You are on page 1of 69

የዉሀ አቅርቦት አገልግሎቶች

የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር --- / 2013


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ማዉጫ

መግቢያ.......................................................................................................................................................... 1

ጠቅላላ ድንጋጌዎች ....................................................................................................................................... 2

አጭር ርዕስ ................................................................................................................................................ 2

ትርጓሜ ...................................................................................................................................................... 2

የተፈፃሚነት ወሰን ..................................................................................................................................... 6

አዲስ የውሃ ቅጥያ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያላባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ................................... 6

1. የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደንበኞች ................................................................................................ 6

2. የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸዉ /ሰነድ አልባ እና አርሶ አደር ደንበኞች .............................................. 7

3. የእምነት ተቋም የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደንበኞች ..................................................................... 8

4. የከተማ መስተዳድሩ (የመንግስት) ቤት ተከራይ የሆኑ ደምበኞች ................................................... 8

5. የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤት ተከራይ የሆኑ ደምበኞች ............................................................ 9

6. በቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበር ስም አገልግሎቱን የሚጠይቁ ደምበኞች ................................. 9

7. የቤት ስራ ህብረት ስራ ማህበር ሽንሻኖ የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደንበኞች ............................. 10

8. በቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበራት በኮንዲሚኒየም መልክ የተሰሩ ቤቶች ደንበኞች ................ 11

9. በግለሰቦች ፤በሽርክና ማህበር ወይም በኃላፊነቱ የተ/አ/ማ የተሰሩ ቤቶች ደንበኞች ...................... 12

10. የሪል እስቴት ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደምበኞች ............................................................. 13

11. የኮንዲሚንየም ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደምበኞች ........................................................... 14

12. የማምረቻ ሼዶች ወይም መሸጫ ማዕከል ደምበኞች ...................................................................... 14

የቦኖ ዉሀ እና የጋራ የዉሀ መጠቀሚያ አገልግሎት ................................................................................ 15

1. የቦኖ ውሃ እና የጋራ የውሃ መጠቀሚያ አገልግሎት መስጠት የሚቻልባቸው ምክንያቶች፡- ...... 15

2. ለቦኖ ውሃና ለጋራ የውሃ መጠቀሚያ አገልግሎት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች .... 15

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

የጋራ መስመር ዝርጋታ ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ ............................................................................ 16

የማሻሻያ እና የማዛወሪያ አገልግሎት አፈፃፀም .......................................................................................... 17

1. የማሻሻያ አገልግሎት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ ...................................................................... 17

2. የማዛወሪያ አገልግሎት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ ................................................................... 18

2.1 በደንበኛዉ ጥያቄ የሚከናወን የማዛወሪያ አገልግሎት .................................................................... 18

2.2 በተቋሙ ተነሳሽነት የሚከናወን የማዛወሪያ አገልግሎት ................................................................ 19

2.3 በመሰረተ ልማት ግንባታ ምክንያት የሚከናወን የማዛወሪያ አገልግሎት ...................................... 19

የሥም ለውጥ አገልግሎት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ ........................................................................ 20

1. ከግዥ/ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚቀርብ የስም ለዉጥ አገልግሎት ጥያቄ........................................ 20

2. በውርስ ፣በስጦታ እና በፍርድ ቤት ክርክር የሚቀርብ የስም ለዉጥ ጥያቄ ................................. 20

3. በመንግሥት ተቋማት፤በኃ/የተ/የግል ማ. እና በአክሲዮን የሚቀርብ የስም ለዉጥ ጥያቄ ............ 21

የውል(የተያያዘ ማስረጃ) ኮፒ ይሰጠኝ/ይያያዝልኝ/ማስረጃ ይጻፍልኝ ጥያቄ የሚስተናገድበት አግባብ ...... 21

1. የውል (የተያያዘ ማስረጃ) ኮፒ ይሰጠኝ/ይያያዝልኝ ጥያቄ የሚስተናገድበት አግባብ ...................... 21

2. ከባለስልጣኑ ጋር ውል ያላቸው ክሊራንስ የሚጠይቁ ደምበኞች የሚስተናገዱበት አግባብ ........... 21

3. ከተቋሙ ጋር ዉል የሌላቸው ክሊራንስ የሚጠይቁ ደንበኞች የሚስተናገዱበት አግባብ ............... 22

የደንበኞች ዉል መዝገብ ቤት ፋይል አያያዝና አጠቃቀም ........................................................................ 22

የማመልከቻ ቅጽ ስለመሙላትና ክፍያ ስለመፈጸም .................................................................................. 24

የውሃ ቆጣሪ ንባብ፣ የገቢ አሰባሰብና ውዝፍ ክትትል ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ .............................. 25

1. የቆጣሪ ንባብ ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ ................................................................................... 25

2. የገቢ አሰባሰብና ውዝፍ ክትትል ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ .................................................... 26

የሒሳብ እርማት እና ክፍያ አፈጻጸም ተግባራዊ የሚደረግበት አግባብ ..................................................... 27

1. የሒሳብ እርማት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ ፡- ........................................................................ 28

2. በቆጣሪ ንባብ ስህተት መነሻነት የሚደረግ የሂሳብ እርማት ........................................................... 29

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

3. በቆጣሪው ምርመራ ውጤት መነሻነት የሚደረግ የሂሳብ እርማት ፡- ........................................... 32

4. በየጊዜው የቆጣሪ ንባብ ባለመወሰዱ ምክንያት የብዙ ወራት ክፍያ ተጠራቅሞ የተጋነነ ሂሳብ

በመጠየቁ ምክንያት የሚደረግ የሂሳብ እርማት .............................................................................. 38

5. የደንበኞች ክፍያ ምድብ (category) ትክክል ባለመሆኑ የሚደረግ የሂሳብ እርማት .................... 39

6. ቆጣሪው ሮቢሾ በመገጠሙ ምክንያት የሚከናወን የሂሳብ እርማት .............................................. 43

6.1 ለምርመራ የተነሳ እና ተመልሶ በስህተት ሮቢሾ ከተገጠመ .................................................. 43

6.2 አዲስ ቆጣሪ ሮቢሾ ከተገጠመ ................................................................................................. 44

6.3 በሕገ ወጥ መንገድ ሮቢሾ የተገጠመ ቆጣሪ፡- ........................................................................ 45

7. ከቆጣሪ በፊት ሕገወጥ ቅጥያ በመፈፀሙ የሚደረግ የሂሳብ እርማት ........................................... 47

8. በቆጣሪ ምርመራም ሆነ ንባብ ላይ ስህተት ሳይገኝ ክፍያቸው እጅግ በጣም የተጋነነ ሆኖ

በመገኘቱ የሚደረግ የሂሳብ እርማት ............................................................................................... 48

9. ደንበኛው ውል ፈፅሞ ቆጣሪ ከተቀጠለ በኋላ ወደ ክፍያ ስርዓት ውስጥ ሳይገባ በቆጣሪዉ ላይ

አደጋ ቢደርስ፤ቢሰረቅ፤ደንበኛዉ ሆን ብሎ ቢሰዉረው ፤በተጨማሪም አንባቢው አንብቦት

የማያውቅ ከሆነ እና የመሳሰሉት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት ፡-............................................... 49

10. አማካኝ ፍጆታ አከፋፈልን በተመለከተ ፡- ....................................................................................... 50

11. በተለያየ ምክንያት ሒሳባቸውን ያልዘጉ ደንበኞችን በተመለከተ .................................................... 52

11.1 የደንበኞች ቆጣሪ ተነስቶ ገቢ ከሆነ......................................................................................... 53

11.2 የደንበኛው ቆጣሪ በተለያየ ምክንያት ገቢ ሳይሆን ሲቀር....................................................... 53

11.3 የደንበኛው ቤት በልማት ወይም በተለያየ ምክንያት ፈርሶ ቆጣሪው ገቢ ሳይሆን ሲቀር ፡- 54

የክፍያ ጊዜ ስለማራዘም .............................................................................................................................. 55

ቆጣሪ ለምርመራ ማንሳት እና መልሶ መቀጠል ........................................................................................ 56

1. በተለያዩ ምክንያታዊ ኮዶች ለምርመራ የሚነሱ ......................................................................... 56

2. ደንበኛው በሂሳብ በዛብኝ ጥያቄ መስመር እና ቆጣሪ እንዲመረመር ሲጠይቅ ............................... 56

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ቆጣሪ በዕዳ ማንሳት እና መልሶ መቀጠል ................................................................................................. 57

የተከለከሉ ተግባራት.................................................................................................................................... 58

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ................................................................................................................................... 59

መመሪያውን በግልጽ ስለማሳወቅ ............................................................................................................... 59

የመተባበር ግዴታና ኃላፊነት ...................................................................................................................... 60

1. የመተባበር ግዴታ ............................................................................................................................ 60

2. የደንበኞች ግዴታና ኃላፊነት ........................................................................................................... 60

3. ቅሬታ የማቅረብ መብት................................................................................................................... 60

ተጠያቂነት ................................................................................................................................................... 61

ቅጣት ........................................................................................................................................................... 61

ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ............................................................................................................ 62

መመሪያው ስለሚሻሸልበት ሁኔታ.............................................................................................................. 62

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

መግቢያ

በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ

ስራ ከጀመረበት ወዲህ ባሉት ጥቂት አመታት ዉስጥ ተገልጋዩን ማህበረሰብ በተሻለ ደረጃ

ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችሉ በርካታ የአስራር ማሻሻያዎች ተቀርፀዉ ተግባራዊ መደረጋቸዉ

ይታወሳል ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም እስከአሁን የተተገበሩ ማሻሻያዎች በተሻለ ደረጃ ተፈፃሚ እንዲሆኑ

የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ እና በተለይም

 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የሚቀርቡ የውሃ አቅርቦት

አገልግሎቶችን በተመለከተ ደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት ማሟላት ያለባቸውን

ቅደመ ሁኔታዎች በግልጽ ለማስቀመጥ በማስፈለጉ፤

 በባለስልጣኑ ለደንበኞች የሚቀርቡ አገልግሎቶች በተቀመጠላቸዉ ስታንዳርድ መሠረት

ተፈፃሚ እንዲደረጉ እና ደንበኞችም በአግባቡ ቅሬታ ለማቅረብ የሚያስችላቸውን ምቹ

አሰራር ለመዘርጋት በማስፈለጉ፤

 የቆጣሪ ንባብ ጥራትን አሁን ያለበትን ደረጃ በማሳደግ የገቢ አሰባሰቡን ስርዓት

ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል በማስፈለጉ፤

 የደንበኞችን መረጃ በዘመናዊ መልክ ማደራጀትና በተፈለገው ጊዜ በቀላሉ አገልግሎት

ለመስጠት የሚያስችል የአስራር ስርዓት ማስፈን በማስፈለጉ፤

 ባለስልጣኑ ለደንበኞች የሚሰጣቸውን የአዲስ ውሃ ቅጥያ፣ ማዛወሪያ፣ ማሻሻያ፣ የቦኖ

ቅጥያ፣ የቆጣሪ ምርመራ ወዘተ… አገልግሎቶች በማቀላጠፍ በሚሰጡት አገልግሎቶች

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 1| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ደንበኞችን ማርካት የሚያስችልና ተጠያቂነት የሰፈነበት ወጥ የሆነ ምቹ አሰራር

ማስፈን ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና

ለማቋቋም በወጣዉ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን

መሠረት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ይህንን የዉሀ አቅርቦት አገልግሎቶች

የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር --- / 2013 አዘጋጅቶ ስራ ላይ እንዲዉል አድርጓል፡፡

ክፍል አንድ
ጠቅላላ ድንጋጌዎች

አንቀጽ -1-
አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ የውሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር--- / 2013 ተብሎ

ሊጠቀስ ይችላል ፡፡

አንቀጽ -2-
ትርጓሜ

የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም ሊያሰጠው የሚችል ካልሆነ በስተቀር ለዚህ መመሪያ አፈፃፀም

የሚከተሉት ቃላትና ሀረጎች ከዚህ በታች የተሰጣቸውን ትርጓሜ ይኖራቸዋል፤

1. “ከተማ” ማለት፡- አዲስ አበባ ከተማ ማለት ነው፡፡

2. “ባለስልጣን” ማለት፡- የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስሥልጣን ማለት ነው፡፡

3. “ዋና ሥራ አስኪያጅ” ማለት፡- የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ

ማለት ነው፡፡

4. “ዘርፍ” ማለት ፡- የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ማለት ነው፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 2| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

5. “ቅርንጫፍ ወይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት” ማለት፡- እንደ ቃሉ አግባብ በባለስልጣኑ ሥር ያለ

ቅርንጫፍ ወይም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለት ነው፡፡

6. ”ባለሙያ” ማለት፡- በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዉስጥ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተቀጥሮ

በማገልገል ላይ ያለ ፈፃሚ ማለት ነው፡፡

7. “ደንበኛ” ማለት፡- እንደ ቃሉ አግባብ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ጋር ዉል ተዋዉሎ የውሃ አቅርቦት /

የፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎትን በመጠቀም ላይ ያለ ወይም በባለስልጣን መ/ቤቱ የሚሰጡ

አገልግሎቶችን ለመጠቀም ጥያቄ ያቀረበ / በማቅረብ ላይ ያለ የከተማው ነዋሪ ማለት ነው ፡፡

8. “አዲስ ቅጥያ” ማለት፡- ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር ውል ለተዋዋለ ደምበኛ አዲስ የውሃ መስመር

መዘርጋትን፣ መስመሩን ከባለስልጣኑ የስርጭት መስመር ጋር ማገናኘትን እና የዉሀ ቆጣሪ

መግጠምን ባካተተ መልኩ ተፈፃሚ የሚደረግ ተግባር / አገልግሎት ማለት ነው

9. “ማሻሻያ” ማለት ፡- አገልግሎት በማግኘት ላይ ያለ ደምበኛ በሚያቀርበዉ ጥያቄ መሰረት

የደንበኛዉን የውሃ መስመር እና/ወይም የቆጣሪ ስፋት ከፍ ወይም ዝቅ በማድረግ ተፈፃሚ

የሚደረግ ተግባር / አገልግሎት ማለት ነው፡፡

10. “ማዛወሪያ” ማለት፡- አገልግሎት በማግኘት ላይ ያለ ደምበኛ በሚያቀርበዉ ጥያቄ መሰረት

የደንበኛዉ የውሃ መስመር እና የቆጣሪ ስፋት መጠኑ ሳይቀየር የዉሀ መስመሩን እና / ወይም

የዉሀ ቆጣሪዉን ወደ ሌላ ቦታ በማንቀሳቀስ / በማዛወር ተፈፃሚ የሚደረግ ተግባር / አገልግሎት

ማለት ነዉ፡፡

11. “ታሪፍ” ማለት፡- የደምበኞች ወርሀዊ የዉሀ ፍጆታ ሲጨምር መጠኑ እየጨመረ በሚሄድ መልኩ

በተለያዩ የፍጆታ ዕርከን ደረጃዎች ላይ ተወስኖ የተቀመጠ ለአንድ ሜትር ኪዩብ ዉሀ የሚከፈል

የገንዘብ ክፍያ መጠን ማለት ነዉ፡፡

12. “ቆጣሪ” ማለት፡- ደንበኛው የተጠቀመውን የውኃ መጠን በሜትር ኪዩብ ለክቶ የሚያሳይ የልኬት

መሣሪያ ነው፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 3| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

13. “የውሃ ፍጆታ“ ማለት፡- በባለስልጣን መ/ቤቱ ለደምበኛዉ ከተገጠመዉ የዉሀ ቆጣሪ ላይ የሚነበብ

ጥቅም ላይ የዋለ የውሃ ልኬት መጠን ማለት ነው፡፡

14. “ቆጣሪ አንባቢ” ማለት፡- የውሃ ቅጥያ ያላቸው ደንበኞችን የውሃ ቆጣሪ በየወሩ ቤት ለቤት

በመሄድ ንባቡን የሚመዘገብ ግለሰብ ማለት ነው፡፡

15. “የቆጣሪ አንባቢዎች አስተባባሪ” ማለት፡- በቆጣሪ ንባብ ሥራ ላይ የተሰማሩትን የቆጣሪ አንባቢዎችን

ሥራ የሚቆጣጠር ሰራተኛ ማለት ነው፡፡

16. “የማንበቢያ መጽሃፍ ወይም ስማርት ፎን ሪዲንግ ቴክኖሮጂ” ማለት፡- ቆጣሪ አንባቢዎች

የንባብ ሥራን ለማከናውን ከቅርንጫፍ ጽ/ ቤቶች የሚረከቡት የደንበኞችን አድራሻ፤ የውል ቁጥር

እና (X, Y, COORDINATE ) የያዘ የውሃ ቆጣሪ ንባብ የሚመዘገብበት መፅሃፍ ወይም የማንበቢያ

ተንቀሳቃሽ ስልክ ማለት ነው፡፡

17. “የንባብ ምክንያታዊ ኮዶች ማጠቃለያ ( Reason code summery report)” ማለት፡-

የቆጣሪ ንባብ ወደ ኮምፒዉተር ከተመዘገበ በኃላ ከባለፈው ወር አጠቃቀም አንጻር ሲነጻጸር ምንም

ያልተጠቀመ (Zero Consumption) ወይም ከመጨረሻ የተመዘገበ ንባብ ያነሰ ንባብ (Over

Charge) ወይም ከፍተኛ አጠቃቀም (Increased Consumption) ወይም የቀነሰ ፍጆታ

(Decreased Consumption) እና ከ A እስከ Z reason code የያዘ ሪፖርት ማለት ነው፡፡

18. “ዉል መዝገብ ቤት” ማለት፡- ደንበኞች ከባለስልጣኑ ጋር የተዋዋሉበት ሰነድ እንዲሁም

ተያያዥነት ያላቸውን ሰነዶች የሚቀመጡበት ክፍል ማለት ነው፡፡

19. “የደንበኞች ፋይል” ማለት ፡- የውሃ ቅጥያ ያገኘ ደንበኛ ውልና ደጋፊ ሰነዶች እንዲሁም

በተከታታይ የተሰሩ ሥራዎችን የያዘ ሰነድ ማለት ነዉ፡፡

20. “የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች ጽ/ቤት” ማለት፡- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራይዞች ልማት ቢሮ እና በሥሩ የተዋቀሩ በክ/ከተማ ወይም በወረዳ

