Professional Documents
Culture Documents
የመስጂድ እቅድ
የመስጂድ እቅድ
መግቢያ
እንደሚታወቀው የቡታጅራ አህለል ሱና ወልጀመዓህ በገጠሩም በከተማው በስሩ ከ20 በላይ መሳጂዶች ያሉ
ሲሆን እነዚህን መስጂዶቸ በመጠቀም ካለፉት 2 አስርት አመታት ጀምሮ ከሞላ ጎደል አቅሙን በፈቀደው
ትክክለኛውን የሸሪዓ አስተምህሮ ለማህበረሰቡ ለማድረስ ደፋቀና በማለት ላይ ሆኖ እስከዛሬ ደርሷል።ሆኖም
ጀመዓው እነዚህን መስጂዶች በበቂ ሁኔታ ማገልገል ባይችልም ግን ዛሬ ላይ የምናየውን የሱናው ማህበረሰብ
መብዛት በአላህ ፈቃድ የአቅሙን አስተዋጽኦ ማድረግ ችሏል፡፡ አነዚህን ስራዎች ሲከውን ግን በተለያዩ ችግሮች
የተፈተነና ከችግሮቹም ጋር ግን ስራውን በተለይም በቂርኣትና በዳዕዋው ዘርፍ ላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል አሁንም
ድረስ እየሰራ ይገኛል፡፡
ከዚህ በፊት የሱናው ጀመዓህ ላይ የነበሩና አሁንም ድረስ የቀጠሉ ችግሮችን እንደሚከተለው በ3 ከፍዬ ለማቅረብ
እሞክራለሁ፡-
1. ኢኮኖሚያዊ ችግር
ጀመዓው የአቅም ውስንነት ያለበት መሆኑ ግልጽ ነው ከዚህም አንፃር ማለትም ከመስፋፋት እና
ከተደራሽነት አኳያ የተሰሩ ስራዎች አነስተኛ ናቸው።ማህበረሰቡም ይንን ጀመዓ መደገፊያ ምረኩዝ አድርጎ
ቢቆጥረው እንጂ ጀመዓውን ለማገዝ የሚሆኑ አቅሞች መፈጠር ላይ ብዙ አልተሰራም
ጀማዓውም የማህበረሰቡም ይሁን የራሱ ፍላጎቶች ካላው አቅም አንፃር ተገቢውን ምላሽ የሚሰጥ ሆኖ
አልተገኘም።
አስፈላጊ የሆኑ የጀመዓው ወጪዎች ከተወሰኑ ሰዎች የሚሸፈኑ ቢሆንም ጀመዓው ከመስፋፋቱ አንፃር ዛሬ
ከደረሰበት ፍላጎት እና ተመጣጣኝ አቅም በየትኛውም ሚዛን መጣኝ ስላልሆነ፣ጀመዓው የውስጡም ይሁን
ከማህበረሰቡ ለሚመጡ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥበት ሂደት የደከመ እና አሰልቺ ስለሆነ ጀመዓውን
ሊመጥን እና ሊያሳድግ የሚችል የገቢ አቅም የለውም።
የኡስታዞች ደሞዝ ለመክፈል፤መድረሳዎች ለማስፋፋት፤መስጂዶች ለማስፋፋት፤ያሉትም መስጂዶች
በኢኮኖሚ ለማጠንከር፤ወዘተ መሰል ችግሮች ለመፍታት አለመቻሉ፡፡
2. ማህበራዊ ችግሮች
ማለትም የሱናው እንግዳ ሆኖ መቆጠር ባይተዋርነትና ጭራቅ አርጎ ማህበረሰቡ ዘንድ መሳሉ ሱናን
ለማስተማር እንቅፋት ሆኖ ታይቷል፡፡በተለያየ ጠሪቃ ውስጥ የተዘፈቀ ማህበሰብ መሆኑን የተብሊግን
