You are on page 1of 188

የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 ዓመት መሪ እቅድ

/ከ 2013-2022 ዓ.ም/

ሰኔ /2013 ዓ.ም

ደሴ

10 2013 -2022 / Page


1
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የእቅድ አዘጋጅ ኮሚቴ

ትዕዛዙ እንግዳ
1.

አጋዥ ሰብሳቢ
------------------------------------------

ክብረት 2.

አሰፋ ም ሰብ
------------------------------------------------ /

ሳቢ
3. አበበ
አረጋ --------------------------------------------------------

አባል
4. ሰይድ
አወል ------------------------------------------------------

አባል
ጌታቸው መሃመድ
5.

አባል
------------------------------------------

10 2013 -2022 / Page


2
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አህመድ መሀመድ
6.

አባል
------------------------------------------

ሲሳይ ከበደ 7.

ባንቲ አባል
------------------------------------------------

8. ሁሴን
ሙህዩ ---------------------------------------------------

አባል
9. ኤልያስ
ተክሌ ---------------------------------------------------

አባል
10. አህመድ
ጫኔ --------------------------------------------------- አባል
10 2013 -2022 / Page
3
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

11. መሀመድ
አሊ ------------------------------------------------- አባል
12. ወንድወሰን
አረጋ ----------------------------------------------- አባል
13. ሰይድ
እብሬ ----------------------------------------------------

አባል
14. ሙህዲን አሊ
------------------------------------------------- አባል

10 2013 -2022 / Page


4
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አማካሪዎች

1. አቶ አበበ ገ/መስቀል ----- የደሴ ከተማ ከንቲባ


2. አቶ መላኩ ሚካኤል--ም/ከንቲባና ተ/ሙ/ል/መምሪያ ሀላፊ
3. ዶ/ር አባተ ጌታሁን ------ ወሎ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት
4. አቶ ታምሩ ካሳ ----------- የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ
5. አቶ ብርቁ ዳኘ ------- የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ
6. አቶ አጥሌ ከበደ -------- የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ
7. አቶ አበራ ተፈራ ------- የህዝብ ተወካይ

10 2013 -2022 / Page


5
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

መግቢያ
ኢትዩጵያ ከድህነትና ኋላቀርነት ወጥታ ቀጣይ አስተማማኝ ወደሆነ እድገትና ብልፅግና ለመሸጋገር
በያዘችዉ ፈጣንና ሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ ስኬት ከተሞች የሚኖራቸዉ አስተዋፅኦ ከፍተኛ
ነዉ፡፡ከተሞች በሁለገብ የልማት እንቅስቃሴ ውስጥ የሚጠበቅባቸዉን ሚና
ለመወጣት ፅዱ፣ዉብ፣ ረንጓዴ፣ለነ ዋሪዎች ምቹና ተስማሚ ፣የአደገ
ኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ማእከል የመልካም አስተዳደር ስርአት የሰፈነባቸዉ
፣የህግ የበላይነት የተከበረባቸው ፣ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት
የተረጋገጠባቸዉ፣ የገበያ ፣የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ማእከል መሆን
ይጠበቅባቸዋል፡፡ይሁን እንጅ በከተሞች ስር ሰዶ የቆየዉና የፖለቲካ ኢኮኖሚዉን
የበላይነት የያዘዉ ኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ከተሞች
በሚፈለገዉ ደረጃ እንዳያድጉ እና የሚጠበቅባቸዉን ሚና እንዳይወጡ ማነቆ ሆኖ
ቆይቷል፡፡

በመሆኑም መንግስት ችግሮቹን ሊፈቱ የሚችሉና የከተሞችን እድገት ሊያፋጥኑ


የሚያስችሉ ልዩልዩ የከተማ ልማት ፖሊሲዎች፣ስትራቴጅዎችና የማስፈፀሚያ
ሰነዶችን በመቅረፅ ተግባራዊ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ከተማችንም ባለፉት 10 አመታት(ከ 2003-2012 ዓ.ም)ተግባራዊ


ሲደረግ የቆየዉንና የከተማዋን መሰረታዊ
የልማትናየመልካምአስተዳደርችግሮችለመፍታት፣ሰፊየህዝብተሳትፎእናተጠቃሚነትን
ለማረጋገጥየሚያስችል፣አስተማማኝሰላምናመረጋጋትን የሚያሰፍን
፣በአጠቃላይበከተማዋ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ለዉጥ
ለማምጣት የሚያስችል ቁልፍ መሳሪያ ቢሆንም 2 ኛ የዕድገት እና ለውጥ እቅድ
በተሟላ ሁኔታ በከተማው ሳይታቀድቢቆይም ሴክተሮች በራሳቸው እቅድ መሰረት

10 2013 -2022 / Page


6
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በየደረጃዉ በሚገኙና በሚመለከታቸዉፈፃሚ መ/ቤቶች እየተፈፀመና አፈፃፀሙም


በየደረጃዉ በሚገኙአስፈፃሚ አካላትና ም/ቤቶች እየተገመገመ ተግባራዊ ሲደረግ
ቆይቷል፡፡

ከባለፈዉ 10 ዓመታት የሴክተሮች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ለመረዳት


እንደተቻለው በእቅዱ መሰረት ተፈፃሚ የሆኑ አበረታች ዉጤቶች የተመዘገቡ
ቢሆንም በከተማዋ ከሚስተዋሉ ስር የሰደዱና ዉስብስብ ችግሮች እንዲሁም
ከነዋሪዎች ሰፊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች አንፃር የሚፈለገዉ
ዉጤት ተመዝግቧል ለማለት አይቻልም፡፡

ከሌሎች ነገሮች ጎን የነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር፣ሙስናና ብልሹ አሰራር


፣የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድችግር፣ህገ ወጥነት፣በቂ የመዝናኛናየስፖርት
ማዘዉተሪያ ቦታዎች የመሰረተ ልማት አለመሟላት አሁንም አንኳር የከተማዋ
ችግሮች እንደሆኑ ቀጥለዋል፡፡ በመሆኑም የክልላችንንና የሀገራችንን ነባራዊ ሁኔታ
በመዳሰስ፤ የከተሞች የልማትናየመልካምአስተዳደርፖሊሲዎችን፣ስትራቴጅዎችንና
የማስፈፀሚያ ፕሮግራሞች መነሻ በማድረግየ 10 አመታት እቅድ አፈፃፀም
ግምገማ ትምህርት በመዉሰድ፣የከተማዋንየልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች
በመፍታትየነዋሪዎችተሳትፎናተጠቃሚነትሊያረጋግጥየሚችል፣ለነዋሪዎቿምቹናተስማ
ሚ፣ሳቢናማራኪየሆነች፣የኢንቨስትመንትእናቱሪዝምመዳረሻየሚያደርጋት፣በንግድ፣በአ
ገልግሎትእና በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚዋ የዳበረ፤ተወዳዳሪና
ተመራጭ ከተማ እንዲትሆን ይህየቀጣይ 10 ዓመት (ከ 2013-2022 ዓ.ም) መሪ
እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

መሪ እቅዱን በውጤታማነት የሁኔታዎች ትንተና፣ የአፈፃፀም አቅጣጫዎች፣


በአፈፃፀምወቅት ሊያጋጥሙየሚችሉ ስጋቶችና የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንዲሁም
የድርጊት መርሀ ግብር ተካተዋል፡፡ ዚህም መሰረት የ 10 አመቱ መሪ እቅድ
በየ 5 አመቱ ከዚያም በየአመቱ ተከፋፍሎተፈፃሚየሚሆን ሲሆን
የእቅድአፈፃፀሙበአስፈፃሚዉ አካል፣በህዝቡና በየደረጃዉ ባሉ ም/ቤቶች
እየተገመገመ የሚመራይሆናል፡

በአጠቃላይ ከተማችን ይህን የ 10 አመት መሪእቅድ በመተግበር በቀጣዮቹ 10


አመታት ዉስጥ ተጨባጭና እምርታዊ የኢኮኖሚ፣የማህበራዊናየፖለቲካ ለዉጥና

10 2013 -2022 / Page


7
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

እድገት አስመዝግባ ‹‹ ደሴን በ 2022 በኢትዩጵያ ውስጥ ከሚገኙት ሪጅዩ ፖሊስ


ከተሞች ተወዳዳሪ፣ ምቹና ሁለገብ ብልፅግና ያላት ከተማን እዉን እናደርጋለን
››፡፡

ክፍል አንድ
የደሴ ከተማ አመሰራረት አጭር ታሪካዊ ዳራ
1.1 ቅድመ ምስረታ
የደሴ ከተማን ቅድመ ትውፊቶችን ስንቃኝ ዐፄ ቴዎድሮስ የአንድነት ግዛታቸውን
ለማስፋፋት በ 1840 ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ወደ ወሎ መጥተው ጊዚያዊ የጦር
ሰፈራቸውን ጀሜ ተራራ ላይ አድርገው እንደነበር ታሪክ ይጠቁመናል፡፡ ከአጼ ቴዎድሮስ
ሞት በኋላም አጼ ምኒሊክ ወሎ ወደ ግዛታቸው ለማጠቃለል ሲሉ በወቅቱ የወሎ
ራሶች በነበሩት በአመዴ ሊበን / አባዋጣው / እና በመሀመድ አሊ / ኋላ ንጉሥ ሚካኤል /
ላይ ዘምተው ነበር፡፡ አጼ ዮሐንስም እንዲሁ ከሰሜን ወደ ወሎ በመዝለቅ ወሎን ወደ
ግዛታቸው ለማጠቃለል ጥረትያደርጉ እንደነበርናከዚያም አልፈዉ ሁለቱን የወሎ ራሶች
አመዴ ሊበንና ሙሀመድ አሊን ቦሩ ሜዳ ላይ አስቀምጠዉ አመዴ ሊበንን ራስ
ወልደማሪያም፣ሙሀመድ አሊን ደግሞ ራስ ሚካኤል ተብለዉ እንዲሰየሙ አድርገዋል ፡፡
ወሎን ወደ ግዛታቸዉ ለማጠቃለል ፍላጎት የነበራቸዉ አፄሚኒልክም ከአፄዮሀንስ ጋር
ለመነጋገር ወደ ትግራይ ሲያቀኑ ባለቤታቸዉን እቴጌ ጣይቱን ደሴ ጀሜ ተራራ አካባቢ
እንዲቆዩ አድርገዋል፡፡ አፄሚኒሊክ ትግራይ ደርሰዉ እስከሚመለሱ ድረስ እቴጌ ጣይቱ
ለሁለት ወር ያህል ጀሜ ተራራ ላይ መክረማቸው ይነገራል፡፡ ከዚህ አጭር ቅድመ ከተማ
ምስረታ ታሪክ የምንረዳው ጀሜ ኮረብታ ለደሴ ከተማ መመስረት ቁልፍ መሰረት
መሆኑንና በሁሉም ነገሥታት እይታ ደሴና አካባቢዋ እጅግ ማራኪና l ኑሮም የተመቸች
እንደነበር ታሪክ ይጠቁመናል፡፡
ሶስቱ መንግስታዊ ሀላፊነት በተለያየ አጋጣሚና ምክንያት ወደ ጀሜ ከመምጣታቸውም
በተጨማሪ አካባቢው ከለሌሎች አካባቢዎች በመልክዐ ምድር ባለው ትስስር ለንግድ
እንቅስቃሴ መተላለፊያ ዋና ቢሮ እና ማእከል መሆኑ ለታጁራ፣አሰብና ጅቡቲ ወደቦች

ቅርብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የንግድ እንቅስቃሴዉ በጢጣ በር በኩል ወደ ትግራይ እና

አስመራ፣በቢለን ወይም ገራዶ በኩል ወደ ሸዋና ጎጃም፣በኩታበር በኩል ወደ

በጌምድርወይም ወደ ጎንደርእና በቁርቁር በር በኩል ወደ የጁ፣ ራያ እና ወደ ሌሎችም


አካባቢዎች በከፍተኛ ሁኔታ የንግድ እንቅስቃሴ ይደረግ ነበር፡፡

10 2013 -2022 / Page


8
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

1.2 የደሴ ከተማ አመሰራረት


በ 1885 ዓ.ም አካባቢ የንግሥና ማዕረጋቸውን የያዙት ንጉስ ሚካኤል ደሴን ዋና

ከተማቸው አድርገው ሲመርጡ ከበርካታ ምክንያቶች መካከል አካባቢው ጠላት ሲመጣ

በሩቅ ለመቆጣጠር አመች በመሆኑ ፣የንግድ እንቅስቃሴ መተላለፊያ ዋነኛ በር በመሆኑ

፣አየሩ ለኑሮ ተስማሚ እና የግብርና ምርቶች፣ በቂ ውሃ የሚገኝበት በመሆኑ፣ የጦሣና


የአዘዋ ተራሮች አስደሳችና ማራኪ በመሆናቸውና ሌሎች ምክንያቶች ለቋሚ
አስተዳደራዊ ማእከልንት መርጠውታል፡፡
በ 1880 ዎቹ መጨረሻና በ 19 ዐዐዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የንጉሥ ሚካኤል
ቤተመንግሥትና አይጠየፍ አዳራሽ መገንባት ፣በሳምንት አንድ ጊዜ ግብይት
የሚካሄድበት ትልቁን የሰኞ ገበያ መቋቋም ፣በ 1913 አካባቢ የደሴ ከተማ
በሰፈርሹሞችተከፋፍላ የመጀመሪያውአስተዳደራዊመዋቅር መጀመሩ፣ከንጉሥ
ሚካኤል ኋላም ወ/ሮ ስኂን ፣ እቴጌ መነንና መምህር አካለወልድ የመሳሰሉ ዘመናዊ
የመንግስት ተቋማት መመስረት ለደሴ ከተማ መስፋፋት ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው፡፡
በአምስት ዓመቱ የኢጣሊያ ወረራ ወቅትም ደሴ ከተማ የዘመናዊ የከተማነት ባሕሪ
በመላበስ በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ማዕከልነቷ እየተጠናከረ መጥቷል፡፡
1.3 ስያሜ
የሀገራችን ታሪክ ፀሀፊዎች ትልልቅ አባቶችን ጠቅሰዉ ደሴ ከተማ
ስያሜዋንያገኘችበትን መላምቶች እንደሚከተለዉ ጠቅሰዋል፡፡ ዓፄ ዩሀንስ በአካባቢዉ
በመጡበት ወቅት አካባቢዉን ሲቃኙ በልምላሜዉና በተፈጥሮአዊ አቀማመጡ
ስለተማረኩ ‹ደስ›የሚል ቦታ ነዉ ሲሉ ደስታየ ነዉ ደስ ብሎኛል በሚል ስሜትበዚያዉ
‹ደሴ› የሚለዉን ስያሜ ይዟል የሚሉ አሉ፡፡
ዓፄ ቴወድሮስም በአካባቢዉ ዘልቀዉ ጀሜ አካባቢ በሰፈሩበት ወቅት ድንኳናቸዉን
ተክለዉ ነበር፡፡ በጊዜዉ የተቀመጡባት ድንኳን ‹ደስታ› የሚል ስያሜ ነበራት ፡፡ ከዚሁ
ከድንኳኗ ስያሜ ጋር በማመሳሰል ለአካባቢዉ ደስታ ‹ደሴ› ብለዉ ሰየሙት ይባላል፡፡
ከተማዋ ደሴ ተብላ ከመሰየሟ በፊት ላኮመልዛ ተብላ ትጠራ እንደነበር ይነገራል፡፡

አሁን ሰኞ ገበያ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ጠላ በመሸጥ የሚተዳደሩ ደሴ የሚባሉ


ሴት ነበሩ፡፡ ከሩቅ አካባቢ የሚመጡ ነጋዴዎች በቅሎና በአህያ ለገበያ ጭነዉት
የሚመጡትን እቃ ሳይሸጥ ሲቀርናሲተርፍባቸዉ እኝህ ሴትዮ ቤት ያስቀምጡወይም
በገበያተኛዉ አባባል ደፍተዉ ይሄዱ ነበር፡፡ታዲያ ሁል ጊዜ እርስ በርስ ሲያወሩ ዕቃየን
ደሴ ቤት አስቀምጨዋለሁ ደሴ ቤት እንገናኝ እየተባባሉ የወ/ሮ ደሴ ቤት መቀጣጠሪያም
ሆኖ የሴትዩዋ ስም ለከተማዋ ስያሜ ሆነ የሚሉ አሉ፡፡

10 2013 -2022 / Page


9
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

1.4 የደሴ ከተማ አጠቃላይ ገፅተ


1.4.1 መልከዐ ምድርና የአየር ንብረት ሁኔታ
ደሴ ከተማ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ስር ከሚገኙ ሶስት ሬጅኦ ፖሊስ
ከተሞች መካከል አንዷ ስትሆን ከሀገራችን መዲና አዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ 401
ኪ.ሜርቀትላይ፣ ከክልላችን ርእሰ ከተማ ባህር ዳር በስተ ምስራቅ 480 ኪ.ሜ ርቀት ላይ
ትገኛለች፡፡ ከተማዋን የቃሉ ወረዳ የአልብኮ እና ደሴ ዙሪያ ወረዳዎች፣ በምዕራብ
ሰንሰለታማዉ የጦሳ ተራራ እና የደሴ ዙሪያ ወረዳ፣በስተ ሰሜን የኩታበር እና ተሁለደሬ
ወረዳ ያዋስኗታል፡፡

በመልከዐ ምድራዊ አቀማመጥ ደሴ ከተማ በ 11°05’ ሰሜን ኬክሮስ እና በ 39° 40´


ምስራቅ ኬንትሮስ ከባህር ወለል በላይ በ 2470 እና 2250 ሜትር ከፍታ ላይ
በአስደማሚዎቹ የጦሣና የአዘዋ ተራሮች ተከባ በድምቀት የተከተመች ከተማ ስትሆን
ከጠቅላላ የቆዳ ስፋትዋ 16800 ሄክታር ዉስጥ 62%የሚሆነዉ ደጋ የአየር ንብረት ያለዉ
ሲሆን ቀሪዉ 38% ደግሞ ወይና ደጋ የአየር ንብረት አለው፡፡ የከተማዋ አመታዊ
የሙቀት መጠን እንደ ወቅቱ 4.1-25.3 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ሲሆን አማካይ ሙቀት
19.82 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እና አመታዊ የዝናብ መጠን 1900 ሚሊ ሊትር ይደርሳል፡፡
ይህም በመሆኑ ከተማዋ ለስራና ለመኖሪያ ምቹ የሆነ የአየር ንብረት እንዲኖራት አስተዋፅኦ
አድርጓል፡፡

1.4.2 የህዝብ ብዛት


የደሴ ከተማ ሕዝብ ብዛት ከአብክመ ፕላን ኮሚሽን በ 2013 ዓ.ም በተገኘ የትንበያ
መረጃ መሰረት ወንድ 127,625 ሴት 145,680 ድምር 273,305 ሲሆን በከተማ
አስተዳደር የልማት እቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ቡድን በ 2013 ዓ.ም ከክፍለ ከተሞችና
የገጠር ቀበሌዎች መረጃ ተሰባስቦ በተጠናቀረው መሰረት ወንድ 220,894 ሴት
259,843 ድምር 480,737 ህዝብ እንደሚደርስ ይገመታል፡፡
1.4.3 አስተዳደራዊ መዋቅር

የደሴ ከተማ በህዝብ የተወከሉ የምክር ቤት አባለት፣ በከንቲባው የሚመራ ስራአስፈጻሚ


እና በፍትህ አካላት የተዋቀረ ሲሆን በትክክል ከተሰራበት አደረጃጀቱ ለዲሞክራሲ፣
ሰላም፣ ለልማት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ምቹ ሁኔታዎች
ፈጥሯል፡፡ ከተማው 5 ክፍለ ከተሞች፣ 18 የከተማ ቀበሌዎች እና በ 8 የገጠር ቀበሌዎች

10 2013 -2022 / Page


10
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ተዋቅራለች፡፡ በሁሉም የአስተዳደር እርከኖች አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ


ሁኔታዎችና የሰዉ ሀይልም ከሞላ ጎደል ተሟልቶ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

1.4.4 የሰላም ሁኔታ

ደሴከተማ ነዋሪዎቿ በዘር/ጎሳ፣ በቀለም፣ በሀይማኖት ሳይለዩ በፍቅር በመከባበር


የሚኖሩባት አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት የፍቅርና የጥበብ ከተማ ናት፡፡ ደሴ ከተማ
ከምትታዎቅባቸዉ እሴቶቿ መካከል ፍቅር፣ አንድነት፣ መከባበር፣ እንግዳ ተቀባይነት፣
አቃፊነትና አርሂቡ ባይነት በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡

ክፍል ሁለት
የዘርፎች ያለፉት 10 ዓመታት አፈፃፀም

2.1 የለውጥ ኃይል ግንባታን ማሻሻል


የሲቪል ሰርቪስ/ ስራው የከተማ አስተዳደሩን የልማት ኃይል ግንባታ ባለበት እንዲቀጥል
በማድረግ የእቅድ ግቦች ለማሳካት በማሳለጫነት እየተጠቀመ ይገኛል፡፡ የከተማ
አስተዳደሩን ተግባር በተደራጀ የለውጥ ኃይልመፈፀም ጠቀሜታዉ የጎላ መሆኑን በመገንዘብ
የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡን፣ ለማጠናከር በየጊዜው ክትትል እና ድጋፍ ሲደረግ የቆየ ቢሆንም
በውጤት ደረጃ ብዙ ለውጥ ያላመጣ እና ችግር ፈች አለመሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ የተቋም
አመራሮች ተቋማቸዉንከማብቃት ይልቅ በሌሎች ተግባሮች ላይ በመጠመዳቸው ለልማት ኃይል
ግንባታዉ ትኩረት ያለመስጠት ይስተዋላል፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ ተጨማሪ የክፍለ-ከተማና
ቀበሌ አደረጃጀት በመፈጠራቸው ምክንያት ለውጥ ሳይኖር አደረጃጀት መፍጠር ተችሏል።
አደረጃጀቶችን መሰረት በማድረግ የልማት ተግባራት በህብረተሰቡ እና የለውጥ ቡድን
ውይይቶች በመንግስት ሰራተኛው፣የእርስ በእርስ መማማርና ግምገማዎች ሲካሄድ
ቆይቷል።

10 2013 -2022 / Page


11
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በከተማ አስተዳደሩ የለውጥ ሀይል ግንባታ ተግባራትን በማስፈፀም ረገድ ባለፉት 10

አመታት ከአመለካከት አኳያ እየተመዘገቡ ያሉ መጠነኛ ለውጦች ታይተዋል፡፡ ከነዚህም

መካከል ከአመለካከት አንጻር የታዩ ለውጦች የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ ከጊዜ ወደ

ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱ፣ የለዉጥ ቡድን አደረጃጀቱ የሥራ ማሳለጫ መሆኑን

በአስተሳሰብ መያዙ፣ የተዛቡ አመለካከቶችን ለማስተካከል የሚደረገዉ ጥረት አያደገ

መሆኑ፣በሚደረግ ዉይይት ላይ የበሰለ ሃሳብ የሚቀርብ መሆኑ፣ የሥራ መነሳሳት

አዝማሚያ በአብዛኛው የህብረተሰብ ክፍልና በመንግስት ሰራተኛው መታየቱ

መልካም እድል የፈጠረ ነበር፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የተቋሙን ተልዕኮ በግልፅነት ወይም በተፈጠረው ግንዛቤ የተቋሙን


ርዕይ፣የተቋሙን አሰራር ደንብ ግልፅነት በመያዝ በእውቀት ላይ ተመስርቶ ለመስራት
የሚደረገው ጥረት አበረታች ነበር፡፡ በጋራ መስራት ያለውን ፋይዳ በመረዳት የአሰራር
ክፍተቶችን በወቅቱ ለማረም እና ለማስተካከል አግዟል፡፡ለሰራተኛው የስድስት ወር እቅድ
በውጤት- ተኮር ስርዓት ተሰፍሮእንዲሰጥ እና የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ተግባር
በውጤት ተኮር ስርዓት ለመምራት ጥረት ተደርጓል፡፡

ከክህሎት አንጻር የታዩ ለውጦችን ስንመለከት የለዉጥ ሰራዊት እቅድ እየተዘጋጀ

፣የመማማር ዕቅድ፣ የህዝብ ክንፍ ዕቅድ በመስራትና በመማማር እና እድገት በሚቀርቡ

ዉይይቶች አቅምን የማሳደግ ስራ ተከናዉኗል፡፡ አመታዊ እቅድ ህብረተሰቡንና


ሰራተኛውን አሳታፊ በሆነ መንገድ በውጤት- ተኮር ዕቅድ መሰረት
መታቀዱ፣የኮምፒዩተር አጠቃቀም እያደገ መምጣቱ ተግባራትን በሚዛናዊ ውጤት
ተኮር አተቃቀድ በማቀድ የመፈጸምና አፈጻጸሙንም ለመከታተል የሚረዱ ስልቶችን
ለመጠቀም የሚደረገዉ ጥረት ለምሳሌእቅድን ቆጥሮ የመስጠትና
የመቀበል፤ግብረመልስ የመስጠት ክህሎት እያደገ የመጣበት ሁኔታ ነበር፡፡

የልማት ሀይል ግንባታው ከእዉቀት አንጻር የታዩ ለዉጦች መሰረት በማደረግ ሲቃኝ የስራ
ሪፖርትን በአግባቡ የማደራጀትና የመግለጽ ብቃት እየተሻሻለ የመጣ

ቢሆንምየዉይይትመቆራረጥታይቷል፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየጊዜው


በመገምገም እየለዩ በመፍታት ውስንነት መኖሩ፣የሲቪል ሰርቪስ የአሰራር መርሆዎች
ደረጃ በደረጃ በመፈጸም በኩል በሚፈለገውደረጃ አለመድረስ፣ፈፃሚው ጥንካሬና
ድክመትን በአግባቡአለመለየት ያልተሻገርናቸው ችግሮች ናቸው፡፡ አሁንም ቢሆን

10 2013 -2022 / Page


12
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በየጊዜው በመገምገም እየለዩ በመፍታት ረገድ ለውጡ


የህብረተሰቡን እርካታ ያላመጣ ነው፡፡
በመሆኑም በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ልዩ ልዩ አደረጃጀት

በመፍጠርየለዉጥአስተግባሪቡድን፣የመማማርናእድገትአደረጃጀት፣ የልማት ቡድኖችን


አደረጃጀት ሳምንታዊ ውይይት እና እርስ በርስ ለመማማር በሚረዳ ሁኔታ ለማደረጀት
ሰፊ ጥረት ተደርጓል፡፡
የለዉጥ አስተግባሪ ቡድኑ የተቋቋመ ቢሆንም በመጀመሪያዉ ግለት ሊቀጥል
ያልቻለበትና ከተማ አስተዳደሩም አስፈላጊውን አደረጃጀት እየፈጠረ ተከታትሎ
ተግባራዊ በማድረግ በኩል ሰፊ ክፍተት የነበረበትና በወቅታዊው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ
ምክንያት እየተቀዛቀዘ የመጣበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ የለውጥ
ሀይልአደረጃጀት አሁንም ቢሆን የደንበኞችን ጥያቄ ሊመልስ በሚችል መልኩ የተደራጀ
ባለመሆኑ በቀጣይ በአዲስ መልኩ አደረጃጀቱ መጠናት እንዳለበት ታሳቢ ሊደረግ
ይገባል፡፡
ባለፉት 10 አመታት አሰራርመሰረት አድርጎ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ

የከተማው አስተባባሪ፣ የካቢኔ አባላት፣ ጠቅላላ አመራሩና በስራ መለያ ዝርዘር መሰረት

ቆጥሮ በማስረከብ እና ቆጥሮ የመረከብ ባህል እየዳበረ መምጣቱ እና ለከተማው

የተመደቡ የሥራ መገልገያዎች በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም ረገድ መሻሻል የታየበት


ነው፡፡
የሰራተኛ ዉጤት ተኮር በየወሩ ለመሙላት ሚዛናዊ ውጤት ተኮር አተቃቀድ እቅድ

በከተማ አስተዳደሩ ባሉ ተቋማት ለየስራ ክፍሎች፣ ከስራ ክፍሎች ለባለሙያዉ

በመስጠት በወቅቱ ዉጤቱ እየተሰፈረ በአበይትና ቁልፍ ተግባራት ዙሪያ በመወያየት

ክፍተቶችን በመሙላት ስራዎችን ማከናወን የተቻለ ሲሆን ሆኖም ግን በ 2012 ዓ.ም

አጋማሽ ጀምሮ አለማአቀፋዊ የኮሮና ቫይረስ ምክንያት በአበይት እና ቁልፍ ተግባር

ዙሪያ ዉይይት መቀዛቀዙ የታየበት ነበር፡፡ ተቋማዊ አገልግሎትን አስፈላጊውን ግብአት

በማሟላት አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ረገድ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በጀትን

መሰረት ያደረገ የግዥ ፍላጎት ተለይቶ ለግዥ ክፍሉ በማሳወቅ ግዥዉ ተፈፅሞ

የተገዙ ማቴሪያሎች ለአስፈላጊው ስራ እንዲደርስ መደረጉ እና ከተማ አስተዳደሩ

አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በቁጠባ መጠቀም ተችሏል፡፡

2.1.1 የአመራርና የፈጻሚውን ብቃት ማሳደግ

10 2013 -2022 / Page


13
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አቅም በማሳደግ የህዝብ አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ አንጻር በተለያዩ የስልጠና


መስኮች የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስልጠና በመስጠት የሙያተኛውን ዕውቀት
እና ሥነ-ምግባር ማሳደግ ተገቢ በመሆኑበተለያየ ጊዜ በአስር ዓመቱ የዕድሉ ተጠቃሚ
ማድረግ ተችሏል፡፡ በአጫጭር ስልጠናዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና
በመሥጠት ግንዛቤያቸውን የማሳደግ ተግባር የተከናወነ ቢሆንም ለባለሙያ የረጅም
ጊዜ ትምህርት እድል በማመቻቸት በኩል ሰፊ እጥረት የታየበት ነው፡፡

2.1.2 የዘርፉን ውስን የገንዘብና ሰብአዊና ሀብቶች አጠቃቀም


የበጀት አጠቃቀም፤
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከ 2007---2012 ድረስ የመደበኛና የካፒታል በጀት አጠቃቀም

በተመለከተ በ 2007 ዓ.ም የተመደበ ስራ ማስኬጃ በጀት ብር 30,609,924.00 ሲሆን


ስራ ላይ የዋለ ብር 27,477,060.27 አፈጻጸሙም 89.76% ነበር፡ በ 2012 ዓ.ም ደግሞ
የተመደበ ስራ ማስኬጃ በጀት ብር 63,577,798.99 ሲሆን ስራ ላይ የዋለ ብር
58,746,103.46 አፈጻጸም 92.40% ደርሷል፡፡
የደመወዝ በጀት አጠቃቀምን በተመለከተ የ 2007 ዓ.ም የተመደበ በጀት ብር
153,892,919.00 ስራ ላይ የዋለ ብር 152,289,782.96 ሲሆን አፈጻጸሙ 98.95%
ሲሆን የ 2012 ዓ.ም የተመደበ በጀት ብር 347,356,194.98 ስራ ላይ የዋለ
34,7352,373.51 አፈጻጸም 100% ነበር፡፡ በአጠቃላይ የደመወዝ በጀት ከ 2007 ዓ.ም
ጋር ሲነጻጸር በ 2012 ዓ.ም የተመደበው የደመወዝ በጀት በመብለጥ በብር
186,826,927.07 እድገት አሳይቷል፡፡ የካፒታል በጀት አጠቃቀምን በተመለከተ በ 2007
ዓ.ም የተመደበ ካፒታል በጀት ብር 261,607,650.00 ሲሆን ላይ ስራ ላይ የዋለ ብር
127,352,458.27 አፈጻጸም 97.39% ነበር፡፡
በ 2012 ዓ.ም የተመደበ ካፒታል በጀት ብር 215,370,882.03 ስራ ላይ የዋለ ብር
146,191,348.03 አፈጻጸም 67.88% ነው፡፡ የከፒታል በጀት እድገት እያሳዩ ያልመጣ
በመሆኑ በጀትን መሰረታዊ ለሆኑ ፕሮጀክቶች በማዋል ትኩረት ያልተሰጠው ተግባር
ነው፡፡
 የሰው ኃይል

የሰው ሀይል ተግባራትን ለመፈጸም መሰረታዊ እና ወሳኝ ቢሆንም ያለውን የሰው ሀይል
በአግባቡ ስራን ማሰራት ከልተቻለ ለብክነት የሚዳርግ ይሆናል፡፡

10 2013 -2022 / Page


14
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

2.2 የአበይት ተግባራት አፈፃፀም


2.2.1 ከተማ ልማት ዘርፍ ተግባር አፈጻጸም
 የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈፃፀም ስራዎች

ከፕላን አፈፃፀም ጋር በተያያዘ በከተማችን የፕላን ትግበራ አፈጻጸምን ለማሻሻል 8 ጊዜ


የፕላን ኦዲት ለማድረግ ታቅዶ 6 ጊዜ የተከናወነ ሲሆን አፈጻጸሙ (75%) ነበር፡፡

በከተማችን ለቀረቡ የዞኒንግ ለውጥ ጥያቄዎችን ምላሽ ከመስጠት አንጻር በቁጥር 16


ታቅዶ 43 (100%) ተፈጽሟል፣እንዲሁም የመንገድ አቅጣጫ ለውጥ ለሚጠይቁ
ግለሰቦችሙያዊ አስተያየት በመስጠት በሚመለከታቸው እንዲፀድቁ ማድረግና ወደ ስራ
እንዲገቡ ለማድረግ በቁጥር 25 ታቅዶ 25 (100%) ተፈጽሟል፡፡ በሌላ በኩል የፕላን
ስምምነት ቅጽ ሞልቶ ለተጠቃሚው መረጃ በጥራት ለመስጠት በእቅድ 7184

ተይዞ፤7878 (100%) የተከናወነ ሲሆን፣ እንደዚሁምለተለያዩ ግለሰቦች የይዞታ ልኬታ

ለማድረግ 3200 ታቅዶ ክንውኑ 3324(100%) ተፈጽሟል ፡፡

የተመቻቸ የመሰረተ ልማት ስራዎች ለማከናወን መንገድ ከፈታ 110 ኪ.ሜ/ በእቅድተይዞ
31.8307 (53.05%) ተከናውኗል፣ብቻቸውን መልማት የማይችሉ /የይዞታ መጠናቸው ከደረጃ
በታች/ የሆኑ ይዞታዎችን የተከለሉ ቤቶች አደረጃጀት (በብሎክአሬንጅመንት) ለማልማት
በእቅድ 99 ይዞታዎች የተለዩ ሲሆን ከተለዩት 88 ይዞታወች (88.89%) ማልማት ተችሏል፣ነባር
አካባቢ የልማት መርሀ ግብር ቦታን በመለየት ወደ ተግባር ለማስገባት በቁጥር 4 ታቅዶ 3
(75%) ተፈፅሟል::

የከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ስራዎች

የከተማውን የአስተዳደር ወሰን በመለየት ቋሚ የወሰን ምልክቶች በማስቀመጥና በካርታ


ላይ ማመላከት ተችሏል፡፡ በከተሞች የአስተዳደር ወሰን ክልል ውስጥየሚገኙ የመሬት
ሀብትን በአግባቡ ለመጠቀም እንዲያስችል 282 ሄክታር ክፍት ቦታ እና በጊዜያዊነት
የተሰጠ ቦታ ቆጥሮና መዝግቦ ለመያዝ ታቅዶ 232 ሄክታር መሬት 82.5%/ መቁጠር
ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


15
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በከተማዋ ማስፋፊያና በመሃል ከተማ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል/ ለመኖሪያ፣


ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ፣ለጥቃቅንና አነስተኛ ወዘተ… 34 ሄ/ር በጨረታና 166
ሄ/ር በምደባ በድምሩ 200 ሄ/ር ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ታቅዶ 17.8 በጨረታ እና
78.4 በምደባ በድምሩ 96.2 ሄ/ር(48.1%)ለማስተላለፍ ተችሏል:: ከዚህም ውስጥ 8.8
ከመቶ ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተቋማት፣ 24.48 ከመቶ ለአምረች ኢንደስትሪና
(ኢንቨስትመንት)፣ 12.36 ከመቶ ለማህበራዊ አገልግሎት፣ 46.17 ከመቶ ለመኖሪያ ቤት

መስሪያ እና ቀሪው 5.1% ለሌሎች አገልግሎቶች የተላለፈ ነበር፡፡

በኢንቨስትመንትለተጠቃሚዎችየተላለፉቦታዎችለተፈለገውአገልግሎትጥቅም ላይ
ስለማዋላቸውክትትልበማድረግበከተማችን ታጥረው የተቀመጡ እና በውላቸው መሰረት
ያልለሙ ይዞታዎችን በመለየት ለታለመላቸው አላማ እንዲውሉ ከአልሚዎቹ ጋር
በመወያየት ወደ ስራ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ወደ ልማት መግባት ያልቻሉይዞታዎችን
ደግሞ በመንጠቅ 1.8 ሄ/ር መሬት ወደ መሬት ባንክ እንዲመለሰ ተደርጓል፡፡

በከተማችን ጥንታዊ ከተማ እንደመሆኗ መጠን በመልሶ ማልማትና ማደስ ፕሮግራም


በማልማት የከተማዋን እድገት በማሻሻል ተወዳዳሪ ለማድረግ የደቀቁ አካባቢዎችን
በመልሶ ማልማት 11.59 ሄ/ር መሬት ለማልማት ተችሏል፡፡

ከሊዝ ህጉ ጋር ተያይዞ አንዱ ምላሽ የተሰጠበት የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሰነድ አልባና ከፊል
ሰነድ አልባ ይዞታዎችን የመለየት፣የማጣራትና ሰነድየመስጠት ጉዳይ ሲሆን በሁለተኛው
እድገትና ትራንሰፎርሜሽንባለውጊዜ ውስጥ 1537 የግል ሰነድ አልባ ይዞታዎችን
በመለየት ለ 3161 ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ/ ሰነድ መስጠት ተችሏል፡፡

በተመሳሳይሁኔታጥያቄ ላቀረቡ አስተዳደራዊ ተቋማት፣ ልማት ድርጅቶች፣ በጎ


አደርጎትና ማህበራዊ ተቋማት እንዲሁም የእምነት ተቋማትን ይዞታዎች በመለየት
በከተማው ዕድገት ፕላንና ምደባ መሰረት የይዞታማረጋገጫ ሰነድ እንዲያገኙ በማድረግ
ህጋዊ የይዞታ ባለቤትነታቸውን እንዲያረጋግጡ ማድረግ ተችሏል ፡፡

በ 10 አመቱ እድገትና ትራንስፎርሜሽን ወቅታዊ የገባያ ሁኔታን መሰረት ያደረገ


የአካባቢ ቀጠና ዋጋና የቦታ ደረጃን በማሻሻል የመንግስት ገቢን ለማሳደግ 5 ጊዜ
ታቅዶ 2 ጊዜ ማከናወን ተችሏል፡፡

ለመሬት ይዞታ ምዝገባ ሥራው የቅድመ ዝግጅት አካል የሆነው የከተማ መሬት ይዞታ
መረጃ/ፋይል የማደራጀት ስራ ሲሆን በተዘጋጀው የይዞታ መዝገብ ፎርማት መሰረት
ለ 40362 ይዞታ ፋይሎች በሃርድ ኮፒ እና በሶፍት ኮፒ እንዲደራጁ በማረግ
ደህንነታቸውን በመጠበቅ ህገወጥ አሰራርን በመከላከል ዘመናዊ አሰራርን ማሳደግ
ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


16
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ይሁን እንጅ የከተማ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥራዎቻችን ውስጥ የተወሰኑ


ሥራዎች በተሻለ ደረጃ የተፈጸሙ ቢሆንም በተለይ ልማትን ያፋጥናሉ ተብለው
ለሚገመቱ ሥራዎች በቂ መሬትና የተጎሰቆሉአካባቢዎችን ሽፋን በማጥናት ከመቀነስ፣
ለመሬት ይዞታ ምዝገባ ሥራው ቅድመ ዝግጅት አካል የሆነውን የመሬት መረጃ/ፋይል
በአግባቡ ከማደራጀት እናህገ-ወጥ ይዞታን ስርዓት ከማስያዝ አንጸር የተቀመጡ ግቦች
በሚፈለገው ደረጃ የተፈጸሙ አይደሉም፡፡

እንዲሁም የመሬት ግብይት ማዕከላት /ኮርፖሬሽን/ በማቋቋም እና ከተሞች ልማትን


በሚያፋጥን፣በተረጋጋ ዋጋ፣በቀጣይነትና በቅልጥፍና የለማ መሬት የማቅረብ ስርዓትን
በመገንባት ለተለያየ አገልግሎት የሚውል በቂ መሬት በማዘጋጀት የአቅርቦቱን ቀጣይነት
ከማረጋገጥ አንጻር የመሬት ዝግጅት ሥራ ሰፊ መዋዕለ ንዋይ እና ጠንካራ የሎጂስቲክስ
አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ አሰራሩ በተቀናጀ የመሬት መረጃ ባንክ ስርዓት እና የፋይናንስ
አቅርቦት /ተዘዋዋሪ ፈንድ/ መደገፍ እንዳለበት ግልጽ የፖሊሲ አቅጣጫ ተቀምጦ የነበረ
ቢሆንም አልተተገበረም፡፡

ከከተማ መሬት አቅርቦትና ግብይት አኳያ ቦታ ከሶስተኛ ወገን ነጻ ለማድረግ


የሚጠይቀው የካሳ ወጭ እና ለመሰረተ ልማት አቅርቦት የሚያስፍልገው በጀት ከአቅም
በላይ በመሆኑ በከተማው እያደገ የመጣውን የመሬት ፍላጎት ለማስተናገድ የሚያስችል
የመሬት ዝግጅት ለማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት ተከታታይነት ያለው የቦታ አቅርቦት
ካለመኖሩና የመሬት ጨረታ ዋጋ በየጊዜው እየጨመረከመሄዱ ጋር ተዳምሮየመሬት
ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣም ይታያል፡፡ይህም የከተማው መሬት አቅርቦትና ግብይቱ
የተደራሽነትና የፍትሀዊነትችግር ያለበት መሆኑን በስፋት የሚያሳይ ሲሆን በሊዝ ይዞታ
ስሪት ትግበራ ሂደቱም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳደረሯል ፡፡

በአጠቃላይ የከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ጉዳይ ትልቅ የሌብነትና የመልካም


አስተዳደር ችግር የሚታይበት በመሆኑ ከችግሩ ለመውጣት የሚያስችል የመሬት
ዝግጅትና አቅርቦት ስልት በመከተል፣ ለተጠቃሚዎች የተላለፈው መሬት በአግባቡ
ጥቅም ላይ እንዲውል ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል በማድረግ፣ ወደ ልማት ያልገባውን
ፈጥኖ በመንጠቅ መልሶ ለግብይት እንዲውል በማድረግ፣ የህገ-ወጥ ግንባታን እና መሬት
ወረራን በመከላከልና በማስወገድ በአንድ በኩል የህግ ተፈጻሚነትን ማጠናከር በሌላ
በኩል ደግሞ የመሬት አቅርቦቱን ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ በቀጣይ የሁሉንም
ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡

 መንገድ እና መሰረተ- ልማት ስራዎች

10 2013 -2022 / Page


17
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በዕቅድ ዘመኑ የማኀበራዊና አካባቢ ደህንነትን መሠረት ያደረገና የጥራት ደረጃውን


የጠበቀ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ግንባታየተከናወኑ ሲሆንከነዚህም ውስጥ
ዋናዋና ዎቹ ጠጠር መንገድ 146.9 ኪ/ሜ ለመገባት ታቅዶ 166.9 ኪ.ሜ ተገንብቷል፣
ጠጠር መንገድ ጥገና 131 ኪ/ሜ ታቅዶ ክንውን 92.59 ኪ.ሜ ተፈጽሟል ፣ አዲስ
መንገድ ከፈታ 370 ኪ/ሜ ታቅዶ ክንውን 113.21 ኪ.ሜ ፣ የድጋፍ ግንብ 8000 ሜ/ኩብ
ታቅዶ ክንውን 5909.7 ሜ/ኩብ ፣ 6000 ሜ/ኩብ ካናል ለመስራት ታቅዶ ክንውን 3849
ሜ/ኩብ ፣ በቁጥር 31 ካልቨርት ጥገና ታቅዶ ክንውን 18 ፣ ኮብልስቶን ጥገና 30000
ካ/ሜ ታቅዶ 22933.17 ካ/ሜ እንዲሁም አስፋልት መንገድ ስራ 15.24 ኪ/ሜ ታቅዶ 2
ኪ/ሜ ተከናውኗል፣ አዲስ ኮብልስቶን ግንባታ 93.4 ከ/ሜ ታቅዶ 93.41 ተከናውኗል፣
ድልድይ ግንባታ በቁጥር 61 ታቅዶ 61 ድልድይ መገንባት ተቸሏልእንዲሁም የውስጥ
ለውስጥ መብራት ዝርጋታ 27 ኪ/ሜ፣ መማከናወን ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በከተማችን የሚገነቡ የመሰረተ ልማት ስራዎችከህብረተሰቡ ከሚያነሳው


የልማት ጥያቄዎች አንጻር ተደራሽ ለማድረግ ብዙ ያልተሰራና የተሰሩትምየጥራት
ችግር የሚስተዋልባቸው በመሆኑ ለረጅም ጊዜ የማገልገል እድላቸው ዝቅተኛ
በመሆኑበቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አለበት፡፡

 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ሬጉላቶሪና አቅምግንባታ


የግንባታ ዘርፉን የሰው ሀይል ልማት በስልጠና አመለካከቱን በማስተካከልና ክህሎቱን
በማሳደግ የማሰፈፀም አቅሙን ለማጎልበት እንዲቻል ከምዘና ማዕከላት ጋር በቅንጅት
በመስራት በ 10 አመቱ ባለሙያዎችን ምዘና የሚያደርጉ 40 መሪ መዛኞችን ለማፍራት
ታቅዶ 34 (85%) መሪ መዛኞችን ማፍራት ተችሏል ፡፡ለ 525 ባለሙያዎች ቅድመ
ምዘና ምዝገባ ለማድረግ ታቅዶ ለ 365 (ከ 69.5%) ምዝገባ ተድርጓል፡፡ለ 1072
አነስተኛና መለስተኛ ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ለማድረግ ታቅዶ 626 (58.4%)
ባለሙያዎች የተመዘኑ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 418(69.7%)
አነስተኛናመለስተኛባለሙያዎች የብቃት ምዘናውን አልፈው የምስክር ወረቀት
መውሰድ ችለዋል፡፡

የካባ ቦታዎች ዝግጅት እና ማልማት ስራዎችን በቁጥር 17 የካባ ቦታዎች ለማዘጋጀትና


ለማልማት ታቅዶ 16(94.12%)ቦታዎችን በማዘጋጀት 2 ቱ እንዲለሙ ተደርጓል፣
ሌላው የግንባታ ማቴሪያል ጥራት ፍተሻን በተመለከተ ከደንበኞች በሚቀርቡ የፍተሻ
ጥያቄዎች መሰረት ለ 19 የተለያዩ ዓይነት የግንባታ ግብዓቶች ፍተሻ ለማድረግ ታቅዶ
15 (79%) የፍተሻ ስራ መስራት ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


18
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በመንግስት በጀት ለሚሰሩ 17 ሕንፃዎች የውለታና የንድፍ ዝግጅት እንዲሁም በግንባታ


ሂደት የቁጥጥርና ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ታቅዶ ለ 13 (76.5%) ፕሮጀክቶች ድጋፍ
ተደርጓል፡፡

የግንባታ በዘርፉ ለተሰማሩ 1200 አዲስ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎች ምዝገባ ለማድረግ


ታቅዶ ለ 1000 ባለሙያዎች ምዝገባ ተደርጓል፡፡ ለ 40 የስራ ተቋራጮችና ለ 10
የአማካሪ ድርጅቶች የድጋፍና ኢንስፔክሽን ስራዎችን ለማከናወን ታቅዶ ለ 26 (65%)
የስራ ተቋራጮችና ለ 7 (70%) የአማካሪ ድርጅቶች ድጋፍና ኢንስፔክሽን
ተደርጎላቸዋል፡፡

ይሁን እንጅ የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦትና በምርምር የተደገፈ ቴክኖሎጅ ሽግግር


እንዲኖር ከማድረግ አንፃር እና የኮንስትክሽን መሳሪያ አቅራቢ ድርጅቶች ዘመናዊ
የኮንስትራክሽን አመራርና አደረጃጀት (ISO 9001/2015) እንዲኖራቸው እና ዓለም
አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ድጋፍና ዕገዛ ከማድረግ አኳያ የታቀዱ ተግባራት
ያልተከናወኑ ናቸው፡፡

እንዲሁም የባለሙያዎችየብቃት ምዘና፣ አነስተኛና መለስተኛ ባለሙያዎችን ከፍ


ወደአለ ደረጃ እንዲያድጉ የማድረግና የኩባንያ ትብብር ስልጠና አፈፃፀም ዝቅተኛ
ነው፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች፣ በምዘና ማዕከላት፣
በቴ/ሙ/ኢ/ል/ ቢሮ እና በየከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ መካከል ያለው
የቅንጅት ችግር (ሌሎች አጋር አካላትንማስተባበር) አለመቻሉ፤እንዲሁም
የመለስተኛና አነስተኛ ባለሙያዎችን የምዘናና የማብቃት ስራ ለመከታተል እና
በግንባታው ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ በጀት አንዱ ችግር ነው፡፡

ከግንባታ ፍቃድና እድሳት ጋር በተያያዘ በባለፉት 10 አመታት ለ 9,928 የፕላን


ስምምነቶችን፣ 9,658 ፕላኖችን ለመመርመርለ 9,781 ፕላኖችን ለማጽደቅና የግንባታ
ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ 8,284 ፕላን ስምምነቶችን ፣ ለ 7,996 ፕላን ምርመራ እና
ለ 7,591 ፕላን ማጽደቅና የግንባታ ፈቃድ መስጠት ተችሏል፡፡

 በቤቶች ልማት አስተዳደር ስራዎች

የመንግስት ቤቶችን (በአዋጅ 47/67 የተወረሱና በከተሞች በመንግሰትና በህዝብ የተገነቡ ቤቶች)
የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲኖራቸው ክትትልና ድጋፍ የማድረግ ተግባር የተከናወነ ሲሆን
በዚህም መሰረት ለ 4737 ለመግስት ቤቶች እና 1555 ለዝቅተኛ ነዋሪ ቤቶች ካርታ
ለመስጠት ታቅዶለ 3398 ለመግስት ቤቶች 2754/81%/ የዝቅተኛ ነዋሪ ቤቶች ካርታ/
ሳይት ፕላን/ መስጠት ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


19
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በከተማችን የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤት ችግሮች ለመቅረፍ የተለያዩ የቤት አማራጮች ከማቅረብ


አንጻር እቅድ በግል 230፣ በቤት አልሚዎች 181፣ በማህበር 2400 በቤቶች ልማት 186
እንዲሁም ለዝቅተኛ ኗሪ ቤት ግንባታ 1760 ድምር 2397 ቤት ለመገባትና ለማስተላለፍ
ታቅዶ በግል 310፣ በቤት አልሚዎች 188፣ በማህበር 66፣ በቤቶች ልማት/የድርጅትና መኖሪያ/
186 እንዲሁም ለዝቅተኛ ኗሪ ቤት ግንባታ 278 ድምር 1028/42.8%/ ቤቶች ተገንብተው
ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፉ ተደርገዋል፡፡

በአጠቃላይ የመንግስት ቤቶችን የይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው በማድረግ በህገ ወጥ መንገድ


ወደ ግለሰብ እንዳይዞሩና እንዳይሸጡ ከማድረግ አንጻርና ለከተማው ማህበረሰብ የተለያዩ የቤት
አማራጮችን በመገንባትበተለይም ለዝቅተኛና ለመካከለኛ ገቢ ላላቸው የቤትፍላጎትን ከማሟላት
አንጻርብዙ የሚቀርና ያልተሰራበት ሲሆን በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶች የመንግስት
ቤቶች አስተማማኝ ጥበቃና የህዝቡን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አባራጭ የት
ፍላጎቶች በስፋት ሊሰራባቸውይገባል፡፡

የጽዳት፣ አረንጓዴ ልማትና ውበት ስራዎቻችን

በከተሞች ቆሻሻን ከምንጩ በመለየት እና መቀነስ መልሶ በመጠቀም እንዲሁም


አረንጓዴ፣ ፅዱ፣ ውብና ማራኪ በማድረግ ለኑሮ ተስማሚ እና ለጎብኝዎቻቸው
የሚመቹ እንዲሆኑ ከማድረግ አኳያ ባለፉት ሁለት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
ዘመናት የፅዳትና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን ለማስፈፀም የሚያስችሉ የደረቅና ፍሳሽ
ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስልት ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ አይበገሬ የአረንጓዴ ልማት
ስትራቴጂዎች እና ስትራቴጂዎችን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ደረጃዎች እና
መመሪያዎች (ማኑዋሎች) ተዘጋጅተው ወርደው ስራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ በነዚህ
ሰነዶች ላይም በየደረጃው ለሚገኙ የከተማ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና
ተሰጥቷል፡፡

ከደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ማሻሻያ ሥራዎች አንዱ በከተማ
ፅዳትና ውበት ስራዎች ዙሪያ የተለያዩ የንቅናቄ ሰነዶችን በማዘጋጀትና የከተማውን
ህዝብ በማወያየት በአብዛኛው ከተሞች የጽዳት ቀን ተወስኖ ነዋሪው ሰፈሩንና
አካባቢውን እንዲያጸዳ በማድረግ በፅዳት ስራው በላቀ ደረጃ እንዲሳተፍ ማድረግ
ተችሏል፡፡በዚህም ለ 15000 (ወንድ 7000 ሴት 8000) የህብረተሰብ ክፍል ግንዛቤ
በመፍጠር 14500(ወንድ 6960 ሴት 7540) ወይም 96.6 በመቶ የህብረተሰብ ክፍል
በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስራ ላይ በቀጥታ እንዲሳተፍ ተደርጓል፡፡

ውጤታማ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ሥርዓት ከመፍጠር አንፃር


በከተማው 1 ዘመናዊ እና 10 ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎችን ለማዘጋጀት

10 2013 -2022 / Page


20
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ታቅዶ ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ግንባታ ያልተከናወነ ሲሆን 4 ወይም (40%)
ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ መጣያ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል፡፡በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ
በከተማው የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ ሽፋንን 90 ከመቶ ለማድረስ ታቅዶ
ከተመረተው ደረቅ ቆሻሻ ውስጥ 65.8%፣በተዘጋጀላቸው የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ላይ
በአግባቡ ማስወገድ ተችሏል፡፡

ሌላው በፕላን የተመላከቱ የአረንጓዴ ቦታዎችን በመለየት የይዞታ ካርታ እንዲሰራላቸው


ከማድረግ አንጻር 147 ቦታዎች ላይ ታቅዶ 76 ቦታዎች ካርታ የተሰራላቸው ሲሆን

አፈጻጸሙ 37.2% ነው ፣ በአዲስ አረንጓዴ ልማት ስራ 42 ሄ/ር መሬት ለማልማት

በዕቅድ ተይዞ 39.5 ሄ/ር መሬት በአዲስ እንዲለማ ተደርጓል፡፡

ይሁን እንጅ በቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ላይ ከሰራናቸው ይልቅ የሚቀሩት ስራዎችና

አስከፊ ገፅታዎች ጎልተው የሚታዩ በመሆኑ የተቀናጀ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አያያዝና

አወጋገድ ስርዓት ላይ ተገንብቶ የነበረው የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ ፕሮጀክት በክትትል


ማነስ መክኗል፡፡

አመራሩም ሆነ ባለሙያው በቂ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ባለመሆኑ ህብረተሰቡን እና


ባለድርሻ አካላትን በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ በማሣተፍ፣ የተደራጁ ማህበራትን
በመደገፍና በማብቃት፣ እንዲሁም ቆሻሻን የሚጠየፍ ህብረተሰብ በመፍጠር በኩል
ውስንነት ያለ ሲሆን ህብረተሰቡም ቢሆን ደረቅ ቆሻሻ በየአካባቢው ሲጣል እያየ
የተለመደ አድረጎ የሚቆጥርና ቆሻሻን የመጠየፍ ባህሉ የዳበረ ባለመሆኑ በመኖሪያና
በሥራ ቦታዎች አካባቢውን ውብ፣ ጽዱና ሳቢ በማድረግ በኩል የድርሻው እየተወጣ
አይደለም፣በአረንጓዴ ልማት ላይም ቢሆን ውብ መናፈሻዎችና የመንገድ ዳርቻ
ቦታዎችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩበማፋፋት እንዲዘጋጁ ከማረግ አንጻር ውስንነት
አለ፡፡

 የትራንስፖርት ዘርፍ ስራዎች፤

የትራንስፖርት ስምሪትመስመሮችን ሽፋን ይሰጥ ከነበረው በ 2012 ዓ.ም ወደ 43


የደረሰ ሲሆን በእነዚህ የስምሪት መስመሮች በከተማዉ ባሉ መስመሮች ተደራሽነቱን
በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ፍትሃዊና ቀልጣፋ የስምሪት አገልግሎት ለመስጠት
ተችሏል፡፡በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ታክሲ አነስተኛ አውቶብስ (ሚኒባስ) 585 ፤ባለ 3
እግር ሞተር ብስክሌት (ባጃጅ) 711 ፣ ባለ 4 እግር ኪዉትና ሱዚኪ 129፣ ላዳ 3 ድጋፍ
ሰጭ 11 አዉቶብስ 5 በድምሩ 1444 ተሸከርካሪዎች በ 6 የህዝብ ትራንስፖርት
ማህበራት ተደራጁተው አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን እነዚህ ተሸከርካሪዎች በተከፈቱ

10 2013 -2022 / Page


21
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የህዝብ መጓጓዣ መስመሮች ላይ 91,510,740 ተሸከርካሪዎችን በድግግሞሽ ስምሪት


ለመስጠት ታቅዶ 76,534,069 ተሸከርካሪዎች ስምሪት ተሰጥቷል ይህም ከእቅዱ
83.63% ተፈጽሟል ፡፡

ሌላው ከተማው አማራጭ የመናኸሪያ አገልግሎት ባለመኖሩ የህበረተሰቡን ጥያቄዎችና


አገልግሎት ፈላጊዎችን ማርካት አልተቻለም፣ ነግር ግን በከተማ አስተዳደሩ ተነሳሽነት
የገራዶ መናኸሪያና የሰኞ ገበያ መናኸሪያ ለማሰራት ጅምር ስራዎች አሉ፡፡በባለፉት
አመታት በከተማው 10 መኪኖች ማቆሚያ (ተርሚናል) ለመገንባት /በእቅድ የተያዘ
ቢሆንም ለስራዉ ትኩረት ያልተሰጠዉ እና የፋይናን እና የቦታ እጥረት በመኖሩ
ምክንያት ተግባሩን ማከናወን አልተቻለም፡፡

ለመንገድ ትራፊክ አደጋ መንስኤ የሚሆኑ አደገኛ ቦታዎች በጥናት በመለየት አደጋን
ለመከላከልና ለመቀነስ 145 ምልክትና ማመልከቻ ለመትከል ተችሏል፣ እንዲሁም በ 10
አመቱመጨረሻ 2 የትራፊክ መብራት ተሰርተዉ ስራ ጀምረዋል፡፡ የእግረኛ ማቋረጫ
ዜብራ መስመሮችና የተጓደሉ የትራፊክ ምልክትና ማመልከቻዎችን የእግረኛ መንገድ
በመለየት እንዲሟሉ ለማድረግ ተችሏል፡፡በአጠቃላይ የተሻሉት አፈጻጸሞች እንዳሉ
ሆኖ በከተማው ወሰን ክልል ውስጥ ነባርና አዳዲስ አካባቢዎች ላይ የትራንስፖርቱን
አገልግሎት ያልደረሰባቸውን ቦታዎችን በመለየት ተደራሽ ማድረግ፣ የትራፊክ
አደጋዎችን ለመቀነስ ከግንዛቤ ፈጠራ አንስቶ የአሽከርካሪና ተሸስከርካሪ ብቃትን
ማሳደግ አማራጭ መንገዶችን መጠቀም ፣የደረቅ ጭነት መኪና ማቆሚያና የህዝብ
ማመላለሻ መናኸሪያዎች ግንባታ በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል፡፡

10 2013 -2022 / Page


22
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 የኢንቨስትመንት ዘርፍ ተግባራት

ኢንዱስትሪዎችን ከማበረታቻ ስራዎች አንጻር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ለባለሃብቱ

ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንዱ ከጉምሩክ ቀረጥነጻ ማበረታቻ ተጠቃሚ በማድረግ

የኢንቨስትመንት አቅማቸውን በማሳደግ የባለሃብቶችን ውጤታማነት ከፍ ማድረግ ዋናው

ተግባሩ ነው፤በዚህም መሰረት በባለፉት 10 አመታት ለባለሀብቶች ከቀረጥ ነጻ ማበረታቻ

ለመስጠት ታቅዶ ለ 183 በሆቴል፣ በጨርቃጨርቅ ፣ በብረታ ብረት ወዘተ ዘርፍ ለተሰማሩ

ባለሀብቶች ከቀረጥ ነጻ ማበረታቻ ለመስጠት ተችሏል፡፡ እንዲሁም የከተማችን ምቹ ሁኔታ


የሀብት ምንጮች በማስተዋወቅ ለባለሀብቶች የሚሰጡ አገልግሎትእና ወደ አፈፃፀም
የሚገቡፕሮጀክቶችን በመለየትና በማስተዋወቅ ለ 495 የኢንቨስትመንት ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡

በኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጅው በተቀመጡ ዕድገት- ተኮር በሆኑና ለኢኮኖሚ

ግንባታውም ሆነ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የላቀ ጠቀሜታ ላላቸው እንዲሁም የግብርናውን

ምርት በግብዓትነት ለሚጠቀሙ አምራች ኢንዱስትሪዎች / በአግሮ ፕሮሰሲንግ/ ፣በጨርቃ

ጨርቅ፣አልባሳትና ቆዳ እንጨትና ብረታ ብረት ላይ ለመሰራት ከተማው ለዚህ ምቹ

በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በከተማው 91 አነስተኛ፣52 መካከለኛ እና 10 ከፍተኛ በአጠቃላይ

በድምሩ 152 አምራች ኢንዱስትሪዎች በማቋቋም አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ

ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ በከተማው ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት እድገት ለማሳደግ በዘርፉ ምቹ

ሁኔታን በመፍጠር ባላሃብቱን ከመሳብና ከማሳተፍ አንጻር ውስንነት ስላለ በቀጣይ ትኩረት

ሊደረግበት ይገባል፡፡

አገልግሎት አቅርቦት አስተዳደር ተግባራት

ቅድመና ድህረ ምርመራ የተደረገላቸው እንሰሳት ለእርድ ከማቅረብ አንጻር 65745 ታቅዶ
49797 የተከናወነ ሲሆን አፈጻጸሙ 75.74% ነው፡፡በጨው ተዘጋጅቶ ወደ ቆዳ ፋብሪካ የበሬ
ቆዳ ከመላክ አንጻር 35100 ታቅዶ 23440 እንዲላክ የተደረገ ሲሆን አፈጻጸሙ 66.8 %
ደርሷል፡፡

10 2013 -2022 / Page


23
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የገበያ ማእከላትን ከማሳደግና ከማስፋፋት እንጻር በባለፉት 5 አመታት 1977 ሸዶችን


ለመገንባት ታቅዶ 1654 ሸዶች የተገነቡ ሲሆን አፈጻጸሙ 83.6% ነው፣በተጨማሪም
በከተማው 5 የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን በመግዛት ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡና
ለከተማው በገቢ ምንጭነትም እንዲያገለግሉ ማድረግ ተችሏል፡፡

ይሁን እንጅ ዘርፉ በክልል መዋቅር የሌለው በመሆኑ እንደ ከተማ ሰፊ አገልግሎት የሚሰጥ
እንደ መሆኑ ትኩረት ያልተሰጠውና እንደ ከተማችንም አገልግሎት ሰጭ ተሸከርካሪዎች/
እሳት አደጋ፣ቄራ የከተማ አውቶብስ/ ፣የቄራ ማእከል አገልግሎት የሚሰጡት ለረጅም
አመታት በጥገና ስለሆነ ከከተማው እድገትና ፍላጎት አንጻር የሚፈለገውን ያህል ማርካት
ያልተቻለ በመሆኑም በቀጣይ የእቅድ አካል አድርጎ አሰራሩን ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡

ህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች

በከተማችን በህብረተሰቡና በመንግስት በጋራ የተከናወኑ የአካባቢ ልማት ስራዎችና


ፕሮጀክቶች፡-ካናል ጠረጋ፣መንገድ ከፈታና ጎርፍ መከላከል ስራ፣የፅዳት ዘመቻ፣ችግኝ
ተከላ፣ጠጠር መንገድ ግናባታና ጥገና፣የጋራ መፀዳጃ ቤት ስራ፣ካልቨርት ስራ፣ጋቢዎን ስራ ና
የዝቅተኛ ኗሪ ቤት ስራ የተከናወኑ ሲሆን በዚህም ስራ፣50%የህብረተሰቡ አስተዋጽኦ
እንዲኖረው ለማድረግ ታቅዶ በጥሬ ገንዘብ 12231630 ብር፣ በጉልበት 39701280
ብር፣በቁሳቁስ 11045150 ብር እና በእውቀት 5071785 ብር በድምሩ 57004695 ብር
የሚገመትገንዘብ ለልማት ስራዎች አስተዋጾ አድርጓል፡፡ በዚህም ወንድ 542441 ሴት
588722 በድምሩ 1131163 የህብረተሰብ ክፍል ተሳትፏል፡፡ በመሆኑም የህብረተሰብ
ተሳትፎ ድርሻን በአማካይ 50% ተሳትፎ ድርሻ ማድረስ ተችሏል፡፡

2.2.3ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ተግባር አፈጻጸም


 ግብርናና መሬት አስተዳደር ተግባራት
 የኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ዘርፍ አፈጻጸም
10 2013 -2022 / Page
24
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ተሳትፎአዊ የግብርና ኤክስቴንሽን ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ በግብርና ሥራ የተሰማራውን


የኀብረተሰብ ክፍል የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶ እየተሰራ ሲሆን. የአርሶ
አደር ሥልጠና፤ በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ተቋማትና በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ ላይ
ለአባወራ፣ለእማወራ፣ለባለ ትዳር በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመንቶችና ወጣቶች
በድድግሞሽ 2150 ለመስጠት ታቅዶለ 4578 የተሰጠ ሲሆን አፈጻጸሙም የተሸለ መኆኑ ነው፡፡
በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች ማለትም ለቀበሌ 80 (68.4%ለመምሪያ 52 (89%) በአጠቃላይ
132 (76%)የተለያዩየ ፓኬጅ ሥልጠናዎች በድግግሞሽ ተሰጥቷል፡፡

የግብርና ኤክስቴንሽን አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ከማድረግ አንጻር 4213 አባወራ 1232
እማወራ 4213 ባለትዳር ሴቶች 2193 ወጣቶች 6660 የኤክስቴንሽን የምክር አገልግሎት
ለመስጠትታቅዶ በድግግሞሽ 5445 ወይም ከዕቅድ 82% የሚሆኑ አርሶአደሮችን የኤክስቴንሽን
ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላትን ማጠናከርና ውጤታማ ማድረግ፤ 4 የአርሶ አደር ማሰልጠኛ
ተቋማት በአዲስ ለመገንባት ታቅዶ ክንውን አንድ 25%የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት ደረጃ
ማሳደግን በተመለከተ ባላቸው ቁመና መሰረት ከቅድመ ወደ መሠረታዊ 5 ታቅዶ 4
(80%)፣ተከናውኗል፡፡

የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት ማሣያ መሬት ለማሟላት 6 ታቅዶ 2 በመፈፀም ከዕቅዱ በታች
የተከናወነ ሲሆን አብዛኛዎቹየአርሶአደር ማሰልጠኛ ተቋማት የመሬት ይዞታቸዉ ከደረጃ በታች መሆኑን
ነው፡፡

ካለፉት ዓመታት 59 ሰርቶ ማሣያ ውስጥ በአርሶ አደር ማሣ 48 (88%) ፣በአርሶአደር ማሰልጠኛ
ማዕከላት 5 (ከ 100%)፣በድምሩ 53 (89%) የሚሆኑ ሰርቶ ማሳያዎች በሰብል ልማት፤ በእንስሳት
ሀብትልማት፤ በተፈጥሮ ሀብት፤በመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ማከናወን ተችሏል፡፡

ስርዓተ ምግብ ተኮር ግብርና ባልተመጣጠነ የአመጋገብ ስርዓት ችግር ምክንያት የህፃናት መቀንጨር
እንደ ሃገርም ሆነ እንደ ክልል ያለ በመሆኑ መምሪያውም ይኸው ችግር ሰለሚንፀባረቅ
ለመቅረፍ 1000 የሚሆኑ የቤተሰብ ኃላፊዎች የተመጣጠነ ምግብ ለመመገብ የሚያስችላቸዉን
እንዲያመርቱና እንዲመገቡ ለማድረግ ታቅዶ በተደረገዉ እንቅስቃሴ 745 ወይምከዕቅዱ 74.5%
መፈፀም ተችሏል፡

የገጠር ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ፤በ 2 ኛው የእድገትና ተራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን 922 ለሚሆኑ
ወጣቶች በተለያዩ የግብርና ዘርፎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ 275 (30%) በቋሚና በጊዜያዊ
የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡

10 2013 -2022 / Page


25
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ይሁንእንጂ የኤክስቴንሽን ስርፀቱንና ያመጣዉን ዉጤት በየጊዜዉ በማረጋገጥ ረገድ ጉድለቶች


ተስተዉለዋል፡፡በቀጣይመስተካከል ያለባቸው ችግሮች የሚታቀዱ የልማት ተግባራት በሥርዓቱ
መሰረት ህብረተሰቡን በበቂ ሁኔታ ያላሳተፉ መሆን፡የጠባቂነት መንፈስ መኖር፤ያልተደረሱ አርሶ
አደሮችን ትኩረት ሰጥቶ አለመስራት፣የኤክስቴንሽን አተገባበሩና የማበረታቻ ስርዓቱ በተቀመጠው
አሠራር መሠረት ተግባራዊ አለመሆኑ እና በልማት አካላት መካከል ያለው ግንኙነት ዝቅተኛነት
ክትትልና ግምገማ አለመኖርና በየደረጃውየተሰጡ ግብረመልሶችን ተግባራዊ አለማድረግ፣የአርሶአደር
ማሰልጠኛ ማዕከላትን ቋሚ የቴክኖሎጅ ማስተላለፊያና የመረጃ ማዕከል አለማድረግናየተሻሻሉ
ቴክኖሎጂዎች አተገባበር ላይ የክህሎት ክፍተት መኖርና የባለሙያዎች የተግባቦት እና የማሳመንአቅም
ውስንነት፣የከተማ ግብርና አደረጃጀት ለሥራምቹ አለመሆን፣የተጠናከረ የገበያ እና የግብርና
ኤክስቴንሽን አገልግሎት አለመስጠት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የሰብል ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ የነበረ አፈጻጸም

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በመኽር


ሰብል የተሰሩ አንጻር በዋና ዋና የምግብ ሰብሎች 3929 ሄ/ርየእርሻ መሬት በማልማት

80457.45 ኩ/ልምርትየተገኘሲሆንምርታማነቱም 20.4 ኩ/ል በሄ/ርነበር፡፡ምርትና

ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ግብዓቶችንና የተሻሻሉ አሠራሮችን አሟጦ በመጠቀም

የመረሀ ግብሩ መጨረሻ ምርትዘመን 73604 ኩ/ል ምርት ለማድረስ ታቅዶ 2953.5

ሄ/ርየእርሻ መሬት በማልማት 58261 ኩ/ልምርት ለማምረት ተችሏል።ምርታማነት


በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽንምርት ዘመን ከነበረበት 19 ኩ/ል በሄ/ር ወደ 24
ኩ/ል በሄ/ር ዕድገት አሳይቷል፡፡

የበልግ ሰብል ልማት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ባሉአምስት ቀበሌዎች

የበልግ ወቅት ሰብል ማምረት የሚያስችል በመሆኑ በሁለተኛው የእድገትና

ትራንስፎርሜሽን ዘመን የዕቅድ መነሻዓመት 2008 ዓ.ም 1656.5 ሄ/ር መሬት በማልማት

ወደስራ የተገባ ቢሆንም በወቅቱ ባጋጠመው የተፈጥሮ አደጋ ምክኒያት ምርት አልተገኘም፡፡

10 2013 -2022 / Page


26
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በዕቅዱ መጨረሻ ዓመት በ 2012 ዓ.ምወደ 3570 ሄ/ር በማሳደግ 52468 ኩ/ል ለማምረት

