You are on page 1of 24

ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዋና አስተዳደር

አረካ

ጉዳዩ፤-የፕላን ጥሰትን ይመለከታል

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ በከተማ ፕላን አዋጅ 574/2008 መሠረት አንድ የከተማ ፕላን
5-10 ዓመት የከተማው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ አከባቢያዊ ዕድገት የሚመራበት በከተማው ም/ቤት
የጸደቀ የመሬት አጠቃቀም ህግ ነው፡፡ በዚህ ፕላን ላይ ለተለያዩ አገልግሎቶች ማለትም ለመኖሪያ፣
ለንግድ፣ ለማህበራዊ አገልግሎት፣ ለአረንጓዴ ልማት፣ ለመንገድ ወዘተ… የተመለከቱ ቦታዎች አሉ፡፡
ከዚህ ውጭ መሬት መሸንሸን ሆነ መጠቀም አይቻልም፡፡ ይሁን እንጂ የወረዳችሁ ከተማ ውስጥ አንዱ
በነበረችው ዶላ ከተማ ለይ ከፍተኛ የፕላን ጥሰት ሆን ብሎ በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡ 1 ኛ)
ለመዋለህጻናት በፕላን ላይ የተያዜ ቦታ እያለ በንግድ ቦታ ላይ መዋለህጻናት ትምህርት ቤት ግንባታ
ቦታ መስጠት፣ 2 ኛ) ለአስተዳደር ተቋማት ግንባታ በተያዘው ቦታ ላይ ለእንሰት ፕሮጀክት ፕላንን
በሚቃረን መልክ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ይህ ደብዳቤ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ህገወጥ የፕላን
ጥሰት እንዲቆምና ምንም ዓይነት ግንባታ እዳይካሄድ እያሳሰብን ካልሆነ ግን በህግ ተጠያቂ የሚናደርግ
መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለወላይታ ዞን ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተ/አደ/ ፕላን ዘርፍ

ሶዶ፤

 ለዶላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት


ለ------------------------------ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

----------

ጉዳዩ፤-የከተማነት ዕውቅናን ይመለከታል

በወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በ 2013/14 በጀት ዓመት መሠረታዊ ፕላን ተዘጋጅቶላቸው
የከተማነት ዕውቅና እንዲሰጣቸው ለቢሮ ጥያቄ የቀረበባቸው የገጠር ማዕከላት መኖራቸው ይታወሳል፡፡

በመሆኑም የከተማነት ዕውቅና ለመፍቀድ ያመች ዘንድ የገጠር አገልግሎት ማዕከሉ መሠረታዊ ፕላን
የተዘጋጀበትን በፕላን ወሰን ክልል ውስጥ ነዋሪ የሆኑትን አባወራ /እማወራ ብቻ በመለየት የይዞታቸው ስፋት
በሄ/ር፣ የአ/አደር መጠቀሚያ ደብተር ያላቸው መሆኑ እና ሁሉም የይዞታ ባለቤቶች የፈረሙቤትን በተዘጋጀው
ቅጽ መሠረት ተሞልቶ እና በጽ/ቤት ኃላፊ ተረጋግጦ እስከ መጋቢት 5/2014 ዓ.ም ድረስ ለዞኑ ከተማ ልማትና
ኮንስትራክሽን መምሪያ እንዲላክልን እንጠይቃለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለወላይታ ዞን ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተሞች ፕላን ዘርፍ

ሶዶ፤

ለ------------------------------ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