ያሉ ጽ/ቤቶች ማለት ነው፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 4| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

21. ”የውኃ መስመር” ማለት፡- ንፁሕ ውኃ ለማስተላለፍ በመሥሪያ ቤቱ የተዘረጋ ወይም እንዲዘረጋ

የተፈቀደ ማናቸውም የውኃ ቧንቧ ማለት ነው፡፡

22. “የቦኖ ውሃ አገልገሎት” ማለት፡- በከተማው ሥር ባሉ ወረዳዎች ውል ተዋዋይነት በግል ውሃ

ለማስገባት ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ለጋራ መጠቀሚያ እንዲውል የተተከለ የዉሀ ማደያ

አገልግሎት ማለት ነው፡፡

23. .“የጋራ የውሃ መጠቀሚያ” ማለት ፡- የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ለሌላቸው እና ላላቸው በአንድ

አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች በወረዳው ውል ተዋዋይነት ለጋራ መጠቀሚያ እንዲውል የተተከለ የውሃ

አቅርቦት አገልግሎት ማለት ነው፡፡

24. “ሽንሻኖ” ማለት፡- በቤት ሥራ ህብረት ሥራ ማህበራት ካርታ ላይ አባላት ያላቸው ይዞታ በአባላቱ

ቁጥር ልክ ተከፋፍሎ የተቀመጠበት የአከላለል አግባብ ማለት ነው፡፡

25. “ሪልስቴት” ማለት፡- መሬት አልሚዎች ማለትም በግለሰብ ፣ በሽርክና ኃላፊነቱ የተወሰነ አክስዮን

ማህበር በመደራጀት ከሚመለከተው አካል መሬት ተረክቦ በቤት ልማት ቤት ሰርቶ ለተጠቃሚ

የሚያስተላልፍ አካልማለት ነው

26. “የውሃ መሰረተ ልማት” ማለት፡- ማንኛውም የውሃ ምርት እና ስርጭት የሚከናወንባቸው

ግድቦች፣ ጉድጓዶች፣ ማጠራቀሚያዎች፣ ግፊት መስጭያ ጣቢያዎች፣ የውሃ መስመሮችና በላያቸው

ላይ የተገጠሙ መገጣጠሚያ መሳሪያዎች እና የመሳሰሉት ማለት ነው፡፡

27. “ከቆጣሪ በፊት ያለ መስመር” ማለት፡- ከባለሥልጣኑ ሁለተኛ ደረጃ መስመር ጀምሮ በደንበኛው

ቤት ፤ ሕንፃ ወይም ቦታ ውስጥ እስከተተከለው የውኃ ቆጣሪ ድረስ ተዘርግቶ ያለው የውሃ

መስመር ማለት ነው፡፡

28. “ከቆጣሪ በኋላ ያለ መስመር” ማለት፡- ከቆጣሪው ጀምሮ ወደ ደንበኛው ቤት፤ ህንፃ ወይም ቦታ

የተዘረጋ የውኃ መስመር ማለት ነው፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 5| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

29. “የጋራ መስመር“ ማለት፡- ደንበኞች በጋራ ከባለስልጣኑ መስመር ላይ ዘርግተው በየግላቸው ውል

ፈፅመው የሚጠቀሙበት መስመር ማለት ነው፡፡

30. “የግል መስመር” ማለት፡- ከባለስልጣኑ መስመር ላይ ተቀጥሎ ወደ ደንበኛው ቤት የሚዘረጋ

የውሃ መስመር ማለት ነው፡፡

31. “የይዞታ ማረጋገጫ“ ማለት፡- የቤት ወይም የመሬት ባለቤትነት ካርታ ወይም ደብተር ማለት

ነው፡፡

አንቀጽ -3-
የተፈፃሚነት ወሰን

ይህ መመሪያ በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋናውመስሪያ ቤትና እንዲሁምበቅርንጫፍ

ጽ/ቤቶች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

ክፍል ሁለት

አንቀጽ -4-
አዲስ የውሃ ቅጥያ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያላባቸው ቅድመ ሁኔታዎች

1. የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደንበኞች

1.1 የይዞታው ማረጋገጫ ካርታ ወይም ደብተር ዋናውና ፎቶ ኮፒውን፣

1.2 ባለ ይዞታው የታደሰ የነዋሪነትመታወቂያ ወይም ፖስፓርት ወይም መንጃ ፍቃድ

ዋናውና ፎቶ ኮፒውን፣

1.3 ባለ ይዞታው በተለያየ ምክንያት የማይገኝ ከሆነ ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ቅድመ

ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፤ ውል ለመዋዋል የሚያስችል በሰነዶች ማረጋገጫ

ጽ/ቤት የተሰጠ ሕጋዊ ውክልና ዋናውና ፎቶኮፒ፣

1.4 ሕጋዊ ተወካይ ከሆነ እራሱን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም

የመንጃ ፍቃድ ዋናውና ፎቶኮፒ፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 6| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

1.5 ቀደም ሲል በዚሁ ይዞታ የዉሃ አገልግሎት አለመሰጠቱ ከተረጋገጠ በኋላ

አገልግሎቱን የሚያገኙ ሲሆን ከዚህ በፊት የውሃ አገልግሎት አግኝተው የተቋረጠ

ከሆነ እዳቸው ተጣርቶ የተጣራበትን ሰነድ ሲያቀርቡ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

1.6 በአንድ ካርታ የሚካተት ህጋዊ ይዞታ ዉስጥ ከአንድ በላይ ህንጻ ገንብቶ የራሳቸዉ

መግቢያና መዉጫ በርለየብቻው ያላቸዉ ከሆነ አገልግሎት ሲጠይቅ ካርታዉን፤

የግንባታ ፍቃዱን የነዋሪነት መታወቂያ ሲያቀርብ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ፡፡

1.7 ይዞታዉ የባለቤትነት ደብተርም ሆነ ካርታ ኖሮት በጋብቻ ፍቺ፤ በዉርስ ፤በስጦታ

የተገኘ ቦታ ከሆነና በፍርድ ቤት ዉሳኔ ክፍፍል የተደረገበት ሰነድ ሲቀርብ በክፍፍሉ

መሰረት አዲስ ካርታ እስከሚዘጋጅ ድረስ ቀድሞ የነበረዉን ካርታ በዋስትናነት

በማቅረብ የሚስተናገዱ ይሆናል ፡፡

1.8 የልማት ተነሺ ለሆኑ ደንበኞች የልማት ተነሺ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ

ሲያቀርቡአዲስ የውሃ አገልግሎት ሊያገኙ የሚችሉት ይኖሩበት ከነበረው አከባቢ

ካለው የውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን ቅ/ጽ/ቤት ከእዳ ነጻ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ

ይኖርባቸዋል፡፡

2. የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸዉ /ሰነድ አልባ እና አርሶ አደር ደንበኞች

2.1 በተለያየ መንገድ ለረዥም ጊዜ በከተማ ክልል ውስጥይዞታ ኖሯቸው ነገር ግን ህጋዊ

ካርታ ወይም ደብተር ማቅረብ ለማይችሉ የከተማዉ ነዋሪዎች በክፍለከተማዉ

መሬት ማኔጅመንትየቦታዉን አቀማመጥ የሚገልጽ GISንመሰረት ያደረገ

ማስረጃከደብዳቤ ጋር ተያይዞ ሲቀርብ እና ውሃ የሚገባለትን ሰው ስም

የሚገልጽደብዳቤ ሲቀርብ የሚስተናገዱ ይሆናል ፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 7| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2.2 በአዲስ አበባ ከተማ ክልል ውስጥ ላሉ አርሶ አደሮች ካሉበት ክፍለ ከተማ መሬት

ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት ሃላፊ በከተማው ክልል ውስጥ ይዞታቸው ያለ መሆኑን

ሲያረጋግጥ እና የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አርሶአደር መሆናቸውን

ማስረጃ ሲጽፉላቸው በደብዳቤው ላይ ስሙ የተጻፈው ሰው ወይም ህጋው

ወኪሉየውክልና ማስረጃ እና መታወቂያ ሲያቀርቡ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

3. የእምነት ተቋም የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደንበኞች

3.1 የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም ደብተር ዋናውና ፎቶ ኮፒውን፣

3.2 ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ማቅረብ ለማይችሉ ተቋማት ከሚመሩበት የእምነት

ጠቅላይ ምክር ቤቶች ውሃ እንዲገባ የሚገልፅ ደብዳቤ ሲያቀርቡ የሚስተናገዱ

ይሆናል ፡፡

3.3 የእምነት ተቋማቱ በያዙት ክልል ውስጥ ከአንድ የውሃ ቆጣሪ በላይ አገልግሎት

መስጠት የተከለከለ ነዉ፡፡

3.4 ከእምነት ቦታው ቅጥር ግቢ ውጭ በንግድና በመኖሪያ ቤት ለሚያስተዳድሯቸዉ

ቤቶች በእምነቱ ጠቅላይ ምክር ቤት በተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ መሠረት የሚስተናገዱ

ይሆናል፡፡

3.5 ከተቋማቱ ህጋዊ ዉክልና የተሰጠዉ ተወካይ እራሱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ

ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡

4. የከተማ መስተዳድሩ (የመንግስት) ቤት ተከራይ የሆኑ ደምበኞች

4.1 ቤቱን ከሚያስተዳድረዉ አካል የውክልና ደብዳቤ ዋናውን ሲያቀርብ፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 8| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

4.2 የተወካይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና

ፎቶ ኮፒ፣

4.3 ውል እንዲዋዋል ከሚመለከተው የከተማ አስተዳደር በደብዳቤ የተወከለ ሰዉ በአካል

ካልቀረበ የውሃ አገልግሎቱ አይሰጥም፣

4.4 ቀደም ሲል በዚሁ የቤት ቁጥር የዉሃ አገልግሎት አለመሰጠቱ ከተረጋገጠ በኋላ

አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል ፡፡ ከዚህ በፊት የውሃ አገልግሎት አግኝተው

የተቋረጠ ከሆነ እዳቸው ተጣርቶ የተጣራበትን ሰነድ ሲያቀርቡ የሚስተናገዱ

ይሆናል፡፡

5. የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤት ተከራይ የሆኑ ደምበኞች

5.1 ቤቱን ከሚስተዳድረዉ አካል የአገልግለሎት ጥያቄ በደብዳቤ ሲያቀርብ፤

5.2 ቀደም ሲል በዚሁ ቤት ቁጥር የዉሃ አገልግሎት አለመሰጠቱ ከተረጋገጠ በኋላ

አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል ፡፡ ከዚህ በፊት የውሃ አገልግሎት አግኝተው

የተቋረጠ ከሆነ እዳቸው ተጣርቶ የተጣራበትን ሰነድ ሲያቀርቡ የሚስተናገዱ

ይሆናል፡፡

5.3 ቤቱን ከሚስተዳድረዉ አካል ውል እንዲዋዋሉ በደብዳቤ የተወከለ ሰዉ በአካል

ሲቀርብ ብቻ የውሃ አገልግሎቱን ሊያገኝ ይችላል ፡፡

5.4 የተወካይ የታደሰ መታወቂያ ፤ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ዋናውንና ፎቶ

ኮፒውን፣ማቅረብ ይኖርበታል ፡፡

6. በቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበር ስም አገልግሎቱን የሚጠይቁ ደምበኞች


(ይዞታው የቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበር ሆኖ አባላቱ ቦታዉን ሳይከፋፈሉ በግንባታ
በማህበሩ ሥም ዉሃ እንዲገባላቸዉ ሲጠይቁ፤)

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 9| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

6.1 ከህብረት ሥራ ማህበሩ ዉሃ እንዲገባላቸዉ በማህበሩ ስም በደብዳቤ ሲጠይቁ፤

6.2 ከማህበራት ማደራጃ ህጋዊነቱን የሚገልጽ የአባላቱን ሥም ዝርዝር የያዘ ደብዳቤ

ሲያቀርቡ፤

6.3 የቤት ሥራ ማህበሩን ካርታ እና የግንባታ ፍቃድ ሲያቀርቡ፤

6.4 ጉዳዩን እንዲከታተሉ የቤት ሥራ ማህበሩ የተወከለዉ ተወካይ የታደሰ የነዋሪነት

መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒዉን፣

6.5 አገልግሎት ጠያቂዎቹ ይዞታውን ስላልተከፋፈሉት ውሀው የሚገባው በማህበሩ

ስም ያሆናል

6.6 አባላቱ በየግላቸዉ ዉሃ ማስገባት ሲጠይቁ ቀደም ሲል ለግንባታ ስራ ገብቶ

የነበረዉን የዉሃ ቆጣሪ አስነስተዉ ሒሳብ ከዘጉ በኋላ አገልግሎቱን ማግኘት

የሚችሉ ይሆናል፡፡

7. የቤት ስራ ህብረት ስራ ማህበር ሽንሻኖ የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደንበኞች


(ይዞታው የቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበር ከሆነና ካርታው ላይ ለእያንዳንዱ ማህበር
አባል ሽንሻኖ ያለበት ሆኖ የማህበሩ አባለት የተከፋፈሉ ከሆነ)

7.1 የቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበር የማህበሩ አባላት በይዞታ ማረጋገጫ ካርታ

ፎቶ ኮፒ ላይ በማረጋገጥ የተፃፈ ደብደቤ ዋናውን፣

7.2 ከማህበራት ማደራጃ ህጋዊነቱን የሚገልጽ የአባላቱን ሥም ዝርዝር የያዘ ደብዳቤ

ሲያቀርቡ፤

7.3 ካርታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን፣

7.4 የባለይዞታው የታደሰ መታወቂያ፤ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ ዋናውና ፎቶ

ኮፒ፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 10| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

7.5 በሽንሻኖ መሰረት ካርታዉ በማህበሩ ሥም ቢሆንም በተጠቀሰዉ ቦታ ያለዉ

ባለይዞታ የግል ካርታ ለጊዜዉ ባያቀርቡም የማህበሩ አባልነትን የሚገልጽ

ማረጋገጫ ከማህበሩ ደብዳቤ ሲጽፍላቸዉ በስማቸዉ ይስተናገዳሉ ፡፡

7.6 ባለ ይዞታው በአካል ካልተገኘ ከዚህ በላይ የተገለፁት ቅድመ ሁኔታዎች

እንደተጠበቁ ሆኖ፣

ሀ/ ውል ለማዋዋል የሚያስችል በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ ህጋዊ

ውክልና ዋናውንና ፎቶ ኮፒ

ለ/ የህጋዊ ተወካይ የታደስ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም

የመንፈጃ ፍቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ

8. በቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበራት በኮንዲሚኒየም መልክ የተሰሩ ቤቶች ደንበኞች

8.1 ከማህበራት ማደራጃ ህጋዊነቱን የሚገልጽ የአባላቱን ሥም ዝርዝር የያዘ ደብዳቤ

ሲያቀርቡ፤

8.2 የቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበሩ ካርታውን ፎቶ ኮፒ በማድረግና ፎቶ ኮፒዉ

ላይ የይዞታ ወለል በማስቀመጥና የባለይዞታውን ይዞታ በማመላከት ለአባሉ ውሃ

እንዲገባለት የተጻፈውን ደብዳቤ ዋናውን፣

8.3 የቤት ሥራ ህብረት ሥራ ማህበሩ ካርታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣

8.4 የባለይዞታውየታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ፤ ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ

ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣

8.5 በሕንፃው የተዘረጋው የውሃ መስመር የራይዘሩ ዝርጋታ የውሃ ቆጣሪ

ለማስቀመጥ በግድጋዳው ውስጥ ያልተቀበረና ለቆጣሪ ንባብ ምቹ መሆኑን

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 11| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

በተቋሙ ባለሙያ ተረጋግጦ ሲገኝ ለእያንዳንዱ ቤት የግል ውሃ እንዲገባለት

ሊፈቅድ ይችላል፡፡

8.6 የቤት ሥራ ሕብረት ሥራ ማህበር የየፎቁን ወለል ኘላን ፎቶኮፒ በማያያዝና

የአባሉን ይዞታ በማመላከት የተፃፈ ደብዳቤ ዋናውንና እና የጋራ ካርታውንፎቶ

ኮፒ ይዘዉ በመቅረብ በስማቸዉ መዋዋል ይችላሉ፡፡

8.7 ባለይዞታው የማይገኝ ከሆነ ከአንቅጽ ከዚህ በላይ የተገለፁት ቅድመሁኔታዎች

እንደተጠበቁ ሆኖ ውል ለመዋዋል የሚያስችል በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት

የተረጋገጠ ሕጋዊ ውክልና ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣

8.8 ህጋዊ ተወካዩ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ፤ ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ

ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣

9. በግለሰቦች ፤በሽርክና ማህበር ወይም በኃላፊነቱ የተ/አ/ማ የተሰሩ ቤቶች ደንበኞች


(ለሥራም ሆነ ለመኖሪያ የተለዩ ከሆነ)

9.1 የሽርክና ማህበሩ የተመሰረተበት ወይም የተመዘገበበት ከሚመለከተው ተቋም

የማህበሩን ህጋዊነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ

9.2 ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን

9.3 የህንፃውን አጠቃቀም ኘላን /Lay out Plan/ ዋናውንና ፎቶ ክፒ

9.4 የባለይዞታው የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ

9.5 ይዞታው የሽርክና ማህበር ወይም የተወሰነ የግል ማህበር ከሆነ ውል ለመዋዋል

የሚያስችል ውክልና ዋናውን እና መታወቂ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፡-

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 12| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

10. የሪል እስቴት ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደምበኞች

ለሪል እስቴት የሚዘረጉ መጋቢ መስመሮች ዝርጋታ ክፍያው የሚፈጸመው በሪል እስቴት

አልሚው ሆኖ ሥራው በባለስልጣንኑ መ/ቤት የሚሰራ ይሆናል ፡፡ቤቶቹ ፎቅ ከሆኑ

የራይዘሩ ግንባታ የውሃ ቆጣሪ ለማስቀመጥ በግድጋዳው ውስጥ ያልተቀበረና ለቆጣሪ ንባብ

ምቹ ሆኖ ሲገኝ ለእያንዳንዱ ቤት የግል ውሃ እንዲገባበት ሊፈቅድ ይችላል ፡፡ ሆኖም ይህ

ሊሆን የሚችለዉ ከዚህ በታች የተገለጹት መሟላታቸው ከተረጋገጠ ነው፡፡

10.1 ሪልእስቴቱ የተመሰረተበትን ወይም የተመዘገበበትንሰነድ ከሚመለከተው ተቋም

ህጋዊነት የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለበት

10.2 በሪልስቴት ስም የተሰጠውን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ዋናውና ፎቶ ኮፒውን ፣

