You are on page 1of 23

u›w¡S ¾ ANRS So/Wo/Ad/zone Agriculture Department

Å/¨ KA µ” Ów`“ SU]Á


የዴቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ

በኤክስቴሽን ኮሚኒኬሽን ቡድን የ2012 ዓ.ም ምርት ዘመን ምርጥ


ተሞክሮዎች ቅመራ ሰነድ
አዘጋጅ ምሳዉ ጋሻዉ
የካቲት 2012 ዓ.ም

1
Contents
1.መግቢያ ......................................................................................................................................................... 2
2. የልምድ ቅመራው ዓላማ .................................................................................................................................... 3
3. የልምድ ቅመራው አሠራር ስልት .......................................................................................................................... 3
4. የልምድ ቅመራው የተካሄደባቸው ርዕሶችና ቅመራው የተካሄደበት ወረዳ ዝርዝር ................................................................ 4
5. የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ አርሶአደሮች ቴክኖሎጅዎችን የፈጸሙበት ዝርዝር አሰራር ........................................................... 4
5.1. የኮትቻ አፈርን በዝቆሽ ዘዴ አጠንፍፎ ስንዴ ማልማት.......................................................................................... 4
5.1.1 የወረዳውና የቀበሌው አጠቃላይ ገፅታ........................................................................................................... 4
5.1.2.አሰራሩ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የነበሩ ሁኔታዎች ............................................................................................ 6
5.1.3.አሰራሩን ተግባራዊ በማድረግ የተገኘ ውጤት .................................................................................................. 6
5.1.4. ውጤቱ የተገኘበት ዝርዝር ሂደት ................................................................................................................ 7
5.1.5. ተግባሩን በመፈጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች እና የተፈቱበት አግባብ ..................................................................... 9
5.1.6. ለውጡን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የእያንዳንዱ ባለድርሻ የነበረው .................................................................... 10
5.1.7. ከዚህ ምርጥ ልምድ የተገኘ ተሞክሮ........................................................................................................... 10
5.1.8. የአ/አደሮቹ ወጭ እና ገቢ ....................................................................................................................... 11
5.1.9. የወጭ ዝርዝር ..................................................................................................................................... 11
5.1.20 የገቢ ስሌት........................................................................................................................................ 12
5.1.21.የኮትቻ አፈርን በቢቢኤም በማጠንፈፍ ስንዴን የማምረት ዘዴ ............................................................................. 13
5.12.1.የወረዳውና የቀበሌው አጠቃላይ ገጽታ ...................................................................................................... 13
5.12.2.ቀደም ሲል ቴክኖሎጅውን በመተግበር ረገድ የነበሩ ሁኔታዎች.......................................................................... 14
5.12.3.አሰራሩን ተግባራዊ በማድረግ የተገኘ ውጤት .............................................................................................. 15
5.12.5.ተግባሩን በመፈጸም ሂደት የነበሩ አደናቃፊ አመለካከቶችና የተፈቱበት አግባብ ...................................................... 17
5.12.6.ተግባሩ ተከናውኖ ውጤት ከተገኘ በኋላ የመጣ የአመለካከት ለውጥ .................................................................. 18
5.12.7.ተግባሩ በሚከናወንበት ወቅት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች .................................................................................. 18
5.12.8.ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ ዕርምጃዎች ................................................................................................. 19
5.12.9.የተገኘውን ውጤት ለማምጣት የባለድርሻ አካላት ሚና .................................................................................. 19
5.13.7.ከዚህ ምርጥ ልምድ የተገኘ ተሞክሮ ......................................................................................................... 20
6. የወጭ ዝርዝር ............................................................................................................................................... 21
6.1. የአ/አደሮቹ የገቢ ስሌት............................................................................................................................. 21
6.1.2.ማጠቃለያ........................................................................................................................................... 22

1
1.መግቢያ
ዞናችን በክልላችን በሠብል አምራችነታቸው ከሚታወቁ ዞኖች ውስጥ አንዱ
ነዉ ። በ 2011/2012 ምርት ዘመን በሀገሪቱ ከተመረተው አጠቃላይ ምርት
ውስጥ 10 % የሚሆነው በዚህ ዞን ዉስጥ የተመረተ ነው። በዞኑ የዕድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ እንደተመለከተው በ 2011/2012 ምርት ዘመን 12.2
ሚሊዮን ኩ/ል ምርት ለማምረት የታቀደ ሲሆን ይህም በ 2011/2012 ምርት
ዘመን 10.7 ሚሊየን ኩ/ል ምርት ተገኝቷል ። የዋናዋና ሠብሎች ምርታማነት
በ2011/2012 ምርት ዘመን ከተገኘው 24 ኩ/ል በሄ/ር ወደ 28 ኩ/ል ማደግ
ይኖርበታል። ይህንን ውጤት ለማምጣት ደግሞ በተለያዩ አካባቢዎች ለእያንዳንዱ
ሠብል በፓኬጅ አጠቃቀም መመሪያ ላይ የተቀመጠውን ምክረ-ሃሳብና
የራሣቸውን ዕውቀት በመጨመር ተግባራዊ አድርገው የተሻለ ምርታማነት
ያስመዘገቡ አርሶአደሮችን ተሞክሮ በመቀመር ወደ ሌሎች አካባቢዎች የማስፋት
ስራ (Scalling up) መስራቱ ወሳኝ ተግባር ነው።
በዚህም መሠረት የማስፋት ስትራቴጂውን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል
በተወሰኑ አርሶ አደሮች ተተግብረዉ ዉጤት ያስገኙ አሰራሮች ወደ ሌሎች አርሶ
አደሮች በአጭር ጊዜ ውስጥ በስፋት እንዲደርሱ ለማድረግ እንዲቻል ምርጥ
ልምዶቹ ከመገኘታቸው አስቀድሞ የነበረውን ነባራዊ ሁኔታ፣ አሁን የተገኘውን
ውጤት፣ ውጤቱ የተገኘበትን ዝርዝር ሂደት፣ ውጤቱን በማስገኘት ሂደት
ያጋጠሙ ችግሮችና የተፈቱበት አግባብ እና ከዚህ ምርጥ ልምድ የተገኙት
ተሞክሮዎች ተዘርዝረው ተቀምረዉ ለሚመለከተዉ ደርሰዋል ፡፡

