You are on page 1of 20

የማሸከርከር ህግና ሰነ ሰርዓት

 ትራፊክ ማለት ማንኛውም እንቅሰቃሴ /መተላለፍ /ማለት ነው


 የትራፊክ አደጋ መንሰኤዎች በአጠቃላይ በ 3 ተ ይከፈላል
1 የአሸከርካሪ ባህሪ
2 የተሸከርካሪ ባህሪ
3 የአከባቢ ባህሪ / እግሮኞች/
1 የአሸከርካሪ ባህሪማለት የትራፊክ ህጎች ጠንቅቀው እያወቁ አለሰፈላጊ የግል ባህሪያት አደጋ ያደርሳል
 አላሰፈላጊ የአሸከርካሪ ባህሪያት
 በቸለልተኝነት ማሸከርከር
 አደንዛዥ ዝፅ ወሰዶ ማሸከርከር
 እድሜ -ወጣት አሸከርካሪ =ላይ በጣም አደጋ ይደርሳል
 አዛውንት አሸከርካሪ
2 የተሸከርካሪ ባህሪማለት የቴክኒክ አቋም ነሚገባ ካልተጠበቀና ካልተሞላ ለአደጋ ያጋልጣል
 ተሸከርካሪን ለአደጋ የሚያጋልጡ ክፍሎች
 የመቆጠቀጠርያ መሰሪያዎች ብልሸት
 የመገናኛ መሳሪያዎች ብልሸት
 የቴክኒክ አቋም መሳሪያዎች ብልሸት
3 የአከባቢ ባህሪበሚያሽከረክሩበት ጎደናላይ የሚያጋጥሙ የተለያየ የተፈጥሮ ገፅታዎችን ለኣደጋ ሊያጋልጡ ይችላሉ ::
 አላስፈላጊ የኣከባቢ ባህሪ
 አደገኛ ቁልቁለት ያለበት መንገድ
 አደገኛ ዳገት ያለበት መንገድ
 ዝናብ የሚያበዛባቸው አከባቢዎች

አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች


1 የሚያሰጠነቅቁ
2 የሚቆጣጠሩ
3 መረጃ የሚሰጡ

1 የሚያሰጠነቅቁ ፦ የመንገድ ዳር ምልክቶች- ቅርፃቸው 3 ት ማኣዝን

- መደባቸው ነጭ
- መልእክታቸው በጥቁር ቀለም

2.የሚቆጣጠሩ ፦ በ 3 ት
ንኡሰ ክፍሎች ይመደባሉ

ሀ የሚከላከሉ
ለ የሚያሰገድዱ
ሐ ቅድሚያ የሚሰጡ

ኣዘጋጅ መኣርግ

ሀ.የሚከላከሉ፦የመንገድ ዳር ምልክቶች - ቅርፃቸው ክብ


- መደባቸው ነጭ
- መልእክታቸው በጥቁር

ለ.የሚያሰገድዱ፦የመንገድ ዳር ምልክቶች - ቅርፃቸው ክብ

- መደባቸው ሰማያዊ
- መልእከታቸው በነጭ

ሐ.ቅድሚያ የሚያሰጡ፦ የመንገድ ዳር ምልክቶች - ቅርፃቸው የተለያየ

- መልእክታቸው አንድ አይነት

3. መረጃ የሚሰጡ፦ በ 2 ት
ንኡሰ ክፍሎች ይመደባሉ።

1. ራሱ መረጃ ሰጪ
2. አቅጣጫ አመልካች

አለም አቀፍ የመንገድ ላይ መሰመሮች


1. በመንገዱ አግድመት የሚሰመሩ /ዜብራ/

2. በመንገዱ አቅጣጫ የሚሰመሩ

1. በመንገዱ አግድመት የሚሰመሩ /ዜብራ/፦ አግልግሎታቸው ለእግረኞች ሲሆን በአጭር ርቀት መንገድን በፍጥነት
እንዲያቋርጡ የተሰመረ።
2. በመንገዱ አቅጣጫ የሚሰመሩ፦ አግልግሎታቸው ለተሸከርካሪ ይውላል።
 በመንገድ አቅጣጫ የሚሰማሩ፦በ 3 ት ይከፍላል።
ሀ. የተቆራረጠ መሰመር
ለ. ድፍን መሰመር
ሐ. ድፍን እና የተቆራረጠ መሰመር

 መሰመር ሲሰመር በ 2 ትቀለም ይሰመራል ።

1. በነጭ

2.በቢጫ ፦የትራፊክ መጨናነቅ ወይ አትክሮት እንድደረግበት

ኣዘጋጅ መኣርግ ሙላው

አለም አቀፍ የትራፊክ ማሰተላለፊያ መብራቶች ፦ አቀማመጣቸው ከላይ ወደ ታች ነው ።

 3 ትዓይነት ቀለሞች አለበት ።


 ቀይ
 ቢጫ
 አረንጓዴ
 የትራፊክ ማሰተላለፊያ መብራቶች በ 2 ትይከፈላል ።
1. የተሸከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራቶች
2. የእግረኞች ማሰተላለፊያ መብራቶች

1. የተሸከርካሪ ማሰተላለፊያ መብራቶች፡- በአበራራቸው 4 ትይከፈላሉ።

 ቀይ
 ቀይ አና ቢጫ
 አረንጓዴ
 ቢጫ
 ቀይ፦ረድፍን ጠብቆ የአግረኛ ማቆረጫ መሰመር ሳይረግጡ መቆም አለበት።
 ቀይ አና ቢጫ፦ቁሞ የነበሩትን ተሸ/ሪዋችን ለመሃድ ይዘጋጃሉ።
 አረንጓዴ፦ ረድፍን በመረጡበት መሄድ ይጀምራሉ።
 ቢጫ፦በመሰቀለኛ መንገድ መሀል የገቡትን በፍጥነት እንዲወጡ አና በመግባት ላይ ያሉትን ግን የአግረኛ ማቋረጫ መሰመር ሳይረግጡ
መቆም ።
 2. የእግረኛ ማሰተላለፊያ መብራቶች ፦ በአበራራቸው በ 2 ትይከፈላል።
 ቀይ የሰው ምሰል ያለበት
 አረንጓዴ የሰው ምሰል ያለበት
 ቀይ የሰው ምሰል ያለበት፦ ሲበራ እግረኞች ይቆማሉ።
 አረንጓዴ የሰው ምሰል ያለበት፦ ሲበራ እግረኞች በፍጥነት መንገድ ማቋረጥ አለባቸው።

 የተለየ የተሸ/ሪ ማሰተላለፊያ መብራት፦በአበራራቸው በ 2 ትይከፈላል።


 ቀይ
 ቢጫ

1. ቀይ፦ ብልጭ ጥፍት እያለ ሲበራ የደረሰ ተሸ/ሪይ እግረኛውን ማቋረጫ ሳያልፍ በመቆምአ

ግራ ና ቀኝ በማየት ማለፍ።

2.ቢጫ፦ብልጭ ጥፍት እያለ ሲበራ የደረሰ ተሸ/ሪ ፍጥነቱን በመቀነሰ ግራ ቀኝ አይቶ


በጥንቃቄ ማለፍ አለበት።

N.B ጥቅማቸው፦የትራፊክ ፖሊሰ የእጅ ምልክትን ተክተው ይሰራሉ ።


-ተሸ/ሪዎች ተራቸውን እየጠበቁ እንድተላለፉ ይረዳል።

የፍጥነት ወሰን /ገደብ/


* የፍጥነት ወሰን /ገደብ/ በኣገራችን በሁለት ተከፍለዋል::

- በከተማ ክልል ውስጥ


- ከከተማ ክልል ውጭ

* ከከተማ ክልል ውጭ ፈፍጥነት ወሰን በ 3 ት ንኡስ ክፍሎች ይከፈላል

ሀ ኣንደኛ ደረጃ ኣውራ ጎደና

ለ ሁለተኛ ደረጃ ኣውራ ጎደና

ሐ ሶስተኛ ደረጃ ኣውራ ጎደና

ሀኣንደኛ ደረጃ ኣውራ ጎደና:- የሚባለውኣንድንኣገር ከጎረቤት ኣገር የሚያገናኝ መንገድ ነው::

ለ ሁለተኛ ደረጃ ኣውራ ጎደና:-የሚባለው ክፈለ ኣገር ከክፍለ ኣገር የሚያገናኝ መንገድ ነው::

ሐ ሶስተኛ ደረጃ ኣውራ ጎደና:-የሚባለው ኣውራጃ ከኣውራጃ የሚያገናኝ መንገድ ነው::

