You are on page 1of 12

የመንገድ ሥነ-ስርዓት እና የማሽከርከር ሕግ

(1) አለም አቀፍ የመንገድ ዳር ምልክቶች


በአገልግሎታቸው በ3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም፡-
1. የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች
2. የሚቆጣጠሩ ምልክቶች
3. መረጃ ሰጭ ምልክቶች

አለምአቀፍ የመንገድ ዳር
ምልክቶች

የሚያስጠነቅቁ የሚቆጣጠሩ መረጃ ሰጭ


ምልክቶች ምልክቶች
ምልክቶች

የሚከለክሉ አገልግሎት
ጠቋሚ
ምልክቶች ምልክቶች

የሚያስገድዱ አቅጣጫ
ምልክቶች ጠቋሚ
ምልክቶች

ቅድሚያ
የሚያሰጡ
ምልክቶች

 የሚያስጠነቅቁ ምልክቶች
- ቅርፃቸው በአብዛኛው 3 ማእዘን፣
- ጠርዛቸው ቀይ፣
- መደባቸው ነጭ፣
- መልክት ማስተላለፊያቸው ጥቁር ነው፤

© Filagote Abate Hailu 1


ለምሳሌ

 የሚቆጣጠሩ ምልክቶች
በ3 ንዑስ ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-
1. የሚከለከሉት ምልክቶች
2. የሚያስገድዱ ምልክቶች
3. ቅድሚያ የሚያሰጡ ምልክቶች

 የሚከለክሉ ምልክቶች
- ቅርፃቸው ክብ፣
- ጠርዛቸው ቀይ፣
- መደባቸው በአብዛኛው ነጭ፣
- መልእክት ማስተላለፊያቸው ጥቁር ነው፤

ለምሳሌ

© Filagote Abate Hailu 2


 የሚያስገድዱ ምልክቶች
- ቅርፃቸው ክብ፣
- መደባቸው ሰማያዊ፣
- መልእክት ማስተላለፊያቸው ነጭ ነው፤

ለምሳሌ

 ቅድሚያ የሚያሰጡ ምልክቶች


- በቅርፅ፣ በጠርዝ፣ በመደብ ወ.ዘ.ተ ይለያያሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም
ቅድሚያ ስጥ የሚል መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡

ለምሳሌ

 መረጃ ሰጭ ምልክቶች
በ2 ንዑስ ክፍሎች ይከፈላሉ፡፡ እነሱም፡-
1. አገልግሎት መስጫ ጠቋሚ ምልክቶች
2. አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክቶች

© Filagote Abate Hailu 3


- ቅርፃቸው 4 ማዕዘን፤
- ጠርዛቸው ነጭ፣ ጥቁር፣ ሰማያዊ፤
- መደባቸው ሰማያዊ፣ አረንጓዴ፣ ነጭ፤
- መልእክት ማስተላለፊያቸው ነጭ፣ ጥቁርና ቀይ ነው፡፡

ለምሳሌ

(2) አለም አቀፍ የመንገድ ላይ መስመሮች


 አገልግሎት
 የመንገዶችን መሀልና ጠርዝ ያመለክታሉ፤
 ባለ አንድ ነጠላ መንገዶችን በሁለት አቅጣጫ ይከፍላሉ፤
 ባለ አንድ አቅጣጫ መንገዶችን በተለያዩ ረድፎች ይከፍላሉ፤
 የእግረኛ ማቋረጫ መንገዶችን ያመለክታሉ፤
 የተሸከርካሪ መቅደሚያ፣ መታጠፊያና ዞሮ መመለሻ ቦታዎችን
ያመለክታሉ፤
 የትራፊክ መጨናነቅ የሚበዛባቸውን እና የማይበዛባቸውን
መንገዶችን ያመለክታሉ፤
 መንገዶች ለእይታ አመች መሆናቸውንና አለመሆናቸውን
ያመለክታሉ፤
 አንዳንድ የመንገድ ዳር ምልክቶችን ተክተው ያገለግላሉ፤

