You are on page 1of 25

Table of Contents

0
ዋና ማጠቃለያ (Executive Summary)................................................................................................2
መግቢያ..............................................................................................................................................2
1.1 የዞኑ አጠቃላይ ገጽታ...........................................................................................................................2
1.2 የወረዳው አጠቃላይ ገጽታ.....................................................................................................................3
1.3 የቀበሌው አጠቃላይ ገጽታ.....................................................................................................................4
2.የአርሶ አደሩና የንግድ ሥራው አጠቃላይ ገፅታ......................................................................................5
2.1 የአርሶ አደሩ ሁኔታ..............................................................................................................................5
2.2 የእርሻ ሥራና የንግድ ሥራ ሁኔታ.............................................................................................................5
2.3 ጠንካራና ደካማ ጎኖች፣ ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች............................................................................................6
3. የአርሶ አደሩ ራዕይና ተልዕኮ...............................................................................................................7
4. የንግድ ሥራ ዕቅዱ ግቦች..................................................................................................................7
5. የግብርና ምርትና ሜካናይዜሽን አጠቃቀምና አገልግሎት አሰጣጥ ዕቅድ.................................................7
5.1. የግብርና ምርት እቅድ..........................................................................................................................8
5.2. የግብርና ሜካናይዜሽን ፍላጎት እቅድ.......................................................................................................12
5.3. የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት አሰጣጥ (የግብይት) ዕቅድ..........................................................................14
5.4. የአርሶ አደሩን አገልግሎት ማስተዋወቅ፣....................................................................................................16
6. የግብርና ምርት ማሳደጊያ እና የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስትራቴጂ............................16
6.1. የግብርና ምርት ማሳደጊያ ስትራቴጂ........................................................................................................16
6.2. የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስትራቴጂ....................................................................................16
6.3. የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለመስጠት (የመስሪያ ቦታ) በተመለከተ.......................................................................17
6.4. የአርሶ አደሩ የግብርና ምርት እና ንግድ ስራ አመራር.....................................................................................17
7. የፋይናንስ ዕቅድ.............................................................................................................................19
7.1. አጠቃላይ የፋይናንስ ዕቅድ..................................................................................................................19
7.2. የግብርና ምርቶችና የአገልግሎት ሽያጭ እቅድ.............................................................................................19
7.3. የሀብትና ዕዳ መግለጫ.......................................................................................................................21
7.4. የትርፍና ኪሣራ መግለጫ...................................................................................................................22
7.5. የጥሬ ገንዘብ ፍሰት መግለጫ................................................................................................................23
8. የብድር አከፋፈል መርሃ-ግብር......................................................................................................23
የአመላለስ ጊዜው የተሰላው በዓመት 2 ጊዜ (በየስድስት ወሩ) ነው፡፡...................................................................23
9. የትርፋማነት መለኪያ.................................................................................................................24
9.1.ከአጠቃላይ ኢንቨስትመንት የሚገኝ ትርፍ..................................................................................................24
9.2.የንግድ ሥራ ዕቅዱ አዋጭነት................................................................................................................24

1
ምዕራፍ አንድ፤ አጠቃላይ ገጽታ

1.1. የዞኑ አጠቃላይ ገጽታ

የጋሞ ዞን በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከሚገኙ አስራ ስድሰት ዞኖች መካከል አንዱ ነው፡፡ ዞኑ
8222.4 ካሬ ኪ/ሜትር ወይንም 822,242.8 ሄክታር አጠቃላይ ቆዳ ስፋት ያለው ሲሆን የክልሉ 11.5 በመቶ
ነው ፡፡ ከዚህ ውስጥ ለእርሻ የዋለ 490,213.85 ሄ/ር ፤ በደን የተሸፈነ 133759 ሄ/ር ለግጦሽ የዋለ 88222 ሄ/ር
በሌሎች የተያዘ 107281.8 ሄ/ር፤ ሊለማ የሚችል 19414 ሄ/ር፤ ሊለማ የማይችል 53772 ሄ/ር እና በውሃ አካል
የተሸፈነ 78020.5 ሄ/ር ነው፡፡

የዞኑ ህዝብ ዋነኛ መተዳደሪያ እርሻ ሲሆን በቆሎ፤ ጤፍ፤ ቦሎቄ ስንዴ፤ ገብስ ማሽላ ሲሆን ከጥራጥሬ ሰብል
አተር፤ ባቄላ እና ከስራሰር ሰብል ድ/ድንች፤ እንሰት፤ ካሳቫ ጉልህ ድርሻ ያላቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪም
ከፍራፍሬ ልማት አኳያ ሙዝ፤ ማንጎ፤ አፕል ዋነኛ የሚመረቱ ሲሆኑ ከቅባት ሰብል ሰሊጥ፤ ለውዝ እና
ከጭረት ሰብል የጥጥ ምርት ዞኑ ከሚታወቅባቸው የግብርና ምርቶች ተጠቃሽ ናቸው ፡፡

በዞኑ የሚታረሰ መሬት 490648.9 ሄ/ር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የብርዕ ሰብሎች 111093.4 ሄ/ር፣ የአገዳ ሰብሎች
59335.48 ሄ/ር፣ ጥራጥሬ ሰብሎች የሚለማ ማሳ 63419.56 ሄ/ር፣ በስራስር ሰብሎች የሚለማ ማሳ
84933.84 ሄ/ር፣ በጓሮ አትክልት የሚለሙ ሰብሎች ማሳ 30702.5 ሄ/ር፣ የጭረት ሰብሎች የሚለማ ማሳ
32680.79 ሄ/ር፣ ቅመማ ቅመም ሰብሎች ማሳ 3049.9 ሄ/ር፣ ቋሚ አዲስና ነባር ሰብሎች ሚለማ ማሳ
96863.29 ሄ/ር ነው ፡፡

በዞኑ 14 የገጠር ወረዳና 4 የከተማ አሰተዳደር በድምሩ 18 መዋቅር የሚገኝ ሲሆን በአግሮ ኢኮሎጂ የአየር
ቀጠና ስንመለከት ደጋ 47 በመቶ፤ ወ/ደጋ 27 በመቶ እና ቆላ 26 በመቶ ነው፡፡ በዞኑ ውስጥ የሚኖር ህዝብ ብዛት
1,800,817 ሲሆን አባወራ 170681 እማወራ 14396 ድምር 185077 ነው ፡፡ ከዚህ ውስጥ የግብርና
ኤክስቴንሽን ተጠቃሚ አርሶ አደሮች ብዛት ወንድ 193656 ሴት 70186 ድምር 263842 ነው ፡፡

የዞኑ ርዕሰ ከተማ አርባ ምንጭ ከአዲስ አበባ 505 ኪሎ ሜትር እንዲሁም ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ሀዋሣ 275 ኪሎ
ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ ዞኑ ከክልሉም ሆነ ከሀገሪቱ ርዕሠ መዲና ወደ ዞኑ የሚያደርሱ ከአንድ በላይ

2
አማራጭ አስፋልት መንገዶች ያሉትና ከአብዛኞቹ በዞኑ ሥር ከሚገኙ ወረዳዎች ጋር በአስፋልት መንገድ
ከቀሩት ወረዳዎች ጋር በጠጠር መንገድ የተገናኘ ነው፡፡

በዞኑ ውስጥ በስፋት ከሚመረቱ ሰብሎች እንደ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄ፤ ማሾ፤ ሰሊጥ፤ ማሽላ፤ ጥጥ፤ ስንዴ፣
ገብስ፤ ድ/ድንች፤ ባቄላና አተር ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ዞኑ የተለያዩ የውሃ አማራጮችን እንደ አባያና ጫሞ ሃይቅ
እና ሌሎች ትላልቅ ወንዞች፣ ጅረቶችና ምንጮችን በመጠቀም የሆርቲካለቸር ሰብሎች ፍራፍሬ ማንጎ፤
ሙዝ፤ የደጋ አፕል እና የጓሮ አትክልት ቲማቲም፣ ቀ/ሽንኩርት፣ ቃሪያ፣ ካሮት፣ ቀ/ስር፤ ጥቅል ጎመን፣ አበሻ
ጎመንና ሌሎችንም አትክልቶችን በማምረት ለአዲስ አበባ፣ አዳማ፤ ባህር ዳር፤ ጎንደር፤ መቀሌ፤ ሌሎችም
ከተሞች የሚያቀርብ ሲሆን ወደፊትም እነዚህንና የመሣሰሉ ምርቶች በብዛትና በጥራት አምርቶ ለማቅረብ
የሚያስችል እምቅ የመሬት፣ የውሃ ሀብትና ተስማሚ የአየር ንብረት ያለው በክረምት በቂ ዓመታዊ ዝናብ
የሚያገኝ ዞን ነው፡፡ አጠቃላይ በዞኑ ውስጥ ካሉት 14 ወረዳዎች መካከል ለእርሻ ሜካናይዜሽን ምቹ የሆኑ
ወረዳዎች ዳራማሎ ፤ ቁጫ፤ ቦረዳ፤ ምዕራብ አባያ፤ አርባምንጭ ዙሪያ እና ካምባ ናቸው ፡፡