10.3 ቤቶቹ ያረፉበትን /site plan/፣

10.4 ቤቶቹ ፎቅ ከሆነ ሸንሻኖ ኘላን/Floor plan/ ፎቶ ኮፒ፤

10.5 ለሪል እስቴት ቤቶች ግንባታ የታደሰ የግንባታ ፍቃድ ኮፒ፤

10.6 ከሪል እስቴት ጋር ያደረጉትን ውል ዋናውንና ፍቶ ኮፒ፣

10.7 በስሙ የውሃ መስመር እንዲያስገባ የተወከለበትንደብዳቤ ዋናውን እና የተወካይ

የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና

ፎቶ ኮፒ ይዞ በአካል በመቅረብ በስሙ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

10.8 ባለይዞታው የማይገኝ ከሆነ ከላይ የተገለጸው እንደተጠበቀሆኖበሰነዶች ማረጋገጫ

ጽ/ቤት የተረጋገጠ ውክልና ዋናውንና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም የተወካዩ የታደሰ

የነዋሪነት መታወቂያ ፡ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዞ

በአካል መቅረብ አለበት፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 13| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

11. የኮንዲሚንየም ቤት የይዞታ ማረጋገጫ ያላቸዉ ደምበኞች

11.1 ከቤቶችልማት ጽ/ቤት ጋር ያደረጉትን ውል ዋናውንና ፍቶ ኮፒ

11.2 ደንበኞች ከባንክ ጋር ያደረጉት የብድር ውል ስምምነት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፣

11.3 ከቤቶች ማስተላለፍ ጽ/ቤት ቁልፍ የተረከቡበት ሰነድ ኮፒ ሲያቀርቡ ፡፡

11.4 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ፤

11.5 በልማት ምክንያት የቤት እደለኞች የሆኑ እና በዕጣ የደረሳቸው ደንበኞች አዲስ

የውሃ አገልግሎት ሊያገኙ የሚችሉት ይኖሩበት ከነበረው አከባቢ ካለው የውሃና

ፍሳሽ ባለሰልጣን ቅ/ጽ/ቤት ከእዳ ነጻ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11.6 ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ዉክልና ይዘዉ በመቅረብ የሚስተናገዱ ይሆናል፡

11.7 ከላይ የተጠቀሱትን የሰነድ ማስረጃዎች አሟልተዉ ሲያቀርቡ በባለእድለኛዉ ስም

መዋዋል ይችላሉ፡፡

12. የማምረቻ ሼዶች ወይም መሸጫ ማዕከል ደምበኞች

በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ለተደራጁ ለማምረቻ ሼዶች ወይም መሸጫ ማዕከሎች

የአዲስ የውሃ ቅጥያ አገልግሎት ለማግኘት የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርኘራዞች ልማት

ጽ/ቤት በስማቸዉ አገልግሎት እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ፡-

12.1 ካደራጀዉ መንግስታዊ አካል ህጋዊ ደብዳቤ፤

12.2 ኢንተርፕራይዙ የተደራጀበት የንግድ ፍቃድ፤

12.3 የማህበራት ማደራጃ ሰርተፍኬት

12.4 ውሉን እንዲዋዋል በማህበሩ የተወከለበት ደብዳቤ ዋናውን የወኪሉን መታወቂያ

ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 14| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አንቀጽ -5-
የቦኖ ዉሀ እና የጋራ የዉሀ መጠቀሚያ አገልግሎት

1. የቦኖ ውሃ እና የጋራ የውሃ መጠቀሚያ አገልግሎት መስጠት የሚቻልባቸው ምክንያቶች፡-

1.1 በአንድ አከባቢ እየኖሩ ያሉ ነዋሪዎች በራሳቸው አቅም ውሃ ለማስገባት

ለማይችሉ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ፤

1.2 በአንድ አከባቢ እየኖሩ ያሉ ነዋሪዎች በግላቸው ውሃ ለማስገባት አቅም

ኖሯቸዉ ነገር ግን ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ ለማይችሉ

1.3 ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ኖሯቸዉ ነገር ግን የውሃ መሰረተ ልማት

በአከባቢያቸው ባለመኖሩ ምክንያት፤ መሰረተ ልማቱ እስከሚሟላ ድረስ

በጊዜዊነት የጋራ የውሃ መጠቀሚያ ሊጠይቁ ይችላሉ ፡፡

2. ለቦኖ ውሃና ለጋራ የውሃ መጠቀሚያ አገልግሎት መሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
(ከዚህ በላይ በተገለጹት ምክንያቶች)

2.1 ከአከባቢው የወረዳ አስተዳዳር በህጋዊ ደብዳቤ ነዋሪነታቸው ተረጋግጦ የስም

ዝርዝራቸው ተጠቅሶ የወረዳው ማህተም ተደርጎበት ሲቀርብ እና የአባወራ

/እማወራ/ ብዛት ከ20 ያለነሰ ሆኖ ርቀቱ በ150 ሜትር ራዲየስ ዉስጥ (ዙሪያ

ርቀት) ላይ ሌላ የቦኖ ውሃ አገልግሎት ያለመኖሩ ሲረጋገጥ በወረዳው ስም

አገልግሎቱ ሊሰጥ ይችላል፤

2.2 ጉዳዩን እንዲያስፈጽሙም ከመካከላቸው ተወካይ ሰው ወረዳው መርጦ ውል

በወረዳው ስም እንዲዋዋል በመሸኛ ደብዳቤ ዝርዝራቸውን በማያያዝ ማቅረብ

የሚገባው ሲሆን ወረዳው የሚወክለው ሰው የአዲስ ቦኖ ውሃ ተጠቃሚወች

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 15| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አንዱ የታደሰ መታወቂያ፤ የታደሰ ፓስፖርት ወይም የታደሰ መንጃ ፈቃድ

ዋናው እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

2.3 ይሁንና ወረዳው በሚፅፈው ደብዳቤ ላይ የነዋሪዎቹን የኑሮ ሁኔታ ወይም

የአቅም ውስንነት ወይም አቅም ኖራቸው ህጋዊ የይዞታ የሰነድ ማቅረብ

ባለመቻላቸው መሆኑ በአግባቡ በወረዳው ተረጋግጦ ሲቀርብ ብቻ

የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

2.4 የቦኖ ዉሀ አገልግሎት ክፍያ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባስቀመጠው የቦኖ ታሪፍ

መሠረት የሚሰላ ሲሆን የጋራ የውሃ መጠቀሚያ አገልግሎቶች ክፍያ ግን

በመኖሪያ ቤት ታሪፍ የሚሰላ ይሆናል ፡፡

አንቀጽ -6-
የጋራ መስመር ዝርጋታ ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ

1. የባለስልጣኑ መለስተኛ መስመር ከአገልግሎት ጠያቂዎችመኖሪያ አከባቢ በመራቁ የተነሳ

ከአንድ በላይ የሆኑ ባለይዞታዎች ወይም ተጠቃሚዎች ለአዲስ ቅጥያ፣ ለማዛወሪያ፣

ለማሻሻያ አንድ ኢንች እና ከ አንድ ኢንች በታች እስከ አንድ መቶ(100) ሜትር ድረስ

የሆነ የጋራ መስመር እንዲዘረጋላቸው ከጠየቁ አገልግሎት ፈላጊዎች የራሳቸው ይዞታ

ከሆነ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ወይም ደብተር አቅርበው በደንበኞች አገልግሎት ክፍል

ሊዘረጋላቸው ይችላል ፣

2. የመንግስት ቤት ከሆነ ቤቱን በባለቤትነት ከሚያስተዳድረው መንግስታዊ አካል በስሙ

ውል ለመዋዋል የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረባቸው ተረጋግጦ በራሳቸው ወጪ ማዘርጋት

ይችላሉ፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 16| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

3. በዚህ አንቀስ ንኡስ አንቀስ /1/ የተጠቀሰው ደንበኞች ያዘረጉት የጋራ የውሃ መስመር

ለሌላ ደንበኛ አዲስ የውሃ መስመር ለመቀጠል የሚችል ሆኖ ሲገኝና ባለስልጣኑ ሲፈቅድ

ቅጥያውን ማካሄድ የሚቻል ሲሆን ለባለመስመሩ ተገቢውን ካሳ እንዲከፈለው ያደረጋል፡፡

ነገር ግን ከአንድ ኢንች በላይ በጋራ የተዘረጉ መስመሮች ባለሥልጣኑየሚያስተዳድራቸው

ስለሆነ ደንበኛው የባለሥልጣኑን ውሳኔ በመቃወም የመስመር ቅጥያ ተግባሩን ሊያውክል

አይችልም፡፡

አንቀጽ -7-
የማሻሻያ እና የማዛወሪያ አገልግሎት አፈፃፀም

1. የማሻሻያ አገልግሎት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ

1.1 አገልግሎቱን ጠያቂ ከባለስልጣኑ ጋር በውል የውሃ ቅጥያ ያለው ሆኖ በመጨረሻ

የተከፈለበትን ማስረጃ በማቅረብ የአገልግሎት ጥያቄ ያቀርባል ፡፡

1.2 ደንበኛው ቀደም ሲል ሲጠቀምበት ከነበረው የቧንቧ ስፋት መጠን ከፍ ለማድረግ

በሚጠይቅበት ጊዜ የግንባታ ፍቃድና ለሚገነባው ግንባታ የሚያስፈልገውን የቧንቧ

ስፋት መጠን የሚገልጽ የሳኒተሪ ዲዛይን መሠረት በማድረግ በአከባቢዉ ላይ

ያለው ውሃ አቅርቦትና ሥርጭት በመለስተኛ የውሃ መስመር ዝርጋታ ጥናት፤

ቁጥጥርና ውሃ ሥርጭት ንዑስ የስራ ሂደት መሪ ታይቶ መወሰን ይኖርበታል ፡፡

ደንበኛው ቀደም ሲል ሲጠቀምበት ከነበረው የቧንቧ ስፋት መጠን ዝቅ ለማድረግ

ቢፈልግ በጠየቀው መሠረት አገልግሎቱን ማግኘት የሚችል ሆኖ፡-

1.2.1 የሥራ ክፍሉ ደንበኛው ያልከፈለው ዕዳ ተቀማጭ ልዩነት ካለ አጣርቶ

እንዲከፍል በማድረግ አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 17| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

1.2.2 ቀድሞ ሲገለገልበት የነበረውን መስመር ከመነሻው ለማዘጋት ወጪው

በደንበኛው የሚሸፈን ይሆናል፡፡

1.3 ደንበኛው ራሱ ባይገኝ ሕጋዊ ወኪሉ ውክልናውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤የመጨረሻ

የተከፈለ ቢልና የታደሰ መታወቂያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒዉ በማቅረብ የማሻሻያ

ፎርሙን መሙላት ይኖርበታል፡፡

2. የማዛወሪያ አገልግሎት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ

የማዛወሪያ አገልግሎት በሶስት የተለያዩ መንገዶች ሊቀርብ ይችላል ፡-

I. በደንበኛዉ ጥያቄ መሰረት

II. በተቋሙ ተነሳሽነት

III. በመሰረተ ልማት ግንባታ ምክንያት ፡-

2.1 በደንበኛዉ ጥያቄ የሚከናወን የማዛወሪያ አገልግሎት

2.1.1 አገልግሎቱን ጠያቂ ከባለስልጣኑ ጋር በውል የውሃ ቅጥያ ያለው ሆኖ

በመጨረሻ የተከፈለበትንማስረጃናመታወቂያ ኮፒ በማያያዝ የአገልግሎት ጥያቄ

ያቀርባል፡፡

2.1.2 የሚዛወርበት መስመር መነሻው በስርጭት ላይ ችግር የማይፈጥር መሆኑን

በስርጭት ክፍሉ መረጋገጥ ይኖርባታል፤

2.1.3 የሥራ ክፍሉ ደንበኛው ያልከፈለው ዕዳናተቀማጭ ልዩነት ካለ አጣርቶ

እንዲከፍል በማድረግ አገልግሎቱን የሚያገኙ ይሆናል፡፡

2.1.4 ቀድሞ ሲገለገልበት የነበረውን መስመር ከመነሻው ለማዘጋት ወጪው በደንበኛው

የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 18| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2.2 በተቋሙ ተነሳሽነት የሚከናወን የማዛወሪያ አገልግሎት

2.2.1 ተቋሙ የአንድን አከባቢ መሥመር በተለያየ ምክንያት መቀየር ከፈለገ

የደንበኞች ውሃ አገልግሎት እንዳይቋረጥ ለያንዳንዱ ደንበኛ አስቀድሞ

ያሳውቃል፡፡

2.2.2 ደንበኛው የመጨረሻ ዉሃ ሒሳብ የከፈለበትን ኮፒ እና መታወቂያ ይዞ

በመቅረብ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

2.2.3 የአገልግሎት ክፍያው በደንበኛው የሚሸፈን ሲሆን ቀድሞ የነበረው መስመር

የብረት ከሆነ ሙሉ በሙሉ ወደ ፕላስቲክ (HDPE) የሚቀየር ይሆናል፡፡

2.3 በመሰረተ ልማት ግንባታ ምክንያት የሚከናወን የማዛወሪያ አገልግሎት

2.3.1 ዋናው መጋቢ መሥመር በተለያየ የመሰረተ ልማት ምክንያት የሚቀየር

(የሚነሳ) ከሆነ አጠቃላይ የመስመር ዝርጋታውንና የደንበኞች የማዘዋወሪያ

ወጪዉን መሰረተ ልማቱን ለሚያሰራው ተቋም ባለሥልጣን መ/ቤቱ

በሚያቀርበው ጥናት መሰረት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

2.3.2 ደንበኛው የመጨረሻ ዉሃ ሒሳብ የከፈለበትን ኮፒ እና መታወቂያ ይዞ

በመቅረብ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

2.3.3 ካላይ የተዘረዘሩት ስራዎች ከተሰራ በኋላ እስከ ሰላሳ (30) ቀን ድረስ በተለያየ

ምክንያት መስመሩ ውሃ ቢያፈስ ጥገናዉ የሚከናወነዉ በደንበኞች አገልግሎት

ክፍል ይሆናል፡፡

2.3.4 ባለስልጣኑ ለደንበኞች ዕቃ የሚያቀርብ ከሆነ ወቅታዊ የእቃዎች የዋጋ ዝርዝር

በየጊዜው ከፋይናስ ቡድን መቅረብ አለበት፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 19| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አንቀጽ -8-
የሥም ለውጥ አገልግሎት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ

የሥም ለውጥን በሚመለከት የሚቀርብ የአገልግሎት ጥያቄ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሶስት

ንዑስ አንቀፆች ዉስጥ ተዘርዝሮ በቀረበዉ መሰረት የአገልግሎት ጥያቄዉ የሚስተናገድ

ይሆናል፡፡ ከዚህ በታች ከንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 3 ድረስ ተዘርዝሮ በቀረበዉ አግባብ መሰረት

አገልግሎቱ የሚቀርብ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ደምበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት መጨረሻ

የከፈሉበትን ማስረጃ እና የመታወቂያ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

1. ከግዥ/ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚቀርብ የስም ለዉጥ አገልግሎት ጥያቄ

1. በሁለቱ ወገኖች መካከል በተደረገ ህጋዊ የሽያጭ ውል በዉልና ማስረጃ ተረጋግጦ

ሲቀርብ ፡፡

2. የሽያጭ ውሉ በውልና ማስረጃ ያልተመዘገበ (የመንደር ውል) ከሆነና ሽያጩ ከተከናወነ

አሥር (10) አመት ካለፈዉ በቀረበው የሽያጭ ውል የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

3. ይዞታው በተደጋጋሚ ሽያጭ የተካሄደበት ከሆነ ይዞታውን በመጨረሻ የያዘው ደንበኛ

ንብረቱን ወደ እራሱ ያዛወረበትን ሰነዶች ሲያቀርብ እና ያቀረበው ማስረጃ በ X,Y

Coordinate ተረጋግጦ ቀድሞ የነበረው የውሃው ውል የባለይዞታው መሆኑ ከተረጋገጠ

የሥም ዝዉዉሩ የሚደረግ ይሆናል ፡፡

2. በውርስ ፣በስጦታ እና በፍርድ ቤት ክርክር የሚቀርብ የስም ለዉጥ ጥያቄ

2.1 የፍርድቤት ውሳኔ ማስረጃ በማቅረብ

2.2 ከውሃ ውል ጋር ያለው ግንኙነትን በማጣራት

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 20| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2.3 የመጨረሻ የተከፈለበትን ማስረጃና መታወቂያ ኮፒ በማያያዝ የአገልግሎት ክፍያ

ፈጽመው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

3. በመንግሥት ተቋማት፤በኃ/የተ/የግል ማ. እና በአክሲዮን የሚቀርብ የስም ለዉጥ ጥያቄ

3.1 አገልግሎት ጠያቂ ደንበኛ ከውሃ ውል ጋር ያለው ግንኙነት ተጣርቶ

3.2 ይዞታውሥም የተዛወረበትን የሚገልጽ ከሚመለከተው ህጋዊ ተቋም በሚያቀርቡት

ማስረጃ መሰረት ሊዛወር ይችላል፡፡

3.3 የአገልግሎት ክፍያ ፈጽመው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

አንቀጽ -9-
የውል(የተያያዘ ማስረጃ) ኮፒ ይሰጠኝ/ይያያዝልኝ/ማስረጃ ይጻፍልኝ ጥያቄ የሚስተናገድበት
አግባብ

1. የውል (የተያያዘ ማስረጃ) ኮፒ ይሰጠኝ/ይያያዝልኝ ጥያቄ የሚስተናገድበት አግባብ

1.1 አገልግሎቱን ጠያቂ ከባለስልጣኑ ጋር በውል የውሃ ቅጥያ ያለው ሆኖ በመጨረሻ

የተከፈለበትን ማስረጃና መታወቂያ ኮፒ በማያያዝ የአገልግሎት ጥያቄ ያቀርባል፤

1.2 የአገልግሎት ጠያቂ ደንበኛ ከውሃ ውል ጋር ያለው ግንኙነት ተጣርቶ የአገልግሎት

ክፍያ ፈጽመው የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡

2. ከባለስልጣኑ ጋር ውል ያላቸው ክሊራንስ የሚጠይቁ ደምበኞች የሚስተናገዱበት አግባብ

2.1 የአገልግሎት ጠያቂ ደንበኛ ከውሃ ውል ጋር ያለው ግኑኝነት ተጣርቶ

2.2 የመጨረሻ የከፈሉበትን ደረሰኝ እና ውዝፍ እዳ ካለ ተጣርቶ እንዲሁም ቆጣሪ

ሲነሳ በቆጣሪዉ ላይ ያሳየዉን ንባብ ሒሳቡ ተሰልቶ ክፍያዉን ከፈፀሙ በኋላ

ማስረጃ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 21| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

