You are on page 1of 7

ፍርቱና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

ስነ-ባህሪ

የሙከራ ጥያቄ

1. የጤና መታወክ የሚሰማዉ አሽከርካሪ ማስተዋልና ማገናዘብ ይችላል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት


2. የመወሰን ችሎታ ማነስ የምን ምልክት ነው?

ሀ. የጤና ችግር ለ. የችሎታ ችግር ሐ. “ሀ” እና “ ለ መ. መልሱ አልተሰጠም

3. የመንገድ ላይ ትህትና የሥነ ባህሪ ጉዳይ ክፍል ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

4. ጠጥቶ ማሽከርከር የሞገደኛ አሽከርካሪ ባህሪ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

5. የተሳሳተ ውሳኔ ማስተላለፍ የብቃት ማነስ ምልክት ነዉ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

6. አካባቢ ለባህሪ መንስኤ አይሆንም፣ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

7. የትራፊክ ምልክቶችን ማክበር የሙያ ሥነ ምግባር ጉድለት ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

8. የራስን ፍላጐት ብቻ መጠበቅ የአሽከርካሪዎች አላስፈላጊ ባህሪ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

9. አለመረጋጋት ለአሽከርካሪዎች አላስፈላጊ ባህሪ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

10. አልኮል መጠጥ ጠጥቶ ማሽከርከር የውሳኔ አሰጣጥን ያዛባል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

11. በድብርት ስሜት ውስጥ ሆኖ ማሽከርከር ለአደጋ ያጋልጣል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

12. ራስን ዝቅ አድርጐ የማየት ስሜት ከአላስፈላጊ ባህሪያቶች አንዱ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

13. አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት በቂ ዝግጅት ማድረግ አለበት ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

14. ለማሽከርከር ፍላጐትና ተነሳሽነት ያስፈልጋል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

15. በማሽከርከር ወቅት አለመረጋጋት ቅንነት የጐደለው የማሽከርከር ባህሪ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

16. የተጓደለ የማሽከርከር ባህሪ ራስንና አካባቢን ከአደጋ ይከላከላል ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

17. አሽከርካሪዎች ሲያሽከረክሩ የሚያሳዩትን ባህሪ የሚያጠና ሳይንስ የማሽከርከር ስነ-ባህሪ ይባላል፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

18. ከ8ዐ% እስከ 9ዐ% አካባቢን ለማወቅና ስለ አካባቢ መረጃ ለመሰብሰብ የሚቻለው በመስማት ነው

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

19. አንድ አሽከርካሪ የአይን እይታው ባይስተካከልም ማሽከርከር ይችላል ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

20. አትኩሮትን በማሽከርከር ላይ ሳያደርጉ ማሽከርከር የጥንቃቄ ጉድለት ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

21. አሽከርካሪዎች አስፈላጊ የማሽከርካር በህሪያትን ለይቶ ማወቃቸው ለውሳኔ አሰጣጥ ይረዳቸዋል

ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
ፍርቱና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም
22. በሥልጠና አማካኝነት ባህሪን ማሻሻል ይቻላል ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

23. የአሽከርካሪነት ሙያ በትምህርትና ሥልጠና የተገኘውን ዕውቀት፣ክህሎትና አስተሳሰብን በመጠቀም ለህብረተሰቡ


ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የስራ መስክ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

24. አሽከርካሪዎች ባለማወቅ፣ በቸልተኝነትና ስነ-ስርዓት በጐደላቸው አሽከርካሪዎችና እግረኞች ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን
አስቀድሞ የመጠንቀቅ ኃላፊነት አለባቸው ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

25. አሽከርካሪዎች የእንቅልፍ ስሜት በተሰማቸው ጊዜ የሚያነቃቃ ነገር ወስደው ማሽከርከር አለባቸው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

26. አሽከርካሪዎች በህክምና ባለሞያ ካልተፈቀደ በስተቀር መድሀኒት ወስደው ማሽከርከር አይችሉም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

