You are on page 1of 11

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ

በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ከአካባቢ መስተዳድር አካላት ጋር የምክክር መድረክ


ለማካሄድ የተዘጋጀ ቢጋር

ኅዳር 2012 ዓ.ም


ማውጫ

ርዕስ ገፅ

1 መግቢያ..................................................................................................................... 1

2 ዓላማ....................................................................................................................... 1

3 ማኅበረሰብ ተኮር የሆኑ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዋና ችግሮች.................................................................2

4 የሚጠበቅ ውጤት.......................................................................................................... 8

5 ተሳታፊዎችና የውይይት አካሄድ............................................................................................. 9

6 ሎጅስቲክና የጉዞ ወጪ...................................................................................................... 9

7 አባሪ 1 የባለድርሻ አካላት ምክክር መድረክ ዝግጅት አፈፃፀም መርሀ-ግብር................................................11

i
1 መግቢያ

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ከአካባቢያቸው ጋር የሚኖራቸው መልካም ግንኙነት ያቀዱዋቸውን ተግባራት


ለመፈጸም ከማገዙም በላይ ዘላቂነት ያለው ዕድገት ለማምጣት ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርታማና ተወዳዳሪ
ሆነው መዝለቅ እንዲችሉ የሚኖረው አስተዋፅዖ የጎላ ነው፡፡

በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ የኦፕሬሽን ዘርፍ ከሚከታተላቸው ድርጅቶች መካከል
የስኳር ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው በመስራት ምርትና ምርታማነታቸውን በማሳደግ የተቋቋሙለትን ዓላማ
ማሳካት እንዲችሉ እንዲሁም የስኳር ፕሮጀክቶች በተቻለ መጠን በተከለሰው መርሀግብራቸው መጠናቀቅ እንዲችሉ
ከአካባቢያቸው ህብረተሰብ ጋር በትብብር መስራት እና ፋብሪካዎቹና ፕሮጀክቶቹ ያጋጠሙዋቸውን ችግሮች
በመፍታት ረገድ የአካባቢያቸው መስተዳድር አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡

ነባር የስኳር ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው በማምረት የህብረተሰቡን የስኳር ፍላጎት ለማርካት ኮርፖሬሽኑ ከውጭ
ሀገር የሚያስገባውን ስኳር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ለሚደረገው ርብርብ የድርሻቸውን እንዲወጡ እንዲሁም
የስኳር ፕሮጀክቶች በቶሎ ተጠናቀው ወደ ምርት መሸጋገር እንዲችሉ ፋብሪካዎቹና ፕሮጀክቶቹ ከሚያጋጥሙዋቸው
ችግሮች መካከል ህብረተሰብ ተኮር የሆኑትን ከአካባቢ ህብረተሰብ ጋር የምክክር መድረክ በመፍጠር መፍታት
ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ሲባል የግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ ዳይሬክቶሬት ክትትልና ድጋፍ የሚደረግላቸው የስኳር
ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ያለባቸውን ችግሮች በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር ችግሮቹ እንዲፈቱ
ማድረግ በማስፈለጉ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ለማካሄድ መነሻ የሚሆን ቢጋር ተዘጋጅቷል፡፡

2 ዓላማ
ዋና ዓላማ

የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ነባር የስኳር ፋብሪዎችና እየተካሄዱ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ዕቅዶች ለማሳካት ተግዳሮት የሆኑ
ማህበረሰባዊ ጉዳዮችን፣ የፋብሪካዎቹንና ፕሮጀክቶቹን የሥራ ሂደት የሚጎዱ ተግባራትን ከአካባቢ መስተዳድር አካላት
ጋር በመወያየት ችግሮቹ በማን እንደሚፈቱ በመለየት በባለቤትነት መፍትሔ እንዲያገኙና የኮርፖሬሽኑ ዕቅድ እንዲሳካ
ማስቻል ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማ፡-

1. ከአካባቢ መስተዳድር አካላትና ማኅበረሰብ አንፃር ፋብሪካዎቹንና ፕሮጀክቶቹን ያጋጠሙዋቸውን


ችግሮቹ ምን እንደሆኑ የጋራ ግንዛቤ እንዲያዝ ማድረግ፤
2. የተለዩት ችግሮች በምን አግባብ እንደሚፈቱ የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ፣
3. ችግሮቹን ለመፍታት የእያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ኃላፊነት ድርሻ ላይ መግባባት መፍጠር፤
4. ለችግሮቹ አፈታት የጋራ ዕቅድ ማዘጋጀት ናቸው፡፡