አጠቃላይ በዞኑ ከሚታረሰ መሬት 490,648.9 ሄ/ር ላይ ለእርሻ ሜካናይዜሽን ምቹ የሆነ እርሻ መሬት መጠን
------- ሄ/ር ስሆን ከዚህ ውስጥ ዳራማሎ ------ ሄ/ር፤ ቁጫ 34080 ሄ/ር ቦረዳ ------- ሄ/ር፤ ምዕራብ
አባያ------- ሄ/ር፤ አርባምንጭ ዙሪያ------ ሄ/ር እና ካምባ----ሄ/ር ነው፡፡ በእነዚህ እርሻ ሜካናይዜሽን
በትራክተር በሚታረሱ ወረዳዎች እጅግ በጣም ሰፋፍ ዘመናዊና ባህላዊ መስኖ ውሃ ያለባቸው ወረዳዎች
ከመሆናቸውም በላይ በዓመት ሶስት ጊዜ በልግ፤ በጋ መስኖ እና መኽር ማልማት የሚያስችል አቅም ያለባቸው
አከባቢዎች ናቸው ፡፡

1.2. የወረዳው አጠቃላይ ገጽታ

የቁጫ ወረዳ በጋሞ ዞን ከሚገኙ አስራ አራት ወረዳዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ወረዳዉ 98661.851 ሄክታር
አጠቃላይ ቆዳ ስፋት ያለው ሲሆን የዞኑ 12 በመቶ ነው ፡፡ ከዚህ ውስጥ ለእርሻ የዋለ 34080 ሄ/ር ፤ በደን
የተሸፈነ 2606.8 ሄ/ር ለግጦሽ የዋለ 29487 ሄ/ር፣ ቁጥቋጦ 8498 ሄ/ር በሌሎች የተያዘ 7655.75 ሄ/ር፤ ሊለማ
የሚችል 19233 ሄ/ር፤ ሊለማ የማይችል 5599 ሄ/ር ነው፡፡ የወረዳዉ ህዝብ ዋነኛ መተዳደሪያ እርሻ ሲሆን
ከአገዳ ሰብሎች በቆሎ እና ማሽላ፣ ከብርእ ሰብሎች ጤፍ፣ ከጥራጥሬ ሰብል ባቄላ፣ ቦሎቄ እና ማሾ ከስራሰር
ሰብል ስ/ድንች፣ እንሰት፤ ካሳቫ ጉልህ ድርሻ ያላቸው ናቸው፡፡ በተጨማሪም ከፍራፍሬ ልማት አኳያ ሙዝ፤
ማንጎ፤ ብርቱካን ዋነኛ የሚመረቱ ሲሆኑ ከቅባት ሰብል ሰሊጥ፤ ተልባ እና ከጭሬት ሰብል ጥጥ፣ ከአንቂ ሰብል
ቡና በስፋት የሚመረት ምርት ወረዳዉ ከሚታወቅባቸው የግብርና ምርቶች ተጠቃሽ ናቸው ፡፡ በወረዳዉ
የሚታረሰ መሬት 34080 ሄ/ር ስሆን ከዚህ ውስጥ በአመታዊ ሰብሎች 30647 ሄ/ር እና ቋሚ ሰብሎች ሚለማ
ማሳ 3433 ሄ/ር ነው ፡፡ ወረዳዉ 24 ገጠር ቀበሌ እና 1 ታዳጊ ማዘጋጃ ከተማ አሰተዳደር በድምሩ 25 መዋቅር
የሚገኝ ሲሆን አግሮ ኢኮሎጂ የአየር ቀጠና ስንመለከት ደጋ 24 በመቶ እና ቆላ 76 በመቶ ነው፡፡

3
አጠቃላይ በወረዳዉ ከሚታረሰ መሬት 34080 ሄ/ር ላይ ለእርሻ ሜካናይዜሽን ምቹ የሆነ እርሻ መሬት መጠን
12258 ሄ/ር ስሆን ከዚህ ውስጥ ባሶ 1100 ሄ/ር፤ ስቆሌ 475 ሄ/ር፤ ኩሎ 310 ሄ/ር፤ ወዛቴ 1120 ሄ/ር፣ ሾጮራ 70
ሄ/ር፣ ሞርካ 1140 ሄ/ር እና ካፕሳ 210 ሄ/ር ጋሌ 1200 ሄ/ር ዳና 130 ሄ/ር ነው፡፡ በእነዚህ እርሻ ሜካናይዜሽን
በትራክተር በሚታረሱ ቀበሌዎች እጅግ በጣም ሰፋፍ ዘመናዊና ባህላዊ መስኖ ውሃ ያለባቸው ቀበሌዎች
ከመሆናቸውም በላይ በዓመት ሶስት ጊዜ በልግ፤ በጋ መስኖ እና መኽር ማልማት የሚያስችል አቅም ያለባቸው
አከባቢዎች ናቸው፡፡

1.3. የቀበሌው አጠቃላይ ገጽታ

ባሶ ቀበሌ በቁጫ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ ከ 24 ቀበሌያት አንዷ ስትሆን የቀበሌዉ ሕዝብ ብዛት ወ 3162 ሴ
2950 ድምር 6112፣ አባወራ 830 እማወራ 19 ድምር 849 በቀበሌዉ የሚታረስ ማሳ 1500 ሄ/ር ሲሆን ከዚህ
ዉስጥ በትራክተር ለማረስ ምቹ የሆነ 1100 ሄ/ር ነዉ፡፡ በቀበሌዉ የሚለሙ ሰብሎች በቆሎ፣ ጤፍ፣ ማሾ፣
ማሽላ፣ ሰሊጥ፣ ቦሎቄ፣ሽምብራ፣ ከአትክልት ቀይ ሽንኩርትና ሌሎች ሰብሎች ይመረታሉ፡፡ አ/አደር ፍፁም
ደስታ የዚህ የዉዘቴ ቀበሌ ነዋሪና በእርሻ ሥራ የሚተዳደር ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆን እስከአሁን
ባለው ሁኔታ ያለኝን 2.05 ሄ/ር ማሣ በራሴና ከአካባቢው በኪራይ በማገኛቸው በሬዎች እንዲሁም አልፎ አልፎ
የትራክተር የኪራይ አገልግሎት በሚሰጡ ግለሰቦች የሚቻለኝን ያህል መሬቴን እያለማሁ በበልግና በመኸር
ወቅት በቆሎ፣ ማሾ፣ ሰሊጥ፣ በርበሬ፣ ቦሎቄ እና ሌሎች ሰብሎችን አመርታለሁ፡፡ ሆኖም ይዞታዬ ከሆነው
መሬት ወስጥ ባለኝ ባህላዊ መሣሪያና የአመራረት ዘይቤ በጣም ጥቂቱን ብቻ ማልማት የቻልኩ ስለሆነ ገቢዬ
በቂ ወይንም አጥጋቢ የሚባል አይደለም፡፡ ከእርሻ ሥራ ባሻገር የግብርና ምርቶችን ከአ/አደሩ በተሻለ ዋጋ
በመግዛትና ራሴ ያመረቱክትን ምርት ወደ ሌሎች አጎራባች ገበያዎች በመዉሰድ እየሸጥኩ ተጨማሪ ገቢ
አገኛለሁ፡፡ ሆኖም ከዚህ በላይ የግብርና ሥራዬን ለመሥራት የሚያስችል በቂ መሬትና ጊዜ እያለኝ ተወስኖ
የቆየውን የእርሻ ሥራዪን ለማሰፋፋት የሚያስችል የብድር አቅርቦት በመንግሥት በኩል በመመቻቸቱ በዋናነት
ያለኝን አጠቃላይ ማሣ በበልግ ማሾ፣ ቄይሽንኩርት እና ቲማቲም በመኸር ማሾ፣ ሰሊጥ፣ ቄይሽንኩርት እና
ቲማቲም እንዲሁም በበጋ መስኖ ቄይሽንኩርት እና ቲማቲም ከፍተኛ ምርት ለማግኘት እንዲያስችለኝ
የተለያዩ የምርት ማሣደጊያ ግበዓቶችንና ምርት ማሣደጊያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የማመርት ሲሆን
ለአካባቢዬ አርሶ አደሮች የተለያዩ የኪራይ አገልግሎቶችን በማቅረብ ገቢዬንና ሥራዬን ለማሻሻል አቅጃለሁ፡፡

ክፍል ሁለት፤ የአርሶ አደሩና የንግድ ሥራው አጠቃላይ ገፅታ

4
2.1. የአርሶ አደሩ ሁኔታ

እኔ አርሶ ፍፁም ደስታ የተባልኩ የባሶ ቀበሌ ነዋሪ የሆንኩ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባትና በእርሻ ሥራ ተሰማርቸ
የሚሰራበት 2.05 ሄ/ር መሬት በእጄ ይገኛል፡፡ ይህንን መሬትም ከሌላ ወረዳ ትራክተር ተከራይቼ በማምጣት ግማሽ ያህሉን
በማረስ እየተጠቀምኩ ቢሆንም የፈለግኩትን ያህል ምርት ማሳደግ አልቻልኩም፡፡ ፡፡ በቅርብ ጊዜ እየተስፋፋ ከመጣው
የሜካናይዜሽን አገልግሎት አንጻር ትራክተር ተከራይቼ ከመጠቀም ገዝቼ የትራክተር ተጠቃሚ ብሆን እርሻ ማሳዬን አሁን
ካለኝ 25 በመቶና በላይ በማሳደግ ምረታማነቴን ለመጨመርና ኑሮዬን ለማሻሻል የበለጠ ይረዳኛል፡፡ ስለሆነም ይህንን
ዕቅዴን ለማሳካት እና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲሁም የበለጠ ውጤታማ ለመሆን ትራክተር መግዛት
አስፈልጎኛል፡፡

