Professional Documents
Culture Documents
የተስተካከለ
የፕሮጀክቱ ቦታ: - አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ በደብረብርሃን ከተማ በቀበሌ 07
የአማካሪው መግለጫ
ሀመን የምክር ኃ/የተ/ግ/ማህበር በፌዴራል አካባቢ፣ የደን እና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የተመዘገበ
እና ፍቃድ ያገኘ አማካሪ ድርጅት በዚህ የአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካ የወሰን ዘገባ የተካተቱት
መረጃዎች በሙሉ በእውነተኛ እና በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረቱ መሆንን ያረጋግጣል፡፡
ማውጫ
ሠንጠረዥ ዝርዝር ................................................................................................................................................ 4
የምስሎች ዝርዝር.................................................................................................................................................. 4
1. መግቢያ ............................................................................................................................................................ 5
ሠንጠረዥ ዝርዝር
የምስሎች ዝርዝር
1. መግቢያ
ይህ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በሰሜን ሸዋ ዞን፣ በደብረብርሃን ከተማ በቀበሌ 07 አስተዳደር
በ14,000 ካሬ ሜትር ላይ በአቶ አበባው ተፈረ ባለቤትነት ለሚቋቋመው የልብስ ስፉት ፋብሪካ የአካባቢ
ወሰን ጥናት ዘገባ ነው፡፡
የአካባቢ ወሰን ጥናት ሂደት ለአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ የመጀመሪያው ደረጃ ሲሆን ዓላማውም ዋና ዋና
የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖዎችንና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ለአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማው ጥናት
አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት እንዲያደርግ የሚያስችል ሂደት ነው፡፡ በተጨማሪም የአካባቢ
ወሰን ጥናት ሂደት ለአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርት ዝግጅት የሚረዱ ግብዓቶችን የያዘ ሲሆን እነዚህም
ስለፕሮጀክቱ አጭር መግለጫ እና አማራጮች፣ ፕሮጀክቱ በመቋቋሙ ምክንያት ጉዳት የሚደርስበትን
አካባቢ፣ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ አካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖዎች፣ የጥናቱን ቢጋር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በጥናቱ ወቅት ፋብሪካው በሚቋቋምበት አካባቢ የሚኖሩና ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚም እና ተጐጂ
