You are on page 1of 73

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ.

የግብርና ሚኒስቴር
የቅባት ሰብሎች አመራረት እና አያያዝ
ቴክኖሎጂ ፓኬጅ

ግብርና ሚኒስቴር

ታህሳስ 2007

0
ማማማ
አጠቃላይ መግቢያ ..................................................................................................... 8
የፓኬጁ አላማ ........................................................................................................... 9
የፓኬጁ ግብ .............................................................................................................. 9
የፓኬጁ አስፈላጊነት .................................................................................................. 9
ሰሊጥ (Sesame: Sesamum indicum L.) ........................................................ 10
1. መግቢያ ............................................................................................................ 10
2. የሰሊጥ ፓኬጅ አስፈላጊነት ............................................................................... 11
3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ─ምህዳር ........................................................................ 11
4. የተሻሻሉ ዝርያዎች ............................................................................................ 12
5. የአመራረት ዘዴዎች .......................................................................................... 14
5.1 ማሳ መረጣ .................................................................................................. 14
5.2 የማሳ ዝግጅት ........................................................................................... 14
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ .................................................................... 14
5.3.1 የዘር ወቅት ........................................................................................... 14
5.3.2 የአዘራር ዘዴ ........................................................................................ 15
5.3.3 የዘር መጠን .......................................................................................... 15
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ .................................................................. 16
5.5 አረም ቁጥጥር ............................................................................................. 16
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር ............................................................... 17
5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር ......................................................................... 17
5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር .................................................................................... 17
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ ................................................... 18
5.7.1 አጨዳ ................................................................................................... 18
5.7.2 ማድረቅ ................................................................................................. 18
5.7.3 ማራገፍ እና ማበጠር ........................................................................... 18
5.7.4 ማጓጓዝና ክምችት ................................................................................ 19
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት........................................................................... 19
5.9 ዘመናዊ የሰሊጥ የእርሻ መሳሪያ ................................................................. 20
5.10 የምርት አዋጭነት ..................................................................................... 20

1
ኑግ (Niger seed: Guizotia abyssinica L.)..................................................... 21
1. መግቢያ ............................................................................................................ 21
2. የኑግ ፓኬጅ አስፈላጊነት ................................................................................ 22
3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር .......................................................................... 22
4. የተሻሻሉ ዝርያዎች ......................................................................................... 22
5. የአመራረት ዘዴዎች........................................................................................ 23
5.1 ማሳ መረጣ .................................................................................................. 23
5.2 የማሳ ዝግጅት .............................................................................................. 23
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ ................................................................. 23
5.3.1 የዘር ወቅት ........................................................................................... 23
5.3.2 የአዘራር ዘዴ ........................................................................................ 23
5.3.3 የዘር መጠን .......................................................................................... 24
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ .................................................................. 24
5.5 አረም ቁጥጥር ............................................................................................. 24
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር ............................................................... 25
5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር ......................................................................... 25
5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር .................................................................................... 25
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ ................................................... 26
5.7.1 አጨዳ ................................................................................................... 26
5.7.2 ማድረቅ ................................................................................................. 26
5.7.3 ውቂያ .................................................................................................... 26
5.7.4 ማጓጓዝ እና ክምችት.......................................................................... 27
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት........................................................................... 27
5.9 የምርት አዋጭነት ................................................................................... 27

2
ተልባ / Linum usitatissimum L / ..................................................................... 28
1.መግቢያ ................................................................................................................ 28
2.ፓኬጁ አስፈላጊነት ............................................................................................... 29
3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ ምህዳር .......................................................................... 29
4. የተሻሻሉ ዝርያዎች ........................................................................................ 29
5. የአመራረት ዘዴዎች........................................................................................ 31
5.1 ማሳ መረጣ .................................................................................................. 31
5.2 የማሳ ዝግጅት .............................................................................................. 31
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ ................................................................ 31
5.3.1 የዘር ወቅት ........................................................................................... 31
5.3.2 የአዘራር ዘዴ ........................................................................................ 31
5.3.3 የየየ የየየ ............................................................................................ 31
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ .................................................................. 32
5.5 አረም ቁጥጥር ............................................................................................. 32
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር ............................................................... 33
5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር ......................................................................... 33
5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር .................................................................................... 33
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ ................................................... 35
5.7.1 አጨዳ ................................................................................................... 35
5.7.2 ማድረቅ ................................................................................................. 35
5.7.3 ውቂያ .................................................................................................... 35
5.7.4 ማጓጓዝና ክምችት ................................................................................ 36
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት........................................................................... 36
5.9 የምርት አዋጭነት ................................................................................... 36

3
ጎመንዘር .................................................................................................................. 37
1. መግቢያ ............................................................................................................ 37
2. የፓኬጁ አስፈላጊነት ........................................................................................ 38
3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር .......................................................................... 38
4. የተሻሻሉ ዝርያዎች ......................................................................................... 38
5.የአመራረት ዘዴዎች ............................................................................................ 39
5.1ማሳ መረጣ .................................................................................................... 39
5.2 የማሳ ዝግጅት .............................................................................................. 39
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ .................................................................... 40
5.3.1 የዘር ወቅት ........................................................................................... 40
5.3.2 የአዘራር ዘዴ ........................................................................................ 40
5.3.3 የዘር መጠን .......................................................................................... 40
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ .................................................................. 40
5.5 የአረም ቁጥጥር ........................................................................................... 41
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር ............................................................... 41
5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር ......................................................................... 41
5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር .................................................................................... 42
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ ................................................... 44
5.7.1 አጨዳ ....................................................................................................... 44
5.7.2 ማድረቅ ..................................................................................................... 44
5.7.3 ውቂያ .................................................................................................... 44
5.7.4 ማጓጓዝ እና ክምችት.......................................................................... 44
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት......................................................................... 45
5.9 የምርት አዋጭነት ....................................................................................... 45

4
ለውዝ ....................................................................................................................... 46
1. መግቢያ ............................................................................................................ 46
2. የፓኬጁ አስፈላጊነት ........................................................................................ 47
3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር .......................................................................... 47
4. የተሻሻሉ ዝርያዎች ......................................................................................... 47
5. የአመራረት ዘዴዎች........................................................................................ 48
5.1 የማሳ መረጣ .............................................................................................. 48
5.2 የማሳ ዝግጅት .............................................................................................. 49
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ .................................................................... 49
5.3.1 የዘር ወቅት ........................................................................................... 49
5.3.2 የአዘራር ዘዴ ........................................................................................ 49
5.3.3 የዘር መጠን .......................................................................................... 50
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ .................................................................. 50
5.5 አረም ቁጥጥር ............................................................................................. 50
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር ............................................................... 51
5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር ......................................................................... 51
5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር .................................................................................... 53
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ ................................................ 55
5.7.1 አጨዳ / ነቀላ ....................................................................................... 55
5.7.2 መሰብሰብ እና ማድረቅ......................................................................... 55
5.7.3 መፈልፈል..................................................................................................... 55
5.3.2 ማጓጓዝ እና ክምችት ................................................................................ 55
5.4 የሰብሉ አመራረት ስርዓት ........................................................................... 56
5.8 የምርት አዋጭነት ........................................................................................ 56

5
የፈረንጅ ሱፍ (Heliantus annuus L.) ................................................................ 57
. 1. መግቢያ ........................................................................................................... 57
4. የፓኬጁ አስፈላጊነት ........................................................................................ 58
5. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር .......................................................................... 58
6. የተሻሻሉ ዝርያዎች ......................................................................................... 58
7. የአመራረት ዘዴዎች........................................................................................ 60
5.1 ማሳ መረጣ .................................................................................................. 60
5.2 የማሳ ዝግጅት .............................................................................................. 60
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ .................................................................... 60
5.3.1 የዘር ወቅት ........................................................................................... 60
5.3.2 የአዘራር ዘዴ ........................................................................................ 60
5.3.3 የዘር መጠን .......................................................................................... 61
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ ................................................................ 61
5.5 አረም ቁጥጥር ............................................................................................. 61
 ማሳን ማፈራረቅ .............................................................................................. 61
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር ............................................................... 62
5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር ......................................................................... 62
 የጓይ ትሉን ለመከላክል፡─ .............................................................................. 62
5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር .................................................................................... 62
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ ................................................... 63
5.7.1 አጨዳ ................................................................................................... 63
5.6.2 ማድረቅ ................................................................................................. 63
5.6.3 ውቂያ/መፈልፈል .................................................................................. 63
5.6.4 ክምችት እና ማጓጓዝ............................................................................ 63
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት........................................................................... 63
5.9 የምርት አዋጭነት ................................................................................... 64

6
የአበሻ ሱፍ (Safflower: Carthamus tinctorius L.) ........................................ 65

1. መግቢያ ............................................................................................................ 65
2. የፓኬጁ አስፈላጊነት ........................................................................................ 66
3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር .......................................................................... 66
4. የተሻሻሉ ዝርያዎች ......................................................................................... 66
5. የአመራረት ዘዴዎች........................................................................................ 67
5.1 ማሳ መረጣ .................................................................................................. 67
5.2 የማሳ ዝግጅት .............................................................................................. 67
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ .................................................................... 67
5.3.1 የዘር ወቅት ........................................................................................... 67
5.3.2 የአዘራር ዘዴ ........................................................................................ 68
5.3.3 የዘር መጠን .......................................................................................... 68
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ .................................................................. 68
5.5 አረም ቁጥጥር ............................................................................................. 68
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር ............................................................... 69
5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር ......................................................................... 69
5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር .................................................................................... 69
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ ................................................... 70
5.7.1 አጨዳ ................................................................................................... 70
5.7.2 ማድረቅ ................................................................................................. 70
5.7.3 ውቂያ የየ የየየየ .............................................................................. 70
5.7.4 ማጓጓዝ እና ክምችት.......................................................................... 70
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት........................................................................... 71
5.9 የምርት አዋጭነት .................................................................................... 71

7
አጠቃላይ መግቢያ

ኢትዮጵያ ለብዙዎቹ የቅባት ሰብሎች ተስማሚ ስነ-ምህዳር እንዳላት መረጃዎች


የሚጠቁሙ ሲሆን በዋናነት ሰሊጥ ፣ ኑግ እና ተልባ እንደዚሁም ለውዝ፣
ጎመንዘር፣ የአበሻ እና የፈረንጅ ሱፍ በቀጣይነት በሀገሪቱ በመመረት ላይ
የሚገኙ ናቸው። የ2005/06 የምርት ዘመን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ
መረጃ እንዳመላከተው በአገራችን የቅባት ሰብሎች የሸፈኑት ማሳ መጠን
816,125 ሄ/ር ሲሆን ከዚህም የተገኘው አጠቃላይ ምርት 7112592 ይህም
መሬት ከጠቅላላው የአዝርዕት ማሳ መካከል 6.58 በመቶ ድርሻን መያዙን
መረጃው ያመለክታል፡፡

ይሁን እንጂ እስከቅርብ ጊዜ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት በሄክታር


እየተገኘ ያለው ምርታማነት ሲታይ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ያመላክታል፡፡
እነዚህ በሀገሪቱ እምቅ አቅም ያላቸው ዋና ዋና የቅባት ሰብሎችን የፓኬጅ
አሰራር ዘዴን ተግባራዊ በማድረግ ከሄክታር የሚገኘውን ምርትና ምርታማነት
በመጨመር ለአለም ገበያ በሰፊው በማቅረብ በገበያ ተወዳዳሪ በመሆን በሀገር
ኢኮኖሚ ላይ ከቅባት ሰብል ተገቢውን አዎንታዊ ተፅእኖ ማስመዝገብ መቻል እና
በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የምግብ ዘይት
ፍላጎት ምላሽ መስጠት አስፈላጊና ወቅታዊ ጉዳይ ነው።

የቅባት ሰብሎች በሀገራችን በርካታ ጥቅሞችን የሚሰጡ ሲሆኑ ከነዚህም መካከል


ለምግብነት፣ ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት፣ ለቀለም ስራ ለቫርኒሽና ለሳሙና እና
ለመሳሰሉት ጥቅም ላይ ይውላል። በሰብል ፈረቃነትም በመጠቀም የመሬት
ለምነትን ማሻሻሽ የሚቻል ሲሆን ተረፈ ምርታቸውም ለእንስሳት መኖነት
ከፍተኛ ጠቀሜታ እየሰጠ ይገኛል።

8
የፓኬጁ አላማ

 የቅባት ሰብሎች ምርት በጥራትና በመጠን በማምረት ከዘርፉ


የሚጠበቀውን ሀገራዊ ጠቀሜታ ማግኘት።

የፓኬጁ ግብ

 የቅባት ሰብሎች ዘመናዊ አመራረት እና ድህረ- ምርት አያያዝ


ቴክኖሎጅን ፓኬጅ ጥንቅሮችን ለተጠቃሚ ማድረስ፣
 ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ፍጆታ ጥራቱን የጠበቀ በቂ ምርት ማቅረብ፣
 በአለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ምርት ማቅረብ እና የገበያ ተፎካካሪ መሆን፣
 የቅባት ሰብሎች ለዘለቄታዊ የግብርና ልማት ያላቸውን ሚና ማሳደግ፣

የፓኬጁ አስፈላጊነት

ቀደም ሲል በስራ ላይ የነበረውን የቅባት ሰብሎች ፓኬጅ ውስንነቶች


በመለትና በመቅረፍ ለተለያዩ አግሮ-ኢኮሎጅዎች ተስማሚ የሆኑ
የተሻሻሉ የአሰራር ዘዴዎችንና ቴክኖሎጅዎችን በፓኬጁ አካትቶ
በማዘጋጀት አሁን የሚገኘውን የቅባት ሰብሎችን ዝቅተኛ ምርትና
ምርታማነት በማሻሻል ከቅባት ሰብሎች የሚጠበቀውን ከፍተኛ ሀገራዊ
ጠቀሜታ ማግኘት ።

9
ሰሊጥ (Sesame: Sesamum indicum L.)

