Professional Documents
Culture Documents
ስነ-ባህሪ
ስነ-ባህሪ
2- ስነ-ባህሪ፡- ባህሪን እና የአእምሮ የአስተሳሰብ ሂደት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና ዲሲፒሊን ነው፡፡
3. ባህሪ፡- የሰው አስተሳብ አመለካከትና ድርጊት ውጤት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት በቀጥታ ሊቃኝ ሊመዘገብና
ሊለካ የሚችል ይሆናል፡፡
ተፈጥሮና አካባቢ በባህሪ ላይ ያላቸው ሚና
የሰው ልጅ ባህሪ የውርስ (heredity) እና የአካባቢ ( Environment) የጋራ ውጤት እንደሆነ የተለያዩ
የስነ-ባህሪ ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡
የስነ-ባህሪ ግቦች
የስነ-ባህሪ ግቦች የሚባሉት
A. ባህሪን መግለፅ
B. የተለያዩ ባህሪያትን መንስኤ ማብራራት
C. ወቅታዊ የባህሪን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የወደፊቱን መተበይ
D. ባህሪን ማሻሻል
E. የሰው ልጅ መልካምና መጥፎ ባህሪያን ሊያዳብር ይችላል፡፡ ነገር ግን መልካም ያልሆነው ባህሪ
በተለያዩ የስነ-ባህሪ ዘዴዎች መለወጥ ሌላኛው የስነ-ባህሪ ግብ ነው፡፡
የማሽከርከር ስነ-ባህሪ
የማሽከርከር ስነ-ባህሪ አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት የሚያሳዩትን ባህሪ
የሚያጠና የሥነ-ባህሪ ዘርፍ ነው፡፡
የማሽከርከር ስነ-ባህሪ ጠቀሜታ
የማሽከርከር ስነ-ባህሪ ዋና አላማው በተሸከርካሪ የሚደርስ አደጋን መቀነስ ነው፡፡ ይህም
ሲባል በዋናነት ሊከናወን የሚችለው አላስፈላጊ የማሽከርከር ባህሪን በማስተካከል ነው፡፡
የግኙነት ክህሎቶች
ትህትና፡- ለመንገደኞች ትሁት መሆን
ርህራሄ፡- -ሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎችን ስሜት መጠበቅ
እንደዜጋ ህግንና ደንብን አክባሪ መሆን ፡- ለመንገድ ወይም ለእንቅስቃሴ ህግጋት
ተገዢ መሆን
ከሌሎች መንገድ ተቃሚዎች ጋር መንፈሳዊ ትስስር መፍጠር
የፈጠራ የአነዳድ ልምዶችን እና የዘመኑን የሳይንስ ግኝቶችን ማዳበር
የሌላን መንገድ ተጠቃሚ ስሜት መጋራት ናቸው፡፡
የማሽከርከር ሥነ- ባህሪ ጉዳዮች
ዝግጁነት
መነቃቃት
መረጃ ን የ መስብስብ እና የመተረጎም ሂደት
1.ዝግጁነት፡- የብስለት ፣ የችሎታ ፣ የትምህርትና የመነሳሳት የጋራ
ውጤት ነው፡፡ በመሆኑም የዝግጁነት መገለጫ የሆኑት
ለማሽከርከር ጤነኛ መሆንህን ማረጋገጥ
መፈተሽ ያለብህን ነገር መፈተሽ ( ተሽከርካሪን ለጉዞ ዝግጁ
ማድረግ)
የመንገድ የአየር እና የትራፊክ ሁኔታ በማሽከርከር ሂደት ላይ
የሚፈጥረውን ችግር ቀድሞ መገመት፡፡
2 .
