You are on page 1of 129

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት

ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት
የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ጥናትና ምርምር
ዳይሬክቶሬት

የግንባታ አካባቢ ደህንነት የዳሰሳ


ጥናት

ሐምሌ 2009 ዓ.ም

አዲስ አበባ
 ም ስ ጋ ና
ይህንን ጥናት እንድናከናውን ርዕስ በመምረጥና ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን እንዲሟሉ
በማድረግ እንዲሁም ጥናቱን ሚያግዙ ስልጠናዎችን እንድንወስድ ሙሉ ድጋፍ ያደረገልንን
ተቋማችንና አመራሩን ማመስገን እፈልጋለን፡፡ በተጨማሪም የጥናትና ምርምር ጠቅላላ
ባለሙያዎችና ዳይሬክተራችንን ከጎናችን በመሆን የሀሳብ ድጋፍና አቅጣጫ ስለሰጡን
እናመሰግናለን፡፡ በመጨረሻም መረጃ በመስጠት የተባበሩን የ40/60 ቤቶች ልማት ኤጀንሲ፤
20/80 ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፤ ቂርቆስ ክ/ከተማ፤ ቦሌ ክ/ከተማ፤ አራዳ ክ/ከተማ፤
አዲስ ከተማ ክ/ከተማ፤ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ፤ የባህርና ትራንዚት ሎጂስቲክ አገልግሎት
ድርጅት፤ የባህልና ቱሪዝም፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን፤
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር፤
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ፤ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ሚኒሊክ
ሆስፒታል፤ የካቲት 12 ሆስፒታል፤ ዘውዲቱ ሆስፒታል፤ ጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል፤
የራስ ደስታ ሆስፒታል፤ ቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታልን እናመስግናለን፡፡

i
ማውጫ
የሠንጠረዥ ዝርዝር ............................................................................................................................................. vi
ማጠቃለያ (Abstract) ................................................................................................................................ viii
ክፍል አንድ ................................................................................................................................................... 1
መግቢያ.......................................................................................................................................................... 1
1.1. ዳራ (Back ground of the study) ........................................................................................... 1
1.2. ሰበበ ጥናት (Statement of the problem) ............................................................................... 2
1.3. የጥናቱ አስፈላጊነት፣ ..................................................................................................................... 3
1.4. የጥናቱ ዓላማ ................................................................................................................................ 3
1.4.1. ጥቅል አላማ .......................................................................................................................... 3
1.4.2. ዝርዝር አላማ ........................................................................................................................ 4
1.5. የጥናቱ ወሰን ................................................................................................................................. 4
1.6. የሚጠበቅ ውጤት፣ ....................................................................................................................... 4
1.7. የጥናቱ ዘዴ፣ ................................................................................................................................. 5
1.7.1. የናሙና አመራረጥ ዘዴ ........................................................................................................ 5
1.7.2. የመረጃ ማሰባሰቢያ መሳሪያዎች (Data gathering tools) ................................................ 8
1.7.3. የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ..................................................................................................... 11
1.8. የጥናቱ ውስንነት (Limitation) ................................................................................................... 11
1.9. ያጋጠሙ ችግሮች (Challenges of the study)...................................................................... 11
ክፍል ሁለት ................................................................................................................................................ 12
2. የቀደምት ጥናቶች ዳሰሳ (Literature review) .................................................................................. 12
2.1. ትርጉም........................................................................................................................................ 12
2.1.1. ደህንነት................................................................................................................................ 12
2.1.2. የግንባታ አካባቢ ደህንነት ትርጉም ..................................................................................... 12
2.2. የስራ ላይ ደህንነት ፕሮግራም ክፍሎች/ Elements of safety program.............................. 12
2.3. የደህንነት ልምድን አስቀድሞ በፕሮጀክት ላይ ማቀድ ያለው ጠቀሜታ ................................... 12
2.4. የግንባታ ቦታ ላይ አደጋዎች ...................................................................................................... 13
2.5. በግንባታ አካባቢ የአዳጋና የጉዳት መንስኤዎች .......................................................................... 14
2.6. የግንባታ ደህንነትን የሚጎዱ ሁኔታዎች .................................................................................... 16
2.7. የግንባታ ደህንነትን የተመለከቱ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ህጎች ........................................ 16
2.7.1. የግንባታ ደህንነት የተመለከቱ ህጎች ...................................................................................... 16
2.7.2. የግንባታ ደህንነትን የተመለከቱ ደንቦች.............................................................................. 19

ii
2.8. የውጪ ሀገር ተሞክሮዎች ......................................................................................................... 33
2.8.1. የብራዚል ተሞክሮ ............................................................................................................... 33
2.8.2. የሲንጋፖር ተሞክሮ ............................................................................................................ 35
2.9. ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች (Case study) .......................................................................... 37
2.10. የሀገር ውስጥ ተሞክሮ ............................................................................................................ 38
2.10.1 የስራ ላይ ደህንነትና ጤንነት በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ በአዲስ አበባና በወልቂጤ በ2014
እ.ኤ.አ የተደረገ ጥናት ........................................................................................................................ 38
2.10.2 በደህንነትና ጤንነት ላይ ያለው አፈጻጸም ማሳያ በአዲስ አበባ በመንገድና ቤት ግንባታ
እ.ኤ.አ በ2014 የተደረገ ጥናት ........................................................................................................... 39
ክፍል ሶስት ................................................................................................................................................. 41
3. ትንታኔ እና የጥናቱ ግኝቶች .............................................................................................................. 41
3.1. ከመጠይቅ የተገኙ ትንታኔዎች ................................................................................................... 41
3.1.1. ከህንጻ ግንባታ የተገኙ ትንታኔዎች .................................................................................... 41
3.1.2. ከመንገድ ፕሮጀክቶች የተገኙ መጠይቆች ትንታኔ ............................................................ 62
3.1.3. የደህንነት ዕቃ አቅራቢዎችን የተመለከተ መጠይቅ ትንተና .............................................. 83
3.2. የጥናቱ ግኝቶች ........................................................................................................................... 87
3.2.1. ደህንነት በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ ............................................................................. 87
3.2.2. ደህንነትን የተመለከቱ ህጎች እና አፈጻጸማቸው................................................................. 88
3.2.3. የደህንነት አስተዳደር ........................................................................................................... 88
3.2.4. በግንባታ ቦታ ላይ በደህንነት መጓደል ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎች ............................ 91
3.2.5. በኮንስትራክሽን ስራ ምክንያት የደረሱ አደጋዎችን የመመዝገብ ልምድ እና የተመዘገቡ
አደጋዎች 100
3.2.6. የስራ ደህንነት ተግባራዊ እንዳይሆን የሚጠቀሱ ምክንያቶች .......................................... 102
3.2.7. የስራ ላይ ደህንነት መጓደል ያለው ተጽእኖ ..................................................................... 103
3.2.8. ከመንገድ ፕሮጀክቶች ጋር የተያያዙ ግኝቶች ................................................................... 104
4. የጥናቱ ድምዳሜ ............................................................................................................................... 110
5. የመፍትሄ ሀሳቦች (Recommendation) ......................................................................................... 114
6. ዋቢ .................................................................................................................................................... 119
7. አባሪ ................................................................................................................................................... 120
7.1. መጠይቆች ................................................................................................................................. 120
7.2. ቼክ ሊስት .................................................................................................................................. 120
7.3. ከተለያዩ የግንባታ ቦታዎች የተወሰዱ ፎቶ ግራፎች ............................................................. 120

iii
የምስል ዝርዝር
ምሰል 2.1፡ የአዳጋ ድግግሞሽ መጠን እና የአደጋው ክብደት መጠን ................................................................................. 37

ምሰል 3-1፡ የተጻፈ ህግ ....................................................................................................................................... 41

ምስል 3-2፡ የደህንነት ወጪ በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ ስለመካተቱ ............................................................................ 43

ምስል 3-3፡ የህግ/አዋጅ/ደንብ ተፈጻሚነት .............................................................................................................. 45

ምስል 3-4፡ የደህንነት ዕቃዎች ስለመሟላታቸው....................................................................................................... 46

ምስል 3-5፡ የተሟሉ የደህንነት ዕቃዎች .................................................................................................................. 48

ምሰል 3-6፡ የደህንነት ባለሙያ ስለመኖሩ ............................................................................................................... 49

ምስል 3-7፡ በሴፍቲ ጉድለት ምክንያት አደጋ ሲያጋጥም ተጠያቂው አካል ማን ነው............................................................ 50

ምስል 3-8፡ ሰልጠና በቋሚነት ስለመሰጠቱ ............................................................................................................. 51

መስል 3-9፡ አደጋ ሲያጋጥም ሪፖርት ስለመደረጉ...................................................................................................... 52

ምሰል 3-10፡ ብቁ ባልሆኑ ሰራተኖች የተፈጠሩ አደጋዎች ............................................................................................. 54

ምስል 3-11፡ በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች .................................................................................................. 55

መስል 3-12፡ የግንባታ ደህንነት ባለመተግበሩ ምክንያት ከስራው ውጪ የሆኑ የማህበረሰብ ከፍሎች ላይ የደረሱ አደጋዎች............ 56

ምስል 3-13፡ የኢንሹራንስ ዋስትና ስለመኖሩ ............................................................................................................ 57

ምስል 3-14፡ አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች ስለመለየታቸው ............................................................................................. 58

ምስል 3-15፡ በዋናነት የሚጠቀሱ የአደጋ መንስኤዎች ................................................................................................. 59

ምስል 3-16፡ ስለ ግንባታ ደህንነት የተጻፈ ህግ ስለመኖሩ ............................................................................................. 62

ምስል 3-17፡ ለደህንነት የሚወጣው ወጪ በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ ስለመካተቱ ......................................................... 64

ምስል 3-18፡ የህግ/ደንብ/አዋጅ ተፈጻሚነት ............................................................................................................. 66

9 ምሰል 3-19፡ የደህንነት ዕቃዎች ስለመሟላታቸው.................................................................................................... 67

ምስል 3-20፡ የተሟሉ የደህንነት እቃዎች ................................................................................................................ 68

ምስል 3-21፡ አደጋ ሲያጋጥም ሪፖርት ስለመደረጉ ..................................................................................................... 70

ምስል 3-22፡ የደህንነት ባለሙያ ስለመኖሩ .............................................................................................................. 71

ምስል 3-23፡ ብቁ ባልሆኑ ሰራተኞች የተፈጠሩ አደጋዎች ............................................................................................ 72

ምስል 3-24፡ ብቁ ባልሆኑ ሰራተኞች የተፈጠሩ አደጋዎች ............................................................................................ 74

ምስል 3-25፡ በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች.................................................................................................. 75

ምስል 3-26፡ አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች ስለመለየታቸው ............................................................................................ 76

ምሰል 3-27፡ በዋናነት የሚጠቀሱ የአደጋ መንስኤዎች................................................................................................. 76

iv
ምስል 3-28፡ ስልጠና በቋሚነት ስለመሰጠቱ ........................................................................................................... 79

ምስል 3-29፡ ደህንነት ባለመተግበሩ ምክንያት ከስራ ውጪ የሆኑ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰው ጉዳት..................................... 82

ምስል 3-30፡ የኢንሹራንስ ዋስትና ስለመሰጠቱ ......................................................................................................... 83

ምስል 3-31፡ የደህንነት ምርቶቹ የየት ሀገር ምርቶች ናቸው .......................................................................................... 84

ምስል 3-32፡ የደህንነት ዕቃዎቹ ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ አካል ...................................................... 85

ምስል 3-33፡ በግባ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋምት የደህንነት አልባሳትን የመግዛት ልምድ ............................................................ 85

ምስል 3-34፡ ተጠቃሚ ድርጅቶቹ ዋጋ ላይ ወይስ ጥራት ላይ ያተኩራሉ ......................................................................... 86

ምስል 3-35፡ ሰራተኞች የደህንነት ዕቃዎች ሳይሟላላቸው ........................................................................................... 89

ምስል 3-36፡ ዕድሜያቸው የገፋ የቀን ሰራተኞች እና የደህንነት አልባሳት ያልተሟላላቸው ሰራተኞች ....................................... 90

ምስል 37፡ ምቹ የስራ ቦታ ................................................................................................................................... 91

ምስል 3-38፡ ሰራተኞች የደህንነት አልባሳት ሳይሟላላቸው የፊኒሺንግ ስራ በመስራት ላይ .................................................... 93

ምሰል 3-39፡ ደህንነቱ ባልተጠበቀ የቁፋሮ ሰራ ላይ .................................................................................................... 94

ምስል 3-40፡ ከ2002-2008ዓ.ም ከህንጻ ግንባታ ጋር ተያይዘው የተከሰቱ አደጋዎች ............................................................ 95

ምስል 3-41፡ ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታ ....................................................................................................................... 96

ምሰል 3-42፡ የእንጨት እስካፎልዲንግ.................................................................................................................... 97

ምሰል 3-43፡ የእንጨት እስካፎልዲንግ ................................................................................................................... 98

ምስል 3-44፡ ሰራተኞች ለአደጋ በሚያጋልጥ የሥራ ሁኔታ ላይ ...................................................................................... 99

ምስል 3-45 ግንባቸው ሳይጠናቀቅ ለተጠቃሚ ክፍት የሆኑ መንገዶች ........................................................................... 105

ምስል 3-46፡ ሠራተኞች የደህንነት አልባሳት ሳይሟላላቸው በመንገድ ስራ ላይ ................................................................ 106

ምስል 3-47፡ ምልክት ሳይቀመጥላቸው እየተገነቡ ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች ................................................................... 108

ምስል 3-48፡ የወሰን ማስከበር ሂደቱ ሳይጠናቀቅ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ............................................................ 109

ምስል 3-49፡ ግንባታቸው በአግባቡ ያልተጠናቀቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች ........................................................................ 109

v
የሠንጠረዥ ዝርዝር
ሠንጠረዥ 2-1፡ የሳይት ምልከታ ድግግሞሽ .............................................................................................................. 37

ሠንጠረዝ 3-1፡ ደህንነት በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ ................................................................................................ 42

ሠንጠረዥ 3-2፡ ስለ ግንባታ ደህንነት ያለው ግንዛቤ..................................................................................................... 44

ሠንጠረዝ 3-3፡ የግንበታ ደህንነትን በተመለከተ ህግ ስለመኖሩ ...................................................................................... 44

ሠንጠረዥ 3-4፡ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ስለመኖሩ ................................................................................................. 47

ሠንጠረዥ 3-5፡ ለጎብኚ የሚደረገው ጥንቃቄ ............................................................................................................ 48

ሠንጠረዥ 3-6፡ የደህንነት አልባሳት ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው........................................................................... 50

ሠንጠረዥ 3-7፡ ሰዓት እላፊና ትራፊክ በሚበዛበት የሚከናወኑ ሥራዎች ለአደጋ መፈጠር ያላቸው አስተዋጽኦ............................ 53

ሠንጠረዥ 3-8፡ የደህንነት ምልክቶችን ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎች ........................................................................ 53

ሠንጠረዥ 3-9፡ የግንባታ ደህንነት በሥራ ላይ ያለው አስተዋጽኦ.................................................................................... 60

ሠንጠረዥ 3-10፡ የአደጋዎች መቀነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለው አስተዋጽኦ ......................................................................... 61

ሠንጠረዥ 3-11፡ ደህንነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቢሰጥ ያለው አስተዋጽኦ ............................................................... 61

ሠንጠረዥ 3-12፡ ደህንነት በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ.............................................................................................. 63

ሰንጠረዥ 3-13፡ ስለ ግንባታ ደህንነት ያለው ግንዛቤ ................................................................................................... 65

ሠንጠረዝ 3-14፡ ደህንነት የተመለከቱ ህጎች/ደንቦች/አዋጆች........................................................................................... 65

ሠንጠረዥ 3-15፡ ስለ መጀመሪያ ደረጃ የህክምና መስጫ .............................................................................................. 67

ሠንጠረዥ 3-16፡ ለጎብኚ ስለሚደረገው ቅድመ ጥንቃቄ ............................................................................................... 69

ሠንጠረዥ 3-17፡ የደህንነት አልባሳት ደረጃቸውን ስለመጠበቃቸው ................................................................................. 71

Table 3-18 ሠንጠረዥ 3-18፡ ሰዓት እላፊና የትrፊክ ፍሰት ለአደጋ መፈጠር ያላቸው አስተዋጽኦ .......................................... 73

ሰንጠረዥ 3-19፡ ደህንነት ምልክቶችን ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎች ......................................................................... 73

ሠንጠረዥ 3-20፡ የግንባታ ደህንነት ለሥራው ያለው አስተዋጽኦ .................................................................................... 77

ሠንጠረዥ 3-21፡ ደህንነት በከፍተና የትምህርት ተቋማት ውስጥ ቢሰጥ ያለው ጠቀሜታ ....................................................... 78

ሠንጠረዥ 3-22፡ የአደጋዎች መቀነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው አስተዋጽኦ ................................................................... 78

ሠንጠረዥ 3-23፡ በርክክብ ወቅት ከደህንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥራዎች ስለመጠናቀቃቸው ......................................... 80

ሠንጠረዥ 3-24፡ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ የሚበረታቱበት ሁኔታ ..................................................................................... 80

ሠንጠረዥ 3-25፡ በግንባታ ስራ ደህንነት ምክንያት ስለሚፈጠጥ የትራፊክ አደጋ ................................................................ 81

ሠንጠረዥ 3-26፡ ደህንነት መተግበሩ በሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት ላይ ያለው ሚና ............................................................. 82

ሠንጠረዥ 3-27፡ ስለ ደህንነት አልባሳት ያለው ግንዛቤ ................................................................................................ 83

vi
ሠንጠረዥ 3-28፡ ደህንነትን ውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ መግባ አለበት ብለው የሚያምኑ እና ያስገቡ ..................................... 87

ሠንጠረዥ 3-29፡ ከ2002-2008ዓ.ም ከህንጻ ግንባታ ጋር ተያይዘው የተከሰቱ አደጋዎች ....................................................... 95

vii
ማጠቃለያ (Abstract)
ጥናቱ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ የህንጻ እና የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ
ያለውን የደህንነት ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ እዳለ ለመለየት የተደረገ የዳሰሳ ጥናት ሲሆን
አላማውም በግንባታ አካባቢ ደህንነት ዙሪያ ያለውን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ በማጤን በስራ
በደህንነት ባለመተግበሩ ምክንያት የተፈጠሩ የአደጋ አይነቶችንና መንስኤያቸውን መለየት፣
የአደጋ መረጀ አያያዝ ስርዓቱ ምን እንደሚመስል መቃኘት እንዲሁም በግንባታ አካባቢ
ደህንነት ስላሉ ህጎችና የአፈጻጸም ደረጃቸውን ማጥናት ነው፡፡

ጥናቱ የመጀመሪያ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎችን በመጠቀም


ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማለትም ከተቋራጮች፣ ከአማካሪዎች፣ ከግንባታ ባለቤቶች፣
ከሠራተኞች እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን መረጃ ለመሰብሰብ
ተችሏል፡፡ በተሰበሰበው መረጀ መሰረትም ጥናቱ አጠቃላይ በአዲስ አበባ የግንባታ ፕሮጀክች ላይ
ያለውን የግንባታ ደህንነት ነባራዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ የጥናቱ
ግኝትም እንደሚያሳየው ምንም እንኳን የግንባታ ደህንነትን ለማስጠበቅ የተለያዩ አለም አቀም
እና የሀገር ውስጥ ህጎችና ደንቦች ቢኖሩም ተከታትሎ የማስፈጸም ስርዓቱ የላላ እንደሆነ
አሳይቷል፡፡ በባለድርሻ አካላት በኩልም ስለ ግንባታ አካባቢ ደህንነት የግንዛቤ እጥረት እንደሌለ
ግን በቸልተኝነት እና በቂ ትኩረት አለመስጠት የሚስተዋል ችግር ነው፡፡

እንነዚህንና መሰል ችግሮችን ለመፍታት ጥናቱ ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ጠቋሚ


የሄኑ የመፍሄ ሀሳቦችን አስቀምጧል፡፡ ለምሳሌ ያህል መንግስት የግንባታ አካባቢ ደህንነትን
በተመለከተ የተቀመጡ ህጎች ተፈጻሚ የሚሆኑበትን አስገዳጅ የሆነ የህግ ማዕቀፍ እንዲሆን
ቢያደርግ የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡

የስራ ላይ ጤንነትና ደህንነት ቅድመ ጥንቃቄን ተግባራዊ በማድረግ አንድ ስራ በተያዘለት


ወጪ፣ ጥራትና ጊዜ እንዲጠናቀቅ በማድረግ የግንባታውን ዘርፍ የተሸለ የአሰራር ስርአትና
ትርፋማነቱን በመጨመር ለአገር እኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲኖረው ማድረግ
ሲቻል ነገርግን በተጨባጭ አሁን ባለው የሀገራችን የኮንስትራክሽን ነባራዊ ሁኔታ የግንባታ
ደህንነት ቅድመ ጥንቃቄ በልምድና በዘፈቀደ እየተሰራ ያለና የደህንነት ባለሙያ (safety
Engineer) የሌለው በመሆኑ በአጠቃላይ ትኩረት ያልተሰጠዉ የተረሳ ጉዳይ ሆኖአል፡፡

viii
ክፍል አንድ
መግቢያ

1.1. ዳራ (Back ground of the study)


የኮንስትራክሽን ስራ ቦታ ደህንነት የሚጀምረው ከንድፍ ስራ ጀምሮ እስከ ስራ
ማጠናቀቂያ/ማስረከቢያ ድረስ ነው፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ባለፉት አስር ዓመታት
በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መሆኑ ይታወቃል እንደ እድገቱ መጠን ሁሉ
በኮንስትራክሽን የስራ ቦታ ብዙ አደጋዎች በሰው እና በንብረት ላይ እየደረሰ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ የሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባባቅ ገጽታ በተመለከተ


የግንባታው ዘርፍ ከ850,000 በላይ ለሚገመቱ ዜጎቻችን የሥራ እድል የፈጠረ የኢንዱስትሪ
ዘርፍ ነው፡፡ እድሜያቸው ከ30 ዓመት በታች የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችና ሴቶቸ
በተለያዩ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን የቅጥራቸው ሁኔታ ቀደም ሲል
ለመግለፅ እንደተሞከረው በጊዜያዊነት ወይም በኮንትራት ለተወሰ ጊዜ የተቀጠሩ ናቸው፡፡ በዚህ
መልክ የተቀጠሩ በርካታ የኮንስትራክሽን ሰራተኞች ከተቀጣሪ ድርጅቶቻቸው ጋር በመሰረቱት
የቃል/የጽሁፍ ውል መሰረት በቀን፤ በሳምንት፤ በሁለት ሳምንት ወይም በወር/በ26 የሥራ
ቀናት/ የታሰበ ወይም በቁጥር ሥራ የተሰላ የደመወዝ ክፍያ ያገኛሉ፡፡ [14]

የኮንስትራሽን ኢንደስትሪ ከስራ ባህሪ አኳያ ለተለያዩ ፊዚካል፣ ኬሚካል፣ ባዮለጂካልና


ኢኮኖሚካል ጠንቆች የሚያጋልጡ የስራ ሁኔታዎች ያሉት ሲሆን ከትራንስፖርት ዘርፍ ቀጥሎ
ከፍተኛ የሞት እና ከባድ የአካል ጉዳት የሚከሰትበት የስራ ዘርፍ ነው፡፡ [14]

የሙያ ደህንነት አጠባበቅ አለማቀፋዊ ገፅታ ስንመለከት እ.ኤ.አ 2013 የዓለም ስራ ድርጅት
ባወጣው ጥናታዊ ሪፖርት መሰረት በዓለማችን በየዓመቱ 331.5 ሚሊዮን የሚገመቱ የሥራ
ላይ አደጋዎችና 168.1 ሚሊዮን በስራ ምክንያት የሚከሰቱ በሽታዎች በሁሉም የኢንዱስትሪ
ዘርፎች ሰራተኞች ላይ እንደሚደርሱ ታውቋል፡፡ በዚህም የተነሳ 2.34 ሚለዮን ሠራተኞች
በስራ ላይ አደጋዎች ሳቢያ እንደሚያጡ ያለመከተው የድርጅቱ ሪፖርት በአማካይ በየአስራ
አምስት ሰከንድ አንድ ሰራተኛ ህይወት በስራ ላይ በሚደርስ አደጋ ሳቢያ እንደሚቀጠፍ
አስገንዝቧል፡፡

1
የስራ ላይ አደጋዎችና በስራ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በአሳሳቢ ደረጃ
እየጨመሩ መምጣታቸውን የጠቆመው ይህ ሪፖርት በተለይ አደገኛ የስራ ባህሪ ባላቸው
/ኮንስትራክሽ፣ ማዕድን፣, እርሻ/ የተሰማሩ የታዳጊ ሀገር ሰራተኞች የጉዳቱ ዋነኛ ተጠቂዎች
መሆናችን አመልክቷል፡፡ በስራ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችና የጤና ጉዳቶች በህይወት፣ በአካልና
በንብረት ላይ ያስከተሉት ውድመት በወጪ ሲሰላ የሀገሪቱን አጠቃላይ ብሄራዊ ገቢ እስከ 4%
እንደሚሸፍን ሪፖርቱ አሰታውቆ መንግስታት ይህን አሳሳቢ የልማት ችግር ትኩረት ሰጥተው
የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር እንቅሰስቃሴ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡[14]

አደጋ ማለት ማንኛውም በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ማለት ነው፡፡[3]
ይህም በሰው ሕይወት ላይ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡ በንብረት ላይ የሚደርሰው ጉዳት
በኢኮኖሚ እድገት ላይ ክፍተኛ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡ ይህ ሁኔታ በተመሳሳይ የሚቀጥል ከሆነ
በሀገራችን ያለውን የኮንስትራክሽኑን ኢንዱስትሪ ክፉኛ ይጎዳል በመሆኑም ይህ ጉዳይ ትኩረት
ይሻል፡፡ እንደ ILO መረጃ መሰረት 160 million አደጋዎች በየአመቱ እና 6,000 የሞት አደጋ
በየቀኑ በአለማችን ይከሰታል፡፡ የአለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት (International Labour
Organization) ዘገባ በየቀኑ በአለም ዙሪያ ቢያንስ 6,000 አደጋዎች በኮንስትራክሽን ስራ
አከባቢ ይፈጠራል ብሏል፡፡ በተለይ ባደጉት ሀገራት በስራ አከባቢ ከሚፈጠሩት የሞት አደጋዎች
ውስጥ ከ25-40% ያለው የሞት አደጋ የሚፈጠረው በኮንስትራክሽን ስራ አከባቢ ነው፡፡
እንዲሁም እንደ አለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት በአንዳንድ ሀገራት 30%ቱ የኮንስትራክሽን
ሰራተኞች በጀርባ ህመምና በጡንቻ መሸማቀቅ ህመም እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ገልጿል፡፡ በተለይ
በሀገራችን በኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ እየደረሰ ያለው አደጋን የሚያሳይ
መረጃ ባይኖርም ነገር ግን በኮንስትራክሽን ስራ አከባቢ ብዙዎች በደረሰባቸው አደጋ
ሕይወታቸውን አጥተዋል ብዙዎች የአካል ጉዳተኛ ሆነዋል በተለይ ደግሞ እጅግ የሚሳዝነው
ለዚህ አደጋ የተጋለጡት በስራው ላይ ያሉት ብቻ ሳይሆኑ በስራው ላይ ተሳታፊ ያልሆኑ
አዋቂዎችና ህፃናትም ጭምር ነው፡፡ [4]

1.2. ሰበበ ጥናት (Statement of the problem)


እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባሉት ሀገራት የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው በኢኮኖሚ
እድገት ላይ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ይታወቃል፡፡ ነገር ገን በሚያጋጥመው ተደጋጋሚ አደጋና
በጤንነት ለይ በሚፈጥረው ችግር ምክንያት ኢንደስትሪው አስጊ/አደገኛ እየሆነ መጥቷል፡፡
በኢንደስትሪው ውስጥ የሚከሰቱት አደጋዎች ቁጥር በጣም ከፍተኛ ሲሆን ይህ ቁጥር

2
ከኢንደስትሪው እድገት ጋር አብሮ የሚጨምር ይሆናል፡፡ ለዚህም ስለ ግንባታ አካባቢ ደህንነት
የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆን እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳል፡፡ በግንባታ አካባቢ ደህንነት
መጓደል ምክንያት የሰውን ህይወት አደጋ ላይ እሰከመጣልና ለሞት እስከ ማድረስ የሚደርስ
አደጋ ሲደርስ ይስተዋላል፡፡ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ በመሆኑ የተነሳ አደጋው በሰው ህይወት
ላይ ብቻ ሳይሆን በንብረት ላይ እንዲሁም አንድ ስራ በተያዘለት ወጪ፣ ጥራትና ጊዜ መሰረት
እንዳይጠናቀቅ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ ነው፡፡ ይህም የግንባታውን ጊዜ፤ ገንዘብና የሰው ሀይል
የታለመለትን ግብ እንዳይመታ ትልቅ እንቅፋት ከመሆኑም ባሻገር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ
ያዳክማል፡፡

1.3. የጥናቱ አስፈላጊነት፣


በሀገራችን ኢትዮጲያ እያደገ የመጣውን ኢኮኖሚ ተከትሎ በርካታ የኮንስትራክሽን ስራዎች
እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን በኮንስትራክሽን ስራ ደህንነት (work zone safety) ላይ ያለው
ነባራዊ ሁኔታ፣ የአሰራር ስርአት ወጥ ባለመሆኑ ምክንያት እና ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ
ባለመሆኑ በርካታ አደጋዎች ሲደርሱ ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን
ፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት በግንባታ ስራ አካባቢ ምክንያት የሚፈጠሩ በሰውም ሆነ
በንብረት ላይ የሚደርሱ ዋና ዋና አደጋዎችንና መንስኤያቸውን በመለየት እንዲሁም በአጠቀላይ
በሀገራችን ያለው የግንባታ አከባቢ ደህንነት ነባራዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ማጥናት
በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ውስጥ በደህንነት መጓደል ምክንያት የሚፈጠረውን የጊዜ፣
የገንዘብና የሰው ኃይል ብክነትን እንዲቀንስ በማድረግ ለተለያዩ በኢንደስትሪው ውስጥ የሚገኙ
ባለድርሻ አካላትን ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ እንዲሁም ለተቆጣጣሪው አካል በደህንነት ዙሪያ ያሉ
የህግ አፈጻጸም እና የአሰራር ክፍተቶችን በመለየት የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ አቅጣጫ
መጠቆም ለማስቻል ነው፡፡

1.4. የጥናቱ ዓላማ

1.4.1. ጥቅል አላማ


የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ፣ በመዲናችን አዲስ አበባ በኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት
ተግባራት ከሆኑት አንዱ የሆነውን የኮንስትራክሽን ስራ አካባቢ ደህንነት (work zone safety)
በአሁኑ ሰዓት ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መዳሰስ ነው፡፡

3
1.4.2. ዝርዝር አላማ
 በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የግንባታ አካባቢ ደህንነትን በተመለከተ የተቀመጡ ህጎቸችና
ደንቦች እና ተፈጻሚነታቸውን መለየት እንዲሁም በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ
መካተታቸውን ማረጋገጥ

 በደህንነት መጓደል ምክንያት የሚከሰቱ የአደጋ አይነቶች፣ መንስኤያቸውንና


ስፋታቸውን መለየት

 በግንባታ ስራ ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎችን ሪፖርት የማድረግ እና መረጃዎችን


በተደራጀ መልኩ የመያዝ ልምዱ ምን እንደሚመስል ማጥናት

 በግንባታ ስራ ላይ ቁልፍ ተዋናይ የሆኑት ባለድርሻ አካላት በግንባታ ቦታ ደህንነት ላይ


ያላቸውን የአሰራር ስርአት መለየት

1.5. የጥናቱ ወሰን


ይህ ጥናት ትኩረት ያደረገው በመዲናችን አዲስ አበባ በህንጻ ግንባታ ማለትም በጋራ መኖሪያ
ቤቶች ግንባታ (20/80 እና 40/60 ፕሮጀክት)፣ መንግስት በባለቤትነት እያስገነባቸው ያሉ
የተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ የግል የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች እና የመንገድ ግንባታ
ፕሮጀክቶች ላይ በግንባታ ስራ አከባቢ ደህንነት (work zone safety) በሚገባ ባለመተግበሩ
ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎችን መለየት ሲሆን ለአደጋው መፈጠር ጉልህ ድርሻ አላቸው
ተብሎ የሚታመንባቸውን መንስኤዎች አንጥሮ በመለየትና ስራውን በሚያካሂዱት ባላድርሻ
አካላት ላይ ያሉ የአሰራር ስርአቶችን፣ የህግ ተፈጻሚነቱን እና ስለ ግንባታ ስራ አከባቢ
ደህንነት (work zone saftey) ያላቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን በመለየት የመፍትሄ ሀሳቦችን
ማቅርብ ነው፡፡

1.6. የሚጠበቅ ውጤት፣


በግንባታ ስራ አከባቢ ደህንነት (work zone safty) በሚገባ ባለመተግበር ምክንያት የሚፈጠሩ
በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መንስኤቸውን በጥልቅ በመመርመር፣
ስራውን በሚያካሂዱት ባላድርሻ አካላት ላይ ያሉ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የመፍትሔ
ምክረ-ሃሳቦች ማመላከት ከዚህ ጥናት የሚጠበቅ ውጤት ነው፡፡ ከዚህ የዳሰሳ ጥናት መጠናቀቅ
በኋላ ቀጥሎ የተመለከቱ ዝርዝር ውጤቶች ይገኛሉ።

4
ሀ) በአሁኑ ጊዜ በአገራችን በተጨባጭ ያለው የግንባታ ስራ ደህንነት ሁኔታ

ለ) በኮንስትራክሽን ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶችና መንስኤዎቻቸው

ሐ) የመፍትሄ ሀሳቦች፣

መ) የተጠናቀቀ የመሰረታዊ የጥናቱ ሠነድ፣

1.7. የጥናቱ ዘዴ፣


ይህን የዳሰሳ ጥናት በመዲናችን አዲስ አበባ በሚገኙ የህንፃ እና የመንገድ ግንባታዎች ላይ
በግንባታ ስራ አከባቢ ደህንነት (Construction work zone safety) ጥንቃቄ ባለማድረግ
ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎችን ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡ ጥናቱ የገላጭ ምርምር ንድፍን
(Descriptive Research Design) መሰረት በማድረግ የተከናወነ ሲሆን ለጥናቱ ግብአት የሆኑ
የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ መረጃዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሸ አካላት፣ የግንባታ ቦታ ላይ
እና ቢሮዎች ላይ በአካል በመገኘት፣ ሪፖርቶችን፣ ጥናታዊ ፅሁፎችን እና የመረጃ መረብን
(Internet) በመጠቀም ተሰብስበዋል፡፡

1.7.1. የናሙና አመራረጥ ዘዴ


ለዚህ ጥናት የሚውል መረጃ ለመሰብሰብ በዋናነት ጥቅም ላይ እንዲውል የተመረጠው አላማ
ተኮር የናሙና አመራረጥ ዘዴ (Purposive sampling) ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ
የኮንስትራክሽን ስራ ብዙ አካላት የሚሳተፉበት በመሆኑ ለጥናቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸውን
አካላት የጥናቱን ልዩ ባህሪና ዓላማ መነሻ በማድረግ፣ በመለየት እና ከእነርሱም ሊወክል
የሚችል የናሙና መጠን በመውሰድ ጥናቱን ማከናወን በማስፈለጉ ነው፡፡

5
የግንባታ ቦታ አመራረጥን በተመለከተ ናሙና ለመውሰድ እንደ መመዘኛነት የተጠቀምናቸው
መስፈርቶች፤ በመንግስት ባለቤትነት እየተሰሩ ያሉ የግንባታ ስራዎች( የጋራ መኖሪያ ቤቶች
እና ሌሎች ግንባታዎች)፣ የግል ፕሮጀክቶች እና የመንገድ ፕሮጀክቶች ሆነው ከደህንነት ጋር
ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች ለማየት በግንባታ ላይ የሚገኙ ወይም ግንባታቸው ወደ
መጠናቀቅ የደረሱ የተመረጡ ሲሆኑ በነዚህ የግንባታ ቦታዎች በአካል በመገኘት መረጃ
ለመሰብሰብ ተችሏል፡፡ በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ መንንዶች ባለስልጣን በባለቤትነት
እያስገነባቸው ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶችን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ የግል
ፕሮጀክቶችን እንዲሁም መንግስት እያስገነባቸው ያሉ የፌደራል መንግስት ህንፃዎች፣
የኮንስትራክሽን እና አስተዳደር ቢሮዎች፣ የክፍለ ከተማ ግንባታዎች፣ ሌሎች የመንግስት
ድርጅቶች እንዲሁም በ20/80 እና በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች
በናሙናነት ተመርጠዋል፡፡ እነዚህንም የግንባታ ቦታዎች ሙሉ ለመሉ ተደራሽ ለማድረግ
ተችሏል፡፡

ይንንም ተግባራዊ ለማድረግ በግንባታ ቦታ ላይ የሚገኙትን ባለድርሻ አካላት ማለትም


ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ የግንባታ ባለቤቶች እንዲሁም የግንባታ ሰራተኞችን የናሙና
መጠኑም 95% ትክክል ቢሆንና(Level of Confidence) 5% ደግም ስህተት ቢኖረዉ
(Possible errors) በሚለው አግባብ በብዛት መለኪያ (Sample size calculator
application)ሦፍትዌር የተሰላ ነው፡፡ ይህን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚከተለው ሰንጠረዥ
በዝርዝር ተቀምጧል፡፡