1. መግቢያ

ሰሊጥ በሞቃታማ አካባቢ የሚበቅል የቅባት ሰብል ሲሆን ከሚሰጠዉ የዘይት


መጠን አንፃር የቅባት ሰብሎች ንጉስ በመባልም ይታወቃል፡፡ ሰሊጥ በአለም
ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ ተፈላጊ ከሆኑት የቅባት ሰብሎች መካከል አንዱ ነው፡፡
በዓለም ከፍተኛ አምራች ሀገራት መካከል ማይማር፣ቻይና፣ህንድ፣ኢትዮጵያ
ተጠቃሽ ሲሆኑ ከአፍሪካ ሀገራችን በአንደኛ ደረጃ ትገኛለች፡፡ አገራችን
ኢትዮጵያ ከቡና ቀጥሎ ከሰሊጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ሰብል
ከመሆኑም ባሻገር አጠቃላይ ምርቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሰብል
ሆኗል፡፡

በ 2006 ዓ/ም በወጣው የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከሰሊጥ 617.2 ሚልየን


የአሜሪካ ዶላር ተገኝቷል፡፡ሰሊጥ በአነስተኛ አርሶ አደር 299,724 ሄ/ር የማሳ
በመሸፈን 36.73 % የቅባት ሰብሎችን ሽፋን የያዘ ሲሆን በምርት ደረጃ
2,202,160 ኩ/ል ከጠቅላላው የቅባት ሰብሎች (31%) ድርሻ እንዳለው እና
ምርታማነቱም 7.35 ኩ/ል በሄ/ር መሆኑን መረጃው ያመለክታል /CSA
2013/14 /

ምንም እንኳ ሰሊጥ ለአገሪቷ ኢኮኖሚ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ቢሆንም


ሰብሉ ከአመራረት እና ድህረምርት አያያዝ ችግሮች ምክንያት የሚጠበቀውን
ከፍተኛ ምርት ማግኘት አልተቻለም፡፡ ስለሆም የሰብሉን የምርታማነት አቅም
ለማሳደግና የተሻለ ምርት ለማግኘት እንዲያስችል የተሻሻሉ ዝርያዎች እና
የአመራረት ስልት በማቀናጀት ምርትና ምርታማነቱን ማሻሻል ይቻላል፡፡

10
2. የሰሊጥ ፓኬጅ አስፈላጊነት
ሰሊጥ አምራቹ በቂ ግንዛቤ እንዲይዝ ሰብሉ የሚያስፈልገውን የጥራት ደረጃ
ተጠብቆ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን የምርታማነት እና የጥራት
ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚያስችል የአመራረት ቴክኖሎጅ ፓኬጅ በማስፈለጉ
ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚ ቀርቧል።

3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ─ምህዳር


 ከፍታ ፡- ከባህር ጠለል በላይ ከ 500-1500 ሜትር
 ተስማሚ የአየር ሙቀት ፡- ከ 25 ዲ/ሴ/ግ እስከ 37 ዲ/ሴ/ግ
ለተፋጠነ ብቅለት ፣ ለመጀመሪያ እድገት እና ለአበባ ማበብ የአየር
ሙቀት ያስፈልገዋል፡፡
 ሰሊጥ ሲዘራ የአፈር ሙቀት ከ 21 ዲ/ሴ/ግ በታች መዉረድ
የለበትም ከዚህ በታች በሚሆንበት ግዜ ላይበቅል ይችላል፡፡

 የዝናብ እና የመስኖ ውሃ መጠን

o ከ 500-800 ሚ.ሜ በእድገት ዘመኑ ተስማሚ ሲሆን


፡ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ከ500-650 ሚሜ ዝናብ
o ሰሊጥ በመስኖ በሚመረትባቸዉ አከባቢዎች ሰብሉ
እንደተዘራ ለመጀመርያ ጊዜ የሚሰጠዉ የዉሃዉ ጥልቀት
መጠን 150 ሚ.ሜ ሁኖ ከሁለተኛዉ ዙር ጀምሮ በየሁለት
ወይም ሶስት ሳምንት ጊዜ ዉስጥ እንደአከባቢዉ የአየር
ሁኔታ እይታ ከ 75-100ሚ.ሜ ዉሃ በማጠጣት የተሻለ
ምርት ማግኘት ይቻላል፡፡
o ሰሊጥ በሰፋፊ እርሻዎች ሲመረት በስፕሪንክለር መስኖ
ማምረት ያቻላል፡፡
o በተጨማሪም የዝናብ እጥረት ሲያጋጥም በመስኖ አግዞ
አስፈላጊዉን ምርት ሊሰጥ ይችላል፡፡

11
 ተስማሚ አፈር
 አሸዋ ቀመስ ለም አፈር እና ዉሃ በቀላሉ የሚያሰርግ ጥቁር
አፈር፣
 የአፈር ጣዕም / ፒ.ኤች/ 6.0─ 8.0 የሆነ አፈር ለምርታማነቱ
ተስማሚ ነዉ፡፡

4. የተሻሻሉ ዝርያዎች

በአገራችን በተደረገው የሰሊጥ ምርምር ሥራ 20 ዝርያዎች ለተለያዩ ስነ


ምህዳር የተለቀቁ ሲሆን የዝርየዎቹ ምርታማነትና ባህሪያት በሰንጠረዥ 1.
ተጠቅሰዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አባሴና፣ዲቾ፣እና ኦብሳ የተባሉት ባክቴሪያል
ብላይት ወይም ምች የተባለውን በሽታ የመቋቋም ባህሪ ያላቸው ሲሆን
የዝናብ ስርጭቱ የተሻለ በሆነበት አካባቢ የተሻለ ምርት ይሰጣሉ።
በመካከለኛዉ አዋሽ የሚስማሙ ዝርያዎች ቀላፎ፣መሃዶ፣አርገነ እና ሰርካሞ
ሲሆኑ ሊዳን እና ባርሳን በሶማሊ በመስኖ የሚለሙ ዝርያዎች ናቸዉ፡፡
ሰቲት 1 እና ሁመራ 1 ዝናብ አጠር ለሆኑት አካባቢዎች ተስማሚ ዝርያዎች
ናቸው፡፡ እነዚህ ዝርያዎች በምርምር ማዕከል ከ11─12 ኩ.ል/ሄ/ር ፣ በሞዴል
አርሶ አደር ማሳ ከ 8-9 ኩ/ል/ሄ/ር እነዲሁም በመስኖ ሲለሙ እስከ 24
ኩ/ል/በሄ/ር ምርት ይሰጣሉ፡፡ በዓለም ገበያ በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈለገዉ
የሰሊጥ አይነት ነጭ ቀለም ያለዉ ሆኖ የ1000 ዘር ክብደት ከ3-3.5 ግራም
ሲሆን ቡናማ መልክ ያለውም የዘይት ይዘቱ ከፍተኛ በመሆኑ ለዘይት
መጭመቂያ እንዲውል ይመከራል።

12
ሠንጠረዥ1 በምርምር የተለቀቁ የሰሊጥ ዝርያዎች ዓይነትና ባሕሪያቸው፣

ተ.ቁ የዝርያ ስም የተለቀቀበ የዘይት የመድረሻ ቀን የዘር ምርታማነት ኩ.ል/ሄር


ት መጠን ቀለም በዝናብ በመስኖ
ዓመት/ / %/
እ.ኤ.አ/
1 ቲ-85 1976 43-48 100-115 ነጭ 5-7 9-20
2 ኢ 1978 45-48 110-120 ግራጫ 4-12 12-16
3 ኤስ 1978 43-47 110-120 ግራጫ 4-12 12-16
4 ቀላፎ 1976 44-47 110-120 ጥቁር 3-6 10-20
ቡናማ
5 መሐዶ-80 1989 45-46 110-120 ነጭ 4-8 16-20
6 አባሴና 1990 43-48 110-120 ግራጫ 5-12 12-19
7 አዲ 1993 42-48 85-95 ነጭ - 16-22
8 አርገኔ 1993 43-46 95-105 ግራጫ - 15-18
9 ሰርካሞ 1993 44-48 95-105 ነጭ - 15-18
10 ታቴ 1989 48 110-120 ግራጫ 7-9 7-10
11 አሀዱ 2007 49-51 105-115 ቡናማ 7-8 -
12 ቦርኪና 2007 47-48 105-120 ቡናማ 6-8 -
13 ዲቾ 2010 50-52 120-140 ነጭ 8-20 -
14 ኦብሳ 2010 52-54 130-150 ደብዛዛ 8-10 -
ነጭ
15 ሊዳን 2010 45-46 80-90 ቡናማ - 7-8
16 ባርሳን 2010 46-47 80-90 ቡናማ - 7-8
17 ሰቲት-1 2011 54 80-90 ነጭ 7-10 20-24
18 ሁመራ-1 2011 52 90-100 ነጭ 8-10 -

19 ጫልሳ 2013 ─ 95-120 ደብዛዛ 10.5- -


ነጭ 14.8
20 ኤሲሲ 00047 2013 50.4 105-120 ነጭ 7-8 -

13
5. የአመራረት ዘዴዎች

5.1 ማሳ መረጣ
 ውሃ የማይተኛበት፣ በጣም ተዳፋታማ ያልሆነ ከአረም የፀዳ
እና በጣም ኮትቻ ያልሆነ ማሳ ያስፈልገዋል፡፡

5.2 የማሳ ዝግጅት

 የሰሊጥ ሰብል በተደጋጋሚ ታርሶ የለሰለሰ ማሳ ይፈልጋል፡፡


 የመጀመርያ የእርሻ ወቅት ሰብል እንደተሰበሰበ ፣
 ሁለተኛው እርሻ ማሳ ማለስለስ ዝናብ እንደዘነበ፣
 ሶስተኛው እርሻ በዘር ወቅት ማከናወን ይገባል፡፡
 ትላልቅ ጓሎችም መከስከስ ይኖርባቸዋል፡፡
 በየ 3 ዓመቱ አንድ ጊዜ ሰብሉ እንደተሰበሰበ ጠለቅ ያለ
/ከ20-30 ሳ.ሜ./ እርሻ ማረስ ያስፈልጋል

5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ

5.3.1 የዘር ወቅት

በዝናብ ለሚያመርቱ
 እነደ ዝናብ አጀማመር እና የአፈሩ እርጥበት መጠን ከሰኔ አጋማሽ

እስከ ሀምሌ አጋማሽ


በመስኖ ለሚያመርቱ
 በመካከለኛ አዋሽ አካባቢ ከሰኔ አጋማሽ እሰከ ሰኔ መጨረሻ
መዘራት አለበት
 በጎዴና አካባቢዉ በህዳር እና በታህሳስ ወር ይዘራል፡፡

14
5.3.2 የአዘራር ዘዴ

 የተሻለ ምርት ለማግኘት ሰሊጥ በመስመር መዘራት አለበት፡፡


 በመስመር አዘራር በመስመሮች መካከል 40 ሳ.ሜ ርቀት እና
በዘር መካከል 10 ሳሜ ርቀት በመዝራት ወዲያውኑ በስስ አፈር
ማልበስ ያስፈልጋል።
 የዘር መዝሪያ መሳሪያ በሌለበት ወቅት በተክሉ መካከል
ያለውን ርቀት መጠበቅ አዳጋች ስለሚሆን አንድ እጅ ዘር
ከ 3 እጅ የማሳ ላይ አፈር ጋር በመቀላቀል በመስመር
መዝራት ያስፈልጋል፡፡
 የዘር ትልቀት፤ ከ 3-5ሳ.ሜ መሆን አለበት፡፡
 ሰሊጥ በሰፋፊ እርሻዎች በትራክትር የሚጎተት የመስመር
መዝሪያ/ ፐርሲሽን ረዉ ፕላንተር/ መጠቀም ይቻላል

5.3.3 የዘር መጠን

 ከ 1 እስከ 2 ኪሎ ግራም በሄክታር መጠቀም፤ ሆኖም


ከላይ በተጠቀሰው የተከላ ርቀት መሰረት ጥራት ያለው ዘር 1
ኪሎ ግራም በቂ ሲሆን ከዛ በላይ ለሚጠቀሙ የማሳሳት ስራ
ማካሄዱ ይመከራል።

 ማሳሳት የሚያስፈልግ ከሆነ መከናወን ያለበት የሰብሉ


እድገት ደረጃ ከ2-3 ቅጠል በሚሆንበት ወቅት ነው፡፡

15
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ

 100 ኪ/ግ ዳፕና 50 ኪ/ግ ዩሪያ ማዳበሪያ በሄ/ር


 አጠቃቀሙም 100 ኪ/ግ ዳፕና 25 ኪ/ግ ዩሪያ በዘር ወቅት
መጠቀም እና የቀረዉን 25 ኪ/ግ ዩሪያ በአበባ ወቅት
መጀመሪያ በመጨመር መጠቀም አለብን፡፡
 ሰሊጥ በደረቅ/እርጥበት በሌለበት/ የሚዘራ ከሆነ ግን
የመጀመርያዉ ዩርያ መደረግ ያለበት በመጀመርያ የአረም
ወቅት ነዉ፡፡ ይህ ሰደረግም አረምን በተገቢዉ ሁኔታ
ማስወገድ/ማረም ይኖርበታል፡፡
 ማደበሪያ አጠቃቀም ለዘር በሚወጣው ትልም ጥልቀት /7─10
ሴ.ሜ/ የሚቀመጥ ሲሆን ዘሩ ከማዳበሪያው ጋር ንክክኪ
ሊኖረው አይገባም፡፡

5.5 አረም ቁጥጥር

 ማሳን በደንብ አለስልሶ በማረስ መዝራት፤

 ሰብሉን ማፈራረቅ፤ / ሰሊጥ ─ ማሽላ ─ ማሾ/አኩሪ አተር─


ሰሊጥ/

 ንፁህ ዘር መዝራት፤

 በእጅ ማረም፤

o 1ኛ አረም ከበቀለ ከ 7-14 ቀናት በኋላ፤

o 2ኛ አረም ከበቀለ ከ 28-35 ቀናት ፤

o 3ኛውና የመጨረሻው አረም ከ56-65 ቀናት ቀሪ አረሞችን


በጥንቃቄ የማፅዳት ስራ ይከናወናል፤

16
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር

5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር

የአድሪ ትል እና የጋልሜጅ
 የማሳ ክትትል በየሳምንቱ ማድረግ
 በተባዩ የተጠቁ አምስት እና ከዛ በላይ ቅጠሎች ሲታዩ እና
በውስጡ ነጣ ያለ ሆኖ ጭንቅላቱ ጥቁር /አድሪ ትል/ ወይም ነጣ
ያለ ቢጫ ትል (ጋልሜጅ) መኖሩ ሲረጋገጥ ማላታዮን 50% ኢሲ፣
ዲያዚኖን 60% እና ዲያሜቶኤት 48% ኢሲ 2 ሊትር ኬሚካል
በሁለት መቶ ሊትር ውሃ በጥብጦ ለአንድ ሄ/ር መርጨት
 ተባዩ ወደ መጋዘን እንዳይገባ በመስክ ላይ አስፈላጊውን ክትትል
እና ቁጥጥር ማድረግ
 መጣጭ ተባይ

 የሂላ የማከማቻ ስፍራን እና አካባቢውን ማፅዳት


 በበጋ ወቅት ለተባዩ መቆያ የሆኑ አማራጭ አረሞችን ማስወገድ
 የመጋዘን ንጽህናን መጠበቅ
 ፈጥኖ በመውቃት ወደ መጋዝን ማስገባት
 በመጋዝን አካባቢማላታዮን 50% EC ዳይሜቶኢት 48% EC 2
ሊትር በሁለት መቶ ሊትር ውሃ በሄ/ር በጥብጦ መርጨት፣