2.2. የእርሻ ሥራና የንግድ ሥራ ሁኔታ

እኔ አርሶ አደር ፍፁም ደስታ በምኖርበት ዉዘቴ ቀበሌ ሥነ ምህዳር የሚመሩቱ የግብርና ምርቶችን ማለትም
በበልግ 2.05 ሄ/ር መሬት፡- ለማሾ 1 ሄ/ር፣ ለቀይሽንኩርት 0.55 ሄ/ር ለቲማቲም 0.5 ሄ/ር በድምሩ 2.05 ሄ/ር፤
በመኸር 2.05 ሄ/ር መሬት፡- ለማሾ 1.5 ሄ/ር፣ ለቀይሽንኩርት 0.5 ሄ/ር እና በበጋ መስኖ 2.05 ሄ/ር መሬት፡-
ለቀይ ሽንኩርት 1.05 ሄ/ር ለቲማቲም 1 ሄ/ር በድምሩ 2.05 ሄ/ር በማረስ በአጠቃላይ በዓመት 844 ኩ/ል ምርት
አገኛለሁ፡፡ ከማገኘው ምርት ውስጥም ለቤተሰብ ፍጆታ ከሚውለው 10 ኩ/ል ባሻገር ለአካባቢውና አጎራባች
ከተሞች ገበያ በማቅረብ እና በመሸጥ ገቢ በማግኜት እተዳደራለሁ፡፡

ከፍ ሲል እንደገለጽኩት የግብርና ምርቶችን የማመርተው በባህላዊ መንገድ የነበረ ሲሆን ከዚህ ዓመት ጀምሮ
ደግሞ ከግብርና ሜካናይዜሽ ቴክኖሎጂዎች መካል አንዱ በሆነው ትራክተር ዘመናዊ የእርሻ ሥራየን ለማናወን
አቅጃለሁ፡፡ ትራክተር ስገዛም ታሳቢ ያደረኩት በዋናነት ለግሌ የእርሻ ማረስ ሥራና በተጨማሪነት ሌሎች
ተቀጽላዎችን በመጠቀም የማስፋፊያ ስራ አካሂዳለሁ፡፡ ለዚህ እንዲረዳኝ የምገዛው ትራክተር በዋናነት የራሴ
እርሻ በበልግ 2.05 ሄ/ር መሬት፣ በመኸር 2.05 ሄ/ር መሬት ለግሌ በማረስ ጊዜ፣ ወጪና ጉልበትን በሚቆጥብ
ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ ባሻገር ገቢዬን ማሳደግ በሚያስችል ስራዬን በተደራጀ መልክ ለመምራት
አቅጃለሁ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የትራክተር እርሻ አገልግሎት ሌሎች የአካባቢው እና አጎራባች ወረዳ ለሚገኙ
አርሶ አደሮች ወቅቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት በማገኘው ገቢ ኑሮዬን ከማሻሻል ባለፈ መካከለኛ ገቢ
ያለው አርሶ አደር ለመሆን የሚያስችለኝ የግብርና የንግድ ስራ ዘርፍ እንደሚሆን እተማመናለሁ፡፡

ለዚህ እንዲረዳኝም የግብርና ምርቶችን የማምረት ስራዬና የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎቴ ውጤታማ
እንዲሆኑ የኤክስንሽን ምክር አገልግሎት የሚሰጡ፣ የተሟላ የግብርና ግብአት ፓኬጅ የሚያቀርቡና
ለሜካናይዜሽን አገልግሎት ስራ ደግሞ ትራክተር ኦፕሬተርና የሂሳብ ሠራተኛ በመቅጠር የማሰራ ስሆን
ከተማሩ ልጆቼ ጋር በመሆን አስተዳደራዊ ሥራዎችን የማከናውን ይሆናል፡፡

5
2.3. ጠንካራና ደካማ ጎኖች፣ ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች

 ጠንካራ ጎኖች
 በእርሻ ሥራ የዳበረ ልምድ ያለኝ መሆኑ
 ሞዴል አርሶ አደር መሆኔ
 በቂ መሬት ያለኝ መሆኔ
 የመካናይዜሽን አገልግሎት መጠቀም መጀመሬ (ትራክተር ተከራይቼ ማሳረሴ)
 የተማርኩና ማንበብና መጻፍ መቻሌ
 ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር ተቀራርበና በመናበብ መሥራት መቻሌ፣
 ደካማ ጎኖች
ትራክተሩን ራሴ ኦፕሬት ማድረግ አለመቻሌ

ቀደሞ በቀበለዉ ትራክቴር ገዝቶ የተለማመደ ሰዉ ስለሌለ ልምድ ልዉዉጥ ዉስንነት

 ምቹ ሁኔታዎች
 አካባቢው ለመካናይዜሽን ምቹ መሆኑ
 የግብርና ተክኖሎጂዎችን ለማቅረብ ምቹ መንገድ መኖሩ፣
 መንግስት ብድር ማመቻቸቱ፣
 በአካባቢው የሜካናይዜሽን ተክኖሎጂዎች የመጠቀም ፍላጎት መኖሩ፣
 የሜካናይዜሽን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ድጋፍ ከመንግስትና ከሌሎች አካላት የሚገኝ መሆኑ
 ስጋቶች
 የአየር ሁኔታ መለወጥ
 ከፍተኛ የሆነ የገበያ ውድድር ሊኖር ይችላል
 የመለዋወጫ እቃዎች በመጠንና በጊዜ ያለመገኘት

3. የአርሶ አደሩ ራዕይና ተልዕኮ


ራዕይ- በ 2018 መጨረሻ መካከለኛ ገቢ ካላቸው የግብርና ኢንቨስተሮች ውስጥ አንዱ መሆን

ተልዕኮ- የራሴንና የከባቢዬን የእርሻ ሥራን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ

ዓላማ-የግብርና ምርቶችን የማምረት ዘዴ በመቀየር ምርትና ምርታማትን ማሳደግና ኮሜርሻላይዜሽንን በማስፋፋት ገበያ ተኮር
ምርቶችን አምርቶ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን፣

6
4. የንግድ ሥራ ዕቅዱ ግቦች
የንግድ ሥራ ዕቅዱ በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ዋና ዋና ግቦች ይኖሩታል ፡፡

1. በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የግብርና ምርቶችን በዓይነትና በመጠን በማሳደግ ከዘርፉ


የማገኜውን ገቢ በ 15 በመቶ ማሳደግ፣
2. ጊዜ፣ ወጪ ቆጣቢና የምርት ብክነትን የሚቀንሱ የግብርና ቴክሎጂዎችን በመጠቀም ከግብርና
ምርቶች በተጨማሪ በሜካናይዜሽን ዘርፍ የማገኜውን ገቢ በ 60 በመቶ ማሳደግ፣
3. እኔን መሰል የአከባቢው አርሶ አደሮች በግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ምርትና
ምርታማነትን እንዲያሳድጉ የሚያግዝ አገልግሎት በመስጠት ከዘርፉ የማገኜውን ገቢ ማሳደግ፣

5. የግብርና ምርትና ሜካናይዜሽን አጠቃቀምና አገልግሎት አሰጣጥ ዕቅድ

5.1. የግብርና ምርት እቅድ

በሚቀጥሉት አምስት አመታት (ከ 2014-2018 ዓ.ም ድረስ) በምገኝበት ቀበሌ በራሴ ይዞታ የሚገኘውን 2.05
ሄ/ር የእርሻ መሬት በበልግና በመኸር ለማምረት የሚያስችሉ የአሰራር ስልቶችን በመጠቀምና በተጠቀሱት
ወቅቶች ተመርተው ለገበያ ሊቀርቡ የሚችሉ የግብርና ምርቶችን በማምረትና ለገበያ በማቅረብ እና
ትራክተር ተጠቃሚ ሲሆን ያለኝን የእርሻ ማሳ 25 በመቶ በማሳደግ የመስራት እቅድ አለኝ፡፡ ዕቅዴ ስከታማ
እንዲሆንም ለምርትና ምርታማነት እድገት አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ከኅብረት ሥራ ማህበራትና ከሌሎች
ግብአት አቅራቢ ድርጅቶች የምጠቀም ሲሆን በወረዳችን ከሚገኘው የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጸ/ቤትና
የቀበሌያችን የግብርና ባለሙያዎች የሚሰጠኝን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ጥቅም ላይ አውላለሁ፡፡
የእነዚህ ሥራዎቼ ዕድገትና ስኬታማነትም የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆንና ጥገና አገልግሎት
በሚሰጡ፣ የኢንዱስትሪ ግብዓቶችንና ውጤቶችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ቴክኖሎጂዎች በሚያቀርቡና፣ የፋይናንስ ተቋማት
በሚያመቻቹልኝ የብድር አገልግሎትና ሌሎች አካላት በሚሰጡት ያልተቋረጠ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ላይ የተመሰረተ
ይሆናል፡፡