 አሰማመር
በአሰማመራቸው በዋናነት በ2 ይከፈላሉ፡፡ እነዚህም፡-
1. በመንገድ አቅጣጫ (ቀጥታ) የሚሰመሩ መስመሮች
2. በመንገድ አግድመት (ወደጎን) የሚሰመሩ መስመሮች

© Filagote Abate Hailu 4


በመንገድ አቅጣጫ (ቀጥታ) የሚሰመሩ መስመሮች
አሰማመርና አገልግሎት
(1) መሀሉ በተቆራረጠ መስመር የተሰመረ መንገድ
- የትራፊክ መጨናነቅ የማይበዛበት እና ለእይታ ግልፅ (አመች) መንገድ
መሆኑን ይገልጻል፤
- ይህ አይነት መስመር በተሰመረበት መንገድ ላይ ስናሽከረክር
መስመሩን አቋርጠን መቅደም፣ ወደግራ መታጠፍ እና በስተግራ
በኩል ዞሮ መመለስ ይቻላል፡፡

(2) መሀሉ በድፍን (ባልተቆራረጠ) መስመር የተሰመረ መንገድ


- የትራፊክ መጨናነቅ (ፍሰት) የሚበዛበት መንገድ መሆኑን ወይም
ለእይታ ግልፅ ያልሆነ (የማያመች) መንገድ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- ይህ አይነት መስመር በተሰመረበት መንገድ ላይ ስናሽከረክር
መስመሩን አቋርጠን መቅደም፣ ወደ ግራ መታጠፍ እና በስተግራ
በኩል ዙሮ መመለስ አይቻልም፡፡

(3) መሀሉ በተቆራረጠ እና በድፍን (ባልተቆራረጠ) መስመር የተሰመረ


መንገድ
- በተቆራረጠው መስመር በኩል የሚጓዙ ተሸከርካሪዎች መስመሩን
አቋርጠው መቅደም፣ ወደ ግራ መታጠፍ እና በስተግራ በኩል ዞሮ
መመለስ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በድፍን መስመር በኩል የሚጓዙ
ተሽከርካሪዎች መስመሩን አቋርጠው መቅደም፣ ወደ ግራ መታጠፍ
እና በስተግራ በኩል ዞሮ መመለስ አይችሉም፡፡

© Filagote Abate Hailu 5


(4) መሀሉ በመስመር ከተሰራ ደሴት የተከፈለ መንገድ
- ደሴቱን አቋርጦ መቅደም፣ ወደ ግራ መታጠፍ እና በስተግራ በኩል
ዞሮ መመለስ አይቻልም፡፡ ነገር ግን ደሴቱን ሳንነካ መቅደም፣ ወደ
ግራ መታጠፍ እና በስተግራ በኩል ዞሮ መመለስ ይቻላል፡፡

(5) ባለ አንድ አቅጣጫ መንገዶች በተለያየ ተከፍለው ሲሰመሩ


- የረድፍ መስመሩን በማቋረጥ መቅደምና ረድፍ መቀያየር ብቻ
ይቻላል፡፡

በመንገድ አግድመት (ወደ ጎን) የሚሰመሩ መስመሮች


አሰማመርና አገልግሎት
እግረኞች መንገድ እንዲያቋርጡበት ተብሎ የተዘጋጁ መስመሮች ሲሆኑ፣
እነዚህ መስመሮች በተሰመሩበት መንገድ ላይ ምንጊዜም ለእግረኞች
ቅድሚያ መስጠት አለብን፤ እንዲሁም በ12 ሜትር ክልል ውስጥ
ተሽከርካሪን አለማቆም እና በ30 ሜትር ክልል ውስጥ መቅደም
የለብንም፡፡

(3) አለም አቀፍ የትራፊክ ማስተላለፊያ መብራቶች


 አገልግሎት
በመገናኛ መንገዶች ላይ ከተለያየ አቅጣጫ የሚመጡ ተሽከርካሪዎችን
እና እግረኛችን በተራና በቅደም ተከተል እንዲተላለፉ ያደርጋሉ፡፡

