጣይነት ባለው ሁኔታ መገንባት፣
2.3 የለውጥ ሠራዊት የሚመራባቸው መርሆዎች

1. የሕግ የበላይነት
2. ቀልጣፋነትና ውጤታማነት
3. ለጋራ ስኬት በጋራ መረባረብ
4. ተሳትፏአዊነት
5. የጋራ መግባባት
6. ግልጽነት
7. ተጠያቂነት
8. የህዝብን ጥቅም ማስቀደም
9. ሴኩላሪዝም እና
10. በሥራ አፈጻጸም ውጤት ብቻ መመዘን
ናቸው፡፡
2.4 የለውጥ ሰራዊት ሊኖረው የሚገባው
ባህሪያት
የራሱ የሆነ የጋራ ራዕይና ተልዕኮ ያለው፣ ዕቅድን
በጋራ የሚያቅድ፣
የየዕለት ተግባሩን ከስትራቴጂያዊ ዕቅድ ጋር
በማስተሳሰር የሚተገብርና የሚገመግም፣
 ጠባቂነትን ያስወገደ እና በራስ ተነሳሽነት የሚሰራ፣
ለለውጥ ሰራዊት ግንባታ መርሆዎች ተገዥ የሆነ፣

07/27/22 19
2.4 የለውጥ ሰራዊት ሊኖረው የሚገባው …

 አፈፃፀምን መሰረት ያደረገ ምዘናን ተግባራዊ የሚያደርግ፣


 ለተገልጋይ ተገቢውን ክብር የሚሰጥ፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ
ውሳኔ የሚሰጥ፣
 የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባር በስራው ላይ
የሚጠላና የሚታገል፣
 ያለውን ዕውቀት፣ ክህሎትና መልካም ልምድ ለሌሎቹ
የሚያካፍል

07/27/22 20
2.4 በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ተገንብቷል
የሚባለው መቼ ነው?...
በአመለካከት ደረጃ ኪራይ ሰብሳቢነትና ልማታዊነት
በተደበላለቀበት ሁኔታ የለውጥ ሰራዊት ብሎ ነገር ሊኖር
አይችልም፣
አንዱ ቁልፍና አበይት ተግባራትን ለመፈጸም ሲረባረብ፣
ሌላው በሚያደናቅፍበት ወይም ግዴለሽ በሆነበት ሁኔታ
የለውጥ ሰራዊት ሊኖር አይችልም፣
ስለሆነም የለውጥ ሰራዊት እንዲፈጠርና እንዲገነባ
ሁሉም ፈጻሚዎች በወቅቱ በተያዙት ቁልፍና አበይት
ተግባራት ላይ ድርሻ ድርሻቸውን ይዘው በውጤታማነት
የሚረባረቡበት ሁኔታ ሊኖር ይገባል፣
3. የለውጥ ሠራዊት አካላት
3. የለውጥ ሠራዊት አካላት…

 የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሠራዊት ሁለት ክንፎች


አሉት፡፡ እነዚህም የመንግስት ክንፍና የህዝብ ክንፍ ናቸው፡፡
 የመንግስት ክንፍ በየደረጃው የተዋቀሩ የመንግስት
አደረጃጀቶችን ያቀፈ ነው፣
 የህዝብ ክንፉ ደግሞ የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶችንና
ዜጋውን የሚመለከት ነው፣
 ሁለቱም ክንፎች ራሱን የቻለ አደረጃጀት፣ ተልዕኮና
አሰራር ሊኖራቸው ይገባል፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ

 በማንኛውም ደረጃ በተቋቋመ የመንግስት   መስሪያ


ቤት   ውስጥ   ያለው የተቋሙ አመራርና መላው
ሰራተኛ   አንድ   የሰራዊት   ክንፍ   ሆኖ እንደ
ተቋሙ ተጨባጭ ሁኔታ አምስት   እርከን አሊያም ከስራ
ሂደት በታች ቡድን ከሌለ በአራት እርከን   ይደራጃል፣  
 ስለዚህ   የመንግስት መዋቅር   አንድ  የሰራዊቱ  ክንፍ
 ሆኖ የአምስት ወይም የአራት እርከኖች ውህድ  ሆኖ
ይደራጃል፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ

እነዚህም፡-  
 የተቋሙ ከፍተኛ አመራር፣
 መካከለኛ አመራር፣
 የቡድን መሪ
 ግንባር ቀደም እና
 መላው ፐብሊክ ሰርቪስ ሰራተኛ ሲሆኑ
ይህም በአንድ የመንግስት   ተቋም   ውስጥ   በዝቅተኛው  
የስራ   ደረጃ   ላይ   ከተመደቡት   ሰራተኞች   እስከ  
ተቋም   ከፍተኛ   አመራር   የሠራዊት   አካል  
ሆነውና   እንደ አንድ አሀድ/አካል   ተዋህደው  
የሚደራጁበትና   የተቋም   ተልዕኮን   በጋራ   ለማሳካት
የሚንቀሳቀሱበት   አደረጃጀት   ነው፡፡
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ

3.1.1. ከፍተኛ አመራር


 የተቋሙ ከፍተኛ   አመራር   ሲባል   የመንግስት   ተቋማትን  
እንዲመሩ   የተሾሙ ሚኒስትር፣ ሚኒስትር ዴኤታ፣ ጽ/ቤት ሀላፊ፣ ዋና
ዳሬክተር እና ምክትሎቻቸውን እንዲሁም በነዚህ ደረጃ የተሾሙ የፖለቲካ
አመራሮችን ያጠቃልላል፡፡
 ይህ   አካል   የሠራዊት   አመራር   ሊያሟላ   የሚገባውን
የስራ   አመራር   ብቃትና   ስነ   ምግባር   ማሟላትም  
ይጠበቅበታል፣
 ጠንካራ መሪ የሌለው   ሠራዊት   የተሟላ   ስብእና   እና  
አደረጃጀት   ተከትሎ   የተሟላ ውጤት   ለማምጣት የሚሳነው  
ከመሆኑ   ጋር   ተያይዞ   ሲታይ   የከፍተኛ   አመራሩን  
ተልኮ   ቁልፍ ያደርገዋ፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…
3.1.1. ከፍተኛ አመራር…
 የለውጥ ሠራዊት   አመራሩም   የሚፈጠረው   በተግባራዊ  
እንቅስቃሴ   ውስጥ   ገብቶ የሚረባረብ   የለውጥ   ሠራዊት  
በማደራጀትና   በመምራት   ሂደት   ነው፣  
 ከበታች   ያሉትን   የመካከለኛ   አመራሮችና   መላውን  
ፐብሊክ ሰርቪስ   በመገንባትና   በማሰማራት   ሰፊ   ልማታዊ  
ተነሳሽነት   በመፍጠር ለውጡን በባለቤትነት   መምራት፣
 ሠራዊት   በሙሉ   ልማታዊና   ዲሞክራሲያዊ   በሆነ መንገድ
ተልኳቸውን   በብቃት እንዲወጡ ማስቻል ፣
 ጥራት   ያለው   እቅድ   በሠራዊት   ክንፎች   ሙሉ  
ተሳትፎ   በማዘጋጀት   ፈጻሚን   ለተልዕኮው ማዘጋጀት፣
 የለውጡን እንቅስቃሴ መከታተል፣ መገምገምና ማረጋገጥ፤
እንዳስፈላጊነቱ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ እና ቀጣይ አቅጣጫ
መስጠት ይጠበቅበታል፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…

3.1.2. የተቋም መካከለኛ አመራር


 የመንግስት   መካከለኛ አመራር   ማለት   በመንግስት   ተቋማት  
ውስጥ   በሙያው   አመራር   የሚሰጥ   እና   በሜሪት  
የተመደበ   ሙያተኛ   አመራር   ሲሆን፣ የስራ ሂደት መሪዎችን ወይም
ዳይሬክተሮች እና በዚህ   ደረጃ   ከተቋሙ   ከፍተኛ   አመራር  
ቀጥሎ   የተመደቡ   የፐብሊክ   ሰርቪስ   የስራ ኃላፊዎችን
የሚያጠቃልል ነው፡፡
የዚህ አካል ተልዕኮዎች ውስጥ ዋናዋናዎቹ፡-
 በስሩ ያለውን ፐብሊክ ሰርቫንት የለውጥ ሠራዊት አንድ አካል አድርጐ
በማደራጀት ማስተባበርና መምራት፣
 በስሩ የተደራጀው የለውጥ ሠራዊት ግንባር ቀደም ሚናውን እንዳይወጣ
እንቅፋት የሚሆኑ የአመለካከት፣ የክህሎት እና የቅርቦት እጥረቶችን እለት
በእለት እየተከታተሉ መፍታት፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…

3.1.2. የተቋም መካከለኛ አመራር …


 የለውጥ ሠራዊቱ በተግባራዊ የሥራ እንቅስቃሴው ግንባር
ቀደም ሆኖ እንዲወጣ ተግባር ቆጥሮ በመስጠት አፈጻጸሙን
የመከታተልና የመመዘን ስራ መስራት፣
 ለሚመራው አካላት አብነታዊ ሆኖ መገኘትና ሌሎችም
አርአያነቱን እንዲከተሉ መንቀሳቀስ፣
 የለውጥ ሠራዊት ቡድንና ግለሰቦችን በስራ ውጤታቸው
መሰረት በጋራ በመለካት፣ በአፈጻጸማቸው ወደፊት የወጡትን
ማበረታታት፣ የደከሙትን የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው እንዲማሩ
ማድረግ፣ እንዲሁም በደረጃቸው ማስቀመጥ፤
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…