ታቅዶ 3090 ሄ/ር በማልማት 45475 ኩ/ልተገኝቷል፡፡

የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት) የአፈር ለምነትን በማሻሻል፣እርጥበት የመያዝ አቅምን

በማሳደግና የአፈር ጤና እንዲጠበቅ በማድረግ የሰብል ምርታማነት እድገትን ዘላቂ

ከማድረግ አንፃር፤ 25000 ሜትር ኩዩብ ለማድረስ ታቅዶ 18500 ሜ/ኩ ወይም የዕቅዱ

74% ለማሳካት ተችላል፡፡.ይሁን እንጂ ካለው የእርሻ መሬት ስፋት አንፃር ሲታይ

አነስተኛነው፡፡

የሰብል ጥበቃ ሥራዎች፤ ቅንጨ፣ቦረን፣አቀንጭራ፣የኑግ አንበሳና የጅብ ራስ የመሳሰሉት

መጤና ጥገኛ አረሞችን ለመከላከል 3551 ሄ /ርመሬት ታቅዶ 2921 ሄ/ር መሬት በማረም

ለመከላከል ተችሏል፡፡

ይሁን እንጅ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት ያለባቸው ተግባራት የሰብል ምርትና

ምርታማነት በሚፈለገው መልኩ አለማደግ፤ለገበያ የሚቀርቡ ሰብሎችን በኩታ-ገጠም

የአመራረት ዘዴ በተሟላ ሁኔታ አለመፈጸም የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች አቅርቦትና

ስርጭት የተሳለጠ አለመሆን፤የተቀናጀ የአፈር ለምነት ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎችን

በስፋት፤ለማስፋት ስትራቴጂ ትኩረት ሰጥቶ በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ

አለማድረግ፤በሰብል ልማት የሚካሄዱ ስረቶማሳያዎችን ውጤታማ እንዲሆኑ ትኩረት

ሰጥቶ አለመስራት፤ለአግሮ ኢንዱስትሪዎች የሚቀርብ የሰብል ምርት ማምረት በቀጣይ 10

አመት በትኩረት መስራት ይጠይቃል፡፤

የመስኖ ልማት ከማስፋትና ምርትና ምርታማነትን አፈጻጸም

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የመስኖ ልማት ስራ በከፍተኛ ተነሳሽነትና


ቁርጠኝነት የከተማ አስተዳደሩ አርሶ አደሮች የተሸለ አፈፃፀም እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

በመስኖየሚለሙሰብሎች አጠቃላይ የምርታማነት እድገት 115668 ከተመዘገበው 56.04 ኩ/ል በሄ/ር


ወደ 68 ኩ/ል በሄ/ር ወይም የ 11.96% እድገትተመዝግቧል። ይህም መድረስ ከነበረበት 122 ኩ/ል
በሄ/ር ሲታይ አፈጻጸሙ 55.7% ላይ ይሆናል።

10 2013 -2022 / Page


27
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በመስኖ የሚለሙ ሰብሎች ስብጥር ከዓመት ዓመት ገበያ ተኮር ሰብሎችን ለይቶ ከማልማት አንጻር
እየተሻሻለ መጥቷል። በ 2011 ዓ.ም የመስኖ ሰብል ስብጥር አዝርዕት 48.4%፣ አትክልት 41.97%፣
ቅመማ ቅመም 2.3%፣ ጥራጥሬ 2.3%፣ ቋሚ ሰብል 2.311% የመሬት ሽፋን አላቸው፡፡ በዚህም
አርሶ አደሩ ገበያ-ተኮር ወደሆኑ የቡና፣ አትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን ማምረት እየተቀየረ መሆኑን
ያሳያል፡፡ በዋናነት በየጊዜው ለባለሙያዎችና አርሶ አደሩ የተሰጡ የአቅም ግንባታ ሥራዎችና በከተሞች
አካባቢ በተፈጠረው የአመጋገብ ባህል መዳበር የተፈጠረዉ የገበያ ዕድል አበረታች እንደነበረ ያሳያል።
ስለሆነም በመስኖ የሚለሙ ሰብሎች ምርታማነት በአማካኝ 120 ኩ/ል በሄ/ር ወይም ከመኸር
ምርታማነት ጋር ሲነፃፀር በ 13% ብልጫ መኖሩን ያሳያል።

በአጠቃላይ በዕድገትና ትራንስፎፎርሜሽን እቅድ ዘመን የመስኖ ልማት እንቅስቃሴ እያደገ የመጣ
ቢሆንም በርካታ ችግሮች ያሉበት መሆኑ ይታያል፡፡ ይህም የተለያዩ የውሀ ማግኛ ቴክኖሎጂዎችን
አለመጠቅሞ እና ባህላዊ የሆነውን መስኖ አሠራር ወደ ዘመናዊ ዘዴ የመቀየር ሂደት ብዙ ርቆ
አለመሄዱ ብሎም የክትትልና ድጋፉ ተግባር አናሳ መሆን ናቸው፡፡ በመስኖ ከለማው መሬት ውስጥ
በዘመናዊ መንገድ እየለማ ያለው ከ 325 ሄ/ር ወይም ከ 10% አይበልጥም፡፡ በተለያየ የውሀ ዕቀባ ዘዴ
የዝናብ ውሀን በማቆር ለመስኖና ለልዩ ልዩ አገልግሎት የማዋል፣ በመስመር መዝራትና ውሀ በቦይ
የማጠጣት ልምድም እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ከተለምዶ አሰራር አለመዉጣትና አማራጭ የዉሃ
አቅሞችን አለመጠቀምና የፓኬጅ አሰራሩን አለመተግበር ምክንያት በተፈለገው ደረጃ መድረስ
አልተቻለም፡፡

የመስኖ መሬትን m ልክዓ ምድራዊ አቅጣጫን በሚያሳይ በመለካት ባለፉት አምስት ዓመታትአጠቃላይ
በመስኖ የለማው የመሬት ሽፋንበ 2153.5 ወደ 649 ሄ/ር 68.3% ቀንሷል።

አነስተኛመስኖመሰረተልማትማስፋፊያ አፈጻጸም

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን 8 ነባርና አዲስ አውታሮችን በመገንባትና


ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በማስተላለፍ ከ 628 ሄ/ር መሬት በላይ ወደ ልማት
ማስገባትበዚህ ዘርፍ አ/አደሩ የመጠቀም ልምዱና ፍላጎቱ ከዓመት ዓመት እየጨመረ
መጥተቷል።ይሁን እንጂ በመምሪያ ደረጃም እራሱን የቻለ ባለሙያ ባለመኖሩና በውክልና
የሚሰራ በመሆኑ ወደስራ የሚያስገባ ስልጠና በበጀት እጥረት ምክንያት መስጠት
ባለመቻሉ በአጠቃላይ በስራዉ ጥራት፣ ውጤታማነትና ወቅታዊነት ላይ ችግሮች
ተስተዉሏል፡፡

የግብአትና ቴክኖሎጅ አፈጻጸም

10 2013 -2022 / Page


28
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አንዱና


ዋነኛወ የግብአትና ቴክኖሎጅአጠቃቀም ሲሆን ለመኽር የአፈር ማዳበሪያ 4658 ኩንታል
ታቅዶ 8795 ኩ/ል ከእጥፍ በላይ ሊቀርብ ችሏል፡፡ ለመስኖ 657.5 ኩንታል ታቅዶ 252.5
ኩ/ል 38.4% ማዳበሪያ ቀርቦ ተሰራጭታል፡፡

ምርጥ ዘር ለመኸር 1814.4 ኩንታል ታቅዶ 200.5 ኩ/ል 11.5% እና ለመስኖ 145 ኩንታል
ታቅዶ 61.25 ኩ/ል 42.2% ለማከናውን ተችላል፡፡ አትክልትና ፍራፍሬ ዘር ለመስኖ 33.17
ኩንታል 27.32 ኩ/ል 82.36 % ለማቅረብ ተችላል፡፡ ፕላስቲክ ምንጣፍ ለመስኖ 160
ኩንታል ታቅዶ 72 ኩ/ል 45% ለማቅረብ ተችላል፡፡ በአፈጻጸም ሲታይ በጥንካሬ፤ ከክልል
የሚቀርቡ ግብዓቶች በወቅቱ እንድቀርቡ በማድረግ ተሻለ አቀራረብ ታይታል በቅንጅ
ለመሰራት ጥረት ተደረጋል፡፡የነበሩ እጥረቶች በክልሉየሚጠየቁ ምርጥዘር አካባቢን መሰረት
ያደረገ ሲጠየቅ አለማቅረብ በተለይ ባቄላና ገብስ ፤በዙሪያው የማባዣ ማእከል ያለመኖር
በቀጣይ መፈታት ያለባቸው ናቸው፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃናአጠቃቀም ዘርፍ አፈጻጸም

የተፈጥሮ ሃብት ልማት ስራ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ሰፊየተቀናጀ


ተፋሰስ ልማት ስራዎች ተሰርተዋል 16 ተፋሰሶች(7242 ሄ/ር) በመስራት በ 21 ተፋሰሶች
(10156 ሄ/ር) ለማድረስ ታቅዶ በአምስት አመቱ መጨረሻ 19 ተፋሰሶች(5772..01 ሄ/ር)
በማድረስ 56.8% ለመፈጸም ተችሏል፡፡

በተለይም በተፋሰስ ልማት ስራ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ለማከናወንከ 30-45- ቀናት 4239 በላይ
የሚሆን የሰውሃይል የጉልበት ስራ በመስራት በቀበሌዎች የሚገኙየተፋሰሱ ማህበረሰብ የተሸለ
ተግባራት ተከናወናል፡፡በዚህም መሰረት በመምሪያችን በጥናት ከተለዩት 23 ተፋሰሶች ውስጥበ 19
ተፋሰሶች የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ የተሰራባቸው ሲሆን ከዚህውስጥም 12 ተፋሰሶች ወደ
ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ደረጃ ማሸጋገርተችሏል፡፡ከዚህ ውስጥ 16 ተፋሰሶች የመጀመሪያ ደረጃ
ፊዚካል ስራቸውን ማገባደድ ደረጃ ላይ የደረሱና ተጠቃሚነትንም ማረጋገጥ የጀመሩ
ናቸው፡፡

በተፈጥሮ ሃብት ዋና ዋና የስነ-አካላዊ ስራዎች 297 ሄ/ር መሬት ለማከናወን ታቅዶ


የተከናወነ 224.5 ሄ/ር መሬት ወይም 75.7 % በተለያዩ ፊዚካላዊ የአፈር ጥበቃና የዕርጥበት
ዕቀባ ሥራዎች መሸፈን ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


29
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የደን ሽፋንን 14% ወደ 19.3 % ማድረስ ወይም ከ 3245 ሄ/ር በላይ ለማድረስ ተችሎል፡
3029 በላይ መሬት በሰው ሰራሽ ደን ተሸፍኗል፣እንዲሁም የችግኝ የፅድቀት መጠንን ወደ
78% እና አጠቃላይየደን ሽፋንም 19.3% ማድረስ ተችሏል፡፡

የእንሰሳት ሀብት ልማት ጥበቃ ዘርፍ አፈጻጸም

የእንሰሳት ሀብት ምርትናምርታማነት ከማሳደግ አካያ፤የወተት ምርትን 12447.6 ቶን

ለማድረስ ታቅዶ 1,10917 ቶን (87.7) ለማከናወን ተችላል ፡፡ የሥጋምርትናምርታማነት

3996 ቶን ለማድረስ ታቅዶ 2818.7 (70.5℅) የእንቁላል ምርታማነት በለፉት አመታት


የነበረውን 1(አንድ) ሚሊዮን የእንቁላል ምርት ዓመት 10.8 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዶ 8.3

ሚሊዮን (76.2%) እንዲደረስ ተደርጓል፡፡ከዶሮ ልማት አኳያ 49870 ዓመታዊ የአንድ ቀን

ጫጩት ስርጭት 229693 ለማሰራጨት ታቅዶ 162440 (70.7% በመፈጸምተችላል፡፡

ማርና ሰም ምርታማነትና ምርት የማር ምርትን 2.4 ቶን ዓመት 28 ቶን ለማድረስ


ታቅዶ 20.5 (73.2%) ማድረስ የተቻለ ሲሆን የሰም ምርትን በተመለከተ በትኩረት
አልተሰራም

የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል፤የዳልጋ ከብት ዝርያ፤የተሻሻሉ ዝርያዎች ቁጥር 17870 ለማድረስ


ታቅዶአሁን የተደረሰበት በቁጥር 15590 (87%) ከአጠቃላይ የዳልጋ ከብት አንጻር
ድርሻቸው ደግሞ 63.0%ተከናወናል፡፡ የበግና ፍየል ዝርያ ማሻሻያ፤እናት በጎችን በአዋሲ

ዝርያ አዉራ ማስጠቃት 4800 ታቅዶ 2902(60.4%) ለመስራት ተችላል የእንስሳሰት መኖ

አቅርቦት እና አጠቃቀም 70120 ቶን ለማድረስ ታቅዶ ከእቅዱ 66703 (93 %) ማድረስ


ተችሏል፡፡.

የእንስሳት ጤና አገልግሎት የክትባት አገልግሎት 282000 ለማድረስ ታቅዶ 162879(57%)

በማድረስ .የእንስሳት ጤና አገልግሎት ተደራሽነት 179208 የመከላከል ህክምና እና 87120


የፈዉስ ህክምና ለመስጠት ታቅዶ የመከላከል ህክምና 105751 (59%)፤የፈዉስ ህክምና
51028(58%) ለመስጠት ተችሏል፡፡

ይሁን እንጅ ከተያዘው ዕቅድ አንጻር የነበሩ ወስንነቶች የተሸሻለ ዝርያን አቅርቦትን፤ችግር

አለመፍታትየመኖ እጥረት ሊቀርፉየሚያስችል አሰራር በመቀየስ ወደ ተግባር ያለመግባት ፤

የእንስስት ጤናአገልግሎትጥራትን በላቀ ደረጃ በማሻሻል እና አሰራርና አደረጃጀት

10 2013 -2022 / Page


30
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በማስተካከል ክፍተቶች መኖር የእንስሳት ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የህብረተሰቡን

ተጠቃሚነት በማሳደግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት የሚጠይቅ ተግባር ነው ፡፡

የሀይል ዘርፍ አፈጻጸም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የተሸሻሉ መገዶ
ቆጣቢ ምድጃዎች ፍላጎት ፍጠራና ስርጭት 9100 ታቅዶ 8325 በማከናውን
91%ተሰራጭታል የፀሀይ ይል ቴክኖሎጅ ስርጭት 2300 ታቅዶ 1350 በማሰራጨት
56%ተከናወናል፡፡

የተሸሻሉ የኤሌክትሪክ ምድጃዎች ስርጭት 3800 ታቅደው 4400 በማከናውን የተሻለ


አፈጻጸም ተሰርታል፡፡ይሁን እንጅ ለዘርፉ ከላይ እስከ ታች ትኩረት ማነስ የሚታይ በመሆኑ
በቀጣይ ትኩረትያሻዋል፡፡

የገጠር መሬት አስተዳደር አፈጻጸም

የመሬት ይዞታ ለውጦች (ግብይት)በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን


ከታቀደው ባለይዞታዎች ያለ ኑዛዜ ዉርስን በማጣራት ለመመዝገብና ደብተር ለመስጠት
ታቅዶ ለ 85% (842) ወራሾች በመመዝገብ ደብተር ተሰጥቷ፣ የመሬት ስጦታን መርምሮ
ለማፀደቅና ደብተር ለመስጠት የታቀደ ሲሆን 98%(329) ባለይዞታዎች ስጦታ ፀድቆ
ደብተር ተሰጥቷል፡፡

በሁሉም የመሬት ግብይቶች 1332 አጣርቶ ለመመዝገብ ታቅዶ የ 1199 (90%) የመሬት
ይዞታ ለውጦች ተጣርቶ ተመዝግቧል፡፡የመጀመሪያ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ሁሉም
ባለይዞታ እንዲያገኙ የተደረገው ጥረትና ወደ 10296 (99%)፤መድረስ መቻሉ ከመሬት ጋር
የተያያዙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተደረጉ ጥረቶችበገጠር መሬት ይዘው
የመጠቀም መብት ከሌላቸው ግለሰቦች ወደ መሬት ባንክ ማስመለስን የዕቅዱን 5 ሄ/ር
(70%) መሬት ማስመለስ ተችሏል፡፡

የወል መሬት ወረራ የመልካም አስተዳደር ችግር መንስኤ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት ከህገ
ወጥ አራሾች ለማስመለስ ታቅዶ 6 ሄ/ር (75%) መሬት ማስመለስ ተችሏል፡፡

ይሁን እንጅ የመጀመሪያ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ለሁሉም ባለይዞታዎች


ለመስጠትበካርታ የተደገፈ የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርትፍኬት
ለመስጠትእስካሁን ያልተከናውኑ ተግባራት ሲሆኑ ሌላው የኢስላ ሶፍት ዌርን በመጠቀም
የሁሉንም ባለይዞታዎችና ማሳዎች የመሬት ሀብት መረጃን ወደ ኮምፑዩተር ለመመዝገብ
በታቀደው መሰረት ማስገባትየመረጃ ጥራት ችግር መሰረታዊ ተግዳሮት ሆኗል ፡፡

10 2013 -2022 / Page


31
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የገጠር መሬት አያያዝና አጠቃቀም አፈጻጸም በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ


ዘመን፤ለገጠር መሬት ባለ ይዞታዎች አዲስ የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ አዘጋጅቶ ርክክብ ማካሄድ እና
ነባሩን የመሬት አጠቃቀም ለማስቀጠ ል 610 ባለይዞታዎች 1831 ማሳዎች እና 5 ቀ በሌዎች
ቁጥጥር ማድረግ ተችሏል፡፡

በከተማ አስተዳደሩየሚገኙ ክ/ከተሞች የገጠር መሬት ባለይዞታ ካርታና ፕላን


ሲሰጡ የመኖሪያ አካባቢ እንዲረጋገጥላቸዉ የጠየቁ ባለይዞታዎች ብዛት 121 ሲሆኑ የመኖሪያ
ቦታቸዉ ተረጋግጦ ወደ ሚመለከተዉ ተቋም የተላከላቸዉ ባለይዞታዎች/ ብዛት 79 ተረጋግጣል
፡፡

ይሁን እንጅ የመሬት አጠቃቀም ተግባራት የህዝብን ተሳትፎ መሰረት ያደረጉ ቢሆንም
በየደረጃው ባሉ አመራሮች ትኩረት ሰጥቶ በባለቤትነት ይዞ በመፈፀም በኩል ያለው
ቁርጠኝነት አናሳ መሆኑ፡፡የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስልጠና
ለፈፃሚ አካላት ወቅቱን ጠብቆ አለመሰጠቱ፤ በህገወጥ ተግባራት ላይ ተሳታፊ የሆኑ
አካላትን በህግ ተጠያቂ ያለማድረግ ፡፡

የመሬት ሀብት ዋጋ ትመናካሳ ክፍያና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ አፈጻጸም

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የካሳ ክፍያ ለህዝብ ጥቅም ሲባል መሬታቸውን
የሚለቁ የገጠር ባለይዞታዎችን መልሶ ለማቋቋም እና ይዞታቸውን ለማስተዳደር ዘርፉ ከተመሰረተበት
ጊዜ አንስቶ የካሳ ክፍያ ስንመለከት ባለፉት 3 ዓመታት ለህዝብ ጥቅም ሲባል 458 የመሬት

ባለይዞታዎች 66 ሄ/ር መሬት ክፍያ ተፈፀሞላቸዋል፡፡ለ 351 ባለይዞታዎች እና 144


እድሜቸው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ የተፈናቃይ ቤተሰብ ወጣቶች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታና
ለ 2 ተፈናቃዮችና ቤተሰቦቻቸዉ የመስሪያ ቦታ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
በልማት ምክንያት የተፈናቀሉ ባለይዞታዎችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም በተደረገዉ

ጥረት በራሳቸው መዋዕለ ንዋይ አቅም 23 የልማት ተነሽዎች በተለያዩ የኑሮ አማራጭ የስራ ዘርፎች
እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡
ይሁን እንጅ፤ በከተማችን ባለፉት አመታት በከተማ መፋፋትም ይሁን በሌሎች ልማቶች
ለህዘብ ጥቅም ሲባል መሬቱን በሚወሰድበት ወቅት ተገቢዉን እና ተመጣጣ ካሳ ሳይከፈለዉ
እንዲሁም በዘላቂነት መልሶ የሚቋቋም ዕቅድ ሳይዘጋጅለት ሲፈናቀል በመቆየቱ በርካታ

10 2013 -2022 / Page


32
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አርሶ አደሮች ለችግር ተጋልጠዋል፤ቤተሰቦቻቸዉም እንዲሁ ለስደትና ለተለያዩ እንግልት


ተጋልጠዉ በቀጠይ ትኩርት ተሰጥቶ በ 10 አመቱ ይሰራል፡፡

የህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ተግባር አፈጻጸም


በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በከተማችን ውስጥ 10 አይነት የኀብረት ሥራ
ማህበራትን በማቋቋም በጥቅሉ 19306 (ሴት 7333) አባላትን የያዙ 194 መሰረታዊ ኀብረት
ሥራማህበራት እና 1 የሁለተኛ ደረጃ ኀብረት ሥራ ማህበር የሚገኙ ሲሆን አንድ የልማት አጋር
በመሆን በኢኮኖሚውና በማህበራዊ የልማት እንቅስቃሴው የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡
የኀብረትሥራማኀበራትንማስፋፋት፣የመሰረታዊ ኀ/ሥራ ማህበራትን ቁጥር ከ 85 ወደ 120
ለማሳደግ ታቅዶ 109 መሰረታዊ ህብረት ሥራ ማህበራትን በማቋቋም ወደ 194 ማድረስ
ተችሏል፡፡

ከእነዚህ ዉስጥ 101 የመኖሪያ ቤቶች የኀ/ሥራ ማህበራት በማደራጀት የመኖሪያ ቤት


ችግርን ለመፍታት የሚያስችል ሥራ ተከናዉኗል፡፡

በኀብረት ሥራ ማህበራት አባላትን ቁጥር ማሳደግ 10647 ያህል ግለሰቦችን በኅብረት ሥራ


ማህበራት አባል ማድረግ የተቻለ ሲሆን የሴቶች ድርሻ 26.78% እንዲሁም የወጣቶች
የአባልነት ድርሻ 19% ማድረስ ተችላል፡፡ የመሰረታዊ ኀብረት ሥራ ማህበራትን አባላት ቁጥር
17147 ለማድረስ ታቅዶ 8659 አባላትን በመጨመር በአጠቃላይ በኅብረት ስራ ማኅበራት
የታቀፉ አባላትን ቁጥር 19306 (ሴት 7333) ማድረስ ተችሏል፡፡ .

የብዕርእናየአገዳሰብሎችምርትግብይትአፈጻጸምየኅብረትስራማኅበራትለአባላትናለከተማውነዋሪገበያበማ
ፈላለግበስፋትከሚሳተፉባቸውየብዕርእናአገዳሰብሎችመካከልጤፍናሩዝይገኙበታል፡፡በመሆኑምባለፉት
5 ዓመታት 542700 ኩንታልጤፍና 13300 ኩንታልሩዝና 600 ኩንታል ጥራጥሬ በማቅረብ
ለከተማው ነዋሪ በማቅረብ የገበያ ማረጋጋት ስራ ሰርተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ምርት ግብይት፤ ኅብረት ሥራ ማኅበራት የአባላትን የግብርና ምርት ወደ ተሻለ ገበያ
እንዲያገኝ ከማድረግ ጎን ለጎን በአባላቱ የማይመረቱ የተለያዩ የኢንዱስትሪ/የፍጆታ ምርት ውጤቶችን
በአይነት፣ በመጠን፣ በተመጣጣኝ ዋጋ እና በወቅቱ ማቅረብ እና ገጠሩን

ከከተማው ጋር በኢኮኖሚው እንዲተሳሰር በማድረግ 1,600,000,000 ብር የሚያወጣ የኢንዱስትሪ


ምርት በህበረት ስራ ማህበራት ለአባላት ለማቅረብ ችለዋል፡፡

10 2013 -2022 / Page


33
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የካፒታል መጠናቸውም በመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት ብር 145,070,987፤

በኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒዬን ብር 9,673,998 በድምሩ ብር 154,744,985 ካፒታል

ደርሷል፡፡

በመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ብር 64,621,471 በቁጠባ

የሰበሰቡት ሲሆን ብር 66,467,857 ብድር በማቅረብ አባላት ወደ ተለያዩ የቢዝነስ ዘርፎች

እንዲሰማሩ ማድረግ ችለዋል፡፡

የአባላትሽፋንማሳደግ 5385 (ሴት 2610) ለማድረስታቅዶበ 53 መሰረታዊማህበራት 691 (ሴት


413 ) አባላትን በመጨመር የአባላትን ቁጥር ወደ 3516 (ሴት 1746) ማድረስ የተቻለ ሲሆን ይህም
በአማካይ በአንድ መሰረታዊ የገ/ቁ/ብ/ኅ/ሥ/ማህበር 67 አባል መድረሱን የሚያመለክት ነው፡፡

ካፒታልግንባታየህብረትስራማህበራትዋናየካፒታል 12336453 ለማድረስ ታቅዶ 5094082


ካፒታልበ ማሰባሰብ የመሰረታዊ የገ/ቁ/ብ/ህ/ሥ/ማ/ትን ካፒታል ወደ ብር 9430535 ማድረስ
ተችሏል፡፡

የቁጠባ ማሰባሰብ በከተማና በገጠር ተቋቁመው በእንቅስቃሴ ላይ ያሉ መሰረታዊ የገ/ቁ/ብ/ኀ/ሥራ


ማህበራት 22,055,190 ለማድረስ ታቅዶ ባለፉት 5 ዓመታት ብር 51,355,080 በመሰብሰብበ
ጠቅላላ ብር 63,410,270 በማድረስ ለማሳደግ ተችሏል፡፡

የብድር አቅርቦት እና ሥርጭት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀ/ሥራ ማህበራት አባሎቻቸዉ የተለያዩ
ገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ በመሰማራት ያገኙትን ገቢ በአግባቡ በመቆጠብ ተጨማሪ ሃብት እንዲፈጥሩ
ግንዛቤ ከማስያዝ ጎን ለጎን የተለያዬ ተግባራትን ለማከናወን 20,068,036 ለማድረስ ታቅዶ ብር
54,899,821 ብድር በመጨመር እስካሁን ብር 66,467,857 መፈጸም የተቻለ መሆኑን
መረጃውያሳያል። የተሰራጨው ብድር የዋለበት ተግባር ሲታይ ለእንስሳት እርባታ እና ማድለብ፣
ለግበዓት ግዥ፣ ለአነስተኛ ንግድ፣ ለተሸከርካሪ ግዢ፣ ለመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ ለደሮ እርባታ እና
ለመሳሰሉት ሥራዎች ላይ በማዋል አባላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡

የኢንስፔክሽን አገልግሎት እንደ ተቋም መስጠት በአማካይ በዓመት 60 የኅብረት ሥራ ማህበራትን


ቁጥጥር ለማድረግታቅዶ በአማካይበዓመት 45 ማህበራትንወይምየእቅዱን 75% ማከናወን ተችሏል፡፡

ይሁን እንጅ በቀጣይ ሊፈቱ የሚገባቸዉ በርካታ የኅብረት ሥራ ማህበራት ተግዳሮቶች

መካከል የተጠናከሩና የዘመኑ የኅበረት ሥራ ማህበራት በሚፈለገው ልክ አለማደግ፣

የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ውስንነት፣ የግብይት ተሳትፎ እና ድርሻ በሚፈለገው

10 2013 -2022 / Page


34
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ፍጥነት አለማደግ፣ በእሴት መጨመር ተግባር ላይ በስፋት መግባት አለመቻልና ያሉትንም

የእርሻ ውጤቶች ማምረቻ ኢንዳስትሪዎች በሙሉ አቅም መጠቀም አለመቻል፣ የቁጠባ

ባህል በሚፈለገው ደረጃ አለመዳበር፣ ለገጠር ትራንስፎርሜሽን እና ኢንዱስትሪ ልማት

የሚያስፈልግ የኢንቨስትመንት ፋይናንስ በሚፈለገው መጠን አለመገኘት፣ዘመናዊ የመረጃ

አያያዝስርዓት እና የቴክኖሎጅ ዝርጋታና አጠቃቀም አለመጠናከር የኦዲት እና የኢንስፔክሽን

የተደራሽነትና የጥራት ችግር እና የህብረት ሥራ ማህበራት የብቃት ደረጃቸዉን

አለመመዘን የሚሉት በቀጣይ በእቅዱ የሚፈቱና የመፍትሄ ቁልፍ ተግዳሮቶች ሆነው

ተለይተዋል፡፡

ምግብ ዋስትናና የከተማ ሴፍቲኔት ተግባር አፈጻጸም


በደሴ ከተማ የሚገኙ ክፍለ ከተሞችን የድህነት ምጣኔን የማዕከላዊ ስታስቲክስ ባለሥልጣን በሰጠው
መረጃ መሰረት 34,189 የህብረተሰብ ክፍሎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን የማይችሉና በዝቅተኛ
የድህነት ደረጃ እንደሚኖሩና የከተማው የድህነት ምጣኔም 22.4% መድረሱን የማዕከላዊ ስታስቲክስ
ባለሥልጣን የ 2018 ጥናት ያመለክታል፡፡
በድህነት ደረጃ ከተመዘገበው ሕዝብ 55 በመቶ ያህሉን ማለትም 18,804 ነዋሪዎችን ለማካተት
ቅድሚያ በፕሮግራሙ የሚካተቱ የክፍለ ከተሞችን የድህነት ደረጃ የመለየት ሥራ ተከናውኗል፡፡

ከዚህ አንጻር ባለፉት አራት የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ዕቅድ ዘመን(ከ 2009-2012)
በደሴ ከተማ ለዜጎች በቂ የስራ ዕድል በየአካባቢያቸው በመፍጠር ከድህነት ወለል በታች ያለውን
የዜጎች አኗኗራቸውን በቀጣይነት እየቀነሱ በመሄድ ለማስወገድ በተደረገው ጥረት በሦስት ዙር አምስት
ክፍለ ከተሞች በፕሮግራሙ ታቅፈው በአካባቢ ልማት 15,795 እና በቀጥታ ድጋፍ 3,009 በድምሩ
18,804 ነዋሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
ባለፉት አራት ዓመታት በሦስት ዙር በፕሮግራሙ በተዘረጉ በ 5 ቱ የከተማ ልማት ፓኬጆች
የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና አወጋገድ (22,789 ኩንታል ቆሻሻ መሰብሰብና ማስወገድ፣ 71,686
ሜትር ክፍትና ዝግ ካናል ማጽዳት)፣ የአረንጓዴ ልማት (168,215 ሜ 3 ቦታ ማልማትና
140,415 ችግኞችን መትከል)፣ የከተማ የተቀናጀ የውሃ ተፋሰስ ልማት (60 ሄክታር ተፋሰስ
ማልማት)፣ የከተሞችን ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት (31 የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣

3 ሸድ ግንባታ ሥራ) እና ልማትና ለከተማ ግብርና ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር በሦስቱም ዙር


ወንድ 2,498 ሴት 3,217 ድምር 5,715 ሰሪ ኃይሎችን በማሳተፍ ወንድ 6,870 ሴት 8,907

10 2013 -2022 / Page


35
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ድምር 15,795 የኅብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዋስትና ድጋፍ ማግኘት ችለዋል፡፡ የሴቶች
ተሳትፎ ከሰሪ ኃይል አኳያ 56.3% ከአጠቃላይ ድጋፍ ደግሞ 56.5% ነው፡፡
ከዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ አኳያ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዙር ዕድሜአቸው ከ 18 ዓመት
በላይ ለሆኑ ለ 5,395 የቤተሰብ ተጠሪዎች በዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ፣ የህይወት ክህሎትና
የገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና የተሰጣቸው ሲሆን በመጀመሪያው ዙር
ተጠቃሚ ለሆኑ የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ስልጠና የወሰዱ ለ 2,146 የቤተሰብ ተጠሪዎች
በስነልቦና እንዲነሳሱና ግባቸው ላይ እንዲያተኩሩ ከወሎ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር
የማነቃቂያ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
በ 2012 በጀት ዓመት ወደ ዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ለተሸጋገሩ 2,140 የቤተሰብ ተወካዮች ብር
30,695,800 በዋስትና የሚሰጣቸውን ገንዘብ በመክፈል የተመረቁ ሲሆን የሚያስፈልጋቸው
የማምረቻ ቦታና የብድር መጠን በመለየት የቤተሰብ ተወካዮችንና የስራ መስክ ማስመረጥ፣
የንግድ እቅድ ዝግጅት በማከናወን በመረጡት የሥራ መስክ በማኑፋክቸሪንግ፣
በኮንስትራክሽን፣ በከተማ ግብርና፣ በአገልግሎት፣ በንግድና በቅጥር እንዲሰማሩ ተደርጓል፡፡
በአካባቢ ልማት ሥራ መርሀ ግብሮች የሚሳተፉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በዘላቂ የኑሮ
ማሻሻያ ሥራዎች በማሳተፍ የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ፣ የህይወት ክህሎትና የገንዘብ አጠቃቀም
እንዲሁም የሥራ ማነቃቂያ ስልጠና ያገኙ ሲሆን መርሀ ግብሩ ሲጠናቀቅ በመረጡት ሥራ
ተሰማርተው ራሳቸውን በዘላቂነት ከድህነት ለማላቀቅና የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ
ከሚደረግላቸው ድጋፍ ገቢያቸው እንዲሻሻል ከሚያገኙት ወርሃዊ ክፍያ 20% በመቆጠብ
በአጠቃላይ በሦስት ዓመት ድረስ ብር 20,218,287.00 ቁጠባን ማድረስ ተችሏል፡፡

የንግድና ገበያ ልማት ተግባር አፈጻጸም

የንግድ ማሻሻያ ስርዓት ተዘርግቶ ተግበራዊ መደረግ የተጀመረበት ዘመን የዕድገትና


ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ወደ ተግባር የተገባበት ወቅት ነበር፡፡ለነጋዴዎች፣ ለሸማቹ
ህብረተሰብና ለአጋር አካላት በንግድ ዉድድርና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅና ተያያዥነት ባላቸው
ጉዳዮች ያለውን የክህሎት እውቀትና መረጃ ክፍተት ለመሙላትና በንግዱ ህብረተሰብ
የሚታየውን የሌብን አመለካከትና ድርጊት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል ግንዛቤ
የማሳደግ ስራ ተሰርቷል፡፡

ምርትን ወደ ውጭ የመላክ ስራ ለመስራት ቅድመ ሁኔታዎች መመቻቸት የነበረባቸው


ቢሆንም በከተማችን አልፎ አልፎ የቁም እንስሳት ላኪ ቢኖርም የተጠናከረ ባለመሆኑ በ 10

10 2013 -2022 / Page


36
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አመት አፈጻጸም ዝቅተኛ ሲሆን የቁም እንስሳት 1176 ወደ ውጭ ለመላክ እቅድ ተይዞ 500
የተላከ ሲሆን አፈጻጻም (42.5%) ተከናወናል፡፡

ይሁን እንጅ በንግድ ዘርፉ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ማድረግ፤ ምርትን በመገደብና
በመደበቅ እንዲሁም ከተፈቀደው የግብይት መስመር አለመነገድ፣ ፀረ-ውድድር ተግባራት
መፈጸም/ የምርት ጥራት ማጓደል በተለይም በሸማቹ ደህንነትና ጤንነት ላይ አደጋ
የሚጥሉ ጊዜያቸው ያለፉ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለሸማቹ የማቅረብ፤ ለተከፈለ ክፍያ
ተገቢውን መጠን ለክቶ አለማስጠት፣ ማጭበርበር፣ማታለል፤ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ
አለመስጠት/አለመቀበል ...ወዘተ አሁንም ጎልተው የሚታዩና ያልተፈቱ የገበያ ችግሮች
በመሆናቸው ይህን ችግር ሊቀለብስ በሚችል አግባብ በቀጣይ መስራት ይጠይቃል፡፡
ከምዝገባና ፍቃድ ተግባራት አፈጻጸም፤የንግድ ድርጅቶችን ቁጥር ወደ 12423 ለማሳደግ
በዕቅድ ተይዞ እስከ 2 ዐ 12 በተሠሩ ሥራዎች የንግድ ድርጅቶቹን ቁጥር ወደ 11294
(90.9%) ማድረስ ተችሏል፡፡

በዕቅድ ዘመኑ መጀመሪያ 4379 የነበረውን የንግድ ማህበረሰብ ቁጥር በየአመቱ 15%
በማሳደግ 12423 ታቅዶ አዳዲስ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ 3200 የተከናወነ ሲሆን
(62.5%)ተከናወናል፡፡፤ነባር ምዝገባና ፈቃድ የማደስ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 4052
የተከናወነ 2247(55.4%)ለመፈጸም ተችላል፡፡ የንግድ ፍቃድ ዕድሳት በዕቅድ ዘመኑ
መጨረሻ ላይ ወንድ 6777 ሴት 4517 በድምሩ 11294 (30.8%) ነጋዴዎችን አገልግሎት
መስጠት የተቻለ ሲሆን ከጠቅላላ ነጋዴው 475500 ብር ካፒታል ተመዝግቧል፡፡

ይህ አፈፃፀም በየበጀት ዘመኑ ከፈቃድ መስጫ መደቦች አመዳደብ ደንብ አኳያ በ 10 ሩ ዋና


ዘርፎች ሲታይ የንግዱ ማህበረሰብ በውስን ዘርፎች ላይ ሲረባረብ ይታያል፡፡ ከተሰጡ
ፈቃዶች ከ 95% በላይ የሚገመቱት የጅምላና ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሲሆን
አብዛኛው ደግሞ በተመሳሳይ የንግድ ስራ ከመረባረብ ያለፈ የንግድ ዘርፉን ልማት በሚደግፍ
መልኩ በመምራት በኩል ውስንነት ታይቶበታል፡፡

በህብረት ሽርክና በአዲስ ምዝገባ 450 ለማድረስ ታቅዶ 185 (41.1%) ፣


ኃ/የተ/የግ/ማህበር 34 ታቅዶ 25 (73.5%) ፣ በንግድ ስራ ፍቃድ ዕድሳት 841 ለማድረስ
ታቅዶ 742 (88.3%) ማድረስ ተችሏል፡፡ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ መረጃዎችን በቀጥታ
መስመር ላይ እንዲመዘገብ በስትራቴጅክ ዘመኑ በአዲስ ወደተግባር የተገባበት ሲሆን 100
% ወደ ኮምፒተር ለማስገባት ታስቦ 95 % ማከናወን ተችሏል፡፡ ሸማቾች ጥበቃ የንግድ
ውድድር ለማሳደግና የሸማቹን ማህበረሰብ መብት ለማስከበር ልዩ ልዩ ተግባራት

10 2013 -2022 / Page


37
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ተፈጽመዋል፡፡ ባሳለፍነው 10 አመት ህጋዊ ደረሰኝ የሚሰጡ የንግድ ድርጅቶች ክትትል


ለማድረግ 11294 ታቅዶ 5082 በማከናወን ከዕቅዱ (44.9%) ማድረስ ተችሏል፡፡
በከተማችን ከሚገኘው 11294 ጠቅላላ የንግድ ድርጅት ቁጥር አኳያ ከአመት አመት
በተደረገው ጥረት ደረሰኝ ያላቸው ቁጥር 50% እንዲደርስ አስችሏል፡፡ ሆኖም ዝቅተኛ
ነጋዴዎች ደረሰኝ ለማሳተም ወጪው ከፍተኛ ነው በሚል ፈቃደኛ አለመሆን፣በየንግድ
ድርጅቱ የዋጋ ዝርዝር የመለጠፉ ተግባርም ለንግድ ውድድሩ ካለው ፋይዳ አኳያ እንዲለጥፉ
ክትትል ለማድረግ 10684 ዕቅድ ተይዞ 8750(81.9%) ማድረስ ተችሏል፡፡

በንግድ ድርጅቶች ተግባራዊነቱን ለማረጋገጥ የንግድ ድርጅት የበር ከበር ለመጎብኘት


ከተየዘው 479930 እቅድ 442220 በመተግበር አፈጻጸሙ 92% መሆን ችሏል፡ ፡
ከኢንስፔክሽን ቁጥጥር አፈጻጸም የበር ከበር ጉብኝት/የውጭ ኢንስፔክሽን/ ለማከናወን
479930 በድግግሞሽ ንግድ ድርጅት በር ከበር ለመጎብኘት ታቅዶ 442220 /92%/
ተፈፅሟል፡፡ የስትራቴጅክ ዕቅዱ ሲታቀድ 10% የነበረውን የህገ-ወጥ ነጋዴ ሽፋን በዕቅዱ
መጨረሻ ዘመን 7.24% በመሆን ህገ-ወጥነቱ ቀንሷል ለማለት ቢቻልም በዕቅድ ለመድረስ
የታቀደውን 3% ማሳካት አልተቻለም፡፡ የመለኪያ መሳሪያዎችን ከማረጋገጥና ከመከታተል
አኳያ ሸማቹን ህብረተሰብ በከፈለው ገንዘብ ልክ ተጠቃሚ እንዲሆን ባሳለፍነው
ስትራቴጅክ የዕቅድ ዘመን 211860 ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ ልኬታ ትክክለናነት
ለማረጋገጥና 541890 በድግግሞሽ ለመከታተል ቁትጥርና ክትትል ለማድረግ እቅድ ተይዞ
የነበረ ሲሆን አፈፃጸሙ በቅደም ተከተል 180630 ወይም 85 % እና 361260 ወይም 66.6%
ማከናወን ተችሏል፡፡ ግብይት ዘርፍ ግብይት ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት አንዱ ወቅታዊና
ታማኒነት ያለዉ መረጃ ለተገልጋዮች ማድረስ ነዉ ፡፡ 5 የግብርና ምርት ዋጋ 15
የኢንዱስትሪ ምርት ዋጋና ለመንግስት ግዥ አንዲደግፍ 10 የፅህፈት መሳሪያዎች መረጃ
በመሰበሰብ በማደራጀትና ትንተና በመስራት ለተገልጋዮችና መረጃዉን ለሚፈልጉ
መንግስታዊና መግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት ማሰራጨት ተችሏል፡፡
የግብርና ምርት ትስስር 158190 ኩንታል የተለያዩ የምርት አይነቶች ምርቱ ከሚመረትበት
አካባቢ ትስስር መፈጸም የተቻለ ሲሆን የብእር እህል 84174 ኩንታል፣ አትክልትና ፍራፍሬ
60824 ኩ/ል፣ጥራጥሬ 10700 ኩ/ል እና ቅመማ ቅመም 2492 ኩ/ል ማስተሳሰር ከታቀደው
75% ማድረስ ተችሏል፡፡

ንግዱን በዘመነ መልኩ መምራት እንዲቻል ከ 20 በላይ የሸማች ማህበራት፣ 60 የአትክልትና


ፍራፍሬ እና የብእር እህል የንግዱ ህብረተሰብ የምክር አገልግሎት በመስጠት አንዲሁም

10 2013 -2022 / Page


38
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በተለያዩ የትስስር መድረኮች ለ 23493 ግንዛቤ ፈጠራ በመስራቱ ከጎንደር፣ከሰቆጣና ከቆቦ


አካባቢዎች ጋር የሽንኩርት የምርት ትስስር ተደርጓል፣ ጤፍ እና በርበሬ ከላኮመልዛ ዩኔንና
ጋር በመሆን ለከተማችን እንዲቀርብ ተደርጓል ፡፡
እንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ግብይት ዘርፍ ተግባራት አፈጻጸም ወደ ውጭ ለመላክ ከተያዘው 500
የቁም እንስሳት፤ በመላክ 40000 የአሜሪካ ዶላር የተገኘ ሲሆን ቁም እንስሳት 96678 ወደ
አንደኛ ደረጃ የገበያ መዕከላት በህጋዊ መንገድ እንዲላኩም ተደርጓል፡፡

የንግድና ግብይት ስርዓቱን ተከትሎ የሃገር ዉሰጥ ግብይት በተረጋጋ ሁኔታ እንዲካሄድ
ለማድረግ ባለፉት አመታት ለሀገር ውስጥ ገበያ 126317 የቁም እንስሳት ወደ ማዕከላዊ
ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ 96678 የቁም እንስሳት ቀርቧል፡፡ በተጨማሪ የቆዳና ሌጦ ምርት
2002093 በቁጥር ወደ ማእከላዊ ፋብሪካ እንዲቀርብ ከተያዘው እቅድ ውስጥ 1632910
ቆዳና ሌጦ ምርት ደረጃ በማውጣጥ ወደ ፋብሪካ እንዲቀርብ ተደርጓል ጉዞ መሸኛም
ተሰጥቷቸዋል ፡፡

ንግዱን በዘመነ መልኩ ለመምራት እንዲቻል ከ 25973 በላይ የንግዱ ህብረተሰብ የምክር
አገልግሎት በመስጠት አንዲሁም በተለያዩ የትስስር መድረኮች የግንዛቤ ፈጠራ በመስራቱ
196483.8 ቶን ወተት፣3889.97 ቶን ቅቤ፣ 937.21 ቶን አይብ፣863488.8 ቶን የእንስሳት
መኖ፣12995.6 ቶን ማር ምርቱ ካለበት አካባቢ ወደ ከተማችንና ከከተማችን ያለውን
ምርት ወደ ሌላ አካባቢዎች ጋር በማስተሳሰር ዉጤታማ ስራ ተሰርቷል፡፡

 የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ተግባር አፈጻጸም


የካፒታል ፕሮጀክት ሥራዎች አፈፃፀም
የካፒታል ፕሮጀክት ለማስፈፀም ወደ ከተማችን የሚፈሰው ሀብት ከፍተኛ ዕድገት
እየታየበት ይገኛል፡፡በመሆኑም የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም እየገመገሙና እየተከታተሉ
መምራት የላቀ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ይሁንና አጠቃላይ የካፒታል ፕሮጀክቶችን
ከማስተዳደርና ከመምራት አፈጻጸማቸውን በየጊዜው ከመከታተል አንፃር ያለው ክፍተት
ሠፊ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ፕሮጀክቶች ሲቀርቡ አጠቃላይ ኢኮኖሚውን
ከማሳደግ፣የሥራ ዕድል ከመፍጠር፣ ወዘተ ከከተማው የልማት ቅደም ተከተልና ካላቸው
ፋይዳ በአግባቡ የተጠና፣ በዶክመንት በተደራጀ መልኩ የሚቀርቡበት ሁኔታ ባለመኖሩ

10 2013 -2022 / Page


39
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ምክንያት በየጊዜው ለተጨማሪ እና ለለውጥ ሥራ እየተባለ ብዙ ገንዘብ የሚመደብበት እና


ፕሮጀክቶችም ለረጅም ጊዜ የሚራዘሙበት ሁኔታ ይታያል። ከጥራት አንፃርም ተሠርተው
ሳይጠናቀቁ መፍረስ የሚጀምሩ ፕሮጀክቶችም ያጋጥማሉ። በዚህ ምክንያትም
ህብረተሰቡ በሚፈለገው ደረጃ የልማቱ ተጠቃሚ እንዳይሆን አድረገውታል
የበጀት አስተዳደር ዘርፍ
የወጪ አፈጻጸማችን ሲታይ በ 2003 ዓ.ም ከነበረበት ብር 137,978,294.00 በ 2012 ዓ.ም
ወደ ብር 446,536,028 ዕድገት አሳይቷል። የገቢ አፈጻጸማችን ከወጪያችን አንጻር በጥቅሉ
ሲታይ በ 2003 በ 54,602,752 ብር/በ 39.6%/ ወጪያችን በልጦ የነበረ ሲሆን በ 2012
ደግሞ በ 167,607,006 ብር/በ 37.5%/ ብልጫ ነበረው፡፡ ይህም የሚያሳየዉ የልማት
ፍላጎታችን በከፍተኛ ደረጃ ማደጉና የገቢ አሰባሰባችን እጅግ ዝቅተኛና የህ/ሰቡን ጥያቄ
ሊመልስ የማያስችል መሆኑን ነዉ፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ዓመታት የህዝባችንን ጥያቄ
በአግባቡና በተሟላ ሁኔታ ለመመለስ የገቢ አሰባሰባችንን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግና በልዩ
ትኩረት ስር ነቀል ለዉጥ ማምጣት ይጠበቅብናል፡፡
የውጭ ሀብት ግኝትና አስተዳደር መንግስት እያደረገ ካለው ሰፊ የልማትና የመልካም
አስተዳደር እንቅስቃሴ በተጨማሪ የተለያዩ ለጋሽና አበዳሪ እንዲሁም ህጋዊ አዉቅና
አግኝተዉ እየተንቀሳቀሱ ካሉ በጐ አድራጐት ድርጅቶችና ማህበራት ከመንግስት ጐን
በመሆን የከተማዋን ህዝብ የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻል ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ ላይ
ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም በከተማችን የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ባለፋት


1 ኛ እና 2 ኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዓመታት የመንግስትን ጥሪ ተቀብለዉ
ከከተማው የልማት እና መልካም አስተዳደር የትኩረት አቅጣጫዎች አንጻር የተዘጋጁ 139
ኘሮጀክቶች የውል ስምምነት በመፈፀም ወደ ሥራ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን በዚህ
የፕሮጀክቶች ከ 2008 ጀምሮ ባለዉ መረጃ መሰረት የውል ስምምነት ብር 78,430,444.42
በጀት ወደ ከተማችን እንዲገባ በማድረግ 201,197 የከተማዋን ህዝብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ
አድርገዋል፡፡
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ የመንግስት ሀብት በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል
ለማስቻል በዕቅድ ዘመኑ የግዥ ፈፃሚ አካላትን አቅም በመገንባት በግዥና ንብረት
አስተዳደር አሰራር ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፣ ግልጽነት ያለዉና ተጠያቂነትን

10 2013 -2022 / Page


40
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የሚያስከትል የጨረታ ሂደት መከተል፣ ጥራት ያለዉና ፈጣን የግዥ ስርአትን ማረጋገጥ፣
ግዥን በዕቅድ መምራት፣ ወዘተ… በእቅድ ዘመኑ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ይሆናል፡፡

የገቢ ተግባር አፈጻጸም


የግብር ትምህርት የሂሳብ መዝገብ መያዝ ለሚጠበቅባቸው 10712 የደረጃ “ሀ” እና “ለ”
ግብር ከፋዬች ስለ ሂሳብ መዝገብ አያያዝ ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ለ 12818 /83. %/
ለሚሆኑ ግብር ከፋዬች ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡ ደረሰኝ ለማይሰጡ፣ ተጨማሪ እሴት
ታክስ እና ተርን ኦቨር ታክስ በወቅቱ ሪፖርት ለማያቀርቡ፣ ታክስ አሳንሰው ለሚያሳውቁ፣
ያለ አግባብ ተመላሽ ለሚጠይቁና ውዝፍ ግብር ያለባቸውን 7123 የደረጃ ሀ እና ለ ግብር
ከፋዬችን ግንዛቤ ለመፍጠር ታቅዶ ለ 7860 (110%) ለሚሆኑ ግብር ከፋዮች ግንዛቤ
ተፈጥሯል፡፡

ስለ ግብር ጠቀሜታና ዓላማ፤ ስለ ገቢ ግብር ህጐች /አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች/


ለ 8616 የደረጃ ሀ፣ለ፣እና ሐ የንግድ ስራ ግብር ከፋዬች ግንዛቤ ለመፍጠር
ታቅዶ፤ለ 5776 /67%/ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡ለንግድ ስራ ግብር ከፋዬች፣ ቤት አከራዬች፣
ለከተማ አገልግሎት ግብር ከፋዮች፣ ለየግል ተቀጣሪዎች ድርጅቶች ግብራቸውን በወቅቱና
በትክክል እንዲከፍሉ ለ 8000 ለሚሆኑ በየድርጅታቸውና በየቤታቸው በመንቀሳቀስ ቤት
ለቤት ግንዛቤ ለመስጠት ታቅዶ ለ 17359 (219%) ቤት ለቤት ቅስቀሳ ተደርጓል፡፡

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ፣ እንዲገዙ የሚገደዱ ግብር ከፋዮች ደረጃ “ሀ” 2396፣ ደረጃ “ለ” 1100
በድምሩ 3496 ሲሆን የገዙ 1938 (55.%)ግብር ከፋዮች መሳሪያውን ገዝተው እንዲጠቀሙ
ማድረግ ተችሏል፡፡ እየተጠቀሙበት/ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ማሽን ብዛት 1601 ናቸው፡፡ የማሽን
አገዛዙ አፈፃፀም ማነስ ምክንያት አቅራቢ ድርጅቶች ማቅረብ ባለመቻላቸው ነው፡፡የደንበኞችን
አገልግሎት የቅሬታ ምላሽ አሰጣጥበግብርዘመኑ ከግብር ጋር በተያያዘ ለቅሬታ ሰሚ ቡድን 5275
አቤቱታዎች ቀርበው 2721 ወይም 51.58% በማጽናት፣ 1541 (40.83%) በመቀነስ፣ 11 ወይም
0.29% በመጨመር በድምሩ ለ 3,774 (100%) ግብር ከፋዮች ምላሽ (ውሳኔ) መስጠት ተችሏል፡፡
በገንዘብ ሲታይ ቅሬታ የቀረበበት የገንዘብ መጠን ብር 14,999,199፤ በመቀነስ
2,537,304.1 ብር፣ በማጽናት 11,830,898 ብር እንዲሁም በመጨመር ብር 54,680 ነው፡፡
ቅሬታ በገቢ ተቋሙ የሚታይ በመሆኑ ፈጥኖ ምላሽ በመስጠት በኩል ውስንነቶች ታይተዋል፡፡ በዚህ
ደግሞ ግብር ከፋዩ የመልካም አስተዳደር ችግር እያነሳ ይገኛል፡፡ ስለዚህ በቀጣይ የቀረበውን ፍትሃዊ

10 2013 -2022 / Page


41
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በሆነ አግባብ ፈጥኖ ማየት ይገባል፡፡ የይግባኝ ምላሽ አሰጣጥ በዕቅድ ዘመኑ ለግብር ይግባኝ ጉባኤ
17016 አቤቱታዎች ቀርበው መልስ የተሰጣቸው ለ 16945 (99.58%) ውሳኔ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
ኦዲትና ህግ ማስከበር
በዕቅድ ዘመኑ 2098 በባህሪና በስጋት የተለዩትን የደረጃ ሀ እና ለ ግብር ከፋዮችን ክትትል
ለማድረግ ታቅዶ 1597 የንግድ ድርጅቶች ላይ ክትትል ተደርጓል፡፡
አፈፃፀሙም 76.12% ሲሆን በተደረገው ክትትልም ግብርና ታክስ ብር 4662244.88 ግኝት
ተገኝቷል፡፡የኦዲት ሽፋንን ከማሳደግ አኳያ ከውዝፍ እና በዘመኑ 3537 ሂሳብ መዝገብ
ለመመርመር ዕቅድ የተያዘ ሲሆን 3708 ሂሳብ መዝገብ ተመርምሯል፡፡ አፈጻጸሙ 104.83%፣
ሲሆን የኦዲት ውጤታማነት የግብር ከፋዩ የግብር ህግ ተገዥነት እያደገ ሲመጣ የኦዲት
ውጤታማነት እንደሚቀንስ ቢታወቅም አሁን ባለንበት ደረጃ የግብር ከፋዩ የህግ ተገዥነት ያላደገ
በመሆኑ የኦዲት ውጤታማነትን ማሳደግ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡በዚህም መሰረት ከሚመረመሩ ሂሳብ
መዝገቦች ብር 118.888.778 በልዩነት ግብር እና ታክስ ለማግኘት እቅድ የተያዘ ሲሆን የተገኘ
ውጤት 86 661 339.ወይም 72.89%/ ነዉ፡፡
 የምርመራተግባራት
348 በኦዲት ተመርምረው ወደ ግብር አወሳሰን አሰባሰብና ክትትል ዋና የስራ ሂደት

የተላለፈ የኦዲት ሪፖርቶችን በትክክል መወሰናቸውንና መክፈላቸውን በማረጋገጥ

የምርመራ ሥራ ለመስራት ዕቅድ ተይዞ፤ 283 (81.32%) ሂሳብ መዝገብ ላይ የምርመራ

ሥራ በመስራት ግብር ብር 5,037,626.85፤ ታክስ ብር 3,129,630.16 በድምሩ ብር

8,167,257.01 ግኝት ተገኝቷል፡፡


የገቢ አሰባሰብ ዘርፍ
ባለፉት አመታት ከክል ገቢ ብር 2,300,090,801.90 ከከተማ አገልግሎት ገቢ ብር
684,825,627.22 በድምሩብር 2,984,916,429.12 ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር
2,224,243,418,26 /74.51%/ተሰብስቧል። አፈፃፀሙ የቀነሰ ሲሆን የቀነሰበት ምክንያት
የደረሰኝ ክትትሉ የተዳከመ መሆን፣ የደረጃ “ለ” ዳግም ውሳኔ በተገቢው አለማስከፈል፣
ውዝፍ ግብር አለማስከፈል፣ መወሰን የሚገባቸውን በወቅቱ ወስኖ አለማስከፈል፣ ይግባኝ
በፍጥነት አይቶ ገቢው እንዲሰበሰብ አለማድረግ በቀጣይከነዚህ ችግሮች መውጣት
ይጠይቃል፡፡ በጥንካሬ ዘመናዊ የታክስ አስተዳደር ስርዓት ግንባታው አገልግሎት
አሠጣጥን ማሳለጡ ነው፡፡

10 2013 -2022 / Page


42
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የክልል እና ከተማ ገቢን በአንድ ተቋም መሰብሰብ መቻሉ አገልግሎት አሠጣጥን


ማሳደጉ፣የቀን ገቢ ጥናትን የፍትሃዊነት ችግር በሥራ አመራር ኮሚቴ እየገመገሙ
ማረም መቻሉ፣t ቸማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ፣ ደረጃ ሽግግር እና የደረሰኝ አጠቃቀም
ችግርን የሚፈቱ ተግባራት መፈፀማቸው፣ ወደ ግብር መረቡ ያልገቡትን እየተከታተሉ
ለማስገባት ጥረት መደረጉ፣የግብር ዕዳውን ላልተወጣ ግብር ከፋይ አልፎ አልፎ የክፍያ
ማረጋገጫ n ጻ ምስክር ወረቀት መስጠት፣የካፒታል ዋጋ ዕድገት ገቢ አሰባሰቡ
ከሌብነት የፀዳ አለመሆኑና በየጊዜው የሚወጡ አሠራሮች ይኸን የሚቀይሩ
አለመሆናቸው፣የታክስ አሰባሰቡ t ጨማሪ እሴትና ተርን ኦቨር ታክስ እና ደረሰኝ
አጠቃቀም ችግር አለመፈታት በተለይ ያለደረጃቸው ግብር የሚከፍሉ መኖራቸው እና
ወደ ግብር መረቡ ያልገቡ መኖራቸው ነው፡፡
 የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ተግባር አፈጻጸም
ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ፤
ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር የህዝብን ገቢ ማሻሻል፣ ድህነትን ለመቀነስ እንዲሁም ፍትሃዊ
የሀብት ክፍፍል እንዲፈጠር ማድረግ ወሳኝ ተግባር ነው፡፡ ባለፊት 10 ዓመታት ተከታታይ
ዓመታት ለ 12229 ስራ አጥ ዜጎችን በመመዝገብና ለስራ ፈላጊነት ሳይመዘገቡ ወደ ስራ
የተሰማሩትን ጨምሮ ወንድ ለ 46393 ሴት ለ 27599 በድምሩ ለ 73992 (14645 ጊዚያዊ)
ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን አፈጻጸሙ 11.33% ተከናውኗል፡፡
በስራ እድል መፍጠሪያ አይነቶች ሲተነተን አዲስ ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም ለ 19258 ስራ
አጥ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ 3861 ዜጎች (20%) የስራ እድል የተፈጠረ
ሲሆን፤ ነባሮችን በማጠናከር ለ 129229 ስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ
ለ 73992 ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን አፈጻጸሙ 57.25% ነው፤ በአጠቃላይ በእቅድ
ዘመኑ ያለው በቀጥታ ድጋፍ በመንግስት ፕሮጀክት ነባርን ከማጠናከርና በመንግስት መስሪያ
ቤቶችና ልዩ ልዩ ተቋማት ላይ የተቀጠሩትን ጨምሮ አፈጻጸም ስንመለከት በአጠቃላይ
ከተፈጠረው ስራ እድል ውሰጥ 40.79% ቋሚ 56.2% ጊዚያዊ ሲሆን ስራ እድል ለመፍጠር
ታቅደው 80% ቋሚ 20% ጊዜያዊ ነበር፡፡

በአጠቃላይ የተፈጠረ ስራ እድል ወንዶች 59‚982 ሴቶች 32759 ድምሩ 92741 ሲሆን
አፈጻጸሙ 49.55% ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚህ መካከል ቋሚ ስራ እድል የተፈጠ l ቸው
38346 ሲሆን ከዚህ ውስጥ ሴቶች 22281 ሲሆኑ ጊዚያዊ ስራ ዕድል የተፈጠረ 42663
ነበሩ፡፡ የሴቶች ተሳትፎ በስራ እድል 93566 ሴት ስራ እድል ይፈጠራል ተብሎ ታቅዶ 32759
ሴት ስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን አፈጻጸሙ 35.01% ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡በቋሚ የስራ

10 2013 -2022 / Page


43
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

እድል 149707 (80%) የስራ እድል ይፈጠራል ተብሎ ታቅዶ 38346 (25.61‚) ተከናውኗል፡፡
ጊዚያዊ የስራ እድል የተፈጠረ 37427 (20%)ይከናወናል ተብሎ ታቅዶ ስራ እድል የተፈጠረ
100% (422663) መሆኑን የተሰበሰቡ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡
ግንባታ፣ግብአት አቅርቦት አፈጻጸም
ሸድና ክላስተር ህንፃዎች በመገንባትና መሰረተ ልማት በማሟላት ለተደራጁ አምራች
ኢንተርኘራይዞች በማስተላለፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተሰራ
ያለበት ሁኔታን ነው፡፡ በዚሁም መሰረት ከመንግስት ካዝና ላለፉት 10 አመታት ለመብራት
ማስገቢያ ለ 14 ትራንስፎርመርና ከመቶ በላይ ቆማሪዎችን ከ 12 ሚሊዮን ብር በላይ ፤
ለሽድ ግንባታ ለ 102 ሽድ ከ 60 ሚሊዮን ብር በላይ ፤ ለውሀ ማስገቢያ ከ 400 ሺ ብር በላይ
ወጭ በማድረግ የኢንተርፕራዞችን t ጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሎአል፡፡
ለስራ ዕድል የመሬት ዕቅድ 1500000 ካ/ሜ ሲሆን የለማ መሬት 269770 ካ/ሜትር ሲገኝ
ክንዉን 95300 ካ/ሜትር ለተጠቃሚዎች ተላልፏል ይህ አሀዝ የገጠር ግብርናን አያካትትም
፡፡
ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች የማምረቻ ክላስተር ሸድ የዋለ በቁጥር 102 ዳስና ከ 100 ኮንቴነር
በመገንባት ከ 500 በላይ ኢንተርፕራይዞችንና ከ 2000 በላይ አንቀሳቃሾችን ማስጠቀም
ተችሎአል፡፡
ባለፉት አመታት በለማ መሬት ዳስና ህንፃ ተጠቃሚዎች የሴቶች ተጠቃሚነት ከ 40
ሲሆን የወንዶች ደግሞ ከዚህ በላይ 60% ነው፡፡ ከተማችን ምንም እንኳ የለማ መሬት ዳስ
ተጠቃሚ አካል ጥያቄ እየጨመረ ቢሄድም ካለው የቦታ ጥበት የተነሳ ለማስተናገድ
አልተቻለም ወደ ስራ ከተሰማሩትም መካከል ለአካል ጐዳተኞች የተሰጠው መስተንግዶ
አናሳ መሆኑን ታይቷል ፡፡
የሚሰራው ሸድና ህንፃ አገልግሎት መስጠት የሚችለው ከሌሎች አጋር መስሪያ ቤቶች ጋር
ማለትም መብራት ሃይል፣ ውሃ አገልግሎት፣ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት፣
ፋይናንስ መምሪያ፣ አብቀተ፣ ክ/ከተማች ማህበረሰቡና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር
ተቀናጅቶ በመስራት ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ከታየው የስራ ልምድ አንጻር
እስከ አሁን በየቦታው የመብራት አገልግሎት ችግር በመኖሩ እንደታሰበው መጓዝ
አልተቻለም፡፡ በመብራት ችግር የተሰሩ ወይም የታደሱ ዳሶች እንኳን አገልግሎት መስጠት
ያልቻሉበት ሁኔታ ነበር ፡፡
በአጠቃላይ የሥራ እድል መፍጠሪያ ዳስ ግንባታና የመሬት ስርጭት ባለፉት 10 አመታት
ከታቀደው አንጻር ማስተናገድ የተቻለው ከ 20% አይበልጥም፤ ይህ የሆነው በከተማችን

10 2013 -2022 / Page


44
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የቦታ እጥረት በመኖሩ ነው፡፡ ስለዚህ መፍትሔው ቦታ ለማግኘት ከተማችንን ወደ ላይ


የማሳደግ ስልት መከተል ይኖርብናል፡፡
የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አፈጻጸም
የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ በማቋቋም ለኢንዱስትሪው ልማት አስተማማኝ
መሰረት ለመጣልና በከተማችን ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠርና መሰረት ያለው ልማታዊ
ባለሀብት በመፍጠር ወደ ኢንዱስትሪ- መር የሚደረገውን ሽግግር እውን ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም በ 5 ዓመቱ 19258 አዲስ ኢንተርፕራይዝ ለመደገፍ ታቅዶ 3861
ኢንተርፕራይዞችን የተደገፉ ሲሆን አፈጻጸሙ ከእቅዱ 20% ተከናውኗል ፡፡ በእቅድ ዘመኑ
5691 ኢንተርፕራይዞችን የተደገፍ ታቅዶ 4289 ኢንተርፕራዝ የተደገፍ ሲሆን ከእቅዱ
ያለውን አፈጻጸም 75.36% ተከናውኗል፡፡64 ኢንተርፕራይዞችን ወደ ታዳጊ መካከለኛ
ባለሃብትነት ማሸጋገር መቻሉ፣ በከተማ ግብርና እንስሳት ሀብት ዘርፍ ያለውን አንጻራዊ
በሆነ መንገድ ለማሳካት መቻሉ፣ኢንተርፕራይዞች ለማቋቋምና ለማጠናከር የሚያስፈልጉ
ግብአቶችን በ 10 ዓመቱ ውስጥ ለማሟላት ጥረት መደረጉ፣ የሚጠበቀውን
ያክልውጤትማስመዝገብ ባይቻልም በእድገት ተኮር ዘርፎች ኢንተርፕራይዞችን
በማሰማራት አመራሩ፣ ባለሙያዎችና ሌሎች አካላት ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውና
በኢንተርፕራይዞች ቆጠራ የኢንተርፕራይዞችን መረጃ በዘርፍና ስራ መስክ ለየቶ ለማወቅ
ጥረት መደረጉ በጥንካሬ የሚገለጹ ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ እድገት ተኮር ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች በማደራጀትና ወደ ስራ


በማስገባት በኩል በተለይም በማኒፋክቸሪንግና ኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰራው ስራ ከተማ
ግብርና ላይ ባለው x ድገትና ለውጥ እቅድ የተፈጸመውን ስንመለከት አነስተኛ መሆኑ፣
ለዚህም ምክንያቱ ዘርፉ ከፍተኛ ካፒታል፣ እውቀት፣ ቴክኖሎጂ፣ ጉልበት የሚጠይቅ
መሆኑና ከዘርፍ የሚገኘው ውጤት ጊዜ ወሳጅ መሆኑ፣ በቂ የግብአት አቅርቦትና የመሰረተ
ልማት አለማሟላት፤ በቂ የገበያ ትስስር አለመፈጠሩ፣የተጠናከረ የኢንተርፕራይዝ
ኤክስቴንሽን አገልግሎት አለመስጠት፤ በቂና ሊተገበሩ የሚችል የንግድ ስራ እቅድ
ማደራጀት ለመቻል፤ በቂ እውቀትና ክህሎት ሳይኖራቸው ወደስራ ማስገባት፤ የመረጃ
አያያዝ ችግር መኖር፤ ለአብነት ይጠቀሳሉ፡፡ ከላይ በተጠቀሱትና ሌሎች የተቋማት በብዛት
መክሰም ተከስቷል፡፡ ስለሆነም የተጠቀሱ ችግሮችን ለመቅረፍ በቀጣዮ እቅድ ዘመን
የእድገት ተኮር ዘርፎች ላይ በማተኮር የኢንተርፕራይዞችን ቀጣይነት ማረጋገጥ፤

10 2013 -2022 / Page


45
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የቴክኖሎጂ አቅርቦትን ማጠናከር፤ የገበያ ትስስርና የኢንተርፕራይዞቸን የተጠናከረ መረጃ


በብቃት በመተንተንና በመሰብሰብ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት ይኖርበታል፡፡

የገበያና ግብይት ትስስር አፈጻጸም


በሀገር ውስጥ ገበያ በዕድገት ተኮር ዘርፍ የተሰማሩትን ኢንተርፕራይዞች ምርትና
አገልግሎት ከመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ከተቋማት ጋር እርስ በርስ በገበያ
በማስተሳሰር ከሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ 518625000 በማድረስ ለ 7000
ኢንተርፕራይዞች እና 20745 አንቀሳቃሾችን ተጠቃሚ በማድረግ የገበያ ተወዳዳሪነትን
ለማሳደግ በተያዘው ዕቅድ በኢንተርፕራይዝ 4325 አፈፃፀሙ 61% በአንቀሳቃሾች
ወንድ 9515 ሴት 7150 በድምሩ 16665 በአፈፃፀሙ 80.3% በብር 542530010
በአፈፃፀም ከ 100% በላይ ተከናውኗል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በመምሪያ ደረጃ 6 የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽን ብር 2000500
በማስገኘት 315 ኢ/ዞችን 867 አንቀሳቃሾችን ተሳታፊ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 7
የንግድ ትርኢትና ኤግዚቪሽን የተካሄደ ሲሆን 210 ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾችን
670 በማሳተፍ ብር 3411500 አፈፃፀም ኢንተርፕራይዞች 67% በአንቀሳቃሽ 77% በብር
100% በላይ የገበያ ትስስር ተሰርቷል፡፡
የውጭ ሀገር ገበያ ትስስር በመፍጠር 600610 ሽህ ዶላር በማግኘት 50
ኢንተርፕራይዞችን እና 197 አንቀሳቃሾችን በአለም አቀፍ ገበያ በምርት ጥራትና
ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ በተሰራው ስራ 30 ኢ/ዞች 75 አንቀሳቃሾች በማሳተፍ
185670 ሽህ ዶላር የተገኘ ሲሆን በአፈፃፀም ኢንተርፕራይዝ 60% በአንቀሳቃሽ 38%
በገንዘብ 30% ማከናወን ተችሏል ፡፡
የዕድገት ደረጃ ክፍተትን መሰረት ባደረገ የኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ድጋፍ
ለ 5780 ኢ/ዞች ቅድመ ኦዲትና ለ 3910 ኦዲት አገልግሎት በመስጠት ከደረጃ ደረጃ
በማሸጋገር የመፈፀም አቀማቸውን ማሳደግ በተመለከተ ለ 7685 ኢንተርፕራይዞች
የቅድመ ኦዲት አገልግሎትና ለ 3320 ኢንተርፕራይዞች Y ሂሳብ ምርመራ ምርመራ
አገልግሎት፡፡ አፈፃፀሙ ቅድመ- ኦዲት ከ 100% በላይ ሲሆን የኦዲት ምርመራ 85%
ማከናወን ተችሏል ፡፡ የቁጠባና የብድር አገልግሎት ለጥቃቅንና አነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ ችግር ለመቅረፍ የብድር አቅርቦት ከነበረበት ብር
130935732 ይቆጠባል ተብሎ ሲታቀድና 375203600 ብር ብድር ስርጭት ለ 6700
ኢንተርፕራይዞችና ለ 20300 አንቀሳቃሾች ለማሰራጨት በታቀደው መሠረት