© Filagote Abate Hailu 6


 የመብራቶቹ አይነት
ከአግልግሎታቸው አንፃር ሁለት አይነት የትራፊክ ማስተላለፊያ
መብራቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
1. የተሽከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት
2. የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት

የተሸከርካሪ ማስተላለፊያ መብራት


 ቀለማቸው ከላይ ወደ ታች፡-
- ቀይ
- ቢጫ
- አረንጓዴ

 የአበራ ቅደም ተከተላቸው እና የሚያስተላልፉት መልዕክት፡-


- ቀይ ቁም
- ቀይና ቢጫ ለመሄድ ተዘጋጅ
- አረንጓዴ ሂድ
- ቢጫ ለመቆም ተዘጋጅ

 ቀይ መብራት ብቻውን ብልጭ ጥፍት እያለ ሲበራ


 ፍትነት መቀነስ፣
 መቆም፣
 ግራና ቀኝ መመልከት፣
 ቅድሚያ መስጠት፣
 በጥንቃቄ ማለፍ፤

ቀይ መብራት ብልጭ ጥፍት እያለ የሚበራበት ምክንያቶች፡-


1. በባቡር ሀዲድ ማቋረጫ አካባቢ፤
2. የአደጋ አገልግሎት መስጫ ተሽከርካሪዎች በሚበዙበት
አካባቢ፤
3. አደገኛ ሁኔታ ባለበት አካባቢ፤

 ቢጫ መብራት ብልጭ ጥፍት እያለ ብቻ ሲበራ


 ፍጥነት መቀነስ
 ግራና ቀኝ መመልት
 ቅድሚያ የሚሰጥ ካለ ቅድሚያ መስጠት
 በጥንቃቄ ማለፍ

© Filagote Abate Hailu 7


ቢጫ መብራት ብልጭ ጥፍት እያለ የሚበራበት ምክንያቶች፡-
1. በምሽቱ ወቅት የትራፊክ ፍሰቱ አነስተኛ በሚሆንበት ጊዜ፤
2. የትራፊክ ፍሰቱ አነስተኛ በሆነበት መገናኛ እና መስቀለኛ
መንገድ ላይ በማንኛውም ጊዜ (ሰዓት) ላይ፤

የእግረኛ ማስተላለፊያ መብራት


 ቀለማቸው ከላይ ወደ ታች፡-
- ቀይ
- አረንጓዴ

 የአበራ ቅደም ተከተላቸው እና የሚያስተላልፉት መልዕክት፡-


- ቀይ ቁም

- አረንጓዴ ሂድ

(4) የፍጥነት ወሰን


 የፍጥነት ወሰን ማለት ለተሽከርካሪዎች በህግ የተፈቀደ ከፍተኛ
የፍጥነት መጠን ነው፡፡
 የተሽከርካሪዎች ፍጥነት በዋናነት በሁለት ነገሮች ይወሰናል፡፡
እነዚህም፡-
1. በመንገዶች ደረጃ (አይነት)
2. በተሽከርካሪዎች አይነት (መጠን)

የመንገድ አይነቶች
1. ከከተማ ውስጥ ክልል መንገድ
2. ከከተማ ክልል ውጭ መንገድ
 1ኛ ደረጃ መንገድ
 2ኛ ደረጃ መንገድ
 3ኛ ደረጃ መንገድ

የተሽከርካሪ አይነቶች
1. አነስተኛ /ትንሽ/ ተሽከርካሪ
2. መካከለኛ ተሽከርካሪ
3. ከባድ ተሽከርካሪ

© Filagote Abate Hailu 8


 የከተማ ክልል የፍጥነት ወሰን
ለአነስተኛ ተሽከርካሪ 60 ኪ.ሜ በስአት
ለመካከለኛ ተሽከርካሪ 40 ኪ.ሜ በስአት
ለከባድ ተሽከርካሪ 30 ኪ.ሜ በስአት