6
የጥናቱን የናሙና አወሳሰድ ዘዴ የሚያሳይ ሠንጠረዥ
ተ በአዲስ አበባ በመንግስት ባለቤትነት የሚሰሩ የፕሮጀክት በጥናቱ ተደራሽ በጥናቱ ተደራሽ ምርመራ

ቁ ፕሮጀክቶች ብዛት መደረግ ያለበት ተደራሽ ተደርገው


በቁጥር የናሙና ብዛት የተደረገ ምላሽየሰጡ

በቁጥር በቁጥር
1 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት 13 የናሙና መጠኑም 90% ትክክል ቢሆንን
(Level of confidenece) 10% ደግሞ
ቢሮ
ሥህተት ቢኖረዉ (possible/megin of
2 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን 49 Errors) በሚለዉ አግባብ የተሠላ ነዉ
ቢሮ
3 በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር 5
4 በአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ 7
5 በተለያዩ የመንግስት ድርጅቶች የሚገነቡ 6
48 52
6 በተለያዩ የግል የግንባታ ፕሮጀክቶች 80
ድምር 160
7 በአዲስ አበባ ከተማ ግንባታቸው እየተካሄደ ያለ 21 18 18
የመንገድ ፕሮጀክቶች

በ2008 ህንፃ ፕሮጀክቶቹ ላይ የሚሣተፉ ብዛት በጥናቱ ተደራሽ በጥናቱ በጥናቱ የናሙና መጠኑም 95% ትክክል ቢሆንን
መደረግ ተደራሽ (Level of confidenece) 5% ደግሞ ሥህተት
የተቋራጭና የግንባታ አማካሪወች ብዛት በቁጥር ያለበት ተደራሽ
ናሙና ብዛት በቁጥር ተደርገው ቢኖረዉ (possible/margin of Errors)
የተደረገ
ምላሽ የሰጡ በሚለዉ አግባብ የተሠላ ነዉ
በቁጥር
1 የሥራ ተቋራጮች 1462 323 359 217
2 የግንባታ አማካሪዎች 60 53 53 31
በ2008 ግንባታቸው እየተከናወኑ ላሉ የመንገድ
ፕሮጀክቶቹ ላይ የሚሣተፉ የተቋራጭና
የግንባታ አማካሪወች ብዛት
የሥራ ተቋራጮች 21 18 18 17
የግንባታ አማካሪዎች 13 13 12 11

በዚህም መሰረት በድምሩ በመንገድና በህንፃ ግንባታ 377 የሥራ ተቋራጮችን ተደራሽ
ተደርገው ነገርግን 234 ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ 65 አማካሪዎች ተደራሽ ተደርገው 42 ምላሽ
ሰጥተዋል፣ 34 የግንባታ ባለቤቶቸ ተደራሽተደርገው 34 ምላሽ ሰጥተዋል በተጨማሪም 812
የግንባታ ሰራተኞች ተደራሽ ተደርገው 474 ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

7
1.7.2. የመረጃ ማሰባሰቢያ መሳሪያዎች (Data gathering tools)
ይህን የዳሰሳ ጥናት ዓላማ ከግብ ለማድረስ በኮንስትራክሽን ስራ ደህንነት (work zone safety)
በሚገባ ባለመተግበሩ ምክንያት የሚፈጠሩ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን
መንስኤቸውንና መደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ከስራ
ተቋራጭ፣ አማካሪ፣ ከግንባታ ባለቤት ፣ስራውን ከሚያከናውኑት የግንባታ ሰራተኞች፣
ከሆስፒታል፣ ከትራፊክ ማኔጂመንት ኤጀንሲ፣ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና
መቆጣጠር፤ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፤ ከሰራተኛና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከመንገዶች
ባለስልጣን እና የመሳሰሉት መረጃ ለማሰባሰብ የሚያስፈልጉ የአጠናን ስልቶች እንደሚከተለው
ተገልጿል፡፡

ሀ. በመጠይቅ (Questioner based sample survey) ፡

የግንባታ ስራውን የሚያከናውኑ ባለድርሻ አካላት ማለትም የስራ ተቋራጮችን፣


አማካሪዎችን፣ የግንባታ ባለቤቶችን፣ ሰራተኞችን እንዲሁም የደህንነት ዕቃ አቅራቢዎችን
መጠይቅ በመስጠትና በመቀበል መረጃ ተሰብስቧል፡፡

ለ. ቃለ-መጠይቅ በማከናወን (Key Informant Interview)

በተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክቶች የሚገኙ 34 ባሙያዎችን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ


ተችሏል፡፡ በቃለ መጠይቁ ውስጥ የተካካቱት ባለሙያዎች

 ከተቋራጭ ፕሮጀክት ማኔጀሮችና የሳይት መሀንዲሶች

 ከአማካሪ ፕሮጀክት ተቆጣጣሪ መሀንዲሶች፣ የሳይት መሀንዲሶች

 ከግንባታ ባለቤቶች የፕሮጀክት ፅ/ቤት ኃላፊዎች

 የግንባታ ቀጥጥር የስራ ሀላፊ

የግንባታ ስራውን በቀጥታ ከሚያከናውኑት ባለድርሻ አካላት በተጨማሪ

 ከሆስፒታሎች ሜዲካል ዳይሬክተሮች

 ከትራፊክ ማኔጂመንት ኤጀንሲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ

 ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና መቆጣጠር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ

 ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ


8
 ከሰራተኛና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ጋር ቃለ-መጠቅ
በማድረግ መረጃ ለመሰበሰብ ተችሏል፡፡

ሐ. የትኩረት ቡድን ውይይት በማከናወን (Focous group discussion)

በግንባታ አካባቢ ደህንነት ላይ ቁልፍ ድርሻ ያላቸውን ባለድርሻ አካላት በመለየት እና


የእነርሱም ወኪሎች በውይይት እንዲካፈሉ በመጋበዝ በግንባታ አካባቢ ደህንነት ላይ በ11
የቡድን ውይይቶች ውስጥ 183 ባለሙያዎችን በማሳተፍ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በእነዚህ
ውይይቶች ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ማለትም ከአሰሪ፣ ከተቋራጭ፣ ከአማካሪ እና
ከመንግስት የኮንስትራክሽን ቢሮዎች የተወከሉ ግለሰቦች በተለያዩ ጊዜና ቦታዎች ላይ
ተካፋይ ሆነዋል፡፡ በውይይቱም ላይ ተሳታፊ የሆኑት ባለሙያዎች እንደሚከተለው
ተዘርዝረዋል፡፡

 የግንባታ ባለቤት፣ የስራ ተቋራጮች እና የአማካሪ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆችና


ምክትል ሥራ አስኪያጆች

 የግንባታ ግብዓት ጥራትና ቁጥጥር ባለሙያዎች

 የግዥ ሲኒየር መኮንኖች (ኦፊሰር)

 የግንባታ ክፍል ዉል/ዉለታ አስተዳደር ሲኒየር እና ጁኒየር ኦፊሰሮች

 የግንባታ ክትትል ዉለታ አስተዳደር የስራ ሂደት መሪ

 የግንባታ ባለቤት እና የአማካሪ ተቆጣጣሪ መሃንዲሶች/ኮኦርዲኔተር

 በፕሮጀክት ላይ ያሉ የአማካሪና የተቋራጭ የቢሮ እና ሳይት መሃነዲሶችን

 ሣይት ፎርማን

 የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልታን ክተኛ የስራ ሀላፊዎችና መሀንዲሶች እንዲሁም


ግንባታውን የሚያከናውኑት ተቋራጮች እና አማካሪዎች

መ. በግንባታ ሳይቶች ተገኝቶ ተግባራዊ ምልከታ በማድረግ፣

ለናሙና በተመረጡት በአዲስ አበባ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች


ማለትም፣ በከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የፌደራል መንግስት ህንፃዎች ኮንስትራክሽን
እና አስተዳደር ቢሮዎች፣ በተለያዩ የመንግስት ድርጅቶች የሚሰሩ ህንፃ ግንባታዎች፣ በአ/አ

9
ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተር ፕራይዝ (40/60)፣ በአዲስ አበባ ቤቶች
ልማት ኘሮጀክት ጽ/ቤት (20/80)፣ የግል የግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የመንገድ
ፕሮጀክቶች ላይ የመስክ ምልከታ በማካሄድ አጠቃላይ የደህንነት ሁኔታው ምን
እንደሚመስል በፎቶግራፍ እና በቪዲዮ ማስረጃ በማከል መረጃ ተሰብስቧል፡፡

በአጠቃላይ በመጠይቅ፣ በቃለመጠይቅ እና በትኩርት ቡድን ውይይት ተሳታፊ የሆኑት


በሚከተለው ሰንጠረዥተጠቃለዋል

ተ.ቁ ባለድርሻ ተቋማት(ጽ/ቤቶች) የተሣፊ ባለሙያዎች ብዛት ምርመራ

1 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ (ዋና መስሪያ ቤት) 13 ስድስት ኪሎ

2 የአዲስ አባባ ከተማ የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ 40/60 ዋና መስሪያ ቤት 8 አራት ኪሎ

3 የ40/60 ቁጠባ ቤቶች፤- ቦሌ ቡልቡላ ፕሮጀክት ቅ/ፅ/ቤት 8 ቅርንጫፍ


ፅ/ቤት
4 የ40/60 ቁጠባ ቤቶች፤- ቦሌ አያት ቅ/ጽ/ት 7 ቅርንጫፍ
ፅ/ቤት
5 የ40/60 ቁጠባ ቤቶች፤-እህል ንግድና ቱሪስት ቅ/ፅ/ቤት
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኘሮጀክት ጽ/ቤት (20/80)
1 ቦሌ ቤቶች ግንባታ ቅ/ፅ/ቤት፤የካ/ክ/ከተማ ቅ/ፅ/ቤት፤ቦሌ አራብሣ ቅ/ፅ.ቤት 03 23 የሶስት
ፕሮጀክት
ቅ/ፅ/ቤቶች
2 ኮየ ፈቼ ፕሮጀክት 11 ፤17 እና 18 23 የሶስት
ፕሮጀክት
ቅ/ፅ/ቤቶች
3 ኮየ ፈቼ ፕሮክት 16፤12 እና አቃቂ 28 የሶስት
ፕሮጀክት
ቅ/ፅ/ቤቶች
4 አራዳ ክ/ከታማ ቤ/ል/ቅ/ፅ/ቤት (ፉሪ ሃና ሳይት) 13
5 ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ቤ/ል/ቅ/ፅ/ቤት/(የካ ጣፎ) 10
ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸዉ አካላት የስራ ድርሻ
1 የፌደራል መንግስት ህንፃዎች ኮንስትራክሽን እና አስተዳደር ቢሮ (የዳኞች መኖሪያ)
አልተገኙም

2 የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ተቋራጭ፤አማካሪና ሣይት
መሃንዲስ

3 የኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ምኒስቴር ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ተቋራጭ አማካሪዉ


አልተገኘም
4 የአራዳ ክ/ከተማ ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ተቋራጭ እና አማካሪ
5 የቂርቆስ ክ/ከተማ ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ተቋራጭ እና አማካሪ
6 የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ህንፃ ግንባታ ፕሮጀክት ተቋራጭ እና አማካሪ
7 የአ.አ ቤቶች ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት (ፕሮጀክት 11) ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ
8 የአ.አ ቤቶች ግንባታ ፕ/ጽ/ቤት (ፕሮጀክት 18 ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ
9 የአቃቂ ክ/ከተማ ቤቶች ግንባታ ቅ/ጽ/ቤት-ስራ አስኪያጅ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ
10 የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና
መሀንዲሶች

10
11 ሪፈራል ሆስፒታሎች የሆስፒታሉ ሜዲካል
ዳይሬክተሮች

12 የግል የግንባታ ፕሮጀክቶች የተቋራጭ እና የአማካሪ


መሀንዲሶቸ

13 የግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን የስራ ሀላፊ

14 ከትራፊክ ማኔጂመንት ኤጀንሲ ከፍተኛ የስራ ሀላፊ

15 ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከያና መቆጣጠር ከፍተኛ የስራ ሀላፊ

16 ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ የስራ ሀላፊ

17 ከሰራተኛና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊ

1.7.3. የመረጃ መተንተኛ ዘዴ


ለጥናቱ ግብአት የሚሆኑ መጠናዊ እና አይነታዊ መረጃዎች (Qualitative and quantitative
data) የተሰበሰቡ ሲሆን ለዚህ አመቺ የሆኑ መጠናዊ እና ገላጭ የመረጃ መተንተኛ ዘዴዎችን
ማለትም ስታቲስቲካል (SPSS) እና Excel በመጠቀም የመረጃ ትንተናው ተከናውኗል፡፡
በጥናቱ ውስጥ የተካተቱ መረጃዎች ርእሰ ጉዳዮች መሰረት በማድረግ በየፈርጁ በመመደብ
ትንታኔ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

1.8. የጥናቱ ውስንነት (Limitation)


ይህ ጥናት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የመንገድና የህንፃ ግንባታዎችን ብቻ ተደራሽ ያደረገ
ሲሆን ይህ ደግሞ በኢንዱስትሪው ላይ እንደ አጠቃላይ ያለውን የግንባታ አካባቢ ነባራዊ ሁኔታ
እና በዘርፉም እየደረሰ ያለውን አደጋ በበቂ ሁኔታ ሊያሳይ አይችልም፡፡ በመሆኑም የጥናቱ
ውጤት ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ከተሞችን ላይወክል ይችላል፡፡

1.9. ያጋጠሙ ችግሮች (Challenges of the study)


ጥናቱ ከብዙ ባለድርሻ አካላት ጋር ስለሚያገናኝ መጠይቅ ለማስሞላትና አንዳንድ የጽሁፍና
የቃል መረጃዎችን ለማግኘት እንደ አጠቃላይ በሀገራችን ካለው የመረጃ አያያዝ ስርአትና
መረጃን የመስጠት ባህላችን ዝቅተኛ በመሆኑ አንዳንድ ተቋማት የተሰጡትን መጠይቆች
ትኩረት ሰጥቶ በአግባቡ ያለመሙላትና ሙሉ ለሙሉ ባዶ የመመለስ እንዲሁም መረጃ
ለመስጠት ማመላለስና ማጉላላት፣ የቀን ሰራተኛው ማንበብና መፃፍ የማይችል መሆኑ
እንዲሁም አንዳንዶቹ አማርኛ ቋንቋ መስማትና መናገር አለመቻላቸው በተጨማሪም በተደረጉ
ውይይቶች ላይ ባለድርሻ አካላቱ በደህንነት ጉዳይ ትኩረት ባለመስጠት ጠቃሚ የሆኑ ሀሳቦችን
ያለማንሳት በጥናቱ ውስጥ ትልቅ እንቅፋት ሆኖብናል፡፡

11
ክፍል ሁለት
2. የቀደምት ጥናቶች ዳሰሳ (Literature review)

2.1. ትርጉም

2.1.1. ደህንነት

2.1.2. የግንባታ አካባቢ ደህንነት ትርጉም


የስራ አካባቢ ደህንነት ማለት በስራ ቦታ ላይ የሚደርስ የሰራተኞች ጤናን ሊያውኩና ሊጎዱ
የሚችሉ አደጋዎችን የማጤን፣ የመለየት፣ የመገምገም እና የመቆጣጠር ሳይንሳዊ ሂደት ነው፡፡

2.2. የስራ ላይ ደህንነት ፕሮግራም ክፍሎች/ Elements of safety program


 የስራ ሀላፊነትን መመደብ

 አደጋን ቀድሞ መለየትና መቆጣጠር

 ስልጠና መስጠትና ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግ

 የስራ ቦታ ደህንነት ህጎችና ደንቦችን በተደራጀ መልኩ መያዝና ተፈፃሚ ማድረግ

 ምቹ የስራ ሁኔታን ማስጠበቅ

 ለሚከናወነው ስራ የአፈፃፀም ኢላማ ማስቀመጥ

 በስራ ደህንነት ላይ የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን ማበረታታት

 ለአደጋ አጋላጭ የሆኑ ሁኔታዎችን መከለስ እና ማጥራት እንዲሁም አስፈላጊውን


የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ

 የደህንነት አፈፃፀም አላማን በሁሉም የማኔጅመንት ደረጃዎች ማስቀመጥ

 የስራ ደህንነትን በማኔጅመንት አፈፃፀም ውስጥ አንዱ አካል እንዲሆን ማድረግ

 ለተፈፃሚነቱ ልኬት ማስቀመጥ እና

2.3. የደህንነት ልምድን አስቀድሞ በፕሮጀክት ላይ ማቀድ ያለው ጠቀሜታ


 በሰራተኞች በኩል የሚቀርብ የካሳ ይገባኛል አቤቱታን ይቀንሳል

 ለአደጋና ህመም የሚወጣ ወጭዎችን ይቀንሳል

 ከስራ መቅረትን ይቀንሳል

 የተቀጣሪዎችን ቅሬታ ይቀንሳል

 የተቀጣሪዎችን የስራ ተነሳሽነትና እርካታ ይጨምራል

 ዉጤታማትን ይጨምራል

12
 ያልታሰቡ ወጪዎችን ይቀንሳል

 አደጋ በሚከሰት ጊዜ የሚከፈል ካሳን ይቀንሳል

2.4. የግንባታ ቦታ ላይ አደጋዎች


1. ስካፎልዲንግ
ስካፎልዲንግ አካባቢ የሚሰሩ ሰራተኞች እራሳቸውን ከሚወድቁ ዕቃዎች፤ ከኤሌክትሪክ
ገመድ መጠበቅ አለባቸው፡፡ እነዚህን አደጋዎች ከምንም በላይ መቆጣጠር አለብን፡፡
ትክክለኛ እስካፎልዲንግ (steel scaffolding) በሁሉም አቅጣጫ ከመውደቅ የሚከላከል
ብሎኖች የተገጠመለት እና ብሎኑም ከስካፎልዲንጉ ጋር የተጣጣሙ መሆን አለባቸው፡፡
2. መውደቅ
መውደቅ ለከባድ ጉዳት ብሎም ለሞት የሚያደርስ አደጋ ነው፡፡ ስራን በከፍታ ቦታ ላይ
የሚሰሩ ሠራተኞች ሰለሚጠቀሙት መሳሪያዎች እና ሊከሰቱ ስለሚችለው አደጋ ስልጠና
መውሰድ አለባቸው፡፡ ብቁ የሆነ ሠራተኛ ወደ ስራ ከመግባቱ በፊት የተጠቀመውን
መሳሪያዎች እንዳልተበላሹ ፤ ጉድለት እንደሌለባቸው ማረጋገጥ አለበት፡፡
3. የበሽታዎች አደጋ
ሠራተኞችን ለመተንፈሻ በሽታዎች እንዳይጋለጡ እራሳቸውን ከኬሚካል ጋር ተያያዥነት
ያለው ስራዎች በሚሰሩ ጊዜ መጠንቀቅ እና መከላከያ መሳሪያዎች መጠቀም አለባቸው፡፡
4. መሠላል
አብዛኛው መውደቅ የሚከሰተው በመሠላል ምክንያት ነው፡፡ እያንዳንዱን መሠላል
ከመጠቀም በፊት የተበላሸ ወይም እማይሰራ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ በምንጠቀምበት
ጊዜ በትክክለኛ አንግል ላይ ማስቀመጥ አለበን፡፡ ሌላ አማራጭ ካለ ልክ አንደ ስካፎልዲንግ
ወይም ሊፍቲንግ መሠላልን መጠቀም የለብንም፡፡
5. የደህንነት መሳሪያ ባለመኖር
ሰራተኛውን ቀጥሮ የሚያሰራው አካል ለሰራተኛው ሙሉ የደህንነት መሳሪያ ማሟላት እና
በየጊዜው የማደስ ግዴታ አለበት፡፡ ሁሉም ስራተኛ እራሱን ከሚወድቁ አቃዎች፤ ከአቧራ፤
ከኬሚካሎች፤ ከሚስማር አና ከመሳሰሉት የመጠበቅ መብት እና የሚጠቀምብትን መሳሪያ
ጉድለት የሌለበት እና ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፡፡
6. እሳት አደጋ
በግንባታ ቦታ ላይ እንጨት እስካለ ድረስ የእሳት አደጋ በጣም ትኩረት መሠጠት ያለበት
ጉዳይ ነው፡፡ የእሳት ማጥፊያው በየቦታው መቀመጥ እና በቀላሉ የሚታይበት ቦታ ላይ

13
መሆን አለበት፡፡ ሠራተኞቹ አደጋ በሚደርስ ጊዜ ማድረግ ስላለባቸው ድርጊቶች መሰልጠን
አለባቸው፡፡
7. አደጋን አለመመዝገብ እና አለማስቀመጥ
ማንኛውንም ሠራተኛ ላይ የደረሰን አደጋን፣ የተወሰደውን ህክምና አለመመዝገብ ለወደፊት
ሊደርሱ ለሚችሉ አደጋዎች መፍትሄ እንዳይኖር ያረጋል፡፡ ከሌሎች ተሞክሮ እንዳየነው
የግንባታ ቦታ ድህረ-ገፅ መፅሀፍ ስለ ተከናወኑት ስራዎች ሁሉ የሚተርክ እና አንድ ችግር
ሲፈጠር መፍትሄ የካተተ መፅሀፍ ማዘጋጀት አመዘጋገቡን ቀላል ያደርገዋል፡፡
8. ብየዳ
መበየድ የተለመደ የግንባታ ቦታ ላይ ስራ ሲሆን አብዛኛው በያጅ ስራውን አቅልሎ በማየት
እና የደህንነት መሳሪያ መጠቀም አመቺ ስላልሆን ቸልተኛ ይሆናል፡፡ ምንም ቸልተኛ
ቢሆንም በሚበየድበት ወቅት የብረት ፍንጣቂዎች አይን ውስጥ እንዳይገባ ግዴታ የአየን
መከላከያ መነፅር መጠቀም አለበት፡፡
9. ስልጠና አለመኖር
የስራ ቦታ ላይ አደጋዎች ለመቀነስ በየጊዜው ስልጠና መስጠት ዋናው ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡
የግንባታ ቦታ ተቆጣጣሪው ሠራተኞቹ በየጊዜው ስልጠና አንደሚወስዱ እነ ስለ ስራ ቦታ
ደህንነት በቂ አውቀት እንዳላቸው የማወቅ ገዴታ አለበት፡፡ ሠራተኛው የስራውን ህግ
ማወቅ እና እራሱን ብሎም በአካባቢው ላለው ማህበረሰብ ደህንነትን ስለ መጠበቅ ስልጠና
መውሰድ አለበት፡፡

2.5. በግንባታ አካባቢ የአዳጋና የጉዳት መንስኤዎች

2.5.1.1. እንደ አጠቃላይ በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ የሚደርሱ የአደጋ መንስኤዎች


የኮንስትራሽን ኢንደስትሪ ከስራ ባህሪው አኳያ ለተለያዩ ፊዚካል፣ ኬሚካል፣ ባዮሎጂካልና
ኢኮኖሚካል ጠንቆች የሚያጋልጡ የስራ ሁኔታዎች ያሉት ሲሆን ከትራንስፖርት ዘርፍ ቀጥሎ
ከፍተኛ የሞት እና ከባድ የአካል ጉዳት የሚከሰትበት የስራ ዘርፍ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በዘርፉ
ከአደጋ የተጠበቀና ምቹ የስራ ሁኔታ በመፍጠር ረገድ በተጨባጭ የታዩ ክፍተቶች
እደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

14
1. የፖሊሲ/ የህግ ክፍተት
2. የአደረጃጀት ክፍተት
3. የግንዛቤ ክፍተት
4. የመረጃ ክፍተት
5. የቅንጅት ክፍተት
6. የህግ አፈጻጸም ክፍተት
7. የጥናትና ምርምር ክፍተት
8. የክትትልና ግምገማ ክፍተት

2.5.1.2. በግንባታ አካባቢ የተለመዱ የአደጋና የሞት መንስኤዎች የሚከተሉትን ይመስላሉ


 መውደቅ፡ ወደ ስራ ቦታና ከስራ ቦታ ወደ ውጪ የሚወስዱ መንገዶች የተመቹና በቂ
ባለመሆናቸው ምክንያት ብዙ ሰራተኞች የመውደቅ አደጋ ያጋጥማቸዋል፡፡
 የግብአቶች መወደቅና የመደርመስ አደጋ፡- የስትራክቸራል መደርመስ ማለትም ግድግዳ
መፍረስ (ፋውንዴሽን ስራ በሌላ የቁፋሮ ስራ ምክንያት የመፍረስ አደጋ ሊያጋጥመው
ይችላል) እንዲሁም ሙሉ ህንፃው ሊፈርስ ይችላል፡፡ ይህ ደግሞ በሰራተኞች ላይ ቀላል
የማይባል አደጋን ያስከትላል፡፡
 የኤሌክትሪክ አደጋ፡- መሬት ውስጥ የተቀበሩ የኤሌክትሪክ መስመሮች፣ ደህንነታቸው
ያልተጠበቁ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና ተገቢውን የሆነ የደህንነት አልባሳትን
ባለመጠቀም ምክንያት ሰራተኞች በኤሌክትሪክ የመያዝና የመቃጠል አደጋ ሊደርስባቸው
ይችላል፡፡
 እንቅፋት(Trip)፡- እንቅፋት በጣም የተለመደ የግንባታ አካባቢ የአደጋ መንስኤ ነው፡፡
 አስቤስቶስ:- በውስጡ በሚይዘው ኬሚካል ምክንያት ለመተንፈሻ አካል በሽታ ሊያጋልጥ
ይችላል፡፡
 Manual handling:- ከባድ የሆኑ እቃዎችን በማንሳትና በመግፋት ምክንያት የጀርባ
ህመምን ያስከትላል፡፡
 ድምፅና መንቀጥቀጥ፡- በግንባታ አካባቢ ላይ የሚሰማው ከፍተኛ የሆነ ድምፅ የጆሮ
ህመምን ሊያስከትል ይችላል፡፡ Vibrating ማሳሪያዎችን ደጋግሞ በመስራት የእጅ
ህመምን ሊያስነሳ ይችላል፡፡
 ኬሞካሎች፡- እንደ ሲሚንቶ ያሉ የተለያዩ ኬሚካል ያላቸው ግብአቶች የቆዳ በሽታን
ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡
15
 Mobile plant፡- በግንባታ አካባቢ የሚገኙ መሳሪያዎች ከባድ በመሆናቸው ምክንያት
ባልተመቻቸ የመሬት አቀማመጥና ጭቃማ በሆነ ቦታ ላይ የሚንቀሳቅሱት ሰራተኞች
አደጋ ሊደርስባቸው ይችላል፡፡

2.6. የግንባታ ደህንነትን የሚጎዱ ሁኔታዎች


 ፕሮጀክት ማኔጀሮች ወይም ስራ ተቋራጮች ስለ ደህንነት በቂ ትኩረት አለመስጠት
 ሰራተኞች ስለ ደህንነት በቂ ትኩረት አለመስጠት
 በቂ ሆነ ስልጠና አለማግኘት
 የደህንነት እቃዎች እጥረት
 ለደህንነት ስራ በቂ በጀት አለመመደብ

2.7. የግንባታ ደህንነትን የተመለከቱ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ ህጎች

2.7.1. የግንባታ ደህንነት የተመለከቱ ህጎች

2.7.1.1. የፍትሀ ብሄር ህግ (አንቀፅ 2548-2556)


አንቀፅ 2548፡

1. የሰራተኛውን ህይወት ሙሉ ሰውነቱን ጤንነቱን የህሊና(የሞራል)፣ ክብሩን በመጠበቀ


ረገድ አሰሪው ለስራው ልዩ ሁኔታዎች ተገቢ የሆኑትን ጥንቃቄዎች ሁሉ ማድረግ
አለበት፡፡
2. በልምድና በቴክኒክ ስራዎች መሰረት በዚሁ ረገድ ለስራ ማካሄጃ ቦታዎችን ማቋቋምና
አስፈላጊ መሳሪያዎችን በተለይ ማደራጀት አለበት

አንቀፅ 2549፡ በሥራ ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎች

በሥራው ምክንያት በሰራተኛው ላይ ለሚደርሱ አደጋዎች አሰሪው ኃላፊ ነው፡፡

አንቀፅ 2550፡ ለሥራው ተመሳሳይ ለስለሚሆን ሌላ ሥራ፡፡

ይህ ሥራ በአሰሪው የታዘዘም ባይሆን ለስራ ማካሄጃ ጥቅም ሰራተኛው በሚሰራው ስራ


ማካሄድ ምክንያት ለሚደርሱበት አደጋዎች አሰሪው ኃላፊ ነው፡፡

አንቀፅ 2551፡ በሠሥራው ጊዜና ቦታ ስለሚሆኑ አደጋዎች

16
1. ሰራተኛው በአንድ በተወሰነለት መሬት ወይም ቦታ ውስጥ የስራውን አገልግሎት
ሲፈጽም የሆነ እደሆነ በስራው ጊዜና ቦታ በሰራተኛው ለሚደርሱበት አደጋዎች አሰሪው
ኃላፊ ነው፡፡
2. በሥራ ሰዓት የሚፈቀደው የእረፍት ጊዜ እንደ ስራ ጊዜ ሆኖ ይቆጠራል፡፡
3. በነዚሁ የእረፍት ጊዜ የሰራተኞች ማረፊያ የተዘጋጁ ቦታዎች እንደ ስራ ቦታ ክፍል
ሆነው ይቆጠራሉ፡፡

አንቀጽ 2252፡ በሙያ ሰራተኞች ላይ ስለሚደርሱ አደጋዎች

1. በሰራተኛ ላይ በስራው ምክንያት ለሚደርሱበት በሽታዎች አሰሪው ኃላፊ ነው


2. ምንም ተቃራኒ ማስረጃ ቢኖር እንኳ የአስተዳደር ደንቦች በልዩ ልዩ ኢንደስትሪዎች
የሚደርሱትን በስራ ላይ እንደደረሱ የሚቆጠሩትን በሽታዎች ይወስናሉ፡፡
3. ከነዚህ በሽታዎች ዝርዝር ውጪ ለሆነው ወይም የነዚህ ዝርዝር በሌላ ጊዜ ሰራተኛው
በስራው ምክንያት በሽታው የደረሰበት ለመሆኑ በማንኛቸውም ጊዜ ለማስረዳት ይቻላል፡፡

አንቀጽ 2253፡ ስለ አሰሪው ከኃላፊነት መዳን

ጉዳት የደረሰበት ሰው ጥፋት

1. አደጋ ወይም በሽታው የደረሰበት ሰው አስቦ ባደረገው ጥፋረ መሆኑ አሰሪው ካስረዳ
ከዚህ በፊት ባሉት ቁጥሮች ከተወሰነው ኃላፊነት አሰሪው ነጻ ይሆናል፡፡
2. እንዲሁም አደጋው ወይም በሽታው የደረሰበት ሰራተኛ በግልጽ በጽሁፍ የተሰጠውን
ትእዛዝ በመተላለፍ መሆኑን ካስረዳ አሰሪው ነፃ ይሆናል፡፡

አንቀፅ 2554፡ ከሥራው ጋር ግንኙነት ስላለመኖር

አደጋው ከሰራተኛው ስራ ጋር ወይም ሰራተኛው ግንኙነት ካለው ከስራ ውል ጋር ምንም


ግንኙነት የሌለው መሆኑን ካስረዳ አሰሪው ኃላፊነት የለበትም፡፡

አንቀፅ 2555፡ ሌሎች ምክንያቶች

አሰሪው በሌላ በማንኛቸውም ምክንያት ከኃላፊነት አይድንም

አንቀፅ 2556፡ የኃላፊነት መጠን

የህክምናና ሌሎች ወጪዎች

17
1. አሰሪው ስለ ህክምና መድሀኒቶች፣ ሆስፒታልና ሌሎችም አደጋ ወይም በሽታው
ሰራተኛውን የሚያስገድዱትንና በሚገባ አኳኋን የተደረጉትን ወጪዎች ሁሉ መክፈል
አለበት፡፡
2. በአደጋው ወይም በበሽታው ጠንቅ ሰራተኛው የሞተ እንደሆነ በዚሁ አኳኋን ለመቃብር
ሥርአቶች አስፈላጊ የሆኑትን ወጪዎች አሰሪው መክፈል አለበት፡፡

2.7.1.2. ከፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ አንቀጽ 31 - 32


"1. በግንባታ ወቅት መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የዚህ አዋጅ አንቀጽ" ደንጋጌዎች እንደ
ተጠበቁ ሆነው፤

1. ማንኛውም ግንባታ በግንባታው አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን፣ የግንባታው ሠራተኞ


ችን፣ የሌሎች ግንባታዎችን ወይም ንብረቶችን ደህንነት በማያሰጋ መንገድ ዲዛይን
መደረግና መገንባት ይኖርበታል፣
2. ከግንባታ ጋር የተያያዘ ቁፍሮ የማንኛውንም ንብረት ወይም አገልግሎት ደህንነት ጉዳት
ላይ የሚጥል ሲሆን የግንባታ ቦታው ባለቤት የንብረቱን ወይም የአገልግሎቱን ደህንነት
ለመጠበቅ በቂ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፣
3. የተቆፈረው ጉድጓድ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ወይም በጉድጓዱ ውስጥ መሠረት
በሚገነባበት ጊዜ ባለቤቱ ወይም ቁፋሮውን ያካሄደው ሰው ጉድጓዱን ለደህንነት
በማያሰጋ ሁኔታ መጠበቅ አለበት፤
4. ከግንባታ ጋር የተያያዘ ቁፋሮ የማንኛውንም ንብረት ወይም አገልግሎት ደህንነት አደጋ
ላይ ሊጥል የሚችል መሆኑ ሲገመት የግንባታ ቦታው ባለቤት በቅድሚያ የመከላከያ
ዘዴዎችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን ለከተማው አስተዳደር ወይም ለተሰየመው አካል
በማቅረብ የፅሁፍ ፈቃድ ማግኘት አለበት፣
5. ማንኛውም አዲስ የሚገነባ ህንፃ መሠረት ጭነት በነባር መሠረቶች፣ የአገልግሎት
መስመሮች ወይም ሌሎች ሥራዎች ላይ ችግር የሚፈጥር መሆን የለበትም፡፡

"2. በግንባታ ቦታ ላይ ስለሚከናወኑ ሥራዎች

1. ማንኛውም ህንፃ ሲገነባ ወይም ሲፈርስ በሕዝብ ላይ አደጋ ወይም ከፍተኛ መጉላላት
ሊያስከትል የሚችል ከሆነ የግንባታ ቦታው ባለቤት ሥራውን ከመጀመሩ በፊት አስፈላ

18
ጊውን የመከላከያ ሥራ እንዲያከናውን በከተማው አስተደደር ወይም በተሰየመው አካል
ሊጠየቅ ይችላል፡
2. አንድን ህንፃ ከመገንባት ወይም ከማፍረስ ጋር የተያያዘ ሥራ የከተማው አስተደደር
ወይም የተሰየመው አካል ንብረት በሆነ ወይም በእርሱ ቁጥጥር ሥር ባለ ንብረት
ጥንካሬ፣ ደረጃ፣ ደህንነት፣ ጥራት ወይም አቀማመጥ ላይ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ
የከተማው አስተደደር ካመነ ባለቤቱ በሥራው ምክንያት ለሚያደርሰው ጉዳት መጠገኛ
የሚውል ማስያዣ ወይም ዋስትና እንዲሰጥ ሊጠይቀው ይችላል፡፡
3. ከግንባታ ቦታ ክልል ውጪ የግንባታ ቁሳቁስ ወይም ተረፈ ግንባታ የተጠራቀመ ከሆነ
የከተማው አስተዳደር ወይም የተሰየመው አካል በጽሑፍ ማስታወቂያ በሚገለጽ የጊዜ
ገደብ ውስጥ ባለቤቱ እንዲያነሳ ሊያዝ ይችላል፡፡
4. ማኛውም የግንባታ ቦታ ባለቤት ወይም ከህንፃ ግንባታ ወይም ማፍረስ ጋር የተያያዘ
ስራ የሚሰሩ ሰዎች ሥራውን በሚያከናውኑበት ጊዜ በሥራው ቦታ ላይ እንደ
አስፈላጊነቱ ጊዜያዊ መጠለያ ሊያሰሩ ይችላሉ፡፡
5. ማንኛውም የግንባታ ቦታ ባለቤት ወይም የህንፃ ግንባታ ወይም ማፍረስ ስራ የሚሰራ
ሰው በሥራው ላይ ለሚሰማሩ ሰዎች የሚሆን ተቀባይነት ያለው የንጽህና ቦታ በግንባታ
ሥፍራው ላይ ወይም በከተማው አስተዳደር ወይም በተሰየመው አካል ፈቃድ በሌላ ቦታ
ላይ ሳያዘጋጅ የግንባታም ሆነ የማፈረስ ሥራውን መጀመርም ሆነ መቀጠል
አይችልም፡፡ እንዲህ ያለው ዝግጅት እስኪደረግ ድረስ ሥራው እንዲቆም ይደረጋል፡፡

2.7.2. የግንባታ ደህንነትን የተመለከቱ ደንቦች

2.7.2.1. የግንባታ ደህንነትን የተመለከቱ የሀገር ውስጥ ደንቦች

2.7.2.1.1. የስራ አካባቢ በPPA የውል ሁኔታ ሥር

በGCC (በአጠቃላይ የውል ሁኔታዎች) አንቀጽ 45 "ጤና እና ደህንነት በግንባታ ቦታ ላይ»


 ንዑስ አንቀጽ 45.5 "ተቋራጩ ሰራተኞቹ ሥራዎች በሚያከናውኑበት ወቅት አግባብነት
ያላቸወን የጤና እና የደህንነት እንዲሁም ለሌሎች የሕግ መስፈርቶች ተገዢ
መሆናቸውን ያረጋግጣል"፡፡
 በንዑስ አንቀጽ 45.6 " ተቋራጩ በጤናና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ከመሐንዲሱ ጋር በጋራ
መስራት የሚችል አንድ የጤና እና የደህንነት ተወካይ በእጩነት ይመርጣል"፡፡

19
 በንዑስ አንቀጽ 45.7 "የተቋራጩ ሠራተኞች ተቋራጩ በቀረጸው የአደጋ አያያዝ
ሥርዓት መሰረት ሂደቱን ተከትለው አደጋን ሪፖርት ማድረግ አለባቸው"፡፡
 በንዑስ አንቀጽ 45.9 "ተቋራጩ የእሳት፣ ወይም ሌላ ማንኛውም አደጋ ላይ የተነደፉ
የመከላከያ እርምጃዎች ላይ በሰራተኞች መካከል አብሮ መስራትን ማረጋገጥ እንዲሁም
የተቋራጩ የስራ ልምዶች ወይም ሌሎች ክስተቶች ላይ ማንኛውም ለውጥ ሲኖር እና
ከላይ የተጠቀሱ አደጋዎችን የሚጨምሩ ወይም የአዲስ አደጋ ምክንያቶችን ለሕዝብ
አካል ማሳወቅ አለበት፡፡
 ንዑስ አንቀጽ 45.10 "ተቋራጩ የመጀመሪያ እርዳታ መገልገያዎችን ማቅረብ እና
የህዝቡ አካል እንደሚፈልገው ሰራተኞች ለመጀመሪያ እርዳታ ሂደት መገዛታቸውን
ማረጋገጥ አለበት"፡፡

የግንባታ አካባቢ በPPA የውል ሁኔታ ሥር

አንቀጽ 5 "የፕሮጀክት የምልክት ቦርድ"

 "ተቋራጩ በግንባታ ቦታዎች ዋና ዋና ድንበሮች ላይ የፕሮጀክት የምልክት ቦርዶችን


ያስቀምጣል፣ በተበላሹ ጊዜም ይጠግናል፡፡ የምልክት ቦርዶችን ለማስቀመጥ የሚወጣው
ወጪ ለሌላ ስራ ከሚወጣው ወጪዎች ጋር አብሮ ይካተታል እንጂ ለብቻው ተነጥሎ
አይሰራለትም፡፡ "

አንቀጽ 34 "ስለ ተቋራጭ አጠቃላይ ግዴታዎች"

 በንዑስ አንቀጽ 34.2 " ተቋራጩ በውሉ መሠረት ለሚከናወኑት የግንባታ ሥራዎች
እና ዘዴዎች መረጋጋት እና ደህንነት ሙሉ ኃላፊነት ይወስዳል."

