You are on page 1of 13

ማውጫ

1. አጠቃላይ ስለ ዕቅዱ መግለጫ


2. የኢንተርፕራይዙ አደረጃጀትና አስተዳደር መዋቅር
3. የምርት ዓይነት እና ማመልከቻ
4. የገበያ ጥናት እና አጠቃላይ ምርት ዕቅድ
4.1. የገበያ ጥናት ዕቅድ
4.2. አጠቃላይ ምርት እና የምርት ዕቅድ
5. የግብዓት እና የጥሬ ዕቃ ዕቅድ
5.1. የጥሬ ዕቃ ዕቅድ
5.2. መሠረታዊ አገልግሎቶች
6. የግብዓት አዘገጃጀት ሂደት እና የማሽነሪ ዕቅድ
6.1. የግብዓት አዘገጃጀት ሂደት ዕቅድ
6.2. የቋሚ ማሽነሪ ዕቅድ
7. ቀጥተኛ የሰው ሀይል ዕቅድ
7.1. ቀጥተኛ የሰው ሀይል ፍላጐት ማሳያ
7.2. ሌሎች ዓመታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች
8. የኢንተርፕራይዝ የገበያ ዕቅድ
8.1. የኢንተርፕራይዙ የአንድ ዓመት የሽያጭ ዕቅድ
9. የኢንተርፕራይዙ የፋይናንስ ዕቅድ
9.1. የመነሻ ካፒታል ዕቅድ
9.2. የማምረቻ ወጪ
9.3. ዓመታዊ የትርፍ ኪሳራ መግለጫ

1. የኢንተርፕራይዙ አጠቃላይ መረጃ

1
1.1. የኢንተርፕራይዙ ስም አብዱልመጂድ፣ ሰፊነሽ እና ጓደኞቻቸው ያገለገሉ የፕላስቲክ ምርቶች መልሶ
መጠቀም፣

1.2. አድራሻ፡- ክልል አዲስ አበባ ከተማ ልደታ

1.3. የኢንተርፕራይዙ የተሰማራበት የሥራ ዓይነት ያገለገሉ ፕላስቲኮች መልሶ መጠቀም፣

1.4. የበጀት ዕቅድ ዓመት ከሐምሌ 01 እስከ ሰኔ 30 ባለው የሥራ ዘመን

1.5. የኢንተርፕራይዙ ባለቤት/ ባለቤቶች ግላዊ መረጃ

1.5.1. ሥም፡- ሰፊነሽ ጀማል መልካ


የትምህርት ደረጃ፡- 6 ኛ ያጠናቀቀና የሲኦሲ ምዘና የወሰደ፣
1.5.2. ሥም፡- አብዱልመጂድ ጀማል ዑመር
የትምህርት ደረጃ፡- 10 ኛ ያጠናቀቀና የሲኦሲ ምዘና የወሰደ፣
1.5.3. ሥም፡- ፈቲያ አህመዲን ሀሰን
የትምህርት ደረጃ፡- በዲግሪ የተመረቀ
1.5.4. ሥም፡- ረሒም ጀማል ዑመር
የትምህርት ደረጃ፡- 8 ተኛ ክፍል የሲኤሲ ምዘና የወሰዱ
5.5. ሥም፡- አህመዲን ጀማል ዑመር
የትምህርት ደረጃ፡- በዲግሪ የተመረቀ
1.8. ኢንተርፕራይዙ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ/ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት የሚያበረክተው
አስተዋጽኦ

1.8.1. ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት የሚኖረው ጠቀሜታ

 ዘርፍ ለአስራ ዘጠኝ (19) ሠራተኛ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፣


 በዘርፍ የአንቀሳቃሾችን የገቢ ምንጭ በመሆን ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ ይረዳል፣
 የዘርፍ አንቀሳቃሾች ያላቸውን ዕውቀት በጋራ በመጠቀም የኢንተርፕራይዙን ልማት ውጤታማ
ለማድረግ ያስችላል፣

