You are on page 1of 14

የጉዞ መረጃዎችን መሰብሰብና

እቅድ ማወጣት
አዘጋጅ፡- መርዕድ በሻህ
 0968573578
አሽከርካሪዎች መረጃ ለመሰብሰብና ለማስተላለፍ የማስታወሻ ደብተር፣ሬዲዮና
ሞባይል፡ቪዲዮ ካሜራና ፎቶ ካሜራ የመሳሰሉትን መጠቀምይችላሉ፡፡

1. የጉዞ መዳረሻ
አንድ አሽከርካሪ ጉዞውን ከመጀመሩ በፊት የጉዞውን ርቀትና መዳረሻውን ማወቁ
የሚከተሉተን ጠቀሜታ ይሰጠዋል፡፡
• የጉዞ እቅድ በትክክል ለማዘጋጀት
• ተሸከርካሪውን ለጉዞ ለማዘጋጀት
• የነዳጅ መጠን ለማወቅ
• የጉዞ ግዜን በአግባቡ ለመጠቀም
• በስነ-ልቦና ለመዘጋጀት
2. የመንገድ ላይ መረጃዎች
 የመንገድ ካርታዎችን ማንበብ እጅግ የሚረዳ ሲሆን በጉዞ ወቅት ከግምት ውስጥ መግባት
ከሚገባቸው የአገልግሎት አይነቶች መካከል፡፡
•የነዳጅ ማደያዎች
•ሆቴሎች
•የስልክ አገልግሎት መስጫ
•የፖሊስ ስልክ አድራሻ
•ባንክና ኢንሹራንስ
•የአውቶቢስ ማቆሚያ
3. የመንገድ ሁኔታዎች መረጃ

የመንገድ ደረጃ/ዓይነት/ የመንገዱ መልከዓምድራዊና የመስመሩ አከባቢያዊ የአየር ሁኔታ


ሁኔታ • ነፋሻማ
• አስፓልት
• ወጣ ገባ
• ኮሮኮንች • ጸሀያማ
• ከርቭ
• አንሸራታች • ደመናማ
• ቁልቁለት
• ዝናባማ
• ዳገት
የጉዞ ሰነዶች እና መረጃዎች
የግል መረጃዎች
• መንጃ ፈቃድ
• የመታወቂያ ካርድ
• ፓስፖር
ከስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰነዶች
• ለጭነት የተሰጠ የይለፍ/መውጫ/
• ፍተሻ የማያስፈልግ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ
• የጭነት አይነት መግለጫ
• የኢንሹራስ ምስክር ወረቀት
የማህበረሰቡ ቋንቋ፡ባህልና ሀይማኖት
አሽከርካሪዎች በጉዞ መስመር ላይ የሚገኙ ማህበረሰብ ቋንቋ፡ ባህል፡
ሀይማኖት፣ እመነትና እሴት ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ለመረዳት መሞከርና
በጉዞ ላይም ልብ ብለው ማስታወሻ መውሰድ አለባቸው፡፡
ምቹ መንገዶች መምረጫ መስፈርቶች