አንቀጽ 45 "ጤና እና ደህንነት በግንባታ ቦታዎች"

 በንዑስ አንቀጽ 45.1 "ተቋራጩ ፍቃድ ከተሰጣቸው መሐንዲሶች በስተቀር በውሉ


ውስጥ ለሥራ ያልተካተተ ማንኛውም ሰው ወደ ጣቢያ ግንባታ ቦታ እንዳይገቡ
የመከልከል መብት አለው."
 ንዑስ አንቀጽ 45.2 "ተቋራጩ የግንባታ ቦታዎች ላይ ሥራዎች እስኪጠናቀቁ ድረስ
ድህንነትን የማስጠበቅና እና በሰራተኞች፣ በመንግስት አካል እና በሶስተኛ ወገኖች
ፍላጎት መሰረት ሥራ በሚከናወንበት ወቅት የሚፈጠሩ አደጋዎችንና ጥፋቶችን
ለመከላከል አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ኃላፊነት አለበት"

20
 በንዑስ አንቀጽ 45.3 "ተቋራጩ በራሱ ኃላፊነትና ወጪ አስፈላጊ እርምጃዎችን
በመውሰድ ያሉቱን ስትራክቸሮችና ዝርጋታዎችን መጠበቅ እና ሲበላሹም ማስተካከል
አለበት፡፡ ሥራዎች በአግባቡ እንዲከናወኑ ወይም በመሀንዲሱ አስፈላጊ የሆኑ እንደ
መብራት፣ ጥበቃ፣ አጥር እና የደህንነት መሣሪያዎችን በራሱ ወጪ የማቅረብና
የመጠበቅ ኃላፊነት አለበት፡፡"
 በንዑስ አንቀጽ 45.9 "ተቋራጩ የእሳት፣ ወይም ሌላ ማንኛውም አደጋ ላይ የተነደፉ
የመከላከያ እርምጃዎች ላይ በሰራተኞች መካከል አብሮ መስራትን ማረጋገጥ እንዲሁም
የተቋራጩ የስራ ልምዶች ወይም ሌሎች ክስተቶች ላይ ማንኛውም ለውጥ ሲኖር እና
ከላይ የተጠቀሱ አደጋዎችን የሚጨምሩ ወይም የአዲስ አደጋ ምክንያቶችን ለሕዝብ
አካል ማሳወቅ አለበት፡፡"

2.7.2.1.2. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መመሪያ ቁጥር 5/2003


35.2.1. የእንጨት መሰላሎች አስተማማኝ በሆነ ጥንካሬ የተሰሩ እና በሚሰጡት አገልግሎት
ምክንያት የሚደርስባቸውን ጫና መሸከም የሚችሉ ሆነው መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፣
35.2.2. ከእንጨት የተሰሩ መሰላሎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ቀለም የተቀቡ መሆን
ይገባቸዋል፣
35.2.3. ከቦታ ወደ ቦታ ሊዘዋወሩ የሚችሉ ተንቀሳቃሽ መሰላሎች አገልግሎት ላይ
ከመዋላቸው በፊት ተገቢው ፍተሻ ሊደረግላቸው ይገባል፣
35.2.4. የላሉ ወይም የተሰበሩ ወይም የጎደሉ መወጣጫዎች ወይም የተሰነጠቁ የጎን ቋሚዎች
ያሏቸው መሰላሎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ አይፈቀድም፣
35.2.5. የተንቀሳቃሽ መሰላል የጎን ቋሚዎች የታችኛው ጫፎች ጠንካራ በሆነ እና በተደላደለ
መደብ ላይ ማረፍ የሚኖርባቸው ሆነው የጎን ቋሚዎቹ የላይኛው ጫፍ የሚሸከመውን
ክብደት ለመደገፍ በሚችል በቂ ጥንካሬ ባለው ደጋፊ አካል እንዲገፉ ማድረግ ይገባል፣
35.2.6. ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ነጠላ ወይም ተደራራቢ ወይም ተቀጣጣይ መሰላሎች
እንዳይንሸራተቱ ተንሸራታች ያልሆነ መደብ እንዲኖራቸው ወይም እንዲያያዙ ወይም
እንዲታሰሩ መደረግ ይኖርባቸዋል፣
35.2.7. የኤሌትሪክ ፍሰት ባለበት አካባቢ የሚያገለግሉ መሰላሎች ኤሌክትሪክ የማያስተላልፉ
ዓይነት ሆነው በመሰላሎቹ እና በኤሌትሪክ አስተላላፊዎቹ መካከል በቂ ክፍት ቦታ
መኖሩን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፣

21
35.2.8. ከብረት የተሰሩ መሰላሎች ወይም በእንጨት ተሰርተው በሽቦ የተጠናከሩ መሰላሎች
በሃይል የተሞላ የኤሌክትሪክ መሣሪያ ባለበት ቦታ ላይ መጠቀም የተከለከለ ነው፣
35.2.9. የመሰላሎች ርዝመት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት መሆን ይኖርበታል፣
ሀ) ለባለድጋፍ መሰላሎች ወይም ተቀጣይ ለሆኑ ባለድጋፍ መሰላሎች 4.8 ሜትር፣
ለ) ከመሰላሉ የታችኛው ክፍል ከ2.5 ሜትር በላይ ለሆነ ከፍታ ሠራተኞች
እንዳይወድቁ ለመከላከል የሚስችል የደህንነት መጠበቂያ አጥር (ኬጅ) ሊኖረው
ይገባል፣
35.2.11. የማይንቀሳቀሱ መሰላሎች መተከል ያለባቸው በየመሐከላቸው የ3 ሜትር ርቀት
እንዲኖር ተደርጎ ሆኖ ከላይ እስከታች ያለው አካላቸው ይህን ርቀት መጠበቅ
ይኖርበታል፣
35.2.12. በተተከሉ መሰላሎች ላይ ከሚገኙ መወጣጫዎች በስተጀርባ በትንሹ 1.75 ሜትር
ስፋት ያለው ቦታ በቋሚነት እንዲኖር ማድረግ ይገባል፣
35.2.13. ከመሰላሎቹ በላይ መወጣጫዎች እንዳይኖሩ ሆኖ የጎን ቋሚዎቹ ከመሰላሎቹ
ማረፊያ በላይ 90 ሳ.ሜ እስከሚቀረው ድረስ መቀጠል ይኖርባቸዋል፣
37. ስለ ከፍታ እና የጣሪያ ላይ ሥራዎች
37.1. የከፍታ ላይ ሥራዎች
37.1.1. ሠራተኞች ከወለል ከ3 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ የሚሰሩ ሆኖ ሲገኝ የመጠንጠልጠያ
ገመዶች፣ የደህንነት መጠበቂያ ቀበቶዎች ወይም የአደጋ መከላከያ መረቦች መቅረብ
ይኖርበታል፣
37.1.2. ሠራተኞች ሊወድቁ ወይም ሊንሸራተቱ የሚችሉበት በወለል ላይ የሚገኝ ክፍት ቦታ
በከለላ ድጋፍ እና በእግር መደገፊያ ጣውላ መሸፈን ወይም መከደን ይኖርበታል፣
37.1.3. በማንኛውም በከፍታ ቦታ ላይ የመገንባት ወይም የማፍረስ ሥራ የሚሰራ ሠራተኛ
ከአደጋ መከላከል የሚያስችሉ የጭንቅላት፣ የእጅ እና የእግር መጠበቂያ ማቴሪያሎችን
መጠቀም ይኖርበታል፣
37.2. የጣሪያ ላይ ሥራዎች
37.2.1. ማንኛውም የጣሪያ ሥራ በቅድሚያ የታቀደና ተገቢው ቁጥጥር ሊደረግለት ይገባል፣
37.2.2. በጣሪያ ሥራ ላይ የሚሰማራ ማንኛውም ሠራተኛ የፊዚካላዊ እና ሳይኮሎጂካዊ ብቃት
ያለው፣ በጣሪያ ሥራ ላይ በቂ እውቀት እና የሥራ ልምድ ያለው መሆን ይገባዋል፣

22
37.2.3. የጣሪያ ሥራ የሠራተኞችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል የአየር ሁኔታ በሚኖርበት
ጊዜ መቋረጥ ይኖርበታል፣
37.2.4. ለጣሪያ ሥራ የሚውሉ የመንፏቀቂያ እንጨቶች፣ መረማመጃዎች እና የጣሪያ
መሰላሎች ከቋሚ ግንብ ጋር በአስተማማኝ ሁኔታ መታሰር ይኖርባቸዋል፣
37.2.5. የጣሪያ ተሸካሚዎች ወይም ድጋፎች ከጣሪያው ቁልቁለማነት/ዝቅዝቃት ጋር
እንዲገጥሙ እና በእስተማማኝ ሁኔታ የተደገፉ መሆን ይገባቸዋል፣
37.2.6. በጣሪያው ጠርዝ ዙሪያ መንበርከክ ወይም ቁጢጥ ማለት ሲያስፈልግ ሠራተኛው
በደህንነት መጠበቂያ ገመድ መጠቀም ይኖርበታል፣ ይህ ካልሆነ ደግሞ በመካከሉ
ድጋፍ መኖር አለበት፣
37.2.7. በጣሪያ ላይ ለሚገኙ ክፍት ቦታዎች መዝጊያ ክዳኖች በሙሉ ጠንካራ ከሆነ ቁሳቁስ
የተሰሩ ሆነው በትክክል መገጠም ይኖርባቸዋል፣
37.2.8. በቁልቁለታማ ጣሪያዎች ላይ ለሚከናወኑ ሥራዎች አስተማማኝ እና ተስማሚ
የመንፏቀቂያ ጣውላዎች ወይም የጣሪያ መሰላሎች ተዘጋጅተው በተገቢው ቦታ
እንዲቀመጡ መደረግ ይኖርበታል፣
37.2.9. ረዥም ጊዜ ለሚወስዱ የጣሪያ ሥራዎች ሠራተኛውን ከአደጋ መከላከል የሚያስችሉ
ጠንካራ የሆኑ ማገጃዎች ወይም ከለላ ድጋፎች እና እግር እንዳይንሸራተት የሚከላከሉ
ጣውላዎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፣
37.2.10. አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ ጣሪያዎች ወይም ተሰባሪ ጣሪያዎች ባሏቸው ሕንፃዎች
ላይ ወደ ጣሪያው መውጫ አካባቢ የማስጠንቀቂያ ጽሁፍ በግልጽ በሚታይ መልኩ
እንዲኖር መደረግ ይኖርበታል፣
38. የመሬት ውስጥ ሥራዎች
38.1. ጠቅላላ
38.1.1. ማንኛውም የቁፋሮ እና የመሬት ውስጥ ሥራዎች በሚከናወኑበት ወቅት በሠራተኞች
ላይ የመውደቅ፣ የአፈር መናድ፣ የውሃ ሙላት እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ
አደጋዎች እንዳይደርሱ ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፣
38.1.2. ከመሬት በታች ለሚከናወኑ የቁፋሮ ሥራዎች ብርሃን እና አየር ለማስገባት የሚስችሉ
ክፍተቶች መኖራቸውን እና የአደጋ ጊዜ መውጫ መንገድ መዘጋጀቱ መረጋገጥ
ይኖርበታል፣

23
38.1.3. በመሬት ውስጥ የሚዘረጉ የኤሌክትሪክ መሥመሮች በኢትዮጵያ የሕንፃ ኮድ እና
ስታንዳርድ በተቀመጡት የአሠራር ሥርዓቶች መሠረት ይሆናል፣
38.1.4. ትላልቅ የቁፋሮ እና የመሬት ውስጥ ሥራዎች ሲከናወኑ የእለት ከእለት ቁጥጥር እና
ክትትል በተቆጣጣሪ መሐንዲሱ መደረግ ይኖርበታል፣
38.2. የቁፋሮ ሥራ
38.2.1. ማንኛውም የቁፋሮ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ከዚህ በታች የተመለከቱት ሁኔታዎች
መረጋገጥ አለባቸው፣
ሀ) የሚፈለገው የቁፋሮ ሥራ በሚገባ የታቀደ እና የአቆፋፈር ዘዴው በግልጽ ተለይቶ
የተቀመጠ መሆን ይኖርበታል፣
ለ) የመሬቱ የተፈጥሮ ሁኔታ በተገቢው ባለሙያ ተመርምሮ መታወቅ ይኖርበታል፣
ሐ) የሚካሄደው የቁፋሮ ሥራ በአካባቢው ላይ የሚገኙትን ሕንፃዎች፣ መንገዶችእና
ሌሎች የመሠረተ ልማት አውታሮችን የማይጎዳ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፣
መ) በቁፋሮ ወቅት አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ የውሃ መስመሮች፣ ከመሬት በታች
የቆሻሻ መውረጃ መስመሮች ወይም ቱቦዎች፣ እና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያዎች
በሚመለከተው አካል ቁጥጥር እና ክትትል የሚደረግባቸው መሆኑን ማረጋገጥ
ይገባል፣
ሠ) ቁፋሮ የሚካሄድበት ቦታ በጎጂ ኬሚካሎች ወይም ጉዳት ሊያመጡ በሚችሉ
አደገኛ ቁሶች ያለመበከሉ በሚመለከተው አካል መረጋገጥ ይኖርበታል፣
ረ) የተቆፈሩ ጉድጓዶች ጎን በሠራተኞች ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ከከባድ ዝናብ፣
ከመሬት መንሸራተት እና ከፈንጂዎች መፈንዳት በኋላ በተገቢው ባለሙያ
ቁጥጥር እና ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል፣
ሰ) የተቆፈረውን ጉድጓድ እንዲናድ ወይም እንዲንሸራተት የሚያደርጉ ከባድ
መሣሪያዎች እና ማሽነሪዎች እንዲሁም የማምረቻ ተቋማት በአካባቢው መቀመጥ
ወይም መተከል አይኖርባቸውም፣
ሸ) እግረኞች እና ተሸከርካሪዎች የተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ እንዳይገቡ የመከለያ
አጥሮች እና የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያዎች ተዘጋጅተው መተከል ይኖርባቸዋል፣
38.3.2. ማንኛውም በቁፋሮ ሥራ ላይ የተሰማራ ሠራተኛ ከቁፋሮው የወጣውን ማቴሪል
ከተቆፈሩ ጉድጓዶች ጠርዝ ጀምሮ በ1.2 ሜትር ርቀት ውስጥ ማከማቸት
አይኖርበትም፣

24
38.3.3. ከተቆፈሩ ጉድጓዶች ውስጥ የወጡትን ማቴሪሎች ለማስወገድ ጥቅም ላይ የሚውሉ
የማዘለያ እቃዎች ወይም ባልዲዎች የመደገፊያ አካላቸውእንዳይነቀሉ ተገቢው ጥንቃቄ
መደረግ ይኖርበታል፣
42. ስለ የመጀመሪያ እርዳታ አሠጣጥ
42.1. በማንኛውም የሥራ ቦታ ላይ የመጀመሪያ የእርዳታ አገልግሎት መስጫ ቁሳቁስ ክፍል
በአሰሪው መደራጀት ይኖርበታል፣
42.2. በሥራ ቦታ ውስጥ የመጀመሪያ የህክምና መስጫ ቦታን የሚያመለክቱ ምልክቶች በግልፅ
በሚታዩ ቦታዎች መለጠፍ ወይም መተከል ይኖርበታል፣
42.3. በሥራ ቦታ ላይ ጉዳት የደረሰበት ማኝኛውም ሠራተኛ በሥራ ላይ የደረሰበትን አደጋ
ወይም ጉዳት በተመለከተ አግባብ ባለው መ/ቤት ተዘጋጅቶ በተፈቀደ ፎርም መመዝገብ
ይኖርበታል፣ አሠሪውም በሠራተኛው ላይ የደረሰው ጉዳት መመዝገቡን የማረጋገጥ
እና የምዝገባ ዝርዝሩን ወደ ሚመለከተው አካል የማስተላለፍ ግዴታ አለበት፣
42.4. ማንኛውም አሠሪ በሥራ ቦታ ላይ በከባድ ሕመም ወይም አደጋ የተጎዳን ሠራተኛ ወደ
ሕክምና ተቋም የመውሰድ ሃላፊነት አለበት፣
42.5. በግንባታ ቦታዎች ለድንገተኛ አደጋ አገልግሎት የሚሠጡ የሕክምናና የአምቡላንስ
አገልግሎት ተቋማት አድራሻው መመልከት አለባቸው፣
44. ስለ ሠራተኞች እና የሥራ ቦታዎች ደህንነት አጠባበቅ
44.1. የሠራተኞች ደህንነት
44.1.1. የታወቀ አካላዊ ወይም አእምሯዊ ችግር ያለበት ሰው በግንባታ ሥራ ላይ እንዲመደብ
መደረግ የለበትም፣
44.1.2. ማንኛውም የግንባታ አሰሪ ወይም ተቆጣጣሪ ወይም ሠራተኛ በሰዎች ጤንነት እና
ደህንነት ላይ አደጋ በሚያስከትል ሁኔታ አስካሪ መጠጦች ጠጥቶ ከተገኘ ወደ ሥራ
ቦታ መግባት ወይም ሥራው ወደ ሚገኝበት ቦት ላይ መቆየት አይፈቀድም፣
44.1.3. ማንኛውም በሥራ ቦታ ላይ የሚገኝ ሠራተኛ በሠራተኞች ላይ አደጋ ሊያስከትል
በሚችል መልኩ እንደ ግብግብ፣ አላስፈላጊ ሩጫ እና ዝላይ እንዲሁም ቀልዶችን
በሰዎች ላይ መሞከር ወይም በሌላ ተመሳሳይ ረብሻ ላይ መሳተፍ የለበትም፣
44.1.4. ማንኛውም ሠራተኛ በሥራ ቦታው ላይ ደህንነቱን እና ጤንነቱን ለመጠበቅ
የተሰጡትን መሣሪያዎች በአግባቡ መያዝ እና መጠቀም ይኖርበታል፣

25
44.1.5. አሠሪው የሠራተኞቹ ደህንነት እና ጤንነት ሊያስጠብቁ የሚችሉ የመከላከያ
መሣሪያዎች እና ሌሎች አልባሳት እንዲያገኙ ማድረግ እና በስራ ላይ መዋላቸውን
ማረጋገጥ ይገባዋል፣
44.2. የሥራ ቦታዎች ደህንነት
44.2.1. ማንኛውም አሠሪ የሥራ ቦታዎች በሠራተኞች ደህንነት እና ጤንነት እንዲሁም
በሕብረተሰቡ እና በአካባቢው ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ማድረግ ይኖርበታል፣
44.2.2. አሠሪው በሁሉም የሥራ ቦታዎች የደህንነት መጠበቂያ ሥነ-ስርኣቶች በሥራ ላይ
መዋላቸውን በየጊዜው ማረጋገጥ ይኖርበታል፣
44.2.3. ማንኛውም የሥራ ቦታ ከቆሻሻ የፀዳ እና በጽዳት የሚጠበቅ መሆን ይኖርበታል፣
44.2.4. ማንኛውም የሥራ ቦታ ለወንዶች እና ሴት ሠራተኞች መገልገያ የሚሆኑ እና በተለያየ
ቦታ የተገነቡ ጊዜያዊ የመታጠቢያ እና የንፅህና መጠበቂያ አገልግሎት መስጠት
የሚችሉ ክፍሎች ሊኖሩት ይገባል፣
44.2.5. ማንኛውም የሥራ ቦታ ከመንግስት ዋና ምንጭ ወይም በሚመለከተው አካል ፍቃድ
ካገኘ ሌላ የተለየ ምንጭ የተገኘ በቂ እና ለጤና ተስማሚ የሆነ የመጠጥ ውሃ
ሊኖረው ይገባል፣
44.2.6. በሥራ ቦታዎች የሚገኙ ለእሣት አደጋ እና ለበሽታ የሚያጋልጡ ደረቅ ቆሻሻዎች
በወቅቱ መወገድ አለባቸው፣
44.2.7. በግንባታው አካባቢ ብክለት እንዳይከሰት ጊዜያዊ የፍሳሽ ማከማቻ እና ማስወገጃ
መዘጋጀት አለበት፣
44.2.8. ህዝብ በሚተላለፍበት መንገድ የሚከማች የግንባታ ቁሳቁስ ከከተማው አስተዳደር
ፈቃድ ካልተሠጠ በስተቀር ማከማቸት አይፈቀድም፣
44.2.9. ከሀምሣ እና ከዚያ በላይ ቁጥር ያላቸው ሠራተኞች በሚሠሩባቸው ማናቸውም የሥራ
ቦታዎች የደህንነት እና የጤንነት ሁኔታዎችን የሚከታተል የደህንነት መኮንን ሊኖር
ይገባል፣ የደህንነት መኮንኑ፣
ሀ) የሥራ ቦታ የደህንነት እና ጤንነት አጠባበቅ የሙያ ሥልጠና የተሰጠው ሊሆን ይገባል፣
ለ) ከሥራ ተቆጣጣሪዎች ጋር በመመካከር በአሠሪው የተቀመጡትን የደህንነት እና ጤንነት
ተግባራትን ያከናውናል፣ በሠራተኞች መተግበሩንም ይቆጣጠራል፣
45. የሚደርሱ አደጋዎችን ስለ መመዝገብ እና ማሳወቅ

26
45.1. ማንኛውም ሠራተኛ በሥራ ቦታ ላይ የደረሰበትን አደጋ ወይም የደረሰበትን አደገኛ
ሁኔታ ለአሰሪው ወይም ለተቆጣጣሪው ወዲያውኑ ማሳወቅ ይኖርበታል፣
45.2. በሥራ ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎች እና በሥራ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎች
እንዲሁም አደገኛ ክስተቶች ተመዝግበው ለዚሁ ሥራ በተመደበ ሰው በአግባቡ መያዝ
ይኖርባቸዋል፣
45.3. በሥራ ቦታ ላይ ተመዝግበው የተያዙ መረጃዎች ተጠብቀው የሚቆዩበት ጊዜ ቢያንስ
ከ10 ዓመት ቢበዛ ደግሞ ከ20 ዓመት መብለጥ የለበትም፣
45.4. ማንኛውም በሥራ ቦታ ላይ የሚደርስ አደጋ በ3 ቀናት ውስጥ ለሚመለከተው አካል
ሪፖርት መደረግ አለበት፣ ሪፖርቱ የሚከተሉትን የሚካትት ይሆናል፣
45.5.5 አደጋው የሞት አደጋን የሚስከትል ሆኖ ሲገኝ በስልክ ወይም በማናቸውም ሌሎች
የመገናኛ ዘዴዎች አደጋው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት መደረግ ይኖርበታል፣

2.7.2.1.3. የኢትዮጲያ የህንጻ መተዳደሪያ ስታንዳርድ (EBCS 14)


ሀ/የሥራ ቦታ ደህንነት ዕቅድ

አንድ ኮንትራክተር የሰራተኞችን የሥራ ቦታ ደህንነት ዕቅድ ከታች የተዘረዘረውን በማቀናጀት


ማዘጋጀት አለበት

1. የደህንነታ መኮንን እና/ወይም የደህንነትን እና የጤና ኮሚቴ መመስረት እና አባላቱም


አሠሪዎች እና ሰራተኞችን ያካተቱ አካላትን መመደብ አለበት፡፡ የደህንነት ዝግጅቶችን እና
አፈፃፀሞችን መከታተል ላይ ሹሙ/ ኮሚቴው ተጠሪ ብሎም ተጠያቂ ይሆናል፡፡

2. የደህንነት ኦፊሰር እና/ወይም የደህንነት ኮሚቴ አባላት እና ሠራተኞች የሥራ ስልጠና ላይ


ስልጠናው በግንባታ ቦታ ላይ ስለሚተገበሩ ማናቸውም እርምጃዎች ላይ መረጃዎችን
ማካተቱን እና ሠራተኛው ደህንነትን በተገቢው መንገድ መረዳቱን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

3. ተጨማሪ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እንደሚከተሉት ናቸው

ሀ) ከአደጋዎች ጋር ተያያዥነት ያላቸው በግንባታ ቦታ ላይ የሚካሄዱ የግንባታ ሥራዎች፤


ሥራውን ለመስራት እሚፈጀውን ጊዜ ግምት፤ ለስራው ተጠሪ የሆነውን ሰው ዝርዝር
አድራሻ እና የሠራተኞችን ደህንነትን ለማረጋገጥ የተወሰዱ እርምጃዎችን መዘርዘር

27
ለ) አደጋ በሚደርስበት ጊዜ መወሰድ ስላለባቸው መመሪያዎች፣ እና ለስራው ተጠሪ የሆነውን
ሰው ስምና ዝርዝር አድራሻ

ሐ) የመጀመሪያ እርዳታ የሚሰጡትን ሰዎች ስም እና ዝርዘር አድራሻ; በአቅራቢያ የሚገኝ


የድንገተኛ ሕክምና ዕርዳታ አድራሻ እና የመዳረሻ መንገዶች ማውቅ

ለ/የማስጠንቀቅያ ምልክቶች

 የማስጠንቀቅያ ወይም ተዓማኒነት ያላቸው ምልክቶችን አስፈላጊ በሚሆንበት ቦታ


መቀመጠ አለባቸው
 ምልክቶቹን ስራ በሚከናወኑባቸው ጊዜያት ሙሉ በሙሉ መታየት አለባቸው
አደጋዎች ሊፈጥሩ የሚችሉባቸው ሁኔታዎች ሲያቆሙ ምልክቶቹ እንዲወገዱ ማድረግ
አለብን
 አደገኛ ምልክቶች: የአደጋ ምልክቶች ጥቅም ላይ መዋል ያለባቸው አስቸኳይ አደጋ
ሲኖር ነው፡፡ አደገኛ ምልክቶች ስንጠቀም ቀይ ቀለም ጎልቶ ስለሚታይ ለላይኛው ፓኔል
እንጠቀመዋለን; ጥቁር ደግሞ ለድንበሮች; እና ታችኛውን ነጭ ለተጨማሪ
ምልክቶቸን ለመፃፍ

የማስጠንቀቂያ ምልክቶች: የማስጠንቀቅያ ምልክቶች አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ


ነገሮችን ወይም አደገኛ ከሆኑ ልምዶች ለማስጠንቀቅ ብቻ ጥቅም ላይ እናውላቸዋለን፡፡

 ማስጠንቀቂያ ምልክቶች ላይ ቢጫ ጎልቶ እሚታይ ቀለም ነው ጥቁርን ደግሞ ለላይኛው


ሰንጠረዥ እና ለድንበሮቸ እንጠቀመዋለን፡፡

28
 መውጣት (exit) ምልክቶች- እነዚ ምልክቶችን ስንጠቀም በነጭ መስክ ላይ በቀይ
ቀለም የተፃፈ፤ ፊደሉ ርዝመት ከ 6 ኢንች (15 ሴ.ሜ) ያላነሰ ስፋቱ ቢያንስ ቢያንስ
ሦስት አራተኛ ኢንች (2 ሴንቲሜትር) መሆን አለበት፡፡

 የደህንነት መመሪያ ምልክቶች: እነዚህን ምልክቶችን ስንጠቀም አረንጓዴ መስክ ላይ


ነጭ ፊደል ጎልቶ እንዲነበብ ያድርጉታል ፡፡ ማንኛውም ተጨማሪ ቃል ነጭ ጀርባ ሆኖ
በጥቁር ፊደላት መፃፍ አለበት፡፡

 አደጋ መከላከያ ታጎች: የአደጋ መከላከያ ታጎች የምንጠቀመው ሠራተኞችን ከተፈጠሩ


አደጋዎች ጊዜያዊ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት እንደ ጉድለት ካለባቸው መሳሪያዎች፣
ከማሽኖች ወዘተ ለመጠበቅ ነው:: የአደጋ መከላከያ ምልክቶቹ ቦታን ተክተን መጠቀም
ግን የለብንም::

29
ፍላግሜን፡ ከሀይዌይ ወይም ከመንገድ ጎን ለጎን ምልክቶችን ማስቀመጥ ከአደጋ
ለመከላከል በቂ ሳይሆን ሲቀር፣ ፍላግሜን ወይም ሌላ ጠቋሚዎች ተገቢ የትራፊክ
መቆጣጠሪያዎች መቅረብ አለባቸው ፍላግሜን ጠቋሚዎች በሚውሉበት ጊዜ ቀይ
ወይም ብርቱኳናማ የማስጠንቀቂያ ልብስ ማልበስ አለብን፡፡ በምሽት ላይ
የምንጠቀማቸው ፈላግሜኖች የሚየንፀባርቁ መሆን አለባቸው፡፡

ሐ/ የአደጋዎች አያያዝ

የጤና ችግር፣ የመጀመሪያ እርዳታ፣ የሕክምና እና ደህንነት አገልግሎት

1. የመጀመሪያ እርዳታ

 የግንባታ አሰሪዎች የመጀመሪያ እርዳታ መሳሪያዎች እና መገልገያዎቸ በግንባታ ቦታ


ላይ ሠራተኞቻቸው በሚጎዱበት ወይም በስራ ቦታ በሚታመሙበት ጊዜ ሊያቀርቡ
ይገባል፡፡
 እያንዳንዱ የሥራ ቦታ ሊደርሱ ለሚችሉ ድንገተኛ ሁኔታዎች አስቀድሞ እንደ
የመጀመሪያ እርዳታ፣ የመጀመሪያ እርዳታ ሰራተኞችን፣ የመገናኛ መንገድ፣
የመጓጓዣ መንገዶች እና መሳሪያዎች የመሳሰሉትን በተገቢው መንገድ መዘጋጀት
አለበት፡፡
 ስራው ከፍተኛ አደጋን የሚያሰከስት፣ እራስን የመሳት ወይም የኤሌክትሪክ አደጋን
የሚያካትት ከሆነ የመጀመሪያ እርዳታ ሰራተኞች ሳይደነግጡ እና ሌሎች የህይወት-
ቁሳቁሶችን ቴክኒኮችን በመጠቀም ማዳን አለባቸው፡፡

30
 አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው የመጀመሪያ መሳሪያዎችን፣ የመሣሪያው ቦታንና ተቋማት
እና ሠራተኞች ጨምሮ ማሳወቅ አለባቸው፡፡
 ሁሉም ጉዳት በሂደቱ መሰረት ሪፖርት መደረግ፣ መያዝ እና መመዝገብ አለበት፡፡
 በማንኛውም የግንባታ ቦታ ላይ ቢያንስ አንድ የእርዳታ ሳጥን ሊኖር ይገባል፡፡

2. የሕክምና እንክብካቤ

 የግንባታ ቦታ ሰራተኞች ከመቀጠራቸው በፊት ቅድመ-ቅጥር አካላዊ እና


ሳይኮሎጂካል ሁኔታዎች መመርመር አለባቸው::
 የፕሮጀክቱ ቦታ ለወረርሽኝ የተጋለጥ ከሆነ ሥራ ተቋራጭ ለሠራተኞቹ ጥበቃ
ማድረግ አለበት::

3. የአስቸኳይ የድርጊት መርሃ ግብር

 አሰሪ የድንገተኛ ድርጊት መርሃ ግብር ሊኖረው ይገባል፡፡ የድንገተኛ አደጋ ድርጊት
መርሃ ግብር በጽሁፍ ስራ ቦታ ላይ መቀመጥ እና ሠራተኞች መገምገ አለባቸው::
ይሁን እንጂ 10 ወይም ከዚያ በታች ሠራተኞች ያለው አሠሪ እቅዱን ለሠራተኞች
በቃል ማነጋገር ይችላል፡፡

እቅዱ የሚከተሉትን ማካተት አለበት፤ ነገር ግን በነዚህ ብቻ ያልተወሰነ መሆን አለበት:

ሀ/ ጉዳት የደረሰባቸው ሰራተኛ/ጎብኚ ሊወሰዱበት የሚችል በአካባቢው የሚገኙ የጤና


ተቋማት (በአደጋው አይነት መሰረት);

ለ / ወደ ተቋሙ የመዳረሻ መንገድ,

ሐ / ከተቋማት ጋር የመገናኛ ዘዴዎች;

መ / ኃላፊነት ካለባቸው ሰዎች እንዲነገሩ ማድረግ

4. ሥልጠና

 ሰራተኞች በተገቢው እና በሚመች ሁኔታ አደጋን ስለ መከላከል እና መቆጣጠር


ብሎም አደጋን ሊያስከትሉ ከሚችሉ አደጋዎች መከላከያ ስልጠና ሊኖራቸው ይገባል

31
 በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ አሰሪው ተገቢውን መመሪያ እና ስልጠና መስጠት
ይኖርበታል ይህም የሠራተኞቹን ጤና እና ደህንነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
እንዲህ ዓይነቱ ሥልጠና አካላዊ ሎጂስቲክስ ያካትታል፡፡
 ቀጣሪው አካል ለአዲስ ሠራተኞች የድርጅቱ አደረጃጀት እና አስተዳደርን፣
የሰራተኞችና የደህንነት እቅድ፣ ጤና እና ደህንነት እና የሰራተኞች መገልገያዎች
ዝርዝር ያካትታል አጫጭር ኮርሶችን መሰጣት አለበት፡፡

2.7.2.2. የግንባታ ደህንነትን የተመለከቱ አለም አቀፍ ደንቦች

2.7.2.2.1. FIDIC (2006)


የሰው አካባቢ በFIDIC የውል ሁኔታዎች ስር

 FIDIC.2006 አንቀጽ 4.21 ስለ የአካባቢ ገጽታዎች፤ የሂደት ሪፖርቶች እና የህዝብ


ግንኙነት ጋር በተያያዘ ማንኛውንም የደህንነት ስታትስቲክስ፣ አደገኛ ክስተቶች እና
እንቅስቃሴዎች ዝርዝርን ጨምሮ ያብራራል፡፡
 FIDIC.2006 አንቀጽ 4.8 የደህንነት ሂደቶች ተብራርተዋል፡፡
 FIDIC.2006 አንቀጽ 6.4 ተቋራጩ ከሰራተኛ ህጎች ጋር አግባብነት ያላቸውን እንደ
የቅጥር፣ ጤና፣ ደህንነት፣ ኢሚግሬሽን እና መሰደድ ጋር በተያያዘ የጉልበት ሕጎችን
ጨምሮ ማክበር እና ሁሉንም ሕጋዊ መብት መፍቀድን በሰራተኛ ህጎች ውስጥ
ይገልጻል፡፡
 FIDIC.2006 አንቀጽ 6.7 በጤና እና ደህንነት ርዕስ ውስጥ እንደተቀመጠው ተቋራጩ
ሁልጊዜ የሠራተኞቹን ጤንነት እና ደህንነት ለመጠበቅ ማንኛውንም አይነት ጥንቃቄ
መውሰድ አለበት ይላል፡፡ ከአካባቢው ጤና ባለስልጣናት ጋር በመተባበር ተቋራጩ
የሕክምና ሠራተኞችን፣ የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ፣ ሲክ ቤይና የአምቡላንስ
አገልግሎት በግንባታ አካባቢ ላይ መኖሩን እንዱሁም ተቋራጮቹ እና የመሥሪያ ቤቱ
ሠራተኞች አስፈላጊ የደህንነት አጠባበቅ መስፈርቶችን በተጨማሪም የወረርሽኝ መከላከያ
ተስማሚ የሆኑ ዝግጅቶች መኖራቸውን ያረጋግጣል፡፡
 FIDIC.2006 አንቀጽ 18.3 ውሉ ላይ በተቀመጠው መሰረት በተቋራጩ አፈጻጸም እና
የአፈጻጸም ሰርተፊኬት ከመሰጠቱ በፊት የሚያረጋግጠው አካል በእያንዳንዱ ፓርቲ
አካላዊ ንብረት ላይ ማንኛውንም ሊከሰት የሚችል ኪሳራ፣ መጎዳት፣ ሞት ወይም
በአካል ጉዳት ላይ (ንዑስ አንቀጽ 18.2 [ኢንሹራንስ ለስራዎች እና የተቋራጩ