2
2. የልምድ ቅመራው ዓላማ
በክልሉ የሠብል ል/ጥበቃና የአፈር ለምነት ቴክኖሎጅ አጠቃቀምን
በተዘጋጀው የፓኬጅ ምክረ-ሃሳብና የራሳቸውንም ዕውቀት በመጨመር
ተግባራዊ አድርገው ውጤት ያስመዘገቡ አርሶአደሮችን መልካም ተሞክሮ
በጽሁፍና በፎቶግራፍ ዶክመንት በማድረግና ወደሌሎች አካባቢዎች
በማስተላለፍ የ5 ዓመቱን የሰብል ምርት ዕቅድ ማሣካት ነው።

3. የልምድ ቅመራው አሠራር ስልት


 ለልምድ ቅመራው የሚያገለግል የመነሻ ሃሳብ (TOR) ማዘጋጀት፣

 ለእያንዳንዱ ቴክኖሎጅ ለልምድ ቅመራ የሚያገለግል መጠይቅ


ማዘጋጀት፣

 ቴክኖሎጅው በተሻለ ሁኔታ የተፈጸመበትን ወረዳ ዞኖች እንዲመርጡ


ማድረግና ወረዳዎች ደግሞ ቀበሌውን እንዲመርጡ ማድረግ፣

 የልማት ጣቢያ ሙያተኞችን በማነጋገር ውጤቱ የተገኘበትን ዝርዝር


ሂደት መረጃ ማሰባሰብ፣በአካል ተገኝቶ መመልከት

 በተመረጠው ቀበሌ በመገኘት አርሶአደሩ ተግባሩን እንዴት


እንደፈጸመው የቅመራ ስራውን መስራት፣በአካል ተገኝቶ መመልከት
ተግባሩን በመፈጸም ሂደት በወረዳና በቀበሌ ደረጃ የነበሩ አደናቃፊ
አመለካከቶችንና ችግሮችን እንዲሁም የተወሰዱ መፍትሄዎችን
ማሰባሰብ፣

 መስክ ላይ ያሉ ስራዎችን በፎቶግራፍ ማንሳት መስክ ላይ ያልተገኙትን


ደግሞ ቀደም ብለው የተነሱትን መውሰድ፣

3
 በተዘጋጀው መጠይቅ መሠረት የተሰበሰበውን መረጃ ልምዱን
ለመቅሰም በሚያስችል መልኩ መጻፍ ዋናዋናዎቹ ነበሩ።

4. የልምድ ቅመራው የተካሄደባቸው ርዕሶችና ቅመራው የተካሄደበት ወረዳ ዝርዝር


የሠብል ምርትና ምርታማነትን ለማሣደግ የተለያዩ ቴክኖሎጅዎችን
በተዘጋጀው የፓኬጅ ምክረ-ሃሳብ መሠረት መተግበር ወሳኝ ሥራ ነው።
በመሆኑም በቴክኖሎጅዎች አጠቃቀም ምክረ-ሃሳብ መሠረትና
ሌሎችንም ልምዶች በማካተት ተሰርተው ውጤት የተመዘገበባቸው
በመሆናቸው ወደሌሎች አካባቢዎች ቢስፋፉ የሠብል ምርትና
ምርታማነትን በማሣደግ ረገድ ጉልህ ድርሻ ይኖራቸዋል ተብሎ
በሚታመንባቸው ከዚህ በታች በተዘረዘሩ ቴክኖሎጅዎች አጠቃቀምና
ልምድ ዙሪያ የቅመራ ስራው ተከናውኖ ሰነዱ እንዲዘጋጅ ተደርጓል።
ተ.ቁ የልምድ ቅመራ ስራው የወረዳዉ ስም የቀበሌዉ ስም
የተካሄደበት ቴክኖሎጅ
ዓይነት

1 የኮትቻ አፈርን በዝቆሽ ዘዴ ጀማ ወረዳ ሽልአፋፍ (015


አጠንፍፎ ስንዴ ማልማት
ቀበሌ )
2 የኮትቻ አፈርን በቢቢኤም ለገሂዳ ወረዳ ሴደሬ (09 ቀበሌ)
አጠንፍፎ ስንዴ ማልማት

5. የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ አርሶአደሮች ቴክኖሎጅዎችን የፈጸሙበት ዝርዝር አሰራር

5.1. የኮትቻ አፈርን በዝቆሽ ዘዴ አጠንፍፎ ስንዴ ማልማት


የወረዳው ስም- ጀማ የቀበሌው ስም- ሽል አፋፍ (015 ቀበሌ)

5.1.1 የወረዳውና የቀበሌው አጠቃላይ ገፅታ


የጃማ ወረዳ በደቡብ ወሎ ዞን ከሚገኙት 21 ወረዳዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን
ከዞኑ ከተማ ከደሴ በስተምዕራብ አቅጣጫ በ120 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

4
ወረዳው በሰሜን ለገሂዳ ወረዳ፣ በደቡብ የሰሜንሸዋ ወረዳ፣ በምዕራብ ከለላ
ወረዳዎች እንዲሁም በምስራቅ ወረኢሉ ወረዳዎች ያዋስኑታል።
ወረዳው 21 የገጠር ቀበሌዎች 1 የንዑስ ከተማ ቀበሌዎች በድምሩ 22 ቀበሌዎች
ያሉት ሲሆን የአ/አደር ብዛቱም ወንድ 17763 ሴት 2582 በድምሩ 20345
ይደርሳል። የወረዳው ዋና ዋና የግብርና ምርቶ
ጤፍ፣ስንዴ፣በቆሎ፣ማሽላ፣አተር፣ባቄላናቸው። እነዚህ ሰብሎች የሚመረቱት
በመኸር ነዉ ።

ስዕል1.የጃማ ወረዳ ካርታ

ጥቁር አፈርን በዝቆሽ በማጠፈፍ ስንዴን በመዝራት ጥሩ ተሞክሮ የተገኘበት


የሽል አፋፍ ቀበሌ ከወረዳው ዋና ከተማ ጀማ በደቡብ አቅጣጫ በ13 ኪ/ሜ
ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ የቀበሌው የህዝብ ብዛት በድምሩ 7550 ይደርሳል። አጠቃላይ
የቀበሌው የቆዳ ስፋት --3761.2 ካ.ሜትር ስኮየር ሲሆን ከዚህ ውስጥ -2086
ሄ/ር ለእርሻ ስራ ሲዉል ቀሪዉ ለሌሎች አገልግሎቶች የሚዉል ነዉ ነው፡፡
የሽልአፋፍ ቀበሌ የመኸር የዝናብ ተጠቃሚ ሲሆን ጤፍ፣ ፣ስንዴ፣ ማሽላ ና
ባቄላ በዋናነት በመኸር ወቅት ይመረታሉ። በ2011/2012 ምርት ዘመን በቀበሌው