ታ/ቁ የተሽክርካሪ ኣይነት በከተማ ክልል ከከተማ ክልል ውጭ


1 ደ/ኣ/ጎ

2 ኛ ደ/ኣ/ጎ 3 ኛ ደ/ኣ/ጎ
በሰኣት በሰኣት በሰኣት በሰኣት
1 ከ 0-3500 ኪ/ግ ጠቅላላ ክብደታቸው 60 ኪ/ሜ 100 ኪ/ሜ 70 ኪ/ሜ 60 ኪ/ሜ
2 ከ 3500 -7500 ጠቅላላ ክብደታቸው 40 ኪ/ሜ 80 ኪ/ሜ 60 ኪሜ 50 ኪ/ሜ
3 ከ 7500 በላይ ጠቅላላ ክብደታቸው 30 ኪ/ሜ 70 ኪ/ሜ 50 ኪ/ሜ 40 ኪ/ሜ

N.B ኣንድን ኣሽከርካሪ መገንዘብ ያለበት የተሽከርካሪ ፍጥነት እየጨመረ በሄደ ቁጥር የተሽከርካሪውን የመቆጣጠር ችሎታ እየቀነሰ ይሄዳል ::

የጉዞ መረጃ እና ሰነዶች ማሰባሰብ ፦


 ይምንሄድበትን ቦታዎች ርቀት እና የአገልግሎት መሰጫ ቦታዎችን ጠንቅቆ ማወቅ
 የመንገድ ሁኔታን ማወቅ
 ለጉዞው አሸከርካሪውንና ጉዞውን የሚያከናውነው ድርጅት ጉዞ ከመጀመር በፊት መሟላት
 የምንጓዝበት አከባቢ ባህልና ፣ቋንቋ እና ሃይማኖት ማወቅና መረዳት ያሰፈልጋል
 የጉዞ ምርጫዎች መረዳት
 ይምንሄድበትን ቦታዎች ርቀት የአገልግሎት መሰጫ ቦታዎችን ጠንቅቆ ማወቅ ፦
# የነዳጅ ጣብያ
# ሆቴል
# ሰልክ ወዘተ መታወቅ አለበት
 የመንገድ ሁኔታን ማወቅ ፦ ሰንል በምንጓዝባቸው ምንገዶች ደረጃ
# አሰፓልት
# ጠጠር
 መንገድ አቀማመጥ
# ጠመዝማዛ
# ኩርባ
# ጠባባ ድልድይ
 የአከባቢው የአየር ንብረት
# ነፋሻማ
# ደመናማ
# ፀሃያማ ወዘተ መታወቅ አለበት
 ለጉዘው አሸከርካሪውና ጉዘውን የሚያከናውነው ድርጅት ጉዞን ከመጀመር በፊት መሟላት፦
 የአሸ/ሪውና የረዳቱ
# ፓሰፖርት

# የይለፍ ደብዳቤ

# ማንጃ ፍቃድ
# መታወቅያ ወዘተ
 ከሰራው ጋራ ተዛማድነት ያላቸው ሰነዶች
# የመሄጃ ሰነድ
# ኢነሹራንሰ ሰርተፍኬት
# የአገልግሎት ሰርተፍኬት
# የጉዞ ቅደም ተከተል
# የድርጅቱ አመራር ሰርዓት ቅደም ተከተል
 የምንጓዝበት አከባቢ ባህልና ቋንቋ አና ሀይማኖት ማወቅና መረዳት ያሰፈልጋል
# የምንናገረው ነገር ሰድብ እንዳይሄን
# የምትበላው የምታደርገው ነገሮች
 የጉዞ ምርጫዎች መረዳት
# የጉዞ ማብቅያው ማወቅ
# የጉዞ አቅጣጫ አሰቀድሞ ማወቅ
# አማራጭ አቅጣጫን መረዳት

እሳት ከ 3 ትውህድ ነገሮች ይፈጠራል

1 ነዳጅ /ተቀጣጣይ/
2 ሙቀት
3 ኦክሰጅን/ንፁህ አየር/

# ከ 3 ቱ አንደም ቢጎድልም እሳት መፍጠር አይችልም፡፡

1 ነዳጅ /ተቀጣጣይ/ የሆኑ ነገሮች በ 3 ትንኡሰ ክፍሎች ይከፈላል።

i. ጠጠር ነገሮች ፦እንጨት ፣ ወረቀት፣ ጥጥ…………..


ii. ፈሳሸ ነገሮች ፦ናፍጣ ፣ቤንዚን ፣ኬሮሲን
iii. ጋዝነት ነገሮች ፦ ቡታጋዝ ፣ ሚቴን
 አሳት ለማጥፋት በ 3 ትዘዴዎች
- በማሰራብ
- በማቀዝቀዝ
- በማፈን

1. በማሰራብ፦ተቀጣጣይ ወይም ነዳጅ የሆኑ ነገሮች በማሻሸ ወይም በመራቅ እሳቱ ባለበት እንዲቀር ማድረግ ማለት ነው።

2.በማቀዝቀዝ ፦የተቀጣጠለው ነገር እንዲቀዝቅዝና ሙቀቱን እንዲቀንሰ ማድረግ ነው።

3. በማፈን ፦በመቀጣጣይ ላይ ያለው ነገር ተጨማሪ ኦክሰጅን /አየር/ እንዳያገኝ የማፈን ጠባይ ባላቸው ነገሮች መጠቀም ። ለምሳሌ ፦ኬሻ

እሳት በማጥፍያ መሳሪያዎቹ በ 4 ት ደረጃ ይከፍላል ።


ሀ. ተራ የሆኑ ተቀጣጣይ ነገሮች ናቸው ። እነሱም ፦ እንጨት ፣ ወረቀት ፣ጨርቃጨርቅ የመሳሰሉ ነገሮች ናቸው ። ለማጥፋት የምንጠቀመው
መሳርያ ውሃ ነው።
ለ. ቤንዚን ፣ ናፍጣ ፣ላንባ፣ ዘይቶችና ቅባቶች የመሳሰሉት ናቸው።

ለማጥፋት የምንጠቀመው መሳርያ፦ ድይፓውዳር ፣ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ፣ ፎም ፣ግፊት ያለው ማፈን፣ ውሃ ይቻላሉ።

ሐ. የኤሌክትሪክ እሳትና ጋዞች ሲሆኑ ለማጥፋት የምንጠቀመው መሳርያ ፦ ካርቢን ዳይ ኦክሳይድ ድራይፓውደር……….ወዘተ ናቸው።

መ. ካልሲየም፣ ፖታሸየም ፣ማግንዝየም፣ የመሳሰሉት ለማጥፋት የምንጠቀመው መሳርያ ድራይፓውደር ፣ታክኖራፕ ፣ደረቅደቃቅ አሸዋ

መሰረታዊ የተሸከርካሪ ክፍሎች


 የተሸ/ሪ አወቃቀር ከ 5 ቱየተዋቀረ ነው ።
1. ኢንጅን /ሞተር/
2. ኤሌክትሪክ ክፍሎች
3. ሀይል አሰተላላፊ ክፍሎች
4. ቻሲሰ /መሪ፣ ፍሬን፣ ተሸካሚ፣ ክፍሎች አና ጎማ……./
5. ቦዲ /የተሸ/ሪ አካል/ ኣዘጋጅ መኣርግ ሙላው

1 ኢንጅን /ሞተር/ ፦ ማለት የተለያዩ ክፍሎች አንዲንቀሳቀሱ የሚያደርግ የተሸ/ሪ ዋና ክፍል ነው።
 ኢንጅን/ሞተር/ ፦ የሙቀትን ሀይል ወደ መካኒካል ሀይል ይቀይራል
 ኢንጅን /ሞተር/ ፦ በ 3 ት ዋና ዋና ክፍሎች የተዋቀረ ነው።
ሀ. ሰሊንደር ሄድ /ቴሰታታ/
ለ .ሲሊንደር ብሎክ /ማኖ ብሎክ/
ሐ .ክራንሰ ኬዝ

ሀ.ሲሊንደር ሄድ /ቴሰታታ/

 ደብራተር
 ቫልቮትን
 ቫልቨ ጋይይትን
 ቫለቨ ሰፕሪንጎችን
 የቫልቭከቨር /ሰቶኮፓን/
 ብላንቸሪዎችን
 ካርብረተርን
 ካመቫፍትን
 የራድያተር የላይኛው ማኒኮቶ/ሆዝ/
 ሮኮርአርም
 ፊውለ ፓምፕ
 -የጭሰ ማውጫ …….የመሳሰሉት የሚታሰርበት ወይም የሚይዝ ክፍል ነው።

ለ ሲሊንደር ብሎክ /ማኖ ብሎክ/

 ሲሊንደር
 ፒሰተን
 ክራይክሻፋት /ኮሎ/፣ የዘይት ፈልትሮና ፓምፐ የተለያዩ ክፍሎች የሚታሰርበት ወይም የሚይዝ ዋነኛ ክፍል ነው።