1.8.2. ለሀገር ኢኮኖሚ የሚኖረው አስተዋፅኦ

 የኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ስትራቴጂ ለማፋጠን ይረዳል፣

2
 ዘርፍ ከፍተኛ ግብር ለመክፈል ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል፣
 ከፍተኛ የሥራ ዕድል ይፈጥራል፣
 ዘርፍ ከውጭ የሚመጣውን ፕላስቲክ ለመግዛት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በሀገር ውስጥ እንዲተካ
ያደርጋል፣
 ዘርፍ በየአካባቢው ተጥለው የሚገኙትን ፕላስቲኮችን ጥቅም ላይ በማዋል የባቢ ምንጭ እንዲሆን
ይደረጋል፣
 ዘርፍ በየአካባቢው ከመጠን በላይ እየተስፋፋ ያለው የአካባቢ ብክለት እንዲቀንስ ያደርጋል፣

2. የኢንተርፕራይዙ የአደረጃጀትና አስተዳደር መዋቅር

2.1. የኢንተርፕራይዙ አስተዳደራዊ መዋቅር ግራፍ

ዋና ሥራ አስኪያጅ

ምክትል ሥራ አስኪያጅ

ገንዘብ ያዥ/ኤዲት
ፀሀፊ አባል

3. የግብአት ዓይነትና ማመልከቻ

 ዘርፍ የሚያተኩረው ያገለገሉ የፕላስቲክ ምርቶች መልሶ መጠቀም ላይ ነው፡፡


 ያገለገሉ የፕላስቲክ መልሶ መጠቀም ምርት ለአገልግሎት የሚውለው ብቻውን ወይም ከሌሎች
ግብዓቶችን በአነስተኛ መጠን በማቀንቀል መጠቀም ይቻላል፡፡ ምርቶቹም ቢሆኑ ቀላልና አነስተኛ ዋጋ
ያላቸው በመሆኑ በታዳጊ ሀገራት ተፈላጊነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ከሚመረቱት ምርቶች
መካከል ቀለል ያሉ የቤት ውስጥ ዕቃዎች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል፡- ሳህን፣ የፕላስቲክ ጭልፋ፣
ፕላስቲክ ማንኪያ፣ ዕቃ መያዣ ፌስታሎችና የመሳሰሉትን ተያያዥ ምርቶች ማምረት ይቻላል፡፡

4. የገበያ ጥናት እና አጠቃላይ የምርት ዕቅድ

4.1. የገበያ ጥናት ዕቅድ

3
4.1.1. ከዚህ በፊት ጠቅላላ የነበረ አቅርቦት እና በአሁን ሰዓት የሚፈለገው ጠቅላላ ፍላጐት

- በሀገራችን ውስጥ የተሰማሩ የፕላስቲክ አምራቾች በሙሉ ጥሬ ዕቃ የሚጠቀሙት ሙሉ በሙሉ ከሁሉም


በሚመጣው ብቻ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ከ 2010-2012 ዓ.ም. ብቻ ጠቅላላ ፕላስቲክ አምራቾች ያስገቡት
የምርት መጠን በአማካይ 87235 ቶን የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ መግባቱን መረጃዎች
ያሳያሉ፡፡

ሠንጠረዥ 4.1.1. አጠቃላይ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ምርት ማሳያ በቶን

የምርት ዓይነት/ዓ.ም 2010 2011 2012 Average %Share


Poly ethylane and related 27,006.1 27,006.1 27839.1 27283.8 40.58
Polyviny/Chlorie and
related 9,270.3 13,071.0 16955.7 13099.0 19.48
Ethylene-vinyi acetate &
related 14,836.3 9,251.2 8928.2 11005.2 16.37
Other poly ether 5,484.7 5,647.7 7990.2 6374.2 9.48
Poly (Ethylene tere
phthalate) 3,042.2 2,454.9 2447.8 2648.3 3.94
Poly esters 1,215.0 1,971.3 4081.5 2422.6 3.60
Polymers of hologenated
polymers 935.5 494.14 944.6 790.4 1.18
Alkyd resins 446.1 555.5 1154.5 718.7 1.07
Poly styerene and related
polymers 29.0 1,152.7 349.2 510.3 0.76
Acryclic 1,011.7 156.8 292.6 487.1 0.72
Polymids 167.0 980.4 130.3 425.9 0.63
Epoxide resins 343.2 12.6 887.5 414.4 0.62
Poly carbonates 5.5 0.3 16.7 7.5 0.01
Poly/Methyl Methacryylate 0.6 5.9 10.7 5.8 0.01
Total 64,622 63,911 73,172 67,235 100
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