1
3 ማኅበረሰብ ተኮር የሆኑ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዋና ችግሮች
ሀ. ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ

 ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ወጭ ተደርጎበት በአውትግሮወር ሞዳሊቴ ወደ ሸንኮራ አገዳ ልማት

ከገባ በኋላ በተለያየ ምክንያት ከአውትግሮወር የወጣ 2509.34 ሄ/ር መሬት መኖሩ፤
 ህጋዊ የፋብሪካው ይዞታ ላይ የዛሬ 10 ዓመት አርባ አምስት ሺህ ብር በሄ/ር የተከፈለ ካሳ
ገንዘብ ትንሽ ነው በማለት በህገወጥ መንገድ የመሬት ወረራ መደረጉ፤ በተጨማሪ በአዳማ
ወረዳ በአሮጌው የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የሚገኝ የፋብሪካውን ይዞታ በሀይል ማረስ፣
 ፋብሪካው የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ያለው ቢሆንም ከማስፋፊያ ፕሮጀክት ትግበራ ጋር
ተያይዞ ወደ ፋብሪካው የተካለለ በቦሰት ወረዳ 57.56 ሄ/ር እና በአዳማ ወረዳ 5.92 ሄ/ር መሬት
ለዞንና ወረዳዎች የቀረበውን የይዞታ ማረጋገጫ ጥያቄ ዕልባት ማስገኘት፤
 በፋብሪካው ኮማንድ ክልል ውስጥ የሚታየውን የጸጥታና የህገወጥነት ችግር በስራ ላይ ተጽእኖ

መፍጠሩ፤
 በአውትግሮወርስ ልማት ክልል በውጭ ምንዛሪ ተገዝተው ሥራ ላይ የዋሉ የመስኖ መሠረተ ልማቶች
ስርቆት መበራከት /የተለያዩ ስፕሪንክለር፣ መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሆዝ ወዘተ…/
 ፋብሪካውን እና የአከባቢውን ህብረተሰብ አደጋ ላይ ይጥላል ተብሎ የእርሻ ሥራ እንዳይሰራበት
የተባሉ የአዋሽ ግድብ ግርጌዎችን ለእርሻ ልማት መዋል፤
 ቀደም ብሎ ልማቱ ሲጀመር የልማቱ አካል የነበሩ የመንገድ፣ የውሃ ቦዮች፣ ኩሬዎች፣ ወዘተ፣

ቦታዎች ላይ ያልተከፈሉ የካሳ ክፍያዎች በህብረተሰቡ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ

ማስነሳት፤ በፋብሪካውና በአውትግሮወር ላይ ኪሳራ እያስከተለ መሆኑ፤


 በአርሶ አደሮች መሬት ላይ የሚለማውን ልማት ከመሬት ዝግጅት እስከ አገዳ ማጓጓዝ ድረስ

ያለውን ስራ በዋናነት የሚከናወነው በፋብሪካው መሆኑ፤


 ምርትና ምርታማነትን በመጨመር የአርሶ አደሩን ገቢ እንዲያድግ ከማድረግ ይልቅ የአገዳ

መሸጫ ዋጋ እንዲጨምርና በዚህ አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ

ያለመኖሩ፤ የስኳር ማምረቻ ወጪን እንዲጨምር ያደረገ መሆኑና የስኳር ዋጋ በመንግሥት

የሚወሰን በመሆኑ ይህንን የአገዳ ዋጋ ጭማሪ ለመሸከም ማስቸገሩ፤


 የጐርፍ መከላከያ ግድብ ጥገና ሥራ ባለቤት አለማግኘት፣
 ለማህበራዊ ተቋማት ግንባታ የተለቀቀ ገንዘብ ሰነድ እንዲወራረድ ያለመደረጉ፤
 በኮርፖሬሽኑ ወጭ ለአካባቢ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት

ርክክብ ያለመደረጉ

ለ. መተሀራ ስኳር ፋብሪካ

2
 የፋብሪካው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተለያየ ጊዜ የልኬት ስራ የተሰራ ቢሆንም ካርታውን