ሐ ክራንሰ ሴዝ

 ሰቶኮፓ/አይልፓን/
 ፍላይ ዊል/ቮላኖ/
 ክራንክ ቫፋት /ኮሉ/የሚታሰርበት ክፍል ነው።

*ኢንጅን /ሞተር/ ፦ በሚጠቀመው ነዳጅ አይነቶች በ 2 ትይከፈላል።

1 የቤንዚን 2 የናፍጣ

 ኢንጅን /ሞተር/ ፦ በማቀዝቀዝ ዘዴ በ 2 ት ይከፍላል።

1 በውሃ የሚቀዘቅዝ 2 በአየር የሚቀዝቀዝ

 ኢንጅን /ሞተር/፡-የፒስተን እንቅስቃሲ በ 2 ት ይከፈላል፡፡


ሀ. ባለ ሁለት ምት እንቅስቃሲ- ማስወጣት እና ሃይል መፍጠር
- ማስገባት እና የእምቃን
ለ. ባለ ኣራት ምት እንቅስቃሲ - ማስገባት
- እምቃን
-ሃይል ምት
-ማስወጣት

ሀ. ባለ ሁለት ምት እንቅሰቃሴ ኢንጅን ፦ ማለት በአንድ ሙሉ ዙር የክራንክ ቫፍተ /ኮሎ / እንቅሰቃሴ ፒሰተን ወደታች ሲወርድ
የማሰወጣትና የሀይል ምትን እንዲሁም ወደላይ ሲወጣ የማሰገባትና የእሙቃን ሰራ የሚሰራ ነው።

ለ. ባለ አራት ምት እንቅሰቃሴ ኢንጅን ፦ በሁለት ሙሉ ዙር የክራንክ ቫፋት /ኮሎ/ እንቅሰቃሴ በማሰገባት ፣በእመቃ፣ በሀይለ ምትንና
በማሰወጣትን የሚሰራ ነው።

የኢንጅን ዋና ዋና ክፍሎችና ተግባራቸው


-ሲሊነደር - ፒሰተን ፒን -ፒሰተን ሪንግ /ፋሻዎች/ቀለበቶች/
- ፒሰተን - ኮኔክቲንግ ሮድ/ቤላ/አገናኝ ዘንግ/ - ከምሻፋት /አልብሮካም/
- ክራንክሻፋተ/ኮሎ/ -ፍላይዊል /ቨላኖ/
 ሲሊንደር ፦ጣሰ መሰል ቅርፅ ኖሮት ከላይ እና ከታች ደግሞ ክፍት ነው።
 ሲሊንደር ፦ በውሰጡ አየርና ነዳጅ ወይም አየር ብቻ በማሰገባት ከታወቀ ቡሀላ በመቀጣጠል ሀይል የሚፈጥርበት ክፍል ነው።
 ፒሰተን ፦በሲሊንደር ውሰጥ በመሆን በተለያየ ግዜ ወደላይ አና ወደታች በማለት አየርና ነዳጅ ወይም አየር ብቻ እየሳበ በማሰገባት
አምቆ ሀይል እንዲፈጥር የሚያደርግ ነው።
 ፒሰተን ፦ የተቀጣጠለውን /ጭሰ/ ከሲሊንደር ውሰጥ የሚያሰወጣ ክፍል ነው።
 ፒሰተን ፒን፦ ፒሰተን እና ኮኔክቲንዕ ሮድ /ቬላ/ አገናኝ ዘንግ ጋር የሚያያይዝ ክፍል ነው።
 ኮኔክቲንግ ሮድ /ቬላ/ አገናኝ ዘንግ ፦ ፒሰተን እና ክራንክ ሻፋትን /ኮሎ/ የሚያገናኝበፒሰተነ እናተ ላይ የሚያርፈውን ሃይል ለክራንክ
ሸፋት /ኮሎ/ የሚያሰተላለፍ ክፍል ነው።
 ፒስተን ሪንግ/ፋሻዎች/ቀለበቶች፡- ሁለት ዓይነት ፋዎሻች ኣሉት፡፡
 የእመቃ ፋሻ -ከፒሰተን እናት ማቀጣጠያ ክፍል ወደ ሰሊንደር ክፍሎች ማሀል እንዳያልፍ በማድረግ ጥሩ ጉልበት /እመቃ/ እንዲፈጠር
ይረዳል።
 የዘይት ቀቢ ፋሻ -ዘይት በመቀበት ሰበቃ/prkshen/እንዳይኖር እንዲሁም ዘይት ወደ ፒሰተን እናተ ማቀጣጠያ ክፈል እንዳያልፍ
ያደርጋል።
 ክራንሰሸፋት/ኮሎ/ ፦ወጣ ገባ ቅርፅ አለው
- የሙቀትን ሃይል መሰከሚ ይችላል.።
- ፒሰተንን በተለያየ ግዜ ወደ ላይና ወደታች የሚያንቀሳቅስ ።

- የፒሰተን ቀጥታ እንቅሰቃሴ ወደ ክብ እንቅሰቃሴ የሚለውጥ ነው።


- የውሃ ፓምፕን ፣ኮምፕሬሰርን፣የመሪዘይት ፓምፐን ፣ፋን /ቬንትሌተርን/እንዲሁም ካምቫፋትን በ 3 ትዘዴዎች ተገናኝቶ የተለያዩ
ተግባራት እንዲያከናውን የሚያደርግ ክፍል ነው።
 ካምሻፋት/አልብሮካም/ ፦በክራንክ ሻፋት /ኮሎ/ ላይ እንደ ተሸከርካሪው ዓይነት በ 3 ትሰዴዎች ይገጥማሉ።

1 ጥርሰ ለጥርሰ በመገጠም

2 በቺንግያ በመገጠም }-ሰራቸው -የኣሰገቢና አሰወጪ ቫልቨት እንዲከፈት

3 በሰንሰለት/ቼይን/ በመገጠም -የዘይትና የነዳጅ ፓምፕ እንዲሰሩ

 ፍላይዊል /ቮላኖ/ ፦ በክራንክ ሻፋት ላይ በሰተሀላ በመገጠም 3 ትተግባራት ያከናውናል


1 የሞተርን ሚዛን ይጠብቃል
2 ዙርያው ባሉት ጥርሶች ለሞተር ማሰነሻነት ያገለግላል።
3 3 ለፍሪሰዮን መገጠሚያነት ያገለግላል።

N.B በቤንዚን ሞተር ላይ የዲሰትርቢውተር ሻፋት እንዲሸከረከር ይሰራሉ።

የእንጅን /ሞተር/ አጋዥ ክፍሎች

1 የነዳጅ አሰተላላፊ ክፍሎች 2 የማቀዝቀዝ ክፍሎች


3 የማለሸለሻ ክፍሎች 4 የእሳት አቀጣጣይ ክፍሎች

1.የነዳጀ አሰተላላፊ ክፈሎች ፦ ይምንላቸው ከነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን እሰሰ ሰሊንደር ያሉትን ክፍሎች ነው።

 የነዳጅ አሰተላላፊ ክፍሎች በ 2 ትይከፋላል።


1 የቤንዚን ነዳጅ 2. የናፍጣ ነዳጅ
የቤንዚን ነዳጅ ኣስተላላፊ ክፍሎች
 ሳልቫትዮ ፦ የነዳጅ ማጣርያ /ፈልትሮ / - የነዳጅ ፓምፐ/ ፓምፔታ/
 ሳልቫትዮ ፦የነዳጅ መጠራቀምያ በውሰጡ ማጣርያ እና የነዳጅ መጠንን የሚያሳይ መሳርያ የሚይዝ ክፍል ነው።
 የነዳጅ ማጣርያ /ፈልትሮ/ ፦ ወደ ካርቡሬተር ና ወደ ሲሊንደርየሚገባውን ነዳጅ አጣርቶ የሚያሰተላልፍ ክፍል ነው።
 የነዳጅ ፓምፐ /ፓምፔታ/ ፦ ነዳጅን ከነዳጅ ማጠራቀሚያ በመሳብ በግፊት ወደ ካርቡሬተር የሚሰተላልፍ ክፍል ነው።
 የነዳጅ ፓምፐ /ፓምፔታ/ በ 2 ትመንገድ ይሰራል።
1 በኤሌክትሪክ 2 በመካኒካል
 ካርቡሬተር ፦ እንደ ሞተር እንቅሰቃሴ አየርና ነዳጅን መጥኖና ቀላቅሎ ወደ ሲሊንደር የሚያሰተላልፍ ክፍል ነው።
 ቾክ ቫልቨ ፦በካርቡሬተር በላይኛው ክፍል በመገጠም የአየር ማሰገቢያን ለመዘጋት ወይም ለመክፈት የሚያገለግል ክፍል ነው።
 ቾክ ቫልቨ ፦ጥዋት በቅሰቃሴ ግዜ ሞተር ሰናሰነሳ የአየሩ መጠን አነሰ ብሎ የነዳጅ መጠን መብዛት ሰላለበት የአየር ማሰገቢያን
በመዝጋት ሞተር ቶሎ እንዲነሳ የሚያደርግ ክፍል ነው።
 ቾክ ቫልቨ ፦በ 2 ት ዓይነት ይሰራል።
1. ብአውቶማቲክ 2. ብመካኒካል
 ፍሎት ቦል/ተንሳፋፊ ኳሰ/፦ በካርቡሬተር ውሰጥ መጠኑን የጠበቀ ነዳጅ እንዲ ዋር የሚቆጣጠር ክፍል ነው።
 ኒድል ቫልቨ ፦በፍሎት ቦል አማካኝነት ወደ ሲሊንደር የሚሄደውን ነዳጅ በመዝጋትና በመክፈት የሚያሰተላልፍልን ክፍል ነው።
 ቬንቹሪ ወይም ጠባቡ የካርቡሬተር ጎሮሮ፦በካርቡሬተር ውሰጥ አየርና ነዳጅ ተመጥነው የሚደባለቁበት ክፍል ነው።
 ትሮትል ቫልቭ ፦ከነዳጅ መሰጫው ፔዳል ጋር የተያያዘ ሆኖ በቬንቹሪ ውሰጥ የተቀለቀለው ወደ ሲሊንደር ውሰጥ ሲገባ መጠኑን
ለመጨመርና ለመቀነሰ ይምንጠቀምበት ቫልቭ ነው።
 የአየር ማጣርያ /ድብራቶር/ የላይኛው ክፍል ላይ በመሆን 3 ትተግባራት ያከናውናል።
1 ወደ ካርቡሬተር /ሲሊንደር /አየር ያጣራል።
2 በካረቡሬተር አናት በኩል የሚነሳውን አሳት ያሰቀራል።
3. ከሞተር አከባቢ ሊነሳ የሚችልን ድምፅ አፍኖ ያሰቀራል።
 አየር መጣርያ /ድብራቶር/፦በ 3 ትመንገድ ይሰራል።
ሀ. በደረቅ /ካርቱሸ/
ለ. በዘይት
ሐ. በደረቅ አና በዘይት