10 2013 -2022 / Page


46
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

29220540 ብር ብድር የተሰራጨ ሲሆን 4450 ኢንተርፕራይዞችን ወንድ 2850 ሴት


2697 በድምሩ 5547 አንቀሳቃሾች የብድር አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሆነዋል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስትራቴጅ በሃገሪቱ ብቁ ተነሳሽነትና የፈጠራ ክህሎት
ያለው ሰራተኛ ሃይል በመፍጠር በሀገራችን ድህነትን ማስወገድና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ ነው። በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ፍላጎት ላይ
የተመሠረተና ከፍተኛ ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በሁሉም
ደረጃ ክህሎታቸውን ለማዳበር ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ የተመቻቸ ነው።
የህገወጥ ድርጊት መከላከል ደንብ ማስከበር ተግባር አፈጻጸም
ስራውን ለማጠናከር በየጊዜው ክትትልና ድጋፍ ሲደረግ የቆየ ቢሆንም በውጤት ደረጃ ብዙ ለውጥ
ያላመጣና ችግር ፈች አለመሆኑ መገንዘብ ተችሏል፡፡በአጠቃላይ ሲታይ ተግባሩ በሚገባዉ ደረጃ
ላይ ደርሷል ባይባልም የተሻለ ቁመና ፈጥሮ ተልዕኮዉን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ የተግባራት
አፈጻጸሞቹም ውጤታማ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
ይሁን እንጅ በታታሪነት መጓደልና ከኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር መውጣት
ባልቻሉ በአመራሮችና ፈጻሚዎች ምክንያት ዛሬም እንደትናንቱ የመልካም አስተዳደር
ችግር ያለባቸዉ ወገኖች ስላሉንና ልማታዊ አስተሳሰብ የበላይነቱን ስላልያዘ ከችግሩ
ለመውጣት ጠንካራና የማያቋርጥ ትግል ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ለዉጤታማ የተግባር
አፈጻጸም ከጠራ አመለካከት ቀጥሎ የተሟላ እውቀትና ሥነ-ምግባር ወሳኝ ናቸው ፡፡
በመሆኑም ለአመራሩና ፈጻሚዉ በማያቋርጥ መንገድ እውቀትና ሥነ-ምግባር የሚያሳድግ
ስልጠና መስጠት የማይታለፍ ተግባር መሆን አለበት፡፡
ተግባራትን በተበተነ መንገድ በመምራት ዉጤታማ መሆን አይቻልም፡፡ በመሆኑም
በየደረጃዉ የተፈጠሩ አደረጃጀቶች በሰዉ ኃይል እንዲሟሉና ምቹ የስራ ቦታ
እንዲፈጠርላቸዉ አስፈላጊዉን ግብዓት በማሟላትና ያለውን በስርዓት በመጠቀም
አደረጃጀቶቹ በተግባር ላይ ተመስርተዉ አቅማቸዉን እየገነቡ እንዲቀጥሉ ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ የጽ/ቤት አደረጃጀት እያደገ ከመሄዱ ጋር በተያያዘ፣መዋቅራዊ ሽግግሩ
የሚጠይቀው የኢንዱስትሪ ልማት ሰፊ አደረጃጀት የሚጠይቅ በመሆኑ፣ የህገወጥ ተግባራት
እንቅስቃሴ ከመምሪያው የልማት ፍላጎት ጋር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ በመሆኑ፣ተቋሙ
ከመምሪያ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ በጽ/ቤት ደረጃ በተደራጀው መሰረት አደረጃጀቱን
ውጤታማ በሆነ መንገድ በማስቀጠል በከተማችን የሚስተዋለውን የህገወጥ ድርጊት
በአመለካከት፣ በክህሎትና በስነ ምግባር በብቃት ሊከላከል የሚችል ተቋም መገንባት በቀጣይ
ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡

10 2013 -2022 / Page


47
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ጽ/ቤቱ የሀገሪቱንና የክልሉን ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች በመፈፀም የዜጎችን የሠላም፣ የልማት፣


የዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ጥያቄ/ ፍላጎት ማሟላት ተቀዳሚ እና መሰረታዊ ተልዕኮው ነው፡፡
ስለሆነም የደሴ ከተማ አስተዳደር የህገ ወጥ ድርጊት መከላከል ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ተገልጋዮችንና ባለድርሻ አካላትን መለየትና አገልግሎቱንም ከዚህ አኳያ መመዘንን ተደራሽ ማድረግ
የግድ ይሆናል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር የህገ ወጥ ድርጊት መከላከል ደንብ ማስከበር ዋነኛ ተልእኮ እንቅፋት
የሆኑ ህገ ወጥ ድርጊቶችን በማስተካከል ህግ ማስከበር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የዚህ ውጤት እና ስኬት
ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሆነው አጠቃላይ ህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት ሲሆን በጽ/ቤቱ የስራ አፈፃፀም
ውጤትና ስኬት የግሉ ሴክተር፣ የሙያና የብዙሃን ማህበራት፣ የህብረት ስራ ማህበራት እና የመንግስት
መ/ቤቶችና ሠራተኞች የከተማ አስ/ተገልጋዮች/ ባለድርሻ አካላት ሲሆኑ በጽ/ቤቱ አፈፃፀም ውጤትና
ስኬት እንዲሁም የዜጎችን ተጠቃሚነት በተመለከተ የተገልጋይና ባለድርሻ አካላት ማንነት በመነሳት
የእነዚህን አካላት ፍላጎት በመለየት አገልግሎት የመስጠት ተግባር ተከናውኗል፡፡
የጽ/ቤቱን አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ፍትሀዊ ለማድረግና ችግሮችም ሲከሰቱ
ቅሬታዎችን ተቀብሎ ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት፤ ፍትህን ለማረጋገጥና አገልግሎት
አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ፤ ደንበኞች የሚፈልጉትን ኃላፊም ይሁን ባለሙያ በቀላሉ
ለማግኘት የሚያስችል በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ከነዚህም ተግባራት መካከል
የደንበኞች አገልግሎት ደረጃ የዜጎች ቃልኪዳን ማዘጋጀት፣ ተገልጋዮች በተቋሙ አገልግሎት
አሰጣጥ ዙሪያ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት የሃሣብ መስጫ ሳጥኖችና
መዛግብቶች እንዲሟሉ ማድረግ ይገኙበታል፡፡ይሁን እንጅ በአጠቃላይ የደንበኞች እርካታ
ሊያመጣ የሚችል አገልግሎት በመስጠት በኩል ከላይ የተቀመጡት ስራዎች የተሰሩ
ቢሆንም አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ክፍተት ነበር፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የጽ/ቤቱ አመራሮች
ፈፃሚዎች ለአገልግሎት አሰጣጥ ተመሳሳይ ግንዛቤና ተነሳሽነት የሌላቸው መሆኑ ነው፡፡ይህ
የሚያሳያው በቀጣይ እቅዶቻችን ለመፈፀም የሚያስችል ከአመራሩ እስከ ፈፃሚው ብዙ
ስራ መስራት የሚጠይቅ መሆኑ ነው ፡፡

2.2.4 ማህበራዊ ልማት ዘርፍ ተግባር አፈጻጸም


 የከተማ ምክር ቤት ተግባር አፈጻጸም
10 2013 -2022 / Page
48
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የደሴ ከተማ ም/ቤት መደበኛ ጉባዔ በም/ቤቱ የአሰራር ስነ-ስርዓትና የስነ -ምግባር ደንብ
ቁጥር 10/2006 ዓ.ም መሰረት በአመት 4 ጊዜ መደበኛ ጉባኤ ያካሂዳል የሚል ሲሆን
ባሳለፍናቸዉ 10 አመት 4 ጊዜ በጠቅላላዉ 40 መደበኛ እና 7 አስቸኳይ ጉባኤዎችን 100%
አካሂዷል፡፡

የቀበሌ ም/ቤቶች በአመት እያንዳንዳቸው 12 መደበኛ ጉባዔ ማካሄድ ያለባቸው መሆኑን


ታሳቢ በማድረግ በጠቅላለዉ ባሉን ቀበሌዎች በ 10 አመቱ ማካሄድ ከነበረባቸው 2160
መደበኛ ጉባዔዎች ዉስጥ የተካሄደ 1968 አፈጻጸም በአማካይ 91% ነበር፡፡ በም/ቤቶች
የሚቀረፁ አጀንዳዎች ጥራት ፣ ወቅታዊነት ፣ የሚደረጉ ውይይቶችና ክርክሮች የህዝቡን
ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ውክልናን ለመወጣት የሚደረገው ጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ
የመጣ መሆኑን ያሳያል፡፡

ይሁን እንጅ በየደረጃዉ የሚገኙ ምክር ቤቶች ተልዕኳቸዉን ለመወጣት በተቀመጠላቸዉ


የጉባዔ ጊዜ መሰረት በየወቅቱ እየተገናኙ በአካባቢያቸዉ የሰላም ፣ የልማት ፣ የመልካም
አስተዳደር፣ በወቅታዊ አጀንዳዎችና በክትትልና ቁጥጥር ስርዓት ላይ እየመከሩ ጉባዔ
የሚያካሂዱበት ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ሆኖ እያለ ባለፋት 10 አመታት የዕድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመናት የቀበሌ ም/ቤቶች ሙሉ በሙሉ ጉባዔዎችን ማካሄድ
ሲገባቸዉ በተለያዩ ምክንያቶች በተወሰኑ የቀበሌ ም/ቤቶች ላይ የጉባዔ መቆራረጦች
መኖራቸዉ በክፍተት ታይቷል፡፡

የህዝብ ውክልናን መወጣት


የፌደራል የህዝብ ተወካዮችና የክልሉ ም/ቤት አባላት በአመት 1 ጊዜ በጋራ ከመረጣቸው
ህዝብ ጋር የሚያካሄዱት የመራጭ ተመራጭ መድረክ በበቂ ዝግጅት እንዲፈፀም
ከማድረግ አንጻር በ 10 አመታት ዉስጥ በሁለቱም ም/ቤቶች ከ 2004 እስከ 2012 ዓ. ም
ድረስ በደሴ ምርጫ ክልል በተፈጠሩ መድረኮች ወንድ 9984፣ ሴት 5016 ድምሩ 15000

ታቅዶ ወንድ 5947 ፣ ሴት 4844 ድምሩ 9781 ተሳትፈዋል አፈጻጸም 65% ነው፡፡ ይሁን
እንጅ የመራጭ ተመራጭ መድረክ በተከታታይ አመታት አለመካሄዱ ህዝቡ አያዉቁንም
ማለትና በየመድረኩም የተገኘ የተሳታፊ ቁጥርም በቂ አለመሆን በእጥረት የታየ ነበር ፡፡
ምክር ቤቱ የሚያወጣቸውን ህጎች ጥራትና ተደራሽ ማድረግ፤ የከተማዉ ምክር ቤት

በተሸሻለዉ የከተሞች እንደገና ማቋቋሚያ ማደራጃና ስልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ

ቁጥር 245/2009 አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀጽ 2/ሀ/ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት የክልሉንና

10 2013 -2022 / Page


49
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የፌዴራሉን ህገ-መንግስት የማይፃረሩ ልዩ ልዩ ደንቦችን እንዲያወጣ በተደነገገዉ መሰረት


ባለፉት 10 አመታት 6 ደንቦችን አዉጥቶ ታትመዉ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ሆነዋል፡፡

ይሁን እንጅ ረቂቅ ደንቡ ከአስፈጻሚ አካሉ በወቅቱ አለመምጣት ከመጡም በኋላ
መጣደፍ ፣ በወጡ አዋጆች ላይና ደንቦች ላይ የህዝብ አሰስተያየት መድረክ ከመፍጠር አንፃር
ዝቅተኛ መሆን፣ ፣ ረቂቅ ደንቦች ከጉባኤ በፊት ረጅም ጊዜ ተሰጥቷቸዉ ቀድመዉ
መምጣት አለመቻላቸዉ ፣ ም/ቤቱ ካፀደቃቸዉ በኋላ አልፎ አልፎ በፀደቀበት አግባብ
ተግባራዊ አለመሆን እና በየደረጃው ላሉ አካላት በሚፈለገው ደረጃ ተደራሽ አለመሆናቸዉ
ባለፉት አስር አመታት በክፍተት የታዩ ናቸው፡፡

የክትትልና ቁጥጥር አፈፃፀም፤ በመንግስት አካላት አሰራርና አፈፃፀም ላይ ክትትልና


ቁጥጥር ማድረግ ለም/ቤቶች በህግ ተደንግጐ ከተሰጣቸዉ በርካታ ተግባርና ኃላፊነቶች

አንዱ ነዉ ፡፡ ከዚህም አንፃር ባለፉት 10 አመታት በተቋቋሙት ቋሚ ኮሚቴዎች


አማካኝነት በከተማ አስተዳደሩ ላይ 40 ጊዜ በጋራና በተናጠል ክትትልና ቁጥጥር ለማካሄድ
ታቅዶ 35 ጊዜ በማካሄድ 87.5% መፈፀም ተችሏል፡፡ ከክትትልና ቁጥጥር ሥራው ከሽፋን
አንፃር ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻሎች ያሉ ቢሆንም በተያዘው እቅድ ልክ መፈፀም አለመቻልና
በክትትልና ቁጥጥር የተገኙ የአሰራር ድክመቶች ፣ችግሮችና የህዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ
በማድረግ በኩል ክፍተት ይታያል፡፡

በተዋረድ ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች በየወሩና በየሩብ አመቱ በሚያደርጉት ክትትልና ቁጥጥር


የሚፈጠሩ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ለመከላከል ኃላፊነታቸዉን
ለመወጣት ጥረት አድርገዋል፡፡ ይሁን እንጅ የሴክተር መ/ቤቶች ዕቅድ በጥራት አለማቀድና
የተግባር መንጠባጠቦች ታይተዋል፡፡ ፤ ምክር ቤቱ የወሰናቸዉን የዉሳኔ አቅጣጫዎች
ተግባራዊ አለማድረግ በአንዳንድ መ/ቤቶች ተግባራዊ አለማድረግ ታይቷል፡፡
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በሚፈታ መንገድ አቅዶ አለመፈጸም የክትትልና ቁጥጥር
ስራዉ ተደራሽ አለመሆን በእጥረት የታዩ ናቸዉ፡፡
ሆኖም ግን ም/ቤቱ ተግባር እና ሃላፊነታቸውን በማይወጡ ተቋማት ላይ የማስተካከያ
ርምጃ አለመውሰዱ እና የተጠያቂነት መርህ በመከተል በኩል ሰፊ ክፍተት የታየበት አመታት
ነበር፡፡

10 2013 -2022 / Page


50
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 የሲቭል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ተግባር አፈጻጸም


 የመንግሥት ሠራተኞች

የአደረጃጀትና የአሠራር ሥርዓቱ ያለበት ሁኔታ

በዕቅድ ዘመኑ ቀልጣፋና ውጤታማ የመንግሥት አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል በተለያዩ

ጊዜያት የአደረጃጀት ለውጦች ሲደረጉቆ ይተዋል፡፡ ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ መርህን

ተግባራዊ ለማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት ሲጠናቀቅ

የሠራተኛ ድልድል ተካሂዷል::ነገር ግን በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ መ/ቤቶች የሚቀርቡ

አደረጃጀቶች ወጣቱን ትውልድ ሊያሳትፍ የሚችል የስራ መደብ ደረጃ አድርጎ በመቅረጽ

በኩል ውስንነት መኖሩ ነው፡፡

የክልሉን ተጨባጭ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ ተዘጋጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡ የተደረጉት

በተለይም ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በሲቪል

ሰርቪሱ ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንጻር ልዩ መመሪያ ተዘጋጅቶ ሥራ

ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡

በመሆኑም የተዘጋጁ በርካታ መመሪያዎች የወጡበትን አብይ ምክንያት በአግባቡ ተገንዝቦ

በየአስተዳደር እርከኑና በተለያዩ ተቋማት የሰው ሃብቱን ወጥ በሆነ መንገድ በመምራት

ረገድ አበረታች ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከዚህ አኳያ በስምሪት ሥራዎች ምርመራ/ኢንስፔክሽን እና በአስተዳደር ፍርድ ቤት

የሚከናወኑ የይግባኝ ጉዳዮች ውሳኔ አሰጣጥ ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን በዋናነት መጥቀስ

ይቻላል፡፡

የሰውሃብት ልማትና አስተዳደር ያለበት ሁኔታ

በመጀመሪያውና ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመናት የሰው ሃብት

ልማትና አስተዳደሩን ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ፍትሃዊ ለማድረግ የመንግስት ሰራተኛው ላይ

በየደረጃው ለሚገኙ የሰው ሃብት አስተዳደር ባለሙያዎችና የስራ ሃላፊዎች የግንዛቤ

ማስጨበጫ መድረኮች ተመቻችተው ተከታታይ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡ የመንግስት

ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በፈጻሚዎች ዘንድ እንዲታወቁና እንዲተገበሩ፣ የወጡ የሕግ

10 2013 -2022 / Page


51
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ማዕቀፎች በአግባቡ ስለመፈጸማቸው ተከታታይ የድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ስራዎች

እንዲሰሩ፣ በሰው ኃይል ስምሪት አፈጻጻም ላይ ይታዩ የነበሩ የአፈጻጻም ግድፈቶች

እንዲታረሙ፣እንዲሁም ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ልዩ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች

በሲቪል ሰርቪሱ ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲያድግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት

በመቻሉ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በየተቋማቱ የሚገኙ

የአመራሩንና የሠራተኛውን የመፈፀም አቅም ለማጎልበት እንዲቻል ሲቪል ሰርቪስ ከክልሉ

መንግስትና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በረዥም ጊዜ በተሰጠው

ስልጠና እድል የተወሰኑ አመራሮችና ሠራተኞች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረጉ

በአዎንታ የሚጠቀስ ተግባር ነው፡፡ይሁን እንጂ ከሲቪል ሰርቪሱ የሚጠበቀውን አገልግሎት

በመስጠት ረገድ ቀላል የማይባሉ ክፍተቶች ታይተዋል፡፡ከመንግሥት ፖሊሲዎችና

ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣመ ዕቅድ ያለማዘጋጀት፣መ/ቤቶች ከተሰጣቸው ተግባርና

ኃላፊነት ጋር ሳያዛምዱ ለፈጻሚው የትምህርት ዕድሎችን ማመቻቸት ፣አንዳንድ

የስምሪት ሥራዎችን በአድሎአዊነት መፈፀም በተሰራው ልክ የተደራጀና የተሟላ መረጃ

ለመያዝ አለመቻል የሚሉት ዋና ዋና ችግሮች ሆነው ታይተዋል፡፡

በአጠቃላይ የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር ፖሊሲ ባለመኖሩ የሰው ሀብት ልማትና

አስተዳደር ዘርፉ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠሩ በተጨማሪ የሰው ሃይል ዕቅድን፣

ምልመላና መረጣን፣ የሰው ሃይል ልማትን፣ የጥቅማ ጥቅምና ማበረታቻ ሥርዓትን፣ የስራ

አካባቢ ደህንነትና ጤንነትን፣ የሥራ አፈፃፀምም ምዘና ስርዓትን፣ የሰው ሃይል መረጃ

ሥርዓትን፣ ጥናትና ምርምርን እና ሌሎች ተግባራትን ከመሰረታዊ የኢኮኖሚ አቅም

በመነሳት በተቀናጀ አግባብ የመከታተል፣የመደገፍ፣ ሥራቸው ላይ ተረጋግተው እንዲቆዩ

እና አቅማቸውን ገንብቶ የመጠቀም ልምዱ የዳበረ አይደለም ፡፡

የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘናሥርዓት

በሁለቱም ስትራቴጂ ክዕቅድ ዘመናት ለአብዛኛው አመራርና ባለሙያ በዕቅድ ዝግጅትና

አፈፃፀምም እና ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ የመለኪያ ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ

10 2013 -2022 / Page


52
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የመንግስት ሰራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ሥራ ላይ ውሏል፡፡ ከላይ

የተገለጹት ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው ሥርዓቱን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ የተከሰቱ

ጉድለቶች፡- የተቋሙ ስትራቴጂያዊና ዓመታዊ እንዲሁም ለየቡድኑ ዕቅድ በትስስር

ለማዘጋጀት በአመራሩና በፈጻሚው የክህሎትና የአመለካከት ችግር መኖር፣የፈፃሚዎች

ግማሽ አመት ዕቅድ ከቡድኑ ዕቅድ ጋር ትስስር እንዲኖረው በማድረግ በኩል ውስንነት

መኖሩ፣በአለፉት አምስት አመታት በመምሪው ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች መካከል

በአማካይ 36.5% ለሚሆኑት የስራ አፈጻጸም ውጤት አልተሟላላቸውም ነበር፡፡

 ጤና ጥበቃ መምሪያ ተግባራት አፈጻጸም

 የከተው የጤና ዘርፍ ሁኔታ ትንተና

የማህበረሰብ ጤና የልማትና የእድገት ምንጭ በመሆኑ በአካልና በአዕምሮ ሙሉ ጤናማ የሆነ ዜጋውን
በብቃት መምራት ይችላል፡፡ አገር የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም እንዲኖራት ካስፈለገ የዜጎቿን ጤንነት
መጠበቅ፣ ለጤናው ዘርፍ የተሻለ በጀት መመደብ ይጠበቃል ይህም በፖሊሲና ስትራተጂ የሚወሰን
ይሆናል፡፡

የጤናው ዘርፍ ከሌሎች ዘርፎች ጋር በመሆን በበከተማዉ ኢኮኖሚያዊ እድገት እንዲኖረ የበኩሉን
ድርሻ እየተወጣ ይገኛል። ስለሆነም አጠቃላይ ልማቱን ለመደገፍ በጤናው ዘርፍ መዋዕለ ንዋይ
ማፍሰስ ያስፈልጋለ። ምክንያቱም በጤና ላይ ኢንቨስት ማድረግ አሁን ባለውና በቀጣይ ትውልድ ዘላቂ
ልማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ነው፡፡ ጤና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገት መለኪያ ነው። የኢኮኖሚ
እድገቱ ከማህበራዊ እድገቱ ጋር አብሮ ማደግ ካልቻለ እድገቱ ዘላቂነት አስተማማኝ ስለምሆን የጤናው
ሴክተር ለማህበራዊ ፍትህ እና ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ መሆኑ በጉልህ ታውቆ ዘርፉ ትኩረት ሊሰጠው
ይገባል።

የእናቶች እና ህጻናት ጤና አጠባበቅ

በ 2020 ከተማዉ በወሊድ ጊዜ መታፈን፣ አዲስ የተወለደ ህጻናት እና የጽንስ ጤና መታወክ እና


ድንገተኛ ራስን መሳት/ ስተሮክ ሦስቱ ዋና ዋና የጤና ችግሮች መሆናቸውን ያሳያል። ከተማዉ ባለፉት

10 2013 -2022 / Page


53
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አስርተ ዓመታት በእናቶች፣ ከአምስት ዓመት በታች ዕድሜ ያሉ ህጻናት እና ከአንድ አመት በታች
ህፃናት ሞት መቀነስ ተጨባጭ ለውጥ አስመዝግባለች፡፡ የህጻናት ሞት ምጣኔም ሲታይ ከአምሰት
ዓመት በታች ህጻናት ከ 2005 ዓ.ም ከነበረው ከ 154 ወደ 85/ 1000፤ 2006 በህይወት ከተወለዱ
ህጻናት ዝቅ ሲል ከአንድ ዓመት በታች ህጻናት ሞት ምጣኔ 94/1000፤ በ 2005 ዓ.ም ከነበረው ወደ
67/1000 በ 2006 ዓ.ም መቀነስ ተችሏል፡፡

የጨቅላ ህጻናት ሞት ግን ብዙም ሳይቀንስ በ 2006 ዓ.ም እንዳለው ሳይቀንስ 47/1000 ቆይቷል፡፡
አዲስ የተወለዱ ህጻናት ሞት ከጠቅላለው የህጻናት ሞት 43% ያህል ስጋት እንደያዘ በዚህ አምስት
አመት ቆይቷል፡፡

ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች

በከተማው ለሰዎች ሞት፣ ህመም እና ስቃይ ምክንያት የሆኑት ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች
ሲሆኑ በማንኛውም የእድሜ ክልል ውስጥ ያለ ሰው የሚጠቃ ቢሆንም በህጻናት እና በመውለጃ
የእደሜ ክልል ውስጥ ባሉ እናቶች ላይ ያመዝናል፡፡

በከተማው ዋና ዋና የሞት እና የህመም መንሰኤ የሆኑት ተላላፊ በሽታ፣ ከእናቶች ጤና፣ አዲሰ
ከተወለዱ ህጻናት ጤና እና ከምግብ ጋር የተያያዘ በሽታዎች ናቸው፡፡ በተመሳሳይ በብዛት የሚከሰቱ
በሽታዎች እንደ ወባ፣ ኤች.አይ.ቪ.እና በክትባት ልንከላከላቸው የምንችላቸው በሽታዎች ሊመጣ
ከሚችል ስቃይ እና ሞት ባልተጠበቀ ሁኔታ ሊቀንስ ችሏል፡፡

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እንደ የአዕምሮ ጤና መታወክ መጨመር ባሻገር የከተሞች መስፋፋት፣
የአኗኗር ዘየ መቀየር ተጨማሪ ጫና እየፈጠረ ይገኛል፡፡ተላላፊያልሆኑበሽታዎች አሰተዋጽኦም እ.ኤ.አ.
በ 2017 ለቅድመ ብስለት ሞት በመዳረግ በቅደም ተከተል 6 ኛ እና 10 ኛ ከሆኑት አብሮ ከሚወለድ
የጤና እክል እና ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የደም መጠን ማነስ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የልብ በሽታ ጋር
ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ የመጨመር ሁኔታ ታይቶባቸዋል።

እ.ኤ.አ. ከ 2007 እስከ 2017 ባለው ጊዜ ውስጥ ኩፍኝ፣ ኤች አይ ቪ እና የታችኛው የመተንፈሻ


አካላት ቁስለቶች ለቅድመ ብስለት ሞት የነበራቸው አስተዋጽዖ በአንጻራዊ ሁኔታ ሲታይ የመቀነስ
ሁኔታ ታይቷል፡፡ በኩፍኝ ምክንያት የሚከሰት ሞት በአስር አመት ጊዜ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ 78.4
ከመቶ ቀንሷል እናም ከ 10 ቀዳሚ ገዳይ በሽታዎች ዝርዝር ውስጥ የለም፡፡ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች
ወደ ሰውነት የሚሰራጭ የደም መጠን ማነስ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የልብ እና በተለያዩ ምክንያቶች
በሚከሰት የጉበት (cirrhosis) ጋር በመሆን ከቀዳሚ 10 ገዳይ በሽታዎች ውስጥ የገቡ ሲሆን ላለፉት
አስርት ዓመታት በቅደም ተከተል በ 6.4% እና በ 17.2% የመጨመር ሁኔታ ታይቶባቸዋል።

10 2013 -2022 / Page


54
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በተጨማሪም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከተማዋ ለአካል ጉዳት ዋና መንስኤዎች ሆነዋል፡፡እ.ኤ.አ


በ 2017 በኢትዮጵያ የአካልጉዳት/አቅመ ውስኑነት መንስኤ ከሆኑት ዋና ዋና በሽታዎች መካከል
የመጀመሪያዎቹ ስድስቱ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ሲሆኑ ዝቅተኛ የጀርባ ህመምና የመጨነቅ/ድብርት

ህመም አካልጉዳት/አቅምውስንነት በማስከተል በቅደም ተከተል 1 ኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይይዛሉ።

ከተማችን ስር በሰደደ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በይበልጥ የተጋለጠ ሲሆንችግሩን ለመቀነስ የተለያዩ
ጥረቶች ተደረግዋል፡፡ በተደረገው ጥረትም በመጠኑ የመሻሻል ሁኔታ እያሳየ መሆኑን የጥናቶች
EDHS 2000 እሰከ 2010 ጥናቶች ያመላከቱ ሲሆን መቀንጨር ከ 57% ወደ 41%፣ ዝቅተኛ
ክብደት ከ 52% ወደ 27% እና ከባድና የሚታይ ደግሞ ከ 10% ወደ 8% ሊቀንስ ችሏል፡፡

 የትምህርት መምሪያ ተግባራት አፈጻጸም


የትምህርትና ስልጠና ተደራሽነት እና ተሳትፎ አስመልክቶ

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ አፈጻጸም

የቅድ መመደበኛ ትምህርት መርሀ ግብር ህፃናት ለተስተካከለ የአካልና የአእምሮ፣የስሜትና

የማህበራዊ ግንኙነት እድገት በማዳበር እንዲዘጋጁ የሚያመቻች ሲሆን ይህንን አገልግሎት

ለማስፋፋት በከተማችን ልዩ ትኩረት በመስጠት በልዩ ልዩ አማራጮች ማለትም የ”ኦ“

ክፍል በማደራጀት ህፃናት ትምህርት እንዲያገኙ በማድረግ በስፋት በማዳረስ ላይ ሲሆን

በ 2007 ዓ.ም በ 30 አጸደ ህጻናት እና በ 25 ህ/ብ አቀፍ ቅድመ መደበኛ ት/ቤትወንድ 2533

ሴት 3226 በድምሩ 5759 ህፃናትን ተቀብሎ ማስተማር ታቅዶ ጥቅል የትምህርት

ተሣትፎው ወንድ 3348 ሴት 3144 በድምሩ 6429 ሲሆን አፈጻጸሙ 111% ነበር፡፡ በ 2012

ዓ.ም ደግሞ ወንድ 5968 ሴት 5683 ድምር 11651 ህፃናትን ለማስተማር ታቅዶ ጥቅል

የትምህርት ተሣትፎ ክንውን ወንድ 5438 ሴት 5278 ድምር 10716 ወይም 91.97%

ደርሷል፡፡ ወንድ 91.11% ሴት 92.87% ከመነሻው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ 2012 ዓ.ም ጥቅል

የትምህርት ተሣትፎ ቀንሷል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ አፈጻጸም

10 2013 -2022 / Page


55
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የመጀመሪያ ደረጃት ምህርት በስድስት ዓመት የሚጠናቀቅ ሆኖ፣ በመሠረታዊና አጠቃላይ

ትምህርት ለሚቀጥለው የትምህርት ደረጃ የሚያዘጋጅና መርሀ ግብሩ መሠረታዊ

ትምህርትን (ማንበብ፣ መፃፍ፣ሃሣብን በቃል መግለጽ፣ መሠረታዊ ስሌትና ችግሮችን

መፍታት መቻልን) ለተማሪዎች የሚያስጨብጥ ሲሆን በ 2007 ዓ.ም 1 ኛ ደረጃ ት/ቤት

በ 27 የመንግስት እና በ 11 የግል በድምሩ 38 ት/ቤቶች በድምሩ 27746 ወንድ 14162 እና

ሴት 13584 ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል የትምህርት ተሣትፎው 111% የነበረ ሲሆን

በ 2012 ዓ. ም ደግሞ 32 የመንግስት እና 16 የግል 1 ኛ ደረጃና በድምሩ በ 48 ት/ቤቶች

27841 (14145 ወንድ ፣ 13669 ሴት) ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል የትምህርት

ተሣትፎው 96.69% (ወንድ 96.15%፣ሴት 97.25%) ደርሷል፡፡በሌላ በኩል ከንጥር

የትምህርትተሣትፎ አኳያ በ 2007 ዓ/ም 111% ከነበረው ሲነጻጸር በ 2012 ዓ/ም 96.69%

(ወንድ 96.15%፣ሴት 97.25%) ደርሷል፡፡

የሁለተኛ ደረጃ (9-10 ክፍል) ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ አፈጻጸም

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዓላማ በመካከለኛ ደረጃ የተማረ የሰው ሃይል ማፍራትና

ወጣቶችን ለከፍተኛ ትምህርት ማዘጋጀት ሲሆን በዚህ መርሃግብር ዘመን ጥራቱንና

ፍትሃዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቷል፡፡

ይህዘርፍየመካከለኛገቢራዕያችንንበአጭርጊዜውስጥለማሳካትቴክኖሎጂየሚጠቀም፣በእው

ቀት፣በክህሎት፣በአስተሳሰብ፣በችሎታና በተወዳዳሪነት ላይ የተመሰረተ ዜጋ ለማፍራት

ጥረት ተደርጓል በመሆኑምበ 2007 ዓ.ም 11077 (ወንድ 5601 ሴት 5476) ተማሪዎችን

በማስተማር የደረጃውን ጥቅል የትምህርት ተሳትፎ ምጣኔ 145% (ወንድ 147.9%፣ ሴት

142.49%) የነበረሲሆን እስከ 2012 ዓ.ምደግሞ 12598 (ወንድ 6205፣ሴት 6393)

ተማሪዎችንበማስተማርጥቅልየትምህርትተሣትፎው 109.66% (110.31% ወንድ፣

109.04% ሴት) ማድረስ ተችሏል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ (11 ኛ-12 ኛክፍል) ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ አፈጻጸም

10 2013 -2022 / Page


56
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ተማሪዎችን ለከፍተኛ ትምህርት ማዘጋጀትና ተማሪው በምርጫው መሠረት በተማረውና

በሰለጠነበት ሙያ በቂ ችሎታና ክህሎት ኖሮት በቀጥታ በሚመለከተው የሥራ መስክ

ተሰማርቶ መስራት እንዲችል ሲሆን በዚህ መርሃግብር ትኩረት የተሰጠው ጥራቱንና

ፍትሃዊነቱን በጠበቀ መልኩ የደረጃውን ትምህርት ማስፋፋት ነበር፡፡ በዚህ መሠረት በ 2007

ዓ.ም 2928 (ወንድ 1476፣ሴት 1452) ተማሪዎችን በማስተማር የደረጃውን ጥቅል

የትምህርት ተሳትፎ ምጣኔ 56.34% (ወንድ 15.5%፣ሴት 13.17%) የነበረ ሲሆን በ 2012

ዓ.ም ደግሞ 6156 (ወንድ 3044፣ሴት 3112) ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል የትምህርት

ተሣትፎው 38.16% (38.91% ወንድ፣ 37.38% ሴት) ማድረስ ተችሏል፡፡

የልዩ ፍላጎት ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ አፈጻጸም

ልዩ ፍላጐት ያላቸውን ጨምሮ ሁሉም ህፃናትና ወጣቶች እንደ ችሎታቸውና እንደ

ፍላጐታቸው መማር ያለባቸው ሲሆን መርሀ ግብሩ በከተማችን የሚሰጠው የመጀመሪያው

ከ 1 ኛ-4 ኛ ክፍል ላሉ ህፃናት የተለየ ክፍል በማደራጀት የሚሰጥ ሲሆን መርሀ ግብሩ

በከተማችን የሚሰጠው ሁለተኛው ደግሞ ከ 5 ኛ -12 ኛ ክፍል ላሉ ህፃናት በአካቶ

ትምህርት መርሀ ግብሩ አማካይነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረት በ 2007 ዓ.ም 216

ህፃናት በቅድመ መደበኛ ትምህርት መርሀ ግብሩን በመከታተል ላይ የነበሩ ሲሆን

ከመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ትምህርት አንፃርም በ 2007 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ 158

(ወንድ 103፣ሴት 55) ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን ይህም መሻሻልን በማሣየት በ 2012 በጀት

ዓመት በት/ቤቶች (ወንድ 128፣ሴት 99) ደርሷል፡፡ በመሆኑም በ 2007 ዓ.ም 65.4% (ወንድ

76.5%፣ሴት 56.7%) የነበረው ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ በ 2012 ዓ.ም 82.41% (ወንድ

85% ፣ ሴት 79.17%) ሆኗል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መርሀ ግብሩ ደግሞ በ 2007

ዓ.ም 65.4% (ወንድ 76.5%፣ሴት 56.7%) ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል የትምህርት

ተሣትፎ ነበረው፡፡

በ 2012 ዓ.ም ደግሞ 40 (ወንድ 25፣ሴት 15) ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ጥቅል

የትምህርት ተሣትፎው 82.4% (ወንድ 63.33%፣ሴት 106.25%) ደርሷል፡፡

የጎልማሶችና መደበኛያልሆነ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ አፈጻጸም

10 2013 -2022 / Page


57
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የጎልማሶች ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ምርታማነቱን፣ ጤናውን፣ ኑሮውንና ማህበራዊ

ተሣትፎውን ትርጉም ባለው ሁኔታ እንዲያሻሽል ማድረግ ያስፈልጋል ፡፡ በመሆኑም

የፌደራል ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በ 2009 ዓ.ም በወጣው ሪፖርት መሰረት

በከተማችን ከሚኖረው ጎልማሣ መካከል ማንበብና መፃፍ የማይችሉት 19.8% (ወንድ

16.71%፣ሴት 21.4%) ይሆናሉ፡፡ ከዚህ መካከል አብዛኛው በገጠር አካባቢ የሚኖረው ህዝብ

ነው፡፡ከዚህ አንፃር የክልላችን 47.28% (58.74% ወንድ፣ 36.75% ሴት) እና የከተማችን

55.8% (55.62% ወንድ፣ 56.05% ሴት) አፈጻጸም ስናየው መካከለኛ ገቢካላቸው አገሮች

(76.4%) ተርታ ለመሰለፍ በሚቀጥሉት ጊዚያት በጣም በርካታ ስራ መፈፀም ይጠብቀናል፡፡

የትምህርት ፍትሃዊነትን፤አካታችነት አፈጻጸም

የትምህርት ጥቅል ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት አፈጻጸም

የአንድ የትምህርት ስርጭት ፍትሃዊነት ከሚገለጽባቸው መለኪያዎች አንዱ በወንድና

በሴት መካከል ያለውን የትምህርት ስርጭት ማመጣጠን ነው፡፡ ከዚህም በመነሣት

በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር መጨረሻ ላይ በሁሉም ደረጃዎች ላይ

በጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት 1 ለማድረስ ታቅዶ የተለያዩ ተግባራት

ተከናውነዋል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት ተግባራት ድምር ውጤትም ሲታይ የጥቅል ትምህርት

ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት በተመለከተ በ 2007 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ 48% በአጠቃላይ 2 ኛ

ደረጃ 41% ላይ ደርሶ ነበር፡፡ይህም መሻሻልን በማሣየት በ 2012 ዓ.ም እንደየ ቅደም

ተከተላቸው በመጀመሪያ ደረጃ 0.84 እና በአጠቃላይ 2 ኛደረጃ 0.91 ሆኗል፡፡

ይህም በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር የሴቶችን ትምህርትተሣትፎ

ከወንዶች ጋር በማመጣጠን ረገድ የተከናወኑ ተግባራትና የተገኘው ተጨባጭ ውጤት

አበረታች መሆኑን ያመለክታል፡፡

 የትምህርት ፍትሃዊነትን፤አካታችነትን አንፃር

ከቅድ መ አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ለሚገኙ ተማሪዎች ትምህርትን በፍትሀዊነትና

በአካታችነት ተደራሽበ ማድረግ ብዝሀነትን ያረጋገጠ፣ ፍላጎትና ችሎታን መሰረት ያደረገ

10 2013 -2022 / Page


58
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ለዜጎች ማድረስ ነው፡፡በተለይም ይህ ሁኔታ ጎልቶ

የሚታየው በሴት ተማሪዎች፣ በገጠራማ ቀበሌዎች እና አስቸጋሪ አካቢዎች በሚኖሩ

ልጆች፣በከተማ በሚኖሩ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ቤተሰብ ልጆች ፣በአካል

ጉዳተኞች፣ኤች.አይቪ. ኤድስ በደማቸው ባለባቸውና ከፍተኛ የጤና ችግር በሚታይባቸው

ልጆች፣ በስደተኞች፣በጎዳና ተዳዳሪዎችና ሌሎች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ልጆችን

ያካትታል፡፡ እነዚህን ቁልፍ ተግዳሮቶች ለመፍታት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ

ደረጃ ትምህርት ተደራሽ፣ጥራቱን የጠበቀ፣ ፍትሀዊና አካታች ትምህርትና ስልጠና ለዜጎች

ለማዳረስ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራባቸው ይገባል፡፡

የከተማ-ገጠር ትምህርት ጥቅል ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት አፈፃፀም

በከተማ እና በገጠር የሚታየውን የትምህርት ስርጭት አለመመጣጠን ለማጠበብ ትኩረት

የተደረገው በገጠር አካባቢዎች ትምህርትን ማስፋፋትሲሆን በዚህ መሰረት በመጀመሪያ

ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም በ 2007 ዓ.ም 0.84 የነበረው በጥቅል የትምህርት ተሣትፎ

የገጠር-ከተማ ክፍተት እስከ 2012 ዓ/ም ድረስ 0.6 (0.29 ወንድ፣ 0.29 ሴት) ደርሷል፡፡

ስለሆነም ክፍተቱ ከመጥበብ ይልቅ እየሰፋ በመሄድ ላይ በመሆኑ በእቅዱ ዓመታት ገጠርን

ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን አልሞ መስራት የሚጠይቅ ይሆናል፡፡

የልዩ ፍላጎት ትምህርት ጥቅል ፆታዊ ክፍተት አፈጻጸም

ከመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ትምህርት አንፃር በ 2007 ዓ.ም በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች

158 (ወንድ 103፣ሴት 55) ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን ይህም መሻሻልን በማሣየት እስከ 2012

በጀትዓመት 227 (ወንድ 128፣ሴት 99) ደርሷል፡፡በመሆኑም በ 2007 ዓ.ም 65.4% (ወንድ

76.5%፣ሴት 56.7%) የነበረው ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ በ 2012 ዓ.ም 82.41% (ወንድ

85%፣ ሴት 79.17%) ሆኗል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መርሀ ግብሩ ደግሞ በ 2007 ዓ.ም

65.4% (ወንድ 76.5%፣ሴት 56.7%) ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል የትምህርት ተሳትፎ

ነበረው ፡፡ በ 2012 ዓ.ም ደግሞ 40% (ወንድ 25፣ሴት 15) ተማሪዎችን ተቀብሎ

በማስተማር ጥቅል የትምህርት ተሣትፎው 82.4% (ወንድ 63.33%፣ሴት 106.25%)

ደርሷል፡፡

10 2013 -2022 / Page


59
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የጎልማሶችና መደበኛያልሆነ ትምህርት ጥቅል ፆታዊ ተሳትፎ አፈጻጸም

የፌደራል ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ በ 2009 ዓ.ም በወጣው ሪፖርት መሰረት

በከተማችን ከሚኖረው ጎልማሣ መካከል ማንበብና መፃፍ የማይችሉት 19.8% (ወንድ

16.71%፣ሴት 21.4%) ይሆናሉ፡፡ ከዚህ መካከል አብዛኛው በገጠር አካባቢ የሚኖረው ህዝብ

ነው፡፡ከዚህ አንፃር የክልላችን 47.28% (58.74% ወንድ፣ 36.75% ሴት) እና የከተማችን

55.8% (55.62% ወንድ፣ 56.05% ሴት) አፈጻጸም ስናየው መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች

(76.4%) ተርታ ለመሰለፍ በሚቀጥሉት ጊዚያት በጣም በርካታ ስራዎችን መፈፀም

ይጠብቀናል፡፡

 ከትምህርት ውስጣዊ ብቃትና ጥራትን ማስጠበቅ አኳያ

የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትተማሪዎች ማቋረጥ እና ክፍል መድገም አፈፃፀም

በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም በ 2007 ዓ.ም 2.8% የነበረውን የማቋረጥ ምጣኔ

በ 2012 ዓ.ም 0.6% ለማድረስ፣እንዲሁም በ 2007 ዓ.ም 8.08% የነበረውን ክፍል

የመድገም ምጣኔ በ 2012 ዓ.ም 2% ለማድረስ ታቅዶ ነበር፡፡በዚህም መሠረት በዓመታዊ

የትምህርት ስታስቲክስ የተረጋገጠ ባይሆንም እስከ 2012 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች

ማቋረጥ ምጣኔ 0.6% (0.68% ወንድ፣ 1.02% ሴት) ነበር፡፡ የተማሪዎችን ክፍል መድገም

ከ 2% እንዳይበልጥ ለማድረግ ታቅዶ በ 2011 የትምህርት ዘመን ለፈተና ከተቀመጡት

መካከል በነበሩበት ክፍል የደገሙት 1.06% (1.36% ወንድ፣ 0.74% ሴት) ናቸው፡፡

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ማቋረጥ እና ክፍል መድገም አፈፃፀም

በ 2007 ዓ.ም 2.6% (1.1% ወንድ፣ 1.5% ሴት) የነበረውን የአጠቃላይ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት

ማቋረጥ በ 2012 ዓ.ም 2.82% ማድረስ ግብ ተጥሎ ፡፡ እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት

መሠናዶ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም በተመለከተ በ 2007 ዓ.ም 3.61% (3.64%

ወንድ፣ 3.56% ሴት) የነበረውን የደረጃውን ትምህርት ማቋረጥ እስከ 2012 ዓ.ም 2%

ለማድረስ ታቅዶ በ 2012 ዓ.ም የተማሪዎች ማቋረጥ በተመለከተ በአጠቃላይ 2 ኛደረጃ

2.82% (3.38% ወንድ፣ 2.27% ሴት) ሆኗል፡፡

ተማሪዎች ጥቅል ውጤት ምዘና አፈጻጸም

10 2013 -2022 / Page


60
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በትምህርት ዘርፍ ልማትመርሃ ግብር የተማሪዎች ውጤት የትኩረት ጉዳይ ሲሆን በ 2007

ዓ.ም ዕቅድ ዘመን በየደረጃው የሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች 50% እና በላይ፣ 35% የሚሆኑ

ተማሪዎች 75% እና በላይ እንዲሁም 15% የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ 85% እና ውጤት

ማምጣት የሚል ግብ ተጥሎ በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን አፈፃፀሙ

እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ከዚህ አኳያ የተገኘው ውጤት ሲታይ በ 2007 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት

ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል 50% እና በላይ ያስመዘገቡት 75.38% (ወንድ

78.79%፣ሴት 72.26%) ሲሆኑ ይህም በ 2011 ዓ.ም 73.41% (ወንድ 72.29%፣ሴት

74.57%) ደርሷል፡፡ የተማሪዎች ውጤት ሲታይ በ 2007 ዓ/ም የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ

ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱት መካከል ወደ ከፍተኛ ትምህርትመሠናዶ 2 ኛ

ደረጃ ት/ቤት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡት 45.35% (ወንድ 49.21%፣ሴት 41.85%)

ሲሆኑ ይህም በ 2011 ዓ.ም 74.20% (ወንድ 73.48%፣ሴት 74.88%) ደርሷል፡፡

እንዲሁም በ 2007 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ከወሰዱት መካከል

ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያውጤት ያስመዘገቡት 57.99% (ወንድ 62.41%፣ሴት 49.44%)

ሲሆኑ ይህም በ 2011 ዓ.ም 61.48% (ወንድ 62.40%፣ሴት 60.45%) ደርሷል፡፡

ንጥር የትምህርት ተሳትፎ

መምህራን ጥቅል የማስተማር ብቃት አፈጻጸም

በማንኛውም ት/ቤት የመምህራን ችሎታና የሥራ አፈፃፀም ለትምህርት ጥራት መጠበቅ

ወሣኝ ጉዳይ በመሆኑ የሰርተፊኬት የትምህርት ዝግጅት ያላቸውን መምህራን በዲኘሎማ

ደረጃ፤ ዲፕሎማ ያላቸውን በዲግሪ ፤ዲግሪ ያላቸውን በሁለተኛ ዲግሪ ለማሰልጠን

ታቅዷል፡፡ በዚህም መሠረት ከ 2007 ዓ.ም እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የቅድመ መደበኛ

ትምህርትመምህራን 373 (ወንድ 1፣ሴት 372) የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትመምህራን፣ 490

(ወንድ 192፣ሴት 298) ፤ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ 9-10 ኛ ክፍል የሚያስተማሩ

መምህራን 423 (ወንድ 273፣ሴት 150) ፣ ከ 11-12 ኛ ክፍል የሚያስተማሩ መምህራን 92

(ወንድ 80፣ሴት 12) ናቸው፡፡ በመሆኑም የማስተማር ብቃትን ለማሻሻል የተሄደው ርቀት

10 2013 -2022 / Page


61
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በ 2007 በመጀመሪያ ደረጀ ትምህርት ላይ 88.1% (ወንድ 87% ሴት 88.6%) ሲሆን

በ 2011 98.5%(ወንድ 98.4% ሴት 98.5%) ሁለተኛ ደረጃ ት/ት መርሃ ግብር ላይ በ 2007

99.2%(ወንድ 99.3% ሴት 98%) የነበረ ሲሆን በ 2011 69.7% (ወንድ 69.9% ሴት 68%

ማሟላት ተችሏል፡፡

የት/ቤት የማስተማር ደረጃ ጥቅል አፈጻጸም

በየደረጃው የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ቁጥጥር አደረጃጀት ማጠናከርና አቅም መገንባት

በተመለከተ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ቁጥጥር ለማካሄድ በታቀደው

መሠረት በ 2012 የትምህርት ዘመን በከተማችን የሚገኙትን 27 የአፀደ ሕፃናት ት/ቤቶች

ደረጃ 2፤ ሃያ ት/ቤት እና ደረጃ 3፤ አንድ ት/ቤት ሲሆኑ ፤ የመጀመሪያ ዙር 7 ቁጥጥር

አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 7 (100%) አገልግሎቱን አግኝተዋል። ከ 40 በቅድመ መደበኛ

ት/ቤት ደረጃ 1- እንድ ፤ደረጃ 2 - ሰባት ፤ደረጃ 3- ሃያ ስምንት ት/ቤት ፤ከ 48 መጀመሪያ

ደረጃ ት/ቤቶች 33 ታቅዶ 12 ተከናውኗል 36.3% ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ደረጃ 2 - ሃያ

አንድ ት/ቤት እና ደረጃ 3 - ሃያ አራት ት/ቤት ፤ከ 13 የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስንመለከት 4

ት/ቤት ታቅዶ 2 ተተግብሯል (50%) ከዚህ በመነሳት አብዛኛዎቹ ደረጃ 2፤ ስድስት ደረጃ

3፤ ስደስት እና ደረጃ 1፤ አንድ ት/ቤት ላይ ይገኛሉ፡፡

በአጠቃላይ የትምህርት ተሣትፎ/ተደራሽነት እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናትንና


ነባር ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት መረጃን በጥራት የመለየት፣ የመመዝገብና ወደ
ት/ቤት እንዲመጡ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር የተማሪዎችን ምዝገባ በአጭር ቀናት
የማጠናቀቅ አቅም መፍጠር ተችሏል፡፡ የትምህርት ፍትሃዊነት የትምህርት ፍትሀዊነትን
ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለው ምጥጥን በእጅጉ
ማቀራረብ ከመቻሉም በላይ በ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት (9-10 ኛ ክፍል) የሴቶች ድርሻ በልጦ
ታይቷል፡፡ በገጠርና በከተማ መካከል ያለው ክፍተት አሁንም ትኩረት የሚሻ ቢሆንም
አፈጻጸሙ በከፍተኛ ደረጃ መሻሻል አሳይቷል፡፡

የትምህርት ጥራት አዲስ ገቢ የአንደኛ ክፍል ተማሪዎችን በተቀመጠው ደረጃ መሠረት


የማንበብ፣ መፃፍና ማስላት መሠረታዊ ክህሎቶችን እንዲችሉ ማድረግ አስመልክቶ
ተጨባጭ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ የአምስተኛ ክፍል ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋን

10 2013 -2022 / Page


62
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በብቃት መናገር፣ ማንበብና መፃፍ ማስቻል በተመለከተ በት/ቤቶች ተጨባጭ ውጤቶች


ታይተዋል፡፡ በየዓመቱ ሁሉም ተማሪዎች በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች 50% እና በላይ
እንዲያስመዘግቡ በተደረገው ርብርብ ለደረጃው የተቀመጠውን ትምህርት በሚገባ
አጠናቅቀው ወደ ቀጣይ ደረጃ የተሸጋገሩት ተማሪዎች ብዛት እንዲጨምር አስችሏል፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው ደረጃ መሠረት መምህራንን ለየደረጃው ብቁ እንዲሆኑ
ለማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት በቅድመ ሥራና በሥራ ላይ ሥልጠና በተደረገው ጥረት
በሁሉም ደረጃዎች የት/ቤት አመራሮችና መምህራን ለደረጃው የተቀመጠውን ፕሮፋይል
እንዲያሟሉ ተደርጓል፡፡ በየዓመቱ የክልላችን መንግሥት ከመቶ ሚሊዩን ብር ያላነሰ በጀት
በመመደብ መፃህፍትን በስፋት ማሳተም በመቻሉ የመፃህፍት አቅርቦት ከሞላ ጐደል
1 ለ 1 ማድረስ ተችሏል፡፡ የሌሎች ግብዓቶች አቅርቦት በተለይም የኘላዝማ፣ ኮምፒዩተርና
የቤተ ሙከራ ኬሚካልና አፓራተስ አቅርቦት አበረታች ውጤት አሳይቷል፡፡

ይሁን እንጅ የትምህርት ተሳትፎ/ተደራሽነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ተሳትፎ ዝቅተኛ


መሆኑ፣ የመጀመሪያ ደረጃ 2 ኛ ሳይክል ትምህርት ተሳትፎ ከዘላቂ የልማት ግብ ላይ ያልደረሰ
መሆኑ፣የ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋን/ተደራሽነት ከመካካለኛ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው አገሮች
ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ፣የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ተሳትፎ መካከለኛ ገቢ
ካላቸው አገሮች ጋር ሲወዳደር ዝቅተኛ መሆኑ፣ የትምህርት ፍትሀዊነት በቅድመ መደበኛ፣
በመጀመሪያና 2 ኛ ደረጃ ትምህርት በገጠርና በከተማ የፍትሀዊነት ክፍተት መኖሩ፣በተግባር
ተኮር ጎልማሶች ትምህርት የሴቶች ተሳትፎ አነስተኛ መሆኑ፣የልዩ ፍላጎት ትምህርት
በሚፈለገው ደረጃ እየተስፋፋ ቢሆንም ተማሪዎችና መሠረተ ልማት በሚፈለገው ሁኔታ
አለማሟላቱ፣

የትምህርት ውስጣዊ ብቃት የተማሪዎች አዘውትሮ በትምህርት ገበታ ላይ አለመገኘት፣


ትምህርት ማቋረጥና ክፍል መድገም /የትምህርት ብክነት/ ያልተሻገርነው ችግር
መሆኑ፣በመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል የተማሪዎች የማጠናቀቅ ምጣኔ በተፈለገው
ደረጃ ላይ አለመድረስ፣ የትምህርት ጥራት ሁሉም ተማሪዎች የመማር ውጤትና ስነ
ምግባር በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ከተቀመጠው አንፃር ሲነፃፀር ሙሉ በሙሉ
አለማሣካቱ፣ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም ግንባታ፣ የሪፖርትም ሆነ የመረጃ ልውውጥ
ሥርዓታችን የጥራት፣ የወቅታዊነትና የታዓማኒነት እንዲሁም አልፎ አልፎ የውሸት መረጃ

10 2013 -2022 / Page


63
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የመስጠት ችግሮች ያለበት በመሆኑ ወቅታዊነትና አስተማማኝ የሆነ መረጃ ማግኘት


አለመቻል ከፍተኛ ተግዳሮት ነበሩ፡፡

የማስፈፀሚያ ስልቶች

የትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሀዊነትና ውጤታማነትን ለማሻሻል የባለድርሻ አካላትን

ተሳትፎ በተለይም የልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን (የቀበሌው የልማት ቡድን፣ የወጣቶች፣የሴቶች

ልማት ቡድን በመጠቀም የትምህርት ቤቶች ስርጭት ካርታ መሰረት በማድረግ ፍትሀዊና

ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡

በትምህርት ዘርፍ የሚተገበሩ መመሪያዎች፣ ደንቦች፣ዕቅዶች፣ መርሀ ግብሮችና ስርዓተ

ትምህርቱ የስርዓተ-ፆታና የልዩ ፍላጎት ጉዳዮችን አካታች ስለመሆኑ ስርዓት መዘርጋት፣

በገጠርና በከተማ ያሉ የትምህርት ተቋማት ሥርጭትን በማስተካከል ክፍተቱን ማጥበብ፣

በአፍ መፍቻ ቋንቋ የትምህርት ተደራሽነትን በማረጋጋጥ ለዜጎች ፍትሀዊ ትምህርት

እንዲዳረስ ለማድረግ የሥርዓተ ትምህርት ቁሳቁሶችን አስማምቶ ማዘጋጀት፣ መምህራን

ማሠልጠን እና ትምህርቱን በሬዲዮ ማሠራጨት የምንከተለው የማስፈጸሚያ ስልቶች

ናቸው፡፡

 ባህል፤ ቱሪዝምና ስፖርት ተግባራት አፈጻጸም


ከባህል ልማት አንፃር

በአራቱ የኪነጥበብ ዘርፎች ማለትም በተውኔት፣በግጥም፣በአጭር ልብወለድ፣በስዕል፣ ቅርጻቅርጽና


በሙዚቃ የፈጠራ ስራዎች በየአመቱ 1 ጊዜ በከተማ አስተዳደር ደረጃ ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡
በእነዚህ ውድድሮች 645 የፈጠራ ሥራዎችን ለማቅረብ ታቅዶ 643 የፈጠራ ሥራዎች ለመድረክ
ማቅረብ የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙ 99.6% ነው፡፡

በባለፉት 10 አመታት 27,100 መጽሐፎችንና ህትመቶችን በማሰባሰብ ለህዝብ ቤተ-መጻሕፍት


ለማሰራጨትና ተደራሽ ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ 22,467 የህትመት ውጤቶችን የማሰባሰብና
የማሰራጨት ሥራ ተከናውኗል፡፡ አፈጻጸሙም 82.9% ነበር፡፡ ስነ-ቃሎችን በ 10 ሰነዶች ለማሰባሰብና
በየባህሪያቸው ለማደራጀት በዕቅድ ተይዞ በ 10 ሰነዶች ማሰባሰብ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙም 100%
ነው፡፡

10 2013 -2022 / Page


64
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በስትራቴጅክ ዘመኑ 2 ቤተ-መጻሕፍትን በሙያና በቁሳቁስ ለማጠናከር በዕቅድ ተይዞ 2 ቤተ-


መጻሕፍት በተለያዩ ግብዓቶች ተጠናክረዋል፡፡ አፈጻጸሙም 100% ነበር፡፡ እንዲሁም 3 ንባብ ቤቶችን
በሙና በቁሳቁስ ለማጠናከር በዕቅድ ተይዞ 3 ንባብ ቤቶችን በሙያና በተለያዩ ግብዓቶች
ተጠናክረዋል፡፡ አፈጻጸሙም 100% ነበር፡፡

 ከቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ልማት አንጻር

በቅርስ ዘርፍ ለ 8 ቋሚ ቅርሶች የቅርስ ጉዳት መጠን ልየታ ሰነድ ለማዘጋጀት ታቅዶ ለ 6 ቅርሶች
የጉዳት መጠንል የታሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡አፈጻጸሙም ከ 75% ነዉ፡፡የጉዳትመጠን ልየታ የተዘጋጀላቸው
ቋሚ ቅርሶች የንጉስ ሚካኤል ቤተመንግስት፣የደሴ ሙዚየም፣ የመርሆ ቤተ መንግስት፣ ወሎ ባህል
አምባ፣የቦሩ ስላሴ ቤተክርስቲያንና የቢለን ጊዮርጊስ ይጠቀሳሉ፡፡ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠሩ
የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ለማስተማሪያነትና ለታሪክ መረጃነት መጠበቅ ይኖርባቸውል፡፡ ከዚህ
አንፃር ምንም ጥናትና የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ስምምነት ሳያገኙ ጠላት የገነባቸው ጥሩ ህንፃዎች
ፈርሰዋል፡፡ ለአለፈው ክረምት ቤት አይሰራምና ወደፊት በእቅ ዘመኑ እንዲህ ዓይነት ስህተት
እንዳይደገም መምሪያው ጥብቅ ክትትል ያደርጋል፡፡

የጎብኝዎች ፍሰት እና ገቢን አስመልክቶ

በከተማችን የጎብኝዎች ፍሰት ለመጨመር እና የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም በርካታ ተግባራት


ተከናዉነዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የሀገር ዉስጥ የጎብኝዎች ፍሰት 1,350,500 ለማድረስ ታቅዶ የ 2 አምስት
ዓመት ስትራቴጅክ መረጃ ተወስዶ 955,050 ማድረስ የተቻለ ሲሆን አፈጻጸሙ 70.7% ደርሷል፡፡
በተመሳሳይ መንገድ የዉጭ አገር የጎብኝዎች ፍሰት 15,500 ለማድረስ ታቅዶ 11,504 ማድረስ
ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙም 74.2% ነበር ፡፡

ከተማውን ከሚጎበኙ የሀገር ውስጥ የጎብኝዎች 251,807,650 ብር ገቢ ለማግኘት በዕቅድ ተይዞ


የሁለት አምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዘመን የተደረሰበት መረጃ ተወስዶ 178,428,779 ብር ገቢ
ማግኘት በመቻሉ አፈጻጸሙ 71 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡ እንዲሁም ከተማውን ከሚጎበኙ የውጭ
ሀገር የጎብኝዎች 11,299,500 ብር ገቢ ለማግኘት በዕቅድ ተይዞ 8,386,416 ብር ገቢ ማግኘት
በመቻሉ አፈጻጸሙም 74.2 ከመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


65
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 በስፖርት ዘርፍ፡-
ባለፉት 10 ዓመታት የተለያዩ የአሠራር ስርዓቶችን በመዘርጋት በዘርፉ ውስን የነበረውን የባለሀብት
ቁጥር ለማሳደግ እንቅስቃሴዎች ተድርገዋል፡፡ ሁለት ባለሀብቶች የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ወስደው
በዘርፉ 4,786,435 ሚሊዮን ብር የካፒታል መጠን ለዘርፉ ዕድገት አስተዋፅዖ እንዲያደርጉ ማድረግ
ተችሏል፡፡ ሌሎች ውስን ባለሀብቶች የስፖርት ትጥቅና መሳሪያዎችን በማቅረብ የስፖርቱን ልማት
በማጠናከር ተሳትፈዋል፡፡
ይሁን እንጂ በዘርፉ የግል ባለሀብቱን ለመሳብ የሚያስችሉ ግንዛቤ የመፍጠርና የማበረታቻ ስርዓቶች
ባለመኖራቸዉ ስፖርቱን ወደ ንግድ ስራ በመቀየር አትራፊ ለማድረግ የተሰራዉ ስራ ዝቅተኛ መሆኑ
በአፈፃፀም ግምገማዎች ታይቷል፡፡
ስለዚህ በቀጣይ 10 አመታት ባለሀብቶች በስፖርቱ ዘርፍ የሚሰማሩባቸውን የስራ መስኮች በመለየትና
ደረጃ በመስጠት፤ የስፖርት ኢንቪስትመንቱ የሚጠይቀውን የማበረታቻ ሁኔታ በማመቻቸት
ባለሀብቶች ወደ አስጎብኝ ድርጅትነት እንድገቡ መስራት የብድር አቅርቦት እንደ ሌሎች ልማቶች ሁሉ
የሚያገኙበትን ስርዓት በመዘርጋት ባለሀብቶች በስፖርት ኢንቪስትመንት እንዲሳተፉ በማድረግ
ስፖርቱ ለከተማው ብሎም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የራሱን ድርሻ እንዲያበረክት የማድረግ ስራ
መስራት ይገባል፡፡
የሀብት ምንጮችን በማስፋት ስፖርቱን ከመንግስት ድጎማ ለማላቀቅ እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ብር 96,928,189 ከአርሶ አደሩ፤ ከመንግሰት ሠራተኞች፤ ከከተማ ነዋሪዉና ከንግዱ ማህበረሰብ
በመሠብሰብ ስፖርቱን በገንዘብና ቁሳቁስ መደገፍ ተችሏል:: ነገር ግን ስፖርቱን ከመንግስት የበጀት
ድጎማ በዘላቂ ለማላቀቅ የሚያስችሉ ቋሚ የገቢ ምንጮችን ፈጥሮ ለስፖርቱ ልማት
ማዋልአልተቻለም፡፡
ከተለያ ዩምንጮች የሚገኘውን ሀብት ወደ ልማት አስገብቶ በረጅም ጊዜ እቅዶች ላይ ከመስራት ይልቅ
ከመንግሰት የመጠበቅ፤ የአካባቢን ፀጋ በአግባቡ ተመልክቶ ሀብት አለመሰብሰብ፤ የአሰባሰብ ስርዓቱም
በህግ ማዕቀፍ የተደገፈ አለመሆኑና የሚሰበሰበዉንም በመረጃ አደራጅቶ የመያዝና የመጠቀም
ክፍተቶች ስተዋልበት ነበር፡፡ በመሆኑ በቀጣይ የስትራቴጂክ የዕቅድ አመታት ገንዘብና ቁሳቁስ
ምንጮችን በቋሚነት ማበልፀግና መተግበር ይጠይቃል፡፡ በባለፉት አመታት በተደረገው ቆጠራ
መሰረት 3 በከተማ ካርታና ፕላን ያላቸው 15 ማዘውተሪያዎች ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ አግኝተዋል፡፡
40 ህጋዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ የሌላቸው፤እድሳት፤አዲስ ግንባታ የሚያስፈልጋቸዉ እና በግንባታ ላይ
ያሉ መሆናቸዉ በቆጠራ ሰነዱ ተመላክቷል፡፡
በአዋጅ 729/2004 የማዘዉተሪያዎች እንዴት እንደሚስፋፉ ቢደነገግም በቂ የሆነ ግንዛቤ
ባለመፈጠሩ፤ ቅንጅታዊ አሠራሮች ባለመዘርጋታቸው በከተሞች መዋቅራዊ ፕላን ለማካተት የሚሰጠው
ትኩረት አንስተኛ ሆኖ ታይቷል፡፡ በርካታ የስፖርት ማዘውተሪያዎች ሕጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ
እንዳይኖራቸው በመደረጉ ለሌሎች ኢንቪስትመንቶችና ለግለሰቦች ተላልፈው እንዲሠጡ መደረጉ፣

10 2013 -2022 / Page


66
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በየስፖርት አይነቱ ያሉት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ከከተማው የህዝብ ብዛት አንፃር ቁጥራቸው
አንስተኛ መሆናቸዉ ለሕብረተሰቡ ተደራሽ አለመሆን ናቸው፡፡
የሚገነቡ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችና ማሰልጠኛ ማዕከላትም አካል ጉዳተኞችን እና ዕድሜን
ታሳቢ ያለማድረግ እና ደረጃዎችን ጠብቀዉ ከመገንባት አንፃር ክፍተቶች የተስተዋሉባቸዉ መሆን
ደረጃቸውን የጠበቁ የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁሶችም በሚፈለገው ቁጥርና አይነት ያለመኖር በዘርፉ
የሚሳተፉ የግል ባለሀብቶች ቁጥር ዝቅተኛ መሆን የተስተዋሉ ክፍተቶች ሆነዉ ታይቷል፡፡ በቀጣዩ
እነዚህን ዘርፈ-ብዙ ክፈተቶችንና ማነቆዎችን ለማስወገድ የሁሉን አቀፍ ቅንጅታዊ ስራዎችን መስራት
የሚገባ ይሆናል፡፡

 ሴቶች፤ህጻናትና ወጣቶች መምሪያ ተግባራት አፈጻጸም


ከሴቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት አኳያ

ኢኮኖሚ ዘርፍ፤

የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አኳያ የንቅናቄ ስራዎችን በመስራት


በሴቶች በልማት ቡድን ተደራጅተው የመቆጠብ ባህላቸው እየዳበረ በመምጣቱ
ፆታቸውን መሰረት ያደረገ በገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ማደራጀት
አሰፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አንድ ገ/ቁ/ብ/የህ/ ማህበር በማቋቋም 50 ሴት አባላትን
በማደራጀት ብር 56,000 እንዲቆጠብ ማድረግ ተችሏል፡፡ እነዚህ ማህበራት
በመደራጀታቸው ሴቶች የቁጠባ ባህል እንዲዳብሩ ከማድረግ ባለፈ ራሳቸው ሴቶች
የአመራር ሚናውን የሚወጡ በመሆኑ በራስ የመተማመን አቅማቸው ከማሳደግ
አንፃር አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል፡፡

በብድር እና ቁጠባ አገልግሎት ተደራሽነት በመሆኑ ባለፉት ሁለት አምስት ዓመታት


የዕድገትና ትራንስፎርሜሽ ዘመን ለ 265,673 ለሚሆኑ ሴቶች በገንዘብ ብድርና ቁጠባ
ጠቀሚታና አስፈላጊነት ዙሪያ በድግግሞሽ ግንዛቤ በመፍጠር መደበኛ በሆነ 31,443
እቅድ የተያዘ ቢሆንም መረጃዉን ከአብቁተ ማግኘት አልተቻለም፡፡ ነገር ግን መደበኛ
ባልሆነ 10,520 ሴቶች የብድር አገልግሎት እንዲያግኙ ታቅዶ 2,295 ሴቶች መደበኛ
ባልሆነ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን በዚህም ለብድር የዋለ
ገንዘብ መጠን ብር 32,549,930 ነው፡፡ የሴቶች የብድር ተጠቃሚነት ድርሻ በአበዳሪ
ተቋማት ያለዉን የብድር አገልግሎት ሳይጨምር 21.8% ነው፡፡ በተፈጠረው ግንዛቤም
የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ በባለፉት ሁለት አምስት ዓመታት የዕ.ት.ዕ ዘመን 583

10 2013 -2022 / Page


67
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ሴቶች ብር 2,097,258 እንዲቆጥቡ ማድረግ ተችሏል፡፡ የሴቶች የቁጠባ ተጠቃሚነት


ድርሻ 0.18% ነው፡፡

በማህበራዊ ዘርፍ፤
በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና የኃይል ጥቃቶች ለጤና ችግር
የሚያጋልጡ የማህበራዊ ችግሮች ናቸዉ፡፡እነዚህን ችግሮች ለመቀነስ ብሎም
ለማስወገድ ይቻል ዘንድ በባለፉት ሁለት አምስት የዕ.ት.ዕ ዘመን 842730 የህበረተሰብ
ክፍሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና የኃይል ጥቃቶች ዙሪያ በድግግሞሽ ግንዛቤ
መፍጠር ተችሏል፡፡ በዚህም ከዋና ዋና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች 990 የሴቶች ልማት
ቡድን፣ 26 ቀበሌዎች እና 5 ክ/ከተማ ቢኖርም ነጻ ለመሆናቸዉ በተቀመጠው ደረጃ
መሰረት በጥናት አልተረጋጋጠም ፡፡ ግንዛቤ ከተፈጠረለት ዉስጥ 79.3 በመቶ ጎጂ
ልማዳዊ ድርጊት ይጉዳል ብለው እንደሚያምኑ፣ የልጅነት ጋብቻ 57.7 በመቶ፣ የሴት
ልጅ ግርዛት 41.2 በመቶ እንደሆነ በ 2008 አብክመ ሴ/ህ/ወ/ጉ/ቢሮ ባጠናው ጥናት
ያመለክታል፡፡ በሌላ በኩል (EDHS 2016) ጥናት የልጅነት ጋብቻ 42.9 በመቶ እና
የሴት ልጅ ግርዛት ከ 0-14 የዕድሜ ክልል 34.8 በመቶ መሆኑን የሚያሳይ ቢሆንም
በከተማ ደረጃ በጥነት አልተረጋጋጠም በቀጣይ ትኩረት የሚሻ ጉዳይነዉ፡፡
በህጻናት ዘርፍ

የህጻናት መብት፣ ደህንነት እና ተሳትፎ

በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ ዝውውርና የጉልበት ብዝበዛን መከላከል እንዲቻልም ለ


3.7 ሚሊዩን (ወንድ 2.1 ሚ ሴት 1.6 ሚ) የህብረተሰብ ክፍሎች በድግግሞሽ ግንዛቤ
የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡የአብክመ ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ በ 2010 በተጠናው
ጥናት ማህበረሰቡ ስለ ህፃናት ጉልበት በዝብዛ ያለው ግንዛቤ 66.9 በመቶ፣ በህፃናት ጉልበት
ብዝበዛ ያለው የአመለካከት ደረጃ 51.7 ከመቶ፣ ድርጊቱን የመፈፀም ደግሞ 55.7 ከመቶ
መሆኑን የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡ስለዚህ በህፃናት ላይ የሚፈፀመው ጉልበት በዝበዛ
እንዲቀንስ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ የህፃናት ተሳትፎ አሁን ያለበት
ደረጃ በሁሉም አካባቢዎች ላይ ማለትም በገጠርና በከተማ፣ በፆታ፣ በእድሜና ልዩ ፍላጎት
ሲታይ ተመጣጣኝ አለመሆኑ፣ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለህፃናት አደረጃጀቶች
መጠናከር የሚያደርጉት ድጋፍ እንዲሁም ህብረተሰቡ ስለ ህፃናት ተሳትፎ ጠቀሜታ ያለው
ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑ የህፃናት ተሳትፎ በሚፈለገው ደረጃ ላለመድረሱ በክፍተት የሚታዩ

10 2013 -2022 / Page


68
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዋና ዋና ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብና ልዩ


ትኩረት ሰጥቶ መስራትን ይጠይቃል፡፡

በህጻናት ዘርፍ

በህጻናት ላይ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ ዝውውርና የጉልበት ብዝበዛን መከላከል እንዲቻልም


