You are on page 1of 1

የ4ኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ

ውሃማ አካል

- በውሃ የተሸፈነ የመሬት ክፍል ውሃማ አካል ይባላል፡፡


- የመሬት ¾ የሚሆነው በውሃ የተሸፈነ ነው፡፡
- ¼ የሚሆነው የመሬትክፍል በየብስ ወይም ደረቅ መሬት የተሸፈነ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ውሃማ አካላት

- ኢትዮጵያ በውሃ ሃብት ከአፍሪካ ከኮንጎ ኪኒሻሳ ቀጥላ በ2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ ነገር
ግን ኢትዮጵያ ከውሃ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እያገኘች አይደለም፡፡ ምክንያቱም
ከኢትዮጵያ የሚነሱ ወንዞች በቀላሉ ወደ ጎረቤት ሃገሮች ይፈሳሉ፡፡ ይህይሆነበት
ምክንያትደግሞ ኢትዮጵያ የመሬት አቀማመጥከፍተኛ ስለሆነ ነው፡፡
- ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ ትባላለች፡፡
- የኢትዮጵያ ውሃማ አካላት በሁለት ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-
1. ወንዞች
2. ሃይቆች ናቸው

የኢትዮጵያ ወንዞች

- ወንዞች በውሃ ሃይል የሚፈጠሩ ሸለቆዎች ናቸው፡፡


- ወንዞች ከፍተኛ ቦታ በመነሳት ወደ ዝቅተኛ ቦታ እናሸለቆዎች ይፈሳሉ፡፡
- በሚፈሱበት አቅጣጫ ላይ በመመስረት የኢትዮጵያ ትላልቅ ወንዞች በሶስት ይከፈላሉ፡፡
1. በሳሜን ምዕራብ አቅጣጫየሚፈሱ ወንዞች
ተከዜ፣አባይ፣ባሮ እና ገባሮቹ ናቸው፡፡
2. ወደ ደቡብ ምስራቅ የሚፈሱ ወንዞች
ዋቤ ሸበሌ፣ገናሌ፣ዳዎ እና ነባሮቹ ናቸው፡፡
3. ወደ ስምጥ ሸለቆ የሚፈሱ ወንዞች
አዋሽ፣ጊቤ እና ነባሮቹ ናቸው፡፡

You might also like