5
በመኸር ወቅት ስንዴ 1096 ሄክታር የተዘራ ሲሆን 65 ኩንታል ምርጥ ዘር
ጥቅም ላይ ውሏል።

5.1.2.አሰራሩ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የነበሩ ሁኔታዎች


በወረዳው ስንዴ ዋና የገበያ ሰብል በመሆኑ በስፋት ይመረታል። ስንዴ ቀደም
ሲል የሚዘራው በብተና ሲሆን ከዘሩ መጠን ማነስ ጋር ተያይዞ ስንዴን በጥቁር
አፈር ላይ በዝቆሽ ለመዝራት ይቻላል ተብሎ የተሞከረበት ጊዜ አልነበረም። ከዚህ
በተጨማሪ ስንዴ በጥቁር አፈር ላይ ከተዘራ ብዙ ምርት አይሰጥም ብሎ ማሰብ
ነበር። ይህም አመለካከት በየደረጃው ባለ አመራር፣ ባለሙያና አርሶአደር ጎልቶ
ይታይ ነበር። በዞን ና በወረዳ ደረጃ በስንዴ አመራረት ላይ ከዚህ በፊት የሚሰጡ
ስልጠናዎችም የተሻለ ዝርያ ከመጠቀምና የማዳበሪያ አጠቃቀምን ከማሻሻል አንፃር
ብቻ የተቃኙ ነበሩ።

5.1.3.አሰራሩን ተግባራዊ በማድረግ የተገኘ ውጤት


ስንዴን በጥቁር አፈር ላይ በማጠፈፈ መዝራት በወረዳውም ሆነ በቀበሌው
አዲስ ከመሆኑ አንፃር ወረዳው በስርቶ ማሳያነት በሁሉም ቀበሌዎች
በመሞከር ውጤታማነቱን ለማሳየትና የበለጠ እንዲሰፋ ለማድረግ እንዲቻል
በ2011/2012 ምርት ዘመን 1096 ሄክታር ስንዴ በጥቁር አፈር በማንጣፈፍ
በተሟላ ፓኬጅ እንዲዘራ ተደርጓል። ስንዴን በጥቁር አፈር በማጣፈፍ
በተሟላ ፓኬጅ ስልጠና ወስደው ተግባራዊ በማድረግ ጥሩ ውጤት
ያስመዘገቡት አርሶ-አደር ሀሚድ የሱፍ በ 0.25 ሄክታር ማሳ ላይ ደፍረው
አዲሱን አሰራር ተግባራዊ አድርገዋል። እንደ አርሶ-አደሩ ገላፃ ከሆነ ስንዴን
በጥቁር አፈር ላይ በማጠፈፍ/በዝቆሽ/ መዝራት ምቹ እንደሆነና የሰብሉ
አቋምም በጣም የፋፋ ወፍራም ግንድና የፍሬ አያያዙም የበለጠ እንደሆነ
ገልፀው በተለይ ለማረምና ለመሰብሰብ ምቹ እንደሆነ ገልፀዋል። የፍሬ
አያያዙን ሲገልፁም በአንድ ራስ እስከ 25 ዘር እንዳገኙጠቁመዋል።በመስመር
የተዘራው ስንዴ ማዘርዘር የጀመረውም ከብተና ከተዘራው ቀድሞ ነው።
6
ማሳው አረምም በብዛት አልታየበትም በዚህም የተነሳ ከሁለት ጊዜ በላይ
አላረሙም።
በአጠቃላይ ስንዴን በዝቆሽ በመዝራታቸው ከአንድ ሄክታር ማሳቸው 39
ኩንታል ምርት አግኝተዋል።በነባሩ አሰራር (በብተና) ቢሆን ግን ከ 20
ኩንታል በላይ አግኝተው እንደማያውቁና በአርሶአደርነት ቆይታቸው እንደዚህ
አይነት የስንዴ ምርት አያያዝ አይተው እንደማያውቁም ገልፀዋል።