በአጠቃላይ የእኔ እቅድ የ 5 ዓመታት እንደመሆኑ መጠን አሁን ያለኝን የማምረት አቅምና የተሟላ ምርትና
ምርታማነት ማሳደጊያ ግብአት አጠቃቀም በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በመጠንና በዓይነት በ 15 በመቶ በማሳደግ
እና ተገቢ የሆኑ የኤክስቴንሽን አገልግሎቶችን በመጠቀም የማስመዘግበው የግብርና ምርት እድገትና
የማገኜው ገቢ በ 2018 ዓ.ም መጨረሻ በ 100% ያድጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡

ሠንጠረዥ 1 የአርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ የ 5 ዓመታት የግብርና ምርት እቅድ (ከ 2014- 2018)

7
የምርት ወቅት በልግ

የምርት የ አም ስት አመ ታ ት ስር ጭ ት
ተ .ቁ
አይ ነት 2014.000 2015.000 2016.000 2017.000 2018.000
የሚ ለማ የሚ ለማ የሚ ለማ የሚ ለማ የሚ ለማ
የሚ ገኝ የሚ ገኝ የሚ ገኝ የሚ ገኝ የሚ ገኝ
ማሳ ማሳ ማሳ ማሳ ማሳ
ምርት ምርት ምርት ምርት ምርት
መ ጠን መ ጠን መ ጠን መ ጠን መ ጠን
በኩ /ል በኩ /ል በኩ /ል በኩ /ል በኩ /ል
በሄ /ር በሄ /ር በሄ /ር በሄ /ር በሄ /ር
1.000 ማ ሾ 1.000 7.000 1.000 8.050 1.000 8.208 1.000 8.231 1.000 8.235
2.000 ቀ /ሽ ን 0.550 110.000 0.550 126.500 0.550 128.975 0.550 129.346 0.550 129.402
3.000 ቲ ማ ቲ 0.500 100.000 0.500 115.000 0.500 117.250 0.500 117.588 0.500 117.638
ድም ር 2.050 217.000 2.050 249.550 2.050 254.433 2.050 255.165 2.050 255.275

ሠንጠረዥ 2 የበልግ ግብአት ፍላጎት እቅድ

የ ግ ብአ ት የ አም ስ ት ዓመ ታ ት በል ግ ስ ር ጭ ት
ተቁ መ ለኪያ
ዓይ ነት
መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ
ኤንፒ ኤስ
1 2.05 4510.00 2.05 4510.00 2.05 4510.00 2.05 4510.00 2.05 4510.00
ቦሮ ን
2 ዩ ሪያ 2.05 4100.00 2.36 4715.00 2.71 5422.25 3.12 6235.59 3.59 7170.93
ም ር ጥ ዘር
በኪ . ግ
1 ማሾ 0.51 3075.00 0.51 3075.00 0.51 3075.00 0.51 3075.00 0.51 3075.00
የ ጓሮ
አ ት ክል ት
1 ቀ /ሽ ን ኩ ረት 2.20 8360.00 2.20 8360.00 2.20 8360.00 2.20 8360.00 2.20
8360.00
2 ቲማቲም 0.15 600.00 0.15 600.00 0.15 600.00 0.15 600.00 0.15 600.00

ኬሚ ካል 4.50 6750.00 4.50 6750.00 4.50 6750.00 4.50 6750.00 4.50 6750.00

ሠንጠረዥ 4 የምርት ወቅት መኸር

የምርት የ አም ስት አመ ታ ት ስር ጭ ት
ተ .ቁ
አይ ነት 2014.000 2015.000 2016.000 2017.000 2018.000
የሚ ለማ የሚ ለማ የሚ ለማ የሚ ለማ የሚ ለማ
የሚ ገኝ የሚ ገኝ የሚ ገኝ የሚ ገኝ የሚ ገኝ
ማሳ ማሳ ማሳ ማሳ ማሳ
ም ርት ም ርት ም ርት ም ርት ም ርት
መ ጠን መ ጠን መ ጠን መ ጠን መ ጠን
በኩ /ል በኩ /ል በኩ /ል በኩ /ል በኩ /ል
በሄ /ር በሄ /ር በሄ /ር በሄ /ር በሄ /ር
1.000 ማ ሾ 1.000 7.000 1.000 8.050 1.000 8.208 1.000 8.231 1.000 8.235
2.000 ቀ /ሽን 0.550 110.000 0.550 126.500 0.550 128.975 0.550 129.346 0.550 129.402
3.000 ቲ ማ ቲ 0.500 100.000 0.500 115.000 0.500 117.250 0.500 117.588 0.500 117.638
ድም ር 2.050 217.000 2.050 249.550 2.050 254.433 2.050 255.165 2.050 255.275

8
ሠንጠረዥ 5 የመኸር ግብአት ፍላጎት እቅድ

የ ግ ብአ ት 2014.00 2015 2016 2017 2018


ተቁ መ ለ ኪያ
ዓይ ነት
መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ
ኤንፒ ኤስ
1 2.05 4510.00 2.05 4510.00 2.05 4510.00 2.05 4510.00 2.05 4510.00
ቦሮ ን
2 ዩሪያ 2.05 4100.00 2.36 4715.00 2.71 5422.25 3.12 6235.59 3.59 7170.93
ም ር ጥ ዘር
በኪ . ግ
1 ማሾ 0.51 3075.00 0.51 3075.00 0.51 3075.00 0.51 3075.00 0.51 3075.00
የ ጓሮ
አ ት ክል ት
1 ቀ /ሽ ን ኩ ረ ት 2.20 8360.00 2.20 8360.00 2.20 8360.00 2.20 8360.00 2.20
8360.00
2 ቲማቲም 0.15 600.00 0.15 600.00 0.15 600.00 0.15 600.00 0.15 600.00
ኬ ሚ ካል 4.50 6750.00 4.50 6750.00 4.50 6750.00 4.50 6750.00 4.50 6750.00

ሠንጠረዥ 6 የምርት ወቅት በጋ መስኖ

የ ሚ ለማ የ ሚ ለማ የ ሚ ለማ
የ ሚ ገኝ የ ሚ ለማ የ ሚ ገኝ የ ሚ ለማ የ ሚ ገኝ የ ሚ ገኝ የ ሚ ገኝ
ማሳ ማሳ ማሳ
ምርት ማ ሳ መ ጠን ም ር ት ማ ሳ መ ጠን ም ር ት ምርት ምርት
መ ጠን መ ጠን መ ጠን
በኩ /ል በሄ /ር በኩ /ል በሄ /ር በኩ /ል በኩ /ል በኩ /ል
በሄ /ር በሄ /ር በሄ /ር
1.00 ቀ /ሽ ን 1.05 210.00 1.05 241.50 1.05 246.23 1.05 246.93 1.05 247.04
2.00 ቲማቲ 1.00 200.00 1.00 230.00 1.00 234.50 1.00 235.18 1.00 235.28
ድምር 2.05 410.00 2.05 471.50 2.05 480.73 2.05 482.11 2.05 482.32

ሠንጠረዥ 7 የበጋ መስኖ ግብአት ፍላጎት እቅድ

9
ተቁ የ ግ ብአ ት ዓይ ነት የአምስት አመት ስርጭት
መ ለ ኪያ መ ጠ ን ዋ ጋ መ ጠን ዋ ጋ መጠን ዋጋ መጠን ዋጋ መጠን ዋጋ

1.0 ኤ ን ፒ ኤ ስ ቦሮ ን
ኩ /ል 1.1 2310.0 1.1 2310.0 1.1 2310.0 1.1 2310.0 1.1 2310.0
2.0 ዩሪያ ኩ /ል 1.1 2100.0 1.2 2415.0 1.4 2777.3 1.6 3193.8 1.8 3672.9
የ ጓ ሮ አ ት ክል ት
ዘር በኪ /ግ
1.0 ቀ /ሽ ን ኩ ረ ት ኪግ 4.2 15960.0 4.2 15960.0 4.2 15960.0 4.2 15960.0 4.2 15960.0

2.0 ቲማቲም
ኪግ 0.3 1200.0 0.3 1200.0 0.3 1200.0 0.3 1200.0 0.3 1200.0

ኬ ሚ ካል
ሊ /ር 4.5 6750.0 4.5 6750.0 4.5 6750.0 4.5 6750.0 4.5 6750.0

ሰንጠረዥ 8 ግዛቸዉ ገብሬ ከበልግ፣ ከመኸር እና ከበጋ መስኖ የሚገኝ ዓመታዊ የግብርና ምርት ውጤት ማጠቃለያ
(ከ 2014 እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ)

የምርት
የ አ ም ስ ት ዓመ ታ ት ስ ር ጭ ት
ተ .ቁ አ ይ ነት መ ለ ኪያ
በኩ / ል 2014 2015 2016 2017 2018
1 ማሾ ኩ /ል 14.0 16.1 16.4 16.5 255.3
2 ቀ /ሽ ን ኩ /ል 430.0 494.5 504.2 505.6 505.8
3 ቲማቲ ኩ /ል 400.0 460.0 469.0 470.4 470.6
ድም ር 844.0 970.6 989.6 992.4 1231.7

ሰንጠረዥ 9 የአርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ ለበልግ፣ ለመኸርና ለበጋ መስኖ የሚፈለግ የግብርና ምርት ማሳደጊያ ግብአቶች
ማጠቃለያ (ከ 2014 እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ)