- በበጀት ዓመት 2010-2012 ዓ.ም. ዓመታዊ ጠቅላላ የፕላስቲክ ዋጋ በሁሉም የአምራቾች ዘርፍ ከ 185.05
ሚሊየን ወደ 1.19 ቢሊየን ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በአማካይ ፐርሰንታይል ሲሰላ 13% ዓመታዊ ዕድገት
አሳይቷል፡፡ በዚህም የተነሳ በዘንድሮ በጀት ዓመት ዘርፍ በአማካይ 15% ዕድገት የሚያሳይ ሲሆን ይህንን
የፕላስቲክ ፍላጐት ከግምት በማስገባት በሀገር ውስጥ ያሉ ያገለገሉ የፕላስቲክ ምርቶች መልስ
በመጠቀም ሀገራችን በውጭ ምንዛሪ የምታጣውን ኪሳራ መቀነስ ይቻላል፡፡

4
4.1.2. የፕላስቲክ ምርት ፍላጐቱ

 የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ጥናት እንደሚያሳየው በመጪው ሁለት እና ሦስት ዓመታት የኢኮኖሚ
እድገቷ በ 15.2% ታድጋለች ተብሎ ይገመታል፡፡
 በዚሁ በተመሳሳይ ዓመት የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዕድገት 20 ጭማሪ እንደሚያሳይ ይገመታል፡፡
በዚሁም የተነሳ ከላይ የተነሱት ምክንያቶች መሠረት በማድረግ ያገለገሉ የፕላስቲክ ግብዓቶች መልስ
መጠቀምም በ 10% እንደሚጨምር ያሳያል፡፡

ሠንጠረዥ ለቀጣይ 5 ዓመታት የሚፈለገው ምርት በቶን ሲገለጽ

ዓ.ም. የሚፈለገው መጠን


2013 26,872
2014 29,559
2015 32,515
2016 35,769
2017 39,343

ምንጭ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን

4.1.3. የጥሬ ዕቃ ዋጋ እና ስርጭት

 በአለም አቀፍ መሠረት አጠቃላይ የፕላስቲክ ምርት ከተመረተበት አገር እስከ ሀገራችን ድረስ
ሁሉንም መመዘኛ ጨርሶ የሚፈጀው በቶን ብር 50,311 /ሃምሣ ሺህ ሦስት መቶ አስራ አንድ ብር/
ደርሷል፡፡
 በዚህም የተነሳ የሚፈለገው ምርት መጠን በቂ ሁኔታ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ይሆናል፡፡

4.2. አጠቃላይ የምርት ዕቅድ

4.2.1. የድርጅቱ የማምረት አቅም

 ዘርፍ በጣም አዋጭና ተፈላጊነት ያለው ስለሆነ


 በሀገራችን የፕላስቲክ ፍላጐት ከፍተኛ ቢሆንም በቂ ጥሬ ዕቃ ማግኘት አለመቻል ዋነኛው ሲሆን
በተጨማሪም የተቀናጀ ያገለገሉ የፕላስቲክ ግብዓቶች አሰባሰብ ባለመኖሩ ትልቅ ተግዳሮት ሆኗል፡፡

5
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ተግዳሮቶች ቢስተካከሉ ኢንተርፕራይዙ በሙሉ አቅሙ በሰዓት የሚያመርተው
62.5 ኪ.ግ ይደርሳል፡፡ ድርጅቱ በሁለት ሽፍት በአመት 300 ቀናት ቢሰራ አጠቃላይ የሚያመርተው ምርት 300
ቶን ይደርሳል፡፡

4.2.2. የምርት ዕቅድ

በመጀመሪያው ዓመት የምርት ዕቅድ 80% ሲሆን በሁለተኛው ዓመት ደግሞ 90% ይደርሳል፡፡ ድርጅቱ በሙሉ
አቅሙ /100%/ የሚያመርተው ከሦስተኛው ዓመት ጀምሮ ይሆናል፡፡