3. ከተቋሙ ጋር ዉል የሌላቸው ክሊራንስ የሚጠይቁ ደንበኞች የሚስተናገዱበት አግባብ

3.1 ከሚኖሩበት ወረዳ የቤት ቁጥሩን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲያቀርቡ ፤

3.2 በቆ/ን/ቢ/ዝ/ሽያጭ ቡድን በተጠቀሰው ቤት ውስጥ ውሀ ውል ያለመኖሩን አረጋግጦ

ሲያቀርብ፤

3.3 በሚኖሩበት አካበቢ ካለው ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የውሀ ውል የሌላቸው መሆኑን

የሚገልጽ ማስረጃ የአገልግሎት ክፍያ ከፍለዉ ሊሰጣቸዉ ይችላል፡፡

አንቀጽ -10-
የደንበኞች ዉል መዝገብ ቤት ፋይል አያያዝና አጠቃቀም

የደንበኞች ዉል መዝገብ ቤት ደንበኞች ከባለስልጣኑ ጋር የተዋዋሉበት ሰነድ እንዲሁም ሌሎች

ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶች የሚቀመጡበት ክፍል ሲሆን መረጃዎች በሚመለከተው መልኩ

መደራጀት አለባቸዉ ፡-

1. ሁሉም ደንበኞች ከባለስልጣኑ ያገኙትን የአዲስ ውሃ ቅጥያ፣ የፍሳሽ ቅጥያ፣

የማዛወሪያ፣ የማሻሻያ፣ የቆጣሪ ለውጥ የሥራ ትዕዛዝና፤ የሂሳብ እርማት መረጃዎች

በአንድነት የያዘ የግል ፋይል እንዲኖራቸው ይደረጋል፡፡

2. የደንበኞች ፋይል አቀማመጥ በውል ቁጥር ቅደም ተከተል መሠረት መደራጀት

አለበት፡፡

3. የእያንዳንዱ ደንበኛ ፋይል ውስጥ ያሉ ሰነዶች ተከታታይ ቁጥር ተሰጥቶት ፋይል

መደረግ ይኖርበታል፡፡

4. የሁሉም ደንበኞች ፋይል በላቴራል ፋይል ውስጥ ተቆልፎበት መያዝ ይኖርበታል፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 22| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

5. የደንበኞችን ፋይል ከውል መዝገብ ቤት በማውጣት መጠቀምና መመለስ የሚችሉ

ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ዝርዝር በቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ ወይም በውሃ ደንበኞች

አገልግሎት ሓላፊ በደብዳቤ ለውል መዝገብ ቤት መገለጽ አለበት፡፡

6. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 በተገለፀው ደብዳቤ ከተዘረዘሩት ውጪ የደንበኞች

ፋይል ማውጣትም ሆነ መስጠት አይፈቀድም፡፡ ሆኖም የውስጥና የውጭ ኦዲተሮች

በፋይናንስ ሕግ፣ ደንብና መመሪያ መሠረት መጠቀም ይችላሉ፡፡

7. የውል መዝገብ ቤት ሰራተኞችም ሆኑ ፋይሎቹን አውጥተው የሚጠቀሙ ሃላፊዎች

ወይም ሰራተኞች ከደንበኛው ፋይል የተገኙ መረጃዎችን ለሌሎች ላለተፈቀደላቸው

ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች በማናቸውም መንገድ አሳለፎ መስጠት የለባቸውም፡፡

8. የደንበኞች ፋይል ከባለስልጣኑ ውጭ በሕግ ለተፈቀደላቸው አካላት በደብዳቤ

እንዲላክላቸው ከተጠየቀ በመሸኛ ደብዳቤ ይላክላቸዋል፡፡ በግልባጭ የውል መዝገብ

ቤት እንዲያውቀው መደረግ አለበት፡፡ መሸኛው ደብዳቤ የደንበኛው ስም፣የውል

ቁጥር፣ በፋይሉ ውስጥ ያሉ ሰነዶች ብዛት እናፋይሉ የተጠየቀበት ደብዳቤ ቀንና

ቁጥር መያዝ ይኖርበታል፡፡

9. ፋይሉን ከውል መዝገብ አውጥተው አገልግሎት የሚሰጡ ሃላፊዎች ወይም

ሰራተኞች በሕግ ባለመብት ለሆኑ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ወይም መንግስታዊ

አካላት እንደአስፈላጊነቱ የውል ኮፒ የመስጠት፣ በመመሪያዉ መሠረት ስም

ማዛወሪያ የመፈፀም፣ውል የማደስ አገልግሎት እና ለሚመለከተው አካል በሕጉ

መሠረት በደብዳቤ መረጃ የመስጠት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 23| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

10. ለባለስልጣኑ የውስጥ ሥራ የወጡ ፋይሎች በወጡበት እለት ለውል መዝገብ ቤት

ተመላሽ መደረግ አለባቸው፡፡ ሆኖም በደብዳቤ በሕግ ለሚመለከታቸው አካላት የተላኩ

ከሆነ የደብዳቤው ግልባጭ ዉል መዝገብ ቤት ገቢ ይሆናል፡፡

11. በደብዳቤ ለሚመለከታቸው አካላት የተላኩ የደንበኞች ፋይልን ጉዳዩ እንዳለቀ

ተከታትሎ የማስመለስ ሃላፊነት የደንበኞች ዉል መዝገብ ቤት ኦፊሰር ይሆናል፡፡

አንቀጽ -11-
የማመልከቻ ቅጽ ስለመሙላትና ክፍያ ስለመፈጸም
(ከአንቀፅ 4 እስከ 9 ድረስ ለተዘረዘሩት አገልግሎቶች)

1. አገልግሎት ጠያቂዎቹ ከላይ እንደ አገልግሎቱ ዓይነት ከአንቀጽ 4 እስከ 9

የተጠቀሱትን መስፈርቶች አሟልተው ሲቀርቡ የሚጠይቁትን የአገልግሎት አይነት

በማመልከቻ ቅጽ ይሞላሉ፡፡

2. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ/1/ የተጠቀሰውን ላሟሉ ደንበኞች እንደየ አገልግሎቱ

ዓይነት ግምት በባለሙያ ይሰራላቸዋል፡፡

3. አገልግሎት ጠያቂው አዲስ ደንበኛ ከሆነ ውሉን ከተዋዋለ በኋላ ክፍያውን

እንዲፈፅም ተደርጎ ለሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችም እንደ አገልግሎቱ ዓይነት

ክፍያ የሚፈፅም ይሆናል ፡፡ አገልግሎት ጠያቂዉ ደንበኛ አዲስ ደንበኛ ባይሆንም

ቅድሚያ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል ይኖርበታል ፡፡

4. አገልግሎት ጠያቂዎች ከተቋሙ የሚፈልጉትን አገልግሎት ሲጠይቁና ጥያቄያቸው

በክፍሉ ኃላፊ ሲፈቅድ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ ያስቀመጠውን የአገልግሎት ክፍያ

በቅድሚያ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 24| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ክፍል ሶስት

አንቀጽ-12-
የውሃ ቆጣሪ ንባብ፣ የገቢ አሰባሰብና ውዝፍ ክትትል ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ

1. የቆጣሪ ንባብ ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ

1.1 የደንበኞች ቆጣሪ በየወሩ በተመሳሳይ ቀን አንድ ቀን ወደፊት እና አንድ ቀን ወደኋላ

በመሳብ ንባብ መወሰድ ይኖርበታል ፡፡ ይህም የሆነበት ቀኑ የዐረፍት እና የህዝብ

በዓል ቀን ሊሆን ይችላል ተብሎ ታሳቢ በመደረጉ ነው፡፡

1.2 ደንበኞች የውሃ ቆጣሪያቸውን ከዋናው መግቢያ በር በሶስት ሜትር ራድየስ ሳይርቅ

መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ለንባብ አመቺ የሆነ ቦታ እንዲሆንና አከባቢዉ

ንፁህ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡

1.3 ደንበኞች ቆጣሪ አንባቢ በሚመጣበት ወቅት በሩ ክፍት በማድረግ ለንባብ አወሳሰድ

ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ግን ደንበኞዉ ከላይ በተራ ፊደል ለ

የተገለፀዉን ሳይተገብር ቀርቶ የአገልግሎት ሒሳቡ ተጠራቅም ለሚጠየቀዉ ክፍያ

ተቋሙ ተጠያቂ ስለማይሆን ደንበኛዉ የተጠየቀዉን ሒሳብ የመክፈል ግዴታ

ይኖርበታል፡፡

1.4 የደንበኛዉ ቅጥር ግቢ ዉስጥ ንባብ ለመዉሰድ በሚኬድበት ወቅት በደንበኛዉ

ቸልተኝነት ሰራተኛዉ በዉሻ ቢነከስ እና ሌሎች ችግሮች ቢደርስበት የደንበኛዉ የዉሃ

አገልግሎት ተቋርጦ በህግ አግባብ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡

1.5 የቆጣሪ አንባቢ ሰራተኛው በየወሩ የቆጣሪ ንባብ የማይወስድ ከሆነ ደንበኛዉ

ለቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአካል በመገኘት ማመልከት ይኖርበታል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 25| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2. የገቢ አሰባሰብና ውዝፍ ክትትል ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ

የባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የሚከተሉት ሥራዎች መከናወን

ይኖርባቸዋል እነሱም፡-

2.1 ጥራት ያለው የቆጣሪ ንባብ ሥራ መሥራት

2.2 ትክክለኛ ቢል ለሽያጭ እንዲቀርብ ማድረግ

2.3 ደንበኞች በወቅቱ ሂሳባቸውን እንዲከፍሉና የገቢ አሰባሰቡ እንዲያድግ ያልተቆጠበ

ጥረት ማድረግ

2.4 ከፍተኛ ፍጆታ ያላቸዉን ተጠቃሚዎችን በከፍተኛ ትኩረት በመከታተል ንባባቸውን

በወር ሁለት ጊዜ በመውሰድ የተጠቀሙበትን ወርሃዊ ሂሳብ የቆ/ን/ቢ/ዝ/ቡድን

እየተከታተለ እንዲከፍሉ ማድረግ ይኖርበታል

2.5 ትክክለኛ ያልሆኑ ሂሳቦች ካሉ በበቂ መረጃ ተደግፎ እንዲታረም ማድረግ

2.6 ከታረመ በኋላ የማስተካከያ መረጃ ለፋይናንስ ቡድን፤ለኢንፎርሽሜን ቴክኖሎጂ

አገልግሎትና ለቅርንጫፍ ገቢ የማይሰበሰብበት ውሃ ምርመራ እና ቁጥጥር ንዑስ

የሥራ ሂደት መላክ ናቸዉ

ከላይ የተጠቀሱት ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነዉ ፡-

2.7 አንድ ደንበኛ የተጠቀመበትን የውሃ ፍጆታ ክፍያ ወቅቱን ጠብቆ ተቋሙ

ባስቀመጠዉ የመክፈያ መንገዶች (ዘዴዎች) ክፍያዎችን መፈፀም ይኖርበታል፡፡

2.8 ወቅቱን ጠብቀው የማይከፍሉ ደንበኞች በተመለከተ ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ

ማስጠንቀቂያ የውሃ አገልግሎት የሚያቋርጥ ይሆናል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 26| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2.9 ደንበኛው አገልግሎቱን መልሶ ለማግኘት ቢፈልግ የነበረበትን ዉዝፍ እዳ ከነ ባንክ

ወለዱንና የማስቀጠያ ከፍሎ አገልግሎት ማግኘት ይችላል፡፡

2.10 አንድ ደንበኛ በአንድ አመት ዉስጥ ከሶስት ጊዜ በላይ ቆጣሪያቸው በዕዳ ከተነሳ

መልሶ አገልግሎቱን ለማግኘት የማስቀጠያ አገልግሎት ክፍያ በእጥፍ እንዲከፍሉ

ይደረጋል፡፡

2.11 አንድ ደንበኛ ቆጣሪው በዕዳ ተቆርጦ ከስልሳ (60) ቀን በላይ ከሆነ ቢል ህትመቱ

ስለሚቋረጥ መልሶ አገልግሎቱን ለማግኘት ያለበትን ዉዝፍ እዳ ከነባንክ ወለዱ

ከፍሎ በተጨማሪም የማስቀጠያ እና የዉል ማደሻ ከፍሎ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

2.12 የደንበኛው የውሃ ቆጣሪ በቤት ዉስጥ ሳይገኝ ሲቀርና ቤቱ በተለያየ ምክንያት

በቦታዉ ከሌለ ከዚህም ጋር በተያያዘ ቆጣሪው የተነሳበት የስራ ትእዛዝ ከጠፋ ቢል

እንዳይወጣ ለማድረግ እንዲቻል የባለስልጣኑ መ/ቤት የሚመለከተውን ባለሙያ

ወደ ደንበኛው ቤት በመላክ ቆጣሪው እቦታው አለመኖሩን አካባቢው ላይ ካሉ

ነዋሪዎች መረጃ በማሰባሰብ እና በማጣራት መስመሩ ከመነሻው እንዲዘጋ

ይደረጋል ፡፡ የማጣራት ስራዉን የፈፀመዉ ሠራተኛ በስራ ትእዛዙ ላይ ሙሉ

ስሙን ጽፎ ማስረከብ ይኖርበታል ፡፡ የቢል ህትመቱ እንዲቋረጥ ሲስተም ላይ

ያለው የመጨረሻውን ንባብ ተሞልቶ መላክ ይኖርበታል ፡፡

2.13 ከዚህ በላይ ከንዑስ አንቀፅ 2.7 እስከ ንዑስ አንቀፅ 2.12 በተዘረዘረዉ መሠረት

ተፈፃሚ ያልተደረጉ ክፍያዎችን በሚመለከት አስፈላጊ ማስረጃዎች ተጠናቀረዉ

ባለዕዳ የሆኑ ደንበኞች በህግ አግባብ እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ-13-
የሒሳብ እርማት እና ክፍያ አፈጻጸም ተግባራዊ የሚደረግበት አግባብ

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 27| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

1. የሒሳብ እርማት ተፈፃሚ የሚደረግበት አግባብ ፡-

ከሚከተሉት በአንድ ወይም ከአንድ በላይ በሆኑ መነሻዎች የደንበኞች የውሃ ሂሳብ ሊታረም

ይችላል፡፡

1.1 በቆጣሪ ንባብ ስህተት፣

1.2 በቆጣሪ ምርመራ ውጤት፣

1.3 በወቅቱ የቆጣሪ ንባብ ባለመወሰዱ የተነሳ የብዙ ወራት ክፍያ ተጠራቀሞ በከፍተኛ

ታሪፍ የተጋነ ነሂሳብ በመጠየቁ

1.4 የደንበኞች ምድብ አይነት ትክክል ባለመሆኑ፣

1.5 ቆጣሪው በስህተት ሮቢሾ በመገጠሙ፣

1.6 ቆጣሪውሆንተብሎየውሃ ክፍያለመቀነሰ ሲባል በሕገ ወጥ መንገድሮቢሾበመገጠሙ፣

1.7 ከቆጣሪ በፊት ሕገ ወጥ ቅጥያ በመፈፀሙ ፣

1.8 በቆጣሪው ላይ የቆጣሪ ምርመራ ጉደለት ሳይኖርና የማይታይ ፍሳሽ በምርመራ

አለመኖሩ ተረጋግጦ ነገር ግን እጅግ የተጋነነ ሂሳብ ሲጠየቅና በሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ

እንዲታይ ሲወሰን፣

1.9 ደንበኛው ውል ፈፅሞ ቆጣሪ ከተቀጠለ በኋላ ወደ ክፍያ ስርዓት ሳይገባ በቆጣሪዉ

ላይ አደጋ ቢደርስ ፤ ቢሰረቅ ፤ ደንበኛዉ ሆን ብሎ ቆጣሪዉን ቢሰዉረው ወዘተ…

ይህንን እና የመሳሰሉት ችግሮች በሚያጋጥሙበት ጊዜ የሂሳብ እርማት ሊደረግ

ይችላል ፡፡

አማካኝ የውሃ ፍጆታ አከፋፈልን በተመለከተ ከላይ በተጠቀሱት መነሻዎች የደንበኞችን ሂሳብ

ለማረም በመጀመሪያ መነሻዎችን በትክክል መረዳት የሚጠይቅ በመሆኑ እያንዳንዱን መነሻ

በአብነት ለማሳየት ይቻል ዘንድ እንደሚከተለው በዝርዝር ለማቅረብ ተሞክሯል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 28| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2. በቆጣሪ ንባብ ስህተት መነሻነት የሚደረግ የሂሳብ እርማት

