Professional Documents
Culture Documents
የመመሰረቻ ጽሑፍ
አንቀጽ አንድ
ምሥረታ
በሰነዱ ግርጌ ፊርማችንን ባሰፈርነዉ መካከል በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ በዚህ መመሰረቻ ጽሐፍና ተያይዞ በሚገኘዉ የመተዳደሪያ ደንብ ስምምነቶች
የሚገዛና ዓላማዉም ከዚህ በታች በአንቀጽ 4 ሥር የተመለከተትን የንግድ ሥራ ተግባራት ማከናወን የሆነ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር
ለመመሥረት ስምምነት ተደርጓል፡፡
አንቀጽ ሁለት
አድራሻ
ዘግነት
ተ.ቁ
ሰም
ከተማ
ከተማ
የቤ.ቁ
ወረዳ
ክፍለ
አቶ አበበ ባንጃዉ ወንድምአገኘሁ
1 ኢትዮጵያዊ አ/አ ን/ስ/ ላፍቶ 12 አዲስ
(ADP in BLDG.ENG + BSc in COTM + MSc in COTM)
ወ/ሮ አፀደ አርሼ ዲዶ
2 ኢትዮጵያዊ አ/አ ን/ስ/ ላፍቶ 12 አዲስ
(ADP in BLDG.ENG)
ወ/ሪት አምሮት አንጀሎ አርሼ
3 ኢትዮጵያዊ አ/አ ን/ስ/ ላፍቶ 12 አዲስ
(BSc in CIVIL ENG. + MSc in COTM)
አቶ ደረጀ ባንጃዉ ወንድምአገኘሁ
4 ኢትዮጵያዊ አ/ም ሼቻ በሬ
(ADP in BLDG.ENG + BSc in CIVIL ENG.)
አቶ ተድላ ወርቁ አበራ
5 ኢትዮጵያዊ አ/ም ሼቻ
(BSc in ARCHITECTURE)
አቶ ዮሰፍ አሸናፊ አርሼ
6 ኢትዮጵያዊ አ/አ ን/ስ/ ላፍቶ
(BSc in CIVIL ENG.)
አቶ ክሩቤል አንጀሎ አርሼ
7 ኢትዮጵያዊ አ/ም ሼቻ
(BSc in CIVIL ENG.)
ወ/ሪት ዮኋና አምሳሉ አሰፋ
8 ኢትዮጵያዊ አ/ም ሼቻ
(BSc in CIVIL ENG.)
አቶ ዳግማዊ ነገዱ ባንጃው
9 ኢትዮጵያዊ አ/ም ሲቀላ
(BSc in MECHANICAL ENG.)
አቶ ዳኛቸው አማኑ ወንድምአገኘሁ
10 ኢትዮጵያዊ ሲቀላ
(DP in ELEC.ENG + BSc in CIVIL ENG.)
አቶ ሸበለው በድሉ ወንድምአገኘሁ
11 ኢትዮጵያዊ አ/ም ሼቻ
(ADP in Water + BSc in URM + MSc in COTM.)
አቶ በዕውቀቱ አወቀ አልቶ
12 ኢትዮጵያዊ አ/ም ሼቻ
(BSc in Wat t& Env + MSc in Hyd ENG.)