ሰዕል.2. የጀማ ወረዳ 015 ቀበሌ አ/አደሮች የስንዴ ክላስተር ተሞክሮ

5.1.4. ውጤቱ የተገኘበት ዝርዝር ሂደት


የእነዚህ አርሶ አደሮች ተሞክሮ ለሌሎችም ስንዴ አምራች አርሶ አደሮች
ማስፋፋት እንዲቻል ስኬቱ የተገኘበትን ዝርዝር ሂደት እንደሚከተለው
ለመቀመር ተሞክሯል፡፡
ዞኑ በተለያዩ ወረዳ ዎች የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን ወዴ ሌሎችም
አካባቢዎች በማስፋፋት ምርትና መርታማነትን ለማሳደግ በያዘው እቅድ
መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ ስለ እስትራቴጅው እውቅና እንዲኖር በየደረጃው
ላሉ ባለሙያዎች፣ አመራሮችና አርሶአደሮች ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ የግንዛቤ
መፍጠር ስራዎች ተሰርተዋል። ከዚህ በተጨማሪ በ2010/2011 ምርት ዘመን
7
በአዲሱ ፓኬጅ መሰረት ለአርሶአደሮች የክህሎት ስልጠና የተሰጠ ሲሆን
ከተሳተፉት አርሶአደሮች ውስጥ አርሶአደር ሀሚድየሱፍ፣አህመድ መሃመድ
፣ካሳዉ አሰፋ፣ዳምጠዉ ለገሰ፣ዱባለ አየለ እና በላይገዙ ናቸው። አርሶአደሮቹ
በስልጠናው ባገኙት ግንዛቤ መሰረት ስንዴን በማጠፍፈ/ዝቆሽ/ በመዝራትና
ሌሎችን የእንክብካቤ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ለሌሎችም አርዕያ
የሚሆን ውጤት አግኝተዋል።
አርሶአደር አህመድ መሃመድ በ 2011/2012 ምርት ዘመን መኸር ወቅት
ስንዴን በጥቁር አፈር ላይ በዝቆሽ የዘሩበት 1.25 ሄክታር ማሳ ባለፈው
አመት ጤፍ ተዘርቶበት የነበረ ማሳ ነው። አርሶአደሩ ማሳቸውን ሶስት ጊዜ
ደጋግመው አርሰዋል፤ አንደኛ እርሻ መጋቢት14፣ ሁለተኛ እርሻ ማዚያ 20፣
ሶስተኛ እርሻ ሰኔ 5፤ አርሰዋል። በመጨረሻም በአራተኛዉ እርሻ ሀምሌ 5
ቀን 135 ኪሎ ግራም ስንዴ ምርጥ ዘር ዳንፊን ዝርያ በአንድ ሄክታር
ማሳቸው ላይ ዘሩ። የዘር ስራውን ያከናወኑት በሶስት ዕቃ በሬ ሲሆን ሶስት
የሚያርስ ሰው ፣ ሶስት የዝቆሽ ስራ የሚሰሩ በድምሩ 6 ሰው በዘር ወቅት
ተጠቅመዋል።
በዘር ወቅት 120 ኪሎግራም ዳፕና 100 ኪሎ ግራም ዩሪያ ቀላቅለው
ዘርተዋል፡፡
አርሶአደሮቹ ስንዴን በዝቆሽ ከዘሩ በኋላ የተለያዩ የእንክብካቤ ስራዎችን
ሰርተዋል። የአረም ድግግሞሽን በተመለከተ ሶስት ጊዜ አርመዋል፤
የመጀመሪያ ዙር አረም ሀምሌ 30 ፣ሁለተኛ ዙር አረም መስከረም መጨረሻ
ሳምንትና ሶስተኛ አረም ጥቅምት ወር መጀመሪያ አካሂደዋል። የመጀመሪያ
ዙር አረም እንዳረሙም ዩሪያ በአናት ላይ ጨምረዋል። እንደ አርሶአደሮቹ
ገላፃ ከሆነ በሽታና ተባይ በማሳቸው ላይ አንዳልተከሰተ ገልፀዋል።

8
5.1.5. ተግባሩን በመፈጸም ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች እና የተፈቱበት አግባብ
ስንዴን በጥቁር አፈር በዝቆሽ ከመዝራት አንፃር በአካባቢው የሚታዩ ብዙ
ጎታች የአመለካከት ችግሮች ነበሩ። በበጋ ደጋግሞ አለማረስ፣ ስንዴ ሞላ ብሎ
ካልተዘራ ምርት አይሰጥም፣ የተሻሻሉ ዝርያዎችን በስፋት አለመጠቀምና
ዋጋውን አጋኖ ማየት፣ማሳው ሰፊ ስለሆነ ሁሉንም በዝቆሽ ለመሸፈን ጉልበት
ያንሳል ብሎ ማሳብ፣ አምና የተከሰተውን ቢጫ ዋግ ዘንድሮም ይከሰታል ብሎ
በመፍራት ስንዴ ለመዝራት አለመፈለግ ጎልተው የሚታዩ ችግሮች ነበሩ።
ከዚህ በተጨማሪ በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ በሚሰጡ ስልጠናዎችም
የተሻሻለ የስንዴ ዝርያና የማዳበሪያን አጠቃቀምን ከማሳደግ አንፃር ብቻ
የተቃኙ ነበሩ።
ይህንን የአመለካከትና የክህሎት ችግር ለመፍታት በዞን እና በወረዳ ደረጃ
የሰብል ልማት ፓኬጅ ስልጠና በየደረጃው ላሉ ሙያተኞች፣ አመራር አካላት
እና አ/አደሮች ስልጠና በየደረጃው የወረዳና የቀበሌ ሙያተኞች በዘር ስራው
እገዛ አድርገውላቸዋል።የእነዚህ የአርሶአደሮች ስንዴን በጥቁር አፈር ላይ
በዝቆሽ መዝራት በብተና ከተዘራው የበለጠ የሰብል አቋም ያለው በመሆኑ
በቀበሌ ደረጃ ሶስት ዙር የአርሶአደር ባዕል በማዘጋጀት አርሶአደሮችን
ተሞክሮ እንዲወስዱና በቀጣይ ጊዚያት በተመሳሳይ መልኩ እንዲሰሩ
ለመቀስቀስ ተችሏል።

9
ስዕል 3. የአ/አደር ባዕል ሲካሄድ ጀማ ወረዳ በተሰራዉ ስራ
5.1.6. ለውጡን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት የእያንዳንዱ ባለድርሻ የነበረው ሚና
የእነዚህ አ/አደሮች ስንዴን በዝቄሽ በመዝራት ውጤት ሊያመጡ የቻሉት
የተለያዩ የአመራርና ባለሙያዎች ድጋፍ ከፍተኛ ስለነበረ ነው። የቀበሌ
ሙያተኞች በአርሶአደር መረጣ በዘር ወቅት በሙያና በጉልበት በማገዝና
በየጊዜው የመስክ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ተሳትፈዋል። የወረዳ
ሙያተኞች ስልጠና በመስጠት በዘር ወቅት የሙያና የጉልበት ድጋፍ
በማድረግና ከተዘራም በኃላ የመስክ ድጋፍ በማድረግ አስታዋፅኦ ነበራቸው።
የቀበሌ አስተዳደር አካላት በዘር ወቅት የጉልበት እገዛ አድርገዋል ።
የአገልግሎት የህብረት ስራ ማህበራትም በወቅቱ የስንዴ ምርጥ ዘርና
ማዳበሪያ በማቅረብ እገዛ አድርገዋል።

5.1.7. ከዚህ ምርጥ ልምድ የተገኘ ተሞክሮ


በእነ አርሶ-አደር አህመድ መሀመድ የተገኘው ጥሩ ተሞክሮ የሚሳየው ስንዴን
በጥቁር አፈር ላይ በዝቆሽ በመዝራትና ሌሎችን የእንክብካቤ ስራዎችን
በፓኬጁ መሰረት ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ ምርት ማግኘት እንደሚቻል
ያሳያል። በዝቆሽ በመዝራታቸው ለማረምና ሌሎችን የእንክብካቤ ስራዎችን