ማግኘት አለመቻሉ፤
 በፋብሪካው ኮማንድ ክልል ውስጥ የሚታየውን የጸጥታና የህገወጥነት ችግር በስራ ላይ ተጽእኖ

መፍጠሩ
 ፋብሪካው ለረጅም ጊዜ እያለማ ያለውን መሬት የአካባቢው ማህበረሰብ እንደ አዲስ የካሳ ክፍያ

እንዲፈጸም ጥያቄ ማቅረብ


 ለማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለወረዳው የተለቀቀ ገንዘብ ሰነድ እንዲወራረድ ያለመደረጉ፤
 በኮርፖሬሽኑ ወጭ ለአካባቢ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ተቋማት ርክክብ

ያለመደረጉ

ሐ. ፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ

 በየደረጃው የሚያጋጥሙ ችግሮችን በየጊዜው እየተወያዩ መፍትሄ መስጠት የሚችል የስትሪንግ

ኮሚቴ አደረጃጀት ያለመኖር፣


 በአመርቲ ኔሼ ሀይድሮ- ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብ ምክንያት አርሶ አደሮች ወደ ነሼ አካባቢ

ሄደው አገዳ እንዲያለሙ በወቅቱ ሁኔታው የተመቻቹ ቢሆንም በመግባባት ላይ የተመሰረተ

ባለመሆኑ በልማቱ አቅራቢያ በመስፈር በልማቱ ላይ ተሳታፊ ለመሆን ፈቃደኛ ያለመሆናቸው፤


 የኩይሳ መንደር በፋብሪካው ንብረት ላይ የሚፈጸሙ ስርቆቶች እንዲሁም በተለያዩ አካባቢ

ወንጀል የሚፈጽሙ አካላት መሸሸጊያ መሆን፣ በአጠቃላይ ለልማቱም ሆነ ለማህበረሰቡ የጸጥታ

ስጋት መሆን፤ ህብረተሰቡም እየኖረ ያለው በህጋዊ መንገድ የያዘው ይዞታ ላይ ስላልሆነ ቋሚ

ንብረት ማፍራትም ሆነ እንደ መብራት ያሉ የመሰረተ ልማቶችን ተጠቃሚ መሆን ያለመቻል፤


 ለፋብሪካው የይዞታ ማረጋገጫ ቀደም ብሎ የተሰጠ ቢሆንም በካርታው መሰረት ይዞታውን
የማካለል ስራ ያልተሰራ መሆኑ፤
 በፋብሪካው ኮማንድ ክልል ውስጥ የሚታየው የጸጥታና የህገወጥነት ችግር በስራ ላይ ተጽእኖ
መፍጠሩ፤
 በልማቱ ተፋሰስ አካባቢ የደን ጭፍጨፋ በመበራከቱ በልማቱ ዘላቂነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ
መፍጠሩ፤
 ለካሳ ክፍያ እና ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለዞኑ የተለቀቀ ገንዘብ ሰነድ እንዲወራረድ

ያለመደረጉ፤
 በኮርፖሬሽኑ ወጭ ለአካባቢ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት

ርክክብ ያለመደረጉ

3
መ. አርጆ ዴዴሳ ፋብሪካ

 ፋብሪካው በሚያለማው ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ማግኘት አለመቻል


 በፋብሪካው ኮማንድ ክልል ውስጥ የሚታየውን የጸጥታና የህገወጥነት ችግር በስራ ላይ ተጽእኖ

መፍጠሩ፤
 ለፋብሪካው የመጀመሪያ ምእራፍ ለሚያስፈልገው የሸንኮራ አገዳ ልማት የሚሆን መሬት በጅማ

አርጆ ወረዳ በተቋቋመው ኮሚቴ 5,273 ሄ/ር መሬት በመለየት 3,946.79 ሄ/ር መሬት

በሰነድ ተደግፎ ለፋብሪካው የተሰጠ ቢሆንም በዳቦ ሀና ወረዳ የቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ

1326.3 ሄ/ር መሬት ተለይቶ ቀሪ ቦታዎችን የመለየት ስራ ግን የወረዳ አስተዳደር አካላት

በወቅታዊ ስራዎች መደራረብና አልፎ አልፎ በሚከሰት የጸጥታ ችግር ምክንያት የተጓተተ

መሆኑ፤
 በልማቱ ምክንያት ለሚፈናቀሉ አርሶ አደሮች ተተኪ መሬት አለማግኘት
 የክልል መንደር ማሰባሰብ ፕሮግራም ከፋብሪካው ዙሪያ የሚነሱ አርሶ አደሮችን አለማቀፍ
 ለካሳ ክፍያ እና ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለዞኖች የተለቀቀ ገንዘብ ሰነድ እንዲወራረድ