----------
ጉዳዩ፤-የፕላን ዘመን የጨረሱ ማዘጋጃ ቤቶችን ይመለከታል

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ በከተማ ፕላን አዋጅ 574/2008 መሠረት የከተማ ፕላን ዕድሜ 5-10
ዓመት ነው፡፡ የከተማ ፕላን ዘመን ካበቃ በኃላ መጠቀም ሆነ ማስተዳደር አይቻልም፡፡ በዚህ መሠረት በዞናችን
ውስጥ የፕላን ዘመን የጨረሱና የቦታ ደረጃ ጥናት ጊዜ ያለፈባቸው ከተሞች የከተሞች የመልካም አስተዳደር
ጥያቄ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በነዚህ ከተሞች የፕላን ክለሳ ሳይሰራና ቦታ ደረጃ ሳይጠና ፕላን ማውረድ፣ መሬት
መሸንሸን ሆነ ጨረታ ማውጣት አይቻልም፡፡ እነዚህ ከተሞች ሞሌ ማንእሳ በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ፣ ጎጮ በኪንዶ
ድዳዬ ወረዳ፣ አንካ ሮብ በድጉና ፋንጎ ወረዳ፣ ጃጌ በዳሞት ጋሌ ወረዳ፣ እና ሃንጩቾ በዳሞት ሶሬ ወረዳ
ናቸው፡፡ ስለዚህ ይህ ደብዳቤ ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ከመምሪያችን ከተሞች አደረጃጀት ፕላን ጥናትና
ምርምር ትግበራ ክትትል ዳይረክቶሬት ጋር በመነጋገር በ 2015 ዓ.ም ፕላኑ እንዲከለስ እያሳሰብን ፕላን
ዘመን ያለፈበትን መጠቀም የማይቻል መሆኑን አጠብቀን እናሳዉቃለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለወላይታ ዞን ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተ/አደ/ ፕላን ዘርፍ

ሶዶ፤

 ለ-------------------ወረዳ ዋና አስተዳደር
 ለ--------------------ማዘጋጃ ቤት

-------------

ለ------------------------------ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

----------

ጉዳዩ፤- የፕላን ዘመን የጨረሱ ማዘጋጃ ቤቶችን የፕላን አፈጻጸም ኦዲት ይመለከታል፣
ከፕላን ውጭ የሆነ የከተማነት መስፋፋትና የፕላን ጥሰት በነዋሪው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ በመሆኑ
በዚህ ሳቢያ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችን ለመቆጣጠር ስታንዳርዱን በጠበቀ በከተማ ፕላን ከተሞች
እንዲመሩ ለማድረግ ነው፡፡ የከተማ ፕላን አፈጻጸም በከተማ ፕላን አዋጅ 574/2000 አንቀፅ 55 ንዑስ
አንቀፅ 2 በተሰጠው ስልጣን መሰረት(የሚዘጋጁ ፕላኖች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚጣጣሙ ስለመሆናቸው
ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ የተመጣጠነና የተቀናጀ የከተማ ልማት መኖሩን ያረጋግጣል፡፡)፣ አንቀፅ
18(የከተማ ፕላን አፈጻጸም ግልፅ በሆነ የማስፈጸሚያ ስትራቴጂ፣ ደንብና መመሪያዎች ስለመፈጸሙ
ማጣራት)፤ አንቀፅ 16 ንዑስ አንቀፅ 1(የከተማው ፕላንና የማስፈጸሚ የአካባቢ ልማት ፕላኖች ወደ ትግበራ
ከመግባታቸው በፊት አግባብነት ባለው ሕጋዊ በሆነ የከተማው አስ/ምክር ቤት እንዲፀድቁ ስለመደረጉ በሰነድ
ማጣራት) ተብሎ በተጠቀሰው አንቀፅ ከተሞች በፕላን በመመራት ተወዳዳሪነታቸው ተጠብቆ
ለነዋሪዎቻቸው ምቹ የመኖሪያና የመስሪያ ማዕከል እንዲሆኑ በተመጣጠነና በተቀናጀ ልማት
መተግበራቸውን ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምት መወሰዱን ማረጋገጥ
ይገባል፡፡ በዚህ መሠረት በወረዳችሁ ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ግራራና ሳኬ ከተሞች የክላሳ ፕላን
ከመሠራቱ በፍት የፕላን አፈጻጸም ኦዲት የሚያደርጉ ባለሙያዎች የላክን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለከተሞች አደ/ ፕላን ዘርፍ

ሶዶ፤

 ለ--------------------ማዘጋጃ ቤት
-------------

ለ------------------------------ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

ለ----------------------------- ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት

----------

ጉዳዩ፤-የሠፈር ልማት ፕላን/NDP ይመለከታል


ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ በከተማ ፕላን አዋጅ 574/2008 መሠረት መዋቅራዊና
ስትራተጅክ ፕላን በተሠራባቸው ከተሞች የሠፈር ልማት ፕላን/NDP ሳይሰራ ፕላን መትግበር
የማይቻል መሆኑን ይደነግጋል፡፡ የሠፈር ልማት ፕላን የህንጻ ከፍታ ለመወሰን፣ መንገድ፣ ዋናዋና
መሠረተ ልማትና ትራንስፖርት አገ/ት፣ የቤት ልማት፣ አረንጓዴ ቦታ፣ የከተማ ማደስና መልሶ
ለማቋቋምና ሌሎች የአከባቢ ጉዳዮችን ለመወሰን የሚሠራ ፕላን ነው፡፡

ነገር ግን በዞናችን ውስጥ ያሉ ፈርጅ 1-3 ያሉ ከተሞች የሠፈር ልማት ፕላን ሳይሠራ መዋቅራዊና
ስትራተጅክ ፕላን ተጠቅሞ ፕላን ወደ መሬት ማውረድና የተጀመሩ የሠፈር ልማት ፕላን ሥራዎች
ትኩረት ሰጥተው ያለማሰራታቸው ተስተውሏል፡፡

ስለዚህ መዋቅራዊና ስትራተጅክ ፕላን በተሠራባቸው ከተሞች የሠፈር ልማት ፕላን/NDP ሳይሰራ
ፕላን መትግበር፣ መሬት መሸንሸን ሆነ ለሎች አገልግሎት መጠቀም በአዋጁ መሠረት በህግ
የሚያስጠይቅ መሆኑን አውቀው ከመምሪያው ፕላን ዘርፍ ጋር በመቀናጀት ተግባራዊ እንዲያደርጉ
አጥብቀን እናሳታዉቃለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለወላይታ ዞን ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለፕላን ዘርፍ
 ለመሬት አቅርቦትና ማናጅመንት ዘርፍ

ሶዶ፤

ለ -------------------------------------- ከተማ አስተዳደር ማ/ቤት/ፕላን ዘርፍ

---------------

ጉዳዩ፤- በስልጠና የሚሳተፉ ባለሙያዎችን መልምላችሁ እንዲትልኩልን ስለመጠየቅ

ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተሞች ፕላን ኢንስቲትዩት በቁጥር ከልኮቢ/ፕ/ኢን/237 በቀን


21/04/14 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ በተገለጸልን መሠረት የከተማ ፕላንና መሬት ዘርፍ ተቋማት የተሰጣቸውን
ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም ከሚገጥማቸው ዋናዋና ማነቆ አንዱ በዘርፉ ብቁ የሰው ሃይል እጥረት መሆኑ
ይታወቃል፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ እንዲያስችል ሚኒስተር መስሪያ ቤቱ ምዘናና ስልጠና አዘጋጅቷል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የሚመለከታቸውን ባለሙያዎች መልምለው በአስቾካይ እንዲትልኩ እያሳሰብን ለምልመላው
ይረዳቸው ዘንድ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ------- ገጽ አባሪ አድርገን የላክን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለፕላን ዘርፍ

ለወላይታ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

ሶዶ፡-

ጉዳዩ፡- የሞተር ሳይክል ጥገና ይመለክታል

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ታርጋ ቁጥር ------- የሆነች ሞተርሳይክል ጥገና የሚያስፈልገው
ስለሆነ፡-

