You are on page 1of 10

1

በደቡብ ክልል በጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ፣

ቡናና ቅመማ ቅመም ጽ ቤት /

የአሪቲ ቅመማ ቅመም

ልማት ለማስፋት የተዘጋጀ አጭር

ሰነድ

ነሐሴ 11-12-2014 ዓ ም

መግቢያ

ጎፋ ዞን በደቡብ ክልል ከፍተኛ የቅመማ ቅመም ምርት አምራችና ለገበያ ከሚያቀርቡ ዞኖች አንዱ ሲሆን፣
በተለይም መደኃኒታማና መዓዛማ አገር በቀል ቅመማ ቅመም አምራች ዞን ነው፡፡

ይኸውም አሪቲ፣ ኮረርማ፣ ዝንጅብል ፣ጤና አዳም፣ በሶብላ፣ ድንብላል፣ ኮሥራት፣ሥጋ ማጥበሻ ወይም
ሮዝመሪ፣ ጠጅ ሣር፣ ነጭ አዝሙድ፣ ጥቁር አዝሙድ፤ አብሽ ፣ጦስኝ ወዘተ… ለሁሉም ቅመማ ቅመም ተክል
2

ምቹ በሆነው በዞን ዉስጥ ባሉ ወረዳዎች በሙሉ ይመረታል፡፡ ከእነዚህ ቅመማ ቅመም ምርቶች አንዱ የጎፋ
አገር በቀል ቅመም አርቲ ነው፡፡ ስለሆነ በዞናችን አግሮ እኮሎጂ ማምረት የሚንችለዉን ቅመማ ቅመም
ተክሎች እርሻን በማስፋት በዘርፉ ማግኘት የሚንችለዉን ገቢ በማግኘት የአምራቹ አ/አደር ሆነ የዞናችን
ኢኮኖሚ ለማበልጸግ መረባረብ ይጠብቅብናል፡፡

ዓላማ

በጎፋ አገር በቀል የሆነውን አሪቲ ቅመም በሁሉም አከባቢ አየር ጸባይ በሚስማማው ወረዳዎቹና ቀበሌያት
በማስፋት ምርት እና ምርታማነትን መጨመር ነዉ፡፡

 በግብርና ምርመር ማዕከላት በአርቲ ቅመም ዙርያ ለሚያደርጉ ጥናትና ለክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም
ባለሥልጣን መሠረታዊ መረጃ እና ትክክለኛ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ማቅረብ፣
 የአርቲ ምርት የሕግ ማቀፍ ኖሮት የገበያ ትሥሥር አንድፈጠር እና አ/አደሩ፣ በግልም ሆነ በማህበር
ተደራጅተው በሕብረ ሥራ ማህበረ አማካይነት በተሻለ ሁኔታ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃም እንድሆኑ
ማስቻል፣
 የአርቲ ምርት በብዛትና በጥራት በማምረትና ለገበያ በማቅረብ አከባቢውንና አገርን ተጠቃሚ ማድረግ፣

ግብ

አርቲ ቅመም በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል በጎፋ ዞን አገር በቀል ቅመም መሆኑን አውቆው ቅመሙን አግሮ
ኢክሎጅ በሚስማማው አከባቢ ሁሉ አ/አደሩ በብዛትና በጥራት አምርተው ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ
በማቀረቢ የሕዝብንና የአገርን ኢኮኖሚ እንድያሳድግ በምርምር እና በጥናት ለተሸለ ውጤት ማብቃት ነዉ፡፡

