You are on page 1of 6

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር


የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት
የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት

ለማዕክል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የቢሮ ህንፃ ለመገ


ለማዕክል የተዘጋ
ሴክተጀር መስሪ
የ ዲ ዛያይቤቶ
ን ችመ ነየቢ
ሻ ሮሃህን
ሳ ፃብ ለመገንባት
(Concept
የተዘጋጀ የ ዲ ዛ ይ ን መ ነdሻe sሃi ሳ
g nብ)( C o n c e p t
design)

ሰኔ 2013 ዓ.ም.

ሰኔ 2013 ዓ.ም.
1. መግቢያ

የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ ፣ የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና
ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ ልዑካን መሰብሰቢያ የ ሆ ነ ች ው አ ዲ ስ አ በ ባ ከተማ ከአራቱ የሀገራችን ማዕዘናት
ለሚመጡና በከተማው ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎቻችንም ሆነ ከውጭ የሚመጡ እንግዶችን በመንግስት፤ በግልና በማህበራት
አስፈላጊውን አገልግሎት እንዲያገኙ እያደረገች ትገኛለች፡፡

እነዚህን መንግሰታዊ አገልግሎት የሚፈልጉ ተገልጋዮችን በአግባቡ ለማስተናገድ፤ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታን ለማስጠበቅ፤ ህዝቡ
የሚፈልጋቸው አገልግሎቶች በቅርብ እንዲያገኝ ለማድረግ የተለያዩ መዋቅሮች ከከተማ እስከ ወረዳ ተዘርግተው አገልግሎት እየሰጡ
ይገኛሉ፡፡

አሁን ባለንበት ዘመን እንዲሁም ዘመኑ ከደረሰበት ዘመናዊ የንግድ፣ የኢንዱስትሪና የቱሪዝም የአገልግሎት አድማስ ስፋት የተነሳ
መንግስት የሚሰጠው አገልግሎት በአይነትም ሆነ በብዛት ቀደም ሲል ከሚሰጠው በእጅጉ የሰፋ በመሆኑ ከዚህ በፊት በመንግስት
ህንፃ ውስጥ ብቻ ይሰጥ የነበረው አገልግሎት በቂ ስላልሆነና ዘመኑ የሚጠይቀውን የተሳለጠ አገልግሎት ለመስጠት የመንግስት
መስሪያ ቤቶች መብዛታቸውና የሚሰጡት አገልግሎትም ዓይነት እየበዛ ስለሆነ አንዳንድ የመንግስት ተቋማት የግለሰብ ህንፃዎችን
ተከራይተው አገልግሎት እየሠጡ ይገኛሉ፡፡

ይሁን እንጂ ህንፃ ተከራይተው የሚገኙ አንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች የመንግስት ህንፃዎችን የሚጠቀሙ ተቋማትን ምቹ
ባለመሆኑ እንዲሁም በተበታተነ መልኩ በመገኘታቸው አገልግሎቶች አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር
እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ህንፃዎች ሲሰሩም አገልግሎት ታሳቢ አድርገው ባለመሰራታቸው ከደንበኞችና ሠራተኞች እርካታ አኳያ፤
የተለያዩ ማዕከላት /ፖርኪንግ፣ የህፃናት ማቆያ፣ ካፌ፤የመጀመሪያ እርዳታ ማዕከል፣ የመኪና እጥበት የመሳሰሉት/ ስላልተሟሉ
ለሥራ ምቹ አይደሉም፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ በየአመቱ ለህንፃ ኪራይ የሚያወጣው ከ 746,000,000.00
(ሰባት መቶ አርባ ስድስት ሚሊዮን ብር) በላይ ወጪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመምጣቱም በላይ የከተማ አስተዳደሩ
ለሌሎች ልማቶች የሚያውለውን ሀብት እየባከነ በመገኘቱ የቢሮ ህንፃዎችን በአንድ አካባቢ መገንባት ያስፈልጋል።