5. የግብዓት እና ጥሬ ዕቃ ዕቅድ

5.1. የጥሬ ዕቃ ዕቅድ

 የዘርፍ ዋነኛው የጥሬ ዕቃ ምንጮቹ /ዓይነቶቹ ያገለገሉ የፕላስቲክ ግብዓቶች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል፡-
ፒፒሲ፣ ጀሪካን፣ የውሀ ማሸጊያ፣ የፕላስቲክ ሸራ፣ የወተት ማሸጊያ፣ ቢፒአር (BPR)፣ የተለያዩ የፕላስቲክ
ቁርጥራጮች ናቸው፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ድርጅቱ በዓመት ጠቅላላ ማምረት የሚችለው 360 ቶን
ሲሆን ያገለገሉ ፕላስቲኮች በኪሎ የሚገዙት በአማካይ 35 ብር አካባቢ በመሆኑ አጠቃላይ በዓመት
ለፕላስቲክ መግዣ የሚያስፈልገው በ 12.6 ሚሊየን ብር አካባቢ ያስፈልጋል፡፡ ሆኖም ግን በተለያዩ ዕቃ
አቅራቢዎች የሚሰራ ስለሆነ እቃዎች የሚገኙት አዛኛውን በሚባል ደረጃ በብድር የሚሰራ ነው፡፡

5.2. መሠረታዊ አገልግሎቶች

 ዘርፍ የተለያዩ መሰረታዊ የሆኑ ግብዓቶች የሚያስፈልጉት ሲሆን ከእነዚህም መካከል ዋነኞቹ ውሀ እና
መብራት ናቸው፡፡ በዋነኛነት ውሀ የሚያስፈልገው ለማሽኑ ማቀዝቀዣነት እና ፕላስቲኮችን
ለማጠቢያነት ጭምር ነው፡፡
 ለማሽኑ አገልግሎት የሚያስፈልገው የመብራት ሀይል 260 kw,11or-220 V አካባቢ የሚያስፈልገው
ሲሆን የኤሌክትሪክ አገልግሎት በበቂ አለማግኘት ዘርፍ በሚያስፈልገው ደረጃ አለማደጉ ዋነኛው
ተግዳሮቱ ነው፡፡

6. የምርት አዘገጃጀት ሂደት እና የማሽነሪ ዕቅድ

6.1. የግብዓት አዘገጃጀት ሂደት ቅጽ

6.1.1. የግብዓት አዘገጃጀት ሂደት

6
 የተሰበሰበው ያገለገሉ የፕላስቲክ ግብዓት ወደ ምርት ከመቀየሩ በፊት የተለያዩ ሂደቶችን ማለፍ
አለበት፡፡ ከእነዚህም ሂደቶችን መካከል መጀመሪያ፡-
 በጥቅል የመጣውን ፕላስቲክ መለየት
 መፍጨት
 ማጠብ
 በሚታጠብ ጊዜ ዕቃው ውስጥ የቀረ ውሀ ማስወጣትና ማድረቅ
 ወደ ማሽኑ ቋት በመጨመር ለምርት ማዘጋጀት፣
 በመጨረሻም ለሚፈለገው ምርት ጥቅም ላይ ማዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- በጥቅል የመጣውን በዓይነት መለየት ማለት በጥቅል የመጣውን ፕላስቲክ በየመደቡ እየለዩ
ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡ ምርቱ ጥራቱ የጠበቀና በሚፈለገው መልኩ ሥራ ላይ ለማዋል በዚህ
መልኩ ማለፍ ዓይነተኛ መፍትሔ ነው፡፡

6.1.2. ለአካባቢውና ለሀገሪቱ የሚሰጠው ጥቅም

 ያገለገሉ የፕላስቲክ ግብዓቶች በቀላሉ የማይበሰብሱ እና በየቦታው እየተጠራቀመ በመጣ ቁጥር


በአካባቢው ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ሆኖም ግን በየቦታው ተጥለው እና
ተጠራቅመው የሚገኙትን ፕላስቲኮች በመሰብሰብ ለአገልግሎቶች ማዋል አካባቢያችን ከማፅዳት
ባለፈ የገቢ ምንጭም ይሆናል፡፡ ስለዚህ ያገለገሉ የፕላስቲክ ግብዓቶች መልሶ መጠቀም ለአካባቢያችን
የሚሰጠው ጥቅም ቢበዛ እንጂ ጉዳት የለውም፡፡