 3.1.3. ቡድን መሪ
 በመንግስት ተቋማት አደረጃጀት የስልጣን ተዋረድ ከመካከለኛ
አመራሩ(የስራ ሂደት) ቀጥሎ ባለው እርከን በአንዳንድ ተቋማት
የስራ ቡድን የሚደራጅበት ሁኔታ አለ፡፡
የቡድን መሪው፡-
 በቡድኑ ስር ያሉትን የሠራዊት አባላት በአመለካከትና በክህሎት
ያላቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን ለይቶ ማወቅ፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…
3.1.3. ቡድን መሪ…
 ደካማ ጎናቸውን ለመፍታት ተገቢውን ሁሉ ለማድረግ አቅዶ
መስራት፣
 በየዕለቱ መከታተልና በየሳምንቱ በቋሚ ግንኙነት ፕሮግራም
በተልዕኳቸው ዙሪያ ያላቸውን አፈጻጻም መገምገምና ከፍተቶች
ሳይሰፉ የሚደፈኑበትን አግባብ በመቀየስ ስራ ላይ ማዋል፣
 ሁሉም ወደ ግንባር ቀደምነት እንዲመጡ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣
 የሠራዊት መንፈስ እንዲዳብርና ይህንን የሚጎዳ ማንኛውም ሁኔታ
ተከታትሎ እንዲወገድ ማድረግ፣
 አስፈላጊውን መረጃ መያዝና የአፈጻፀም ሪፖርት ለስራ ሂደቱ መሪ
በየሳምንቱ ማቅረብ፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…

3.1.4 ግንባር ቀደም

 ግንባር ቀደም ማለት በአንድ የስራ ሂደት ወይም በቡድን አደረጃጀት


ውስጥ ካሉት ሰራተኞች በአመለካከቱ፣ በክህሎቱ፣ በስነምግባሩ፣ በስራ
አፈጻፀሙ፣ በፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት አቋሙና ትግሉ፣ በተባባሪነቱ፣ በስራ
ተነሳሽነቱ፣ ወዘተ ከሌሎች ሰራተኞች በተግባር ውጤቱ ጎላ ብሎ
በአርአያነት የሚታይ የስራ ሂደት ኃላፊ፣ የቡድን መሪ ወይም ሰራተኛ
ሊሆን ይችላል፡፡
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…
ግንባር ቀደም የውጤት ተኮር የሥራ አፈጻጸም ሥርዓትን ተከትሎ
የሚመረጥ ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያከናውናል፡፡
የራሱን ተልዕኮ በተሟላ መጠንና ጥራት መፈፀም
ሌሎች ሰራተኞችን ራሱ በደረሰበት የአመለካከት እና የአፈጻፀም
ደረጃ እንዲደርሱ ማገዝ፣
ልምዱን በማካፈል ሌሎች በአመለካከትና በክህሎት ያለባቸውን
ክፍተት ለመሙላት ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣
ለላቀ ውጤት የሚያበቁ የራስ አቅም ማጎልበቻ ተግባራትን
ማከናወን፣
አዳዲስ አሰራሮችን ማመንጨትና እንዲለመዱ እገዛ ማድረግ፣
ከአቻ ግንባር ቀደሞች ጋር በመመካከር የተቋሙ ወይም የሥራ ሂደቱ
ተልዕኮ ስለሚሳካበት ሁኔታ ለአመራሩ ሀሳብ ማቅረብ፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…
3.1.5 መላው ፐብሊክ ሰርቫንት (ሠራተኛ)
መላ   ፐብሊክ   ሰርቫንት የምንለው ከስራ ሂደት መሪዎች/
ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ቀጥሎ በመንግስት ተቋማት
በሙያው ህዝብን   ለማገልገል   የተቀጠረውን መላ ሰራተኛ
ያጠቃልላል::
መላው ሲቪል ሰራተኛ የሚደራጀው በዋነኛነት የስራ ሂደትን
መሰረት አድርጎ ይሆናል፣
በአንድ የስራ ሂደት አንድ ወይም ከዚያ በላይ የአንድ
ለአምስት የለውጥ ሰራዊት ይደራጃል፣
3.1. የለውጥ ሠራዊቱ የመንግስት ክንፍ…
 እንደ ቡድን የዕለትና የሳምንት እቅድ በትክክል ለተቋሙ ተልዕኮ ማሳካት
ያለውን ፋይዳ በማረጋገጥ አቅዶ ይፈጽማል፣
 የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት በተቋሙ ዕቅድና የአሰራር ስርአቶች ላይ በቂ
ግንዛቤ ጨብጦ ህዝቡን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል ይኖርበታል፣
 የጋራ ተልዕኮን ለማሳካት የመተጋገዝና የእርስ በርስ መማማሪያ መድረኮችን
ከዕለት ተዕለት ስራ ጋር አዋህዶ በመፈጸም አቅሙን ማሳደግም
ይጠበቅበታል፣
 በተቋሙ ካሉ ሌሎች የሠራዊት ቡድኖች ጋር ትስስር በመፍጠርና
በማጠናከር ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ ጥሩ አፈጻጸሞችን ያጎለብታል፤
እጥረቶች እንዳይደገሙ ይሰራል፣
 ከሂደቱ፣ ከቡድኑ የወረደለትን ተግባራት በየቀኑ፣ በየሳምንቱና በየወሩ
ከፋፍሎ በጥራት፣ በመጠንና በጊዜ በማቀድ፣ አፈፃፀሙንም በየሳምንቱ
ለሂደት/ለቡድን መሪው ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ

የለውጥ ሰራዊቱ የህዝብ ክንፍ የለውጥ ሰራዊቱ ሁለተኛ


ክንፍና ዋነኛ የለውጡ ባለቤትና ተጠቃሚም ነው፣
ህዝቡ በተደራጀ መልኩ የሰራዊቱ አካል መሆን አለበት፣
የህዝብ የተደራጁ አካላት በተለይም የብዙሃንና የሙያ
ማህበራት የአባላቶቻቸውን መብትና ጥቅም
ለማስጠበቅና የልማትና የመልካም አስተዳደር
ፍላጎቶቻቸው እንዲሟላላቸው ሚናቸውን
ለመጫወት ዋነኛ የለውጡ ፈፃሚ ሃይሎች ሆነው
መገንባት አለባቸው፣
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ…

የህዝብ ክንፍ ልየታ፡-


 ማንኛውም የመንግሥት ሴክተር መ/ቤት መጠኑና ስፋቱ
ይለያይ እንጂ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አገልግሎት የሚሰጠው
የህብረተሰብ ወይም የህዝብ ክንፍ ይኖረዋል፣
 በመሆኑም በየተቋሙ የህዝብ ክንፍ ሆኖ የሚለየው እንደ
ተቋሙ ተልዕኮና የአገልግሎት አይነት የሚለያይ ነው፣
 እያንዳንዱ ተቋም የህዝብ ክንፍን ሲለይ፡-
 የሙያ ማህበራት፣ የብዙሃን ማህበራት እና አጋሮችን
እንዲሁም ልዩ ልዩ ተገልጋዮችን በዝርዝር መለየት፣
የሚለየው የህዝብ ክንፍ የተደራጀ ተቋማዊ ህልውና ያለው
መሆኑን ማረጋገጥ፣
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ…

የብዙሀንና ሙያ ማህበራት አደረጃጀት


 የተደራጁ የፆታ፣ የእድሜ ወይም የሙያ ማህበራት እንደ
ሴቶችና ወጣቶች፣ መምህራን፤ ሰራተኛ ወ.ዘ.ተ ያሉትን
ናቸው፣
 ነጻ ማህበራት ስለሆኑ ነፃነታቸውን በማክበርና በመጠበቅ
በአጋርነት መርህ በጋራ ለመስራት የሚያስችል አቅጣጫን ነው፣
 ምንም እንኳን ሁሉንም ማህበራት መደገፍና ማጠናከር የሚገባ
ቢሆም ሰፋ ያለ የህብረተሰብ ክፍል ለሚያንቀሳቅሱት የሴቶች፣
ወጣቶች፣ የአርሶ አደር፣ የሰራተኛ፣ የመምህራን፣ የአነስተኛና
ጥቃቅን ተቋማት አደረጃጀቶች ትኩረት መስጠት አለብን፣
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ…

አጋር የህዝብ ክንፍ


 በዚህ ደረጃ የሚታዩት በአብዛኛው የግል ልማታዊ ባለሃብት
አደረጃጀቶች ናቸው፣
 ስለሆነም ፈጣን ልማትን ለማረጋገጥ ይህንን ኃይል በልማታዊ
መንገድ በሰፊው ማሳተፍና በሂደትም በቁጥርና በአቅሙ
በከፍተኛ ደረጃ እንዲጠናከር ማድረግ ይገባል፣
 ከባለሃብቱ ጋር የሚኖረን መስተጋብር በዋናነት እነዚህን
የባለሃብቱን አደረጃጀቶች በመጠቀም የሚፈፀም መሆን አለበት፣
 የተፈጠሩት አደረጃጀቶች ባለሃብቱ በልማታዊ መንገድ
ያልተቆጠበ ድጋፎችን የምንሰጥባቸውና የምናስተጋባባቸው
መድረኮች መሆን አለባቸው፣
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ…

ሌሎች ተገልጋዮች
ሌሎች ተገልጋዮች የሚባሉት ከላይ በህዝብ ክንፍ
ከተጠቀሱት ውጭ የሆኑ ነገር ግን ከመንግስት ተቋማት
አገልግሎት የሚያገኙ ግለሰቦች ወይም ሌሎች የመንግስት
ተቋማት ናቸው፡፡
ለምሳሌ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ልማት ሚኒስቴር፣
የፐብሊክ ሰርቪስ ሚኒስቴር “ሌሎች ተገልጋዮች”
በሚለው ምድብ ውስጥ ይሆናሉ፣
ተቋማት እነዚህን ተገልጋዮች ለህዝብ ክንፍ
እንደሚደረገው የራሳቸውን መድረክ በቡድን፣ በስራ ሂደት
ወይም በተቋም ደረጃ በማመቻቸት እንደሰራዊት
የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል፣
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ…
የህዝብ ክንፍ ልየታ…