1 ኛ. የፍት ጎማ

2 ኛ. የእጅ ፍረን ጥገና እንዲደረግ እንጠይቃለን፡፡

ከሠለምታ ገር!
ለወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ

ሶዶ

ጉዳዩ፤- የመስክ ስምሪት ይመለከታል

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ በከተማ ፕላን አዋጅ 574/2008 መሠረት የከተማ ፕላን ዕድሜ
5-10 ዓመት ነው፡፡ የከተማ ፕላን ዘመን ካበቃ በኃላ መጠቀም ሆነ ማስተዳደር አይቻልም፡፡ በዚህ
መሠረት በዞናችን ውስጥ የፕላን ዘመን የጨረሱና የቦታ ደረጃ ጥናት ጊዜ ያለፈባቸው ከተሞች
የከተሞች የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በነዚህ ከተሞች የፕላን ክለሳ ሳይሰራና ቦታ
ደረጃ ሳይጠና ፕላን ማውረድ፣ መሬት መሸንሸን ሆነ ጨረታ ማውጣት አይቻልም፡፡ እነዚህ ከተሞች
ሄምበቤ፣ ዋራዛ ላሾ፣ አንካ ሮብ፣ አባያ ጉርቾ፣ ጋልቻ ሳኬ፣ ግራራ፣ ጉሩሞ ላድሳና ሃናዜ ጋሞ ናቸው፡፡
የፕላን ጥሰት፣ የአረንረጓዴና ክፍት ቦታዎች መሸንሸን፣ የህንጻ ከፍታና ግንባታ ሬሽዮ አለመጠበቅ፣ የሰፈር
ልማት ፕላን ሳይሠራ ፕላን መትግበር (ወ/ሶዶ፣ ቦዲቲ፣ ገሱባ፣ ጉኑኖ፣ አረካ እና ጠበላ ከተሞች እና በሌሎች
ከተሞች የሚታዩ ችግሮች ናቸው፡፡ በእነዚህ ከተሞች የፕላን ትግበራ ክትትል ያስፈልጋል፡፡ የፕላን ዘመን
የጨረሱ ከተሞች መሠረታዊ ፕላን ክለሳ እንዲሠራ ወረዳዎች በተጠየቁት መሠረት በሶዶ ዙሪያ ወረዳ
የላሾ በድጉና ፋንጎ ወረዳ ቢጠናና በአባላ አባያ ወረዳ የአባያ ጉርቾ ከተሞች መሠረታዊ ፕላን ክለሳ
የሚሠሩ ባለሙያዎች ከዚህ ሸኚ ደብዳቤ አባሪ አድርገን ---- ገጽ የላክን መሆኑን እየገለጽን ለሥራው
አስፈላጊ ትብብር እንዲደረግላቸው እናሳስባለን፡፡
ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለወላይታ ዞን ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
 ለመምሪያችን ሰ/ሀ/ሥራ አመራር ሥ/ሂደት

ሶዶ፤

ከወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ የተመደቡ ባለሙያዎች

ተቁ የባለሙያዎች ስም የሥራ ድርሻ የተመደቡበት ከተማ መስክ የሚወጡበት ጊዜ


1 ተመስገን ፋንታ ሶሽዮ ላሾ ማ/ቤት 21-28/06/2014
2 ጤናዬ ቡቄ ፕላነር ላሾ ማ/ቤት 21-28/06/2014
3 ጥበቡ ፊልሞን አደረጃጀት ላሾ ማ/ቤት 21-28/06/2014
4 ብሩክ ሞላ ሰርቨየር ላሾ ማ/ቤት 21-28/06/2014
5 ሳሙኤል መና ትግበራ ክትትል ላሾ ማ/ቤት 21-28/06/2014
6 ታምራት ብርሃኑ ፕላነር አባያ ጉርቾ 21-28/06/2014
7 ታረቀች አይዛ ሶሽዮ አባያ ጉርቾ 21-28/06/2014
8 አየለ ዱባለ አደረጃጀት አባያ ጉርቾ 21-28/06/2014
9 ፀሐይ መለሠ ትግበራ ክትትል አባያ ጉርቾ 21-28/06/2014
10 ሀና ዳዊት ሰርቨየር አባያ ጉርቾ 21-28/06/2014
11 አብርሃም አየለ ሶሽዮ ቢጠና ማ/ቤት 21-28/06/2014
12 ብሩክ ተስፋዬ ትግበራ ክትትል ቢጠና ማ/ቤት 21-28/06/2014
13 አለማዬሁ ጎልዳ ሶሽዮ ቢጠና ማ/ቤት 21-28/06/2014
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ለከተሞች ፕላን ኢንስትቲዩት

ሀዋሳ፤

ጉዳዩ፤- መሠረታዊ ፕላን የተሠራላቸው ከተሞች ፀድቀው እንዲላኩ ስለመጠየቅ ይሆናል

በወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከተ/አደ/ፕላ/ዝግ/አፈ/ክት ዘርፍ በ 2015 ዓ.ም 1 ኛ


ሩብ ዓመት መሠረታዊ ፕላን የተዘጋጀላቸው፡-

1 ኛ) ጋልቻ ሳኬ ክለሳ ፕላን፡ በዳሞት ወይዴ ወረዳ እና

2 ኛ ወይቦ ወጋ፡ ክለሳ ፕላን በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ፀድቀው እንዲላክልን እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታጋር!!!