27. ትኩረት ለመሳብ መሞከር የአሽከርካሪ መልካም ባህሪ ነው ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

28. ፍጥነት መቀነስና በማይታመን ሁኔታ ፍጥነት መጨመር አልኮል መጠጥ ጠጥቶ የሚያሽከርከር አሽከርካሪ ባህሪ ነው

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

29. በአልኮል መጠጥ ተመርዘው የሚያሽከረክርሩ አሽከርካሪዎችን በተመለከቱ ወቅት አሽከርኮሪዎቹን ተጠግቶ ማስቆም የተሻለ
አማራጭ ነው ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

30. ሞገደኛ አነዳድ በመጥፎ ስሜት ውስጥ ሆኖ የማሽከርከር ውጤት ነው ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

31. አሽከርካሪው በሚያሽከረክርበት ወቅት አስፈላጊውን የትራፊክ ምልክት ለሌሎች አሽከርካሪዎች አለማሰየት ትዕግስት
ማጣታትንና ትኩረት አለመስጠትን ያሳያል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

32. ለሰው ልጅ ክብር መስጠትና ይቅር ባይ መሆን የማሽከርከር ሥነ-ባህሪ ጠቀሜታ ነዉ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

33. ስድቦችንና ጸያፍ ምልክቶችን ችላ ማለት ትክከለኛው የማሽከርከር ስነ-ባህሪ ተግባራዊ ምላሽ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

34. የተነሳሺነት ስሜት መቀነስ የአነዳድ ስህተትን ያስከትላል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

35. በማሽከርከር ተግባር ትክከለኛ ውሳኔ ለማድረግ አዕምሮን በንቃት ማሠራት ተገቢ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

36. በራስ ላይ የደረሰን ችግር በሌሎች ላይ እንዲደርስ መሻት ትክክለኛው የማሽከርከር ባህሪ ነውሀ. እውነት ለ. ሀሰት

37. የሌሎች አሽከርካሪዎችን የማሽከርከር እንቀስቃሴ አለማስተጓጎል የኃላፊነት መገለጫ ባህሪ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

38. ጥሩ ስነ ምግባር የተላበሰ አሽከርካሪ ሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች ለአደጋ እንዳይጋለጡ የመጠበቅ ሀላፊነት የለበትም ሀ.
እውነት ለ. ሀሰት

39. ደንብ ማክበርና ልበ-ሙሉነት የብቃት መገለጫ ባህሪያት ናቸው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

40. በመደበኛ የማሽከርከር ሁኔታ ውስጥ ተስፋ የመቁረጥና ያለመረጋጋት ለአደጋ መንስኤ ይሆናሉ፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

41. በማሽከርከር እንቅስቃሴ ስሜታችንና ሀሳባችንን በሚገባ ማወቅ የብቃት መገለጫ ባህሪ ነውሀ. እውነት ለ. ሀሰት

42. መንገዱ በሚፈቅደው የፍጥነት ገደብ መሠረት ከማሽከርከር ይልቅ ትራፊክ ፖሊሶች ባሉበት ቦታ ብቻ ፍጥነት መቀነስ

የባህሪም የብቃትም ችግር ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

43. ያለበቂ ትኩረትና በሌላ ሀሳብ ተጠምዶ ማሽከርከር ትክክለኛ ያልሆነ የማሽከርከር ሂደት ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
ፍርቱና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

44. የማሽከርከር ስህተት ፈጽመን አደጋ ባለማድረሳችን ስህተት የመደጋገም ልምድ ተፈጥሮአዊ ክስተት ስለሆነ መቆጣጠር
አይቻልም ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

45. አሽከርካሪዎች አሉታዊ ባህሪያቸውን እራሳቸው ደረጃ በደረጃ መለወጥ ይችላሉ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

46. የማሽከርከር ስነ-ባህሪ የአሽከርካሪዎችን የማሽከርከር ተግባር ያጠናል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

47. ስነ-ምግባር ባህሪን የሚያጠና የጥናት ዘርፍ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