32
መሣሪያዎች] ላይ ከተጠቀሱት ነገሮች በስተቀር) ወይም ማንኛውም ሰራተኛ (ንዐስ
አንቀጽ 18.4 [ለተቋራጩ ሠራተኞች ኢንሹራንስ] ላይ ከተጠቀሱት ሰራተኞች በስተቀር)
ተጠያቂ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

የግንባታ አካባቢ በFIDIC የውል ሁኔታዎች ሥር

FIDIC አንቀጽ 2.3 አሰሪ ሰራተኞች

 ተቋራጩ/ የግንባታ ስራ አስኪያጅ የግንባታ ሠራተኞችና ለህብረተሰቡ ጉዳት ለመከላከል


ሁሉንም አስፈላጊ ጥንቃቄ መውሰድ ይኖርባቸዋል:: ለምሳሌ ያህል ወደ ፕሮጀክቱ
የሚያስገቡ ካልተፈቀዱ መዳረሻዎች መጠበቅ እና ተገቢ የሆኑ የማስጠንቀቂያ ምልክት
መቀመጥ አለበት፡፡ በሥራ ምክንያት የመኪና መንገድና የእግረኛ መንገድ ግዴታ ዝግ
ሲሆን፣ የተሽከርካሪዎችን እና እግረኞች ፍሰት እንዲያዞር እና ከግንባታ እንቅስቃሴዎች
ለመጠበቅ በቂ የሆነ አቅጣጫ ማሳያ መተከል አለበት፡፡ የሕዝብ ጥቅም ለመጠበቅ
የሚሰሩ የሥራ አካባቢዎች (እንደ ሕንፃዎች፣ መኖሪያዎች፣ መተላለፊያዎች፣ የእግረኛ
መንገድ፣ መንሸራተቻዎች እና ወደ ህንፃ መግቢያ….) መጠበቅ አስፈላጊ ሲሆን ጊዜያዊ
አጥሮችን ከአናት መጠበቂያ ዘዴዎችን ወይም ጊዜያዊ ክፍልፋዮችን በመጠቀም መጠበቅ
ይኖርባቸዋል፡፡

2.8. የውጪ ሀገር ተሞክሮዎች

2.8.1. የብራዚል ተሞክሮ


በብራዚል ውስጥ በግንባታ አካባቢ የሚደርሱ አደጋዎችን መቀነስ

በብራዚል ኢኮኖሚ ውስጥ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ትልቅ የሆነ ድርሻ አለው፡፡ በሁሉም
ደረጃ ለሚገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች የሀብት እና የስራ ዕድል ምንጭ ነው፡፡ የመንግስት
የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች እና የሪል እስቴቶች ቁጥር መጨመር ኢንዱስትሪው እንዲስፋፋና
ትርፋማ እንዲሆን አድርገውታል፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው 2.6 ሚሊዮን መደበኛ የስራ
መደብን በመያዝ ከሀገሪቱ ጠቅላላ የስራ ድርሻ 7.1% ይሸፍናል፡፡

በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ወስጥ የሚፈጠሩት አደጋዎች ለሞት ስለሚያጋልጡ ካሉት


ሴክተሮች አደጋ የበዛበት ሴክተር እንደሆነ ይታመናል፡፡ በብራዚል ውስጥ በኮንስትራክሽን ስራ
ላይ ከተሰማሩ ሰራተኞች ለሞት አደጋ የሚጋለጡት ቁጥር በ2000ዓ.ም ከ100,000 ሰራተኞች
32.7 ከነበረው በ2009ዓ.ም ወደ 18.6 ቀንሷል፡፡ ለሚፈጠረው የሞት አደጋ መወደቅ

33
ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ምንም እንኳን የሞት አደጋው እየቀነሰ ቢመጣም በአለም ላይ
ተሻለ ልምድ ካላቸው ሀገራት እንደ አሜሪካ፣ እንግሊዝ እና ፊንላንድ ጋር ሲነፃፀር ለአደጋ
የመጋለጡ አዝማሚያ ከፍተኛ ነው፡፡ የግንባታ ስራው በጤና ላይ የሚያደርሰውን አደጋ በመረጃ
እጥረት ምክንያት ለመገመት አዳጋች ቢሆንም በስራ ቦታ ላይ በሚደርሱ አደጋዎች ምክንያት
ጊዜያዊ የህመም ፍቃድ ከ15 ቀን በላይ የሚወስዱ ሰራተኞችን ከግምት ውስጥ በማስገባት
በአመት ወደ 1 ሚሊዮን የሚደርስ የስራ ሰአታትን የብራዚል የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
ያጣል፡፡

በብራዚል በኮንስትራክሽን ስራ ላይ የሚፈጠረውን አደጋ ለመቀነስ የተወሰደው አንዱ መፍትሄ


Quick Win Team ከአሰሪ መስሪያ ቤቶች፣ ከህዝቡ እና ከሰራተኞች የተውጣጣ ቡድን
ማቋቋም ነው፡፡ ይህ ዘዴ በግንባታ አካባቢ ቀላል መፍትሄዎችን፣ በፈጣን መንገድ፣ በአነስተኛ
ወጪ እና በተወሰነ ቴክኖሎጂ ሰፊ የሆነ ውጤትን የሚያስገኝ ዘዴ ነው፡፡ በዚህ ቡድን ውስጥ
ካላቸው የስራ ቅርበት የተነሳ የሰራተኞች ተሳትፎ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ውጤታማነቱም
በደርጅቶች አመራርና በሰራተኞች ተሳትፎ የሚወሰን ይሆናል፡፡

Quick win team ውጤታማ እንዲሆን የተከተሏቸው ሂደቶች

 የመጀመሪያ ደረጃ፡- ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ሂደቶች መለየት እና ቡድኑ ውስጥ


መካተት ያለባቸውን አካላት ይለያሉ፡፡ አመራሩ ከአደጋ ጋር ግንኙነት ያላቸው የህክምና
ፍቃድ እና ሌሎች ከስራ አካባቢ ደህንነት ጋር ግንኙነት ያላቸው መረጃዎች ይለያሉ፡፡
በአንድ የግንባታ ስራ ቦታ ላይ ከአንድ በላይ ቡድን ሊቋቋም ይችላል፡፡
 ሁለተኛ ደረጃ፡- በአንድ ቡድን ውስጥ የሚካተቱት ሰራተኞች በፆታ፣ በእድሜ፣ በስራ
ሰረጃ እና በስራ ልምድ ይለያሉ፡፡ የተለዩት ባለሞያዎች በስራ አካባቢ ደህንነት ላይ
የተሻለ ልምድ እና ተሞክሮ ያላቸው ሆነው በሌሎች ሰራተኞች ላይ አዎንታዊ ትፅእኖን
ማሳደር የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 ሶስተኛ ደረጃ፡- ለተመሰረተው ቡድን ስልጠና መስጠት፡፡ መሀንዲስ ወይም በደህንነት
ላይ በቂ ልምድ ያለው ባለሙያ ስለ ስራ አካባቢ ደህንነተ ምንነት፣ በስራ አካባቢ
ስለሚፈጠሩ አደጋዎች፣ መንስኤዎች እና መወሰድ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች የአራት
ሰአት ስልጠና ይሰጣል፡፡ እንዲሁም የተለያዩ ከደህንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው
መረጃዎች በፎቶ በተደገፈ መልኩ ለቡድኑ አባላት ይቀርባሉ፡፡

34
 አራተኛ ደረጃ፡- የቡድኑን አጠቃላይ ተግባራት መቆጣጠርና መገምገም፡፡ የመቆጣጠርና
የመገምገም ሂደት የሚከናውነው ቢያንስ በሁለት ወር ውስጥ ሶስት ጊዜ በግንባታ
ቦታው ላይ የመስክ ምልከታ በማካሄድ ነው፡፡ በግምገማ ወቅት የቡድኑ አባላት በግንባታ
ቦታ ላይ የተፈጠሩትን አደጋ፣ ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን እና የተወሰዱ
መፍትሄዎችን በፎቶግራፍ በተደገፈ መረጃ ያቀርባሉ፡፡

ይህንን ዘዴ በመጠቀም በብራዚል ውስጥ ከ2009ዓ.ም እስከ 2012ዓ.ም 120 ቡድኖች


ተቋቁመው ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ የዚህ ቡድን መቋቋም ዋና አላማው ሰራተኞችና
ተወካዮቻቸው በግንባታ ቦታ ላይ የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ
እንዲያደርጉ ማስቻል ነው፡፡

2.8.2. የሲንጋፖር ተሞክሮ


ሲንጋፖር በኮንስትራክሽን ዘርፉ በማደግ ላይ በነበረችበት ወቅት በግንባታ ስራ ላይ ደህንነት
የነበረው በጣም አስጊ ሁኔታ ነበረ፡፡ የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን (Land Transport
Authority) በሚል ተቋም የሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ የሚደርሰው አደጋ ለመቀነስ ሲነሳ
መጀመሪያ በኮንስትራክሽን የሴፍቲ ፖሊሲ ስታንዳርዱ በጠበቀ ሁኔታ በማዘጋጀት ወደ ስራ
ገባ፡፡ ለኮንስትራክሽን ሴፍቲ ትግበራ እንዲመች ፕሮጀክቱ በመንገድ (የብስ) ትራንሰፖርት
ፕሮጀክትና በባቡር ትራንስፖርት ፕሮጀክት ሲስተም ላይ የኮንስትራክሽን ሴፍቲ አጠባበቅ ብሎ
በመሰየም በሰትራክቸርና ዲዛይን ወቅት፣ በግንባታ ወቅትና በከባድ ማሽኖች በስራና ጥገና
ወቅት በስራ ላይ ደህንነት ጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት የሚያጋጥመው አደጋ ለመቀነስና
ለማስወገድ አላማ አድርጎ መስራት ጀመረ፡፡ (Safe to build and safe to use) የሚል
መርህ አንግቦ የኮንስትራክሽን ሴፍቲ፡

1. በግንባታ ወቅት ስራ ላይ ስልጠና


2. በሴፍቲ የተመለከተ የሚሰጥ ትምህርት/ማስተዋወቅ
3. በስራ ላይ የሚደረግ የሴፍቲ አስገዳጅነት (Enforement) በመከፋፈል መተግበር
ጀመረ፡፡

በተደጋጋሚ የሚደርስ አደጋ በመለየት፡

 በግንባታ ወቅት ስራ ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በተቋሙ የሚገኘው ማህበረሰብ


ረጅምና አጭር ስልጠና እንዲሁም ሴሚናሮች በማዘጋጀት እንዲታደሙ በማድረግ፡

35
 የተለዩ ርእሶች መሰረት በማድረግ ጥልቀት ያለው ስልጠና በመስጠት፡
 ጥሩ ተሞክሮ በማምጣትና በማስፋፋት፡
 በየ3ወሩ በሚታተመው የተቋሙ የውስጥ ጋዜጣ ስለግንባታ የስራ ላይ ደህንነት
ትኩረት ተሰጥቶት በስፋት በመተንተን እንዲነበብ በማድረግ፡
 የግንባታ የስራ ደህንነት በተመለከተ በዉስጥ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ የተለያዩ ፅሁፎች
በመለጠፍና እንዲነበቡ በማድረግ የግንዛቤ ለዉጥ እንዲኖር አድርጓል፡፡

ሴፍቲን የተመለከተ የሚሰጥ ትምህርት/ማስተዋወቅ

የተሰጡት ስልጠናዎች የሚጠናከሩ ትምህርቶችና ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እንዲጠናከሩ


በማድረግ፡

1. በስራ ላይ የሚደረግ የሴፍቲ አስገዳጅነት (Enforement) ፡


 ደረጃ በደረጃ ክትትል እየተደረገ የኮንስትራክሽን የስራ ደህንነት ጥንቃቄ
እንዲጠናከር የኮንስትራክሽን የስራ ላይ ደህንነት በዲፓርትመንት ደረጃ እንዲዋቀር
ተደርጎ በቂ ባለሙያዎች እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡
 እንደገና የተለያዩ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፡፡
 በዋና ዳይሬክተር የሚመራ የመምርያው ሃላፊና ከፍተኛ የምህንድስና ባለሙያዎች
በአባልነት የተካተቱበት፡
 በም/ዋና ዳይሬክተር የሚመራ ፕሮጀክት ማናጀርና ከፍተኛ መሃንዲሶች በአባልነት
የያዘ፡
 የቡድን መሪዎችና ከየክፍሉ የሚወከሉ አባላት ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ
የየራሳቸው ቋሚ ፕሮግራም በማዉጣት ክትትል በማድረግ በክትትሉ ወቅት
የተገኙት ግኝቶች በግብአትነት በመጠቀም መሻሻል እንዲመጣ ተደርጓል፡፡
በመጨረሻም የግንባታ የስራ ላይ ደህንነት ሽልማት በሚል ተዘጋጅቶ የሽልማት
ስነ-ስርአት ተደርጓል፡፡ ከዚህ ከጥሎ በበለጠ የሚብራሩ ሰንጠረዦች ተቀምጧል፡፡

36
ሠንጠረዥ 2-1፡ የሳይት ምልከታ ድግግሞሽ
የሳይት ምርመራ/ምልከታ የሚካሄድነት ድግግሞሽ
አይነት ድግግሞሽ ምልከታውን የሚያካሂደው አካል
የደህንነት ጉብኝት በየ 6 ወር ፕሮጀክት ዳይሬክተር
የደህንነት ክትትል በየ 3 ወር ፕሮጀክት ማናጀር
አጠቃላይ የታቀደ የደህንነት በየወሩ/ በየሳምንቱ ሲኒየር ፕሮጀክት መሀንዲሰ
ምርመራ

ምሰል 2.1፡ የአዳጋ ድግግሞሽ መጠን እና የአደጋው ክብደት መጠን

2.9. ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች (Case study)


የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ልማት ቦርድ እ.ኤ.አ በ2012 ኮሚሸን
ባደረገውና ከሰሀራ በታች ባሉ 9 የአፍሪካ ሀገሮች ውስጥ በሚገኙ 216 ትላልቅ የኮንስትራክሽን
ካምፓኒዎች ላይ ባካሄደው Analysis of economic impacts and associated costs of
occupational injuries in construction industries, ጥናት ከሰሀራ በታች ባሉ የአፍሪካ
ሀገሮቸ በአመት በአማካይ 25.3/100000 ሰራተኞች የሞት አደጋ ምጣኔ እንዲሁም
12150/100000 ሰራተኞች ላይ ሞት ያላደረሱ ከባድና ቀላል ጉዳቶች ምጣኔ መመዝገቡ
ተገልጧል፡፡ በጥናቱ ዘመን በዘርፉ ከተመዘገቡ እነኚህ የሥራ ላይ ጉዳቶች መካከል 78%
የሚገመቱት መሰረታዊ የመከላከያ እርምጃዎችን በዝቅተኛ ወጪ(Nominal cost) በመተግበር
እንዳይከሰቱ ማድረግ ይቻል እንደነበር ትንትናው አመልክቶ ጉዳቶቹ በመከሰታቸው ሳቢያ
የወጣው አጠቃላይ ወጪ ግንባታውን ለማጠናቀቅ ከወጣው አጠቃላይ ወጪ ከ5.4%-7% ያህል
ድርሻ እንደነበረው ተመልክቷል፡፡[14]

37
በጥናቱ ከተሸፈኑ 216 የኮንስትራክሽን ድርጅቶች የተጠናቀረው የስራ ላይ አደጋ መረጃ
የመለከተው ሌላ እውነታ በሥራ ቦታዎች የተከሰቱ የስራ ላይ አደጋዎች እና የጤና ጉዳቶች
እንዳይደርሱ በቅደሚያ መደረግ የነበረባቸው የመከላከል ስራዎች አጠቃላይ ወጪ ከግባታው
ጠቅላላ ወጪ 0.54%-3.1% ድርሻ ነበራቸው፤ ይህ የመከላከል ወጪ ከአደጋ ወጪ ጋር
ሲነጻጸር ከ81.5%-83.2% ዝቅተኛ ከመሆኑም በተጨማሪም በቀጣይ ለሚከናወን የአደጋ
መከላከል እርምጃ ኢንቨስትመንት ከመሆኑም በተጨማሪ የመከላል ስራ ወጪ ቆጣቢ፣ ተቋማዊ
የሴፍቲ አቅምን ደረጃ በደረጃ የሚያጠናክርና ውጤታማ አሠራርን የሚዘረጋ መሆኑን
አመልክቷል፡፡ በመሆኑም በብሄራዊ ደረጃ የሚነደፍና ተግባራዊ የሚደረጉ ሙያ ደህንነትና
ጤንነት ፕሮግራሞች ለኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ትኩረት እንዲሰጡ አስገንዝቧል፡፡[14]

2.10. የሀገር ውስጥ ተሞክሮ

2.10.1 የስራ ላይ ደህንነትና ጤንነት በኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ በአዲስ አበባና በወልቂጤ
በ2014 እ.ኤ.አ የተደረገ ጥናት
በሀገራችን የግንባታ አካባቢ ደህንነት ላይ የተደረጉ ብዙ ጥናቶች ባይኖሩም ከተደረጉት
የተወሰኑ ጥናቶች ውስጥ በሰይፈዲን ሰርሞሎ በኢትዮጵያ የግንባታ ቦታ ደህንነት እና ጤና
በሚል ርዕስ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው፡-[10]

 አብዛኛዎቹ ግኝቶች በሌሎች ታዳጊ አገሮች ውስጥ ካለው ቀደምት ሥነ-ጽሑፍ ጋር


የተያያዙ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ግንባታ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚሠሩ የሙያ እና የጤና
አጠባበቅ ልምዶች በጣም ደካማ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የኮንስትራክሽን ኩባንያዎች
የሥራ ቦታ ጤናና ደህንነት (OHS) ደረጃውን ማሟላቱን እና ፖሊሲዎች የመተግበር
ሁኔታ በጣም ደካማ ናቸው::

 ስለ የሥራ ቦታ ጤናና ደህንነት (OHS) ስልጠና መሰጠቱ አስፈላጊ ቢሆንም


ለሰራተኞች የሚሰጠው ስልጠና አነስተኛ ነው፡፡ አብዛኛው የግንባታ ድርጅቶች የሥራ
ቦታ ጤናና ደህንነት (OHS) አገልግሎቶችን እንደ የደኅንነት ፖሊሲ፣ የደህንነትን
ተወካይ፣ የጤና እና የደህንነት ኮሚቴ፣ አደጋን የመለያ ስራ፣ የሪፖርት አቀራረብ
ፕሮግራም እና በአግባቡ የደህንነት ምልክቶችን ማስቀመጥ የመሳሰሉት የሉትም::

 ነገር ግን ከመልካም ባህሪያት መካከል መሀንዲሶች/ፎርማን እንደሚናገሩት ከሆነ


ብዙዎቹ ኩባንያዎች የህክምና መድህን እና ለሰራተኞች የሥራ አደጋ ክፍያ ማካካሻ

38
ይሰጣሉ:: በተጨማሪም ዋና ዋናዎቹ የኩባንያው ክፍሎች አስፈላጊ የሆኑ የመጀመሪያ
ደረጃ ዕርዳታዎችን እና የጤና ባለሙያዎችን ይይዛሉ፡፡

 ምቹ ያልሆነ የሥራ ሁኔታ/ አካባቢ እና የግል መከላከያ መሣሪያዎች (PPE) አለመኖር


በግንባታው ኢንዱስትሪ ውስጥ ለአደጋዎች ዋነኛው ምክንያቶች ናቸው፡፡ በሌላ በኩል
በኢንዱስትሪ ውስጥ የእግር እና የእጅ ጉዳት እንዲሁም ከመሬት ከፍታ ላይ የመውደቅ
በከፍተኛ ሁኔታ በተደጋጋሚ የሚከሰቱ አደጋዎች ናቸው::

2.10.2 በደህንነትና ጤንነት ላይ ያለው አፈጻጸም ማሳያ በአዲስ አበባ በመንገድና ቤት ግንባታ
እ.ኤ.አ በ2014 የተደረገ ጥናት
በ2014 እኤአ በዘሩ ታሪኩ በተደረገው ጥናት እንደሚያመለክተው [9]

 በአዲስ አበባ የመንገድና ህንጻ ግንባታ ላይ በጣም አነስተኛ የሆነ የደህንነት ሁኔታ
እንዳለ ሲያመላክት ለዚህም እንደማስረጃነት ያስቀመጠው በመስክ ምልከታ ወቅት ለስራ
የተሰማሩ ሰራተኞች ምንም አይነት የደህንነት መጠበቅያ ቁሳቁሶችና አልባሳትን
አለመጠቀማቸዉን ገልጻል፡፡

 ጥናቱ እንደሚያመልክተው 50% የሚሆኑት የበላይ አመራር አካላቱ በሃሳብ ደረጃ


የደህንነት ጤንነት (safety and Healthy) ላይ መሰራት እንዳለበት ቢያምኑም በተግባር
ግን ለሰራተኞች አስፈላጊዉን ስልጠናም ሆነ ሌሎች ጠቃሚ ተግባራትን ከማከናወን
ይልቅ የግንባታ ስራውን ቶሎ መጠናቀቅና ትርፋማነትን የበለጠ ትኩረት የመስጠት
ሁኔታ ይታይቸዋል፡፡

 ጥናቱ እንደሚያሳየው 50% የሚሆኑት የግንባታ ቦታዎች በባለቤት ወይም በሌሎች


አካል በግንባታ ስራ ደህንነትና ጤንነት ላይ ክትትል እንደሚደረግላቸው ቢጠቁሙም
ይህ ግን በደህንነት ባለሙያና በግንባታ ቁጥጥር አድራጊው አካል በቋሚነት ክትትልና
ቁጥጥር እንደማይደረግና አፈጻጸሙም ደካማ መሆኑ ተገልጻል፡፡

 የግንባታ ዘርፉ እያደረሰ ያለው አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሆነና ይህም
ከሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ መሆኑ ያሳያል፡፡ በተጨማሪም
በግንባታ ቦታ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን መዝግቦ የመያዝ ስርአቱ በቂና በተደራጀ
መልኩ አለመሆኑ ተገልጸል፡፡ በተጨማሪም በጣም ከፍተኛ የሆነና ወደ ሆሰፒታል
ለህክምና የሚሄዱት ላይ የደረሱ አደጋዎችን እንጂ ሌሎች ቀለል ያሉት

39
እንደማይመዘገቡም ያሳያል፡፡ እንዲሁም በከተማው ጤና ቢሮም ሆነ በሆስፒታል
ከግንባታ ስራ ጋር ተያያዥነት በሆነ ምክንያት አደጋ ደርሶባቸው ለህክምና
የሚመጡትን የመመዝገቢያ ስርአት አለመኖሩን ጠቁሟል፡፡

 በአጠቃላይ ሴፍቲ በሃገራችን ምንም እየተሰራበት እንዳልሆነና በአንጻሩ ግን የግንባታው


ዘርፍ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ያለ በመሆኑ በግንባታ ስራ ያሉት በተለይም በታችኛው
ሰራተኛ በተለያየ መልኩ ከስራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑ
አመላክቷል፡፡

 ከተለያዩ አገሮች ጤንነትና ደህንነት ጋር በተያያዘ የተቀመጡ ወጪዎች እንደሚሳዩት


ዩናየትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ጠቅላላ የአደጋ ወጪው 6.5% የሚሆነውን ሙሉ
ለሙሉ ስራውን ለማጠቃለል ከሚወጣውን ወጪ እንደሚሸፍን፤ በዩናይትድ ኪንግደም
ወደ 8.5% እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ 4.3% -5.4% የጨረታ ዋጋን እንደሚይዝ
ያመለክታል፡፡ ይህም በአጠቃላይ ሲታይ በጣም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚያዊ ቁጠባን
የስራ ላይ ጤንነትና ደህንነትን ተግባራዊ በማድረግ ጠቀሜታ ሲኖረው በተጨማሪም
የፕሮጀክት መዘግየትን ያስወግዳል፤ በስራተኞች በኩል የሚቀርብ ቅሬታን በመቀነስ
የፕሮጀክት አፈጻጸምን ያሳድጋል፤ የሰራተኛን ከስራ መቅረት በማስወገድ የስራ ሞራልን
አብሮ የመስራት ሁኔታን እና የመሳሰሉትን እንዲዳብር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው
ጥናቱ ያሳያል፡፡

40
ክፍል ሶስት

3. ትንታኔ እና የጥናቱ ግኝቶች

3.1. ከመጠይቅ የተገኙ ትንታኔዎች

3.1.1. ከህንጻ ግንባታ የተገኙ ትንታኔዎች


ደህንነት በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ

 የግንባታ ደህንነት (Safety and healthy) ህግ

ምሰል 3-1፡ የተጻፈ ህግ

ድርጅቱ ስለግንባታ ደህንነት (Safety and healthy) የተፃፈ ህግ አለው ወይ ለሚለው ጥያቄ
በአማካሪ፣ በስራ ተቋራጭ እንዲሁም በግንባታ ባለቤት የተሰጠው ምላሽ እንደሚያመለክተው
የህግ አፈጻጸማቸው ከ50% በታች መሆኑን ነው፡፡ እንዲሁም ምንም ምላሽ ያልሰጡም
ይገኛሉ፡፡ይህም እንደሚያለክተው ምንም ግንዛቤ የሌላቸው በግንባታ ዉስጥ እየሰሩ ያሉ ቁልፍ
ተዋናዮች መኖራቸው ነው፡፡ በተለይም ለግንባታው ዋና የስራ ባለቤት የሆነው ስለግንባታ
ደህንነት ያለው የህግ እውቀት በጣም ዝቅተኛ መሆኑ ያሳያል፡፡ ይህም አንድን ስራ ለጨረታ
በሚያወጡበት ጊዜ የግንባታ ደህንነትን በተመለከተ ትኩረት ከመስጠት ይልቅ በዝቅተኛ ዋጋ
የሚሰራለትን የመምረጥ አዝማምያ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

41
 ሴፍቲን በተመለከተ ያለው የውል ስምምነት ሁኔታ
ሠንጠረዝ 3-1፡ ደህንነት በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ
አማካሪ ተቋራጭ ባለቤት

የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት


መጠን መጠን ስሌት መጠን

አዎ 30 96.8 204 94.0 22 91.7

አላምንበትም 0 0 13 6.0 2 8.3

መልስ ያልሰጡ 1 3.2 0 0 0 0

ጠቅላላ 31 100.0 217 100.0 24 100.0

ሴፍቲ የውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ መካተት አለበት ወይ ለሚለው አማካሪ፣ የስራ ተቋራጭ
እንዲሁም የግንባታ ባለቤት በአማካኝ 94% አዎ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ይህም
እንደሚያሳየው በዉል ስምምነቱ ዉስጥ መካተቱን ሁሉም በከፍተኛ ደረጃ መስማማታቸውን
ያመለክታል፡፡ይሁን እንጂ በቃለመጠይቅና በትኩረት ቡድን ዉይይት እንደተገለጸው በአማካሪ
በኩል ሴፍቲን በተመለከተ በዝርዝር የተቀመጠ የስራ ዉል ስምምነት አለመኖሩ በበጎ
ፈቃደኝነት ከሚያሟሉት ዉጭ ህጉን ለማስፈጸም አስቸጋሪ መሆኑን ሲገልፁ በተቋራጮች
በኩል የስራ ውል የሚገቡበት ዝቅተኛ ዋጋ በመሆኑ፣ በዉል ስምምነት አለመካተቱ እንዲሁም
ወጭን በመፍራት የሴፍቲ አልባሳትን ያለማሟላት በጣም ጎልቶ የሚታይ ችግር ነው፡፡ ለዚህም
እንደምክንያት የሚያስቀምጡት እንኳንስ ለቅድመ ጥንቃቄ ደህንነት ለማውጣት ያላቸው
ትርፍ አናሳ እንዲሁም ኪሳራ ውስጥ ስለሆነ ይህንን ጉዳይ ማንም ቦታ አይሰጠውም፡፡
በአሰሪው አካል በኩል ዝቅተኛ ዋጋን የመምረጥ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለደህንነት
መጠበቂያ አሰፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በማካተት ዋጋ የሚያቀርቡ የስራ ተቋራጮችን
አያበረታታም፡፡ ይህም በተደጋጋሚ በሁሉም ባለድርሻ አካላት በዉል ስምምነት ዉስጥ መካተት
አለበት የሚል የመደምደምያ ሃሳብ መኖሩን ተገንዝበናል፡፡

 ለግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) የሚወጣ ወጪ (በcontract agreement)


የሚካተትበት ሁኔታ በተመለከተ

42
ምስል 3-2፡ የደህንነት ወጪ በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ ስለመካተቱ

ከላይ በግራፉ እንደሚታየው ለግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) የሚወጣ ወጪ


(በcontract agreement) ይካተታል ወይ ለሚለዉ በአማካሪ፣ በስራ ተቋራጭ እንዲሁም
በግንባታ ባለቤት የተሰጠዉ ምላሽ የሚያመለክተው በአማካይ 55% አለማካተቱ ነው ፡፡
በተጨማሪም በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ያልሰጡ በአማካይ 10% የሚደርሱ ሲሆኑ
እነዚህም ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠታቸውን ያሳያል፡፡ እኛም ባደረግነው ቃለመጠይቅና
ዉይይት ለመረዳት እንደቻልነው ለደህንነት መጠበቂያ ተብሎ በስራ መዘርዝር ዉስጥ
የሚካተት ወጪ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ምንም እንኳን በዉል ስምምነት
መካተት አለበት ብለው ቢያምኑም በተጨባጭ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር አፈጻጸሙ አነሳ
መሆኑም ጭምር ተገንዝበናል፡፡

ደህንነትን የተመለከቱ ህጎች እና አፈጻጸማቸው

 ስለግንባታ አካባቢ ደህንነት (work zone Safety) ያለዉ እውቀት

43
ሠንጠረዥ 3-2፡ ስለ ግንባታ ደህንነት ያለው ግንዛቤ
አማካሪ ተቋራጭ ባለቤት ሠራተኛ

የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ


መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ስሌት

አዎ 31 100.0 189 87.1 23 95.8 320 80.4

አላውቅም 0 0 28 12.9 1 4.2 76 19.1

ምላሽ ያልሰጡ 0 0 0 0 0 0 2 .5

ጠቅላላ 31 100.0 217 100.0 24 100.0 398 100.0

ስለ ግንባታ አካባቢ ደህንነት (work zone Safety) ከዚህ በፊት ያውቃሉ ወይ ለሚለው
በአማካሪ፣ በስራ ተቋራጭ፣ በግንባታ ባለቤት እንዲሁም በጉልበት ሰራተኛ በአማካይ 91%
እንደሚያዉቁ ገልጸዋል፡፡ በአማካሪ በኩል ሙሉ ለሙሉ ግንዛቤው ሲያመለክት በጉልበት
ሰራተኛ በኩል ያለዉ ከሌሎቹ ዝቅ ያለ መሆኑ ይስተዋላል፡፡ ባደረግነው ዉይይትም ያስተዋነው
በሁሉም አካላት የግንዛቤ ማነስ አለመኖሩን ሲሆን ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ ማድረግ ላይ
ከፍተኛ ችግር መኖሩን ነው፡፡
 በሀገራችን ከ Safety ጋር ተያያዥነት ያለው ህግ/አዋጅ/ደንብ/ በተመለከተ

ሠንጠረዝ 3-3፡ የግንበታ ደህንነትን በተመለከተ ህግ ስለመኖሩ


አማካሪ ተቋራጭ ባለቤት

የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ


መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ስሌት

አዎ 14 45.2 22 10.1 5 20.8

አላውቅም 17 54.8 148 68.2 19 79.2

ምላሽ ያልሰጡ 0 0 47 21.7 0 0

ጠቅላላ 31 100.0 217 100.0 24 100.0

በሀገራችን ከደህንነት ጥንቃቄ ጋር ተያያዥነት ያለው ህግ/አዋጅ/ደንብ/አለ ወይ ለሚለው


በአማካሪ፣ በተቋራጭ እንዲሁም በግንባታ ባለቤት የተሰጠው ምላሽ በአማካይ 67% ያህሉ
እንደማያዉቁ ገልጸዋል፡፡በተለይም የግንባታው ባለቤት ያለዉ ግንዛቤ ከሁሉም ያነሰ ሲሆን
አማካሪው የተሻለ እዉቀት መኖሩን ይጠቁማል፡፡በተቋራጭ በኩል ስለግንባታ ደህንነት ህግ
መኖሩና አለመኖሩን እንኳን የማያዉቁ 22% የሚደርሱ ነገር ግን ግንባታዉን በግንባር
44
ቀደምትነት የሚያከናዉኑ መኖራቸዉን ያመለክታል፡፡ሆኖም ግን ከደህንነት ጥንቃቄ ጋር
ተያያዥነት ያላቸው የፍትሃቤር፣ ፊዲክ፣ ፒፒኤ፣ የህንጻ አዋጅ፣ ኢቢሲኤስ እና የመሳሰሉት
ህጎችና ደንቦች ያሉ ሲሆን ባደረግነው የትኩረት ቡድን ዉይይት እንዲሁም ቃለመጠይቅ
አብዛኛዉ ህጎቹና ደንቦቹ መኖራቸውን እንደማያዉቁ ተረድተናል፡፡

 የህግ/አዋጅ/ደንብ/ ተፈፃሚነት

ምስል 3-3፡ የህግ/አዋጅ/ደንብ ተፈጻሚነት

የህግ/አዋጅ/ደንብ/ በአግባቡ ተፈፃሚ ነው ወይ ለሚለው በአማካሪ፣ ተቋራጭ እንዲሁም ባለቤት


የተሰጠው ምላሽ በአማካይ 5% አዎ ሲሆን ይህም በአፈጻጸም ላይ ያለው ትግበራ እጅግ በጣም
ዝቅተኛ መሆኑን ያመላክታል፡፡እኛም ባደረግነው የትኩረት ቡድን ዉይይትና ቃለመጠይቅ
ለህጉ ተፈጻሚ አለመሆን እንደአንድ ምክንያት የሆነው የህጉን መኖርና አለመኖር እንኳን
የማያዉቁት አብዛሃኛው የግንባታው ባለድርሻ አካላት በመሆናቸው ስለተፈጻሚነቱ ለመናገር
አለመቻላቸዉን ነው፡፡

45
የደህንነት አስተዳደር

የደህንነት እቃዎችና መሳሪያዎች

 የጥንቃቄ ዕቃዎችን ስለመሟላታቸው

ምስል 3-4፡ የደህንነት ዕቃዎች ስለመሟላታቸው

ድርጅቱ ለሰራተኞቹ የጥንቃቄ ዕቃዎችን አሟልቷል ለሚለው አማካሪ 29% አሟልቷል 65%
አላሟላም ሲሉ ተቋራጭ ደግሞ 48% አሟልቷል 49% አለማሟላታቸውን ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም በሁለቱም በኩል ምላሽ ያልሰጡት ዝቅተኛዉን ፐርሰንት ይይዛሉ፡፡ነገር ግን
በተቋራጭ የተገለጸው ዉጤት እንደሚያሳየው ግማሽ በግማሽ የተሟላና ያልተሟላ ሲሆን
በተጨባጭ ያለዉ ግን የደህንነት እቃዎች አለማሟላታቸዉንና በአማካሪዎቹም በኩል
አልተሟላም የሚለው ከፍተኛ ሲሆን ተቋራጭ በበጎ ፈቃደኝነት ካላሟላ በስተቀር ማስገደድ
እንደማይችሉና አሁን ያለዉ ነባራዊ ሁኔታ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በመስክ
በተዘዋወርንባቸው የግንባታ ቦታዎች አብዛኛዎቹ የድህንት አላባሳትም ሆነ የጥንቃቄ
ምልክቶቹን ምንም የማይጠቀሙ ሲሆን በቁጥር እጅግ አናሳ የሆኑ በተሻለ መልኩ ከደህንነት
ባለሙያ እስከ አስፈላጊዉን ቁሳቁስ ያሟሉና ለሌሎችም ምሳሌ መሆን የሚችሉ ተቋማት
መኖራቸዉን ተረድተናል፡፡

46
 የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና (First aid)
ሠንጠረዥ 3-4፡ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና ስለመኖሩ
ተቋራጭ ሠራተኛ

የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት

አለ 164 75.6 276 69.3

የለም 53 24.4 119 29.9

ምላሽ ያልሰጡ 0 0 3 0.8

ጠቅላላ 217 100.0 398 100.0

ከላይ በሰንጠረዥ እንደተገለጸው የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና(First aid) አለ ወይ ለሚለው


ተቋራጭና ሰራተኛ በአማካይ 73% መሟላቱን ገልጸዋል፡፡ በሁለቱም በኩል እንደተገለጸው
የመጀመርያ ደረጃ ህክምና መኖሩን ያሳያል፡፡ነገር ግን ባደረግነው ዉይይት እንደተገነዘብነው አለ
የሚል ምላሽ ቢሰጡም እንኳን በተሟላና በተደራጀ መልኩ እንዲሁም ሁሉንም ተጠቃሚ
ባደረገ ሁኔታ አለመሆኑ አስተዉለናል፡፡በተጨማሪም በቁጥር እጅግ አናሳ የሆኑ ተቋማት
አስፈላጊዉን የመጀመርያ ደረጃ ህክምና ከዚያ አልፎ ተጎጂዉ ተኝቶ ቀለል ያሉ ህክምናዎችን
የሚያደርግበት አልጋ እና ጊዚያዊ ክፍል እንዲሁም በህክምና ዘርፉ እዉቀት ያለው ባለሙያ
በግንባታ ቦታ ላይ ያሟሉ እንደሚገኙ አስተዉለናል፡፡ ይህም ሊበረታታ የሚገባው ተግባር
ነው፡፡