ግልባጭ

 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
 ለወ/ዞ/ፋ/ኢ/ል መምሪያ

ሶዶ፤
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ለከተሞች ፕላን ኢንስትቲዩት

ሀዋሳ፤

ጉዳዩ፤- መሠረታዊ እና የሠፈር ልማት ፕላን የተሠራላቸው ፀድቀው እንዲላኩ ስለመጠየቅ ይሆናል

በወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከተ/አደ/ፕላ/ዝግ/አፈ/ክት ዘርፍ በ 2015 ዓ.ም 1 ኛ


ሩብ ዓመት መሠረታዊ ፕላን የተዘጋጀላቸው፡-

1 ኛ) አባያ ጉርቾ ክለሳ ፕላን፡ በአባላ አባያ ወረዳ እና

2 ኛ) ሆቢቻ ቦንጎታ ፕላን ከዕውቅና ጋር፡ በሆቢቻ

3 ኛ) ቆርኬና ፋቴ ሠፈር ልማት ፕላን በቦዲቲ ከተማ

4 ኛ) ቴክኒክና ሙያ ሠፈር ልማት ፕላን በገሱባ ከተማ ፀድቀው እንዲላክልን እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታጋር!!!

ግልባጭ

 ለወላይታ ዞን ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
 ለወ/ዞ/ፋ/ኢ/ል መምሪያ
ሶዶ፤

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ለከተሞች ፕላን ኢንስትቲዩት

ሀዋሳ፤

ጉዳዩ፤- የቦዲቲ ከተማ ስትራተጅክ ፕላን ሀርድና ሶፍት ኮፒ እንዲላክ ስለመጠየቅ ይሆናል

ከቦዲቲ ከተማ ማ/ቤት በቁጥር ቦማቤ 744 በቀን 30/02/2015 በተጻፈ ደብዳቤ የከተማው ስትራተጅክ ፕላን
በ 2010 ዓ.ም ተሠርቶ አስፈላጊ እርምቶች ከተደረገ በኃላ በቦዲቲ ከተማ ም/ቤት ቀርበው የፀደቀው ሀርድ
ኮፒና ሶፍት ኮፒ ከክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ስላልመጣ እስካሁን ለትግበራ መቸገራቸውን
ጠቅሰው የጠየቁ ስለሆነ የፕላኑ ሀርድ ኮፒና ሶፍት ኮፒ እንዲላክልን እንጠይቃለን፡፡

ከሠላምታጋር!!!

ግልባጭ

 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ለከተሞች ፕላን ኢንስትቲዩት

ሀዋሳ፤

ጉዳዩ፤- መሬት አጠቃቀም ለዉጥ እንዲደረግ ስለመጠየቅ

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ ከሶዶ ከተማ አስተዳደር በቁጥር-----------------በቀን----------------

መሠረት መሬት አጠቃቀም ለዉጥ እንዲደረግ፡

1 ኛ. በአቶ ገበየሁ ኡታሎ ስም የተመዘገበዉ ቦታ ከአረንጓዴ (recreation and formal Green area) ወደ ንግድ

(commerce) አገልግሎት መሬት አጠቃቀም ለዉጥ እንዲደረግ፡

2 ኛ. የሻለቃ ሀይሌ ገ/ስላሴ እንቨስትመንት ቦታ ከማህበራዊ አገልግሎት (social service) ወደ ንግድ

(commerce) አገልግሎት መሬት አጠቃቀም ለዉጥ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ስለሆነም በክልሉ ፕላን

ኢንስትቲዩት በኩል መሬት አጠቃቀም ለዉጥ ተደርጎ መስማሚያ ደብዳቤ እንዲላክልን እየጠየቅን አጠቃላይ

መረጃዎችን አያይዘን መላካችንን እናስታዉቃለን፡፡

ከሠላምታጋር!!!

