You are on page 1of 2

3ኛ ክፍል

የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት

Lesson 1

አካባቢያችን እንቅስቃሴ

ሰዎች በህይወት ለመኖር የሚያስፈልጋቸው መሰረታዊ ነገሮች አሉ፡፡ እነርሱም፡- ምግብ፣


ልብስና መጠለያ ናቸው፡፡ እነዚህን መሰረታዊ ነገሮች ለማግነኘት ሰዎች
ስራመሰ4ራትአለባቸው፡፡ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ለማሟላት የሚሰሯቸው ስራዎች
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ኢንዱስትሪ፣ንግድ፣ትራንስፖርት እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

አፈር እና የሰብል ምርት

ተክሎች ለማደግ ከሚያስፈልጓቸው ዋና ዋና ነገሮች ውስጥ አንዱ አፈር ነው፡፤ ተክሎች


ከአፈር ውስጥውሃ እና ማዕድናትን ያገኛሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አፈርየተክሎችን ስር ደግፎ
በመያዝ ተክሎች እንዲቆሙ ያደርጋል፡፡ በአከባቢያችን የተለያዩ የአፈርአይነቶች ይገኛሉ፡፡
እነዚህ የቸፈር አይነቶች በሶስት ይከፈላሉ፡፡

እነርሱም፡-

- ለም አፈር
- አሸዋማ አፈር
- የሸክላ አፈርናቸው

ከነዚህ የአፈርአይነቶች ውስጥለተክሎች እድገት ተስማሚ የሆነው ለም አፈር ነው፡፡ ይህ


አፈርለተክሎች እድገት ተስማሚ የሆነ ባህሪ አለው፡፡ ሰም አፈርየሚሰራው ከፍግ፣ከእፅዋ፣
ብስባሽ እና ከሞቱ እንሰሳት ፍርስራሽ ነው፡፡

የለም አፈር ባህሪያት

- ቀላል ነው
- በማዕድናት የበለፀገ ነው
- በይ ለማውጣት አመቺ ነው
- የተክሎችን ስርበቀላሉ ያሳልፋል
- ውሃየመያዝ ባህሪ ስላለው በቀላሉ አይደርቅም
- ለተክሎች የሚሆን ምግብ አለው

ተክሎችን መትከል እና መንከባከብ

ተክሎች/እፅዋት/ ህይወት ላላቸው ነገሮች በጣም አስፈላጊ ነገር ናቸው፡፡ ስለዚህ ተክሎችን
መትከል እና መንከባከብ አስፈላጊ ነው፡፡ ተክሎችን ከመትከላችን በፊት ማድረግየሚገባን ነገሮች
አሉ፡፡

እነርሱም፡-

- ትክክለኛ ቦታ መምረጥ
- መሬቱን መመንጠርእና ማፅዳት
- ማረስ
- መደብ ማዘጋጀት
- ዘር መዝራትእና
- መትከል ናቸው

ተክሎችን ከተከልን በኋላ ልናደርግላቸው የሚገባ እንክብካቤዎች አሉ፡፡

እነርሱም፡-

- ውሃ ማጠጣት
- ማረም
- መከትኮት
- ፍግ መጨመር ናቸው

You might also like