 የአንዳንድ ተቋማት ሰራተኞች በልዩ የሥራ ባህሪያቸው


ምክንያት በተናጠል እንደ ግለሰብ ሲሰማሩ ፈጻሚ የመንግሥት
ክንፍ (ፐብሊክ ሰርቫንት) ይሆናሉ፣
 በሌላ በኩል ደግሞ እንደሙያቸው በማህበር ተደራጅተው
ሲመጡ እንደ ህዝብ ክንፍ የሚወሰዱ ሊሆኑ
ይችላሉ(መምህራንና የመምህራን ማህበር፣ነርሶችና የነርሶች
ማህበር ወ.ዘ.ተ. )
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ…

የሚሰጡትን አገልግሎት በተዘዋዋሪ የሚጠቀም የህብረተሰብ ክፍል ወይም


የህዝብ ክንፍ ያላቸው የመንግስት መ/ቤቶች፣
 ለአብዛኞቹ አስፈጻሚ አካላት የጋራ የህዝብ ክንፍ ሆነው
የሚያገለግሉ አደረጃጀቶችን በጥንቃቄ በመለየት በተዘዋዋሪ
የራሳቸው የህዝብ ክንፍ አድርገው ይጠቀማሉ፣
 የመድረኮችን ድግግሞሽ ለመቀነስ ሲባል መደበኛ የግንኙነት
መድረክ በየስድስት ወሩ ይካሄዳል፣
 ካለው ልዩ የስራ ባህርይ አንጻር ከውጭ ተገልጋይ ጋር ፊት ለፊት
የሚያገናኝ አሰራር የሌለው የመንግስት ተቋም በህዝብ ክንፍነት
የሚያሳትፋቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ወይም አደረጃጀቶች
ከመለየት አንጻር ችግር ካጋጠመው ጉዳዩን ለፐብሊክ ሰርቪስና
የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አቅርቦ የጋራ መፍትሄ አቅጣጫ
የሚቀመጥ ይሆናል፣
3.2. የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ…

የህዝብ ክንፍ ልየታ…


 እያንዳንዱ ተቋም የየራሱን የህዝብ ክንፍ በከፍተኛ አመራር፣
በመካከለኛ አመራሮችና በመላው ሠራተኛ ስምምነት
በተደረሰበት መልኩ ሊያረጋግጥ ይገባል፣
 የህዝብ ክንፉ የውይይት አጀንዳ የሚያተኩረው፡-
በሀገራዊ የልማት ዕቅዶች፣
በየዓመቱ የሚታቀዱ የውጤት ተኮር ዕቅዶች፣
በዜጎች ቻርተር የተመለከቱ የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ
ስታንዳርዶችና የመሳሰሉት ይሆናሉ፡፡
4. የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና አሰራር
4.1. የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና አሰራር

4.1.1. የተቋም የበላይ አመራር


 የተቋም የበላይ አመራር የመንግስት   ተቋማትን   የሚመሩ
ሚኒስትሮች፣  ሚኒስትር ዴኤታዎች፣  ጽ/ቤት  ሀላፊዎች፣ 
ኮሚሸነሮች፣  ም/ኮሚሸነሮች ዋና ዳሬክተሮች እና ምክትሎቻቸውን
እንዲሁም በነዚህ ደረጃ ያሉ ተሿሚዎችን የሚያጠቃልል ነው፣
 የተቋሙ የበላይ አመራር የውይይት መድረክ በሁለት ሳምንት አንድ
ጊዜ ይካሄዳል፣
4.1. የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና አሰራር…
4.1.2 የተቋሙ የስራ አመራር/ማኔጅመንት መድረክ
የተቋሙ የስራ አመራር/ማኔጅመንት የተቋሙን የበላይ አመራሮች እና
መካከለኛ አመራሮችን የሚያጠቃልል ነው፣
ይህ መድረክ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ የሚካሄድ ሆኖ በዋናነት የተቋሙን
ወርሃዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫን
ያስቀምጣል፣
ተጠሪ ተቋማት ያላቸው ሚኒስቴር መ/ቤቶች የተጠሪ ተቋማት ሃላፊዎች
የሚገኙበት ተጨማሪ አደረጃጀትና የግንኙነት ጊዜ ሊኖራቸው ይችላል፣
(የበላይ እና መካከለኛ አመራር በወር አንድ ጊዜ የሚኖራቸው መድረክ
እንደተጠበቀ ሆኖ የተቋሙ የበላይ አመራሮችና የተጠሪ ተቋማት የበላይ
አመራሮች የጋራ መድረክም በየወሩ የሚካሄድ ይሆናል)
4.1. የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና አሰራር…

4.1.3 የዘርፍ ሃላፊዎችና የመካከለኛ አመራሮች መድረክ


 በፌዴራል ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ምክትል
ዳይሬክቶሬቶች ወይም በእነሱ ደረጃ የሚመደቡ ሃላፊዎች
የሚመሩአቸው ዘርፎች አሏቸው፣
 የዘርፎቹ የበላይ አመራሮች በየዘርፉ ከሚገኙ መካከለኛ
አመራሮች ጋር በየአስራ አምስት ቀኑ የጋራ መድረክ ይኖራቸዋል፣
 በዚህ መድረክ የዘርፉና በዘርፉ ስር የሚገኙ የስራ ሂደቶች የቁልፍ
ተግባርና የአበይት ተግባራት አፈጻጸም ይገመገማል፤ አፈጻጸም
የታዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶች ተለይተው ቀጣይ የትኩረት
አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ፣
4.1. የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና አሰራር…