10
ለመስራት ምቹ እንደሆነም አሳይተዋል። በዝቆሽ የተዘራው ስንዴ በአካባቢው
በብተና እና ያለዝቆሽ ከተዘራው ይልቅ በፍሬ አያያዙ የግንዱ ውፍረትና
ዝናብ በተከሰተበት ወቅትም መሬቱ ዉሃ ያላዘለ መሆኑን ከዚህ ተሞክሮ
ለማወቅ ተችሏል። በአዲሱ አሰራር (ስንዴን በዝቆሽ) በመዝራታቸው 39
ኩንታል/ሄክታር ያገኙ ሲሆን በነባሩ አሰራር (በብተና) ግን ከ 20 ኩንታል
በላይ አግኝተው እንደማያውቁ ገልፀዋል ።

5.1.8. የአ/አደሮቹ ወጭ እና ገቢ

5.1.9. የወጭ ዝርዝር


ተ. ተግባራት በላይ ገዙ ዱባለ አየለ ሀሚድ አህመድ ካሳዉ አሰፋ ዳምጠዉ ለገሰ
ቁ የሱፍ መሃመድ

ወጭ ገ ወጭ ገቢ ወጭ ገ ወጭ ገቢ ወጭ ገ ወጭ ገቢ
ቢ ቢ ቢ
1 ማዳበሪያ 1245 1460 1420 1556 1556 1420
1.1 ም/ዘር 780 500 450 1400 750 450
1.2 አረም 300 500 450 650 550
1.4 አጨዳ 400 250 800 1000 1000 700
1.5 ለግዞሽ 160 100 100 200 100
1.6 ለዉቂያ 200 150 120 150 1000 100
1.7 መሬት
ኮንትራት
1.8 ለቀን ሰራተኛ

1.9 ጠ/ወጭ 3085 3060 3340 4956 4306 3320

11
5.1.20 የገቢ ስሌት
ተ. ተግባራት በላይ ገዙ ዱባለ አየለ ሀሚድ አህመድ ካሳዉ አሰፋ ዳምጠዉ
የሱፍ መሃመድ ለገሰ

ወ ገቢ ወጭ ገቢ ወ ገቢ ወ ገቢ ወ ገቢ ወ ገቢ
ጭ ጭ ጭ ጭ ጭ
2 የገቢ ዝርዝር

2.1 የምረት ሽያጭ 45500 56000 31500 68250 66500 59500


ገለባ 2000 1500 1000 2500 2000
2.2 1500
ጠ/ገቢ 47500 57500 32500 70750 68500
2.3 61000
ትርፍ(2.3-1.9) 44415 54440 29160 65794 64194
3 57680
ገቢ÷ለወጭ(2.3÷1.9) 14.4 17.8 8.7 13.3 15
4 17.4

12
5.1.21.የኮትቻ አፈርን በቢቢኤም በማጠንፈፍ ስንዴን የማምረት ዘዴ
የወረዳው ስም- ለገሂዳ የቀበሌው ስም- ሴደሬ (09 ቀበሌ)
5.12.1.የወረዳውና የቀበሌው አጠቃላይ ገጽታ

ስዕል 4.የለገሂዳ ወረዳ ካርታ

የለገሂዳ ወረዳ በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ከሚገኙት 21 ወረዳዎች ውስጥ አንዱ


ሲሆን ከደሴ ከተማ 105 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።ወረዳው በሰሜን ለጋምቦ
ወረዳ፣በደቡብ ጀማ፣ በምስራቅ ወረኢሉ ወረዳ ይዋሰናል። የወረዳው የቆዳ ስፋት
51607.4 ሄ/ር ሲሆን ከዚህ ውስጥ ለእርሻ አገልግሎት 27607 ሄ/ር፣ለግጦሽ
12340 ሄ/ር፣ ለደንና ቁጥቋጦ 4392.5 ፣ ለመንደር አገልግሎት 4274 ሄ/ር፣
ቀሪው 2992.1 ሄ/ር ደግሞ ለሌሎች አገልግሎቶች እንደዋለ ከወረዳው ግብርና
ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ወረዳው 15 ቀበሌዎች ያሉት ሲሆን የህዝብ ብዛቱም 39182 ወንድና 39659
ሴት በድምሩ 78841 እንደሚሆን ይገመታል።የወረዳው የአየር ንብረት 24.4 %

13
ወርጭ 5.16 ወይናደጋና 70.44% ደጋ ሲሆን ከባህር ወለል በላይ ከፍታው
ከ1644_3409 ሜ ይደርሳል።ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ ከ 900-1200 ሚ.ሜ
ሲሆን አመታዊ የሙቀት መጠኑ ደግሞ ከ10-22.5 ዲ.ሴ ነው። በወረዳው ውስጥ
ከአለው አፈር 24.3 % ኮትቻ ፣44.8 % ቡናማና 10.8 % ቀይ እንደሆነ ነጭ
አሸዋማ 6.9% ይገመታል አለታማ 10.31% ።
በወረዳው ከሚመረቱ ሰብሎች ውስጥ ስንዴ፣ ጤፍ፣ ምስርና ባቄላ የሚጠቀሱ
ናቸው። በ 2010/2011 ምርት ዘመን በወረዳው 22169 ሄ/ር መሬት ታርሶ
በተለያዩ ሠብሎች ተሸፍኗል።
የኮትቻ አፈርን በማጠንፈፍ ስንዴን በመጀመሪያው ዙር በማልማት ልምድ
የተቀመረበት የሰደሬ ቀበሌ ከወረዳዉ ከተማ ያለው ርቀት 17 ኪ. ሜ ነው። የቆዳ
ስፋቱም 3,402 ሄ/ር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 2,224 ሄ/ር መሬት ለእርሻ አገልግሎት
፣370 ሄ/ር ለግጦሽ፣307 ሄ/ር በደንና ቁጥቋጦ ፣ 35 ሄ.ር በውሃ የተሸፈነና 397
ሄ/ር ለመንደር ግንባታ ስራ የዋለ ነው። ቀበሌው በሰሜን ከደንቀዝ፣በደቡብ
ከይማዳ፣ በምዕራብ ከጀይራና ደጎላ ቀበሌና በምስራቅ ከአምባጨራ ቀበሌ ጋር
ይዋሰናል። የአየር ንብረቱ 100% ወይና ደጋ ሲሆን ዓመታዊ የዝናብ መጠኑ
ሰብልን ለማምረት በቂ ነው። ከባህር ወለል በላይ ከፍታው ደግሞ ከ1800-2000
ሜ ነው። አፈሩም 71% ቡናማ፣26% ቀይ እና 4% ኮትቻ አፈር ነው።
በቀበሌው 1026 ወንድና 571 ሴት በድምሩ 1597 አባወራና እማወራዎች
የሚኖሩ ሲሆን አጠቃላይ የህዝብ ብዛቱ 3,183 ወንድና 3,257 ሴት በድምሩ
6440 ነው። ጤፍ፣ ስንዴ፣ ባቄላና ምስር በቀበሌው የሚበቅሉ ዋናዋና ሰብሎች
ናቸው ።
5.12.2.ቀደም ሲል ቴክኖሎጅውን በመተግበር ረገድ የነበሩ ሁኔታዎች
ወረዳው ሠፊ የኮትቻ አፈር ሽፋን ያለው ቢሆንም በክላስትር የማምረት ተግባር