5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር

 የሰሊጥ ዋግ /ባክቴሪያል ብላይት


 ከመሬት የተነሳው የውሃ ትነት በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ወበቅ
ሲፈጥር የሚከሰት በሽታ ሲሆን መከላከያውም፣
 በበሽታው የማይጠቁ ዝርያዎችን እና ንጹህ ዘር መጠቀም
 ውሃ ማንጣፈፍ
 ተገቢው የተክል ቁጥር በማሳ እንዲኖር በማድረግ

17
 እርሻን በጥልቀት በማረስ የሰብል ቅሪትን መቅበት
 ሰብል ማፈራረቅ

 ፋይሎዲ/አጀንጉል /
 ይህ በሽታ ፈይቶፕላዝማ በሚባል ተዋህስ የሚመጣ ሲሆን ጃሲድ
በሚባል ተባይ ይተላለፋል፡፡ መከላከያ ዘዴውም፤

 ፋይሎዲ ከተከሰተበት ማሳ የተገኘ ዘር አለመጠቀም


 በሽታው የታየበትን ተክል ከማሳአርቆ መቅበር ወይም ማቃጠል

5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ

5.7.1 አጨዳ

 ሰሊጥ ከ90-150 ቀናት ውስጥ ለአጨዳ ይደርሳል


 ሁለት ሦስተኛው የተክሉ ቆምባ /የዘር አቃፊ / ወደ ቢጫነት
ሲቀየር መታጨድ አለበት
 ሰሊጥ በሰው ኃይል ወይም በማሽን ሊታጨድ ይችላል፡፡

5.7.2 ማድረቅ

 ሰሊጥ ወደ ላይ በማቆም ለሁለት ሳምንት ፀሀይ ላይ


መድረቅ ያስፈልጋል
 የታጨደው ሰብል ለውቂያ እስኪደርስ ንጽህናውን በጠበቀ
ሥፍራ ከ8 እስከ 10 ሂላ በአንድ አካባቢ ማቆየት
 በዚህ ጊዜ ነፋስ ምስጥ እና መጣጭ ተባይ ጉዳት
እንዳያደርሱ መከታተል ያስፈልጋል

5.7.3 ማራገፍ እና ማበጠር

 ሂላው በተከመረበት አቅራቢያ ንጹህ ሸራ በማንጠፍ ማራገፍ

18
 የተራገፈዉን ሰሊጥ 99% ንፁህ እስኪሆን ድረስ ማበጠር

 በንፁ ማዳበሪያ ከረጢት መሙላት

5.7.4 ማጓጓዝና ክምችት

 የሰሊጥ ምርት ለማጓጓዝ ከኬሚካል ወይም ቅባቶች ንክኪ


የፀዳ እና እርጥበት የሌለው የማጓጓዝያ መሳሪያ መጠቀም
ያስፈልጋል።
 ለማከማቸት የዘሩ የእርጥበት መጠን ከ 7% በላይ መሆን
የለበትም

 በሰሊጥ ማከማቻ መጋዘን ንጹህ ፣ ወለሉ በሲምንቶ የተለሰነ በቂ


መተላለፊያ ያለውና በውስጡ በቂ አየር የሚያንሸራሽር መሆን
አለበት፡፡

 ሰሊጡን የያዘ ማዳበያ ከረጢት ሲደረደር በ2 ድርዳሮ መካከል 2


ሜ ክፍተት መኖር አለበት

 በማከማቻ መጋዘን ውስጥ ተባይ እንኳ ቢከሰት ሰሊጥ በያዘ


ማዳበሪያ ላይ ምንም ዓይነት ኬሚካል መርጨት አይፈቀድም

5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት


የሰብል ፈረቃ / ስርዓተ አመራረት/

 የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ሰሊጥን በየአመቱ አከታትሎ


በአንድ የተወሰነ ማሳ ላይ መዝራት ምርትን ይቀንሳል፡፡ በመሆኑም
ማሳን አፈራርቆ ለመዝራት ፡─
o ሰሊጥን ከጥራጥሬ ሰብሎች /አኩሪ አተር፣ ማሾ/
o ሰሊጥ - ማሽላ - ጥራጥሬ
 ሰሊጥ - ጥጥ - ጥራጥሬ

19
5.9 ዘመናዊ የሰሊጥ የእርሻ መሳሪያ

 ሰሊጥን በተለመደው አመራረት ዘዴ ከማምረት ባሻገር ዘመናዊ


የእርሻ መሳሪያዎችን በመጠቀም ምርታማነትን እንደሚጨምር
በቅርቡ በምርምር የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ
 ከ 110 የፈረስ ጉልበት በላይ ያላቸው ትራክተሮችን መጠቀም
 ሞልድ ቦርድ ወይም ዲስክ ፕሎው በመጠቀም ከ 20─ 30 ሴ.ሜ
ጥልቀት ማረስ
 ዘመናዊ የመስመር መዝሪያ መሳሪያ /ፕሪሲሽን ሮው ፕላንተር/
 ዘመናዊ የማጨጃ መሳሪያ ማሽኖችን መጠቀም

5.10 የምርት አዋጭነት

 የጉልበት ወጪን በዝርዝር አሳይ


 መሬት ለማዘጋቸት፣ዘር መዝርያ፣መዳበርያ መዝራያ1ኛ፣2ኛ እና
3ኛ አረም
 ማጨጃ፣መዉቂያ፣ማጓጓዣ፣ማራገፍያና መጫኛ
 ለግብዓት ግዥ የወጣውን ወጪ በዝርዝር አስቀምጥ፤
 ለዘር፣ማዳበርያ፣ፀረ ተባይ
 መጋዘን ወጪ
 ወለድ ወጪ
 በምርት ትመና አርሶአደሩ ያገኘውን ምርት በሄ/ር መመዝግብ፤
 ተረፈ ምርቱ ያወጣውን ዋጋ በብር አመልክት፤
 የምርቱን ሆነ ተረፈ ምርቱን ጠቅላላ ሽያጭ አሳይ፤
 ጠቅላላ ወጪን ደምር፤
 ጠቅላላ ገቢውን ደምር፤
 ገቢውን ለወጪው አካፍል፤
 በማካፈል የተገኘው ውጤት ሁለት እና ከሁለት ሰሊጥን
ማምረት አዋጪ ነው፡፡

20
ኑግ (Niger seed: Guizotia abyssinica L.)

1. መግቢያ

በኢትዮጵያ ከሚመረቱ የቅባት ሰብሎች መካከል ኑግ ከሰሊጥ ቀጥሎ ከፍተኛውን


ድርሻ የሚይዝ ሀገር በቀል የቅባት ሰብል ነው። ሰብሉ ከጥንት ጀምሮ ለዘይት
ምንጭነት ህብረተሰቡ ሲጠቀምበት የነበረ ሲሆን በተለይ አነስተኛ የዘይት
ጨማቂዎች በዋናነት ለዘይት ጥሬ ዕቃነት ተመራጭ ያደርጉታል፡፡ ኑግ በአሁኑ
ወቅት ወደ ውጭ ሃገር እየተላከ ለውጭ ምንዛሪ እያስገኘ ይገኛል፡፡ የኑግ ዘይት
ከምግብ ዘይት ምንጭነት ባሻገር ለሳሙና፣ለቀለም፣ ለቫርኒሽ አገልግሎት
ይውላል፡፡ ተረፈ ምርቱም የፕሮቲን ይዘት ስላለው ለከብቶች መኖነት ያገለግላል፡፡

በ 2005/06 የማዕከላዊ ስታትስቲክ ባወጣው መረጃ መሠረት ኑግ 285,303 ሄ/ር


ማሳ በመሸፈን 35% የቅባት ሰብሎችን ሽፋን የያዘ ሲሆን በምርት ደረጃ
2,202,112 ኩ/ል ከጠቅላላው የቅባት ሰብሎች (31%) ድርሻ እንዳለው እና
ምርታማነቱም 7.72 ኩ/ል በሄ/ር መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡

የኑግ ዘይት በምግብነቱ በሃገራችን ተመራጭነት ያለው ቢሆንም በምርቱ


ዝቅተኛነት የሚፈለገውን ያህል ምርት በአርሶአደሮች ተመርቶ ለኢንዱስትሪዎች
ጥሬ እቃነትም ሆነ ለውጭ ገበያነት ማቅረብ አልተቻለም።

21
2. የኑግ ፓኬጅ አስፈላጊነት

የተሻሻለ የኑግ አመራረትና አያያዝ ዘዴን በአምራቹ ዘንድ ግንዛቤ በማሳደግ


በምርታማነቱም ሆነ በጥራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ፡፡

3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር

 ከፍታ፥ ከባህር ወለል በላይ ከ1600-2400 ሜትር ከፍታ


 የዝናብ መጠን፦ ከ500-1000 ሚሜ
 የአየር ሙቀት መጠን፦ ከ15-25ዲግሪ ሴንቲግሬድ
 የአፈር አይነት፣ የአፈሩ ጣዕም ከ 6.8 እስከ 7.3 በሆነ ቡናማ ሆኖ
ቀላል አሸዋማ እና ቀይ አፈር እንዲሁም ውሃ በማይቋጥር ጥቁር አፈር
ጥሩ ምርት ይሰጣል።

4. የተሻሻሉ ዝርያዎች
የኑግ ምርታማነትን ለመጨመር የተለያዩ የምርምር ስራዎች የተሰሩ ሲሆን እስከ
አሁን ባለው ጊዜ አምስት ዝርያዎች የተለቀቁ ሲሆን የዝርያዎቹ ምርታማነት እና
ባህሪያት በሰንጠረዥ 2. ተጠቅሰዋል

ሰንጠረዥ2. በምርምር የተለቀቁ የኑግ ዝርያዎች ዓይነትና ባሕሪያቸው፣

የዝርያው ተስማሚ የሚሰጠው ምርት በኩ/ል የተለቀቁበት


ስም ከፍታ የመድረሻ የዘይት በምርምር በአርሶ እ.ኤ.አ
ቀናት መጠን ማሳ አደር ማሳ
በመቶኛ
ኩዩ 2200-2700 147 38.0 10 1994
ፎገራ 1600-2200 147 39.6 9 3.9 1988
እስቴ-1 2200-2700 147 39.6 8.9 4.1 1988
ሻምቡ-1 2000-2400 145 39.3 9.4 5.6 2002
ጊንጭ-1 1600-2500 149 39.8 10 6-7 2010

22
5. የአመራረት ዘዴዎች

5.1 ማሳ መረጣ
 ውሃ የማይተኛበት፣ በጣም ተዳፋታማ ያልሆነ ከአረም የፀዳ
ማሳ ያስፈልገዋል፡፡

5.2 የማሳ ዝግጅት

 በደንብ የለሰለሰና ከአረም የጸዳ ማሳ ማዘጋጀት ፡፡


 የማሳ ዝግጅቱ እንደ ማሳው ተጨባጭ ሁኔታ የሚወሰን ሆኖ
በአማካኝ ከ 3 ጊዜ ያላነሰ የእርሻ ድግግሞሽ ያስፈልገዋል።
 ገልባጭ ማረሻን ተጠቅሞ የማሳ ዝግጅትን ማከናዎን ጠቃሚ
ነው።

5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ

5.3.1 የዘር ወቅት

 ከፍታቸው ከ2000ሜ ባህር ጠለል በላይ በሆኑ አካባቢዎች


ለሚመረተው ኑግ / አባት ኑግ/ ከሰኔ ወር አጋማሽ እስከ ሀምሌ
መጀመሪያ ድረስ ያለው ጊዜ ተመራጭ የመዝሪያ ወቅት ሲሆን
 ከ2000ሜ ከፍታ በታች ላላቸው አካባቢወች ደግሞ ከሰኔ አጋማሽ
እስከ ሰኔ መጨረሻያለው ጊዜ ተስማሚ የዘር ወቅት ነው።

5.3.2 የአዘራር ዘዴ

 ኑግ በመስመር ሲዘራ በመስመሮች መካከል ያለው ርቀት 30 ሳ.ሜ


ሆኖ በበሬ የወጣውን መስመር በመከተል ዘሩን በመመጠን መዝራት
ያስፈልጋል፡፡
 የዘር ጥልቀቱ 2 ─ 3 ሴ.ሜ መሆን አለበት

23
 መስመር እያወጣ የተዘራውን ዘር በሬው ሲመለስ እንዲያለብስው
ወይም ሰው እየተከተለ በእጅ እንዲያለብስው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

5.3.3 የዘር መጠን

 ኑግ በመስመር ሲዘራ 5─10 ኪሎ ግራም በሄ/ር መጠቀም


ይገባል።

5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ

 እንደ ማሳው ሁኔታ ታይቶ ለኑግ 50 ኪ/ግ ዳኘ እና 30 ኪ/ግ


ዩሪያ በዘር ወቅት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

5.5 አረም ቁጥጥር

ኑግ ቅጠለ ሰፋፊ እና የሳር አረሞች እንዲሁም ጥገኛ አረሞች ይጠቃል፡፡


ከሰፋፉ ቅጠል ካላቸው አረሞች ውስጥ መጭ ወና የኑግ አረም ነው፡፡
በአጠቃላይ የኑግ አረምን ለመከላከል፡

 ሰብሉ ከበቀለ ከ20-25 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ መታረም አለበት።


 ከአረም ዘር የጸዳና በሚገባ የተበጠረ ዘር መጠቀም፣
 ማሳን በወቅቱና በጥሩ ሁኔታ አለስልሶ ማዘጋጀት፣
በኑግ ላይ ከፍተኛ የምርት መቀነስ የሚያደርሰው ዋነኛ አረም የኑግ
አንበሳ (Dodder) የተባለው ጥገኛ አረም ነው።የዚህን አረም ጉዳት
ለመቀነስ የሚከተሉት ተግባራት ሊከናወኑ ይገባል።
 የአረሙ ዘር የሌለበትና በሚገባ የተበጠረ ንጹህ ዘር መጠቀም፣

24
 አረሙን ከኑግ ተክል ላይ በእጅ ብቻ በማረም መከላከል
ስለማይቻል በአረሙ የተጠቁ ተክሎች ሙሉ በሙሉ ከነአረሙ
ተነቅለው መቀበር ወይም መቃጠል ይኖርባቸዋል።
 አረሙ በማሳው ላይ ከታየ የተከሰተበትን ማሳ ቢያንስ ለ 3 ዓመት
ኑግ እና ሌሎች አረሙ ሊያጠቃቸው የሚችሉ ሰብሎችን ከመዝራት
መቆጠብ፡፡