ግልባጭ

 ለወ/ዞ/ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
ሶዶ፤
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ለከተሞች ፕላን ኢንስትቲዩት

ሀዋሳ፤

ጉዳዩ፤- መሬት አጠቃቀም ለዉጥ እንዲደረግ ስለመጠየቅ

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረዉ ከአረካ ከተማ አስተዳደር በቁጥር-----------------በቀን----------------

መሠረት መሬት አጠቃቀም ለዉጥ እንዲደረግ፡

1 ኛ. ------------------------------------- የተመዘገበዉ ቦታ ከ---------------- ወደ -----------------------

አገልግሎት መሬት አጠቃቀም ለዉጥ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ስለሆነም በክልሉ ፕላን ኢንስትቲዩት

በኩል መሬት አጠቃቀም ለዉጥ ተደርጎ መስማሚያ ደብዳቤ እንዲላክልን እየጠየቅን አጠቃላይ መረጃዎችን

አያይዘን መላካችንን እናስታዉቃለን፡፡

ከሠላምታጋር!!!

ግልባጭ

 ለወ/ዞ/ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
ሶዶ፤
ለወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ

ሶዶ

ጉዳዩ፤- የ 2014 የ 6 ወራት የዕቅድ አፈጻጻም ጠንካራና ደካማ ጎኖች መለከታል

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው የከተሞች አደረጃጀት ፕላን ዝግጀትና ትግበራ አፈጻጻም ክትትል
ዳይሬክቶሬት የ 2014 የ 6 ወራት የዕቅድ አፈጻጻም ጠንካራና ደካማ ጎኖች 1 ገጽ መረጃ ከዚህ ሸኚ ጋር አባሪ
አድርገን የላክን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለወላይታ ዞን ከ/ል/ኮ/መምሪያ
 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
 ለመምሪያችን ል/ዕ/ክትትል ሥ/ሂደት

ሶዶ፤
ስም ዝርዝር መላኪያ ፎርም

ክልል/ከተማ አስተዳደር ----------------------------------------------------

ተ.ቁ ሙሉ ስም ፆታ ከተማ አስተዳደር የት/ት የት/ት ዝግጅት የሥራ ክፍል በመስራት ላይ ምርመራ
ደረጃ የሚገኝበት መደብ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት S. ET .REG. STATE Wolaita Zone Urban
የወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ Development and Construction Department
Tohossa T /D/M/Kawotettan Wolaytta
ቁጥር/Ref.No /
Mootta Ambbaa Dichchaanne
Konistirakishiniya Kaalettuwa
ቀን/Date / /

ለከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፤

ጉዳዩ፤- የስልጠና ተሳታፊዎችን ስለመላክ ይሆናል፡፡

ከተማና መሰረተ ልማት ሚ/ር በቁጥር 85800250/30 በቀን 19/06/2016 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ በከተማ ፕላን
ዝግጅትና አፈጻጸም ዙሪያ ስልጠና ለሰክተራችን ባለሙያዎች ከጥር 30/2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ
ለአምስት ተከታታይ ቀናት ለመስጠት ፕሮግራም መያዙን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና መሰረተ
ልማት ቢሮ በቁጥር ከ/ል/መ/ል/ቢ 05/86 በቀን 21/06/2016 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ ገልፆልናል፡፡

በዚህ መሠረት ከወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከተማ ፕላን ዝግጅት 02(ሁለት) የስልጠና
ተሳታፊዎችን ከ 25/06/16 ዓ.ም ጀምሮ ለ 5 ተከታታይ ቀናት በአርባምንጭ ከተማ በስልጠና እንዲሳተፉ ከዚህ
በታች ባለው ሠንጠረዥ መሠረት የላክን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ተ. ስም የመጡበት ዞን/ወረዳ/ከተማ የደመወዝ የአካውንት ቁጥር


ቁ መጠን
1 በቀለ ቦጋሌ ከወላያታ ዞን ፕላን ኢንስቲትዩት
2 አስረት ወ/ሰማያት ከወላያታ ዞን ፕላን ኢንስቲትዩት
3 ታጋሽ ሰጠኝ ከወላያታ ዞን ፕላን ኢንስቲትዩት

ከሠለምታ ጋር!