የህብረተሰብ አካላትን በማወያየት ሃሳባቸው በዋናው የዚህ ሰነድ አካል እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የፕሮጀክቱ ባለቤት አቶ አበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካን የአካባቢ ወሰን ዘገባ ሪፖርት እና የአካባቢ
ተፅዕኖ ግምገማ (አተግ) ሪፖርት ለማዘጋጀቱ ለሀመን የምክር አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሥራ
ውክልና የተሠጠው የአማካሪ ድርጀት ሲሆን፤ የአማካሪው ቡድኑም ነባራዊ የአካባቢን ባህሪይ
(የአካባቢውን መግለጫ) መሠረት በማድረግ የታቀደው የልብስ ስፌት ፋብሪካ በሚቋቋምበት እና ወደ ሥራ
በሚገባበት ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ተፅዕኖዎችን፣ እንዲሁም ማቃለያ መንገዶቹን በማጥናት ሙሉ የአካባቢ
ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርት በመስራት ያቀርባል፡፡
የአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ተለያዩ ያለቀላቸውን ልብሶች ማለትም ካናቴራዎችን፣ ጅንስ
ሱሪዎችን፣ ሹራቦችን እና ካልሲዎችን በመስፋትና በማዘጋጀት ሥራ ላይ በመሰማራት ምርቶቹን ለሀገር
ውስጥ እና ለውጪ ገበያ በማቅረብ የአገር ውስጥና የውጪ ንግድ የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ዓላማ አድርጐ
ተቋቋመ ነው፡፡ የፕሮጀክቱ ባለቤት አቶ አበባው ተፈራ ሲሆኑ በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች
ተሰማራተው በመስራት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ ፋብሪካው በዓመት በቁጥር 1,141,526
የተለያዩ አልባሳትን ለማምረት በዕቅድ የያዘ ሲሆን ፕሮጀክቱ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረብርሃን ከተማ በቀበሌ 07 በ14,000 ካሬ ሜትር የሚቋቋም ይሆናል፡፡ የፕሮጀክቱ
ቆይታ ለ80 ዓመት ሲሆን የቆይታው ጊዜ ካበቃ በኃላ ለልብስ ስፌት ፋብሪካ ምርት ግብዓት የሚሆኑትን
ምርቶች ወደ ማምረት ይሸጋገራል፡፡
ፕሮጀክቱን የሚቋቋምበት ዋና ዓላማ አሁን ያለውን ሀገር ውስጥ የተዘጋጁ ልብሶች እጥረት መነሻ
በማድረግ ክፍተቱን ለመሙላት እና በየተዘጋጁ የተለያዩ ልብሶችን በአገር ውስጥ ባሻገር ለዓለም አቀፍ
ገበያ ለማቅረብ ነው፡፡
የልብስ ስፌት ፋብሪካው የጥሬ ዕቃነት የተለያዩ ግብዓቶችን ይጠቀማል፡፡ ከሚጠቀማቸው ጥሬ ዕቃዎች
በዋናነት የጥጥ፣ የፖሊስተር እና የናይለን ጨርቆችን እንዲሁም የፖሊስተርና የጥጥ ቅልቅል ጨርቆችን እና
የጅንስ ጨርቆችን በአገር ውስጥ ካሉ ፋብሪካዎች በመግዛት የሚጠቀም ይሆናል፡፡ ፋብሪካው
ያለቀላቸውን ምርቶች ስለሆነ የሚጠቀመው ምንም አይነት ኬሚካሎችን በግብዓትነት አይጠቀምም፡፡
ሠንጠረዥ 1፡ ዓመታዊ የጥሬ ዕቃ ፍላጐት
የጥሬ ዕቃው የአንዱ Cost (Birr)
ተ.ቁ. አይነት መለኪያ ብዛት ዋጋ LC FC Total Cost
1 ጨርቆችና ናይለንኖች ኪ.ግ 780,289 85.00 66,324,565.00 - 66,324,565.00
የፕሮጀክቱ ጠቅላላ የመነሻ ካፒታል የሥራ ማስኪያጃን ጨምሮ ብር 42.48 ሚሊዮን ነው፡፡ ከጠቅላላው
ፕሮጀክት 25% በገንዘብ ከባለሀብቱ የሚገኝ ሲሆን የተቀሪው 75% ወይም ብር 31,860,000.00 ከባንክ
ብድር ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የዕዳ መክፈያ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ የኮንስትራክሽን ሥራዎችን