ያልተለመደ ተግባር ነበር፣ማሣው በዓመት አንድ ጊዜ ጤፍ እና ምስር ይዘራ


ነበር። የኮትቻ አፈር ውሃን የመያዝ አቅሙ ከፍተኛ ስለሆነና በዓመት ሁለት ጊዜ

14
ለማምረት የሚያስችል ሁኔታ ቢኖርም በአካባቢው በኮትቻ አፈር ላይ ስንዴ
አይመረትም፣ውሃውን ማጠንፈፍ አይቻልም፣ቢቢኤምን በሬው መጎተት
አይችልም በሚል ጎታች አስተሳሰብ ምክንያት በኮትቻ አፈር ላይ ሰብልን ሁለት
ጊዜ በማምረት መገኘት የሚገባውን ያህል ምርት ሳይገኝ ቆይቶ ከ2002 ምርት
ዘመን ጀምሮ በ 145 ሄ/ር መሬት ላይ በ 420 አርሶአደሮች ተሳትፎ የአፈሩን
ትርፍ ውሃ በቢቢኤም በማጠንፈፍ የመጀመሪያውን ዙር ሰብል ምርታማነት
ከማሣደግ በተጨማሪ የመጀመሪያው ሰብል እንደተሰበሰበ በሚኖረው ዕርጥበት
ሁለተኛ ሰብልም ለማምረት ተችሏል።

5.12.3.አሰራሩን ተግባራዊ በማድረግ የተገኘ ውጤት


በወረዳው ከ 2010/2011ምርት ዘመን ጀምሮ በየደረጃው በአሉ የመስተደድርና
የግብርና አካላት በተደረገው የቅስቀሳ ስራና ሠርቶ ማሣያዎችን ሰርቶ የገበሬ
በዓል በማዘጋጀት ሌሎች አርሶአደሮች እንዲማሩበት በመደረጉ በ 50 ሄ/ር መሬት
ላይ የተጀመረው የክላሰተር ስራ በ 2011/2012 ምርት ዘመን 5566.58 ሄ/ር
የኮትቻ አፈርን 10603 አርሶአደሮች የማጠንፈፍ ስራ በመስራት የስንዴ ሰብልን
በክላሰተር በመዝራት ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል።

15
ስዕል 5 . በቀበሌው ኮትቻ አፈርን በክላስተር በማጠንፈፍ የተዘራ የስንዴ ሰብል
የኮትቻ አፈርን ትርፍ ውሃ አጠንፍፈው ከዘሩ አርሶአደሮች ውስጥ አንዳንድ
አርሶአደሮች በመጀመሪያው ዙር ልማት ብቻ በሄ/ር ስሌት እስከ 70 ኩ/ል የስንዴ
ምርት አምርተዋል።በዚህ ምርት ዘመን በ 09 ቀበሌ አቶ አራጋዉ ዘይኑ ከ
0.25 ሄ/ር መሬት ላይ 17.5 ኩ/ል ወይም በሄ.ር ስሌት 70 ኩ/ል፣ አቶ ይመር
ከበዴ ከ 0.25 መሬት ላይ 14.5 ኩ/ል በሄ/ር 58ኩ/ል ፣አቶ አረብ መሃመድ ከ
0.75 ሄ.ር መሬት ላይ 16 ኩ/ል በሄ/ር 21 ኩ/ል እና አቶ ሁሴን መሃመድ ከ
0.25 ሄ/ር መሬታቸዉ ላይ 12-ኩ/ል በሄ/ር 48 የስንዴ ምርት አግኝተዋል።
5.12.4.ውጤቱ የተገኘበት ዝርዝር ሂደትና አሠራር
በወረዳው በምርት ዘመኑ የኮትቻ አፈርን በማጠንፈፍ በክላስተር የስንዴ ሰብል
የዘሩ 10603 አርሶአደሮች የነበሩ ቢሆንም ከወረዳው ውስጥ በ09ቀበሌ ነዋሪ
የሆኑት የአቶ አራጋዉ ዘይኑ፣አቶ ሁሴን መሃመድ ፣ አቶ አረብ መሃመድ ና
አቶ ይመር ከበዴ አሰራር እንደሚከተለው ቀርቧል።
እነ አቶ አራጋዉ ዘይኑ ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ማሣቸውን ጤፍ፣ሽብራ ፣
ምሰር እና ጓያ ወይንም መሬቱን ጦም በማክረም የክረምቱ ዝናብ ከወጣ በኋላ
ሽምብራ ብቻ ያመርቱበት የነበረ ሲሆን ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን ማሣውን
በዓመት ሁለት ጊዜ በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን ችለዋል። አርሶአደሮቹ