47
 የተሟሉ የደህንነት ዕቃዎች

የተሟሉ የደህንነት ዕቃዎች


35.00% 33.30%

30.00% የእጅ ጓንት


26.30%
25.00% 23.60% አንጸባራቂ ልብስ
የመቶኛ ስሌት

19.00% ሄልሜት
20.00% 17.50%
16.20%
14.90% የደህንነት ጫማ
15.00% 11.70%
10.50% 9.90% መነፀር
10.00%
የአቧራ መከላከያ
5.00% 3.50%
1.10% ሁሉንም
0.00%
አማካሪ ተቋራጭ ሰራተኛ

ምስል 3-5፡ የተሟሉ የደህንነት ዕቃዎች

በናንተ በኩል የተሟሉ የደህንነት ዕቃዎች የትኞቹ ናቸው ለሚለው በአማካሪ፣ ተቋራጭ
እንዲሁም የግንባታ ስራተኛ የተሰጠው ምላሽ የደህንነት ዕቃዎችን በሚገባ አለመሟላታቸዉን
ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም በሁሉም ወገን በኩል ሄልሜት በተወሰነ መልኩ የተሟላ ሲሆን
አንጻባራቂ ልብስ ደግሞ ሁለተኛዉን ደረጃ ይይዛል፡፡ በእየአንዳንዱ የግንባታ ባለድርሻ አካላት
አልፎ አልፎ በስብጥር አንዳንድ እቃዎችን ከማሟላት የዘለለ ለደህንት አስፈላጊ የሆኑት
አልባሳት በተሟላ መልኩ የሌለ መሆኑን በግልጽ ይታያል፡፡እኛም በመስክ ምልከታችን
ያረጋገጥነው ይህንኑ ነው፡፡
 ማንኛውም ጎብኝ ወደ ግንባታ ቦታ (construction site) በሚመጣበት ጌዜ ስላለው ቅድመ
ጥንቃቄ

ሠንጠረዥ 3-5፡ ለጎብኚ የሚደረገው ጥንቃቄ


አማካሪ ተቋራጭ

የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ


መጠን ስሌት መጠን ስሌት

አለ 11 35.5 82 37.8

የለም 19 61.3 135 62.2

ምላሽ ያልሰጡ 1 3.2 0 0

ጠቅላላ 31 100.0 217 100.0

48
ከላይ በሰንጠረዝ እንደተገለፀው ማንኛውም ጎብኝ ወደ ግንባታ ቦታ (construction site)
በሚመጣበት ጌዜ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተቋሙ ያለው የአሰራር ሁኔታ አለ ወይ
ለሚለው አማካሪና የስራ ተቋራጭ በአማካይ 62% ጥንቃቄ እንደማያደርጉ ገልፀዋል፡፡ይህም
ጥንቃቄ ያለማድረጉ ሁኔታ ከፍተኛ መሆኑን ያለው የመቶኛ ውጤት ያሳያል፡፡በመሆኑም
ለሰራተኛው ሆነ ከሰራተኛው ውጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚደረገው ጥንቃቄ አናሳ
ነው፡፡ እኛም ባደረግው የመስክ ምልከታ እንዳሰተዋልነው እንኳን ከስራው ዉጭ ለሆኑት
የህብረተሰብ ክፍሎች ይቅርና በግንባታ ስራ ላይ ለተሰማሩትም ቢሆን አሰፈላጊውን የደህንነት
አልባሳት እንዲሁም የቅድመጥንቃቄ ምልክቶች አለመሟላታቸውን ነው፡፡

የደህንነት ባለሙያ

 አጠቃላይ ከደህንነት (Safety) ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስራዎች የሚያከነውን Safety

professional ባለሙያ ስለመኖር

ምሰል 3-6፡ የደህንነት ባለሙያ ስለመኖሩ

በተቋምዎ በግንባታ ቦታም ሆነ በቢሮ ደረጃ አጠቃላይ ከደህንነት (Safety) ጋር ተያያዥነት


ያላቸውን ስራዎች የሚያከነውን የደህንነት ባለሙያ (Safety professional) አለወይ ለሚለው
አማካሪ፣ የስራ ተቋራጭ እንዲሁም የግንባታ ባለቤት በአማካይ 86% የሌለ መሆኑን
ገልጸዋል፡፡ በመስክ ምልከታ ወቅት እንዲሁም በተደረገው የቡድን ዉይይት የደህንነት ባለሙያ
አለመኖሩን አረጋግጠናል፡፡ምንም እንኳን በደህንነት (Safety professional) የተመረቀ ባለሙያ

49
ባይኖርም በሌላ የምህንድሰና ዘርፍ የተመረቁ ባለሙያዎች እንደ ደህንነት ባለሙያ ሆነው
እንዲሰሩ የተደረገበት ሁኔታ በቁጥር እጅግ አናሳ የግንባታ ተቋማት መኖሩን አስተዉለናል፡፡

 የደህንነት መከላከያ (Safety) አልባሳት ደረጃውን (standard) የጠበቁ ስለመሆናቸው


ሠንጠረዥ 3-6፡ የደህንነት አልባሳት ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው
አማካሪ ተቋራጭ

የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት

አለ 5 16.1 46 21.2

የለም 26 83.9 168 77.4

ምላሽ ያልሰጡ 0 0 3 1.4

ጠቅላላ 31 100.0 217 100.0

ከላይ በሰንጠረዥ እንደተገለጸው ለሰራተኞች የደህንነት መከላከያ (Safety) አልባሳት ተብሎ


የሚጠቀምባቸው ደረጃውን (standard) የጠበቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ አካል አለ ወይ
ለሚለው በአማካሪ፣ በተቋራጭ በአማካይ 81% የለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይህም
የሚያመለክተው የደህንነት እቃዎች ደረጃቸው የጠበቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ አካል
አለመኖሩን ተረድተናል፡፡

በsafetyጉድለትአደጋሲያጋጥመውስላለውተጠያቂነት

በsafety ጉድለት አደጋ ሲያጋጥመው ስላለው ተጠያቂነት


100
83.3
80 76
71.4
ሰራተኛው
የመቶኛ ስሌት

60 አሰሪው መስሪያቤት
ተቋራጭ
40
ሌላ አካል
ምላሽ ያልሰጡ
16.1 17.1
20 12.5 9.8
6 4.2
0.51.4 0 0 1.30.5
0
ተቋራጭ ባለቤት ሰራተኛው

ምስል 3-7፡ በሴፍቲ ጉድለት ምክንያት አደጋ ሲያጋጥም ተጠያቂው አካል ማን ነው

50
አንድ ሰራተኛ በsafety ጉድለት አደጋ ሲያጋጥመው ተጠያቂው አካል ማን ነው ለሚለው
በተቋራጭ፣ በአሰሪው መ/ቤት እንዲሁም በጉልበት ሰራተኛው በአማካይ 77% ያክሉ የስራ
ተቋራጭ መሆኑን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይህም እንደሚያመለክተው ማንኛዉም በስራ ምክንያት
በስውም ሆነ በንብረት ላይ ለሚደርስ አደጋ ከፍተኛውን የተጠያቂነት ድርሻ የሚወስደው የስራ
ተቋራጩ መሆኑ ያሳያል፡፡

 ስለግንባት ቦታ ደህንነት ስልጠና (training) በቋሚነት ስልጠና ስለመሰጠት

ምስል 3-8፡ ሰልጠና በቋሚነት ስለመሰጠቱ

ከላይ በሰንጠረዥ እንደሚታየው ስለስራ ቦታ ደህንነት ከአሰሪ መስሪያ ቤትዎ ተገቢው ስልጠና
(training) በቋሚነት ይሰጣል ወይ ለሚለው በሰራተኛ፣ በተቋራጭ፣ በአማካሪ በአማካይ 79%
አይሰጥም በማለት መልሰዋል፡፡ እኛም ባደረግነው የመስክ ምልከታና ውይይት እንደተረዳነው
አብዛኛው የጉልበት ሰራተኛው ከማንበብና መጻፍ የዘለለ የእዉቀት ደረጃ የሌለዉ መሆኑ፣
እንዲሁም የመግባብያ ቋንቋ እንኳ በቅጡ ለመናገር የማይችሉ ከተለያየ የአገሪቱ አካባቢ
የመጡ የጉልበት ሰራተኞች ባለበት ሁኔታ በተጨማሪም ስለግንባታ ደህንነት ምንም ስልጠና
አለመሰጠቱ በኢንዱስትሪዉ የሚደርሰው አደጋ ዉስብስብና ከፍተኛ እንደሚያደርገው
አስተውለናል፡፡

51
በግንባታ ቦታ ላይ በደህንነት መጓደል ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎች

በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ የሚደርሱ አደጋዎች

 በግንባታ አካባቢ አስፈላጊው የደህንነት ጥንቃቄ ባለመደረጉ ምክንያት አደጋ ሲያጋጥም

ያለው የሪፖርት አደራረግን በተመለከተ

መስል 3-9፡ አደጋ ሲያጋጥም ሪፖርት ስለመደረጉ

በግንባታ አካባቢ አስፈላጊው የደህንነት ጥንቃቄ ባለመደረጉ ምክንያት አደጋ ሲያጋጥም ያለውን
የሪፖርት አደራረግ በተመለከተ የግንባታ አማካሪ 61%፣ ተቋራጭ 34%፣ ስራተኛ 34%
ሪፖርት አለመደረጉን ገልፀዋል፡፡ በሰራተኛና በተቋራጭ መካከል ያለው አስተያየት ተመሳሳይ
ሲሆን አማካሪው አጠቃላይ በግንታው ላይ ያለዉን ሁኔታ የሚቆጣጠረው አካል የሰጠው ምላሽ
ግን ከነሱ ፍጹም የተለየና የሪፖርት አደራረግ ሰርአቱ ዝቅተኛ መሆኑን ነው፡፡ ይህም
የሚያመለክተው በተቋራጭ በኩል ሪፖርት ይደረጋል ማለቱ ተጠያቂነትን ከመሸሽ አንጻር
ሲሆን እኛም ባደረግነው ውይይት የተገነዘብነው አደጋ ሲያጋጥም በተደራጀ መልኩ ሪፖርት
አለመደረጉን ነው፡፡

52
 ሰአት እላፊና ትራፊክ ፍሰት በሚበዛበት የሚከናወኑ ስራዎች ለአደጋ መፈጠር ያላቸው
አስተዋጸኦ

Table 3-1 ሠንጠረዥ 3-7፡ ሰዓት እላፊና ትራፊክ በሚበዛበት የሚከናወኑ ሥራዎች ለአደጋ መፈጠር ያላቸው አስተዋጽኦ

ተቋራጭ ሰራተኛው
የድግግሽ የመቶኛ የድግግሽ መጠን የመቶኛ ሰስሌት
መጠን ሰስሌት
ከፍተኛ 146 67.3 203 51.0
መካከለኛ 52 24.0 117 29.4
ዝቅተኛ 19 8.8 70 17.6
ምላሽ ያልሰጡ 0 0 8 2.0
ጠቅለላ 217 100.0 398 100.0
ሰአት እላፊና ትራፊክ ፍሰት በሚበዛበት ሰአት የሚከናውኑ ስራዎች ለአደጋ መፈጠር ያላቸው
አስተዋፅኦ ምን ያክል ይሆናል ለሚለው ተቋራጭና የግንባታ ሰራተኛ በአማካይ 59% ከፍተኛ
መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ መረዳት እንደሚቻለው በምሽትና የትራፊክ ፍሰት በሚበዛበት ወቅት
ለሚከናወኑ ስራዎች ከሌሎች በተለየ ሁኔታ ግልጽና ማንኛዉም በቀላሉ ሊረዳው የሚችል
የቅድመ ጥንቃቄ ምልክቶች መቀመጥ እንዳለባቸው ነው፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ለሚፈጠረው
አደጋ ያለው አስተዋጾ በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡

 የደህንነት (Safety) ምልክቶችን ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎች

ሠንጠረዥ 3-8፡ የደህንነት ምልክቶችን ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎች

ሰራተኛው ተቋራጭ
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ ሰስሌት
መጠን ሰስሌት መጠን

አዎ 206 51.7 112 51.6


የለም 187 47.0 99 45.6
ምላሽ ያልሰጡ 5 1.3 6 2.8
ጠቅላላ 398 100.0 217 100.0

ከላይ በሰንጠረዥ እንደተገለፀው አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት (Safety) ምልክቶችን በአግባቡ


ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎችን በተመለከተ የስራ ተቋራጭና የጉልበት ሰራተኛ በአማካይ
52% የተፈጠሩ አደጋዎች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡ ይህም ከ50% በላይ አስፈላጊው የጥንቃቄ
ምልክት ባለመቀመጡ ምክንያት አደጋ መከሰቱን ያመላክታል፡፡ እኛም ያስተዋልነው የቅድመ
ጥንቃቄ ምልክትን በማስቀጥ ብቻ የሚከሰት አደጋን በቀላሉ መቀነስ መቻሉን ነው፡፡
53
 በመጠጥ ወይም ለስራ ብቁ ሳይሆኑ ስራ በማከናወናቸው የተፈጠረ አደጋ

ምሰል 3-10፡ ብቁ ባልሆኑ ሰራተኖች የተፈጠሩ አደጋዎች

ከላይ በግራፉ እንደሚታየው ሰራተኞች ጠጥተው ወይም ለስራ ብቁ ሳይሆኑ ስራቸውን


በማከናወናቸው ተቋራጭ 41%አደጋ እንደሚከሰት ሲገልጽ፤ ሰራተኛ 45% ጠጥተው ወይም
ለስራ ብቁ ሳይሆኑ ስራቸውን እንዳያከናዉኑ አስገዳጅ የሆነ ህግ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡
ይህም ማለት ሰራተኞች መጠጥ ጠጥተው ወደ ስራ በመግባታቸው ምክንያት እንዲሁም
በእድሜ የገፉ ወይም ለስራ ያልደረሱ ወይም በተለያየ ምክንያት ለስራው ብቁ ያልሆኑ
ስራተኞች ለስራ በመሰማራታቸው የሚደርስ አደጋ እንዳለ ያመላክታል፡፡

54
 በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች

ምስል 3-11፡ በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች

ከላይ በግራፉ ለማየት እንደተሞከረው በግንባታ ቦታ በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች


ዉስጥ አብዛኛው የአደጋ አይነቶች በተመሳሳይ ደረጃ መከሰታቸውን ሲያመለክት ከፍተኛዉን
ቦታ የያዘው ከላይ በሚወድቁ እቃዎች/ከላይ መዉደቅ ሲሆን በተጨማሪም በመስክ ምልከታ፣
በትኩረት ቡድን ዉይይት እንዲሁም በቃለ መጠይቅ በተገኘው መረጃ መሰረት ከመዉደቅ አደጋ
ቀጥሎ በቁፋሮና አፈር መደርመስ፣ በቁርጥራጭ ብረቶችና ምስማሮች፣ በዊንች መበጠስ
እንድሁም በኤሌትሪክ፣በማሽነሪ ስራና ጥገና መሆናቸው በሚያደርሱት የአደጋዎች ቀደም
ተከተል መሰረት እንደሆኑ ለመገንዘብ ችለናል፡፡ በተጨማሪም የድህንነት መጠበቅያ እቃዎችን
በአገባቡ አለመጠቀም እንዲሁም የእንጨት ሰካፎልዲንግ ከሚፈቀደው የወለል ከፍታ በላይ
ላላቸው በስራ ላይ ማዋል ለአደጋ መፈጠር መንስኤ መሆናቸዉንም ጭምር አስተውለናል ፡፡

55
 በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) አለመተግበር ከስራው ውጭ የሆኑ
ማህበረሰብ ላይ ስለሚደርሰው ጉዳት

መስል 3-12፡ የግንባታ ደህንነት ባለመተግበሩ ምክንያት ከስራው ውጪ የሆኑ የማህበረሰብ ከፍሎች ላይ የደረሱ አደጋዎች

በኮንስትራክሽን ስራ ውስጥ በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) በሚገባ ባለመተግበሩ


ምክንያት ከስራው ውጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጎጂ የሚሆኑበት ሁኔታ አስመልክቶ
በተቋራጭና ሰራተኛ በአማካይ 29% ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፤ ነገር ግን በአማካሪው በኩል
ከፍተኛ የሚለው አመዛኙን፣ መካከለኛ ሁለተኛውን እንዲሁም ዝቅተኛ በጣም አናሳ የሆነውን
ድርሻ እንደሚይዙ ገልጸዋል፡፡ ይህም በአንድ ሃሳብ ላይ የተለያየ አመለካከት መኖሩን ያሳያል፡፡
ነገር ግን በተጨባጭ ከግንባታ ስራ ዉጭ የሆኑት የህብረተሰብ ክፍሎች ተጎጂ እየሆኑ ያለበት
ሁኔታ መኖሩን የጥናት ቡድኑ በግንባታ ቦታ በመገኘት፤ የትኩረት ቡድን ዉይይት በማድረግ
የተከሰተ አደጋ መኖሩን አስተዉለናል፡፡

56
 በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ለሚደርስ አደጋ የኢንሹራንስ ዋስትና ስለመስጠቱ

ምስል 3-13፡ የኢንሹራንስ ዋስትና ስለመኖሩ

አንድ ተቋራጭ በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ለሚደርስ አደጋ የኢንሹራንስ ዋስትና መስጠቱን


የምትከታተሉበት ሁኔታ አለ ወይ ለሚል 52% የኢንሹራንስ ሽፋን ክትትል እንደሌለ ያሳያል፡፡
ይህም ማለት በግንባታ ቦታ ለሚሰሩት ሰራተኞችም ሆነ ለግንባታ ስራ የሚያገለግሉ ንብረቶች
የሚሰጥ ዋስትና አናሳ መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን በግንባታ ቁጥጥር መ/ቤት ከመጀመርያው
የህንጻ ስራ ፈቃድ ሲሰጥ በስራው ላይ ላሉ ሰራተኞች እንዲሁም በንብረት ላይ ለሚደርስ አደጋ
የኢንሹራንስ ዋስትና የተገባበት ማስረጃ ማቅረብ እንደግዴታ የተቀመጠ መሆኑ ይታያል፡፡
ከዚህ አንጻር እየተሰራ ያለው በህጉ መሰረት አለመሆኑ መገንዘብ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም
በተለያየ የግንባታ ቦታ በተዘዋወርንባቸው ግንባታቸው ሳያልቁ ለባንክና ለትልልቅ የንግድ
ተቋማት የሚከራዩ በመሆናቸው አስተውለናል ነገር ግን የግንባታ ቁጥጥር መ/ቤት የስራ ሀላፊ
እንደገለፁልን ከእነሱ እይታ የተሰወረ ካልሆነ በስተቀር ይህን አድራጎት እንደሚቆጣጠሩ
አስለድተውናል፡፡ይሁን እንጂ በተጨባጭ ያለው እውነታ ከዚህ የተለየና አሳሳቢ በመሆኑ
ከስራው ውጭ የሆኑ ማህበረሰብም ተጎጂ የሚሆኑበት አጋጣሚ ስላለ የሶስተኛ ወገን
ኢንሹራንስ አስፈላጊ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡

57
በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ የሚደርሱ የአደጋ መንስኤዎች

 በግንባታ ስፍራ ለደህንነት አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች

ምስል 3-14፡ አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች ስለመለየታቸው

በግንባታ ስፍራ ለደህንነት አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች 54% በግልፅ ተለይተዋል ሲሉ 43%
አለመለየታቸውን ገልጸዋል፡፡ 2% ደግሞ ምንም አይነት ምላሽ አልሰጡም፡፡ ከዚህም መረዳት
እንደሚቻለው 46% አካባቢ የሚሆነው ለአደጋ በሚያጋልጡ ሁኔታዎች የግንታ ስራ
እየተከናወነ መሆኑን ነው፡፡ይህም በስራተኛው በስራ መንፈስ ላይ ከፍተኛ የስጋት ስሜት
ስለሚፈጥር የሚጠበቅበትን ስራ እንዳያከናዉን እንቅፋት ይሆናል፡፡

58
 በዋናነት የሚጠቀሱ የአደጋ መንስኤዎች

ምስል 3-15፡ በዋናነት የሚጠቀሱ የአደጋ መንስኤዎች

በግንባታ ቦታ ላይ ለሚፈጠሩ አደጋዎች በዋናነት የሚጠቀሱ መንስኤዎች የሚለው ዉስጥ


ቸልተኝነት የመጀመርያዉን ድርሻ ሲይዝ ሌሎች መንስኤዎች ተቀራራቢ የሆነ ዉጤትን
ያሳያሉ፡፡ እንደአጠቃላይ ሲታይ ሁሉም ለአደጋ መከሰት መንስኤ እንደሚሆኑ ያመላክታል፡፡
ባደረግነው ዉይይትና በመስክ ምልከታ እንዳስተዋልነው በጣም ቀላልና ብዙ ወጭን
የማይጠይቁ የሴፍቲ ምልክቶችን እንኳን የመጠቀም ልምዳችን አናሳ ነው፡፡ለሚሰሩት ስራዎች
የቅድመ ማስጠንቀቅያ ምልክት በማስቀመጥ ብቻ ህይወትና ንብረት መታደግ ሲቻል ነገር ግን
ለጉዳዩ አስፈላጊዉን ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት በርካቶችን አካል ጉዳተኛ እንዲሁም
ህይወት እስከመነጠቅ በተጨማሪም ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ የወጣባቸዉ ንብረቶች እየወደሙ
መሆናቸውን ተገንዝበናል፡፡በተጨማሪም በቁጥር እጅግ አናሳ የሆኑ ተቋማት የሴፍቲ አልባሳት
ቢያቀርቡም እንኳን በሰራተኛ በኩል የደህንነተ እቃዎቹ ለአጠቃቀም ምቹ ባለነሆናቸዉና
የመጠቀም ልምዱም አናሳ ስለሆነ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡

59
የደህንነት መጓደል በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪው ላይ ያለው ተጽእኖ

 አንድ ስራ በታቀደለት ጊዜ፣ ወጪ እና ጥራት ለማጠናቀቅ የግንባታ ቦታ ደህንነትን (work


zone Safety) ያለው አስተዋፅኦ

ሠንጠረዥ 3-9፡ የግንባታ ደህንነት በሥራ ላይ ያለው አስተዋጽኦ


ተቋራጭ አሰሪው መስሪያቤት አማካሪ ሰራተኛው
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
መጠን ሰስሌት መጠን ሰስሌት መጠን ሰስሌት መጠን ሰስሌት
95 43.8 15 62.5 26 83.9
ከፍተኛ 233 58.5
68 31.3 9 37.5 5 16.1
መካከለኛ 113 28.4
44 20.3 0 0 0 0
ዝቅተኛ 41 10.3
10 4.6 0 0 0 0
ምላሽ ያልሰጡ 11 2.8
217 100.00 24 100.00 31
ጠቅለላ 100.00 100.0
398

አንድ ስራ በታቀደለት ጊዜ፣ ወጪ እና ጥራት ለማጠናቀቅ የግንባታ ቦታ ደህንነትን (work


zone Safety) መተግበርን በተመለከተ ተቋራጭ፣ የግንባታ ባለቤት፣ አማካሪ፣ ሰራተኛ
በአማካይ 62%ቱ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን በተጨባጭ
ባደረግነው ዉይይት ከአደጋ የጸዳ የስራ አካባቢ ለመፍጠር፣ የሰራተኛዉን የስራ ተነሳሽነት
ለማጎልበት፣ በአደጋዉ ምክንያት የሚፈጥረው አሉታዊ ተጽእኖ ለማስቀረት፣ በአደጋ መፈጠር
ምክንያት የሚባክነው የስራ ጊዜ፣ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ የሚወጣ አላስፈላጊ ወጪ
እንዲሁም በተረጋጋ መንፈስ ስራውን በጥራት ለማከናወን በአጣቃላይ የግንባታ ስራውን
በሁሉም መልኩ የተዋጣለት ከማድረግ አንፃር ያለው ፋይዳ እጅግ የጎላ መሆኑን
ተገንዝበናል፡፡

60
 የአደጋዎች መቀነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለው አስተዋፅኦ
Table 3-2 ሠንጠረዥ 3-10፡ የአደጋዎች መቀነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለው አስተዋጽኦ

ተቋራጭ አሰሪው መስሪያቤት አማካሪ ሰራተኛው


የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ስሌት
175 80.6 23 95.8 26 83.9 331 83.2
ከፍተኛ
21 9.7 1 4.2 3 9.6 50 12.6
መካከለኛ
15 6.9 0 0 29 0 16 4.0
ዝቅተኛ
6 2.8 0 0 2 6.5 1 0.3
ምላሽ ያልሰጡ
217 100 24 100 31 100.0 398 100
ጠቅለላ

ከላይ በሰንጠረዥ እንደተገለጠው በጥንቃቄ (safety) ጉድለት ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎች


መቀነስ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለው አስተዋፅኦ ከፈተኛ መሆኑን ሁሉም በግንባታው
ላይ ያሉት ዋና ባለድርሻ አካላት በአንድነት መስማማታቸውን ያሳያል፡፡ይህ ደግሞ እንደ
ኢትዮጲያ በማደግ ላይ ላለ አገር ያለውን ውስን ሀብት እንዳይባክንና በከፍተኛ እድገት ላይ
ያለውን የኮንስትራክስን እንደስትሪ ጤናማና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከማድረግ አንፃር
የጎላውን ደርሻ ይይዛል፡፡

 ከኮንስትራክሽን ነባራዊ ሁኔታ የSafety profession በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢሰጥ


ስላለው ጠቀሜታ

ሠንጠረዥ 3-11፡ ደህንነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቢሰጥ ያለው አስተዋጽኦ


ተቋራጭ አሰሪው መስሪያቤት አማካሪ ሰራተኛው

የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ


መጠን ስሌት መጠን መጠን ስሌት መጠን ስሌት

ከፍተኛ 180 82.9 22 91.7 29 93.5 336 84.4

መካከለኛ 31 14.3 2 8.3 1 3.2 49 12.3

ዝቅተኛ 6 2.8 0 0.0 1 3.2 12 3.0

ምላሽ ያልሰጡ 0 0.0 0 0.0 0 0.0 1 .3

ጠቅለላ 217 100.0 24 100.0 31 100.0 398 100.0

61
አሁን ካለዉ የሃገራችን ኮንስትራክሽን ነባራዊ ሁኔታ Safety professional እንደ አንድ
አይነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢሰጥ ያለው ጠቀሜታ ለሚለው ተቋራጭ፣ የግንባታ
ባለቤት፣ አማካሪ እንዲሁም የግንባታ ሰራተኛ በአማካይ 88 በከፍተኛ ደረጃ ጠቀሜታ እንዳለው
አመላክተዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ለኢንዱስትሪዉ በሴፍቲ ሙያ የተመረቀ ባለሙያ በጣም
አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን በአብዛኛው የግንባታ ቦታ የሴፍቲ ባለሙያ ተብሎ ይህንን
ጉዳይ የሚከታተል የለም በተመሳሳይ ይህንን በተግባር ሊያከናዉኑ የሞከሩት በቁጥር እጅግ
ኣናሳ የሆኑ ተቋማትም በዘርፉ የተመረቀ ባለሙያ ገበያ ላይ የማግኘት ሁኔታ አስቸጋሪ
ሆኖባቸዋል፡፡ በቁጥር እጅግ ዉስን በሆኑ የግንባታ ቦታዎች እንደ ደህንነት ባለሙያ ሆነዉ
ቢሰሩም የራሳቸውን ስራ ወደጎን በመተው በሌሎች ሙያዎች የመሳብ አዝማምያ ስለሚየሳዩ
ዉጤቱ እንደተፈለገው አይደለም፡፡ በመሆኑም እነዚህንና መሰል ችግሮች ከመቅረፍ አንጻር
የSafety professional እንደ አንድ የሙያ ዘርፍ በከፍተኛ የትምህርት ተቋምት ቢሰጥ
ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡

3.1.2. ከመንገድ ፕሮጀክቶች የተገኙ መጠይቆች ትንታኔ

ከደህንነት አስተዳደር (safety management) አንፃር


 የግንባታ ደህንነት (Safety and healthy) ህግ

ምስል 3-16፡ ስለ ግንባታ ደህንነት የተጻፈ ህግ ስለመኖሩ

ስለግንባታ ደህንነት (Safety and healthy) የተፃፈ ህግ አለው ወይ ለሚለው አማካሪ 46%
ተቋራጭ 71% እንዲሁም ባለቤት 30% አለ ሲሉ አማካሪ 55% ተቋራጭ 29% እንዲሁም
ባለቤት 50% የተፃፈ ህግ አለመኖሩን ገልጸዋል፡፡ ይህም የሚያመለክተው በተቋራጭ በኩል

62
የተሻለ የህግ ግንዛቤ መኖሩን እንዲሁም በግንባታ ባለቤት በኩል ግማሽ የሚሆኑት ስለህጉ
መኖር እውቀት የሌላቸው ሲሆኑ 20% የሆኑት ደግሞ ህጉ መኖሩና አለመኖሩ የማያውቁት
ናቸው፡፡ በጥናት ቡድኑ በኩል በቃለመጠይቅና በትኩረት ዉይይት ለማየት እንደሞከረው
አብዛኛው ህግ መኖሩን የማያዉቁ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ ህጉ ቢኖሩም ተግባራዊ
አለመደረጉን ገልፀዋል፡፡

 ሴፍቲን በተመለከተ ያለው የውል ስምምነት ሁኔታ


ሠንጠረዥ 3-12፡ ደህንነት በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ
አማካሪ ተቋራጭ ባለቤት
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
ስሌት
መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን
አዎ 11 100.0 16 94.1 10 100.0
አላምንበትም 0 0 1 5.9 0 0
መልስ ያልሰጡ 0 0 0 0 0 0
ጠቅላላ 11 100.0 17 100.0 10 100.0

የስራ ደህንነት (Safety) የውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ መካተት አለበት ወይ ለሚለው
አማካሪ፣ ተቋራጭ፣ እንዲሁም የግንባታ ባለቤት በአማካይ 98% በዉል ስምምነት መካተት
አለበት ብለው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም መረዳት እንደሚቻለው ሁሉም ስራው
የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች (Safety) በዉል ስምምነት መካተት እንዳበት ቢያምኑም እንኳን
በተግባር ግን እየተሰራበት አለመሆኑን ባደረግነው ዉይይት እንዲሁም በቃለ መጠይቅ
ለመገንዘብ ችለናል፡፡

63
 ለግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) የሚወጣ ወጪ (በcontract agreement)
የሚካተትበት ሁኔታ በተመለከተ

ምስል 3-17፡ ለደህንነት የሚወጣው ወጪ በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ ስለመካተቱ

ለግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) የሚወጣ ወጪ (በcontract agreement)


ይካተታል ወይ ለሚለው በአማካሪው በኩል 82% እንደማይካተት ሲያሳይ ነገር ግን ተቋራጭ
እና በግንባታ ባለቤት በአማካይ 30% አይካተትም በማለት መልሰዋል፡፡ ይህም የሚያመለክተው
በአንደ አይነት ሃሳብ ላይ የተለያየ አስተያየት መኖሩን ነው፡፡ ከላይ በግራፉ እንደተቀመጠው
ቢያምኑበትም በተግባር እየተሰራበት አለመሆኑን በአንድነት የተስማሙበት ሲሆን ወጭው
ተካቷል የሚለው ከዚህ ሀሳብ ጋር የሚጋጭ መሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም የግንባታው አማካሪ
እንዲሁም የጥናት ቡድኑ ባደረገው የትኩረት ቡድን ውይይት እንዳስተዋልነው ራሱን ችሎ
ለደህንነት (Safety) ተብሎ በአይተም (unite price) ደረጃ የተቀመጠ ዋጋ አለመኖሩ
ለቁጥጥርም ሆነ እርምጃ ለመውሰድ አስቸጋሪ በመሆኑ ተግባራዊም አለመደረጉን ተገንዝበናል፡፡
ስለ ደህንነት ህጎች (work zone Safety laws)

64
 ስለግንባታ አካባቢ ደህንነት (work zone Safety) ያለዉ እውቀት

ሰnጠረዥ 3-13፡ ስለ ግንባታ ደህንነት ያለው ግንዛቤ


አማካሪ ተቋራጭ ባለቤት ሠራተኛ
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
ስሌት ስሌት
መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን መጠን
አዎ 11 100.0 17 100.0 10 100.0 48 63.2
አላውቅም 0 0 0 0 0 0 28 36.8
ምላሽ ያልሰጡ 0 0 0 0 0 0 0 0
ጠቅላላ 11 100.0 17 100.0 10 100.0 76 100.0

ስለ ግንባታ አካባቢ ደህንነት (work zone Safety) ከዚህ በፊት ያውቃሉ ወይ ለሚለው
አማካሪ፣ የስራ ተቋራጭ እና የግንባታ ባለቤት 100% እንደሚያዉቁ ሲገልጹ ነገር ግን
የግንባታ ሰራተኛ 63% አዎ በማለት መልሰዋል፡፡ ይህም የስራው ቁልፍ ተዋናኞች ሙሉ
ለሙሉ ስለ ደህንነት (Safety) ከዚህ በፊት ግንዛቤው እንዳላቸው ነገር ግን በዋናነት ስራውን
የሚያከናውነው የጉልበት ሰራተኛው የእውቀት ማነስ እንዳለበት ያመላክታል፡፡ እንደአጠቃላይ
ከጉልበት ሰራተኛ ውጭ የግንዛቤ ማነስ ሳይሆን ትኩረት ያለመስጠት ጉዳይ መሆኑን ባደረገነው
ውይይት ለመረዳት ችለናል፡

 በሀገራችን ከ Safety ጋር ተያያዥነት ያለው ህግ/አዋጅ/ደንብ/ በተመለከተ

ሠንጠረዝ 3-14፡ ደህንነት የተመለከቱ ህጎች/ደንቦች/አዋጆች


አማካሪ ተቋራጭ ባለቤት
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
ስሌት
መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን
አዎ 2 18.2 1 5.9 4 40.0
አላውቅም 9 81.8 16 94.1 6 60.0
ምላሽ ያልሰጡ 0 0 0 0 0 0
ጠቅላላ 11 100.0 17 100.0 10 100.0

በሀገራችን ከደህንነት (Safety) ጋር ተያያዥነት ያለው ህግ/አዋጅ/ደንብ/ካለ ቢጠቅሱ ለሚለው


አማካሪ፣ ተቋራጭ እንዲሁም የግንባታ ባለቤት በአማካይ 79% አናውቅም በማለት መልስ
ሰጥተወል፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቻለው ምንም እንኳን በሀገራችን በተጨባጭ ከግንባታ

65
ደህንነት ጋር የተያያዙ ህግና ደንቦች ቢኖሩም በኢንዱስትሪው ተዋናኞች ግን ህግና ደንቦችን
መኖራቸዉን የማያውቀው ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል፡፡ ባደረግነው ውይይትም የተረዳነው
ይህንኑ ነው፡፡
የህግ/አዋጅ/ደንብ/ ተፈፃሚነት

ምስል 3-18፡ የህግ/ደንብ/አዋጅ ተፈጻሚነት

ያለው ህግ/አዋጅ/ደንብ/ በአግባቡ ተፈፃሚ ነው ለሚለው በአማካሪ 63% ዝቅተኛ ተፈጻሚነት


እንዳለው ሲገልጹ፣ ተቋራጭ 24% ተፈጻሚ አለመሆኑን ሲገልጹ 47% ደግሞ መልስ
ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ እንዲሁም የግንባታ ባለቤት የተሰጠው ምላሽ ደግሞ 50%ህጉ
ተፈጻሚ መሆኑ ገልጸዉ 50% መልስ አልሰጡም፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቻለው በቅድሚያ ህጉ
መኖሩን ባለማወቃቸው በተፈፃሚነቱ ላይ ለመናገር የሚያስችል እውቀት አለመኖራቸውን
ሲሆን እኛም ከውይይቱ እንደተረዳነው በቁጥር እጅግ አናሳ የሆኑ ሕጉ መኖሩን የሚያውቁት
እንኳን ህጉ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ችግር እንዳለ ገልፀዋል፡፡

66
ስለ ደህንነት ዕቃዎችና ምልክቶች (safety equipment, signs and signals)
 የጥንቃቄ ዕቃዎችን ስለመሟላታቸው

ምሰል 3-19፡ የደህንነት ዕቃዎች ስለመሟላታቸው

ድርጅቱ ለሰራተኞቹ የጥንቃቄ ዕቃዎችን አሟልቷል ወይ ለሚለው አማካሪው 73%


እንዳልተሟላ ሲገልጹ በስራ ተቋራጭ ግን 82% አሟልተናል ብለዋል፡፡ ነገር ግን ሁለቱ
ባለድርሻ አካላት የሰጡት ምላሽ እርስ በራሱ የሚጋጭ ሲሆን በተጨባጭ ባደረግነው የመስክ
ምልከታ እንዲሁም የትኩረት ቡድን ዉይይት እንደተገነዘብነው የደህንነት እቃዎችና የቅድመ
ጥንቃቄ ምልክቶች ሙሉ ለሙሉ አለመሟላታቸውን ነው፡፡ቢሆንም ከህንጻ ግንባታ የተሻለ
ሁኔታ መኖሩ ይስተዋላል፡፡
 የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና(First aid)

ሠንጠረዥ 3-15፡ ስለ መጀመሪያ ደረጃ የህክምና መስጫ


ተቋራጭ ሠራተኛ
የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት
አለ 13 76.5 43 56.6
የለም 4 23.5 33 43.4
ምላሽ ያልሰጡ 0 0 0 0
ጠቅላላ 17 100.0 76 100.0