የቆጣሪው ንባብስህተትቆጣሪ አንባቢው በትክክል ቦታውድረስ ባለመሄድና ባለማንበቡ እንዲሁም

በቆጣሪው ላይ ያለውን ዲጅት አዘበራርቆ በማንበቡ ወይም የሌላደንበኛ ቆጣሪንባብ በስህተት

በመመዝገቡ የደንበኛውንየውሃ ፍጆታ የመቀነስ ወይም የመጨመር ሁኔታ ሊከሰትይችላል፡፡

በዚህን ጊዜ ሁኔታውን በትክክል በመረዳት ተገቢውን የሂሳብ ማስተካከያ ማድረግ ተገቢ

ይሆናል፡፡

የአንድ ደንበኛ የቆጣሪ ንባብ ስህተት መኖሩን ለማጣራት፣

2.1.1 የደንበኛው ስም እና ዉል ቁጥር ትክክል መሆኑን ማረጋገጥ፣

2.1.2 የደንበኛውን ቆጣሪ ንባብ በትክክል መውሰድና በወቅቱ ደንበኛው በውሃው

ተጠቅመው የተለየ ሥራ አለመሰራታቸውን ማረጋገጥ፣በዕለቱ ከተወሰደው ንባብ

ቀደም ሲል የተከፈውን ቢል ሂሳብ የመጨረሻ ንባብ በመቀነስ ትክክለኛ ፍጆታውን

በሜትር ኪዩብ ማስቀመጥ፣

2.1.3 በዕለቱ ከተወሰደው ንባብ ቀደም ሲል የተከፈለውን ማረጋገጥ፣

2.1.4 በንዑስ አንቀፅ 2.1.3 መሠረት የተሰላው ፍጆታ የስንት ወር እንደሆነና

የደንበኛውን ዓይነት መለየት፣

2.1.5 በንዑስ አንቀፅ 2.1.3 የተገኘውን የደንበኛውን ፍጆታ ለተጠቀመበት ወራት

በማካፈል ወርሃዊ ፍጆታውን በሜትር ኪዩብ ማግኘት፣

2.1.6 የየወሩን ፍጆታ በደንበኛዉ ዓይነት ታሪፍ መሠረት በማስላት ሂሳቡን ማዘጋጀት፣

2.1.7 የተዘጋጀውን ክፍያ በማስከፈል የደንበኛዉን መረጃ እንዲስተካከል በተዘጋጀው ቅጽ

መሠረት ሞልቶ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማስተላለፍና አፈፃፀሙን መከታተል፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 29| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2.1.8 ክፍያ የተፈፀመበትን ሰነድ ለውል መዝገብ ቤት አስፈርሞ ማስረከብ እና ከደንበኛዉ

ማህደር ጋር እንዲያያዝ ይደረጋል፡፡

አብነት1

በንፋስ ስልክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኝ

1. አንድ ደንበኛበውል ቁጥር 97500

2. በቆጣሪ ቁጥር EG 00220

3. የቆጣሪ ስፋት ¾

4. ንባብበ10/10/2012350M3በመሆኑ፤

 ባላፉት ሶስት ወራት ውሃውን ተጠቅመው የሰሩት የተለየ ሥራ እንደሌለ

ተረጋግጧል፤

 የአካባቢው ቆጣሪ አንባቢ ተቆጣጣሪ አረጋግጦ በተዘጋጀው ቅጽ ላይ ፈርሞ ለቆጣሪ

ንባብ፣ ቢል ዝግጅትና ሽያጭ ቡድን አስተባባሪ አቅርቧል፡፡

 ቤቱም የመኖሪያ ቤት መሆኑ ታውቋል፡፡

 ቤቱ የፍሳሽ ቅጥያ ያለዉ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

 በሌላ በኩል የደንበኛው የሚያዝያ 2012 የውሃ ሂሳብ የያዘ ቢል የመጨረሻንባብ 470

M3 ይዞየወር ፍጆታ 201 M3 ሆኖ መታተሙና ከየካቲት 2012 እስከመጋቢት 2012

የመጨረሻ ንባብ 269 M3 ይዞ “በይበልጥ ከፈሉ” በሚል የቆጣሪ ኪራይ ከፍለዋል

በቢሉያለው የደንበኛዉ ዓይነት መኖሪያ ያልሆነቤት የሚል ነው፡፡

ከቀረበው መረጃ፡-

 የንባብስህተት መሆኑና ትክክለኛ የሰኔ 2012 ንባብ 350M 3

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 30| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

 የደንበኛው ዓይነት መኖሪያመሆኑ

 ትክክለኛ ያልሆነ የሚያዝያ 2012 ቢል ክፍያ የመጨረሻ

ንባብ 470 M3 ሆኖ ብር 4,697.59መሆኑ /ዝርዝሩከታችቀርቧል/

የፍሳሽ ቅጥያ የሌለዉ ከሆነ የፍሳሽ ቅጥያ ያለዉ ከሆነ

201X19.42 = 3,903.42 201X19.42 = 3,903.42

የቆጣሪ ኪራይ 13.49 የቆጣሪ ኪራይ 13.49

1% የጥገና 39.03 1% የጥገና 39.03

19 % የጽዳት 741.65 19 % የጽዳት 741.65

የፍሳሽ 7X1.00 7.00

194 X 3.00 582

ጠቅላላ ክፍያ ብር 4,697.59 ጠቅላላ ክፍያ ብር 5,286.59

1. የየካቲትና መጋቢት 2012 ደንበኛዉ የቆጣሪ ኪራይ ብቻ የከፈሉ መሆኑ፣

2. የጥር 2012 ክፍያ የመጨረሻ ንባብ 269 M3 መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡

3. እነዚህን መረጃዎች መነሻ በማድረግ የደንበኛው የሂሳብ እርማት ሥራ ይሰራል፡፡

4. ሰኔ 10/2012 የተወሰደ የመጨረሻ ንባብ350M3

5. ጥር 2012 ክፍያ የተፈፀመበት የመጨረሻ ንባብ 69 M3

81 M3 ፍጆታው የሚሸፍነው ጊዜ ከየካቲት 2012 እስከ ሰኔ 2012 ለ5 ወር ሂሳቡ ሲሰላ፡-

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 31| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

የፍሳሽ ቅጥያ የሌለዉ ከሆነ የፍሳሽ ቅጥያ ያለዉ ከሆነ

25 M3X2.40, 60.60 25 M3በ2.40 60.60

56 M3X4.85 271.60 56 M 3 በ4.85 271.60

የቆጣሪ ኪራይ የሚያዝያ 2012 ብቻ 13.49 የቆጣሪ ኪራይ 13.49

የጥገና 3.32 የጥገና 1% 3.32

10 % የጽዳት 33.22 የዉበትና ጽዳት 10 % 33.22

የፍሳሽ 7X 1.00 7.00

194 X 3.00 582.00

ጠቅላላ ክፍያብር 382.23 ጠቅላላ ክፍያ ብር 971.23

በሰህተት የተጠየቀዉ ብር 4,697.59 ወይም ፍሳሽን ጨምሮ ብር 5,286.59 የያዘው ቢል

ይታረምና በሂሳብ እርማቱ ማስተካከያ መሰረትብር 382.23 ወይም ብር 971.23 በደረሰኝ

እንዲከፍሉ ተደርጎ ለፋይናንስና ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት ሪፖርት ይደረጋል፡፡

ማስታወሻ ፡- 56 M3 በብር 4.85 የተባዛው 14M3X5= 70M3 በመሆኑና ቀሪው 56M3 ከ70 M3

በታቸ ስለሆነ2ኛ እርከን ታሪፍ ውስጥ በመሆኑ የተነሳ ነው፡፡

3. በቆጣሪው ምርመራ ውጤት መነሻነት የሚደረግ የሂሳብ እርማት ፡-

የደንበኛው የቆጣሪ ምርመራ ውጤት አራት አይነት ሊሆን ይችላል፡፡

1. ቆጣሪው “ትክክል” ይሰራል፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 32| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2. ቆጣሪው “ቆሟል”

3. ቆጣሪው - % በማነስ ይቆጥራል

4. ቆጣሪዉ - % በይበልጥ ይቆጥራል

እነዚህን መነሻ በማድረግ የደንበኛው የሂሳብ ማስተካከያ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡

ቆጣሪው “ትክክል” ይሰራል የሚል የቆጣሪ ምራመራ ውጤት ከደረሰን በቆጣሪው ላይካለው

ንባብ ከዚህ በፊት የተከፈለበትን ንባብ በመቀነስ ልዩነቱን በሜትር ኪዩብ ክፍያ

ላልተፈፀመባቸው ወራት በማካፈል በደንበኛው ዓይነት ታሪፍ በማስላት ደንበኛውን ማስከፈል

ይኖርበታል፡፡

ሆኖም አልፎ አልፎ ቆጣሪዎች ከደንበኛው ቤት ተነሰተው እስከ ቆጣሪ ምርመራ ወርክሾኘ

በሚጓጓዙበት ወቅት የቆጣሪው ጥርስ እንዳይቆጥር ያደናቀፉት ጠጠር፣ አሸዋ የመሳሳሉት

ከቆጣሪው ጥርስ በመውደቃቸው ቆመው የነበሩ ቆጣሪዎች ምርመራ “ትክክል” ይሰራል ተብሎ

ሊመጣ ይችላል፡፡ በዚህን ጊዜ የቆጣሪውን ሂሳብ የሚሰራ ባለሙያ ከቆጣሪ አንባቢ በተደጋጋሚ

የተወሰዱ ንባቦች በመውሰድ ቀደም ሲል ከነበራቸው ወርሃዊ ፍጆታ ማነፃፀርና የተለየ ሥራ

በቅርብ ጊዜ ውስጥ አለመሰራቱን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

በእነዚህ ሂደቶች ቆጣሪው ከቆጣሪ አንባቢበተገኘ የንባብ መረጃ መሠረትቆሞ የነበረ ወይምከቆመ

በኋላ ሌሎች ከመደበኛው ፍጆታ በላይ ደንበኛው መጠቀማቸው ከተረጋገጠ በዚህ አግባብ

ሂሳባቸውን መሥራት ትክክል ይሆናል፡፡ አፈፃፀሙ በደንብ ቁጥር 31/1994 አንቀጽ 16

መሠረት ይሆናል፡፡

አብነት -1፡- (በ 25% ይበልጣል የተሰራ )

 በጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኝ ደምበኛ

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 33| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

 በውል ቁጥር 32300

 ስፋቱ ½” የሆነና ቆጣሪ ቁጥር AB 7218 ተጠቃሚ ደበንኛሲሆኑ

 በጥር 2012 ቢል 6200 M3 የመጨረሻ ንባብና 6100M3 ያለፈው ንባብ ይዞ ብር 852.20

ተጠይቀዋል፡፡

 ቤቱን በሆቴልነትእንደሚጠቀሙም ታውቋል፡፡

ደንበኛዉ ሂሳባቸውን ለመከፍል መጋቢት 14 ቀን 2012 ዓ.ም ክፍያ ጣቢያ በሄዱ ጊዜ

ብር12,059.74 የያዘ ሂሳብ መሆኑ ሲገለጽ ሳይከፍሉ ቅሬታቸውን ለጉለሌቅርንጫፍ

አቅርበዋል፡፡

ቅሬታ ባቀረቡበት ወቅት የቆጣሪያቸው ንባብ 6413M3 የደረሰ በመሆኑ የቆጣሪ ምርመራ ሂሳብ

ከፍለው ይህንኑ ንባብ ይዞ ተመርምራል፡፡ የቆጣሪ ምርመራ ውጤቱም ቆጣሪው 25% በብልጫ

እንደሚቆጥር አረጋግጧል፡፡

የቆጣሪ ንባብ ተስተካክሎ እንዲቀጠል የሚል ነው፡፡

ለሂሳብ እርማት የሚረዱና የተገኙ መረጃዎች፡-

5. የቆጣሪ ስፋቱ ½” መሆኑና የመጨረሻ ንባብ 6413 M 3

6. ያለፈው ንባብ 6000 M3

7. ፍጆታ 413 M3

 ቆጣሪው 25% በይበልጥ የቆጠረ መሆኑ

 ፍጆታውየሚሸፍነውጊዜ፣ ከጥር 2012 እስከ መጋቢት 2012 የ3 ወር መሆኑና

 የደንበኛዉ ዓይነት መኖሪያ ያልሆነ መሆኑ ፡፡

በዚህ መሠረት ከ 413 M3ፍጆታ ውስጥ በስህተት 25% በይበልጥ የቆጠረው ንባብ

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 34| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

413M3 x .25 = 82.6 M3


1.25

413M3-82.6M3 = 330.4M3

ወይም 413M3 x 100 = 330.4M3


125

ድምር= 413 M3ይሆናል

 የ413 M3 በቢል ታትሞ የወጣው ሂሳብ ፡-

413 M3x24.28 = 10,027.64

የጥገና1% = 100.27

የጽዳት 19% = 1,905.25

የቆጣሪኪራይ (የሶስት ወር) 26.58

ጠቅላላ የ3ቱ ወራት ክፍያ 12,059.74

 ታርሞ ወይም 25% ተቀንሶ ሂሳቡ ሲሰራ ፡-

ወርሃዊ ፍጆታ ለማወቅ ፡ 413 - 82.6 = 330.4 M3 (የ3 ወርፍጆታ)

330.4 ÷ 3 ወር = 110.13 M3 / የአንድ ወር ፍጆታ/

330.4x19.42 = 6,416.37

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 35| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

የጥገና1% = 64.16

የጽዳት 19% = 1,219.11

የቆጣሪ ኪራይ (የሶስት ወር)= 26.58

ጠቅላላ የ3ቱ ወራት ክፍያ = 7,726.22

ከላይ የቀረበው ምሳሌ በጥር 2012 ደንበኛው ለ 413M3 ፍጆታ መኖሪያ ባልሆነ ታሪፍ ብር

12,059.74 ወርሃዊ ክፍያ ነበር የተጠየቁት፡፡ ሆኖም በዚህ ሂሳብ መነሻ ቆጣሪያቸው

ሲመረመር 25% በይበልጥ የሚቆጥር መሆኑ በመታወቁ ብር 12,059.74በቢል ማስከፈል

አይቻልም፡፡ በመሆኑም ቆጣሪው 25% በይበልጥ ቆጥሯል ተብሎ ለተያዘው ጊዜ ከጥር 2012

እስከ መጋቢት 2012 ላሉት ሶስት ወራት ፍጆታ በማውጣት የሂሳብ ማስተካከያ ሰርቶ

ማስከፈሉ ተገቢ ይሆናል፡፡

ስለዚህ ቆጣሪው በይበልጥ 25% ያሳየው ተቀንሶለት የተገኘዉ ውጤት ማለትም 413M3

ሲቀነስ 82.6M3ቀሪዉ 330.4M3ሒሳብ ተሰልቶ የመጣው ብር 7,726.22 በደረሰኝ በማስከፈል

አዲስቆጣሪ ወጪ ተደርጎበመቀጠል የመረጃ ማስተካከከያ ሥራ ባለው አሰራር አግባብ መፈፀም

ይገባል፡፡ የጥር ወር 2012 ቢል የያዘው በብር 12,059.74 ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል፡፡

አብነት -2፡- በ 25% በማነስ የተሰራ

በአዲስከተማ ቅርንጫፍ ነዋሪ የሆኑ ደንበኛ

 በውል ቁጥር 53700

 በቆጣሪ ቁጥር BG 129223 ተጠቃሚና

 ቤቱንም በመኖሪያነት ብቻ እንደሚጠቀሙና የቆጣሪው ስፋት ¾” መሆኑ ታውቋል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 36| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

 በውሃ አጠቃቀማቸው ላይ ለውጥ ሳይኖር ሂሳባቸውን ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ

መሆኑን የአካባቢው ቆጣሪ አንባቢ መረጃ በመስጠቱ ቆጣሪያቸው ተነስቶእንዲመረመር

ተደርጓል፡፡

 የቆጣሪዉ ምርመራ ውጤት “ቆጣሪው 20% በማነስ እንደሚቆጠርና መለዋዋጫ ስለሌለ

ይለወጥ” ይላል፡፡

 የቆጣሪው የመጨረሻ ንባብ 900M3 ነው፡፡

 ቆጣሪው የተመረመረው በ15/10/2012 ሲሆን የሚያዝያ 2012 ሂሳብእስከ 870 M 3

ተከፍሏል፡፡


ያልተከፈለው ሂሳብ 900-870=30 M3

ቆጣሪው 20% በማነስ የሚቆጥር መሆኑናየፍጆታ ጊዜ ከግንቦት 2012 እስከ ሰኔ 2012 ነው፡፡

 የደንበኛው ዓይነት መኖሪያ ቤት ሆኖ ስሌቱ ሲሰራ፡-

30x100= 37.5 M3

80

ይህ ሂሳብ በ2 ወር ታስቦ ይከፈላል፡፡

10x 2.40 24.40

27.5x4.85 133.37

የቆጣሪ ኪራይ 26.98

የጥገና 1% 1.57

የጽዳት 10% 15.77

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 37| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ጠቅላላ ክፍያ 201.79 ይህን ሂሳብ በመክፈልወይም ንባቡን 870M3+37.50M3= 907.5M3

በማድረግ የግንቦትና የሰኔ 2012 ለይቶ እንዲከፈሉ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለደንበኛዉአዲስ ቆጣሪ

ወጪ በማድረግ ይቀጠልና ተገቢው መረጃ ማስተካከያ ተሰርቶለት ሰነዱ ለሚመለከተው

ክፍል ይተላለፋል ፡፡

4. በየጊዜው የቆጣሪ ንባብ ባለመወሰዱ ምክንያት የብዙ ወራት ክፍያ ተጠራቅሞ የተጋነነ
ሂሳብ በመጠየቁ ምክንያት የሚደረግ የሂሳብ እርማት

አብነት 1፡-በአቃቂ ቅርንጫፍ ነዋሪ የሆኑ ደንበኛ

 በውል ቁጥር 96255

 በቆጣሪ ቁጥር DF 128762

 ነሐሴ 02 ቀን2011 ዓ.ም ቆጣሪ ተቀጥሎ በ½ ቆጣሪ ውሃ እያገኙ መሆናቸው

ታውቋል፡፡

 ቤቱ መኖሪያ ሲሆን የውሃ ሂሳብ 620 M3ይዞ ቢሉ የወጣው ሐምሌ 2012 ሲሆን

 በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ከ0-620 M3 ይዞ ብር 14,509.73ተጠይቋል ፡፡

 የቆጣሪ ንባብ ሲታይ ስህተት የለበትም፡፡ ደንበኛው ሂሳብ በዛብኝ የሚል ቅሬታ

ያቀረቡሲሆን ስህተቱ ሲጣራ የ12 ወራት ፍጆታ በአንድ ወር ተደምሮክፍያመጠየቅ

ያስከተለው ውጤት በመሆኑ ለተጠቀሙበት 12 ወራት ሂሳቡተተንትኖእንዲከፈል

ውሳኔ አግኝቷል፡፡

 የተጋነነው ሂሳብ የያዝው ቢል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

7m3 x 12 ወር = 84m3 x 1.75 =147.00

13m3 x 12 ወር =156m3 x 3.80 = 592.80

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 38| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