4.1.4 የስራ ሂደት መሪና የሰራተኞች መድረክ


 በስራ ሂደቱ የሚገኙ አጠቃላይ ሰራተኞች ከስራ ሂደት መሪው
ጋር የሚያካሂዱት ሲሆን መድረኩም በየሳምንቱ የሚካሄድና
ከስራ ሂደቱ ዕቅድ በሳምንቱ የሚተገበሩ ስራዎች የሚለዩበትና
አፈጻጸሙ የሚገመገምበት ይሆናል፣
 በስራ ሂደት ስር ያሉ የቡድን አደረጃጀቶች በሳምንት ሁለት
ጊዜ የግንኙነት መድረክ ይኖራቸዋል፣
4.1. የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና አሰራር…

4.1.5 የ1ለ5 የለውጥ ቡድን መድረክ


 ይህ መድረክ በስራ ሂደት ወይም በስራ ቡድን ውስጥ አንድ ግንባር
ቀደም/የተሻለ ፈጻሚ የሚያስተባብራቸውን ከ3-7 (በአማካይ 5)
ፈጻሚዎችን የያዘ የ1ለ5 የለውጥ ሰራዊት ቡድን መድረክ ነው፣
 የ1ለ5 የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት ከተቋም ተልዕኮ ተመንዝረው
የሚወርዱ ስራዎችን የሚፈጽሙ ሰራተኞችን ያቀፈ በመሆኑ
የሰራዊት ግንባታን ከማጠናከር አንጻር ቁልፍ ሚና ያለው ነው፣
 መድረኩ የቡድኑ አባላት ዕለታዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ
አፈጻጸማቸውን በየቀኑ የሚገመግሙበት፣ በመማማር
አቅማቸውን የሚያጎብቱበት፣ በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠማቸውን
ችግር የሚለዩበትና ለቀጣይ የተግባር ምዕራፍ የሚዘጋጁበት ነው፣
4.2 የለውጥ ሠራዊት ክንፎች ትስስርና
የግንኙነት አሰራር
4.2.1 የግንኙነት አሰራርና የውይይት አጀንዳዎች

 የመንግስት ክንፉና የህዝብ ክንፉ ሀገራዊ ተልእኮንና ግብን


ለማሳካት በቅንጅትና በጋራ መንቀሳቀስ አለባቸው፣
 ለዚሁም እነዚህን ሁለት ክንፎች በማስተሳስር ለጋራ
ውጤትና ስኬት በጋራ የሚሰሩበትን አግባብ ማመቻቸት
ያስፈልጋል፣
 በዚሁ መሰረት የመንግስት ክንፍ ከህዝብ ክንፍ አካላት ጋር
ቢያንስ በየሶስት ወሩ በመገናኘት ውይይት ያደርጋሉ፣
4.2 የለውጥ ሠራዊት ክንፎች ትስስርና …
የመንግስት ክንፉ የጋራ የውይይት አጀንዳ ከሚያተኩርባቸው ዋና ዋና
ጉዳዮች ፡-
 የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም፣
 በየዓመቱ የሚታቀዱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ፣ የሪፎርምና የመልካም
አስተዳደር እንዲሁም የልማት ተግባራት ዕቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም
ግምገማ፣
 በመንግስት ክንፉ በሚዘጋጁ የአሰራርና የአደረጃጀት ማሻሻያ
ስራዎች፣
 የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በዜጎች ቻርተር ላይ
በተቀመጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዶች መሰረት መሆኑን
የመገምገም፣
 በመንግስት ክንፉ አካላትም ሆነ በህዝብ ክንፉ አካላት ውስጥ በሚታዩ
የኪራይ ሰብሳቢነትና አስተሳሰብና ተግባር የሚታዩ ችግሮች፣
4.2 የለውጥ ሠራዊት ክንፎች ትስስርና …

 የመንግስት ክንፉ በሚያመቻቸው መድረክ በመገኘት ተልዕኮን


በጋራ ለማሳካት የሚደረገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የህዝብ
ክንፉ የራሱን አጀንዳ ቀርጾ ተቋማትን ሱፐርቫይዝ
የማድረግና በሱፐርቪዥኑ ግኝት ላይ ተመስርቶ ከተቋማት
ጋር መወያየትና ቀጣይ አቅጣጫንም ማስቀመጥ
ይጠበቅበታል፣
4.2 የለውጥ ሠራዊት ክንፎች ትስስርና…
4.2.2 የመንግስትና የህዝብ ክንፎች የጋራ የውይይት መድረክ አካሄድ
 አንዳንድ የሕዝብ ክንፍ አካላት ከአንድ በሚበልጡ የመንግሥት
ተቋማት እንደ ሰራዊት ክንፍ በጋራ የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ ይኖራል፣
 ይህ የፕሮግራም መደራረብን ከማስከተሉም በላይ በተሳትፎ
ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ጫና ሊኖረው ይችላል፣
 በመሆኑም የህዝብ ክንፉ ከእሱ የሚጠበቀውን ተልዕኮ በአግባቡ
እንዲወጣ የመድረኮችን ድግግሞሽ የሚቀንስ አሰራር መከተል
አስፈላጊ ይሆናል፣
4.2 የለውጥ ሠራዊት ክንፎች ትስስርና…