ለማጠናቀቅ፤ ማሽነሪዎችን እና የመኪና ግዥዎችን ለማካሄድ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ብድሩም የ2 ዓመት
የእፎይታ ጊዜን ሳይጨምር በ10 ተከታታይ ዓመታት ውስጥ በየሩብ ዓመቱ ተመሳሳይ ዕዳዎች የሚከፈል
ይሆናል፡፡ ፋብሪካው በ50% የማምረት አቅም በመጠቀምና በዓመት በ5% በመጨመር እስከ 90%
የማምረት አቅም በመድረስ የተሻለ ገቢ ለማግኘት አቅዷል፡፡ ፕሮጀክቱ ወደ ሠራ ሲገባ ለ199 ዜጐች
የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡
3.3. የአመራረት ዘዴ
ፕሮጀክቱ የተለያዩ አልባሳትን በማምረት ለአገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ አስቧል፡፡ ይህን
ለማድረግ ኩባንያው ያለውን ሀብት እና አቅም በተገቢ ሁኔታ ይጠቀማል፡፡ በዚህም መሰረት ፕሮጀክቱ
የተለያዩ አልባሳትን ለማምረት በአሁን ወቅት በአልባሳት ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን ዘመናዊ ቴክኖሎጂና
የአመራረት ሂደት ይጠቀማል፡፡ ዝርዝር የምርት ሂደትና የቴክኖሎጂና የማሽኖች ግብዓት ሙሉ የአካባቢ
ተፅዕኖ ሰነዱ ሲዘጋጅ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
የአካባቢ ተፅዕኖ ሰነድ ሂደት ውስጥ ከሚካተቱት አንዱ ስለሚቋቋመው ፕሮጀክት የተለያዩ አማራጮችን
በማስቀመጥ የሚቋቋመው ፋብሪካ ከአካባቢ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ እንዲሰራ ማድረግ ነው፡፡
አማራጮችም ፕሮጀክቱ የሚጠቀመው ቴክኖሎጂ፣ የሚጠቀመው ግብዓትና የፕሮጀክቱ የትግበራ ቦታን
መሰረት በማድረግ ከዚህ በታች የተለያዩ አማራጮችን ለማስቀመጥ ተሞክሯል፡፡
ይህን አማራጭ በሁለት አይነት መንገድ ማየት የሚቻል ሲሆን የታቀደው የልብስ ስፌት ፋብሪካ
ቢተገበርና ባይተገበር የሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት አንጻር የሚታይ ይሆናል፡፡ የአበባው የልብስ ስፌት
ፕሮጀክት ሲተገበር ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ ተፅዕኖዎች የሚኖሩት ሲሆን ከእነዚህም መካከል በሚፈጠረው
የሥራ ዕድል ምክንያት የቤተሰብ ገቢ መጨመር፤ የቴክኖሎጂ ልውውጥ ማጐልበት እና በተለያዩ ታክስ
ክፍያዎች አማካይነት ለመንግስት ገቢ ማስገባት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ከፕሮጀክት ግንባታ እስከ ምርት ማምረት ወቅት ድረስ የሚኖረው አሉታዊ ተፅዕኖዎች
መከላከል የውሃ አካለት ብክለት፣ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አማካይነት የሚደርስ ተፅእኖ፤ የድምጽና የአየር
ብክለት፤ የአፈር መሸርሸር፤ የእጽዋት መቆረጥና መጥፋት ዋና ዋናዎቹ ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡ እነዚህ እና
መሰል አሉታዊ ተፅዕኖዎች የማቃለያ እርምጃዎች በሚተገበሩበት ወቅት መቀነስ እና ማስወገድ ይቻላል፡፡
ነገር ግን ፕሮጀክቱ ባይተገበር የተጠቀሱት ጥቅሞች እና ሌሎች የአካባቢው ህብረተሰብ ተጠቃሚ
የሚሆኑበት ሁኔታ አይፈጠርም፡፡
ፕሮጀክቱ ከመቋቋሙ በፊት በተደረገው የቦታ ቅድመ-ጥናት ደብረብርሃን ከተማ ለጥሬ ዕቃ አቅርቦት፣
ምርትን ወደ ገበያ ማድረስ እና የሰራተኛ ሰው ኃይል አቅርቦት እና ከሌሎች ከተማ ከአዲስ አበባ በቅርብ
ርቀት ላይ መገኘቱ ተመራጭ አድርጐታል፡፡
