You are on page 1of 2

ክ/ከተማ------ቦሌ ከ/ክተማ

ወረዳ----------17
ቀበሌ-----------24

የቀረበው ችግር----አካባቢውን የበከለ የሴፕቲክ ታንክ ፍሳሽ በተመለከተ ከወረዳ 05 ጽ/ቤት የቀረበ ደብዳቤ
መግቢያ ፦ከላይ የተገለጸውን ችግር ለመመልከት እና የመፍትሄ ሀሳብ ለማቅረብ ቦታውንና አካባቢውን ተመልክተናል።
ቅሬታ ያቀረቡትን የግል ቤት ባለይዞታ ግልስብም በእካል ማግኝት ባንችልም በስልክ ተገቢውን ምረጃ ለማግኘት
ችለናል።

ነባራዊ ሁኔታ፦ ከላይ የተገለጸው የቀድሞ ወረዳ 17 ቀብሌ 24 በተለይ በተለምዶ (ቆሻሻ ገንዳ) የሚባልው አካባቢ
በተለየ ሁኔታ ረግረጋማ የሆነ እና ውሃ አዘል (Ground water) ያለበት መሬት ሲሆን ይህም በሴፕቲክ ታንከሮች ዲዛይን
እና አገልግሎት ላይ ያልተካተተ ተጨማሪ ከፍተኛ የፍሳሽ ጫና ፈጥሯል፡፡ከዚህ በተጨማሪ ያካባቢው መስተዳድር
የውስጥ ለውስጥ መንገድ በሚያሰራብት ወቅት የተሰራው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ባግባቡ ዲዛይን ባለመደረጉ
የመንገድ ስራውም በሚስራበት ወቅት ተገቢው ጥንቃቄ ባለመደርጉ ምክንያት የመንገዱን ፍሳሽ እንዲቀበል
በማንሆሎች አፍ ላይ የተሰራው ፍሳሽ መቀበያ (Diversion Opening) በተቃራኒው ከማንሆሎች ፍሳሽ ውሃ ወደ
መንግዱ በምፍሰስ መንገዱን በማጥለቅለቅ ላይ ይግኛል።ይሄም በዋናነት ለፍሳሽ ማስወገጃነት የተሰራው የፍሳሽ
መስመር በደለል በመሞላቱ ምክንያት ነው፡፡

ሌሎች ይታዩ ችግሮች፦ ከአካቢው ነዋሪዎች እነደተረዳነው የደርቅ ቆሻሻ ማከማቻው የተስራው ለአካባቢው ላሉ
የኮርፖሬሽናቸን ቤቶቸ በተሰራው የሴፐቲክ ታነክ ስላብ ላይ ተጨማሪ የኮንክሪት ሙሌት በማድረግ ሲሆን የሴፐቲክ
ታነኩ ዲዛይን እና አገልግሎት ተጨማሪ ሸክምና ጫናዎችን እነዲሸክም ታስቦ ስላልሆነ በተጨማሪም ግዙፍ ይቆሻሻ
መጫኛ ምኪኖች በላዩ ላይ ስለሚንቀሳቀሱበት የከፋ ጉዳት ሊከስት ይችላል የሚል ስጋት እንዳልን ለመግልጽ እንወዳል።