ግልባጭ፤

 ለከተ/አደ/ፕላን ዘርፍ
 ለመምሪያችን ሰ/ሀ/ሥራ አመራር ሥ/ሂደት

ሶዶ፤
ለውሃና ኢነርጂ ሚኒስተር

አ/አበባ፤

ጉዳዩ፤- የወርክሾፍ ተሳታፊ ስለመላክ ይሆናል፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በቁጥር ወሶው/11-20/315 በቀን 27/07/2014 ዓ.ም
በጻፈው ደብዳቤ የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት፣ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስተር
እንዲሁም ከዓለም ባንክ ጋር በትብብር እየሠራ ላለው የሳኒተሸን ፐሮጀክት የአጭር ጊዜ
መፍተተሄዎች የፊዝብሊት እና ዲዛይን ጥናት ስለተጠናቀቀ በአርባምንጭ ከተማ ፓራዳይዝ ሎጅ
የጥናት ውጤቱን ማስተቼት መፈለጉነ ጠቅሰው አንድ የከተማ ልማት ባለሙያ እንዲንልክ
ጠይቀውናል፡፡

በዚህ መሠረት ከወላይታ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከተማ ፕላነር ባለሙያ የሆኑትን
አቶ ሚሊዮን ሾያ የደመወዝ መጠን 10521/አስር ሺህ አምስት መቶ ሃያ አንድ ከ 30/07/14 ዓ.ም
ጀምሮ በአርባምንጭ ፓራዳይዝ ሎጅ በወርክሾፕ እንዲሳተፉ የላክን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!
ለወላይታ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

ሶዶ፡-

ጉዳዩ፡- ንብረት ወጪ ሆኖ እንዲሰጥ ስለመጠየቅ ይሆናል

ከክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ፕላን ኢንስትቲዩት በቀን 02/09/2014 ዓ.ም በሞዴል 22
ቁ/933837 በአቶ ዮሴፍ አናሞ ስም ከተሰጡ 3 ታብለቶች መካከል አንዱን ከዚህ በታች ለተጠቀሱ የከተሞች
አደረጃጀት ፕላን ጥናትና ምርምር ትግበራ ክትትል ባለሙያ ስም ወጪ ሆኖ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

ተ.ቁ የእቃው/ንብረት ሞደል ብዛት ያንዱ ዋጋ ጠቅላላ ተረካቢ የሥራ ድርሻ


ኣይነት ዋጋ ባለሙያ ስም
1 Tablet Huawei EPHC143355 1 9501 9501 ዮሴፍ አናሞ ሥ/ሂአሰተባባሪ

ከሠለምታ ጋር!

ለወላይታ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

ሶዶ፡-
ጉዳዩ፡- ንብረት ወጪ ሆኖ እንዲሰጥ ስለመጠየቅ ይሆናል

ከክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ፕላን ኢንስትቲዩት በቀን 02/09/2014 ዓ.ም በሞዴል 22
ቁ/933837 በአቶ ዮሴፍ አናሞ ስም ከተሰጡ 3 ታብለቶች መካከል አንዱን ከዚህ በታች ለተጠቀሱ የከተሞች
አደረጃጀት ፕላን ጥናትና ምርምር ትግበራ ክትትል ባለሙያ ስም ወጪ ሆኖ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

ተ.ቁ የእቃው/ንብረት ሞደል ብዛት ያንዱ ዋጋ ጠቅላላ ተረካቢ የሥራ ድርሻ


ኣይነት ዋጋ ባለሙያ ስም
2 Tablet Huwaei EPHC142531 1 9501 9501 ሚሊዮን ሾያ ፕላነር

ከሠለምታ ጋር!

ለወላይታ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

ሶዶ፡-

ጉዳዩ፡- ንብረት ወጪ ሆኖ እንዲሰጥ ስለመጠየቅ ይሆናል


ከክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ፕላን ኢንስትቲዩት በቀን 02/09/2014 ዓ.ም በሞዴል 22
ቁ/933837 በአቶ ዮሴፍ አናሞ ስም ከተሰጡ 3 ታብለቶች መካከል አንዱን ከዚህ በታች ለተጠቀሱ የከተሞች
አደረጃጀት ፕላን ጥናትና ምርምር ትግበራ ክትትል ዘርፍ ሀላፍ ስም ወጪ ሆኖ እንዲሰጥ እንጠይቃለን፡፡

ተ.ቁ የእቃው/ንብረት ሞደል ብዛት ያንዱ ዋጋ ጠቅላላ ተረካቢ የሥራ ድርሻ


ኣይነት ዋጋ ባለሙያ ስም
3 Tablet Huwaei EPHC142797 1 9501 9501 አስፋው ሴታ ዘርፍ ሀላፍ

ከሠለምታ ጋር!

