You are on page 1of 1

ቁጥር----------------------------

ቀን--------------------------

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ልማት መምሪያ

ሀዋሳ

ጉዳዩ ፡-በ 2016 ዓ.ም በታቦር ክ/ከተማ ሂጣታ ቀበሌ የሻለቃ መንደር የልማትና የመልካም አስተዳደርና ጥያቄን
ይመለከታል፡፡

በመግቢያዉ ላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረዉ መንደሩ በሀዋሳ ከተማ ያለዉ ከተማዉን ከፍሉን የጎርፍ መዉረጃ
ቦይዎችን የሚያስተናግድ በመሆኑ፤የሪፌራል ሆስፒታል ተረፈ ምርት/westage / የሚለቀቅበት፤ከአከባቢ ጥበቃ
ስራዎችም አንጻር የሀዋሳ ከተማ ዉቤት የሆነዉ ሀዋሳ ኃይቅ የሚገኝበት፤ከጸጥታ ስጋት አንጻር ደግሞ
የሪፌራል ሴርኪል አከባቢ በተለምዶ የጸጥታ ስጋት መንደር ተብሎ የተለየ መንደር እንደመሆኑ መጠን
የመንደሩ ነዋሪዎች የአከባቢዉን ልማት፤መልካም አስተዳደርና ለሠላም አስጊ የሚሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ
የማህበረሰብ ንቅናቄን በመፍጠር የሮንድ ቅኝት፤የአከባቢ ዉቤትና ጽዳት በመጠበቅ የከተማዉን 18 ቱን
አጀንዳዎች ለማሳካት የበኩሉን ጥረት በማድረግ ሂደት ላይ የቆዬ ቢሆንም ከመንግስት ምንፈልጋቸዉ
ድጋፎችንና በመንደሩ ነዋሪዎች የሚሸፈኑትን ጉዳዮች በመለየት ከመንግስት አካላት ድጋፍ የሚያሻቸዉን
ጉዳዮችን በተለይ በፕርካስት ያልተሸፈኑ ዲቾችን ከ 200 ሜትር በታች የሚገመት አስፋልት መንገድ ከሰርክል
አድናቆሬ መናፈሻ ፤የልማት ተነሺዎች የቤት ካሳና ተለዋጭ ቦታ ባለማግኘታቸዉ የተዘጉ መንገዶች እና
በተለይ አድናቆሬ መናፈሻ አከባቢ የከተማዉ ፕላን አጥንቶ ለባለይዞታዎች ሳይት ፕላን ባለመስጠቱና ዉስጥ
ለዉስጥ ለተወሰኑ ሰዎች ተሰጥቶ ለሌላዉ ተገቢነትና ፍተኃዊነት የጎደለዉ ምላሽ እየተሰጠ የመልካም
አስዳደር ችግር ከመሆኑም በላይ መንግስት የሚያጣዉንም ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ታሳቢ ተደርጎ አጽንዖት
እንድሰጥና የመንድ ከፈታ ፤መንገድ ዳር መብራቶች እና የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ እንድጠናና ተገቢዉን
መንግስታዊ ትኩረት ተሰጥቶበት እንድታይልንና ከህ/ሰቡ የሚጠበቀዉን ማናቸዉንም ተዋጽዖ ለማድረግ
ዝግጁ መሆናችንን ኢያረጋገጥን የመንደሩን የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ከዚህ ሸኚ ጋር አያይዘን
ያቀረብነዉን መምሪያዉ በጥልቀት ተመልክቶ መንደራችንንም ወርዶ በማት ለሚሰጠን አፋጣኝ ምላሽ
ምስጋናችን የላቄ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ግልባጭ

 ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት


 ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ብ/ፓርቲ ጽ/ቤት
 ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ጸጥታ መምሪያ
 ለታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር ጸ/ቤት
 ለታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር ብ/ፓርቲ ጸ/ቤት
 ለታቦር ክ/ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ጽ/ቤት

ሀዋሳ

You might also like