You are on page 1of 5

/ //

የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ስራ እድል ፈጠራ ኢ ል መምሪያ ከባለድርሻ ሴክተር መስሪያቤት ጋር በጋራ የሚሰሩ
ስራዎችን ለማከናወን የተደረሰ ስምምነት ሰነድ

የካቲት 2016 ዓ.ም

አሶሳ፣

መግቢያ
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ለኢንዱስትሪ ልማት መሰረት የሚጥሉ በመሆናቸው እንደ ሀገር
ብሎም በክልልና በከተማችን ደረጃ የሚታየውን የስራ-አጥነት ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ፣ ምሩቃንን ከስራ
ጠባቂነት ይልቅ የስራ ፈጣሪነት አድማስ በማስፋት ልማታዊ አስተሳሰባቸውን በማሳደግ፤ ልማትን ለማፋጠንና
0
ድህነትን ለመቀነስ፤ ኢንተርፕራያዞችን በመመስረት የወጣቶችን የሥራ ዕድል ማስፋት ለዜጎች የስራ ዕድል
በመፍጠር እንዲሁም ኢንተርፕራይዞች በልማታዊ መንገድ የተዘረጋውን የአሰራር ሥራዓቱን በመከተል
ለአገራዊ ኢኮኖሚው ራዕይ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት አበረታች ውጤቶች እያስመዘገቡ መሆኑ
ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ይህ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ስራእድል ፈጠራ /ኢ/ል/መምሪያ የ 2016 በጀት ዓመት እቅድ
በቢኤስሲ እቅድ ፎርማት መሠረት የትኩረት መስኮች ዋና ዋና ግቦች ብሎም ተግባሮች ድረስ በዝርዝር
በማካተት የመምሪያውን የ 2016 በጀት ዓመት የታቀደ ሲሆን የመምሪያውን እቅድ እስከ ባለሙያዎች ድረስ
በማውረድ የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ስርዓት በዕቅዱ በማካተት በመስራት ላይ የምንገኝ ቢሆንም
ለመምሪያችን ስራ የላቀ ውጤታማነት የሴክተሮች ሚና ስለአለው ከባለድርሻ መስሪያቤቶች ጋር በጋራ
ሰለሚሰሩት ስራዎች በዚህ ሰነድ የጋራ ስምምነት ተደርሷል፡፡

ዓላማ
የስራ እድል ፈጠራ ስራን ዘላቂና ውጤታማ ለማድረግ የባለድርሻ መስሪያቤቶች ጋር ተገናጅቶ መስራት
ስለሚያስፈልግ መቀናጀት የሚጠበቅባቸውን መስሪያቤቶች እና የሚያቀናጃቸው ዝርዝር ተግባሮች ተለይተው
በጋራ በማከናወን ስኬታማ ማድረግ ማስቻል ነው፡፡

ክፍል-አንድ
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ የስራ እድል ፈጠራ ስራ መሪ ቢሆንም
ለውጤታማነቱ ሌሎች ባለድረሻ መንግስታዊ መስሪቤቶች በመኖራተው የጋራ እቅድ በማውጣት በቅንጅት መስራት
የዘርፉን ስራ የበለጠ ውጤታማ ስለሚያደርገው ቀጥሎ የተዘረዘሩት መስሪያቤቶች ጋር የጋራ ስምምነት ተዘጋጅቷል

1. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ እና የአሶሳ ከተማ አስ/ር ግብርና ልማት መምሪያ
1.1. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ
1
 በከተማ ግብርና ዘርፍ መደራጀት የሚፈልጉ ስራ ፈላጊዎችን ልየታ እና ምዝገባ ማከናወን
 ለተለየትና ለተመዘገቡት ስራ ፈላጊዎች በከተማ ግብርና በኩል የሚገኙ ጸጋዎች ግንዛቤ መፍጠር

 በከተማ ግብርና መደራጀት ለሚፈልጉ በማደራጀት ለዜጎች የስራ እድል መፍጠር

 ለዘርፉ ዚንተርፕራይዞች ሰርቲፊኬት እድሳት ማድረግ

 አንቀሳቃሾች መካከል እርስ በእርስ መተማመንና መግባባት እንዲኖር ማድረግ

 ለኢንተርፕራዞች መንግስታዊ ድጋፍ ማድረግ

1.2. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ግብርና ልማት መምሪያ

 የዘርና ዝርያ መረጣ ሙያዊ እገዛ ማከናወን

 የእንስሳት እርባታ ወይም ማድለቢያ ቦታ መረጣና ቤት አሰራር ድጋፍ

 የእንሰሳትና እጸዋት ጤና ጥበቃ ድጋፍ

2. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ እና የአሶሳ ከተማ አስ/ር አገ/ጉዳዮች ልማት መምሪያ
2.1. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ

 በኮንስትራክሽን ዘርፍ እና በጽትና ውበት አገልግሎት መደራጀት የሚፈልጉ ስራ ፈላጊዎችን ልየታ እና ምዝገባ
ማከናወን፤
 ለተለየትና ለተመዘገቡት ስራ ፈላጊዎች በኮንስትራክሽን ዘርፍ እና በጽትና ውበት አገልግሎት ለመደራጀት
መሟላት ያለበትን ግንዛቤ መፍጠር፤

 በኮንስትራክሽን እና በጽትና ውበት አገልግሎት መደራጀት ለሚፈልጉ በማደራጀት ለዜጎች የስራ እድል
መፍጠር

 ለዘርፉ ኢንተርፕራይዞች ሰርቲፊኬት እድሳት ማድረግ

 የሲፒኦ እና ዋስትና መስጠት

 የመሸጫና መስሪያ አገልግሎት የሚውል ሸድ በአግባቡ ማስተዳደር፤

 አንቀሳቃሾች መካከል እርስ በእርስ መተማመንና መግባባት እንዲኖር ማድረግ

 ለኢንተርፕራዞች መንግስታዊ ድጋፍ ማድረግ

2.2.የአሶሳ ከተማ አስ/ር አገ/ጉዳዮች ልማት መምሪያ

 በተቋሙ የሚፈጠሩ የስራ እድሎች ለኢንተርፕራዞች ቅድሚያ እንዲሰጡ ማድረግ፣

 በኢንተርፕራይዞች የሚሰሩ ስራዎችን በጋራ መከታተል፣

 ለመሸጫና መስሪያ አገልግሎት የሚውል ሸድ መገንባትና መጠገን፤

2
 ለኢንተርፕራይዞች የተፈጠረ ስራ እድል ወቅቱን የጠበቀ መረጃ መለዋወጥ፤

3. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ እና የአሶሳ ወረዳ ብድርና ቁጠባ ተቋም


3.1. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ

o ለኢንተርፕራይዞችና ለስራ ፈላጊዎች ስለብድር አገልግሎት ግንዛቤ መፍጠር

o መበደር ለሚፈለግ ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግሎት ድግፍ መስጠት

o የተበደሩ ኢንተርፕራይዞች ወቅቱን ጠብቀው እየሰሩ እንዲመልሱ ሁለንተናዊ ድጋፍ ማድረግ፤

o የኢንተርፕራይዞችን የቁጠባ ባህል ማሳደግ የሚችሉ ተግባሮችን ማከናወን

3.2. የአሶሳ ወረዳ ብድርና ቁጠባ ተቋም

o ለኢንተርፕራይዞችና ለስራ ፈላጊዎች ስለብድር አገልግሎት ግንዛቤ መፍጠር

o የብድር አገልግሎት ለማግኘት ድግፍ ደብዳቤ ለተሰጣቸው ኢንተርፕራይዞች የብድር አገልግሎት መስጠት

o የተበደሩ ኢንተርፕራይዞች ወቅቱን ጠብቆ ብድር ማስመለስ

o የኢንተርፕራይዞችን የቁጠባ ባህል ማሳደግ የሚችሉ ተግባሮችን ማከናወን

4. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ እና የአሶሳ ከተማ አስ/ር መሬት ልማት መምሪያ
4.1. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ

 የመስሪያና የመሸጫ አገልግሎት የሚውል መሬት ጥያቄ ማቅረብ

 በመምሪያው ስም ለኢንተርፕራይዞች እንዲሰጡ ከመሬት ልማት የተዘጋጀውን ካርታ መቀበል እና በአግባቡ


ማስተዳደር

 ቀደም ሲል በከተማ መሬት ልማት መምሪያ በኩል ለኢንተርፕራይዞች የተሰጡ ቦታዎችን በአድሱ አሰራር
መስመር ማስያዝ

4.2 .የአሶሳ ከተማ አስ/ር መሬት ልማት መምሪያ

 ለኢንተርፕራይዞች መስሪያና መሸጫ አገልግሎት ሚውል መሬት ማዘጋጀት

 የተዘጋጀውን መሬት በከተማ ካቢኔ በማስወሰን በስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ስም ይዞታ
በመስራት ማስረከብ

 ቀደም ሲል በከተማ መሬት ልማት መምሪያ በኩል ለኢንተርፕራይዞች የተሰጡ ቦታዎችን በአድሱ አሰራር መስመር
ማስያዝ

5. የአሶሳ ከተማ አስ/ር ስ/እ/ፈ/ኢ/ል/መምሪያ እና የአሶሳ ከተማ አስ/ር ሴቶች ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ
በስራ እድል ፈጠራ ስራ ላይ የሴቶችንና ወጣቶችን እንዲሁም ሌሎች የማህበራዊ ችግር ተጠቂዎች የስራ እድልና
ሌሎች ድጋፍ ተጠቃሚነትን በጋራ ማከናወን
3
4

You might also like