ለ 350856 (ወንድ 129816 ሴት 221039) የህብረተሰብ ክፍሎች በድግግሞሽ ግንዛቤ
የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡የአብክመ ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ በ 2010 በተጠናው
ጥናት ማህበረሰቡ ስለ ህፃናት ጉልበት በዝብዛ ያለው ግንዛቤ 66.9 ከመቶ፣ በህፃናት ጉልበት
ብዝበዛ ያለው የአመለካከት ደረጃ 51.7 ከመቶ፣ ድርጊቱን የመፈፀም ደረጃ 55.7 ከመቶ
መሆኑን የጥናቱ ውጤት ያሳያል፡፡በከተማችን ግን ድርጊቱ በጥናት የተረጋጋጠ መረጃ የለም፡፡
ስለዚህ በህፃናት ላይ የሚፈፀመው ጉልበት በዝበዛ እንዲቀንስ ትኩረት ሰጥቶ መስራት
ይጠይቃል፡፡

ይሁን እንጂ የህፃናት ተሳትፎ አሁን ያለበት ደረጃ በሁሉም አካባቢዎች ላይ ማለትም
በገጠርና በከተማ፣ በፆታ፣ በእድሜና ልዩ ፍላጎት ሲታይ ተመጣጣኝ አለመሆኑ፣
የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለህፃናት አደረጃጀቶች መጠናከር የሚያደርጉት ድጋፍ
እንዲሁም ህብረተሰቡ ስለ ህፃናት ተሳትፎ ጠቀሜታ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ መሆኑ
የህፃናት ተሳትፎ በሚፈለገው ደረጃ ላለመድረሱ በክፍተት የሚታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶች
ናቸው፡፡ በመሆኑም በቀጣይ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብና ልዩ ትኩረት ሰጥቶ
መስራትን ይጠይቃል፡፡

የህጻናት ድጋፍና እንክብካቤ አገልግሎት

በ 2007 ከነበረበት 18 ቀበሌዎች በ 2012 ወደ 26 ቀበሌዎች የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍ እና


እንክብካቤ ጥምረቶች በማቋቋም ከነበረበት 4592 (ወንድ 2802 ሴት 1790 ወደ 29774
(ወንድ 18163 ሴት 11611) የህብረተሰብ ክፍሎችን አባል ማድረግ የተቻለ ሲሆን
በተመሳሳይ ሀብት ማሰባሰብ ከነበረበት 165000 ወደ 2164324 ብር በማሰባሰብ ለ 6337
(ወንድ 1838 ሴት 4499) ወላጆቻቸውን በሞት ላጡና ለችግር ለተጋለጡ ህጻናት የተለያዩ
ድጋፍና እንክብበካቤ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ በባለፉት ሁለት አምስት የዕ.ት.ዕ ዘመን 15134 በአስቸጋሪ የኑሮ ሆኔታ ውስጥ
የሚገኙ ህፃናትን በተለያዩ የህፃናት ድጋፍ እንክብክቤ አመራጭ መረሀ ግብሮች ለመደገፍ
በዕቅድ ተይዞ 14936 (ወንድ 5851 ሴት 9085) ህፃናትን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


69
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ይሁን እንጂ በየደረጃው የሚገኙ የጥምረቱ ኮሚቴዎች ስራውን በወቅቱ እየገመገሙ


የመምራት ውስንነት መኖር፣ የሚሰበሰበው ሀብት ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ህፃናት እና
ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተገቢው መንገድ ተጠቃሚ አለማድረግ፣ የዕድሳት
ጊዜያቸውን ጠብቆ የማያደርጉ ጥምረቶች መኖራቸው፣ የሀብት ብክነት እንዳይኖር በወቅቱ
ኦዲት የማያደርጉ ጥምረቶች መኖራቸው የሚታዩ ዋና ዋና ችግሮች በመሆናቸው በቀጣይ
ለተግባሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠይቃል፡፡

የወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት

የከተማችን ወጣት 30 በመቶ የሚሆነውን የህብረተሰብ ክፍል የሚሸፍን ከመሆኑም ባሻገር


ከጠቅላላው ህዝብ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ህጻናትና አረጋዊያን የህብረተሰብ
ክፍሎች የኢኮኖሚ ጥገኝነት የሚሸከም ዋነኛ አምራች ሃይል ነው፡፡ ወጣቶች አዳዲስ
ሃሳቦችን ከማፍለቅና ከመቀበል ባሻገር የማምረት እምቅ አቅም ባለቤቶች በመሆናቸው
ለአንድ ሃገር ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ልማትና ዕድገት መምጣት ያላቸው ሚና የላቀ ነው፡፡
በመሆኑም ወጣቱን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ ጅምር ስራ ነው፡፡

ይሁን እንጅ በዘርፉ በተሰማሩም ሆነ ባልተሰማሩ ወጣቶች፣ በወጣት አደረጃጀቶች፣


በወላጆች፣ በህብረተሰቡና አስፈጻሚ አካላት የሚታዩ የአመለካከት፣ የአሰራር፣
የአደረጃጀትና የማስፈጸም አቅም ውስንነቶች ለስራ እድል ፈጠራዉ ተግዳሮት ሆነው
ተስተውለዋል፡፡ሌላው በየደረጃዉ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ከነበረበት አንድ
በ 2012 ስድስት ለማድረስ ታቅዶ ስድስቱም ተፈጽሟል፡፡

የተጠናከረ የመረጃ ስርዓት ባለመኖሩ ካለፉት ስትራቴጂክ ዓመታት አፈፃፀም ሪፖርት ላይ


አሉ የተባሉት ማዕከላት ቁጥር ቀንሶ መገኘት፣አመራሩ ለማዕከላቱ አስፈላጊውን ትኩረት
በመስጠት የግንባታ ቦታ እና በጀት መድቦ መተግበር ላይ ውስንነት መኖር፣ ወጣቱ ራሱ
በማዕከላት የመጠቀም ልምዱ አለመዳበር፣ የማህበረሰቡ ድጋፍ አነስተኛ መሆን፣ ማዕከላት
የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ በጠበቀ መንገድ ለወጣቶች ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት፣
ተቋማት የማዕከላትን ሚና ተገንዝበው በማዕከላት አለመጠቀም፣ ማዕከላቱ ሳቢ እና
ወጣት- ተኮር፣ ለአካል ጉዳተኛ እና ሴት ወጣቶች ምቹና ተስማሚ አለመሆን፣
የአስተዳደራዊ ችግሮችበመንግስት መኖራቸው፣ በማዕከላቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች
ወቅታዊ የወጣቶችን ፍላጉት መሰረት ያላደራጉ እና የተቋቋሙለትን ዓላማ ከማሳካት
አንፃር ባሳለፍነው ሁለት አምስት የእድገትና ቅየራ እቅድ ዘመን ከፍተኛ ውስንነት ያለባቸው

10 2013 -2022 / Page


70
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

መሆን የታዩ ስርዓቱ ሥራ ፈጠራ ወጣቶችን ማፍራት በሚያስችል መልኩ ያለመቃኘቱ፣ ልዩ


ትኩረት ለሚሹ (ሴት ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኛ፣ የጎዳና ተዳዳሪ….ወዘተ.) ፍትሃዊ ተጠቃሚ
ያለመሆናቸዉ በዘርፉ የተስተዋሉ ማነቆዎች ሲሆኑ በቀጣይ የዘርፉ የስራቴጂክ እቅዶች
ዘርፈ ብዙ ምላሽ ይሻሉ፡፡

የወጣቶች ማህበራዊ ተጠቃሚነት

ማህበራዊ ዘርፍ ብቁ፣ ጤናማና አምራች ዜጋ የሆነ ትውልድ በመፍጠር ለአንድ ሃገር
የልማት ዕድገት በሚደረገው ርብርብ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ስለሆነም የተማረና ጤናማ ተተኪ
ወጣት መፍጠር በመካሄድ ላይ ላለው የልማት ና የመልካም አስተዳደር ስርዓት ግንባታ
ዘለቄታዊነት ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ የወጣቶችን ማህበራዊ ጠንቆች ተጋላጭነት በመከላከል
የተሟላ ስብዕና ያላቸውና አምራች ዜጎች እንዲሆኑ ለማድረግ በባለፋት ሁለት አምስት
የእድገትና ቅየራ እቅድ ዘመኑ መጨረሻ የወጣት ማዕከላት ቁጥርን በ 2002 ዋና ዋና ችግሮች
ናቸው፡፡ በመሆኑም ቀጣይ ማዕከላቶቹ ካላቸው ፋይዳ አንጻር ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው
ይገባል፡፡

የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የወጣቶችን አስተሳሰብ ለመገንባትና አመለካከት


ለመቀየር፣ ማህበራዊ ኃላፊነት ስሜት እንዲያጎለብቱ፣የማህረሰቡን ኢኮኖሚያዊና
ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት እንዲሁም በልማቱ የራሳቸውን ድርሻ ማበርከት እንዲችሉ
በባለፉት ሁለት አምስት የዕ.ቅ.ዕ ዘመን ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ይህም በበጎ
ፈቃድ አገልግሎት የሚሳተፉ ወጣቶችን ቁጥር ከጠቅላላው የወጣቶች ብዛት አንፃር
ድርሻው በ 2002 የነበረበት ጠቅላላ መረጃ አልተገኛም ፡፡ በ 2012 ወደ 21.1 በመቶ ማሳደግ
ተችሏል፡፡

 የሠራተኛና ማህበራዊ መምሪያ ተግባራት አፈጻጸም

በባለፉት 10 አመታት በአዋጁ የተሰጠዉን ተግባርና ሃላፊነት ለማከናወን ተገልጋይ


ደንበኞችን መሠረት ያደረገ ቀልጣፍና ጥራት ያለዉ አገልግሎት በእድገትና ትንስፎሜሽን
እቅድ መሰረት የአሠሪና ሠራኛተኛ ግንኙነታቸዉን በህጉ ላይ ተመስርተዉ መብትና
ግዴታቸዉን ለይተዉ የኢንዱስትሪ ሠላም በማስፈን ለከተማው ሁለንተናዊ እድገትና
ልማት በመተባበር በጋራ እንዲሰሩና የዜጎች ማህበራዊ ደህንነት የሚጠበቅበትና
የሚሻሻልበትን ዘዴ በመለየትና በስራ ላይ በማዋል የማህበራዊ ችግሮች እንዳይከሰቱ

10 2013 -2022 / Page


71
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ለመከላል በአሠሪና ሰራተኛ ህግ ማዕቀፍ ዙሪያ የግንዛቤ ትምህርት አግኝተው መብትና


ግዴታቸውን እንዲረዱ የተደረጉ አሰሪና ሰራተኞች እቅድ 16,500 ሲሆን ክንውኑ 10,713
አፈጻጸም 65%ነው፡፡ በሰራተኛች ጉባኤ የጋራ ምክክር መድረኮች የተሳተፉ አሰሪዎች፣
ሰራተኞች፣ የማህበር አመራሮች፤ የግልግል ዳኞች፣ የመደበኛ ፍርድ ቤት ዳኞች አስፈጻሚና
ባለድርሻ አካላት እቅድ 6,743 ክንውኑ 2,611 አፈጻጸም 38.7%ሲሆን የቅርብ ድጋፍና
ክትትል ተደርጐላቸው የተጠናከሩ መሰረታዊ የሰራተኛ ማህበራት እቅድ 118 ክንውኑ 92
አፈጻጸም 78% ነበር፡፡

ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል የተሰጠ የግንዛቤ ትምህርት እቅድ 167,635 ክንውን
112,942 አፈጻጸም 67.3% ደርሷል፡፡ ተሰብስቦ ከተጠናቀረ በኋላ ለተጠቃሚዎች
የተሰራጨ በአሠሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ የሚተዳደሩ ድርጅቶች ውስጥ በጀት የተያዘለት
ክፍት የስራ መደብ እቅድ 1662 ክንውን 1738 አፈጻጸም 104.5% ሲሆን የስራ ላይ
አደጋዎች ሪፖርት ያደረጉ ድርጅቶች እቅድ 84 ክንውን 84 አፈጻጸም 100% ማድረስ
ተችሏል፡፡ ይሁን እንጅ የህገውጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል የተለያዩ አካላትን ትግል
የሚጠይቅ በመሆኑ አሁን መሳካት ያልቻልነው ተግባር ሁኗል፡፡

የስራ ቦታ ቁጥጥር በሚደረግባቸው ደርጅቶች የስራ ቦታ ምዝገባ ማካሄድ እቅድ 11707


ክንውን 838 አፈጻጸም 7% ሲሆን ለስራ ወደ ውጭ ሀገር ለሚሄዱ ኢትዮጱያውያን የሰው
ሀይል ምልመላ ማከናወን እቅድ 4924 ክንውን 5082 አፈጻጸም 103.2% ሆነዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ሀብት ማሰባበብ እቅድ ብር 800,000 ክንውን ብር 549,042
አፈጻጸም 68.6% ማድረስ ተችሏል፡፡

የማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያስችል የማህበራዊ ጠንቅ መንስኤዎችን


ስለመከላከል፣ አካል ጉዳተኝነትን፣ አረጋዊነትን፣ ስለጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ኤችአይ ቪ
ኤድስን በተመለከተ ቢያንስ ከ 1 ሰአት ያላነሰ በሰነድ የተደገፈ በፊት ለፊት ገለጻ
ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ (50% ሴቶች) (30% ወጣቶች) (10% ህፃናት) እቅድ
130,629 ክንውን 140,839 አፈጻጸም 107.8% ደርሷል፡፡ በየደረጃዉ የሚገኙ የአካል
ጉዳተኞች ማህበራት ህብረትን በማጠናከር ዉጤታማ ማድረግ እቅድ 1 ክንውን 1
አፈጻጸም 100 ነው፡፡

በጎዳና የሚኖሩ ወገኖች የማህበራዊ ደህንነት ድጋፎችና አገልግሎቶች ተጠቃሚ ሆነዉ ወደ


ተሻለ ኑሮ እንዲለወጡ ማስቻል እቅድ 2630 ክንውን 131 አፈጻጸም 4.9%፤ በልመና
ለሚኖሩ ወገኖች የግንዛቤ፣ የአመራርና የምክር አገልግሎቶችን በመስጠት ከለምኖ አዳሪነት

10 2013 -2022 / Page


72
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

እንዲወጡ ማስቻል እቅድ 2825 ክንውን 382 አፈጻጸም 13.5% ማድረስ ተችሏል፡፡
በሴተኛ አዳሪነት የሚኖሩ ወገኖች የማህበራዊ ደህንነት ድጋፎችና አገልግሎቶች ተጠቃሚ
ሆነዉ ወደ ተሻለ ህይዎት እንዲለወጡ ተደርጓል፡፡ ነገር ግን አሁንም ለምኖ አዳሪ እና ሴተኛ
አዳሪትን በመቀነስ በኩል አሁን ያተሻገርነው በመሆኑ በቀጣይ በትኩረት ይሰራል፡፡

 የመልካም አስተዳደር ተግባር አፈጻጸም


በከተማችን በልማት እና በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ በተወሰኑ የመንግስት ተቋማት ማለትም በግዥና
ፋይናንስ፤በገቢዎች ፤በፍትህ አካላት እና በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ተቋማት ውስጥ
ባለፉት አመታት በርካታ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ነበሩ፡፡

ሆኖም ግን በዚህ ሁለት አመታት እስከ አሁን ከጊዜ ወደ ጊዜ መልካም አስተዳደር ችግር
ለመቀነስ በአጭር ፤በመካከለኛ እና በረጅም እቅድ ተይዞ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከነዚህም ውስጥ
በቅርብ ጊዜ በከተማ ልማት በኩል የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ውስጥ በ 2011
ዓ.ም ቦታ የተረከቡ ማህበራት ሊዝ ማዋዋልና ካርታ በመስጠት ረገድ ለ 1000 ሰዎች
መሰጠቱ እና መሬት በመንሸራተት ምክንያት ከመንበረ ፀሃይ ለተነሱ 55 ሰዎች ምትክ ቦታ
ተሰጥቷል ፡፡ ሌላው ካሳ የተከፈላቸውና ያልተከፈላቸው መረጃ አለመኖር ለህገወጥ ግንባታ
በር የከፈተ የነበረ ሲሆን መረጃውና አጠናቅሮ ለመለየት ተችሏል ፡፡

በመካከለኛ ጊዜ ደግሞ ለ 24 አካል ጉዳተኞች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ


መስጠቱ፤በማህበር ተደራጅተዉ ለነበሩ 1000 ሰዎች በፕላኑ መሰረት የመንገድ
መክፈት ስራ በመስራት ችግሩተፈቷል፡፡ በክፍለ ከተሞች (በአራዳ፣ ሆጤ፣ ቧንቧ
ውሃ) የወሰን ማካለል ፤የቄራ መስጅድ አካባቢ መሬት መንሸራተት፤የገራዶ መናኸሪ
ግንባታ የመሰረተ ልማት የጥራት ችግር መፍታት እና የስፖርት ማዘዉተሪያ
ቦታዎች ወሰን ማካለል በመሰራት የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት ተችሏል፡፡

በአምስቱም ክ/ከተሞች የኮብልስቶን ጥገና በማድረግ ችግሩ ተፈቷል፤ ኪዳነ ምህረት


አካባቢ የተቋረጠ ኮብልስቶን ስራ እንዲጨረስ በማድረግ ችግሩ ተፈቷል፤ ከጎንደር በር
እስከ መዋእለ ህጻናት ድረስ መፋሰሻ ስራ ተሰርቷል፤ ከዚህ ቀደም ቦታ ወስደዉ
ካርታ የሌላቸዉ ባለ ይዞታዎች / ባህር ሸሽ /ካርታ እንዲሰጣቸዉ ተደርጓል፤ መናፈሻ
ክ/ከተማ ቀጠና 1፣2፣6፣7 እና 8 መፋሰሻ ስራዎችን በማጠናቀቅ ችግሩ ተፈቷል፤
ቀደም ሲል በአዘዋ ገደል አካባቢ በ 1999 ዓ.ም የተከበረላቸውን ባለ 104 ይዞታዎች
ፋይል እንዲከፈትላቸው ተደርጓል፤ ጊዜያዊ ሊዝ በመታገዱ ሰኞ ገበያ ክ/ከተማ

10 2013 -2022 / Page


73
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ተፈጥሮ የነበረውን ችግር አገልግሎቶች እንዲፈቀድ በማድረግ ችግሩ ተፈቷል፤


የቀለም ሜዳ አርሶ አደሮች በተከበረልን ቦታ ካርታ ይሰራልን ጥያቄ እንዲፈታ
ተደርጓል፡፡ የተላያዩ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ለጠየቁ ባለሃብቶች እንዲስተናገዱ
በማድረግ ችግሩ ተፈቷል፡፡

በረጅም ጊዜ የተፈቱ የመልካም አስተዳደር ችግር ደግሞ 17 ማህበራት /ወሎ


ዩኒቨርስቲ አካባቢ/ ካርታ በ 2009 እና በ 2010 ወስደዉ ቦታዉን አርሶ አደሩ ሁከት
በመፍጠሩ ለብዙ አመት ወደ ስራ መግባት ያልቻለ ማህበራት ቦታ የማስረከብ ስራ
ተሰርቷል፤ በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ምክኒያት ከመኖሪያ ቦታቸዉ ተነስተዉ ምትክ ቦታ
ያልተሰጣቸዉ 30 ግለሰቦች የመኖሪያ ቦታ እንዲሰጥ ተደርጓል፤ የኮሽም በር ገራዶ
መንገድ በታቀደለት ጊዜ አለመጠናቀቁ በህብረተሰቡ ላይ ችግር በመፍጠሩ በአፋጣኝ
እርምጃ ተወስዶ ከ 95% በላይ ተጠናቋል፤ ለልማት ቦታ ተሰጥቷቸዉ ወደ ልማት
ያልገቡ 8 /ስምንት/ ግለሰቦች ላይ በከፊል ርምጃ ተወስዷል፡፡በከተማው አገልግሎት
እየሰጠ የሚገኘው የቄራ ማእከል የቆየ በመሆኑ ከንጽህና ጋር በተያያዘ ከህብረተሰቡ
የሚነሱ ጥያቄዎች ስለነበሩ በጀት በመመደብ እድሳት እንዲደረግለትና አገልግሎቱ
እንዲሻሻል ተደረጓል፤ የተለያዩ መውጫና መግቢያ መንገዶች ጥያቄዎችን ግምት
ውስጥ በማስገባት በጥቅል 108 ሜትር መንገድ በመክፈት የግለሰቦች ችግር ለመቅረፍ
ተችሏል፡ ፡የሳላይሽ ሰኞ ገበያ በአስፓልት ላይ የሚሄድ ውሃን በካናል እንዲሄድ
በማተካከል የአካባቢውን ህዝብ ጥያቄ ለመፍታት ተችሏል ::

 ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጅ ልማት


የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አፈጻጸም
በከተማችን የተዘሩጉትን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎች በአግባቡ ስራ ሊያሰሩ
የሚችሉ ቴክኖሎጅዎች እንዲስፋፉ እገዛ ማድረግ መቻሉ እና በጥቅሉ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ
የሆነ ማህበረሰብ መፍጠር፤ በቴክኖሎጂ ዙሪያ የተሰማሩ ግለሰቦች እና የሥራ እውቅና
በመስጠት፣ እንዲሁም የኔትወርክ ዝርጋትን የመስራት፣ የዳታ ቤዝ መረጃ አያያዝ ዝርጋታን
የመጠቀም፣ የኢንተርኔት አገልግሎት በከተማችን እንዲኖር ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም
ከተማው የራሱ የሆነ ደረ-ገጽ እንዲኖረው ለማድረግ የማልማት ስራ ለመጀመር ጥረት
ተደረጓል፡፡ሌላው በኮምፒውተር ሳይንስና መረጃ ቴክኖሎጂ የተማሩ ግለሰቦችን በተለያዩ
ተቋማት ለመቅጠር በመመዘን ወደ ስራ ገበታ እንዲገቡ ትልቁን ድርሻ ወስዶ እየሰራ የቆየ
የስራ ክፍል ነው፡፡

10 2013 -2022 / Page


74
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

እንዲሁም በከተማው ለሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች መሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና


በመስጠት ብቁ የሆነ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የተሻለ ሰራተኛ በመፍጠር ደረጃ የተሰራ
ቢሆንም ይህ ክፍል ብዙ የቢሮ ቁሳቁስና ግብዓት እንደሚያስፈልገው ቢታመንበትም ግን
እስከአሁን ቴክኖሎጂውን በማስፋት እና በቂ የአይሲቲ ማሰልጠኛ ክፍል እና ኮምፒዩተር
አለመገኘቱ የተፈለገውን ያህል መጓዝ አልተቻለም፡፡

ከዚህ ባሻገር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ጽ/ቤቱ


በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ በመታገዝ ፈጣን የመረጃ ልውውጥና ውጤታማ
የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲኖር ለማድረግ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች እለት በእለት
በኮምፒውተር በመታገዝ በሚያከናውናቸው ስራዎች ዙሪያ የአጠቃቀም ችግር
ላጋጠማቸው አመራርና ሠራተኞች ሙያዊ እገዛ መደረጉ፣ በግዥ ክፍል ለተጠየቁት
እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ የማውጣት እና በግዥ የቀረቡትን እቃዎች አቅራቢ
ድርጅቱ በዝርዝር መግለጫቸው መሰረት ማቅረባቸውን የመፈተሸ ስራ ማከናወን
ተችሏል፡፡ ከዚህ ባሻገር የግል ኢንተርኔት ካፌ ላላቸው ተቋማት ፈቃድ የመስጠት

አገልግሎት ተከናውኗል፡፡ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የብሮድካስት

ቴክኖሎጅን በመጠቀም ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም በ 2007 ዓ.ም የሬዴዮ

ትምህርት 100% ግብ ቢጣልም እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ 97.2% ሲሆን፤የፕላዝማ

ትምህርት 78.2% የነበረ ሲሆን ወደ 89.78% ማደግ ችሏል፤የኮምፒውተር ቤተ ሙከራ

በ 13 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በማደራጀት 98.3% እንዲያድግ ተደርጓል፤የኢንተርኔት

አገልግሎት በ 2007 ዓ.ም 31% ነበረ ቢሆንም በ 2012 ዓ.ም በ 10 ት/ቤት ላይ ተዘርግቶ

96.92% ለማድረስ ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


75
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

2.2.5 አስተዳደር እና ፍትህ ልማት ዘርፍ አፈጻጸም


 የህዝብቅሬታ ተግባራት አፈጻጸም
ባለፉት 10 ዓመታት ከ 2003-2012 ዓ.ም አጠቃላይ 10894 አቤቱታዎች ቀርበው ለ 10645
ደንበኞች ምላሽ ተሰጥቷል። የቀረበው አቤቱታ ከተሰጠው ምላሽ አኳያ 97.71% አፈፃፀም የሚያሳይ
ሲሆን ከቀረበው 10894 አቤቱታዎች ዉስጥ ደረጃውን ጠብቀዉ የቀረቡ 3147 ሲሆን አፈጻጸሙም
28.88% ነዉ ይህም ግንዛቤዉ ባለመኖራቸዉ ደረጃዉን ሳይጠብቁ ወደ ክፍሉ የሚመጡ ባለጉዳዩች
ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ያመላክታል፡፡ እንዲሁም ደረጃዉን ጠብቀዉ ከመጡት አቤቱታዎች ዉስጥ
የጽሁፍ ውሳኔ የተሰጣቸው ደግሞ 1169 ሲሆን አፈፃፀሙም 54.94% መሆኑን ያሳያል፡፡

ከዚህም የምንገነዘበው ደረጃቸውን ጠብቀው ለቀረቡ ጉዳዮች በየደረጃው ለሁሉም አቤቱታዎች


የጽሁፍ ውሳኔ አለመሰጠቱ እና በስምምነት እና በድርድር የተፈቱ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ባለፉት
ተከታታይ አመታት ባለጉደዮች ያቀረቡትን አቤቱታ በአግባቡ የማስተናገድ እንዲሁም የሚወሰኑ
ውሳኔዎች ጥራት ችግር ያለ መሆኑ እና ዉሳኔ ተሰጥቷቸዉ ሳይፈጸሙ ለበርካታ ጊዜያት የሚቆዩ
አቤቱታዎች ያሉ እና ከዚህ ጋር ተያይዞ በርካታ ችግሮች መኖራቸዉን ለማየት ተችሏል፡፡

ባለፉት ተከታታይ አመታት በብዛት አቤቱታ የቀረበባቸው የአገልግሎት ዘርፎች የከተማ ልማትና
ኮንስትራክሽን፤አስተዳደራዊ አገልግሎት አሰጣጥ፣ ከጥቃቅን የስራእድል ፈጠራ ጋር የተያያዙት ጉዳዩች
ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ይህም የሚያመላክተው ተቋማት በአዋጅ የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት
በአግባቡ መወጣት አለመቻላቸውን ነው፡፡

በመሆኑም በቀጣይ አስር አመታትዝቅተኛ አፈጻጸም የታየባቸውን ተግባሮች አሻሽሎ በማቀድ


የህዝቡን የአገልግሎት እርካታ ከፍ የሚያደርጉ ስልቶችን ቀይሶ በመስራት የተቋሙን አሰራር የዘመነና
የመረጃ አሰራር ስርዓትን መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡

 የከንቲባ ጽ/ቤት ተግባራት አፈፃፀም

ባለፉት 10 ዓመታት ከደንበኞች የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደ አመጣጣቸው በመቀበል እና


በመመዝገብ እንዲሁም የአጀንዳዎችን ብቃት የመገምገምና ውሣኔ የመስጠት ሥራ
ተከናውኗል፡፡ አጀንዳዎችም በቃለ ጉባኤ መዝገብ የተደራጁ ሲሆን ውሳኔ ከተሰጠባቸዉ
በኋላ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስ ተደርጓል፡፡ የሚቀርቡ አጀንዳዎች በታቀደዉ
መሰረት ለማከናወን አመራሩ ለተለያየዩ ስራዎች ወደ መስክ ስለሚንቀሳቀስና በልዩ ልዩ

10 2013 -2022 / Page


76
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ስብሰባዎች የማይገኙ ሲሆን የከንቲባ ኮሚቴ ጊዜን እንዳይሻሙ በማድረግ በኩል ዉስንነቶች
የነበሩ በመሆኑ በቀጣይ መስተካከለ የሚገባቸዉ ናቸዉ።

በከተማችን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የጀመሩ የምዝገባ ጣቢያዎች 26 ሲሆን በከተማችን


የምዝገባ ጣቢያዎች ማቋረጥ 0% ስለሆነ በቀጣይ ይህን አፈጻጸም ማስጠበቅ
ያስፈልጋል፡፡ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሽፋንን ማሳደግ በተመለከተ በገጠር እና በከተማ
ጊዜን መሰረት አድርጎ ወቅታዊ/ የዘገየ ምዝገባ ሁሉንም የተከሰቱ ኩነቶች ዉስጥ
20% ተከናዉኗል፡፡ ጊዜ ገደቡ ያለፈ ምዝገባ 13660 መመዝገብ ተችሏል፡፡

የመረጃ አጠቃቀምን ሲታይ ግለሰቦች ተመዝግበዉ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ እቅድ


4786 ክንዉን 4471 አፈፃፀም 93.42% ባለቤት በመሆን የተለያዩ ማህበራዊ እና
ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት እንዲገኙ ተችሏል፡፡

የሥነ-ምገባር ጥሰትና ብልሹ አሰራር መልኩን እየቀያየረ እና እየተሰፋፋ የመጣ


በመሆኑ በተደራጀ የህዘብ ንቅናቄ መመከት ካልቻልን ለእድገት እንቅፋት ከመሆን
ባሻገር የሰላማችንና የአብሮነታችን ስጋት መሆኑ አይቀሬ ይሆናል፡፡ ሙስናና ብልሹ
አሰራርን መከላከልና መቆጣጠር ከሚያስችሉ ሁኔታዎች አንዱ በከተማ አስተዳደሩ
ውስጥ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶችና ህዝባዊ
ተቋማት ውስጥ የሥነ-ምግባር መከታተያ አውታሮችን በማቋቋም ነው፡፡

በመሆኑም ከተማችን በሴክተሮች፣ ት/ቤቶች እና በንግድ ም/ቤቶች የሥነ-ምግባር


አውታሮችን ማደራጀት የተጀመረ ሲሆን ይህንን በማጠናከር ሙስናና የሥነ-ምግባር
ጥሰት የመከላከል ስርዓትን ማስፈን በቀጣይ እቅድ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን
መንቀሳቀስ ይጠበቃል፡፡ ሙስናና ብልሹ አሰራርን አስቀድሞ የመከላከል አንዱ አካል
የሆነው የሃብት ማሳወቅና ማስመዝገብ ስራን በክልላችን ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል
አዋጅ 187/2003 ዓም እና ይህን ለማስፈፀም ደንብ ቁጥር 93/2004 ዓም እና
መመሪያ ቁጥር 01/ 2010 ዓ.ም ወጥቷል፡፡

በመሆኑም የሀብት ምዝገባ የማሳወቅ መረጃ የማደራጀት መመዝገብና የህግ ማእቀፍ


ተግባራት አፈጻጸም ለ 250 ሰው ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፤፤ እንዲሁም የኦዲት
አስመላሽ ግብረ ሀይል አሰራርን በመደገፍ በግኝቱ መሰረት እንዲፈጸም እገዛ

10 2013 -2022 / Page


77
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ተደርጓል፡፡፡ በአጠቃላይ ብልሹ አሰራርና የሥነ- ምግባር ጥሰትን የሚመለከቱ


ጥቆማዎችና ቅሬታዎች ተቀብሎ የማስተካከል ስራ ተኩረት መስጠት ያስፈልጋል፡፡

የልማት ስራዎችን መሰረት በማድረግ በከተማ አስተዳደሩ መምሪያዎች የሚዘጋጁ የልማት


መነሻ ዕቅዶች በማሰባሰብ የተመጣጠነ ዕቅድ በማዘጋጀት በም/ቤት ፀድቆ ስራ ላይ
እንዲዉል ተደርጓል፣ የሚቀርቡ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ከከተማዉ ልማት ጋር የተገናዘቡ
መሆናቸዉን በመመርመር ለሚመለከታቸዉ አካላት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን
ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እና ጥራት ስለ መፈፀማቸዉ ክትትል በማድረግ በኩል ሰፊ
ክፍተት ነበር ፡፡ ሆኖም ወቅታዊ የሆነ የአፈፃፀም ሪፖርት በማዘጋጀት በም/ቤት
እንዲገመገም ዝግጁ በማድረግ ስለአፈጻጸሙ በየጊዜዉ ለከተማ አስተዳደሩ ወቅታዊ
ሪፖርት ቀርቧል፡፡

ለዕቅድ ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ የሥነ-ህዝብ ትንበያዎችን /የህዝብ ብዛት


/መረጃዎችን በእድሜ ክፍፍልና በፆታ በመለየት መረጃዎችን በማጠናቀር
ለተጠቃሚዎች ተደራሽ የተደረገ ሲሆን የማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ መረጃዎችን
በማሰባሰብ የባለፉት 2 /ሁለት/ ዓመታት 126 የልማት አመልካች መጽሔት ተዘጋጅቶ
ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ የከተማዉን የልማት አመልካቾች መሰረት ያደረገ ዓመታዊ የሶሽዮ-ኢኮኖሚ


መረጃዎች ማሰባሰብና ለተጠቃሚዎች/ ለመረጃ ፈላጊዎች ለማድረስ ጥረት ተደርጓል፡፤
ይሁን እንጂ መረጃዎችን ከመረጃ ምንጮች የዘርፎቹ ከሌሎች አካላት ለማሰባሰብ
የሚደረገዉ ስራ ፈታኝ፣አስቸጋሪና መረጃዎች በተፈለገዉ ወቅቱ ባለመገኘቱ የመረጃ
ተደራሽነት ሰፊ ክፍተት ያለዉ በመሆኑ በቀጣይ በጋራና በርብርብ ሊሰራ የሚገባዉ ተግባር
ነዉ፡፡

 የዐቃቤ ህግ ተግባራት አፈፃፀም


ባለፉት 10 ዓመታት አቃቤ ህግ የወንጀል መዛግብት መርምሮ ዉሳኔ ከመስጠት አንጻር የማጥራት
ምጣኔ 100% ለመፈፀም ታቅዶ 99.95% መፈፀም ተችሏል ፡፡ አቃቤ ህግ የወንጀል መዛግብትን
መርምሮ ውሳኔ ከመስጠት አንጻር ያለውን የማስቀጣት ምጣኔ አፈፃፀም በቀጥታ ክስ 98% ለማድረስ
ታቅዶ 98.56 %፣ የማቋረጥ ምጣኔን 1% ለማድረስ ታቅዶ አፈፃፀሙም 3.8 % ነበር፡፡ ከታቀደው
ግብ ላይ ሳይንጠባጠብ ሙሉ በመሉ መፈጸም ያልተቻለው የተለያዩ የውስጥና የውጭ ችግሮች
መኖራቸው መሆኑ ተስተውሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


78
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ከውስጥ ችግሮች መካከል ዓቃቤ-ሕግ የወንጀል ሥነ-ስርዓት ህጉን መሰረት ያደረገና ጥራት ያላቸው
ክሶች፣መልሶችና ክርክሮችን ካለማድረግ አንጻር የሚታይ ሲሆን ከውጫዊ ችግሮች መካከል ደግሞ ዋና
ዋናዎቹ ፖሊስ የሚያሰባስባቸው የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች፣ ምስክሮች በአካል ቀርበው በፍርድ ቤት
ከሚሰጡት ቃል ጋር የማይገናኝበት ሁኔታ መኖርና የሀሰተኛ ምስክርነት መበራከት፣ፍርድ ቤቶች
ክርክሮችን በአግባቡ ያለማስኬድና ውሳኔዎችንና ትዕዛዛትን በአግባቡ ካለመስጠት ጋር የሚያያዙ
ችግሮች በመኖራቸው በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት በቅንጅት መስራትና መፍታትን ይጠይቃል፡፡
በፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደሩ ረገድ ተቀዳሚዉ ተግባር የመንግስት፤የህዝብ እና ነፃ ድጋፍ
የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች መብትና ጥቅም እንዲከበር ሰፊ የቅድመ መከላከል ስራ
መስራት ያስፈልጋል፡፡

የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውል ከመግባታቸው በፊት ዉሉን በመመርመር አስተያየት


እንድንሰጥባቸው ከቀረቡት መዛግብት ውስጥ 100% የውል ረቂቅ ምርመራና ዝግጅት ድጋፍ
በመስጠት ከውሉ የሚጠበቀውን መብትና ጥቅም እንዲያገኙና የሚጠበቅባቸውን አንጻራዊ ግዴታ
ለይተው እንዲያውቁ በማድረግ ከፍተኛ ግምት ያለው የመንግስትን ሀብትና ንብረት ከብክነት በማዳን
የሕዝብና የመንግስትን ጥቅም ማስጠበቅ ተችሏል፡፡

ይሁን እንጅ ይህ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሰጠው ድጋፍ ተከታታይነት የሌለው ከመሆኑም በላይ
የሚሰጠው ድጋፍ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ያልደረሰ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የሀብት ብክነት እና
ምዝበራ የሚፈፀምባቸው ተቋማት ቁጥር ቀላል ባለመሆኑ በቀጣዩ የእቅድ ዘመን ትኩረት ተሰጥቶት
ሊከናወን ይገባል፡፡

የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅትች ከሌሎች አካላት ጋር ባደረጉት ግንኙነት አለመግባባት
ሲፈጠር ከፍርድ ቤት ውጭ ጉዳያቸው በድርድር እንዲፈታ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ
አግባብ በድርድር እልባት ያገኙ ጉዳዮች ከታቀደው 40% ግብ አኳያ በንፅፅር ሲታይ በመዝገብ 32%
በገንዘብ 21% መፈፀም ተችሏል፡፡ በከተማ አስተዳደሩውስጥ ከሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና
ነጻ ድጋፍ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ያቀረቡዋቸውን ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ በመቀበል የተለያየ
ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን በ 10 አመቱ መጨረሻ ላይ መዝገብን የማጥራት አቅም ምጣኔ ከተያዘው
100% እቅድ ውስጥ 99.47% መፈፀም ተችሏል፡፡ይሁን እንጂ በተቀመጠዉ ደረጃ መሰረት በተወሰኑ
መዝገቦች ላይ ዐቃቤ ህግ አፋጣኝ ዉሳኔ አለመሰጠቱ፣የመዛግብት ፍሰት ከጊዜ ወደጊዜ መጨመርእና
የዐቃቤያነ-ህግ ቁጥር ማነስ ፣ዉሳኔ ለመስጠት አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎች በቀላሉ የማይገኙ በመሆኑ
በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ የሚገባዉ ወሳኝ ጉዳይ ነዉ፡፡

10 2013 -2022 / Page


79
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በመንግስት እና ነፃ የህግ ድጋፍ ለሚሹ አካላት በፍርድ ቤት ክርክር ከተደረገባቸዉ መዛግብት ውስጥ
የማሸነፍ አቅም አፈፃፀም 96% ለማድረስ ታቅዶ በመዝገብ 93.457℅ ሲሆን በገንዘብ መጠን
90.61% መፈጸም ተችሏል፡፡

በክርክር ወቅት ከሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮች መካከል ከመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚላኩ የሰውና
የሰነድ ማስረጃና ምስክሮች በቂ አለመሆን፤ማስረጃዎችን አለመስጠት፣ውሉን ያለበቂ ምክንያት ማቋረጥ
በተጋነነ ዋጋ ውል መስጠት፤ የግንባታ አማካሪ ድርጅቶች የሚሰጡትን ውሳኔ አለመቀበል፤በተቋራጩ
መሐንዲስ እና በከተማ አስተዳደሩ የዋጋ ልዩነት ውል ከተዋዋሉ በኋላ የመንግስት /ቤቶች
በሚከሰሱበት ጊዜ በፍ/ቤት የተያዘው ቀጠሮ እስኪደርስ መጥሪያውን በእጃቸው አቆይተው ቀጠሮዉ
ሲደርስና በቀጠሮው ቀን ለዐ/ህግ የማቅረብ፣ አልፎ አልፎም በራሳቸው መልስ ከሰጡ በኋላ ስጋት ላይ
ሲወድቁ ለዐቃቤ ህጉ ድጋፍ መጠየቅ፣ ከዚያም አልፎ በሞተ ክርክር ላይ ገብታችሁ ተከራከሩልን
የማለት ችግሮች እየጎሉ መጥተዋል፣፣ ፍርድ ቤቶችም ክርክሮችን በአግባቡ ያለ ማስኬድና አንዳንድ
ውሰኔዎችና ትዕዛዞች የህግ መሰረትና ተገማችነት የሌላቸው ስላሉ በቀጣይ ማስተካከል ይጠበቃል፡፡

የሰነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ስርዓት በመዘርጋት ዜጎች በቅርብ ርቀትና በአነስተኛ ወጭ
አገልግሎት የሚያገኙበት ሁኔታ በመፍጠር የተለያይ ስራዎች ተሰርቷል፡፡ በዚህም በተሰጠዉ
አገልግሎት ለመንግስት ገቢ በማስገኘት አጋዥ ሆኗል፡፡

 የኮሚኒኬሽን ተግባራት አፈፃፀም


ባለፉት 10 ዓመታት የመንግሥትን ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫ መሠረት ያደረጉ ተግባራት
የተከናወኑ ሲሆን በየደረጃው ያለውን የተግባቦትና የህዝብ ግንኙነት ፈፃሚ አቅም
ለመገንባት በየደረጃው የተሰማራው የተግባቦትኃይል የመንግስትን የልማትና የዴሞክራሲ
ስርዓት ለማፋጠንና የከተማዋን ገፅታ ለመንባት በሚደረገው ጥረት የተሸለ ነበር፡፡ ይሁን
እንጂ ይህ አፈፃፀም እንደተጠበቀ ሆኖ በተቋሙ ያለው ሃይል የከተማውን ገፅታ
ለመገንባትና አፍራሽ አስተሳሰቦችን ለመመከት በአስተሳሰቡና በክህሎቱ በላቀ ደረጃ የበቃ
ሀይል ገና እንዳልተፈጠረ ለማየት ተችሏል፡፡ በተለይ የከተማውን ህብረተሰብ በዋና ዋና
የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት በሚያደርሱ ተግባራት ላይ
አተኩሮ ከመስራት ይልቅ በደራሽ ስራዎች የመጠመድ እና የጥራት ችግር እንዳለባቸው
ተስተውሏል፡፡

በተመረጡና በወቅታዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችና ዕቅዶች አፈፃፀም ዙሪያ


የመንግስትን አቋም የሚተነትኑ መግለጫዎችን በማዘጋጀት ህዝባዊ ንቅናቄና ድጋፍ
እንዲፈጥር ጥረት የተደረገ ቢሆንም የሚሰጡ መግለጫዎች ተቀባይነትና ወቅታዊነት
እንዲሁም ፋይዳቸውን እየገመገሙ መምራት የሚጠይቅ መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡

10 2013 -2022 / Page


80
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የፓናል ውይይቶችም የጥራት፣የውጤታማነት ደረጃቸው ችግር ያለበት እና በቀጣይ ትክረት


የሚሻ ተግባር ነው ፡፡

ህብረተሰቡን የመረጃ ተጠቃሚ ለማድረግ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በተመረጡ

ይዘቶች ዙሪያ መረጃ ሰብስቦ የተለያዩ የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችን

በመጠቀም ህብረተሰቡ የመረጃ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል፡፡ ለአብነት

በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ስራዎች የፅሁፍ ዜናዎችን፣ የምስል ዜናዎችን እና ዜናዎችን በሚኒ

ሚዲያ ማስተላለፍ የተቻለ ሲሆን በተጨማሪም ከፋና 96.0 ጋር በመተባበር በየሳምነቱ 1

መርሀ ግብር በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ ሆኗል፡፡

 የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ተግባራት አፈጻጸም

ባለፉት 10 ዓመታት የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ የሚፈታተኑ አደጋዎችን በመከላከል ረገድ


በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በመጀመሪያው የስትራቴጅክ እቅድ ዘመን ሁለንተናዊ የእድገት ጉዞ ውስጥ የዜጎችን ሰላምና


ድህንነት በማረጋገጥ የልማት እንቅስቃሴው ያለምንም ስጋት እንዲፈጸም ተደርጓል፡፡
ከለውጡ ማግሰትም ህዝብ ተከባብሮ የመኖር እሴትና ባህል በእጅጉ የሚለያዩ የውጭና
የውስጥ ሠላምን ሊያዉኩ የሚችሉ አካላት የተለያዩ አጀንዳዎችን እየነደፋ በመስጠት
ህብረተሰቡን ብጥብጥና ሁከት ውስጥ ለማስገባት ያደረጉትን ጥረት በህብረተሰቡ አርቆ
አሳቢነትና አስተዋይነት አንዲሁም የፀጥታ አካሉ እና አመራሩ ተናቦ በመስራት ሰላምን
ሊያዉኩ የሚችሉ አካላትን ሴራ መመከት ተችሏል፡፡ለዚህም የወጣቱ ድርሻ የጎላ ነበር
ብሎ መዉሰድ ይቻላል፡፡

በከተማችን ባለ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ማንነትንና ሃይማኖትን መሠረት ያደረጉ


ያለመግባባቶችና ግጭቶች በየጊዜው እየተከሰቱ በከተማዋ ሰላምና ድህንነት ላይ አሉታዊ
ተጽእኖ ሲያሳድሩ ቆይተዋል፡ ይህን ተከተሎ በተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ የመማር
ማስተማሩን ሂደት ከማደናቀፉ በተጨማሪ በህይዎትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡የሰላም
ችግሮች ለከተማችን ጎጂ እንጂ ጠቃሚ ባለመሆናቸዉ ህብረተሰቡ ለዉጡን በማስቀጠል
በኩል ድርሻዉን እንዲወጣ ተከታታይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተሰርተዋል አሁንም
እየተሰሩ ይገኛል፡፡

በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ ህዝቦች መካከል ከሃብትና መሬት አጠቃቀም ከመልካም

10 2013 -2022 / Page


81
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አስተዳደር እጦት ጋር በተያያዘ አለመግባባቶችና ግጭቶች የሚፈጠሩበት አጋጣሚ ይታያል፡፡


በመሆኑም በከተማችን ውስጥ በሚገኙ ህዝቦች መካከል የሰላም እሴት ለመገንባትና
በዘላቂነት መልካም ግንኙነት ለመመስረት የሰላም ክበባትንና ኮሚቴዎችን የማደራጀትና
የማጠናከር፣ የህዝብ ለህዝብ ትልልቅ ስብሰባዎችን የማካሄድ ሥራ ባለፉት ዓመታት
በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል፡፡

የግጭት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ እና ፈጣን ምላሽ ስርዓት በተለይ ለግጭት ተጋላጭ ተብለዉ


በተለዩ አካባቢዎች የመረጃ ባለሙያዎችን እና ፎካል ፐርሰን በመመደብ የ 24 ሰዓት መረጃ
ልውውጥ ይደረጋል፡፡ ጥራት ያለው መረጃን በቀጣይነት እና በተከታታይነት ለማቅረብ
ያለው ተነሳሽነት በጣም እየወረደ መጥቷል፡፡ በዘርፉ ባለሙያዎች መረጃ የመለዋወጥ ሂደቱ
አስፈላጊ እና ለውጥ የሚያመጣ ነው ብለው ከልብ በማመንና ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን
ድጋፍ ከመስጠት አንፃርም በሚጠበቀው ልክ እየተሰራ አይደለም፡፡ ስለሆነም በቀጣይ
የግጭት አደጋዎችን ቀድሞ ለመተንበይና በቀን 24 ሰዓት የሚሠራ አስተማማኝ የትንበያና
ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ጠንካራ ሳይንሳዊ መሠረት እንዲኖረው ለማደረግ፤ በባለሙያ
የተሟላ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የግጭት መረጃ መለዋወጥ ሊኖር ይገባል፡፡

ከአጎራባች ዞንና ወረዳዎች ጋር የጋራ ዓመታዊ የፀጥታ እቅድ በማዘጋጀትና ቋሚ የግንኙነት


አግባብ በመዘርጋት በየጊዜው የተዘጋጀውን እቅድ በጋራ በየደረጃው በመገምገምና የታዩ
ጉድለቶችን በየጊዜው በማረም ግንኙነቱን ለማጠናከርና በህዝቦች መካከል መግባባት
እንዲፈጠር ተከታታይ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በየጊዜው የሚከሰተውን ጥፋት ግጭትና
ብጥብጥ ከማስከተሉ በፊት በአካባቢ በተቋቋሙ የሠላም ኮሚቴዎች አማካኝነት
በአካባቢው ወግና ባህል መሰረት እርቅ እንዲፈጠር በማመቻቸት ለችግሩ መፍትሄ
ለመስጠት ጥረቶች ተደርገዋል፡፡

በአጠቃላይ በከተማችን ውስጥ እያደገ ከሚመጣው የልማት ፍላጎት ጋር በተያያዘ ሊከሰቱ


የሚችሉ አለመግባባቶችና ግጭቶችን በመለየትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ
በመስራት ዘላቂነት ያለው መልካም የሆኑ የሰላም እሴቶችን መገንባት ይገባል፡፡

 ከተማ-ነክ ጉዳዮች ፍ/ቤቶች

እልባት የሚያገኙ መዝገቦች ከአቅርቦት በሁለተኛው የእድገት እና ትራስፎርሜሽን እቅድ


አንደርስበታለን ተብሎ ከተቀመጠው ግብ አንፃር ያለው አፈፃፀም በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት

10 2013 -2022 / Page


82
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የአቅርቦቱን 98% እና በመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶት ደግሞ የአጠቃላይ አቅርቦቱን 96%
እልባት ለመስጠት ግብ የተቀመጠ ሲሆን በከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች የቀረቡ መዝገቦች 98%
እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ የተመዘገበውን ውጤት ግብን ያሳካ ነበር፡፡

የማጥራት አቅም በጥቅል ሲታይ 100% የማጥራት አቅም ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ይህም
አዲስ የቀረቡትን እና ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሱትን 100% መፈፀማቸውን እና ካለፈው
ከተላለፉ መዝገቦች ለማጥራት ብዙ መስራት የሚጠበቅባቸው መሆኑን፡፡

በከተማ-ነክ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ደግሞ በእድገት እና ትራንስፍርሜሽን እቅዱ


መጨረሻ 96% የመዛግብት የማጥራት እቅድ ተይዞ ከነበረው ግብ አንፃር የተመዘገበው
ውጤት 98% መሆኑን ያሳያል፡፡

ውሳኔ ያገኙ መዝገቦች በእድሜ ቆይታ ሲታይበከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ደረጃ


ባለፉት አስር አመታት እልባት ካገኙት መዝገቦች ውስጥ 97% ያህሉ እስከ 6 ወር ቆይታ
እልባት ያገኙ፣ 2% መዝገቦች ከ 6 ወር እስከ 1 አመት ቆይታ ያላቸው እና (1%) መዝገቦች
ደግሞ ከ 1 አመት በላይ ቆይታ የነበራቸው ናቸው፡፡ ከከተማ ነክ መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት
ደግሞ አጠቃላይ እልባት ካገኙት መዝገቦች ውስጥ (95%) ያህሉ እስከ 6 ወር ቆይታ እልባት
ያገኙ፣ (3%) መዝገቦች ከ 6 ወር እስከ 1 አመት ቆይታ ያላቸው እና (1%) መዝገቦች ደግሞ
ከ 1 አመት በላይ ቆይታ የነበራቸው ናቸው፡፡ ይህም የሚያመለክተው በከተማ ነክ ይግባኝ
ሰሚ እና መጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ደረጃ እልባት የሚያገኙ መዛግብት እድሜ ቆይታ
ባለፉት አስር አመታት ተመሳሳይ በሚባል ደረጃ በአጭር የጊዜ ቆይታ እልባት እያገኙ
መምጣታቸውን ነው፡፡

በክርክር ላይ ያሉ መዝገቦች እድሜ ቆይታ በተመለከተ በከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት


ደረጃ ባለፉት አስር አመታት በቀጠሮ ከተላለፉት መዝገቦች ውስጥ 97% ያህሉ እስከ 6
ወር ቆይታ እልባት ያገኙ፣ 2% መዝገቦች ከ 6 ወር እስከ 1 አመት ቆይታ ያላቸው እና (1%)
መዝገቦች ደግሞ ከ 1 አመት በላይ ቆይታ የነበራቸው ናቸው፡፡ከከተማ ነክ መጀመሪያ ደረጃ
ፍርድ ቤትአንፃር አጠቃላይ እልባት ካገኙት መዝገቦች ውስጥ (95%) ያህሉ እስከ 6 ወር
ቆይታ እልባት ያገኙ፣ (3%) መዝገቦች ከ 6 ወር እስከ 1 አመት ቆይታ ያላቸው እና (1%)
መዝገቦች ደግሞ ከ 1 አመት በላይ ቆይታ የነበራቸው ናቸው፡፡

በከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ታይተው ውሳኔ ካገኙ በኋላ በጠቅላይ ፍርድ ቤት


በይግባኝ የመፅናት ምጣኔ በ 2003 በጀት ዓመት ከነበረበት 72% በ 2012 በጀት ዓመት
መጨረሻ ወደ 75% ከፍ ያለ መሆኑን ያሳያል፡፡

10 2013 -2022 / Page


83
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በተመሳሳይ ሁኔታ በከተማ ነክ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሳኔ ካገኙ በኋላ በከተማ ነክ
ይግባኝ ሰሚ ፍርድ በይግባኝ የመፅናት ምጣኔ በ 2003 በጀት ዓመት ከነበረበት 70% በ 2012
በጀት ዓመት ወደ 75% ማሳደግ ተችሏል፡፡

ባለፉት አስር አመታት በሁሉም እርከን ፍርድ ቤቶች የዳኞችን ቁጥር ለመጨመር ጥረት
በመደረጉ፣ ብቃት እና ክህሎታቸውን ለማሳደግ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን መስጠት
በመቻሉ እንዲሁም በፍርድ ምርመራ በተገኙ ግኝቶች ላይ ዳኞች እንዲወያዩባቸው እና
ትምህርት እንዲወስዱባቸው በመደረጉ እና በመሳሰሉት ጥረቶቸ ምክንያት በከተማ ነክ
ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ውሳኔ ካገኙ በኋላ በይግባኝ የሚፀኑ መዛግብት ምጣኔ ጎላ ባለ መልኩ
ያደገ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡

2.6 ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎች ትንተና

/Internal& External Situational


ጥንካሬና ድክመት፤ መልካም አጋጣሚዎችና ስጋቶች ትንተና ስትራቴጂያዊ ትንተና ለማካሄድ በርከት ያሉና
የተለያዩ ዘዴዎች መኖራቸው ይታወቃል፡፡ በአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የስትራቴጂያዊ እቅድ አዘገጃጀት ሂደት
በተለይ ባለ ዘርፈ ብዙ የከተማው እቅድ እየተሰራበት ያለው “የጥንካሬና ድክመት እንዲሁም “የመልካም
አጋጣሚ እና ስጋት ትንተና ዘዴ ነው፡፡ጥ.ድ.መአ.ስ ትንተና ስትራቴጂያዊ ጉዳዬችን ለመለየት ተመራጭ
ከሆኑት ዘዴዎች አንዱ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ የውስጣዊ ሁኔታዎች ትንተና የተካሄድውም የአሰራር ሂደት
እና ስርዓት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የአመራር ብቃት፣ የፋይናንስ መሳሪያዎችና ቴክኖሎጅዎች እና በተቋማዊ
ግንባታ የከተማ አስተዳደሩ ያለበትን ጠንካራና ደካማ ጐኖች የሚዳስስ ሲሆን የውጫዊ ሁኔታዎች ትንተና ደግሞ
ሃገራዊ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ አካባቢ፣ ቴክኖሎጂ እና ህጋዊ ሁኔታዎች ለከተማ አስተዳደሩ ስራ
የሚያበረክቱት መልካም አጋጣሚና ስጋቶች የሚተነተኑበት ሂደት ነው፡፡

 ጥ.ድ.መአ.ስ ትንተና የሚካሄድባቸው የመረጃ ምንጮች ብዙ ቢሆኑም ለዚህ የ 10 ዓመት መሪ እቅድ


የተጠቀምንበት የመረጃ ምንጭ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አመራር ካስቀመጡት የቀጣይ ስትራቴጂያዊ
ጉዳዬች ወይም ዋነኛ አሳሳቢ ጉዳዩች የከተማው ም/ቤት በ 2 ዐ 11 እና 2 ዐ 12 በጀት ዓመት መደበኛ
ጉባኤ ሪፖርት፣ የከተማ አስተዳደሩ የ 2 ዐ 12 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ በ 2 ዐ 12 በከተማ ደረጃ
ከተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ቅሬታዎች ከህብረተሰቡጋር በተደረጉ ውይይት ከተገኘ መረጃ፣ ከስራ
ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች /ፈፃሚዎች/ ጋር በግንባር በመወያየት አእምሮን በመጭመቅ
አስተሳሰብን በማስፋት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የደሴ ከተማ አስተዳደር ጥንካሬና ድክመት /ውስጣዊ

10 2013 -2022 / Page


84
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዳሰሳ/ እንዲሁም መልካም አጋጣሚዎችና ስጋቶች /ውጫዊ ዳሰሳ/ ዝርዝር መረጃዎች እንደሚከተለው በአጭሩ
ቀርቧል፡፡

2.6.1 የውስጣዊ ሁኔታዎች ትንተና

1. የአሰራር ሂደትና ስርዓቶች

ጥንካሬ

የነጥብ ምዘና ዘዴ የሥራ ምዘና ደረጃ ጥናት በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ተጠናቆ ተግባር ላይመዋሉ፣
የአሰራር ማንዋል በስራ ላይ መዋሉ፣የነጥብ ምዘና ዘዴ ጥናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በየደረጃው ላሉ አካላት
መሰራቱየከተማ አስተዳደሩ መዋቅራዊ ኘላንና በመዘጋጀት ላይ መሆኑ የከተማ መሬት ይዞታ
ምዝገባና መረጃ /ካዳስተር/ መዘጋጀቱ የተሻሻለና ልማትን የሚያፋጥን አደረጃጀትመጀመሩ /በከተማ
አስተዳደሩ፣ በክ/ከተማና በከተማና ገጠር ቀበሌ የአውትሶርሲንግ መጀመሩ( ጽዳትና ውበት፣የኮብል
ድንጋይንጣፍ)፤ በየደረጃው ምክር ቤቶች ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍ
መጀመራቸውየኢንቨስትመንትና መሰረተ ልማት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ መምጣቱ፤የገቢ መሰረትመስፋት፣
የከተማ አስተዳደሩ የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራምን ተግባራዊማድረጉ፣ የከተማ ነክ ጉዳዬች ፍርድ ቤትን
ማቋቋሙና ተግባሩን እያከናወነ መሆኑ፡፡በልማትስራዎች ህብረተሰቡን ለማሳተፍ ጥረት መደረጉ
ድክመት

የመረጃ ስርዓት ደካማ መሆንና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያለመታገዝ፣ /ግልጽ ያለመሆንም አለመኖር፣ የብሮድ
ባንድ አገልግሎት ኔት ወርክድ አለመሆን፣ የተቀናጀና ውጤታማ የሆነ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት አለመኖር
፣በሁሉም እርከኖች ቅንጅታዊ አሰራር ያለመኖር፣ በቦታ ምሪትና መልሶ ማልማት እንቅስቃሴ ወጥ የሆነ አሰራር
አለመዘርጋት፣ ለጥናትና ምርመራ ትኩረት አለመስጠት፣ ጠንካራ የሆነ የከተማና የገጠር ትስስር አለመኖር፣
የግንባታና መሰረተ ልማት የጥራትና ደረጃ ችግርና የተሰሩ በወቅቱ እንክብካቤ ያለማድረግ፣ የከተማዋን ጽዳትና
ውበት አለመጠበቅ /በተለይም የመፋሰሻ ችግር/፣ የተሻሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየት አቅም
ያላቸውን ልማታዊ ባለሃብቶች በመለየት ወደ ስራ ለማስገባት የለማ የኢንቨስትመንት መሬት ዝግጀት
እጥረት መኖር፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት ያለመኖር ፣ በሚፈለገው መጠን ሴቶችና
ወጣቶችን ውጤታማ ለማድረግ ስርዓቱን አለመጠቀም፣ ለባለ ብዙ-ዘርፈ ጉዳዬች ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ያለ
መስራት፣በሁሉም ስራዎች በህዝብ ዘንድ የባለቤትነት መንፈስ እየፈጠሩ የተሰሩ የልማት ስራዎችን በዘላቂነት
እንዲጠበቅ አለማድረግ፣ መከላከል ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎት ስራ ደካማ መሆን፣ መልካም ተሞክሮን ቀምሮ
ያለማስፋት፣ ምርትና ምርታማነትን አለማሳደግ፣ ጐልማሶች ትምህርትና ልዩ ፍላጐት ትኩረት አለመስጠት፣
የአስተባባሪ ኮሚቴ፣የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ መርሀግብር ፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ኘሮግራም አስተባባሪ ኮሚቴዎች
ውጤታማ አለመሆን ፣የቤቶች ልማት ኘሮግራም መጓተትና የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ አለመቻል፣
ከከተማዋ እድገት ጋር የተመጣጠነ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ/ውሃ፣መብራት፣ስልክና መንገድ/ አለመዳረስ ፣

10 2013 -2022 / Page


85
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ለመዋለ ንዋይ/ ኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ወደስራ ያልገቡ ባለሀብቶች መኖራቸዉ፣ የቴክኖሎጂ ጥገና
ማዕከል አለመኖር፣ የቴክኒክ እውቀትን ቀድቶ የማላመድና የመጠቀም አቅም አለመፍጠር ፣ በከተማ አስተዳደሩ
ስር የሚገኙ ያለሙ መሬቶችንና ሌሎች የሃብት ምንጮችን ፍትሃዊና ግልጽ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ የማዋል
እጥረት መኖሩ፣ በከተማዋ ውስጥ እየተስፋፋ የመጡ ህገወጥ ድርጊቶችን የመከላከልና የመቆጣጠር ውስንነት፣
የከተማዋን የቱሪዝም መስህቦችን ለይቶ አለማልማትና አለማስተዋወቅ /ለምሳሌ በጦሳ ተራራ፣ አዝዋ ገደል
ተራራ፣ ባህር ሸሽ ወዘተ/፣ ከተማ ከከተማ ያለ ትስስር አለመጠናከር ፣ የመሰረተ ልማት ሳይዘረጋ የከተማ
ማስፋፋት ተግባር መከናወኑ፣ በመዋቅራዊ እቅድ ካዳስተር መሰረት አለመተግበር /ለምሳሌ የገራዶ ውሃ
ኘሮጀክት አካባቢ የሚኖሩ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ውሃውን ሊበክሉ መቻላቸው ይጠቀሳሉ፡፡

2. የአገልግሎትአሰጣጥ

ጥንካሬ

ለደንበኞች የተቀላጠፈ /ተደራሽ/ አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ መሰረታዊ መዋቅሮች እስከ ቀበሌ ድረስ
በመዘርጋታቸው የስራ ውጣ ውረድና ድግግሞሽ ማስቀረት መቻሉ፣የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ መዘጋጀቱ፣
የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት እና የሥነ-ምግባር መከታተያ ተዘርግቶ ተግባራዊ መደረጉ፣ በተቋማት የአንድ
ማዕከል አገልግሎት መስጠት ናቸው፡፡

ድክመት

የፍትህ አካላቱ በፍትህ ነፃነት ሰበብ ለልማት ፍጥነት እንቅፋት መሆን ፣ አስተያየቶችን እንደ ግብዓት
አለመጠቀም፣ ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት በአንድ ቦታ ተሟልተው መሰጠት
አለመቻሉ፣ወደ ክፍለ ከተማ የወረዱ ስራዎችን መሰረት አድረጎ የተፋጠነ አገልግሎት ያለመሰጠት ፣ ከአድሎ የጸዳ
አገልግሎት መስጠት ውስንነት ፣የፈፃሚውና ተገልጋይ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት መኖር፣ በተቀመጠው
የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃዎች ጉዳዬች አለመፈጸማቸው ፣ጉዳይ አስፈፃሚዎች በሌሎች ባለጉዳዬች የአገልግሎት
ጊዜ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለማስተካከል የሚደረግ ጥረት ውስን መሆን ፣ የአገልግሎት አሰጣጡ በዘመናዊ
ቴክኖሎጂ ከሞላ ጎደል ተጠቃሽ ናቸው፡፡

3. የሰው ሀብት ልማት

ጥንካሬ

የሰው ሀብትን አቅም ለማሳደግ የሚደረግ ጅምር ጥረት መኖሩ ፣ የሰው ሃይልን ለማሟላት ጥረት መደረጉ፣ የሰው
ሀብትን ለማብቃት የረጅምና የአጭር ጊዜ ስልጠና መሰጠቱ፣ በከተማ አስተዳደሩ በከተማ ስራአመራር እና
መሬት አስተዳደር የሰለጠኑ በርካታ ባለሙያዎች መኖራቸው፣ በተለያዩ የሙያ ስብጥርና ልምድ ያላቸው
ሰራተኞች መኖራቸው፣ የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ ህግና ደንብን የሚያውቅ ሰራተኛ መፈጠሩ ፣ የባለሙያ

10 2013 -2022 / Page


86
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የመወሰን /ኃላፊነትን ከተጠያቂነት የመውሰድ/ ጅምር መኖር፣ የተረጋጋ አሰራርን ለመፍጠር ይቻል ዘንድ በስራ
ምክንያት የተለያዩ ሰራተኛ ቤተሰቦችን ለማገናኘት የተሞከረ ጅምር ፣ የሰው ሀብትን በተቋም ደረጃ መሰረታዊ
የኮምፒውተር ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ድክመት

የተቀናጀ የአቅም መገንባት ስራ አለመኖር፣ የማበረታቻ ስርዓት አለመኖርና ሰራተኛን በውጤት ያለመለካት፣
የሰው ሀብት ልማት በእቅድ አለመምራት፣ በተገቢው ቦታያለመመደብ ፣ ሰራተኛው የአመለካከት፣የክህሎትና
እውቀት ክፍተት ያለበት መሆኑ፣ የተሰጡ ስልጠናዎች ያመጡትን ለውጥ ያለመገምገም ፣ሰራተኛው
ከቴክኖሎጂና አይሲቲ ጋር ያለው ትስስር አናሳመሆን፣ የተደራጀ የልማት ሀይል በተሟላ ቁመኛ ላይ
ያለመገኘት፣ለሰራተኛዉ መጓጓዣ አገልግሎት ያለመኖር፣ የአደረጃጀቶችን ጠቀሜታ አሳንሶ ማየት፣እርካታ
ያለመኖር፣የጠባቂነት መንፈስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

4. የአመራር ብቃት

ጥንካሬ

የከተማዋን ዋና ዋና አንገብጋቢ ጉዳዩች በከንቲባ ኮሚቴ በጋራ መወሰን መቻል ፣ የሰራተኞችን የውሳኔ ሰጭነት
እያረጋገጡ መሄድ፣ ትኩረት የሚሰጣቸው ተቋማትን /ከተማ ልማት፣ገቢዎች፣ገንዘብ፣ አነስተኛና ጥቃቅን/
የመደገፍ ስራ መሰራቱ፣ መልካም ተሞክሮና ውጤቱን የማስፋት ጅምር መኖሩ፣ ለስራ እድል ፈጠራ የአመራሩ
ፍላጐትና ቁርጠኝነትበጥንካሬ ይታያሉ፡፡
ድክመት

በሁሉም እርከኖች የተቀናጀ አመራር አለመኖር፣ የተረጋጋ አመራር ያለመኖር፣ የተደራጀ የልማት ሀይል
አለመፍጠር፣ የአለመካከትና የክህሎት ችግር ፣ባለራዕይ አመራር አለመኖር፣ ውሳኔዎችን በወቅቱ ተከታትሎ
አለማስፈጸም፣ የአመራሩ በደራሽ ስራ መጠመድ ለተቋማት ስትራቴጂያዊ አመራር መስጠት አለመቻሉ፣
የአመራር አላስፈላጊ ጣልቃገብነት መኖር፣ የአመራር የክትትልና የድጋፍ አሰጣጥ ስርዓት ችግርፈቺ አለመሆን፣
ስራን በእቅድ መሰረት እየገመገሙ ያለመሄድ፣ ሚስጥር አለመጠበቅ፣ በአሰራር ላይ የጥቅም ሰንሰለትና
ቡድንተኝነት መኖር፣ የተገኙ ውጤቶችና መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት ያለማስፋት ችግር፣ በጀት
ለማስመደብ እንጂ ገቢን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ ያለመስራት ናቸው፡፡

5. የገንዘብ አቅም

ጥንካሬ

የከተማዋን የገቢ አቅም ለማጠናከር የአገልግሎት ማሻሻያ መደረጉ፣ የውስጥ ገቢ ማስገኛ ምንጮችን ማስፋፋት
መጀመሩ፣ የበጀት ድልድል ላይ ለመሰረተ ልማትና ለድህነት ተኮር ተግባራት ቅድሚያመስጠት፣ አዲሱን
የፋይናንስ ስርዓት አሰራር ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ፣ ለግብር ከፋዬች የመለያ ቁጥር መሰጠቱ፣ የገቢ አሰባሰብ

10 2013 -2022 / Page


87
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ስርዓቱን በመምሪያና በክፍለ ከተማ ደረጃ ማውረድመቻሉ፣ በውስጥ በጀት ስራን አጣጥሞ ለመስራት ጥረት
መደረጉ ናቸው፡፡
ድክመት

የግዥና ፋይናንስ ስርዓቱ የሚዘገይና የጥራት ችግር የሚታይበት መሆን፣ ግብር ከፋዬን ማህበረሰብ መሰረታዊ
መረጃዎች አለመያዝና ትክክለኛውን የግብር መጠን መሰብሰብ አለመቻል ፣ ከመደበኛ በጀት ተጨማሪ የገቢ
ማስገኛ ስራዎችን የመስራት ውስንነት መኖሩ /የገቢመሰረትን አሟጦ አለመጠቀም/፣ ውጤታማ የንብረት
አስተዳደር ስርዓት አለመኖር፣ ልዩ ልዩ ገቢዎችን በህጋዊ ደረሰኝ ባለማሰባሰብ የገቢ አቅም መዳከምና የፋይናንስ
ስርዓቱን አለመከተል፣ ለመሰረተ ልማት ግልጋሎት አስፈላጊ ማሽነሪዎች ባለመኖራቸው ለከፍተኛ ወጭዎች
መዳረግ፣ ሊዝ ገቢን በአግባቡ አለመሰብሰብ ናቸው፡፡

6. ፋሲሊቲዎች

ጥንካሬ

በከተማ አስተዳደሩ ሰልጣን ክልል የሚተዳደሩ የትምህርት፣ የጤና፣ የከተማ ልማትና ሌሎች መምሪያዎችና ጽ/ቤቶች
በተወሰነ መልኩም ቢሆን ስራን ለማሰራት የሚያስችል ግብዓቶች መኖራቸው በትንካሬ ጎን ይታያል ፡፡

ድክመት

የመኖሪያ ቤትናመጓጓዣ አገልግሎት ለሰራተኛው አለማሟላት፣ ለስራ ምቹ የሆነ የቢሮ አቀማመጥና አደረጃጀት
አለመኖር፣ ለስራ መሳለጥ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በተገቢው ሁኔታ አለመኖር ለምሳሌ ፋክስ፣ ኢንተርኔት፣
ለመስክ ስራ አገልግሎት የሚውል የትራንስፖርት አገልግሎት በተሟላ መልኩ ያለመኖር፣ የፍሳሽና ደረቅ
ቆሻሻ ማስወገጃ፣የእሳት አደጋ፣ የአምቡላንስና የከተማ አውቶብስ ተሽከርካሪዎች እጥረት መኖር ፣ ጡት
ለሚያጠቡ ሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ያለመኖር ናቸው፡፡

7. ተቋማዊ ባህል

ጥንካሬ

በየተቋሙ የአገልጋይነትና የባለቤትነት ስሜት እየዳበረ መምጣት መጀመሩ ፣ የአሰራር ግልፀኝነት እየዳበረ
መምጣቱ፣ ተቀናጅቶ በቡድን የመስራት ባህል እየዳበረ መምጣቱ፣ በተቋሙ ውስጥ ብቁ ፈፃሚ ሆኖ ለመገኘት
የመማር አቅሙን የማሳደግ ባህል እየዳበረ መምጣቱ ተጠቃሽ ናቸው፡
ድክመት