 ከተማ ክልል ውጭ የፍጥነት ወሰን


ለአነስተኛ ለመካከለኛ ለከባድ
ተሽከርካሪ ተሽከርካሪ ተሽከርካሪ
በ1ኛ ደረጃ 100 ኪ.ሜ 80 ኪ.ሜ 70 ኪ.ሜ በሰዓት
መንገድ በሰዓት በሰዓት
በ2ኛ ደረጃ 70 ኪ.ሜ 60 ኪ.ሜ 50 ኪ.ሜ በሰዓት
መንገድ በሰዓት በሰዓት
በ3ኛ ደረጃ 60 ኪ.ሜ 50 ኪ.ሜ 40 ኪ.ሜ በሰዓት
መንገድ በሰዓት በሰዓት

(5) የርቀት ወሰን


የርቀት ወሰን ማለት ተከታትለው በሚጓዙ ተሽከርካሪዎች መካከል
መኖር ያለበት በህግ የተፈቀደ አነስተኛ የርቀት መጠን ነው፡፡
የተሽከርካሪዎች ርቀት በዋናነት በተሽከርካሪዎች ፍጥነት ይወሰናል፡፡

የተሽከርካሪ ፍጥነት በተሽከርካሪ መካከል መኖር ያለበት


ርቀት
ከ40-50 ኪ.ሜ በስዓት 20 ሜትር
ከ50-60 ኪ.ሜ በስዓት 25 ሜትር
ከ70-80 ኪ.ሜ በስዓት 30 ሜትር
ከ90-100 ኪ.ሜ በስዓት 36 ሜትር

(6) ተሽከርካሪን ማቆም የተከለከለባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች


 በ50 ሜትር ክልል ውስጥ፤
-
በማንኛውም መታጠፊያ እና ኩርባ መንገድ ላይ፤
 በ30 ሜትር ክልል ውስጥ፤
- ከአውቶብስ ማቆሚያ (ፌርማታ) ከፊት በ15 ሜትር፣ ከኋላ
በ15 ሜትር

© Filagote Abate Hailu 9


 በ20 ሜትር ክልል ውስጥ፤
-
ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ
 በ12 ሜትር ክልል ውስጥ፤
- ከእግረኛ ማቋረጫ መንገድ፣
- ከመገናኛ (መስቀለኛ) መንገድ፣
- ከድልድይ እና መሿለኪያ፣
- ከመንገድ ዳር ምልክቶች፣
- ከነዳጅ ማደያ፣
-
ከተሸከርካሪ መግቢያና መውጫ በር
 በ5 ሜትር ክልል ውስጥ፤
-
ከጎርፍ ማስተላለፊያ ፉካ (ቦይ/ቱቦ)
 በሌሎች ሁኔታዎች ማቆም የተከለከለባቸው
- የመንገዱ ስፋት ከ12 ሜትር በታች በሆነ መንገድ ላይ በቆመ
ተሽከርካሪ ትይዩ አድርጎ መቆም፤
- ከመንገድ ዳር ላይ ከቆሙ ተሽከርካሪዎች ላይ ደርቦ መቆም፤
- አደባባይ ክልል ውስጥ፤
- መቆም ክልክል ነው የሚሉ ምልክቶች ባሉበት ቦታ፤
- አንድ ተሸከርካሪ በመንገድ ላይ ቢበላሽ፡- ከተማ ክልል ውጭ
ከሆነ ለማንኛውም ተሽከርካሪ ከ48 ሰዓት በላይ ማቆም
አይቻልም፡፡ በከተማ ክልል ውስጥ ከሆነ አነስተኛና መካከለኛ
ተሽከርካሪዎችን ከ6 ሰአት በላይ፣ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ከ2
ሰዓት በላይ ማቆም አይቻልም፤ ወዘተ

(7) ተሽከርካሪን መቅደም የተከለከለባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች


 ከእግረኛ ማቋረጫ መንገድ፣ ከመገናኛ (መስቀለኛ) መንገድ፣ ከባቡር
ሀዲድ ማቋረጫ በ30 ሜትር ክልል ውስጥ፤
 በድፍን መስመር በተከፈለ መንገድ፣ መስመሩን በማቋረጥ መቅደም፤
 በተቆራረጠ መስመር በተከፈለ መንገድ፣ በ3ኛነት ተደርቦ መቅደም፤
 በጠባብ ድልድይ ላይ፣
 በማንኛውም መታጠፊያ እና ኩርባ ቦታ ላይ፤
 አደባባይ ክልል ውስጥ፤
 መቅደም ክልክል ነው የሚሉ ምልክቶች ባሉበት ቦታ፤ ወዘተ