N.B በናፍጣ ሞተር ፦ካርቡሬተር የለውም ሰለዚ አየር ማጣርያ የሚገጥመው

በአሰገቢ አንገት ነው።

የናፍጣ ነዳጅ አሰተላላፊ ክፈሎች


 ጋን /ሳልቫትዮ/
 መጋቢ ፓምፐ/ፋድ ፓምፐ/
 ነዳጅ ማጣርያ /ፈልትሮ/
 ኢነዳከሸን ፓምፐ/ፓምፐ ኤቮቶሪ/
 ኢንዳክሸን ኖዝል /ኢኖቶሪ/
 መላሸ መሰመር
 ካንዴሌት /ግሌው ፕላግ/
 ጋን/ ሳልቫትዮ/፦ነዳጅ የሚይዝ ዕቃ ነው።
 መጋቢ ፓምፐ /ፈድፓምፐ/፦ከጋን /ሳልቫትዮ/ በመሳብ በአንሰተኛ ግፊት ወደ ኢንጄክሸን ፓምፐ የሚልክ ነው።
 ነዳጅ ማጣርያ /ፈልትሮ/፦ ነዳጅ ለማጣራት ወደ ኢንጄክሸን ፓምፐ የሚልክ ክፍል ነው።
 ነዳጅ ማጣርያ ፦በናፍጣ ሞተር ላይ በ 2 ትይከፈላል።
1 የመጀመርያ ነዳጅ ማጣርያ
2 ሁለተኛ ነዳጅ ማጣርያ

N.B በናፍጣ ሞተር ነዳጅ ማጣርያ ላይ ሁለት ማጣርያ የሰፈለገበት ምክንያት ናፍጣ ቆሻሻ የመሳብ ባህር ሰላለው ነው።

 ኢንጄክሸን ፓምፐ/ፓምፐ ኤሾቶሪ/፦ ከመጋቢ ፓምፐ /ፈይን ፓምፐ/ በአነሰተኛ ግፊት የሚመጣው ነዳጅ ተቀብሎ በከፍተኛ ግፊት ወደ
ኢንጆክተር ኖዝል /ኢናቶሪ/ በቅድም ተከተል በተወሰነ ግዜ የሚያሰተላልፍ ክፍል ነው።
 ኢንጀክተር ኖዝል /ኢኖቶሪ/፦ከኢንዳክሸን ፓምፐ ከፍተኛ ግፊት ተገፍቶ የመጣውን ነዳጅ ተቀብሎ በጉም /በተንት/ መልክ ወደ ሲሊንደር
ውሰጥ የሚረጨ ክፍል ነው።
 መላሸ መሰመር፦በኢንጀክተር ኖዝል /ኢኖቶሪ/ ላይ በመሆን ትርፍን ናፍጣ በማሰብሰብ ወደ ነዳጅ ማጠራቀምያው ጋን የሚመልሰ ክፍል
ነው።
 ካንዴሊቲ /ግሎውፕላግ/፦ በናፍጣ ሞተር ሲሊንደር ውሰጥ ተጨማሪ ሙቀት እንዲፈጥር ለማድረግ ሞተር ተሎ እንዲነሳ የሚረዳ ክፍል
ነው።
ለነዳጅ አሰተላላፊ ክፍሎች መደረግ የሚገባ ጥንቃቄ
 የነዳጅ ክፍሎች በንፅህና መያዝ
 መሰመሮቹ በጥብቅ የታሰሩና የማይፈሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ
 የነዳጅ ጋን ብትክክለኛ ክዳኑ መክደን አለበት ምክንያቱ ነዳጅ ንፋስ እንዳያባክነው እሳት እንዳይፈጠር
2. የማቀዝቀዝ ክፍሎች

 ኢንጅን /ሞተር/ ፦ በሁለት ዓይነት መንገድ ይቀዘቅዛል።


1 በአየር 2 በውሃ

1.በአየር የማቀዝቀዝ ዘዴ፦ ከፍተኛ ሙቀት የሚፈጥርበት ሲሊንደር አከባቢ የሚገኑ ፈንሶች /ሸንሸን ብረት/ ውሰጥ አየር በመዘዋወር
ሙቀትን ይቀንሳል።

2.በውሃ የማቀዝቀዝ ዘዴ ፦ ከፍተኛ ሙቀት በሚፈጥርበት ሲሊንደር አከባቢ በሚገኝ የውሃ ቦይ /ወተር ጃኬት/ ውሰጥ ውሃ በመዘዋወር
ሞተር የሚቀዘቅዝበት ዘዴ ነው ።
በውሃ የሚቀዘቅዝ ኢንጅን /ሞተር / ዋና ዋና ክፍሎችና ተግባራቸው ።
 ራድያተር፦ ውሃ ይሸከማል ። ከሞተር ሙቀት ተሸክሞ የተመለሰውን ውሃ በፈን /ቬንትሌተር/ አማካኝነት ለመቀዝቀዝ የሚያሰችል
ቱቦና የተሸነሸነ ብረት የለው ክፍል ነው።

የራድያተር ክዳን- በራድያተር ውሰጥ ያለውን ውሃ ወደ ውጭ እንዳይፈስ ይዘጋል።

- ሞተር በሚሰራበት ግዜ በአንሰተኛ ግፊት ውሃ ወደ ውጭ እንዳይባክንና ከፍተኛ ሙቀት ሲፍጥር ሞተር ከመጠን በላይ እንዳይሞቅ
በሙቀት ምክንያት የተፈጠረውን ግፊት በአሰካሪኮ በኩል የሚያሰወጣ ፓልቭ ነው።
- ሞተር ከጠፋ ቡሃላ በራድያተር ውሰጥ ያለው ውሃ በተን መልክ ሰለሚወጣ በራድያተር ውስጥ ቫኪውም /ባዶ ቦታ/ እንዳይፈጠርና
የዚህ ባዶ ቦታ መፍጠር ራድያተሩን ሊያጨማድደው ሰለሚችል ቫልቭ በመክፈት ከአከባቢው አየርና ወይም ከሪዘርቨየር ውሃ ወደ ራድያተር
እንዳያሳልፍና እንዳይጨማደድ የሚያደርግ ክፍል ነው።
 የውሃ ፓምፐ/ፓምፐ ዲላኳ/፦ ሞተር ከተነሳ ብሃላ በራድያተር ውሰጥ ያለውን ውሃ በማቀዝቀዝ ክፍሎች አንዲዘዋወር ያደርጋል።
 ዋተር ጃኬት /የውሃ መተላለፊያ ቦይ/ ፦ በሞተር ውሰጥ የሚዘዋወርበት ክፍል ነው።
 ቬንት ሌተር /ፋን/ ፦ በመካኒካል ወይም ኤሌክትሪካል ሃይል እየሰራ ራድያተርና የሞተር አከባቢን የሚያቀዘቅዝ ክፍል ነው።
 ቴርሞሰታት ፦ የውሃ መንገድ መዝጊያና መክፈቻ ቫልቭ ሲሆን የሞተሩ የመሳርያ ሙቀት መጠን እሰከሚደረሰ ድረሰ መሰመሩን
በመዝጋት ውሃ ከሞተር ወደ ራድያተር እንዳያልፈ ዘግቶ የሚቆይ መሳርያ ነው።
 በአንድ ራድያተር ላይ ሁለት ዓይነት ሆዝ /ማኒኮቶ/ መሰመር ይገኛል።
1 ወሳጅ መሰመር /ወሳጅ ሆዝ / ወሳጅ ማኒኮቶ ፦ ከራድያተር ውሃ ወደ ሞተር የሚያሰተላልፍ መሰመር ነው።
2 መላሸ መሰመር /መላሸ ሆዝ/ መላሸ ማኒኮቶ ፦ የሞቀ ውሃ ከሞተር ወደ ራድያተር የሚያጓግጨጉዝ መሰመር
ነው።