የቀረቡ ምፍትሄዎች፥- መፍትሄዎቹን በሁለት ከፍለን ማለትም የአጭር ግዜና እና ዘላቂ መፍትሄ ብለን ከፋፍለን
እናያለን፡፡
1. የአጭር ግዜ (ጊዜያዊ መፍትሄ)፡- ከአሰራር እና አጠቃቀም ጉድለት በደለል የተሞላውን የፍሳሽ መስመር እንደ
አዲስ መስራት፡፡ ለዚህም ስራ ወጪ የሚጠይቅ ስለሚሆን የፍሳሽ መስመሩ ዲዛይንና ስራ ዝርዝር በስራ
ክፍላች በፍጥነት መዘጋጀት ይኖርበታል ፡፡
በዚህ ስራ ላይ ወጪ ከመጋራትም ሆነ የአካባቢውን መሀበረሰብ በስራው ላይ ተገቢ ግንዛቤ እና ትብብር
እንዲያደርግ የወረዳ 5 አስተዳደር የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
2. ዘላቂ መፍትሄ፡- ከጊዜያዊው መፍትሄ ጎን ለጎን ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር
የአካባቢውን ቤቶች የፍሳሽ መስመር ለአካባቢው በቅርበት ከሚገኝ የከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር
ማገናኘት፡፡ የዚህንም ጉዳይ ተፈጻሚነት ባለው አሰራር መሰረት የቅ/ጽቤታችን በሃላፊነት ክትትል ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
ሳይቱን በምናይነት ወቅት የተመለከትነውን ሌላ አሰሳሳቢ ችግር በአካባቢው የተገነባው የደረቅ ቆሻሻ ማከማቻ ጉዳይ
ነው፡፡ ከነዋሪዎች ባገኘነው መረጃ መሰረት ይሄው የቆሻሻ ማከማቻ ግንባታ ያረፈው ሙሉ በሙሉ በአካባቢው ላሉ
የኮርፖሬሽናቸን ቤቶች በተሰራው የሴፕቲክ ታንከር ላይ ሲሆን በዚሁ ቆሻሻ ማካማቻ ላይ ከፍተኛ ክብደት ያላቸው
ተሸከርካሪዎች ቆሻሻ ለመጫን የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ይህም ሴፕቲክ ታንከሩ ላይ እና በዚያው በሚንቀሳቀሱ
ተሸከርካሪዎች ላይ አደጋ ሊስከትል እና የሰው ህይወት እና ንብረት ላይም የካፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል
ተገንዝበናል፡፡
በዚህም መሰረት በሴፕቲክ ታንኩ ላይ መሰል ከፍተኛ እንቅስቃሴ የሚፈልግ ግንባታ በምን አግባብ እንደተሰራ ደህንነትን
ከማስጠበቅ አንጻር ምን ስራ እንደተሰራ ዝርዝር ማብራሪያ ከወረዳ 05 አስተዳደርን እንዲቀርብልን ያስፈልጋል፡፡

ማጠቃለያ፡-
 ከጽቤታችን የሚጠበቅ
 እንደጊዚያዊ መፍትሄ በደለል የተሞላውን የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር እንደ አዲስ ለመስራት
የሚያስፈልገውን ዲዛይንን የስራ ዝርዝር በተቻለ ፍጥነት ማዘጋጀት ማዘጋጀት፡፡
 ለስራው የሚያስፈልገውን በጀት እና የስራውን ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት ወደስራው መግባት
 በወጪ መጋራት ላይ የወረዳ 05 አስተዳደር እና የአካባቢው ነዋሪ በተለይ የችግሩ ተጋላጭ የሆኑ የግል
ቤት ባለቤቶች ተሳተፋ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
 በዘላቂነት የአካባቢው አጠቃላይ የፍሳሽ ችግር ሊፈታ የሚችለው የየቤቶቹን ፍሳሽ መስመር
ከከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር እንዲገናን ክፍተኛ ትኩረት በመስጠት መስራት፡፡
 ከወረዳ 05 አስተዳደር የሚጠበቀው
 የቅ/ ጽቤታችንን ጥረት በበጎ በመረዳት በራስ አቅምም ሆነ ነዋሪው ህብረተሰብን በማስተባበር
የመፍትሄው አካል መሆን፡፡
 በተለይ ከወጪ መጋራት አንጻር ስራውን ለመስራት የሚያስፈልገውን ወጪ ህብረተሰቡን
በማስተባበር ጭምር ድጋፍ ማድረግ፡፡
 ሌሎች የተጠየቁ ማለትም ቆሻሻ ማከማቻውን በተመለከተ ያሉ ነገሮችን ሃላፊነት ወስዶ ምላሽ
መስጠት፡፡
 የግል ቤት ባለቤቶችን በተመለከተ፡-
 የችግሩ ዋና ተጎጂዎች ከመሆናቸው አንጻር በተለይ በስራው ላይ በቂ ግንዛቤ ሊይዙ ይገባል፡፡
 ለስራው የሚያስፈልገው የበጀት ዝርዝር በጽ/ቤታችን ተዘጋጅቶ ሲቀርብ በሃላፊነት እና በባለቤትነት
ስሜት በተለይ በወጪ መጋራቱ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ፡፡
 የተከራዮቻችን ድርሻ ፡-
 አሁን በቅ/ጽቤታችን የታቀደው በዋናነት ደንበኞቻችንን በተገቢው ለማገልገል እና አካባቢያቸውንም
የበለጠ ለመኖሪያነት ምቹ ለማድረግ ከመሆኑ እንጻር ከማንም በላይ በሃላፊነት በመነሳት ሌሎች
የአካባቢዎቻቸው መሰል ተከራየች እንደሚያደርጉት ለስራው የሚያስፈልገውን በጀት በማዋጣት
መደገፍ ይኖርባቸውል፡፡

You might also like