የአሪቲ ቅመም ታሪካዊ ዳራ፣

መደኃኒታማ እና መዓዛማ አሪቲ ቅመም የጎፋ ዞን አገር በቀል ቅመም መሆኑን የዕድሜ ባለፀጋ የሆኑት አባቶች
ይናገራሉ፡፡ ከነዚህ አባቶች በዛላ ወረዳ በዳዳ ገላይሴ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የዘጠና ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ አቶ ዋና
ውንደ የአርቲ ቅመምን በ 1970 ዓ ም ከቡልቂ ምንደሬ በ 2 ሸልንጌ ገዝተው እንዳመጡና ተክለው ማምረት
እንደ ጀምሩ ይመሰክራሉ፡፡ የአከባቢው አ/አደሮቹም ከእሳቸው ዘር እየወሰዱ እንዳሰራጩና እንዳባዙ
ይናገራሉ፡፡ እንድሁም ሌሎች የጎፋ ዕድሜ ባለፀጋ የሆኑ አባቶች አርቲ ቅመም የጎፋ አገር በቀል ቅመም
መሆኑን አምኖ ወደ ቡልቂ ምንደሬ አከባቢው የመጣው ከጥንታዊቷ የጎፋ ሕዝብ መነሻ ከሆነችው “ ከካዎ
ቡራቃና ጋሞ-ጎበ (ጎፋ) “መነሻ ከሆነቿ ከውርክ ነው ይላሉ ወይም ይመስክራሉ፡፡ በእርግጥም በዞናችን አረቲ
ቅመምን ከሚያመርቱ ወረዳዎች ከዛላ ቀጠለው የደምባ ጎፋ ወረዳ አንዱ ነው፡፡
3

የወርክ፣ የወይደ እና የውርጭ ላይማ……..ወዘተ ቀበሌያት የአርቲ ቅመም ያመርታሉ፡፡ በተለይም ዛላ ወረዳ
ገልጣ ገላይሴ ቀበሌን ጨምሮ 8 ከፍተኛ አርቲ ቅመም በማምረትና ለገበያ በማቅረብ በጎፋ ዞን
ምርታማነታቸውን እና ተጠቃምነታቸውን ያረጋገጡ ዛላ ወረዳ ካሉት 34 ቀበሌዎች በስፋት የሚያመርቱት
ገላይሴ፣ገልጣ፣ሳልቤ፣ዛራ፣ጻንጋ፣ ሻቻ፣ ጋርችንደ እና ባንዳ ……..ወዘተ ፡፡

የአርቲ ቅመም ስያመ፤

 ሳይሳዊ ስያመ አብስኒክ አኬሸያ ወይም አርጠምጃ አፍትስቴያ

 በአማራኛ አሪቲ ቅመም ፤

 በጎፍኛ “ ናትራ ሳዎ “ ፤

 መልኩ -ነጭ ግራጫ ነው፤

አሪቲ ቅመም ባሕላዊ ጠቀመታ፤

አሪቲ ለሆድ ሕመም፣ ለወባ/ኡኖ/፣ ለራስ ምታት፣ ለጨጋራ፣ለካንሰር ፣ለተለያዩ ለዉስጥ ደወ እና ለቆዳ
በሽታዎች ፈዋሽ መድኃኒት ነው፡፡ ለሕፃናት፣ ለወላድ እናቶች እና አቅሜ ደካሞች እንድሁም አዛዉንቶች
ከቡና ቅጠል ጋር እና ከቅቤ ጋር በመጠጣት ይበረታታሉ ወይም ይነቃቃሉ፡፡

 ለመዓዛነት ይጠቅማል፤ በሽቶነት ለበዓለት፣ ለሠርግ ጊዜ፣ከበሕላዊ አልባሳት ጋር ከቡሎኮና ከጋቢ


ተጠቅልሎ በትላልቅ ጋን ውስጥና በሣጥን ውስጥ ይቀመጣል፡፡
 አዲስ ቤት ተሰርቶ በሚገቡበት ጊዜ ለመልካም መዓዛ፤ ለውቤት በከሰል ማንዳጃ ወይም በእንክርት ማጨስ
/ማጠን/ የተለመደ ጠቀሜታ አለዉ፣
 አሪቲ ቅመም ለክብር እንግዳ ከቁጢ ቡና /ሃይሳ ቱኬ/ ጋር ምግብ በሚቀርብበት ወቅት ይቀርባል፤

 አሪቲ ቅመም በመልክም መዓዛነቱ ለወዳጅ ዘመድ ሥጦታ ይሰጣል፤ይላካል እንድሁም ወጣቶች ለፍቅር
መገለጫ ወንዱ ለሴቷዋ እና ሴቷዋ ለወንዱ የፍቅር ስጦታነት ይጠቀማሉ፣