5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር

5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር


ኑግን ከሚያጠቁ ነፍሳተ ተባዮች ዋናዎቹ የኑግ ዝንብ
(Eutetosoma sp.
 የኑግ ዝንብን ጥቃት የሚቋቋሙ ዝርያዎችን
መጠቀም

5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር

ኑግን የሚጠቁ በሽታዎች ውስጥ የሰብሉን ግንድና ቅጠሉን የሚያቃጥለው Blight


“(Alternaria spp.) ፣የቅጠሉን መሃል የሚሸነቁረው ሹት ሆል " Shoot hole"
(Septoria guizotia) እና አመዳይ (Powdery mildew) ዋና ዋናዎቹ በሸታዎች
ናቸው፡፡ እነዚህንም በሽታ ለመከላለል፡─
 በሽታውን የሚቋቋሙ ዝርያዎችን መጠቀም
 የሰብል ፈረቃን መጠቀም
 ለሹት ሆል በሽታ ፖሊራም ዲኤፍ 1.8 ኪ.ግ በሄ/ር፣
ሚስትራል 1 ሊትር በሄ/ር እና ቲልት 0.5 ሊትር በሄ/ር
ደጋግሞ በመርጨት በሽታውን መቀነስ ይቻላል፡፡

25
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ

5.7.1 አጨዳ

 የኑግ ሰብል በወቅቱ ካልተሰበሰበ ዘሩ ረግፎ ለኪሳራ ስለሚዳርግ


50 በመቶ አበባው ከረገፈ ከ3 ሳምንት በኋላ ወይም የዘሩ የርጥበት
መጠን ከ8-12 በመቶ ሲሆን እና የተክሉ የላይኛው ቅጠል
ከአረንጓዴነት ወደ ቢጫነት ሲቀየር፣ የታችኛው ቅጠል ደግሞ ወደ
ቡናማነት ሲቀየር ቢታጨድ ለምርትም ሆነ ለዘይት ይዘቱ ከፍተኛ
ጠቀሜታ ስላለው በዚህ ወቅት ማጨድ ያስፈልጋል፡፡
 በአጨዳ ወቅት ከግንዱ ዝቅ አድርጎ በማጨድ ዘሩ እንዳይረግፍ
በጥንቃቄ ተይዞ ወደ መውቂያ ቦታ መሄድ ይኖርበታል።

5.7.2 ማድረቅ
 ኑግ ከመወቃቱ በፊት በአውድማ ላይ የዘር እርጥበቱ 10%
እስኪደርስ መድረቅ ይኖርበታል።
 ነዶውን በጥንቃቄ በማሰር ለጥቂት ቀናት በማቆም ማድረቅ

5.7.3 ውቂያ

 በንፁህ አውድማ ላይ መወቃት፣ yzR _‰TN bbl- lm-bQ


b-Nµ‰ ¹‰ wYM bs!¸Nè btzUj wlL b!w”
tm‰+nT YñrêLÝÝ

 bxnSt¾ ¥ú §Y n#G b¸gÆ btzUj xWD¥ bǧ


Xytm¬ wYM bbÊ Xytrg- Yw”LÝÝ

 bsÍð XRšãC bmwqEÃ ¥>N mW”T y¸ÒL s!çN ngR


GN ymWqEW ¥>N yn#GN yzR m-N TN>nT ÆgÂzb
mLk# mStµkL YñRb¬LÝÝ

26
5.7.4 ማጓጓዝ እና ክምችት

 ኑግ ከተወቃ በኋላ የዘር እርጥበቱ ከ8% በታች ሆኖ ንፁህ፣ ደረቅና ነፋሻ


በሆነ ማከማቻ ውስጥ ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
 የኑግ ምርት ለማጓጓዝ ደረቅና ንጹህ በሆነ ማዳበሪያ ከረጢት መጠቀም
ይገባል፡፡

5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት

ኑግ እንደዋና ሰብል ሆኖ ብቻውን ቢዘራም የበሽታ፣ አረም እና ነፍሳተ ተባይ


መስፋፋትን ለመቆጣጠር የሰብል ፈረቃ ማጠቀም ተገቢ ነው፡፡
 ኑግ─ ጥራጥሬ ─ጤፍ

5.9 የምርት አዋጭነት

 የጉልበት ወጪን በዝርዝር አሳይ፤


 ለግብዓት ግዥ የወጣውን ወጪ በዝርዝር አስቀምጥ፤
 በምርት ትመና አርሶአደሩ ያገኘውን ምርት በሄ/ር መመዝግብ፤
 ተረፈ ምርቱ ያወጣውን ዋጋ በብር አመልክት፤
 የምርቱን ሆነ ተረፈ ምርቱን ጠቅላላ ሽያጭ አሳይ፤
 ጠቅላላ ወጪን ደምር፤
 ጠቅላላ ገቢውን ደምር፤
 ገቢውን ለወጪው አካፍል፤
 በማካፈል የተገኘው ውጤት ሁለት እና ከሁለት በላይ ከሆነ ኑግን
ማምረት አዋጪ ነው፡፡

27
ተልባ / Linum usitatissimum L /

1.መግቢያ

በኢትዮጵያ ደጋማ ሥነ- ምህዳር ከሚመረቱት ዋና ዋና የቅባት ሰብሎች ውሰጥ


አንዱ ተልባ ነው፡፡ የእዚህ ሰብል ዓይነተኛ ጠቀሜታ ለአምራቹ ተጨማሪ የገቢ
ምንጭ ማስገኛ ከመሆኑም በላይ ለምግብነት ያገለግላል፡፡ በአገራችን ውስጥ
የተልባ የምግብ ጠቀሜታ በዘልማድ የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ዘመን ከምግብ
ይዘቱ ልዩ ባህርይ የተነሳ በዓለም ላይ ከጤናማ የምግብ ሰብሎች ምድብ
በመካተቱ ተፈላጊነቱ እያደገ መጥቷል፡፡

እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክ ባለስልጣን በ2005/6 መረጃ ተልባ 95,583 ሄ/ር ማሳ


በመሸፈን 11.7 % የቅባት ሰብሎችን ሽፋን የያዘ ሲሆን በምርት ደረጃ 879,459
ኩ/ል ከጠቅላላው የቅባት ሰብሎች (12.4%) ድርሻ እንዳለው እና ምርታማነቱም
9.2 ኩ/ል በሄ/ር መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡

ተልባ በአገሪቷ ለገበሬው የገቢ ምንጭነት፣ ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት በጣም


ተፈላጊ ቢሆንም ምርታማነቱ በተለያዩ በሸታዎች እና አረም ስለሚጠቃ እነዲሁም
አምራቹ ዘመናዊ የአመራረት ስልት ባለመጠቀሙ ምርቱ አናሳ ሆኗል፡፡
በመሆኑም የተልባን አዳዲስ ዝረያዎችን እንዲሁም የተሻሻሉ አመራረት ሰልት
አምራቹ እንዲጠቀም ለማስቻል ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል፡፡

28
2.ፓኬጁ አስፈላጊነት

በተልባ አመራረት ረገድ የሚታዩ ወቅታዊ የምርት ማነቆዎች መፍታት


የሚያስችል አዳዲስና የተሻሻሉ አመራረት ቴክኖሎጂ ፓኬጅ ለኤክስቴንሽን
ባለሙያዎችና ለአምራቾች ማስተዋወቅ በማስፈለጉ፣

3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ ምህዳር

 ከፍታ፦ ከ1600 - 2800 ሜ ከባህር ጠለል በላይ ባላቸው ቦታዎች ተልባ


ይመረታል፣ በተለይ ከ 2300-2800 ሜ. የባህር ጠለል ከፍታ ያላቸው ቦታዎች
ተክሉ የበለጠ ይስማማዋል፡፡
 የአየር ሙቀት፦ ከ12-17.5 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ለተልባ ተስማሚ ነው፣
 የዝናብ መጠን፦ በእድገት ጊዜው ከ 500-700 ሚ.ሜ. ተስማሚው ነው፡፡
 የአፈሩ ሁኔታ፡ ለም ሸክላማ አፈር ሆኖ የአፈር ጣዕሙ 6.6 -7.6 ሲሆን
ውሃን የሚያቁር እና መረሬ አፈር እንዲሁም በጣም አሸዋማ አፈር
አይስማማውም፡፡/ሆለታ ግ/ም/ማዕከል/

4. የተሻሻሉ ዝርያዎች

የተልባ ምርታማነትን ለመጨመር የተለያዩ የምርምር ስራዎች የተሰሩ ሲሆን


እስከ 2007 ዓ/ም ባለው ጊዜ 13 ዝርያዎች የተለቀቁ ሲሆን የዝርያዎቹ
ምርታማነት እና ባህሪያት በሰንጠረዥ 3. ተጠቅሰዋል

29
ሠንጠረዥ 3. በምርምር የተለቀቁ የተልባ ዝርያዎች ዓይነትና ባሕሪያቸው፣

ምርትታማነት ኩ/ል
በሄ/ር
በአርሶ የዘይት
የተለቀቀበት
የዝርያው የመድረሻ በምርምር አደር መጠን
ተ.ቁ እ.ኤ.አ
ስም ቀናት ማዕከላት ማሳ (%)
1 38.5
ሲአይ-1525 1984 146 14.30 8.10
2 38.6
ሲአይ-1652 1984 146 13.60 8.80
3 35.2
ጭላሎ 1992 140 16.70 9.00
4 36.3
በላይ-96 1996 141 16.80 9.00
5 37.0
በረነ 2001 140 16.17 9.10
6 36.0
ቶሌ 2004 143 16.90 10.00
7 37.1
ቁልምሳ-1 2006 141 17.85 11.00
8 37
ጀልዱ 2010 180 15.1 11.2
9 37.1
ጂቱ 2012 152 19-20 16─18
10 37.45
ካሳ-2 2012 143 12.59 ─
11 37.1
ብሊስታር 2013 152 19─20 16─18
12 38
ፉርቱ 2013 152 17.61 15.55
13 38.6
በቆጂ14 2014 149 15.14 10─12

30
5. የአመራረት ዘዴዎች

5.1 ማሳ መረጣ

 ተዳፋታማ ያልሆነ የተዳፋትነት መጠኑ ከ15% ያልበለጠ እና ውሃ


የማይቋጥር ቀይ/ ቡናማ አፈር መሬት መምረጥ፡፡

5.2 የማሳ ዝግጅት

 ተልባ በሚገባ የታረሰ ፣ የለሰለሰ እና ከአረም የፀዳ ማሳ ያስፈልገዋል፡፡


 እርሻው ከ2-3 ጊዜ በበሬ ማረስ ወይም
 በሚገለብጥ /ሞልድ ቦርድ/ ማረሻ ማረስ እና ማለስለስ፡፡

5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ

5.3.1 የዘር ወቅት

 እንደ ዝናቡ አጀማመር ከሰኔ መጀመሪያ እስከ ሐምሌ መጨረሻ


አካባቢ አፈሩ በቂ እርጥበት እንዳገኘ መዝራት ለድርቅ፣ ለውርጭና
ለበሽታ እንዳይጋለጥ ይረዳል፡፡

5.3.2 የአዘራር ዘዴ

 በመስመር መካከል 20 ሴ.ሜ. ርቀት አራርቆ ለማሳው የተመጠነው


ዘር አብቃቅቶ መዝራት
 የዘር ጥልቀት፤ ከ 3 ሳ.ሜ ያልበለጠ

5.3.3 ማማማ ማማማ


 25 ኪ.ግም፤ ዘር በመስመር ለአንድ ሄክታር በቂ ነው፡፡

31
5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ

 እንደ አፈሩ ሁኔታ 50 ኪሎ ግራም ዳፕ እና 30 ኪሎግራም ዩሪያ


በሄክታር ለሰብሉ እድገት እና ምርታማነት መስጠት፡፡ በዘር ወቅት
በመስመር ከ 7-10 ሳ.ሜ. ጥልቀት በማድረግ አፈር እስከ ዘር
ጥልቀቱ ማልበስ፡፡

5.5 አረም ቁጥጥር

ተልባን የሳርና ቅጠለ ሰፋፊ አረሞች ያጠቁታል እነዚህንም ለመከላከል


 ከአረም ዘር የጸዳና በሚገባ የተበጠረ ዘር መጠቀም፣
 ማሳን በወቅቱና በጥሩ ሁኔታ አለስልሶ ማዘጋጀት፣
 ሁለት ጊዜ በእጅ ማረም ይህም
o ሰብሉ ከተዘራ ከ አንድ ወር በኋላ
o ለአበባ ወቅት ሊደርስ ሲል
 አረሙን በእጅ ለማረም የሰው ጉልበት ከሌለ የአረም መከላከያ
መድሃኒት መጠቀም፣ ፔንዲሜንታሊን 1 ሊትር/ሄ 200 ወሃ
መጠቀም ያስፈልጋል
ተልባ እንደ ኑግ ኩስኩስታ ወይም ዶደር / Dodder / የተባለው ጥገኛ
አረም ያጠቃዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን አረም ለመከላከል የሚከተሉት
ተግባራት ሊከናወኑ ይገባል።
 የአረሙ ዘር የሌለበትና በሚገባ የተበጠረ ንጹህ ዘር መጠቀም፣
 አረሙን ከኑግ ተክል ላይ በእጅ ብቻ በማረም መከላከል
ስለማይቻል በአረሙ የተጠቁ ተክሎች ሙሉ በሙሉ ከነአረሙ
ተነቅለው መቀበር ወይም መቃጠል ይኖርባቸዋል።

32
 አረሙ በማሳው ላይ ከታየ የተከሰተበትን ማሳ ቢያንስ ለ 3 ዓመት
ተልባ እና ሌሎች አረሙ ሊያጠቃቸው የሚችሉ ሰብሎችን
ከመዝራት መቆጠብ፡፡

5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር

5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር

 ተልባን የጓይ እና ፕሉሲያ ትሎች ያጠቁታል እንዚህንም ነፍሳተ


ተባዮች በማሳው ውስጥ ስርጭታቸው ለሰብሉ መጎዳት አስጊ ደረጃ
ሲደርስ የሚከተሉትን ኬሚካሎች ተጠቅሞ መቆጣጠር
ይቻላል፡─
 ላምዴክስ /ካራቴ/ 5 % EC ከ 250─400 ሚ.ሊ በሄክታር
 ዲያዞኒን 60% ኢሲ 1 ሊትር በሄክታር ከላይ የተገለጹትን ፀረ-
ተባዮች በ200 ሊትር ውሃ በጥብጦ መርጨት፡፡

5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር

ተልባን የሚከተሉት በሽታዎች ያጠቁታል እነሱም፡─

 ተክል አጠውልግ
o ተክል በማጠውለግ የሚታወቅ የፈንገስ በሽታ ነው፡፡
o የአፈር ሙቀት እና እርጥበት ከፍ ሲል በከፍተኛ ደረጃ
ይከሰታል፡፡