አንድ ጉዞ መስመሩ ምቹ የሚያደርገው፡-


• ህጋዊና ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ
• አደጋዎች በተደጋጋሚ የማያስተናግድ መሆኑ
• የተጨናነቀ የትራፊክ እንቅስቃሴ አለመኖሩ
1. አንድን መረጃ ለማሰባሰብና ለማዘጋጀት ቀላልና ርካሽ የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ማስታወሻ ደብተር ለ. ቪዲዮ ካሜራ ሐ. የድምፅ መቅረጫ ቴፕሪከርደር መ. ሁሉም
2. የጉዞ መረጃዎችን ለማግኘት ከሚከተሉት ውስጥ ወደ የትኛው መ/ቤት መሄድ ይመረጣል?
ሀ.ባንክና ኢንሹራንስ ለ.ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሐ.ጤና ወይም ትምህርት ቢሮ መ.መንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮ
3. ለአንድ አሽከርካሪ የጉዞ መረጃን ለማሰባሰብ ከሚከተሉት ውስጥ ጠቀሜታ የሌለው የቱ ነው?
ሀ. አካባቢውን (መንገዱን) ከሚያውቁት ጋር መወያየት ለ. ስለ መንገዱ በፅሁፍ የተዘጋጀን መረጃ ማንበብ
ሐ. የሕዝቡ ቁጥር ስንት እንደሆነ ማወቅ መ. የመንገዱን ካርታ ማወቅ
4. አንድ አሽከርካሪ አማራጭ መንገዶችን ለመጠቀም ሲያወዳድር በዋናነት መርሳት የሌለበት
ሀ. የመንገዱን ለትራፊክ መከፈት ለ. የአገልግሎት መስጫ ተቌማት የተሟሉ መሆኑን ማረጋገጥ
ሐ. የመንገዱ ፀጥታ አስተማማኝ መሆኑን ማረጋገጥ መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
5. አንድ አሽከርካሪ ለጉዞው መያዝ ያለበት ጠቃሚ የመረጃ አይነት የሆነው የቱ ነው?
ሀ. የይለፍ ወረቀት ለ. የጭነት ማዘዣ ወረቀት ሐ. መንጃ ፍቃድ መ. ሁሉም መልስ ነው
6. አንድ አሽከርካሪ ስለ ሚሄድበት መንገድ መረጃ ማግኝት የሚያስፈልገው ለምንድን ነው?
ሀ. የመንገዱን አይነት ለመለየት ለ. የአየር ሁኔታውን ለመረዳት
ሐ. የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ለመለየት መ. ሁሉም መልስ ይሆናሉ
7. አንድ አሽከርካሪ መረጃ ማሰባሰብ ያለበት ምክንያት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ. የተገልጋዩን ሕብረተሰብ ባህልና ሃይማኖት ለማወቅ ለ. የተቆጣጣሪዎችን ባህሪ ለማወቅ
ሐ. ለጉዞ አስፈላጊና ከሥራው ጋር ግንኙነት ያላቸውን ተቋማት ለማወቅ
መ. አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን ለማወቅ
8. አገልግሎት መስጫ ተቋማት የምንላቸው
ሀ. ነዳጅ ማደያና ካፌ ለ. ቀይ መስቀልና የአውቶቡስ ፌርማታ ሐ. ፖሊስ ጣቢያና መከላከያ
መ. ሁሉም መልስ ናቸው
9. አሽከርካሪዎች በጉዞ ላይ ቀይ መስቀል ወይንም ጤና ጣቢያ የሚገኝበትን አድራሻ ማወቅ ይገባቸዋል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
10. አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ስለጉዞው እቅድ ማውጣት አለበት፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
11. መረጃዎችን ለመያዝ የሚጠቅም አስፈላጊ ቁስ የትኛው ነው?
ሀ. ብዕር ወይም እርሳስ ለ. ማስታወሻ ደብተር ሐ. ቪዲዮ ካሜራና ፎቶ ካሜራ መ. ሁሉም
12. አሽከርካሪዎች ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት ማወቅ የሚገባቸው የትኛውን ነው?
ሀ. የጉዞውን ርቀት ለ. የጉዞውን መነሻ ሐ. የጉዞውን መዳረሻ መ. ሁሉም
13. አሽከርካሪዎች በመንገድ ላይ ከሚገኙ አገልግሎቶች መካከል ማወቅ የሚገባቸው ነው፡፡
ሀ. ነዳጅ ማደያዎች ለ. ሆቴሎች ሐ. ስልክ መደወያ ቦታዎችንን መ. ሁሉም መልስ ነው
14. ከሚከተሉት መካከል የአንዱን አድራሻ ማወቅ ለአሽከርካሪዎች አይጠቅምም
ሀ. ባንክና ኢንሹራንስ ለ. ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት
ሐ. አውቶቢስ ተራ መ. መልስ የለም
15. አሽከርካሪዎች የሚጓዙበትን የመንገድ ገጽታ የሚለዩት በ ነው፡፡
ሀ. በመንገድ አይነትና ገጽታ ለ. በመንገድ መልክዓምድር ሁኔታ