10 2013 -2022 / Page


88
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የስነ ምግባር መርሆዎችና እሴቶች እንደ ባህል አድርጐ አለመፈፀም፣ የቁጠባ ባህልን አለማዳበር፣ ተቋማዊና
ማህበራዊ ግንኙነት አነስተኛ መሆን፣ ተቋማዊ እርካታ ያለመኖር፣ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ የጋራ አድርጐ
አለመያዝ፣ የጊዜ አጠቃቀምን በሚጠብቀው ደረጃ አለማዳበር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባህል አለመዳበርና
የጠባቂነት መንፈስ መኖር፣ የሃብትና ንብረት አጠቃቀምና አያያዝ ባህል አለመዳበር፣ በዘመቻና ደራሽ ስራ
የመጠመድ ባህል መዳበር፣ ዘርፈ- ብዙ ጉዳዩች እንደ ባህል አለመውሰድ፣ ፈጠራ፣ጥናትና ምርምርን እና ሌሎቹን
የስራ ዘዴዎችን ባህል አድርጐ ያለመሄድ፣ የተቋሙን እቅድ መሰረት አድርጐ አፈፃፀምን የመከታተል ባህል
አለመዳበር ናቸው፡፡

ውጫዊ ሁኔታዎች /የመልካምአጋጣሚና የስጋት/ ትንተና

ፖለቲካዊ ሁኔታዎች
መልካም አጋጣሚዎች

ከተማዋ የራሷ አስተዳደር እንዲኖራት በክልሉ መንግስት መወሰኑ፣ ሶስቱ የመንግስት አካላት ምክር ቤት፣
አስፈጻሚ እና ፍትህ አከል መኖር፣ ምክር ቤቱ በህዝብ ምርጫ መቋቋሙ፣ ያልተማከለ እና መልካም አስተዳደር
ስርዓት መኖሩ፣ መልካም የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መኖር፣ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እየዳበረ መምጣቱ፣
በየደረጃው የምክር ቤቶች አደረጃጀት መኖሩ የህዝብ ተሳትፎ፣የተለያዩ ሴክተሮች ፖሊሲና ማስፈጸሚያ ስልቶች
መኖር፤ በፖሊሲና ስትራቴጂዎች ላይ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እያደጉ መምጣቱ ፣ የከተማ ልማት ፖሊሲና
የኢንዱስትሪ ልማት ፖኬጅ መኖሩ፣ ከተማዋ ሪጅኦ ፖሊስ ደረጃ ላይ መመደቧ ፣ከሌሎች ክልሎች፣
ከተሞችና ወረዳዎች ጋር መልካም ግንኙነት መኖር፣ ከተማዋ በሌሎች ከተሞች በጐ ገጽታ ያላት መሆኗ እና
የሰላም ከተማ ተብላ በክልል እውቅናና ሽልማት መሰጠቱ በጉልህ ይጠቀሳሉ፡፡
ስጋቶች

የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚረብሹና አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ጸረ ሰላም ድርጊቶች መኖር ፣ ለምሳሌ፡-
ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ፣ የመልካም አስተዳደር ስርዓት አለመጠናከር፣ለሙስናና ኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካዊ
ኢኮኖሚ የተመቸ ሁኔታ መኖር ናቸው፡፡

ኢኮኖሚያዊ ጉዳዬች
መልካምአጋጣሚ

ደሴ የምስራቅ አማራ የንግድ ፣ የጤና ተቋማት ማዕከል መሆኗ፣ ባለሃብቶች ተሳትፎ እያደገ መምጣቱ፣
የነፃ ገበያ ስርዓት መኖሩ፣ ከአለም አቀፍና ሃገር በቀል ድርጅቶች የገንዘብና የሙያ ድጋፍ ማግኘት መቻሉ፣
በተከታታይ የተመዘገበ የኢኮኖሚ እድገት መኖሩ፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተግባር ትኩረት መሰጠቱ፣ ለከተሞች
እድገት ትኩረት መሰጠቱ፣ የታክስ ማሻሻያ ኘሮግራም ለገቢ እድገት በር ከፋች መሆኑ፣የሰው ጉልበት፣ ሰፊ
መሬትና የውሃ ሃብት መኖር፣ የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠን የሚያስችሉ የመሰረተ ልማቶች ዝርጋታ እየተሻሻለ

10 2013 -2022 / Page


89
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

መምጣቱ/ መንገድ፣ መብራት፣ ቴሌ፣ውሃ/ ለወደብ ቅርብ መሆኗ፣ የኢንዱስትሪ ዞን ሆና ከተመረጠችው


ኮምቦልቻ ጋር በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቷ ፣የአየርመንገድ፣ በቅርብ ጊዜ ለባቡር መስመርና ወዘተ ቅርብ መሆኗ፣
ሰፊ የፋይናንስ ተቋማት መበራከት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ስጋቶች

የሸቀጦችና የግንባታ ቁሳቁሶች ዋጋ መናርና የኑሮውድነት መከሰቱ ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የአለም አቀፍ ገበያ
አለመረጋጋት፣ የህዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ እድገት አለመመጣጠን፣ በግሎባላይዜሽን ምክንያት እየተፈጠረ ባለው
ጠንካራ ውድድር ተወዳዳሪ የሆነ ምርትና አገልግሎት የማቅረብ ውስንነት ፣ የስራ አጥነት መስፋፋት፣
በመንግስት፣በግል ሴክተሩና መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅቶች መካከል ባለው የባለሙያ ክፍያ መጠን ልዩነት
እየጨመረ መምጣቱ፣ ቁጠባ በሚፈለገው ደረጃ ያለማደግና ብድር አለመመለስ ናቸው፡፡

ማህበራዊ ጉዳዬች

መልካምአጋጣሚ

የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች፣ በሰላምና በፍቅር መኖራቸው፣ የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት መስፋፋት
፣ለምሳሌ፡- የትምህርትና ጤና ተቋማትወዘተ፣ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ በሽታ እና የጤና መከላከልና
መቆጣጠር ስርዓት መዘርጋቱ፣ ለልማት አጋዥ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶች መኖር /እድር፣እቁብ፣ ወዘተ/፣ ልምድ
ያለውና የተማረ የሰው ሃይል ማግኘት መቻል ፣ ኋላቀርና ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እየቀነሱ መምጣታቸው አና
የንጽህና አጠባበቅ እየተሸሻለ መምጣቱ ይጠቀሳሉ፡፡
ስጋቶች

የህዝብ መጨመር እና የኢኮኖሚው በተመጣጠነ መልኩ አለማደግ ፣ ስራአጥነት መስፋፋቱ፣ የድህነት መጠንን
መጨሩ፣ የኑሮ ደረጃ ልዩነት በህብረተሰቡ መካከል መስፋፋትን አስከትሏል፡፡ ከዚህም ሌላ ከገጠር ወደ
ከተማው የሚፈልስ የህዝብ ቁጥር መጨመርና ማህበራዊ ችግሮችመባባስ /ወንጀል፣ ዝሙት አዳሪነት፣ጐዳና
ተዳዳሪነት፣ ጫትና ሸሻ ቤቶች፣ ልመና፣ የትራፊክ አደጋ መበራከት ናቸው፡፡

ቴክኖሎጂያዊ ሁኔታዎች
መልካምአጋጣሚ

የመረጃ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጅምር መኖሩ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በሰፊው በገበያ ላይ መኖራቸው፣በክልል
ደረጃ መረጃ ግንኙነት ቴክኖሎጅ ሽግግር እድገት ትኩረት መሰጠቱና በከተማችን የ ICT ማዕከል መኖር
፣የቴክኒክና ሙያ ተቋም መኖሩና የፈጠራ መስፋፋት ናቸው፡፡

ስጋቶች

10 2013 -2022 / Page


90
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የቴክኖሎጂ ሽግግር የተጠናከረ አለመሆን፣ የቴክኖሎጂዎች ዋጋ ከተጠቃሚዎች አቅም በላይ መሆን ፣ጥራትና
ደረጃቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጂዎች አለመቅረብ፣ ቴክኖሎጂዎችን የሚመለከቱ ዝርዝር መረጃ የሚሰጡ አካላት
ውስንነት፣ በአለም ላይ ባለው ፈጣንና ተለዋዋጭ የቴክኖሎጂ ለውጥ ምክንያት የምንገዛቸው ቴክኖሎጂዎች
ፈጥነው ከገበያ ውጭ መሆን፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመጡ አላስፈላጊ መረጃዎች መበራከት ናቸው፡፡

አካባቢያዊ ጉዳዬች
መልካምአጋጣሚ

በከተማዋና በአካባቢዋ ለቱሪስት መስህብ የሚሆኑ ታሪካዊ ቦታዎችና የሃይማኖት ተቋማት መኖራቸው
/የአይጠየፍ አዳራሽ፣ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም፣ ገታ፣ ጀማ ንጉስ፣ ሃይቅ እስጢፋኖስ ወዘተ/፣ መንግስታዊ
ያልሆኑ ድርጅቶች አካባቢን መጠበቅና ማስዋብ መጀመራቸው፣ አካባቢን ለመጠበቅ የሚያስችል የመንግስት
ፖሊሲና ስትራቴጂ መኖር ለዚህም የሚረዳ አደረጃጀት መኖር፣ የግል ባለሃብቱ በቱሪዝም ኢንቨስትመንት መስክ
ተሳትፎ አካባቢን መጠበቁ፣ የአካባቢ ጥበቃ አለም አቀፋዊ አጀንዳ መሆኑ ፣ ተስማሚ የአየር ፀባይ መኖሩ
ናቸው፡፡
ስጋቶች

የአየር መዛባትና የተፈጥሮ ሃብት መመናመን፣ የመሬት መንሸራተት፣ የአለም አማካኝ የሙቀት መጠን መጨመር በጉልህነት
ይጠቀሳሉ፡፡

ህጋዊ ሁኔታዎች
መልካምአጋጣሚ

ሊያሰሩ የሚችሉ ልዩ ልዩ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መኖር፣ ተግባርና ኃላፊነትን፣ ተጠሪነትን በግልጽ
የሚያሳይ የህግ ማዕቀፍ መኖሩ፣ የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ኘሮግራም መኖር በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡

ስጋቶች

የሙስና መስፋፋት፣ የህግ ማዕቀፍ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዬች ፈጥነው አለመዘጋጀታቸው ናቸው፡፡

2.6.3 አስቻይና ፈታኝ ሁኔታዎችን መለየት


የከተማ አስተዳደሩ የጥ.ድ.መዕ.ስ ትንተና ከተጠቃለለ በኋላ ቀጣዩ አስቻይና ፈታኝ ሁኔታዎችን መለየትና
ማደራጀት ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ አስቻይ ሁኔታዎች የተለዩት ከተቋሙ ውስጣዊ ጥንካሬና ውጫዊ መልካም
አጋጣሚዎች ሲሆን ፈታኝ ሁኔታዎቹ ደግሞ ከውስጣዊ ድክመቶችና ከውጫዊ ስጋቶች ከተገኙት መረጃዎች
በመነሳት ነው፡፡ በዚህም መሰረት የደሴ ከተማ አስተዳደር ዋና ዋናዎቹ አስቻይና ፈታኝ ሁኔታዎች የሚከተሉት
ናቸው፡፡

10 2013 -2022 / Page


91
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አስቻይ ሁኔታዎች /ጥንካሬ + መልካም አጋጣሚ/

የነጥብ ምዘና ዘዴ ጥናት በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ተጠናቆ ተግባር ላይ መዋሉ፣ የአሰራር ማንዋል/
በስራ ላይ መዋሉ፣የነጥብ ምዘና ዘዴ ጥናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በየደረጃው ላሉአካላት መሰራቱ፣ተቋማት
ለስራ በሚያመች መልኩ መደራጀታቸው፣የከተማ አስተዳደሩ መዋቅራዊ ኘላንና በመዘጋጀት ላይ መሆኑና
በኮምፒውተር የታገዘ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ (ካዳስተር) መዘጋጀቱ፣ የተሻሻለና ልማትን
የሚያፋጥን አደረጃጀት በከተማ አስተዳደር፣ ክ/ከተማና የከተማና ገጠር ቀበሌ መጀመሩ፣ የአውትሶርሲንግ
ተግባር መጀመሩ /ጽዳትና ውበት፣የጌጠና ድንጋይ ንጣፍ/፣ በየደረጃው ምክር ቤቶች ሁሉንም የህብረተሰብ
ክፍል አሳታፊ መሆናቸው፣የኢንቨስትመንትና መሰረተ ልማት እንቅስቃሴ እየተስፋፋ መምጣቱ፣ የገቢ መሰረት
መስፋት፣ የከተማ አስተዳደሩ የከተማ ጤና ማስፋፊያ መርሀ ግብር ተግባራዊ ማድረጉ፣ የከተማ ነክ ጉዳዬች
ፍርድ ቤት ማቋቋሙና ተግባሩን እያከናወነ መሆኑ፡፡

ለደንበኞች የተቀላጠፈ/ተደራሽ አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድ መሰረታዊ መዋቅሮች እስከ ቀበሌ ድረስ
በመዘርጋታቸው የስራ ውጣ ውረድና ድግግሞሽ ማስቀረት መቻሉ፣የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ መዘጋጀቱ፣
የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት እና የሥነ-ምግባር መከታተያ ተዘርግቶ ተግባራዊ መደረጉ፣ በተቋማት የአንድ
ማዕከል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ፣

የሰው ሀብትን አቅም ለማሳደግ የሚደረግ ጅምር ጥረት መኖሩ ፣ የሰው ሀብትን ለማሟላት ጥረት መደረጉ፣ የሰው
ሃይልን ለማብቃት የአጭርጊዜ ስልጠና መሰጠቱ፣ በከተማ አስተዳደሩ በከተማ ስራአመራር እና መሬት
አስተዳደር የሰለጠኑ በርካታ ባለሙያዎችመኖራቸው፣ በተለያዩየ ሙያ ስብጥርና ልምድ ያላቸው ሰራተኞች
መኖራቸው፣ የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂ፣ህግና ደንብን የሚያውቅ ሰራተኛ መፈጠሩ፣ የባለሙያ የመወሰን
/ኃላፊነትን ከተጠያቂነትየመውሰድ/ ጅምር መኖር፣ የተረጋጋ አሰራርን ለመፍጠር ይቻል ዘንድ በስራ ምክንያት
የተለያዩ ሰራተኛ ቤተሰቦችን ለማገናኘት የተሞከረ ጅምር፣ የሰው ሀብትን በተቋም ደረጃ መሰረታዊ
የኮምፒውተር ስልጠና መስጠት መጀመሩ፣ የባለሙያ የመወሰን ኃላፊነትን ጋር የመውሰድ ጅምር መኖር፣

የከተማዋን ዋና ዋና አንገብጋቢ ጉዳዩች በከንቲባ ኮሚቴ በጋራ መወሰን መቻል ፣ የሰራተኞችን የውሳኔ ሰጭነት
እያረጋገጡ መሄድ፣ ትኩረት የሚሰጣቸው ተቋማትን /ከተማ ልማት፣ገቢዎች፣ገንዘብ፣ አነስተኛና ጥቃቅን/
የመደገፍ ስራ መሰራቱ፣ መልካም ተሞክሮና ውጤቱን የማስፋት ጅምር መኖሩ፣ ለስራ እድል ፈጠራ የአመራሩ
ፍላጐትና መኖር፤

የከተማዋን የገቢ አቅም ለማጠናከር የአገልግሎት ማሻሻያ መደረጉ፣ የውስጥ ገቢ ማስገኛ ምንጮችን ማስፋፋት
መጀመሩ፣ የበጀት ድልድል ላይ ለመሰረተ ልማትና ለድህነት-ተኮር ተግባራት ቅድሚያ መስጠት፣ አዲሱን
የፋይናንስ ስርዓት አሰራር ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ፣ ለግብር ከፋዬች የመለያ ቁጥርመሰጠቱ፣ የገቢ አሰባሰብ

10 2013 -2022 / Page


92
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ስርዓቱን በመምሪያና በክፍለ ከተማ ደረጃ ማውረድ መቻሉ፣ በውስጥ በጀት ስራን አጣጥሞ ለመስራት ጥረት
መደረጉ፣ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ስራን ማሰራት የሚችል ግብዓቶች መኖራቸው፡፡

በተቋሙ የአገልጋይነትና የባለቤትነት ስሜት እየዳበረ መምጣት መጀመሩ ፣ የአሰራር ግልጸኝነት እየዳበረ
መምጣቱ፣ ተቀናጅቶ በቡድን የመስራት ባህል እየዳበረ መምጣቱ ፣በተቋሙ ውስጥ ብቁ ፈፃሚ ሆኖ ለመገኘት
የመማር አቅሙን የማሳደግ ባህል እየዳበረ መምጣቱ፤

ያልተማከለ እና መልካም አስተዳደር ስርዓት መኖሩ ፣ መልካም የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መኖር፣ የዲሞክራሲያዊ
ስርዓት ግንባታ እየዳበረ መምጣቱ፣ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት መኖሩ፣ በየደረጃው የምክር ቤቶች
አደረጃጀት መኖሩን የህዝብ ተሳትፎ ማደጉ፣ በፖሊሲና ስትራቴጂዎች ላይ የህብረተሰቡ ግንዛቤ እያደጉ
መምጣቱ፣ የከተማ ልማት ፖሊሲና የኢንዱስትሪ ልማት ፖኬጅ መኖሩ ፣ ከተማዋ ሪጅኦ ፖሊስ ደረጃ ላይ
መመደቧ ፣ከሌሎች ክልሎች፣ ከተሞችና ወረዳዎች ጋር መልካም ግንኙነት መኖር፣ ከተማዋ በሌሎች
ከተሞች በጐ ገጽታ ያላት መሆኗ እና የሰላም ከተማ ተብላ በክልል እውቅናና ሽልማት መሰጠቱ፣

ከተማይቱ የምስራቅ አማራ የንግድ ፣ የጤና ተቋማት ማዕከል መሆኗ፣ ባለሃብቶች ተሳትፎ እያደገ
መምጣቱ፣ የነፃ ገበያ ስርዓት መኖሩ፣ ከአለም አቀፍና ሃገር በቀል ድርጅቶች የገንዘብና የሙያ ድጋፍ ማግኘት
መቻሉ፣ በተከታታይ የተመዘገበ የኢኮኖሚ እድገት መኖሩ፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተግባር ትኩረት መሰጠቱ፣
ለከተሞች እድገት ትኩረት መሰጠቱ፣ የታክስ ማሻሻያ ኘሮግራም ለገቢ እድገት በር ከፋች መሆኑ ፣ የሰው
ጉልበት፣ ሰፊ መሬትና የውሃ ሃብት መኖር ፣ የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠን የሚያስችሉ የመሰረተ ልማቶች
ዝርጋታ እየተሻሻ ለመምጣቱ/ መንገድ፣ መብራት፣ ቴሌ፣ውሃ / ለወደብ ቅርብ መሆኗ፣ የኢንዱስትሪ ዞን ሆና
ከተመረጠችው ኮምቦልቻ ጋር በቅርብ ርቀት ላይ መገኘቷ ፣የአየርመንገድ፣ ባቡር መስመርና ወዘተ ቅርብ
መሆኗ፣ ሰፊ የፋይናንስ ተቋማት መበራከት፣

የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች፣አብረው መኖራቸው፣ የማህበራዊ አገልግሎት ተቋማት መስፋፋት ፣ለምሳሌ፡


የትምህርትና ጤና ተቋማት ወዘተ፣ የተቀናጀ የኮሮና ቫይረስ በሽታ እና የጤና መከላከልና መቆጣጠር ስርዓት
መዘርጋቱ፣ ለልማት አጋዥ የሆኑ ማህበራዊ እሴቶችመኖር /እድር፣እቁብ፣ ወዘተ/፣ ልምድ ያለውና የተማረ
የሰው ሃይል ማግኘት መቻል፣ ኋላቀርና ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እየቀነሱ መምጣታቸው አና የንጽህና አጠባበቅ
እየተሸሻለ መምጣቱ፣

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጅምር መኖሩ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በሰፊው በገበያ ላይ


መኖራቸው፣በክልል ደረጃ ለኢኮቴ ሽግግር እድገት ትኩረት መሰጠቱና በከተማችን የ አይሲቲ ማእከል መኖር
፣የቴክኒክና ሙያ ተቋም መኖሩ፣ የፈጠራ መስፋፋት፣

10 2013 -2022 / Page


93
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በከተማዋና በአካባቢዋ ለጎብኝዎች መስህብ የሚሆኑ ታሪካዊ ቦታዎችና የሃይማኖ ትተቋማት መኖራቸው
/የአይጠየፍ አዳራሽ፣ ግሸን ደብረ ከርቤ ገዳም፣ገታ፣ጀማ ንጉስ፣ሃይቅ እስጢፋኖስ ወዘተ/፣ መንግስታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶች አካባቢን መጠበቅና ማስዋብ መጀመራቸው፣ አካባቢን ለመጠበቅ የሚያስችል የመንግስት ፖሊሲና
ስትራቴጂ መኖር ለዚህም የሚረዳ አደረጃጀት መኖር፣ የግል ባለሃብቱ በቱሪዝም ኢንቨስትመንት መስክ ተሳትፎ
አካባቢን መጠበቁ፣ የአካባቢጥበቃ አለም አቀፋዊ አጀንዳ መሆኑ ፣ ተስማሚ የአየር ጸባይ መኖሩ፣ ሊያሰሩ
የሚችሉ ልዩ ልዩ አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች መኖር፣ ተግባርና ኃላፊነትን፣ ተጠሪነትን በግልጽ የሚያሳይ
የህግ ማዕቀፍ መኖሩ፣ የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ኘሮግራም መኖር ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ፈታኝ ሁኔታዎች/ድክመት + ስጋት/


ድክመት

የመረጃ ስርዓት ደካማ መሆንና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ያለመታገዝ፣ /ግልጽ ያለመሆንም ድረ-ገጽ አለመኖር፣
የብሮድ ባንድኢንተርኔት አገልግሎት ኔትወርክድ አለመሆን፣ የተቀናጀና ውጤታማ የሆነ የክትትልና ድጋፍ
ስርዓት አለመኖር፣በሁሉም እርከኖች ቅንጅታዊ አሰራር ያለመኖር፣ በቦታ ምሪትና መልሶ ማልማት እንቅስቃሴ
ወጥ የሆነ አሰራር አለመዘርጋት፣ ለጥናትና ምርመር ትኩረት አለመስጠት፣ ለአሰራር የሚያመች ደንቦች
መመሪያዎችና ወዘተ… በበቂ ሁኔታ ያለመሟላት፣ ጠንካራ የሆነ የከተማና የገጠር ትስስር አለመኖር፣ የግንባታና
መሰረተ ልማት የጥራትና ደረጃ ችግርና የተሰሩ በወቅቱ እንክብካቤ ያለማድረግ፣ ህብረተሰቡን በልማት ስራዎች
በሰፊው አለማሳተፍ /በቂ ግንዛቤ አለመፍጠርም/፣ የከተማዋን ጽዳትና ውበት አለመጠበቅ /በተለይም
የመፋሰሻ ችግር/፣ የተሻሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመለየት አቅም ያላቸውን ልማታዊ ባለሃብቶች
በመለየት ወደ ስራ የማስገባት እጥረት፣ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ የአሰራር ስርዓት ያለመኖር፣
በሚፈለገው መጠን ሴቶችና ወጣቶችን ውጤታማ ለማድረግ ስርዓቱን አለመጠቀም ፣ ለባለ ብዙ ዘርፈ ጉዳዬች
ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ያለመስራት፣ በሁሉም ስራዎች በህዝብ ዘንድ የባለቤትነት መንፈስ እየፈጠሩ የተሰሩ
የልማት ስራዎችን በዘላቂነት እንዲጠበቅ አለማድረግ፣ መከላከል ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎት ስራ ደካማ
መሆን፣ መልካም ተሞክሮን ቀምሮ ያለማስፋት፣ ምርትና ምርታማነትን አለማሳደግ ፣ ጐልማሶች ትምህርትና ልዩ
ፍላጐት ትኩረት አለመስጠት፣ ከተለያዩ መ/ቤቶች የተውጣጡ አማካሪዎች ፣ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ
ኘሮግራምና ፍትህ ስርዓት ማሻሻያ ኘሮግራም አስተባባሪ ኮሚቴዎች ውጤታማ አለመሆን ፣የቤቶች ልማት
ኘሮግራም መጓተትና የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ አለመቻል፣ ከከተማዋ እድገት ጋር የተመጣጠነ የመሰረተ
ልማት ዝርጋታ /ውሃ፣መብራት፣ስልክና መንገድ/ አለመዳረስ ፣ለኢንቨስትመንት ቦታ ወስደው ወደ ስራ የገቡና
ያልገቡ ባለሃብቶች መረጃ ያለመያዝ፣ የቴክኖሎጂ ጥገና ማዕከል አለመኖር፣ ቴክኖሎጂን ቀድቶ የማላመድና
የመጠቀም አቅም አለመፍጠር፣ በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ያለሙ መሬቶችንና ሌሎች የሃብት ምንጮችን
ፍትሃዊና ግልጽ በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ የማዋል እጥረት መኖሩ ፣በከተማዋ ውስጥ እየተስፋፋ የመጡ ህገ ወጥ
ድርጊቶችን የመከላከልና የመቆጣጠር ውስንነት፣ የከተማዋን የቱሪዝም መስህቦችን ለይቶ አለመስራት ለምሳሌ

10 2013 -2022 / Page


94
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በጦሳ ፣ አዝዋ ገደል ተራራ፣ ባህር ሸሽ ወዘተ/፣ ከተማ ከከተማ ያለ ትስስር አለመጠናከር፣ የመሰረተ ልማት
ሳይዘረጋ የከተማ ማስፋፋት ተግባር መከናወኑ፣ በመዋቅራዊ ኘላንና ካዳስተር መሰረት አለመተግበር ለምሳሌ
የገራዶ ውሃ ኘሮጀክት አካባቢ የተሰጡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ውሃን ሊበክሉ መቻላቸው፤

የፍትህ አካላቱ በፍትህ ነፃነት ሰበብ ልማት ፍጥነት እንቅፋት መሆን ፣ አስተያየቶችን እንደ ግብዓት አለመጠቀም፣
ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት በአንድ ቦታ ተሟልተው መሰጠት አለመቻሉ፣ወደ ክፍለ
ከተማ የወረዱ ስራዎችን መሰረት አድረጎ የተፋጠነ አገልግሎት ያለመሰጠት፣ ከአድሎ የጸዳ አገልግሎት መስጠት
ውስንነት ፣የፈፃሚውና ተገልጋይ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት መኖር፣ በተቀመጠው የአገልግሎት አሰጣጥ
ደረጃዎች ጉዳዬች አለመፈጸማቸው ፣ጉዳይ አስፈፃሚዎች በሌሎች ባለጉዳዬች የአገልግሎት ጊዜ የሚያሳድሩትን
ተጽዕኖ ለማስተካከል የሚደረግ ጥረት ውስን መሆን፣ የአገልግሎት አሰጣጡ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አለመደገፍ፤

የተቀናጀ የአቅም መገንባት ስራ አለመኖር፣ የማበረታቻ ስርዓት አለመኖርና ሰራተኛን በውጤት ያለመለካት ፣ የሰውሃይል
ልማት በእቅድ አለመምራት፣በተገቢው ቦታ ያለመመደብ፣ ሰራተኛው የአመለካከት፣ የክህሎትና እውቀት ክፍተት
ያለበትመሆኑ፣ የተሰጡ ስልጠናዎች ያመጡትን ለውጥ ያለመገምገም ፣ የሰራተኛ ፍልሰት መኖር፣ ሰራተኛው ከቴክኖሎጂና
አይሲቲ ጋር ያለው ትስስር አናሳ መሆን፣ የተደራጀ የልማት ሀይል በተሟላ ቁመኛ ላይ ያለመገኘት፤

በሁሉም እርከኖች የተቀናጀ አመራር አለመኖር፣ የተረጋጋ አመራር ያለመኖር፣ የተደራጀ የልማት ሀይል
አለመፍጠር፣ የአለመካከትና የክህሎት ችግር ፣ባለ ራዕይ አመራር አለመኖር፣ ውሳኔዎችን በወቅቱ ተከታትሎ
አለማስፈጸም፣ የአመራሩ በደራሽ ስራ መጠመድ ለተቋማት ስትራቴጂያዊ አመራር መስጠት አለመቻሉ፣
የአመራር አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት መኖር፣ የአመራር የክትትልና የድጋፍ አሰጣጥ ስርዓት ችግር ፈቺ አለመሆን፣
ስራን በእቅድ መሰረት እየገመገሙ ያለመሄድ፣ ሚስጥር አለመጠበቅ፣ በአሰራር ላይ የጥቅም ሰንሰለትና
ቡድንተኝነት መኖር፣ የተገኙ ውጤቶችና መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት ያለማስፋት ችግር፣ በጀት
ለማስመደብ እንጂ ገቢን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ ያለመስራት፤

የግዥና ፋይናንስ ስርዓቱ የሚዘገይና የጥራት ችግር የሚታይበትመሆን ፣ ግብር ከፋዬን ማህበረሰብ ለይቶ ውዝፍ
ግብር የከፈሉና ያልከፈሉ መረጃ ያለመያዝ ትክክለኛውን የግብር መጠን መሰብሰብ አለመቻል ፣ ከመደበኛ በጀት
ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ስራዎችን የመስራት ውስንነት መኖሩ /የገቢ መሰረትን አሟጦ አለመጠቀም/፣ ውጤታማ
የንብረት አስተዳደር ስርዓት አለመኖር፣ ልዩ ልዩ ገቢዎችን በህጋዊ ደረሰኝ ባለማሰባሰብ የገቢ አቅም መዳከምና
የፋይናንስ ስርዓቱን አለመከተል፣ ለመሰረተ ልማት ግልጋሎት አስፈላጊ ማሽነሪዎች ባለመኖራቸው
ለከፍተኛወጭዎችመዳረግ፣ የመሬት ገቢን ኪራይ ሊዝ ጨምሮ በአግባቡ አለመሰብሰብ ፣

የመኖሪያ ቤትና ትራንስፖርት ለሰራተኛው አለማሟላት፣ ለስራምቹ የሆነ የቢሮ አቀማመጥና አደረጃጀት
አለመኖር፣ ለስራ መሳለጥ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች በተገቢው ሁኔታ አለመኖራቸው መኪና፣ ፋክስ፣ የቢሮ
መገልገያዎች ፣ኢንተርኔት፣ ለመስክ ስራ አገልግሎት የሚውል የመጓጓዛ መኪና አገልግሎት በተሟላ መልኩ

10 2013 -2022 / Page


95
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ያለመኖር፣ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ፣ የእሳትአደጋ፣ የአምቡላንስና የከተማ አውቶብስ ተሽከርካሪዎች
እጥረት መኖር፤

የስነ ምግባር መርሆዎችና እሴቶች እንደ ባህል አድርጐ አለመፈጸም፣ የቁጠባ ባህልን አለማዳበር፣ ተቋማዊና
ማህበራዊ ግንኙነት አነስተኛ መሆን፣ ተቋማዊ እርካታ ያለመኖር፣ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ የጋራ አድርጐ
አለመያዝ፣ የጊዜ አጠቃቀምን በሚጠብቀው ደረጃ አለማዳበር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ባህል አለመዳበርና
የጠባቂነት መንፈስ መኖር የሃብትና ንብረት አጠቃቀምና አያያዝ ባህል አለመዳበር፣ በዘመቻና ደራሽ ስራ
የመጠመድ ባህል መዳበር፣ ዘርፈ ብዙ ጉዳዩች እንደ ባህል አለመውሰድ፣ ፈጠራ፣ጥናትና ምርምርን እና ሌሎቹን
የስራ ማሳለጫ ባህል አድርጐ ያለ መሄድ፣ የተቋሙን እቅድ መሰረት አድርጐ አፈፃፀምን የማየት ባህል
አለመዳበር፤

የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ የሚረብሹና አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ጸረ ሰላም ድርጊቶች መኖር ፣ ለምሳሌ፡-
ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ፣ የመልካም አስተዳደር ስርዓት አለመጠናከር፣ ለሙስና ኪራይ ሰብሳቢ ፖለቲካዊ
ኢኮኖሚ የተመቸ ሁኔታ መኖር፤

የሸቀጦችና የግንባታ ማቴሪያል ዋጋ መናርና የኑሮ ውድነት መከሰቱ ፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የአለም አቀፍ ገበያ
አለመረጋጋት፣ የህዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ እድገት አለመመጣጠን፣ በግሎባላይዜሽን ምክንያት እየተፈጠረ ባለው
ጠንካራ ውድድር ተወዳዳሪ የሆነ ምርትና አገልግሎት የማቅረብ ውስንነት ፣ የስራ አጥነትመስፋፋት፤ በመንግስት፣
በግል ሴክተሩና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች መካከል ባለው የባለሙያ ክፍያ መጠን ልዩነት እየጨመረ
መምጣቱ፣ ቁጠባ በሚፈለገው ደረጃ ያለማደግና ብድር አለመመለስ፤

የህዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ መጨመር ፣የስራ አጥነት መስፋፋትና የድህነትመጨመር፣ የኑሮ ደረጃ ልዩነት
በህብረተሰቡ መካከል መስፋት፣ ከገጠር ወደ ከተማው የሚፈልስ የህዝብ ቁጥር መጨመርና ማህበራዊ ችግሮች
መባባስ /ወንጀል፣ ዝሙት አዳሪነት፣ጐዳና ተዳዳሪነት፣ ጫት፣ ሺሻ ቤቶች፣ ልመና ወዘተ/፣ የትራፊክ አደጋ
መበራከት፤የቴክኖሎጂ ሽግግር የተጠናከረ አለመሆን፣ የቴክኖሎጂዎች ዋጋ ከተጠቃሚዎች አቅም በላይ መሆን
፣ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጂዎች አለመቅረብ ፣ ቴክኖሎጂዎችን የሚመለከቱ ዝርዝር መረጃ የሚሰጡ
አካላት ውስንነት፣ በአለም ላይ ባለው ፈጣንና ተለዋዋጭ የቴክኖሎጂ ለውጥ ምክንያት የምንገዛቸው
ቴክኖሎጂዎች ፈጥነው ከገበያ ውጭመሆን፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚመጡ አላስፈላጊ መረጃዎች
መበራከት፣የአየር መዛባትና የተፈጥሮ ሃብትመመናመን፣ የመሬት መንሸራተት፣ የአለም አማካኝ የሙቀት መጠን መጨመር
፤ የሙስና መስፋፋት፣ የህግ ማዕቀፍ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዬች ፈጥነው አለመዘጋጀታቸው፤

10 2013 -2022 / Page


96
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ክፍል ሶስት
3. የመሪ ዕቅዱ መነሻዎች፣ የትኩረት አቅጣጫዎች፣ ዓላማዎችና ግቦች
3.1 የእቅዱ መነሻ ሁኔታዎች/ የሁኔታዎች ትንተና
3.1.1 ክልላዊና ከተማዊ ሁኔታዎች

የ 10 ዓመት ዕቅድ ይዘትና ዋና ዋና ግቦች በአግባቡ ለመወሰን በርካታ ጉዳዮችን ከግምት


ዉስጥ ማስገባት ይጠይቃል፡፡ መነሻ ታሳቢዎችን ከወዲሁ በግልጽ ማስቀመጥ ካልተቻለ
ጥራት ያለዉ ግብ ለማስቀመጥ እንዲሁም የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ተገቢነት ያላቸዉ
ተግባራት በትክክል መወሰንና መፈጸም አዳጋች ያደርገዋል፡፡ በዚህ ደረጃ መተሳሰር
ያለባቸዉን ጉዳዮች ከወዲሁ በአግባቡ ለይቶ ወደ ስራ መግባት ከተቻለ ግን ተገቢዉን
ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እቅዱን ለማሳካት ምቹ ሁኔታ መፍጥር ይቻላል፡፡ ስለዚህ የእቅድ

10 2013 -2022 / Page


97
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዝግጅት መነሻዎች በተሟላ መንገድ ተተንትነዉ መቀመጥ ያለባቸዉ በመሆኑ ዋና ዋና


መነሻዎች እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

3.1.2 የከተማ አስተዳደሩ ራዕይ

የከተማ አስተዳደሩ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ራዕይ ለ 10 ዓመቱ መሪ ዕቅድ ዝግጅት


በመነሻነት መዉሰድ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ይህንን ራዕይ እዉን በማድረግ ሂደት የከተማዉን
ነባራዊ ሁኔታ መሰረት ያደረገ በቀጣይ 10 ዓመት የዕቅድ ዘመን ባለዉ ጊዜ ዉስጥ
የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ራዕዩን ማሳካት የሚችሉ መሆናቸዉን ማረጋገጥ ይጠይቃል፡፡

3.1.3 የመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች

አገራችን ከድህነትና ኋላቀርነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ያላት ሀገር እንድትሆን የተለያዩ


የከተማ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተቀርፀዉ በመተግበር ላይ ሲሆኑ ከዚህ
በተጨማሪ የትምህርት፣ የጤና፣ የኢንቨስትመንት፣ የማህበራዊ፣ የአካባቢ ጥበቃ ወዘተ
ፖሊሲና ስትራቴጅዎች በመሻሻል ስራ ላይ እየዋሉ ይገናሉ፡፡

የቀጣዩን 10 ዓመት እቅድ ስናዘጋጅ የፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን መሰረታዊ


አቅጣጫዎችንና እነዚህ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመመራት የመጣዉን ለዉጥ ለእቅድ
ዝግጅት መነሻ ማድረግ የማይታለፍ ጉዳይ ነዉ፡፡ ስለሆነም ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች
ለእቅድ ዝግጅት መነሻ አድርጎ መዉሰድ በአንድ በኩል በፖሊሲዎቹ አማካኝነት የመጣዉን
ለዉጥ በአግባቡ ለመመዘንም ሆነ ከዚሁ ጋር አያይዞ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን
በጥልቀት ለመገንዘብ የሚያግዝ ይሆናል፡፡

3.1.4 የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም

የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሲዘጋጅ መሰረታዊ መነሻዎችን ተቀምጠዉ የነበሩ


ግቦችና ግቦችን ለማሳካት በተደረገዉ ርብርብ የተገኙ ዉጤቶች፣እቅዱን በመተግባር ሂደት
የነበሩ ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን በተለይም ለቀጣዩ እቅድ ዝግጅት ካላቸዉ ፋይዳ አንጻር
ታይቶ በዝርዝር መገምገምና ዉጤቱን ለቀጣዩ እቅድ ዝግጅት በመነሻነት መጠቀም የግድ
ይላል፡፡

ስለሆነም የባለፈዉን እቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ ግምገማ በማካሄድ በግምገማዉ ላይ


ከሁሉም የሚመለከታቸዉ ጋር መግባባት መፍጠር፣ለመጭዉ ዘመን እቅድ ዝግጅትም ወሳኝ
መነሻ አድርጎ መጠቀም ይገባል፡፡

3.1.5 የህዝባችን አዳዲስ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች

10 2013 -2022 / Page


98
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት ህዝቡ ለአዳዲስ የልማት ጥያቄዎችና ፍላጎቶች


መነሳሳት እንዲፈጥር አድርጎታል፡፡ በመሆኑም የቀጣዩ የ 10 ዓመት መሪ እቅድ ዝግጅት
እነዚህን አዳዲስ የህዝብ ፍላጎቶችና ጥያቄዎች ለመመለስና ህዝቡን በላቀ ደረጃ ተሳታፊና
ተጠቃሚ ለማድረግ በመነሻነት መዉሰድ አስፈላጊ ይሆናል ፡፡ በዚህ ረገድ የህዝቡን ተሳትፎ
ባረጋገጠ መንገድ ሊመልሱ የሚገቡ ጥያቄዎችን ከወዲሁ መለየትና በእቅድ መመለስ
እንዲቻል ተገቢዉን ትኩረት መስጠት ይኖርበታል፡፡

3.1.6 የመረጃ ስርዓት

መረጃን በተመለከተ ያለዉ ግንዛቤ አናሳ ከመሆኑ ባሻገር የሚሰጠዉ ትኩረት ዝቅተኛ
ነዉ፡፡ በዚህም በእቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ስራዎች ላይ አሉታዊ
ተጽኖ እያሳረፈ ይገኛል፡፡ ለዚህም የመረጃ ስርዓት በአግባቡ በተደራጀ ስርዓት
ለመዘርጋት የሚያስችል አደረጃጀት እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም የመረጃ
ማሰባሰብ፣ማደራጀትና ለተጠቃሚ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር የመረጃ ስርዓት መዘርጋት
አስፈላጊ በመሆኑእንደ መነሻ ተወስዷል፡፡

3.1.7 የመልካም አስተዳደርና ፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ተግባራት አፈጻጸም

የመልካም አስተዳደርና ፍትህ ስርዓት ማሻሻያን በተመለከተ የሥነ ምግባር ጥሰትን መከላከል
የህዝብ ቅሬታ ሰሚተግባር ያለውን የፍትህ ጥራት መጓደል ችግር ሊፈታ የሚያስችልበት
ሁኔታ ከፍተኛ ነው፡፡ ከአስተዳደራዊ ጉዳዮች አንፃር የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም
አስተዳደር ማሻሻያ ኘሮግራሞችን ተፈፃሚ ለማድረግ በጽ/ቤቱ ስር ያሉ አመራሮች እና
ሰራተኞች በሙሉ የራሳቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በአጠቃላይ
ሀገራዊ ጉዳዮች ወደ ታች ለሚፈጸሙ ተግባራት ትልቅ ማስፈጸሚያ መሳሪያ ሆነው
የሚጠቅሙ ናቸው፡፡

3.1.8 የክልሉ የቀጣይ 10 አመት መሪ እቅድ

3.2 የተገልጋይ ፣ባለድርሻና አጋር አካላት ትንተና

ያለፈውን መሪ እቅድ መነሻ በማድረግ በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ ማለትም

10 2013 -2022 / Page


99
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በተገልጋይነት ህዝቡ፤በአጋርነት የግል ድርጅቶች፣መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣አጎራባች


ክልሎች፣ዞኖች፣የእምነት ተቋማት፣የምርምርና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ሲቪክ
ማህበራት፣ባለድርሻ አካላት ደግሞ የከተማ ልማት፣ሴክተር መ/ቤቶች፣ክፍለ
ከተሞች፣ቀበሌዎች፣የሚጠቀሱ ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

3.2.1 የዜጋው/ህብረተሰቡ ፍላጎት

የህብረተሰብ ክፍል ሲባል የከተማ ነዋሪውን፣ ከከተማው ውጭ ያሉ ዜጎችና በክልሉ


የሚንቀሳቀሱ ተገልጋዮችን ያካተተ ሲሆን መሰረታዊ ፍላጎቱ የልማት፤የመልካም አስተዳደር
እና ዴሞክራሲ ፤ሰላም እና ምቹ ከባቢ ነው፡፡ በመሆኑም ለዜጋው የሚሆኑ የኢኮኖሚ፣
የማኅበራዊ እና የመሰረተ ልማቶችን መዘርጋት፤ ወቅታዊ እና ታአማኒነት ያለው መረጃ
የማገኘት፣ እንዲሁም በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገልግሎት
የማግኘት መብቱ እንዲከበርለት፤እንዲሁም ቅሬታዎቹ በአግባቡና በወቅቱ እንዲፈቱለት፣
ቀልጣፋ ውሳኔና የፍትህ አገልግሎት ማግኘትም ይፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ ሠላምና ደህንነቱ
ተከብሮ ያለስጋት የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራው በማጠናከር ከተማዋን የዜጎች
ምቹ እና መኖሪያ አንድትሆን ይፈለጋል፡፡ከማህበረሰቡም ህግና ስርአትን አክብሮ መብትን
መጠየቅ፣የሚጠበቅባቸዉን ግዴታ መወጣትይጠበቅባቸዋል፡፡

3.2.2 የመንግስት መ/ቤቶች እና ሠራተኞች

የመንግስት መ/ቤቶች ፍትሃዊ የበጀት ድልድልና ወቅቱን የጠበቀ የበጀት ስርጭት የሚፈልጉ ሲሆን
በተመደበላቸውም በጀት በአግባቡ ለመጠቀም ይቻል ዘንድ ግልፅ የሆነ የፖሊሲ አቅጣጫዎችና ለሥራ
አጋዥ የሆነ ህግና የህግ ከለላ ይፈልጋሉ፡፡

በተመሣሣይ መ/ቤቶች ልዩ ልዩ የግብዓት አቅርቦቶችን በወቅቱ ማግኘትና አቅማቸውንም በስልጠና፣


በምክር አገልግሎት ማጐልበት ይሻሉ፡፡ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሠራተኞች ለተልዕኮ የሚያበቃ
ስልጠና፣ምቹየሥራአካባቢና የሥራ ዋስትና የሚያስፈልጋቸው ከመሆኑም በላይ ወቅቱን የጠበቀ
የደመወዝና የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ፣ የመልካም አስተዳደር ችግራቸው እንዲፈታላቸውና የተረጋጋ
አመራር እንዲያገኙ ይፈልጋሉ፡፡በሚሰጡት አገልግሎቶች የረካ ህብረተሰብ መፍጠር ይጠበቅባቸዋል፡፡

10 2013 -2022 / Page


100
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

3.2.3 የብዙሀን ማህበራት

የብዙሃንና የሙያ ማህበራት ቀጣይነትና ተከታታይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራእና የክትትልና ድጋፍ
አገልግሎት የሚፈልጉ ሲሆን በተለይም የመስሪያ ቦታ፣የፋሲሊቲና የብድር አቅርቦት ሊጠቀስ ይችላል፡፡
ማህበራቱ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሙያ ነፃነታቸው እንዲጠበቅላቸውና የህግ ጥበቃና ከለላ
እንዲደረግላቸው ይፈልጋሉ፡፡ በአጠቃላይ የማህበሩ አባላት ሠፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው፣ተገቢ
መረጃ እንዲደርሳቸው እና የሁለንተናዊ የልማት ተሳታፊነታቸው መረጋገጥን ይፈልጋሉ፡፡የአባላትን
መብት ማስከበርና ለዲሞክራሲ ስርአት እዉን መሆን መታገል ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.2.4 የግል ዘርፍ ፍላጐት

የግል ዘርፉ ከሚያነሳቸው ፍላጐቶች መካከል የለማ መሬት አቅርቦት፣ የተረጋጋ ፖለቲካዊና ማክሮ
ኢኮኖሚ እንዲፈጠርለት እና በተሠማራበት መስክም የሠለጠነ የሰው ኃይል ማግኘት ይፈልጋል፡፡
ለልማታዊ እንቅስቃሴውም ፈጣንና ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት፣ አጋዥ የሆነ አስተማማኝ የልማት
ፋይናንስ አቅርቦት እና ፍትሀዊ የግብርና የቀረጥ ሥርዓት እንዲዘረጋለት ይሻል፡፡ ዘርፉ በዓለምና በሀገር
አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖለ መገኘት የገበያ መሠረተ ልማትና የመረጃ ሥርዓት፣ ልዩ ልዩ የማበረታቻ፣
የግብዓትና የቴክኖሎጅ አቅርቦት እንዲኖር ይፈልጋል፡፡ በተመሳሳይ የአቅም ግንባታ ድጋፍ የሚፈልግ
ሲሆን በአጠቃላይ ለዘርፉ በሚወጡ የህግ ማዕቀፎች ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን ይሻሉ፡፡ ከግል ዘርፉ
ህግና ስርአትን አክብሮ መንቀሳቀስ፣ህገወጥነትን መፀየፍ፣ግዴታቸዉን በቅንነት መወጣት
ይጠበቅባቸዋል፡፡

10 2013 -2022 / Page


101
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

3.2.5 የልማት ድርጅቶች

የከተማ አስተዳደር የመልካም አስተዳደር ግንባታ ለማገዝ የተሰማሩ የተለያዩ ኢንተርፕራይዞች፣የልማት


ማኅበሮች፣ኢንዶውመንቶች በከተማው ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የመሰረተ ልማት ግንባታ የነቃ
ተሳትፎና ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከት፣ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር፣የሰለጠነ የሰውኃይልና
የአቅም ግንባታ አገልግሎት፣ አስተማማኝ የግብዓት አገልግሎት፣ የግብይትና የመረጃ
ልውውጥ፣የተፋጠነና ውጤታማ የመንግስት አገልግሎት፣እንዲሁም ለስራቸው አጋዥ የሆነ የመሰረተ
ልማት አገልግሎት ይፈልጋሉ፡፡የልማት ድርጅቶች ከከተማ አስተዳደር ጋር ተደጋግፎና ተቀናጅቶ
ለመስራት ምቹ ሁኔታን ይፈልጋሉ፡፡ከልማት ድርጅቶች የሚሰሩት ስራ የመንግስት የልማት እቅድን
መሰረት ያደረገ መሆኑን ማሳየት፣የአሰራር ግልፅነት ማስፈን፣ህግና ስርአትን ተከትሎ መንቀሳቀስ
ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.2.4 የእምነትተቋማት

በከተማችን የተለያዩ የዕምነት ተቋማት እንደ መኖራቸው ማንም ሰው የፈለገውንና ያመነበትን


ሃይማኖት የመከተል መብት፤የእምነት ነፃነት እና እኩልነት እንዲኖር ይፈለጋሉ፡፡ ለዚህም ሠላምና
ፀጥታ፣ በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት በቀጥታ ተሳታፊ መሆንን ይፈልጋሉ፡፡ ከሀይማኖት ተቋማት
ተከታዮቻቸዉን በእኩልነት፣በፍቅር፣ በመከባበረና በሰላም ዙሪያ ማስተማር ይጠበቅባቸዋል፡፡

10 2013 -2022 / Page


102
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

3.2.7 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች

የተለያዩ የእርዳታና ብድር አገልግሎት መስጠት የሚፈልጉ ለጋሽ ድርጅቶች በቀጥታ ገብተው የከተማ
አስተዳደሩ በሚፈልጋቸው ኢኮኖሚያዊ ወይም ማህበራዊ መስኮች የተሰለፉ መንግስታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶች ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር፣ሊያሰራ የሚችል ተስማሚ የፖሊሲና የአሰራር
ማዕቀፍ፣ድጋፍ በሚያደርጉባቸው የልማት መስኮች ከመነሻ እቅድ ጀምሮ እስከ አፈፃፀም ውጤቶችና
ስኬቶች ግልፅ መረጃና ግብረ-መልስ፣የተሟላ መሰረተ ልማት፣ የሰለጠነ የሰውኃይል፣ ሠላምና ፀጥታ
በእጅጉ ይፈልጋሉ፡፡ወቅታዊ ሪፖርት፣የላቀ የሃብትአጠቃቀም፣ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት፣ተሳትፎና
የተረጋጋ የመንግስት መዋቅር መኖሩንም ይፈልጋሉ፡፡ በኩል በአሰራራቸዉ የግልፅነትና ተጠያቂነት
ስርአትን ማስፈን፣ ከመንግስት የልማት እቅድ ጋር የተዋሀደና የማይቃረን ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.2.8 አጎራባች ዞኖች

በጋራ ማደግና መልማት ለሕዝቦች ሰላማዊ ኑሮ እና ፈጣንና ዘላቂ ልማት ለማስመዝገብ የሚኖረው
ፋይዳ በእጅጉ ጉልህ ነው፡፡ስለሆነም አጎራባች ዞኖች በልማት በኩል ሊኖሩ የሚገቡ የትብብር መስኮች
እንዲለዩና የተጠናከረ የትብብር መስክ እንዲኖር፣ ባዋሳኝ አካባቢ በጋራ እና በቅንጅት በመስራት
የተረጋጋና ሠላማዊ ግንኙነት እንዲኖር፣የህዝብ የእርስ በእርስ፣የንግድ፣የባህል ትስስርና ወዳጅነት
እንዲጠናከር በአጠቃላይ በፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስኮች የተጠናከረ ግንኙነት
እንዲፈጠር፣ በልምድና በዕውቀት መደገጋገፍን ይፈልጋሉ፡፡ ከአጎራባች ዞኖች በትብብር ለመስራት
ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

10 2013 -2022 / Page


103
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

3.2.9 ከፍተኛ የምርምርና የትምህርትተቋማት

ለምርምር፣ለትምህርትና ስልጠና ምቹ የስራ ሁኔታ እንዲፈጠር፣ በዩኒቨርሲቲና ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ


ተቋማት መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲኖር፣የቅርብ አመራርና ድጋፍ እንዲያድግና ማህበረሰብ አቀፍ
አገልግሎት እንዲስፋፋ ይፈልጋሉ፡፡ከተቋማቱ የስልጠና ድጋፍ መስጠት፣አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን ማፍለቅ
እና የማህበረሰብ ድጋፍ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.2.10 የክልል መንግስት

ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ግንኙነት በአጋር አካልነት ወይም እንደ ባለድርሻ አካላት
የሚታዩ ሲሆን በመሠረታዊነት ከከተማ አስተዳደሩ እና ከተለያዩ የከተማ መምሪያዎች ወይም
ጽ/ቤቶች ወቅታዊ፣ ታማኝ እና ግልጽ መረጃ ይፈልጋሉ፡፡በክልል ደረጃ የሚወጡ የአፈጻጸም
ደረጃዎችም በከተማ አስተዳደር ደረጃ እንዲጠበቁና ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት አሠራርና የሀብት
አጠቃቀም እንዲኖር፣ከተማ አስተዳደሩ ከአጎራባች ዞኖች ጋር ጥብቅ ቅንጅት በመፍጠር ለሀገር እድገት
የድርሻውን እንዲያበረክትና የከተማ አስተዳደሩ የልማት እንቅስቃሴ ለክልል እድገት ያለው ድርሻ
እንዲጠናከር ይፈልጋሉ፡፡ በአጠቃላይ ከተማ አስተዳደሩ የህዝብ የርስ በርስ የባህል
ትውውቅ፣መቀራረብ፤መቻቻልና ትስስር የጎለበተበት፣ የተጠናከረ ያልተማከለ አስተዳደር
የሚተገበርበት እና ለኢንቨስትመንት፣ ለንግድና ለቱሪዝም ምቹ ሆኖ እንዲገኝ በማድረግ በክልል ደረጃ
አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ይፈልጋሉ፡፡ከክልሉ መንግስት ተገቢዉን ድጋፍ
መስጠት፣አዳዲስ አሰራሮችን፣መመሪያዎችንና ደንቦችን በወቅቱ ማድረስና ተገቢና ወቅታዊ ግብረ
መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

3.2.11 የግልና የመንግስት የፋይናንስ ተቋማት

እነዚህ ተቋማት የከተማ ህዝብ ያደገ የገቢ አቅም ያለው፣የቁጠባ ባህሉ የዳበረ፣ታማኝ ተበዳሪ እና
አስተማማኝ ብድር ከፋይ እንዲሆን፣የተሟላ መሠረተ ልማት እና የሰው ሃይል፣ትክክለኛና ሁሉ አቀፍ
መረጃ፣ የህግ ከለላና የጥበቃ አገልግሎት እንዲያገኙና ለደንበኞቻቸው ምቹ እና አስቻይ ሁኔታ በከተማ
አስተዳደሩ እንዲኖር ይፈልጋሉ፡፡

ከላይ ከተተነተነው የሁኔታ ግምገማ፣ የዜጎችና የባለድርሻ አካላት ፍላጎት ትንተና እንዲሁም በክልል
ደረጃ የተዘጋጀውን መሪ ዕቅድመነሻ በማድረግ የቀጣዩ አስር አመት የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10
ዓመት መሪ ዕቅድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

10 2013 -2022 / Page


104
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

3.3. ስትራቴጅካዊ ጉዳዮች

ባለፉት 10 አመታት የእቅድ አፈፃፀም ወቅት የከተማዋ ቁልፍ ተግባራት የነበሩ ነገር ግን
በሚፈለገዉ ደረጃ ተፈፃሚ ያልሆኑና ተሻጋሪ ችግሮችን በአግባቡ መለየትና የቀጣይ 10
አመት ስትራቴጅካዊ ጉዳዮችን መለየትና ችግሮቹ የሚፈቱበተትን አቅጣጫ ማስቀመጥ
ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለዉ ለመለየት ተሞክሯል፡፡

ጠንካራ የተቋም ግንባታ ያለመኖር፣የማስፈፀምና የመፈፀም ዉስንነት፣የስራ አጥነት


መብዘትና በከተማው ድህነት መኖር፣የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአት ችግር፣
የመሬት ምዝገባና የመሬት ልማት ስርአቱ ያለመዘመን፣ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን
ቀልጣፋና ዉጤታማ አለማድረግ፣ህጋዊና ፍትሃዊ የንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ
ስርአት አለመጠናከር፣ የከተማ ግብርና የግብርናዉ ምርትና ምርታማነት ያለማደግ፣
የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር፣ የተጎሳቆሉና ያረጁ አካባቢዎች ያለመታደስ፤
ከአደጋ የፀዳና ተደራሽ የሆነ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት
አለማስፋፋት፣ማህበራዊ አገልግሎቶች ጥራትና ተደራሽነት አለመሆን፣
ለኢንቨስትመንትና ቱሪዝም መስፋፋት ትኩረት ያለመሰጠት፣ የመዝናኛ፣ የአረንጓዴ
ልማትንና የስፖርት ማዘዉተሪያ ቦታዎች በበቂ ደረጃ ያለመኖር ፣የመልካም
አስተዳደር ስርአትን ማስፈን አለመቻል፣ህገወጥ ተግባራትን፤ ኪራይ ሰብሳቢነትን እና
ብልሹ አሰራር ለመቀነስ ያለው ትግል አነስተኛ መሆኑ ፣የተቀናጀ የመሰረተ ልማት
ግንባታ ስርአት ያለመኖር በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸዉ፡

10 2013 -2022 / Page


105
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ክፍል አራት

4. የደሴ ከተማ አስተዳደር ተልዕኮ፣ እሴቶችና ራዕይ

4.1 ተልዕኮ

ሁሉንም የከተማውን የልማት ኃይሎች በተቀናጀ መንገድ በማሳተፍና ያለንን ፀጋዎች/ ሀብቶች በላቀ
ደረጃ በመጠቀም አስተማማኝ ሰላም፣ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር በማስፈን፤ ሁሉን አቀፍ
የከተማ ልማት በዘላቂነት በማረጋገጥ ህዝቡ በየደረጃው ተጠቃሚ የሚሆንበትና ለአገራዊ ልማት
ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የሚያበረክት እድገት በከተማ አስተዳደሩ ማምጣት፡፡

4.2 እሴቶች
የዳበረ የዴሞክራሲ ባህል ስር እንዲሰድ እናደርጋለን፤
የህዝብ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን እናረጋግጣለን፤
ቁጠባና ኢንቨስትመንት ባህሉ የሆነ የከተማ ህዝብ እንፈጥራለን፤
የስራፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ሥነ-ምግባር እናጐለብታለን፤
ለለውጥ የሚተጋ አመራርና ፈጻሚ እንገነባለን፤
የዜጎችን ፍትሀዊና እኩልነትን እናረጋግጣለን፤
የህዝብ አገልጋይነት ስሜትና የስራ ተነሳሽነት ባህልን እናዳብራለን፤
በቡድናዊ አሰራርና በውጤት መለካትን እናምናለን፤

10 2013 -2022 / Page


106
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዘላቂነት ያለው የከተማ ልማት እናረጋግጣለን፤


4.1 ራዕይ

በ 2023 ዓ.ም ደሴ ከተማ ባህሏን፣ አብሮነቷን እና የተፈጥሮ ፀጋዋን የጠበቀች፣ መሰረተ


ልማት የተሟላላት፣ መልካም አስተዳደርና ሰላም የሰፈነባት ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች
የንግድ፣ የቱሪዝም፣ የጤና እና የኢንዱስትሪ ማዕከል ሆና ማየት፡፡

ክፍል አምስት
5. የመሪ ዕቅዱ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች፤
ዓላማዎች እና ግቦች
5.1 የመሪ እቅዱ ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች
የቀጣይ 10 አመት (2013-2022) እቅድ ሲዘጋጅ ያለፉትን 10 አመታት ማለትም
የመጀመሪያዉ እ.ት.እ (ከ 2003-2007) እና የሁለተኛዉ እ.ት.እ (ከ 2008-2012)
መነሻዎች፣ አላማዎችና የትኩረት አቅጣጫዎችን አፈፃፀም፣ የሀገራችንንና የክልላችንን
ነባራዊ ሁኔታ፣የከተማ ልማት ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጅዎችንና የማስፈፀሚያ ሰነዶችን
በጥልቀት በመፈተሽ በመነሻነት ለመዉሰድ ተሞክሯል፡፡ በዚህም መነሻነት በቀጣዮቹ
10 አመታት ልዩ ትኩረት ሊደረግባቸዉ የሚገቡ ጉዳዮችን እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡

5.1.1 በቀጣዮቹ 10 አመታት በየዘርፉ ለማከናወን የታቀዱ ተግባራትን


በዉጤታማነት ለመፈፀምና የተቀመጠዉን ግብ ለማሳካት የሚቻለዉ የተደራጁ
ተቋማት ሲኖሩ እንዲሁም ጠንካራ የመፈፀምና የማስፈፀምና አቅም ያለዉ የለዉጥ
ሀይል ሲኖር ነዉ፡፡ በመሆኑም የተቋማት ግንባታን ማሻሻል፣ጠንካራ የማስፈፀምና
የመፈፀም አቅም ያለዉ የለዉጥ ሀይል በመገንባት ቀልጣፋና ፍትሀዊ የአገልግሎት
አሰጣጥ ስርአትን ማስፈን ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል፡፡
5.1.2 ስራ አጥነትንና ስር የሰደደ ድህነት አሁንም የከተማችን ቁልፍ ችግሮች
እንደሆኑ ከግምገማችን ለመረዳት ተሞክሯል፡፡ በመሆኑም የከተማችን ነዋሪዎች
የራሳቸዉ የስራ ባለቤት እንዲሆኑና ገቢ እንዲኖራቸዉ እና የእድገት ምሰሶ የሆኑ

10 2013 -2022 / Page


107
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ኢንተርፕራይዞችና አካባቢዎችን መርጦ በማልማት ድህነትና ስራ አጥነትን መቀነስ


በቀጣይ ትኩረት የሚሰጠዉ ተግባር ይሆናል፡፡

5.1.3 የከተማዋ m ልክዐ ምድራዊ አቀማመጥ ተዳፋታማና ወጣ ገባ ከመሆኑ ተያይዞ


የጎርፍ አደጋና የመሬት መንሸራተት ዋነኛ ተሻጋሪ ችግሮች ሆነዉ ቀጥለዋል፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአቱ ያልዘመነ በመሆኑ በጎርፍ መፋሰሻ
ካናሎችና ቱቦዎች ላይ የሚጣል ቆሻሻ ለጎርፍ አደጋዉ መባባስ የራሱን አሉታዊ
ተፅዕኖ አበርክቷል፡፡

በመሆኑም የከተማዋን የጎርፍ አደጋ እና የመሬት መንሸራተት መቀነስ፣የደረቅ እና


ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአትን በማዘመን ከተማዋን ዉብ፣ፅዱና አረንጓዴ የማድረግ
ስራ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ የሚከናወኑ ተግባራት ይሆናሉ፡፡

5.1.3 በልማት ዘርፎች በኩል ያልተቀናጀ የመሰረተ ልማት ግንባታ በከተማዋ


የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸዉ፡፡ በመሆኑም ህገ ወጥነትን የመከላከልና
የማስወገድ፣የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስርአትን በመዘርጋት የከተማዋን
የመሰረተ ልማት ሽፋን ጥራትና ተደራሽነት ማሳደግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ
ይሆናሉ፡፡

5.1.4 የአረንጓዴ ልማትን ማስፋፋት፣የመዝናኛና የስፖርት ማዘዉተሪያ ቦታዎችን


ማስፋፋት በማስፋፋት የከተማዋን ነዋሪዎች ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ የቀጣይ
ትኩረት መስኮች ይሆናሉ፡፡

5.1.5 በከተማዋ የሚካሄደዉን የንግድ እንቅስቃሴ ፍትሃዊ የዉድድር ስርአትን የተከተለ


እንዲሆን ማድረግ፣ኢንቪስትመንትና ቱሪዝም ማስፋፋት የከተማውን የገቢ ምንጮች
በማስፋት ገቢን ማሳደግ በዋነኝነት በቀጣይ የሚሰሩ የትኩረት አቅጣጫ ይሆናሉ፡፡

10 2013 -2022 / Page


108
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

5.1.6 በከተማዋ በመንግስትና በግል ሴክተሩ በኩል የተከናወኑ በርካታ የማህበራዊ ልማት
ስራዎች ቢኖሩም ከጥራት፣ከፍትሀዊነትና ከተደራሽነት ጋር በተያያዘ በርካታ ችግሮች
አሉባቸዉ ፡፡በመሆኑም የማህበራዊ ልማትን ጥራት፣ ፍትሀዊነትና ተደራሽነት ማሻሻል
የቀጣይ ትኩረት ነጥብ ይሆናል፡፡
5.1.7 ሰላም የህልዉናችን መሰረት ነዉ፡፡ በመሆኑም በከተማችን የህግ የበላይነት
በማሰከበርና ሰላምን በማረጋገጥ በኩል በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ዉጤት ሊመዘገብ
ችሏል፡፡ይህም በመሆኑ ከተማችን የሰላም ተምሳሌት የሚል ስያሜ አግኝታለች፡፡
በመሆኑም የህግ የበላይነትን የማረጋገጥና የከተማዋን ሰላም ማስቀጠል እና በአስተማማኝ
መሰረት ላይ መገንባት የቀጣይ የትኩረት ነጥብ ይሆናል፡፡
5.1.8 በከተማችን እየታየ ያለዉ የነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ
መጥቷል፡፡ በመሆኑም ከከተማችን እድገት ጋር የሚመጣጠን የነዋሪዉን ህዝብ አቅም
ያገናዘበ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ስርአት በመዘርጋት የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር
መፋታት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል፡፡

5.1.9 የግብርናዉን ዘርፍ የአሰራር ስርአት በማዘመንና የከተማ ግብርናን በማጠናከር


ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ይሆናል፡፡

5.2 የእቅዱ ዓላማዎች


የቀጣይ 10 ዓመት (2013-2022) መሪ እቅድ ዓላማዎች በ 2022 ደሴ በኢትዩጵያ ውስጥ
ከሚገኙ ሪጂኦ ፖሊታን ከተሞች ቀዳሚ፣ ተወዳዳሪ የሆነች አስተማማኝ ሰላም፣ ዲሞክራሲና
መልካም አስተዳደር የሰፈነባት፣ ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት፣ ለመኖሪያና ለስራ ምቹ የሆነች፣መካከለኛ
ገቢ ያላት ታላቅ ከተማ ሆና ማየት የሚለዉን ርዕይ ለማሳካት የጀመርነዉን የልማት ጉዞ በላቀ ደረጃ
ለመፈፀም የሚያስችሉ ይሆናሉ፡፡ በዚህም መሰረት የሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች አሉት፡፡

5.2.1 የመንግስት ተቋማት ግንባታን በማዘመን ጠንካራ የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም ያለዉ የለዉጥ
ሀይል በመገንባት ቀልጣፋ፣ፍትሀዊና ዉጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን ማስፈን፤
5.2.2 የጀመርነዉን የልማት ጉዞ እዉን የሚያደርጉ ሁሉን አቀፍ የልማት ስራዎችን በማከናወን
የነዋሪዎችን ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤
5.3 የእቅዱ ዋና ዋና የእድገት ግቦች

10 2013 -2022 / Page


109
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የእቅዱ ዋና ዋና ግቦች እቅዱ ሁለንተናዊ ለዉጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ ለመምራትና ከፍ ብሎ


የተቀመጡ ዋና ዋና አላማዎችን በቀጣይነት ለማሳካት የሚያስችሉና ለሴክተሮች እቅድም በመነሻነት
የሚያገለግሉ ናቸዉ፡፡በዚህም መሰረት ዋና ዋና ግቦቹ እንደሚከተለዉ ተቀምጠዋል
5.3.1 በከተማዋ የሚገኙ የመንግስት ተቋማትን በማዘመን ጠንካራ የማስፈፀምና የመፈፀም የመፈፀም
አቅም ያለዉ የለዉጥ ሀይል በመፍጠር ቀልጣፋ፣ፍትሀዊና ዉጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን
ማስፈን፤
5.3.2 የገቢ ምንጮ በማስፋት ፣የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በማዘመንና ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ የከተማ
ገቢን ማሳደግ፤
5.3.3 የተቀናጀ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስርአትን በመዘርጋት፣ጥራትና ተደራሽነትን በማሻሻል
የከተማዋን የመሰረተ ልማት ሽፋን ማሳደግ፤
5.3.4 የከተማዋ ነዋሪዎች የራሳቸዉ የሆነ ስራና ገቢ ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ ሥራ አጥነትንና
ድህነትን መቀነስ፤
5.3.5 ለአረንጓዴ ልማት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአትን
በማዘመን፣የመዝናኛና የስፖርት ማዘዉተሪያ ቦታዎች ልማት በማስፋፋት የነዋሪዎችን ፍትሀዊ
ተጠቃሚነትን ማሳደግ፤
5.3.6 የመሬት ልማት አስተዳደርን፣የይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ስርአትን ተግባራዊ በማድረግ የዘርፉን
አሰራር ማዘመን፤
5.3.7 የሰላምና የፍትህ ተቋማትን አሰራር በማጠናከር የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ዘላቂና አስተማማኝ
መሰረት ላይ ማድረስ፤
5.3.8 የማህበራዊ ልማት ፍትሀዊነት፣ጥራትና ተደራሽነትን በማሳደግ የነዋሪዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት
ማሳደግ፤
5.3.9 ፍትሀዊ የንግድ ዉድድርና የሸማቾች ጥበቃ ስርአትን በመዘርጋት ኢንቨስትመንትን በማጠናከር
የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ማሳደግ፤
5.3.10 የግብርናዉን ዘርፍ አሰራር በማዘመን የአርሶ አደሩንና የከተማ ግብርናን ምርትና ምርታማነት
ማሳደግና ወንዞችና የውሀ አካላት ጥቅም ላይ ማዋል፡
5.3.11 የኮንስትራክሽን ዘርፉን በማጠናከር የከተማዋን ዉበትና እድገት ሊያንፀባርቁ የሚችሉ
ግንባታዎች እንዲስፋፉ ማድረግና፣
5.3.12 በከተማዋ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በልማታዊ ኮሙኒኬሽን ስራ
በማጀብ የመረጃ ተደራሽነትን ማሳደግ፤
5.3.13 የሴቶችንና የወጣቶችን ብቃት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ፤
5.3.14 የከተማዋን እድገት እና የዝቅተኛ ነዋሪዎችን የገቢ አቅም ያገናዘበ
የቤቶች ልማት ግንባታን በማፋጠን የነዋሪዎችን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት

10 2013 -2022 / Page


110
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ማረጋገጥ፤
5.4 የመሪ እቅድ አላማዎች፤ግቦች እና ተግባራት
5.4.1የለዉጥ ሀይል ግንባታ ዘርፍ ግቦች
 የመንግስት ተቋማትን ዉጤታማነት ማሻሻል

በከተማ አስተዳደሩ በቀጣይ 10 አመታት ዉስጥ ለመፈፀም የታቀዱ ተግባራትን


በዉጤታማነት መፈፀም የሚቻለዉ በየደረጃዉ የሚገኙ ተቋማትን በአሰራር፣
በአደረጃጀት፣ በግብአት፣ የመስሪያ ቦታን በተገቢ ሁኔታ ማደራጀት አሰራሩን ማዘመን
ሲቻል ነዉ፡፡በመሆኑም በየደረጃዉ የሚገኙ ተቋማትን በተፈላጊዉ የሰዉ ሀይል
ማሟላት፣ተቋሞችን ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ፣ ማራኪና አካታች ማድረግ፣ለተቋማቱ
የሚያስፈልገዉን የማስፈፀሚያ ግብአቶችን ማሟላት፣ተቋማቱ የሚመሩበትን
አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎች በአግባቡ ማደራጀት ፣ሁሉም ተቋማት በእቅድ እንዲመሩ
ማድረግ፣የተቋማቱን የመረጃ አያያዝ ስርአት ማዘመን፣የተቋማትን አላማና ግብ በህዝብ
ግንኙነት ስራ መደገፍ፣በየተቋማቱ የአገልጋይነት ስሜት የተላበሰ የለዉጥ ሀይል መፍጠር
ትኩረት ተሰጥቷቸዉ የሚከናወኑ ተግባራት ይሆናሉ፡፡
በየደረጃዉ የሚገኘዉን አመራር የማስፈፀም አቅም ማሳደግ
ለተቋማት ዉጤታማነት በየደረጃዉ የሚገኘዉ አመራር ድርሻ ጉልህ ነዉ፡፡በመሆኑም
የአመራሩን የማስፈጸምና የዉሳኔ ሰጭነት አቅም በማሳደግ በቀጣይ 10 አመታት ዉስጥ
ለማከናወን የታቀዱ ተግባራትን በዉጤታማነት መፈፀም ተገቢ ይሆናል፡፡ በመሆኑም
በየደረጃዉ የሚገኘዉን አመራር የማስፈፀም አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ የአመራር
ኡደት ፣ማነቆዎችን የመለየትና መፍትሄ የማስቀመጥ ፣የስትራቴጅካዊ እቅድ ዝግጀትና
የለዉጥ ስራ አመራር ጥበቦችን አመራሩ በሚገባ እንዲያዉቃቸዉና እንዲተገብራቸዉ
ማድረግ፣የአመራሩን ተቋሙን የመምራትና ዉሳኔ የመስጠት አቅሙን የማሳደግ፣አመራሩን
በአጭርና በረጅም ጊዜ ስልጠና፣በስራ ላይ ግምገማ ማብቃት በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ
የሚከናወኑ ተግባራት ናቸዉ፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ጠንካራ የመፈፀም አቅም ያለዉ የለዉጥ ኃይል መገንባት
በየተቋሙ የሚገኘዉን የልማት ኃይል ግንባታ ባለበት እንዲቀጥል በማድረግ የተቋሙን
የእቅድ ግቦች ለማሳካት በማሳለጫነት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በመሪ እቅዱ ዘመን ችግር
ያለባቸውን የስራ ክፍሎች ፣ የለወጥ ኃይሎች አደረጃጀትን እና የማኔጅመንት ካዉንስል
አደረጃጀቶችን እንደገና በመፈተሸ መልሶ የማደራጀት ስራ ይሰራል፡፡ሁሉም አደረጃጀቶች ችግር ፈች
ውይይትና ግምገማ እንዲያደርጉ ተከታትሎ መደገፍ፣ የእርስ በርስ መማማር፣ልምድ የመለዋወጥ