 ፓዝም
o እርጥበት አዘል ሞቃት የአየር ሁኔታ ለበሽታው አምጪ
ተህዋስያን ፈጥኖ መራባት አንዱ እና ዋንኛው ምክንያት
ነው፡፡

33
o በሽታዉ የተክሉን ግንድ እና ጓይ ይለበልባል፣

34
 የቅጠል ሻጋታ /ፓውደሪ ሚልዲው/
o ቅጠሉን በዱቄት መሰል ሻጋታ በመሸፈን ምግብ
የሚያዘጋጀውን አካል ያጠቃል፡፡

መከላከያ ዘዴ፡-
o በሽታውን የሚቋቋም ዝርያ መጠቀም፡፡
o ሰብልን እያፈራረቁ መዝራት
o በፈንገሱ የተጠቃውን ገለባ ማቃጠል
o ከበሽታ አምጪ ከሆነ ተዋስያን ነጻ የሆነ ማሳ ላይ መዝራት

5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ

5.7.1 አጨዳ

 ቅጠሉ ሲደርቅ እና አብዛኛው ጓዮች ወደ ቡናማ መልክ ሲቀየሩ፣


 ዘሩ በጓዮች ውስጥ የመንኮሻኮሽ ድምፅ ሲያሰማ ፣
 የዘር እርጥበት መጠኑ 10%─15% መካከል ላይ ሲሆን ማጨድ፡፡

5.7.2 ማድረቅ

 ከተሰበሰበ እስከ ሶስት ሳምንት ድረስ በማሳው ላይ በማቆየት


ማድረቅ ፡፡

5.7.3 ውቂያ

 ለውቂያ በተዘጋጀ ንጹህ አውድማ ( ሸራ) ላይ ማድረግና


መውቃት፡፡
 ሰፋፊ ለሆኑ እርሻዎች ኮምባይን ሃርቨስተር ተጠቅሞ መውቃት
ይቻላል፡፡

35
5.7.4 ማጓጓዝና ክምችት

 ከሽታ እና ባዕድ ነገሮች ከያዙ የማጓጓዣ እቃዎች ከመጠቀም


መቆጠብ፣
 ከፍሳሽ እና ከቆሻሻ ምርትን መጠበቅ፣
 የዘር እርጥበት ከ 9% በታች ሲሆን ማከማቸት፣
 ለረዥም ጊዜ ማቆየት፡ ከተፈለገ አየር እንደልብ በሚዘዋወርበት
ቀዝቃዛ መጋዘን ውስጥ ማከማቸት፡፡

5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት

የሰብል ፈረቃ / ስርዓተ አመራረት/

ተልባ እንደዋና ሰብል ሆኖ ብቻውን ቢዘራም የበሽታ፣ አረም እና ነፍሳተ


ተባይ መስፋፋትን ለመቆጣጠር የሰብል ፈረቃ ማጠቀም ተገቢ ነው፡፡
ተልባ─ ድንች ─ገብስ

5.9 የምርት አዋጭነት


 የጉልበት ወጪን በዝርዝር አሳይ፤
 ለግብዓት ግዥ የወጣውን ወጪ በዝርዝር አስቀምጥ፤
 በምርት ትመና አርሶአደሩ ያገኘውን ምርት በሄ/ር መመዝግብ፤
 ተረፈ ምርቱ ያወጣውን ዋጋ በብር አመልክት፤
 የምርቱን ሆነ ተረፈ ምርቱን ጠቅላላ ሽያጭ አሳይ፤
 ጠቅላላ ወጪን ደምር፤
 ጠቅላላ ገቢውን ደምር፤
 ገቢውን ለወጪው አካፍል፤
 በማካፈል የተገኘው ውጤት ሁለት እና ከሁለት በላይ ከሆነ ተልባን
ማምረት አዋጪ ነው፡፡

36
ጎመንዘር

1. መግቢያ

በኢትዮጵያ ደጋማ ሥነ- ምህዳር ከሚመረቱት ዋና ዋና የቅባት ሰብሎች ውሰጥ


አንዱ ጎመንዘር ነው፡፡ የሰብሉ ዓይነተኛ ጠቀሜታም ለገበሬው የገቢ ምንጭ
ማስገኛ ከመሆኑም በላይ ቅጠሉ ለምግብነት ይውላል እንዲሁም ለተለያዩ
ዘልማዳዊ ጥቅም ለምሳሌ እንደ ማሰሻና መድሃኒት ይውላል፡፡ ሰብሉ በአሁኑ
ወቅት በውስጡ ያለው ንጥረ ነገር ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት ባለው ተፈላጊነት
ወደ ውጭ ተልኮ ለውጭ ምንዛሪ ምንጭነት ያገለግላል፡፡

እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክ ባለስልጣን በ2005/6 መረጃ መሠረት ጎመንዘር


44041 ሄ/ር ማሳ በመሸፈን 5.4 % የቅባት ሰብሎችን ሽፋን የያዘ ሲሆን በምርት
ደረጃ 624,503 ኩ/ል ከጠቅላላው የቅባት ሰብሎች (8.8%) ድርሻ እንዳለው እና
ምርታማነቱም 14.2 ኩ/ል በሄ/ር መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡

ጎመንዘር ለገበሬው የገቢ ምንጭነት፣ ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት በጣም ተፈላጊ


ቢሆንም የሰብሉ የምርት ሽፋን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መጥቷል፡፡ በመሆኑም
የተልባን አዳዲስ ዝረያዎችን እንዲሁም የተሻሻሉ አመራረት ሰልት አምራቹ
እንዲጠቀም ለማስቻል ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል፡፡

37
2. የፓኬጁ አስፈላጊነት

ጎመን ዘር የሚያስፈልገውን የጥራት ደረጃ በመያዝ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ


እንዲሆን የምርታማነት እና የጥራት ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚያስችል
የአመራረት ቴክኖሎጅ ፓኬጅ በማስፈለጉ ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚ
ቀርቧል።

3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር

 ተስማሚ ከፍታ ፡- ከ 2200-2600 ሜትር ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ


የሆነ፣
 የዝናብ መጠን ፡- 600-900 ሚሊ ሜትር የዝናብ መጠን፣
 የአየር ሙቀት ከ 12-18 ዲግሪ ሴንቲግሬድ፣
 የአፈር ዓይነት፡- ቀይ እና ቡናማ፣ ውሃ የማይቋጥር ፣የአፈር ጣዕም ከ
6-7.5 የሆነ ለም አፈር ይስማማዋል

4. የተሻሻሉ ዝርያዎች

የጎመዘን ዘር ምርታማነትን ለመጨመር የተለያዩ የምርምር ስራዎች የተሰሩ


ሲሆን እስከ 2007 ዓ/ም ባለው ጊዜ ዝርያዎች የተለቀቁ ሲሆን የዝርያዎቹ
ምርታማነት እና ባህሪያት በሰንጠረዥ 4. ተጠቅሰዋል

38
ሠንጠረዥ 4. በምርምር የተለቀቁ የጎመንዘር ዝርያዎች ዓይነትና ባሕሪያቸው

የ.የ. የየየ የየየየየየየ የየየየየየ የየየየ


የ.የ የየየ /%/

የየየየየ የየየየ
1 የየየ -1(ACC-153) 2006 9.4 - 38
2 የየየ-1 (PGRC/E/1/2/208507) 2006 10.6 - 33.5
3 Holetta-1 2005 30.3 15 39.1
4 የየየ (PGRC/E 20021) 2002 15.3 3.3 ─
5 የየ (PGRC/E 21163) 2002 15.4 15.2 ─
6 የየ (s-67x zem-1/xs-67c6) 1993 18 14-16 42.5
7 የየ የየየ 1986 30 16.8 44.1
8 የየ-67 1976 30 17.8 40.5

5.የአመራረት ዘዴዎች

5.1ማሳ መረጣ
 ተዳፋታማ ያልሆነ የተዳፋትነት መጠኑ ከ15% ያልበለጠ
እና ውሃ የማይቋጥር ቀይ/ ቡናማ አፈር መሬት መምረጥ፡፡
 ለማሳ ዝግጅት የተመረጠው ቦታ ከ 3 ዓመታት ወዲህ
የጎመን ዘር ያልለማበት ቢሆን ይመረጣል፡፡

5.2 የማሳ ዝግጅት

 እርሻው አንድ ጊዜ ጠለቅ ያለ እንዲሆን በማድረግ እና ከ2-3 ጊዜ አለስልሶ


በማረስ ከአረም እንዲጸዳ መዘጋጀት አለበት፡፡

39
5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ

5.3.1 የዘር ወቅት

ጎመንዘር የመዝሪያ ወቅት እንደ ዝናቡ አጀማመር እና የአፈር ሁኔተ


ይለያያል፡፡

 በቀይ እና ቀላል አፈር ላይ ዝናብ እንደጀመረ መዝራት /ከግንቦት


መጨረሻ እስከ ሰኔ መጨረሻ/

 በጥቁር አፈር ከሆነ ከሐምሌ መጀመሪያ እስከ ሐምሌ መጨረሻ


መሆን አለበት፡፡

5.3.2 የአዘራር ዘዴ

 ጎመን ዘር ሲዘራ በመስመሩ መካከል ያለው ርቅት 30 ሳ.ሜ መሆን


አለበት፣

 የዘር ጥልቀቱ 2─ 3 ሴ.ሜትር መሆን አለበት፡፡

5.3.3 የዘር መጠን

 የጎመን ዘር መጠን 10 ኪ.ግ ዘር በሄ/ር ያስፈልጋል፡፡

 ዘሩን በመስመሩ መጥኖ መዝራት ያስፈልጋል፡፡

5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ

 ጎመን ዘር ለማዳበሪያ የሚያሳየው ምላሽ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡

 150 ኪ.ግ/ሄ ዳፕ እና 41 ዩሪያ ኪ.ግ/ሄ በዘር ወቅት መጠቀም

 የማዳበሪያ ስንጠቀም አስቀድሞ ማዳበሪያውን በመስመር ላይ ከ 7-


10 ሳንቲ ሜትር ጥልቀት ዘርቶ ከትልሙ ከንፈር 2 ሳንቲ-ሜትር
ዝቅ በማለት ዘሩን በመዝራት ሁለተኛውን መስመር በሚወጣበት ጊዜ
ዘሩንና ማዳበሪያውን በአፈር ማልበስ ይጠበቃል፡፡

40
5.5 የአረም ቁጥጥር

 ሰብሉ ከበቀለ ከ20-30 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ አንድ ጊዜ በእጅ


ማረም

 ጎመንን ኦሮባንኬ ራሞስ የተባለ ጥገኛ አረም ያጠቃዋል ይህንን አረም


ለመከላከል

o አረሙ ከማበቡ በፊት ከሥር ነቅሎ ማቃጠል ያስፈልጋል፡፡

o ማሳን አርሶ የአረሙን ሥር ለፀሐይ ማጋለጥ

o ተጓዳኝ አረሞችን ማስወገድ

o ማሳን ማፈራረቅ

5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር

5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር

ጎመንዘርን የተለያዩ ነፍሳተ ተባች ያጠቁታል፡፡ ከነዚህ ውስጥ


ዋና ዋናዎቹ እና መከላከያ ዘዴያቸው ፡─
 ወርቂት ( Flea beetles)

እነዚህ ነፍሳት ተክሉን በመጀመሪያዎቹ የዕድገት ወቅት


የታችኛውን የቅጠል ክፍል በመመገብና ቀዳዳ በማውጣት
ዕድገቱን ያቀጭጫሉ

መከላከያ መንገዱ

o ሲንተቲክ ፕሪትሮይድ /synthetic pyrethroid/


ላምብዳ ሲያሎትሪን /Lambda-cyhalothrin/ 5%
EC 1.4 ሊትር በሄክታር መጠቀም
o ካርባሪይል /Carbaryl/ 85% በሟሟት/Wet powder/ 1.5
ኪ.ግ. በሄክታር መጠቀም

41
 ክሽክሽ (Cabbage aphid)

ይህ ተባይ ተክሉን በመውረር ቅቤያማ መሰል የሆነ ነጭ ቀለም


ይሸፍነዋል፡፡ መከላከያውም ፡
o ላምዴክስ /ካራቴ/ 5 % EC ከ 250─400 ሚ.ሊ
በሄክታር
o ለክሽክሽ ብቻ የሚሆን /aphid specific/ ካርባሜት
ፕሪሚካርብ 50% WP 500 ግራም በሄክታር
መጠቀም

 የጎመን ትል (Diamond-back moth)

ይህ ነፍሳት የተክሉን ቅጠል ቀዳዳ በማውጣትና የሥረኛውን ክፍል


በማጥቃት ይታወቃል፡፡ መከላከያውም፤
o ሲንቴቲክ ፕሪትሮይድ ሲፐርሜትሪን /synthetic
pyrethroid, Cypermethrin / 25% EC 200
ሚ.ሊ. በሄክታር መጠቀም

5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር

 ጠቃጠቆ (Leaf and pod spot)

ይህ በሽታ በፈንገስ /Fungus/ የሚመጣ ሲሆን የተክሉን


ቅጠል፣ግንድ፣ የዘር አቃፊውን እንዲሁም ዘሩ ላይ ጥቁር ጠባሳ
በመፍጠር ጉዳት ያደርሳል ፡፡ መከላከያ ዘዴ፡-
 ከበሽታ ነፃ የሆነ ዘር መጠቀም
 በሽታውን የሚቋቋሙ የተለቀቁ ዝርያዎች መጠቀም
 የሰብል ፈረቃ መጠቀም
 በበሽታ የተጠቃውን የተክል አካል ከማሳ ማጽዳት

42
 ፀረ-ፈንገስ መዲሃኒት ለምሣሌ ባይሊቶን /bayleton/
መጠቀም
 ዋግ (White Rust)

ይህም በሽታ በፈንገስ / Fungus / የሚመጣ ሲሆን ፡ የተክሉን አበባ


እንዲሁም የቅጠሉን የሥረኛውን ክፍል በማጥቃት ይታወቃል ፡፡
መከላከያ ዘዴ፡-
 በሽታውን የሚቋቋሙ የተለቀቁ ዝርያዎች መጠቀም
 ንጹህ ዘር መጠቀም
 በበሽታው የተጠቃውን ተክል ማስወገድ
 የሰብል ፈረቃ መጠቀም

 ዳውኒ ሚልዲው
ዳውኒ ሚልዲው የጎመንን እራሱን የሚጨመድድ በሽታ ሲሆን
መከላከያውም፡─
 በሽታውን የሚቋቋሙ የተለቀቁ ዝርያዎች መጠቀም
 ንጹህ ዘር መጠቀም
 በበሽታው የተጠቃውን ተክል ማስወገድ
 የሰብል ፈረቃ መጠቀም

ማሳሰቢያ ፡-

 የጎመንዘር ለዘሩ ከመመረቱ ባሻገር በልጅነቱ በሰፊዉ በአርሶ


አደሮች ዘንድ ለአትክልትነት /ቅጠሉ ለምግብነት/ ጥቅም ላይ
ይዉላል፡፡ በመሆኑም ለአትክልትነት በሚመረተዉ ማሳ ላይ
ነብሳተ ተባዮችንም ሆነ በሽታን ለመከላከል ኬሚካሎችን
ከመጠቀም ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ይመከራል፡፡