የማለሰለሻ ክፍሎች ፦ ኢንጅን የሚለሰልሰው በዘይት ነው።

 ሞተር ውሰጥ የተለያዩ እንቅሰቃሴዎች የሚያደርጉ ክፍሎች ይገኛሉ።


 ዘይት በሞተር ውሰጥ በመዘዋወር ብዙ ሰራዎች ያከናውናል ።
 ሰበቃን ይቀንሳል
 ድምፅን ይቀንሳል
 ሙቀትን ይቀንሳል
 ዝገትን ይከላከላል
 ቆሻሻን ይፀዳል -
 ጥሩ እመቃና ጉልበት እንዲኖረው ያደርጋል።
 ዘይት በሞተር ውሰጥ በሁለት ዓይነት መን ገድ ይሰራጫል።
1 በክራንክ ሻፋት ርጭት /በመጨለፍ/
2. በአይል ፓምፐ ግፊት
የማለሸለሻ ዋና ዋና ክፍሎች ተግባራቸው
 አይል ፓን /ሰቶኮፓ/ ፦ የሞተር ዘይት መያዝ ነው። በውሰጡ መጣርያና ዲፕሰቲክ የሚይዝ ክፍል ነው።
 ኦይል ፈልተር /የዘይት ፈልተር/፦ ከአይልፓን የመጣለትን ዘይት ተቀብሎ አጣርቶ ወደ ኦይል ጋላሪ የሚያሰተላልፍ ክፍል ነው።

 የዘይት መሰመር ፦ ዘይትን ከኦይል ፓን እሰከ ሮከር እርም ድረሰ የሚያሰተላልፍ መሰመር ነው።
 እሰክሪነር /የመጀመርያ ማጣርያ/ ፦ ኦይል ፓን ውሰጥ የሚገኝ ሲሆን ዘይትን አጣርቶ ወደ ዘይት ፓምፐ የሚያሰተላልፍ ክፍል ነወ።
 ዲፕሰቲክ /ሊቤሎ/ ፦ በሰቶ ኮፓ /አፐይል ፓን / የሚቀመጥ የይት መጠንን እና የዘይት መቆሸሸ ወይም ውፍረት ቅጥነትን
ይምንመለከትበት ዘንግ ነው።
 የዘይት ግፊት አመልካች/ጌጅ/ ፦ በዳሸ ቦርድ ላይ የሚገኝ ሲሆን ዘይቱ በሞተር ውስጥ መዘዋወሩን የሚጠቁም መሳርያ ነው።

ለማለሰለሻ ክፍሎች ማድረግ የሚገባቸው ጥንቃቄ

 የማለሰለሻ ክፍሎችን ብንፅህና መያዘ


 ማንዋሉ በሚይዘው መሰረት ዘይት መለቀጥ
 ቀላል ሰራ ለሚሰሩ ተሸ/ሪዎች ከ 2 – 3 ወር መቀየር ቀይም በየ 5000 ኪሜ
4.የተሸ/ሪ ኤሌክትሪክ ክፍሎች
 የተሸ/ሪ ኤሌክትሪክ ክፍሎች በ 4 ትይከፈላል።
1 እሳት የማቀጣጠል ዘዴ /ኢግኒሸን ሲሰተም/
2 የማሰነሳት ዘዴ /ሰታርቲንግ ሲሰተም/
3 ባትሪን የሞሙላት ዘዴ /ቻርጂንግ ሲሰተም/
4 4 የተለዩ የመብራት ከፍሎች /ላይቲንግ ሲሰተም/
የእሳት አቀጣጣይ ዘዴ ዋና ዋና ክፍሎችና ተግባራቸው
 ኢግኒሸን ኮይል /ቦቢና/ ፦ ከባትሪ አነሰተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ወሰዶ ወደ ከፍተኛ የሚለውጥ ለዲሰትሪቢውተር /አቫንሰ /
የሚያሰተላልፍ ክፍል ነው።/ከባትሪ ከ 6-12 ቮልት ወሰዶ ከ 10.000-30.000 ቮልት ያባዛል።
 ዲሰትሪቢዩተር /አቫንሰ/ አገልግሎቱ፦
 ከኢግኒሸን ኮይል /ቦቦና/ እና በባትሪ /ቁልፍ/ መካከል የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲኖር ወይም እንዳይኖርው /እንዲቋረጥ/ማድረግ
 ከኢግኒሸን ኮይል/ቢቢና / የመጣልተን የተበዛ የኤሌክትሪክ ሀይል በክፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ ሸቦዎች አማካኝነት ለእሰፓር ፕላግ
/ካንዴላ/ ይሰጣል።
 በዲሰትሪቢዩተር /አቫንሰ/በውሰጡ የተለያዩ ክፍሎች አሉት።
 ሮተር /ሰፓሶላ/፦ በዲሰትሪቢውተር ሻፋት ላይ በመሆን እየተሸከረከረ ከቦቢና የመጣው ሀይል ለካንዴላ ገመይች በየተወሰነ ጊዜ በየተራ
ያከፋፍላል።
 ኮንታክት ፓይነት /ፑኒትና /፦ የኤሌክትሪክ ሀይል አማካኝቶ በመያዝ ኮንታክት ፓይነት /ፑንቲና / እንዳይቃጠል የሚከላክል
መሳርያ ነው።
 ካንዴላ /እሰፓርክ ፕላግ/፦ በዲሰትሪቢዩተር ና ካንዴላ ገመድ አማካኝነት የተቀበለውን በሲሊደር ውሰጥ በታመቀው /የአየር
ና የቤንዚን / ድብልቅ የእሳት ብልጭታ በመፍጠር እንዲቃጠልና ሀይል እንዲያገኝ ያደርጋል።

ሞተርን የማሰነሳት ዘዴ /ሰታርቲንግ ሲሰተም/

 ባትሪ
 ቁልፍ /ኳድሮ/
 ሰታርተር ሞተር /ሞተሪኖ/
 ባትሪ ፦ ሰነፍታ ነገቲፕ /-/ ወይም ቀጭናን
 ባትሪ ፦ ሰናሰር ፖዘቲብ /+/ ወይም ፍፍራውን
 ባትሪ ፦ ሞተር ሳይነሳ በተሸከርካሪ ላይ የሚገኑ የኤሌ/ሪክ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ሀይል ይሰጣል።
 ባትሪ ፦ የመጀመርያ የኤሌክትሪክ ሀይል የሚፈጠርበት ነው።
 ባትሪ ፦የኬሚካል ጉልበት ወደ ኤሌክትሪካል ጉልበት የሚቀይር ነው።
 ባትሪ ፦በውሰጡ አሲድና ውሃ የያዘ ነው /አሲድ 35% ውሃ 65%

 ቁልፍ (ኳድሮ)፦ ሞተርን በማሰነሳት የሚያሰፍልገውን የኤሌክትሪክ ሀይል ከባትሪ የሚወሰደው ነው።
 ቁልፍ (ኳድሮ) ፦ወደ ተለያየ ክፍሎች ኤሌክትሪክ ያሰገኛል።
 ሰታርተር ሞተር(ሞተሪኖ)፦ ከባትሪ የወሰደውን የኤሌክትሪክ ሀይል ወደ ሚካኒካል ሀይል ይለውጣል።
 ሰታርተር ሞተር (ሞተሪኖ)፦ ሞተርንለማሰነሳት የሚያገለግል ክፍል ነው።

ባትሪን የመሙላት ዘዴ ( ቻርጂንግ ሲሰተም)

 ዲናሞ (ጄኔሬተር) ፦ በቺንግያ አማካኝነት ሰኮሎ መካኒካል ሀይል ወደ ኤሌክትሪካል ሀይል በመለወጥ ባትሪን ቻርጅ
ያደርጋል።
 የኤሌክትሪክ ሬጉኬተር ፦ ጀኔሬተር እያመነጨ የሚያሰተላልፍውን የኤሌክትሪክ ሀይል ባትሪ ሰልክ በላይ ቻርጅ እንዳይሆን
የሚቆጣጠር መሳርያ ነው።

የተለያየ የመብራት ክፍሎች (ላይቲንግ ሲሰተም)


 መብራት፦ይግንባር (የፊት) እና የሃላ
 ፍሬቻ ፦ የግሪና የቀኝ
 ጡርንባ፦በንፋሰና በኤሌክትሪክ የሚሰራ
 የዝናብ መጥረግያ፦የኤሌክትሪከ ሀይል ወደ መካኒካል ጉልበት በመቀየር የሚሰራ አካል ነው
 ፈውዝ ፦ ራሱን በመቃጠል ሊላ የኤሌክትሪክ መሰመርን ያድናል
የሀይል አሰተላላፊ ክፍሎች
 ፍሪሲዮን (ክላች) ፦ ሀይል እንዲተላለፍና እንዲቆርጥ የሚያደርግ ነው።