10 2013 -2022 / Page


111
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

እንዲካሄድ መከታተል፣የዉጤት ተኮር ምዘና ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ፣የተሻለ አፈጻጸም የሚያሳዩ


ኮኮብ ሰራተኞች መለየት፣ ግንባር ቀደሞችን በመለየት በአሰራሩ መሰረት ማበረታቻ መስጠት የለውጥ
ሀይል ግንባታ ስራው ያመጣውን ለውጥ ተከታትሎ በመገምገም የአሰራር አቅጣጫ የማስቀመጥ አሰራር
ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ፈፃሚ ባለሙያዉን በአጭርና በረጅም ጊዜ ስልጠና በስራ ላይ ግምገማ የማብቃት
ስራ ትኩረት ተሰጥቶ የሚከናወን ተግባር ይሆናል፡፡

 የሰዉ ሀይል አስተዳደር ሥርዓትን ማሻሻል


የሰዉ ሀይል አስተዳደር ስርአቱን ማዘመን፣ቀልጣፋ፣ዉጤታማ፣ፍትሀዊና አካታች
ማድረግ የአገልጋይነት ስሜት የተላበሰ ሰዉ ሀይል ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋፅኦ
አለዉ፡፡በመሆኑም በሰዉ ሀይል አስተዳደር ስርአት ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን
በመለየት ክፍተቶቹን የሚሞላ ስልጠና መስጠት ፣ዲሞክራሲያዊና አሳታፊ
የአስተዳደር ስርአትን መዘርጋት፣በየተቋማቱ ያለዉን የስምሪትና ጥቅማጥቅም
ስራዎች (ቅጥር፣ዝዉዉር፣ደረጃ እድገት፣ክፍያ ወዘተ ስርአትን) በተጠናከረ የክትትልና
ድጋፍ ስርአት ተደግፎ በፍትሀዊነት ላይ እንዲመሰረት ማድረግ፣ሴቶች፣አካል
ጉዳተኞችና ልዩ ፍላጎት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በሲቪል ሰርቪሱ ያላቸዉን
ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ፣የሰራተኛዉን የስራ ተነሳሽነት የሚያሳድጉ
(የትራንስፖርት አገልግሎት፣የህፃናት ማቆያ ወዘተ) የአሰራር ስርአቶችን በመዘርጋት
ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡

የግልፅነት፣ተጠያቂነት ፣የአሳታፊነትናመልስ ሰጭነት የአሰራር ስርአትን ማስፈን


በየተቋማቱ የሚሰጠዉን አገልግሎት ግልፅነትን፣ተጠያቂነትን፣አሳታፊነትንና መልስ
ሰጭነትን የተላበሰ እንዲሆን ማድረግ በተቋማቱ የሚነሱትን የመልካም አስተዳደር
ችግሮችን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ በመሆኑም በየተቋማቱ የሚሰጠዉን የአገልግሎት
አሰጣጥ ደረጃ ለተገልጋዮች ግልፅ ማድረግ፣በአገልግሎት አሰጣጥዙሪያየሚስተዋሉ
የብልሹ አሰራሮችንና የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባራት መታገል፣ተቋሙ
ያከናወናቸዉን ተግባራት ለተገልጋዮች ግልፅ ማድረግ፣ከህዝቡ ለሚሰጡ ጥቆማዎችና

10 2013 -2022 / Page


112
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አስተያየቶች ፈጣን ግብረ መልስ መስጠት፣አዋጆችን፣ደንቦችንና መመሪያዎችን


የተቋሙ ዋነኛ የስራ ማስፈፀሚ አድርጎ መተግበር ትኩረት ተሰጥቷቸዉ የሚከናወኑ
ተግባራት ይሆናሉ፡፡
 የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ
ቀልጣፋ፣ፍትሀዊና ዉጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአት እንዲሰፍን
ማድረግ፣የተቋሙን አሰራር ዘመናዊ ማድረግ፣የተገልጋዮችን እርካታ በዳሰሳ ጥናት
በመለየት ፈጣን የማሻሻያ እርምጃ መዉሰድ፣በአጠቃላይ በተቋማቱ በሚሰጥ
አገልግሎት የረካ ተገልጋይ ለመፍጠር በመሪ እቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይወደ 85
%የማሳደግ ስራ ይሰራል፡፡

5.4.2 የአበይት ተግባራት ዘርፍ ግቦች

5.4.2.1 የከተማ ልማት ዘርፍ


 ከተማልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ
 የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ፕሮግራም

ዓላማ 1፡- የከተማ ዕድገትን የሚያፋጥን፣፣ በተሟላ የሕግ ማዕቀፍና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ
የተደገፈ፣ አካታች፣ አሳታፊ እና ዘላቂ ልማትን በሚያቀናጅ አግባብ ውጤታማና ወጪ
ቆጣቢ የከተማ ኘላን ዝግጅትና ትግበራ እንዲኖር በማድረግ ከተማዋ በተሟላ ፕላን
እንድትመራ ማድረግ ነው፡፡

ግብ 1፡- የተመቻቸ የከተማ ፕላን ዝግጅት አፈፃፀም ተግባራት ተጠብቀው ከተማዋ በፕላን
የምትመራበትን አሰራር ማሻሻል፤
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የከተማውን የፕላን ትግበራና አፈጻጸም በሚያስችል 10 ጊዜ የፕላን ኦዲት ይደረጋል ፡፡


 የተሻለ የፕላን ክለሳ በማድረግ የዞኒንግ ለውጥ ጥያቄዎችን 0% እንዲሆን ይሰራል፡፡
14400 ባለይዞታዎች በፕላኑ መሰረት የፕላን ስምምነት ፎርም አገልግሎት በመስጠት
ፕላኑ እንዲጠበቅ ይደረጋል፡፡
 የከተማውን መዋቅራዊ ፕላን ለማሻሻልና ዘመናዊ ለማድረግ 1 ጊዜ የፕላን ክለሳ
የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡

10 2013 -2022 / Page


113
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

40 ብቻቸውን መልማት የማይችሉ ይዞታዎችን (ብሎክ አሬንጅመንት


የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች) በመለየት በብሎክ እንዲለሙ ማድረግ፡፡

 የከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ማሻሻል ፕሮግራም

ዓላማ 2፡- የለማ የከተማ መሬት በቀጣይነት አዘጋጅቶ ለማቅረብ የመሬት ግብይትና
አሰጣጥ ስርዓቱን ተደራሽ፣ ግልጽ፣ ፍትሃዊና ተጠያቂነትን የተከተለ እንዲሆን
በማድረግዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት በከተማችን ሁለንተናዊ ልማትን
ማረጋገጥ

ግብ 1፡- በከተማዋ 100% ግልጽ የአስተዳደር ወሰን እንዲኖር በማድረግ የመሬት ሃብትን
በሚገባ ማስተዳደር፤

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የከተማዋ የአስተዳደር ወሰን እንደገና እንዲካለል በማድረግ የተሟላ መረጃ እንዲደራጅ


ይደረጋል፡፡
በከተማዋ ቋሚ የወሰን ድንበር ምልክቶችን እንዲተክሉ ይደረጋል፡፡
 በከተማዉ የተተከሉ የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦችን በመለየት መረጃቸው ተደራጅቶ
እንዲያዝና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ይደረጋል፡፡
 የጠፉትንና የተነቀሉትን የቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች በመለየት በአዲስ እንዲተኩ
ይደረጋል፡፡

ግብ 2፡- የመሬት ሀብትን በመቁጠር በመሬት መረጃ መመዝገቢያ ቋት በተደራጀ መልኩ


በመመዝገብ ከብክነት እና ከወረራ መታደግ፤

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በከተማዋ የመሬት ሀብት ቆጠራና ምዝገባ ሥርዓት በመዘርጋት በአገልግሎት አይነት 1000
ሄ/ር ከ 3 ኛ ወገን ነፃ የሆኑ ክፍት ቦታዎችን እና 600 ሄ/ር በጊዜያዊነት የተላለፉ ቦታዎችን
በመቁጠርና በመመዝገብ ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ ይረጋል ፡፡

ግብ 3. በአዋጅ 47/67 የተወረሱ የመንግስት ቤቶችን 100 % የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ


እንዲኖራቸው ማድረግ፤

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

10 2013 -2022 / Page


114
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

6188 የተወረሱ የመንግስት ቤቶችና በመንግሰትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ 1555


የዝቅተኛ ኗሪ ቤቶች ጥገና ይደረገላቸዋል፡፡
 በአዋጅ 47/67 የተወረሱ የመንግስት ቤቶችና የቀበሌ ቤቶች 7743 ካርታ የሌላቸው
የመንግስት ቤቶችና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ የዝቅተኛ ኗሪ ቤቶችን በመለየት ካርታ
እንዲሰራላቸው ይደራጋል፡፡
 ያለ አግባብ የመንግስት ቤት የያዙ በህግ ተጠያቂ በማድረግ ፍትሀዊ ክፍፍል እንዲኖር
ይሰራል፡፡
የተወረሱና በህበረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ቤቶች የኪራይ ዋጋ በጥናት የተመሰረተ የማሻሻል
ስራ ይሰራል፡፡

ግብ 4፡- በከተማዋ መሰረተ ልማት በማሟላት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል የመሬት


አቅርቦት በማስፋት ለተጠቃሚ የማስተላለፍ ስራን ማረጋገጥ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል መሰረተ ልማት የተሟላለት 40 ሄ/ር መሬት ለጨረታ እና 60 ሄ/ር
መሬት ለምደባ እንዲዘጋጅ ይደረጋል፡፡
በከተማዋ 40 ሄ/ር መሬት በጨረታ እና 60 ሄ/ር መሬት በምደባ (ለ 80 መኖሪያ ቤት ህብረት ስራ
ማህበራት 30 ሄ/ር እና ከህብረት ስራ ማህበራት ውጭ 10 ሄ/ር እንዲሁም ለቱሪስት መዳረሻ
ከተሞች በልዩ ሁኔታ የሚተላለፍ 20 ሄ/ር) ለተጠቃሚ እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡
በቦታ ደረጃ ምደባ መስፈርት መሰረት በከተማዋ በፕላን ወሰን ክልል ውስጥ የሚገኝ ቦታ ዎች የቦታ
ደረጃ ምደባ እና የቀጠና ዋጋ ዝግጅት ይደረጋል፡፡
በጨረታ እና በምደባ ቦታ ለተለያየ አገልግሎት ተወስደው በውላቸው መሰረት ጥቅም ላይ
ያላዋሉ (ወደ ልማት ያልገቡ) 50 ቦታዎች (10 ሄ/ር) ውላቸውን በማቋረጥ እንዲለሙ
ይደረጋል፡፡

ግብ 5 ፡- በከተማዋ የደቀቁና የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን በመለየት በመልሶ ማልማትና ማደስ


ፕሮግራም የከተማዋን እድገት ማሻሻል፤

በከተማዋ ገጽታ ሊቀይሩ የሚችሉ 10 የደቀቁና የተጎሳቀሉ አካባቢዎችን የመለየት ስራ ይሰራል፡፡


በመልሶ ማልማት ለሚነሱ 5000 የህብረተሰብ ክፍሎች የምትክ ቦታ ዝግጅትና የካሳ ክፍያ በጀት
የማመቻቸት ስራ የሚከናወን ይሆናል ፡፡
በከተማዋ 66 ሄ/ር መሬት በመልሶ ማልማትና 72 ሄ/ር መሬት በከተማ ማደስ እንዲለማ
ይደረጋል፡፡

10 2013 -2022 / Page


115
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የከተማ ካርታ ማምረት፣ ቅየሳና የመሬት መጠቀም መብት ምዝገባ


ፕሮግራም

ዓላማ፡- በከተማዋ የህጋዊ ካዳስተር ስርዓትን በመገንባት የመሬት ሀብትን በዘመናዊ


አሰራር፣ ቴክኖሎጂ፣ በተሟላ ክህሎትና ብቃት በመመዝገብና በማደራጀት የነዋሪዎችን
የንብረት ዋስትና በማረጋገጥ መሬት ነክ ንብረትን በመጨመር የኢኮኖሚዉን ፍጥነትና
ፍትሀዊነት ለመደገፍ የሚያስችል ስርዓት መዘርጋት

ግብ 1፡-የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና ፕሮግራምን ለማስፈፀም አቅም መገንባት

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

በከተማዋ 200000(35% ሴቶች) የከተማ መሬት ባለይዞታዎችን ግንዛቤ በመፍጠር

በይዞታ ማረጋገጥ ሥርዓት ትግበራ ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡

ለ 200000 (ለ 35% ሴቶች) ባለድርሻ አካለት ስለ ከተማ መሬት ይዞታ መብት ምዝገባ

ፕሮግራም ግንዛቤ በመሰፍጠር በትግበራ ሂደት እንዲሳተፉ ይደረጋል፡፡

ለ 400 (ለ 35% ሴቶች) የዘርፉ አመራሮችና ፈፃሚዎች በህጋዊ ካዳስተር የህግ

ማዕቀፎች፣በቅየሳ፣በፎቶ ግራሜትሪ፣በየቅየሳ መቆጣጠሪያ ነጥቦች ማስፋፋት እንዲሁም

በሲስተም አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ይሰጣል፡፡

ግብ 2፡-የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ ስርአትን ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የይዞታ ማህደሮች/ ፋይሎች በቀጠና፣ በሰፈርና በብሎክ ደረጃ በሃርድና በሶፍት በአዲስ መልክ
እንዲደራጁ እና በቁራሽ መሬት ልዩ መለያ/ኮድ መሰረት እንዲተሳሰሩ ይደረጋል፡፡
በከተማችን የአየር ላይ ፎቶው በመነሳት 33,700 ይዞታዎችን ዲጂታይዜሽን ይደረጋል፡፡
ጠቋሚ ካርታ /ኢንዴክስ ካርታ በማዘጋጀት ለ 33,700 ቁራሽ መሬቶች መለያ/ኮድ /UPIN/
በመስጠት ወደ ጅኦ ዳታ ቤዝ እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
የ 40362 ይዞታዎችን ሙሉ በሙሉ የመሬት መረጃን ከወረቀት ነጻ በሆነ
የኤሌክትሮንኪስ አገልግሎት መቀየር፡፡

10 2013 -2022 / Page


116
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 የመሬት ይዞታ ማህደርንና አስተዳደርን በማዘመን የይዞታ ማህደሮች በሶፍት ኮፒና በዳታ
ቤዝ በዘመናዊ መልኩ እንዲደራጁና ስካን በማድረግ ማህደሮች ለአገልግሎት ሲፈለጉ ፈጣን
በሆነ መንገድ በማቅረብ የማህደርን መጥፋት 100 % እንዲቀር ይደረጋል፡፡
 የከተማችን የ 40362 የይዞታ ማህደር መረጃ እና ዝርዝር ሠነዶች በመዝገብ ተለይቶ
እንዲታወቅ ማድረግ፡፡
 በከተማችን የ 40362 ይዞታ ማህደር ወጥነት ባለው ኮድና መለያ እንዲደራጅ ማድረግ፡፡

ግብ 3፡-በከተማችን መሬትን በአግባቡ በመቁጠር ፣ምዝገባናጥበቃ በማድረግ የመሬት


ሀብትን 100% ከብክነትና ከወረራ መከላከል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በከተማችን ውስጥ ከይገባኛልና ከ 3 ኛ ወገን ነፃ የሆነ 500 ሄ/ር መሬት መለየትና በሳይትና
በኘላን በማስደገፍ የምዝገባ ስራ ይከናወናል፡፡

 የተመዘገበዉን 500 ሄክታር መሬት በአገልግሎት አይነት በመለየት መረጃውን ማደራጀትና


ለመሬት ባንክ ገቢ ማድረግ ለተጠቃሚዎች እስኪተላለፍ ድረስ አስፈላጊው ጥበቃ
የሚደረግበት ይሆናል፡፡

 የተቀናጀ የከተሞች መሰረተ ልማት አቅርቦት ፕሮግራም

ዓላማ፡-ደረጃውን የጠበቀና የተቀናጀ መሰረተ ልማት ለመዘርጋትየሚያስችል የፋይናንስ


አቅም በማመቻቸት፣ የመሰረተ ልማትና አገልግሎት አቅራቢ ተቋማትን ትስስር
በማጠናከር እና የቴክኖሎጅና የክህሎት ሽግግርን በማጎልበት ልማትን የሚያፋጥን የህዝብ
ተጠቃሚነትንና ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት በቀጣይነት እና
በተደማሪነት በከተሞች ማስፋፋት

ግብ 1፡- በ 10 አመቱ የማህበራዊና አካባቢ ደህንነትን መሠረተ ያደረገና የጥራት ደረጃውን


የጠበቀ መሰረተ ልማቶችን ሽፋንማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

10 2013 -2022 / Page


117
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የመንገድ ግንባታ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች መለየትና ቅደም ተከተል ተሰጥቶ ቅድመ ዝግጅት ስራ
ይሰራል፡፡
 የተጠረበ ድንጋይ ንጣፍ መንገድ 100 ኪ.ሜ፣ ጠጠር መንገድ 150 ኪ.ሜ፣ የጥርጊያ
መንገድ (መንገድ ከፈታ) 60 ኪ.ሜ፣የአስፋልት መንገድ 50 ኪ.ሜ፣ የጎርፍ ማስወገጃና
መከላከያ ግንብ ግንባታ 90 ኪ.ሜ፣ ከፍተኛና መለስተኛ ድልድይ በቁጥር 20 ስላብ ከልቨርት
60 ኪ/ሜ ይገነባል፡፡ ነባር የመሰረተ ልማቶች በ 10 አመቱ 30 ኪ.ሜ ጌጠኛ መንገድ፣ 40
ኪ.ሜ ጠጠር መንገድ እና 30 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ ጥገና ይከናወናል፡፡
 በከተማችን ውስጥ የመንገድ መብራት መስመር ዝርጋታ፣ እና የውሃመስመር ዝርጋታ
ግንባታ በማሳደግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንዲሻሻል ይደረጋል ፡፡
በ 10 አመቱ 30 ኪሎ ሜትር የመብራትና 100 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር
ዝርጋታየሚያስፈልጋቸውን አካባቢዎች መለየትና ቅደም ተከተል ተሰጥቷቸው እንዲሰራ ይደረጋል፡፡
 የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነትን መሠረተ ያደረገ እና ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ አንድ
የደረቅ ቆሻሻ እና አንድ የፍሳሻ ቆሻሻ እንዲሁም ጊዚያዊ 52 የደረቅ ቆሻሻ እና 52 የፍሳሽ
ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች እንዲዘጋጁ ይደረጋል፡፡
 የማህበራዊና አካባቢ ደህንነትን መሠረተ ያደረጉና የጥራት ደረጃውን የጠበቁ በቁጥር 50
ሸዶች፣ አንድ ቄራ፣ 100 የህዝብ መጸዳጃ፣ አንድ የእሳት አደጋ መከላከያ ጣቢያ፣ ሁለት
የሕዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ፣10 የታክሲ 1 የከባድ መኪና ማቆሚያ፣ 2 የገበያ
ማዕከላት እና 4 የወጣት ማዕከላት እንዲገነቡ ይደረጋል፡፡
 የማህበራዊና አካባቢ ደህንነትን መሠረተ ያደረጉና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ሁሉንም
የከተማዋን አካባቢ ያማከለ የፍሳሽ ስርአት በመዘርጋት የከተማዋን የፍሳሽ ችግር መቀነስ፤

ግብ 2 የከተማዋን ለጎብኝዎች ምቹ ከማድረግ አኳያ የከተማዋን ተፈጥሯዊ መስህቦች


ማእከል ባደረገ መልኩ የከተማዋን ገጽታ መገንባት

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የኬብል ትራንስፖርት 3 ኪሎ ሜትር ግንባታ ስራዎችን በጥራት በመስራት የከተማዋን


ገጽታ መገንባት እና አማራጭ መጓጓዣ ማቅረብ፤
 የከተማዋን ለጎብኝዎች ምቹ ከማድረግ አኳያ 3 ኪሎ ሜትር ደራጃዉን የጠበቀ የተራራ
ላይ ደረጃ በማልማት የቱሪዝም ተደራሽነትን ማሳደግ፤
 የከተማዋን ለጎብኝዎች ምቹ ከማድረግ አኳያ 3 ኪሎ ሜትር በአዝዋ ተራራ በዋሻ ዉስጥ
አቋርጦ የሚሄድ የፍጥነት መንገድ በማልማት ለሚፈለገዉ ጥቅም ማዘጋጀት፤

10 2013 -2022 / Page


118
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የ 3 ኪሎ ሜትር የከተማ ወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችን በጥራት በመስራት የከተማዋን


ገጽታ መገንባት፤

የግንባታ ባለሙያዎች ክህሎት እና ብቃት ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም

ዓላማ፡- ከምዘና ማዕከላት ጋር በቅንጅት በመስራት በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩትንና ወደፊት


የሚሰማሩትን ባለሙያዎች በስልጠና እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በማሳደግ
ብቃታቸው በምዘና እየተረጋገጠ ወደ ዘርፉ እንዲቀላቀሉ በማድረግ የዘርፉን የሰው ሀይል
ማልማት

ግብ 1፡- በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩ 1000 ባለሙያዎች በተሰማሩበት ዘርፉ የተሟላ ዕውቀት
እና ክህሎት ያላቸው መሆኑን በሙያ ብቃት ምዘና በማረጋገጥ ዘርፉን ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 ከሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ኤጀንሲና ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጋር


በቅንጅት በመስራት 60 ተጨማሪ መሪ መዛኞችን እንዲሰለጥኑ ይደረጋል፡፡
በህንጻ ግንባታ ዘርፍ የሚሰማራ የሰው ኃይል ለተመደበበት ቦታ የተሟላ ዕውቀት እና ክህሎት ያለው
መሆኑን ለማረጋገጥ 600 አነስተኛ እና መለስተኛ ባለሙያዎች የቅድመ-ምዘና ምዝገባ
ይከናወናል፡፡
ከሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ኤጀንሲና ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጋር በመተባበር
በህንጻ ዘርፍ የተሰማሩ 600 አነስተኛና መለስተኛ ባለሙያዎች የሙያ ብቃታቸው በምዘና
ይረጋገጣል፡፡
ከሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ኤጀንሲና ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጋር
በመተባበር ምዘናውን ያላለፉ 40 አነስተኛና መለስተኛ ባለሙያዎች ከአሰሪዎቻቸው ጋር
በሚደረግ ስምምነት መሠረት የክህሎት መሟያ የኩባንያ እና ትብብር ሥልጠና እንዲያገኙ
ይደረጋል፡፡

ግብ 2፡- የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ብቃት ማረጋገጫና ምዝገባ ስርዓቱን ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ለ 1200 ግንባታ ባለሙያዎች የሙያ ፍቃድ ምዝገባ ይደረጋል፤


 በከተማዉ ለሚንቀሳቀሱ 600 ስራ ተቋራጮች፣40 አማካሪዎች እና 400 ባለሙያዎች
ብቃት በማረጋገጥ ምዝገባ ይካሄዳል፡፡

10 2013 -2022 / Page


119
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ለ 600 ሥራ ተቋራጮች (አዲስ 290፣እድሳት 300 እና እድገት 10) የሙያ ብቃት

በማረጋገጥ ምዝገባ ይደረጋል፡፡

ለ 50 አማካሪዎች (አዲስ 20፣እድሳት 25 እና እድገት 5 ) የሙያ ብቃት በማረጋገጥ


ምዝገባ ይደረጋል፡፡

 የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ኮንትራት አስተዳደር ስራዎች

ዓላማ፡- በመንግስት በጀት የሚገነቡ ግንባታዎች በሚያርፉበት አካባቢ የግንባታ ንድፉ


የሚጣጣም መሆኑን እና የአገሪቱን ህንፃ መለያ ደረጃዎች ያሟሉ መሆናቸውን በማረጋገጥ
ጥራታቸውን ማስጠበቅ

ግብ 1፡- በከተማው የሚከናወኑ የመንግስት ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ፣ወጪ እና ጥራት


መፈጸማቸውን ማረጋገጥ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በመንግስት በጀት ለሚሰሩ ህንፃዎች በውለታዎች ዝግጅት፤በተፈጠረ ብልሹ አሰራሮች

ዙሪያ ውሳኔ በመስጠት እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመከታቸው አካላት ጥያቄ ሲቀርብ

100% ተገቢውን ሙያዊ ውሳኔ መስጠት

 የግንባታኘሮጀክቶችን ወቅታዊ የግንባታ ዋጋ በየአመቱ 4 ጊዜ በማጥናት ለሚመለከታቸው

ክፍሎችየጥናት ሰነድ ተደራሽ ማድረግ

 በመንግስት ሴክተር መ/ቤቶች የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ግምገማ እንዲደረግ ሲጠየቅ

በቁጥር 40 ጊዜ ድጋፍ ይደረጋል፡፡

 በመንግስት በጀት ለሚገነቡ ግንባታዎች የጊዜ ማራዘሚያ አገልግሎት ሲጠየቅ ሰነዶችን

በመመርመር 20 ጊዜ ምላሽ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡


 ከሚመለከታቸው ጋር በመቀናጀት የግንባታግብዓት ፍለጋና ምርምር በማካሄድ 26
የግንባታ ግብዓት ቦታዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፡፡

አካባቢ ጥበቃ ጽዳትና ውበት ዘርፍ

10 2013 -2022 / Page


120
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዓላማ 1. ከተማችንን ጽዱ፣ውብና አረንጓዴ ስራዎችንበማስፋፋት ለሰራ እና ኑሮ ምቹ


እንዲትሆን ማስቻል

ግብ 1፡ በከተማችን የሚመነጩ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻዎችን በዘመናዊ መልኩ 90%


ማስወገድ አቅም መፍጠር

የሚከናዎኑ ዋና ዋና ተግባራት

ዘመናዊ 2 የደረቅ እና ፍሳሽ እንዲሁም 52 ጊዜያዊ ቆሻሻ ማስወገጃ ቦታዎች በማዘጋጀት


ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል፣

ደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም የሚያስችሉ ሁለት የተሻሻለ ቴክኖሎጂን ስራ


ላይ ማዋል፤

የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ግንዛቤ በማሳደግ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻን


ከምንጩ መቀነስና የማስወገድ ሰራ እንዲሰሩ ማስቻል፤

የመንገድ ላይ ደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ 400 አገልግሎት እንዲውሉ ይደረጋል፤

አስር ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ መኪኖችን በማቅረብ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆነ
አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል፤

ግብ 2፡ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ማሳደግ

የሚከናዎኑ ዋና ዋና ተግባራት

በአረንጓዴ ልማት 20 አዲስ ደረጃቸውን የጠበቁ መናፈሻዎች እንዲለሙ ይደረጋል፤

አዲስና ነባር የዛፍና ፍራፍሬ ችግኝ ጣቢያዎች ደረጃውን የጠበቀ ንድፍ ተዘጋጅቶ
እንዲለሙ ይከናወናል፣
ፕላን የተመላከቱት አረንጓዴ ቦታዎች ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ እና የመልሶ
ማልማት ስራ በሚሰራበት ወቅት ቢያንስ የይዞታዉ 30 በመቶ በአረንጓዴ እንዲለማ
ይከናወናል፡፡
የተለዩ የውሃ አካላት ዳርቻ ቦታዎች ደረጃውን የጠበቀ ንድፍ ተዘጋጅቶ እንዲጠበቁና

እንዲለሙ ይደረጋል

 አገልግሎት አቅርቦት አስተዳደር ዘርፍ

10 2013 -2022 / Page


121
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አላማ፡- በከተማው አገልግሎት አቅርቦት አስተዳደርን ዘመናዊ በማድረግ የህብረተሰቡን

ተጠቃሚነት ማረጋገጥ

ግብ 1፡-በአገልግሎት አቅርቦት አስተዳደር የሚሰጡ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ጥራትና


ተደራሽነትን ማሻሻል
የሚከናወኑ ተግባራት

 አሁን ያለውን 5 የከተማ አውቶብስ ስምሪት 35 ማድረስ፤


 የነባሩን ቄራ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በማደስ አገልግሎቱን ዘመናዊ የማድረግ እና

በከተማችን ተጨማሪ አዲስ 2 ዘመናዊ ቄራ መገንባት፤


ሁሉም የገበያ ማእከላት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲኖራቸው ይደረጋል
በከተማው ያሉትን 3 የገበያ ማእከላት ደረጃው ን በጠበቀ መልኩ 100% ማሻሻል እና

ተጨማሪ ደረጃውን የጠበቀ 3 የገበያ ማእከል መገንባት፤

 በከተማው ተጨማሪ 3 የእሳት አደጋ መከላከያ እና 2 የቄራ መኪናዎችን ግዥ እንዲፈጸም

ይደረጋል፤

ህንጻ ሹም ዘርፍ
አላማ፡-የሚገነቡ ግንበታዎች ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ምቹናየከተማዉን
ውበት ሊያጎናጽፉ ሀገራዊ ቅርስን የጠበቁ እንዲሆን ማስቻል

ግብ 1፡-በከተማችን ግንባታዎች የከተማዋ መዋቅራዊ ፕላን፣የህንጻ ህጉ እና ደረጃ 100%

ማድረስ

ዋና ዋና ተግባራት

 ፕላን ስምምነት ሲሰጥ ከከተማዉ መዋቅራዊ ፕላን የተቀዳ አካባቢዉን የሚያሳይ


አካባቢያዊ ፕላን እንድያቀርብ ማድረግ፤
 የሚገነቡ ህንጻዎች ደረጃቸውን መሰረት አድርገዉ መሰራታቸዉን መመርመር፤
ግንባታዎች በጸደቀዉ ፕላን መሰረት ጥራታቸዉን ጠብቀዉ 100% እንድሰሩ ይደረጋል፤

 ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ዘርፍ

10 2013 -2022 / Page


122
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዓላማ 1፡-ከተማውን ተወዳዳሪ እና የተሻለ የኢንቨስትመንት መዳረሻ

በማድረግ፣የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን በማስፋፋትና በሙሉ አቅማቸው ምርት


እንዲያመርቱ/ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚኖረውን

ድርሻ በማሳደግ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣

ግብ 1፡-የኢኮኖሚ እድገት ሊያመጡ በሚችሉ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ የሚሰማሩ

ባለሃብቶች ቁጥር በመጨመር የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማሳደግ

ዋና ዋና ተግባራት

 በከተማው ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ዘርፎች 5000 ባለሃብቶች በመለየት የማሰተዋወቅ

ስራ መስራት፤

 የኢንቨስትመንት ፈቃድ ለማውጣት የሚመጡ ባለሀብቶችን 100% ፈቃድ መስጠት፤

 በከተማው አሁን ያለውን 152 አምራች ኢንዱስትሪ በቀጣይ 10 አመት 252 ማድረስ፤

ዓላማ 2 ፡ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል የመሬት እና ሌሎች መሰረተ-ልማት

አቅርቦትን በማሟላት የተሻለ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማደራጀት እንዲስፋፉ እና

ውጤታማ እንዲሆኑ ማስቻል

ግብ 1.ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል መሰረተ ልማት የተሟላለት የመሬት

አቅርቦትን 100% ማሳደግ

ዋና ዋና ተግባራት

 ለሁሉም የኢንዱስትሪ ቀጠናዎች ለተዘጋጀው መሬት 100% ካሳ ተክፍሎ ከሶስተኛ ወገን

የፀዳ እንዲሆን ማድረግ፤

 ለኢንዱስትሪ አገልግሎት እንዲውል ለተዘጋጀ መሬት 100% የመሰረተ

ልማት/መንገድ፣ውሃ፣ቴሌ፣መብራት፣የውሃ ማፋሰሻዎች፣ድልድይ/ እንዲሟላ ማድረግ፤

 የኢንዱስትሪ ሸዶዎችን፣ ክላስተር ማዕከላትን በተዘጋጀላቸው መሬት ላይ በመገንባት

ለተጠቃሚዎች 100% እንዲተላለፍ ይደረጋል፡፡


ትራንስፖርት ዘርፍ

10 2013 -2022 / Page


123
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አላማ 1፡-የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ


ቀልጣፋ፣ፍትሀዊና ደህንነቱ የተጠበቀ የትራንስፖርት ስርአት ማስፋፋት

ግብ 1፡-የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ፍትሃዊና ተደራሽነትን ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የህዝብ ትራንስፖርት መናኻሪያዎችን አሁን ካለበት ከ 2 ወደ 3 ማሳደግ፤


 የጭነት ትራንስፖርት 5 ተርሚናሎችን በመገንባት አገልግሎቱን ለማሳደግ ጥረት
ይደረጋል፡፡
 የታክሲማቆሚያ ግንባታ 10 እንዲገነባ በማድረግ አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ተደራሽ
ይደረጋል፡፡
ግብ 2፡-የተሸከርካሪና የአሽከርካሪ ብቃትን በማሳደግ የትራፊክ አደጋን መቀነስ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በመንገድ ትራፊክ አደጋ ምክንያት የሚደርስውን የሰው ሞት አሁን ካለው ወደ 0%


ማድረስ፤
በከተማችን ላይ የብዙሃን እና ሞተር አልባ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር ማድረግ፤

 በገጠር መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ሽፋንን 100%ማድረስ፣

 በቴክኖሎጅ የተደገፈ የተሸከርካሪ ምዝገባና ምርመራ 100% እንዲተገበር ማድረግ፡፡

 ድንገተኛ የተሸከርካሪ የቴክኒክ ምርመራ ይደረጋል፤

ቤቶች ልማት አስተዳደር ዘርፍ


አላማ 1፡ አማራጭ የቤት m ርሀ ግብሮችን በመተግበር የመኖሪያ ቤት ዕጥረትን በመቅረፍ
የህብረተሰቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ

ግብ 1.ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ የሚያደርጉ አማራጭ የቤት መርሀ ግብሮችን


በመተግበር የመኖሪያ ቤት እጥረት መቅረፍና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማሳደግ

የሚከናወኑዋና ዋና ተግባራት

10 2013 -2022 / Page


124
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 በሪልስቴት 315 ቤቶች ተገንብተው ፤ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፤


 በማህበራት 10000 ቤቶች ይገነባሉ ፤ አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል፤
 በቤቶች ልማት ድርጅት 126 ቤቶች ለመኖሪያና ለንግድ እንዲሰሩ ይደረጋል፤
 በግለሰቦች 3720 የግል የመኖሪያ ቤቶች አማራጮች ተይዘው የሚገነቡ ይሆናል፤
 ለዝቅተኛ ኗሪዎች 5461 ቤቶች በመንግሰትና በህብረተሰብ ተሳትፎ ተገንብተው
ለተጠቃሚዎች የሚተላለፍ ይሆናል፤
50 ብሎክ የጋራ መኖሪያ ቤት/ኮንዶሚኒየም/በመገንባት ለተጠቃሚዎች እንዲተላለፍ
ይደረጋል፡፡

ህብረተሰብ ተሳትፎ ዘርፍ

አላማ ፡-የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በህዝቡና በመንግስት በጋራ በሚከናወኑ የአካባቢ


ልማት ፕሮጄክቶች ላይ የማህበረሰብ አቀፍ የክትትል ስርዓት በመዘርጋት ህብረተሰቡን
የልማት ተሳትፎ ማሳደግ

ግብ 1፡-በከተማው በሚከናወኑና ህብረተሰቡ ሊሳተፍባቸው በሚገቡ የማህበራዊና


ኢኮኖሚያዊ መሰረተ ልማት ስራዎች የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሻሻል

የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት

የሰፈር አደረጃጀቶችን በማጠናከር ህብረተሰቡ በቅንጅት ማሰራት፤ የሴቶችንና


የወጣቶችን ተሳትፎ ድርሻ 50% ማድረስ፣
በህብረተሰቡና በመንግስት በጋራ የአካባቢ ልማት ስራዎች በጥሬ ገንዘብ 12,231,630
ብር ከነበረው ተሳትፎ ወደ 134,547,930 ብር ፣ በጉልበት 39,701,280 ብር ከነበረው ወደ
397,012,800 ብር በቁሳቁስ 11,045,150 ብር ከነበረው ወደ 121,496,650 ብርእና
በእውቀት 5,071,785 ብር ከነበረው ወደ 5,071,785 ብር በድምሩ 57,004,695 ብር
ከነበረው ወደ 703,775,230 ብር እንዲያድግ ይደረጋል፡፡

5.4.2.2 የኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ

10 2013 -2022 / Page


125
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 ግብርናና መሬት አስተዳደር ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ፤-የአካባቢ አቅም መሠረት ያደረገ የተቀናጀ የግብርና ልማትን በማካሄድ


ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እና የተሻሻሉ አሠራሮችን በመተግበር ምርትና ምርታማነትን
ማሳደግና የአርሶ አደሩን ገቢ ማሻሻል

የግብርና ኤክስቴንሽን ኮምኒኬሽን ዘርፍ፤

ዓላማ፤- የተሻሻሉ አዳዲስ አሰራሮችን እና ቴክኖሎጅዎችን በማስተዋወቅ፣ በማስረፅ፣ ፍላጎት


በመፍጠርና የባህሪ ለውጥ በማምጣት፤ የአርሶ አደሩን የአመራረት ዘዴ ዘመናዊ በማድረግ
ገቢውን ማሳደግ

ግብ 1.ገበያ-መር ተሳትፏዊ የኤክስቴንሽን አገልግሎትን በማጠናከርና የግብርናውን ዘርፍ ምርትና

ምርታማነት ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የኤክስቴሽን አገልግሎት አደረጃጀቶችንና አሰራሮችን በማሻሻል፤ የተጠቃሚዎችን ቁጥር


ማሳደግ፣ለሁሉም የአርሶ አደር ማሰልጠኛ ማዕከላት የተሟላ የኤክስቴንሽን አገልግሎት
የሚሰጡበት ተግባራት እንድከናወኑ ማድረግ
የግብርናውን ዘርፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ተቋማዊ የመፈፀምአቅምን በየደረጃው ማሳደግ

የዘር ድንች ማቆያ መጋዘን በአርሶ አደር ማሰልጠኛ 5 እና በማህበራት 1 በድምሩ 6


እንዲገነባ ይደረጋል
የምግብ ድንች ማቆያ በአርሶ አደር 10 በአርሶ አደር ማሰልጠኛ 5 እና በማህበራት 1
በድምሩ 16 እንዲገነባ ይደረጋል

የሴቶችንና የወጣቶችን አቅም በማሳደግ በግብርናው ዘርፍ የስራ እድል ፈጠራ ስራን ፈፃሚ አካላትን
በመከታተልበቁጥር 5650 ስራአጥ ፀጋዎችን በመለየት ወደ ተግባር እንድገቡ መስራት

የሰብል ልማት ጥበቃ ዘርፍ


አላማ፤- የአካባቢን ምቹ ሁኔታን መሰረት ያደረገ የተቀናጀ ሰብል ልማትን በማካሄድ ዘመናዊ
እና የተሻሻሉ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ
ግብ 1.የመኸር ሠብል ምርትናምርታማነት ማሳደግ
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፤

10 2013 -2022 / Page


126
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ለየስነምህዳሩ ተስማሚና ምርታማነት የሆኑ ግሽበትን የሚቋቋሙ 75 ከመቶ በምርጥ


ዘር ማቅረብ ፤ማዳበሪያ መጠቀም እና በመስመር ማዘራት
ከ 2011/12 የምርት ዘመን ከዋና ሰብሎች በመኸር 2953.5 ሄ/ር መሬት በማልማት የተገኘውን
58261 ኩ/ል ምርት፣በ 2021/22 ም/ዘ 3241 ሄ/ር መሬት በማልማት ምርቱን ወደ 134894 ኩ/ል
ማድረስ (በ 131.5%ማሳደግ)፤
አማካይ ምርታማነቱንም በ 2011/12 ም/ዘ 19.7 ኩ/ል/ሄ/ር የነበረውን በ 10 አመቱ መጨረሻ
በ 2021/22 ም/ዘ ወደ 41.6 ኩ/ል/ሄ/ር ማድረስ (በ 111%ማሳደግ)፤
የምግብ ሠብል (ጤፍ፣የምግብ ገብስ፣ አጃ ፣ በቆሎ ዘንጋዳ ፣አተር ፣ ምስር እና ጓያ) በ 2011/12
ም/ዘ ከምግብ ሰብሎች በመኸር 1810 ሄ/ር መሬት በማልማት የተገኘውን 37223 ኩ/ል
ምርት፣በ 2021/22 ም/ዘ 2376 ሄ/ር መሬት በማልማት ምርቱን ወደ 103689 ኩ/ል ማድረስ (በ
178.5 %ማሳደግ)
ኢንዱስትሪ ሰብሎች በ 2011/12 የምርት ዘመን ከዋና ዋና አንዱስትሪ ሰብሎች በመኸር 566.5
ሄ/ር መሬት በማልማት የተገኘውን 13333 ኩ/ል ምርት፣በ 2021/22 ም/ዘ 519 ሄ/ር መሬት
በማልማት ምርቱን ወደ 22840 ኩ/ል ማድረስ (በ 71.3%ማሳደግ)

አማካይ ምርታማነቱንም 2011/12 ም/ዘ 23.5 ኩ/ል/ሄ/ር የነበረውን በ 10 አመቱ መጨረሻ


በ 2021/22 ም/ዘ ወደ 44 ኩ/ል/ሄ/ር ማድረስ (በ 87%ማሳደግ)፤
የኤክስፖርት ሰብሎች በ 2011/12 የምርት ዘመን ከዋና ዋና የኤክስፖርት ሰብሎች በመኸር 577
ሄ/ር መሬት በማልማት የተገኘውን 7725 ኩ/ል ምርት፣በ 2021/22 ም/ዘ 346 ሄ/ር መሬት
በማልማት ምርቱን ወደ 8365 ኩ/ል ማድረስ (በ 8.3 %ማሳደግ)
አማካይ ምርታማነቱንም በ 2011/12 ም/ዘ 13.4 ኩ/ል/ሄ/ር የነበረውን በ 10 አመቱ መጨረሻ
በ 2021/22 ም/ዘ ወደ 24.2 ኩ/ል/ሄ/ር ማድረስ ( 80.6%)፤
 በዋና ዋና ጥሬ ዕቃ ምርት ሰብሎችን በኩታ ገጠም በመዝራት እና ፓኬጁን ተግባራዊ
በማድረግ(ጤፍ፣ ስንዴ ፣ ቦቆሎ እና የቢራ ገብስ)2011/12 የምርት ዘመን ከዋና ዋና ጥሬ ዕቃ
ምርት ሰብሎች በበኩታ ገጠም አሰራር 17 ሄ/ር መሬት በማልማት የተገኘውን 476 ኩ/ል
ምርት፣በ 2021/22 ም/ዘ 180 ሄ/ር መሬት በማልማት ምርቱን ወደ 8440 ኩ/ል ማድረስ (በ 8.3
%ማሳደግ)
አማካይ ጥሬ ዕቃ ምርት ሰብሎችን ምርታማነቱንም በ 2011/12 ም/ዘ 28 ኩ/ል/ሄ/ር የነበረውን
በ 10 አመቱ መጨረሻ በ 2021/22 ም/ዘ ወደ 46.9 ኩ/ል/ሄ/ር ማድረስ (በ 80.6%ማሳደግ)፤

10 2013 -2022 / Page


127
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 በከተማው በተመረጡ ጥሬ ዕቃ ምርት ሰብሎች ኩታ ገጠም የሆኑና ተመሳሳይ ሰብሎችን

የሚያመርቱ ቀበሌዎችን b ጉድኝት በማደራጀት የተመረጡ ሰብሎችን በጥራትና በመጠን

በማምረት ለሃገርውስጥ አግሮ ኢንዱስትሪዎች ገበያ ጋር የማስተሳሰር ስራ ይሰራል፡

 ጥሬ ዕቃ ምርት የሚሳተፉ አርሶ አደሮች የተሟላ ፓኬጅ ለመፈጸም ማዳበሪያና ምርጥ

ዘር፤በመስመር መዝራትና የዘር መጠንና የተሸሻሉ አሰራሮችን ይጠቀሳሉ፡፡

ግብ 2.የበልግ ሰብል ምርት እና ምርታማነትን ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግራት

2011/12 የምርት ዘመን በበልግ 2995 ሄ/ር መሬት በማልማት የተገኘውን 52668 ኩ/ል ምርት፣
በ 2022 ም/ዘ 2074 ሄ/ር መሬት በማልማት ምርቱን ወደ 58072 ኩ/ል ማድረስ (በ 10.3%
ማሳደግ)
አማካይ ምርታማነቱንም በ 2011/12 ም/ዘ 17.6 ኩ/ል/ሄ/ር የነበረውን በ 10 አመቱ መጨረሻ
በ 2021/22 ም/ዘ ወደ 28 ኩ/ል/ሄ/ር ማድረስ (በ 59%ማሳደግ)፤
 በዋና ዋና ጥሬ ዕቃ ምርት ሰብሎችን በኩታገጠም በመዝራት እና ፓኬጁን ተግባራዊ
በማድረግ ምርታማነትን ማሻሻል
(ጤፍ፣ ስንዴ ፣ ቦቆሎ እና የቢራ ገብስ) ከዋና ዋና ጥሬ ዕቃ ምርት ሰብሎች በበኩታ ገጠም
አሰራር 46.9 ኩ/ል/ሄ/ር (በ 80.6%ማሳደግ)፤

የአፈር ለምነትን በማሻሻል ምርትና ምርታማነትን በላቀ ደረጃ ማሳደግ የኮምፖስት


ዝግጅትና አጠቃቀም በ 231 ሄ/ር ጥቅም ላይ የዋለውን አንድ አባወራ/እማወራ 20 ሜ/ኩብ
ኮምፖስት እንደሚያዘጋጅ ታሳቢ በማድረግ 70000 ሜ/ኩብ ማድረስ እቅድ ተይዟል፤
 በአማካይ 875 ሄ/ር መሬት በማልማት የበልግ የጥራጥሬ ሰብል ምርታማነትን ማሳደግ፤

ግብ 3. የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ


የሚከናውኑ ዋና ዋና ተግባራት

10 2013 -2022 / Page


128
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የአትክልትና ፍራፍሬ ምርትና ምርታማነት አሁን ካለበት 69650 ኩ/ል በ 2022 ወደ


6881731 ኩ/ል ማድረስ፤
የአትክልትና ፍራፍሬ ምርታማነትን በ 2012 ከነበረበት 157.4 ኩ/ል በሄ/ር በ 2022 ወደ 330.5
ኩ/ልበሄ/ር ምርታማነትን በማሳደግ፤

አጠቃላይ አመታዊ ምርቱን ከነበረበት 35955 ኩ/ል በ 2022 ወደ 166802 ኩ/ል ማድረስ፤

የደጋ ፍራፍሬ ተክል ሽፋንና ምርታማነትን በነባር የለማውን የደጋ ፍራፍሬ (15 ሄ/ር )
የድጋፍ እና ክትትል አግባባችንን ውጤታማ በሆነ መልኩ በመተግበር ምርታማነትን ከ 57.8
ኩ/ል\ሄ/ርወደ 65 ኩ/ል\ሄ/ር በማሳደግ ፤ 1800 ኩ/ል/ሄ/ር ምርት በማምረት አርሶ አደሮችን
ተጠቃሚ ማድረግ፤
የደጋ ፍራፍሬ ልማት በሚካሄድባቸው ቀበሌዎች ችግኝ በማዘጋጀት 7800 ችግኝ በ 8 ሄ/ር
ላይ ተከላ በማካሄድ (225 ሴት) አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ማድረግ፤

የአፕል ጉድኝት ልማት በ 2012 ለአፕል ጉድኝት ልማት በተመረጡ በ 3 ቀበሌዎች 7800

በነባር ችግኝ ጣቢያ ላይ የደጋ ፍራፍሬ ችግኝ በማዘጋጀት ለተካለ 95% (7410 የተከተበ

አፕል በ 7.6 ሄ/ር ተከላ በማካሄድ (175 ሴቶች) አርሶ አደሮች በአማካኝ 20 ችግኝ ለአንድ
ሰው ተጠቃሚ ማድረግ፤

10 2013 -2022 / Page


129
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

110 ሄ/ርመሬት አትክልትና ፍራፍሬ እና ሌሎች ሰብሎች ጉድኝት ልማት ማስፋፋትና


ገበያ ትስስርን በስፋት በመስራት አ/አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ
በነባር የለማውን የደጋ ፍረፍሬ (15 ሄ/ር ) የድጋፍ እና ክትትል አግባባችንን ውጤታማ
በሆነ መልኩ በመተግበር ምርታማነትን ከ 57.8 ኩ/ል\ሄ/ርወደ 65 ኩ/ል\ሄ/ር በማሳደግ እና
1800 ኩ/ል/ሄ/ር ምርት በማምረት- አ/አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ፡
የደጋ ፍራፍሬ ልማት በሚካሄድባቸው ቀበሌዎች ችግኝ በማዘጋጀት 7800 ችግኝ በ 8 ሄ/ር
ላይ ተከላ በማካሄድ (225 ሴት) አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ማድረግ፤
የአፕል ጉድኝት ልማት በ 2013 ዓም ለአፕል ጉድኝት ልማት በተመረጡ በ 3 ቀበሌዎች

7800 በነባር ችግኝ ጣቢያ ላይ የደጋ ፍራፍሬ ችግኝ በማዘጋጀት ለተካለ 95% (7410

የተከተበ አፕል በ 7.6 ሄ/ር ተከላ በማካሄድ (175 ሴቶች) አርሶ አደሮች በአማካኝ 20 ችግኝ
ለአንድ ሰው ተጠቃሚ ማድረግ

ግብ 4.የዘር ብዜትና የግብርና ግብዓት አቅርቦት ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የግብርና ምርት ማሳደጊያ ግብዓቶች አጠቃቀምን 2011/12 ምርት ዘመን በመኽር፣ በበልግና
በመስኖ ሰብል ልማት ጥቅም ላይ የዋለውን 9052 ኩ/ል የአፈር ማዳበሪያ በ 2021/22
ምርት ዘመን ወደ 28.725 ኩ/ል ማድረስ፤

በ 2011/12 ምርት ዘመን በመኽርና በበልግ ጥቅም ላይ የዋለውን 2790 ኩ/ል የአፈር
ማዳበሪያ በ 2021/22 ምርት ዘመን ወደ 25650 ኩ/ል ማሳደግ፤
 በመስኖ ልማት ዘርፍ የአፈር ማዳበሪያን በ 2022 ዓ.ም 3075 ኩ/ል በማድረስ
ምርታማነትን ማሳዳግ፣
 በመኸር ሰብል ልማት በአንድ ሄ/ር መሬት ላይ ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን 0.55
ኩ/ል የአፈር ማዳበሪያ በመጨረሻው የዕቅድ ዘመን ወደ 2 ኩ/ል (263 %) ማድረስ፣
 የአሲዳማ አፈርን ምርታማነት ለማሳደግ በ 2011/12 መኸር ወቅት ከነበረበት
22,351 ኩ/ል በ 2021/22 ምርት ዘመን ወደ 1000 ኩ/ል ማድረስ፣

10 2013 -2022 / Page


130
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 የተለያዩ ምርጥ ዘር በአይነቶችን ለምርት ዘመኑ 2011/12 ምርት ዘመን በመኽር፣


በበልግና በመስኖ ሰብል ልማት ጥቅም ላይ የዋለውን 655 ኩ/ል ምርጥ ዘር
በ 2021/22 ምርት ዘመን ወደ 5314 ኩ/ልበማቅርብ በማሳደግ ፡
ከ 2011/12 ምርት ዘመን በመኽርና በበልግ ጥቅም ላይ የዋለውን 3007 ኩ/ልምርጥ
ዘር በ 2021/22 ምርት ዘመን ወደ 4105 ኩ/ልማሳደግ፤
 በመስኖ ልማት ዘርፍ ምርጥ ዘር በ 2022 ዓ.ም 1209 ኩ/ል በማድረስ፣
በ 2021/2022 ምርትዘመንየኬሚካልአጠቃቀማችንወደ 126,773 ሊትርማድረስ፣
 የተሻሻሉ አነስተኛ የእርሻ መሳሪያዎችን ለአ/አደሩ በማቅረብ የአፈር ምርታማነትን
ማሳደግ

አነስተኛ መስኖ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ዘርፍ

ዓላማ 1፤- የመስኖ መሰረተ ልማትን በላቀ ደረጃ በማስፋፋት እና አዳዲስ የመስኖ

ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ የከተማዉን አርሶ አደሮች በመስኖ አውታር ተደራሽ በማድረግ

ከድርቅ ተጋላጭነት እና ከዝናብ ጥገኝነት የተላቀቀና ቀጣይነት ያለው የህብረተሰብ

ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ

ግብ 1. የመስኖ መሰረተ ልማትን በላቀ ደረጃ በማስፋፋት አዳዲስ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን

በማላመድ የመስኖ አውታር ሽፋንን ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

አዲስ 314 ዘመናዊ የመስኖ መሰረተ ልማት አውታሮችን በመገንባት ቁጥሩን ወደ 338

የመስኖ መሰረተ ልማት አውታሮች ማድረስ፤


 በዘመናዊ ነባርና አዲስ የመሰኖ አውታሮች፣በጥልቅ ጉድጓዶች፣በማህበረሰብ ኩሬዎችና
አቅማቸው ከፍ ባለ የነዳጅ እና በፀሀይ ሀይል ለሚሰሩ የውሀ መሳቢያዎች ለነባር 628 ሄክታር
መሬት እና ለአዲስ 159.5 ሄክታር በጠቅላላው ለ 787.5 ሄ/ር የመስኖ መሬት ውሀ ማቅረብ
በሁሉም የመስኖ አማራጮች በከተማው የሚኖሩ አርሶአደሮች ቢያንስ አንድ የውሀ አማራጭ
እንዲኖራቸው በማድረግ ቁጥሩን 2967 ወደ 3495 በማሳደግ የመስኖ ውሀ ተደራሽ ማድረግ፤

የተፈጥሮ ሃብት ልማትናጥበቃ ዘርፍ

10 2013 -2022 / Page


131
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አላማ 1- የተቀናጀ ተፋሰስ ልማትና ጥበቃ በመተግበር፤ የተፈጥሮ ሃብት መራቆትን


በመቀነስ፣ ምርትና ምርታማነትን በማሻሻል ህብረተሰቡን በዘላቂነት ተጠቃሚነቱን
ማረጋገጥ

ግብ 1.የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሽፋን ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
 እስካሁን የተ/ሀብት ልማትና ጥበቃ ከተሰራባቸዉ 19 ንኡስ ተፋሰሶች/12 ማህበረሰብ
ተፋሰሶች/የተቀናጀ የክለሳ እቅድ በማዘጋጀት በድምሩ 19 ንኡስ ተፋሰሶች/12 ማህበረሰብ
ተፋሰሶች/ ላይ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራ መስራት፤
 የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የሚጠይቀው 4451.43 ሄ/ር መሬት በአዲስ የአፈርና ውሀ ጥበቃ

እና ማገገምና ማልማት ስራዎች በመስራት 100 % ማድረስ፤


 የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ስራ ሊሰራበት የሚገባው ማሳ ላይ 2627.86 ሄ/ር በአዲስ
የማሳ ላይ እርከን ይሰራል፣251.1 ሄ/ር ተራራማ መሬት በአዲስ በጋራ ላይ እርከን ስራ
ይሸፈናል፣508.83 ሄ/ር መሬት በጠረጴዛማ እርከን ይሸፈናል፤
 ቦረቦር የመከላከልና የማዳን ስራ አሁን የቀረዉን 21.01 ሄ.ር /100%/ ላይ የስነ-አካላዊና
ስነ-ህይወታዊ ስራዎች ይሰራሉ፤
ዝቅተኛ ተዳፋት 12%/ ያላቸዉን መሬቶች በሥነ-ህይወታዊ የአፈር ጥበቃ ዘዴዎች ለምሳሌ ዘርፈ
ብዙ ጠቀሜታ ባላቸዉ ዕፅዋቶች እንደ ሳር ሰርጥ የመሳሰሉትን በመጠቀም 290.83 ሄ.ር መሬት
/ይህም ጠቅላላ ከሚሰራዉ እርከን 15%ቱ/ እንዲሸፈን ይደረጋል፤
 እንዲሁም ተከልሎ የነበረ ግን አሁንም ችግር የሚታይበትን ጨምሮ 751.8 ሄ.ር ከመኖሪያ
ቤት የራቀ ማንኛዉም መሬት እና የተራቆተ ተራራማ መሬት ከንክኪ ነፃ ሁኖ እንዲያገግም
የመከለልና የማልማት ስራ ይሰራል፤
 ሌላው በትኩረት የሚሰራው በነባር የተሰሩ ስራዎች ላይ የደረጃ ማሳደግና ጥገና
የሚያስፈልገው 525.57 ሄ/ር መሬት እንዲሸፈን ይደረጋል፡፡

ግብ 2. የጥምር ደን እርሻ ፓኬጆችን ተግባራዊ በማድረግ አጠቃላይ የደን ሽፋን ከ 19.3% ወደ


31% ማሳደግ
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፤

በ 423.3 ሄ/ርመሬት ላይ የጥምር ደን እርሻ ፓኬጆችን ተግባራዊ ማድረግ

10 2013 -2022 / Page


132
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 የረድፍ እርሻ 288.03 ሄ/ር፤በማሳ ደንበርና በመንገድ ዳር ዛፍ ተከላ ማካሄድ 31.8


ሄ/ር፤የነፋስ መከላከያ ዛፍ ተከላ 10.5 ሄ/ር፤በግጦሽ መሬት የዛፍና ቁጥቋጦ ተከላ 5 ሄ/ር፤ጓሮ
ዙሪያ ተከላ 43.9 ሄ/ር እንዲሸፈን ይደረጋል
የከተማ አስተዳደሩን የደን ሽፋን አሁን ካለዉ 19.3 % በየአመቱ በ 1.2% በማሳደግ 31% ማድረስ፣
9.2 ሄ.ር በመንግስት ደን፣1187.5 ሄ.ር የወል፣606.5 ሄ.ርበአ/አደር፣78 ሄ/ር በተቋማት፤በከተማ
82 ሄ/ር እና 56 ሄ.ር በባለሀብቶች በድምሩ 2034 ሄ/ር የሚለማ ይሆናል፡፡
ችግኝ ጣቢያዎችን በማስፋፋት እና ያሉትን በማጠናከር 20.54 ሚሊዮን
ደረጃቸውን የጠበቁ ችግኞች ማዘጋጀትና በመትከል የችግኝ የመፅደቅ መጠኑን አሁን ካለዉ አማካኝ
83% ወደ 90% የማሳደግ ስራ ይሰራል፣
በከተማ አስተዳደሩየሚገኘውን አርሶ አደር የመሬት ይዞታ ካላቸው ውስጥ በደን ልማት በማሳተፍ
አንድ አ/አደር በ 10 ዓመት መጨረሻ 0.125 ሄ.ር የደን መሬት እንዲኖረዉ ለማድረግ ይሰራል፣

 መኖ ልማት እና የእንስሳት እርባታ፤ተዋፅኦ እና ጤና ዘርፍ

ዓላማ 1፤የቴክኖሎጂና የተሻሻለ አሰራርን በብቃት እና በጥራት በመፈጸም የእንሰሳት


ምርትናምርታማነት በገበያ እንዲመራ በማድረግ ለድህነት ቅናሳ ፣ለስራ እድል ፈጠራ፣
እያደገ ለመጣው ኢንዱስትሪ ጥሬ እቃ ማቅረብና በአጠቃላይ አገራዊ
ኢኮኖሚያዊ እድገት የላቀ ድርሻ ማበርከት፤

ግብ 1.እንስሳት መኖ አቅርቦትማሳደግና አጠቃቀምማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በእንስሳቱ የሚፈለገውን ድርቆ መኖ 100% በማሟላት እና 10% ተጨማሪ በጥራት

በየአመቱ በማምረት በ 2022 ተደረሰበትን 70120 ቶን ድርቆ መኖ ከግጦሽ መሬት 26000

ቶን፣ ከተሻሻሉ መኖ ልማት 570 ቶን፣ ከሰብል ተረፈ ምርት 41500 ፣

10 2013 -2022 / Page


133
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 ከአግሮ ኢንዱስትሪ ተረፈ ምርት 2050 ድርቆ መኖ በ 2022 መጨረሻ የሚገኘውን ድርቆ
መኖ 80500 ቶን ማከናወን ፣ ይህን ማሟላት የሚቻለዉ

አሁንእየተመረተያለውንድርቆመኖ ከግጦሽ መሬት 30800 ቶን፣ ከተሻሻሉ መኖ ልማት 645


ቶን፣ ከሰብል ተረፈ ምርት 46805 ቶን፣

 የሰብልን ተረፈ ምርት የንጥረ ነገር ይዘት አሻሽሎ የመጠቀም ስራን በማስፋት በ 2012

መጨረሻ ከተደረሰበት 663 ቶን አፈጻጸምወደ 750 ሽህ ቶንመፈጸም

 የበልግ ዝናብን እና የመስኖ ውሃን ተጠቅሞ በመኖ ልማት የሚለማውን ማሳ ስፋት አሁን
ካለበት 12500 ሄ/ር ወደ 16500 ሄ/ር መተግበር፣
የእንስሳት መኖ የተሸሻለ ዝርያ ያላቸውን መኖ ችግኝ እና ቁርጥራጭ አሁን ካለበት
53000 ችግኝ በቀጣይ 10 አመታት ወደ በ 2022 መጨረሻ 175000 ችግኝ ለተከላ
ማዘጋጀት፣

ግብ 2.የእንስሳት ተዋፅኦ ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ፡

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ከዳልጋ ከብት እና ከፍየል የሚመረተውን የወተት ምርት በ 2012 በጀት ዓመት


ከተደረሰበት 10917 ቶን በ 2022 በጀት ዓመት ዓመታዊ የማምረት ዓቅም ወደ 17816
ቶን ለማድረስ መስራት ፤
የእንቁላል ምርትና ምርታማነትን ማሳደግበ 2012 መጨረሻ ከተደረሰበት 8.3

ሚሊዮን በ 2022 መጨረሻ 14 ሚሊዮን እንቁላል እና በ 2012 ከተደረሰበት ከ 1170 ቶን

በ 2022 መጨረሻ 1984 ቶን የዶሮ ሥጋ በማድረስ የአምራቹን ተጠቃሚነት ማረጋጋጥ፣

2012 በጀት ዓመት መጨረሻ ከተደረሰበት 20.5 ቶን የማር ምርት በ 2022 በጀት ዓመት

መጨረሻ 36.64 ቶን መተግበር፣

10 2013 -2022 / Page


134
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የቆዳና ሌጦ ምርትንበ 2012 ያለውን 191390 በ 2022 በጀት ዓመት መጨረሻ 326577
ማከናወን፤

ግብ 3. እንስሳት ዝርያ ማሻሻል እና ጥበቃ ማጠናከር

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

በ 2012 ከተደረሰበት የተሻሻሉ የዳልጋ ከብቶች ቁጥር 11590 በ 136% በማሳደግ በ 2022

መጨረሻ በከተማ አስተደዳደሩ የተሸሻሉ የዳልጋ ከብትዝርያ ቁጥሩን 27420 ለማድረስ


በ 10 ዓመቱ በድምሩ 43600 ላሞችንና ጊደሮችን ማዳቀል፤

በ 10 አመት ውስጥ 15830 ጥጆች በማስወለድየአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤

የአካባቢና የተሻሻሉአውራ በመጠቀም የበግ ዝርያ 38150 መሻሻል፣

የእንስሳት በሽታዎችን በመከላከል በኩል ድንበር ዘለልና መደበኛ የክትባቶች መጠን

በየአመቱ በ 5 በመቶ በማሳደግ በ 2022 ዓ.ም 689040 መስጠት፤

በእንስሳት ሕክምና የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት ክትባት ከመስጠት አኳያ አሁን ካለበት

26400 ወደ 58000 እና 630 ወደ 4350 በቅደም ተከተል በማሳደግ በህብረተሱ

የሚደርሰዉን ጉዳት ለመቀነስ መተግበር፤

 እንስሳት ጤና አገልግሎት ሽፋን በ 2012 ከነበረበት ከ 50% በ 2022 ዓ.ም ወደ 100%


በማሳደግ በመጠንና በጥራት የተሟላ አገልግሎት መሰጠት፤

 ኢነርጂ ዘርፍ
 ዘመናዊ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃዎችን የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚነት ሽፋን
ማሻሻል

የሚከናወኑ ተግባራት

ለ 260,700 ህዝብ ጠንካራ የማስተዋወቅ ስራ በመስራት በገጠር መንደሮችና ከተሞች ከፀሐይ


ብርሀን የኤሌክትሪክ ሃይል ለመጠቀም 10,000 የፀሀይ ሀይል መብራቶችን ማሰራጨት
ዘመናዊ የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን የከተማው ህብረተሰብ በሰፊውእንዲጠቀም
ለማድረግ 9,36 የኤሌክትሪክ ምጣድ እና 18,731 ኤሌክትሪክ ምድጃ ማሰራጫ

10 2013 -2022 / Page


135
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 የገጠር መሬት አስተዳደር ዘርፍ

አላማ፤-ዘመናዊ የገጠርየመሬት አስተዳደር ስርዓትን በመገንባት ከመሬት ጋር በተያያ ዙ


የሚነሱየመልካም አስተዳደር ችግሮን በመፍታትና ፍትሃዊ የመሬት ተጠቃሚነትን በማ
ረጋገጥ የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት ማሻሻል

ግብ 1.በገጠሩዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ስርዓትን በመገንባት


ፍትሃዊ የመሬት ተጠቃሚነትን ማሻሻል

 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡

 የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ ሰርትፍኬት መስጠት አሁን ካለበት 0 ማሳ ወደ ይዞታና


83200 ማሳ ማድረስ፤
የ 2 ኛ ደረጃ የይዞታ ማረገገጫ ደብተርን የብድር ዋስትና በማድረግ 1560 ባለይዞታዎች
ብር 78000000 የብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል፣
 በገጠር መሬት ያለውን ህገወጥ ተጠቃሚነትን በመከላከል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን
በ 8840 (85%) መቀነስ፤
 በገጠር ህገወጥነትን ለመከላከል ተወሮና ተገፍቶ የተገኘን የወል መሬት 8 ሄ/ር (85%)
ማስመለስ፣

ወደ መሬት ባንክ ከሚገባ መሬት ለ 4810 አዲስ መሬት ጠያቂዎችና ለስራ አጥ ወጣቶች
በቡድንም ይሁን በተናጠል በቋነትና በጊዜአዊነት 484 ሄ/ር መሬት ማቅረብ፣

 የመሬት አጠቃቀም ዘርፍ


አላማ፡-በህዝብ ተሳትፎ የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅዶችን በመፈፀም
የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጃጀጥ፤

ግብ 1.በገጠር ቀበሌ የመሬት አጠቃቀም እቅድን መሰረት ያደረገ የህብረሰተቡ የመሬት


ባለይዞታነት ማረጋገጥ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

ለመጭው ትውልድ ያልተጎሳቆ መሬት ማውረስ


በ 8 ቀበሌዎች ለ 10232 ባለይዞታዎች፣ 30696 ማሳዎች የመሬት አጠቃቀም በማጥናት
ዕቅድ ይዘጋጃል፣

10 2013 -2022 / Page


136
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ተጠንቶ የታቀደውን የመሬት አጠቃቀም ዕቅድ በ 8 ቀበሌዎች ለ 10232 ባለይዞታዎች፣


ለ 30696 ማሳዎች ርክክብ ይደረጋል፡፡
በ 8 ቀበሌዎች ለ 10232 ባለይዞታዎችና ለ 30696 ማሳዎች ማሳዎች በርክክቡ መሰረት
ቁጥጥር ይደረጋል በምክረ ሀሳቡ መሰረት ወደ ተግባር እንዲገቡ ይደረጋል፡፡
ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ክ/ከተሞች የገጠር መሬት ባለይዞታዎችን
ካርታና ፕላን ሲሰጡ ህገወጥ ገንቢዎች ህጋዊ ሰነድ እንዳያገኙ የተገነባዉ ግንባታ ማጨሻ ወይም
የመኖሪያ አካባቢ መሆኑን በማረጋገጥ የተጣራ መረጃ መስጠት፣

 የሀብት ዋጋ ትመና መልሶ ማቋቋምዘርፍ

አላማ 1.ለህዝብ ጥቅም ሲባል በልማት ምክንያት ለሚለቁ የመሬት ባለይዞታዎች ፍትሀ
ዊ መሬት ካሳ ግመታ በማካሄድ እንዲከፈሉና ተፈናቃዮች በዘላቂነት
መልሰው እንዲቋቋሙ ማስቻል

ግብ 1.በልማት ምክንያት ለሚፈናቀሉ ባለይዞታዎች ካሳ መክፈል እና መልሶ ማቋቋም

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 በዘላቂነትመልሰው እንዲቋቋሙ፤ለ 324 የልማት ተነሽዎች ምትክ ቦታ ማዘጋጀት እና


መስጠት
 የይዞታቸዉ መሬት ለሚወሰደባቸዉ ለ 324 ባለይዞታዎች የመሬቱ የቦታ አቀማመጥ፤
ስፋት እና የማምረት ደረጃ ተመጣጣኝ ከሆነ 162 ሄ/ር ምትክ የእርሻ መሬት ይሰጣቸዋል፤
 ከዚህም በተጨማሪ በልማት ምክንያት ለተፈናቀሉ 160 ባለይዞታዎች 8 ሄ/ር መሬት
ለመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ እንዲቀርብላቸው ድጋፍ ይደረጋል፤
ለ 320 የልማት ተነሽዎች የደረሰባችን ጉዳት ማሻሻል እንዲችል በመረጡት የስራ ዘርፍ
እንዲሰማሩ ለማድረግ የመስሪያ ቦታ ይጋጅላቸዋል፤
 ለሁሉም የልማት ተነሽዎች ለሚያመርቱት ምርትና ለሚሰጡት አገልግሎት የገበያ ትስስር
ይደረግላቸዋል፤ ከእነዚህ የልማት ተነሽዎች መካከል 648 (20 %) የብድር ትስስር
ይደረግላቸዋል፤

ኅብረትሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ዘርፍ

10 2013 -2022 / Page


137
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዓላማ፤-የኅብረት ሥራ ማህበራትን በማጠናከር የግብይትተሳትፎ ድርሻ በማሳደግ

፤የማህበረሰቡ የቁጠባ እና የኢንቨስትመንት ባህል በመቀየር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ

ችግሩን በመፍታት በራሱ የሚተማመን ማህበራትመፍጠር

ግብ 1፡- የኅብረት ሥራ ማህበራትን በማጠናከር የግብይት ተሳትፎ ድርሻ ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የኅብረት ሥራ ማህበራት ብዛት አሁን ከተደረሰበት 26 በቀጣይ 75 ማድረስ፣


በገቢያ ተወዳዳሪ የሆኑ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማድረግ፤
የኅብረት ሥራ ማህበራትን የአባላት ቁጥር አሁን ካለበት 19306 በቀጣይ 10 ዓመታት
በየዓመቱ በ 5% በማሳደግ የአባላትን ቁጥር ወደ 28956 ማሳደግ፤
የመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራቱን ቅጥር ሠራተኞች ቁጥር አሁን ካለበት 247 ወደ
400 እንዲሁም የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን አሁን ካለበት 13 ወደ 30 ማድረስ፤
መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ዩኒዬኖች በመሠረተ ልማት ረገድ ለጽ/ቤት፣
ለመጋዝኖች እና ለሌሎች የማምረቻ እና መሸጫ የቦታ ይዞታ ማረጋገጫ መስጠት፤