ለወላይታ ዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ

ሶዶ፡-

ጉዳዩ፡- ንብረት ገቢ እንዲሆን ስለመጠየቅ ይሆናል


ከክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ፕላን ኢንስትቲዩት በቀን 02/09/2014 ዓ.ም በሞዴል 22
ቁ/933837 በአቶ ዮሴፍ አናሞ ስም የተሰጡ 3 ታብለቶች 1) Tablet Huawei EPHC142797፣ 2) Tablet
Huwaei EPHC142531 እና 3) Tablet Huawei EPHC143355 ገቢ እንዲሆን እንጠይቃለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!

ለጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

ለጉኑኖ ሐሙስ ከተማ ማ/ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት

ጉኑኖ ሀሙስ

ጉዳዩ፡- ባለሙያ መላክን ይመለከታል፤


ከጉኑኖ ሐሙስ ከተማ አስተዳደር በቁጥር ጉሐከአ/10582/1 በቀን 01/03/2015 በጻፉት ደብዳቤ የጉኑኖ ሐሙስ ከተማ
ሠፈር ልማት ፕላን፣ ቦታ ደረጃ ጥናት እና ፈርጅ ለውጥ ዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ በ 2015 በጀት ዓመት ከተማዎ በያዘው
ዕቅድ መሠረት ባለሙያ እንድንልክ መጠየቃችሁ ይታወሳል፡፡ በዚህ መሠረት

1 ኛ. ሚሊዮን ሾያ---ፕላነር የደመወዝ መጠን-10521 (አስር ሺህ አምስት መቶ ሃያ አንድ)

2 ኛ. ዮሴፍ አናሞ- ሶሽዮ-ኢኮኖሚ ጥናት ባለሙያ የደመወዝ መጠን-10521 (አስር ሺህ አምስት መቶ ሃያ አንድ)

3 ኛ. ጥበቡ ፊልሞን -- ከተሞች አደረጃጀት መሻሻያ ጥናት ባለሙያ የደመወዝ መጠን-10234 (አስር ሺህ ሁለት መቶ
ሠላሳ አራት)

4 ኛ. ሀብታሙ አይዴ ሰርቨየር የደመወዝ መጠን-10234 (አስር ሺህ ሁለት መቶ ሠላሳ አራት)

5 ኛ. አስፋው ሴታ ዘርፍ ሀላፍ የደመወዝ መጠን 10226 9 አስር ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ስድስት

ከመምሪያችን የተላኩ ስለሆነ ለሥራዉ አሰፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው እናሳስባለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!!

ግልባጭ፤

 ለከተ/አደ/ፕላ/ዝግ/ትግ/ክት/ዋና ሥራ ሂደት

ወ/ሶዶ

ለወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት

ለወላይታ ሶዶ ከተማ ማ/ቤታዊ አገ/ት ጽ/ቤት

ሶዶ

ጉዳዩ፤- ባለሙያ መላክን ይመለከታል

ከላይ በርዕሱ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ከተማ አስተዳደር በቁጥር 08305/9/15 በቀን 9/3/2015 በጻፉት ደብዳቤ
የከተማ ቦታ ደረጃ ጥናትና የቀበሌ አደረጃጀት ጥናት የባለሙያ ድጋፍ በጠየቃችሁት መሠረት፡-
1 ኛ. አቶ ዮሴፍ አናሞ ከተ/አደ/ፕላ/ዝግ/ትግ/ክት/ ዳይረክቶሬት ቡድን መሪ የደመወዝ መጠን-10521 (አስር ሺህ
አምስት መቶ ሃያ አንድ)

2 ኛ. አቶ ጥበቡ ፊልሞን -- ከተሞች አደረጃጀት መሻሻያ ጥናት ባለሙያ የደመወዝ መጠን-10234 (አስር ሺህ ሁለት መቶ
ሠላሳ አራት) ከመምሪያችን የተላኩ ስለሆነ ለሥራዉ አሰፈላጊው ትብብር እንዲደረግላቸው እናሳስባለን፡፡

ከሠለምታ ጋር!!

ግልባጭ፤

 ለከተ/አደ/ፕላ/ዝግ/ትግ/ክት/ዋና ሥራ ሂደት

ወ/ሶዶ

You might also like