You are on page 1of 8

በከተሞች ውስጥ ህገ ወጥ ይዞታና ግንባታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ መመሪያ 37/2000

የመመሪያው አስፈላጊነት
በከተሞች ውስጥ ይዞታዎች ላይ የተገነቡ ህገ-ወጥ ግንባታዎችን

ከከተማ ኘላን አንፃር በማየት የማስተካከያ ዕርምትና ዕርምጃዎችን


መውሰድና ሌሎች ህገ-ወጥ ይዞታዎችንና ግንባታዎችን
እንዳይካሄዱ መከላከል የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣
በህገ-ወጥ ይዞታና ግንባታ ሳቢያ ለልማት አስፈላጉ የሆኑ ቦታዎች

ያለአግባብ ተይዘው ልማቱ በተገቢው መንገድ እንዳይከናወን


እንቅፋት ሆኖ በመገኘቱ፣
 የከተማ መሬት ውስን ሀብት በመሆኑ፣ በቁጠባና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ
መሪ ኘላኑን ተከትሎ ለተለያዩ የልማት አገልግሎቶች ማዋል አስፈላጊ
በመሆኑ፤
 ህገ-ወጥ ግንባታ ለፀጥታ፣ ለደህንነትና ለማህበራዊ ዋስትና ስገት
ከመሆናቸውም ባሻገር የቤቶችንና የመንደሮችን መተፋፈግ
የሚያስከትል መሆኑ ስለታመነበት፤
 በክልሉ ባሉ ከተሞች በህገወጥ መንገድ የተያዙ ይዞታዎችና ተስፋፍተው
የሚገኙ ከመሆናቸው ባሻገር በህገወጥ የተያዙ ይዞታና ግንባታዎች
በከተማው መሪ ኘላን መሰረት ለተለያዩ አገልግሎቶች የተመደቡ
ቦታዎችን በአግባቡ ልማት ላይ ለማዋል እንቅፋት ከመሆናቸው በላይ
የከተማ ቦታ እጥረት ወይም ችግር እንዲባባስ የተደረገ በመሆኑ፣
 የውሃ ቦዩችን በመዝጋት፣ መንገዶችን በማጣበብና ሌሎች ማህበራዊ
ችግሮችን በመፍጠር የከተማውን ውበት በማበላሽት ረገድ እያስከተሉት
ያለው ችግር ከፍተኛ በመሆኑ፣
 
3.ህገ-ወጥ ይዞታዎችንና ግንባታዎችን ስለመለየትና ዕርምጃ
ስለመውሰድ
 በከተማ አስተዳደር ከተሞች ላይ የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤቶች

በዚህ መመሪያ መሰረት ህገ-ወጥ ይዞታና ግንባታ በመለየት መረጃ


ይይዛሉ፣
 በማዘጋጃ ቤቶችና ታዳጊ ከተሞች ላይ ሕገ-ወጥ ይዞታንና

ግንባታን በመለየት መረጃ የሚይዝ 7 አባላት ያሉት የቴክኒክ


ኮሚቴ ይቋቁሟል፡፡
 የቴክኒክ ኮሚቴው አባላት ከከተማ ማዘጋጃ ቤት፣ ከቀበሌ

አስተዳደር ጽ/ቤቱ፣ ከአካባቢው ፖሊስ ጽ/ቤት፣ ከፍትሕ


፤ፍ/ቤት፣ ከወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት እና ከአካባቢ ጥበቃና መሬት
አስተዳደር ጽ/ቤት የተውጣጡ ይሆናሉ፡፡ /ወረዳ አስተዳደር
ጽ/ቤት ሰብሳቢና የከተማው ማዘጋጃ ቤት ፀሐፊ ይሆናሉ፡፡/
4.የከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት /የቴክኒክ ኮሚቴው/ በዚህ መመሪያና በከተማ
ኘላን አፈፃፀምና ቦታ አስተዳደር ደንብና መመሪያዎች መሰረት ተለይቶ
የተያዙትን ሕገ-ወጥ ይዞታዎችንና ግንባታዎችን ካስተያየት ጋር በቃለ ጉባኤ
ለከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ወይም ለወረዳው አስተዳዳር ጽ/ቤት
ያቀርባል፡፡
5. በከተማ አገልግሎት ጽ/ቤቶች /በቴክኒክ ኮሚቴ ተጣርቶ የቀረበውን ሕገ-
ወጥ ይዞታና ግንባታ የከተማ አስተዳደር ካቢኔ ወይም የወረዳ አስተዳደር ካቢኔ
መርምሮና አጣርቶ እንደ የአግባቡ በመለየት ውሳኔ ይሰጣል፡፡ ውሳኔውን
የከተማ አገልግሎቶችና ማዘጋጃ ቤቶች ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
6. በዚህ መመሪያ አፈፃፀም ቅር የተሰኘ ማንኛውም አካል ውሳኔ በተሰጣቸው
በ3ዐ ቀን ውስጥ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል መሬት ስለሚለቀቅበት ሁኔታ ቅሬታን
ለማስተናገድ በከተሞች ውስጥ የተቋቋመው ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ
ይችላል፡፡ በሜትሮፖሊታን የከተማ አስተዳደሮች ቅሬታው የሚቀርበው
በከተማው ለተቋቋማው የከተማ ነክ ጉዳዩች ፍ/ቤት ይሆናል፡፡ ይህ የቅሬታ
ኮሚቴ ባለተቋቋመባቸው ከተሞች እንዲቋቋም ተደርጐ የሚቀርቡ
ቅሬታዎች እንዲታዩ ይደረጋል፡፡
4. ህገ-ወጥ ይዞታዎችና ግንባታዎች ህጋዊ ስለሚሆኑበት ሁኔታ፣
1.ግንባታዎች በከተማው ኘላን መሰረት ከተሰጠው የአገልግሎት ምደባ
ጋር የሚጣጣም፣ የዲዛይን ሕግጋቶችን የጠበቀ፣ በኘላን ላይ
የተቀመጠውንም ይሁን በሽንሸና በሚከፈቱ መንገዶች ላይ ችግር
የማያስከትል መሆኑ ሲረጋገጥ፤
2.በህገ-ወጥ ይዞታ ላይ የተገነቡ ግንባታዎች ሆነው በዚህ አንቀጽ ንዐስ
አንቀጽ 1 ላይ የተመለከተውን አሟልተው ሲገኙ የግንባታውን ግምት
16/100 ተቀጥተው ህጋዊ ይደረግላቸዋል፡፡
5. ህገ-ወጥ ግንባታዎች ስለሚነሱበትና ስለሚፈርሱበት ሁኔታ፡-
1.በአስተዳደሩ ተጣርቶ በቀረበውና እንዲፈርስ በተወሰነው መሰረት
ተነሽዎች ውሳኔ ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ ቤት ገንብተው እየኖሩበት
ከሆነ በ3 ወር ጊዜ፣ ግንባታ ከሌለው በ15 ቀን ውስጥ ንብረታቸውን
በማንሳት እንዲያፈርሱ ወይም እንዲለቁ በግልፅ በደብዳቤ ያሳውቃል፡፡
2. በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያላፈረሱ እንደሆነ በከተማ
የሚቋቀመው የአፍራሽ ግብረ ኃይል ኮሚቴ እንዲፈርስ ይደረጋል፡፡
3.በህገ-ወጥ መንገድ ለሚፈርሱ ግንባታዎች የካሳ ክፍያ
አይከፈልም፡፡
 በህገ-ወጥ ግንባታ የፈረሰባቸው በከተው ውስጥ ምንም አይነት

ቤት እንደሌላቸው ተረጋግጦ የጋራ መኖሪያ ቤት በተገነባባቸው


ከተሞች ቅድሚያ ተሰጥቶአቸው እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡ ከነዚህ
ውጭ ባሉ ከተሞች ውስጥ ያሉ ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት
መስሪያ ቦታ ቅድሚያ የሚያገኙበትን ከተሞቹ እንዲያመቻቹ
ይደረጋል፡፡
6.ስለ ህገ-ወጥ ግንባታ አፍራሽ ኮሚቴ ማቋቀም፡-
1.በህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ ይዞታዎችና የተገነቡ ግንባታዎች
በከተማ አስተዳደርና በወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት እንዲነሱ
ከተወሰነ በሚቋቋመው የአፍራሽ ኮሚቴ እንዲፈርስ ይደረጋል፡፡
2.በከተማ አስተዳደሩ ወይም ወረዳ አስተዳደሩ ከ6 ሴክተር
መ/ቤቶች የተወጣጡ የአፍራሽ ኮሚቴ አባሎች ያዋቅራል፡፡
የኮሚቴው ስብስጥርም
1.ከንቲባ ጽ/ቤቱ ወይም ወረዳ አስተዳደሩ የሚወክለው ሰብሳቢ
2.ከከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ወይም ከማ/ቤት አንድ ተወካይ
አባልና ፀሐፊ
3.ከከተማው ወይም ከወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አንድ ተወካይ አባል
4.ከአካባቢው ፖሊስ ፅ ቤት
5.ከንግድ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት አንድ ተወካይ አባል
6.በከተማው ህገ-ወጥ ግንባታ ወይም ይዞታ የሚገኝበት ቀበሌ
አስተዳዳሪ አባል ይሆናሉ፡፡
7.የተፈፃሚነት ወሰን
 ይህ መመሪያ በክልሉ ውስጥ በደንብ ቁጥር 17/96 መሰረት

በተቋቋመው የከተማ አስተዳደሮች ማዘጋጃ ቤቶችና ታዳጊ


ከተሞች ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

You might also like