የፍሪሲዮን ዋና ዋና ክፍሎች

1 ቮላኖ (ፍላይዊል) 4 ፕሬዥር ፕሌት (ፕላቶ)


2 የፍሪሰዮን ሸራ (ዲሰክ) 5 ሪሊዝ ፈንገር (ጣት)
3 የፍሪሰዮን ፔዳል 6 ሪሊዝ ቤሪንግ( ሪጅሰፒንታ)
i.
ፍሪሰዮን በ 3 ትዓይነት ይሰራል
1 መካኒካል (በካቦ)
2 በዘይት
3. በዘይትና አየር /ልዩ ቅንብር/
 ጊር ቦክሰ (ካምቢዮ) ፦ነጂ ጥርሰና ተነጂ ጥርሰ የሚይዝ ነው።
 ጊር ቦክሰ (ካምቢዮ)፦ በ 3 ትተግባር ይሰራል።
 ጉልበት ያሰገኛል ፦ ተነጂ ጥርሰ ለነጂ ጥርሰ ሲያሸከረክር (ከባድ ማርሸ)
 ፍጥነት ያሰገኛል ፦ ነጂ ጥርሰ ለተነጂ ጥርሰ ሲያሸከረክር (ቀላል ማርሸ)
 አቀጣጫ ለውጥ ፦ሰወሰቱ ጥርሰ ሲነዳዳ የኣቅጣጫ ለውጥ ያስገኛል
 ፕሮፔላር ቫፋት (ትራንሰ ሚሰዩን )፦ ከጊር በክሰ ሀይል ተቀብሎ ላይፈረንሻል ያቀብላል።
 ፕሮፔላር ቫፋት (ትራንሰ ሚሰዩን ) ፦ ሁለት መጋጠሚያዎች ሻፋት አሉት።
1. ዩኒቨርሳል ጀይነት (ኮሬቼራ) ፦ በተለያዩ ሁኔታዎች ፕሮፔለር ሻፋት አንዳይሰበርና እንዳይጣመም ይከላከላል።
2.ሰሊፕ ጀይንት (ተንሸራታት መገናኛ)፦ ነጊር ቦክሰና በዲፈረንሺያል መሀክል የሚያጠረውን ርቀትና ቅርበት በማሰተካከል
እንዳይሰበርና እንዳይጣመም ይከላከላል።
 ዲፈረንሺያል፦ ክትራንሰሚሲን የተቀበለውን ሃይል ለሸሚታሰ (ለአክሰሰ) በሚከተለው መንገድ ያሰተላልፋል።
 ሃልን ለሁለቱም ሸሚያሶች እኩል ይሰተላልፋል።
 ከትራንሰሚሰዩን የተቀበለውን ክብ ዙር ወደ ቀጥታ ተጎማ ዙር ይለውጣል።
 የጎማ ዙርን በኩርቭ ( በኩርባ መንገድ) ላይ ያበላልጣል።
 አክሰል (ሸሚያዝ) ፡- ከዲፈረንሺያል ሃይል ተቀብሎ ለጎማ ነማሰተላለፍ ተሸከርካሪ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሰ ይረዳል።
 ሮዴታ (ኦግዚለር)፦ትራንሰሚሸን የካምቢዩ ረዳተ በመሆን (ተጨማሪ ጉልበት) በጭቃ ፣ በሚያነሸራትት መንገዶች ላይ ፣
አሰቸጋሪ በሆነ ቦታ ላይ በፊተኛው ወይም በኀለኛው ጎማዎች ኃይል እንዲተላለፍ በማድረግ ተሸከርካሪ ከችግር እንዲወጣ
የሚያደርግ ነው። ኣዘጋጅ መኣርግ ሙላው
የሮዴታ ማርሸ አጠቃቀም
H2 ለኖርማል አነዳድ
H4 ክፍተኛ የሆነ ፍጥነት እና አሸዋማ እና የሚያዳልጥ መንገድ ላይ ሰናሸከረክር
L4 ክፍተኛ የሆነ ጉልበት ( ለጭቃ እና እደገኛ ዳገት) መጠቀም ሰንገልግ
 H4 ወደ L4 ወይንም ከ L4 ወደ H4 የማርሸ መለዋወጫ ዘንጉን ሰናንቀሳቅሰ ተሸከርካሪው ሙሉ በሙሉ ቆሞ በመሆን አለበት።
 ኣውቶማቲክ ካምቢዮ፦ የተገጠመለት ተሸከርካሪ ፈሪሰዮን ፔዳል የሌላው የሰውን ደካም ለመቀነሰና ተሸከርካሪ ያለእግባብ ማሸ
በሚቀያየር ጊዜ እንዳይጐዳ በአጠቃላይ ምቾት እንዲኖረው ታሰቦ የተሰራ ነው።
የኣውቶማቲክ ትራንሰሚዩን ሲሰተም ማርሸ አጠቃቀም
 ፓርኪንግ፦ ተሸከርካሪውን ሰናቆም
 ድራይቭ ፦ ተሸከርካሪውን ወደፊት ሰናሸከረክር
 ኒውትራል፦ ሞተር ለማሰነሳት ስንፈልግ
 ሪቨርሰ ፦ ወደ ኃላ ማሸከርከር ሰንፍልግ
 ሎው ድራይቭ ፦ ጉልበትን መጠቀም ስንፈልግ

የማሸከርከር ሰነ ባህሪ

 ሰነ ባሀሪ ፦ ማለት የሰዎች አና የእንሰሳተ ባህሪይ የሚያጠና ዲሲፒሊን ነው።


 ሰነ ባሀሪ ፦ ባህሪ አና የአዕምሮ አሰተሳሰብ የሚያጠና ዲሲፒሊን ነው።
 ሰነ ፦ ማለተ ሰነየ ከሚለወ የግዕዝ ቃለ የተቀሰደ ነው ። ትርጉሙ መልካም ፣ ጥሩ፣ ውበት፣ ቆንጆ ነው።
 ባሀሪ ፦ የሰው አሰተሳሰብ ፣አመለካከትና ድርጊት ውጤት ነው።
 ባህሪ፦ የሰው ልጅ የውርሰ ፣የአከባቢ የጋራ ውጤት ነው።

የሰነ ባህሪ ግቦች


 ባህሪን መግለፅ
 የተለያዩ ባህሪያትን መንሰኤ ማብራራት
 ወቅታዊ የባህሪን ሁኔታን ከግምት ውሰጥ በማሰገባት የወደ ፊቱን መተንበይ
 የሰው ልጅ መላካምና መጥፎ ባህሪያት አለው።
 መልካሙን ባህሪ ማዳበር አለበት።
 መጥፎውን ባህሪ ማሰወገድ አለበት።
የማሸከርከር ሰነ ባህሪ
 ማሸከርከር ፦ - ሙያ ነው
- ችሎታ ነው
- ብቃት ነው

 ማሸከርከር የኣእምሮና የጉልበት እንቅሰቃሴ ነው።


 የማሸከርከር ሰነባህሪ ፦በሚያሸከርክሩበት ወቅት የሚያሳዩትን ባህሪ የሚያጠና የሰነ ባህሪ ዘርፍ ነው።
የማሸከርከር ሰነ ባህሪ ጠቀሜታ
 ትህትና - ማሳየት አለብን።
 ርህራሄ- አዛኝነት መሆን አለብን
 እንደ ዜጋ ህግና ደንብ አክባሪ መሆን - ማንኛውን እንቅሰቃሴ ማክበር
 ክሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች - ቤተሰባዊነት እይታ መፍጠር።
 የፈጠራ የአነዳድ - ልምምዶችን ግኝቶችን ማዳበር።
 የሌሎችን ሰሜት- መረዳት
የማሸከርከር ሰነ ባህሪያዊ ጉዳዮች
1.ዝግጅነት - የራሰህ ጤንነት
-የተሸ/ሪ ጤንነት
-የመንገድና የአየር ሁኔታ

2.መነቃቃት ፦ ባሀሪን ወደ ግብ የሚያንቀሳቅሰ ሂደት ነው።


-ለራሳችን ለማሸከርከር ሙሉ ፈላጎት ያሰፈልጋል።
3.መረጃ መሰብሰብ ፦ በሰሜት ህዋሳቶች መረጃ መሰብሰብ ወደ ኣምሮ መላክ ።
-ማየት - 80-90%
-መሰማት
በሰሜት ሕዋሳት - ማሸተት } 10-20%
-መቅመሰ

ሀ .ግንዛቤ ፦ ማለት መረጃውን ሰብሰቦ ወደ አእምሮ መላክ።


ለ .ትኩረት ፦ ከተላከውን መረጃ ትከክለኛውን /የሚያሰፈልገውን/ መምረጥ ፡፡
ሐ .ማሰተዋል ፦ ትኩረት የተደረገበት /የመረጥውን /መረጃ መተግበር ነው።
ማሰተዋል ፦ ውሳኔ መሰጠት መተርጎም ነው።