የኅብረት ሥራ ማህበራትን የብቃት ደረጃ ማረጋገጫ የአገልግሎት ሽፋን 100% ማድረግ፣

የኅብረት ሥራ ማህበራትን የቁጥጥር ሽፋን ከ 60.6 በመቶ ወደ 100 % ማሳደግ፣


የመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራትን ቁጥር አሁን ካለበት 33 ወደ
45 ማሳደግ፣
የመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት የአባላትን ቁጥር አሁን ካለበት
3516 ወደ 6612 ማሳደግ ፣
በመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት የሴቶችን የአባልነት ሽፋን
አሁን ካለበት 49.65% ወደ 50% ማሳደግ፣

ግብ 2፡- የአባላትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊተጠቃሚነት ያረጋገጡ ኅብረት ሥራ ማኅበራትን


መፍጠር፣

10 2013 -2022 / Page


138
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

100% መሠረታዊ እና ዩኒዬን ኅብረት ሥራ ማህበራት የሥልጠና ወጪ እንዲጋሩ


ማስቻል፤
የመሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራትን ካፒታል አሁን ካለበት ብር 46,217,500 በየዓመቱ
በ 5% ወደ ብር 69,326,250 ማድረስ እንዲሁም የኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ካፒታል
አሁን ካለበት ብር 9,673,998 በየዓመቱ በ 10% በማሳደግ ወደ ብር 19,347,996 ማድረስ፤
የኅብረት ሥራ ማህበራትን የጉድለት አመላለስ በ 2012 ዓ.ም መጨረሻ ከደረሰበት ከ 45
በመቶ ወደ 100 በመቶ ማሳደግ፤
የመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ካፒታል አሁን ካለበት ብር
9,430,535 ወደ ብር 24,945,000 ማድረስ፤
የመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት መደበኛ ቁጠባ አሁን ካለበት
ብር 63,410,270 ወደ ብር 154,812,250 መፈጸም፣
የመሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ብድር ስርጭት አሁን ካለበት
ብር 66,467,857 ወደ ብር 329,700,000 መተግበር፣

ግብ 3፡- የኅብረት ስራ ማኅበራት የሀገር ውስጥ የግብርና እና ኢንዲስትሪ ምርት ግብይት


ድርሻ ማሳደግ ፤

በምርት አቅራቢ እና ምርት ተቀባይ ተቋማት መካከል ጠንካራ የገበያ ትስስር ጠንካራ እና
ዘላቂነት ያለዉ እንዲሆን ማድረግ፣
በቀጣይ 10 ዓመታት 460,000 ኩ/ል የተለያዩ የግብርና ምርቶችን በመሰብሰብ ለከተማው
ገበያ ማቅረብ፤
የኢንዱስትሪ ምርቶች/ፍጆታ ሸቀጦች አቅርቦት መጠን ከ 1.6 ቢሊዮን ብር ወደ 3.84
ቢሊዮን ብር ማሳደግ፤
ደረጃቸውን የጠበቁ መጋዝኖች ግንባታ ብዛት ከ 10 ወደ 13 ማሳደግ፤ ምርት ማከፋፈያ
ሱቆችን ቁጥር ከ 62 ወደ 100 ማሳደግ፤

10 2013 -2022 / Page


139
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የምግብ ዋስትን የከተማ ሴፍትኔት ዘርፍ

አላማ;- በከተማችን በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙትን የህብረተሰብ ክፍሎች በምግብ


ዋስትና መርሀ ግብር ተሳተፊ እና ተጠቃሚ በማድረግ ለከፋ ድህነት የተጋለጡ ዜጎችን
አኗኗር በዘላቂነት መቀየር

ግብ 1፡- ስለከተማ ምግብ ዋስትና ትክክለኛውን አመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት የያዘ


ህብረተሰብ፣ አመራርና ፈጻሚ እንዲሁም ውጤታማ አደረጃጀትን በመፍጠርና
በማጠናከር የከተማ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የከተማ ምግብ ዋስትና ለማስፈጸም አቅም ግንባታ በባለ ድርሻ አካላት ሚና ላይ ትኩረት ሰጥቶ
መስራት፣
በከተማችን ከድህነት ወለል በታች እየኖሩ ያሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች በልማታዊ ሴፍቲኔት
ፕሮጀክት 21,673 (84%) ተጠቃሚ በማድረግ
አጠቃላይ የከተማ ነዋሪውን ከምግብ ዋስትና መረጋገጥ ሥራ አኳያ ትክክለኛውን
አመለካከት እንዲይዝ በማድረግና በየደረጃው ያሉ አደረጃጀቶችን በመጠቀም
እንዲሳተፍና ለስኬቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ይሠራል፡፡
ተጠቃሚዎች በወጣው መርሃ ግብር መሠረት ግልጽ መመዘኛ አስቀምጦ እንዲመረቁ
ማድረግ፣

ግብ 2. በምግብ ዋስትና መርሀ ግብር የአካባቢ ልማት ተጠቃሚዎች ገቢ በሚያስገኝ ሥራ ላይ


ተሰማርተው የቁጠባና የስራ ባህላቸው ጎለብቶ በዘላቂነት ኑሮአቸውን ይመራሉ፤

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

21,673 ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር የሚያደርጉ ሥራዎችን በመሥራት ከሚያገኙት ወርሃዊ


ክፍያቸው 20% እንዲቆጥቡ ማድረስ፤
የድሃ ድሃ የተጠቃሚ ልየታ በግልጽ መመዘኛና የህብረተሰብ ተሳትፎ በማረጋገጥ
የመረጃ ቋት እንዲኖር ማድረግ ፣

ንግድና ገበያ ልማት ዘርፍ


ምዝገባ ዘርፍ

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዓላማ 1፤- የምዝገባና ፍቃድ የንግድና ግብይት አዲስ የንግድ ፍቃድ እና ምዝገባእንዲሁምእድሳት
አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻልና የዘመኑን ቴክኖሎጅ በመጠቀም የአገልግሎት ተደራሽነትን
ማሳደግ

ግብ-1 ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም በዘርፉያለውን የንግድ ምዝገባ፣ ፈቃድ እና እድሳት


አገልግሎት ማሻሻል፣

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

በ 2012 ዓመት የነበረውን 11194 የነጋዴ ቁጥር በየአመቱ 10 % በማሳደግ የነጋዴውን


ቁጥር 29,025 ማድረስ፣
የአዲስ ንግድ ምዝገባ ተግባር አሁን ካለበት 2002 በቀጣይ 10 ዓመታት በ 10 በመቶ
በማደግ ወደ 5187 ማሳደግ፣
የአዲስ ንግድ ስራ ፈቃድ ተግባር አሁን ካለበት 2247 በየበጀት አመቱ በ 10 በመቶ
በማደግ በቀጣይ 10 አመታት ወደ 5,820 ማሳደግ፣
የንግድ ፈቃድ ቁጥር አሁን ካለበት 11194 ወደ 29025 ማድረስ ከዚህ ውስጥ
የሴቶችን ተሳትፎ ከ 30.9% ወደ 50% ማድረስ፡
16 የዘርፍ ማህበራት በማጠናከር፣የንግድ ዘርፍ ማህበራት አሁን ካለበት አባላት 3,173
በቀጣይ 10 ዓመታት በ 10 በመቶ በማሳደግ 34,900 ማድረስ፣
የነጋዴ ሴቶች አሁን ካለበት አባላት 846 በቀጣይ 10 ዓመታት በ 10 ከመቶ በማሳደግ
9,300 በማድረስ በብቃት መወጣት የሚያስችል ቁመና እንዲኖረው ማድረግ፡
ዓላማ 2. የንግድ ውድድር ስርዓትን በመዘርጋት የሸማቹን ህብረተሰብ መብት
በማስከበር በመሰረታዊ ምርት የሚታየውን የአቅርቦትና ብክነትን በመፍታት ስርጭቱ
፤ጤንነቱን አደጋ ላይ የሚጥል የምርት ጥራት በመከታተል የሸማቹን እርካታ ማሳደግ

ግብ 2 ፡የመሠረታዊ ሸቀጦችን ስርጭትን በህብረተሰቡ ሙሉ ተሳትፎ በባለቤትና


ተቆጣጣሪ ሆኖ እንዲመራው በማድረግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣

 ወርሃዊ ስኳር 8,436 ኩ/ል በየአመቱ 10 % በማሳደግ 21,865 መተግበር ፣


ወርሃዊ ዘይት 605,302 ሊትር በየአመቱ 10 % በማሳደግ 1,569,450 ሊትር
በማድረስ ብክነትንና ኢ-ፍትሃዊነትን በማስወገድ የሸማቹን እርካታ ማሻሻል፣
በጥቁር ገበያ የሚባክነውን መሰረታዊ ምርት በማስቆም የህዝቡን ተጠቃሚነት
ማረጋገጥ፤

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ግብ 3 ፡የንግድ ውድድር ስርዓትን በመዘርጋት የሸማቹን መብት በማስከበር የዋጋ ንረትና


የኑሮ ውድነት ችግርን መፍታት ፤

የሚከናወኑ ተግባራት

የግብርና ምርት 14,227 ኩ/ል በየአመቱ 10 % በማሳደግ 36,890 ኩ/ል እንድደረስ


ማከናወን ፣
የኢንዱስትሪ ምርት 10,289 ኩ/ል በየአመቱ 10 % በማሳደግ 26,678 ኩ/ል
መተግበር፤
የአገልግሎት ጊዜ ያለባቸውን አስከ 2012 ዓመት የነበረውን 241,830 ኩ/ል በየአመቱ
10 % በማስቀነስ 0 በማድረስ የሸማቹን ጤንነት ማረጋገጥ፡
የንግድ ውድድር ስርዓትን በመዘርጋት ህብረተሰቡ ከንግድ ድርጅት ደረሰኝ መቀበል
32,510 በቁጥር በየአመቱ 10 % በማሳደግ 84318 የሸማቹን መብቶች ማስከበር፤
የሸማቹን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል የምርት ጥራት ችግሮችን በመከታታል የሸማቹን
ህብረተሰብ መብትና ጥቅም ማረጋገጥ፤
አላማ 3. የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን ፋይሎችን በመመርመር የውጭ ቁጥጥር
አጠናክሮ በመቀጠል የመለኪያ መሳሪያዎችን በቁጥጥር ማረጋገጥ ህጋዊ የንግድ ሽፋን ማሳደግ

ግብ 4፡የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 የምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ቁጥጥር የነበረውን 113,849 ፋይል በየአመቱ


10 % በማሳደግ 295,293 ማድረስ፤
 የውጭ ቁጥጥር (የበር-ከበር ጉብኝት) 404,495 የነበረውን በየአመቱ 10%
በማሳደግ 1,016,939 የውጭ ኢንስፔክሽን ህጋዊ የንግድ ሽፋን ማሳደግ፤
 የዉጪ ቁጥጥር ስራ በመስራት ሁሉም ነጋዴዎች 100 % ወደ ህጋዊነት እንዲገቡ
ማድረግ
 ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ መለኪያ መሳሪያዎችን እስከ 2012 ዓመት
የነበረውን 165,225 ምርመራ ትክክለናት ማረጋገጥ የተደረገውን የቁጥጥር ስራ
የተሰራውን በየአመቱ 10%በማሳደግ 4,28,545 በምርመራ ትክክለናነት
ማረጋገጥ ጉድለት የተገኘባቸውን አንዲስተካከሉ ማድረግ፤

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አላማ 4.፡-የሰብል ምርት ትስስር ግብይትና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራርን በማሻሻል በኢኮኖሚዉ
የሚገኘዉን ገቢ ማሳደግ፡፡
ግብ 5. ለትስስር የሚቀርበውን የሰብል ምርትን ከ 158,190 በዕቅድ ዘመንመጨረሻ ወደ
1,740,090 ማሳደግ፣
የሚከናወኑ ዋና ዋ ተግባራት

 የሰብል ምርት ግብይት ዉጤታማ በማድረግ ፤የብእር እህል 84,174 ከነበረበት 10


በመቶ በመጨመር 9,25,910 ኩንታል ማከናወን ፣

አትክልትና ፍራፍሬ ከነበረበት 60,824 ወደ 669,060 ኩንታል ማድረስ፤ የጥራጥሬ


ምርት ከነበረበት 10,700 ወደ 117,000 ኩንታል ማድረስ፤ ፣የቅባትእህል ከነበረበት 2492
ኩንታል ወደ 27410 ኩንታል ማድረስ፤
ስለገበያ መረጃ አስፈላጊነት የህብረተሰብ ክፍሎች 23493 በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ
234930 በመፈጸም፤የገበያ መረጃን 100% ተደራሽ ማድረግ፤

ግብ 6፡ የገበያ መሰረተ ልማትን በማዘመን ዘመናዊ ግብይት አሰራርን ማጠናከር

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
የከተማ መደበኛ ገበያን በ 2012 ካለበት 2 በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ 4 ማከናወን ፤
የቁም እንሰሳት ገበያ በ 2012 ካለበት 1 በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ 4 ይሰራል፤
የመደበኛ የገጠር ገበያ በ 2012 ካለበት 1 በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ 3 ማከናወን፤
ቆዳና ሌጦ፤ገበያ ማእከላትን በ 2012 ካለበት 0 በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ 10 ማድረግ
በህገወጥ መንገድ ለሚያዙ ለእንስሳት ማቆያ ጣቢያ በ 2012 ካለበት 0 በእቅድ ዘመኑ
መጨረሻ 5 መፈጸም ፤
የገበያ መሰረተ ልማት ችግሮችን በመለየት ችግሮችን የመፍታት ስራዎች ይሰራሉ፡፡
አላማ 5. የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ ግብይትና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራርን በማሻሻል ከንዑስ
ክፍለ ኢኮኖሚዉ የሚገኘዉን ገቢ ማሳደግ

ግብ 7 በእንስሳትና እንስሳት ተዋፅኦ ዘርፍ ጥራቱን ጠብቆ ለአገር ዉስጥ እና ለውጪ የገበያ
ትስስር መፍጠር

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የቁም እንሰሳት ለዉጭ ገበያ ለመላክ በ 2012 ዓ.ም ከነበረው 500 በእቅድ ዘመኑ መጨረሻ
ወደ 1415 በማሳደግ 440000 ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት፤
ጥራቱን ጠብቆ ለመሀል አገር ገበያ የሚቀርበውን የቆዳና ሌጦ ምርትን ከ 1632910
በዕቅድ ዘመንመጨረሻ ወደ 42346531 ማድረስ ፣

ጥራቱን ጠብቆ ለመሀል አገር ገበያ የሚቀርበውን የቁም እንስሳት ዳልጋ ከብት
96678፣ከነበረበት 10 በመቶ በመጨመር 250679 መፈጸም ፣
በግና ፍየል 66616 ከነበረበት 155272 ለማድረስ ፣የጋማ ከብት 15606 ከነበረበት
40383 ለማድረስ መተግበር ፣
ማርና የማር ዉጤቶች፤ የእንስሳት መኖ፤ዓሣ፤ዶሮ በአጠቃላይ የእንስሳት ተዋፅኦ ምርት ትስስር
በመፍጠር ገቢያቸውን ከፍ ማድረግ፤

የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዘርፍ

ዓላማ 1፤-በከተሞች ሰፊ ልማታዊ ባለሀብት በመፍጠር የዘርፉን ልማት በማስፋፋት


የስራ እድል መፍጠር እና ተጠቃሚነታቸውን ለ ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ኢንተርፕራይዞች የልማታዊ ባለሀብቶች መፈልፈያና የኢንዱስትሪ ልማት ማድረግ፤


የትምህርት እና የስልጠና ተቋማትን እና ስራ ፈላጊዎችን በማማከር በስራ ገበያ ፍላጎት እና
አቅርቦትን ማጣጣም፤
በከተማ በመደበኛ ቀጥታ ድጋፍ በመስጠት 22239 አዲስ ኢንተርፕራይዞችን
ማቋቋም፤
ለ 111189 (80% ቋሚና 20% ጊዚያዊ) ኢንተርፐራይዞችን በማጠናከር 57774
በመንግስት ፕሮጀክት 99126 በገጠር ለሚገኙ 20895 ስራ ፈላጊ ዜጎችን የስራ እድል
መፍጠር፤
በከተማ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች ለ 20781 ምሩቃን
የቋሚ ቅጥር ስራ እድል ለመፍጠር፤

የተቋማት ብቃት ማረጋገጫ ዘርፍ


አላማ 2፡-በከተማችንልማት መፋጠን ተገቢውን ድርሻ የሚጫወት በቴክኒክ በእውቀት፣
በክህሎትና በአመለካከት ብቁ የሆነ የሠው ኃይል ማፍራትና ወደ ስራ ለማስገባት

ግብ 1. አመታዊ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የመደበኛ የሰልጣኝ ቅበላ በማሻሻል


ሰልጣኞችን በማፍራት የኢንዱስትሪውን የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማርካት

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በ 20012 በ 1፣12፣10 ጥምርታ ከነበረበት 47240 ወደ 133116 ማድረስ፤


 ጠቅላላ ቅበላውን በእቅድ ዘመኑ 180356 ሰልጣኞችን ማፍራት
 በደረጃ 3 እና 4 አዲስ 55396 (ነባር 122524) ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን፤
 የሴት ሰልጣኞች ተሳትፎ 65%ማስጠበቅ፤
 የአካል ጉዳተኛ ሰልጣኞችን ተሳትፎ በማሳደግ 100% ማድረስ፤
 የቴክኒክናሙያምሩቃንበ 2012 ዓ.ም ከተደረሰበት 39%ወደ 84%ማሳደግ፤
 አጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማትን በማጠናከር በእቅድ ዘመኑ ከነበረበት 13914
ወደ 244808 ሰልጠነኞች ማድረስ፤
 የትብብር ስልጠና ሽፋን በ 2012 ከነበረበት 78.25% ወደ 100%ማሳደግ፤
 የግንባታ ግብዓት አቅርቦት ዘርፍ

አላማ፤- የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ያለባቸውን የማምረቻ፣ ማሳያ፣


የመሸጫ ቦታን፤ የገበያ ማዕከል አቅርቦት ችግር በመቅረፍ በተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ
ውጤታማነትን ለማሳደግ፤

ግብ 1. በጥቃቅንና አነስተኛ አደራጅቶ ኢንተርፐራይዞች ወደ ስራ በማሰማራት


የሚሰጠውን አገልግሎት ሽፋን ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በከተማ 150000 ካ/ሜ በገጠር 250000 ካ/ሜ ቦታ ማዘጋጀት፤


 በከተማ 800 ኢንተርፕራይዞች 1800 አንቀሳቃሾችን፤ በገጠር 250 ኢንተርፕራይዞችን
1200 አንቀሳቃሾችን ተጠቃሚ ማድረግ
 በከተማ 100 ሼድና 5 ጉድኝት ህንፃ፤በገጠር 50 ሼድ በመገንባት 200 ኢ/ዝ 600
አንቀሳቃሽ በከተማ፤ በገጠር 100 ኢ/ዝና 500 አንቀሳቃሽ ተጠቃሚ ማድረግ፤
 4 አዳዲስ ማዕከላትን መክፈትና በቴክኖሎጂ ማጠናከር

 የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዓላማ፤-በከተሞች ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን


አገልግሎት በመስጠት በገበያ ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው ሰፊ የስራ ዕድል እንዲፈጥሩና
ገበያቸውን ለማሻሻል

ግብ 5. በእድገት ተኮር ዘርፎች ክፍተትንና የእድገት ደረጃን መሰረት የኢ/ዞችን


ምርታማነትና የምርት ጥራትን ለማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ለ 6877 ነባርና አዲስ ኢንተርፕራይዞችንና ለ 25594 አንቀሳቃሾች የተሞላ አገልግሎት


በመስጠት 30% ወይም 7678 አንቀሳቃሾች በምዘና ስርዓቱ እንዲያልፉ ማድረግ፤
 ከተመዘኑ አንቀሳቃሾች 80%ብቁ እንዲሆኑ ማስቻል፤
8926 ኢ/ዞች እና 2594 አንቀሳቃሾችን የመረጃና ምክር አገልግሎት መስጠት እና
6144 አ/ዞች በደረጃ 4 ሙያተኞች እንዲመሩ ማድረግ፤
ፍላጎትንና ክፍተትን መሰረት ያደረጉ 10 የእሴት ሰንሰለት ትንተና በመስራት 149
ፕሮቶታይፖችን በማዘጋጀት ወደ ሌሎች ማሸጋገር ፤
 የኢንዱስትሪ ማስፋፊያ አገልግሎት ከሚሰጣቸው ኢ/ዞች መካከል በትኩረት ዘርፍ
የተሰማሩ 448 አርአያ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን በመፍጠር የ 150 ኢ/ዞች ተሞከሮ
ማስፋፋት፤

ገበያና ግብይይት
ዓላማ፤-ለኢንዱስትሪ ልማት አሰተማማኝና ሰፊ የገበያ እድል በማመቻቸት
የኢንተርፕራይዞችን ገቢ በማሻሻል ድህነትን በመቀነስ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል
እንዲፈጠር ኢንተርፕራይዞችን በገበያ ተወዳዳሪነት በማስፈን ቀጣይነት ያለው ፈጣን
ልማት ለማረጋገጥ

ግብ 1. የገበያ ትስስር በመፍጠር ፤ የብድር አቅርቦት ተጠቃሚ በማድረግ


የኢንተርፕራይዞችን ተወዳሪነትና ውጤታማትን ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

ለ 9000 ኢንተርፕራይዞች ፤ለ 27900 አንቀሳቃሾች የሀገር ውስጥ ገበያ ትስስር


በመፍጠር ብር 675000000 ገቢ እንዲያገኙ ማስቻል፤

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 ለውጭገበያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ ማምረቻበማረት 80 ኢንተ


ርፕራይዞችን (240 አንቀሳቃሾችን) የውጭ ሀገር ገበያ ትስስር በመፍጠር የ 208560
አሜሪካ ዶላር እንድያገኙ በማድረግ የውጭ ምንዛሬን ማሳደግ፤
ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ገንዘብ ችግር ለመቅረፍ የብድር አቅርቦቱን
ብር 810963890 በማቅረብ ፤9000 ኢን/ዞች እና 27000 አንቀሳቃሾች ተጠቃሚ ማድረግ፤
ከሚቀርበው ብድር ውስጥ ከቁጠባ ብር 648771110 የሚሸፈን ሲሆን የብድር አመላለስ
ምጣኔን 100% በማስጠበቅ የኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚነት ማሳደግ፤

 ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር


የበጀት አጠቃቀም ዘርፍ

ዓላማ 1፤- ከክልል በቀመር ተደልድሎ የሚላከውን በጀት በበጀት ሰሚ መደልደል፣


በካቢኔና በም/ቤት በማጸደቅ በጀቱ በአግባቡ እየተመራ በጥቅም/ ሥራ ላይ መዋሉን
ለማረጋገጥ

ግብ 1.የዳበረ የበጀት አጠቃቀምና ውጤታማነትን 100% በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን


ማረጋገጥ
የሚከናወኑ ዋናዋና ተግባራት

መደበኛ ደመወዝ ፤ስራ ማስኬጃ እና ካፒታል በጀት ከነበረበት ብር 552.2 ሚሊየን


ወደ ብር 53.168.195.000 ማሳደግ፤
በጀቱን ለመምሪያዎች ደልድሎ ማሳወቅ፣ የፀደቀዉን በጀት ለሚመለከታቸው
አካላት በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ እና ማጠቃለል፤
የበጀት አጠቃቀምን በአግባቡ መቆጣጠር፣
የበጀት አሠራር ሥርአትን ዘመናዊ ማድረግ፤
አሳታፊ ፍትሃዊና ውጤታማ የበጀት ድልድል ማጠናከር፤
 የልማት ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ
ዓላማ፤- የልማት ፋይናንስ አቅምን ለማሳደግ፤ የመንግስት ሀብትና ንብረት በአግባቡ
ለታለመለት አላማ ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ

ግብ 1. የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የልማት ገንዘብ አቅምን ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 ለልማት አገልግሎት የሚውል ያደገ የልማት ገቢ በመፍጠር

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የልማት ገንዘብ አቅምን ከነበረበት ብር 577.9 ሚሊዮን ወደ ብር


21,921,31,000 ማድረስ፤
 ከክልል ድጎማ፣ ከህብረተሰብ ተሳትፎ፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣
ከብድርና እርዳታ የሚገኝ ገቢን ማሰባሰብ፤

ግብ 2.የመንግስት ሀብትና ንብረት በአግባቡ ለታለመለት አላማ ጥቅም ላይ መዋሉን


ማረጋገጥ

በዘመናዊ አሰራር ዘዴ የተመዘገበ ንብረትን ከ 90% ወደ 100%ማሳደግ


የሀብት ብክነትን መቀነስ ከ 75%ወደ 100%ከፍ ማድረግ
 የኦዲት ቁጥጥር፤የግዥና ፋይናንስ ዘርፍ

ዓላማ፤ አጠቃላይ የገቢና የውጪ፤የንብረትና የግዥ አፈፃጸምን እንዲሁም የሀብት


አጠቃቀምን ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የክዋኔ እና ፋይናንስ ኦዲት ሸፋንን
ማሳደግ፤ የመንግስት ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ጥራትና ደረጃዉን የጠበቀ ስርአትን
ለማስፈን

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የገንዘብ ኦዲት ሽፋንን ድግግሞሽ በቁጥር ከ 45 ወደ 70 ማድረስ፤


የጥሬ ገንዘብ ምርመራን ከ 83.1% ወደ 100% ማድረስ፤
የት/ቤቶችና ጤና ጣቢያዎችን የገንዘብና ንብረት ምርመራ ብዛት በቁጥር ከ 16 ወደ
36 ከፍ ማድረግ፤
በእቅድ የተመራ፤ጥራትና ደረጃዉን የጠበቀ ግዥን ከ 80% ወደ 100% ማድረስ፤
የተጠቃለለ ግዥ በመፈጸም የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓለማ እንዲውል
ማድረግ፤ግልፅነትና ተጠያቂነትን የሚያስከትል የጨረታ ሂደት መከተል፤

 የህገ ወጥ ድርጊት መከላከል ደንብ ማስከበር ዘርፍ

ዓላማ 1.ህገወጥ ተግባራትን ወይም ህገ-ወጥ ንግድ በመከላከልና ተገቢ እርምጃ በመውሰድ
ህግና ስርአት ለማስከበር

ግብ 1. ህገወጥ ተግባራትንመከላከል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የተለያዩ የህገወጥ ተግባራትን በመከላከል፤ የተለያዩ የህገ-ወጥ ግንባታዎችን


እስከአሁን የተገነቡ ውዝፍ ጨምሮ ግንባታዎችን 100% በመለየት ሙሉ በሙሉ
እርምጃ መውሰድ፤

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የአካባቢ ብክለትን ማንኛውንም ሰው ወይም ድርጅት ከመኖሪያ ቤቱም ሆነ ከድርጅቱ


d ረቅ ቀሻሻ ወደ ውጭ የሚጥሉ የመፀዳጃ b ትን ጨምሮ ፍሳሽ ቆሻሻ በሚለቁና
በሚያሰርጉ ህገ-ወጦች ላይ 100% እርምጃ መውሰድ፤
ህገወጥ ንግድን በተገቢው መንገድ በመከላከል 90% ህጋዊ የንግድ አሰራር እንዲሰፍን
ማድረግ፤
በከተማው ዋና እና በውስጥ ለውስጥ መንገዶች ላይ አላስፈላጊ ቁሶች
የሚያስቀምጡ እና የሚጠቀሙ ለሰዎች አደጋ ሊያደርስ የሚችሉ ህገ ወጥ ድርጊት
90% መቀነስ፤

5.4.2.3 ማህበራዊ ልማት ዘርፍ


 የከተማ ምክር ቤት ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫዎች
ም/ቤቱ በከተማዉ የሠላም፤ልማት እና የህግ የበላይነት መከበሩን ማረጋገጥ፤
የህዝብ ዉክልናን ከመወጣት አንፃር የመራጭ-ተመራጭ መድረክን ማዘጋጀትና
የህብረተስቡን ጥያቄዎች ማዳመጥና እንዲፈቱ ማድረግ ፤ በየደረጃው ባሉ
ም/ቤቶች መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት፤ አሰራርን ማሳደግ የሚያስችል የተደራጀ
ክትትል፤ድጋፍና ቁጥጥር ሥራዎች ማካሄድ ፤የተጠናከረ የኦዲት ግኝት አመላለስ
ስርዓት መዘርጋት፤ የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረትን ከብክነት መከላከል፤
የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የቀጣይ ስራ ይሆናል፡፡

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዓላማ 1- ጥራት ያላቸው ደንቦችን በማውጣት አፈጻጻማቸውን ክትትልና ቁጥጥር


በማድረግ የህዝብን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ

ግብ-1 በህግ አወጣጥ ሂደት ላይ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚወጡ ደንቦችን


ጥራትና ተፈጻሚታቸው ማረጋገጥ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

በአዋጅ ቁጥር 245/2009 መሰረት ለም/ቤቱ የሚቀርቡ ረቂቅ ደንቦችን ከጉባኤ


ከአንድ ወር በፊት ለሚመለከተዉ አካል እንዲልኩ እና በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች
የህዝብ አስተያየት እንዲሰጥባቸዉ ማድረግ፤
በምክር ቤቱ የሚወጡ እና የፀደቁ አዋጆች፣የማስፈፀሚያ ደንቦችና
መመሪያዎች ተደራሽ በማድረግ ስራ ላይ መዋላቸዉን
መከታተል፤ማረጋገጥ፤መቆጣጠር፤

 የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ

የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት መመሪያ የቀጣይ ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮች
ተቋማት ውጤታማ አደረጃጀት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ የሥራ አፈፃፀም ምዘና ሥርዓት
መዘርጋት፣ ወቅታዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎች በመዳሰስ የሰው ሃብት ልማት ስራን ማስቀጠል እና
ተቋማዊ አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፤ፍትሃዊና ውጤታማ ማድረግ ይሆናሉ፡፡

ዓላማ 1፡- የተሟላ ስብዕናና ቁመና ያለው ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት የተቋማትን ተልዕኮ
ለማሳካት የሚያስችል የአደረጃጀትና የአሠራር ሥርዓት ለማረጋገጥ

ግብ 1፡- የመንግስት ተቋማትን አሰራርና አደረጃጀት ውጤታማነት ማጎልበት፣


የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
 የመንግስት ተቋማት ቀልጣፋና በውጤት ላይ ያተኮረ፣ ወጪ ቆጣቢ የሆነ ተቋማት
የውስጥ አደረጃጀት እና አሰራርን 100% የሚችሉበት ደረጃ ላይ ማድረስ፣
 በሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ከምደባ ሥርዓት ወደ ነጥብ የስራ ምዘና ዘዴ የተደረገውን
ለውጥ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ፤

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 በሰው ሃብት ስምሪትና ጥቅማ-ጥቅም አፈፃፀም ዙሪያ 100% የግል ማህደር ምርመራ
ማካሄድና ግድፈቶች በፍጥነት እንዲታረሙ ማድረግ፤
 የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን 95% ያህሉን መፍታት፤
 በየተቋማቱ ያለው የአደረጃጀት፣ የሰው ሀይል ምልምላ፣ የመረጣ፣ የቅጥር፣ የክፍያና
የዕድገት አሰጣጥ አተገባበር 100% ማጠናከር፤

ግብ 2፡- የሰው ሃብት ልማትና አስተዳደር ሥርዓቱን ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-

 ተቋማትና በተለያዩ የአስተዳደር ዕርከኖች ለሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች


እንዲሁም ፈፃሚዎች የአጫጭርና መካከለኛ ጊዜ በሲቪል ሰርቪሱ አሠራር ዙሪያ የታዩ
ክፍተቶች ሊቀርፍ የሚችሉ ሥልጠና መስጠት፤
 የረጅም ጊዜ የትምህርት እድል ለሲቭል ሰርቫንቱ መስጠት፤
ግብ 3፡- የሠራተኞችን ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና ሥርዓት ማሻሻል
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፡-
 ሁሉም ተቋማት በስትራቴጂ የሚመሩ፣ በስትራቴጂክ የከፍታ ደረጃ ላይ ያሉ
ግቦቻቸውን የሚገመግሙና የሚመዝኑ ወደ መሆን ደረጃ ማሸጋገር፣
 ለሁሉም ሲቪል ሰርቫንቱ የስራ እቅድ መስጠት ፤ የሠራተኞችሥራ አፈፃፀም ምዘና ደረጃ
ማዘጋጀት ወይም ማሻሻል እና ወቅቱን የጠበቀ የስራ አፈጻጸም ግምገማ እና ግብረ መልስ
መስጠት፤
የፈጻሚና የቡድን ማበረታቻ እንዲሁም የተቋማት ማወዳደሪያ ስርዓቶችን
የመዘርጋትና የመተግበር ስራዎችን ማከናወን፣

የዕቅድ ማስፈፀሚያ ስልቶች

በመምሪያው የሰው ሃብት ልማት ሥራው በዕቅድና በአንድ ማዕከል እንዲመራ ማድረግ፣ ደንበኞች
የሚሰጡትን አስተያያት መነሻ በመውሰድ እና ዳሰሳ ጥናት በማድረግ ክፍተቶች m ሙላት፡፡
ከነባራዊ ሁኔታ ጋር የተገናዘቡና ችግሮችን ሊፈቱ የሚችሉ የህገ ማዕቀፎችን መሰረት ያደረገ ሥራ
መስራት ፤ የለውጥ ሥራዎችን መተግበር፣ የተቀናጀ የሲቪል ሰርቪስ መረጃ አያያዝ ሥርዓቱን

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

መተግበር እና ወጥ የሆነ የምዘና ስታንዳርድ ማፀደቅና መፈጸም እና የማሻሻል ሥራ ማከናወን


የቀጣይ 10 አመት እቅድ አፈጻጸም እንዲሳካ ያደርጋል፡፡

ጤና ዘርፍ
የትኩረት አቅጣጫ

የቀጣዮቹ 10 ዓመታት (2013-2022) በጤናው ዘርፉ የተቀመጡ ዓላማዎችን፣ ግቦችንና


ዋና ዋና ተግባራትን ለመፈፀም የምንከተለው የትኩረት አቅጣጫዎች ፈጣን፣ ቀጣይነት
ያለው የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጁ በመተግበር ህዝቡ የራሱን ጤና እራሱ እንዲጠብቅ
ማድረግ ቀዳሚ ስራ ይሆናል፡፡ ሌላው ህብረተሰቡ በአቅራቢያው የህክምና
አገልግሎቶችን እንዲያገኝ በቂ የሆኑ የጤና ተቋማትን ማስፋፋት፣ብቁ የሆኑ
ባለሙያዎች በማፍራት ጥራቱን የጠበቀ የፈውስ ህክምና እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ
አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ ማቅረብ የቀጣይ አመታት ተግባር ነው፡፡ በተጠናከረ
የበሽታ ቅኝት፣ ዝግጁነት፣ ምላሽ፣ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች በመከላከል
እና ወረርሽኝን በመቀነስ ዜጎች በህይወት የመኖር እድሜ ምጥነት መጨመር እና
ጤናማ ትውልድ መፍጠርይሆናል፡፡

ዓላማ 1፡-የእናቶችንና የህጻናትን ሞት በመቀልበስ የእናቶችንና ህጻናትን ጤና ማሻሻል፣


እንደ ኤች አይቪ ኤድስ፣ ወባና ቲቢ የመሳሰሉትን ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ
በሸታዎችን ስርጭት በመቀነስ፤ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር

ግብ 1፡- የእናቶችን እና ህጻናትን ጤና አገልግሎት ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የእናቶች ሞት ምጣኔ ከ 401 / 100,000 ወደ 176 በ 2029 መቀነስ፤


 ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ሞት ምጣኔ ከ 85/1000 በ 2022 ወደ
33/1000 መቀነስ፤
 የህፃናትን ሞት ከ 67/1000 ወደ 25/1000 በ 2022 መቀነስ፤
 የህጻናት የተለያዩ ክትባት አገልገሎት ሽፋን 99% ማድረስ፤
 የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ሽፋን ከ 60% ወደ 75% ማድረስ

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 እድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ሞት ምጣኔን ከ 20/1000 ወደ


12/1000 ሞት ዝቅ ካለ በሕይወት ከሚወለዱ ህጻናት ዝቅ ማድረግ፣
 ስርዓተ ምግብ አስመልክቶ ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት
የመቀንጨርን ሽፋን ከ 41.3% ወደ 13% መቀነስ፤
 ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት መቀጨጭ ከ 7% ወደ 3% መቀነስ፤
ግብ 2፤- ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ስርጭት መቀነስ እና መከላከል ፣
የአዕምሮ ጤና ችግሮች ልየታ በማካሄድ
ከ 1.4 ወደ 0.86፣ አዲስ በኤች አይ ቪ የሚያዙ ሰዎች መጠን ከ 0.03 ወደ 0.01%
መቀነስ፤
 ለአዋቂዎች የሚሰጠውን የጸረ ኤች.አይ.ቪ መድሐኒት ሽፋን ከ 74% ወደ 100%፤
እንዲሁም ለህጻናት የሚሰጠውን የጸረ ኤች አይ ኤቪ መድሐኒት ሽፋን ከ 5.2% ወደ
100% ማድረስ፣
 በወባ ምክንያት የሚከሰተውን ሞት ከ 0.5 ወደ 0.01/100,000 ሰዎች ዝቅ ማድረግ፣
የቲቢ በሽታ ስርጭት መጠንን አሁን ካለበት (እንደ አገር) ከ 211/100,000 ወደ
147/100,000 እንዲቀንስ ማድረግ፣ አዲስ በቲቢ በሽታ የመያዝ መጠን አሁን ካለበት (እንደ
አገር) ከ 224/100,000 ወደ 178/100,000 እንዲቀንስ ማድረግ፣ በቲቢ በሽታ የሞት መጠንን
አሁን ካለበት (እንደ አገር) ከ 32/100,000 ወደ 21/100,000 እንዲቀንስ ማድረግ፣
 ዋና ዋና በሆኑ ተላላፊ-ያልሆኑ በሽታዎች ( CVDS ፣ የስኳር በሽታ ፣ የኩላሊት
በሽታዎች ፣ CRDS እና ካንሰር) የሞት መጠን ከ 20 /100,000 ወደ 13.5 / 100,000 በ
2022 መቀነስ፤
 የአይን ሞራ ግረዶሽ የቀዶ ጥገና መጠን ከ 539 በ ሚሊዮን ወደ 2000 ሚሊዮን
ማድረስ፤
በመውለድ ዕድሜ ክልል ያሉ ሴቶች የማህፀን አፍ ካንሰር ልየታ/ምርመራ ሽፋን ከ 21%
ወደ 46% ማድረስ፣
 የዓይን ቆብ ፀጉር (ትራኮማ ትሪኪያሲስ) በሽታ ሥርጭትን ካለበት 4% ወደ 0.001%
ማድረስ፤
 የዓይን ማዝ (አክቲቭ ትራኮማ) በሽታ ሥርጭት ካለበት 26.3% ወደ 5% ማድረስ፣

ዓላማ 2፤- መሠረታዊ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦትና አጠቃቀም እና


የጤና መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የጤና አገልግሎት ሽፋን ለማሻሻል

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ግብ 3፡- መሠረታዊ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦትና አጠቃቀም ሽፋን


ማሳደግ

በሁሉም የጤና ተቋማት ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተረጋገጡ መድሃኒቶችን እና


መገልገያ መሳሪያዎችን ተደራሽነት 100% ማድረስ፤
 የመድሐኒት ብክነት መጠንን ወደ ዜሮ ዝቅ ማድረግ፣

ግብ 4፡- የጤና መሰረተ ልማትን በማስፋፋት የጤና አገልግሎት ሽፋን ማሻሻል /100%
ማድረስ/

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
 የጤና ኬላዎችን ወደ 2 ማድረስ፤ 4 የጤና ጣቢያ ፤ 2 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና
ሁለት የማገገሚያ ማእከል መገንባት፤
የጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጁን በመከተል ስነ-ንፅህና እና የአካባቢ ጤና ጥበቃ ሽፋን ከ 80%
በ 2022 ዓ.ም 100% ማድረስ፤
የሀገሪቱ አማካይ የመኖር ዕድሜ ጣራ ከ 65.8 ወደ 69.7 ለማድረስ የጋራ ጥረት በማድረግ
የህዝብን ኑሮ ማሻሻል፣
የደምለጋሾች መጠን በ 2012 ከነበረው 0.2% ወደ 0.76% (2022) ከፍ ማድረግ፤

የማስፈጸሚያ ስልቶች

ህብረተሰቡን አሳታፊና ባለቤት ያደረገ የጤና ዘርፍ ስርዓት ግንባታን አጠናክሮ መቀጠል፤
የመሠረታዊ ጤና ክብካቤ አሀድ ከሆስፒታል አገልግሎቶች ጋር የሚኖራቸውን ትስስር
ማጠናከር፤ የግሉ ዘርፍ በጤና አገልግሎት ስርዓት ውስጥ የሚኖረውን ሚና
ማሳደግ፤የጤና ዘርፍ የውስጥ አቅምና የ g ንዘብ ምንጭ የአስተዳደርና አያያዝ ስርዓቱን
አስተማማኝ ማድረግ፣ ዘርፉ ዋነኛ አመራር ለመፍጠር የሚያስችሉ የአቅም ግንባታ
ሥራዎችን በዘላቂነትና በየደረጃው በተጠናከረ መልኩ ማካሄድ፣ መልካም ተሞክሮን

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የማስፋት ስትራቴጂን ተግባራዊ ማድረግ፣ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር፣ የሆስፒታል


ጉድኝት አደረጃጀትን በማጠናከር የእርስ በርስ ተሞክሮ የሚለዋወጡበትን ስርዓት
መዘርጋት የሚሉት ናቸው፡፡

 ትምህርት ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫዎች፤

የቀጣዮቹ 10 ዓመታት (2013-2022) አቅጣጫዎች በተደራጀ የህዝብ ተሳትፎ


ተግባራትን መፈፀም፣ ትምህርት ተቋማትን ማጎልበት ፤ የትምህርት f ትሃዊነት ፤ጥራት
እና ሽፋን መጠበቅ ፤ በመልካም እሴቶች የታነጹ፤ በአለም አቀፍ ደረጃ በሁለንተናዊ
ስብዕናቸው ብቁ የሆኑ ዜጎችን ማፍራት ዋና ትኩረት ይሆናል፡፡

ዓላማ 1፡- በተደራጀ የትምህርት ለውጥ ሠራዊት በሁሉም ደረጃዎች የትምህርት ፍትሀዊነትንና
አካታችነት በመጠበቅ ተደራሽነት/ሽፋን ማሳደግ፤ የትምህርት ጥራትና ብቃት በማስጠበቅ ብቁ
ተማሪዎች/ዜጎች ማፍራት፣

ግብ 1፡-የትምህርት ፍትሃዊነትን እና አካታችነት በመጠበቅ የትምህርት ዕድል ያገኙ


ዜጎች መጠን ማሻሻል፣

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የቅድመ መደበኛ እና መደበኛ ትምህርት ጥቅል እና ንጥረ ምጣኔ ፆታዊ ክፍተትን በ 2012 ዓ.ም
ከነበረበት 2.0 በ 2022 ዓ.ም 1.0 ማድረስ፣
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ተሳትፎን በ 2012 ዓ.ም ከነበረበት 227
ወይም 0.24 % በ 2022 ዓ.ም 637 ተማሪዎች ወይም 0.67 % ማድረስ፣
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (9-12) ጥቅል የተሳትፎ ምጣኔ ፆታዊ ክፍተትን ዜሮ ማድረስ፤
ግብ 2፡- የትምህርት ና ስልጠና ተደራሽነት/ተሳትፎን ማሳደግ፣
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጥቅል የትምህርት ተሳትፎን 100% ማድረስ፣
የመጀመሪያ ደረጃ (1-8) ጥቅል 97.6% እና ንጥር 95.7% የተሳትፎ ምጣኔ ከ 100% በላይ
ማድረስ፤
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (9-12) ጥቅል የተሳትፎ ምጣኔን ከ 100% በላይ ማድረስ፣
በከተማው ካሉት 35 የሳተላይት ክፍሎችን ወደ 55 ማሳደግ
የመንግስት ት/ቤቶች ሥርጭት ዕቅድን መሠረት በማድረግ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶችን አሁን
ካለበት 48 ወደ 50 ማሳደግ ፣
በከተማው ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎች የሚማሩበት አንድ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ማእከል
መገንባት፤

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ግብ 3 ፡-የትምህርት ውስጣዊ ብቃትን እና ጥራትን በማስጠበቅ ብቁ ተማሪዎች/ዜጎች


ማፍራት፣

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የማቋረጥ ምጣኔን ከ 0.95 ወደ ዜሮ እና መድገም ምጣኔን አሁን


ካለበት ከ 0.05 ወደ ዜሮ ማድረስ፣
አጠቃላይ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት የተማሪዎች መጠነ ማቋረጥ ከ 2.82 ወደ ዜሮ ክፍል መድገም
በ 2022 ዓ.ም ወደ ዜሮ % ዝቅ ማድረግ፣
በየትምህርት ዕርከኑ የተቀመጠውን የባህርይ ገጽታ እና የየክፍል ደረጃውን አጥጋቢ የብቃት
መለኪያ መሠረት በማድረግ የተማሪዎችን ውጤት መመዘን ፣
በት/ቤቶች የደረጃ ምደባ መስፈርት መሠረት በ 2022 ዓ.ም 100% ት/ቤቶች ደረጃ ሁለት
እንዲያሟሉ ማድረግ፤
 ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ

በቀጣይ አመታት የከተማውን ባህላዊ እሴቶች በመለየት፣ እንዲለሙና ጥቅም ላይ


እንዲውሉ በማድረግ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ የማንበብ ባህሉ የዳበረ፣
ኪነጥበባዊ የፈጠራ ባህሉ የበለፀገ፣ ህብረተሰብ ለመፍጠር የሚያስችሉ የባህል
ተቋማትን በየደረጃው እንዲስፋፉ ማድረግ፣ ጎጂ ልማድንና መጤ የባህል ወረራን
በቅንጅት በመከላከል በማንነቱ የሚኮራና ስብዕናው ያደገ ማህበረሰብ እንዲፈጠር
ለማስቻልና ጠቃሚ ባህላዊ እሴቶቹም በአግባቡ ተጠብቀውና ለምተው በስራ ላይ
እንዲውሉ ከማድረግም ባለፈ ለመጪው ትውልድ ጭምር የሚተላለፉበትን ሁኔታ
መፍጠር ይሆናል፡፡ የከተማውን ጥንታዊ አካላዊ ቅርሶች እንዲሁም የተፈጥሮ
መስህቦችን አለምአቀፍ ደረጃዉን በጠበቀ እና ዘላቂ ልማት መርህን በመከተል በተቀናጀ
የህብረተሰብ እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በአግባቡ እንዲለዩ፤እንዲመዘገቡ
፣እንዲጠኑ፣እንዲጠበቁ ፣እንዲለሙና እንዲተዋወቁ ማድረግ ቀዳሚ ስራችን ይሆናል፡፡

የ x ገር ጎብኝ ፍሰት ለመጨመርና ዘርፉ ለከተማው ኢኮኖሚ ያለውን አስተዋፅኦ ከፍ


ማድረግ፣ በስፖርት በኩል በሁሉም የስፖርት አይነቶች የፕሮጀክት ተተኪ ስፖርተኞችን
በማያቋርጥ ሁኔታ በስፋት ማፍራት ይጠበቅብናል፡፡

ዓላማ 1፡- በከተማችን የስፖርት አይነቶች በማሳደግ የስፖርት ኢንዱስትሪ


ለማስፉፋት

ግብ 1. የተለያዩ የሃብት ምንጮችን በማጎልበት የስፖርት ዘርፍን ማስፋፋትና


ደረጃቸውን ማሳደግ

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እንዲኖራቸዉ በማድረግ


እስከ 2022 አንድ የ 2 ኛ ደረጃ እና 13 የ 3 ኛ ደረጃ በድምሩ 14 ያህል በመገንባት ወደ
ስራ ማስገባት፤
 የስፖርት የስልጠና ማዕከላት ተቋማት በመገንባት በቁጥር ወደ 4 ማድረስ፤
 አንድ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ግንባታ ማካሄድ፤

አላማ 2፤-በከተማችን የባህል እንዱስትሪ ፤የቋንቋ ልማት አጠቃቀምና የገባያ ትስስርን


ማጎልበት፤የቅርሶችና የመዳረሻዎችጥበቃና ልማትን ለማሳደግ

ግብ 2፤-በከተማችን የባህል እንዱስትሪ ፤ የቋንቋ ልማት አጠቃቀም ና የገባያ ትስስርን


ማጎልበት

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የማይዳሰሱ ሃይምኖታዊ እና ባህላዊ ሃብቶች መሰብሰብ፣ መመዘገብ እና ማደራጀት


 የአፍ መፍቻ እና ሀገር በቀል ቋንቋዎችን ልማት ላይ መስራት፣
 የንባብ ተቋማትን በማስፋፋት በኩል በቀጣይ 10 አመታት 5 ቤተመጽሃፍት እና 5
የንባብ ቤቶች መገንባት፤
የኪነ-ጥበብ ፈጠራን ለማጎልበት አንድ ማሰልጠኛ ማእከል መገንባት

ግብ 3.በከተማችን የቅርሶችና የአገር ጎብኝዎች መዳረሻዎችጥበቃ እናልማትንማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

በከተማችን ያሉትን የቋሚና ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ምዝገባናቁጥጥርማካሄድ፣ ጥገናና


እንክብካቤማድረግ
በቀጣይ 10 አመታት ---- የደሴ ለተራራ ወጭዎች ማዘጋጀት እና ከጦሳ ወደ አዝዋ
ተራራ የሚያገናኝ የአየር ኬብል በማሰራት እንዲሁም ሌሎች ማራኪ መዝናኛ ቦታዎች
እንዲገነቡ በማድረግ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሀገር ጎብኝዎችን ፍሰትን መጨመር፤
ለጎብኝዎች አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ትስስርን ለመፍጠር የቤተሰብ ጉዞ በማዘጋጀት
የማስተዋወቅ ስራ መስራት በየአመቱ ሃገር አቀፍ እና አለም አቀፍ የንግድ ትርኢቶች እና
በቴሌቪዥን፤ሬደዮ፤በህትመት፤ ድረ-ገፅ፣ማህበራዊ ሚዲያ(በፊስቡክ፣ቲውተር፣ ዩቲዩብና ኢንስታ
ግራም ) ወዘተ ስለ ከተማው መረጃ ተደራሽ ማድረግ፤

የማስፈጸሚያ ስልቶች

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዕቅዱን በተሻለ የጥራት ደረጃና መጠን፣ በአጭር ጊዜና ባነሰ ወጪ ለመፈፀም


የሚከተሉት የአፈፃፀም አቅጣጫዎች በፍትህ፣ በፀጥታ፣ በመልካም አስተዳደር ተቋማት
ውስጥ በትኩረትና በጥብቅ ተግባራዊ የሚደረጉ ሲሆን ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት
ናቸው። እነሱም የለውጥ ሃይል አስራር ዋነኛ ማዕከል አድርጐ መንቀሳቀስ፣ ፈፃሚውና
አመራሩን በማብቃት የመሪነት ሚናውን እንዲጫወት ማድረግ /በሥልጠና፣
በሥልጠናዊ ግምገማ/፣ በጥናትና ምርምር የታገዘ አሰራር መከተል፣መልካም
ተሞክሮዎችን በመለየት መቀመርና ማስፋት፣ የህብረተሰብን ተሳትፎና ባለቤትነት
አጠናክሮ መቀጠል፣ የህዝብ ግንኙነት ተግባርን መሣሪያ አድርጐ በመጠቀም
ለሕብረተሰቡ በጥራትና በወቅቱ መረጃ ማድረስ እንዲሁም ሞጋች ማህበረሰብ
በመፍጠር አፈፃፀሙ እንዲጠናከር የፖሊሲዎችና ስትራቴጀዎች ማዕከል አድርጐ
መንቀሳቀስ፣ ሴቶችን ወጣቶችት የላቀ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ናቸው፡፡

ወጣት ፤ሴቶች እና ህጻናት ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ፤-

የሴቶችን ሁለንተናዊ ብቃት በመገንባት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስኮች እኩል


ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፣ በከተማው ልማት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምቹ
ሁኔታዎች በመፍጠር የራሳቸውን ሚና እንዲያበረክቱ ማስቻል፣ እንዲሁም የህጻናትን መብትና
ደህንነት በማክበርና በማረጋገጥ ህጻናት በማህበራዊና በመልካም አስተዳደር መስኮች
እኩል ተሳታፊነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይሆናል ፡፡

በሴቶች ዘርፍ

አላማ 1፤-በየደረጃው ሴቶች፤ወጣቶች እና ህጻናትን በማደራጀት የኢኮኖሚያዊና


ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ፣

ግብ 1 ፡-በየደረጃው ሴቶችን በማደራጀት የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተሳትፎ እና


ተጠቃሚነት ማሳደግ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ ሴቶችን ከነበረበት ከ 32350 ወደ 54606 ከፍ


ማድረግ፣

ለሴቶችየቁጠባ መጠን ከብር 2097258 ወደ 1 ቢሊዮን ማሳደግ እንዲሁም አንድ የሴቶች


የልማት ፈንድ ማቋቋም፤
 ለችግር ለተጋለጡ ሴቶች ምላሽ የሚሰጥ 2 የአንድ መስኮት አገልግሎት የሚሰጡ
ማዕከላት ማቋቋም

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 አንድ የተሀድሶ አገልግሎት መስጫ ማዕከ l ል እና አንድ ጥቃትን ለመከላከል


የሚያስችሉ ባለሶስት ቁጥር ስልክ ፈጣን መስመርአገልግሎት ማቋቋም፤
800 ሴቶች በተሀድሶ ማዕከላት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣

ግብ 2 በሴቶች ላይ የሚፈጠር ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን ና የሃይል ጥቃት መቀነስ

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የሴት ልጅ ግርዛት አሁን ያለበትን 100% ማስቀጠል፤


 ያለ ዕድሜ ጋብቻ ከ 90 በመቶው የቀነሰውን 100% ማድረስ፤
የቤት ውስጥ ጥቃትን እና ጾታዊ ትንኮሳ አሁን ካለበት በ 2022 ወደ 3 ከመቶ መቀነስ፤
በህጻናት ዘርፍ

ግብ 3፤- የህፃናትን ሁለንተናዊ ዕድገት ማጎልበት፤ መብት መጠበቅና ደህንነታቸውን


በማረጋገጥ ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ፣

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የህፃናትን ባህሪይን ለማነፅ በሚሰሩ ስራዎች በተሻለ የሕጻናት አያያዝና


አስተዳደግ ተጠቃሚ የሆኑ ሕጻናት ከ 45% ወደ 50 ከመቶ ማድረስ፤
 በተፈጠሩ የስብዕና ማዕከላት ተጠቃሚ የሆኑ ሕጻናት ከ ዜሮ ወደ 60 ከመቶ
ማድረስ፤
 በምቹና ተስማሚ የህፃናት የቀን ማቆያ ተጠቃሚ የሆኑ ህፃናት ከዜሮ ወደ 50
በመቶ፣ ጥቃት ደርሶባቸው በተቀናጀ የአንድ ማእከል አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ
ህፃናት 90 በመቶ መድረስ፤
 የአደጋ ጊዜ ፈጣን የስልክ ጥሪ መስመር አገልግሎቱን ለማግኘት ተደራሽ የሆኑ ህፃናት
ከዜሮ ወደ 60 በመቶ ማድረስ
 ጥቃት ከደረሳባቸው ህፃናት መካከል ከ 75% ወደ 90 ከመቶ የተሀድሶ አገልግሎት
እንዲያገኙ ማድረግ፣
 ለህጻናት ቤተሰቦች የስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ወደ
ጎዳና የሚወጡ ህፃናትን 100 ፐርሰንት መቀነስ
 የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ከ 51 በመቶ ወደ 20 በመቶ እንዲቀንስ ማድረግ፤
ወጣት ዘርፍ

ግብ 4. የወጣት ማዕከላትን በማጠናከር ወጣቶች የኢኮኖሚና ማህበራዊ ተሳትፎ እና


ተጠቃሚነትን ማሳደግ

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

.የህዝባዊ እና መንግስታዊ ስፖርት አደረጃጀቶችን በማጠናከር እና በማሳተፍ


በቀበሌዎች ደረጃ በአካባቢ ቁሳቁስ የሚገነቡ የወጣት ማዕከላትን ቁጥር ከነበረበት ከ 5
በ 2022 ወደ 8 ማሳደግ፣
 አዳዲስ ማዕከላትን ለመገንባት የሚያስችሉና ደረጃውን ያሟሉ በየአካባቢው 5
የማዕከላት መገንቢያ ቦታዎችን ርክክብ መፈጸምና የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ
ወይም ደብተር እንዲኖራቸው ማድረግ፣
 በከተማ ደረጃቸውን ጠብቀው የሚገነቡ የወጣት ማዕከላትን ቁጥር ከ 1 ወደ 3
ማሳደግ፣
 የማዕከላትን የአገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻልና መስፈርቱን እንዲጠብቁ በማድረግ
በቀጣይ 10 አመታት 30464 (ወንድ 15232 ሴት 15232) ወጣቶችን የአገልግሎቱ
ተጠቃሚ ማድረግ፣
 የወጣቶችን መሰረታዊ መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ ወጣቶችን ከአሉታዊ መጤ
ባህሎችና አደንዛዥ እፆች መከላከል እና የወጣቶችን ስብዕና ለመገንባት ሁለት
ማገገሚያ ማእከል መገንባት፤

የማስፈጸሚያስልቶች

የሴክተሩ የአስር አመት የልማት እቅድ ለማሳካት እንዲቻል ዋነኛው የእቅዱ


ማስፈጸሚያ ስልት ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በመገንባት
የእቅዱ ባለቤት እንዲሆኑ በማድረግ እቅዱን በተቀላጠፈና በተናበበ መልኩ የእቅዱ
የተፈጻሚነቱ ዋና ሃይሎች እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡
የሴቶች፣ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ የሁሉንም አካላት ዘርፈ ብዙ ምላሽ የሚሻ እንደመሆኑ
የዘርፉ ፈጻሚ መ/ቤቶችና በተዋረድም የሚገኙ መ/ቤቶች እንደመሆናቸው መጠን
የትብብር፣ ቅንጅት እና ህብረ- ኃይልን የማጠናከር ስራ እና የተቀናጀ አሰራር እንዲኖር
የሚያስችሉ የውይይት መድረኮችን፣ አውታሮችን፣ጥምረቶችና አደረጃጀቶች
እንዲሁም የሁለትዮሽና ባለብዙ የትብብር ስምምነቶች የመመስረትና የማጠናከር

ስራዎች እንዲከናወኑ ይደረጋል፡፡በዘርፉያሉምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመርና


በማስፋት፣መገናኛ ብዙሀንና የተግባቦት ስራዎችን ማጠናከር፣ መዋቅራዊ አደረጃጀት
የማሻሻል/ የመፍጠር ጉዳይ በላቀ ደረጃ የሚፈጸም ይሆናል፡፡

ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ


የቀጣይ አቅጣጫ

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የማስፈፀም እና የመፈጸም አቅምን በማጎልበት የኢንዱስትሪ ግንኙነትና ምርታማነትን


ማሻሻል፤ አሠሪዎችና ሠራተኞች መብትና ግዴታቸውን እንዲወጡ በማድረግ የሚከሰቱ
የመብት ጥሰቶችን መከላከል እንዲሁም በሥራ ምክንያት የሚመጡ አደጋዎችንና
በሽታዎችን በመከላከል የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነትን ማስጠበቅ በቀጣይ ትኩርት
የሚደረግባቸው ስራዎች ናቸው፡፡

ሌላው ደግሞ በቀጣይ 10 አመታት የሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን በማስፋፋት


የከተማውን የሰው ኃይል ፍላጎትና አቅርቦት የሚጣጣምበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤
የማኅበራዊ ጥበቃ ሥርዓትን በየደረጃው በመዘርጋት የዜጎችን ተጠቃሚነት ማሳደግ፤
የማህበራዊ ደህንነት አገልግሎቶችን በማስፋፋት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ዜጎችን
ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይሆናል፡፡

ዓላማ 1፤-የአረጋዊያንና አካልጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት እና


ተደራሽነት ማሳደግ፣ በማህበራዊ ጠንቆች ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖች የማህበራዊ ደህንነት
ድጋፎች እና አገልግሎቶች ማሻሻል

ግብ 1.የአረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት እና


ተደራሽነት ማሳደግ፣

የሚከናወኑ ዋናዋናተግባራት

 የአረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች መሠረታዊ መረጃ በማሰባሰብ ፤በቴክኖሎጅ


በማደራጀት 100% ተጠቃሚ ማድረግ፤
 በከተማችን ለአረጋዊያን እና ለአካል ጉዳተኞች የገቢ ማስገኛ 2 ማእከላትን
በማቋቋም ዘለቄታዊ ድጋፍ ማድረግ፣
 በተለያዬ የሥራ መስኮች መሳተፍ በሚችሉ አረጋዊያንን የትምህርት፣ የሥልጠና እና
የሥራ ሥምሪት እንዲያገኙ ማድረግ፣

ግብ 2. በማህበራዊ ጠንቆች ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖች የማህበራዊ ደህንነት ድጋፎች እና


አገልግሎቶችን ተደራሽነትን ማሻሻል

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የማህበራዊ ደህንነት ድጋፎችና አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሆኑ ጎዳና ተዳዳሪዎችን ቁጥር


ዜሮ ማድረስ፣
የማህበራዊ ደህንነት ድጋፎችና አገልግሎቶች ተጠቃሚ የነበሩ ለምኖ አዳሪዎችና
ሴተኛ አዳሪዎችን ቁጥር መቀነስ፤
ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በአደንዣዥ ዕጽ የተጠቁ ወጣቶች 100 % ከችግሩ
እንዲወጡ ማድረግ፣

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ዓላማ 2፡- ሠላማዊ የኢንዱስትሪ ግንኙነትን በዘላቂነት በማዳበር ፍትሃዊ እና ዘመናዊ


የሥራ ስምሪትና የሥራ ገበያ መረጃ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት

ግብ 3. የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አስተዳደር የመረጃ ሥርዓት በመዘርጋት በነፃ


የመደራጀትና የመደራደር መብታቸውን ማስከበር

የሚከናወኑ ዋናዋናተግባራት

 የኢንዱስትሪ ብዛት ፤የክፍት የስራ መደብ ፤ በሥራ ላይ የተሰማራውን የሰው ኃይል

እና በሥራ ላይ የሚገኙ ሠራተኞች መረጃ በመሰብሰብ ተንትኖ ለተጠቃሚ አካላት


ማሰራጨት፤
 የስራ ገበያ መረጃ ስርአት በመዘርጋት ቁልፍ ገበያ አመልካቾችን 6 በማድረስ ጥቅም

ላይ ማዋል፤
አሰሪ ማህበራት ማቋቋም እና ማደራጃት እንዲሁም አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎችን
ተጠቅሞ ግጭቶችንና አለመግባባቶችን መፍታት፤

ግብ 4.የመከላከል መርህን መሰረት ያደረገ የሥራ አካባቢ ደህንነት፣ ጤንነትንማስጠበቅ እና የሕግ


ተፈጻሚነትን ማረጋገጥ

የሚከናወኑ ዋናዋናተግባራት

በከተማው በሚገኙ ሁሉም (100%) ድርጅቶች የሥራ ቦታ ምዝገባ ማካሄድ፤


 በድርጅቶች የሥራ ሁኔታ ቁጥጥር አገልግሎትን መሰረታዊ የሥራ ሁኔታ የተፈጻሚነት
ደረጃቸውን 90% ማድረስ፤
 በድርጅት ሥራ ላይ አደጋንና በሥራ ምክንያት የሚመጣ የአካል ጉዳት እና የጤና
እክልን 100% መከላከል፤
 በስራ ስምሪት ላይ ላሉ ለሁሉም ሰራተኞች በፍ/ቤት ደረጃ ህጋዊ ከለላ እንዲያገኙ
ማድረግ፤

ግብ 5. ፍትሃዊ እና ዘመናዊ የሥራ ስምሪትና የሥራ ገበያ መረጃ አገልግሎቶችን


ማስፋፋት

የሚከናወኑ ዋናዋናተግባራት

በአገር ውስጥ የሥራ ስምሪት ድጋፍ አግኝተው በሥራ ላይ የሚሰማሩ ዜጎችን ቁጥር

በየዓመቱ በአማካይ አሁን ከደረሰበት 42173 ወደ 62108 ማሳደግ፣


 የውጭ አገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን አሠራር በተመለከተ በዕቅድ ዘመኑ
20 አዲስ ፈቃድ መስጠት እና ማደስ፤

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በህገ-ወጥ ደላሎች (አዘዋዋሪዎች) ክትትል በማጠናከር በህግ ተጠያቂ በማድረግ

እንቅስቃሴያቸውን በመግታት ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን 95% መከላከል፤

 ከስደት ተመላሽ ዜጎች ውስጥ 80 % መደገፍና በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም

 የመልካም አስተዳደር ዘርፍ

በተጠናቀቀው የዕቅድ ዘመን በሚፈለገው ደረጃ ያልተሳካው እና የህዝቡ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ


የወጣው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት በዚህ የዕቅድ ዘመን የህዝቡን
የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ በዚህም መሠረት ቀዳሚው
ጉዳይ በመንግስት ሥራዎች የህዝቡን የተደራጀ ተሳትፎ ማረጋገጥ ነው፡፡ በመንግስት ሥራዎችና
አገልግሎት አሰጣጥ የህዝብ ተሳትፎ ማረጋገጥ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን ለማዳከም፣
ፍትሃዊነትን፣ ግልፅነትና ተጠያቂነትን፣ እንደዚሁም ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ትልቅ አቅም
ይሆናል፡፡ በመሆኑም የተጀመረው የህዝቡ የተደራጀ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል፡፡

የመንግስት መ/ቤቶች በየደረጃው የህዝብ ክንፍ በማደራጀት የህዝቡንና የባለድርሻ አካላትን


በዕቅድ ዝግጅትና ትግበራ፣ በአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ የህዝቡንና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ
በማሳደግ እና ከህዝብና ከባለድርሻ አካላት ግብረ-መልስ በማሠባሠብ ችግር የመልካም አስተዳደር
ችግሮች በፍጥነት እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ የህዝብ ተሳትፎው ተፅዕኖ የሚያሳርፍ እንዲሆን የህዝብ
ክንፎችን አቅም የመገንባት ሥራ ይከናወናል፡፡ የተሳትፎ ግንኙነቶቹና መድረኮቹ በዕቅድ የሚመሩ፣
ውጤታማ እና ተጠያቂነት ያለባቸው እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ እስካሁን የተሰራውን የተደራጀ የህዝብ
ተሳትፎ የማረጋገጥ እንቅስቃሴ ግምት ውስጥ በማስገባት በዕቅድ ዘመኑ ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ
በመፍጠር በመልካም አስተዳደር እመርታ ለማምጣት ታቅዷል፡፡ ከዚህ አንፃር በዕቅድ ዘመኑ
ሁሉም አካላት በሥራዎቻቸው ዙሪያ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማስፈን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሆኖም ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን መታገል ልማታዊ ኢኮኖሚ በማስፈን ረገድ ትልቅ ትርጉም
ያላቸውን ዘርፎች መንግስት ልዩ ክትትል ለማድረግ ግልፅ ግብ አስቀምጧል፡፡ እነዚህ ዘርፎች
በተጠናቀቀው የዕቅድ ዘመንም ተለይተው የነበሩ ሲሆን በያዝነው የዕቅድ ዘመን መሰረታዊ ለውጥ
እንዲታይባቸው ርብርብ የሚደረግባቸው ይሆናሉ፡፡

ከዚህአኳያባለፈው አስር አመታት በመሬት ልማት ማኔጅመንት እና አስተዳደር፣በገቢዎች


የግብር አሰባሰብ፣በፋይናንስናግዥ ፤በንግድ ውድድር ና ኢንቭስትመንት መሳብ እና ሌሎች
ተቋማት በነበሩ ሙስናን እና ብልሹ አሰራር የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት
የበለጠ በጥልቀት የሚፈተሽ ይሆናል ፡፡

የተጀመረው የከተማ ልማት ፕሮጀክት እና ካዳስተር መሬትና በመሬቱ ላይ ያለውን ንብረት


በዘመናዊ መረጃ ሥርዓት የመመዝገብና የማወቅ፣ በመሬቱ ላይ ማን ምን መብት እንዳለው
የተሟላና ወቅታዊ መረጃ የመያዝ፣ሕጋዊ ዕውቅናና ጥበቃ እንዲያገኝ የማድረጉ ሥራ ሙሉ በሙሉ
ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በዚሁ መረጃ ላይ በመመስረት መሬት ይበልጥ ልማታዊ በሆነ መንገድ ጥቅም

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ላይ እንዲውል በዕቅድ የሚመራ የመሬት ልማት ማኔጅመንት እና አቅርቦት ሥርዓት እንዲኖር


ይደረጋል፡፡

የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን የማሻሻል ሥራ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ የግብር ከፋዩ
ገቢና ሀብት በትክክል የሚታወቅበት፣ ህጋዊ ዕውቅናና ጥበቃ የሚያገኝበት ዘመናዊ የመረጃ
ሥርዓት ይጠናከራል፡፡ የሽያጭ ማሽኖችን መጠቀምና ግብይት የማካሄድ ሥራ በሁሉም የንግድ
ማህበረሰብ አካላት ተግባራዊ ይሆናል፡፡ በዚህ መረጃ ላይ በመመስረት ፍትሃዊ የታክስ አስተዳደር
ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ግብር ከፋዩን የማስተማርና በመጨረሻም በህዝቡ ተሳትፎ የታጀበ
ፈጣን የህግ ማስከበር ሥራ በማከናወን በኪራይ ሰብሳቢዎች ላይ ፈጣን ተጠያቂነት ይረጋገጣል፡፡
በተለይም በከተማችን የኢንዱስትሪ መንደሮች ከተሟላ መሠረተ ልማት ጋር የሚቀርቡበት ሁኔታ
ይመቻቻል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ ሙስና እና ብልሹ አሰራሮች እንዲከስሙ ለማድረግ
ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡ እንደዚሁም የግብይት ሥርዓቱ ግልፅነትና ውድድር የሰፈነበት እንዲሆን
የወጣው የንግድ ሪፎርም ተሟልቶ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

የንግድሥርዓትንበመፍጠርምርታማነትንናተወዳዳሪነትንለማጎልበትበንግድምዝገባናፈቃድአገልግሎ
ትአሰጣጥስር-ነቀልለውጥይካሄዳል፡፡

በአጠቃላይ የታክስ አስተዳደር፤ የመሬትና የንብረት መረጃና የንግድ እንቅስቃሴ መረጃ ሥርዓት
መፍጠር በኢኮኖሚና በፖለቲካው መስክ ግልፅነትና ተጠያቂነትን በማስፈን ረገድ የሚጫወተውን
ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት ሥራው በሚቀጥሉት አስር ዓመታት በተሳካ ሁኔታ ዳር
እንዲደርስ ልዩ ትኩረት ይደረጋል፡፡

በቀጣይ አስርዓመታትየወሳኝ ኩነቶች (የልደት፣የሞት፣የጋብቻእናፍችወዘተ) በመመዝገብ እና


የም/ወረቀት ባለቤት በማድረግ ትክክለኛ የህዝብ ብዛት መረጃ የሚታወቅበት እና
እድሜያቸው 18 እናከዚያበላይለሆኑዜጎች የብሔራዊመታወቂያእንዲኖራቸውይደረጋል፡፡ይህም
በመሆኑ የዜጐች ማንነት ለማወቅ እና በህዝብ ቁጥር መረጃመሰረት የሚገኙ ከተማችን
የኢኮኖሚ፤ማህበራዊ እና ፖሊቲካዊ ልማቶች ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል፡፡

በፋይናንስና ግዥ ዙሪያ የሚታየውን ብልሹ አሰራሮች ለማቀነስ የተነደፉት ማሻሻያዎችን


በቁርጠኝነት ለመተግበር የሰው ሃይሉ የአመለካከትና የሙያ ብቃት ተቋማዊ በሆነ የሥልጠና
ሥርዓት እንዲገነባ ይደረጋል፡፡ ሌላው በውስጥ እና በወጪ ኢድት ድጋፍ ና ክትትል አግባብ
የሚመለከታቸው አካላት ማስተካከያ እርምጃ መውሰዳቸውን ቁጥጥር ይደረጋል እንዲሁም
ተጠያቂነት ይረጋገጣል፡፡ በአጠቃላይ የፋይናንስ፣ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ ብልሹ
አሠራሮች ሲከሰቱም ፈጣን ተጠያቂያነት የሚያሰፍን የአመራር ቁጥጥር ይረጋገጣል፡፡