4.2.2 የመንግስትና የህዝብ ክንፎች የጋራ የውይይት መድረክ አካሄድ

ለዚህም የሚከተሉትን አማራጮች አንዱን ወይም ሁለቱንም


በጣምራ በመጠቀም ያስፈልጋል፡-
 ዋና ተቋማትና ተጠሪ ተቋማት መድረኮቹን በቅንጅት ማካሄድ፣

 ተመጋጋቢ ተልዕኮ ያላቸው ተቋማት በቅንጅት ማካሄድ፣


5.2. የለውጥ ሠራዊት ግንባታ አቅጣጫዎች
 የለውጥ/የለውጥ ሰራዊት የመገንባት ጉዳይ በዘፈቀደ ሊፈጸም
የሚችል አይደለም፣
 የለውጥ ሰራዊት ሊፈጠር የሚችለው በታቀደና በተደራጀ ተግባራዊ
እንቅስቃሴ ብቻ ነው፡፡
 የለውጥ ሰራዊት ሊፈጠር የሚችለው ሶስቱን (የዝግጅት ምዕራፍ፣
የተግባር ምዕራፍ ና የማጠቃለያ ምዕራፍ) የአመራር ኡደቶች
በተመጋጋቢነት የመፈጸም አቅጣጫን በጥብቅ ዲሲፕሊን በመፈጸም
ብቻ ነው፣

5.2. የለውጥ ሠራዊት ግንባታ አቅጣጫዎች
 ዝግጅት ምዕራፍ….. የለውጥ ሰራዊቱ እንዲገነባ አስፈላጊውን
ቅድመ ዝግጅት የማሟላት የተግባር ምዕራፍ….በቅድመ ዝግጅቱ
መሰረት ወደ ተሟላ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የመሸጋገር፣
 የማጠቃለያ ምዕራፍ…..ተግባራቱን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ
አጠቃሎ ለሚቀጥለው ተግባር በአዲስ መንፈስና ደረጃ የመዘጋጀት
 በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ እነኚህን የአመራር
ኡደቶች በውጤታማነት በመፈጸም የሚረጋገጥ ነው፡፡

/የህዳሴው መድረክና የለውጥ አመራር ጥያቄ፣2003/


5. የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ
አቅጣጫዎች
5. የለውጥ ሰራዊት የግንባታ አቅጣጫዎች

የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ስራዎች ሲፈጸሙ


መከተል የሚያስፈልጉ ዋና ዋና አቅጣጫዎች
ሶስቱን የአመራር ኡደቶች በተመጋጋቢነት የመፈጸም
አቅጣጫን መከተል፣
የለውጥ ሰራዊት ግንባታውን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ
አስተሳሰብን ይበልጥ በሚያጎለብት አግባብ መፈጸም፣
በተደራጀ አግባብ የመንቀሳቀስ አቅጣጫን መከተል፣
5. የለውጥ ሰራዊት የግንባታ አቅጣጫዎች….

የሠራዊቱን የማስፈፀም አቅም በሚገነባ መልኩ የመፈፀም


አቅጣጫን መከተል፣
ሁሉንም የለውጥ መሣሪያዎች አቀናጅቶ የመተግበር
አቅጣጫን መከተል፣
በስራ አፈጻጸም ውጤት ምዘና ላይ ተመስርቶ የማበረታታትና
ተጠያቂ የማድረግ አቅጣጫን መከተል፣
6. የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ክትትልና ድጋፍ ስርዓት
6. የለውጥ ሠራዊት ክትትልና ድጋፍ ስርዓት