16
በአለፈው ዓመት ሽብራ ዘርተውት የነበረውን 0.25 ሄ/ር መሬት የመጀመሪያውን
እርሻ መጋቢት መጀመሪያ፣ ሁለተኛውን እርሻ መጋቢት መጨረሻ፣ ሶስተኛውን
እርሻ ሃምሌ 5 አርሰዉ ቢቢኤም ተጠቅመው ሃምሌ 18 ቀን ትክክለኛ የንሽ
ወቅት ስለነበር የዘር ስራውን አከናውነዋል።
አርሶአደሮቹ የተጠቀሙት የስንዴ ዝርያ ዳንፊን ሲሆን የዘር መጠኑ 37.5 ኪ.ግ
ነበር ። ስንዴው የተዘራው በብተና ነው። እያንዳንዳቸዉ የተጠቀሙት የማዳበሪያ
መጠን 0.5 ኩ/ል ዳፕና 0.25 ኩ/ል ዩሪያ ሲሆን አጨማመሩም በዘር ወቅት
ዳፑን ሙሉ በሙሉና አንድ ሶስተኛውን ዩሪያ በመቀላቀል በማሣው ላይ
በትነዋል። የመጀመሪያውን አረም ስንዴው በተዘራ በ 24ኛው ቀን ከአከናወኑ
በኋላ ቀሪውን ዩሪያ የአፈሩን ዕርጥበት ግምት ውስጥ በማስገባት በብተና
ጨምረዋል። ሁለተኛው አረም ደግሞ ሀምሌ መጨረሻ ላይ ተከናውኗል።
አርሶአደሮቹ በክረምት ወቅት የቦይ ከፈታ ስራ የሠሩ ሲሆን ሠብሉ ለመታጨድ
ሲደርስ ታህሳስ 20 /2012 ዓ.ም ተሰብስቦ እንዲከመር ተደርጓል። ከዚያም መሬቱ
መጀመሪያ ተጠርቦ፣ ውሃ ተርከፍክፎ፣ገለባ ተነስንሶና በሰው እግር በሚገባ
ተጠቅጥቆ እንዲደርቅ ከተደረገ በኋላ የዉቂያ ስራዉ የካቲት 20 ቀን የውቂያ
ስራው ተከናውኗል። አርሶአደር አቶአራጋዉ ዘይኑ ከ0.25 ሄ/ር መሬት ላይ
17.5 ኩ/ል የስንዴ ምርት ወይም በሄ/ር ስሌት 70 ኩ/ል አግኝቷል።

5.12.5.ተግባሩን በመፈጸም ሂደት የነበሩ አደናቃፊ አመለካከቶችና የተፈቱበት አግባብ


በወረዳውም ሆነ በቀበሌው የኮትቻ አፈርን በማጠንፈፍ ሂደት ከነበሩ አደናቃፊ
አመለካከቶች ውስጥ በአካባቢው በኮትቻ አፈር ላይ እንዴት ስንዴ ሊመረት
ይችላል፣ ቢቢኤሙ ለበሬዎች ይከብዳቸዋል፣ ስንዴ የምንዘራ ከሆነ የማዳበሪያውን
ዋጋ መክፈል አንችልም፣ (እንከስራለን) አንድ አይነት ሰብል መዝራት በተባይ
ይጠቃል የሚሉት ዋናዋናዎቹ ነበሩ። ኮትቻ አፈርን በማልማት በክላስተር
ማልማት እንደሚቻልና ቢቢኤሙን በንሽ ወቅት ከተጠቀምን ለበሬዎቹ
እንደማይከብድ የቅስቀሳ ስራ በመስራት፣ ስራውን ተግባራዊ ባደረጉና ውጤታማ
17
በሆኑ አርሶአደሮች ማሣ ላይ የገበሬ በዓል በማዘጋጀትና ሌሎች እንዲማሩበት
በማድረግ የተጠቀሱ አደናቃፊ አመለካከቶችን ለመስበር ጥረት በመደረጉ
የሚጠበቀውን ያህል እንኳ ባይሆንም ከላይ የተገለጹ ለውጦችን ለማምጣት
ተችሏል።

5.12.6.ተግባሩ ተከናውኖ ውጤት ከተገኘ በኋላ የመጣ የአመለካከት ለውጥ


በአሁኑ ወቅት በወረዳው የኮትቻ አፈር ባለባቸው ቀበሌዎች በማሣ ላይ
የሚኖረውን ትርፍ ውሃ የማጠንፈፍ ስራ በመስራት የተለያዩ ሰብሎችን
በክላስተር ማምረት በመቻሉ ከዚህ በፊት በቴክኖሎጅው ላይ የነበሩ አሉታዊ
አመለካከቶች እየተለወጡ መጥተዋል። ይህም በመሆኑ ከዚህ በፊት ቴክኖሎጅውን
የማይጠቀሙ በርካታ አርሶአደሮች ወደ ተግባር ስራው በመግባት ላይ ናቸው።
በ2010/11 ምርት ዘመን በወረዳው የኮትቻ አፈርን በማጠንፈፍ ተጠቃሚ
የነበሩት 1260 አርሶአደሮች ብቻ ሲሆኑ በ2011/2012 ምርት ዘመን 10603
አርሶአደሮች ተጠቃሚ ሆነዋል።

5.12.7.ተግባሩ በሚከናወንበት ወቅት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች


 ኮትቻ አፈርን በጋ ላይ ለማረስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ማሣውን
የሚፈለገውን ያህል ማለስለስ አለመቻል፣

 አርሶአደሩ የማዳበሪያ አጠቃቀምን በፓኬጅ ምክረ-ሃሳቡ መሠረት


ተግባራዊ አለማድረግ፣

 አፈሩ ከባድ ኮትቻ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለይ ፉዛርየም የስር አበስብስና


የዛላ በሽታን ሊቋቋም የሚችልና ቶሎ ደራሽ የስንዴ ዝርያ አቅርቦት
አለመኖር፣

 የክረምት ወቅት ከባድ በሚሆንበት ጊዜ ውሃው በሚገባ ስለማይጠነፍፍ


የሰብሉ ምርታማነት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆን ዋናዋናዎቹ ነበሩ።

 በክላስተር ሁሉም በአንድ ቀን ወጥቶ ያለማረስ እና ያለመዝራት


18
 ትርፍ ዉሃን በኩሬ ቆፍሮ ለዳግም ሰብል ሁሉም አ/አደርች ተግባራዊ
አለማድረጋቸዉ፡፡

5.12.8.ችግሮችን ለመፍታት የተወሰዱ ዕርምጃዎች


 አፈሩን ዝናብ የሚጥልበትን ወቅት በመጠበቅ እንዲታረስ በማድረግና
በመደጋገም እንዲለሰልስ ከተደረገ በኋላ በንሽ ወቅት ሰብሉ እንዲዘራ
ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፣

 አርሶአደሮች በምክረ-ሃሳቡ መሠረት እንዲጠቀሙ ለማድረግ ከዚህ


በፊት ፓኬጁን ተግባራዊ ያደረጉ አርሶአደሮችን ተሞክሮ በማሣየት
በምክረ-ሃሳቡ መሠረት እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው።