የልብስ ስፌት ፋብሪካው የተለያዩ ምርቶችን ለማምረት ብዛት ያላቸው የቴክኖሎጂ አማራጮች ቢኖሩም
ካሉት አማራጮች በአካባቢ፣ በሰው ደህንነትና ጤንነት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት አንጻር በማየት በጣም
ዝቅተኛ ተፅዕኖ ሊኖረው የሚችለውን አማራጭ በመምረጥ የሚተገበር ይሆናል፡፡ አማራጮችንም ለማየት
የተለያዩ የቴክኖሎጂ አምራቾችን መስፈርት በማወዳደር ቴክኖሎጂው ምርጫ ተካሂዷል፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት የፕሮጀክቱ አማራጮች በስፋት በዋናው የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነዱ የሚተነተን
ይሆናል፡፡
የልብስ ስፌት ፕሮጀክቱ አራት ምዕራፎች ያሉት ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ሦስቱ ዋና ዋና ምዕራፎች
የሚኖሩትና በሦስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ ፕሮጀክቱ መሬት
ከተረከበበትና አስፈላጊውን የግንባታ ፈቃድ ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ አንድ ዓመት የሚፈጅ ሲሆን የፕሮጀክቱ
የፋብሪካ አጠቃላይ የግንባታና የማሽኖችና የመሳሪያዎች ከውጪ ማስገባት፣ የማጓጓዝ እና ገጠማ ሥራ
ሁለት ዓመት የሚፈጅ ይሆናል፡፡
በፕሮጀክቱ ቅድመ ግንባታ ወቅት ለፋብሪካው ግንባታ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት የሚከናወንበት ሲሆን
ከሚከናወኑት ተግባራት መካካል፡-
ፋብሪካው ግንባታው ተጠናቆ ወደ ምርት ማምረት በሚገባበት ወቅት ከመከናወነኑ ተግባራት መካከል፡-
ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ መሰረት የምርት ማምረት ሥራውን አጠናቆ ሲወጣ ፋብሪካው
በተቋቋመበት አካባቢ ላይ የደረሱ ጉዳቶችን ወደ ነበረበት በመመለስ እንዲያስተካከሉ ያደርጋል፡፡ የደረሱ
ጉዳቶችንም ለማስተካከል በዚህ ሰነድ ላይ የተመላከቱትን የተፅዕኖ ማቃለያ እርምጃዎችን ተግባራዊ
ያደርጋል፡፡
ጥናቱ የሚካሄደው አከባቢ ነክ ህጐችን መሰረት በማድረግ እና በፕሮጀክቱ አካባቢ በሚደረግው የመስክ
ጉብኝት በማካሄድ ነው፡፡ ይህ ጥናት የሚያካትታቸው ፕሮጀክቱ ከሚቋቋምበት እስከ 5 ኪ.ሜ. ራዲየስ
ድረስ ያለውን አካባቢ በመዳሰስ ይሆናል፡፡
ወደ ሥራ የሚገባው ፋብሪካ በደብረ ብርሃን ከተማ ቀበሌ 07 በ14,000 ካሬ ሜትር የሚቋቋም ሲሆን
ለግንባታው የሚሆን መሬት ከከተማው አስተዳደር ለኢንዱስትሪ ከተከለለ ቦታ ተረክቧል፡፡ በደብረብርሃን
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ 130 ኪ.ሜ. ወደ ደሴ በሚውስደው ዋና
አውራ ጐዳና ላይ ይገኛል፡፡ ደብረ ብርሃን ከተማ የኬክሮስ እና የኬንትሮስ ርቀት 9041'N 39032'E/
9.683oN 39.533oE እና 2,840 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡
ደብረብርሃን በ2840 ሜትር ከባህር ወለል በላይ የሚገኝ ሲሆን ደጋማ የአየር ንብረት ያለበት አካባቢ
ነው፡፡ የአካባቢው ዝናባማ ወቅት (ከሰኔ እስከ መስከረም) የሚጠቀስ ሲሆን አጭር ዝናብ (የካቲት,
መጋቢት/ ሚያዝያ) እና በበጋ ወቅት (ከጥቅምት እስከ ጥር) ያካትታል፡፡. አማካኝ ዓመታዊው የሙቀት
መጠን 50C እና በ 230C መካከል ልዩነት አለው፡፡. ዓመታዊ አማካይ ዝናብ መጠን 874 ሚሜ ነው፡፡
በፕሮጀክቱ አካባቢ ውስጥ ዋነኛ የአፈር አይነት የሸክላ አፈር ነው፡፡ በተጨማሪም የአካባቢውን አፈርና