ያለመደረጉ፤
 በኮርፖሬሽኑ ወጭ ለአካባቢ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት

ርክክብ ያለመደረጉ

ሠ. ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ

 በፋብሪካው የሚያጋጥሙ ችግሮችን በየጊዜው እየተወያዩ መፍትሄ መስጠት የሚያስችል

የስትሪንግ ኮሚቴ አደረጃጀት በየደረጃው አለመኖር፤


 ፋብሪካው በሚያለማው ይዞታ ላይ የይዞታ ማረጋገጫ ማግኘት አለመቻል
 በአስቦዳ እና ቦይና 1‚119 ሄ/ር መሬት ላይ በአውትግሮወር ልማት ውስጥ እንዲገቡ የተደረጉ

አርብቶ አደሮች በወቅቱ በነበረው አገራዊ ድርቅ ምክንያት ውጤታማ ባለመሆናቸው

ኮርፖሬሽኑ ለመስኖ መሠረተ ልማት ማሻሻያ እንዲሁም ማህበራቱ በብድር የወሰዱትን ዕዳ

ሳይመለሱ ከልማቱ የወጡ በመሆኑ በድምሩ ኮርፖሬሽኑ ያወጣው ብር 302,529,815.46

ወጪ ተመላሽ ሊደረግ ያለመቻሉ፤


 ከፋብሪካው ምስረታ በፊት ከነበረው የጥጥ ልማት ጀምሮ ሲንከባለል የቆየው ምርታማ ያልሆነ

ከ 1500 በላይ የሚሆኑ ሠራተኞች ለዓመታት ደመወዝ ሲከፍል መቆየቱ እና አሁንም መፍትሄ

ያለማግኘት፤

4
 የፀጥታና የህገወጥነት ችግር መበራከት ለምሳሌ ያህል የመስኖ ሀይድሮ ፍሉም፣ ጅኦሜምብሬን፣

የመስኖ ቼክ ጌቶችና ሌሎች ንብረቶች በግለሰቦች መሰረቅ፣ ሸንኮራ አገዳ በእንስሳት ማስበላት፣

ማሽነሪዎች ስራ ማስቆም፣የመስኖ ካናል መዝጋት፣ ፋብሪካው ለሰራተኞቹ ያሰረውን ቤት

ሰብሮ በህገ ወጥነት መጠቀም፤ የፋብሪካው ሰራተኞችን ከቢሮ ማስወጣት፤የፋብሪካው ሰራተኛ

መመገቢያ ቤቶች/ካንቲን ማዘጋት፤…ወዘተ ችግሮች ልማቱን እያስተጓጎለው መሆኑ፤


 በውሃ መስኖ ኢነርጂ ሚ/ር በ 1.1 ቢሊዮን ብር በ 14 መንደሮች የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት

አርብቶ አደሮችን በተሟላ መልኩ ማስፈር ባለመቻሉ ተቋማቱ ከአግልግሎት ውጪ እየሆኑ

ከመሆኑም በላይ በአርብቶ አደሮች በልማቱ ክልል ውስጥ የሚኖሩበት ሁኔታ በመኖሩ

የእንስሳቶች የእለት ከእለት እንቅስቀሴ በልማቱ ላይ ጉዳት መድረሱ፤


 መንግሰት የአካቢብውን ማህበረሰብ የልማት ተሳትፎና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ

የተንዳሆ ሰኳር ፋብሪካ ካለማው የሸንኮራ አገዳ ማሳ አምስት መቶ አርባ ስምንት ሄክታር

ለተደራጁ አስር የሸንኮራ አገዳ አብቃይ ህብረት ስራ ማህበራት እንዲሰጥ ተወስኖ 10 ሸንኮራ

አገዳ አብቃይ ህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅቶ ወደ ስራ የገቡ ቢሆንም የተደራጁ አርብቶ

