You are on page 1of 8

የኪዳነ ምህረት ፍርሬዎች ማህበር መዝሙር

በ ሰኔ 3 የሚዘመር

ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መጥተኸብኝ


1. እውነተኛ ሰላም
በርህን በመዝጋት ከደጅህ አታስቀረኝ

እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

እርደኝ አልናወጽ እለምንሃለሁ/2/

ኃጢአቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል

ከአንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል

ወደአንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለሁ

እውነተኝ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

ለቅዳሴው ጸሎት ዘወትር እንዳልተጋሁ

በአደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ

ተሰነካክዬ ወድቄአ ለሁና

እር ዳኝ አማኑኤል በሃይማኖት ልጽና

ዓይኔ እንባ ያመንጭ ላልቅስ ስ ለ ኃጢአቴ

የንስሓ ትሁን ቀሪዋ ሕይወቴ

በመዳኔ ሰዓት በዛሬዋ እለት

ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ከአንተ ፊት

ጌታ ሆይ ጸጸቴን እንባዬን ተቀበል

አባትህ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል


የአብራኩን ክፋይ አሳቅፊውና
2. ✞ ሲነግሩሽ ሰሚነሽ
ከኪዳንም በላይ••••••••••••

ያለሽ ልዩ ፀጋ ያለሽ ልዪ ክብር


አዝ__
የሁሉ እመቤት በሰማይ በምድር

አኩራሪተ መዐልት ምራገ ፀሎት


ተይዞ ለሚኖር በአልጋ ቁራኛ
ሲነግሩሽ ሰሚነሽ ኪዳነምህረት
አንቺው እመቤቴ የዴውም ዳኛ

መንገርስ ላንቺ ነው መማፀን ወዳንቺ


በመከራ ላለው ሁኝለት መፅናኛ
ተስፋን ለምትቀጥይ ህልምን ለምትፈቺ
ዕንባውን አብሺው አይዘን ዳግመኛ
ከኪዳንም በላይ••••••••
ጉድለቱን ሙይለት በፈረሰው ቆመሽ

ስለምታስምሪ በልዩ ኪዳንሽ


ሊቀ-መዘምራን
ከኪዳንም በላይ ኪዳንሽ ልዩ ነው
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
እናቴ የሚልሽ አምላክሽ ልጅሽ ነው

አዝ__

ይበጠሰ ከእጁ የወህኒው ሰንሰለት

የሞቱ ደብዳቤ ይቀየር በህይወት

አዲስ ተስፋ ሞልተሽ አዲስ ሰው አድርጊው

መቅበዝበዙ ይርሳ ድንግል አረጋጊው

ከኪዳንም በላይ•••••••••••••

አዝ____

በዕንባ የመጣው ይመለስ በደስታ

መጠማቱ ይቅር ይሞላ በእርካታ

ስለቱ ሰምሮለት ይቁም ለምስጋና


3. * አማኑኤል ተመስገን * የኃጢአት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም

ውጤቱ መሮ ፍጹም አይጥምም

አማን በአማን(፬) እንደ በደሌ ስላልከፈልከኝ

አማኑኤል ተመስገን ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ

ለዚህ ፍቅርህ ምን ልክፈልህ (፪)

ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጸው

ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው

እንደ ሰው በቀል ቢኖር ጌታ

ለኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ

አዝ=======

በየደቂቃው ኃጢአት ስሰራ

ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ

አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም

በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም

አዝ======

ምህረትህን ልከህ አድነኝ ዛሬ

ታክቶኛልና በኃጢአት መኖሬ

አለም በኃጢአት እየሳበችኝ

በጽድቅ ደስታ መኖር አቃተኝ

አዝ=====
ምን ይመልስ ይሆን በጌታ ፊት ሲቀርብ
4. ✞ በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
ለዝች አጭር ዘመን የሚስገበገቡ

አይረኩም አይጠግቡም ድሆች እያስራቡ


በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
ለዝች አጭር ዘመን የሚስገበገቡ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
አይረኩም አይጠግቡም ድሆች እያስራቡ
ተስፋ እንደ ሌላቸው አንሆንም ከቶ

ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ


አዝ______________

ያለቀሱ ሁሉ ይስቃሉ አይቀርም


የእህል ሽታ ጠፍቶ መሶቡም ቢራቆት
ይለዋውጠዋል ጌታ መድኃኔዓለም
ተስፋችን ሙሉ ነው እኛስ በጌታ ፊት
ማንም ያላሰበው ያልጠበቀውን ድል
ይህን ክፉ ዘመን ያሻግራል ጌታ
ለእኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል
ከሰራን በኋላ በፀሎት እንበርታ
ማንም ያልጠበቀው ያልገመተውን ድል
ይህን ክፉ ዘመን ያሻግራል ጌታ
ለእኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል
ከሰራን በኋላ በፀሎት እንበርታ