በሰሜት ሕዋሳቶች መረጃ መሰብሰብ የመተርጎም ሂደት

ግንዛቤ ትኩረት ማሰተዋል ማድረግ/መሰራት


መላክ መምረጥ መተርጎም/ መፈፀም

የባህሪ መለወጥ መንሰኤዎች


 ከተፈጥሮ የሚወረሰ
 አከባቢያዊ ሁኔታዎች
 አካላዊ ሁኔታ
 ሀይል ሰሜታዊ ውጥረት
 ሰልጠና
 ከተፈጥሮ የሚወረሰ ፦ ከቤተሰብ የወረሰናቸው ባህሪያት አመለካከት ፣ አሰተሳሰብና እንቅሰቃሴ ተፅዕኖ አላቸው
 ኣከባኒያዊ ሁኔታዎች ፦ የምንኖርበት ቦታ ፣ የሕ/ሰብ ሁኔታ ፣ የሀዝቡ የሚናገረውና የሚያደርገው ነገሮችን ያካትታል።
 አካላዊ ሁኔታ፦ለባህሪ መለወጥ መንሰኤ ነው።
1. ለምሳሌ ፦ በሕመም ፣በእርጅና ፣በወጣትነት
 ሀይል ሰሜታዊ ውጥረት፦ውሰጣዊ ፍላጎትን ፣ ፍቅርን፣ ጥላቻን፣ ሓዘንን ብሰጭትን ወ.ዘ.ተ ያመለክታል
 ለሰዎች ይሁን ለነገሮች ከምንፈልገው በላይ በሚሆንበት ወቅት ቀደ ሀይል ሰሜት ውጥረት ይከተናል።
 ሰልጠና ፦ የሰው ልጅ በሰለጠነበት የሙያ መሰክ የባህሪ ለውጥ መንሰኤ ነው።

የአሸከርካሪዎች ሙያዊ ሰነ ምግባር

 ሙያ ፦ ክቡር ነው ። የሆነ ይሁን ሙያ።


 ሙያ ፦ በትምህርትና በሰልጠና የሚገኝውን እውቀት ፣ክህሎትና አሰተሳሰብን በመጠቀም ለሕ/ሰቡ ተገቢውን ግልጋሎት መሰጠት ነው።
 ሰነ ምግባር፦መልካምና መጥፎ ለመለየት የሚያሳችለን ነው።
መልካሙን ሰነ ምግባር እንዴበርታታና እንዴያድግ ማድረግ
መጥፎውን ሰነ ምግባርንጨ ርሰን መተው አለብን።
 የሙያ ሰነ ምግባር፦ማለት በተሰማራንበት ሙያ የምንሰራውን ሰራ አመርቆ ውጤታማና ሰነ ሰርዓቶቻችን የተጠበቀና መልካም መሄን
አለብን።
ሙያዊ ሰነ ምግባራቸውን አክብረው የሚያሸከረክሩ አሸከርካሪዎች የሚከተሉትን ያከናውናል

 ከነዳ አይጠጡም ፣ ከጠጡም አይነዱም


 መድሀኔት ወሰደው አያሸከረክሩም
 ያለ ምንም ዕረፍት ከ 4 ትሰዓት በላይ አያሸከረክሩም
 የእንቅለፍ ሰሜት በተሰማቸው ጊዜ ሙሉ ዕረፍት ይወሰዳሉ።
 ሰለ ጉዞአቸው ዕቅድ ያወጣሉ

የአሸከርካሪዎች አላሰፈላጊ ባህሪያት

 ሞገደኝነት
 ራሰ ወዳድነት
 ሃይል ሰሜታዊ
 አለመረጋጋት
 ቸልተኝነት
 ትኩረት ለመሳብ መሞከር (ልታይ ልታይ ባይነት)
 ሃላፊነትን መዘንጋት
 ሱሰኝነት ወዘተ

የአልኮል መጠጥ ጠጥቶ የሚያሸከርከር አሸከርካሪ ባህሪያት

 በራሱ ረድፍ ውሰጥ ያለመቆየት


 በከፍተኛ ፍጥነት ማሸከርከር
 በጣም ዝግ ባለ ፍጥነት ማሸከርከር
 የአልኮል መጠጥና የትራፊክ አደጋ፦ 44% የሚሆነው አደጋ የሚደርሰው የአልኮል መጠጥ ጠጥተው በሚያሸከረክሩ
አሸከርካሪዎች ነው።

# የትራንሰፖርት ደንብ ከጠጡ አይንዱ ከነዱ አይጠጡ የሚለውን ህግ ተከትለን ከአደጋ መቀነሰ አለብን።

ሞገደኛ እና ክልፍልፍ አነዳድ

# ሞገደኛ አነዳድ - ማለት በተደጋጋሚ በመጥፎ ሰሚት ውሰጥ የሚያሸከረክር ነወ


# ክልፍልፍ አነዳድ - ማለት በረድፍ የማይፀና ነወ፡፡

የሞገደኛ አነዳደ ችግሮች በዋናነት የሚካተሉት ናቸው

 ኣልኮል ወሰዶ ማሸከረከር


 ኣደንዛዥ ዕፅ ወሰዶ ማሸከርከር
 ከባደ መድኃኒት ወሰዶ ማሸከረከር
 በእንቅልፍ ስሚት ውስጥ ሁኖ ማሸከርከር
 በድብርት ሰሚት ሁኖ ማሸከረከር
 በከባድ ህመም ሁነው ማሸከርከር
 ተናደወ ናተበሳጭተው ማሸከረከር
 በፍርሃት ና በጭንቀት ማሸከረከር
 በሀሳበ ተጠምደው ማሸከረከር

የሞገደኛ ኣነዳድ ችግሮች

 የሞገደኛ ኣነዳድ- ሂደት በ 3 ት ክፍሎች ማየት


1. ትዕግሰት ማጣት ና ትኩረት ኣለመሰጠት
2. ተፅዕኖ የማድረግ ትግል
3. ግድ የለሸነት እና በመንገድ ላይ ፀብ

1. ትግሰት ማጣት እና ትኩረት አለመሰጠት

 የትራፊክ መብራትን አለማክበር -ቀይ መብራት መጣሰ


ቢጫ መብራት እያበራ ፍጥነት አለ መቀነሰ
 ያለ ኣግባቡ ረድፍን መቀየር -በድፍን መሰመር ላይ
ዙሮ የማይመለሰበት ቦታ መመለስ
 ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሸከርከር

2. ተፅዕኖ የማድረግ ትግል

 መንገድ በተሸከርካሪ መዝጋት


 ለመቀበል ተሸከርካሪን በድንገት ማቋረጥ
 ለበቀል ሰሜት በድንገት ፍሬን መያዝ

3. ግድየልሸነት እና የመንገድ ላይ ፀብ

 በአልኮል ተመርዞ ማሸከርከር


 በከፍተኛ ፍጥነት ማሸከርከር
 መሳርያ መደቀን ወይም መተከሰ

ሞገደኛ አሸከርካሪ ሲያጋጥሞት ማድረግ ያለብዎት ክንዋኔዎች

 ረድፍዎን ላለመልቀቅ ሲሉ ፍክክር ውሰጥ አለመግባት


 ፀያፍ ሰድቦችንና ምልክቶችን ችላ ማልት
 የአይን ለአይን ግንኝነትን ማሰወገድ
 ሳይበሳጩ ዘና ብለው ሁኔታዎችን መከታተል
 ችግሩን ሳይባብሱ በሰላም ለመጨረሰ ጥረት ማድረግ

የማሸከርከር ባህሪያት በሶሰት ዘርፎች ይከፈላሉ።


1 የሰሜት ባህሪይ
2 የመገንዘብ ባህሪይ
3 የክህሎት ባህሪ

1. የሰሜት ባህሪይ ፦ ፍላጎትብ ፣አመለካክትን፣ እሴትን ፣ መነሳሳትና ማንኛውም ግብ ያለው የሰዎች ድርጊትን ይጠቃልላል

2. የመገንዘብ ባህሪ፦ መረዳትን ፣ማሰብን፣ ምክንያትን እና ውሳኔ መሰጠት እና የሰዎችን ድርጊት ውጤትን ያካትታል።

3. የክህሎት ባህሪ፦ በአዕምሮ አዛዥነትና በአካላትን እንቅሰቃሴ የሚፈፀሙ ነው።

የማሸከርከር ባህሪ ሰነ ባህርያዊ ዘርፎች


ሀ. ሀላፊነት
ለ. ጥንቃቄ
ሐ. ብቃት

ሀ. ሀላፊነት ፡-
1. ሰሜታዊ ሀላፊነት
2. አእመሮአዊ ሀላፊነት
3. ክህሎታዊ ሀላፊነት

1.ሰሜታዊ ሀላፊነት፦ለሌሎች ማሰብና ሰነ ምግባራዊነት

 ሰነ ምግባራዊና ሃይማኖታዊ መመሪያዎችን መጠቀም


 በሌሎች ላይ አደጋንና ጉዳያትን ለለመፍጠር መጠንቀቅ
 ለእግረኞች ግብ፣ ዕቅድ እና እነቅሰቃሴ ሰኬታማ እንዲሆን በቅንነት መተባበር