10
የ ግ ብአ ት
የ አ ም ስት ዓመ ታ ት ስር ጭ ት
አ ይ ነት

2 0 1 4 .0 0 2 0 1 5 .0 0 2 0 1 6 .0 0 2 0 1 7 .0 0 2 0 1 8 .0 0
ኤንፒ ኤስ
6 .1 5 6 .1 5 6 .1 5 6 .1 5 6 .1 5
1 ቦሮ ን
2 ዩሪያ 6 .1 5 6 .1 5 6 .1 5 6 .1 5 6 .1 5
ምርጥ ዘር
በኩ /ል
1 ማሾ 1 .0 3 1 .0 3 1 .0 3 1 .0 3 1 .0 3
የ ጓ ሮ አ ት ክል ት
ዘ ር በኪ /ግ
ቀ /ሽ ን ኩ ረ ት 8 .6 0 8 .6 0 8 .6 0 8 .6 0 8 .6 0
1

2 ቲማቲም 0 .6 0 0 .6 0 0 .6 0 0 .6 0 0 .6 0

ኬ ሚ ካ (ሊ .ር ) 8 .0 0 8 .0 0 8 .0 0 8 .0 0 8 .0 0

5.2. የግብርና ሜካናይዜሽን ፍላጎት እቅድ

እኔ በዋነኛነት የምጠቀማቸው የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክሎጂዎች ትራክተር እና ማረሻ፣ ስሆኑ እነዚህን ጊዜ፣

ወጪና ጉልበት እንዲሁም በቅድመ ምርት ወቅት ለምርታማነት እድገት አሉታዊ ተጽዕኖ ያለውን አሰራር

በማስቀረት እንዲሁም በድህረ ምርት ወቅት ደግሞ ብክነትን በመቀነስ ጥራትን የሚየሻሽሉ ዘመናዊ የእርሻ

ሜካናይዜሽን ቴክሎጂዎችን ለመጠቀም አቅጃለሁ፡፡ በመሆኑም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት (ከ 2014-

2018) ድረስ በመጀመሪያ የራሴን ሰፊ የእርሻ መሬት ለማልማትና በበልግና በመኸር የማመርታቸውን የምርት

ዓይነቶች በመጠንና በጥራት በማምረት ከቤተሰብ ፍጆታ አልፎ በገበያው የሚኖረኝን ድርሻ በማሳደግ

ተጠቃሚ የመሆን ስልት እከተላለሁ፡፡

በተጨማሪም በአካባቢዬ ለሚኖሩት አርሶ አደሮች የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት በተመጣጣኝ ክፍያ

በመስጠት ተጨማሪ ገቢ የማገኝበትን አሰራር የምከተል ይሆናል፡፡ እኔ የሚሰጠው የትራክተር እርሻ አገልግሎት

ከዚህ ቀደም በአካባቢዬ ከሚሰጠው አገልግሎት በዋናነት የሚለየው እኔ አ/አደሩ ጋር እዚያው የምኖርና

ከአ/አደሮች ጋር ያለኝ ግንኙነት መልካምና ጥሩ ማህበራዊ መስተጋብር ስላላኝ እንዲሁም በቅርበት ሆኜ

የአ/አደሩን ችግር የምረዳና ለችግሩም መብትሄ በማፈላላግ ስለሚተባበር በዚህ ሂደትም የአካባቢዬ አርሶ

አደሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የመጠቀም ባህልን እንዲያሳድጉና ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግና

ከግብርና ምርቶች የሚያገኙትን ገቢ ከፍ በማድረግ ኑሯቸው እንዲለወጥ የበኩሌን አስተዋጽዖ በማበርከት

ከዚህ ቀደም ከሌላ አካባቢ መጥተው በክራይ አገልግሎት ከሚሰጡት የኔን የተለየ እና የተሻለ የገበያ ዕድል

እንዲኖረኝ ያደርጋል፡፡

11
የእኔ እቅድ የ 5 ዓመታት እንደመሆኑ መጠን አሁን ያለኝን በዘመናዊ ቴክሎጂ የመጠቀም አቅም በማሳደግና
የቴክሎጂ አቅርቦት በማሟላት በቅድመ ምርት ላይ ለምርትና ምርታነት እድገት አሉታዊ ተጽኖ ያላቸውን
አሰራሮች ከማስወገድ አንጻር በ 75 በመቶ በመቀነስ እና ድህረ ምርት ላይ ደግሞ የምርት ብክነትን በ 30 በመቶ
በመቀነስና ጥራትን ከማሻሻል አንጻር ደግሞ 90% በማስቀረት በ 2018 ዓ.ም መጨረሻ በዘርፉ የማገኘው ገቢ
በ 100% ያድጋል ተብሎ ይታሰባል፡፡ በአካባቢዬ የሚገኙት በግብርና ሜካናይዜሽን ቴክሎጂ የሚጠቀሙ አርሶ
አደሮች ቁጥርም በየዓመቱ 25 በመቶ እደገት እንደሚያስመዘግብ ታሳቢ በማድረግ የዘርፉ ገቢዬ አስተማማኝ
ይሆናል ተብሎ ተገምቷል፡፡
ሰንጠረዥ 10 የአርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂ ፍላጎት ማጠቃለያ (ከ 2014 እስከ
2018 ዓ.ም ድረስ)

ተ.ቁ የ5 የአምስት ዓመት ስርጭት


ዓመት
የመካናይዜሽን ማሽነሪ
መለኪያ ፍላጎት 2014 2015 2016 2017 2018
ዓይነት
ብዛት
1 ትራክተር በቁጥር 1 1 0 0 0 0
2 ማረሻ በቁጥር 1 1 0 0 0 0

እኔ የማቀርበው የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ከተፎካካሪዎች ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ፣ ጠቀሜታው፣ የሚያስገኘው ፋይዳ፣
ዘዴዉ በተመለከተ፡-
 እኔ የማቀርበዉ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ለቀበሌው/ለአከባቢው የመጀመሪያ በመሆኑ ከሌሎች አጎራባች

ወረዳዎች አንፃር ሲታይ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት በተመጣጣኝ ክፍያ በመስጠት ማለትም

የአ/አደሩን አቅም ባገናዘበ መልኩ ሌሎች ከዚህ ቀደም ከሚያከራዩት 30 በመቶ ቅናሽ በማድረግ

በርካታ አ/አደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑና እኔን እንዲመርጡ በሂደቱም ተጨማሪ ገቢ የማገኝበትን

አሰራር የምከተል ይሆናል፡፡

 እኔ የሚሰጠው የትራክተር እርሻ አገልግሎት ከዚህ ቀደም በአካባቢዬ ከሚሰጠው አገልግሎት በዋናነት

የሚለየው እኔ አ/አደሩ ጋር እዚያው የምኖርና ከአ/አደሮች ጋር ያለኝ ግንኙነት መልካምና ጥሩ

ማህበራዊ መስተጋብር ስላላኝ እንዲሁም በቅርበት ሆኜ የአ/አደሩን ችግር የምረዳና ለችግሩም

መብትሄ በማፈላላግ ስለሚተባበር በዚህ ሂደትም የአካባቢዬ አርሶ አደሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ

የመጠቀም ባህልን እንዲያሳድጉና ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግና ከግብርና ምርቶች

የሚያገኙትን ገቢ ከፍ በማድረግ ኑሯቸው እንዲለወጥ የበኩሌን አስተዋጽዖ በማበርከት ከዚህ ቀደም

12
ከሌላ አካባቢ መጥተው በክራይ አገልግሎት ከሚሰጡት የተሸለ ተወዳዳሪና ተመራጭ ስለምሆን የኔን

የተለየ ያደርገዋል፡፡
 የማቀርበዉ የግብርና ሜካናይዜሽን በአከባቢው ለሚገኙ አ/አደሮች የኪራይ አገልግሎት ከመስጠቱም ባሻገር
በአከባቢው የሚገኙ አ/አደሮች የግብርና ሜካናይዜሽን ጠቀሜታውንና አገልግሎቱን እንዲያውቁና እንዲጠቀሙ
ያደርጋል፡፡
የሥራ ቦታ
 አገልግሎቱን ለአርሶ አደሩና ለሌሎች የሚሰጥበት ጊዜና ቦታ፡-
የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎቱን የሚሰጠዉ ምርቱን በማመርትበት ጳሳ እና አጎራባች ቀበሌያትና ወረዳዎች ሲሆን ይህም
በአካባቢው የእርሻ ካላንደር መሰረት በዋናነት በዓመት ሁለት ጊዜ የበልግና መኸር ምርት በሚመረትበት ወቅት ሲሆን
እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ የበጋ መስኖን በሚያለሙ ቀበሌያት ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ የእርሻ አገልግሎት
የሚሰጥ ይሆናል፡፡
5.3. የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት አሰጣጥ (የግብይት) እና የግዥ ዕቅድ
ቀደም ሲል እንደገለጽኩት የምጠቀምባቸው የግብርና ሜካናይዜሽን ቴክኖሎጂዎች ለእራሴ አገልግሎት
እንዲሰጡና ከዚህም በተጨማሪ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት በመስጠት
በጋራ ተጠቃሚ መሆን የሚቻልበትን እድል መፍጠር ዓላማዬ ነው፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች በቀረበው
ሰንጠረዥ መሰረት በሚቀጥሉት አምስት አመታት በዘርፉ አገልግሎቱን ለመስጠትና ላገኜው የምችለውን ገቢ
ግምት አስቀምጫለሁ፡፡
ሰንጠረዥ 11 የአርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ የግብርና ሜካናይዜሽን ተክኖሎጂ አጠቃቀም እቅድ (ከ 2014 እስከ 2018 ዓ.ም
ድረስ)
በዓመት
የምርት የአንዱ የሚያርሰው
ተ.ቁ ዓይነት መለኪያ ዋጋ ማሳ መጠን 2014 2015 2016 2017 2018 ድም
የትራክተር
ኪራይ
አገልግሎት
1 (እርሻ) በሄ/ር 2500 420 1050000 1134000 1197000 1260000 1344000 598