የመሬት አቀማመጥ በማየት ቀደም ሲል ምንም አይነት የመሬት መንሸራተት እንዳልነበር ማወቅ ይቻላል፡፡
የጥናት ቡድኑ በመስክ ምልከታ ወቅት እንደተመለከተው በአሁኑ ወቅት ለፕሮጀክቱ መሬት የግጦሽ መሬት
(45%) እና የእርሻ መሬት (40%) ይገመታል፡፡ ከዚህም ባሻገር ቀሪው የመሬት አካባቢ በመንገድ የተያዘ
ሲሆን በአሁኑ ወቅት አካባቢው ለኢንቨስትመንት የተከለለ ነው፡፡
በማዕከላዊ ስታትስቲክስ የ2008 ዓ.ም. የትንቢያ መረጃ መሰረት የደብረብርሃን ህዝብ ቁጥር 100 ሺ 055
እንደሆነ ይገመታል፡፡ ከከተማዋ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ምክንያት
የከተማው ነዋሪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው፡፡ ከነዋሪዎች 94.12% ኦርቶዶክስ ክርስትናን የሚከተል
ሲሆን 3.32% ከሕዝበ ሙስሊሙ እና 2.15% የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ናቸው፡፡
ለኢንቨስትመንቱ ቀረቤታ, የመሠረተ ልማት መሟላት ከሰለጠነ ለገበያ ያለው ቅርበት፣ ጥሬ እቃዎች
አቅርቦት እና የሰው ሀይል አቅርቦት, የፕሮጀክቱን አካባቢ ለመወሰን የሚረዱ ዋና ዋና ነገሮች ናቸው፡፡
በተጠቀሱት መስፈርቶች መሠረት ደብረብርሃን ከተማ ከመንገድ ተደራሽነት፣, የውሃ እና የኤሌክትሪክ
ኃይል አቅርቦትና ምቹ መሆን ለኢንቨስትመነት ተመራጭ አካባቢ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በተጨማሪም
ከተማው በፕሮጀክቱ አካባቢ የአካባቢው ህብረተሰብ አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ተቋማት እና ትምህርት
ቤቶች አሉት፡፡ ስለዚህ በደብረብርሃን የተያዘው የፕሮጀክቱ አካባቢ በብዙ አቅጣጫዎች የበለጠ ተመራጭ
ነው፡፡
ከከተማው አስተዳደር ፋበሪካው በሚቋቋምበት አካባቢ የውሃ አቅርቦት ያመቻቸና ባለሀብቱ ተጠቃሚ
የሚሆኑበት ምቹ ሁኔታ አለ፡፡
በደብረብርሃን ከተማ ሁለት ሆስፒታሎች እና ሦስት የጤና ማእከላት የሚገኙ ሲሆን አንዱ ለፕሮጀክቱ
አካባቢ ይገኛል፡፡
ፋብሪካው በሚቋቋምበት አካባቢ ምንም አይነት ባህላዊ ወይም ታሪካዊ ተቋማት የሉም፡፡
6. የአካባቢ ተፅዕኖዎች
6.1. በጐ ተፅዕኖዎች
የአበባው የልብስ ስፌት ፋብሪካው በሚቋቋምበት አካባቢ የሚኖረው በጐ ተፅዕኖዎች ከዚህ በታች
ተዘርዝረዋል፡-
በታቀደው የልብስ ስፌት ፋብሪካ ለሚቋቋምበት በጠቅላላው ከታክስ ክፍያና በፈቃደኝነት ክፍያዎች እና
በሮያሊቲዎች እንዲሁም በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) መልክ ለአካባቢው መስተዳደርና እና ለሀገሪቱ
ገቢን ያስገኛል፡፡
በልብስ ስፌት ፋብሪካው በግንባታ እና በትግበራ ወቅት የተለያዩ አካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ የሚደርስ
ሲሆን በአካባቢ ወሰን ጥናት ልየታ ወቅት ከተለዩት መካከል አንደሚከተለው የቀረቡ ሲሆን ዝርዝር
ተፅዕኖዎች በሙሉ የአካባቢ ተፅዕኖ ሰነዱ ሲዘጋጅ የሚዘረዘር ይሆናል፡፡
የፍሳሽ ውሃ ብክለት
የደረቅ ቆሻሻ ብክለት
የድምፅ ብክለት
የትራፊክ አደጋዎች
የሥራ ጤንነት እና ደህንነት
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሚካሄዱ የልማቶች ሥራዎች ላይ ህዝብን ማማከር እና ተሳታፊ እንዲሆን
የማድረግ ሥራው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡ በተለይ የህብረተሰብ ተሳትፎን ለመጠቀም