43
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ

5.7.1 አጨዳ
 ጎመን ዘር ከ 156- 160 ቀናት ውስጥ ለአጨዳ ይደርሳል፣
 የዘር አቃፊው /pods/ ወደ ቡናማ እና የግንዱ ቀለም ወደ ነጭ
ሲቀየር
 የዘር እርጥበት መጠኑ ከ 10─15%፣
 የዘር አቃፊው የመንሿሿት ድምጽ ሲያሰማ
 የዘር መርገፍ ለመቀነት አጨዳው መከናወን ያለበት በጠዋት
ነው፡፡

5.7.2 ማድረቅ

በማጭድ ሲታጨድ ከመወቃቱ በፊት እንደ አየሩ ሁኔታ ከ


10─15 ፀሐይ ላይ መድረቅ አለበት፡፡

5.7.3 ውቂያ

 ጎመንዘር በደንብ ከደረቀ በኋላ በንጹህ አውድማ/ሸራ/ ላይ


በማድረግ በከብት ወይም በእንጨት እየደበደቡ መውቃት ይቻላል፡፡
 ሰፋፊ ለሆኑ ማሣዎች ስንዴን አጭደው በሚወቃ ማሽን
/combine harvester/ በመጠቀም መሰብሰብ ይቻላል፡፡

5.7.4 ማጓጓዝ እና ክምችት

 የጎመንዘር ሰብልን ለማጓጓዝ ከኬሚካል ወይም ቅባቶች


ንክኪ የፀዳ እና እርጥበት የሌለው የማጓጓዝያ መሳሪያ
መጠቀም ያስፈልጋል።
 በንጹህ ማከማቻ አና አየር እንደልብ በሚዘዋወርበት ጎተራ
ለረዥም ጊዜ ማቆየት ይቻላል፡፡
 ዘሩን ለረዥም ጊዜ ለማቆየት የዘር ርጥበት በጠኑን ከ 8%
መብለጥ የለበትም፡፡

44
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት

ጎመንዘር እንደዋና ሰብል ሆኖ ብቻውን ቢዘራም የበሽታ፣ አረም


እና ነፍሳተ ተባይ መስፋፋትን ለመቆጣጠር የሰብል ፈረቃ
ማጠቀም ተገቢ ነው፡፡

 ጎመንዘር ─ ገብስ ─ገብስ


 ጎመንዘር ─ ስንዴ ─ ስነዴ

5.9 የምርት አዋጭነት

 የጉልበት ወጪን በዝርዝር አሳይ፤


 ለግብዓት ግዥ የወጣውን ወጪ በዝርዝር አስቀምጥ፤
 በምርት ትመና አርሶአደሩ ያገኘውን ምርት በሄ/ር መመዝግብ፤
 ጠቅላላ ወጪን ደምር፤
 ጠቅላላ ገቢውን ደምር፤
 ገቢውን ለወጪው አካፍል፤
 በማካፈል የተገኘው ውጤት ሁለት እና ከሁለት በላይ ከሆነ
ጎመንዘር ማምረት አዋጪ ነው፡፡

45
ማማማ

1. መግቢያ

በኢትዮጵያ ሞቃታማ ሥነ- ምህዳር ከሚመረቱት ዋና ዋና የቆላ ቅባት ሰብሎች


ውሰጥ አንዱ ለውዝ ነው፡፡ ይህ ሰብል እንደ ጥራጥሬ ሰብሎች ናይትሮጅንን
በተፈጥሮ የመጠቀም ባህሪ ስላለው የመሬት ለምነት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው፡፡
የለውዝ ፍሬ እስከ 50% ዘይት 30% ፕሮቲን እና 20% ኃይል ሰጪ ንጥረ
ነገሮችን በመያዙ ተፈላጊነቱን የጎላዋል፡፡ ለውዝ ወደ ውጭ በመላክ ለሀገራችን
የውጭ ምንዛሪን በማስገኘትም አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክ ባለስልጣን በ2005/6 መረጃ መሠረት ለውዝ 79,947


ሄ/ር ማሳ በመሸፈን 9.8 % የቅባት ሰብሎችን ሽፋን የያዘ ሲሆን በምርት ደረጃ
1128,887 ኩ/ል ከጠቅላላው የቅባት ሰብሎች (15.76%) ድርሻ እንዳለው እና
ምርታማነቱም 14.02 ኩ/ል በሄ/ር መሆኑን መረጃው ያመለክታል ።

ለውዝ ለምግብ ምንጭነት በተለያየ መልኩ በጥሬ፣ በዘይትነት፣ በቅቤነት


እንዲሁም ለአምራቹ የገቢ ምንጭ ሆኖ ቢያገለግልም የሰብሉን ሰፊ ጠቀሜታ
በሚፈለገው መጠን መጠቀም አልተቻለም፡፡ በመሆኑም የሰብሉን የምርታመነት
እና ተደራሽነት ለማሳደግ ይህ የለው የአመራረት ፓኬጅ ተዘጋጅቷል፡፡

46
2. የፓኬጁ አስፈላጊነት

ለውዝ አምራቹ በቂ ግንዛቤ እንዲይዝ ሰብሉ የሚያስፈልገውን የጥራት ደረጃ


ተጠብቆ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን የምርታማነት እና የጥራት
ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚያስችል የአመራረት ቴክኖሎጅ ፓኬጅ በማስፈለጉ
ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚ ቀርቧል።

3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር

 ከፍታ፥ ከባህር ወለል በላይ ከ 500-1600 ሜትር ከፍታ


 የዝናብ መጠን፦ ከ 500 - 900 ሚሜ
 የአየር ሙቀት መጠን፦ ከ 24-28 ዲግሪ ሴንቲግሬድ
 የአፈር አይነት፣ የአፈሩ ጣዕም ከ 5.5- 7.3 በሆነ አነስተኛ የሸክላ

ይዘት ያለውና በቀለላሉ የሚፈረካከስ / friable/ ውሃ በማይተኛነት ቀይ


ወይም ቡናማ አፈር ጥሩ ምርት ይሰጣል።

4. የተሻሻሉ ዝርያዎች

እስከ አሁን በተደረጉ ጥናቶች ለተለያዩ ዘውዝ አብቃይ አካባቢዎች የሚስማሙ

21 ዝርያዎች ተለቀዋል፡፡ እንዚህም ዝርያዎች በሰንጠረዥ 5. ተጠቅሰዋል

47
ሰንጠረዥ5. በምርምር የተለቀቁ የለውዝ ዝርያዎች ዓይነትና ባሕሪያቸው፣

የዝርያው የተለቀቁበት የመድረሻ የዘይት መጠን ምርታማነት


ስም እ.ኤ.አ ቀናት በመቶኛ ኩ.ል/ሄ
ወረር 961 2004 127 46 26
ወረር 962 2004 128 48 21
ወረር 963 2004 128 46 22
ወረር 964 2004 128 46 22
ቡልቂ 01 2002 135 53 22
ሎጤ 2002 130 52 24
ሮቤ 1989 150 49 33
ኤን ሲ 343 1986 140 48 25
ኤን ሲ 4x 1986 140 46 31
ሹላሚዝ 1976 140-165 44-49 20-35
ፍንታ 2010 116 46 -
ማኒፒተር - 155 47 24
ሎቴ 2002 145-157 47 24

5. የአመራረት ዘዴዎች

5.1 የማሳ መረጣ

 ፍሬ የሚያፈራው የለውዝ ተክል አካል አፈር ውስጥ


በቀላሉ እንዲገባ እና ምርቱን በቀላሉ ለመሰብሰብ
የሚመረጠው ማሳ ቀላል ለም አፈር፣ አነስተኛ የሸክላ
ይዘት ያለው፣ ጎርፍና ደለል እንዳይተኛበት የመሬት
አቀማመጡ የተስተካከለ እንዲሆን ይፈለጋል፡፡
 አነስተኛ የአፈር ጥልቀት ባላቸው ማሳዎች ለውዝን
እንድናለማ አይመከርም፡፡

48
5.2 የማሳ ዝግጅት

 የለውዝ ማሳን ከ2-3 ጊዜ ደጋግሞ ማረስ ያስፈልጋል፡፡


 የመጀመሪያ እርሻ ሰብሉ እንደተሰበሰበ እና
 2ኛ እርሻ ዝናብ ጥሎ አረም ከበቀለ በኋላ እንዲከናወን
ይመከራል፡፡

5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ

5.3.1 የዘር ወቅት

የለውዝ የዘር ወቅት እነደ ሰብሉ አመራረት ሁኔታ ይወሰናል፡─

 በመኸር ወቅት ዝናብ እንደጀመረ ከግንቦት አጋማሽ እስከ ሰኔ


አጋማሽ የዘር ሥራ መከናወን ይኖርበታል፡፡
 በመስኖ በሚያለሙ አካባቢዎች ግንቦት አጋማሽ መዘራት
ይኖርበታል፡፡

5.3.2 የአዘራር ዘዴ

 የለውዝ ዘር ከመዘራቱ ከጥቂት ቀናት በፊት ፍሬውን ከገለፊቱ


በመፈልፈል ከተለየ በኋላ ለዘር የሚፈለገውን መጠን ማዘጋጀት
ይገባል፡፡ ከተፈለፈለ በኋላ ሳይዘሩ ማዘግየት የብቅለት ኃይሉን
ይቀንሳል፡፡
 ለውዝ ሲዘራ በመስመር መካከል 60 ሳ.ሜ እና በተክሎች
መካከል ደግሞ 1ዐ ሳ.ሜ ማድረግ፣

 የዘር ጥልቀቱ ከ5─7 ሳ.ሜ መሆን ይኖርበታል::

49
5.3.3 የዘር መጠን

 እንደዝርያው የፍሬ ትልቅነትና ትንሽነት የሚወሰን ሲሆን


በአማካይ ከ60-100 ኪ/ግ የተፈለፈለ ዘር ለሄክታር መጠቀም
ያስፈልጋል፡፡

5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ

 የለውዝ ሰብል ናይትሮጅንን ከአየር በመሳብ ከሚጠቀሙትና


ማሣን በማዳበር ከሚታወቁት ሰብሎች ውስጥ ስለሆነ
ተጨማሪ ማዳበሪያ መጠቀም በምርት ላይ ለውጥ
ስለማያመጣ እንዳንጠቀም ይመከራል፡፡

5.5 አረም ቁጥጥር


o መሬቱን በሚገባ በወቅቱ አለስልሶ መዝራት፣
o ሰብልን ማፈራረቅ፣
o የስብል ቃርሚያን በወቅቱ ስብስቦ ማቃጠል፣
o በእጅ በወቅቱ ማረም፡-
 1ኛ አረም ሰብሉ ከበቀለ ከ30-35 ቀናት
 2ኛ አረም ሰብሉ ከበቀለ ከ55-60 ቀናት
ባለው ጊዜ በማከናወን መከላከል ያስፈልጋል፡፡
o በሁለተኛ ዙር አረም ወቅት ኩትኳቶ
ማካሄድ እና አፈር ማስታቀፍ ያስፈልጋል፡፡

50
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር

5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር

ለውዝን የሚከተሉት በሽታዎች ያጠቁታል፡፡ የተባዮቹ ዝርርዝ እና


መከላከያ ቀጥሎ ተመልክቷል፡─
 ክሸክሽ
በባህላዊ መከላከል
o የእርሻ ቦታ ንጽህናን መጠበቅ፣
o ሰብልን እያፈራረቁ መዝራት፤
o ለተባዩ እንደ አማራጭ ምግብነት የሚያገለግሉ
ተክሎችን ቀድሞ ማስወገድ፣
በኬሚካል መከላከል:-
ተባዩ ከ30 - 40% በሚሆኑ ተክሎች ላይ ሲታይ
ከሚከተሉት ፀረ- ተባይ ኬሚካሎች ውስጥ አንዱን: -
o አክቴሊክ 50% ኢ.ሲ 0.5 ሊትር፣
o ዳይሜቶት ወይም ሮገር 40% ኢ.ሲ 1ሊትር
o ዲያዚኖን 60% ኢ.ሲ 0.5 ሊትር በሄ/ር ሂሳብ በ200
ሊትር ውሃ በርዞ መርጨት አስፈላጊ ነው፡፡

 አፍሪካ ጓይትል

በባህላዊ መከላከል (Cultural practice)

o ምርት ከተሰበሰበ በኋላ ቃርሚያውን ከማሳው ማስወገድና


በበጋ ወራት በተገቢው የእርሻ ድግግሞሽ ጠለቅ አድርጐ
በማረስ ኩብኩባውን ለፀሐይና ለሌሎች የተፈጥሮ ጠላቶች
እንዲጋለጥ ማድረግ፡፡
o ለዚህ ተባይ መራባት ምቹ የሆኑ የተለያዩ አረሞችን
ማስወገድ፣

51
o ትክክለኛ የዘር መጠንና የዘር ወቅትን ጠብቆ በአንድ አካባቢ
ያሉ አአደሮች በተመሳሳይ ጊዜ እንዲዘሩ ማድረግ ፤
o በሰብል ላይ የተከሰተው የጓይትል መጠን አነስተኛ ከሆነ
በእጅ እየለቀሙ መግደል፣

በኬሚካል መከላከ

የጓይ ትልን እድገቱ ገና ትንሽ እንደሆነ ወደ ቋቢያው ውስጥ


ሰርስረው ሳይገባ በኬሚካል መከላከል ይቻላል፡፡ከሚከተሉት
ፀረ-ተባይ ኬሚካሎች ውስጥ አንዱን ፡
o ካርባሪል 85% ደብልዩ.ፒ 1.2-1.5 ኪ/ግ፣
o ሳይፐርሜትሪን 24% ኢ.ሲ 1 ሊትር
o ሄሌራት ወይም ካራቴ 5% ኢሲ 300 ሚሊ ሊትር፣
o ፌኒትሮታዮን 50% ኢ.ሲ 1 ሊትር
o ዲያዚኖን 60% ኢ.ሲ 1 ሊትር በሄ/ር በ200 ሊትር ውሃ
በርዞ መርጨት አስፈላጊ ነው፡፡

 ምስጥን (Termite) ለመከላከል፡-

በባህላዊ መከላከል (Cultural practice) ፡-


o የሰብል ቅሪቶችን ከማሳው ላይ ቶሎ ማንሳት፣
o ሰብሉ እንደታጨደ ማሳውን ወዲያውኑ ማረስ፣
o ኩይሳውን ቆፍሮ ንግስቷን አውጥቶ መግደል፣
o በኩይሳው የተብላላ የከብት ሽንት መጨመር፣