67
በግንባታ ቦታ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና (First aid) አለ ወይ ለሚለው በተቋራጭ 77%
እንዳለ ሲገልጹ በግንባታ ሰራተኛ በኩል ግን ምንም እንኳን 57% እንዳለ ቢገልጹም ከሱ
ባልተናነሰ 43% አለመኖሩን በማስመልከት መልሰዋል፡፡ በግንባታ ሰራተኞች እንደተገለጸው
የስራ ተቋራጩ አሟልቻለሁ ቢልም ሁሉም ሰራተኛ ምቹና ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል
መልኩ አለመሆኑ ነው፡፡ በዉይይት ያስተዋልነውም ይህንኑ ነው፡፡ የህንጻ ግንባታ ከመንገድ
ግንባታ አንጻር ሲታይ በተሻለ መልኩ የመጀመርያ ደረጃ የህክምና እርዳታ አሰጣጥ ያለው
ሲሆን በመንገድ ግንባታ ላይ ያለው ከስራው ባህሪው የተነሳ የግንባታ ቦታው ከጊዜያዊ ግንባታ
ፅ/ቤት (project office) የራቀ መሆኑ በተጠቃሚዎች ላይ ምቹ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡
 የተሟሉ የደህንነት ዕቃዎች

ምስል 3-20፡ የተሟሉ የደህንነት እቃዎች

የተሟሉ የደህንነት ዕቃዎች የትኞቹ እንደሆኑ ሲጠቅሱ በሁሉም ወገን አንጻባራቂ ልብስ
በአንደኛ ደረጃ ሲያስቀምጡ ቀጥሎ የእጅ ጓንት፣ በሶስተኛ ደረጃ ሄልሜት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሌሎቹ አልፎ አልፎና በከፊል እንደሚሟላ አመላክተዋል፡፡በመስክ ምልከታ እንደተመለከትነው
በአብዛኛው ቦታ አንጸባራቂ በተሻለ መልኩ ይገኛል፡፡

68
ስለ ደህንነት ባለሙያ (safety officer)

 ማንኛውም ጎብኝ ወደ ግንባታ ቦታ (construction site) በሚመጣበት ጌዜ ስላለው ቅድመ

ጥንቃቄ

ሠንጠረዥ 3-16፡ ለጎብኚ ስለሚደረገው ቅድመ ጥንቃቄ


አማካሪ ተቋራጭ
የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት
መጠን መጠን
አለ 5 45.5 9 52.9
የለም 6 54.5 6 35.3
ምላሽ ያልሰጡ 0 0 2 11.8
ጠቅላላ 11 100.0 17 100.0

ማንኛውም ጎብኝ ወደ ግንባታ ቦታ (construction site) በሚመጣበት ጊዜ ቅድመ ጥንቃቄ


እንዲያደርግ ተቋሙ ያለው የአሰራር ሁኔታ አለ ወይ ለሚለው በአማካሪ 55% በተቋራጭ
35% የለም ሲሉ በአንጻሩ ግን 53% አለ ብሎ መልሰዋል፡፡ ከዚህም መረዳት እንደሚቻለው
ሁለቱም ስለአንድ የስራ ቦታ የተለያየ ምላሽ መስጠታቸው በጉዳዩ ዙርያ ችግር መኖሩን
ያሳያል፡፡ ባደረግነው ዉይይት እንደተረዳነው ለአደጋ አጋላጭ የሆኑ ስራዎች በሚከናወኑበት
ጊዜ በመገናኛብዙሀን እስከማስነገር እንዲሁም የተለያዩ የቅድመ ጥንቃቄ ምልክቶችን
እንደየአስፈላጊነታቸው ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ተረድተናል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች
የህዝብንና የሃገር ሃብትን እንደራሳቸው በማይቆጥሩ አካላት ያለአግባብ እንደሚሰረቁ
ገልጸዋል፡፡ በመስክ መልከታችንም ያስተዋልነው በቂ የሆኑ የደህንነት ምልክቶች
አለመኖራቸዉን ነው፡፡

69
 በግንባታ አካባቢ አስፈላጊው የደህንነት ጥንቃቄ ባለመደረጉ ምክንያት አደጋ ሲያጋጥም
ያለው የሪፖርት አደራረግን በተመለከተ

ምስል 3-21፡ አደጋ ሲያጋጥም ሪፖርት ስለመደረጉ

በግንባታ አካባቢ አስፈላጊው የደህንነት ጥንቃቄ ባለመደረጉ ምክንያት አደጋ ሲያጋጥም


ሪፖርት ይደረጋል ወይ ለሚለው በአማካሪና በስራ ተቋራጭ በአማካይ 83% አዎ በማለት
መልስ ሰጥተዋል፡፡ነገር ግን የግንባታ ሰራተኛው 54% ያክል ብቻ ሪፖርት እንደሚደረግ
ገልጸዋል፡፡ ይህም የሚሳየው ለአደጋ ተጋላጭ የሆነው አካል የሪፖርት አደራረግ ስርአቱ
አነስተኛ እንደሆነ ቢያመላክትም በአማካሪና በተቋራጭ በኩል ያለው ምላሽ ከዚህ የተለየ ነው፡፡
በተጨማሪም ባደረግነው ዉይይት እንዳስተዋልነው በመንገድ ግንባታ ስራ በተደራጀ መልኩ
ባይሆንም ሪፖርት መደረጉ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ከህንጻ ግንባታ በተሻለ መልኩ ሪፖርት
የመደረግ ጅማሮ እንዳለው ተገንዝበናል፡፡

70
 አጠቃላይ ከደህንነት (Safety) ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስራዎች የሚያከነውን Safety

professional ባለሙያ ስለመኖር

Safety professional ባለሙያ


100
81.8
80
64.7
የመቶኛ ስሌት

60 50 አለ
40 የለም
40
መልስ ያልሰጡ
23.5
18.2
20 11.8 10
0
0
አማካሪ ተቋራጭ ባለቤት

ምስል 3-22፡ የደህንነት ባለሙያ ስለመኖሩ

በተቋምዎ በግንባታ ቦታም ሆነ በኦፊስ ደረጃ አጠቃላይ ከደህንነት (Safety) ጋር ተያያዥነት


ያላቸውን ስራዎች የሚያከናውን የደህንነት ባለሙያ (Safety professional) አለ ወይ
ለሚለው አማካሪ፣ ስራ ተቋራጭ፣ የግንባታ ባለቤት እንዲሁም የግንባታ ሰራተኛ በአማካይ
68% የደህንነት ባለሙያ እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ ይህም የሚያስረዳው በሁሉም የግንባታ ባለድርሻ
አካላት በደህንነት (Safety) የተመረቀና ለዚሁ ስራ ተብሎ የተመደበ ባለሙያ አለመኖሩን
ሲሆን ባደረግነውም ዉይይት ጭምር ይህንኑ ማስተዋል ችለናል፡፡
 የደህንነት መከላከያ (Safety) አልባሳት ደረጃውን (standard) የጠበቁ ስለመሆናቸው
ሠንጠረዥ 3-17፡ የደህንነት አልባሳት ደረጃቸውን ስለመጠበቃቸው
አማካሪ ተቋራጭ
የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት
አለ 1 9.1 7 41.2
የለም 10 90.9 10 58.8
ምላሽ ያልሰጡ 0 0 0 0
ጠቅላላ 11 100.0 17 100.0

ለሰራተኞች የደህንነት መከላከያ (Safety) አልባሳት ተብሎ የሚጠቀምባቸው ደረጃውን የጠበቁ


(standard) መሆናቸውን የሚያረጋግጥ አካል አለ ለሚለው አማካሪ 91% እንዲሁም ተቋራጭ

71
59% የለም ብለዋል፡፡ በአማካሪው የተሰጠው ጥራታቸው የሚያረጋግጥ አካል አለመኖሩ ከስራ
ተቋራጭ ከተሰጠው ምላሽ አንጻር ከፍተኛ መሆኑ የቁጥጥር ስርአቱ ልልና ደካማነቱን ያሳያል
፡፡
 በsafety ጉድለት አደጋ ሲያጋጥመው ስላለው ተጠያቂነት

በsafety ጉድለት አደጋ ሲያጋጥመው ስላለው


ተጠያቂነት
100
84.2
76.5
80
የመቶኛ ስሌት

60
60 ሰራተኛው
40 አሰሪው መስሪያቤት
40
ተቋራጭ
20 11.811.8 9.2 6.6
0
0
ተቋራጭ ባለቤት ሰራተኛው

ምስል 3-23፡ ብቁ ባልሆኑ ሰራተኞች የተፈጠሩ አደጋዎች

አንድ ሰራተኛ በsafety ጉድለት አደጋ ሲያጋጥመው ተጠያቂው አካል ማን ነው ለሚለው


ተቋራጭ፣ የግንባታ ባለቤት እንዲሁም ሰራተኛው በአማካይ 74% ተቋራጭ ተጠያቂ መሆኑ
አመላክተዋል፡፡ የህግ ማእቀፉም በስራ ላይ ለሚደርሰው አደጋ ተጠያቂው አሰሪው አካል መሆኑ
በግልጽ ቢያስቀምጥም ተቋራጩ ግን የተጣለበትን ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አለመሆኑን
ባደረግነው ዉይይት ተገንዝበናል፡፡

72
 ሰአት እላፊና ትራፊክ ፍሰት በሚበዛበት የሚከናወኑ ስራዎች ለአደጋ መፈጠር ያላቸው
አስተዋጸኦ
ሠንጠረዥ 3-18፡ ሰዓት እላፊና የትrፊክ ፍሰት ለአደጋ መፈጠር ያላቸው አስተዋጽኦ

ተቋራጭ ሰራተኛው
የድግግሽ የመቶኛ የድግግሽ የመቶኛ
መጠን ሰስሌት መጠን ሰስሌት
14 82.4 25 32.9
ከፍተኛ
2 11.8 36 47.4
መካከለኛ
1 5.9 13 17.1
ዝቅተኛ
0 0 2 2.6
ምላሽ ያልሰጡ
17 100.0 76 100
ጠቅለላ

ሰአት እላፊና ትራፊክ ፍሰት በሚበዛበት ሰአት የሚከናውኑ ስራዎች ለአደጋ መፈጠር ያለው
አስተዋፅኦ ምን ያህል እንደሆነ ሲያስቀምጡ ተቋራጭ 82% ከፍተኛ መሆኑ ሲገልጹ ሰራተኛው
ደግሞ 47%ቱ መካከለኛ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ በቀኑ የስራ ሰአት
የመንገድ ግንባታ ማከናወን አስቸጋሪ በመሆኑ በአብዛኛው የምሽትን ሰአት ለግንባታ ስራ
ማዋል በሰፊው የተለመደ ነው፡፡ይህም ለአደጋ መፈጠር አስተዋጽኦ ከሚያደርጉት ዉስጥ
በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡ በትኩረት ቡድን ዉይይት እንደተገለጸው በምሽት ለሚከናወኑ
ስራዎች አደጋ ለመቀነስ ሰራተኞችን በፈረቃ የማሰራት ሁኔታ መኖሩን ተገንዝበናል፡፡
 የደህንነት (Safety) ምልክቶችን ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎች

ሰንጠረዥ 3-19፡ ደህንነት ምልክቶችን ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎች

ሰራተኛው ተቋራጭ
የድግግሞሽ የመቶኛ ሰስሌት የድግግሞሽ የመቶኛ ሰስሌት
መጠን መጠን

አዎ 29 38.2 11 64.7

የለም 45 59.2 6 35.3

ምላሽ ያልሰጡ 2 2.6 0 0

ጠቅላላ 76 100.0 17 100

73
አስፈላጊ የሆኑ የደህንነት (Safety) ምልክቶችን በአግባቡ ባለማስቀመጥ የተፈጠሩ አደጋዎች
እንዳሉ ለቀረበው ጥያቄ ሰራተኛው 59% የለም ሲሉ በተቋራጩ በኩል ግን 65% መኖሩን
ያሳያል፡፡ ለዚህም ተቋራጩ እንደምክንያትነት ያስቀመጠው አስፈላጊ የደህንነት ምልክቶች
በተለያዩ አካላት መወሰዳቸውና በጉልበት ሰራተኛው በቂ ግንዛቤ ባለመኖሩ ከጥንቃቄ ጉድለት
የተነሳ መሆኑ ነው፡፡
 በመጠጥ ወይም ለስራ ብቁ ሳይሆኑ ስራ በማከናወናቸው የተፈጠረ አደጋ

ምስል 3-24፡ ብቁ ባልሆኑ ሰራተኞች የተፈጠሩ አደጋዎች

ከላይ በግራ እንደሚታየው ሰራተኞች ጠጥተው ወይም ለስራ ብቁ ሳይሆኑ ስራቸውን


በማከናወናቸው ተቋራጭ 77% አደጋ አለመከሰቱ ምላሽ ሸጥተዋል፡፡ ይህም የሚያመለክተው
ሰራተኞች ጠጥተው ወይም ለስራ ብቁ ሳይሆኑ ወደስራ አለመሰማራታቸውን ነው፡፡ ሰራተኛው
ደግሞ 53% ጠጥተው ወይም ለስራ ብቁ ሳይሆኑ ስራቸውን እንዳያከናዉኑ አስገዳጅ የሆነ ህግ
አለመኖሩን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቻለው ምንም እንኳን አስገዳጅ የሆነ ህግ
በተሟላ መልኩ አለመኖሩን የግንባታ ሰራተኞች ቢገልጹም በተቋራጩ በኩል
እንደሚያመለክተው ብዙ የደረሱ አደጋዎች አለመኖራቸውን ነው፡፡ይህንንም በዉይይት ወቅት
ለመረዳት ችለናል፡፡

74
 በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች

ምስል 3-25፡ በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች

ግንባታ ቦታ ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሱ የአደጋ አይነቶች የትኞቹ ናቸው ለሚለው


በተቋራጩ እንዲሁም በሰራተኛው ከላይ በሚወድቁ እቃዎች መጀመርያ ደረጃ ሲሆን፤
በሁለተኛ ደረጃ ለግንባታ በሚጠቀሙበት ማሽን ምክንያት የሚለውን አስቀምጠዋል፡፡
የደህንነት ምልክት ባለማስቀመጥ ምክንያት ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ መሆኑ ተገልጽዋል፡፡ ምንም
እንኳን ለቀረበው ጥያቄ በአማራጭነት ይህ መልስ ቢሰጥም በመንገድ ግንባታ ምክንያት
በተደጋጋሚ የሚደርሱ አደጋዎች ከኳሪ ሳይት ግብአት ከተወሰደ በኋላ ቦታውን ቀድሞ ወደ
ነበረበት ባለመመለስ፣ በኢንስፕክሽን ወይም ክዳናቸው በጠፉ ማንሆሎች፣ በጎርፍ፣ በማሽን
ስራላይና ጥገና (machine operation and maintenance) ወቅት የሚደርሱ አደጋዎች
መሆናቸውን በቀደም ተከተል ባደረግነው ዉይይት ተገንዝበናል፡፡

75
በግንባታ ስፍራ ለደህንነት አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች

ተቋራጭ

12%

አዎ
አይደለም

88%

ምስል 3-26፡ አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች ስለመለየታቸው

በግንባታ ስፍራ ለደህንነት አስጊ የሆኑ የስራ አይነቶች በግልፅ ተለይተዋል ለሚለው 88% አዎ
የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የአደጋ መንስኤዎች ከህንጻ ግንባታ በተሻለ መልኩ በቅድምያ
ተለይተው አስፈላጊው ጥንቃቄ እንደሚደረግባቸው ያመለክታል፡፡ ነገር ግን ባደረግነው ዉይይት
በተጨባጭ ያስተዋልነው ሪስክ አሳስመንት (risk assessment) ቀድሞ ሰርቶ ወደ ፕሮጀክት
የሚገባ ተቋራጭ በቁጥር እጅግ አናሳ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡
 በዋናነት የሚጠቀሱ የአደጋ መንስኤዎች

? ? ? ? ? ?? ? ? ? ? ?
? ? ? ? ??

12% ?? ???? ?? ? ? ? ?? ? ? ?
19%
12%
? ? ?? ?? ? ? ??? ? ?? ? ? ??
20%
19% ? ? ?? ? ? ?? ? ? ?
18%
? ?? ? ? ? ? ? ? ? ? ? ? ?
? ??

ምሰል 3-27፡ በዋናነት የሚጠቀሱ የአደጋ መንስኤዎች

76
ግንባታ ቦታ ላይ ለሚፈጠሩ አደጋዎች በዋናነት የሚጠቀሱ መንስኤዎች የትኞቹ እንደሆኑ
ለተጠየቀው የደህንነት እቃዎች አለመሟላት የመጀመርያ ደረጃ ሲሆን ቸልተኝነት በሁለተኛ
እንዲሁም ምቹ ያልሆነ የሰራ ቦታና ስለ ስራ ቦታ ደህንነት ግንዛቤ ማነስ በሶሰተኛነት
ተጠቅሰዋል፡፡ ብዙ ወጪ የማይጠይቅ ነገር ግን አደጋ ከተከሰተ በኋላ የሚያስከትለዉን ተጽእኖ
በቀላሉ መታደግ ሲቻል አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ግን ይህ እየተተገበረ አይደለም፡፡
 አንድ ስራ በታቀደለት ጊዜ፣ ወጪ እና ጥራት ለማጠናቀቅ የግንባታ ቦታ ደህንነትን
(work zone Safety) ያለው አስተዋፅኦ

ሠንጠረዥ 3-20፡ የግንባታ ደህንነት ለሥራው ያለው አስተዋጽኦ


ተቋራጭ አሰሪው መስሪያቤት አማካሪ ሰራተኛው
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
መጠን ሰስሌት መጠን ሰስሌት ሽ መጠን ሰስሌት መጠን ሰስሌት
12 70.6 6 60.0 9 81.8 40 52.6
ከፍተኛ
5 29.4 1 10.0 2 18.2 20 26.3
መካከለኛ
0 0.0 3 30.0 0 0.0 9 11.8
ዝቅተኛ
0 0.0 0 0.0 0 0.0 7 9.2
ምላሽ ያልሰጡ
17 100.0 10 100.0 11 100.0 76 100.0
ጠቅለላ

አንድ ስራ በታቀደለት ጊዜ፣ ወጪ እና ጥራት ለማጠናቀቅ የግንባታ ቦታ ደህንነትን (work


zone Safety) መተግበር ያለው አስተዋፅኦ ምን ይመስላል ለሚለው ተቋራጭ፣ በግንባታ
ባለቤት፣ አማካሪ እንዲሁም የግንባታ ሰራተኛ በአማካይ 66% ከፍተኛ ብለው መልስ
ሰጥተዋል፡፡ይህ የሚያመለክተው አንድን ፐሮጀክት በተሳካ መልኩ ለማከናወን የግንባታ
ደህንነት (Safety) ተግባራዊ ማድረግ ከማኛዉም በፊት ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ነው፡፡ነገር
ግን ይህንን ባለማድረጋቸው ላልታሰበና ለከፍተኛ ወጪ እንዲሁም በሰራተኞቹ ላይ የስራ ላይ
ስጋት ተጽእኖ በማሳደር የስራ ቦታው ጤናማ እንዳይሆን ከማድረጉም ባሻገር በጊዜ ሰሌዳው
መሰረት እንዳይጠናቀቅ ትልቅ እንቅፋት ይሆናል፡፡ ይህም እንደአጠቃላይ ሲታይ በግንባታ ዘርፉ
ዉጤታማነትን ይቀንሳል፡፡

77
 ከኮንስትራክሽን ነባራዊ ሁኔታ የSafety profession በከፍተኛ የትምህርት ተቋም
ቢሰጥ ስላለው ጠቀሜታ
ሠንጠረዥ 3-21፡ ደህንነት በከፍተና የትምህርት ተቋማት ውስጥ ቢሰጥ ያለው ጠቀሜታ
ተቋራጭ አሰሪው መስሪያቤት አማካሪ ሰራተኛው
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ሰስሌት መጠን ስሌት
ከፍተኛ 11 64.7 9 81.8 7 70.0 64 84.2
መካከለኛ 10 35.3 2 18.2 3 30.0 6 7.9
ዝቅተኛ 0 0.0 0 0.0 0 0.0 3 3.9
ምላሽ ያልሰጡ 0 0.0 0 0.0 0 0.0 3 3.9
ጠቅለላ 17 100.0 11 100.0 10 100.0 76 100.0

አሁን ካለዉ የሃገራችን ኮንስትራክሽን ነባራዊ ሁኔታ Safety professional እንደ አንድ
የትምህርት አይነት በከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢሰጥ ያለው ጠቀሜታ ለሚለው
ተቋራጭ፣ የግንባታ ባለቤት፣ አማካሪ እንዲሁም ሰራተኛ በአማካይ 75% በከፍተኛ ደረጃ
ጠቀሜታ እንዳለው አመላክተዋል፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቸለው የSafety profession
መኖር አሁን ያለውን የስራ ላይ አደጋ ከመቀነሱም ባሻገር የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን
የላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለው ሚና በቀላሉ የሚታይ አለመሆኑን ነው፡፡
 የአደጋዎች መቀነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ያለው አስተዋፅኦ

ሠንጠረዥ 3-22፡ የአደጋዎች መቀነስ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው አስተዋጽኦ


ተቋራጭ አሰሪው መስሪያቤት አማካሪ ሰራተኛው
የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ
መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ስሌት መጠን ስሌት
14 82.4 7 70.0 6 54.5 61 80.3
ከፍተኛ
1 5.9 2 20.0 3 27.3 7 9.2
መካከለኛ
2 11.8 0 0.0 1 9.1 5 6.6
ዝቅተኛ
0 0.0 1 10.0 1 9.1 3 3.9
ምላሽ ያልሰጡ
17 100.0 10 100.0 11 100.0 76 100.0
ጠቅለላ

በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎች መቀነስ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ


ያለው አስተዋፅኦ ምን ያክል ነው ለሚለው ተቋራጭ፣ የግንባታ ባለቤት፣ አማካሪ እንዲሁም
ሰራተኛ በአማካይ 72% ከፍተኛ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ እንደአጠቃላይ በግንባታ ባለድርሻ አካላት

78
የተሰጠው ምላሽ የሚያሳየው አስፈላጊዉን ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ አደጋ በሚከሰት ወቅት
የሚወጣን ወጪ እንዲሁም ተተኪ ያልሆነውን የሰው ልጅ ሕይወት በማትረፍ በሃገራችን
የኢኮኖሚ እድገት ላይ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ አገራችን
ወደተሻለ ደረጃ እንድትራመድ ያደርጋል፡፡ ባደረግነዉም ዉይይት ያስተዋልነው ይህንኑ ነው፡፡
 ስለግንባታ ቦታ ደህንነት ስልጠና (training) በቋሚነት ስልጠና ስለመሰጠት

ምስል 3-28፡ ስልጠና በቋሚነት ስለመሰጠቱ

ስለስራ ቦታ ደህንነት ከአሰሪ መስሪያ ቤትዎ ተገቢው ስልጠና (training) በቋሚነት ይሰጣል
ለሚለው ሰራተኛው፣ ተቋራጭ እንዲሁም አማካሪ በአማካይ 77% አይሰጥም በማለት
መልሰዋል፡፡ ሁሉም የግንባታው ባለድርሻ አካላት ስልጠና በመሰጠት ዙርያ ያለው የአሰራር
ስርኣት ዝቅተኛ መሆኑን አምነዉበታል፡፡ ይህ መሆኑ በግንባታ ቦታ ላይ የግንባታ ሰራተኛው
በየጊዜው የሚቀያየርበት፣ አብዛኛው ማንበብ አለመቻሉ እንዲሁም የሚቀመጡ የቅድመ
ጥንቃቄ ምልክቶችም ሆነ የአሰራር ማንዋሎችን አለመረዳቱ ስለደህንነት ስልጠና ካለመሰጠቱ
ጋር ተዳምሮ በግንባታ ቦታ ላይ የሚደርሰዉን አደጋ የከፋ ያደርገዋል፡፡

79
 ስራ (project) ተጠናቆ በርክክብ ወቅት ከሴፍቲ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስራዎች
ስለመጠናቀቃቸው

ሠንጠረዥ 3-23፡ በርክክብ ወቅት ከደህንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሥራዎች ስለመጠናቀቃቸው

አሰሪው መስሪያቤት ተቋራጭ አማካሪ

የድግግሞሽ የመቶኛ ሰስሌት የድግግሞሽ የመቶኛ የድግግሞሽ የመቶኛ


መጠን መጠን ስሌት መጠን ስሌት

አዎ 1 10.0 7 41.2 8 72.7


አይደለም 7 70.0 9 52.9 3 27.3
ምላሽ ያልሰጡ 2 20.0 1 5.9 0 0.0
ጠቅላላ 10 100.0 17 100.0 11 100.0

አንድ ስራ ተቋራጭ አንድን ስራ (project) አጠናቆ በሚያስረክብበት ጊዜ ከሴፍቲ ጋር ተያያዥ


የሆኑ ስራዎች በሚገባ መጠናቀቃቸው ይታያል ወይ ለሚለው ግንባታ ባለቤት 70%፣
ተቋራጭ 53% እንደማይታይ ሲጠቅሱ ነገር ግን አማካሪ 73% ሳይጠናቀቅ እንደማይረከብ
ገልጸዋል፡፡በትኩረት ቡድን ዉይይትም እንደተገለጸው የመንገድ ባለስልጣን መ/ቤቱ ማንኛዉም
በዉል ስምምነት ዉስጥ ያለ ስራ ሳይጠናቀቅ ርክክብ እንደማያደርጉ በአፅንኦት አስረድተዋል፡፡
ነገር ግን አስገዳጅ በሆነ መልኩ መንገዱ ለተጠቃሚ ክፍት እንዲሆን በሚታዘዙበት ጊዜ
መንገዱ ተረክቦ ቀሪ ስራዎች ጎን በጎን የሚሰሩበት ሁኔታ መኖሩን ተረድተናል፡፡
 በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ስለማበረታት

ሠንጠረዥ 3-24፡ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ የሚበረታቱበት ሁኔታ

አሰሪው መስሪያቤት ተቋራጭ አማካሪ

የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት የድግግሞሽ የመቶኛ ስሌት


መጠን መጠን መጠን

አዎ 1 10.0 8 47.1 0 0.0


አይደለም 7 70.0 8 47 11 100.0
ምላሽ ያልሰጡ 2 20.0 1 5.9 0 0.0
ጠቅላላ 10 100.0 17 100.0 11 100.0

በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ የሚበረታቱበት ሁኔታ
አለ ወይ ለሚለው 47% የሚሆኑት ተቋራጮች በስራ የተሻለ አፈጻጸም ያሳዩ ሰራተኞችን

80
እንደሚያበራታቱ ሲገልፁ አሰሪው መስሪያቤትና አማካሪው በአማካይ 85% የማበረታቻ
ስርአት እንደሌለ ገልፀዋል፡፡ በመሆኑም የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው በስራቸው የተለያዩ ጥቅማ
ጥቅሞችን የማያገኙ ከሆነ እንዲሁም በተደጋጋሚ በደህንነት ዙሪያ የአሰራር ስርአት
የሌላቸውና በዚህም ምክንያት ብዙ ጊዜ አደጋ የሚያደርሱ ተቋማት አስፈላጊው እርምጀ
የማይወሰድባቸው ከሆነ በግንባታ ዙሪያ ላይ የሚደርሱ አደጋዎች መባባስ ከፍተኛ ምክንያት
እንደሚሆን ባደረግነው ዉይይት ተረድተናል፡፡

 በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) ምክንያት ስለሚፈጠር የትራፊክ አደጋ

ሠንጠረዥ 3-25፡ በግንባታ ስራ ደህንነት ምክንያት ስለሚፈጠጥ የትራፊክ አደጋ

ተቋራጭ
የድግግሽ መጠን የመቶኛ ሰስሌት
ከፍተኛ 3 17.6
መካከለኛ 7 41.2
ዝቅተኛ 7 41.2
ምላሽ ያልሰጡ 0 0
ጠቅለላ 17 100.0

በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያት የሚፈጠር


የትራፊክ አደጋ እንዴት ይታያል ለሚለው 41% ዝቅተኛ ብለው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ነገር ግን
ከመንገድ ደህንነት ጋር ግንኝነት ያላቸው ሌሎች ተቋማት እንደገለጹት በተለያዩ ስራዎች
ምክንያት የተቆፋፈሩ፣ የግንባታ ግብኣትና ተረፈ ምርት በየመንገዱ በመቀመጣቸው እንዲሁም
አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ጥንቃቄ ምልክቶች በግልጽ አለመታየታቸው ለትራፊክ አደጋ መፈጠር
መንስኤ እንደሆኑ በመዲናችን አዲስ አበባ እየተከሰተ ያለው አደጋ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
እኛም ይህንኑ ሃሳብ እንጋራለን፡፡

81
 በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) አለመተግበር ከስራው ውጭ የሆኑ
ማህበረሰብ ላይ ስለሚደርሰው ጉዳት

ምስል 3-29፡ ደህንነት ባለመተግበሩ ምክንያት ከስራ ውጪ የሆኑ ማህበረሰብ ላይ የሚደርሰው ጉዳት

በኮንስትራክሽን ስራ ውስጥ በግንባታ ስራ ደህንነት (work zone Safety) በሚገባ ባለመተግበሩ


ምክንያት ከስራው ውጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጎጂ የሚሆኑበት ሁኔታ ምን ይመስላል
ለሚለው ተቋራጭ፣ ሰራተኛ እንዲሁም አማካሪ በአማካይ 59% ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ በሁሉም በኩል ከፍተኛ የሚለው አብላጫዉን ቦታ ይይዛል፡፡ ከዚህም
መረዳት የሚቻለው ከመንገድ ስራ ጋር በተገናኘ ምክንያት ከስራው ውጭ የሆኑ የህብረተሰብ
ክፍሎች የሚጎዱበት ሁኔታ መኖሩን ይጠቁማል፡፡ እኛም እንዳስተዋነው በተለያየ ሁኔታ ለአደጋ
አጋላጭነቱን ተገንዝበናል፡፡
 የደህንነት (safety) በአግባቡ መተግበሩ በሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት ላይ ያለው ሚና
ሠንጠረዥ 3-26፡ ደህንነት መተግበሩ በሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት ላይ ያለው ሚና

ሰራተኛው
የድግግሽ መጠን የመቶኛ ሰስሌት
ከፍተኛ 61 80.3
መካከለኛ 9 11.8
ዝቅተኛ 3 3.9
ምላሽ ያልሰጡ 3 3.9
ጠቅለላ 76 100.0

82
የደህንነት (safety) በአግባቡ መተግበሩ በሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት ላይ ያለው ሚና ለሚለው
80%ቱ ከፍተኛ ብለዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን
የግንባታ ደህንነት (safety) በሚገባ ባለመተግበሩ አንድን ስራ በተሳካ መልኩ ለማከናወን
የሰራተኛው ሚና ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ስራው የታለመለትን ግብ እንዳይመታ ያደርገዋል፡፡
ይህ ደግሞ ለኢንዱስትሪው እድገት እንቅፋት ይሆናል፡፡
 በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ለሚደርስ አደጋ የኢንሹራንስ ዋስትና ስለመስጠቱ

አማካሪ የመቶኛ ሰስሌት

9%

አዎ
የለም
91%

ምስል 3-30፡ የኢንሹራንስ ዋስትና ስለመሰጠቱ

አንድ ተቋራጭ በንብረትም ሆነ በሰው ላይ ለሚደርስ አደጋ የኢንሹራንስ ዋስትና መስጠቱን


የምትከታተሉበት ሁኔታ ስለመኖር ለሚለው 91.0%የሚሆኑት አማካሪ አዎ ብለዋል፡፡ይህም
ከህንፃ ግንባታ በተሻለ መልኩ የአደጋ ጊዜ የኢንሹራንስ ከለላ መኖሩን ያሳያል፡፡ ነገር ግን
ባደረግነው የመስክ ምልከታ በተጨባጭ ያለው አሰራር ከዚህ የተለየ መሆኑን ለአደጋው
በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ የሆኑት የጉልበት ሰራተኞች ገልፀዋል፡፡በተጨማሪም ከመንገድ
ግንባታ ጋር በተያያዘ መልኩ ከስራው ውጭም ያሉ ማህበረሰብ ላይ ጉዳት ሲደርስ
ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም የሶስተኛ ወገን የኢንሹራንስ ከለላ እንደሚያስፈልግ ለመገንዘብ
ችለናል፡፡

3.1.3. የደህንነት ዕቃ አቅራቢዎችን የተመለከተ መጠይቅ ትንተና


 የግንባታ አካባቢ ደህንነት መጠበቂያ አልባሳት (Safety equipment) በተመለከተ

ሠንጠረዥ 3-27፡ ስለ ደህንነት አልባሳት ያለው ግንዛቤ

የድግግሞሽ መጠን የመቶኛ ስሌት


አዎ 9 90.0
አላውቅም 1 10.0
ጠቅላላ ምላሽ 10 100.0

83
ከላይ በሰንጠረዥ እንደተገለፀው ስለግንባታ አካባቢ ደህንነት መጠበቅያ አልባሳት (Safety
equipment) በቂ እዉቀት አለዎት ለሚለው 90% የሚሆኑት መላሾች አዎ በማለት ምላሽ
ሰጥተዋል፡፡ይህም የሚያመለክተው የእቃ አቅራቢዎች ስለደህንት መጠበቅያ አልባሳት በቂ
ግንዛቤ ያላቸው መሆኑን ነው፡፡
 በድርጅታችሁ የሚገኙት የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት (Safety equipment) ምርቶች

አገር ምርቶች የመቶኛ ስሌት

20%
ዩሮፕ
የሌላ ሀገር

80%

ምስል 3-31፡ የደህንነት ምርቶቹ የየት ሀገር ምርቶች ናቸው

የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት (Safety equipment) በአብዛኛው በድርጅታችሁ የሚገኙት


የየት አገር ምርቶች እንደሆኑ ለሚለው ጥያቄ 80%ቱ የዩሮፕ ምርቶች እንደሆኑ ሲገልጽ
ቀሪዉ 20% ደግሞ የሌላ አገር ምርቶች በማለት መልሰዋል፡፡ ይህ የሚያመለክተው
ለደህንነት መጠበቅያ ተብለዉ የሚገቡት የሀገር ዉስጥ አለመሆናቸዉን ከዉጨ ሃገር የገቡ
ሲሆኑ ለዚህም እንደምክንያት የተቀመጠው ደረጃቸውና ጥራታቸዉን የጠበቁ በመሆናቸው
ነው፡፡ ሆኖም ግን ወደ ሀገር ውስጥ የደህንነት እቃዎችን በሚያስገቡበት ጊዜ የደህንነት
እቃዎችን እንደ ቅንጦት (Luxury item) እቃ በመቁጠር ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ
እንደሚጠየቁ እና ይህም ለተጠቃሚው የተሻለ ጥራት ያለውን እቃ በሚያቀርቡበት ጊዜ
ዋጋው ከፍተኛ ስለሚሆን ተጠቃሚውን እንዳይገዛ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም የደህንነት
እቃዎችን የመጠቀም ልምዳቸን ዝቅተኛ እንዲሆን ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖራዋል፡፡

84
 ደረጃቸውን የጠበቁ የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት (Safety equipment)

የመቶኛ ስሌት

30%
አለ

የለም
70%

ምስል 3-32፡ የደህንነት ዕቃዎቹ ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ አካል

የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት (Safety equipment) ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን


የሚያረጋግጥ አካል ለሚለው ጥያቄ 70% የለም ብለዋል፡፡ ነገር ግን አብዛኘዎቹ የደህንነት
እቃዎች ከውጪ በሚገቡበት ጊዜ ለጉዳዩ ትኩረተት ተሰጥቶት የጥራት ቁጥጥር እየተደረገ
አለመሆኑንም ጭምር የደህነት እቀ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቻለው
ለሴፍቲ የሚመለከተው አካል ትኩረት ያለመስጠቱንና በልምድ እየተሰራ መሆኑን
ያመላክታል፡፡
 በግንባታ (construction) ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት የደህንነት አልባሳትን የመግዛት ልምድ

የመቶኛ ስሌት

0% 20%
ከፍተኛ
መካከለኛ
ዝቅተኛ
80%

ምስል 3-33፡ በግባ ዘርፍ የተሰማሩ ተቋምት የደህንነት አልባሳትን የመግዛት ልምድ

85
በሀገራችን ውስጥ በግንባታ (construction) ዘርፍ የተሰማሩ ተቋማት የደህንነት አልባሳትን
የመግዛት ልምዳቸው ምን ይመስላል ለሚለው 20% መካከለኛ ሲሉ 80% ግን ዝቅተኛ ሲሆን
ከፍተኛ የሚለው 0% መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም የሚያመለክተው የሴፍቲ አልባሳትን
የመጠቀም ልምድ አለመኖሩን ሲሆን ይህም በዘርፉ ለሚፈጠሩ አደጋዎች ትልቁን ድርሻ
ይወስዳል፡፡ ምንም እንኳን በምስል 3-33 እንደተጠቀሰው የደህንነት እቃ አቅራቢዎች
ስለደህንነት አጠባበቅ በቂ ግንዛቤ ያላቸውም ቢሆንም ተጠቃሚዉን ከማሳወቅና ግንዛቤ
ከመፍጠር አንጻር ከሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት መስራት እየሰሩ አይደለም፡፡
 ዋጋ ወይንስ ጥራቱ ለደህንነት (safety) አልባሳት