ሐ. በመንገድ አካባቢያዊ ሁኔታ መ ሁሉም
16. የመንገድ ኮረኮንች ወይም አስፋልት መሆን ምንን ይገልፃል?
ሀ. የመንገድ አይነትና ደረጃ ሐ. የመንገድ አካባቢያዊ ሁኔታ
ለ. የመንገድ መልከዓ ምድር መ. መልሱ የለም
17. የመንገድ ከርቭ የበዛበትና ወጣ ገባ መሆን ምንን ይገልፃል?
ሀ. መልካዓ ምድራዊ ሁኔታ ለ. አይነትና ደረጃ ሐ. አካባቢያዊ ሁኔታ መ. መልስ የለም
18. መንገዱ ዝናባማና ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ይበዛበታል ሲባል ምን እየገለጽን ነው?
ሀ. አካባቢያዊ ሁኔታ ሐ. የመንገድ መልከዓ ምድራዊ ሁኔታ
ለ. የመንገድ ደረጃና ዓይነት መ. ሁሉም
19. ከሚከተሉት አንዱ የአሽከርካሪው የግል መረጃ አይደለም?
ሀ. ፓስፖርት ለ. መንጃ ፈቃድ ሐ. መታወቂያ መ. የግል ማስታወሻ
20. አሽከርካሪው አሟልቶ ሊይዛቸው ከሚገባ መረጃዎች መካከል የሚካተተው የቱ ነው?
ሀ. የግል መረጃ ሐ. የድርጅቱ የስራ አፈፃፀም መረጃ
ለ. ከስራው ጋር ተያያዥነት ያላቸው መረጃ መ. ሁሉም
21. ለጭነት የተሰጠ መውጫ (ይለፍ) ፍተሻ የሚያስፈልገው ደብዳቤ፣ የጭነት ሁኔታ መግለጫ …
ወዘተ የምን መረጃዎች ናቸው?
ሀ. የግል ለ. ከስራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሐ. የድርጅት ስራ አፈፃፀም መ. ሁሉም
22. የጭነቱ አይነት፣ መነሻና መድረሻ የነዳጅ መጠን… ወዘተ የምን መረጃዎች ናቸው?
ሀ. የግል ለ. ከስራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሐ. የድርጅቱ ሥራ አፈፃፀም መ. መልሱ የለም
23. አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የሚጓዝበትን መንገድ ባህሪያት እና የአካባቢውን
የደህንነትና ፀጥታ የሚገልጽ መረጃ ሊኖረው አይገባም፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
24. አሽከርካሪው በሚጓዝባቸው ቦታዎችና አካባቢዎች የሚገኙ ማህበረሰቦች ወግና ባህል፣ እምነት
ማወቁ እጅግ ጠቀሚ ነው፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
25. ከሚከተሉት ውስጥ አሽከርካሪው በአደጋ ጊዜ መረጃ ከሚያስተላልፍባቸው አካላት ውስጥ
አይመደብም፡፡
ሀ. ሆስፒታልና የቀይ መስቀል ለ. ፖሊስ ሐ. ኢንሹራንስና የቅርብ ቤተሰብ መ. መልስ የለም
26. አሽከርካሪው በሚጓዝበት አካባቢ ያሉ ማህበረሰቦችና ባህልና እሴት ማክበር አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
27. ጉዞ ከመጀመሩ በፊት አንድ አሽከርካሪ ጥሩ መንገድ መምረጥ ይኖርበታል፡፡ ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
28. አንድ አሽከርካሪ የጉዞ መስመር /መንገድ/ ሲመርጥ ከግምት ማስገባት ያለበት የትኛሉ ነው?
ሀ. የመንገዱን ዓይነት ደረጃ ለ. የመንገዱን የደህንነት ሁኔታ ሐ. ሀ እና ለ መ. መልሱ የለም
29. አንድ አሽከርካሪ የመነሻና መድረሻ ቦታዎችን መለየት መቻሉ
ሀ. የጉዞ ሰዓቱን በአግባቡ ለመወሰንና ለመጠቀም ያግዘዋል
ለ. ድካምን ለማስወገድና በማረፊያ ቦታዎች በቂ እረፍት ለማድረግ ያግዘዋል
ሐ. የተረጋጋ የማሽከርከር ክንውን እንዲኖር ያግዘዋል መ. ሁሉም
30. ከሚከተሉት አንድ የመንገድን ምቹነትና ጥሩነት ይገልጻል
ሀ. ብቃትና ደህንነቱ የተረጋገጠ ለ. ህጋዊ አገልግሎት መስጠት የጀመሩ መሆኑ
ሐ. አደጋዎች በተደጋጋሚ ያስተናገደ መሆኑ መ. ሀ እና ለ
31. አሽከርካሪው በጉዞ ላይ ያጋጠሙት እንቅፋቶችና ልዩ ልዩ ሁኔታዎች በመመዝገብ ከማህደር
ማኖር አለበት ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
32. በጉዞ ወቅት የተሽከርካሪ ብቃት ሪፖርት ላይ አሽከርካሪው ማቅረብ ያለበት መረጃ የትኛው ነው?
ሀ. ብልሽት ፈጥረው የነበሩና የተስተካከሉ ክፍሎች
ለ. ጥገና የሚያስፈልጋቸው የተሽከርካሪ ክፍሎች
ሐ. በመንገድ ወይም በተሽከርካሪ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች
መ. ሁሉም

You might also like