በወጡ አካባቢ ጥበቃ ነክ ህጐች መሰረት አዲስ በሚቋቋሙ ፕሮጀክቶች ላይ የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ ሆነው
እንዲተገበሩ እየተደረገ ነው፡፡
ስለፕሮጀክቱ በሚደርሱ አዎንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመለየትና የአካባቢ ተፅዕኖው ግምገማ ጥናቱ
አካል ለማድረግ በፕሮጀክቱ በሚቋቋምበት አካባቢ የሚኖሩ በፕሮጀክት ትግበራ ተጠቃሚ፣ ተጐጂ፣
ፍላጐቱ ያላቸውና የሚመለከታቸው የህብረተሰብ አካላትን በማሳተፍ የህብረተሰብ የምክክር መድረክ
በአካባቢ ወሰን ልየታው ወቅት ተካሄዷል፡፡
የህብረተሰቡ ምክክር በደብረ ብርሃን ከተማ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት አካባቢ የተደረገ ሲሆን ከአካባቢው
ከተለያዩ የህብረተስብ አካላት ተሳታፊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በወይይቱ ወቅት ስለፕሮጀክቱ በበቂ ሁኔታ
ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በማጠቃለያ ከቀረቡት ሃሳቦች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡፡
በፕሮጀክቱ አካባቢ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየት የተያዘው ቃለ ጉባኤ ከዚህ ሪፖርት
መጨረሻ በዕዝል ላይ ተያይዟል፡፡
8.1 መግቢያ
የአካባቢ ወሰን ዘገባ ሪፖርት የተዘጋጀው አዲስ ለሚቋቋመው የአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን ከተማ ቀበሌ 07 የኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ ይቋቋማል፡፡
ፕሮጀክቱ መነሻ አድርጐ የተነሳው በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ከውጪ ለሚገቡተት አልባሳት
ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ምክኒያት የአልባሳት የገበያ ዋጋ መናር መኖሩ ባለሀብቱን በዚህ ዘርፍ
ለመሰማራት አስቧል፡፡
የልብስ ስፌት ፕሮጀክቱን የሚቋቋምበት ዋና ዓላማ አሁን ያለውን ሀገር ውስጥ የተዘጋጁ ልብሶች እጥረት
መነሻ በማድረግ ክፍተቱን ለመሙላት እና በየተዘጋጁ የተለያዩ ልብሶችን በአገር ውስጥ ባሻገር ለዓለም
አቀፍ ገበያ ለማቅረብ ነው፡፡ ዝርዝር ዓላማዎቹም፡-
የአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካ የአካባቢ ወሰን ጥናት ዘገባ የሚከተሉት ዓላማዎች አሉት፡-
የልብስ ስፌት ፋብሪካ በደብረ ብርሃን ከተማ ቀበሌ 07 በ14,000 ካሬ ሜትር የሚቋቋም ሲሆን
ለግንባታው የሚሆን መሬት ከከተማው አስተዳደር ለኢንዱስትሪ ከተከለለ ቦታ ተረክቧል፡፡ በደብረብርሃን
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ 130 ኪ.ሜ. ወደ ደሴ በሚውስደው ዋና
አውራ ጐዳና ላይ ይገኛል፡፡ ደብረ ብርሃን ከተማ የኬክሮስ እና የኬንትሮስ ርቀት 9041'N 39032'E/
9.683oN 39.533oE እና 2,840 ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል፡፡ የአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካው
በሰሜን አረንጓዴ ቦታ፣ በደቡብ ባዶ ቦታ፣ በምዕራብ 11 ሜትር መንገድ እንዲሁም በምስራቅ 18 ሜትር
መንገድ ያዋሱኑታል፡፡
በአማካሪ ቡድኑ በአካባቢ ተፅዕኖ ሰነድ ግምገማ ጥናት ወቅት የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