48. የማሽከርከር ስነ-ባህሪ የአስተሳሰብ ስርአትን የሚያጠና ሳይንስ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

49. የማሽከርከር ስነ-ባህሪ የፍጥነት ወሰን አከባበርን ያበረታታል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

50. በቂ እረፍት ሳያደርጉ ማሽከርከር ስነ-ባህያዊ ችግር አይደለም ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

51. የአልኮል መጠጥን ሳይበዛ የወሰደ አሽከርካሪ ማሽከርከር ይፈቀድለታል ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

52. ጫት ቅሞ ማሽከርከር አልኮል ወስዶ የማሽከርከርን ያህል ለአደጋ አያጋልጥም ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

53. ሀላፊነት ከስነ-ባህሪያዊ እሴቶች ውስጥ አይካተትም ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

54. ደህንነት ከስነ-ባህሪያዊ እሴቶች ውሰጥ አንዱ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት


55. ስነ-ባህሪያዊ ግብን ለመምታት ከሚያነሳሱ እሴቶች መሀከል ብቃት አንዱ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

56. ሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎችን ማሠብ አንድ የሥነ-ባህሪ መሠረት ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

57. ጉዞን በዕቅድ ማከናወን ሥነ-ባህሪያዊ ተነሳሽነትን አያሳይም ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

58. መልካም-ምግባር አንዱ የማሽከርከር ሥነ-ባህሪ አላማ ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

59. ስነ-ምግባራዊነት ማለት በራስ ላይ እንዲደርስ የማይፈለገውን ነገር በሌሎች ላይ ማድረስ ማለት ነው ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

60. በቀጥታ ወይንም በተዘዋዋሪ ሊታወቅ የሚችል ነው፡፡ ሀ. ባህሪ ለ. ስነ-ባህሪ ሐ. የማሽከርከር ባህሪ መ. መልስ የለም

61. አሽከርካሪ በሚያሽከርክርበት ወቅት የሚያሳየውን ባህሪ የሚያጠና የሥነ ባህሪ ዘርፍ ምን ይባላል?

ሀ. የማሽከርከር ባህሪ ለ. የማሽከርከር ሥነ ባህሪ ሐ. የአሽከርካሪ ባህሪመ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ

62. የሰው ልጅ ባህሪ የ ውጤት ነው፡፡ ሀ. ውርስ ለ. አካባቢ ሐ. “ሀ” እና ”ለ”መ. መልሱ የለም

63. ትህትናን የተላበሰ አሽከርካሪ አደጋን የመከላከል ብቃቱ አነስተኛ ነው? ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

64. አብሮ የመስራትና አብሮ የመኖር እሴት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ሙያ ለ. የሙያ ስነምግባር ሐ. ስነ ምግባር መ. ሁሉም

65. ከሚከተሉት ውስጥ የሞገደኛ አነዳድ ሂደት የሆነው የቱ ነው?


ሀ. ግዴለሽነት ለ. ትኩረት መሰጠት ሐ. “ሀ” እና “ለ” መ. መልሱ አልተሰጠም

66. የማሽከርከሪ ስነ-ባህሪ ጉዳዮች የሚባለው የቱ ነው?

ሀ. ዝግጁነት ለ. መረጃን ማሰባሰብ ሐ. ርህራሄ መ. “ሀ” እና ”ለ”


ፍርቱና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

67. መረጃን ከአካባቢያችን በስሜት ህዋሳቶቻችን 80-90% የመላክ ሂደት ነው፡፡

ሀ. መገንዘብ ለ. ትኩረት ሐ. ማስተዋል መ. ሁሉም

68. ባህሪንና አእምሮን፣ አስተሳሰብን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና ዘርፍ የሆነው የቱ ነው

ሀ. ስነ ምግባር ለ. ስነ ባህሪ ሐ. ባህሪ መ. ”ለ” እና “ሐ”

69. አሽከርካሪዎች አደጋን ለመከላከል በቂ የማሽከርከር ክህሎት ሊኖራቸው ይገባል? ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

70. የብስለት፣ የችሎታ፣ የትምህርት እና የመነሳሳት የጋራ ውጤት የሆነው የቱ ነዉ ?