አደሮች በተለያየ ምክንያቶች ምርታማ ሳይሆኑ ቀርተዉ ከምርት የወጡ ሲሆን ማህበራቱ

ለማምረቻ ከፋብሪካ የወሰዱትን ብድር ማስመለስ አለመቻሉ፤

ረ. ከሰም ስኳር ፋብሪካ

 በፋብሪካው የሚያጋጥሙ ችግሮችን በየጊዜው እየተወያዩ መፍትሄ መስጠት የሚያስችል

የስትሪንግ ኮሚቴ አደረጃጀት በየደረጃው አለመኖር


 ፋብሪካው እያለማው ባለውና ለልማት በተወሰነው መሬት መጠን የይዞታ ማረጋገጫ ማግኘት

አለመቻል፤
 ፋብሪካው በሙሉ አቅም ወደ ሥራ ለመግባት ከሚያስፈልገው 13 ሺህ ሄክታር ውስጥ በአሁን

ሰዓት ከመሬት እጥረት ጋር በተያያዘ እያለማ ያለው 2,784.28 ሺ ሄ/ር ብቻ በመሆኑ

ፋብሪካው ከአቅም በታች እንዲሰራ መገደዱ፤ የለማውን የሸንኮራ አገዳም ቢሆን ለአከባቢው

ሕብረተሰብ መከፋፈል አለበት የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ በየደረጃው ከሚገኙ የክልሉ አመራሮች

እየቀረበ መሆኑ፤

5
 በፋብሪካው የሸንኮራ አገዳ ልማት ላይ እየደረሰ የሚገኘውን የእንስሳት ጥቃት የሚጠበቀውን

የአገዳ ምርታማነት ማግኘት እንዳይቻል ማድረጉ እንዲሁም የሰፈሩበትን ቦታ ማልማት

አለመቻሉ፤
 የጸጥታ መደፍረስና የህገወጥ ድርጊቶች መበራከት (ፋብሪካው ባዘጋጀው መሬቶች ላይ ህገወጥ

እርሻ መፈጸም፤ ህገወጥ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ ህገወጥ እርሻ አልሚዎች ካናሎችን

በመስበርና በመዝጋት የአገዳ ልማቱም ሆነ ፋብሪካው አስተማማኝ የሆነ የውሃ አቅርቦት

እንዳይኖረው ማድረግ፤ የመስኖ ሀይድሮፍሉም፣ ጂኦ-ሜምብሬን፣ የመስኖ ቼክ ጌቶችና ሌሎች

ንብረቶች በግለሰቦች መሰረቅ፤ ማሽነሪዎች ስራ ማስቆም፤ ወዘተ) ህገወጥ ተግባራት የልማት

ስራውን ማደናቀፍ፣
 በአውትግሮወር ማህበራት የተደራጁ አርብቶ አደሮች በማሳቸው በመገኘት በውሉ ስምምነቱ

መሰረት የአገዳ እንክብካቤ ሥራ እየሰሩ አለመሆኑ፤

ሰ. ጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

 የስትሪንግ ኮሚቴ የተጠናከረ ያለመሆን፤


 ለሰፈሩ አርሶ አደሮች የእርሻና የግጦሽ ቦታ ተሟልቶ ባለመሠጠቱ አርሶ አደሩ ለከፍተኛ ወደ

ልማቱ ኮማንድ ውስጥ በመመለስ የልማቱን ስራ ላይ ተጽእኖ መፍጠር፤ አርሶ አደሩ ወደ

ፕሮጀክቱ ከብት በመልቀቅ ማስቸገር፤


 የፀጥታ እና ህገ-ወጥ የደን ጭፍጨፋ መበራከት፤
 በአማራ ክልል ጃዊ ወረዳ አሻኳሪ ጐጥ ያሉ 38 አ/አደሮች ባለመነሣታቸው የፕሮጀክቱን ሥራ

ማስቆም፤ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ዳንጉር ወረዳ ልጋስ ጐጥ ያሉ ከ 144 አርሶ አደሮች

አለመነሣትና ለሥራ እንቅፋት መሆን


 ፕሮጀክቱ የይዞታ ማረጋገጫ የሌለው መሆኑ፤
 ለካሳ ክፍያ እና ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለክልልሎች የተለቀቀ ገንዘብ ሰነድ እንዲወራረድ