52
በኬሚካል መከላከል፡-
ምስጥን ለመከላከል ኩይሳው ባለበት ቦታ በመቆፈርለአንድ
ኩይሳ የሚከተሉትን ኬሚካ መጠቀም ይቻላል፡፡
o ዱርስባን 48% ኢ.ሲ
o ዲያዚኖን 60% ኢ.ሲ ከ20-30 ሚሊ ሊትር ከ15-20
ሊትር ውሃ እየበረዙ መጨመር፣

5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር

ለውዝ ቀጥሎ የተጠቀሱ በሽታዎች ያጠቁታል፡፡ በሽታዎቹ እና


መከላከለያው
 ዋግና የቅጠል ጠቃጠቆ
በሽታውን ለመከላከል፤
o የተሻሻሉ ዝርያዎችን መጠቀም
o ሰብልን አፈራርቆ መዝራት
o የቅጠል ጠቃጠቆን ለመከላከል ቃርሚያን መሰብሰብና ማቃጠል
ወይም መቅበር፣
o ከተሰበስበው ስብል ቢጫ ሻጋታ ሲታይ እየለቀሙ አውጥቶ

መጣል፡፡

o ሻጋታ/ አስፐርጊለስ/-አፍላቶክሲን የተባለውን መርዛማ ኬሚካል

የሚያስከትል በሽታ ነው።

በሽታውን ለመከላከል፤

ይህንን በሽታ ለመቆጣጠር ሰብሉ እንደደረሰ መሰብሰብና ዝናብ ሳይነካው

አድርቆ እርጥበት በሌለበት ቦታ ማከማቸት ያስፈልጋል፣

53
 የሥርና የጭንቅላት አበስብስ

o የተሻሻሉ ዝርያዎችን መጠቀም


o ሰብልን አፈራርቆ መዝራት

54
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ድህረ ምርት አያያዝ

5.7.1 አጨዳ / ነቀላ

 ለውዝ ዘር ከተዘራ ከ 120 እስከ 150 ቀናት ውስጥ ለነቀላ


ይደርሳል
 የለውዝ ተክል መድረሱን ለማረጋገጥ ስር ካሉት የዘር ከረጢቶች
አንድ ወይም ሁለት በመውሰድ መክፈትና የውስጠኛው የከረጢት
ክፍል ወደ ቡናማ መልክ መቀየሩን በማየት ለነቀላ መድረሱን
ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡

5.7.2 መሰብሰብ እና ማድረቅ

 ሰብሉ ለመሰብሰብ መድረሱ ከተረጋገጠ በኋላ በበሬ በማረስ፣


በፎርክ ወይም በመቆፈሪያ በእጅ በመቆፈር ማውጣት
 በፀሐይ በደንብ ማድርቅ የዘር እርጥበቱ

5.7.3 መፈልፈል

 ከአንደ ወር በላይ የሚከማች ከሆነ ሳይፈለፈል ቢቆይ ከተባይ


ጥቃት ይድናል።

5.3.2 ማጓጓዝ እና ክምችት

 ንፁህ በሆነ ጆንያ በመሰብሰብ እርጥበት በሌለበት ክፍል ማከማቸት


ያስፈልጋል፡፡
 እርጥበት በበዛበት ማከማቻ ውስጥ የሚፈጠር ሻጋታ ሲሆን
አፍላቶክሲን የተባለውን መርዛማ ኬሚካል የሚያስከትል በሽታ
ነው።

55
5.4 የሰብሉ አመራረት ስርዓት

 ለውዝ እንደዋና ሰብል ሆኖ ብቻውን ቢዘራም የበሽታ፣ አረም እና ነፍሳተ


ተባይ መስፋፋትን ለመቆጣጠር የሰብል ፈረቃ ማጠቀም ተገቢ ነው፡፡
o ለውዝ ─ ማሽላ
o ለውዝ ─ ሰሊጥ
 ለውዝ ከማሽላ ጋር በስብጥር መዝራት ይቻላል፡፡
 ለውዝን ከአኩሪአተር ቀጥሎ መዝራት አይቻልም፡፡ ምክንያቱም በሽታ
ሊተላለፍ ስለሚችል፡፡

5.8 የምርት አዋጭነት

 የጉልበት ወጪን በዝርዝር አሳይ፤


 ለግብዓት ግዥ የወጣውን ወጪ በዝርዝር አስቀምጥ፤
 በምርት ትመና አርሶአደሩ ያገኘውን ምርት በሄ/ር መመዝግብ፤
 ተረፈ ምርቱ ያወጣውን ዋጋ በብር አመልክት፤
 የምርቱን ሆነ ተረፈ ምርቱን ጠቅላላ ሽያጭ አሳይ፤
 ጠቅላላ ወጪን ደምር፤
 ጠቅላላ ገቢውን ደምር፤
 ገቢውን ለወጪው አካፍል፤
 በማካፈል የተገኘው ውጤት ሁለት እና ከሁለት በላይ ከሆነ ለውዝ
ማምረት አዋጪ ነው፡፡

56
የፈረንጅ ሱፍ (Heliantus annuus L.)

. 1. መግቢያ

የፈረንጅ ሱፍ መሰረቱ ከሰሜን አሜሪካ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በፊው


ከሚመረትባቸው አገሮች አንዱ ሩሲያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሰብሉ ከገባ ከመቶ
ሃምሳ ዓመት በላይ ቢያስቆጥርም በምግብ ሰብልነቱ ሳይሆን በአበባነቱ
(ornamental) ለማስጌጫ እንደነበር ይነገራል፡፡ ሆኖም ግን የፈረንጅ ሱፍ
በአለም ደረጃ ለምግብ ዘይት ከፍተኛ ተፈላጊ ሰብል ሲሆን በአገራችንም ሰብሉን
ለማምረት ሰፊ ተስማሚ ስነ ምህዳር እንዳለው በጥናት ተረጋግጧል፡፡ የፈረንጅ
ሱፍ ቀደም ሲል በአምራቾች በተለይም በመንግስት አርሻዎች ከሰባዎቹ መጨረሻ
ጀምሮ በስፋት መርት ላይ ቢውልም በሰማኒያዎቹ በተከሰተው የአበስብስ በሽታ
(root rot , head rot and stem rot) ምክንያት ሰብሉን በቀጣይነግ ማምረት አልቻሉም
፡፡

በአሁኑ ጊዜ በአገራችን ያለውን የምግብ ዘይት ፍላጎት ለማዳረስ በዋናነት


ከምንጠቀምባቸው ሰብሎች ኑግ እና ተልባ አማራጭነት ተወስዶ ቢመረት ያለውን
የምግብ ዘይት ክፍተት በሞሙላት ሰብሉ ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል፡፡
በተጨማሪም ሰብሉ ካለው ከፍተኛ የዘይት ይዘት እና የምርት አቅም እንዲሁም
በዓለም ላይ ካለው ከፍተኛ ተፈላጊነት አንጻር ሰብሉን በተሻሻለ የአመራረት ዘዴ
ተመርቶ አምራቹ ተጠቃሚ እነዲሆን ይህ የአመራረት ፓኬጅ ተዘጋጅቷል፡፡

57
4. የፓኬጁ አስፈላጊነት

 የተሻሻለ የፈረንጅ ሱፍ አመራረትና አያያዝ ዘዴን በአምራቹ ዘንድ


ግንዛቤ በማሳደግ አምራቹን በሰፊው የፈረንጅ ሱፍ እንዲያለማ እና
ከሰብሉ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ፡፡

5. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር

 ከፍታ፥ ከባህር ወለል በላይ ከ 1200-2400 ሜትር ከፍታ


 የዝናብ መጠን፦ ከ500-750 ሚሜ
 የአየር ሙቀት መጠን፦ ከ16-23 ዲግሪ ሴንቲግሬድ
 የአፈር አይነት፣ የአፈሩ ጣዕም ከ 6.0 እስከ 7.3፣ ሸክላማ ለም

አፈር ቡናማ እና ጥቁር አፈር ጥሩ ምርት ይሰጣል።

6. የተሻሻሉ ዝርያዎች

የፈረንጅ ሱፍ ምርምር በስልሳዎቹ አጋማሽ የተጀመረ ቢሆንም በተላየዩ


ምክንያቶች አጥጋቢ እንዳልነበረ ይታወቃል ፡፡ እስከ አሁን 11 ያህል ዲቃላ
ዝርያዎች ምርምር የበማላመድ የተመዘገቡ ሲሆን ዲቃላ ካልሆኑ ዝርያ ውስጥ
በምርት የሚገኘው ኦይሳ NSH ─25 ብቻ ነው፡፡

58
\N-r™ 2. bMRT §Y Ãl# ytššl# yfrNJ s#F ZRÃãCÂ
yxGéñ¸ ÆH¶ÃcW

ተ.ቁ የዝርያ ሥም የተለቀቀበት የምርት የዘይት


/የተመዘገበበት መጠን መጠን %
ዓ/ም ኩ/ሄ
1 ካሜራ 2 2014 20─25 42.5

2 ኤን ኤል ኤን 11037 2014 17─ 20 40.4

3 ቪ ሴንዞ 2014 17─ 20 38.7

4 ኤክስ 6859 2014 21─ 25 38.0

5 ሃይሰን 33 2013 25─ 30 45.0

6 ኤን ኤፍ ደልፊ 2012 17.6 44.0

7 ኒዎማ 2012 19.4 46

8 ቪኤስኤፍ ኤች 2074 2012 18 37─40

9 ቪኤስኤፍ ኤች 1006 2012 21 37─40

10 ካዛኖቫ 2011 31 48─51

11 ኤንኤስኤች ─45 2011 18 45─50

12 ኤንኤስኤች ─111 2011 19 48─50

13 ኦይሳ / NSH ─25 2005 18.10 41─45

59
7. የአመራረት ዘዴዎች

5.1 ማሳ መረጣ

 ውሃ የማይተኛበት፣ በጣም ተዳፋታማ ያልሆነ ከአረም የፀዳ ማሳ


ያስፈልገዋል፡፡

5.2 የማሳ ዝግጅት

 ሦስት ጊዜ የታረሰ ከአረም የጸዳ ማሳ መሆን አለበት፡፡


o የመጀመሪያው እርሻ ከግንቦት በፊት በሚጥለው ዝናብ
ተመስርቶ ማካሄድ፣
o ሁለተኛው እርሻ አረምን ለማጥፋት በግንቦት ወር፣
o ሦስተኛው እርሻ በዘር ወቅት መከናወን ይኖርበታል፡፡

5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ

5.3.1 የዘር ወቅት

 የዘር ወቅት ከቦታ ቦታ የሚለያይ ቢሆንም በአብዛው ከሰኔ


መጀመሪያ እስከ ሐምሌ አጋማሽ ይዘራል፡፡

5.3.2 የአዘራር ዘዴ

 የፈረንጅ ሱፍ ሲዘራ በመስመር መካከል 75 ሳ.ሜ ርቀት ሲኖረው


በተክሎች መካከል ደግሞ 25 ሳ.ሜ ርቀት መሆን አለበት፡፡

 የዘር ጥልቀቱ ከ 4─6 ሳ.ሜ መሆን አለበት

60
5.3.3 የዘር መጠን

 የፈረንጅ ሱፍ የዘር መጠን ከ 8─12 ኪ.ግ በሄክታር መሆን አለበት

5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ

 በአዋሳና ደብረዘይት በተደረገ የፈረንጅ ሱፍ የማዳበሪያ ፍላጎት


ጥናት መሠረት ሰብሉ ለናይትሮጅን እና ፎስፈረስ ማዳበሪያ ያለው ምላሽ
በምርታማነቱ ላይ የሚያመጣው ለውጥ ያለማዳበሪያ ከተዘራው ጋር
ሲነጻጸር አናሳ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

5.5 አረም ቁጥጥር

 የፈረንጅ ሱፍ በቡቃያነቱ ዘገምተኛ ስለሆነና በቀላሉ በአረም ሰለሚጠቃ


በመጀመሪያዎቹ 2 እና 3 ሳምንት ከበቀለ በኋላ መታረም አለበት፡፡
 እንዳስፈላጊነቱ ሁለተኛ አረም በዘብሉ ቡቃያነት መታረም አለበት፡፡
 የፈረንጅ ሱፍን ኦሮባንኬ የተባለ ጥገኛ አረም ያጠቃዋል ይህንን አረም
ለመከላከል
o አረሙ ከማበቡ በፊት ከሥር ነቅሎ ማቃጠል ወይንም
መቅበር ያስፈልጋል፡፡

o ማሳን አርሶ የአረሙን ሥር ለፀሐይ ማጋለጥ

o ተጓዳኝ አረሞችን ማስወገድ

 ማሳን ማፈራረቅ

61
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር

5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር

 የፈረንጅ ሱፍ ከሚያጠቁት ተባዮች ውስጥ የአሜሪካ የጓይ ትል እና


ምስጥ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ፡፡
 የጓይ ትሉን ለመከላክል፡─
o ትሉ አነስተኛ ከሆነ መልቀም፣
o ትሉ ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ ካርባሪል/ሴቪን 85%
WP ከ2-2.5 ኪ.ግ በሄክታር ወይም ዱርባን 38% EC
ከ2-2.5 ሊትር/ሄ በ200 ሊትር ውሃ በጥብጦ
መርጨት፡፡
 ምስጥ በአፈር ውስጥ የሚፈጠር ሲሆን የሰብሉነ ስር በመብላት
ግንዱ እንዲወድቅ ያደርጋል፡፡ ይህንንም ነፍሳተ ተባይ ለመከላከል፡─
o ድሩስባን 40% EC ከ 20 30 ሚ.ሊ ከ 15─20 ውሃ

እየጨመሩ ምስጡን መቆጣጠር ይቻላል

5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር

ከዋና ዋናዎቹ የፈረንጅ ሱፍ የፈረንጅ ሱፍ በሽታዎች ተክል አቆርምድ


/ዳዊኒ ሚልዲው/፣ የጭንቅላት እና ግንድ አበስብስ ፣ አጠቅልግ ፣
አመዳይ /ፓውደሪ ሚልዲው/ እና ዋግ /ረስት/ ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህን
በሽታዎች ለመከላከል፡─

 በሽታውን የሚቋቋሙ ዝርያዎች መጠቀም


 ከበሽታው ነጻ የሆነ ዘር መጠቀም
 ሰብሉን በፈረቃ መዝራት
 የሰብሉን ቅሪቶች ከማሳ ማስወገድ እና ለጸሐይ እነዲጋለጡ

ማድረግ

62
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ

5.7.1 አጨዳ

 የሰብሉ ትክክለኛ የአጨዳ ወቅት የሚባለው ፍሬ አዘሉ ጭንቅላት


ከበስተጀርባ በኩል ያለው አካለሉ ከአረንጓዴነት ወደ ቢጫነት
ሲለወጥና በራሱ ዙሪያ ያለው ቅርፊት /Bract/ ወደ ቡኒነት ሲለውጥ
ነው፡፡
 በዚህ ጊዜ ጭንቅላቱ አቅራቢያ በመቁረጥ ይሰበሰባል፡፡