1.1. የሰሜታዊ ሀላፊነት ጉድለት፦ ራሰ ወዳድነትና ቅንነት የጎደለው አሰተሳሰብ

 የበቀለኝነት ሰሜት
 በራሰህ ላይ የደረሰ ችግር በሌሎችን እንዲደርሰ ማድረግ
 የሌላ መብት መጣሰና አቃሎ ማየት

2.አእምሮአዊ ሀላፊነት፦ አዎነታዊ አሰተሳሰብ

 የራሰህ አና የሌሎች ውጤት ቀድሞ መገመት


 ከአሉታዊ ሰሜት ነፃ ማድረግ
 ከሰዎች አና ከንብረቶች አደጋ መጠበቅ

2.1 የአእምሮአዊ ሀላፊነት ጉድለት ፦ አሉታዊ አሰተሳሰብ

 አደገኛ የሆነ የማሸከርከር ምናባዊ ዕቅድን መከተል


 ለተሳሳተ የማሸከርከር ተግባር ዋጋ መሰጠት
 ሌሎች አሸከርካሪዎች የተቹኛል፣ ያወግዙናል ፣ ያጠቁናል የሚል መያዝ

3. .ክህሎታዊ ሀላፊነት ፦ ደሰተኝነትና እርካታ

 ጥንቃቄ የታከለበትን የአነዳድ እንቅሰቃሴያችንን መውደድ


 ንቃትንና የተረጋጋ መልካም ሰሜትን ማዳበር
 አእምሮአዊ ተግባሮችን መፈፀም ለምሳሌ ማቀድ ራሰነ መገመገመና መወሰን

3.1 የክህሎታዊ ሀላፊነት ጉድለት፦ ውጥረትና ድብርት

 የሀዘንና የድብርት ሰሜት ማሳየት


 በሰራናቸው ሰህተቶች ምክንያት ራሰን ዝቅ እድርጎ ማየትና ለራሰ ክብር መንፈግ
 መፍራት ፣ መጨነቅና አለመረጋጋት

ለ. ጥንቃቄ (ደህንነት) ፡-

1. ሰሜታዊ ድህንነት
2. አእምሮአዊ ድህንነት
3. ክህሎታዊ ድህንነት

1.ሰሜታዊ ድህንነት ፦ ራሰን ማአጋጀትና ሚዛናዊነት /እኩልነት/

 ለሌሎች አውራ ጎደና ተጠቃሚዎች ሚዛናዊ ለመሆን መሞክር


 የሌሎች አሸከርካሪዎችን የማሸክርከር እንቅሰቃሴ ላለማሰተኀጎልና በአላማቸው ላይ ጣልቃ ላለመግባት ፍላጎት ማሳየት
 ሌሎች ሰህተት ሊሰሩ ሲሉ ጥንቃቄና ሰፍ ያለ ግንዛቤ መውሰድ

1.1 የሰሜት ድህንነት ጉድለት፦ የሞገደኝነት ሰሜትና በአጋጣሚዎች የመጠቀም ግላጎት

 ራሰህ ለውደደር ውሰጥ መግባት


 ሌሎችን ተጠቃሚዎች የማውገዝና የቁጣን ሰሜት ማንፀባረቅ
 የመገልገልና የመፍራት ሰሜት ማሳየት

2.አእምሮአዊ ድህንነት፦ ሚዛናዊ መለያ ባህሪያት

 ለሌሎች ሃሳብና ባህሪ ሚዛናዊና ምክንያታዊ የሆነ ገለፃ መሰጠት


 ለራሰህ የማሸከርከር ተግባርና ሰሜት ሚዛናዊ የሆነ ምክንያት መሰጠት
 ነገሮችን /ሁኔታዎችን/ ከሌሎች አንፃር መመልከት

2.1 የአእምሮአዊ ድህብነት ጉድለት፦ ሚዛናዊነት የጎደለው መለያ ባህሪያት

 የሌሎች ባህሪይ ሚዛናዊ ባልሆነና መሰረት የለሸ ሁኔታ መሰጠት


 የራሰህ የማሸክርከር ጥፋት በተሳሳተ መንገድ መከላከል
 የራሰህ ጥፋት ወደ ሌሎች አሸከርካሪዎች ለመሳበብ መሞከር።

3.ክህሎታዊ ድህንነት፦ ትህትና የተሞላበት መግባባትና የመረጋጋት ሰሜት

 ፈታኝ ሰሜትን ጎጂ በሆነ ሁኔታ ውሰጥ ማረጋጋትና ግፊትን መቋቋም


 ከሌላ አሸከርካሪ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የተከሰተ ሰሜት ወደ መደበኛ ሰሜት ለመመለሰ መሞከር
 ለእግረኛች ይሁን ለሌላ ፀያፍ የሆኑ ቃላቶችንና ተግባሮችን ከመፈፀም መቆጠብ
3.1 የክህሌታዊ ድህንነት ጉድለት፦ ትህትና የጎደለው ምልልሰና የተጋነነ አፀፋ

 ለሌሎች በቃል ወይም በምልክት /በአካላዊ እንቅሳቃሴ/ መሰደብ


 ሌላ አሸከርካሪ ለሚያሳየው አግባብነት የሌለው ባህሪ ተመሳሳይ /የተጋነነ/አፀፋ
 ሌሎች የአውራ ጎደና ተጠቃሚዎች ይሁን ለእግረኞች አሰገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ማሰገባት

ሐ. ብቃት ፦

1. የሰሜታዊ ብቃት
2. የአእምሮአዊ ብቃት
3. የክህሎታዊ በቃት

1 የሰሜታዊ በቃት ፦ ደንብን ማክበር አና ልበ ሙሉነት


 በማነሸከረክርበት ወቅት ሰህተትን ለማሰወገድ ጠንቃቃ ለመሆን መመኮር
 ለትራፊክ እንቅሰቃሴ ደንብና ሰርዓት ራሰን ማሰገዛት
 የትራፊክ ህጎችንና ደንቦችን ማክበር

1.1 የሰሜታዊ ብቃት ማነሰ፦ ደንብን ሰርዓትን ያለማክበርና በራሰ ያለመተማመን

 ደንብና ሰርዓትን ለሚያሰክብሩ አካሎች ተቆጣጣሪ ሰራተኛች የጥላቻ ሰሜት ማዳበር


 ተሰፋ መቁረጥና ያለመረጋጋት ሰሜት ማሳየት
 በትራፊክ እንቅሰቃሴ ሂደት ታጋሸ ያለመሆን።

2. የአእምሮአዊ ብቃት፦ እውቀትና ግንዛቤ

 የማሸከርከር መረጃዎችን ማወቅና በአዕምሮ መያዝ


 ሌሎች አሸከርካሪዎችና ራሳችን ተሰራናቸውን ሰህተቶች ልብ ማለት
 የማሸከርከር አንቅሰቃሴዎችን ፣ ሰሜታችንንና ሀሳባችንን በሚገባ ማወቅ

2.1 የአእምሮአዊ ብቃት ማነሰ ፦ በመረጃ ያልተደገፈና የተባዛ አሰተሳሰብ

 መንገዱ በሚፈቅደው ፍጥነት ማሸከርከር መንቀርፈፍ እንደሆነ ማሰብ


 ትራፊክ ፖሊሶች ባሉበት ቦታ ፍጥነትን ጠብቆ ማሸከርከር
 ቢያንሰ ከ 15-25 ኪ.ሜ ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ ማሸከርከር

3. ክህሎታዊ ብቃት ፦ ትከከለኛ ተግባርና ጠንቃቃነት /ንቁነት/

 በተለመደ የማሸ/ር ሁኔታ ውስጥ ትከከለኛ የማሐ/ር ተግባራትን ማከናወን


 ለትራፊክ ምልክቶችና ሌሎች የአውራ ጎደናው ተጠቃሚዎች እንቅሰቃሴ ትኩረት መሰጠት
 የአከባቢውን ትራፊክ እንቅሰቃሴ ፍሰት በመከተል የፍጥነት ገደብን ሳያልፍ ማሸ/ር

3.1 የክህሌታዊ ብቃት ጉድለት ፦ ትክክነኛ ያልሆነ አካሄድና የትኩረት ማጣት

 በመደበኛ የማሸከርከር ሁኔታ ውሰጥ ትክክለኛ ያልሆነና ህገወጥ ተግርን መፈፀም


 ያለ በቂ አትኩረትና በሌላ ሀሳብ ተጠምይ ማሸ/ር
 የትራፊክ ምልክቶችን ያለማየትና የአከባቢውን የትራፊክ እንቅሰቃሴ በትኩረት ያለመከታተል።

You might also like