የአሪቲ ቅመም ተፈላጊነት፤

 አሪቲ ቅመም በጎፋ ዞን ሕብረተሰብ ዘንድ ከባሕላዊ ጠቀመታ ባለፈ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጠቀመታ
የሚያመጣ አገር በቀል ቅመም ነው፡፡
 ስለሆነም አርቲ ቅመም በትንሽ ይዞታ ለአ/አደሩ ከፍተኛ የገቢ ምንጭነት ለገበያ ይቀርባል፣ በዓመት
ሦስት ይሰበሰባል ወይም እየተቆረጠ ይቀርባል በተለይም ለወላይታ፣ ለጋሞ እና ለቁጫ ገበያ ይቀርባል፣
4

 አሪቲ ቅመም ተፈላጊነቱ በጎፋ ሕብረተሰብ ዘንድ የሚወደደውን ሰው በጎፍኛ በስሙ ይጠራል “ናትሬ“
በመሎ አከባቢ ‹‹ማል ናቲሮ››ተብለው የፍቅር፤ የሠላምታ እና የአብሮነት መገለጫ አድርገዉ ይጠራሉ
/ለአክብሮነትና ፍቅር ይቀባላሉ፤ በተለይ የሴት እህቶቻችን ዘንድ እስከ ዛሬ የተለመደ እውነት ነው፡፡
አባቶች ልጅ ስወልዱ የልጃቸዉን ስም ናትሬ በማለት ይሰይማሉ፡፡ የዚህ ዋነኛ ምክንያት አሪት ከጥሩ
ማዓዛነቱ፤ የገብ ምንጭ በመሆኑ እና ከመድኃኒትነቱ የተነሳ ነዉ፡፡

የአሪቲ ቅመም ለማምረት የሚያሰፈልገው አየር ንብረት፤

 አሪቲ በጎፋ ዞን ከባሕር በላይ 1200-3500 ከፍታ የአየር ንብረት ባሉባቸዉ አከባቢዎች በሙሉ የሚመረት

ስሆን፤ ለበለጠ ምርታማነት የሚመከረው የአየር ንብረት ወ/ደጋ ሆኖ ከ 1350-1850 ከፍታ የበለጠ
ይመረጣል፤
 አሪቲ ተክል ለምርታማነት የሚፈለገው የዝናብ መጠን ከ 900-1200 ሚ.ሜ፤

 አሪቲ ተክል ለምርታማነት የሚፈለገው የሙቀት መጠን ከ 18-28 co ፤

 አሪቲ ተክል ለምርታማነት የሚፈለገው የአፈር ዓይነት ቀይ፣ አስዳማ፣ ጭንጫማ ውሃ የማይተኛ
በተደጋጋም የታረሰና ከአደገኛ አርም ነፃ የሆነ አፈር ሲሆን ጥላ አይፈለግም፣ ነገር ግን የተፈጥሮ ማዳበሪያ
ወይም ኮምፖስት ይፈልጋል፡፡


 አረቲ በእድገት ባህሪው ከቁጥቋጦ ሰብሎች ቤተሰብ ውስጥ የሚመደብ ሲሆን በእድገት ዘመኑ ደግሞ
ቋሚ ሰብል በመሆን ፤ በሚስማማው አግሮእኮሎጅ በአግባቡ ከተያዘ ምርታማ በመሆን አንዴ ከተተከለ
ከአራት እስከ ሰባት አመት በእራሱ እየተባዛ ሊቆይ ይችላል፡፡