5.6.2 ማድረቅ

 የተቆረጠውን ሱፍ ጸሐይ ላይ ማስጣት እና የዘሩ እርጥበት ከ


9% በታች እስኪሆን ማድረቅ ያስፈልጋል፡፡

5.6.3 ውቂያ/መፈልፈል

 የፈረንጅ ሱፍ በባህላዊ ዘዴ ሲፈለፈል በአጅ በማሸት ምርቱ


ከግርዱ ይለያል

5.6.4 ክምችት እና ማጓጓዝ

 የፈረንጅ ሱፍ ከተወቃ በኋላ በንጹህ በሆነ ማዳበሪያ ወይም


የማጠራቀሚያ በርመወል ሊቀመት ይችላል「፡፡
 የተጠራቀመበት እቃ በአግባቡ መከደን እና የሚጠራቀምበት ስፍራ
በአየር መናፈስ አለበት፡፡
 የፈረንጅ ሱፍ ከተወቃ በኋላ የዘር እርጥበቱ ከ 8% በታች ሲሆን
በንፁህ ደረቅና ነፋሻ በሆነ ስፍራ ይከማቻል፡፡
 ዘሩን ለማጓጓዝ ከተፈለገ ንጹህ ፣ ርጥበት በሌለበት መጓጓዣ
መሆን አለበት

5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት

 የፈረንጅ ሱፍ ከበቆሎ፣ ለማሽላ ጋር በስብጥር ይዘራል፡፡


 የፈረንጅ ሱፍ ብቻውን ቢዘራም ለበሽታ ቁጥጥር አንዲሁም
አረምን ለመከላከል እንዲረዳ ከሎሎች ሰብሎች ጋር በፈረቃ ሊዘራ
ይችላል፡፡

63
o የፈረንጅ ሱፍ ─ ማሽላ
o የፈረንጅ ሱፍ ─ አኩሪ አተር

5.9 የምርት አዋጭነት


 የጉልበት ወጪን በዝርዝር አሳይ፤
 ለግብዓት ግዥ የወጣውን ወጪ በዝርዝር አስቀምጥ፤
 በምርት ትመና አርሶአደሩ ያገኘውን ምርት በሄ/ር መመዝግብ፤
 ተረፈ ምርቱ ያወጣውን ዋጋ በብር አመልክት፤
 የምርቱን ሆነ ተረፈ ምርቱን ጠቅላላ ሽያጭ አሳይ፤
 ጠቅላላ ወጪን ደምር፤
 ጠቅላላ ገቢውን ደምር፤
 ገቢውን ለወጪው አካፍል፤
 በማካፈል የተገኘው ውጤት ሁለት እና ከሁለት በላይ ከሆነ
የፈረንጅ ሱፍ ማምረት አዋጪ ነው፡፡

64
የአበሻ ሱፍ (Safflower: Carthamus tinctorius L.)

1. መግቢያ

የአበሻ ሱፍ ለብዙ ዘመናት በኢትዮጵያ ገበሬወች እጅ እንደነበረ ይታወቃል፡፡


ምናልበትም የአበሻ ሱፍ ስያሜ የመጣው ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሰብሉ መገኛ
ማእከል (center of origin) ትሆናለች የሚባለውን ግምት ከፍ ከማድረጉም በላፈ
የሰብሉ በርካታ ዝርያዎች መገኛ (center of diversity) እንደሆነች ብዙዎች
ዘገባዎች ያረጋግጣሉ ፡፡

እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክ ባለስልጣን በ2005/6 መረጃ መሠረት በአገራችን


የአበሻ ሱፍ በ11526 ሄ/ር መሬት ተዘሬቶ 83470 ኩ/ል ምርት ተገኝቷል፡፡
ይህ በአበሻ ሱፍ የተሸፈነ መሬት ከጠቅላላው የቅባት ሰብል 5.39 % ድርሻ
ስይዝ፤ በሄክታር በአማካይ ምርታማነቱም 7.24 ኩ/ል በሄ/ር እንደሆነ ያሳያል፡፡

የአበሻ ሱፍ ጠቀሜታው ለምግብነት፣ ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃነት፣ ለቀለም ስራ፤


ለቫርኒሽ፣ ለሳሙና ለመኖነት እንደሚውል ይታወቃል፡፡

የአበሻ ሱፍ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ለአለም ገበያ ከነበረው በተሻለ ምርት


ለማቅረብ እንዲቻልና በገበያ ተወዳዳሪ በመሆን በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ተገቢውን
አዎንታዊ ተፅእኖ ከማስመዝገብ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ
የመጣውን የምግብ ዘይት ፍላጎት ምላሽ መስጠት ወቅታዊ ጉዳይ ሆኖ በመገኘቱ
የሰብሉን የአመራረት ዘዴን ተግባራዊ ለማድረግ ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅተዋል።

65
2. የፓኬጁ አስፈላጊነት

አበሻ ሱፍ የሚያስፈልገውን የጥራት ደረጃ በመያዝ በአለም ገበያ ተወዳዳሪ


እንዲሆን የምርታማነት እና የጥራት ማነቆዎችን ለመቅረፍ የሚያስችል
የአመራረት ቴክኖሎጅ ፓኬጅ በማስፈለጉ ይህ ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ለተጠቃሚ
ቀርቧል።

3. የሰብሉ ተስማሚ ስነ-ምህዳር

 ከፍታ፥ ከ1650-1930 ሜትር ከፍታ ከባህር ጠለል በላይ የሆነ


 የዝናብ መጠን፦ ከ500-750 ሚሜ
 የአየር ሙቀት መጠን፦ ከ20-28 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሆነ
 የአፈር አይነት፣ የአፈር ጣዕሙ ከ5-8 ፒኤቼ ያለው ጥቁር አፈር የሆነ፡፡

4. የተሻሻሉ ዝርያዎች
የአበሻ ሱፍ ምርምር በወረር ግብርና ምርምር ሲካሄድ በነበረበት ጊዜ ተስፋ ሰጪ
ዝርያዎች ቢኖሩም በአሁኑ ሰዓት በምርት ላይ የሚገኙ የሚገኘው ቱርካና የተባለ
እሾሃማ ያልሆነ ዝርያ ነው፡፡ የዝርያው ምርታማነት፣ የዘይት መጠን እንዲሁም
ሌሎች ባህሪያት ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

 ቱርካና

 የተለቀቀበት ዓ/ም 2011

 የሚደርስበት ቀን 145

 የምርት መጠን/ ኩ.ል/ 11.3

 የዘይት መጠን /%/ 26─30

 ለዩ ባህሪ እሾሃማ ያልሆነ

66
5. የአመራረት ዘዴዎች

5.1 ማሳ መረጣ

 አበሻ ሱፍ ለማልማት ቦታው ባለፉት 3-4 ዓመታት ሰብሉ ያልለማበት


ቢሆን ይመረጣል፡፡ ይህም በሽታና ተባዮች ሊያደርሱበት የሚችሉትን
ጉዳት ለመቀነስ ሲሆን ማሳው የተስተካከለ እና ሰብሉን ለማልማት
የተመቻቸ መሆን አለበት፡፡

5.2 የማሳ ዝግጅት

 እርሻው አንድ ጊዜ ጠለቅ ኣድርጎ ማረስ


 ከ2-3 ጊዜ አለስልሶ ማረስ
 ከአረም የፀዳ እንዲሆን ማድረግ ይገባል፡፡

5.3 የዘር ወቅት እና የአዘራር ዘዴ

5.3.1 የዘር ወቅት

 የአበሻ ሱፍ ከሰኔ መጨረሻ እስከ ሐምሌ አጋማሽ ባለው ጊዜ ይዘራል፡፡


 ከሐምሌ አጋማሽ በኃላ ዘግይቶ መዝራት ሰብሉን ለተለያዩ በሽታዎች እና
ለውርጭ ስለሚያጋልጠው ምርት በመጠንና በጥራት እንዲቀንስ
ያደርጋል፡፡

67
5.3.2 የአዘራር ዘዴ

 የመስመር አዘራሩ በተክሎች መካከል ከ25 ሳንቲ ሜትር ሲሆን


በመስመር መካከል ያለው ርቀት 45 ሳንቲ ሜትር ነው፡፡
 የዘር ጥልቀቱ ከ2-3 ሳንቲ ሜትር ይሆናል፡፡

5.3.3 የዘር መጠን

 የአበሻ ሱፍ በመስመር ለመዝራት 20 ኪሎግራም ዘር በሄክታር


ያስፈልጋል፡፡

5.4 የማዳበሪያ መጠንና አጠቃቀሙ

 የአፈሩን ለምነት ይዘት በመመርኮዝ ለምነቱን ለማሻሻል በሚጎድለው


የፎስፎረስ እና ናይትሮጂን መጠን ልክ የእነዚህን ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ
ለተክሉ መስጠት ይበልጥ የምርት አቅሙን ያሳድጋል፡፡ አነስተኛ ለሆነ
መሬት 100 ኪሎግራም ዩሪያ እና 100 ኪሎግራም ዳፕ እናበዘር
ወቅት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

5.5 አረም ቁጥጥር

 የአበሻ ሱፍ በአረም በቀላሉ ይጠቃል በመሆኑም ወቅቱን ጠብቆ


ደጋግሞ ማረም ያስፈልጋል::
 ቀድሞ መዝራት ሰብሉ ሊደርስበት የሚችለውን የአረም ጉዳት
ለመቋቋም ይረዳዋል፡፡
 ሰብሉ ከተዘራ ከ18-20 ሳምንት ባለው ጊዜ የመጀመሪያ አረማ
ማካሄድ ያስፈልጋል፡፡
 ሁለተኛው አረም ደግሞ ከተዘራ ከ35-40 ቀናት ባለው ጊዜ ማረም
ይገባል፡፡

68
5.6 ነፍሳተ ተባይ እና በሽታ ቁጥጥር

5.6.1 ነፍሳተ ተባይ ቁጥጥር

 አንበጣ፣ተምችና ቆራጭ ትልና ኤፍዲስ የመሳሰሉት ተባዮች


የአበሻ ሱፍን ከማቀጨጫቸው በተጨማሪ ምርትና ምርታማነት
ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስለሚደርሱ ተገቢው የመከላከል እርምጃ
በወቅቱ ሊወሰድ ይገባል፡፡

መከላከያ ዘዴ

 የእርሻ ቦታ ንጽህናን መጠበቅ፣


 ሰብልን እያፈራረቁ መዝራት፤
 ለተባዩ እንደ አማራጭ ምግብነት የሚያገለግሉ ተክሎችን
ቀድሞ ማስወገድ፣

5.6.2 የበሽታ ቁጥጥር

 ከመደበኛው ወቅት የበለጠ የዝናብና የርጥበት መጠን የአበሻ ሱፍ


በአልተርናአሪያ ሊፍ ስፖትና ሲዶሞናስ ባክተሪል ብላይት በሽታ
እንዲጠቃ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
መከላከያ ዘዴ
 በሽታውን የሚቋቋም ዝርያ መጠቀም እና

69
5.7 ምርት አሰባሰብ እና ደህረ ምርት አያያዝ

5.7.1 አጨዳ

 የአበሻ ሱፍ ከአበበ ከአንድ ወር በኋላ የሚደርስ


ሲሆን(physiologically mature) ለመሰብሰብ ቅጠሎቹ ወደ ሙሉ
ቢጫነት ሲለወጥ በሱፍ ፍሬ መጨረሻ ላይ የሚገኙ አበባ መሣይ
ነገሮች ሲደርቁና ፍሬዎቹን ወስዶ በጥፍር በመጫን በቀላሉ
የማይጠረመስ ከሆነ ሰብል ለአጨዳ መድረሱን ያረጋግጣል፡፡
 የርጥበት መጠን 12 በመቶ ሲሆን

5.7.2 ማድረቅ

 የተቆረጠውን ሱፍ ጸሐይ ላይ ማስጣት እና የዘሩ እርጥበት ከ


9% በታች እስኪሆን ማድረቅ ያስፈልጋል፡፡

5.7.3 ውቂያ ማማ ማማማማ

 ከሲሚንቶ በተሰራ ኣዉድማ ላይ ወይም ሻራ በማንጠፍ ማራገፍ

 የተራገፈዉን አበሻ ሱፍ 99% ንፁህ እስኪሆን ድረስ ማበጠር

 በንፁ ጆንያ ወይም ማዳበሪያ መሙላት

5.7.4 ማጓጓዝ እና ክምችት

 የአበሻ ሱፍ ምርትን ለማጓጓዝ ከኬሚካል ወይም ቅባቶች ንክኪ


የፀዳ እና እርጥበት የሌለው የማጓጓዝያ መሳሪያ መጠቀም
ያስፈልጋል።
 አየር በሚገኝበትና ሊታፈግ በማይችልበት ቦታ ቢቀመጥ
ይመረጣል፣
 በሚከማችበት ጊዜ የዘሩ እርጥበት መጠን ከ5.8% መሆን አለበት፣
 በሲሚንቶ የተሰራ ወለል ወይም ንጹህ አሸዋ በመነስነስ የተባይ
መግቢያ ቀዳዳዎችን መድፈን ያስፈልጋል
 ጆንያ ሲደረደር በ2 ድርዳሮ መካከል 2ሜ ክፍተት መኖር አለበት

70
5.8 የሰብሉ አመራረት ስርዓት

 የአበሻ ሱፍን ከአመታዊ የጥራጥሬና የብርእ ሰብሎችጋር አፈራርቆ


መዝራት ምርትን ይጨምራል።
 የአበሹ ሱፍ- ጤፍ
 የአበሻ ሱፍ- ምስር
 የአበሻ ሱፍን በኋይት ሞልድ በሽታ ከሚጠቁ ሰብሎች ምሳሌ
አተር፣ የፈረንጅ ሱፍ፣ ጎመንዘርና የመሳሰሉት ሰብሎች በቅርብ
በተዘራ ማሳ ላይ እንዲዘራ አይመከርም።

5.9 የምርት አዋጭነት

 የጉልበት ወጪን በዝርዝር አሳይ፤


 ለግብዓት ግዥ የወጣውን ወጪ በዝርዝር አስቀምጥ፤
 በምርት ትመና አርሶአደሩ ያገኘውን ምርት በሄ/ር መመዝግብ፤
 ተረፈ ምርቱ ያወጣውን ዋጋ በብር አመልክት፤
 የምርቱን ሆነ ተረፈ ምርቱን ጠቅላላ ሽያጭ አሳይ፤
 ጠቅላላ ወጪን ደምር፤
 ጠቅላላ ገቢውን ደምር፤
 ገቢውን ለወጪው አካፍል፤
 በማካፈል የተገኘው ውጤት ሁለት እና ከሁለት በላይ ከሆነ የፈረንጅ
ሱፍ ማምረት አዋጪ ነው፡፡

71
72

You might also like