የመቶኛ ስሌት

20%
አዎ
አይደለም

80%

ምስል 3-34፡ ተጠቃሚ ድርጅቶቹ ዋጋ ላይ ወይስ ጥራት ላይ ያተኩራሉ

ከላይ በምስሉ እንደተገለጸው ተጠቃሚ ድርጅቶች የደህንነት መጠበቂያ አልባሳት ሲገዙ


ለጥራት የሰጡት ዋጋ 20% ሲሆን 80% ደግሞ ለዋጋዉ መቀነስ ቅድምያ እንደሚሰጡ
ያመላክታል፡፡ ይህም ለጥራቱ ያላቸው አመለካከት ዝቅተኛ ሲሆን ከዋጋ መቀነስ አንጻር የተሻለ
አትራፊ ለመሆን መፈለግን ያመላክታል፡፡ ለግንባታ ስራ የደህንነት እቃዎች ለተጠቃሚዎች
በሚቀርቡበት ጊዜ ያለው የግዢ ስርአት ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸውን የመምረጥ በመሆኑ የተሻለ
ጥራት ያላቸውን እቃዎች ቢያቀርቡም እንኳን በጨረተው እንደማያሸንፉ ገልጸዋል፡፡ እዚህ ላይ
መሰራት ያለበት ነገር ስለደህንነት ሁኔታ እንደትርፍ ጉዳይ ሳይሆን ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡
በተጨባጭ ያለዉ ሁኔታ "ቅድሚያ ለደህንት (ሴፍቲ ፈርስት) የሚለው ከቃላት የዘለለ ቦታ
አለመኖሩን ነው፡፡

86
3.2. የጥናቱ ግኝቶች

3.2.1. ደህንነት በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ


የግንባታ ባለቤቶች የግንባታ ዉል ወደ ጨረታ ሲያወጡ የግንባታ ስራ ቦታ ደህንነት መጠበቅ
አለበት የሚል መነሻ በማድረግ የደህንነት መጠበቅያ እቃዎችን በግንባታ ስራ ዉል በማካተት
ለጨረታ ማዉጣት አለባቸው፡፡ ቀጥሎ ዉል ስምምነት ሲደረግ ዋጋዉ የስራ ላይ ደህንነትና
ተዛማጅ የሆኑ ጉዳዮችን በሙሉ ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡ ይህንን ፕሮጀክት
እስኪጠናቀቅ ድረስ ምን ያህል አደጋ ሊያጋጥም ይችላል፣ ምን አይነት ቅድመ ጥንቃቄ ቢደረግ
ይሻላል የሚሉትን በሚያሳይ መልኩ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ማስተዋል ይኖርበታል፡፡የስራ
ላይ ደህንነትን በተመለከተ የግንባታ ባለቤት፣ የስራ ተቋራጩ እንዲሁም የአማካሪ ድርጅቱ
የስራ ድርሻ ምን መሆን አለበት የሚለዉን በዉል ስምምነቱ በግልፅ መቀመጡን መጤን
አለበት፡፡

ሠንጠረዥ 3-28፡ ደህንነትን ውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ መግባ አለበት ብለው የሚያምኑ እና ያስገቡ
አሰሪው መስሪያቤት ተቋራጭ አማካሪ
ለግንባታ ስራ ደህንነት የሚወጣ ወጭ ለግንባታ ስራ ደህንነት የሚወጣ ወጭ ለግንባታ ስራ ደህንነት የሚወጣ ወጭ
(በcontract agreement) ይካተታል (በcontract agreement)ይካተታል (በcontract agreement) ይካተታል

ይካተታል አይካተትም ጠቅላላ ይካተታል አይካተትም ጠቅላላ ይካተታል አይካተትም ጠቅላላ


Contract
document አዎ 9 13 22 51 140 191 8 21 29
ሲያዘጋጁ
Safety መግባት አላምንበትም 0 2 2 2 11 13 0 0 0
አለበት
ጠቅላላ 9 15 24 53 151 204 8 21 29

ከላይ በሰንጠረዡ እንደሚታየው ደህንነት በውል ስምነቱ ውስጥ መግባት አለበት ብለው
የሚያምኑት ባለድርሻ አካላት(ተቋራጭ፣ አማካሪ እና አሰሪው መስሪያ ቤት) ቁጥር ትልቅ
ቢሆንም በውሉ ውስጥ ያካተቱት በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ይህም የሚያሳየው የግንዛቤ እጥረት
እንደሌለ እና ግን ተግባራዊ ማድረጉ ላይ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለ ነው፡፡

በስራ ተቋራጮች በኩል የጉልበት ሰራተኛው ዛሬ ስርቶ ነገ ወደሌላ ስፍራ ሊቀይር ስለሚችል
የደህንነት አልባሳት ማሟላት ችግር እንደሆነባቸው ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ስርአቱ(

87
Bidding process) ያነሰ ዋጋ (Least price) መሆኑ የደህንት ጥንቃቄ የበለጠ እንዲቀጭጭ
አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ ይህም የስራ ተቋራጩ የሚከፈለው ዋጋ በጣም አናሳ በመሆኑ
ለሚያከናዉናቸው ስራዎች እንኳን በአግባቡ የማይሸፍንለት ስለሆነ የደህንነት ሁኔታን
ለመተግበር ተግዳሮት ሆኖበታል፡፡

3.2.2. ደህንነትን የተመለከቱ ህጎች እና አፈጻጸማቸው


በመንግስታዊ ተቋምም ያለዉ የአሰራር ሁኔታ የደህንት ጥንቃቄን የሚያበረታታ አይደለም፡፡
ህጉ ቢኖርም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም፡፡ ህጉን የማስፈጸምያ ስርአቱ ላይ መሰራት
አለበት፡፡ ሬጉሌሽን ክፍሉ ትልቅ ስራ ይጠበቅበታል፡፡ በተጨባጭ ያለዉ የቁጥጥር ስርአት ልል
በመሆኑ ጥፋት ባስከተሉ ተቋማት እርምጃ እየተወሰደ አይደለም፡፡ የወጣዉን ህግ ተግባራዊ
የማያደርጉትን የቅጣት እርኮኖቸን በማስቀመጥ በተዋረድ ስራው የሚቀማበትን ከዚያም ሲብስ
የስራ ፈቃዱን እስከመከልከል የሚያደርስ እርምጃ እስካልተወሰደ እንዲሁም የተሻለ አፈጻጸም
ያላቸው ተቋማት ከሌሎች ተነጥለው የሚታዩበትና የሚበረታቱበት የተሻለ ሁኔታ በሌለበት
አሁን ያለዉ ሁኔታ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የኮንስትራክሽኑ ኢንዳሰትሪ አምራች የሆነውን ዜጋ
በመቅጠፍ በሃገራችን ያለዉን የሰውሃይል አልባ ሊያደርገው እንደሚችል መገመት
አያዳግትም፡፡በአጠቃላይ ሲታይ በኮንስትራክሽኑ ስራ ዉስጥ የተሰማሩት ባለድርሻ አካላት
የደህንት ጥንቃቄን በተመለከተ ያሉት ህጎችን ምንድረስ እንደሆኑ አያዉቁም፡፡ ህጉ መኖሩን
የሚያዉቁት አካላት እንኳን አይጠቀሙበትም፡፡

3.2.3. የደህንነት አስተዳደር

3.2.3.1. የደህንነት እቃዎችና መሳሪያዎች


በአብዛኛው የስራ ተቋራጭ የደህንት አልባሳት የማያሟላው ወጭን በመፍራትና የተሻለ
ትርፋማ ለመሆን በማሰብ ሲሆን በቁጥር አናሳ የሆኑት ደግሞ ገንዘቡ ኖሯቸውም እንኳን
የሴፍቲ ግንዛቤ ማነስ ስላለባቸው ሳያሟሉ ይቀራሉ፡፡ ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር
ቢኖር ለሴፍቲ አስፈላጊዉን ትኩረት አለመስጠታቸው ሲሆን ይህ ደግሞ በድምሩ ለአደጋ
መፈጠር ጉልህ ድርሻ ይኖሮዋል፡፡

88
ምስል 3-35፡ ሰራተኞች የደህንነት ዕቃዎች ሳይሟላላቸው

በጣም ቀላልና ብዙ ወጪን የማይጠይቁ የደህንት ምልክቶችን እንኳን የመጠቀም ልምዳችን


አናሳ ነው፡፡ ለሚሰሩት ስራዎች የቅድመ ማስጠንቀቅያ ምልክት በማስቀመጥ ብቻ ህይወትና
ንብረት መታደግ ሲቻል ነገር ግን ለጉዳዩ አስፈላጊዉን ትኩረት ባለመስጠቱ ምክንያት
በርካቶችን አካል ጉዳተኛ እንዲሁም ህይወት እስከመንጠቅ በተጨማሪም ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ
የወጣባቸዉን ንብረቶች ሲወድሙ ማየት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ ይህ ችግር በስራው
ላይ የተሰማሩትን ብቻ ሳይሆንም ከስራው ዉጪ የሆኑትንም ጭምር ተጎጂ እያደረገ ያለ
መሆኑ ገሃድ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ አሰሪዉ አካል በአግባቡ የማይወጣ ከሆነ የግንባታ ቁጥጥር
የሚያደርገው አካል እርምጃ ሊወስድ ይገበዋል፡፡ በቁጥር እጅግ አናሳ የሆኑ ተቋማት የየደህንት
አልባሳት ቢያቀርቡም እንኳን በሰራተኛ በኩል የመጠቀም ልምዱ ስለሌለ ችግር ሲፈጥር
ይስተዋላል፡፡

የቀን ሰራተኛው የእለት ጉርሱን ሰርቶ መዋሉን እንጅ ለወደፊት ስለሚፈጠረው አደጋ
እምብዛም ግድ የለውም፡፡ ስለሚሰራው ስራና ማሽነሪዎች እንኳን በቅጡ ሳያውቅ ወደ ስራ
የሚገባበት ሁኔታ የተለመደ ነው፡፡ በአሰሪዎችም በኩል በሙያው ጠለቅ ያለ እውቀት ያለውና

89
ስልጠና የወሰደ የቀን ሰራተኛ ስለማያገኙና አልፎ አልፎ ቢገኙም ክፍያቸው ስለሚወደድ
ማንኛውንም ያገኙትን ለመቅጠር መገደዳቸው ይህም ለአደጋ መፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ
እንደሚኖረው አስተውለናል፡፡

ምስል 3-36፡ ዕድሜያቸው የገፋ የቀን ሰራተኞች እና የደህንነት አልባሳት ያልተሟላላቸው ሰራተኞች

90
ምስል 3-37፡ ምቹ የስራ ቦታ

3.2.3.2. የደህንነት ባለሙያ


በአሁኑ ሰአት በተለያዩ የግንባታ ቦታዎች የየደህንት ባለሙያ በመሆን የሚሰሩት ከተለያዩ
የኢንጅነሪንግ እና መሰል ዘርፎች ተመርቀው የሚወጡ በመሆናቸው አብዛኛዉን ጊዜ እንደስራ
መፈለጊያ እንጂ በሙያው ለመስራት ፍላጎትና ክህሎት የላቸውም፡፡ ይህም በመሆኑ በቁጥር
ዉስን በሆኑ የግንባታ ቦታዎች እንደ የደህንት ባለሙያ ሆነዉ ቢሰሩም የራሳቸውን ስራ ወደጎን
በመተው በሌሎች ሙያዎች የመሳብ አዝማምያ ስለሚየሳዩ ዉጤቱ አመርቂ አይደለም፡፡
በመሆኑም እነዚህንና መሰል ችግሮች ከመቅረፍ አንጻር የደህንነት (safety profession)
ተያያዥነት ባላቸው የሙያ ዘርፍ አግባብነት ያለውን ስልጠና በመስጠት በደህንነት የብቃት
ማረጋገጫ (Certification) እንዲሰጣቸው ቢደረግ ያለዉ ጠቀሜታ አመርቂ ሆኖ በተጓዳኝ የስራ
ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት እንደማንኛዉም ሌሎች ሙያ(Profession) በመስፈርቱ ዉስጥ ተካቶ
የሚጠየቅበት ሁኔታ ቢመቻች፡፡

3.2.4. በግንባታ ቦታ ላይ በደህንነት መጓደል ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎች

3.2.4.1. በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ የሚደርሱ አደጋዎች


በአሁኑ ሰአት የኮንስትራሽን ስራ ከትራፊክ አደጋ ባልተናነሰ ሁኔታ በሰዉ ህይወትና ንብረት
ላይ ከፍተኛ አደጋ እያደረሰ ነው፡፡ ለምሳሌ ለትራፊክ አደጋ የሚዲያ ሽፋን ተሰጥቶት
ህብረተሰቡ በአደጋው ዙርያ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንዲኖረው እየተሰራ ነው፡፡ ነገር ግን
በኮንስትራክሽን ዙሪያ እየደረሰ ካለው አደጋ አንጻር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ
አይደለም፡፡ ይህ በመሆኑ ቀድሞ ከደረሱት አደጋዎች ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ

91
ስላልተሰራ ተመሳሳይ አደጋ በተደጋጋሚ ሲደርስ ይስተዋላል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ሰአት
በተጨባጭ የደህንት ጥንቃቄን በተመለከተ በአገራችን ያለዉ ሁኔታ ምንም የለም ለማለት
ያስችላል፡፡ በአጠቃላይ ትኩረት ያልተሰጠዉ በልምድና በዘፈቀደ እየተሰራ ያለ የተረሳ ጉዳይ
ነው፡፡ እንዲያዉም እንደተጠቃሚዉ ቸልተኝነትና ትኩረት እንደማጣቱ የአደጋው መጠን አሁን
ካለው ሊብስ ይገባ ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ አደጋ እያስከተሉ ካሉ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ ህንፃዎችን


ለተለያዩ አገልግሎቶች ማዋል ነው፡፡ ምም እንኳን ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ያልተጠናቀቁ
ህንጻዎች አገልግሎት መስጠት እደሌለባቸው በመመሪያው ላይ የተቀመጠ ቢሆንም አሁን
አሁን በመዲናችን ውስጥ የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ግንባታቸው ባልተጠናቀቁ
ህንፃዎች ላይ ተከፍተው መታየቱ እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ድርጅቱ ውስጥ
ተቀጥረው የሚሰሩትን ሰራተኞች ብቻ ሳይሆን አገልግሎት ለማግኘት ወደ ተቋማቱ የሚመጡ
የህብረተሰብ ክፍሎችንም ጭምር አደጋ ላይ የሚጥል ጉዳይ ነው፡፡

ምስል 3-38 ግንባታቸው ያለተጠናቀቁ ህንጻዎች አገልግሎት ሲሰጡ

የማጠናቀቂያ (Finishing) ስራ በሚከናወኑበት ሰአት ሴፍቲ ቤልት ባለመጠቀም በተደጋጋሚ


የመዉደቅ አደጋ ያጋጥማል፡፡ ቤልት አደርጎ መስራት ለስራ እንቅሰቃሴ አይመችም በሚል
ምክንያት የመጠቀም ልምዱ አናሳ ነው፡፡

92
ምስል 3-39፡ ሰራተኞች የደህንነት አልባሳት ሳይሟላላቸው የማጠናቀቂያ ስራ በመስራት ላይ

የጣርያ ስራ በሚከናወኑበት ወቅት የመዉደቅ አደጋ ያጋጥማል፡፡ በህንጻ ስራ በሚቆፈር


ጉድጓድ በስራ ላይ እያሉ የመደርመስ አደጋ ሲያጋጥም በሌላዉ በኩል ለመስረተ ልማት ስራ
ማንሆሎች ተከፍተው ስራዉ ሲጠናቀቅ መልሶ ባለመከደናቸው በአዛዉንቶች፣ ሴቶች፣ ህጻናት
እንዲሁም ጠቅላላ የማህበረሰቡ ክፍል ተጎጂ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባ ካለው የቦታ ጥበት አንጻር በሰፊው እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች ከወለል
በላይ ያላቸው ከፍታ ብዙ ስለሆነ እንዲሁም ለመኪና ማቆሚያና መሰል ስራዎች በሚል
ከወለል በታች ሁለትና ሶስት ቤዝመንት ስለሚገነባ በከፍታው ምክንያት የመዉደቅ አደጋዎች
በብዛት ሲከሰቱ፣ በቤዝመንት ቁፋሮ ምክንያት የአፈር መደርመስ አደጋ በብዛት ሲደርስ
ይስተዋላል፡፡

93
ምሰል 3-40፡ ደህንነቱ ባልተጠበቀ የቁፋሮ ሰራ ላይ

አብነት አካባቢ ለህንጻ ስራ በሚቆፈር ጉድጓድ በስራ ላይ እያሉ የመደርመስ አደጋ

ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በ2007 ዓ.ም በኮንስትራክሽን ስራ


ምክንያት የተፈጠሩ አደጋዎች ቁጥር 1021 እንደሆነ ያሳያል፡፡ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ከ2002-2008ዓ.ም የተከሰቱ ከህንጻ ግንባታ ጋር
የተያያዙ እና የተመዘገቡ አደጋዎች ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ እና ግራፍ ላይ ይታያል፡፡
94
አደጋ የደረሰበት የተቆፈረ የአፈር የድልድይ ቱቦ ውስጥ ግድብ ለካባ የህንፃ የአጥር ግንብ
ዓመት ጉድዷድ ውስጥ መደርመስ መደርመስ በመግባት ውስጥ የተቆፈረ መደርመስ መደርመስ
በመግባት በመግባት ኩሬ

2002 ዓ.ም 1 3 0 0 0 0 0 0
2003 ዓ.ም 7 3 1 5 1 3 0 0
2004 ዓ.ም 4 3 0 0 0 2 0 0
2005 ዓ.ም 4 4 0 0 0 5 10 0
2006 ዓ.ም 6 5 0 0 0 7 0 0
2007 ዓ.ም 3 12 0 2 0 1 0 0
2008 ዓ.ም 3 14 0 1 0 1 5 3
ጠቅላላ 28 44 1 8 1 37 15 3

ሠንጠረዥ 3-29፡ ከ2002-2008ዓ.ም ከህንጻ ግንባታ ጋር ተያይዘው የተከሰቱ አደጋዎች

ምስል 3-41፡ ከ2002-2008ዓ.ም ከህንጻ ግንባታ ጋር ተያይዘው የተከሰቱ አደጋዎች

95
ከአካል ጉዳተኞች ፌዴሬሽን በወሰድነው መረጃ መሰረት በ 2009 ዓ.ም በ አዲስ አበባ በ ኮንስትራክሽን
ምክንያት የደረሰ አካል ጉዳት የሚያሳይ ሰንጠረዥ

ሠንጠረዥ፡ 3-30 በአካል ጉዳተኞች ላይ የደረሰ አደጋ


ተ.ቁ የአደጋ አይነት ሴት ወንድ አጠቃላይ
1 መስማት ከተሳናቸው 15 20 35
2 ዓይነ ስውራን 145 100 245
3 ስጋ ደዌ 205 900 1105
4 ከአህምሮ ውስንነት 210 300 510
5 ከእጅና እግር አካል ጉዳት አንፃር 170 230 400
6 ከፊል ጉዳት 1000 1000
7 ዝቅተኛ አካል ጉዳት 450 200 650
ድምር 1195 2750 3945

ምስል 3-42፡ ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታ

96
በህንጻ ግንባታ ላይ በተደጋጋሚ የጉልበት ሰራተኞችን ለአደጋ ከሚያጋልጡት አንዱ የእንጨት
ስካፎልዲንግ ነው፡፡ ይህም የግንባታ ጊዜው በሚራዘምበት ሰአት ፀሃይና ዝናብ የሚፈራረቅበትና
ግንባታው ሲቀጥል በነበረው ስለሚጠቀሙ ከሰካፎልዲንግ በመወደቅ ለከባድ የአካል ጉዳትና
ለህልፈተ ህይወት ይዳረጋሉ፡፡ ምንም እንኳን ህጉ ከ4ኛ ፎቅ በላይ ለሆኑ ህንጻዎች የብረት
ሰካፎልዲንግ መጠቀም እንዳለበት ቢያስቀምጥም በሳይት ምልከታችን በተዘዋወርንባቸው የጋራ
መኖርያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ በእንጨት የሚሰሩ ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ ግን ዉስን የግንባታ
ቦታዎች ላይ የብረት ሰካፎልድኒግ የሚጠቀሙ አሉ፡፡ ይህ አጠቃላይ ካለው የኮንስትራክሽን ስራ
ጋር ሲነጻጸር እጅግ አናሳ ነው፡፡

ምሰል 3-43፡ የእንጨት እስካፎልዲንግ

97
ምሰል 3-44፡ የእንጨት እስካፎልዲንግ

የብረት ሰካፎልዲንግ መጠቀም የመነሻ ዋጋ (ኢንቨስትመት ኮስት) ቢጠይቅም የሚያገለግለው


ለረጅም ጊዜ በመሆኑ በየጊዜው የእንጨት ስካፎልዲኒግ ከመጠቀም ጋር ሲነጻጸር ያለዉ ዋጋ
የተሻለ መሆኑ፣ ግንባታውን በጥራትና በፍጥነት ከመጨረስ አኳያ ያለዉ ሚና ከፍተኛ
መሆኑ፣ የግንባታ ሰራተኞቹ አደጋ ይደርስብናል ብለዉ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ ስራቸው
ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ ማድረጉ፣ በሌላ በኩልም የእንጨት ሰካፎሎዲኒግ መጠቀም ቢቀር
የአለማችን አሳሳቢ ጉዳይ እየሆነ ለመጣው ግሎባል ዋርሚነግ መቀነስ ያለው አስተዋፅኦ
ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም አንድም የአደጋ መጠን ከመቀነስ በሌላ በኩልም አለንጓዴ አካባቢን
(green environment) ከመፍጠር አኳያ አላቂ የሆነውን የእንጨት ሃብት ከግምት ዉስጥ
በማስገባት አሁን ያለዉን የኮንስትራክሽን የአሰራር ሁኔታ በማዘመን የሚደርሰዉን አደጋ
መታደግ ይቻላል፡፡

98
ምስል 3-45፡ ሰራተኞች ለአደጋ በሚያጋልጥ የሥራ ሁኔታ ላይ

ለኮንስትራክሽን ስራ አገልግሎት የሚዉሉ የቁፋሮ ማሽነሪዎች፣ ክሬኖች፣ የከፍታ ማንሻ


(lifting equipment) የመሳሰሉት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ስለሚያከናዉናቸው ስራዎች በሚገባ
ስልጠና መዉሰድ አለባቸው፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ በክህሎትና በግንዛቤ እጥረት ምክንያት
ለሚፈጠሩት አደጋዎች ስራዉን በሚያከናዉነው ስራተኛ ብቻ ሳይሆን አብረዉ በሚሰሩት የቀን
ሰራተኞች ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡

በተጨማሪም በአካባቢው የሚገኙት ማህረሰብና ንብረት ላይ ጉዳት ሲደርስ ይታያል፡፡ ስለዚህ


የግንባታ ስራ የሚከናወንባቸው ማሽነሪዎች ደረጃቸዉን የጠበቁ መሆናቸዉንና
ስለአጠቃቀማቸው ስልጠና የሚሰጥ በዘርፉ በቂ እዉቀት ያለዉ ባለሙያ ያስፈልጋል፡፡
በማሽኖች ምክንያት የሚከሰት አደጋ በኦፕሬሽን ላይ እያሉ ብቻ ሳይሆን በማሽን ጥገና
(maintanance) ወቅትም ስለሆነ የጥገና ማንዋል ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን በተጨባጭ ያለዉ
ሁኔታ በዘልማድ ብዙ እዉቀት በሌላቸው ስለሚከናወን ለአደጋ ያጋልጣል፡፡

በኮንስትራክሽን ስራ ውስጥ ከሚደርሰው አደጋ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው የጉልበት ሰራተኛው


ነው፡፡ በአሰሪው በጎ ፈቃድ ህክምናም ሆነ አስፈላጊው እርዳታ ካልተደረገለት በስተቀር እስከሞት
የሚደርስ አደጋ ገጥሞት ተገቢው ህክምናም ሆነ ክፍያ ሳይደረግ የሚዘነጋበት ሁኔታዎች

99
አሉ፡፡ አብዛኛው የጉልበት ሰራተኛም ከተለያየ ክፍለ ሀገር የሚመጣ በመሆኑ ለሚደርስበት
ጉዳት ተጠሪ የሚሆን ቤተሰብ እንኳን የላቸውም፡፡ ይህም ችግሩን የበለጠ ያባብሰዋል፡፡

በተለይም በአሁኑ ሰዓት የሴት ጉልበት ሰራተኞች ወደ ግንባታው ስራ በከፍተኛ ደረጃ እየገቡ
እና በስራው ላይ ተሳታፊ እየሆኑ ያለበት ሁኔታ በገልጽ የሚታይ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
የደህንነት እቃዎች እና ምቹ የስራ ሁኔታ ባልተመቻቸበት ሁኔታ እንዲሁም የሚያከናውኑት
ስራ የበለጠ ጉልበትን የሚጠይቅ እና ከባድ ሸክሞችን የማንሳት ስራዎች ስለሚበዙበት ሴቶች
ለጉዳቱ ተጋላጭ ከመሆናቸውም በላይ ለወደፊቱ ከወሊድ ጋር በተገናኘ ሁኔታ
የሚያጋጥማቸውን ችግር እንዲባባስ ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም ሴት ሰራተኞች የግንባታ
ስራቸውን በሚያከናውኑበት አካባቢ ልብስ መቀየሪያ ቦታ፣ ጾታን የለየ የመጻዳጃ ቦታ ባለመኖሩ
ምክንያት ጾታዊ ትንኮሳ እና ሌሎችም ጉዳቶች ሲደርስባቸው ይስተዋላል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከኮንስትራክሽን ስራ ጋር ተያይዞ በሚከሰት አደጋ ምክንያት በርካታ የህብረተሰብ


ክፍሎች አካል ጉዳተኛ እንዲሆኑ ከማድረጉም ባሻገር በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት የእለት
ከእለት ስራቸውን ማከናወን በማይችሉበት ሁኔታዎች ላይ መሆናቸው ገልጸዋል፡፡ ይህም
ጉዳዩን የበለጠ አሳሳቢ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን እየተፈጠረ ያለውን አደጋ ከመግታት
አንጻር ብዙ ስራ እደሚቀረው እና ለአደጋ ሰለባዎችን የሚያቀርቡትን ሮሮ የሚሰማቸው ጉዳዩ
ሚመለከተው አካል አለመኖሩን ጭምር አብራርተዋል፡፡

3.2.5. በኮንስትራክሽን ስራ ምክንያት የደረሱ አደጋዎችን የመመዝገብ ልምድ እና የተመዘገቡ


አደጋዎች
በግንባታ ስራ ቦታ አካባቢ (Construction work zone safety) እና ተዛማጅ በሆኑ ምክንያት
አደጋ ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ ለማግኘት የሚመጡ ታካሚዎችን ከ2005 እስከ 2009
ዓ/ም ድረስ የደረሰባቸው የአደጋ ዓይነት ተገልፆ እንዲሰጠን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ በሰባት
ሪፈራል ሆስፒታሎች መረጃ እንዲሰጡን የጠየቅን ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ አምስቱ መረጃዉን
ለመስጠት የተለመደዉ የሆስፒታል አሰራር በማንኛዉም አደጋ ምክንያት የሚመጡትን
ታካሚዎች የሚያስተናግደው በተመሳሳይ የመረጃ አያያዝ ነው፡፡ በመሆኑም የትኞቹ ጉዳቶች
በግንባታ ቦታ አካባቢና ተዛማጅ በሆኑ ጉዳዮች እንደደረሱ በማወቅ አሁን ባለው የአመዘጋገብ
ሁኔታ ለመለየት አስቸጋሪ ነው፡፡ እነዚህም መሰል መረጃዎች ለማግኘት የታካሚዉን ሙሉ
የጉዳት ታሪከ ከማህደሩ ማየት ወይም የተለየ ዓይነት የመመዝገቢያ ቅፅ ማዘጋጀት
ያስፈልጋል፡፡ ይህንም ለማድረግ ጊዜ፤ የሰው ሃይል በተለይ የኮምፒውተር እዉቀትና ክህሎት

100
ያለው ባለሙያ የሚጠይቅ በመሆኑ መረጃዉን በተፈለገው መልክ ለመስጠት አስቸጋሪ
ሆኖብናል ብለው በደብዳቤ ገለፀዋል፡፡ በቀሪዎች ሁለት ሪፈራል ሆስፒታሎች ዉስጥ አንዱ
በሶስት ወራት ዉስጥ 125 በግንባታ ስራ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ታካሚዎችን ዝርዝር
የገለፀ ሲሆን የአደጋዉ አይነት በጥቅሉ የተቀመጠ በመሆኑ በተደጋጋሚ የሚደርሰዉን አደጋ
የትኛዉ መሆኑ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ ሌላኛው ሆስፒታል ደግሞ በ2008 ውስጥ 531
በመውደቅ 79 በኤሌክትሪክ 27 በማሽን መቆረጥ 122 በኬሚካል ሲሆን በ2009 ደግሞ 681
በመውደቅ 63 በኤሌክትሪክ 47 በማሽን መቆረጥ 176 በኬሚካል ምክንያት መሆኑን
ገልጸዋል፡፡ ከዚህም መረዳት የሚቻለው በኮንስትራክሽን ስራ ምክንያት እየደረሰ ያለው አደጋ
ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መሆኑን ያሳያል፡፡ እንደ አጠቃላይ ምንም እንኳን ሁለቱ
ሆሰፒታሎች ከላይ የተገለፀዉን መረጃ ቢሰጡንም ያለው የመረጃ አያያዝ ስርአት
ኮምፒውተራይዝድ በሆነና በተደራጀ መልኩ አለመሆኑን ሁሉም ይስማሙበታል፡፡ በመሆኑም
በቀጣይ ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተደራጀ የመረጃ ቋት እና ራሱ የቻለ ባለሙያ ተመድቦለት
ቢሰራ በተደጋጋሚ አደጋ የሚከሰትባቸው የኮንስትራክሽን ተቋማትን አስፈላጊዉን ማስተካከያ
እንዲያደርጉና ጥሩ አፈጻጸም ያላቸዉንም የሚበረታቱበትን ሁኔታ በመፍጠር የኮንስትራክሽኑን
ኢንዱስትሪ ወደ ተሻለ የአሰራር ስርአት ለማድረስ ጠቀሜታዉ የጎላ ነወ፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮንስትራክሽን ዙርያ የሚደርሱ አደጋዎችን እንዲሰጡን


በጠየቅነው መሰረት በ2008ዓ/ም የተከሰተ የሞት አደጋን ለካባ ለተቆፈረ ጉድጓድ ዉሃ
አጠራቅሞ በመስመጥ 6 ሰው፣ ከህንፃ በመዉደቅ 2 ሰው፣ ያልተዘጉ ቱቡ በመግባት 2 ሰዉ፣
አፈር ተንዶ 2 ሰው፣ በኤሌክትሪክ ምክንያት 6 ሰው፣ በድምሩ 18 ሰው አደጋ የደረሰበት
ሲሆን ይህም ከወንጀል ጋር ተያያዥነት ያለው ብቻ ሲሆን ከዚህ ወንጀል ነክ ጋር ያልተያያዙት
እንዲሁም አደጋ ደርሶባቸው ነገር ግን ለህልፈት ያልበቁት በዚህ የአደጋ ዝርዝር ዉስጥ
አልተካተቱም፡፡

የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ባለስልጣኑ በሚያስገነባቸው የመንገድ ግንባታ ቦታዎች


አካባቢ በ2008 ዓ/ም በተለያየ ምክንያት በስራ ላይ ጉዳት የደረሰባቸውና በህክምና መስጫ
ክሊኒክ ህክምና ያገኙ ሰራተኞች 305 ወንዶችና 148ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ በድምሩ 453 ስራተኞች
ከኮንስትራክሽን ስራ ጋር በተያያዘ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል::

101
እንደ አጠቃላይ ከ 2005 እስከ 2009 ዓ.ም በግንባታ ስራ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች ከተለያዩ
ተቋማት የተገኘው መረጃ በሚከተለው ሰንጠረዥ ተቀምጧል፡፡

ሠንጠረዥ 3- 31 የአደጋዎች ብዛት

የአምስት ዓመት ከግንባታ ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያት የተከሰቱ አደጋዎችን እንዲሰጡን


የጠየቅናቸው የሚመለከታቸው ተቋማት ካለው የመረጃ አያያዝ ሥርአት ደካማነት የተነሳ
መረጃን በሚፈለገው መልኩ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ይህም የሆነው የመረጃ አያያዝ ስርአቱ
ኮምፒውተራይዝድ በሆነና በተደራጀ መልኩ ስላልሆነ ነው፡፡

3.2.6. የስራ ደህንነት ተግባራዊ እንዳይሆን የሚጠቀሱ ምክንያቶች


 ሴፍቲን በተመለከተ በጨረታ ሰነድና በኮንትራት ዶክመንቱ እንደ ማንኛዉም የስምምነት
አካል እንዲካተት አለመደረጉ፣ የጨረታ ስርአቱ( Bidding process) ያነሰ ዋጋ(List
price) መሆኑ ሴፍቲ የበለጠ እንዲቀጭጭ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡
 በተቋራጮች በኩል ወጪን በመፈራት የሴፍቲ አልባሳትን ያለማሟላት በጣም ጎልቶ
የሚታይ ችግር ነው ፡፡
 የግንባታ ደህንነትን በተመለከተ የተቀመጡ ህጎችን ለመተግበር የሚያስችል አስገዳጅ
የሆነ የህግ ማዕቀፍ አለመኖር፤ ይህም ማለት የግንባታ አካባቢ ደህነትን የተመለከቱ

102
የተለያዩ ህጎች እና ደንቦች ቢኖሩም ህጉን የተላለፉት ላይ የሚወሰድ እርምጃ
አለመኖር፡፡
 በግንባታ ባለቤት፣ አማካሪና የስራ ተቋራጭ በኩል የግንዛቤ ማነስ አለ ብሎ ማለት
አይቻልም ነገር ግን ትኩረት አለመስጠት በትልቁ የሚታይ ችግር ነው፡፡ በጣም ቀላልና
ብዙ ወጪን የማይጠይቁ የሴፍቲ ምልክቶችን እንኳን የመጠቀም ልምዱ በጣም አናሳ
ነው፡፡ ለሚሰሩት ስራዎች የቅድመ ማስጠንቀቅያ ምልክት በማስቀመጥ ብቻ ህይወትና
ንብረት መታደግ ሲቻል ነገር ግን ለጉዳዩ አስፈላጊዉን ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት
በርካቶችን አካል ጉዳተኛ እንዲሁም ህይወት እስከመንጠቅ እና ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ
የወጣባቸዉን ንብረቶች ሲወድሙ ማየት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በግንባታ
ሰራተኛ በኩል ደግሞ የእውቀትና የትምህርት ደረጃ ዝቅ ከማለት ጀምሮ በሚሰሩት ስራ
ላይ ያላቸው ግንዛቤ በጣም አናሳ መሆኑ ይጠቀሳል፡፡
 የግንባታ ደህንነትን የሚቆጣጠረው አካል ስራው በህጉና በደንቡ መሰረት
የሚከታተልበት አግባብ ልል መሆኑ
 በተወሰነ መልኩ ሴፍቲን የተገበሩ አንዳንድ ፕሮጀክቶች አለማበረታታቱ እንዲሁም
ያልተገበሩ ተከታትሎ እርምጃ አለመወሰዱ
 በደህንነት ራሱ የቻለ ሙያ የተመረቀ ባለሙያ አለመኖሩ በራሱ በመንግስትም ትኩረት
አለመሰጠቱ ያሳያል፡

3.2.7. የስራ ላይ ደህንነት መጓደል ያለው ተጽእኖ


 የስራተኞች የካሳ ክፍያ እንዲኖር ያደርጋል

 አዲስ ሰራተኛ በሚቀጠርበት ጊዜ ወይም ለተተኪ ሰራተኛ የሚወጣዉን የስልጠናና


የማተካኪያ ወጪ ያስከትላል

 በስራ ላይ ጥራት ዝቅ እንዲል ያደርጋል

 ስራዉን በአግባቡ ባለማጠናቀቅ ምክንያት ቅጣት ያስከትላል

 አንድ ስራ በታቀደለት ጊዜ ወጭ እና ጥራት እንዳይጠናቀቅ አሉታዊ ተፅእኖ ይኖረዋል

 በሰራተኞች ላይ የስራ ተነሳሽነትን ይቀንሳል

 በሚከሰተው አደጋ ምክንያት አምራች የሆነውን ዜጋ ይቀጥፋል

103
እንደ አጠቃላይ የግንባታው ዘርፍ ከግብርና ዘርፍ ቀጥሎ ክፍተኛውን የሀገሪቱን እኮኖሚ
የሚያንቀሳቅስ እንደመሆኑ መጠን በግንባታ ቦታ ላይ የደህንነት መጓደል ዘርፉ የሚጠበቅበትን
ድርሻ እንዳያበረክት ከማድረጉም በላይ የኢንደስትሪ እድገት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ያሳድራል፡፡
በተጨማሪም ይህ ዘርፍ ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ የስራ እድል የፈጠረና
እየፈጠረም ያለ በመሆኑ የግንባታው ደህንነት ካልጠጠበቀ በስራው ላይ የተሰማራውን ከፍተኛ
የሰው ሀይል ጉዳት ከማድረስም አልፎ በሞት እንዲቀጠፉ ምክንያት ይሆናል፡፡