6.2. የቋሚ ማሽነር ዕቅድ

ሰንጠረዥ 6.2 የቋሚ የማሽነሪ ዕቃዎች ዝርዝር

Description (ዝርዝር) Qty. (ብዛት)


Crusher (combined with screw type automatic washing machine) 1
Washink tank 1
Screul type colveyor 1
Automatic dehydrating machine 1
Twin palletizin machine (including main extruder, co-extruder, 1
and cutting device)
Storage hopper and pneumatic automatic pallet conveying 1
device

7
Double stage granulating machine 1

ማሳሰቢያ፡- ከላይ የተዘረዘሩትን ማሽኖች በጠቅላላ የሚፈጀው በብር 1,950,000 /አንድ ሚሊየን ዘጠኝ መቶ
ሃምሣ ሺህ ብር/ ድረስ ገበያ ላይ ይገኛሉ፡፡

6.2.1. የቋሚ ማሽነሪ ዕቃዎች ምንጭና አቅርቦት

 ኢንተርፕራይዛችን ይህንን ማሽን ለመግዛት እንደ ዕቅድ የያዘው በኢትዮጵያ ከውጭ ሀገር የማምረቻ
ማሽኖች በማስመጣት ድርጅቶች ስላሉ ከእነሱ ለመግዛት ወስነናል፡፡

6.2.2. ማምረቻው ለማንቀሳቀስ የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት

 የኢንተርፕራይዙ የመስሪያ/የማምረቻ ቦታ ከመንግሥት ወይም ከሌሎች የመሥሪያ ቦታ አከራዮች


በኪራይ በማግኘት የሚሰራ ይሆናል፡፡
 የማምረቻ አካባቢ ምርጫን በተመለከተ ኢንተርፕራይዙ የተለያዩ ግብዓቶችን ማስቀመጫ ያለው
በማንኛውም የአዲስ አበባ ከተማ ላይ መሆን ይችላል፡፡
 የመሥሪያ ቦታ መጠኑ ቢያንስ ከ 250 ካሬ ሜትር ያላነሰ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ምክንያቱ ያገለገለ
የፕላስቲክ ግብዓቶች መልስ መጠቀም መሥሪያ ማሽኑ ብዙ ቦታ የሚፈጅ በመሆኑና በተጨማሪም
የግብዓት ማስቀመጫ እና የጥሬ ዕቃ ማስቀመጫ በድምሩ ሰፊ ቦታ ስለሚፈልግ በመሆኑ ነው፡፡
በዚህም የተነሳ መሥሪያ ቦታው ለማሽን ማስቀመጫ፣ ለግብዓት ማስቀመጫ፣ ለጥሬ ዕቃ ማስቀመጫ
እና ለቢሮ የሚሆን ስፋት ያለው ቢሆን ይመረጣል፡፡

7. ቀጥተኛ የሰው ኃይል ወጪ ዕቅድ

ሰንጠረዥ 7.1. ቀጥተኛ የሰው ኃይል ፍላጐት ማሳያ

የሚከፈለው ገንዘብ መጠን


ተ.ቁ የሥራ ድርሻ ብዛት
በወር በዓመት
1 ሥራ አስኪያጅ 1 4,000 48,000
2 ፀሀፊ/ኦዲተር 1 2,000 24,000
3 የሽያጭ ባለሙያ 1 2,000 24,000
4 ተቆጣጣሪ 2 4,000 48,000
5 ቴክኒሺያን 2 6,000 72,000
6 የማሽን ኦፕሬሽን 2 6,000 72,000
7 ረዳት ሠራተኛ 8 8,000 96,000

8
8 ጥበቃ 2 24,000 28,000
ድምር 19 412,800
25% ለደመወዛቸው ታሳቢ የሚደረግ 103,200
ጠቅላላ ድምር 516,000