የሜካናይዘሽን አገልግሎት መስጫ ግብዓቶች እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፤-


- ትራክተር ( sonalika tractor Model) 90 hp የህንድ ሥሪት የሆነ
- ማረሻ(Mounted Disc Plough) ሞዴል Nardy 26’’ የሆነ
እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት የእርሻ መሳሪያ ሲሆኑ የግዥ ዕቅዳቸው ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ የአዋጭነት ዕቅድ ተጠናቅቆ
ተቀባይነት ካገኘ ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡

13
5.3.1 የግዥ ወጪዎች ዕቅድ
ተ.ቁ ዝርዝር ሥራዎች መለኪያ 2013 በጀት ዓመት
ብዛት የአንዱ ጠቅላላ ዋጋ
ዋጋ
1. የግብርና ሜካናይዜሽ
1.1 ትራክተር በቁጥር 1 1780000 1780000
1.2 በቁጥር 1 266741 266741
ማረሻ
ድምር 2046741

5.3.2 አስተዳደራዊ ወጪዎች (ለሜካናይዜሽን አገልግሎት መስጫው ቴክሎጂና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎች በጀት ማጠቃለያ
ሰንጠረዥ)
ተ. የአስተዳደራዊ የ5 ዓመት
ቁ ወጪዎች ዝርዝር በጀት በብር
2014 2015 2016 2017 2018
1 ለቢሮ አገልግሎት 0 0 0 0 0
ሌሎች ቁሳቁስ 200000 37000 39250 42250 46000 39016
ግዥ
ጥገና፣ሰርቪስ 86250 15750 16875 18375 20250 21150
ወዘተ
2 ደመወዝ፤አበልና 1035000 189000 202500 220500 243000 107100
ትራንስፖርት
ትራክተር 483000 88200 94500 102900 113400 20000
ኦፕሬተር
ረዳት ትራክተር 379500 69300 74250 80850 89100 49000
ኦፕሬተር
ገንዘብ ያዥ 172500 31500 33750 36750 40500 30200
ጠ.ድ 1321250 241750 258625 281125 309250 266466

5.3.3. ለበልግ፣ መኸር ለበጋ መስኖ የሚያስፈልግ የግብርና ምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች ወጪ (ከ 2014-2018 ዓ.ም ድረስ)

14
የ ግ ብአ ት 2014.00 2015 2016 2017 2018
ተቁ መ ለ ኪያ
ዓይ ነት
መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ መ ጠን ዋጋ
ኤንፒ ኤስ
1 6.15 13530.00 6.15 13530.00 6.15 13530.00 6.15 13530.00 6.15 13530.00
ቦሮ ን
2 ዩሪያ 6.15 12300.00 7.07 14145.00 8.13 16266.75 9.35 18706.76 10.76 21512.78
ም ር ጥ ዘር
በኪ . ግ
1 ማሾ 1.03 6150.00 1.03 6150.00 1.03 6150.00 1.03 6150.00 1.03 6150.00
የ ጓሮ
አ ት ክል ት
1 ቀ /ሽ ን ኩ ረ ት 8.60 32680.00 8.60 32680.00 8.60 32680.00 8.60 32680.00 8.60
32680.00
2 ቲማቲም 0.60 2400.00 0.60 2400.00 0.60 2400.00 0.60 2400.00 0.60 2400.00
ኬ ሚ ካል 8.00 12000.00 8.00 12000.00 8.00 12000.00 8.00 12000.00 8.00 12000.00
79060.00 80905.00 83026.75 85466.76 88272.78

5.4. የአርሶ አደሩን አገልግሎት ማስተዋወቅ፣

እኔ የግብርና ምርትና ምርታማትን ለማሳደግ፣ ጥራት ያለው ምርት በማረት በገበያ ለማቅረብና ተወዳዳሪ ለመሆን
የሚያስችሉኝን ሙሉ የግብርና ግብአቶች ፓኬጅ የምጠቀምና በግሌም ሆነ በመንግስትና በሌሎች ድጋፍ ሰጪ አካላት
የሚሰጠኝን የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመጠቀም ውጤታማ መሆን እንደምችል አምናለሁ፡፡ ስለሆነም ያለኝን
ተሞክሮዎች በመጥቀስና መንገዴን በማሳየት ወደገቢ ማስገኛ ተግባርነት የምቀይራቸውን አሰራሮችና የምጠቀማቸውን የግብርና
ሜካናየዜሽን ቴክኖሎጂዎችን ልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ለአካባቢየ አርሶ አደሮችና ከወረዳችን ውጪም ለሚገኙ
የዘርፉ ተሳታፊዎች በማተዋወቅ አገልግሎቴ ተደራሽ እንዲሆን እሰራለሁ፡፡

6. የግብርና ምርት ማሳደጊያ እና የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስትራቴጂ

6.1. የግብርና ምርት ማሳደጊያ ስትራቴጂ

እኔ አርሶ አደር እንደመሆኔ መጠን ሙሉ የግብርና ምርቶችን አመራረትና የገበያ ስልት አውቃለሁ የሚል እምነት ባይኖረኝም
በአቅራቢያችን ከሚገኙ የኤክስቴንሽን አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን በማግኘት ምርትና ምርታነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ
ፓኬጆችን በመጠቀም አመርታለሁ፡፡ በተጨማሪም ለምርት ማሳደጊያ የምፈልጋቸውን ግብአቶች፣ ከማን፣ የትና መቼ ማግኜት
እንደምችል አስቀድሞ በተዘጋጄ እቅድ አማካይነት ግንኙነት በመፍጠርና የሚያስፈልገኝን ገንዘብ በማመቻቸት በወቅቱና
በሚፈለገው መጠን ግብአቶችን ተጠቅሞ የማምረት ስልት እከተላለሁ፡፡

6.2. የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት አሰጣጥ ስትራቴጂ

በግዢ የማገኛቸው የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች በቅድሚያ እኔ ለምጠቀምበት የእርሻ አገልግሎት እንዲሰጡ የማደረግ
ሲሆን ይህ አሰራርም በምርት ወቅቶች መሰረት በሚዘጋጅ መርሃ ግብር መሰረት እንዲመራ አደርጋለሁ፡፡ ስለሆነም የማገኛቸው

15
የግብርና ሜካናይዜሽን መሳሪያዎች በየደረጃው የእኔ እርሻ ታርሶ ካለቀ በኋላ ለሌሎችም አገልግሎት መስጠት እንዲችል ምን
ጊዜም በእቅድ የመመራት አሰራርን እከተላለሁ፡፡

በአካባቢዬ የሚኖሩት አርሶ አደሮች ሁሉም ስለ ግብርና ቴክሎጂዎች አጠቃቀም ተመሳሳይ የሆነ ግንዛቤ እንደሌላቸቸው
አውቃለሁ፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የማከናውነው ስራ ውጤታማ መሆን እንዲችል እኔን እያዩ የሚማሩበትንና ግንዛቤ
የሚያገኙበትን ስልት ማለትም በስራ ቦታ ተገኝተው እንዲጎበኙ በማድረግ ቴክኖሎጂው ስለሚሰጠው ጠቀሜታ በማስገንዘብና
የሚያወጡት ወጪ ከሚያገኙት ገቢ ጋር ያለውን ልዩነት በግልጽ በማስረዳት የአካባቢዬ አርሶ አደሮች የግብርና ሜካናይዜሽን
ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ አደርጋለሁ፡፡

6.3. የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለመስጠት (የመስሪያ ቦታ) በተመለከተ

እኔ በምኖርበት አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከራሴ እርሻ በተጨማሪ ሌሎች በቅርበት የሚገኙ አርሶ አደሮች አገልግሎቱን
እንዲያገኙ የማደርግ ይሆናል፡፡ በርቀት የሚገኙ አርሶ አደሮች ደግሞ የጉዞ ሰዓትንና የሥራ ሰዓትን ታሳቢ በማድረግና አስፈላጊ
የሆኑ የሥራ ወጪዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት በአቅራቢያ ለሚገኙ ወረዳዎችም ጭምር አገልግሎቱን የምሰጥ ይሆናል፡፡
ስለሆነም በተለይ የትራክተር እርሻ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር በወረዳው ከሚገኙት ቀበሌያት መካከል ኦቶሎ፣ ጳሳ፣
ጋ/ሃኒቃ፣ ደ/ዳልባ እና ማዜ ቀበሌዎችን በመሸፈን አገልግሎት የምሰጥ ይሆናል፡፡