 ሁለቱም የለውጥ ሠራዊት ክንፎች ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ


ከገቡ በኋላ፡-
 የሚያጋጥማቸውን እንቅፋት ተከታትሎ ለመለየትና
ለመፍታት የሚያስችሉ ወቅታዊ ድጋፎች መሰጠታቸውን ፣
በተግባር ሂደት የሚገኙ ምርጥ ልምዶችን ተከታትሎ
በመለየትና በመቀመር ለማስፋፋት የሚያስችል ሥራ
በቀጣይነት እየተሠራ መሆኑን ማረጋገጥ ፣
የሠራዊት ግንባታውን እውን ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
6. የለውጥ ሠራዊት ክትትልና ድጋፍ ስርዓት…
ከዚህ አኳያ ሦስት ዋና ዋና የክትትል እና የድጋፍ
መስተጋብሮች ተግባራዊ ይደረጋሉ፣
እነሱም፡-
ግምገማና የግብረ-መልስ አሰራር ተጠናክሮ
እንዲቀጥል ማድረግ፣
የሪፖርትና የግብረ መልስ አሠራርን ማጠናከርና
መተግበር፣
የሱፐርቪዥንና ግብረመልስ አሠራር ማጠናከርና
መተግበር ይሆናል፡፡
6. የለውጥ ሠራዊት ክትትልና ድጋፍ ስርዓት…
6.1.1 የጋራ ግምገማና ግብረመልስ ስርዓት
 መደበኛ የሚኒስትሮች የጋራ መድረክ በየወሩ ይካሄዳል፡፡
ከየተቋማቱ ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት
ሚኒስቴር ተልኮ በተጨመቀው ሪፖርት ላይ በሚኒስትሮች
የጋራ መድረክ ውይይት ተደርጎበት የጋራ አቅጣጫ
ይቀመጣል፡፡
 በየስድስት ወሩ ከሁሉም የፌደራል ተቋማት የበላይ አመራር
ጋር የጋር የግምገማና የምክክር መድረክ ይካሄዳል፡
 በየተቋማቱ በየሁለት ሳምንቱ የማኔጅመንት ግምገማ
በማድረግ በየደረጃው ባለው የለውጥ ሰራዊት ግንባታ
ስራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጎ ግብረመልስ
ይሰጥበታል፣
6. የለውጥ ሠራዊት ክትትልና ድጋፍ ስርዓት…

6.1.1 የጋራ ግምገማ ግብረ-መልስ ሥርዓት


 በየሳምንቱ በየስራ ሂደቱ ግምገማ በማድረግ በስራ ሂደት ደረጃ
በሂደቱ ካሉት ሰራተኞች ጋር በለውጥ ሰራዊት አማካኝነት
እየተፈጸመ ያለው የመንግስት ስራ አፈጻፀም ይፈተሻል፣
 እያንዳንዱ ተቋምና ተጠሪ ተቋሞቻቸው እንደአመቺነቱ በጋራ
ወይም በተናጠል በየወሩ ከመላው ሰራተኛ ጋር የግንኙነት
መድረክ በመፍጠር በተቋሙ የለውጥ ሰራዊት ፣ ግንባታ
አፈጻፀም ሪፖርት ላይ ግምገማና ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ
ይቀመጣል፣
 በየዕለቱ በ1ለ5 የለውጥ ቡድን አደረጃጀት ደረጃ አጠር ያለ
የውሎ ግምገማ ይደረጋል፣
6. የለውጥ ሠራዊት ክትትልና ድጋፍ ስርዓት…

6.1.2 ሪፖርትና ግብረመልስ ሥርዓት


ለተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ውጤታማነት ወሳኝ
የሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ በማተኮር በተዘጋጀው ቼክሊስት
መሠረት ዋና ተቋማት የተጠሪ ተቋሞቻቸውን አፈጻጸም
ያካተተ ወርሃዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ለፐብሊክ ሰርቪስና
የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ይልካሉ፡፡ ግብረመልስም
ተዘጋጅቶ ለተቋማቱ ይላካል፡፡
ተጠሪ ተቋማት ወርሃዊ የቁልፍ ተግባርና የአበይት ተግባራት
አፈጻጸም ሪፖርት በየወሩ ለዋና ተቋሞቻቸው ይልካሉ፤ ዋና
ተቋማትም ሪፖርቱን ገምግመው ለተጠሪ ተቋሞቻቸው
ግብረ-መልስ ይሰጣሉ፡
6. የለውጥ ሠራዊት ክትትልና ድጋፍ ስርዓት…

6.1.3 የሱፐርቪዥንና ግብረመልስ ስርዓት


በሪፖርት ከሚደረገው በተጨማሪ የክትትል፣ የድጋፍና
የግምገማ ስራው በአካል ምልከታ በተደገፍ ሱፐርቪዥን
ጭምር ይካሄዳል፣
ሱፐርቪዥኑ እንደየሁኔታው በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ሆኖ
የህዝብ እና የመንግስት ክንፉን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ
ይፈጸማል፡
የሱፐርቪዥን ግኝቱ በግብረ-መልስነት ለተቋማት
ይላካል፤ተቋማትም ግብረ-መልሱን በግብዓትነት በመጠቀም
የዕቅዳቸው አካል ያደርጉታል፡
6. የለውጥ ሠራዊት ክትትልና ድጋፍ ስርዓት…

6.1.3 የሱፐርቪዥንና ግብረመልስ ስርዓት


 ከሱፐርቪዥኑ የሚገኙ መልካም ልምዶች ተቀምረው
ቀጣይ የሱፐርቪዥን ስራን ለማጎልበት ጥቅም ላይ
እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
 ዋና ተቋማት የተጠሪ ተቋሞቻቸውን የለውጥ ሰራዊት
ግንባታ፣ የሪፎርምና የመልካም አስተዳደር ስራዎች
አፈጻጸም ሱፐርቫይዝ ያደርጋሉ፣ ግብረ-መልስም ይሰጣሉ፣

You might also like