የአሪቲ ቅመም አምራች አ/አደሮች እና መሬት ሽፋን፤

 ጎፋ ዞን 7 ወረዳ አስተዳደር፣ 4 ከተማ አስተዳደር እና 189 በገጠር ቀበሌያት እና በከተማ ቀበሌ 27


የተዋቀረ ዞን ነው፡፡
5

 አጠቃላይ የመሬት ሽፋን 455,092 ሄ/ር ሲሆን፣ የቡና መሬት ሽፋን 18,728 ሄ/ር እና ቅመማ ቅመም
መሬት ሽፋን 15,620 ሄ/ር ስሆን ቀረው በሰብል ልማት እና በሌሎች የተያዘ የመሬት ሽፋን 420,746 ሄ/ር
ነው፡፡
 እንዲሁም ቡናና ቅመማ ቅመም አምራች አ/አደር ወ 95,431 ሴ 24,865 ድ 120,296 መሆኑ በተጨባጭ
የተረጋገጠ ነው፡፡
 ከዚህ መሬት ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ አገር በቀል አሪቲ ቅመም አምራች ወረዳዎች ዛላ እና ደንባ ጎፋ ስሆን
የመሬት ሽፋኑ እንደዬ ወረዳዉ ይለያያል፡፡ ኦይዳ፤ ኡ/ደ/ጸሐይ፤ ገዜ ጎፋ፤ መሎ ኮዛና መሎ ጋዳ ወረዳዎች
የአሪቲ ቅመምን አምራች ናቸዉ፡፡ በእነዚህ አከባቢዎች ለቤት ፍጆታና ለአከባቢዉ ገበያ ያቀርባሉ፡፡

1 ኛ/ የዛላ ወረዳ 36 ቀበሌያት ያሉት ሲሆን በ 16 ቱ ቀበሌያት የአሪቲ ቅመም 7,130 ሄ/ር በማልማት
በየዓመቱ በአማካይ 6,770 ቶን ምርት ወደ ወላይታ እና ለሌሎች ገበያ ይቀረባል፡፡ አምራች አ/አደር ብዛት ወ
16,452 ሴ 1262 ድ 17,714 በአሪት እርሻ የተሰማሩ ናቸዉ፡፡

2 ኛ/ የደምባ ጎፋ ወረዳ የአሪቲ ቅመም አገር በቀል መነሻ ሲሆን 34 ቀበሌያት ያሉት እና የመሬት ሽፋን 4630
ሄ/ር፣ በየዓመቱ በአማካይ 2840 ቶን አሪቲ ምርት ወደ ጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ ገበያ እና ወደ ወላይታ ገበያ
ያቀረባል፡፡ አምራች አ/አደር ወ 21021 ሴ 892 ድ 21913 ናቸው፡፡

3 ኛ/ ለሎች በዞናችን ዉስጥ ያሉት ወረዳዎች በአግሮ ኢኮሎጅ መሠሬት ተስማም የሆኑት አሪቲና ሌሎች
ቅ/ቅመም ተክልን ያመረታሉ፡፡ በየዓመቱ በአማካይ 1200 ቶን በላይ ወደ ገበያ ያቀረባሉ፡፡ በአጠቃላይ ከጎፋ ዞን
አሪቲ ምርት ወደ ወላይታ እና ሌሎች ገበያ ከ 10810 ቶን በላይ በየዓመቱ በአማካይ ይቀረባል፡፡

የአሪቲ ቅመም ማሣ ዝግጅት እና ተከላ፣

 የአሪቲ ቅመም ቀይ፣ አስዳማ እና ጭንጫማ አፈር ሆኖ ውሃ የማይተኛ እና በተደጋጋም የታረሰ መሬት
እንዲሁም በተፈጥሮ ማዳበሪያ ወይም ኮምፖስት የተቀላቀለበት ማሣ ሲሆን እንደ የመሬቱ አቀማመጥ
በተለምዶና በተጠና የተከለ ርቀት ተጠብቆ መተከል አለበት፣
 ከተክል ወደ ተክል 30 ሳ.ሜ
 ከመሥመር ወደ መሥመር 60 ሳ.ሜ
 የአሪቲ ማሳ ከፍተኛ ተደፋማነት ካለዉ እና ደባል ሰብል የሚመረት ከሆነ ከተክል ወደ ተክል 40 ሳ.ሜ እና
ከመሥመር ወደ መሥመር 80 ሳ.ሜ ርቀት እንደዬ ሁኔታ ይተከላል፡፡
6

ችግኝ ዝግጅት፣

 ከእናቱ አሪቲ ተክል ግንጣይ ይዘጋጃል፣


 ከ 25 ሳ.ሜ እስከ 30 ሳ.ሜ ርዝመት በስለታማ ብላዋ ተቆርጦ ይተከላል፣

የአሪቲ ግንጣይ ከ 20 ሳ.ሜ እስከ 25 ሳ.ሜ ርዝመት በስለታማ ብላዋ ወይም ማጭድ ተቆርጦ በፓለቲ ቱብ
ብዘጋጅ ይመረጣል፣

የተከላ ጊዜን በተመለከተ፣

 የተከላ ጊዜ በቂ እርጥበት ባለበት ወቅት ጧዋት 12፡00 እስከ 3፡30 እና ማታ ከ 10፡00 ጀምሮ ብተከል
ይመረጣል፣
 ወቅቱ የዝናብ ሥርጭቱ በተሰተካከለ በደቡብ ምዕራብ አከባቢ የመደበኛ ዝናብ ሥርጭት ከበልግ
ወቅት አንስተው እስከ መኸር ወቅት ማለትም ከመጋቢት እስከ ነሐሴ ወር ብሆን ይመረጣል፡፡