20m3 x 12 ወር = 240m3 x 4.75 =1,140.00

ቀሪዉ 140m3x 14.57 = 2,039.80

ጠቅላላ ክፍያ ብር 3,919.60 በደረሰኝ እንዲከፍሉ ተደርጎ ቀደም ሲል በቢል ታትሞ የወጣው

ብር14,509.73 ሙሉ በሙሉ ውድቅ ተደርጎ ምንም አይነት የንባብ ማስተካከያ አይሰራለትም፡፡

ስለሆነም ሰነዱ ከደንበኛው ማህደር ጋር እንዲያያዝ ይደረጋል፡፡

5. የደንበኞች ክፍያ ምድብ (category) ትክክል ባለመሆኑ የሚደረግ የሂሳብ እርማት

የደንበኛውአይነት “መኖሪያ ያልሆነ” ሆኖ እያለ የተያዘው በመኖሪያ ቤትነት ከሆነ በመ/ቤቱ ላይ

ጉዳት ያደርሳል፡፡ እንዲሁም የደንበኛዉ ቤት “መኖሪያ ቤት” ሆኖ እያለ መኖሪያ ቤት ያልሆነ

ታሪፍ የተያዘበት ከሆነ በተቃራኒው ደንበኛውን ይጎዳል፡፡ ደንበኛውምሆነ መ/ቤቱ ላይ ጉዳት

እንዳይደርስ መከላከል የሚቻለው የደንበኛውን ዓይነት በትክክል በመመዝገብ ይሆናል፡፡

አብነት1- መኖሪያ ቤት በሆነ ታሪፍ ሲከፍል የነበረን ደንበኛ መኖሪቤት ባልሆነ ታሪፍ

ለማስከፈል የቀረበ ምሳሌ ፡-

በአራዳ ቅርንጫፍክልል ነዋሪ የሆኑ ደንበኛ

 በውልቁጥር 22300 የሚጠቀሙበት ቤት መኖሪያ የነበረ ሲሆን

 ሰኔ 1/2012 ዓ.ም ጀምሮየንግድቤት ሆኗል ፡፡

 በሐምሌ 2012 ዓ.ም ጀምሮ “መኖሪያ ቤት ባልሆነ” ታሪፍ መያዝ ሲገባው በቀድሞው

“መኖሪያ ቤት” ታሪፍ ተይዞ እንደቀጠለ ነው፡፡

የሐምሌ 2012 የውሃ ፍጆታው 150M3ሆኖ የመጨረሻ ቆጣሪ ንባብ 650M3 ነው፡፡ የንባብ

ስህተት እንደሌላቸውና የቆጣሪው ስፋት ¾ መሆኑ ታውቋል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 39| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ውጤቱም እንደሚከተለው ቀርቧል ፡-

 በመኖሪያ ቤት ታሪፍ የተዘጋጀላቸው ቢል

5X2.40 12.00

15X4.85 72.75

20X9.71 194.20

60X14.57 874.20

50X19.42 971.00

የቆጣሪ ኪራይ 13.49

የጥገና 1% 21.24

የጽዳት 10% 212.41

ጠቅላላ ክፍያ 2,371.30

 በመኖሪያ ቤት ባልሆነ ታሪፍ የተዘጋጀላቸው ቢል

150X19.42 2,913.00

የቆጣሪ ኪራይ 13.49

የጥገና 1% 29.13

የጽዳት 19% 553.47

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 40| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ጠቅላላ ክፍያ 3,509.09

ከላይ ለማየት እንደተቻለው ብር 3,509.09 – 2,371.30 = 1,137.79 ነው፡፡

ልዩነቱ ሲተነተን

የውሃ ክፍያ 2,913.00—2,124.40= 788.85

የጥገና 1% 29.13-21.24 = 7.89

የጽዳት 19% 553.47-212.42 = 341.05

የቆጣሪ ኪራይ 0 .00 (የቆጣሪ ግብር ያልተካተተው ቀደም ሲል በቢልበመከፈሉ

ነው)

ድምር 1,137.79

ልዩነቱ በየአርዕስቱ ተተንተኖ ውጤቱ እኩል ሆኗል፡፡ በመሆኑም ቅርንጫፉየሐምሌ ወር 2012

ብር 1,137.79 ከላይ በተጠቀሱት አርዕስቶች ገቢማስደረግይኖርበታል፡፡ ስለሆነም “ከመኖሪያ

ቤትነት” ወደ “መኖሪያ ቤት ያልሆነ ታሪፍ ማስለወጥ በዋናነት የቆጣሪ አንባቢዎችተግባር

ሲሆን የቆጣሪ አንባቢ ተቆጣጣሪ፣ የቆጣሪንባብ፣ ቢል ዝግጅትና ሽያጭ ቡድን አስተባባሪና

ሌሎችም የሚመለከታቸው ለሥራውልዩ ትኩረት በመስጠት መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡

አብነት 2- መኖሪያ ቤት ባል ሆነ ታሪፍ ሲከፍል የነበረን ደንበኛ መኖሪ ቤት በሆነ ታሪፍ

ለማስከፈል የቀረበ ምሳሌ ፡-

 በመኖሪያ ቤት ባልሆነ ታሪፍ የተዘጋጀላቸው ቢል

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 41| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

150X19.42 2,913.00

የቆጣሪ ኪራይ 13.49

የጥገና 1% 29.13

የጽዳት 19% 553.47

ጠቅላላ ክፍያ 3,509.09

 መኖሪያ ቤት በሆነ ታሪፍ የተዘጋጀላቸው ሒሳብ

5X2.40 12.00

15X4.85 72.75

20X9.71 194.20

60X14.57 874.20

50X19.42 971.00

የቆጣሪ ኪራይ 13.49

የጥገና 1% 21.24

የጽዳት 10% 212.41

ጠቅላላ ክፍያ 2,371.30

ከላይ ለማየት እንደተቻለው ብር 3,509.09 – 2,371.30 = 1,137.79 ነው፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 42| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

 ከላይ በንግድ ቤት የወጣውን ሒሳብ ደንበኛው ከፍሎት ከመጣ ልዩነቱን ብር 1,137.79

ተመላሽ ሊደረግላቸው ይገባል ፡፡

 ደንበኛው ከላይ በንግድ ቤት የወጣውን ሒሳብ ሳይከፍል ካመለከቱ ተጣርቶ ከላይ

በተሳላው መኖሪያ ቤት በሆነው ታሪፍ ስሌት መሰረት የመጣውን ብር 2,371.30

በደረሰኝ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

6. ቆጣሪው ሮቢሾ በመገጠሙ ምክንያት የሚከናወን የሂሳብ እርማት

 ሮቢሾ ማለት የቆጣሪውን አቅጣጫ ለውጦ መግጠም ማለት ሲሆን ቆጣሪው

የሚቆጥረው ንባብ በመቀነስ ይሆናል፡፡

 አልፎ አልፎ ቆጣሪ ለምርመራ ተነስቶ ተመልሶ ሲቀጠል ወይም አዲስ ቆጣሪ ሲቀጠል

ቴክኒሽያኖች በስህተትአዙሮ /ሮቢሾ/ ሊገጥሙ የሚችሉበት ዕድል ወይም ሆን ተብሎ

ሂሳብ ለመቀነስ ሲባል በሕገ ወጥ መንገድ አዙረው ሲገጥሙ ነው፡፡

 በስህተት ለሚገጥሙ አዳዲስ ሥራ ለሚጀምሩ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ

ስልጠና በመስጠት እንዲሁም ነባሮችም ቢሆኑ ተከታታይየግንዛቤማስጨበጫ ሥራ

በመሥራት ችግሩን ማስወገድ ይቻላል፡፡

6.1 ለምርመራ የተነሳ እናተመልሶ በስህተት ሮቢሾ ከተገጠመ

ለምርመራ ተነሰቶ ተመልሶ ሲቀጥል በስህተት ሮብሾ የተገጠመ ከሆነ ቆጣሪው ይዞ

እንዲቀጠል ከተደረገው ንባብ እያንዳንዱን M3 በቆጠረ ቁጥር አንዳንድ M3 እየቀነሰ የቆጣሪ

ንባቡ ይሄዳል፡፡ ለአብነት አንድቆጣሪ 3212 M3ንባብ ይዞ ባለሙያዎችበስህተት ሮቢሾከገጠሙ

ቆጣሪው የሚቆጥረው ወደኋላ ስለሆነ አንድ M3 ሲቆጥር ንባብ 3211 M3 ተጨማሪ አንድ M3

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 43| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ሲቆጥር 3210 እያለ ይቀጥላል፡፡ በዚሁ መሰረት የተጠቀሰው ቆጣሪ ንባቡ 3190 M 3 ይዞ ሮብሾ

መሆኑ ታውቋል፡፡

ስለዚህ 3212-3190= 22 M3 የቀነሰው ንባብና የቆጠረው ፍጆታ ሲሆን3212 + 22 = 3234

M3 ቆጣሪው በትክክል ተገጥሞ ንባቡ ይህ ይሆን ነበር፡፡ ስለሆነም ቆጣሪው ተመርምሮ

የምርመራ ውጤቱ ትክክል ከሆነበ3234 M3ንባብ ተስተካክሎ ቆጣሪው ይቀጠላል፡፡

6.2 አዲስ ቆጣሪ ሮቢሾ ከተገጠመ

ለደንበኞች የሚገጠሙ አዲስ ቆጣሪዎች ቴክኒሽያኖች በስህተት አቅጣጫቸውን አዙረው

የሚገጠሙበት ዕድል አልፎ አልፎ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቆጣሪዎች ምንም /ዜሮ/ ንባብ ይዘው

ስለሚገጠሙ መድረሻ ንባብ የሚሆነው የቆጣሪው ዲጅት በሙሉ 9 ቁጥር ይሆናል፡፡ይህም

ማለት ሮብሾ የተገጠመቆጣሪ ባለ 4 ዲጂት ቢሆን4ቱምዲጂቶች በሙሉ 9 ሲሆኑ 9999

ይሆናል ፡፡ በመሆኑ በእያንዳንዱ M3 ፍጆታ አንዳንድ እየቀነሰ ወደኋላ ይቆጥራል፡፡ ለአብነት

የቆጣሪው ንባብ በመጨረሻ የተገኘው ንባብ 9920M3 ቢሆን ፍጆታው10000-9920= 80M3

ይሆናል፡፡

በዚህ ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሰው ሮብሾ ሆኖ የተገኘው የደንበኛው ፍጆታ 80 M 3 መሆን ሲገባ

የተገኘው 9920 M3 ነው፡፡ በሮብሾ ተገጥመው የተገኙ ቆጣሪዎች ተቆርጠው የቆጣሪ ምርመራ

ወርክሾኘ ለምርመራ ይላኩና ተመርምረው የምርመራ ውጤቱም በዚህምሳሌ ለተገለፀው የውሃ

ቆጣሪ 9920 M3 ንባብ ይዞ” ቆጣሪው ትክክል ይሰራል ሮብሾ በሚል የተነሳ ስለሆነ ለሂሳብ

ክፍል ይቅረብ “ የሚል ነው፡፡ በዚህ መልከ የቆጣሪ ምርመራውጤት የደረሰው የቆጣሪ ንባብ

ቢል ዝግጅትና ሽያጭ ቡደን የምርመራ ውጤቱን መነሻ በማድረግ፡-

1. ቆጣሪው በቅርብ ጊዜ መቀጠል አለመቀጠሉን፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 44| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2. የደንበኛውን የቀድሞ ቆጣሪ የነበረውን የፍጆታ መጠን አማካይ በወር፣

3 አዲስ ቆጣሪ በሮብሾየመጣውለውጥ አማካይ ፍጆታ በወር፣

4 ደንበኛው አዲሱ ቆጣሪ ከተቀጠለ በኋላ የሰራው ተጨማሪ ሥራ ካለ ወርሃዊ

ፍጆታ የሚጨምር መሆን አለመሆኑን ወይም የቀነሰው ሥራ ካለ ወርሃዊ

ፍጆታውን የሚቀንስ መሆን አለመሆኑን በማጠራትናበመተንተን የሂሳቡን

ትክክለኛነት አረጋግጦ ንባቡ ተስተካክሎ እንዲቀጠል የሥራ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡

ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱ ሁሉተጣርተው የቴክኒሽያን ስህትትመሆኑ ከታወቀ

የ80 M3 ሂሳብ ደንበኛ በተጠቀመበት ወራት ተተንትኖ ተዘጋጅቶእንዲከፍል

ይደረጋል፡፡ የቆጣሪው ንባብም በ80 M3 ተስካክሎ እንዲቀጠል ይደረጋል፡፡

6.3 በሕገ ወጥ መንገድ ሮቢሾ የተገጠመ ቆጣሪ፡-

6.3.1 አንዳንድ ደንበኞች ፍጆታ ከፍተኛ ሆኖ እያለ በሕገ ወጥ መንገድ በየጊዜው ቆጣሪውን

ሮብሾ በመግጠም የፍጀታቸውን መጠን በM 3እንዲቀንስ ያደርጋሉ፡፡

6.3.2 የፍጆታ መጠናቸው ሳይቀንስ ወደፊት መቁጠር የሚገባውን የውሃ ቆጣሪ አዙረው

በመግጠም አጠቃቀማቸው በጨመረ ቁጥር ቆጣሪው ወደኋላ እንዲቆጥር በማድረግ

በሕገ ወጥመንገድ የውሃ ክፍያቸው እንዲቀንስያደርጋሉ፡፡በዚህ ሕገ ወጥ ድርጊት

የባለሙያ እግዛ መኖሩይታወቃል፡፡

6.3.3 ደንበኛው ጥፋት መፈፀሙ ሲታወቅ ወዲያው ሕጋዊ እርምጃ መወሰድ አለበት ፡፡

የሚወሰዱ ሕጋዊ እርምጃዎችም፡-

1. ያለአንዳች ቅደመ ሁኔታ የውሃ አገልግሎት ማቋረጥና ይህንኑ ከ3 ያላነሱ

ባለሙያዎች እንዲያረጋገጥ ማድረግ፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 45| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2. ቆጣሪውን ማስመርመርና የምርመራ ውጤቱን ማግኘት፣

3. ከላይ ከተገኙ መረጃዎች ላይ የተመሰረተ ትክክለኛ ፍጆታ መገመት፣

4. ከተገመተው ፍጆታ የከፈሉትን ፍጆታ በመቀነስ የፍጆታ ልዩነትበM 3

ማግኘት፣

ምሳሌ፡- በጉርድ ሾላ ቅ/ጽ/ቤት

በውል ቁጥር 777777 ሲጠቀሙ የነበሩ ደንበኛ ሆን ብለዉ ሮብሾ (ቆጣሪ አዙረዉ) በመግጠም

ሲጠቀሙ በመገኛታቸው ቆጣሪው እንዲነሳ ተደርጓል፡፡

 በዚሁ መሰረት ከቆጣሪው ቀድሞ የተወሰደ ንባብ 620 ሲሆን ቆጣሪውን

አዙረው በመግጠማቸው ቀድሞ ከተወሰደው ንባብ ቀንሶ 530 ሆኖ

ተገኝቷል፡፡

 በመሆኑም ወደ ኋላ የተመለሰውን ንባብ ማለትም የ90ሜ.ኩ ባረፈበት

ታሪፍ በሙሉ ተሰልቶ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

ይኸዉም፡- 90ሜ.ኩ X 14.57 = 1,311.30

ጽዳትና ዉበት 10% =131.13

ጥገና 1% = 13.11

ቅጣት 655.00

ማስቀጠያ 499.00

ጠቅላላ ድምር2,609.54 በደረሰኝ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

ይሁንናየተመረመረው ቆጣሪ ትክክል የሚሰራ ከሆነ ከላይ በተሰላው ስሌት መሠረት ክፍያ

ተፈጽሞ የቆጣሪ ንባቡን አስተካክሎ ለደንበኛው ይቀጠላል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 46| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

የተመረመረው ቆጣሪ በትክክል የማይሰራ ከሆነ ላለመሥራቱ መነሻ የሆነው ደንበኛው

ባልተፈቀደ መንገድ የውሃ ቆጣሪውንበመነካካቱ ስለሆነ ከላይ በተሰላው ስሌት መሠረት

ከመጣው ሒሳብ በተጨማሪም የቆጣሪውን ዋጋ በማስከፈል አዲስ ቆጣሪ ለደንበኛ ይቀጠላል፡፡

7. ከቆጣሪ በፊት ሕገወጥ ቅጥያ በመፈፀሙ የሚደረግ የሂሳብ እርማት

ደንበኛው ከውሃ ቆጣሪ በፊትከባለስልጣኑ መስመር ወይም በደንበኛው ወጪ ባለስልጣኑ

ከዘረጋው መስመር (ውሃው በቆጣሪ ተቆጥሮ ወደ ደንበኛ ግቢ ሳይገባ ) ሕገ ወጥ መስመር

ቀጥሎ በነፃ ሲጠቀም ቢገኝ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የውሃ ቆጣሪውን በማንሳት ከመነሻ

እንዲቋረጥ ይደረጋል ፡፡

በዚህ አግባብ ለሚፈፀመው ሕገ ወጥነት፡-

1. ሕገወጥ መስመሩ ሲቋረጥ ወደፊት ምስክር ሊሆኑ የሚችሉ ከ3 ያላነሱ ባለሙያዎች

እንዲሁም በአካባቢው ያለ ፖሊስ እንዲያዩና ፎቶግራፍእንዲያነሱ በማድረግ በቆጣሪ

መቁረጫ የሥራ ትዕዛዝ ላይ የቆጣሪ ንባቡን በመሙላት ስማቸውን በመጻፍ

እንዲፈራረሙ ይደረጋል፡፡

2. ደንበኛውለደረሰው ጉዳት በሕግ እንዲጠየቅ መረጃ ተጠናቅሮ ለሕግና ኢንሹራንስ

ደጋፊ የሥራ ሂደት መላክና አፈፃፀሙን መከታተል ይገባል፡፡

3. ተቋሙ ላይ ለደረሰውም ጉዳትበተቋሙ ባለሙያዎች በሚቀርበው የ’’ሃይድሮሊክ

ኢንጅነሪንግ’’ ግምት መሰረት የሚጠየቁ ይሆናል ፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 47| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

8. በቆጣሪ ምርመራም ሆነ ንባብ ላይ ስህተት ሳይገኝ ክፍያቸው እጅግ በጣም የተጋነነ ሆኖ

በመገኘቱ የሚደረግ የሂሳብ እርማት

አልፎ አልፎ የውሃ ቆጣሪ ምርመራ ውጤት ቆጣሪው በትክክል እየሰራ መሆኑን እየገለፀ፤

በንባብም ላይ ችግር ሳይኖር፣ ደንበኛው ቀድሞ ከነበረውአጠቃቀም ለውጥ ሳይኖር እጅግ በጣም

የተጋነነ ሂሳብ የሚጠየቅበት ወቅት አለ፡፡ ይህንን ከግምት ውስጥበማስገባት የቅርንጫፍ ሥራ

አስኪያጁ በደንበኛው ጥያቄ መሠረት የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ አቋቁሞ የውሳኔ ሃሳብ