 የክረምት ወቅት ከባድ በሚሆንበት ጊዜ ቦዮችን ተከታትሎ የመክፈት


ስራ ለመስራት ጥረት ተደርጓል።
 አ/አደሮቹ በክላስተር የመዝራት ጥቅምን በስፋት ስልጠና እንዳገኙ
ተደርጓል ፡፡
 ግባዕት እና ተክኖሎጅን ቅድሚያ በክላሰተር ለተደራጁ አ/አደሮች
እንድዴርስ ተደርጓል፡፡

5.12.9.የተገኘውን ውጤት ለማምጣት የባለድርሻ አካላት ሚና


 የኮትቻ አፈር ልማትን ውጤታማ ለማድረግ የወረዳ አስተዳደር
አመራር፣የግብርና ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎችን በየቀበሌው
በመመደብ ለአርሶአደሩ ከፍተኛ የቅስቀሳ ስራ አከናውነዋል፣

 የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ከወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት


10ኛ ክፍል የጨረሱ ተማሪዎችን አሰልጥኖ በዘር ወቅት አርሶአደሮችን
እንዲያግዙ ተደርጓል።

19
 ተግባሩን ለሚያከናውኑ አርሶአደሮች የተግባር ስልጠና በመስጠት
በኩል የወረዳና የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎች ድርሻቸውን
ተወጥተዋል።

 የቀበሌ ባለሙያዎች ተሣታፊ አርሶአደሮችን የመመልመል፣የማሣ


ልየታ ስራን የመስራትና በዘር ወቅት አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍ
የማድረግ ስራ ሰርተዋል።

 የአገልግሎት የኅብረት ስራ ማህበራትም ዘር፣ማዳበሪያና ቢቢኤም


በማቅረብና ብድር በመስጠት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ጥረት
አድርገዋል።

5.13.7.ከዚህ ምርጥ ልምድ የተገኘ ተሞክሮ


በእነ አርሶአደር አራጋዉ ዘይኑ የተገኘው ጥሩ ተሞክሮ የሚያሳየው ከባድ
ኮትቻ አፈር(መረሬ) ባለበት ደጋማ አካባቢ ቢቢኤም ተጠቅሞ ስንዴን
በክላስተር መዝራት እንዴ ሚቻል አሳይተዋል። አርሶአደሮቹ ስንዴን
በጥቁር አፈርላይ በቢቢኤም በማጠፈፍ ሀምሌ አጋማሽ በመዝራታቸውና
ትክክለኛውን የማዳበሪያ መጠን ከምርጥ ዘር ጋር አቀናጅተው
በመጠቀማቸው ከዚህ በፊት በባህላዊ ከሚያገኙት 20 ኩንታል በሄክታር
ወደ 70 ኩንታል በሄክታር አሳድገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከአካባቢው ስነ ምህዳር አንፃር ዳንፊን የስንዴ ዝርያ
ከሌሎች የስንዴ ዝርያዎች የተሻለ ምርት መስጠት የሚችል ስለሆነ የዚህ
ዝርያ ዘር በአካባቢው በስፋት መቅረብ እንዳለበት ያሳያል።

20
የአ/አደሮቹ ወጭ እና ገቢ

6. የወጭ ዝርዝር
ተ.ቀ የስራእና አራጋዉ ይመር አረብ ሁሴን መሃመድ
የግባዕት
ዘይኑ ከበዴ አህመድ
ዝርዝር
ወጭ ገቢ ወጭ ገቢ ወጭ ገቢ ወጭ ገቢ

1 ማዳበሪያ 1369 1369 1369 1300

1.1 ም/ዘር 1530 1200 1200 1200

አረም 1000 500 600 1000


1.2
አጨዳ 1000 500 400 600
1.3
1.4 ለግዞሽ 320 250 250 250

1.5 ለዉቂያ 600 300 600 750

1.6 መሬት 0 0
ኮንትራት
1.7 ለቀን 320 240
ሰራተኛ
1.9 ጠ/ወጭ 6139 4119 4419 5340

6.1. የአ/አደሮቹ የገቢ ስሌት


ተ. አራጋዉ ዘይኑ ይመር ከበዴ አረብ አህመድ ሁሴን
የገቢ ዝርዝር መሃመድ

ወ ገቢ ወ ገቢ ወ ገቢ ወ ገቢ
ጭ ጭ ጭ ጭ

2. የምረት ሽያጭ 122500 101500 36750 48000

2.1 ገለባ 8000 8000 5000 7000


2.2 ጠ/ገቢ 130500 109500 41750 91000
3 ትርፍ(2.3-1.9) 124361 105381 37331 85660
4 ገቢ÷ለወጭ(2. 20.26 25.6 8.4 16.04
3÷1.9)

21
6.1.2.ማጠቃለያ
የግብርናው ዘርፍ የሃገሪቱ ዋናው የኢኮኖሚ ምሰሶ በመሆኑ ግንባር ቀደም/
ምርጥ አ/አደሮች የፈጸሙትን ተግባርና ያገኙትን ውጤት ሌሎችም አ/አደሮች
እንድተገብሩትና ተጠቃሚ እንድሆኑ በስፋት በሰራት ይኖርበታል፤
o በምርጥ /በግንባርቀደሞችም ሆነ በሌሎች አ/አደሮች የሚመረቱ ምርቶችን
በገበያ ተፈላጊና የተሸለ ዋጋ ሊያወጡ የሚችሉ ማድረግ ይጠበቃል፤
o ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር፤ በገበያ ተፈላጊና የተሸለ ዋጋ ያላቸውን
ምርቶች ለማምረት ግብዓትና ቴክኖሎጅን አጠቃቀም ተደራሽነትን በሁሉም
አ/አደሮች በእኩል መጠን፤ ጥራትና ጊዜ ለማስረጽ ሰፊ ርብርብ ማድረግ
ያስፈልጋል፤
o ይህ የምርጥ ልምድ የተለያየ አካባቢዎች የተወሰደ ስለሆነ የተገኘውን
ምርጥ ልምድ ከአንዱ አካባቢ ወደ ተመሳሳይ አካባቢ በማሸጋገር
እንዲተገበር ማድረግ የእያንዳንዱ ወረዳ የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊነት
ሊሆን ይገባል፡፡

o ይህን የምርጥ ልምድ ቅመራ መነሻ በማድረግ ሀገራዊ የማስፋፋት


ስትራቴጂውን ለማሳካት ወረዳዎች የራሳቸውን ምርጥ ልምዶቻቸውን
ቀምረው ወደ ሌሎች በማስተላለፍ ሀገራዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

22

You might also like