የአሪቲ ቅመም በማሣ ላይ እንክብካቤ፤

 አሪቲ ተክል በማሣ ላይ ከ 3-4 ጊዜ ኩትኳቶ እና አረም መቆጣጠርን ይፈልጋል፡፡

 በለሰለሰ አፈር ሥሩ ማሳቀፍን እንዲሁም ደቃቅ ኮምፖስት ወይም የተፈጥሮ ማዳበሪያ በተፈቀደ ጊዜ
መስጠት እን ጤና አዳሚ፣የሥጋ መጥበሻ (ሮዝ መሪ)፣በሶ ብላ፣ ያሉት በደባልነት እየመረቱ እና የክሽክሽ
ተባይ በየጊዜው መከታተል ምርታማ ያደርጋል፡፡ አረቲ ቅመም በአከባቢው ጥላ እንድኖር አይፈልግም፡፡

አሪቲ ቅመም ባሕላዊ ጠቀመታ፤

አሪቲ ለሆድ ሕመም፣ ለወባ/ኡኖ/፣ ለራስ ምታት፣ ለጨጋራ፣ለካንሰር ፣ለተለያዩ ለዉስጥ ደወ እና ለቆዳ
በሽታዎች ፈዋሽ መድኃኒት ነው፡፡ ለሕፃናት፣ ለወላድ እናቶች እና አቅሜ ደካሞች እንድሁም አዛዉንቶች
ከቡና ቅጠል ጋር እና ከቅቤ ጋር በመጠጣት ይበረታታሉ ወይም ይነቃቃሉ፡፡

 ለመዓዛነት ይጠቃማሉ በሽቶነት በበዓለት፣ በሠርግ ጊዜ፣ከበሕላዊ አልባሳት ጋር ከቡሎኮና ከጋቢ ተጠቅልሎ
በትላልቅ ጋኖች ውስጥና በሣጥን ውስጥ ይቀመጣል፡፡
 አዲስ ቤት ተሰርቶ በሚገቡበት ጊዜ ለመልካም መዓዛ፤ ለውቤት በከሰል ማንዳጃ ወይም በእንክርት ማጨስ
/ማጠን/ የተለመደ ጠቀሜታ አለዉ፣
 አሪቲ ቅመም ለክብር እንግዳ ከቁጢ ቡና /ሃይሳ ቱኬ/ ጋር ምግብ በሚቀርብበት ወቅት ይቀርባል፤
7

 አሪቲ ቅመም በመልክም መዓዛነቱ ለወዳጅ ዘመድ ሥጦታ ይሰጣል፤ይላካል እንድሁም ወጣቶች ለፍቅር
መገለጫ ወንዱ ለሴቷዋ እና ሴቷዋ ለወንዱ የፍቅር ስጦታነት ይጠቀማሉ፣

የአሪቲ ቅመም ለማምረት የሚያሰፈልገው አየር ንብረት፤

 አሪቲ በጎፋ ዞን ከባሕር በላይ 1200-3500 ከፍታ የአየር ንብረት ባሉባቸዉ አከባቢዎች በሙሉ የሚመረት

ስሆን፤ ለበለጠ ምርታማነት የሚመከረው የአየር ንብረት ወ/ደጋ ሆኖ ከ 1350-1850 ከፍታ የበለጠ
ይመረጣል፤
 አሪቲ ተክል ለምርታማነት የሚፈለገው የዝናብ መጠን ከ 900-1200 ሚ.ሜ፤