አንቀጽ ሦስት
1.1 የማኀበሩ ስም ጀኔሪክ (GENERIC) አማካሪ አርክቴክቶች እና መሀንዲሶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ነዉ፡፡
1.2 አባላቱ ወደ ፊት በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም ሆነ ከኢትዮጵያ ዉጭ ቅርንጫፍ የመክፈት
መብታቸዉ አንደተጠበቀ ሆኖ የተመዘገበዉ የማኀበሩ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ከተማ
ን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት/ቁ አዲስ ዉስጥ ነዉ፡፡
አንቀጽ አራት
አንቀጽ አምስት
የማኀበሩ፣ ካፒታል
የማኀበሩ ካፒታል ብር 2,220,000.00 ሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ብር/ ሲሆን ይኸዉ ገንዘብ በጠቅላላ በጥሬ ገንዘብ ብር 600,000.00
/ስድስት መቶ ሺህ ብር/ እና በአይነት ብር 1,620,000.00 /አንድ ሚሊየን ስድስት መቶ ሃያ ሺህ ብር/ በሙሉ በአባላት ተከፍሏ፡፡ ጠቅላላዉ
ካፒታል እያንዳንዳቸዉ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ዋጋ ባላቸዉ 2220 /ሁለት ሺ ሁለት መቶ ሃያ/ አክስዮኖች ተከፍሏል፡፡
ገንዘብ በጥሬ
የአንዱ
በአይነት
መዋጮ
ጠቅላላ
ተ.ቁ
ስም
ዋጋ
መጠን
በአይነት የተዋጣ
1. አቶ አበበ ባንጃዉ ወ/አገኘዉ ግምቱ ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ የሚያወጣ የስሌዳ ቁጥር 2-A45719
የሻንሲ ቁጥር NZE120-3076288 የሞተር ቁጥር 2NZ-3461403 ሞዴል CBA-NZE120-AEPNK የሆነዉን
አዉቶሞቢል መኪና እና ግምቱ ብር 200,000.00 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ የሚያወጡ ሁለት ላፕ ቶፖች የሲሪያል
ቁጥራቸው 3424354356465 እና 4586676667 የሆኑትን ዘመናዊ ገሚንግ ላፕቶፖች ለዲዛይን ሥራ የሚያገለግሉ
በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
2. ወ/ሮ አፀደ አርሼ ዲዶ ግምቱ ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ የሚያወጣ የሰሌዳ ቁጥር 2-A23449 የሻንሲ
ቁጥር JT132LNH300008390 የሞተር ቁጥር 2L-4686524 ሞዴል LN170L-CRMDXW የሆነዉን ደረቅ ጭነት ፒካፒ
መኪና እና ግምቱ ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ ብር/ የሚያወጡ ሁለት ላፕ ቶፖች የሲሪያል ቁጥራቸው
3424354356465 እና 4586676667 የሆኑትን ላፕቶፖች ለቢሮ ሥራ የሚያገለግሉ በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ
አድርገዋል፡፡
3. ወ/ሮ አምሮት አርሼ ግምቱ ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/ የሚያወጣ የሰሌዳ ቁጥር 2-A23449 የሻንሲ
ቁጥር JT132LNH300008390 የሞተር ቁጥር 2L-4686524 ሞዴል LN170L-CRMDXW የሆነዉን ደረቅ ጭነት ፒካፒ
መኪና በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
4. አቶ ደረጀ ባንጀው ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ 3424354356465 የሆነ
ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
5. አቶ ተድላ ወርቁ አበራ ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ 3424354356465
የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
6. አቶ ዮሰፍ አሸናፊ አርሼ ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ 3424354356465
የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
7. አቶ ክሩቤል አንጀሎ አርሼ ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ
3424354356465 የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
8. ወ/ሪት ዮኋና አምሳሉ አሰፋ ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ
3424354356465 የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
9. አቶ ዳግማዊ ነገዱ ባንጃው ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ
3424354356465 የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
10. አቶ ዳኛቸው አማኑ ወንድምአገኘሁ ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ
3424354356465 የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
11. አቶ ሸበለው በድሉ ወንድምአገኘሁ ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ
3424354356465 የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
12. አቶ በዕውቀቱ አወቀ አልቶ ግምቱ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የሚያጣ ላፕ ቶፕ የሲሪያል ቁጥሩ
3424354356465 የሆነ ለቢሮ ሥራ እንዲያገለግል በአይነት ወደ ማህበሩ ገቢ አድርገዋል፡፡
አንቀጽ ስድስት
የአባላቱ ኃላፊነት
አባላት ከላይ የተጠቀሰዉን ካፒታል በጥሬ ገንዘብ እና በአይነት በሙሉ የተከፈለ መሆኑን በአንድነት እና በነጠላ አረጋግጠዋል፡፡ ስለሆነም የአባላቱ
ኃላፊነት በማኀበሩ ዉስጥ ባላቸዉ አክስዮን መጠን የተወሰነ ነዉ፡፡
አንቀጽ ሰባት
አባላቱ በተለየ ሁኔታ ካልተስማሙ በስተቀር ከጠቅላላዉ ዓመታዊ ትርፍ ሕጋዊ የመጠባበቂያ ገንዘብ እና ሌሎች ጠቅላላ ወጪዎች ከተቀነሱ በኃላ
ቀሪዉ በአባላት መካከል እንደ አክስዮን ይዞታቸዉ ይከፋፈላል፡፡ ኪሳራም ካለ በተመሳሳይ ሁኔታ በአባላቱ መካከል ይከፋፈላል፡፡ ሆኖም አባላቱ
በማኀበሩ ዉስጥ ካለዉ የአክስዮን ካፒታል በላይ ተጠያቂ ሊሆኑ አይችሉም፡፡
አንቀጽ ሰምንት
ጠቅላላ ጉባዔ
አንቀጽ አስር
የማኀበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሥልጣን ተግባር
10.1. የማኀበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሥራ ዘመናቸዉ ሲያልቅ በድጋሚ ሊመረጡ ይችላሉ፡፡ ማህበሩ በዋና ዳይሬክተር
እንደ አስፈላጊነቱ የሚሾሙ የዘርፍ ሥራ አስኪያጆች ሊኖሩት ይችላል፡፡ የሥራ አስኪያጅ ስልጣንና ተግባር
የሚከተለዉ ይሆናል፡፡
10.2. የዘርፍ ሥራ አስኪያጅን ይሾማል፣ ይሽራል፣ ተግባራቸዉን ዘርዝሮ ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፡፡
10.3. ማኀበሩ በመወከል ይፈርማል፡፡
10.4. ለማኀበሩ ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ተግባሮች ኃላፊ ነዉ፡፡
10.5. የጠቅላላ ጉባዔ ዉሳኔዎችን ሥራ ላይ ያዉላል፡፡
10.6. ለማህበሩ የሚከፈል ገንዘብ መቀበል፣ የማህበሩን ዕዳዎች መክፈል፣ ማናቸዉም የሐዋላ ወረቀት የተሰፋ ሰነድ፣
የባንክ ሰነድ ማዘጋጀትና በጀርባ ላይ መፈረም፣ ማደስና መክፈል እንዲሁም የጭነት ማስታወቂያ ደረሰኞች፣ የቦንድ
ሰርተፊኬቶችን ወይም ማናቸዉንም ሰነዶች ማጽደቅና ከጀርባዉ መፈረም፡፡
10.7. የማኀበሩ ወኪል ወይም ሠራተኛ ይቀጥላል፣ ያሰናብታል፣ ክፍያዉን፣ ደሞዙን ጉርሻን ሌሎች ከመቀጠርና ከመሰናበት
ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች ይወሰናል፡፡
10.8. በማህበሩ ስም የባንክ ሂሣቦች ከፍቶ ገንዘብ ገቢ ያደርጋል፡፡ ሂሣቦቹን በፊርማዉ ያንቀሳቅሳል፡፡
10.9. የማንኛዉም በኢትዮጵያ ዉስጥ ካለ ወይም የዉጭ አገር ባንክ ገንዘብ ድርጅት በመያዣ ወይም በማህበሩ ስም
መፈረም፣
10.10. ማናቸዉም ዉሎች ወይም ስምምነቶች መግባት መፈፀምና መፈረም፡፡