መረጃዎች ለመሰብሰብ የሚከተሉትን ዘዴዎች የሚጠቀሙ ይሆናል፡፡
የግምገማ ጥናት ውጤቱን በማጠቃለያ ሰንጠረዥ (matrix) መልክ ማቅረብ እያንዳንዱ ተግባር
የሚያስከትለውን ተፅእኖ በመመዘን በደረጃ ለማስቀመጥ ከታች የተጠቀሱትን የትናት ቡድኑ ተጠቅሟለ፡፡
የተፅእኖ መጠንና ስፋት ስር የተካተቱት በፕሮጀክቱ አማካኝነት የሚከሰቱ ተፅዕኖዎች ድንበር ተሻጋሪ
ሆነው ዓለም አቀፋዊ፣ በአገር ደረጃ ወይም በክልል ደረጃ መከሰታቸው እንዲሁም ፕሮጀክቱ
በሚቋቋመወበት ዙሪያ ወይም በፕሮጀክቱ በተከለለው ቦታ ብቻ የተወሰኑ ስለመሆኑ የሚገለጽበት ሲሆን
በሚከተለው መሰረት ደረጃ ተቀጦለታል፡፡
የአካባቢ ተፅዕኖው የመከሰት አጋጣሚው ሁኔታና ተፅዕኖ የደረሰበት አካባቢ ወደ ነበረበት መመለስ የሚቻል
መሆኑና አለመሆኑ በዝርዝር የሚተነተንበት ይሆናል፡፡
ከዚህ በታች የተጠቀሱት ተጽእኖዎች በኘሮጀክቱ የሥራ ሂደት ወቅት ሊከሰቱ ይችላሉ ተብለው ታሳቢ
የተደረጉ ሲሆን ሙሉ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርቱ ሲዘጋጅ በፕሮጀክቱ ቅድመ ግንባታ፣ ግንባታ፣
በትግበራ እና ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የሚኖረው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊፈጠሩ የሚችሉ ተፅዕኖዎች
በተገለፁት መነሻ ነጥቦች መሠረት የሚተነተኑ ይሆናሉ፡፡
የአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ይህን የአካባቢ ወስን ዘገባ ሪፖርትና ሙሉ የአካባቢ ተፅዕኖ ሰነድ
ለማዘጋጀት ሀመን የምክር አገልግሎት ኃ/የተ/የግ/ማህበር አማካሪ ድርጅት ጋር የተዋዋለ ሲሆን የጥናት
ቡድኑም የሚከተሉትን ባለሙያዎች ያካትታል፡፡
የጥናት ቡድኑ ለአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ለማካሄድ
አስቀድሞ በዚህ ሰነድ ላይ የተካተተውን የአካባቢ ወሰን ዘገባ ሪፖርት አዘጋጅቶ ማቅረብ፣
የሚመለከታቸውን የህብረተሰብና ተቋማትን በፕሮጀክቶቹ ላይ ማወያየት፣ የአካባቢ ወሰን ዘገባ ሪፓርት
ሰነዱን በሚመለከተው አካባቢ ጥበቃ መ/ቤት በሚሰጠው አስተያየት መሰረት ማስተካከል፣ ሙሉ
የአካባቢ ሰነድን በማዘጋጀትና በተሰጠው አስተያየት በማስተካከል በሚፈለገው ሰነድ ቁጥር መጠን እና
በተፈለገው ውቅት ማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
የአበባው ተፈራ የልብስ ስፌት ፋብሪካ በፕሮጀክቱ ውስጥ ያሉ መንግስታዊ እና የግል ባለድርሻ አካላት
በአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ወቅት ስለፕሮጀክቱ በቂ ሃሳብ እንዲኖራቸው የማረጋገጥ ግዴታ አለበት፡፡
ለዚህም የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ግምገማ ኤክስፐርቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ተፅዕኖ ጥናት ላይ
ሲተገብሩ ማንኛውም ባለድርሻ አካላት የተሟላ ምክክር ያደርጋሉ፡፡
የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናት ሰነዱ በአብክመ የአካባቢ፣ ደንና ዱር እንስሳት ባለስልጣን ባወጣው የአካባቢ
ተፅዕኖ ጥናት ግምገማ መመሪያ ቁጥር 001/2010 መሠረት የሚከተለው ይዘት ይኖረዋል፡፡
1. አጠቃላይ መግለጫ (Excutive Summary)
2. መግቢያ (Introduction)
3. የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናቱ ዓላማ
4. የጥናቱ ወሰን
5. የጥናቱ ስልት ወይም ዘዴ