 አሪቲ ተክል ለምርታማነት የሚፈለገው የሙቀት መጠን ከ 18-28 co ፤

 አሪቲ ተክል ለምርታማነት የሚፈለገው የአፈር ዓይነት ቀይ፣ አስዳማ፣ ጭንጫማ ውሃ የማይተኛ
በተደጋጋም የታረሰና ከአደገኛ አርም ነፃ የሆነ አፈር ሲሆን ጥላ አይፈለግም፣ ነገር ግን የተፈጥሮ ማዳበሪያ
ወይም ኮምፖስት ይፈልጋል፡፡

የተከላ ጊዜን በተመለከተ፣

 የተከላ ጊዜ በቂ እርጥበት ባለበት ወቅት ጧዋት 12፡00 እስከ 3፡30 እና ማታ ከ 10፡00 ጀምሮ ብተከል
ይመረጣል፣
 ወቅቱ የዝናብ ሥርጭቱ በተሰተካከለ በደቡብ ምዕራብ አከባቢ የመደበኛ ዝናብ ሥርጭት ከበልግ
ወቅት አንስተው እስከ መኸር ወቅት ማለትም ከመጋቢት እስከ ነሐሴ ወር ብሆን ይመረጣል፡፡

የአሪቲ ቅመም በማሣ ላይ እንክብካቤ፤

 አሪቲ ተክል በማሣ ላይ ከ 3-4 ጊዜ ኩትኳቶ እና አረም መቆጣጠርን ይፈልጋል፡፡

 በለሰለሰ አፈር ሥሩ ማሳቀፍን እንዲሁም ደቃቅ ኮምፖስት ወይም የተፈጥሮ ማዳበሪያ በተፈቀደ ጊዜ
መስጠት እን ጤና አዳሚ፣የሥጋ መጥበሻ (ሮዝ መሪ)፣በሶ ብላ፣ ያሉት በደባልነት እየመረቱ እና
የክሽክሽ ተባይ በየጊዜው መከታተል ምርታማ ያደርጋል፡፡ አረቲ ቅመም በአከባቢው ጥላ እንድኖር
አይፈልግም፡፡

አሪቲ ቅመም ምርታማነት በሄ/ር፣

 የአረቲ ቅመም በጎፋ ዞን ባሉት ወረዳዎች እንደ የአግሮኢኮሎጅ ተሰማምነት እና የዝናብ ሥርጭት
በተስተካከለ ሁኔታ እና የአምራቹ አ/አደር ውጤታማ የማሣ እንክብካቤ ቦታ በታከለበት ወቅቱ
8

ምርታማነት ከቦታ ወደ ቦታ እንደ ሁኔታው ቢለይም በሄ/ር 40 ኩ/ል እስከ 50 ኩ/ል ይመረታል ወይም
ይታጨዳል፣ይሰበሰባል፣ወደ ገበያም ይላካል፡፡

የአሪቲ ቅመም ምርት አሰባሰብ፤

 አረቲ ቅመም በተስማም አየር ጸባይ የተስተካከለ የዝናብ ሥርጭት የአ/አደሩ ተገቢ የማሣ እንክብካቤ
ተክሎበት በተተከለ በ 3 ወር እና ከዛ በላይ ባሉት ቀናት ለአጨዳ ይደረሳል፡፡ በነባሩ ማሣ ያለው የአሪቲ
ተክል በተቆረጠ በየ 3 ወሩ እየታጨደ በጥሩ የዝናብ ጊዜ ማሣ እንክብካቤ በዓመት 3 ጊዜ እና በላይ
አንዳንዴ ምርት ይሰበሰባል፡፡
 የአጨዳ ወቅት ዝናብ ወይም የጠዛ ሰዓት ባይሆን ይመረጣል፣ የአጨዳ መሣሪያ ስለታማና በአልኮል
የተጠረገ ብላዋ ወይም ማጭድ መሆን አለበት፡፡