10.11. በአገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ሀገር በሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች፣ ፍ/ቤቶች፣ ኮርፖሬሽኞች፣ እና ህጋዊ ተቌማት
ፊት ማህበሩን በመወከል መፈረም፣
10.12. በማህበሩ ስም በማንኛዉም የመንግስት ሆነ የግል ባንኮች ሂሳብ መከፍት እና ሒሳቡንም በፊርማዉ ማንቀሳቀስ፣
10.13. በጠቅላላ የማህበሩ ዓላማ ግብ ለማድረስ ወይም የማህነሩን ጥቅም ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን ይፈፅማሉ፣
10.14. ለማኀበሩ ንግድ በመልካም ሁኔታ መካሄድ የሚጠቅሙ ግዢዎች ሽያጭና የእነዚህን ማዘዣዎች ይወስናል፣ የኪራይ
ዉል ይዋዋላል፡፡
10.15. ከማኀበሩ ንግድ ጋር የተያያዙ ማናቸዉንም የንግድ ልዉዉጥ በተመለከተ ከሦስተኛ ወገኞች ጋር ዉል ይዋዋል፣
በማህበሩ ስም የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ይገዛል ይሸጣል በስጦታ ያስተላልፋል፣ በማህበሩ ስም
ስጦታ ይቀበላል፣
10.16. በማናቸዉም ፍርድ ቤት ማኀበሩ ከሳሽ፣ ተከላሽ ወይም ጣልቃ ገቢ በሚሆንበት ጉዳይ ሁሉ ማኀበሩን በመወከል
አስፈላጊዉን ይፈጽማል፣ እንደዚሁም የሕግ ጠበቃ ወይም አማካሪ በመወከል ይከራከራል፡፡
10.17. ማኀበርቶኞች ሲቀበሉትና ሊያፀድቁት እንዲችሉ የሂሳብ ወጪና የገቢ መዝገብ በደንቡ እንዲያዝ አስፈላጊዉን
እርምጃ ይወስዳል፡፡ የማህበሩ ዓላማ ግቡን እንዲመታ አስፈላጊ መስሎ በታየዉ ጊዜ ለዋናሥራ አስኪያጅ ከተሰጠት
ስልጣንና ተግባር መሀል ማንኛዉንም በሌላ ለሦስተኛ ሰዉ እንዲፈጸም በማኀበሩ ስም ዉክልና መስጠት ይችላል፡፡
10.18. የማኀበሩን የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ይሸጣል ይስዉጣል በባንክ በዋስትና በማስያዝ ገንዘብ
ይበደራል፡፡
10.19. የማኀበሩን ወይም የሌላ ሦስተኛ ወገን የሚንቀሳቀስ ወይም የማንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በማድረግ ከግልም ሆነ
ከመንግስት ባንኮች የብድር ዉሎችን ተዋዉሎ ብድር ይበደራል፡፡
10.20. በማህበሩ ስም የተፃፋ ቼኮች ላይ ይፈርማል፣ ቼክ ያዘጋጃል፣ በፊርማዉ ያንቀሳቅሳል፡፡
10.21. የማህበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ማናቸዉም በሕግም ሆነ በዚህ የመመስረቻ ጽሁፍ የተሰጡትን ስልጣን በሙሉ
ወይም በከፊል ለተወሰነ ጊዜ ለሌላ የማህበሩ አባል በዉክልና ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡እንደዚሁም ዋና ሥራ አስኪያጅ
መቅጠር የሚችሉ ሲሆን ለሚቀጠረዉ ስልጣኑን በሙሉ ወይም በከፊል በዉክልና ማስተላለፍ ይችላል፡፡ ዋና ሥራ
አስክያጅ ለማህበሩ ጥቅም ሲባል ለማህበሩ አባል ለሆነ ስልጣኑን ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ዋና ሥራ አስኪያጅ ለሌላ
አካል እና ለቀጠረዉ የተሰጠዉን ዉክልና ሳይሽሩ በዚያዉ ጊዜ ዉስጥ በዚያዉ ስልጣን በተደራቢነት ሊሰራ ይችላሉ፡፡
ዋና ሥራ አስኪያጅ ከድርጅቱ ኃላፊ ወይም ሰራተኞች የባንክ ሒሳብ እንዲያንቀሳቅሱ ወይም ዉል እንዲፈርሙ
መወከል ይችላል፡፡
10.22. የዋና ሥራ አስኪያጅ ደሞዝ በጠቅላላ ጉባዔ ይወሰናል፡፡
10.23. የማህበሩ ካፒታል ½ በላይ ሲጠፋ አስቸኳይ ልዩ ጉባዔ ይጠራል፣
የማህበሩ ዋና ሥራ አስክያጅ በማይኖሩበት ጊዜ ሁሉ እርሳቸዉን ተክተዉ ይሰራሉ፣ ለእሳቸዉ የተሰጣቸዉን ስልጣን በሙሉ
ያከናዉናሉ፡፡
ጠቅላላ ጉባዔዉ ወይም ዋና ሥራ አስኪያጅ ተቆጣጣሪዎችን ይሾማል፣ ይሽራል፣ የሚከፈላቸዉን የክፍያ መጠን ይወስናል፡፡
ተቆጣጣሪዎች የኩባንያዉን ሒሳብ በየሩብ ዓመቱ ማለትም በዓመት አራት ጊዜ ተመርምሮ በየሩብ ዓመቱ ሪፖርት
እንዲቀርብ በአራተኛዉ ሩብ ዓመት የዓመቱ መጠቃለያ ሒሳብ እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡
አባላቱ በተለየ ሁኔታ ለመወሰን ያላቸዉ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ ማኀበሩ የተቌቌመዉ ላልተወሰነ ጊዜ ነዉ፡፡