3.2.8. ከመንገድ ፕሮጀክቶች ጋር የተያያዙ ግኝቶች


ስለሴፍቲ ያለዉ ነባራዊ ሁኔታ
 ካለን ባህል የተነሳ በሴፍቲ ጉዳይ ላይ ስርነቀል የሆነ ለዉጥ አልተደረገም፡፡ በስራ
ተቋራጭም ሆነ በአማካሪው ላይ ክፍተት አለ፡፡ ለማንኛዉም የግንባታ ስራ ቁጥጥር
እንዳለ ሁሉ በሴፍቲ ላይ ያለዉ የቁጥጥር ስርአት ግን አናሳ ነው፡፡ በተለይ
ተቆጣጣሪው አካል የሚጠበቅበትን ያክል አለመስራቱ ጎልቶ የሚታይ ችግር ነው፡፡
 በስራ ፕሮግራም ላይ አጠቃላይ ስላለው ስለስራዉ ሁኔታ እንጂ ስለ ጤንነትና ደህንነት
(ሄልዚና ሴፍቲን) በተመለከተ ዕቅድ አይዘጋጅም፤ የማስፈጸምያውም ስርዓት አናሳ
ነው፡፡
 ትርፋማ ሆኖ ለመዉጣት ስለሆነ የሴፍቲ ማቴርያል በስራ ዝርዝር ዉስጥ በግልጽ
የራሳቸው ክፍያ ስለሌላቸው ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አይበረታቱም፡፡
 የመንገድ ሃብትን ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ የሚቆጣጠር አካል የሚመቻችበት ሁኔታ
አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ለወደፊቱ እየተሰራ ይገኛል፡፡

104
ምስል 3-46 ግንባቸው ሳይጠናቀቅ ለተጠቃሚ ክፍት የሆኑ መንገዶች

ስለሴፍቲ ያለው ግንዛቤ


በግንባታ ስራተኛው በኩል ስለ ግንባታ አካባቢ ደህንነት በቂ ስልጠና ባለመሰጠቱ እና ባላቸው
ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ስለ ግንባታ ደህንነት ያለው ግንዛቤ አነስተኛ ነው፡፡ ስለሚሰሩባቸው
ማሽኖች ሁኔታና ስለአሰራሩ እንኳን የእዉቀት እጥረት እንዳለ ተገልጸዋለ፡፡ ማሽነሪዎች
በሚገዙበት ወቅት አቅራቢው አካል በተዘጋጀ የማሽኑ ማንዋል መሰረት ለኦፕሬተሮች ስልጠና
ይሰጣል፡፡ ከዚህ በዘለለ ደግሞ ረዳት ሆነው እየሰሩ እዉቀታቸውን እንዲያዳብሩ በማድረግ
የማብቃት ስራ ይሰራል፡፡ ተሰርቶ ጥቅም ላይ ያለ ማነሆል ክዳኑን የመጥፋት ሁኔታ አንዱ
የአደጋ መነስኤ በመሆኑ በመንገድ ባለስልጣኑ በኩል ተጠቃሚዉን ህብረተሰብ የኔነነት ሰሜት
እንዲኖረው የግንዛቤ ስራ በአጥጋቢ ሁኔታ አለመሰራቱ ነው፡፡
 በመንገድ ግንባታ ላይ የተሰማሩ የቀን ሰራተኞች የትምህርት ደረጃቸው ዝቅተኛና
ያልተማሩ በመሆናቸው ሰለደህንነት ጥንቃቄ ምልክቶች ግንዛቤው ስለሌላቸው በአግባቡ
ያለመጠቀም ሁኔታ ይታያል፡፡ ግንባታ

105
ምስል 3-47፡ ሠራተኞች የደህንነት አልባሳት ሳይሟላላቸው በመንገድ ስራ ላይ

ስፔስፊኬሽን በተመለከተ
 የሴፍቲ ግንዛቤ በተመለከተ የምንመራበት ሰታንዳርድ ስፔሲፊኬሽን ግርድፍ በሆነ
መልኩ አለ፡፡ ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት በተለየ መልኩ (ስፔስፊክ) ግን አይደለም፡፡ ጉድለት
የለበትም ባይባልም በአመዛኙ ስራ ላይ ስለማይተገበር ግንዛቤው አናሳ ነው፡፡ ሙሉ
ለሙሉ ግን የለም ማለት አይደለም፡፡
የስራ ውል ስምምነት
 በስራ ውል ስምምነት ላይ ሴፍቲን በተመለከተ አለ ነገር ግን ትኩረት በማጣቱና
አስፈፃሚው አካል የሚወስደው እርምጃ ልል በመሆኑ ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም፡፡
በመንገድ ስራ ላይ የሚስተዋሉ አደጋዎችና የአደጋ መንስኤዎች
ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ የአደጋ አይነቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡

የአደጋው አይነት

 በመንገድ መዘጋቱ በሚፈጠረው የመንገድ መጥበበ ቀድሞ ለማለፍ በአሽከርካሪዎች


መካከል የሚደረግ አላስፈላጊ እሽቅድድሞሽ ሳቢያ ተሸከርካሪ ከተሸከርካሪ ጋር ግጭት
 ተሸከርካሪዎች የእግረኞች መንገድ በመጠቀም እግረኞች ላይ አደጋ ማድረስ

106
 ባልተከደኑ ማንሆሎች ማየት የተሳናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች እና የአቅመ ደካሞች
በመግባት ለከፋ አካል ጉዳት መዳረግ
 ተሸከርካሪዎች በመንገድ መረጣ ሳቢያ በሌላ ተሸከርካረ ላይ አደጋ ማድረስ
 የራሳቸው ተሸከርካሪ መሰበር
 በግንባታ ወቅት በሚፈጠረው የመንገድ መዘጋት ተሸከርካሪዎች ተሳስረው ለረጅም ጊዜ
በመቆመም እርስ በርስ መኮራከም

ከትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ እንደሚየሳየው ከመንገድና ኮንስትራክሽን


ግንባታ ጋር ተያይዞ የአደጋ መንስኤና የጉዳት አይነቶች ተብለው የተገለፁጽት የሚከተለውን
ይመስላሉ፡፡

የአደጋ መንስኤዎች

 በግንባታው አካበባቢ አደጋን ለመከላከል የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ያለማድረግ


 ግንባታው ባለበት አካባበቢ ቅድመ መረጃ ለመንገዱ ተጠቃሚ ያለማድረስ
 በግንባታው አካባቢ መጠቀም ያለባቸውን ቅደሚያ መረጃ ያለመጠቀም፤ ለምሳሌ
መንገደዱ መዘጋቱን፤ ሰራተኞች በስራ ላይ በመሆናቸው አሽከርካሪዎች ተጠንቅቀው
እንዲያሽከረክሩ የሚየስጠነቅቅ መረጃ ወዘተ
 የህንፃ ግንባታ ተረፈ ምርት በእግረኛ መንገድ እና በዋና አስፋልተ ላይ በመከመራቸው
እግረኛው ወደ ተሸከርካሪ መንገድ እንዲገባ ይገደዳል
 የከተማውን የትራፊክ እንቅስቃሴ መሰረት ባላደረገ መንገድዋና አስፋልት ላይ የግንባ
ምርት መጫንና ማራገፍ
 የዳታ ኬብል ቀበራ ከተከናወነ በኋላ የእግረኛ መንገድና ዋና አስፋልትን ወደ ነበረበት
ደረጃ ያለመመለስ አና የትርፊክ እንቅስቃሴውን መግታት
 የፍሳሽ ቱቦዎች፤ የኬብል ማስተላለፊያ ቦዮች እና ማን ሆሎች ክፍት አድርገው መሄድ
 የህንፃ ግንባታ ሲካሄድ አደጋ ይመጣል ብሎ በቂ የመከላከል ስራ ያለማድረግ ለምሳሌ
ቸርቸር ጎዳና ላይ ጉድጓድ ውስጥ የገባው ተክሲ እና የደረሰው የሞት አደጋ
 የማስጠንቀቅያ ምልክቶች በተለያዩ አካላት ስለሚነሱ አደጋ ለመፈጠር ምክንያት ሲሆን
ይስተዋላል፡፡

107
ምስል 3-48፡ ምልክት ሳይቀመጥላቸው እየተገነቡ ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች

 ከግንዛቤ እጥረት ባልተናነሳ ሁኔታ በሴፍቲ ዙሪያ ትኩረት ያለመስጠትም በሰፊው


የሚስተዋል ችግር ነው፡፡
 በአብዛኛው በመንገድ ግንባታ ላይ የምሽት ስራ ስላለ ሰራተኞች በፈረቃ እንዲሰሩ
ይመቻል ፡፡
 መንገዶች ዲዛይን ሲደረጉ በራሳቸው ችግር አለባቸው ሴፍቲን በመዘንጋት ለኮስት
ትኩረት ይሰጣል፡፡
 በእግረኛ መንገዶች ላይ የኤሌክትሪክ ፖል፣ የቆሻሻ ማስቀመጫ እና ሌሎችም
ይቀመጣሉ ይህ ደግሞ በተለያየ ሁኔታ አደጋ ሊፈጥር ይችላል፡፡
 በመንገድ ግንባታ ወቅት ትልቅ ችግር እየፈጠረ ያለው የቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር
ነው፡፡ ይህም የመሰረት ልማት ስራዎችን ለማከናወን ሲባል በቴሌኮሙኒኬሽን፣ ዉሃ
ልማትና የኤሌትሪክ ስራዎች መንገዱ ከተጠናቀቀ በኋላ የሚካሄደው የቁፋሮ ስራዎች
በተጠቃሚዉ ላይ ምቹ ያልሆነና አደጋ የመፍጠር ሁኔታ ያስከትላል፡፡
 የመንገድ ግንባታ ርክክብ በሚደረግበት ወቅት ክፍት የሆኑ ማንሆሎች አለመኖራቸውን
ይረጋገጣል ቢሆን ግን ከርክክቡ በሃላ መንገዱን የኔነው ብሎ ካለማሰብ የተነሳ
በአብዛኛው የማንሆል ክዳን በመሰረቁ ምክንያት በተጠቃሚው ህብረተሰብ ላይ በብዛት
አደጋ ሲደርስ ይስተዋላል፡፡
 በተጨማሪም ለኢንስፔክሽን ተብሎ በሚከፈቱ ማንሆሎች ላይ ተከታትሎ መልሶ
የመክደን ችግር ስላለ ይህም ለአደጋው አሰተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ይህንንም ለመቅረፍ
በተለያየ ምክንያት ክፍት የሆኑ ማንሆሎችን በዘመቻ የመክደን ስራ በመንገድ
ባለስልጣኑ ይከናወናል፡፡

108
 ለመንገድ ግንባታ በግብአትነት የሚውሉ ማቴሪያሎችን ከኳሪ ሳይት ከተወሰደ በኋላ
ቦታውን ቀድሞ ወደነበረበት ስለማይመለስ ከዚህ ጋር ተያይዞ በሰው ላይ የአካል ጉዳት
ብሎም የሞት አደጋ እያስከተለ ይገኛል፡፡ምንም እንኳን በህጉ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም
ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም፡፡

ምስል 3-49፡ የወሰን ማስከበር ሂደቱ ሳይጠናቀቅ የተጀመሩ የመንገድ ፕሮጀክቶች

ምስል 3-50፡ ግንባታቸው በአግባቡ ያልተጠናቀቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች

 በአብዛኛው የመንገድ ግንባታ ከታቀደለት ጊዜ ዉጪ የመዘግየት ሁኔታ ይታይበታል፡፡


ይህም በመሆኑ በተጠቃሚው ህብረተሰብ ላይ በተለያየ መልኩ ጫና የመፍጠርና አደጋ
የማስከተል ሁኔታ ይስተዋላል፡፡
109
ህግንና አሰራርን በተመለከተ
 የመንገድ ሃብትን የሚቆጣጠር (Road Asset Managment) አዲስ አደረጃጀት በአዲስ
አበባ ባለስልጣን በኩል ተቋቁሞ በአሁኑ ሰአት ወደ ስራ እየገባ ያለበት ሁኔታ ላይ
ነው፡፡ከዚህም ጋር የስራ አካበቢ ደሀንነትንና ጥራትን የሚቆጣጠርም አዲስ አደረጃጀት
እየተዋቀረ ይገኛል፡፡
 በመንገድ ፐሮጀክት በኩል ከመንገድ ጥበቃና ደህንነት(safety) ጋር በተያያዘ ጥፋት
የሚያደርሱ ኣካላትን ክትትል አድርጎ የሚቀጣበት ጥብቅ ህግ በተቋሙ አለመኖሩ
በግንባታ ቦታ ላይ የሚቀመጡ የደህንነት(safety) ጠቋሚ ምልክቶች በሰፊው ሲሰረቁ
ይስተዋላሉ፡፡
የመጀመርያ ደረጃ ህክምና
 የመጀመርያ ደረጃ ህክምና በየፕሮጀክት ቦታው ላይ በተሟላ መልኩ የለም፡፡ምንም
እንኳን በህጉ እንደግዴታ የጠቀመጠ ቢሆንም ተግባራዊነቱ ዝቅተኛ ነው፡፡

4. የጥናቱ ድምዳሜ
በሀገራችን የኮንሰትራክሽን ኢንደስትሪ ውስጥ በደህንነት መጓደል ምክንያት በስራው ውስጥ ያሉ
እና ከስራው ውጪ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ተጎጂ የሚሆኑበት ሁኔታ እየተበራከተ ነው፡፡
ለዚህም ደግሞ በግንባታ ቦታ ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቁልፍ ተዋንያኖች ማለትም ተቋራጮች፣
አማካሪዎች፣ የግንባታ ባለቤቶች እና ሰራተኞች በግንባታ ቦታ ላይ ለሚከሰቱ አደጋዎች
ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ በአጠቃላይ ከዚህ ጥናት የተገኙ የማጠቃለያ ሀሳቦች
እነደሚከተለው ተቀምጠዋል፤

 ከግንባታ ደህንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን በተመለከተ የተቀመጡ ህጎች


እንደ የፍትሀብሄር ህግ እንዲሁም መመሪያዎች እንደ PPA፣ FIDIC፣ የከተማ
ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የግንባታ መመሪያ፣ EBCS እና የመሳሰሉት የሕግ
ማዕቀፎች ቢኖሩም በግንታው ባለድርሻ አካላት እነዚህ ህጎችና መመሪያዎች በሚገባ
የሚታወቁ ስላልሆኑና ህግን የማስፈፀሚያ ስርአቱ ደካማ በመሆኑ ተግባራዊ እየተደረጉ
አይደለም፡፡ በመንግስት በኩልም ደህንነትን (safety) በተመለከተ የተቀመጡት ህጎችን
ተከታትሎ የማስፈጸም ስርአቱ የላላ ሲሆን ህጎቹን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይም
እርምጃ የመውሰድ ልምዱ አነስተኛ ነው፡፡ እንዲሁም የተሻለ አፈፃፀም ላላቸው ተቋማት

110
የማበረታቻ ስርአት የለም፡፡ ይህም የሆነው ህጉን ተከታለው በሚያስፈጽሙት አካላት
ላይ ተጠያቂነት ባለመኖሩ ነው፡፡

 በተጨባጭ አሁን ባለው የሀገራችን የኮንስትራክሽን ነባራዊ ሁኔታ የግንባታ ደህንነት


ቅድመ ጥንቃቄ (safety) በልምድና በዘፈቀደ እየተሰራ ያለ በአጠቃላይ ትኩረት
ያልተሰጠዉ የተረሳ ጉዳይ ሆኖአል፡፡ ለዚህም ዋነኛው ምክንያት አጠቃላይ
የConstruction management በሚገባ አለመተግበሩ አንዱ አካል የሆነውን የSafety
management ተግባራዊ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ በተጨማሪም ህዝቡ በደህንነት
(safety) ላይ ያለው ግንዛቤ እና ባህል ዝቀተኛ ነው፡፡

 ወደ ሀገር ውስጥ የደህንነት እቃዎችን በሚገቡበት ጊዜ የደህንነት እቃዎችን እንደ


ቅንጦት (Luxury item) እቃ በመቁጠር ከፍተኛ ግብር እንደሚጣልባቸው እና ይህም
ለተጠቃሚው የተሻለ ጥራት ያለውን እቃ በሚያቀርቡበት ጊዜ ዋጋው ከፍተኛ
ስለሚሆን ተጠቃሚውን እንዳይገዛ ያደርገዋል፡፡

 የኮንስትራክሽን ዘርፉ የግንባታ ደህንነት በአግባቡ ባለመተግበሩ ምክንያት የተለያዩ


የህብረተሰብ ክፍሎችን አካል ጉዳተኛም ከማድረጉም ባሻገር እስከ ሞት የሚያደርስ አደጋ
እያስከተለ ነው፡፡

 በግንባታ መመሪያዎች/ በ General Condition of Contract ውስጥ የደህንነት ጉዳይ


እንዱ አካል ሆኖ ቢቀመጥም special condition of contract ውስጥ ደህንነትን
(safety) በተመለከተ በስራ መዘርዝር (specification) ውስጥ በግልጽ የተቀመጠ
ስላልሆነ አማካሪው ባለሙያ መድቦ ከደህንነት(safety) ጋር ተያያዥነት ያላቸውን
ስራዎች አይቆጣጠርም ተቋራጭም አስፈላጊውን የደህንነት አልባሳት እንዲሁም የቅድመ
ጥንቃቄ ምልክቶች አያሟላም በተጨማሪም አደጋ በሚደርስበት ጊዜ ለተጎጂው ሙሉ
ኃላፊነት ያለመውሰድ ሁኔታ አለ፡፡

 አንድ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት በዕቅድ ዉስጥ አደጋ እንዳይደርስ ቅድመ ዝግጅት
ማድረግ ብሎም የሚያጋጥሙ አደጋዎችን ለመቀነስ እንዲሁም ከተከሰቱ በኋላ
የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በቅድሚ risk assessment ተሰርቶ ወደ ስራ
አይገባም፡፡

111
 በህንፃ ግንባታ ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሱ አደጋዎች የሚጠቀሱት ከላይ በመውደቅ፣
ከስካፎልዲንግ መውደቅ እና የአፈር መናድ ሲሆን በመንገድ ግንባታ በኩል ለኳሪ
የተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ መግባት፣ ባልተከደኑ ማንሆሎች ውስጥ መግባት እና የጎረፍ
አደጋ ከፍተኛውን ደርሻ ይወስዳሉ፡፡ ለዚህም በዋናነት ከሚጠቀሱ ምክንያቶች የቅድመ
ጥንቃቄ ዕቃዎች አለመሟላት፣ በአሰሪውም በሰራተኛውም በኩል የሚታይ ቸልተኝነት፣
ምቹ ያልሆነ የስራ ቦታ እና የግንዛቤ ማነስ በቅደም ተከተል ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ፡፡

 በግንባታ ቦታ ላይ የደህንነት ባለሙያ (safety profession) ባለመኖሩ የግንባታ ስራ


የሚያከናውኑትን ማንኛውም የደህንነት ጉዳዮዮ ራሱን ችሎ እንዳይሰራና ትኩረት
እንዲያጣ አድርጎታል፡፡

 በግንባታ ስራ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎች እንደ ሌሎች አደጋዎች በተደራጀ መልክ


አይመዘገቡም፣ ሪፖርት አይደረጉም እንዲሁም ለሚመለከተው አካል የማቅረብና
ተደራሽ የማድረግ ስርአቱ ዝቅተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም ራሱን ችሎ እንደሌሎች
አስተማሪ በሆነ መልኩ የሚዲያ ሽፋን እየተሰጠው አይደለም፡፡

 በግንባታ ደህንነት ዙሪያ አስፈላጊ የሆኑ ስልጠናዎች ለቀን ሰራተኛው እንዲሁም


ለፕሮፌሽናል ባለሙዎች በቋሚነት እየተሰጠ አይደለም እንዲሁም የግንባ ቦታ ላይ
ደህንነትን (safety) በተመለከተ ያለው የቁጥጥር ስርአት አናሳ ነው፡፡ በተጨማሪም
ሰራተኞችንና ማህበረሰቡን በደህንነት ጉዳይ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበት ሁኔታ ትኩረት
ተሰጥቶት እየተሰራ አይደለም፡፡ ይህም ደግሞ የግንዛቤ ማነስን ያስከትላል፡፡

 በአብዛኛው የግንባታ ቦታ ላይ ለሰራተኞች ተብሎ የሚገባ ኢንሹራንስ የለም፡፡ በግንባታ


ስራ ላይ ከስራው ውጪ የሆኑ ማህበረሰብ ተጎጂ የሚሆኑበት ሁኔታ ቢኖርም በሰውም
ሆነ በንብረት ላይ ለሚደርስ አደጋ የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ ከለላ ሙሉ ለሙሉ
እየተገባ አይደለም፡፡
 የመንገድ ግንባታ በሚከናወንበት ወቅት የወሰን ማከበር ሂደቱ ሳይጠናቀቅ ስለሚጀመር
ግንባታው እንዲጓተት ከማድረጉም በላይ ለተለያዩ አደጋዎች መፈጠር ምክንያት
ሆኗል፡፡
 የመንገድ ግንባታዎች ሙሉ ለሙሉ ሳይጠናቀቁ ለተጠቃሚው ክፍት በመሆናቸው
ምክንያት ያልተከደኑ ማንሆሎች ውስጥ በመግባት፣ ለካባ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ

112
በመግባት፣ የጎርፍ አዳጋ እንዲሁም ለመንገድ ግንባታ የሚውሉ ማቴሪያሎች
ከተገለበጡ በኋላ ግንባታው ሲጠናቀቅ የተረፉት ግብአቶች አለመነሳታቸው ከመንገድ
ጋር ተያይዘው ለሚከሰቱ አደጋዎች መፈጠር ትልቅ አስተጽኦ አላቸው፡፡
 የመንገድ ፕሮጀክቶች በሚከናወኑበት ጊዜ ከሌሎች ዘርፎች ጋር ያለው ቅንጅታዊ
የአሰራር ስርአት አናሳ ነው፡፡

113
5. የመፍትሄ ሀሳቦች (Recommendation)
የውል ስምምነት ሰነድን በተመለከተ

 በውል ስምምነት ሰነድ ውስጥ ደህንነት(safety) በአይነትና በመተን ተለይቶ (unite


price) ወጥቶለት እንደ አንድ የውል አካል ሆኖ ቢገባ

የመረጃ አያያዝን በተመለከተ

 ሁለም ባለድርሻ አካላት ማለትም ሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች፣ የግንባታ ባለቤቶችና

ሆስፒታሎቸ እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች ባለደርሻ አካላትም በግንባታ ቦታ


ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን በተደራጀ እና በተቀናጀ መልኩ መዝግቦ የመያዝ እና መረጃን
የመለዋወጥ ልምዳቸውን የሚዳብርበት የአሰራር ስርዓት ቢዘረጋ፣
 በሆስፒታሎች ውስጥ በኮንስትራክሽን ምክንያት የደረሱ አደጋዎችን በተደራጀ መልኩ

የመያዝ እና ተደራሽ የማድረግ ስርአቱ ዝቅተኛ ስለሆነ ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት


የተደራጀ የመረጃ ቋት (data base system) እና ራሱ የቻለ የኮሚፒውተር ባለሙያ
(IT profesion) ተመድቦለት ቢሰራ፣
 በየኮንስትራክሽን ፕሮጀክቱ ያጋጠሙ አደጋዎች እራሱን የቻለ ባለሙያ ተመድቦለት
መረጃዎች በተደራጀ መልኩ የመያዝና ለሚመለከተው አካል ተደራሽ ማድረግ ሌሎች
የህብረተሰብ ክፍሎችን በማዋቀር ተሳታፊ በማድረግ እንደ ባህል ተደርጎ እንዲለመድ
ቢደረግ፡

ህግን በተመለከተ

 የግንባታ ደህንነትን እና ከደህንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ህጎችን እና መመሪያዎች


(safety rules,regulations and laws) ተግባራዊ ለማድረግ አስገዳጅ የሆነ የህግ
ማእቀፍ ቢዘጋጅ እንዲሁም ክፍተቶችን ለይቶ በማውጣት አስገዳጅ ሁኔታዎችንና
የማስፈጻሚያ ሰርአቶችን ማስቀመጥ፤ አሁን ያለዉን የማስፈፀሚያ ስርአት ተከታትሎ
ሁሉንም እንደ አስፈላጊነቱ እርምጃ በመዉሰድ ወደ መስመር ማስገባት እንዲቻል
ተቋጣጣሪ ክፍሉ የወጡ ህጎችንና መመሪያዎችን ተፈጻሚ ማድረግ ቢቻል፤
 በተጨማሪም ደህንነትን (safety) በተመለከተ ያሉ ህጎችንና መመሪያዎችን ጉዳዩ
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸውን አካላት የማሳወቅ ስራ ቢሰራ፤

114
 የሥራ ተቋራጮችም ሆነ የአማካሪዎች የስራ ፈቃድ በሚሰጥበት ወቅት እንደማንኛዉም
ሌሎች ፕሮፌሽን የደህንነት ባለሙያ (safety profession) በመስፈርቱ ዉስጥ ተካቶ
የሚጠየቅበት ሁኔታ ቢመቻች፤
 በተደጋጋሚ አደጋ የሚከሰትባቸው የኮንስትራክሽን ተቋማትን አስፈላጊዉን ማስተካከያ
እንዲያደርጉና የቅጣት እርኮኖችን በማስቀመጥ በተዋረድ ውለታን ማቋረጥና ከዚያም
ሲብስ የስራ ፈቃዱን እስከመሰረዝ የሚያደርስ እርምጃ ቢወሰድ፤
 እንዲሁም የተሻለ አፈጻጸም ያላቸው ተቋማት ከሌሎች ተነጥለው ተጨማሪ ሥራን
በመስጠት፣ የማበረታቻ ሽልማት በመስጠት እንዲሁም የኢንሹራንስ ተቋማት ቅናሽ
እእዲያደርጉ በማድረግ የሚበረታቱበት ሁኔታ ቢፈጠር፤

 የደህንነት እቃዎች በቀላሉ ሁሉንም ተጠቃሚ ለማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ


የደህንነት እቃዎች እንደ ቅንጦት እቃ(Luxury item) መቆጠራቸው ቀርቶ በዜሮ የታክስ
ዋጋ(zero tax price) እንዲያልፍ በማድረግ ሁሉንም ተደራሽ ማድረግ የሚቻልበት
ሁኔታ ቢመቻች፤

የሴፍቲ ባለሙያን በተመለከተ

 በግንባታ ቦታ ላይ ከደህንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን የሚቆጣጠር


የደህንነት(safety) ባለሙያ ቢመደብ
 በግንባታ ደህንነት መጓደል ምክንያት የሚፈጠሩ አደጋዎችንና ችግሮችን ከመቅረፍ
አንጻር የደህንነት (safety profession) ተያያዥነት ባላቸው የሙያ ዘርፍ አግባብነት
ያለውን ስልጠና በመስጠት በደህንነት የብቃት ማረጋገጫ (Certification) እንዲሰጣቸው
ቢደረግ እና ወደ ስራ የሚገቡበት ሁኔታ ቢመቻች
 በተጨማሪም በግንባታ ቦታዎች ላይ የደህንነት ሁኔታውን ለማቆጣጠርና የተሻለ ደረጃ
ላይ ለማድረስ ከሰራተኛው፣ ከተቋራጩ፣ ከባለቤቱ፣ ከህብረተሰቡ፣ ከሙያ ማህበራ፣
ከባንኮች፣ ኢንሹራንስ ካፓኒዎች፣ ከከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከከፍትኛ የትምህርት
ተቋማት የተውጣጣ ቡድን/ኮሚቴ ቢቋቋምና በደህንነት ዙሪያ ላይ በጋራ መስራት
የሚቻልበት ሁኔታ ቢፈጠር፡፡ በተለይ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደህንነትን
በተመለከተ በጥናትና ምርምር በመደገፍ አስፈላጊውን ክተቶችን ሊሞሉ የሚችሉ
ስልጠናዎቸን በመስጠጥ ችግሩን ከመቅረፍ አንጻር የላቀ ድርሻ ስለሚኖራቸው በሰፊው
የሚሳተፉበት ሁኔታ ቢመቻች

115
የሴፍቲ እቅድን በተመለከተ

 ከመጀመሪያው ፕሮጀክት ሲጀመር ተቋራጩ ስለሴፍቲ አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች


ባካተተ መልኩ ዕቅድ ቢያወጣ እንዲሁም የሚዘጋጀው ዲዛይን ሲሰራ የስራ
ደህንነት(safety) ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ
 በፕላኑ ዉስጥ አደጋ እንዳይደርስ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ፣ የደህንነት(safety)
መጠበቂያ አልባሳት ቢሟሉ፣ የደህንነት ምልክቶች በተገቢው ቦታ ቢቀመጥ፣
የመጀመርያ ደረጃ እርዳታ መስጫ አመቺና ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርግ ሁኔታ
ቢኖር፡ ለግንባታ ሰራተኞች ስለሚያከናዉኑት ስራና ማሽነሪዎች ለስራቸው እገዛና
አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ለማድረግ ይረዳቸው ዘንድ አስፈላጊዉን ስልጠና ቢሰጥ፣ አደጋ
በሚከሰት ጊዜ ከከፍተኛ ህክምና እስከ ህይወት ኢንሹራንስ በመግባት ሰራተኛዉ
ተረጋግቶና የኔነት ስሜት ተሰምቶት እንዲሰራ ቢደረግ፣ የደህንነት (safety) መጠበቅያ
አልባሳትን በአግባቡ በማይጠቀሙ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ቢወሰድ የሚሉት ቢያካትት
 በተደጋጋሚ በግንባታ ቦታዎች ላይ የሚደርሱ አደጋዎችንና የአደጋ መንስኤዎችን
እንዲሁም አሰጊ የሆኑ ስራዎች በቅድሚያ ተለይተው ቢቀመጡ፤
 ለተለዩተት አደጋዎችንና መንስኤዎች አስቀድሞ የመፍትሄ እርምጃዎች ቢቀመጡ፤

ስልጠና እና ትምህርትን በተመለከተ

 በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ለሚሰማሩ ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ባለሙያዎች የቀን


ሰራተኞች በሚሰማሩበት የስራ ዘርፍ ደህንነትን (safety) በተመለከተ አስፈላጊው
ስልጠና እንዲሁም ወርክሾፖችን በማዘጋጀት እንዲሰጥ ቢደረግ፤ በተጨማሪም የሙያ
ብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት የሚሰጥባቸውና በዚህ ስርአት የማያልፉትን ወደ
መስመር ለመስገባት በተቋራጩ በኩል ያለው የቅጥር ሁኔታ ውስጥ ቢቀመጥ፤
 ፕሮፌሽናል ባለሙያዎችም ቢሆኑ በደህንነት (safety) ዙሪያ በቂ ግንዛቤው
እንዲኖራቸውና አምነውበት ተግባራዊ እንዲያደርጉት እንደየደረጃቸው በስልጠና ስርአቱ
ውስጥ ቢካተቱ
 ለኮንስትራክሽን ስራ አገልግሎት የሚዉሉ የቁፋሮ ማሽነሪዎች፣ ክሬኖች፣ ሊፍቲኒግ
ኢኩፕመንትና የመሳሰሉት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ስለሚያከናዉናቸው ስራዎች በማኗል
በተደገፈ በሚገባ ስልጠና ቢሰጣቸው፤

116
 ደህንነትን (Safety) በተመለከተ አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶች እንደየትምህርት ደረጃቸው
ከዝቅተኛ የትምህርት ክፍል ጀምሮ እየተሰጠ ቢመጣ እና ወደ ከፍተኛ የትምህርት
ተቋማትም በሚደርሱበት ጊዜ ከግንባታ ስራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው
የደህንነት ኮርሶች በጥልቀት የሚሰጡበት ሁኔታ ቢመቻች
 እንደ አጠቃላይ ከግንባታ ደህንነት ጋር ተያያዥ የሆኑ ችግሮችን በዘለቄታዊ ሁኔታ
ከመቅረፍ አንጻር ግንባታ ደህንነት ሥልጠና ማዕከል (Safety excellency center)
ቢቋቋም
 ሰራተኞች ወደ ግንባታ ቦታ ላይ ስራ በያከናውኑበት ጊዜ በተለያዩ ሱሶች ምክንያት
እየደረሰ ያለው አደጋ እየጨመረ ስለሆነ በሰራተኞች ላይ ተገቢው የሆነ ቁጥጥር
የሚደረግት ሁኔታ ቢመቻች

የግንባታ ማሽነሪዎችን በተመለከተ

 የግንባታ ስራ የሚከናወንባቸው ማሽነሪዎች ላይ እየተደረገ ያለው ፍተሻ በአግባቡ


እየተሰራ ስላልሆነ በሚመለከተው አካል ማሽነሪዎቹ ደረጃቸዉን የጠበቁ መሆናቸዉን
የCalibration እና የደህንነት ፍተሻ ቢደረግላቸው እና ስለ አጠቃቀማቸው ስልጠና
የሚሰጥ በዘርፉ በቂ እዉቀት ያለዉ ባለሙያ ቢመደብ
 በማሽኖች ምክንያት የሚከሰት አደጋ በኦፕሬሽን ላይ እያሉ ብቻ ሳይሆን በማሽን ጥገና
(maintanance) ወቅትም ስለሆነ የጥገና ማንዋል ቢዘጋጅ፤

የሚዲያ ሽፋንን በተመለከተ

 ከግንባታ አካባቢ ደህንነት (safety) ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በህብረተሰቡ ላይ


ጥልቅ ግንዛቤ ለመፍጠር በቂ የሚዲያሽፋን ተሰጥቶት ተከታታይነት ያለው አስተማሪ
የሆነ ማስተወቂያ ቢሰራለት
 በኮንስትራክሽን ዙሪያ ለሚደርሱ አደጋዎች በዋናነት የሚጠቀሱ መንስኤዎችንና
የመፍትሄ ሀሳቦችን በተመለከተ የራሱ ጊዜ ተሰጥቶት በኢንዱስትሪው ዋና ተዋናዮች
እንዲሁም በህብረተሰቡ በኩል ያሉ ሃሳቦችን ማንሸራሸር የሚቻልበት አስተማሪ የሆነ
ፐሮግራም እንዲመቻች ቢደረግ፡

117
የኢንሹራንስ ሽፋንን በተመለከተ

 እንደትራፊክ አደጋ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ለሚደርስ አደጋ የሶስተኛ ወገን


ኢንሹራንስ ከለላ እንዲኖረው ቢደረግ፡
 የኢንሹራንስ ተቋማት በደህንነት (safety) ዙሪያ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ የግንባታ
ድርጅቶችን የሚያበረታቱበት ሁኔታ ቢፈጠር
 በግንባታ ስራ ምክንያት በሰራተኛው ላይ ለሚደርሰውን አደጋ በአፋጣኝ ምላሽ በመስጠት
ሰራተኛውን ተጠቃሚ ለማድረግ እና የይገባኛል መብቱን በአግባቡ ማቅረብ እንዲችል
የሰራተኞች ማህበር ቢቋቋም
የመንገድ ፕጀክቶችን በተመለከተ
 የመንገድ ግንባታ ከመጀመሩ በፊት የወሰን ማስከበር ሂደቱ ቢጠናቀቅ
 ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ አደጋችን ለመቀነስ መንገዶች ለተጠቃሚ
ክፍት ከመሆናቸው በፊት ሙሉ ለሙሉ ግንባታቸው መጠናቀቁ ቢረጋገጥ
 ከሌሎች ዘርፎች ጋር (ከውሃ፣ መብራት ኃይል፣ ከቴሌ) ቅንጅታዊ የአሰራር ስርአት
እንዲኖር ቢደረግ
 የመንገዱን ደህንነት ለመጠበቅና ተጠቃሚውን ሀብረተሰብ መንገዱ በአግባቡ
አንዲያገለግል ከማድረግ አንፃር ከባለስልጣን መስሪያቤቱና ከህብረተሰቡ የተውጣጡ
አካላት አብረው የሚሰሩበት ሁኔታ ቢመቻች

ይህ ጥናት የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ብቻ ስለሆነ እንደ አጠቃላይ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ተግባራዊ ለማድረግ ተጨማሪ
ጥናቶች በደህንነት ዙሪያ ቢካሄዱ እና የሚገኘውንም መረጃ እንደየ ቦተው ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ የሚደረግበት ሁኔታ በመቻች
የተሻለ ውጤትን ያስገኛል፡፡

118
6. ዋቢ
1. J.K.Tan, Dr. Stolz and S.Mijan,(2003), Safet to build and safe to use- A total safety
management system, land transport authority, Singapore
2. S.Wiliiams, (2006), Health and safety in construction, London
3. Cheng, (2004), Safety management assessment framework
4. Mr.chappeu,(2016), Hazzards in construction, Canada
5. የፍትሀብሄር ህግ

6. የቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒሰቴር የግንባታ መመሪያ


7. ነጋሪት ጋዜጣ

8. Ministry of urban development and construction, (August 2013), Ethiopian building code
standards (EBCS 14), Ethiopia

9. Study of H&S as performance indicators on Ethiopian Public (Roads & Buildings)


Construction Projects in case of Addis Abeba City, By Zeru Tariku, July 12, 2014.

10. study of occupational safety and health in ethiopian construction industry: a case study on
addis ababa and welkiteby Seifedin sermolo,(jan. 2014)

11. Ann Herbert, (March 2012); National profile report on occupational safety and health in
China, China
12. John Kreps, Workzone safety in Europe
13. Journal of construction in developing countries, Penerbit university Saris Malaysia (2013);
14. የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፡፡ 2008/2009ዓ.ም፡፡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ የሙያ ደህንነት፣ ጤንነት
ፖሊሲና ስትራቲጂ ረቂቅ ሰነድ፡፡ አዲስ አበባ
15. Site C Clean energy project, june 2015, Construction safety management plan
16. Land transport authority, September 2012, Construction safety handbook
17. Takele.T & Mengesha. A, 2006, Occupational health and safety, Gondar university
18. J.K Tan, D.R Stolz, S. Mijan, 2003, Safet to build and safe to use/ Atotal safety management system,
RTS conference, Singapore
 ፕሮፌሰር አበበ ድንቁ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ እና ማኔጅመንት ቼር

 ዶ/ር አብረሀም

119
7. አባሪ

7.1. መጠይቆች

7.2. ቼክ ሊስት

7.3. ከተለያዩ የግንባታ ቦታዎች የተወሰዱ ፎቶ ግራፎች

120

You might also like