ያለመደረጉ፤
 በኮርፖሬሽኑ ወጭ ለአካባቢ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት

ርክክብ ያለመደረጉ
ሸ. ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት

 የስትሪንግ ኮሚቴ የተጠናከረ ያለመሆን፤


 የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ያልተሰጠው መሆኑ፤

6
 ለአርብቶ አደሮች የበቆሎ አርሻ መሬት ዝግጅት የአርብቶአደሩን የልማት ተሳታፊነትና

ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲባል የመሬት ዝግጅት ስራዉ በኮርፖሬሽኑ በኩል እየተከናወነ

ቢቆይም ክልሉ ተረክቦ ማስቀጠል ባለመቻሉ የአርብቶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃማ ማድረግ

ያልተቻለ መሆኑ፤
 በፋብሪካ ቁጥር 2 በሃይሉሃ ሁለት አካባቢ የማህበራዊ ተቋማት ግንባታ የሚሆን ገንዘብ ቀደም

ብሎ ለክልሉ የተለቀቀ ቢሆንም የግንባታ ስራው በወቅቱ ሳይጀመር ከመቅረቱም በተጨማሪ

ከተጀመረ በኋላም ግንባታው የተጓተተ መሆኑ፤


 ለካሳ እና ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለክልሉ የተለቀቀ ገንዘብ ሰነድ እንዲወራረድ ያለመደረጉ፤
 በኮርፖሬሽኑ ወጭ ለአካባቢ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት

ርክክብ ያለመደረጉ፤
ቀ. ወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት

 የስትሪንግ ኮሚቴ የተጠናከረ ያለመሆን


 የፕሮጀክቱ የቦታ ማረጋገጫ ደብተር ስለሌለው ከሶስተኛ ወገን ጋር ለሚያደርጋቸው

ማናቸውም ግንኙነቶች ችግር መሆን፤


 በመልሶ ማቋቋም ከኮማንዱ ተነስተው የነበሩ አርሶ አደሮች ተመልሰው በኮማንዱ ውስጥ

እያረሱ በመሆኑ የልማቱ እንቅስቃሴ ላይ ተጽእኖ መፍጠሩ፤


 ለካሳ ክፍያ እና ማህበራዊ ተቋማት ግንባታ ለክልሉ የተለቀቀ ገንዘብ ሰነድ እንዲወራረድ

ባለመደረጉ፤

 በኮርፖሬሽኑ ወጭ ለአካባቢ ለህብረተሰብ አገልግሎት እንዲውሉ የተገነቡ ማህበራዊ ተቋማት

ርክክብ ያለመደረጉ

4 የሚጠበቅ ውጤት
1. በፋብሪካዎቹና ፕሮጀክቶቹ ያጋጠሙዋቸውን ችግሮች በመገንዘብ እያንዳንዱ ባለድርሻ አካል ለችግሮች የበኩላቸውን
መፍትሄ እንዲሰጡ ይደረጋል፤
2. ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል መግባባት ላይ በመድረስ የጋራ የመፍትሄ መርሀግብረ እንዲቀረጽ ይደረጋል፤
3. በሚቀረፁ የመፍትሄ ትግበራ መርሀግብር መሠረት በቀጣይ ባለድርሻ አካላትና ፋብሪካዎቹ፣ ፕሮጀክቱ፣
ኮርፖሬሽኑ የበለጠ ተቀራርበው እንዲሰሩ ማስቻል፣

5 ተሳታፊዎችና የውይይት አካሄድ


ሀ. ተሳታፊዎች
7
1. ከመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ (የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር፣ የዋና
ዳይሬክተር አማካሪ፣ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር፣ የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር
አማካሪ፣ የግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ሁለት ባለሞያዎች)
2. ከስኳር ኮርፖሬሽን (የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ ም/ዋና ስራ አስፈጻሚ፤ ከማኅበረሰብ ተኮር ጋር
ግንኙነት ያላቸው ሦስት ኃላፊዎችና ባለሞያዎች)፣ ከፕሮጀክቱ/ፋብሪካው ቢያንስ ጉዳዩ
የሚመለከታቸው አምስት ተሳታፊዎች፣
3. ከአካባቢ መስተዳድር አካላት (ተቋማቱ የሚገኙበት ዞኖች አስተዳዳሪዎች፣ ተቋማቱ የሚገኙበት ዞኖች
የሚመለከታቸው ጽ/ቤቶች፣ ተቋማቱ የሚገኙበት ወረዳዎች አስተዳዳሪዎች፣ ተቋማቱ የሚገኙበት
የሚመለከታቸው ወረዳዎች ጽ/ቤቶች፣)