2.መነቃቃት፡- በሰዎች ውስጥ ያለ ሁኔታ ሆኖ ባህሪን ወደ ግብ
የሚያንቀሳቅስ ሂደት ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ንቁ ተነሳሽነት ያለው
አሽከርካሪ በማንኛውም የትራፊክ ሁኔታ ውስጥ የሚወስደው ውሳኔና
እርምጃ ፈጣን መሆን እንዳለበት ይረዳል፤ለስራ ዉጤት መነሳሳት
ከፍተኛ ፈላጎት ያለው ሰው የሚገጥሙትን ችግሮች እንደ ፈተና
በመቁጠር ለዉጤቱ የበለጠ ይሰራል፡፡
3. መረጃን የመሰብሰብና የመተርጎም ሂደት
መገንዘብ
ትኩረት
ማስተዋል
መገንዘብ (- Sensation) ፡- መረጃን ከአካባቢያችን በስሜት
ህዋሳቶቻችን የመቀበል የመለወጥና ወደ አእምሮአችን የመላክ ሂደት
ነው፡፡ ማለትም በስሜት ህዋሶቻችን አማካኝነት ማለትም በማየት
በመስማት በማሽተት በመቅመስና በመዳደስ ነው፡፡
ከ80-90 ፐርስንት አካባቢን ለማውቅና መርጃ ለመሰብ የሚያስቸለው
ትኩረት (Attention) ፡- በስሜት ህዋሳቶቻችን አማካኝነት
ከሚደርሱን መረጃዎች መካከል ዋናውንና ተፈላጊውን የመምረጥ ሂደት
ነው፡፡ በመሆኑም መረጃ ላይ ትኩረት ማድረግን ሊያዳብሩት የሚገባ
ጉዳይ መሆኑን ማወቅ ይገባል፡፡
1. ኃላፊት
2. ጥንቃቄ (ደህንነት)
3. ብቃት
1.ኃላፊት
ሀ/ ስሜታዊ ኃላፊነት ፡- ለሌሎች ማሰብና ስነ ምግባራዊነት
1. የስሜታዊ ኃላፊነት ጉድለት፡-ራስ ወዳድነትና ቅንነት የጎደለው አስተሳብ
ለ/ አእምሮአዊ ሃላፊነት፡- አዎንታዊ ህሊናዊ አስተሳሰብና አእምሮአዊ ጤንነት
1. የአእምሮ አዊ ሃላፊነት ጉድለት ፡- ራስ ወዳድነትና ቅንነት የጎደለው አስተሳብ
ሐ/ ክህሎታዊ ኃላፊት ፡-ደስተኝነትና እርካታ
1. የክህሎታዊ ኃላፊነት ጉድለት፡-ውጥረትና ድብርት
2. ጥንቃቄ (ደህንነት)
ሀ/ ስሜታዊ ደህንነት፡- እራስን ማዘጋጀትና ሚዛናዊነት (እኩልነት
1. የስሜታዊ ደህንነት ጉድለት፡-የሞገደኝነት ስሜትና በአጋጣሚዎች የመጠቀም ፍላጎት
ለ / አእምሮአዊ ደህንነት ፡- ሚዛናዊ መለያ ባህሪያት
1.የአእምሮአዊ ደህንነት ጉድለት፡- ሚዛናዊነት የጎደለው መለያ ባህሪያት
ሐ.ክህሎታዊ ደህንነት ፡-ትህትና የተሞላበት መግባባትና የመረጋጋት ስሜት
1. የክህሎታዊ ደህንነት ጉድለት ፡- ትህትና የጎደለው ምልልስ እና የተጋነነ አፀፋ
3 . ብቃት
ሀ/ ስሜታዊ ብቃት ፡-ደንብን ማክበርና ልበ ሙሉነት
1.የስሜታዊ ብቃት ማነስ ፡-ደንብና ስርአትን ያለማክብረና በራስ ያለመተማመን
ለ/አእምሮአዊ ብቃት፡- የማሽከርከር መርህዎችንና መረጃዎችን ማወቅና በአእምሮ መያዝ
1. አእምሮአዊ ብቃት ማነስ ፡-በመረጃ ያልተደገፈና የተዛባ አስተሳሰብ
ሐ/ ክህሎታዊ ብቃት :-ትክክለኛ ተግባርና ጠንቃቃነት (ንቁነት]
1.የክህሎታዊ ብቃት ማነስ :-ትክክለኛ ያልሆነ አካሄድና የትኩረት ማጣት
ሀ/ ስሜታዊ ኃላፊነት
ለሌሎች ማሰብና ስነምግባራዊነት
2. ጥንቃቄ (ደህንነት)
ሀ/ ስሜታዊ ደህንነት
እራስን ማዘጋጀትና ሚዛናዊነት (እኩልነት)
ለሌሎች አውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች ሚዛናዊ ለመሆን መሞከር
የሌሎች አሽከርካሪዎችን የማሽከርከር እንቅስቃሴ ላለማስተጓጎል ፍላጎት
ማሳየት
ሌሎች አውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች ሊሰሩት የሚችሉትን ስህተት በማሰብ
ጥንቃቄና ሰፋ ያለ ግንዛቤ መውሰድ
የስሜታዊ ደህንነት ጉድለት
የሞገደኝነት ስሜትና በአጋጣሚዎች የመጠቀም ፍላጎት
ሌሎች አሽከርካሪዎችን ለመቅደም እራስን በውድድር ስሜት ውስጥ ማስገባት
በሌሎች የአውራ ጎዳና ተጠቃሚዮች ላይ የማውገዝና የቁጣን ስሜት
ማንፀባረቅ
በሌሎች አሽከርካሪዎች ተግባር የመገለልና የመፍራት ስሜትን ማሳየት
ሌሎች አሽከርካሪዎች አስገዳጅና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ መፈለግ
ለ / አእምሮአዊ ደህንነት
ሚዛናዊ መለያ ባህሪያት
ለሌሎች አውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች ሃሳብና ባህሪ ሚዛናዊና ምክንያታዊ የሆነ
ገለፃ መስጠት
ለራስ የማሽከርከር ተግባርና ስሜት ሚዛናዊ የሆነ ምክንያት መስጠት
ነገሮችን (ሁኔታዎችን) ከሌሎች የአውራ ጎዳና ተጠቃሚዎች አንፃር
መመልከት
በምናሽከረክርበት አካባቢ እየተከናወኑ ያሉትን ክስተቶች ለመረዳት
ሁኔታዎችን መተንተን
እውቀትና ግንዛቤ
አመሰግናለሁ!