ተጣርቶእንዲቀርበለት ማድረግ ይችላል፡፡ ሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ አባላት ከቅርንጫፍ ሥራ

አስኪያጁ የተመራላቸውን መነሻ በማድረግ፡-

1. የደንበኛው ቆጣሪ ተመርመሮ ውጤቱ ትክክል መሆኑን፣

2. ከውሃ ቆጣሪ በኋላ ያለው የደንበኛው መስመር የማይታይ ፍሳሽ መኖር

አለመኖሩን ምርመራ ተደርጐ የምራመራ ውጤቱ የደንበኛው መስመር

የማይታይ ፍሳሽ የሌለ መሆኑ ማረጋገጥ፣

3. እጅግ ከፍተኛ የሆነው ሂሳብ የያዘው ቢል የመጨረሻ ንባብ በቆጣሪ

ምራመራ ውጤት ላይ ከተገለፀው የቆጣሪ ንባብ ያነሰ መሆኑን፣

4. ቀደም ሲል የደንበኛ አጠቃቀም አማካይ ፍጆታ ከነበረውበላይ በተጋነነ

መንገድ መጠየቁን፣

5. የቆጣሪ ንባብ የተጋነነ ሂሳብ ከመጠየቁ በፊት የነበረው የንባብ ሂደት

መገምገም፣

6. በቆጣሪው ላይ ካሉ ዲጂቶች አንዱየመዝለል አዝማሚያ ማሳየቱን

ከተጋነነሂሳቡ ጋር በማስተየየት መለየት፣

7. ደንበኛው ውሃን ለተለየ አገልግሎት መዋል አለመዋሉን ማረጋገጥ፣

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 48| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

እነዚህንና ሌሎችም ተገቢ መረጃዎች በመሰብሰብ ደንበኛው የተጠየቀው ሂሳብ እውነትም

ያለበቂ ምክንያት የተጋነነ ሆኖ ካገኘውቀድሞ ይከፍል በነበረው አማካኝ ፍጆታ መሠረት

ለመክፍል የሚያስችለውን የውሳኔ ሀሳብ ለቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ያቀርባል፡፡

የሂሳብ አጣሪ ኮሚቴ ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ የፀደቀ እንደሆነ

የቆጣሪ ንባብ፤ቢል ዝግጅትና ሽያጭ ቡድን አስተባባሪ ይህንኑ መነሻ በማድረግ የሂሳብ እርማት

እንዲሰራ በማድረግ ተገቢው ማስተካከያ ያደርጋል፡፡

ከላይ የቀረቡትን የደንበኞች የውሃ ፍጆታ ትክክል አለመሆኑን መነሻ በማድረግ የሚደረጉ

የሂሳብ እርማት ሪፖርቶች ለሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች በየጊዜ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ደንበኛው ውል ፈፅሞ ቆጣሪ ከተቀጠለ በኋላ ወደ ክፍያ ስርዓት ውስጥ ሳይገባ በቆጣሪዉ

ላይ አደጋ ቢደርስ፤ቢሰረቅ፤ደንበኛዉ ሆን ብሎ ቢሰዉረው ፤በተጨማሪም አንባቢው

አንብቦት የማያውቅ ከሆነ እና የመሳሰሉት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት ፡-

ደንበኛው ሲጠቀምበት የነበረውን የውሃ ፍጆታ ሒሳብ ለማስከፈል መጀመሪያ፡-

1. ውሃዉ የገባበትን ጊዜ እና ቀን ማጣራት

2. የደንበኛውን አይነት መለየት

3. ውሃው ከገባ በኋላ የተገነባ ግንባታ ስለ መኖሩ ማረጋገጥ

4. ደንበኛው ውሃውን ለሁለተኛ ወገን አሳልፎ እንዲጠቀም አለማድረጉን ማረጋገጥ

ይኖርብናል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት መረጃዎች ከተሰበሰበ በኋላ ፡-

5. የውሃ ፍጆታውን በ’’ሃይድሮሊክ ኢንጅነሪንግ’’ ግምት መሠረት የሚጠየቁይሆናል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 49| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

6. ቆጣሪዉ አደጋ ደርሶበት ከሆነ ለምርመራ ላብራቶሪ ገብቶ በውጤቱ መሠረት

የቆጣሪ ዋጋ ክፍያን እንዲሁም ቅጣትና ማስቀጠያን ጨምሮ ከከፈሉ በኋላ አዲስ

ቆጣሪ ወጪ ሆኖ ይቀጠልላቸዋል፡፡

7. ይህ በእንዲህ እንዳለ ሆኖ ቆጣሪ ከተሰረቀ ወይም ከተቃጠለ ከአከባቢው ፖሊስ

ጣቢያ ማስረጃ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ይኸውም ቆጣሪ በተሰረቀበት ወቅት

ወይም በተቃጠለበት እንዲሁም በሚሰበርበት ወቅት የፈሰሰው ዉሃ መጠን ከታች

በተገለፀው በ’’ሃይድሮሊክ ኢንጅነሪንግ’’ ግምት መሰረት ተሰልቶ እንዲከፍል

ይደረጋል፡፡

10. አማካኝ ፍጆታ አከፋፈልን በተመለከተ ፡-

ደንበኛው ውል ፈፅሞ ቆጣሪዉ ከተቀጠለ በኋላ ደንበኛዉ ውሃውን ሳይጠቀም ቢቆይና

አንባቢው በቆመ ቆጣሪ በሚል ቢያስነሳው እና የቆጣሪ ላብራቶሪ ምርመራ ዉጤት ትክክል

ይሰራል ከተባለ ፡-

I. ቆጣሪ አንባቢው ቆጣሪውን ከማስነሳቱ በፊት የደንበኛውን የውሃ አጠቃቀም ሁኔታ

ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

II. ቆጣሪ አንባቢው ሳያጣራ ቆጣሪውን ቢያስነሳ እና ደንበኛዉ ውሃውን አለመጠቀሙ

ከተረጋገጠ ያለምንም አማካኝ ሒሳብ ሳይሰላ ቆጣሪዉ ተመልሶ እንዲቀጠል

ይደረጋል ፡፡

III. ደንበኛው ውሃ እየተጠቀመ ቆጣሪ አንባቢዉ በሚያነብበት ወቅት በተከታታይ ከሶስት

ወር በላይ ቆጣሪው ቆሞ ከተገኘ ቆጣሪዉ ተነስቶ ላብራቶሪ በማስገባት በምርመራ

ውጤቱ መሰረት ዉሉ ላይ በተገለጸው ማለትም አንቀጽ 7 ’’ሠ’’ እንደተገለጸው ’’

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 50| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ደንበኛው የተጠቀመበት ዉሃ መጠን ቆጣሪው በመበላሸቱ ምክንያት በስህተት

ተመልክቶ ሲገኝ ደንበኛው ባለፉት ሶስት ወይም ስድስት ወራት ዉስጥ የከፈለው

የውሃ ዋጋ ከሁለቱ ለሱ የሚጠቅመውን መርጦ ማዕከላዊውን ግምት ይከፍላል ፡፡

ሰለሆነም ደንበኛው ከተለመደው አገልግሎት

ለተለየ ጉዳይ መዋሉን ባለሥልጣኑ ሲያረጋግጥ ደንበኛው ባለሥልጣኑ በተገቢ ሁኔታ

የሚወስነውን ዋጋ ይከፍላል’’፡፡

IV. ይሁንና የደንበኛው ቆጣሪ ለምርመራ ተነስቶ ሒሳብ በሚሰላለት ወቅት ከሙሉ ወር

ያነሰቀናት ካሉት አንባቢዉ ካነበበበት ቀንቆጣሪዉእስከተነሳበት ቀን ድረስ ያለውን

ልዩነት ለማስከፈል፤ ቀደም ሲል አንባቢዉ ንባብ ከወሰደበት ቀን እስከ ተነሳበት ቀን

ድረስ በማሃል ያሉትን ቀናቶች ጨምሮ የሚሰላ ይሆናል፡፡

ለምሳሌ፡-

 በዉል ቁጥር 777778

 ቆጣሪ ቁጥር SINO - 6210102

 የደንበኛዉ አይነት መኖሪያ ቤት

 ቆጣሪዉ የቆመበት ጊዜ ከሚያዝያ 2012 እሰከ ሐምሌ 9/2012

 ቆጣሪው ሲቆም የነበረው ንባብ 350M3

 የደንበኛዉ ወርሃዊ አማካኝ ፍጆታ 20M3

ከሚያዝያ እስከ ሐምሌ አራት ወር ሲሆን

20M3X4 = 80M3

ቆጣሪው ሲነሳ የቀረው ዘጠኝ ቀን የውሃ ፍጆታ መታሰብ ስላለበት፤

በ30 ቀን 20 M3 ከሆነ

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 51| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

በ9 ቀን ስንትይሆናል?

9 X 20 M3 = 180M3= 6M3

30ቀን 30

በመሆኑ ደንበኛዉ ሊከፍል የሚገባዉ የ86M3 ሒሳብ ይሆናልማለት ነዉ፡፡

V. አንድ አዲስ ደንበኛ ውል ተዋውሎ ቆጣሪ ካስቀጠለ በኋላ ቆጣሪው ለሶስት ወራት

እና ከዚያም በላይ ለሆኑ ጊዚያት ምንም ዓይነት የንባብ ለውጥ ሳያሳይ ቢቀር ፡-

 መጀመሪያ የደንበኛውን አይነት መለየት

 ውሃውን ተጠቅሞው በደንበኛው ቅጥር ግቢ ውስጥ ምንም ዓይነት ግንባታ

አለመገንባቱን እና ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ አለመስጠቱን ማረጋገጥ

 ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ከተጠናቀሩ በኋላ በ’’ሃይድሮሊክ ኢንጅነሪነግ’’

ግምት መሠረት እንዲሰራ ይደረጋል፡፡

11. በተለያየ ምክንያት ሒሳባቸውን ያልዘጉ ደንበኞችን በተመለከተ

የደንበኞች ቆጣሪ ፡-

I. በዕዳ ምክንያት ተነስቶ ቆጣሪው ገቢ ከሆነ

II. በዕዳ ምክንያት ተነስቶ ቆጣሪው ገቢሳይሆን ከቀረ

III. የማህበራት የጋራ ቆጣሪ ከሆነ

IV. በልማት ምክንያት የተነሳ ወይም የጠፋ ከሆነ እነዚህና መሰል ጉዳዮች

ሲያጋጥሙ ደንበኖች ያለባቸውን እዳ ሒሳብ ለማስከፈል እንዲያስችል

በሚከተለዉ መልኩ ይስተናገዳል

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 52| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

11.1 የደንበኞች ቆጣሪ ተነስቶ ገቢ ከሆነ

11.1.1 የደንበኛው ሥምና አድራሻ መለየት

11.1.2 ቆጣሪ ሲነሳ የያዘው ንባብ

11.1.3 ቆጣሪው ተነስቶ ገቢ የሆነበት ቀን

11.1.4 የገቢ ቁጥርመኖሩን ማረጋገጥ

11.1.5 ከላይ የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ከተረጋገጡ በኋላ የቢል ህትመቱ

እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡ የቢል ህትመቱ መቋረጡ ከተረጋገጠ በኋላ ፡-

11.1.6 ቆጣሪው ሲነሳ ከያዘው ንባብ በላይይዞ የታተመ ቢል የንባብ ስህተት ካለው

ታርሞ ውድቅ ይደረጋል፡፡

11.1.7 የደንበኛው ቆጣሪ ከተነሳበት ቀን በኋላ የታተመ ቢል ካለ ውድቅ

ይደረጋል፡፡

11.1.8 የደንበኛዉ ቆጣሪ ሲነሳ የያዘው ንባብ እና መጨረሻ የታተመው ቢል

የንባብ ልዩነት ካለው ልዩነቱ ሒሳቡ ተሰልቶ የክፍያ ሰነድ ይዘጋጅለታል፡፡

11.1.9 ከላይ የተዘረዘሩት ማስተካከያዎች ከተሰሩ በኋላ ደንበኛው ያለበት ዕዳ

በተቀማጭ ሒሳባቸው ተካክሶ ቀሪ ካለ ሰነዱ በአግባቡ ተደራጅቶ በህግ

አግባብ እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡

11.2 የደንበኛው ቆጣሪ በተለያየ ምክንያት ገቢ ሳይሆን ሲቀር

የደንበኛው ቤት እያለ የውሃ ቆጣሪዉ በቦታው ላይ ሳይኖርና ውዝፍ እዳው ከተቀማጭ

በላይ ከሆነ፡-

11.2.1 የደንበኛው ሥምና አድራሻ መለየት

11.2.2 ቆጣሪው ተነስቶ ገቢ አለመሆኑን ማረጋገጥ

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 53| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ከላይ የተጠቀሱት ከተረጋገጠ በኋላ ቢል እየታተመ ከሆነ የቢል ህትመቱ

እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡

11.2.3 ለደንበኛው የመጨረሻ የታተመ ቢል ላይ ያለ ንባብ የያዘ የማስቆረጫ

ሥራ ትዕዛዝ በቆ/ን/ቢ/ዝ/ሽ/ቡ/አስተባባሪ ተዘጋጅቶ ደንበኛው እንዲከፍል

ይደረጋል ፡፡

11.2.4 ከላይ በተጠቀሰው መሰረት ደንበኛው ለመክፈል ፍቃደኛ ካልሆነ ሰነዱ

በአግባቡ ተደራጅቶ በህግ አግባብ እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡

11.3 የደንበኛው ቤት በልማት ወይም በተለያየ ምክንያት ፈርሶ ቆጣሪው ገቢ ሳይሆን


ሲቀር ፡-

11.3.1 የደንበኛው ያለበት እዳ ካለው ተቀማጭ በላይ መሆኑን ማረጋገጥ

11.3.2 ቤቱ በቦታው ላይ አለመኖሩን ማረጋገጥ

11.3.3 ቆጣሪው ገቢ አለመሆኑን ማረጋገጥ

11.3.4 ቤቱ መቼ እንደተነሳና ወይም እንደፈረሰ ከወረዳው መስተዳድር እና

በቅርብ ካሉ ከአከባቢ ነዋሪዎች ተቋሙ በሚልካቸው ሰራተኞች ማጣራት

11.3.5 ለደንበኛው የመጨረሻ የታተመ ቢል ላይ ያለ ንባብ የያዘ የማስቆረጫ

ሥራ ትዕዛዝ በቆ/ን/ቢ/ዝ/ሽ/ቡ/አስተባባሪ ተዘጋጅቶ ደንበኛው እንዲከፍል

ይደረጋል ፡፡

11.3.6 ከላይ የተዘረዘሩት ማስተካከያዎች ከተሰሩ በኋላ ደንበኛው ያለበት ዕዳ

በተቀማጭ ሒሳባቸው ተካክሶ ቀሪ ካለ ሰነዱ በአግባቡ ተደራጅቶ በህግ

አግባብ እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 54| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አንቀጽ-14-
የክፍያ ጊዜ ስለማራዘም

1. በተለያየ ምክንያት ክፍያ የተወዘፈባቸው ደንበኞች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት

ባለሥልጣን መ/ቤቱ በቂ ምክንያት አላቸው ብሎ ሲያምን የክፍያ ጊዜ በማራዘም

እንዲፈክፍሉ መፍቀድ ይችላል ፡፡

2. ለደንበኞች የሚሰጠው የክፍያ ማራዘሚያ ጊዜ ከውዝፍ ሂሳቡ የወራት ብዛት ሊበልጥ

አይችልም / በላይ መሆን የለበት፡፡

3. ውዝፉ የብዙ ወራት ቢሆንም ለደንበኛዉ ከዘጠኝ ወራት በላይ የክፍያ ጊዜ

አይራዘምለትም፡፡

4. ውዝፍ ክፍያውን ደንበኛው በየወሩ ሊከፍል በተፈቀደለት ጊዜ ወይም ወቅት

ሳይከፍል ከቀረ ለመክፈል ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ የውሃ አገልግሎት እንዲቋረጥ

ይደረጋል፡፡ ባለስልጣኑ በውሉ መሠረት ለማስከፈል በሕግ ለመጠየቅ መብት አለው፡፡

5. የክፍያ ጊዜ ማራዘሚያ ለመፍቀድ ውክልና የተሰጣቸው አካላት፣

5.1 የቆጣሪ ንባብ፣ ቢል ዝግጅትና ሽያጭ ቡድን አስተባባሪ እስከ አሥር ሺ ብር

ድረስ ከ3 ወራት፣ ባልበለጠ መስጠት ይችላል

5.2 የሥራ ሂደት መሪ እስከ ሃምሳ ሺ ብር ድረስ ከ6 ወራት ባልበለጠ መስጠት

ይችላል፡፡

5.3 ከሃምሳ ሺ ብር በላይ ለሚጠየቁ የጊዜ ገደቦች በቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጁ

ይወሰናል፡፡

6. የቆጣሪ ንባብ፣ ቢል ዝግጅችና ሽያጭ ቡድን ከላይ የተጠቀሱትን በመከታተልና

በማስከፈል ለሥራ ሂደት መሪው በየወሩ ሪፖርት ያቀርባል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 55| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አንቀጽ-15-
ቆጣሪ ለምርመራ ማንሳት እና መልሶ መቀጠል

1. በተለያዩ ምክንያታዊ ኮዶች ለምርመራ የሚነሱ

የቆጣሪ ምርመራ ስራ አሁን ባለው አሰራር ጥያቄዉ የሚቀርበዉ በደንበኞች አገልግሎት ሥራ

ሂደት ሆኖ ሳለ ስራዉ እየተሰራ ወይም እየተተገበረ ያለዉበNRW ክፍል ነዉ፡፡ይሁንና ባለው

አሰራር ለደንበኛዉም ሆነለተቋሙአመቺ ባለመሆኑ ስራዉን በመፈተሸ ተግባርና ኃላፊነቱን

ለዉሃ ደንበኞች አገልግሎት እንዲሆን ቢደረግ የደንበኞችን እንግልትና ምልልስ ሊቀርፍ

ይችላል፡፡

በመሆኑም ቆጣሪ ለምርመራ የሚነሳዉ ባለስልጣን መ/ቤቱ ባስቀመጠዉ አስተዳዳራዊ እና

ቴክኒካዊ ኮዶች፤ እንዲሁም በደንበኛ ሒሳብ በዛብኝ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ስለሆነ እነዚህ