ሀ. መነቃቃት ለ. ግዴለሽነት ሐ. ዝግጁነት መ. “ሀ” እና ”ለ”

71. በሰዎች ውስጥ ያለዉን ባህሪን ወደ ግብ የሚያንቀሳቅስ ሂደት ነው፡፡

ሀ. ዝግጁነት ለ. መነቃቃት ሐ. ግዴለሽነት መ. ሁሉም

72. በፍርሃትና በጭንቀት ውስጥ ሆኖ የማሽከርከር ሂደት ይባላል፡፡


ሀ. ሞገደኛ አነዳድ ለ. ክልፍልፍ አነዳድ ሐ. “ሀ” እና “ለ” መ. መልሱ አልተሰጠም

73. ብቃት ያለው አሽከርካሪ ለአደጋ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዮችን አስቀድሞ መለየት ይችላል? ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

74. ስሜቱ ጥሩ የሆነ አሽከርካሪ ራሱም ሆነ በሌሎች ሊደርስ የሚችልን አደጋ የመከላከል ብቃቱ አነስተኛ ነው?

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

75. ውጤታማ የመግባባት ክህሎት የሚባለው የቱ ነው? ሀ. መንፈግ ለ. መቻቻል ሐ. መነቃቃት መ. ሁሉም

76. በትምህርትና በስልጠና የተገኘ ክህሎት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ሙያ ለ. የሙያ ስነምግባር ሐ. ስነ ምግባር መ. መልሱ የለም


77. ከሚከተሉት ውስጥ የአሽከርካሪዎች አላስፈላጊ ባህሪያት የሆነው የቱ ነው?

ሀ-.ሞገደኝነት ለ. አካላዊ ሁኔታ ሐ. የስሜት ባህሪ መ. “ሀ” እና “ለ”

78. ውስጣዊ ፍላጎትን፣ ፍቅርን፣ ጥላቻን መግለፅን ያመለከታል፡፡

ሀ. ሀይለ ስሜት ለ. የስሜት ባህሪ ሐ. የመገንዘብ ባህሪ መ. መልሱ የለም

79. የሰው አስተሳሰብ አመልካች ድርጊት ውጤት የሆነው የቱ ነው?

ሀ. ስነ ባህሪ ለ. ባህሪ ሐ. ትህትና መ. ሁሉም

80. የሰዎችና የእንስሳትን ባህሪ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡

ሀ. ስነ ባህሪ ለ. ባህሪ ሐ- ዝግጁነት መ. መልሱ የለም

81. አሽከርካሪዎች መረጃን የማሰባሰብና መተርጎም ሂደት የሚያከናውኑበት ዘዴ …….. ነዉ

ሀ. በመገንዘብ ለ. በትኩረት ሐ. በማስተዋል መ. ሁሉም


ፍርቱና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

82. ባለሞያው እንደተሰማራበት የሙያ ዘርፍ የሚከተላቸው መርሆችና ደንቦችን የሚመለከት ዘርፍ ነው፡፡

ሀ. ሙያ ለ. የሙያ ስነ-ምግባር ሐ. ስነ-ምግባር መ. ስነ-ባህሪ

83. ውጤታማ መግባባትን ለመፍጠር ከሚያገለግሉ ክህሎቶች ውስጥ የሚካተተው የቱ ነው?