አዝ______________
መዝሙር

ሊቀ-መዘምራን ይልማ ሀይሉ


ሰዎች ቢጠበቡ ገንዘብ ለመሰብሰብ

ይጠላለፋሉ ባልጠበቁት መረብ

እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ

ክፋት እና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ

እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ

ክፋት እና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ

አዝ______________

ድሆች አስለቅሶ ግፍ የሚሰበስብ


እዝ------------
5. ኑ እንቅረብ
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ/2/
መጥቁ ተወለደ እንቅረብ በእልልታ
ሥጋውን እንብላ /2/ ደሙንም እንጠጣ
በኋላ አይረባም ዋይታና ጫጫታ

ይህንን እድል ፈጥነን እንጠቀምበት


የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይበት
ተሰውቶልናል እንመገበው

እድፉን ኃጢአታችን በንስሓ አንጽተን


እዝ------------
እንቀበልው አምነን በልጅነታችን

አሁኑ ቅረቡ ታውጇል አዋጁ


እዝ------------
የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ

ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ


መቅረብ ወደጌታ በእውነት የሚገባው
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው

ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱት

ከዋክብት በሰማይ የተነጠፉት

ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት/2/

እዝ------------

ቅድስት እናታችን ቤተክርስቲያን

ትመግበናለች ሥጋና ደሙን

የአማኑኤል ሥጋ ይኸው ተዘጋጀ

ለግብዣ ተጠራን አዋጁ ታወጀ


6. #አልተወኝም_ጌታ

አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል (፪)

ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል

ዛሬም ስበድለው ልጄ ነሽ ይለኛል

በበደል ጉራንጉር በኃጢአት ጫካ

ብጠፋበት እንኳ አልተወኝም ለካ

ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል

ለካስ አልጠላኝም ጌተ ይወደኛል (፪)

#አዝ

ለስልጣን ለክብሬ ብዬ ስክደው

ለገንዘብ አድልቼ እኔ ስረሳው

ለእኔ ያለው ፍቅር አልቀነሰብኝም

ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም(፪)

#አዝ

ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለው ወሰን

ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን

በሕይወቴ ሁሉ ፍጹም ለመራኝ

ክብርና ምስጋና አቀርባለሁኝ(፪)

መዝሙር

በማኅበረ ቅዱሳን

"ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም"

ዮሐ ፲፬፥፰
7. እውነተኛ ሰላም

እውነተኛ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

እርደኝ አልናወጽ እለምንሃለሁ/2/

ኃጢአቴን ሳስበው ልቤ ይጨነቃል

ከአንተ መለየቴ ነፍሴን አድክሟታል

ወደአንተ መልሰኝ እኔ እመለሳለሁ

እውነተኝ ሰላም ያለው ከቤትህ ነው

ለቅዳሴው ጸሎት ዘወትር እንዳልተጋሁ

በአደባባይ ቆሜ ስምህን እንዳልጠራሁ

ተሰነካክዬ ወድቄአ ለሁና

እር ዳኝ አማኑኤል በሃይማኖት ልጽና

ዓይኔ እንባ ያመንጭ ላልቅስ ስ ለ ኃጢአቴ

የንስሓ ትሁን ቀሪዋ ሕይወቴ

በመዳኔ ሰዓት በዛሬዋ እለት

ፍቅርህን አስቤ መጣሁ ከአንተ ፊት

ጌታ ሆይ ጸጸቴን እንባዬን ተቀበል

አባትህ ነኝ በለኝ እኔም ልጅ ነኝ ልበል

ዘይት ሳላዘጋጅ ድንገት መጥተኸብኝ

በርህን በመዝጋት ከደጅህ አታስቀረኝ


…አዝ…….
8. እኔ አንተ ቤት እኔ አንተ ፊት

መሻቴን ብቻ ስላየህ
እኔ አንተ ቤት እኔ አንተ ፊት
ደካማ ልጅህን ጎበኘህ
የምቆም ሰው አይደለሁም
ብቃቴ መቼ ሆነና
ግን ፍቅር ነህ ለዘላለም
ያቆመኝ ላንተ ምስጋና
የሚመስልህ ማንም የለም
አንኳኩ ስላልክ አንኳኳሁ

ጠይቁ ስላልክ ጠየቁህ


ፀሎቴ ቢሆን ለወረት
ከፍተሃል በርህን ለኔ
ጎዶሎ ቢሆን የኔ እምነት
የታተምኩብህ መድህኔ
ባረከኝ እኔን ከሰማይ

በደሌን ጥፋቴንም ሳታይ

ቀባኸኝ ጠርተኸኝ ከዱር

ሰጠኸኝ ከፍ ያለ ወንበር

ሳይኖረኝ አንድም በጎነት

ባረከኝ በጅህ በረከት

…አዝ……

ቃል ኪዳንህን አክባሪ

ታማኝ ነህ ሁሌም መሃሪ

የማልከውን መሃላ

አትረሳም አትልም ችላ

መካሪ ድንቅ መምህሬ

ላንተ ነው ዜማ መዝሙሬ

ፍቅር ነህ ከአባትም በላይ

የሰማይ የምድር ሲሳይ

You might also like