የሱፍያው ማህበረሰብ ቀድሞ መስፋፋቱና ቦታ መያዙ ይህንን ጀመዓህ በማህበራዊ ጉዳይ አስተዋጽኦ
እንዳይኖረው ተደርጎ ታፍኖ የቀየ መሆኑ፡፡
3. ፖለቲካዊ ተጽዕኖ
ከፌደራል ጀምሮ እስከ ታችኛው የቀበሌ መዋቅር ድረስ ይህን ጀመዓህ የሚጨቁን እንጂ የሚያግዝ አካል
አለመኖሩ፤
ከላይ በ3 ተከፍለው የቀረቡት ችግሮች ዋናዋናዎቹ ቢሆኑም ሌሎች ዝርዝር ችግሮች እንዳሉና እዚህ ውስጥ
እንደሚጠቃለሉ ታሳቢ ተደርጎ እነዚህን ችግሮች በጀመዓው ላይ ቀላል የማይባሉ እንቅፋቶች እንደነበሩ
ለቤቱ ግልጽ ነው፡፡
እነዚህ ችግሮች ከአሁን በኋላ ከተቻለ ሙሉለሙሉ እንዳይቀጥሉ ካልተቻለም እዲቀንሱ ማድረግ አለብን
ብለን ከእናንተ ጋር የአላህ እርዳታ ከፊታችን አርገን የሚከተሉት የአጭር ጊዜ እቅድ አቅደን ተነስተናል፡፡
እቅዱም ስናቅድ ዋናዋና ጉዳዮችን እንጂ ለዚህ በጣም ለተስፋፋው የሱና ጀማዓህ በቂ እቅድ ነው ብለን
እንደማናስብ ግን እንደ መንደርደሪያ ሁሉም የራሱ እንዲያቅድና እንዲሰራ ያደርጋል፡፡በጊዜያዊነት ጀመዓችን
ላይ በአፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ጉዳዩች ናቸው ያልናቸውን በአመታዊ እቅዳችን ፊት ለፊት አርገን አቅርበናል፡፡
1.1. በከተማው በእጃችን ባሉ መስጅዶች ውስጥ ያሉ ኡስታዞች በአግባቡ እና በሞራል ማህበረሰቡን በእወቀት
የተሻለ ደረጃ ያደርሱት ዘንድ ቢያንስ 10 መስጂዶች ላይ የሚገኙ 10 ኡስታዞችን መቅጠር
ግብ 2. በዳዕዋው ዘርፍ ጠንካራ የሆን ሜምበር ማቋቋምና ዳዕዋውን ተደራሽ ማድረግ (840,000 ብር
ያስፈልገናል።)
1. እቅዱን በተገቢው ሁኔታ አቅዶ ከሚመለከተው አካል ጋር በቂ ግንዛቤ መፍጠርና መተማመን ለዝርዝር
ተግባራት የጊዜ ሰሌዳ ማውጣት
2. በቂ የሆነ የበጀት ምንጭ መፈለግና በአክሽን ፕላን መመራት
3. በበጎ ፈቃደኝነት ስራዎችን የሚሰራ የሰው ሀይል መፈለግና ካልተቻለም እንደ አስፈላጊነቱ ሰው መቅጠር
4. ለዚህ ተግባር በበላይነት የሚመራውና የሚከታተለው መዋቅር ማዘጋጀት
5. ከሌሎች የልምድ ልውውጥ መውሰድና አጋዥ አጋር ሆነው እንዲሰሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት
በየወሩ በየ3 ወሩና በየ6 ወሩ እንዲሁም በየዓመቱ የተሸነሸነ እቅድ ማዘጋጀትና ተግባርን
መከታተል መገምገም ግብረ መልስ መስጠት
በፋይናንሺልም ሆነ በፊዚካል አፈጻተም ዙርያ ግልጸኝነት መፍጠርና የውጭ ኦዲት የሚደረግበትን
አግባብ መፍጠር