© Filagote Abate Hailu 10


(8) ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎች እና ሁኔታዎች
 ዳገት በመውጣት ለሚገኝ ተሽከርካሪ፤
 አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ የአደጋ አገልግሎት መስጫ
ተሽከርካሪዎች፤
 በመገናኛ (መስቀለኛ) መንገድ ላይ ቀጥታ ለሚጓዙ ተሽከርካሪዎች፤
 አደባባይ ላይ ቅድሚያ ገብቶ ለሚዞር ወይም በመዞር ላይ ለሚገኝ
ተሸከርካሪ (ከበስተ ግራ በኩል ለሚመጣ ተሽከርካሪ)፤
 ከጠባብ መንገድ ወደ ሰፊ ወይም (ዋና) መንገድ ለሚገባ ተሽከርካሪ፤
 ቅድሚያ ስጥ የሚሉ ምልክቶች ባሉበት ቦታ፤ ወዘተ

(9) ልዩ ልዩ የትራንስፖርት ሕጎች


 የአደጋ አገልግሎት መስጫ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት በሚሰጡበት
ጊዜ ከ100 ሜትር ባነሰ ርቀት መከተል ክልክል ነው፤
 ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ተበላሽቶ ሲቆም መበላሸቱን ለመግለፅ
ከፊትና ከኋላ በ30 ሜትር ርቀት ላይ ባለ ሶስት ጎን ቀይ አንፀባራቂ
ምልክት መቀመጥ አለበት፤
 ተሽከርካሪ ተበላሽቶ ሲጎተት፣ በጎታቹና በተጎታቹ ተሽከርካሪ መካከል
ያለው ርቀት ከ3 ሜትር መብለጥ የለበትም፤
 ከባቡር ሀዲድ ማቋረጫ በ6 ሜትር ክልል ውስጥ ማርሽ መቀየር
ክልክል ነው፤
 ከተሽከርካሪ አካል ተርፎ የሚወጣ ጭነት፣ ከፊት ከ1 ሜትር ከኋላ ከ2
ሜትር መብለጥ የለበትም፤
 ማንኛውም የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተሳፋሪ አሳፍሮ ነዳጅ
መሙላት የለበትም፤ ወዘተ

(10) የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክቶች


የትራፊክ ፖሊስ በተለያዩ መንገድ ላይ የመንገድን ላይ ስነስርአትን
የሚያስከብር የፖሊስ አባካ ነው፡፡

የትራፊክ ፖሊስ የእጅ የእጅ ምልክቶቹ የሚያስተላልፉት


ምልክቶች መልዕክት

ከትራፊክ ፖሊሱ ከፊት ለፊት በኩል


የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ቁሙ፤

© Filagote Abate Hailu 11


ከትራፊክ ፖሊሱ ከፊት ለፊትና ከኋላ
በኩል የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ቁሙ፤

ከትራፊክ ፖሊሱ ከበስተቀኝ በኩል የሚገኙ


ተሽከርካሪዎች ቁሙ፣ ከትራፊክ ፖሊሱ
በስተግራ በኩል የሚገኙ ተሽከርካሪዎች
እለፉ፤

ከትራፊክ ፖሊሱ ከበስተቀኝ በኩል የሚገኙ


ተሽከርካሪዎች ቁሙ፣ ከትራፊክ ፖሊሱ
ከፊት ለፊት በኩል የሚገኙ ተሽከርካሪዎች
እለፉ፤

ከትራፊክ ፖሊሱ ከበስተቀኝ በኩል የሚገኙ


ተሽከርካሪዎች እለፉ፣ ከትራፊክ ፖሊሱ
ከኋላበኩል የሚገኙ ተሽከርካሪዎች ቁሙ፤

© Filagote Abate Hailu 12

You might also like