በመሆኑም መንግሰት እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ የማዕከል መስሪያ ቤቶች
የሚያወጡትን የህንፃ ኪራይ ወጪ ለማስቀረት፣ የመንግስት ተቋማትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል ለመስጠት፣ ለተገልጋዩን
ህዝብ እና ለአገልጋዩን የመንግሰት ሰራተኛ ምቹ አካባቢ ለመፍጠር በማሰብ ይህ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎችን
(sectoral Office Buildings) በአንድ አካባቢ ለማስገንባት እየሰራ ይገኛል፡፡

2. የፕሮጀክቱ ዓላማ

በከተማ ደረጃ ለህንፃ ኪራይ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ ለማስቀረት እና የሚሰጡ አገልግሎቶችን ምቹና ቀልጣፋ
ለማድረግ፣ ለሠራተኛው ምቹ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር መንግስታዊ አገልግሎት የሚፈልጉ ተገልጋዩችን በአግባቡ
ለማስተናገድ፤ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታን ለማስጠበቅ፤ ህዝቡ የሚፈልጋቸው አገልግሎቶች በቅርብ እንዲያገኝ ለማድረግ፣
ለተጠቃሚው በአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን ለመስጠትና የተገልጋዮችን ከፍተኛ እንግልት ለመቀነስ ያስችል ዘንድ
የአገልግሎት አሰጣጣቸውን መሰረት በማድረግ ከዚህ በፊት ህንፃ ተከራይተው የሚገኙ አንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች
የመንግስት ህንፃዎችን የሚጠቀሙ ተቋማትን አገልግሎቶችን ለተገልጋዮች በተሳለጠ መልኩ መስጠት ነው፡፡

3. የፕሮጀክቱ አስፈላጊነት

ከተማ አስተዳደሩ በዘላቂነት ከሚቀርፋቸው ተግዳሮቶች መካከል የመንግስት ተቋማት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና ተደራሽ
አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የተቋማት አደረጃጀት እና አገልግሎት መስጫ ህንፃዎች እጥረት መቅረፍ ስለሚያስችል ነው፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለቢሮ አገልግሎት የሚወጣውን ከፍተኛ የኪራይ ወጪ ለመቀነስ፣ በአገልግሎት አሰጣጣቸው
የሚቀራረቡትን ተቋማት በክላስተር በማደራጀት ተደራሽ ለማድረግ ተቋሞቹ የሚሰጡትን አገልግሎት በማቀለጠፍ
ለዜጎች/ለተገልጋዮች/ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ብሎም የከተማችን ልማትና ሁለንተናዊ እድገት የሚያፋጥን እና
ለቢሮ ኪራይ የሚውለው ወጪው ለሌሎች የልማት ስራዎች እንዲውል ስለሚያስችል በከተማችን

የሚነሳውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመፍታት ተገልጋዩ ሳይንገላታ ተቀራራቢና ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጡ ሴክተሮችን
አንድ ህንፃ ላይ እንዲሆኑ በማድረግ የደንበኞችን አገልግሎት ለማሳለጥ፣ በመንግሰት ተቋማት ላይ መኖር የሚገባቸው
ማዕከላት እንዲኖሩ ለማድረግ፣ መ/ቤቶች በአንድ ሕንፃ ስር በክላስትር እንዲገለገሉ ሲደረግ የመንግስት ንብረት በአግባቡ
ከመጠበቁ በተጨማሪ መ/ቤቶች በቀላሉ መረጃ እየተለዋወጡ በፍጥነት እንዲሰሩ ስለሚያደርጋቸው የፕሮጀክቱ
አስፈላጊነት የጎላ ነው፡፡

4. የፕሮጀክቱ የዲዛይን መነሻ ሀሳብ (concept design) ዳሰሳ

ከተማ አስተዳደሩ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት በመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር በኩል የቀረበውን የመነሻ
ሀሳብ በመቀበል የፕሮጀከቱ የዲዛይን መነሻ ሃሳብ (concept Design) የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት
አጥንቶ እንዲያቀርብ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ሜጋ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጥናቱን እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