የአሪቲ ቅመም ምርት የግብይት ሥርዓት ፤

 በደቡብ ክልል የሕግ መቀፍና የግብይት ሥርዓት ያልወጣላቸው የቅመማ ቅመም ምርቶች አንዱ
የአረቲ ቅመም ምርት ነው፡፡
 በጎፋ ዞን በሁሉም አሪቲ ቅመም አምራች ወረዳዎች የገበያ ትስስር ስለአልነበረ ደላላዎችና ነጋዴዎች
በመሰላቸው ዋጋ ምርቱን ይገበያሉ ወይም ይገዛሉ፡፡ እንዲሁም ከማሳቸው አሰጭዶ በሚመቻቸው
ዋጋ ይገዛሉ፡፡ ለምሳሌ 1 ኩ/ል በ 800 ብር ይገዛሉ፣በሌላ ቀን 1 ኩ/ል 1500 ብር ይገዛሉ፣ሲያሳሻቸው
በሌላ ጊዜ 1 ኩ/ል 2500 ብር ይገዛሉ፡፡ ጥሩ ገበያ አለበት በተባለ ወቅት የወላይታ ነጋዴዎች እስከ 3000
ብር ይገዛሉ 1 ኩ/ል፡፡ ምክንያቱ የሕግ ማቀፍ የለም

የአሪቲ ቅመም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሚታ፤

 ምርቱ ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ተዘጋጅተው በእርጥብም ሆነ በደረቅ ይቀርባል፡፡


 በንፁህ ጆኒያ ተደርጎ በሞተር ሣይክል፣በባጃጅ፣በመኪና በጋማ ከብት በሰውም ሸክምም ………ወዘተ
ከቦታ ወደ ቦታ ማዘዋወር ይቻላል፡፡
 የአረቲ ቅመም ምርት በግብይት ሥርዓቱ ከማሣ እስከ ገበያ ወይም እስከ ወላይታ ገበያ ድረስ
በየደረጃው የንግድ ተሳታፊ ሁሉ ተጠቃም ሆነዋል፡፡
9

 እንዲሁም የሕግ ማቀፍ ባለመኖሩ ከአ/አደሩ ወይም ከአምራቹ ሕብረተሰብ ይልቅ ደላላና ነጋዴ
በተሸለ ተጠቃም ናቸዉ፡፡
 ምክንያቱም ምርቱ በሕጋዊ ሚዛን ተመዝኖ ሳይሆን በተለምዶ በግምት የግብይት ሥርዓት
ስለሚካሄድ ነው፡፡
 ይሁን እንጅ የአረቲ ቅመም ምርት በባህላዊ ሆነ በሳንሳዊ መንገድ ጠቃም የአገር በቀል ቅመም ስለሆነ
በብዛትና ጥራት በሁሉም አከባቢ በማምረት አምራቹ ህብረተሰብ እና አገርን ተጠቃሚ በማድረግ
የአገርን ኢኮኖሚ ማሳደግ ይቻላል፡፡

የአሪቲ ቅመም ላይ የሚታዩ ማነቆዎች፤

 በአሪቲ ቅመም በስፋት አምርተው ለገበያ በብዛትና በጥራት ከማቅረብ አኳያ ክፍተት መኖሩ፤

 የግብይት ሥርዓት በሕጋዊ መንገድ ያለመደገፍ ክፍተት፣

 የገበያ ትስስር ያለመኖር፣

 መጓጓዣ ሥርዓቱ ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ያለመሆን፣

 የምርቱ አደራረቅና አከመቻቸቱ ሳይንሳዊ ሂደቱን ያለመከተሉ፣

 ለአሪቲ ቅመም ምርት ሕጋዊ እውቅና ያለመሰጠቱ /የሕግ ማቀፍ ያለመኖሩ፤

 የምርምር ማዕከላት በሳንሳዊ መንገድ ያጠኑትን የጥናት ውጤት በጊዜ ያለመድረሱ ዋና ዋና


ማነቆዎች ናቸው፡፡

የአሪቲ ቅመም የጎፋ ዞን የአገር በቀል ምርት ስለመሆኑ ያረጋገጡት፣

 የዕድሜ ባለፀጋ ሽማግሌዎች ፤

 የወንዶገነት የግብርና ምርምር ማዕከል ተመራማረዎች ፤


 በውርክ “በካዎ ጋሮ“ ያለው የአሪቲ ቅመም እንድ የጫካ አረም ዓይነት ሣር ሆኖ መኖሩ ፤እስከ ዛሬ
አሪቲ ቅመም የጎፋ ዞን ነትቨ /የአገር በቀል/ ቅመም መሆኑን የሚያራጋገጥ እውነታ ነው ፡፡

አመሰገናለሁ //
10

You might also like