7.2. ሌሎች ዓመታዊ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች

 በአንድ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ቀጥተኛ ያልሆነ የሠራተኛ ወጪ፣ የሽያጭ ወጪ፣
የእርጅና ቅናሽ፣ ወጪና ሌሎች የስራ ማስኬጃ ዓመታዊ አጠቃላይ ወጪ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሰንጠረዥ 7.2 ሌሎች ወጪዎች

የወጪ መጠን
ተ.ቁ. የወጪ ዓይነት ምርመራ
ብር ሣ
1 ቀጥተኛ ያልሆነ የሠራተኛ ወጪ 24,000 00
2 የመሥሪያ ቤት ኪራይ 36,000 00
3 ሌሎች የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች 54,000 00
ጠቅላላ ድምር 1,140,000 00

8. የኢንተርፕራይዙ የገበያ ዕቅድ

8.1. የኢንተርፕራይዙ የአንድ ዓመት የገበያ ዕቅድ

 ኢንተርፕራይዙ ጠቅላላ ዓመታዊ ግዢ 360 ቶን የሚደርስ ሲሆን ይህንንም ምርት ከገበያ በአማካይ
በ 35 ብር እየገዛ ምርቱን ዓምርቶ በአማካይ በ 40 ብር ይሸጣል፡፡ ስለዚህ ኢንተርፕራይዙ ጠቅላላ
ዓመታዊ ሽያጭ በብር ሲተመን 14.4 ሚሊየን ገደማ ይደርሳል፡፡

9. የኢንተርፕራይዙ የፋይናንስ ዕቅድ

9.1. የመነሻ ካፒታል ዕቅድ/ፍላጐት

9
ሰንጠረዥ 9.1 የመነሻ ካፒታል ዕቅድ ማሳያ

የባለቤቱ አንጡራ ሀብት በብድር የሚገኝ


የካፒታል ድምር
ብር ብር
 የኢንቨስትመንት ካፒታል
 የሥራ ቦታን ለማመቻቸት 20,000
 ለቋሚ ዕቃ ግዢ 1,950,000
 የማምረቻ ወጪ
 ቀጥተኛ የሠራተኛ ደመወዝ 43,000
 ጥሬ ዕቃ 150,000 900,000
 ቀጥተኛ ያልሆነ ደመወዝ 2,000
 ቤት ኪራይ 3,000
 መብራትና ውሃ 3,000
 እርጅና ቅናሽ 1,500
ድምር 222,500 2,850,000

መግለጫ፡- (የፋይናንስ ምንጭ)

 በመነሻ ካፒታል ውስጥ የተካተተው የማምረቻ ወጪ ለአንድ ዓመት ከተያዘው ውስጥ የማምረቻ
ወጪ የአንድ ወሩን ብቻ ነው፡፡
 ከአጠቃላይ መነሻ ካፒታል ውስጥ 8% የሚሆነውን በኢንተርፕራይዙ የሚሸፈን ሲሆን ይኸውም
በቁጠባ መልክ የሚቀመጥ ነው፡፡ ቀሪውን 29.5% የሚሆነው ከእቃ አቅራቢዎች በክሬዲት የሚሰራ
ሲሆን የተቀረው 62.5% ብድር የሚገኘው ከአዲስ ካፒታል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ነው፡፡

10
9.2. የማምረቻ ወጪ (Production cost)

ሰንጠረዥ 9.2 የማምረቻ ወጪ ማሳያ

የወጪ መጠን
ተ.ቁ የወጪ ዓይነት ምርመራ
ብር ሣንቲም
1 የጥሬ ዕቃ 12,600,000 00
2 ቀጥተኛ የሠራተኛ ወጪ 516,000 00
3 የሥራ ማስኬጃ 1,140,000 00
ጠቅላላ የማምረቻ ወጪ 0 00