ለ. የውይይቱ አካሄድና ፕሮግራም

ጊዜን እንዲሁም ሌሎች ሀብትን በአግባቡ መጠቀም እንዲያስችል ፋብሪካዎችንና ፕሮጀክቶችን እንደሚገኙበት ቦታ
በማቀናጀት ውይይቱ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት፡-

1. የወንጂ ስኳር ፋብሪካንና የመተሀራ ስኳር ፋብሪካን በተመለከተ በአዳማ ከተማ ሁሉንም ባለድርሻ
አካላት በማገናኘት በህዳር የመጨረሻው ሳምንት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
2. የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካንና ከሰም ስኳር ፋብሪካን ሰመራ ከተማ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ
ውይይት በጥር ወር ሦስተኛው ሳምንት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
3. የኦሞ ኩራዝ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ የሁሉም ፕሮጀክቶች ባለድርሻ አካላትን ያካተተ ውይይት
በመጋቢትር ወር ሦስተኛ ሳምንት በጂንካ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

4. የበለስ ስኳር ፋብሪካን በተመለከተ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያካተተ የምክክር መድረክ በባህርዳር ከተማ
ፕሮጀክት በሚያዝያ ወር የሚካሄድ ይሆናል፡፡

6 ሎጅስቲክና የጉዞ ወጪ
ለውይይቱ የሚያስፈልገው የስብሰባ አዳራሽ፣ በስብሰባ ጊዜ የሚቀርብ ውኃ፣ በዕረፍት ሠዓት የሚስፈልግ ሻይ፣ ቡና
እና ኩኪስ እንዲሁም ምሳና ወጪ ለግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ ከተያዘው በጀት ላይ በኤጀንሲው የሚሸፈን
ይሆናል፡፡ በስብሰባው ወቅት ለተሳታፊዎች የሚሰጠው ማስታወሻ ደብተር እና እስክሪብቶ በኤጀንሲው ይሸፈናል፡፡
በተጨማሪም ተሳታፊዎች በሁለተኛው ቀን መርሀግብር እንዲያዘጋጁ የሪፍሬሽመንት እና ምሳ ወጪ በኤጀንሲው
ይሸፈናል፡፡ ለባለድርሻ አካላት የሚያስፈልገውን ትራንስፖርት፣ የውሎ አበል ልዩ ልዩ ወጪዎች በስኳር ኮርፖሬሽን
እንዲሸፈን ታሳቢ ተደርጓል፡፡ የኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሞያዎች የሚያስፈልጋቸው የትራንስፖርትና አበል
ወጪ በኤጀንሲው ይሸፈናል፡፡

8
7 አባሪ 1 የባለድርሻ አካላት ምክክር መድረክ ዝግጅት አፈፃፀም መርሀ-ግብር
ተ.ቁ. የሚከናወንበት ሰዓት ክንውን ፈጻሚ

1 2፡30-3፡00 የተሳታፊዎች ምዝገባ ይካሄዳል ግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ ዳይሬክቶሬት

2 3፡00-3፡05 የመርሀ-ግብር ትውውቅ ይደረጋል አማካሪ

4 3፡05-3፡30 የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር መክፈቻ ንግግር ያድርጋሉ ዋና ዳይሬክተር/የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና
ዳይሬክተር

5 3፡30-4፡30 ኮርፖሬሽኑ ፋብሪካዎቹ ያጋጠማቸውን ችግሮች ያብራራል ስኳር ኮርፖሬሽን

6 4፡30-5፡00 የሻይ ሰዓት ኤጀንሲ

7 5፡00-6፡30 በቀረቡት ችግሮች ላይ ውይይት ይካሄዳል በአመራሩና በተሳታፊ

8 6፡30-8፡00 የምሳ ሰዓት ኤጀንሲ

9 8፡00-9፡30 ውይይቱ ይቀጥላል ተሳታፊዎች

10 9፡30-10፡00 የሻይ ዕረፍት ግብርናና አግሮ ኢንዱስትሪ ዳይሬክቶሬት

11 10፡-11፡00 ቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራትን በማመላከት ስብሰባው ማጠቃለያ ይሰጣል ዋና ዳይሬክተር/የኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ዋና
ዳይሬክተር

You might also like