የፕሮጀክቱ የዲዛይን መነሻ ሀሳብ (concept design) ይዘት


 የፕሮጀክቱ ግንባታ ቦታ
o ከመገናኛ ወደ ቦሌ ቀለበት መንገድ ላይ ከአምቼ ፊት ለፊት
 ፕሮጀክቱ የሚገነባበት ቦታ ስፋት
o 6.1 ሄክታር
 የፕሮጀክቱ በጀት
o 19.87 ቢሊየን ብር
 የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜ
o 5 ዓመት
 በህንጣዎቹ እና የስራ ዘዴው በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ግንኙነት ዘዴ የታገዘ
 ሁሉም ህንጻዎች እርስ በእርስ በድልድይ የተገናኙ በመሆኑ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በቀላሉ እንዲደረስ
ታስቦ የተሰራ
 አካል ጉዳተኞችን እና እናቶችን ታሳቢ ያደረገ
 ግንባታው ሲጠናቀቅ
o 34 አገልግሎት ሰጪ የመንግስት ተቋማት(ሴክተር መ/ቤቶች ) በአንድ ቦታ ያሰባስባል
o 7516 የመንግስት ሰራኞችን ይይዛል
o ከ4850 በላይ መኪናዎች ምቹ የማቆሚያ ቦታ ይኖረዋል
o የታክሲ/ባስ ማውረጃ እና መጫኛ ስፍራ ይኖረዋል
o ከ3000 ሰዎች በላይ የሚይዝ መሰበሰቢያ አዳራሽ እና ሌሎች መካከለኛ እና አነስተኛ መሰብሰቢያ
አዳራሾች
o ከ1000 በላይ የስራ እድል የሚከፍት
o ለውጭ ተጠቃሚዎች ሊከራይ የሚችል የገበያ(ሱቅ) ስፍራ ያካተተ ነው
o የህጻናት ማቆያ(day-care) ማዋእለ-ህጻናት(kindergarten)ያለው
o የእስፖርት አገልግሎት(መጫወጫ ስፍራ ፣ጂማናዚየም፣መዋኛ ቦታ )ያለው
o
 የህንጻ ከፍታው
o 5 ህንጻዎች ባለ 3B+G+21 ፎቅ
o 5 ህንጻዎች ባለ 3B+G+15 ፎቅ
 የግንባታው ገጽታ
o ለከተማውም ሆነ ለሀገራችን ልዩ የሆነ ጎልቶ የሚታይ (land mark) ሊሆን የሚችል የስራ ቦታ
o በአይነቱም ሆነ በይዘቱ በአፍሪካ 1ኛ የሆነ የሴክተር መ/ቤት ህንጻዎች የያዘ ግቢ
o ማራኪ እና ዘመናዊ ፕላዛ ያለው ግቢ(Central Plaza)
o ለሰራተኛ እና ለተገልጋዩ ምቾት ያለው እና ንጹህ የስራ አካባቢ
o ምቹ መኪና ማቆሚያ ስፍራ
o ምቹ የትራንስፖርት ተርሚናል ያለው(ለባስ፣ለታክሲ እና በሌላ ትራንስፖርት ዘዴ ለመቻንና
ለማውረድ ምቹ የሆነ)
o ለአይን ማራኪ፣ምቹ እና ዘመናዊ አረንጓዴ ግቢ
o ምቹ እና ክፍት የሆነ የመገበያያ ስፍራ(ፖዲየም)
o በጸሀይ ሀይል ማመንጨት እንዲችሉ የህጻዎቹ ጣሪያዎች ሶላር የተገጠመላቸው
o በቀላሉ ተነቃቅሎ ሊስተካከል በሚችል ወለል እና ግድግዳ የሚሰራ
o የግቢው ደህንነት በዘመናዊ ካሜራ ቁጥጥር የሚደረግለት እና 24 ሰዓት ደህንነቱ የተጠበቀ
o አካል ጉዳተኞችን ፣እናቶችን፣አቅመ ደካሞችን እና ህጻናትን ታሳቢ ያደረገ
o ለስብሰባ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ስብሰባዎች የሚመች አዳራሽ
o የተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶችን ያቀፈ በመሆኑ ሁሉኒም አገልግሎት በአንድ ስፍራ ለመስጠት
የሚያስችል

You might also like