6.4. የአርሶ አደሩ የግብርና ምርት እና ንግድ ስራ አመራር

እኔ አርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ የግብርና ምርቶችን ለማምረትና ለራሴ የምጠቀምበትንና ለአካባቢው አርሶ አደሮች አገልግሎት
የምሰጥበትን የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ከዚህ በታች በሚኖረው ድርጅታዊ መዋቅር መሰረት በመምራትና በማስተዳደር
ተግባራዊ አደርጋለሁ፡፡

16
የእርሻ ሜካናይዜሽን የአርሶ አደር አቶ ግዛቸዉ ገብሬ የእርሻና ንግድ ሥራ ድርጅታዊ መዋቅር

የእርሻና የንግድ ስራው ባለለቤት/ስራ


መሪ

የግብርና ምርት ማምረት

የግብአት አቅርቦትና እርሻ የግብርና ሜካናይዜሽን

ስራዎች፣ምርት መሰብሰብ፣ ግብይት ሥራ አስኪያጅ

የትራክተር ኦፕሬተር ረዳት የትራክተር ኦፕሬተር

ገንዘብ ያዥ

16
7. የፋይናንስ ዕቅድ

7.1. አጠቃላይ የፋይናንስ ዕቅድ

በእቅድ ዘመኑ (ከ 2014-2018) ዓ.ም ድረስ እኔ ለማከናውናቸው ስራዎች በድምሩ ብር 3784722 ያስፈልጋል፡፡
ከዚህ ውስጥ ብር 2463472 ለግብርና ምርቶች ማምረቻ ግብአት ግዥና ማምረት ተግባር እና ለግብርና
ሜካናይዜሽን ማሽነሪ ግዥ የሚውል ሲሆን ቀሪው ብር 1321250 ለአስተዳደራዊ ለሌሎች ወጪዎች
የሚውል ይሆናል፡፡ ለእቅድ ዘመኑ ከሚያስፈልገው ለግብርና ሜካናይዜሽን ማሽነሪ ግዥ የሚውል በጀት ብር
2046741 ውስጥ ብር 1228044.6 በብድር ለመሸፈን የታሰበ ሲሆን ቀሪው ብር 818696.4 በአርሶ አደሩ
የሚሸፈን ይሆናል፡፡ ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችም በአ/አአደሩ የሚሸፈኑ ይሆናል፡፡

በዚህ መሰረት የአርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ የግብርና ምርትና የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ከ 2014
እስከ 2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልግ የፋይናንስ እቅድ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

7.2. የግብርና ምርቶችና የአገልግሎት ሽያጭ እቅድ

እኔ አርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ ቀደም ሲል እንደገለጽኩት በንግድ ስራ እቅዴ በግልጽ በተቀመጠው መሰረት
የግብርና ምርቶችን በማምረትና የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት በመጠቀምና ለሌሎች በመስጠት ዓመታዊ
ገቢ የማገኝ ይሆናል፡፡ በዚህ መሰረት ከምርት ሽያጭና ከግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት የማገኘውን ገቢ
በሚከተለው ሰንጠረዥ መሰረት አጠቃልዬ አቀርባለሁ፡፡

ሰንጠረዥ 12 የአርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ የ 5 ዓመታት ከምርት ሽያጭ የሚገኝ ገቢ እቅድ ከ 2014-2018

ተቁ ከአ ም ስ ቱ አ መ ት ም ር ት ሽ ያ ጭ
መ ለ ኪያ
የምርት ዓይነት 2014 2015 2016 2017 2018
1 ማሾ ብር 112000 128800 131320 131698 2042198
2 ቀ /ሽ ን ብር 860000 989000 1008350 1011253 1011688
3 ቲማቲ ብር 800000 920000 938000 940700 941105

ሰንጠረዥ 13 የአርሶ አደር ግዛቸዉ ገብሬ የ 5 ዓመታት ከግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት የሚገኝ ገቢ እቅድ
(ከ 2014-2018)

17
በዓመ

የሚያር
ተ ሰው
. መለኪ የአንዱ ማሳ
ቁ የምርት ዓይነት ያ ዋጋ መጠን 2014 2015 2016 2017 2018
የትራክተር
ኪራይ
አገልግሎት 105000 113400 119700 126000 134400
1 (እርሻ) በሄ/ር 2500 420 0 0 0 0 0

ማሳሰቢያ፡- አርሶ አደሩ በዓመት ከሚያርሰው አጠቃላይ 422.05 ሄ/ር መሬት ውስጥ 420 ሄ/ር በኪራይ
አገልግሎት እንደሚሰጥና ቀሪው 2.05 ሄ/ር የራሱን በማረስ አገልግሎት የሚሰጥበት ሁኔታ እንዳ ታሳቢ
ተደርጓል፡፡

ሠንጠረዥ- አ/አደር ግዛቸዉ ገብሬ የ 5 ዓመታት የምርት ሽያጭ እና የሚካናይዜሽን አገልግሎት ገቢ ዕቅድ
የአምስት ዓመታት ስርጭት
ተቁ የምርት አይነት 2014 2015 2016 2017 2018
1 ከምርት ሽያጪ ገቢ 1772000 2037800 2077670 2083651 3994991
2 ከትራክቴር ክራይ 1050000 1134000 1197000 1260000 1344000
ድምር 2822000 3171800 3274670 3343651 5338991

18
7.3 የትርፍና ኪሣራ መግለጫ

የንግድ ስራው ስም :- ግዛቸዉ ገብሬ የሜካናይዜሽን እርሻ ሥራ

ተ .ቁ መ ግ ለጫ 2014 2015 2016 2017 2018


1 ገቢ
ከም ር ት ሽ ያ ጭ የሚገኝ ገቢ 1772000 2037800 2077670 2083651 3994990.7
ከግር ና ሜ ካና ይ ዜ ሽ ን አ ገል ግሎ ት የሚገኝ ገቢ 1050000 1134000 1197000 1260000 1344000
ድምር 2822000 3171800 3274670 3343651 5338991
2 ወጪ
2 .1 ለ ቁ ሳ ቁ ስ ግ ዥ ና ዝ ግ ጅ ት 21500 23075 25390 27159 29016
2 .2 የ ግ ብ ር ና ም /ማ ሳ ደ ጊ ያ ግ ብ ዓ ት ግ ዥ 79060 80905 83026.75 85466.76 88272.777
ድምር 100560 103980 108417 112626 1 1 7 2 8 8 .8
2 .3 ቀ ጥ ታ ያ ል ሆ ኑ ወ ጪ ዎ ች
ዓመ ታ ዊ የብ ድ ር ክፍ ያ 386834 358589 330344 302099 273853.95
የብ ድ ር ወለድ ክፍ ያ 141225.13 112980.1 84735.077 56490.052 28245.0258
ድምር 528059 471569 415079 358589 302099
2 .4 አ ስ ተ ዳ ደ ራ ዊ ወ ጪ ዎ ች
ለሰራ ተ ኞ ች ደመ ወዝ 96000 96400 96600 96800 97000
የቀ ን ሠ ራ ተ ኛ ም ንዳ 8000 8000 8000 8000 8000
ስ ራ ማ ስ ከ ሄጃ 73950 75075 76575 78450 79350
ለ ው ሎ -አ በ ል ና ት ራ ን ስ ፖ ር ት 57200 57200 57200 57200 57200
ለ ጽ /መ ሳ ሪ ያ 1000 1000 1000 1000 1000
የመ ጋ ዘን ጥገና 0 0 0 0
ጥገና 15750 16875 18375 20250 21150
መ ብራት 0 0 0 0 0
ስል ክ 0 0 0 0 0
ድምር 251900 254550 257750 261700 263700
2 .5 ዓመ ታ ዊ ል ሽ ቀ ት (Annua l de pre cia tion) 136449 136449 136449 136449 1 3 6 4 4 9 .4
2 .6 አ ጠ ቃ ላ ይ ወ ጪ 1016969 966548.5 917695.2 869364.2 819537.15
7 ሌ ሎ ች ገ ቢ ዎ ች /ወ ጪ ዎ ች / 0 0 0 0 0
ሌሎ ች ገቢዎ ች 0 0 0 0 0
ሌ ሎ ች ወጪ ዎ ች 0 0 0 0 0
ከ ታ ክ ስ በ ፍ ት የተ ጣ ራ ት ር ፍ 1805031 2205251 2356975 2474286 4519453.6
ታ ክ ስ 30% 846600 951540 982401 1003095 1601697.2
8 የ ተ ጣ ራ ት ር ፍ (5 -6 +7 ) 958431 1253711 1374574 1471191 2917756