9.3. ዓመታዊ ትርፍና ኪሳራ መግለጫ

9.3.1. የምርት ወቅት የሚሸፈነው ከሐምሌ 01 እስከ ሰኔ 30 ባለው የሥራ ዘመን ይሆናል፡፡

9.3.2. የትርፍና ኪሳራ መግለጫ

አህመድ ካሚላ እና ጓደኞቻቸው ያገለገሉ ፕላስቲኮች መልሶ መጠቀም


ሽያጭ
ከምርት ሽያጭ የተገኘ ገቢ 1,440,000
ቀጥተኛ የጥሬ ዕቃ ወጪ 12,600,000
ሲቀነስ
ቀጥተኛ የሰው ኃይል ወጪ 516,000 13116000
አጠቃላይ ትርፍ 1284000
ሲቀነስ ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪ 1140000
ያልተጣራ ትርፍ 1170000
ሲቀነስ የወለድ ተከፋይ 4875
ከግብር በፊት የተገኘ ትርፍ 1165125
ሲቀነስ የትርፍ ግብር 349537.50
የተጣራ ትርፍ 815587.50

11
9.4. የትርፍ እና ኪሳራ ነጥብ (BREAK-EVEN POINT)

9.4.1. የትርፍ እና ኪሳራ ነጥብ ሽያጭ

የትርፍና ኪሳራ ነጥብ ሽያጭ (BEP): ዓመታዊ ሽያጭ x ዓመታዊ ቋሚ ወጪ

ዓመታዊ ሽያጭ -- ዓመታዊ ቋሚ ያልሆኑ ወጪዎች

= 14,400,000 x 1,950,000
14,400,000 13,230000
= 24,000,000 pcs/1000 kg = 24000 kg

9.4.2. የትርፍና ኪሳራ ነጥብ ምርት (BEP)

የትርፍና ኪሳራ ነጥብ ምርት (BEP)፡- የትርፍና ኪሳራ ነጥብ ዓመታዊ ሽያጭ
አማካይ የመሸጫ ዋጋ
= 24,000 kg = 600 ምርት
40

ሐ. የኢንቨስትመንት ተመላሽ (Return on investment)


የኢንቨስትመንት ተመላሽ (Return on investment)= ዓመታዊ የተጣራ ትርፍ %100
ጠቅላላ የመነሻ ካፒታል ፍላጐት

= 1176787.5
%100
3072500
= 38.5%

12
መግለጫ፡-
 በፊደል ተራ ‹‹ሀ›› ላይ እንደሚያሳየው ይህ ኢንተርፕራይዝ ዓይነት ትርፍም ሆነ ኪሳራ ሳይገጥምው
ለመቆየት በዓመት ቢያንስ ብር 24,000,000 /ሃያ አራት ሚሊየን ብር/ የሚያወጣ ሽያጭ ማከናወን
ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ በላይ ከሸጠ አትራፊነቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን ከዚህ በታች ቢሸጥ ግን ኪሳራ
ውስጥ እንደሚገባ ያመላክታል፡፡
 በፊደል ተራ ‹‹ለ›› ላይ እንደሚያሳየው የትርፍና ኪሳራ ነጥብ ምርት የሚለውን ስንመለከት
ኢንተርፕራይዙ ያለ ትርፍና ኪሳራ ለመቆየት ቢያንስ አማካይ መጠን ያለውና በአማካይ የአንዱ ኪሎ
ዋጋ ብር 40 /አርባ ብር/ የሆነ 600 ምርቶችን በዓመት ማምረት እንደሚጠበቅበት የሚያመለክት
ሲሆን፣ ከዚህ መጠን በላይ ቢያመርት አትራፊነቱን ሲያረጋግጥ ከዚህ መጠን በታች ቢያመርት ኪሳራ
ውስጥ እንደሚገባ ያመለክታል፡፡
 በፊደል ተራ ‹‹ሐ›› የሚያመለክተው ኢንተርፕራይዙ ከላይ በተጠቀሰው የምርትና የሽያጭ መጠን
ቢጓዝ በዓመት ውስጥ የጠቅላላ ኢንቨስትመንት ወጪውን 38.5 በመቶ መመለስ እንደሚችል
የሚያሳይ ሲሆን አጠቃላይ የኢንቨስትመንት ወጪውን ሦስት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መመለስ
እንደሚችል ያመለክታል፡፡

13

You might also like