በዕቅድ ዘመኑ ሙስናንና ብልሹ አሰራር ለመከላከልና ለመቆጠጠር ተቋማዊ አቅምን የማሳደግ ስራ
ይሰራል፡፡ ከዚህ አንጻር በከተማችን የስነ-ምግባር መከታታያ ክፍል በማቋቋም ፤በማጠናከር እና
አቅም በመገንባት ሌሎች አካላትን የማስተማርና የማነሳሳት ብሎም በተደራጀ አግባብ መልካም
ስነ-ምግባር ተላብሶ የስነ ምግባር ችግር ያለባቸው እና ሙሰኖችን እንዲታገል የማስተባበር
ተግባር ይከናወናል፡፡

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በመንግስት ተቋማት ውስጥ ሙስናና ብልሹ አሰራሮች እንዳይከሰቱ ለመከላከል ከተከሰቱም


አስፈላጊውን የእርምት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ የአሰራር ሥርዓት ጥናቶችና የትግበራ
አፈጻጸም ክትትሎች ተጠናክረው ይካሄዳሉ፡፡

በተለይም ለሙስናና ብልሹ አሰራሮች ይበልጥ ተጋላጭ በሆኑት በመንግስት ግዥና ፋይናንስ
አስተዳደር ስርዓት፣ በመሬት ልማት ማኔጅመንት እና አስተዳደር፣ እንደዚሁም በፍትህ ሥርዓት
አስተዳደር ላይ ያተኮሩ ጥናቶችና ክትትሎች ይደረጋሉ፡፡ ሌላው በመንግስት አሰራር ግልጽነትና
ተጠያቂነትን ለማስፈንና ሙስናን ለመከላከል ከሚረዱ እርምጃዎች አንዱ የህዝብ ተመራጮች፣
የመንግስት ተሿሚዎች እና የሚመለከታቸውን የመንግስት ሰራተኞችን ሃብት መመዝገብና ማሳወቅ
ሲሆን እስካሁን የተሰበሰበውን መረጃ በተሟላ ሁኔታ በማደራጀት ከሙስናና ብልሹ አሰራሮች
ለተያያዙ የምርመራና የክስ ሥራ በተሟላ ሁኔታ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን በሙስና
የተዘፈቁትን ወንጀለኞች ለፍርድ በማቅረብ የጥፋተኝነት ውሳኔ እንዲያገኙ ለማድረግ እየተከናወነ
የቆየውን ሥራ አጠናክሮበ መቀጠል የመንግስትና የህዝብ ሀብትና ንብረትን የማስመለስ ሥራ
ይሰራል፡፡ ሙስናንና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ጉዳይ የሁሉንም የልማት ኃይሎች፣ በተለይም
ደግሞ የአመራሩ ቀጣይነት ያለው ትግልና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ በመሆኑ በቀጣይ ከፍተኛ
ርብርብ ይደረጋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ለመልካም አስተዳደር መስፈን ዋና መሳሪያ የሆነውን የግልፅነትና ተጠያቂነት


ሥርዓት ለመዘርጋት በሚቀጥለው የዕቅድ ዘመን በሁሉም የመንግስት ተቋማት የዜጎች ቻርተርን
እና የአገልግሎት ስታንዳርድ በተሟላ ሁኔታ እንዲዘጋጅና በተለያዩ መንገዶች ህዝቡ በይፋ
በስፋት እንዲያውቀው በማድረግ የመንግስት ተቋማት ግልጽነትና ተጠያቂነት የበለጠ
ይጎለብታል፡፡ በቀጣይ በዚህ መሰረት በአጭር፤ በመካከለኛ እና በረጅም እቅድ ለይቶ የመልካም
አስተዳደር እቅድ በማዘጋጀት ችግሮች ይፈታሉ፡፡

 ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽ ቴክኖሎጅ ልማት ዘርፍ

የቴክኖሎጅ መሰረት ልማት አጠቃቀም ማጎልበት

የቴክኖሎጂ ልማትና ትግበራ ከሚለካባቸው ቁልፍ አመላካቾች ውስጥ የቴክኖሎጂ መሰረተ


ልማትና የአሰራር ስርዓት ሽፋንን ማሳደግ አንዱ ነው።የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና
የአሰራር ስርዓት ሽፋንን ማሳደግ በየደረጃዉ የመረጃ ቅብብሎሽን ሊያሳልጡ የሚችሉ ስራን
ያካትታል፡፡
የከተማ አስተዳደሩን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር ቁልፍ ተግባር በመሆኑ
በምርምርና ጥናት የተለዩ ቴክኖሎጂዎችን የማልማት፣ የማሸጋገርና ጥቅም ላይ የማዋል ስራዎች
የሚሰሩ ይሆናል፡፡

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በየደረጃዉ ካሉ መስሪያ ቤቶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የግል ተቋማት፣ የተለያዩ ማህበራትና


የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር የትብብርና የቅንጅት ስራዎችን በመስራት የአቅም ማጎልበት ስራዎችን
እና የአሰራር ስርዓት ተሞክሮዎችን እና ቴክኖሎጂዎችን ለማግኘት የሚያስችል የአሰራር ስርአት
ይዘረጋል፡፡

የድህረ ገጽ ልማት በመፍጠር አጠቃቀም ማሳደግ


በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት የከተማ አስተዳደሩን ብሎም የከንቲባ
ጽ/ቤት አገልግሎቶች በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ለተጠቃሚዎች ባሉበትእንዲዳረስ ለማድረግ፣በመሰረተ
ልማት ግንባታ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ለማስቻል፤ ለምርምርና ቴክኖሎጂ ልማት አገልግሎት
የሚውሉ አዳዲስ መረጃዎችን ለመጫን፣ ለማሰራጨት የማደራጀትና ተደራሽ ለማድረግ የድህረ
ገጽ ልማት በመፍጠር የሚሰራ ይሆናል፡፡

199 P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

5.4.2.4 አስተዳደርና ፍትህ ልማት ዘርፍ


የፍትህዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ
ውጤታማ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ፣ አሣታፊና ሚዛናዊ ግልፅና ተጠያቂነት ያለበት የፍትህ
ሥርዓትን በማረጋገጥ ንፁሐንን በመጠበቅ ወንጀለኞችን በማስተማርና በማስቀጣት ህገ
መንግሥታዊ ሥርዓቱን በማክበርና በማስከበር የህግ የበላይነትን ማረጋገጥና የተገልጋዩን
እርካታ ማጠናከር እንዲሁም በውጤታማ የፍታብሔር ሥርዓት የመንግስትንና የሕዝብን
መብትና ጥቅም ማስከበር እና በአጠቃላይ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበትና ለልማትና
መልካም አስተዳደር ተግባሮች መፈፀም ምቹነት ያለው እንዲሆን ማድረግ ነው።
ዓላማ፡- ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር በመፍጠርና የተደራጀ የሕዝብ
ተሣትፎን በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ በማረጋገጥ በከተማዉ ውስጥ ኪራይ ሰብሣቢነትን
በጽናት መታገል፣ መልካም አስተዳደርን በማረጋገጥ ንፁሀንን መጠበቅ፣ በፍትሐብሄር
ጉዳዮች የመንግስትና የህዝብን መብትና ጥቅም ማስጠበቅ ነው።
ግብ 1፡- ከፍትህ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታወ አሰራርን በማሳደግ፣የሙስና እና
የብልሹ አሰራር ተግባራትን በመታገል የግልጽነትና ተጠያቂነት አሰራርን ማጎልበት፣
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
በከተማ አስተዳደር ያለውን የፍትህ ስርዓት አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የፍትህና የፖሊስ የጋራ
ኮሚቴ፣ የኦዲት ግኝቶች ስትሪንግ ኮሚቴ፣የሰብዓዊ መብት የድርጊት መርሃ-ግብር ኮሚቴ፣
ህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ተከላካይ ግብረኃይል እና ሌሎች የክላስተር አደረጃጀቶች
ተልዕኳቸውን ማሳካት በሚችሉበት ደረጃ ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣

ውስብስብ የሆኑ የሕዝብንና የመንግስትን ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚጎዱ ወንጀሎችን


በጋራ በክትትልና በቅንጅት መስራት፣
በፍትሐብሄር ጉዳዮች ውል አያያዝና አስተዳደር፣ የመንግስት ንብረት አስተዳደር፣መረጃ
አሰባሰብና ፍርድ አፈጻጸም ከመንግስት መ/ቤቶች ጋር የጋራ ምክክር መድረክ መፍጠር
የግልጽነትና ተጠያቂነት፣ የእኩልነትና ፍትህ የማግኘት መብቶች በመለየት መከበራቸውን
ማረጋገጥ፣
የህግና ፍትህ ኢንስፔክሽን /Legal Auditing/ ስራ በማካሄድ በግኝቱ መሠረት
ስህተቶችን ማረም፤

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ግብ 2 ፡- ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል፣ የፍትህ ስርዓትን በማረጋገጥ ንፁሐንን በመጠበቅ


ወንጀለኞችን በማስቀጣት የከተማዉን ህብረተሰብ በፍትህ አስተዳደሩ ላይ ሊኖረዉ
የሚገባዉን አመኔታ እንዲጨምር ማድረግ ፣
በወንጀል የቀጥታ ክስ መዝገቦች የዓ/ህግ ተከራክሮ የማስቀጣት አቅም 100% ማሣደግ፣
ልዩ ትኩረት በሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የወንጀል መዝገባት የማስቀጣት ምጣኔን እና
የፍርድ ውሳኔዎችን የማስፈጸም አቅምን 100% ማሳደግ፤
 በህግ ጥላ ሥር የዋሉ ሰዎች በህግ የተቀመጠላቸው መብት መከበሩን መከታተልና
ማረጋገጥ፣
 የተከሣሽና ምሥክር አቀራረብን በማጠናከር የክስ መቋረጥ ምጣኔን ከ 3.8% ወደ 1
በመቶ መቀነስ፣
 የወንጀል አቤቱታ አቀባበል፣ ውሣኔ አሠጣጥና የአቤቱታ ተፈጻሚነት 100%
ማድረስ፣
 ተደጋጋሚ አቤቱታ የሚቀርብባቸው ጉዳዮች እና አካባቢዎችን በመለየት የችግሩን
መነሻ አውቆ መፍትሄ መስጠት፣

ግብ 3፡- በፍትሐብሄር ፍትህ አስተዳደር ጉዳዮች የመንግሥስትንና የህዝብን መብትና ጥቅም


ማስጠበቅ፣
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
በፍትሐብሄር ጉዳዮች የቅድመ መከላከል ስራን በማጠናከር የመንግስትና የህዝብን ሀብትና
ንብረት ከብክነት መከላከል፤
በፍትሐብሄር ከሚያዙ ጉዳዮች ውስጥ 40 በመቶውን በድርድር በመጨረስ የጊዜና
የገንዘብ ብክነትን መቀነስ፣
ጉዳዩ በድርድር ካለቀ በፍ/ቤት ያለው ክርክር እንዲቋረጥ ለፍ/ቤት መሳወቅና መዝገቡን
ማዘጋት፣
መዝገብ የማጥራት አቅምን በመዛግብት 99.47% በገንዘብ 95.47% የነበረዉን በሁለቱም
ወደ 100% ማድረስ
 በፍትሐብሄር ጉዳዮች የዓ/ህግ ተከራክሮ የማሸነፍ አቅም ወደ 96%ማሳደግ፤
 ተገቢ ያልሆነ ዉሳኔ በተሰጣቸዉ ጉዳዮች በወቅቱ ይግባኝ በመጠየቅ ዉሳኔዉ
እንዲታረም ማድረግ፤

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

 ክስ በቀረበባቸውጉዳዮች አስቀድሞ ንብረት ፈልጎ ማሳገድ በመዝገብ 95% በገንዘብ


80% ማድረስ
ግብ 4፡-ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሆነ የሠነዶች፣በጎአድራጎት ድርጅቶች፣ማህበራት እና
ጠበቆች ማረጋገጥና ምዝገባ አገልግሎት ስርዓት በመዘርጋት ዜጎች በቅርብና በአነስተኛ
ወጭ አገልግሎት የሚያገኙበትን ሁኔታ መፍጠር፣
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
ሰነዶች ከመመዝገባቸው በፊት በተለያዩ ተቋመት የሚቀርቡ ሰነዶች ለህግና ለሞራል
የማይቃረኑ መሆናቸውን በአግባቡ በመመርመር ህጋዊና ጥራት ያለው ሰነድ አዘጋጅቶ
መስጠት፣
የሠነድ ምዝገባና ማረጋገጥ ጥራትን 100% ማድረስ፣
የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትን ፍቃድ መስጠት፣ ማደስ፣ ክትትልና ቁጥጥር
ማድረግ፣
ጠበቆች በአመለካከት በክህሎት እና ሥነ-ምግባር ዳብረው ለፍትህ ስርዓትአጋዥ
እንዲሆኑ ማድረግ
ጠበቆች ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የሕግ ድጋፍ አንዲሰጡ
ማስቻል፣

 የኮሙኒኬሽን ተግባራት /የተጠናከረ ቁልፍ የህዝብ ግንኙነት ተግባር


መፈፀም/ ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ
የተደራጀ የመንግስት ኮሚኒኬሽን፣ ኢንፎርሜሽንና የሚዲያ የልማት ሠራዊት በመገንባት
እና የተጠናከረ የቃል አቀባይነት ሚናን በመወጣት በዕቅድ ዘመን የተነደፉ ፕሮግራሞችንና
የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ የለውጥ መሣሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ማድረግ ሲሆን በዚህ
ውስጥ ዋነኛ የትኩረት አጀንዳዎች የከተማዉ ሕብረተሰብ በፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች፣
በህግ ማዕቀፎች፣ የለውጥ ፕሮግራሞች ግልፅነት እንዲኖረውና የጠራ አመለካከት ይዞ
እንዲቀጥል ማድረግ ነው፡፡ በሌላ በኩል የከተማዉ ታሪክ፣ ባህል እና እሴቶች እንዲታወቁና
እንዲያገለግሉ የሚያስችል ሁኔታ መፍጠር፣ ገፅታ መገንባት፣ የተነደፉ የልማት፣ የሠላም፣
የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ግንባታ ሥርዓት ውስጥ አጠቃላይ መግባባት ተፈጥሮ
እንቅስቃሴ እንዲደረግ ማድረግ ነው፡፡
ዓላማ፡- ዘላቂነት ባለው የኮሚኒኬሽን ሥራ በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ መግባባት ፈጥሮ
በሠላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳዳር ፕሮግራሞች ውስጥ የራሱ ሚና የሚጫወት

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ለሀገሩና በብሄራዊ ጥቅሞቹ ላይ በምክንያታዊነት ብያኔ የሚሰጥና በመረጃ የረካ


ማሕበረተብ መፍጠር የሚችል አቅም መገንባት፡፡
ግብ 1፡-የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮችአማካኝነት ስለ ከተማችን ሁለንተናዊ የገጽታ
ግንባታ በመፍጠር የከተማዉን ህዝብ አመለካከት ማጎልበት
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
በወቅታዊና ወሣኝ ጉዳዩች ላይ የመንግስትን አቋም የሚንፀባርቁ(የአቋም መግለጫ)
ጽሁፎች በማዘጋጀትና በሚዲያዎች በማቅረብ ግንዛቤ መፍጠርና የህብረተሰቡን ተሳትፎ
ማሳደግ፣
በወሣኝና ወቅታዊ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ የፓናል ዉይይት ማካሄድ፣
በተመረጡ ወቅታዊ ጉዳዩች ላይ የፕሬስ ኮንፈረንስ /የሚድያ መግለጫ /በማካሄድ
የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ፣፣
ወቅታዊ ጉዳዮችን፣ ህዝባዊና መንግሥታዊ በዓላትን፣ ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን
በበቂ ሁኔታ በመዳሰስ ዶክመንተሪ ማዘጋጀት
ሁነቶችን በመፍጠር በሚገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለህዝቡ አስተማሪ የሆኑ መልዕክት ፣ሞቶ
፣ ቋሚ የፎቶ ኤግዚብሽን ፣ ተንቀሳቃሽ የፎቶ ኤግዚብሽን አዘጋጅቶ ለህብረተሰቡ
መረጃዎችን ማስተላለፍ
የሚዲያ ሽፋን ለሚያስፈልጋቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ለሚዲያ አካላት በተደራጀ ሁኔታ
የሚዲያ ዘገባ ጥቆማ የመስጠት ስራ ይሰራል፡፡
ግብ 2 ፡- ህብረተሰቡን ለልማት የሚያነሳሱ የሚድያ ዉጤቶችን ተደራሽነት ማሳደግ
ቴክስት /የጽሑፍ /ዜናዎችን በማዘጋጀት በፌስቡክ እና በሌሎች የሜይንስትሪንግ
ሚድያዎች መረጃዎችን ለህብረተሰቡ ማድረስ፣
የምስል ዜናዎችን ማዘጋጀት እና በተለያዩ የሜይንስትሪንግ ሚድያዎች ማስተላለፍ
ለአካባቢ ማስተማያ የሚዉል የቴሌቴቪዥን ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት በቲቪ ፓርክ
ማስተላለፍ፣
በማህበራዊ በኢኮኖሚያዊ በፖለቲካዊ ጉዳች ዙሪያ ከተዘጋጁ የምስል ዜናዎች
፣ፕሮግራሞች እና ዘጋቢ ፊልሞች ለዩቲብ የሚሆኑ መረጃዎችን ለይቶ በማዘጋጀት
መረጃዎችን ማስተላለፍ፣
አካባቢያችን እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተሬዲዮ ፕሮግራም ማዘጋጀትና
ማስተላለፍ፣

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በአካባቢያዊ ሚድያዎች አማካኝነት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽንና የሚድያ አሰራሮችን


ብቃት በማጎልበት 10 አድስ ሚኒ ሚድያ፣40 አድስ ማስታወቂያ ሰሌዳ፣ 20 አዳድስ የመረጃ
ማእከላትን እና 10 አዳድስ የቲቪ ፓርክ ማቋቋም እና ማስፋፋት ፤

 ከንቲባ አገልገሎት ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ
በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ በማድረግ
ከአቅም በላይ የሆኑትን በከንቲባ ኮሚቴ በማስወሰን ተፈፃሚነታቸዉን
መከታተል፣የሙስናናብልሹ አሰረሰር መከላከል የሚያስችል የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት
የመንግስትና የህዝብ መብትና ጥቅም ማስከበር ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የመረጃ
አያያዝ፣የህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል።
ዓላማ፡- ብልሹ አሰራርና ሙስናን በተሟላ ሁኔታ ለመከላከል የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት
መዘርጋት ፣ህብረተሰቡና አጋር አካላት የማይተካ ሚናቸውን እንዲወጡ ማድረግና
የተጠናከረ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን መገንባት ።
ግብ 1፡- የሀብት ምዝገባ ማሳወቅ መረጃ በማደራጀት ፤በመመዝገብ እና የህግ ማእቀፍ
ተግባራት አፈጻጸም በማሻሻል የሥነ ምግባር አውታሮችን በማጠናከር ሙስናና የሥነ ምግባር
ጥሰት የመከላከል ስርአትን ማሳደግ፣
የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት
የሀብት ምዝገባ የማሳወቅ መረጃ የማደራጀት መመዝገብና የህግ ማእቀፍ ተግባራት
አፈጻጸም ማሳደግ፣
ብልሹ አሰራርና የሥነ-ምግባር ጥሰትን የሚመለከቱ ጥቆማዎችና ቅሬታዎች ተቀብሎ
የማስተካከል ስራ ትኩረት በመስጠት ማከናወን፡፡
የሥነ-ምግባር የሚመለከቱ ህግጋት፣ ደንቦች እና መመሪያዎች የመከታተልና የማማከር
ተግባራትን ማሳደግ ፣
የሥነ-ምግባር አውታሮችን ማደራጀት
በሙስና የተመዘበረ ሀብት ፈጥኖ እንዲታገድ ማድረግና የማስመለስ ሥራ መሥራት፣
ለምስክሮችናጠቋሚዎች ከለላ እንዲያኙ ማድረግ፣
ግብ 2፡ ለከተማዋ ልማት እና እድገት የሚስፈልጉየአጀንዳና ውሳኔ ዝግጅት ስራዎችን
ማጠናከር

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ለካቤኔ ቀርበዉ የሚወሰኑ መደበኛ እና አስቸኳይ አጀንዳዎች ለዉይይት ብቁ እና የበሰሉ


መሆናቸዉ ተጣርቶ በመስፈርቱ መሰረት እየተገመገሙ እንዲያልፉ ማደረግ ፣
ዉሳኔዎችንም በማዘጋጃት በወቅቱ ለሚመለከታቸዉ አካላት ማሰራጨት፡
የካቢኔ ስብሰባን በዲጅታል ድምጽ ሪከርድ በመቅረጽ የእያንዳንዱን ስብሰባ መረጃዎች
በሲዲ በመገልበጥና የተወሰኑ ዉሳኔዎች ተፈጻሚነት ማሰደግ ፡፡
ግብ 3፡- የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሽፋን እና ጥራት በማሻሻል የመረጃ አጠቃቀም ማሳደግ፡
በሁሉንም የተከሰቱ ኩነቶች የወቅታዊ/ዘገየ/ ምዝገባ አፈጻጸም በአማካይ ወደ 70 %
ማሳደግ
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጥራት ለማስጠበቅ በከተማችን ወቅታዊ፣ ምሉዕ፣ ትክክለኛ
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ በማካሄድ ቅጽ ብልሽት ና ተመላሽን ዜሮ ፐርሰንት ማድረስ
ከጠቅላላ ወቅታዊና የዘገየ ምዝገባ ውስጥ በጤና ማሳወቂያ ልደት 100% እና ሞት
ደግሞ 50%እንዲመዘገብ ማስቻል
ኩነትን ላመስመዘገቡ ግለሰቦች ምስክር ወረቀት በመስጠት በኩል 100% ማድረስ
የክብር መዝገብ ሚሰጥርነት እና ደህንነት መቶ በመቶ ማስጠበቅ
ግብ 4፡-የከተማዉ ልማት በእቅድ እንዲመራ በማድረግ ወጥ የሆነ የእቅድ አዘገጃጀት እና
ሪፖርት አቀራረብ ስርአትን ማስፋት
የልማት ስራዎችን መሰረት በማድረግ በከተማ አስ/ መምሪያዎች የሚዘጋጁ የልማት መነሻ
ዕቅዶች በማሰባሰብ ሊያሰራና ሊተገበር የሚችል ተመጣጣኝ ዕቅድ በማዘጋጀት በም/ቤት
ፀድቆ ስራ ላይ እንዲዉል ማድረግ፣
 የሚቀርቡ የካፒታል ፕሮጀክቶችን ከከተማዉ ልማት ጋር የተገናዘቡ መሆናቸዉን
በመመርመር ለሚመለከታቸዉ አካላት ማቅረብ እናፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸዉ ጊዜና በጀት
ስለመፈፀማቸዉ ክትትል ማድረግ፣
ግብ 5፡-ዘመናዊ የስነ ህዝብ ና ሶሾዮ ኢኮኖሚ መረጃ ተደራሽነት እና ተጠቃሚነት ማሳደግ
ለዕቅድ ዝግጅት ግብዓት የሚሆኑ የስነ-ህዝብ ትንበያዎችን/የህዝብ ብዛት
/መረጃዎችን በእድሜ ክፍፍልና በፆታ በመለየትእና በማጠናቀርለተጠቃሚዎች
ተደራሽ ማድረግ፣
የስነ-ህዝብ ምክር ቤት እንዲቋቋም እና እንዲጠናከር ማድረግ ፣
ሴክተር መ/ቤቶች የስነ ህዝብ ጉዳዮችን በልማት እቅዳቸዉ ዉስጥ አካተዉ
እንዲያቅዱና በእቅዳቸዉም መሰረት እንዲፈፅሙ ማድረግ ፣

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ግብ 6፡- በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ያሉ ችግሮችን ለይቶ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ


ልማትን ማሳደግ
የታቀዱ እቅዶችና ውሳኔዎችን አፈጻጸማቸውን በቼክ ሊስት በተደገፈ የክትትልና ድጋፍ
በማጠናከር ለከተማዋ ፈጣን ኢኮኖሚዊና ማህበራዊ እድገት የማምጣትና ህብረሰተሰቡን
ተቃጠሚ እንዲያደርጉ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ፣
በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ የሚሰሩ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በማስተሳሰርና
በማቀናጀት ተናበው እንዲሰሩ ሃብትን በአግባቡ በመጠቀም ለህብረተሰቡ ተደራሽ መሆን
እንዲችሉ ስራዎች ሳይቆራረጥ የማስተባበርና የማቀናጀት ስራ መስራት ፣
በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚ ሴክተሮች አሁን በስራ ላይ ያለውን
አዋጅ ደንብና መመሪያ ተግባራዊና እየተሰራባቸው መሆኑን በማረጋገጥ በተጨማሪም ህግ
እንዲወጣላቸው የሚያስፈልጋቸው አሰራሮች ካሉ በማጥናት መረጃ በማሰባሰብ ለበላይ
አካል በማቅረብ ስራ ላይ እንዲውል ማድረግ ፣
እንዲጣሩና የውሳኔ ሃሳብ እንዲቀርብባቸዉ የሚያስፈልጉ የመንግስትና የግለሰብ
ጉዳዮችን ህግና መመሪያ በሚፈቅደው መሰረት በጥራትና በጥንቃቄ በማጣራት
የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ ፣
በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ለግለሰቦች እና ለስራ አስፈጻሚ የማማከር አሰራርን
ማሻሻል

 የህዝብ ቅሬታሰሚ ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ
በዜጎች ላይ ሚደርሰዉን የአገልግሎት አሰጣጥ እና መለካም አስተዳደር ችግር እንዲፈቱና
የሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎች ደረጃዉን ጠብቀዉ እንዲቀርቡ ፣የቅሬታ ማስተናገጃ
ስርዓት በመዘርጋት በአዋጃ፣ደንብና መመሪያ መሰረት እንዲፈፀም በማድረግ በህግ
ተሰጣቸዉን መብት ማስከበር
ዓላማ፡- በቅሬታ ማስተናገጃ የወጡ ደንብ እና ህጎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በማስፋት ፤የቅሬታ
መረጃዎችን በዘርፍ በመለየት፤ፈጣን እና ፍትሃዊ ውሳኔ በመስጠት የህዝብ ቅሬታ መፍታት

ግብ 1፡-የህዝብ ቅሬታ ሰሚ አሰራር ስርአትን በማሻሻል የሚነሱ የመልካም አስተዳደር


ችግሮችን መቀነስ

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

ወደ ከተማ አስተዳደሩ የሚመጡ ባለጉዳችን ተቀብሎ በማስተናገድ እና አቤቱታዎችን በማጣራት


ፍትሃዊ ዉሳኔ መስጠትና የተወሰኑ ዉሳኔዎች አፈጻጸም እና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ሁኔታን
ማሳደግ ፣
በህብረሰቡ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ደረጃቸዉን ጠብቀዉ ከታችኛዉ የአስተዳደር እርከን
እንዲነሱ ማድረግ ,
ለህዝብ ቅሬታ ሰሚ ቀርበዉ የሚታዩ አቤቱታዎች ዉሳኔ ከመሰጣቸዉ በፊት
ማብራሪያዎችን ከሚመለከተዉ አካል በመጠየቅ እና በመስክ ጉዳዩን የመመርመርና
የማጣራት ስራ በመስራት ተገቢዉን ዉሳኔ መስጠት፣
 የማህበራዊ አሃዝ ካርድ አሰራር ስርዓት በዉጤታማነት በመስራት ቅሬታዎች በተነሱበት
የአስተዳደር እርከን እንዲያልቁ የማድረግ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር፣
ተከታታይነት ያለዉ የአገልግሎት አሰጣጥ ፍተሻ ማካሄድ ፣
የመልካም አስተዳደርጥያቄዎችንናቅሬታዎችንበየደረጃውባለውአካልበቅንጅት 100%

እንዲፈቱማድረግ

 ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ዘርፍ

የትኩረት አቅጣጫ
ሕብረተሰብ አቀፍ በሆነው ባልተማከለ የወንጀልና የግጭት መከላከል ሥርዓት ላይ
የተመሠረተ የመከላከል ሥርዓት በመከተል ወንጀሎችን እና ግጭቶችን መከላከልና
በከተማዉ ውስጥ የፀረ-ሠላም፣ ሀይሎችን እንቅስቃሴ በነቃ የሕዝብ ተሣትፎና ባለቤትነት
መመከት ነው፡፡የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥና በየደረጃው በሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎች
ውስጥ መላ ሕዝቡ ሙሉ አቅሙናን እንዲጠቀም የሚያስችል ዘላቂ ሥርዓት ማረጋገጥና
የደህንነት ዋስትና የሆኑ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ግቦች በተሟላ ሁኔታ
ያለምንም የፀጥታ ሥጋት የሚተገበሩባት ከተማ ማድረግ ነው።
ዓላማ፡-

የሚከናወኑየልማትናየዲሞክራሲግንበታሥራዎችበሁሉምአካባቢያለምንምየፀጥታችግርእን

ዲፈፀሙ በማድረግ የከተማዋን የሠላምናደህንነት ጉዳይ ማረጋገጥ ፡፡

ግብ 1፡-ወንጀሎችን እና ግጭቶችን በመከላከል የፀጥታ ስጋት የሆኑ ኃይሎች ጉዳት

ሳያደርሱ በቅድመ መረጃ ላይ ተመስርቶ 100% በነቃ የህብረተሰብ ተሳትፎ መመከት፣

የሚከናወኑ ተግባራት

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

በአድማወቅትሊፈጠሩየሚችሉጉዳቶችንመቀነስ፣

ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመፅና በነውጥ ለመቀየር የሚንቀሳቀሱ ሐይሎችን

በመረጃ እና ማስረጃ ላይ ተመስርቶ 100% መከታተልናመቆጣጠር፣

የተደረጀ ህገወጥ መሣሪያ ዝውውርን፣ የአመፅና የሁከት እንቅስቃሴዎችን፣ በህገወጥ

የሰወዎች ዝውውር ተሳታ ፊሀይሎችን በመለየት 100% መከላከልና መቆጣጠር፣

በማህበራዊ ድረ-ገጽ የሚሰራጩ አሉባልታዎችን እየተከታተሉ የእርምት እርምጃ 100%

እንዲወስድ ማድረግ፣

በህዝቦች መከካከል አለመተማመን እንደዲፈጠር በማደረግ ግጭት የሚፈጥሩ አካላትን

እና የተደራጁ የዘረፋ እና ቅሚያ ቡድኖችን መለየትና 100% መቆጣጠር፣

የሚካሄዱ ልዩ ልዩ ስብሰባዎች፣ የህዝብ በዓላትና ስፖርታዊ ውድድሮች 100% ያለ ችግር

እንዲጠናቀቁ ማድረግ፣

ግብ 2፡-በከተማዋ ውስጥና ከአጎራባች ዞንና ወረዳዎች መካከል ሰላማዊ ግንኙነትን 100%

ማስጠበቅ፡

የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

የሰላም ኮሚቴዎችን/ የሰላም ምክር ቤቶችን/፣ የሰላም ፎረሞችን ማጠናከር ተግባራዊ

እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ መከታተል፣

በከተማዋ ውስጥና ከአጎራባች ዞንና ወረዳ ሊከሰቱ የሚችሉ የግጭት አመላካቾች

ለመከላከል የቅድመ የ 24 ስዓት የመረጃ ልውውጥን ማሻሻል፣

ለግጭት መንስኤ እንዳይሆን 95% የእርቅና ካሳ ሥራ መስራትና ግጭትን ማስወገድ፣

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በማቋቋምና ነባር የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤን በማጠናከር

ተግባራቸውን እንዲወጡ የድጋፍና ክትትል ሥራ መስራት፡፡


ከአጎራባች ዞኖች እና ወረዳዎች ጋር ትብብር በማጠናከር የመልካም ጉርብትናና
የህዝቦች አንድነትን ማጠናከር
ግብ 3፡- የትጥቅና ጦር መሳሪያ አስተዳደር ስርኣቱን በማጠናከር ለሰላምና ፀጥታ ማስከበር

የሚኖረዉን ሚና ማሳደግ፣

የሚከናወኑ ዋናዋናተግባራት
ለ 520 የመንግስትና ለ 4276 የግል ጦር መሳሪያዎች የፈቃድ እድሳት ማድረግ፣

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የመንግስትና የግል ጦር መሳሪያዎችን በመለየት የአካል ቆጠራ ማድረግ፣


ጥገና የሚያስፈልጋቸዉ የመንግስት ጦር መሳሪያዎች በመለየት ጥገና ማድረግ፣
የጦር መሳሪያ ኦዲት ማድረግ፣
 በኢግዚቢት የተያዙናገቢ እንዲሆኑ የተወሰነባቸዉን ጦር መሳሪያዎች 100% ገቢ
ማድረግ፣
አገልግሎት የማይሰጡ የጦር መሳሪያዎችን በመለየት 100% ማስወገድ፣
የመንግስትና የግል ትጥቅ የሸጡ እና ያጠፉ አካላት 100% በህግ እንዲጠየቁ ማድረግ
ግብ 4፡- ህብረተሰቡን ያሣተፈ የወንጀል መከላከሉን ስራዎችን 100% ማሳደግ
 የኮሙኒቲ ፖሊስንግ ሽፋንና ጥራት በማሣደግ የወ/ል መከላከሉን ስራ 100%
መስራት
 በ 1000 ሰዎች መካከል በአጠቃላይ ወንጀል በገጠር ከ 1.6 ወደ 1.0፣ በከተማ ከ 5.45
ወደ 3.0 እንዲሁም በዋናዋና ወንጀሎች በገጠር ከ 0.6 ወደ 0.5 ፣በከተማ ከ 1.95 ወደ 1.0
ዝቅ ማድረግ፣
 ሞት የሚያስከትል አደጋን በ 10%፣ በትራፊክ አደጋ የሚሞቱ ሰዎችን በ 15% መቀነስ፣
 በግንዛቤ እጥረት የሚደርስ የትራፊክ አደጋ በ 75% መቀነስ፣

 ከተማ ነክ ጉዳዮች ፍ/ቤት ዘርፍ

ግብ ፡-1 ውሳኔ የሚያገኙ መዛግብትን ብዛት መጨመር እና የመዛግብት የማጣራት አቅምን


(Clearance rate) ማሳደግ
በከተማ ነክ ፍርድ ቤቶች የተሻሉ አሰራሮችን በማስፋት፣ የስራ አፈጻጸም ምዘና
ስርአትን በመተግበር፣ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል
ተጨማሪ ዳኞችን በማሾም እንዲሁም የዳኞችን ውሳኔ የመስጠት አቅም ማጐልበት፣
በፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሚሰጥባቸው መዝገቦች ብዛት እንዲጨምር ማድረግ
 በአማካይ ከነበረበት በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት 98% አፈፃፀም ወደ 99%፣ በመጀመርያ
ደረጃ ፍርድ ቤት 96% አፈፃፀም ወደ 98% ከፍ ማድረግ ፡፡
የመዛግብት የማጣራት አቅም በአማካይ ከነበረበት በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት 99%
አፈፃፀም ወደ 100%፣ በመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት 98% አፈፃፀም ወደ 100% ከፍ
ማድረግ ፡፡
ግብ፡-2 የዳኝነት አገልግሎት ጊዜን መቀነስ
ውሳኔዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ እልባት ለመስጠት የሚያስችሉ እርምጃዎች መጠቀም፣

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የምስክር ቃል እና ሌሎች ክርክሮችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን


በተመለከተ በልዩ ችሎት ማስተናገድ፣
ውሳኔ የሚያገኙ መዛግብትና እድሜ ቆይታ መቀነስ
 በቀጠሮ የተላለፉ መዛግብት እድሜ ቆይታ መቀነስ

ክፍል ስድስት

6. በዕቅድ አፈጻጸም ሂደት ታሳቢ የተደረጉ እድሎች፤ ስጋቶችና መከላከያ


ስትራቴጂዎች፤

ባለፉት 10 ዓመታት እቅድ ዘመን ከተገኙት መልካም ተሞክሮዎች መንግስት ከህዝቡና


ከአጋር አካላት ጋር ተቀናጅቶ ባስመዝገባቸው አኩሪ የልማት ተግባራት ከተማችን በፈጣን
የእድገት ጎዳና ላይ እንዲገሰግስ መደረጉ እና ድህነትን ለመቀነስ የተደረገው ሁለንተናዊ
የልማት ርብርብ በህብረተሰብ ዘንድ እና በመንግስት ከፍተኛ የሆነ በራስ የመተማመን
መንፈስ መፈጠሩ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ በሌላ በኩልም በአገር ደረጃ ፋይዳ ያላቸው
ፕሮጄክቶች እንደ የአገር አቋራጭ መንገዶች፣ የባቡር፣ የስኳር ማምረት ፕሮጄክቶች
እንዲሁም የህዳሴ ግድብ መጀመራቸውና ህዝቡም ለፕሮጄክቶቹ ተፈፃሚነት የባለቤትነት
ስሜት እንዲፈጥር በተለያዩ ተግባራቶች እንዲሳተፍ መደረጉ የተጀመረውን ልማት

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

እንደሚያስቀጥል ሙሉ እምነት መፈጠሩ ሊጠቀስ የሚገባው መልካም አጋጣሚ ነው፡፡


ተስፋ ሰጭ ናቸው፡፡
ባለፉት 10 ዓመታት ዕቅድ ዘመን የትግበራ ሂደት ቁልፍ በሆኑ የልማት ጉዳዮች ዙሪያ
ከጫፍ እስከ ጫፍ ከፍተኛ ህዝባዊ መነሳሳትና የጋራ የልማት መንፈስ ተፈጥሯል፡፡ ይኸውም
በሁሉም ዘርፍ በዓይን የሚታዩና በእጅ የሚዳሰሱ አኩሪ የልማት ውጤቶች የተመዘገቡት
ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ሆኖ በተመቻቸ ጎዳና ላይ ሆኖ ሳይሆን በአሠራር ላይ በሚፈጠሩ
መሰናክሎች ላይ አመራሩ፣ ባለሙያውና ህዝቡ በጋራ እየተወያየ ችግሮችን ከስር ከስራቸው
እንዲፈቱ በማድረግ በዋነኝነት ከህዝቡ እንዲሁም ከሁሉም አጋር አካላት ጋር በተፈጠረ
መግባባትና ቅንጅታዊ አሰራርን በመከተላችን የተጎናጸፍናቸው ናቸው፡፡

በሌላ በኩል በሁሉም የገጠር አካባቢዎች ተፋሰስን መሠረት ባደረገው የተፈጥሮ ሃብት
ልማት እንቅስቃሴ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ለአፈርና ውሃ እቀባ ሥራ ያደረገው ርብርብና
ያበረከተው ነፃ የጉልበት አስተዋፅኦ በመሠረታዊነት ሌሎች የሰብል፣ የእንስሳትና የመስኖ
ልማታችን ላይ የማይናወጥ መሠረትን የጣለ ሲሆን ለአፈፃፀሙም በየደረጃው ያለ አመራር
እና ሙያተኛ ህዝቡን አደራጅቶ አወያይቶና አሳምኖ ለልማት ተግባራት በማሰለፉ ምርጥ
ተሞክሮዎች ተገኝተዋል፡፡
በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የዋጋ ንረት መከሰቱ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ የዋጋ
ንረቱ ዝቅ ብሎ በአንድ አሃዝ መቆየቱ የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ የሚፈጥር ስለሆነ በቀጣይ
ባቀድነው የኢኮኖሚ እድገት የስጋት ምንጭ መሆኑ አይቀርም፡፡ በቀጣዩ የእቅድ ዘመን
ከመጀመሪያው የእቅድ ዘመን የአተገባበር ሂደት ብዙ በመማር እንዲሁም ሾልከዉ የቀሩ
ተግባራትን በማካተት በአደገ አስተሳሰብ ኢኮኖሚው ከነበረበት የግብርና ጥገኝነት በጋራ እና
በሰከነ ሁኔታ ከወዲሁ በቂ የሆነ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ወኔያችንን በበለጠ አጠናክረን
የህዝብ ንቅናቄ እንድንፈጥር ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም በሚቀጥሉት አስር ዓመታት መልካም
አጋጣሚዎች/ዕድሎች እንደሚኖሩ የሚጠበቅ ሲሆን በተቃራኒው ስጋቶች እንደሚኖሩ
ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በመሆኑም የዕቅዱ ዘመን ዕድሎች የሚጠበቁ ስጋቶችና የመከላከያ
ስትራቴጅዎች በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
6.1 እድሎች፤ ለውጥ መምጣቱ
ባለፉት 10 ዓመታት እየተመዘገበ የመጣውን የልማት ውጤት ቀጣይነት ለማረጋገጥና
በኢኮኖሚው ውስጥ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል የመንግስት ቁርጠኝነት

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

መኖርና ይህም በተጨባጭ ሥራ ላይ ባሉ አመቺ የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች


የተረጋገጠ መሆኑ፣ ባለፉት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የትግበራ ሂደት ሕዝብን
በማንቀሳቀስ በልማት ሠራዊት አግባብ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች ቀጣዩን ዕቅድ በተሻለ
ለመተግበር ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸው፣ ባለፉት ዓመታት በሁሉም አካባቢዎች በተከናወኑ
የተደራጁና የተቀናጁ የልማት ሥራዎች በኢኮኖሚ ዕድገት፣ በማህበራዊና መሠረተ ልማት
እንዲሁም በልማታዊ መልካም አስተዳደር ከፍተኛና ቀጣይነት ያላቸው ውጤቶች
መመዝገባቸውና በዚህም የከተማችን ገጽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀየረ መጥቷል፡፡ ከዚህ
አንፃር የከተማዉ ህዝብ እየተመዘገበ ካለው እድገት መጠቀም ጀምሯል፡፡ በተለይም ሴቶችና
ወጣቶች እየመጣ ካለው ፈጣን እድገት ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸው፣ ሰፊ ሰሪ ወጣት
የሰዉ ኃይል በመኖሩ በቀጣይም በከተማችን ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድሎች በመኖራቸው
እነዚህን ዕድሎች አሟጦ በመጠቀም በከተማዉ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ርብርብ
ይደረጋል፡፡ በተለይ በከተማችን የተረጋጋ ሰላምመኖርና ለስራ ምቹ መሆኑ፣ ዜጎች እኩል
ተጠቃሚ ሆነዉ በፈለጉት ሁኔታ ሰርተዉናተንቀሳቅሰዉመኖራቸዉ፣ መንግስት ልማታዊ
ባለሃብትን ለመደገፍ የያዘው ቁርጠኛነት እና የተፈጠሩ ምቹ ሁኔታዎች በከተማችን እንደ
አንድ ትልቅ ዕድል የሚወሰድና በአግባቡ የሚተገበር ይሆናል፡፡
በተጨማሪም በግብርናው ዘርፍ በዋነኛነት ምርትን የሚያሳዳጉ የተሻሻሉ አሠራሮችና
ቴክኖሎጂዎች የሚጠቀሙ አርሶ አደሮች ቁጥር ከመጨመሩም ባሻገር አዳዲስ
አሠራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ መላመድ የሚችል አርሶ አደር መፈጠሩ፣ በገጠሩ
የህዝብ ንቅናቄን ለመፍጠር የሚያስችል መሠረት መጣሉ እና ህዝብን ለልማት ሥራና
ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማንቀሳቀስ መጀመሩ፣ መንግስት ግብርናው ዋናው የእድገት
ምነጭ ሆኖ እንደሚቀጥል እና ግብርናው ዘርፍ በየትኞቹ የግብርና ልማት እንቅስቃሴዎች
ላይ አተኩሮ መረባረብ እንደሚገባ የተለየ መሆኑና በመንግስት ደረጃም ግልፅ አቋምና
ቁርጠኛነት የተያዘበት መሆኑ እንዲሁም ኢንዱስትሪው በተለይም አምራች ኢንዱስትሪው
የመሪነቱን ሚና እንዲጫወት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይተው እንዲቀመጡ
መደረጉ፣ እንዲሁም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ስትራቴጅ የልማታዊ
ባለሃብቶች መፈልፈያ እና ለኢንዱስትሪው ሽግግር መሰረት እንደሚሆኑ መለየቱ፣ ሰፊ
የስራ እድል ሊፈጥር የሚችል የተፈጥሮ ፀጋ መኖሩ፣ መሰረተ ልማቶችን ለማስፋፋት
የተመቻቸ የመሬት አቀማመጥ መኖሩ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ በምርጥ ተሞክሮነት ሊወሰዱ
የሚችሉ የዳበሩ ልምዶች መኖራቸው እና ተደራሽ መሆናቸው፣ በሁሉም የትምህርት
ዝግጅት ደረጃ ያሉትን ዜጎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የትምህርት ስርዓት መኖሩ፣ በአገር
ደረጃ የፋብሪካ ጥሬ እቃዎችን በስፋት ለማምረት ግብ መጣሉ፣ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የሰው ኃይል ለማቅረብ የሚያስችል አቅም እየተፈጠረ መሆኑ፣ የማንፋክቸሪንግ ዘርፍ


ጠንካራ ውድድር ያለበት ቢሆንም ዘርፉ ለሚያመርታቸው ምርቶች በአገርና በአለም ደረጃ
ሰፊ የገበያ ዕድል ያለ መሆኑ፣ እንዲሁም ከተማችን ለወደብ ቅርብ የሆነችና ሰፊ የንግድ
እንቅስቃሴ የሚካሄድባት ከተማ መሆኗ፣ የህዳሴዉ ግድብ መጠናቀቅ ለኢኮኖሚያችን
ዕድገት ያለዉ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ፣ እነዚህን መልካም አጋጣሚዎች በአግባቡ በመጠቀምና
ሥራ ላይ በማዋል በዓይነት፣ በመጠንና በጥራት ከባለፈዉ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
አፈፃፀም የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይቻላል፡፡
6.2 ስጋቶች፤ የዋጋ ንረት የኖሮ ውድነት ድህነት እንዳይባባስ
በቀጣይ አስር ዓመታት ለህዳሴ ጉዟችንና ለትኩረት ዘርፎች ግቦች ስኬት በዝቅተኛና
መካከለኛ ደረጃ የተሰማራውንና አዲስ የሚቀላቀለውን የሰው ሃይል ብቃት ማረጋገጥ ወሳኝ
መሆኑንና ሥራውንም የዕቅዳቸው አካል አድርገው የመተግበር አስፈላጊነት ላይ ያለው
ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑ፣ የአመራሩ ቁርጠኝነት ለእቅዱ መሳካት ባለው ፋይዳ ልክ ላይደርስ
ይችላል። ዕቅዱን ለማስፈፀም የሚጠይቀው ከፍተኛ ፋይናንስ በመሆኑ ይኸው በሚፈለገው
መጠን ላይገኝ ይችላል፡፡
በሌላ በኩል የ 10 አመቱን ዕቅድ ስኬታማነትን ከሚፈታተኑ ስጋቶች መካከል የድርቅ
ተጋላጭነት፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ፣ ኢኮኖሚዉ እየሰፋና እየተወሳሰበ ከመሄዱ አንፃር
የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ውስንነት፣ ለግብርና እና ኢንዱስትሪ ልማት አስፈላጊ
ግብዓቶች በአይነት፣ በመጠንና በጥራት የአቅርቦት ክፍተት፣ የግብርና ምርቶች ጥራታቸው
ተጠብቆ ለገበያ በወቅቱና በአስተማማኝ ሁኔታ የሚቀርቡበት አምራችና ሸማቹን
ተጠቃሚ የሚያደርግ ግልጽና ቀልጣፋ የግብይት ሥርዓት ተሟልቶ አለመደራጀት፣ የንግድ
ሥርዓታችን ግልጽነት ተወዳዳሪነትና ቅልጥፍና የጎደለው መሆኑ፣ በአገር ደረጃ ሊከሰት
የሚችል የዋጋ አለመረጋጋት፣ በአምራች ኢንዱስትሪ ለመቀላቀል የአመለካከት የኤሌክተሪክ
ሀይል ማነስ ችግር በቀጣይ የዕቅድ የአፈፃፀም ሂደት ላይ ተፅዕኖ ሊያስከትሉ ይችላሉ
ተብለው የሚጠበቁ ስጋቶች ናቸው፡፡
6.3 የስጋት መከላከያ ስትራተጂዎች፤
በየደረጃዉ ያሉትን ዕድሎች አሟጦ መጠቀም ዋነኛው የስጋት መከላከያ ስትራቴጂ መሆን
አለበት፡፡ የገንዘብ እጥረት ስጋት ለመቀነስ ከፍ ብሎ የተቀመጡ ስጋቶች በተጨባጭ
ከመከሰታቸው በፊት ለመከላከል የተደራጁና የተቀናጁ የልማት ሥራዎች በሁሉም
አካባቢዎች እንዲከናወኑ ይደረጋል፡፡ የድርቅ ተጋላጭነትን ከመከላከል አንፃር በሁሉም
አካባቢዎች የህዝቡን ግንዛቤ ይበልጥ በማስፋትና በማዳበር በተለይ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የተፋሰስ ልማት ባለፉት 10 ዓመታት ዕቅድ የአፈፃፀም ሂደት ያገኘናቸው ምርጥ


ተሞክሮዎች በሁሉም አካባቢዎች በተሟላ ሁኔታ ይተገበራሉ፡፡
የኪራይ ሰብሰቢነት አደጋዎችን ለመከላከል በሁሉም አካባቢዎች የህዝቡን ግንዛቤ በማሳደግ
እና የተደራጁና የተቀናጁ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በመንግስት መዋቅርና በግሉ ዘርፍ
አስተምህሮን ማዕከል ያደረጉ የመከላከያ ስልቶች ተፈፃሚ ይደረጋሉ፡፡
የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ከማጠናከር አንፃር በቀጣይ 10 አመታት ዕቅድ ዘመን
በሁሉም ዘርፎች ትኩረት እንዲሰጠው ይደረጋል፡፡ አመራሩ የቀጣዩ እቅድ ዘመን
የሚጠይቀውን የአመራር አቅም፣ ብቃትና ቁርጠኝነት እንዲይዝ ይሠራል፡፡ ስጋቶችን
በማስወገድና የተያዙ ግቦች በእያዳንዱ ዘርፍ በተቀመጠው አግባብ መፈፀሙን በቅርብ
የመከታተልና ድጋፍ የመስጠት ሥራ ይሠራል፡፡
በሌላ በኩል ለገበያ (ለአገር ውስጥም ሆነ ለአለም ገበያ) የምናቀርባቸውን ምርቶች
በዓይነት፣ በመጠን፣ በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡ እንዲሁም አቅም
በፈቀደ መጠን ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ምርታችንን መሠረት በማድረግ በከተማችን
ውስጥ በሚመረቱ ምርቶች ለመተካት ትኩረት ተሰጥቶ በመሥራት አገራዊና ክልላዊ
አስተዋጽኦ ለማበርከት ይሠራል፡፡

በተጨማሪም የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ከምንጊዜውም በላቀ ደረጃ በማሳደግ በቂ


የምግብ አቅርቦትን ለማረጋገጥ፣ ለቀላልና መካከለኛየአምራች ኢንዱስትሪዎች በዓይነት፣
በመጠን እና በጥራት ግብዓት ለማቅረብ እና የግብርናውን ዘርፍ በዓይነት፣ በመጠን፣
በጥራትና በዋጋ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ
ይሠራል፡፡ ልማታዊ ባለሃብቱ በአምራች ኢንዱስተሪዎች በስፋት እንዲሳተፍ የአመለካከት
ለውጥ ለማምጣት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ደረጃ የሚሠራ ይሆናል፡፡
6.4 የዕቅድ አፈጻጸም የክትትል እና ግምገማ ስርዓት
የቀጣዩ 10 አመታት ዕቅድ በባለፈዉ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ውስጥ
የታዩ ጥንካሬዎችና ለውጦች ተጠብቀው ቀጣይ እንዲሆኑ ማድረግ፣ ባለፋት አመታት
በሁሉም ክፍላተ ኢኮኖሚዎች ውስጥ የታዩትን ክፍተቶችና ድክመቶች መሙላትና
ችግሮችን የመፍታት ሚና ያለውና በዋናነት መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት በሚያስችሉ
ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ለሕዳሴው ጉዞ እውን መሆን አስተዋጽኦ በሚያደርግ መልኩ
መተግበር ያለበት ይሆናል።

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የዚህ ዕቅድ ዘመን የአፈጻጸም ሥርዓትም ሂደቱ ሁለትንናዊ የመፈጸም አቅምን


የሚያጠናክር፣ በበለጠ ታታሪነትና ትጋት የሚፈጸምና በሠራዊት ቁመና የሚተገበር፣
ውጤታማና ወጪ ቆጣቢ በሆነ አግባብ የሚተገብርና የግልፅነትና ተጠያቂነት አሠራርን
የሚከተል፣ አሣታፊና በየደረጃው የመላ ሕዝቡን ባለቤትነትና ተጠቃሚነት የሚያጠናክር፣
የተደራሽነትና የፍትሐዊነት ባህሪው የተጠናከረና ያደገ፣ የአመራር ሥርዓቱ ዴሞክራሲያዊ
የሆነና በላቀ ትብብርና ቅንጅት የሚታገዝ፣ ለዘላቂ ለወጥ ምቹ የሆነና ተደጋጋፊነት
የሚያጠናክርና ያለምንም መንጠባጠብ የሚፈጽም መሆን ይኖርበታል።
ለዚህም ተግባራዊነት እጅግ ጥብቅ በሆነ የክትትልና ግምገማ፣ ድጋፍ ሥርዓት የሚታገዝና
የሚመራ መሆን ይገባዋል። ዕቅዱን በመፈጸም ሂደት ሊኖር የሚገባው የክትትልና ግምገማ
ስርዓት ሲታይም ካለፈው በተሻለ ሁኔታ የተለያዩ አካላትን የሚያካትትና በትኩረት
በየደረጃው የሚተገበር ይሆናል። በመሆኑም በየደረጃው በክትትልና ግምገማ ሥርዓቱ
ውስጥ ተሣታፊ የሚሆኑ አካላት እና የሚኖራቸው ሚና በዝርዝር ተመልክቷል።
የሕዝብ ምክር ቤቶች፡- የሕዝብ ሉአላዊ የሥልጠን ባለቤትነት የማረጋገጥባቸው ምክር
ቤቶች ከሁሉም በላይ በክትትልና ግምገማ ሥርዓት ውስጥ የላቀ ሃላፊነት ይዘው
የሚንቀሣቀሱ ይሆናሉ። ምክር ቤቶች በቋሚ ኮሚቴ አደረጃጀት፣ አሠራር፣ በየደረጃው
በሚካሄዱ የምክር ቤት ጐባዔዎች፣ በሚፈጥሯቸው የሕዝብ ውይይቶች ውስጥ ዋና ዋና
የግብ ማዕከሎችን b ዝርዘር መዝግቦ በመያዝ የመገምገሚያና የመወያያ አጀንዳ አድርገው
በመንቀሳቀስ በተለዩ ችግሮች ላይ አስፈላጊ ውሣኔዎችና መፍትሄዎች እንዲሰጡ ማድረግ፣
የተለዩ ጉዳዮችን በመቀመር ለቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ግብዓት እንዲሆኑ በግማሽ ዓመትና
በዓመቱ መጨረሻ በማዘጋጀት የሚያቀርቡ ይሆናል። ከዚህ ባሻገር በመካከለኛው ዕድሜ
ዘመን አጠቃላይ ሂደቱ እና የተደረሰበት ደረጃን መሰረት አድርጎ ግምገማ እንዲካሄድ
ያደርጋል። ከዚህ ግምገማ የተገኙ ውጤቶችን ለቀሪ አምስት ዓመታት ግብዓት እንዲሆኑ
በማድረግ የቀጣዩን ዕቅድ ዘመን በተያዘለት ደረጃ እየተፈጸመ መሆኑን ያረጋግጣል።
በየደረጀው የሚገኙ የአስፈጻሚ አካላት፡- ከከተማ አስተዳደሩ ጀምሮ እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ
የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት /ከፍተኛ፣ መካከለኛና ዝቅተኛ የመንግሥት አመራሩ/
ዕቅዶች በወቅቱ፣ በጥራት፣ በተጠያቂነትና በተሻለ አመራርና በሕዝብ ተሣትፎ እየተፈፀሙ
መገኘተቸውን መከታተል፣ መገምገም፣ መደገፍና ቀጣይ አቅጣጫና አመራር መስጠት
ይጠበቅበታል። በዕቅዱ ላይ ሰፊ መግባባት የሚፈጠርበት ሁኔታ እንዲመቻቻች ይደረጋል።
በመሆኑም ካለፋት ዓመታት በተሻለ ሁኔታ የሰው ሃይል፣ የቁሳቁስና የገንዘብ አቅምን
በመጠቀም የሕዝቡ ተሣትፎና ባለቤትነት የተለያዩ አካላት ቅንጅት በተረጋገጠበት ሁኔታ

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

መፈጸማቸውንና ለተቀመጡ ዋና ዋና ግቦች ማሣካት አስተዋፅአ በሚያደርጉበት አግባብ


አፈጻጸማቸው መመራቱን ያረጋግጣል።
በየደረጀው የሚዘጋጁ ግምገማዎችና ሪፖርቶችም የዕቅዱን ዋና ዋና ግቦች ማዕከል
በማድረግ በወቅቱ እንዲፈጸሙ ማድረግና ከቀበሌ እስከ ከተማ አስተዳደሩ ባለው
መንግሥታዊ ትስስር ውስጥ በቅብብሎሽ ሊመሩ ይገባል።
መላ የከተማችን ሕዝብ፡- የልማት ባለቤትና ተጠቃሚ መላ ሕዝቡ እስካሆነ ድረስ የዕቅዱ
አፈጻጸም ለመከተተል ፣ለመገምገምና ድጋፍ ለመሥጠት በሚያስችለው መልኩ ሊመራና
ሊንቀሣቀስ ይገባል። ይህንን ለማሣካት አካባቢያዊና ተደራሽ በሆኑ አደረጃጀቶች
አማካኝነት መላ ሕዝቡ በዕቅዱ ላይ ተመሳሳይ ግንዛቤ እንዲይዝና መግባባት ላይ እንዲደርስ
ከማድረግ ባሻገር በየዓመቱ በአፈጻጸሙ ላይ የመላ ሕብረተሰቡ አስተያየት የሚካተትበትን
ሥርዓት መዘርጋትና በየዓመቱ የታዩ ለውጦች በሕዝቡ ፀድቀው ወደ ላይ እንዲመጡ
ማድረግ ይገባል። ከየቀበለውና በክፍለ ከተማ ደረጃ በልማቱ ዕቅድ ውስጥ የሕዝብን
ተሣትፎ የሚፈልጉ ጉዳዮች በውል ተለይተው ሊወርዱና አስተዋፅአ እንዲያደርግባቸው
ማድረግና ይህንን በመቀመር የሚተላለፍበትን ሥርዓት ማበጀት ያስፈልጋል።
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ፡- የሀብት አመዳደብ ሥርዓት ከጊዜና ከግብ ጋር
ጥምረት ፈጥረውና በተሻለ ወጪና ጥራት እንዲፈጸሙ በማድረግ ዙሪያ ግንባር ቀደም
ተቋም በመሆኑ በየደረጃው የሀብት አጠቃቀም ሥርዓት በተጠያቂነት እንዲመራ ማድረግ
ይኖርበታል፡፡
የልማት እቅድ ክትትልና ግምገማ/ፕላን ኮሚሽን፡- በየጊዜው ያልታዩ ጉዳዮችን ከግንዛቤ
ውስጥ በማስገባት ከሚተላለፉ ውሣኔዎችና ከሚሠጡ አቅጣጫዎች በመነሣት በየዘርፋና
በየደረጃው የዕቅድ ክለሳና ማሻሻያ እንዲደረግ ማድረግ ይጠበቅበታል። በዕቅድ ዘመኑ ውስጥ
የተያዙ ዋና ዋና የልማትና የመልካም አስተዳደር ግቦች በሚጠበቀው ደረጃ እየተፈጸሙ ያሉ
ስለመሆናቸው ማለትም መሰረታዊ ግምገማ ለማካሄድ የሚያስችሉ ዋና ዋና ዘርፎች
ውጤት አመልካቾች መለየት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ መረጃዎች ማመንጨትና ለግምገማ
መነሻ እንዲሆኑ ማስቻል፣ ዓመታዊ ዕቅዶችን፣ የየሩብ ዓመታትና የየዓመቱን የዕቅድ
አፈጻጸም ሪፖርቶችን ማዘጋጀት፣ በመስክ ስራ የተደገፈ የአፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣
የመካከለኛ ዘመን እና የ 10 ዓመት ማጠቃለያ የአፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀት፣ የካፒታል
ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ተከታትሎ ሪፖርት ማቅረብ፣ በማጠናቀቂያ ምዕራፍ አጠቃላይ
ውጤት እና ተጽዕኖ መለካት የሚቻልበትን አሰራር መሰረት በማድረግ ከሌሎች ሴክተሮች
ጋር በመሆን መስራት ይጠበቅበታል።

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የሴቶችን፣ የወጣቶችን እና ሌሎች ልዩ ድጋፍ የሚሹ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳይ


የሚከታተሉ አካላት ሚና፡- ሴቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ የሕብረተሰብ
ክፍሎች በልማቱ ውስጥ በየደረጃው ተሣታፊ መሆናቸውን እንዲሁም በልማቱ ሂደት
ውስጥ ፍላጐቶቻቸው የሚሣኩበትንና ችግሮቻቸው የሚፈቱበት አሠራር መኖሩን
ማረጋገጥ ይገባል፡፡ በዚህ ዙሪያም ሴቶች፣ ወጣቶችና የሕፃናት ጉዳይ መምሪያ ፣ ሠራተኛና
ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ እንዲሁም ሌሎች አደረጃጀቶች፣ የወጣቶችና ሴቶች
ማህበራት በክትትልና ግምገማ ሥርዓት የሚሣተፉበትን የአሠራር ሥርዓት መዘርጋትና
ሪፖርቶችን አዘጋጅተው በማቅረብ በመጨረሸም የተፅዕኖ ግምገማ በራሣቸውና ከሌሎች
አካላት ጋር በመቀናጀት ማከናወን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከዚህ ባለፈ የእነዚህ ሴክተሮች ሚና ሌሎች ዘርፎች በሚያካሂዷቸው የልማትና መልካም
አስተዳደር ስራዎች እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ከዕቅድ ዝግጅት እስከ ማጠናቀቂያ ባሉ
ሂደቶች ትኩረት ተሰጥቷቸው ያሉ መሆኑን ማረጋገጥ የሚያስችል የክትትልና ድጋፍ
የአሰራር ስርዓት መዘርጋት ይጠይቃቸዋል።
በአካባቢ ተፅዕኖ ላይ የሚሠሩ የመንግሥት አካላት፣ ድርጅቶችና ተቋማት ተሣትፎ፡-
በገጠርና በከተማ የሚካሄዱ የልማት ኘሮግራሞችና ተግባሮች እንዲሁም የግልና
የመንግሥት የኢንቨስትመንት ኘሮግራሞችና ኘሮጀክቶች በዚህ የልማት ዘመን ከአካባቢ
ጥበቃና ደህንነት አኳያ ቅድመ ግምገማ፣ የሂደትና የአፈጻጸም ግምገማ እንዲሁም
በመጨረሻም ተፅዕኖው እንዲገመገምና በቀጣይ የማስተካከያ ዕርምጃዎች እንደወሰዱ
ማድረግ ይገባል፡፡ ከዚህ አኳያ የሚመለከታቸው አካላት በተለዩ ግቦችና ተግባሮች ላይ
በመመሥረት ቅድመ ምርመራና ግምገማ እንዲሁም በየዓመቱ የማጠቃለያ የግምገማ
ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በተለይም አረንጓዴ አኮኖሚ በመገንባት ስርዓት ሂደት ውስጥ እያንዳንዳቸው ተግባሮቻችን
በአካባቢ ላይ የሚኖራቸውን እንድምታ የመመዘን ጉዳይ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው
ይሆናል፡፡
የፀጥታና የፍትህ አካላት፡- ትክክለኛ የልማት ሂደትና የአተገባበር ሥርዓት ሰላምንና የሕግ
የበላይነትን በቅድመ ሁኔታነት የሚጠይቃቸው ጉዳዩች ከመሆናቸው ባሻገር አጠቃላይ
ልማቱ ያለምንም ሥጋትና ችግር የሚፈጸምበት ሥርዓት መኖሩን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
በተለይ ለትላልቅ የኢንቨስትመንት ኘሮግራሞች በገበያና በንግድ ሥራዓቱ፣ በግዥና በሌሎች
ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት በተለየ የጥበቃ ሥርዓት እንዲፈጽሙ በማድረግ
አጠቃላይ የሕግ የበላይነት መኖሩን ማረጋገጥ ይገባል፡፡ በመሆኑም ይህ አንዱ የክትትልና
ግምገማ ሥርዓት ማዕከል ሆኖ የሚታይ ይሆናል፡፡

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

የቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት ሚና፡- በየትኛውም መሥፈርት ከሕብረተሰቡ የሚነሱ ቅሬታዎች


ከልማት ተሣታፊነት፣ ተጠቃሚነት፣ በልማት አመራር ሥርዓት መጓደልና መዛባት ጋር
ተያይዘው የሚታዩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ይህንን ከሚከታተሉ አካላት የሚቀርቡ ቅሬታዎችን
በዓመት መጨረሻ በመቀመር ለቀጣይ አፈጻጸም ግብዓት አድርጎ መጠቀም አስፈላጊ
በመሆኑ የቅሬታ ሰሚ፣ የሰብአዊ መብት ፣ እንባ ጠባቂና የሌሎች አካላትን ተልዕኮ ግብዓት
አድርጐ መጠቀም ይገባል፡፡
የጥናትና ምርምር ተቋማት፡- የዕቅዱ አፈጻጸም በተሻሉ አስተሣሠቦች፣ አሠራሮችና ክህሎት
ታግዞ መተግበር ያለበት በመሆኑ የዩንቨርስቲዎች፣ ኮሎጆችና የሌሎች የጥናትና ምርምር
ተቋማት ተግባሮችን ግብዓት አድርጐ መጠቀምና እነዚህ ተቋማት በክትትልና ግምገማ
ሥርዓት ውስጥ ሙያዊና ተቋማዊ ተልዕኮ ይዘው እንዲንቀሣቀሱ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የኦዲት ተቋም ተልዕኮ፡- አጠቃላይ የሃብት አጠቃቀም ሥርዓቱ ላይ የአካላዊ እና የገንዘብ
ኦዲት በማድረግ የሃብት አጠቃቀም ሥርዓቱ ከአሠራርና ሕግ አኳያ ትክክል ስለመሆኑ
ከማረጋገጥ ባሻገር ከግቦች መሣካት ጋር ያለውን መመጣጠን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
ከዚህ አኳያ ቢያንስ አመታዊ የኦዲት ማጠቃለያ ሪፖርቶችን ለአጠቃላይ የክትትልና
ግምገማ ሥርዓቱ አካል አድርጎ መውሰድ ይገባል፡፡
የመገናኛ ብዙሀንና የኮሚኒኬሽን ተቋማት፡- ተቋማቱ የሚሠሯቸው የዘገባ፣ የሕዝብ ግንኙነት
ተግባሮችና የሚፈጥሯቸው የሕዝብ ውይይቶችና መድረኮች ለክትትልና ግምገማ ሥርዓቱ
ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ ማድረግና የተቋማቱ እንቅስቃሴዎች ዋና ዋና ግቦች ላይ
ያተኮረ እንዲሆንና ለግቦች መሣካት አስተዋፅኦ በሚያደርግ መልኩ መፈጸምና ማሥፈጸም
ያስፈልጋል፡፡
የብዙሀን፣ የሙያና የሲቪል ማህበራት አስተዋፅኦ፡- ማህበራቱ የሚወከሉበትን ሕዝብና አካል
ድምጽና ፍላጐት የሚወከሉ ከመሆናቸው አኳያ፣ በዓመት አንድ ጊዜ በአፈጻጸሙ ላይ
እንዲመክሩና እንዲወያዩ በማድረግ የሚያነሱዋቸውን ጉዳዩች ግብአት አድርጐ በመጠቀም
የዕቅድን አፈጻጸም ከማሣለጥ ባሻገር የዕቅድ አፈጻጸም ሂደቱ አካታች፣ አሣታፊና መላ
ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ በኩል አንዱ የማረጋገጫ መንገድ ሆኖ እንዲያገለግል
ያግዛል፡፡
ሌሎች አጋር አካላት፡- በቀጥቃም ሆነ በተዘዋዋሪ የዕቅድ አፈጻጸሙን በማጠናከር
አስተዋጽአ ያላቸው አካላት፣ ረጅ ድርጅቶች፣ በጀት ድጋፍ ያደረጉ አካላት ዓለም አቀፍ
ድርጅቶችና የፊዴራል አካላት፣ በውጭ የሚገኙ ትውልደ ኢትዩጵያዊያን፣ የንግድ
ማህበራት፣ ወዘተ በየዓመቱ መጨረሻ በመድረክ በተዘጋጁ የክትትልና የግምገማ ማጠናከሪያ
አሠራሮች የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማድረግ ይጠበቃል፡፡ በአጠቃላይ የዕቅዱን

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አፈጻጸም በመከታተልና በመገምገም ዙሪያ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተሣታፊ የሚሆኑና


ሀላፊነት ያለባቸው አካለት ቅድመ ተግበራ ላይ፣በየዓመቱ፣ በመርሃ ግብር ዘመን አጋማሽ፣
በማጠናቀቂያና መርሃ ግብሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ተፅዕኖን በመገምገም ዙሪያ ተሣታፊ
እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

6.5 ማጠቃለያ
ስለዚህ በቀጣይ 10 አመት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራባቸዉ ተግባራቶች የጥቃቅንና
አነስተኛ ኢንተርፐራይዞችን በማስፋፋት ስራ አጥነትንና ድህነትን በእጅጉ
መቀነስ፣የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ስርአትን በማዘመን ከተማዋን ፅዱ፣ዉብና
አረንጓዴ ማድረግ፣ዘመናዊ የመሬት ምዝገባና ልማት ማኔጀመንትን ማዘመን፣ማዘጋጃ
ቤታዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋና ዉጤታማ ማድረግ፣ህጋዊና ፍትሀዊ የንግድ ዉድድርና
የሸማቾች ጥበቃ ስርአትን ማስፈን፣ የከተማ ግብርና የግብርና ግብአትና ቴክኖሎጅ
ስርጭትን ማስፋፋት ፣ዘመናዊ የመስኖ ልማትን በማጠናከር የአርሶ አደሮችን ምርትና
ምርታማነት ማሳደግ፣የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር መፍታት፣ከአደጋ የፀዳና
ተደራሽ የሆነ ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎትንማስፋፋት፣የማህበራዊ
አገልግሎቶችን ጥራትና ተደራሽነት ማሳደግ፣አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን
ማስፈን፣የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ፣ለኢንቨስትመንትና ቱሪዝም መስፋፋት ምቹ
ሁኔታዎችን በመፍጠር ከተማዋን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ማድረግ፣ የመዝናኛ፣
የአረንጓዴ ልማትንና የስፖርት ማዘዉተሪያ ቦታዎችን በስፋት ማልማት፣የመልካም
አስተዳደር ስርአትንማስፈን፣ኪራይ ሰብሳቢነትንና ብልሹ አሰራርን
መከላከል፣እኩልነትን፣ፍትሀዊ ተጠቃሚነትንና ዲሞክራሲን እዉን ማድረግ፣የተቀናጀ
የመሰረተ ልማት ግንባታ ጥራትና ተደራሽነትን ማሳደግ ይሆናሉ፡፡ከላይ የተረዘረዘሩት
ተግባራት በዉጤታማነት ተፈፃሚ የሚሆኑትና የሚፈለገዉ ለዉጥ ሊመጣ የሚችለዉ
ጠንካራ የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም ያለዉ የለዉጥ ሀይል፣ሰብአዊና ቁሳዊ ሀብት
የተሟላላቸዉ የተደራጁ ተቋማት ሲገነቡ መሆኑ ይታወቃል፡፡በመሆኑም የተቋማትን
ግንባታን ማሻሻልና ማዘመን፣የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ግንባታን ማሳደግ፣
ፍትሀዊ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በማዘመን የከተማዋን ገቢ ማሳደግና የፋይናንስ

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

አስተዳደር ስርአትን ማሻሻል የእቅዱ ቁልፍ ተግባራት ሆነዉ በጥብቅ ዲሲፐሊን


እየተገመገሙ ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

የቃላትና የአኅፅሮተ ቃላት ትርጉም

224P a g e
የደሴ ከተማ አስተዳደር የ 10 አመት መሪ እቅድ ከ 2013 -2022 ዓ/ም

224P a g e

You might also like