ተግባራት መነሻቸዉ ደግሞ ከቆጣሪ ንባብ ጋር በተያያዘ በመሆኑ እና ይህም የቆጣሪ ንባብ

ሥራ በደንበኞች አገልግሎት ስርያለሥራ ስለሆነሥራውንም እየተከታተለ ተጠያቂነት ባለዉ

መልኩ ለመፈጸም ያስችል ዘንድ በዚህ ዘርፍ መሰራት ይኖርታል፡፡

2. ደንበኛው በሂሳብ በዛብኝ ጥያቄ መስመር እና ቆጣሪ እንዲመረመር ሲጠይቅ

ደንበኞች በየወሩ ይከፍሉት የነበረው ሂሳብ ከሌላ ጊዜ የተለየ (ከፍ) ያለ እንዲከፍሉ ሲጠየቁ

ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ የሂሳብ በዛብኝ ጥያቄ በማቅረብ በደንበኛው ፍላጎት መስመሩ ወይም

ቆጣሪዉ እንዲመረመርላቸው ሊጠይቁ ይችላሉ ፡፡ የደንበኛውን ጥያቄ መሠረት በማድረግ ፡-

I. የንባብ ሥህተት ካለው ቆጣሪ አንባቢ እና ንባብ አስተባባሪ አረጋግጠው እንዲታረም

ይደረጋል፤

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 56| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

II. የንባብ ስህተት ከሌለው የመስመር ማስመርመሪያ ብቻ ደንበኛው እንዲከፍል

ተደርጎ የውስጥ መስመሩ እንዲመረመር ይደረጋል፡፡ መስመሩ ላይ ፍሳሽ እንዳለው

ከተረጋገጠ መስመሩን እንዲያሰሩ ለደንበኞቹ ተነግሮ የመጣው ሂሳብ እንዲከፍሉ

ይደረጋል፡፡

III. የውስጥ መስመሩ ችግር ከሌለው በተጨማሪ የቆጣሪ ማስመርመሪያ ከፍለው

ቆጣሪተመርምሮየምርመራዉ ውጤት ሂሳቡን የማያስቀይር ከሆነ የደንበኞች

አጠቃቀም ስለሚሆን ደንበኞች የተጠየቁትን ሂሳብ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ-16-
ቆጣሪ በዕዳ ማንሳት እና መልሶ መቀጠል

ደንበኛዉ በገባው ዉል መሰረት ወርሃዊ ፍጆታውን በወቅቱ ባለመክፈሉ ምክንያት ቆጣሪው

በዕዳ ሊነሳ ይችላል፡፡ ይህም የሚሆነው፡-

I. ደንበኛው በሁለት ወር (በ60 ቀናት) ውስጥ ወርሃዊ የውሃ ፍጆታ ክፍያውን

ካልፈፀመ ቆጣሪው በእዳ ተነስቶ ገቢ ይደረጋል ፡፡

II. ቆጣሪ በእዳ እንዲነሳ ስራ ትዕዛዝ የተዘጋጀላቸዉንደንበኞች ዝርዝር

በቆ/ን/ቢ/ዝ/ሽ/ቡ/አስተባባሪ ተፈርሞ ሲቀርብ ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

III. ቆጣሪውን የሚያነሳው ባለሙያም በማስቆረጫ ሥራ ትዕዛዙ ላይ የደንበኛው ሙሉ

ስም ፤የውል ቁጥር እና የቆጣሪ ቁጥሩ በትክክል መገለፁን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

IV. ቆጣሪውን የሚያነሳው ባለሙያ በዕለቱ ቆጣሪው ላይ ያለውን ንባብ፤ሙሉ

ሥሙን እና ቆጣሪው የተነሳበትን ቀን መዝግቦ መፈረም ይኖርበታል፡፡

V. ደንበኛው ያለበትን እዳ ከባንክ ወለድ እና ከቆጣሪ ማስቀጠያ ጭምር ከከፈለ በኋላ

የተነሳው ቆጣሪ ተመልሶ ይቀጠላል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 57| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

VI. ደንበኛው በስልሳ (60) ቀናት ውስጥ መክፈል ካልቻለ የቢል ህትመቱ እንዲቋረጥ

ተደርጎ ያለባቸውን እዳ ከተቀማጭ እንዲካካስ ይደረግና ቀሪ ሒሳብ ካለባቸው በህግ

አግባብ እንዲጠየቁ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ-17-
የተከለከሉ ተግባራት

1 በውል ቁጥሩ የተቀጠለ የውሃ ቆጣሪን መስበር፤ ማንሳት፤ እሽጉን ማላቀቅ፣

የቆጣሪዉን ንባብ ወደ ኃላ መመለስ፣ የባለስልጣኑ ንብረት ባልሆነ ቆጣሪ መቀየርና

አዙሮ መግጠም የተከለከለ ነዉ ፡፡ ይህንን ተግባር ደንበኛው ፈፅሞ ቢገኝ በህገ- ወጥ

መንገድ የተጠቀሙበትን እና የባከነ ውሃ ክፍያ ባለስልጣኑ ለዚህ አይነት ጥፋት

ባስቀመጠው ከፍተኛ የውሃ ታሪፍ መሰረት ተሰልቶ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

2 ከቆጣሪ በፊት ያለውን የውሃ መስመር መዘርጋት፣ መጠገን፣ መቀየር፣ ማሻሻል፣

መስበር እና በተለያያ ምክንያት ተሰብሮ ውሃ ሲባክን እያዩ ያለማመልከት

አገልግሎቱን በማቋረጥ ደንበኛውን ተጠያቂ ያደርጋል፡፡

3 ከቆጣሪ በኃላ ለሌላ ሰው መጠቀሚያ የውሃ መስመርመዘርጋት ወይም እንዲዘረጋ

መፍቀድ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡

4 የውሃ ቆጣሪው የተቀጠለበት ቦታ ለቆጣሪ አንባቢው ስራ ምቹ አለማድረግ ወይም

በቆጣሪው ላይ ዕቃ ማስቀመጥ የለበትም ፡፡

5 የውሃ ቆጣሪ ደህንነትና ቆጣሪው ያለበትን አካባቢ ንጽህናን መጠበቅ አለበት፤

6 የደንበኛው የውሃ መስመር ውስጥ የሚመጣው ውሃ በቀለሙ፣በጣእሙ እና በሽታም

ያልተለመደ ሁኔታ ያለው ወይም የተበከለ መሆኑ ታውቆ የባለስልጣኑ ባለሙያ

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 58| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

የተበከለውን ውሃ እንዳይጠቀሙ ካሳወቀበት ሰዓት ጀምሮ ችግሩ ተፈትቶ እንዲጠቀሙ

አስኪያሳውቅ ድረስ ደንበኛው ውሃውን መጠቀም የለበትም ፣

7 የውሃ ስርጭት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን በመነካከት የፈረቃ ፕሮግራም

ማዛበት፤የባለስልጣን መ/ቤቱን ገጽታ የሚያበላሽ ያልተረጋገጠ መረጃ ይዞ

ህብረተሰቡን ማሳሳት፣ የውሃ መሸጥ፣ ከመስመር ላይ የግፊት መስጭያ ፓምፕ

መግጠም ፣የመንግስት የውሃ መስመር የተዘረጋበት ቦታ ወይም የውሃ መስመር ላይ

አጥር ማጠር ፣ወደ ግቢው ውስጥ ማስገባት ፣ የጎርፍ መሄጃ ቦይ በላዩ ላይ

መገንባትን፣ የውሃ ማንሆል ላይ ቆሻሻ መድፋት፣ ከቦኖ ውሃ ከቆጣሪ በኃላ የውሃ

መስመር ወደ ግለሰቦች ቤት መዘርጋት፣ከቆጣሪው በፊት መስመር መዘርጋት እና

የውሃ እጥረት በሚኖርበት ጊዜ ባለሥልጣን መ/ቤቱ ከሚፈቅደው የውሃ አጠቃቀም

ውጭ ደንበኛው መጠቀም ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡

8 በአንቀጽ 17 ንኡስ አንቀጽ 1 አስከ 7 የተጠቀሱትን ፈጽሞ የተከለከሉ ተግባራት

ተላለፎ የተገኘ ደንበኛ ለተጎዳው መስመር እና ቆጣሪ ለመጠገኛ ወጭ፣ ለባከነ ውኃ

፣በዚህ ምክንያት ባለስልጣኑ የቀረበትን ማናቸውምገቢ፤ ባለስልጣኑ ላይ ለደረሰው ሌላ

ጉዳትና ኪሳራ ኃላፊ ይሆናል በድርጊቱም በወንጀል ተጠያቂ ይሆናል፡፡

ክፍል አራት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

አንቀጽ-18-
መመሪያውን በግልጽ ስለማሳወቅ

የባለስልጣኑ የሥራ ክፍሎችና ፈፃሚዎች የሚመለከታቸውን አካላትና የባለስልጣኑን ደንበኞች

ስለ አሰራሩ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው የማሳወቅ ግዴታ አለባቸው፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 59| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አንቀጽ-19-
የመተባበር ግዴታና ኃላፊነት

1. የመተባበር ግዴታ

ማንኛውም ሰው መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም ህግና ደንብ

እንዲያስከብር ስልጣን የተሰጠው አካል ይህንን መመሪያ ለማስፈፀም በሚደረግ ማናቸውም

እንቅስቃሴ ጥፋት ተፈፅሞ ሲገኝ ትብብር እንዲያደረግ ሲጠየቅ የመተባባር ግዴታ አለበት፡፡

2. የደንበኞች ግዴታና ኃላፊነት

2.1 ደንበኞች የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው፡፡

2.2 ደንበኛዉ ላቀረቡት ሰነዶች ህጋዊ ስለመሆናቸው ሃላፊነት ይወስዳሉ ሰነዱ

ህጋዊነት የሌለው ሆኖ ከተገኘ በህግ አግባብ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡

2.3 የተዘረጋላቸውን የውሃ መስመር በአግባቡ የመያዝ እና የመጠበቅ ሃላፊነት

አለባቸው፡፡

2.4 የውሃ ቆጣሪ ከባለሰልጣኑ ፍቃድ ውጭ ከቦታ ቦታ ማዛወር የተከለለ ተግባር

ነው፡፡

2.5 ሠ.የውዝፍ ክፍያ ጊዜ ተሰጥቷቸው እንዲከፍሉ የተፈቀደላቸው ደንበኞች በወቅቱ

ክፍያ የመፈፀም ግዴታና ሃላፊነት አለባቸው፡፡

3. ቅሬታ የማቅረብ መብት

በዚህ መመሪያ የተጣለበትን ግዴታ ተወጥቶበተገቢው መገንድ አገልግሎትያላገኘ ደንበኛ

በባለስልጣኑ መ/ቤት ለቅሬታና አቤቱታሰሚ ኮሚቴበፅሑፍ ቅሬታውን ወይም አቤቱታው

ማቅረብ ይችላል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 60| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

አንቀጽ-20-
ተጠያቂነት

1. በዚህ መመሪያ የተጣለበትን ግዴታ ያልተወጣ ፤ተግባሩን በአግባቡና ዲስኘሊን

በተሞላበት ሁኔታ ያልፈፀመ፤ የሥራ መሪ ወይም ፈፃሚ አግባብ ባለው የባለስልጣኑ

የሥራ መሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ወይም በህብረት ስምምነት ወይም በሀገሪቱ ህግ

መሠረት ተጠያቂ ይሆናል፡፡

2. በዚህ መመሪያ መሠረት መብትና ግዴታውን በአግባቡ ያልተወጣ፤ ያሳሳተ ወይም

የሃሰት መረጃ የሰጠ ተገልጋይ አግባብ ባለው የሀገሪቱ ህግ መሠረት ተጠያቂ

ይሆናል፡፡

3. የመመሪያው ሕጋዊነትና ሃላፊነት በተመለከተ ደንበኞች ይህንን መመሪያ በመተላለፍ

የሚፈፀም ግድፈት /ጥፋት በዚህ መመሪያ እናበደንብ ቁጥር 31/1994 የተደነገጉት

ድንጋጌዎች የተመለከቱት ግዴታዎችና ሃላፊነቶች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

4. እንደየአገልግሎቱ ዓይነት ከአንቀጽ 4 እስከ አንቀጽ 18 ለሚሰጡ አገልገሎቶች

የተሳሳተ መረጃ ማቅረብ አግባብ ባለው ህግ ያስጠይቃል፡፡ አገልግሎቱን ያገኙ ከሆነም

እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ-21-
ቅጣት

1. በዚህ መመሪያ ላይ ጥሰት የሚፈፅም ሰራተኛ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96

እና በህብረት ስምምነቱ መሠረት የዲሲፕሊን ቅጣት እና አግባብነት ባላቸው

የወንጀልና ፍትሐብሄር ሕጎች ተጠያቂ ይሆናል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 61| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

2. በዚህ መመሪያ ላይ ጥሰት የሚፈፅም ሃላፊ ወይም የሥራ መሪ በስራ መሪዎች

መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እና አግባብነት ባላቸው የወንጀልና ፍትሐ/ብሄር ህጎች

ተጠያቂ ይሆናል፡፡

አንቀጽ-22-
ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃራኑ መመሪያዎች ወይም አሰራሮች በዚህ መመሪያ ውስጥ

በተመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖራቸውም፡፡

አንቀጽ-23-
መመሪያው ስለሚሻሸልበት ሁኔታ

በባለስልጣኑ የአደራጃጀት ለውጥ ሲኖር ወይም አሰራር ላይ ለውጥ ካደረገ ይህንን መመሪያ

እንደ አስፈላጊነቱ ሊያሻሽል ይችላል፡፡

አንቀጽ-24-
መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በዋናው ሥራ አስኪያጅ ተፈርሞበት እና የመ/ቤቱ ማህተም ካረፈበት ቀን ጀምሮ

ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን


ዋና ሥራ አስኪያጅ

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 62| ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

Hydraulic Engineering Estimation

Pipe .Dia pipe Min.Velocity Max.Velocity Area Discharge Discharge Discharge Per.Capita.Dem
NO Diameter
(mm) (V) m/s (V) m/s (A) m2 (m3/s) (m3/day) (m3/hr) and (l/c/d)
(inch)
1 0.1 4" 0.6 2.5 0.0079 0.0047 406.94 16.956 110
0.020 1695.60 70.65 110
2 0.08 3" 0.6 2.5 0.0050 0.0030 260.44 10.85184 110
0.013 1085.18 45.216 110
3 0.075 2 1/2" 0.6 2.5 0.0044 0.0026 228.91 9.53775 110
0.011 953.78 39.740625 110
4 0.063 2" 0.6 2.5 0.0031 0.0019 161.52 6.7298364 110
0.008 672.98 28.040985 110
5 0.05 11/2" 0.6 2.5 0.0020 0.0012 101.74 4.239 110
0.005 423.90 17.6625 110
6 0.04 1 1/4 " 0.6 2.5 0.0013 0.0008 65.11 2.71296 110
0.003 271.30 11.304 110
7 0.025 1" 0.6 2.5 0.0005 0.0003 25.43 1.05975 110
0.001 105.98 4.415625 110
8 0.02 3/4" 0.6 2.5 0.0003 0.0002 16.28 0.67824 110
0.001 67.82 2.826 110
9 0.015 1/2" 0.6 2.5 0.0002 0.0001 9.33 0.3888 110
0.0005 38.88 1.62 110
Minimum
maximum

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 63 | ገ ፅ


የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን

ይህ የውሃ ስሌት ሲሰራ በደንበኛው መኖሪያ አካባቢ ያለውን የውሃ ስርጭት ሁኔታን (ፈረቃን)
ታሳቢ መደረግ ይኖርበታል ፡፡

 የደንበኛው የቧንቧመጠን ወይም ስፋት ¾ ኢንች ቢሆን፡-


 ደንበኛው ህገወጥ ስራ የሰራበት ወይም የተጠቀመበት ጊዜ 30 ቀን ቢሆን፡-
 ደንበኛ በሳምንት ሶስት ቀን ውሃ የሚያገኝ ከሆነ ፡-
ምሳሌ፡-
 በ3/4 ኢንች በቀን በዝቅተኛ የሚያልፈው የውሃ መጠን 16.28 ሜ.ኪ. ሲሆን
 ደንበኛው በሳምንት ሶስት ቀን ውሃ ስለሚያገኝ በሰላሳ ቀን ውስጥ 12 ቀን ብቻ ያገኛል
ተብሎ ቢታሰብ፤-

ሂሳብ አሰራሩም፡-

 በ3/4 ኢንች ያለፈው የውሃ መጠን x ደንበኛው ውሃ ያገኘበት ቀን ብዛት= ደንበኛው


መክፈል የሚገባው የገንዘብ መጠን (ይህ ሂሳብ ማስቀጠያና ቅጣትን አያካትትም)

16.28 ሜ.ኩ x12ቀን =195.36 ሜ.ኩ

የውሃ ሂሳብ 195.36 ሜ.ኩ x19.42 = 3,793.89

የውበትና ፅዳት 10% 3,793.89 x 10% = 379.39

ጥገና1% 3,793.89 x 1% = 37.93

ጠቅላላ ድምር 4,211.21 በዚህ መንገድ ሂሳቡ ተሰርቶ እንዲከፈል ይደረጋል፡፡

 ይህ ውጤት በፈረቃው መሰረት ደንበኛው ውሃ የሚያገኘው በወር (በ30ቀን) ውስጥ 12


ቀን ብቻ በመሆኑተሰልቶ የመጣ ነው፡፡
 ከላይ በአንቀጽ13 ንዑስ አንቀጽ 8 እና 9 እንደተገለጸው በህገወጥ መንገድ የፈሰሰውን
ወይም የተጠቀመውን የውሃ መጠን ለማስከፈል ከላይ በምሳሌ በተገለፀው መሰረት
የመጣውን ሜትር ኪዩብ ባረፈበት ታሪፍ ተባዝቶ ደንበኛው እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

የዉሃ አቅርቦት አገልግሎቶች የአፈፃፀም መመሪያ 64 | ገ ፅ

You might also like