19
7.5. የጥሬ ገንዘብ ፍሰት መግለጫ

የንግድ ስራው ወይም ባለቤት ስም፡ ግዛቸዉ ገብሬ የሜካናይዜሽን እርሻ ሥራ


የመ ክ ፈ ቻ
ሂ ሳ ብ (P re
o pe ra ting
ወ ደ ው ስ ጥ የ ሚ ፈ ስ ገ ን ዘ ብ (Ca s h Inflo w) pe rio d) 2014 2015 2016 2017 2018
ጥ ሬ ገ ን ዘ ብ በ እ ጅ (Owne rs e quity) 1030118.85
የ ባ ን ክ ብ ድ ር (Loa n Principa l) 1228044.6
ሽ ያ ጭ (s a le s ) 0 1772000 2037800 2077670 2083650.5 3994990.725
ወ ደ ው ስ ጥ የ ሚ ፈ ስ ገ ን ዘ ብ ድ /ር (Tota l Ca s h Inflow) 2258163.45 1772000 2037800 2077670 2083650.5 3994990.725
ወ ደ ው ጪ የ ሚ ፈ ስ ገ ን ዘ ብ (Ca s h outflow)
ጥ ሬ እ ቃ (Ra w Ma te ria ls ) 0 21500 23075 25390 27159 29016
ደመ ዎ ዝ 96000 96400 96600 96800 97000
ሌ ሎ ች ሥ ራ ማ ስኬጃ ወጪ ዎ ች 73950 75075 76575 78450 79350
የ ግ ብ ር ና ም /ማ ሳ ደ ጊ ያ ግ ብ ዓ ት ግ ዥ 79060 80905 83026.75 85466.7625 88272.77688
የብ ድ ር ተ ከፋ ይ 349247.619 349247.619 323747 298246.379 272745.7596
የወለድ ተ ከፋ ይ 386834.049 358589.0232 330343.9974 302098.9716 273853.9458
የ ገ ቢ ግ ብ ር 30% 531600 611340 623301 625095.15 1198497.218
ጠ ቅ ላላ ተ ከ ፋ ይ 1538191.668 1594631.64 1558983.7 1513316.26 2038735.7
የ ተ ጣ ራ የ ገ ን ዘ ብ ፍ ሰ ት Ne t ca s h flows 2 3 3 8 0 8 .3 3 2 4 4 3 1 6 8 .3 6 5 1 8 6 8 6 .3 5 7 0 3 3 4 .2 4 1 9 5 6 2 5 5 .0 2 5
ጥ ቅ ል የ ገ ን ዘ ብ ፍ ሰ ት Cumula tive ca s h flows 2 3 3 8 0 8 .3 3 2 4 4 3 1 6 8 .3 6 5 1 8 6 8 6 .3 5 7 0 3 3 4 .2 4 1 9 5 6 2 5 5 .0 2 5

7.6. የሀብትና ዕዳ መግለጫ

የንግድ ሥራው ስም - ግዛቸዉ ገብሬ የሜካይዜሽን እርሻ ሥራ

20
ተ .ቁ መ ግ ለጫ in itia l 2014 2015 2016 2017 2018
1 ተ ንቀ ሳቃ ሽ ንብ ረት
ጥሬ ገን ዘብ 1030119 1030119 1030118.9 1030119 1030118.85 1030118.9
የተ ቆ ጠረ ዕቃ 0 0 0 0 0
የሚሰበሰብ ሂሳብ 150000 0 0 0 0
ሌሎ ች ተ ንቀ ሳቃ ሽ ንብረቶ ች 0 0 0 0 0
የተ ን ቀ ሳ ቃ ሽ ን ብ ረ ት ድ ም ር 1180119 1030119 1030119 1030119 1 0 3 0 1 1 8 .8 5 1030119
2 ቋሚ ንብ ረት
የረጅ ም ጊ ዜ ኢ ን ቨስት መ ን ት 0 0 0 0 0
ቋሚ ንብረት 1500000 1500000 1500000 150000 1500000 1500000
አ ገል ግሎ ት ተ ቀ ና ሽ 0 33500 34510 35720 36120 38200
የቋ ሚ ን ብ ረ ት ድ ም ር 1500000 1466500 1465490 114280 1463880 1461800
የጠ ቅ ላላ ን ብ ረ ት ድ ም ር 2680119 2496619 2495609 1144399 2 4 9 3 9 9 8 .8 5 2491919
3 ዕዳ
የሚከፈ ል ሂሳ ብ 0 0 0 0 0
የሚከፈ ል ብ ድ ር 0 416194.1 385805.29 355416.5 325027.746 294908.97
የዕዳ ድ ም ር 0 416194.1 385805.29 355416.5 325027.75 294909
4 ካፒ ታ ል 0
የተ ጠራ ቀ መ ካፒ ታ ል 2680119 2496619 2495608.9 1144399 2493998.85 2491918.9
የተ ጣራ ት ር ፍ 2680119 2080425 2109803.6 788982.3 2168971.1 2197009.9
ሌ ሎ ች የ ካ ፒ ታ ል ሂ ሳ ቦች 0 0 0 0 0
የካ ፒ ታ ል ድ ም ር 2680119 2496619 2495609 1144399 2 4 9 3 9 9 8 .8 5 2491919
የዕዳ ና ካ ፒ ታ ል ድ ም ር 2350000 2912813 2881414 1499815 2 8 1 9 0 2 6 .6 2786828

የብድር አከፋፈል መርሃ - ግብር

የታቀደው ብድር በ 5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ የሚያልቅ ሲሆን የብድር አመላለስ መርኀ-ግብሩ
እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል፡፡

የ 5 ዓመታት የብድር አመላለስ መርኀ-ግብር ሰንጠረዥ

P rinc ipa l የ ሚ ከፈ ል ወ ለ ድ ዋና ያልተከፈለ


ዓመ ት የዓመ ቱ ክፍ ያ
pa ym e nt 11.5% የብድር መጠን
0 0 0 1228045
2014 245608.92 141225.129 386834.049 982435.7
2015 245608.92 112980.1032 358589.0232 736826.8
2016 245608.92 84735.0774 330343.9974 491217.8
2017 245608.92 56490.0516 302098.9716 245608.9
2018 245608.92 28245.0258 273853.9458 0

የትርፋማነት መለኪያ
ትርፋማነት በተለያዩ አመልካቾች ሊለካ የሚችል ሲሆን ከእነዚህ አመልካቾች ውስጥ ሥራ ላይ የዋለው እያንዳንዱ አንድ
ወይም መቶ ብር ያስገኘው ትርፍ የሚሰላበት መንገድ አንዱ የትርፋማነት መለኪያ ነው ፡፡ በዚህ መሰረት በበጀት ዓመቱ ሥራ
ላይ የሚውለው እያንዳንዱ አንድ መቶ ብር 74 ብር በላይ የተጣራ ትርፍ የሚያስገኝ ስለሆነ የታቀደው የንግድ ሥራ ዕቅድ
ትርፋማ መሆኑን ያሳያል ፡፡

21
የትርፋማነት መለኪያ አመልካቾች
ተ .ቁ አመ ል ካቾ ች 2014 2015 2016 2017 2018
1 የ ዓመ ቱ የ ተ ጣ ራ ት ር ፍ 9 58 43 1 1 25 37 11 1 37 45 74 1 47 11 91 2 91 77 56
2 የ ሚ ፈ ለ ግ ካፒ ታ ል ድ ም ር 2 14 90 00 2 18 21 15 8 66 73 6 2 25 39 59 2 27 68 00
3 ወቅ ታ ዊ ሀብ ቶ ች 2 14 90 00 2 18 21 15 8 66 73 6 2 25 39 59 2 27 68 00
4 ወ ቅ ታ ዊ ዕዳ ዎ ች 4 16 19 4 3 85 80 5 3 55 41 7 3 25 02 7.8 2 94 90 9

ከአጠቃላይ ኢንቨስትመንት የሚገኝ ትርፍ

ከአጠቃላይ ኢንቨስትመንት የሚገኝ ትርፍ = የዓመቱ የተጣራ ትርፍ X 100


የሚፈለግ ካፒታል ድምር
= 1022998/2517299 X 100 = 40.6%

የንግድ ሥራ ዕቅዱ አዋጭነት

አንድ የንግድ ሥራ ዕቅድ አዋጪ መሆኑን ከሚለካባቸው መንገዶች አንዱ የግለሰቡ ወቅታዊ/ተንቀሳቃሽ ሀብቶች ከግለሰቡ
ወቅታዊ ዕዳ ጋር ያለው ንፅፅር ውጤት ነው ይህ ማለት የግለሰቡ ወቅታዊ/ተንቀሳቃሽ ሀብት ለግለሰቡ ወቅታዊ ዕዳ ሲካፈል
የሚገኘው ውጤት ነው ፡፡ ወቅታዊ ንፅፅር አርሶ አደሩ ያለበትን እያንዳንዱ አንድ ብር ወቅታዊ ዕዳን በምን ያህል ወቅታዊ
ሀብት ሊሸከመው እንደሚችል የሚያሳይ ነው ፡፡ የዚህ ወቅታዊ ንፅፅር ውጤት ሁለት ለአንድ (2፡1) ለንግድ ሥራ ዕቅዱ
አዋጪነት በቂ ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡ ከዚህ በላይ የሚመጣው ውጤት የንግድ ሥራ ዕቅዱ ይበልጥ አዋጪ መሆኑን የሚያሳይ
ሲሆን በዚህም መሰረት የአቶ ታምሩ አሰጉ ወቅታዊ/ተንቀሳቃሽ ሀብት ለወቅታዊ ዕዳ ሲካፈል የንፅፅሩ ውጤት 4፡1 በመሆኑ
የንግድ ሥራ ዕቅዱ ይበልጥ አዋጪ መሆኑን የሚያሳይ ስለሆነ የንግድ ሥራ ዕቅዱ አዋጪ መሆኑን ያመለክታል ፡፡

መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልን!!!

22
23

You might also like