ሀ. መቻቻል ለ. መደራደር ሐ.አዛኝ መሆን መ. ሁሉም

84. ከትክክለኛ የማሸከርከር ባህሪ የሚመደበው የቱ ነው? ሀ. ፍርሀት ለ. ጭንቀት ሐ. በራስ መተማመን መ. ሁሉም

85. ነውጠኛ የማሸከርካር ባህሪ ያለውን ሠው ተከታትሎ መበቀል ይገባል ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

86. በአንድ እጅ እያሽከረከሩ በሌላ እጅ ሌላ ተግባር ማከናወን ተገቢ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
87. አሽከርካሪና እግረኛ ከሁለቱም እኩል የጋራ ደህንነት ጥንቃቄ አተገባበር ይጠበቃል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

88. አነስተኛ የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች እንደ ቢራ ያሉትን ጠጥቶ ማሸከርከር ችግር አያስከትልም፡፡ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

89. የማሽከርከር ተግባር አካል እንቅስቃሴንና የአዕምሮ አመለካከትን በቅንጅት ያጣመረ ተግባር ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

90. ከማሽከርከር ስህተት መማር ለአሽከርከሪዎች መልካም ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

91. ቀልጣፋነት የማሸከርከር መለኪያ ነው ሀ. ብቃት ለ. ባህሪ ሐ. ሀ እና ለ መ. መልሱ የለም

92. የጋራ መጠቀሚያ መሠረተ ልማት እንጂ ለአሸከርካሪዎች ብቻ የተተወ አይደለም

ሀ. መንገድ ለ. መኪና ሐ. ሀ እና ለ መ. መልሱ የለም


93. ሥነ- ባህሪያዊ እሴት የሆነው? ሀ. ብቃት ለ. ደህንነት ሐ. ኃላፊነት መ. ሁሉም

94. በመንገድ ላይ ሲያጠፉ የተመለከትናቸውን አሽከርካሪዎች መገሰፅ ይገባል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

95. ቅድሚያ ያለመስጠት የሞገደኘነት ምልክት ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

96. የትራፊክ መብራት መጣስ የትግሥት ማጣት ምልክት ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
97. የትራፊክ ፖሊስን የእጅ ምልክት ያለማክበር የብቃት ማነስን አያመለክትም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
98. ለሌሎች ያለማሰብ የባህሪ እንጂ የብቃት ችግር አይደለም ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

99. ለሌሎች መንገድ ተጠቀሚዎች ቤተሰባዊ እሴትን ያለማንፀባረቅ የሥነ-ምግባር እንጂ የሥነ- ባህሪ ችግር አይደለም፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሐሰት

100. የፍጥነት ወሰን ገደብን ያለማክበር የግንዛቤ አናሳነትን ያሳያል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሐሰት
ፍርቱና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

መልስ:-

23 ሀ 83 መ 41 ሀ
1ለ 61 ለ
24 ሀ 84 ሐ 42 ሀ
2 ሐ 62 ሐ
43 ሀ
25 ለ 85 ለ
3 ሀ 63 ለ 44 ለ
26 ሀ 86 ለ 45 ሀ
4 ሀ 64 ሐ
27 ለ 87 ለ 46 ለ
5 ሀ 65 ሀ 47 ለ
28 ሀ 88 ለ 48 ሀ
6 ለ 66 መ
29 ለ 89 ሀ 49 ሀ
7 ለ 67 ሀ
50 ለ
30 ሀ 90 ሀ
8 ሀ 68 ለ 51 ለ
31 ለ 91 ሀ 52 ለ
9 ሀ 69 ሀ
32 ሀ 92 ሀ 53 ለ
10 ሀ 70 ሐ
54 ሀ
33 ሀ 93 መ
11 ሀ 71 ለ 55 ሀ
34 ሀ 94 ሀ 56 ሀ
12 ሀ 72 ሐ
35 ሀ 95 ሀ 57 ለ
13 ሀ 73 ሀ 58 ሀ
36 ለ 96 ሀ 59 ለ
4 ሀ 74 ለ
37 ሀ 97 ለ 60 ሀ
15 ለ 75 ለ
38 ለ 98 ሀ
16 ለ 76 ሀ
39 ሀ 99 ለ
17 ሀ 77 ሀ
40 ሀ 100 ሀ
18 ለ 78 ሀ
19 ሀ 79 ለ
20 ሀ 80 ሀ
21 ሀ 81 ሐ
22 ሀ 82 ለ
ፍርቱና የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም

You might also like