Professional Documents
Culture Documents
No 2 1
No 2 1
2.የረድፍ መስመሮች፡- ተሸከርካሪዎች በመንገድ ላይ ረድፋቸውን ጠብቀው እንዲጓዙ የሚረዳ ሲሆን አንድን
መንገድ ለሁለት መንገድ በመክፈል ባለሁለት አቅጣጫ በማድረግ እና ባለ አንድ አቅጣጫ በማድረግ ከአንድ
በላይ የሆኑ ተሸከርካሪዎችን ለማስተላለፍ እንዲቻል በመንገድ ላይ የሚሰመር ነው፡፡
የባለሁለት አቅጣጫ መንገድ መስመር፡-ሁሉም አሽከርካሪዎች የየራሳቸውን አቅጣጫ ተከትለው
ማሽከርከር፤መታጠፍ ዞሮ መመለስ እንደመንገዱና እንደትራፊኩ ሁኔታ በጥንቃቄ የተቆራረጠውን መስመር አልፎ
መሄድ ይችላል፡፡
የትራፊክ ፖሊስ የእጅ ምልክቶች ትርጉምና ተግባር
የትራፊክ ፖሊስ እጅ ምልክት ከፍት ለፊት የሚመጡ አሽከርካሪዎች ያስቆማል፤ ከኋላ የሚመጡትን
ያስቆማል፤ከፊት ለፊት ቆመው የነበሩትን አሽከርካሪዎች ወደፊትና ወደቀኝ አንዲጓዙ ይፈቅዳል፤የተለያየ የእጅ
አቅጣጫ ምልክት በማሳየት የተሳለጠ የትረፊክ ችንቅስቃሴ እንዲኖር ያደርጋል፡፡
የሀገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ በተሸከርካሪ አይነት (ክብደት) በመንገድ ሁኔታ የተከፈለ ነው፡፡
በተሸከርካሪ መሀል ሊኖር የሚገባ ርቀት
በሰዓት 40-50km/h የ 3 መኪኖች እርዝማኔ ወይም 20 ሜትር
በሰዓት 50-60km/h የ 4 መኪኖች እርዝማኔ ወይም 25 ሜትር
በሰዓት 70-80km/h የ 5 መኪኖ
ች እርዝማኔ ወይም 30 ሜትር
በሰዓት 90-100km/h የ 6 መኪኖች እርዝማኔ ወይም 36 ሜትር
የሰኮንዶች ህግ
የ 3-ሰከንድ ህግ፡- አንድን ተሸከርካሪ በመካከለኛ ፍጥነት ስንከተል መኖር ያለበት ክፍተት ነው(የመከተያ
ርቀት)
- ከሁለቱም አቅጣጫ በ 50 ሜትር ርቀት ላይ ለማየት የማይቻልበት አካባቢ ማቆም ክልክል ነው፡፡
- የመንገዱ ስፋት ከ 12 ሜትር በታች በሆነ መንገድ ላይ ማቆም ክልክል ነው፡፡
- በሶስተኝነት መደረብና ያለ በቂ ቦታ መቅደም ክልክል ነው፡፡
- እግረኞችን ለማሳለፍ የቆመን ተሸከርካሪ ቀድሞ ማለፍ ክልክል ነው፡፡
- ከቁልቁለት ፣ በጠመዝማዛና በኩርባ መንገድ ላይ ማቆም ክልክል ነው፡፡
- ፍሬቻ በ 50 ሜትር ርቀት ማሳየት አለበት፡፡
ቅድሚያ የሚያሰጡ ቦታዎችና ሁኔታዎች
- ቅድሚያ የሚያሰጡ ምልክቶች ባሉበት ቦታ ሁሉ
- ወደ መስቀለኛ መንገድ ቀድሞ ለደረሰ ተሸከርካሪ(ለተቃረበ)
- ለህዝብ ማመላለሻ
- ለባቡር
- በዋና መንገድ ላይ ለሚያሽከረክር ተሸከርካሪ
- ዳገት በመውጣት ላይ ላለ ተሸከርካሪ
- ለአደጋ ጊዜ ተሸከርካሪዎች
- ለእግረኞች
የማሽከርከር ሰነ ባህሪ
ስነ ባህሪ ምን ማለት ነው
- ስነ-ባህሪ፡- የሰዎች እና የእንስሳትን የባህሪን እና የአዕምሮን አስተሳሰብ ሂደት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያጠና
ነው፡፡
- ባህሪ፡- የሰውአስተሳሰብ፣ አመለካከት ድርጊት ውጤት ነው፡፡
የማሽከርከር ስነ-ባህሪ- አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ወቅት የሚያሳዩት ባህሪ የሚያጠናየሰነባህሪ ዘርፍ ነው፡፡
የስነ-ባህሪ ግቦች - የባህሪን መግለጽ
- የተለያዩ ባህሪያትን መንስኤ ማብራራት
- ወቅታዊን የባህሪን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የወደፊቱን መተንበይ
- ባህሪን ለማሻሻል፡፡
ለባህሪ መዳበር አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ነገሮች፡-
1. ተፈጥሮ
2. አካባቢ
3. የክህሎት ባህሪ፡- በአእምሮ አዛዥነትና በአካል እንቅስቃሴ የሚፈጸሙ ማናቸውንም የክህሎት ባህሪያት
ያካተተ ነው፡፡
የማሽከርከር ስነ-ባህሪያዊ ጉዳዮች
1. ዝግጁነት፡- የብስለት፣ የችሎታ፣ የትምህርትና የመነሳሳት የጋራ ውጤት ነው፡፡
ዝግጁነት መገለጫዎች - ጤነኛ መሆንን ማረጋገጥ
- ተሸከርካሪን ለጉዞ ዝግጁ ማድረግ
- የመንገድ፣ የአየርና የትራፊክ ሁኔታን በማሽከርከር ላይ ያለውን ተፅኖ መገመት መቻል
2.መነቃቃት፡- በሰዎች ውስጥ ያለ ሁኔታ ሆኖ ባህሪን ወደ ግብ የሚያንቀሳቅስ ሂደት ነው፡፡
ደስተኛነትና እርካታ
በማሽከርከር ወቅት የተረጋጋና መልካም የሆነ ስሜት ማዳበር
በማሽከርከር ወቅት መልካም የሆኑ ተግባሮችን መፈጸም ለምሳሌ፡- ማቀድ ራስን መገምገምና መወሰን)
ክህሎታዊ ሃላፊነት ጉድለት
ውጥረትና ድብርት
በማሽከርከር ወቅት መፍራት፣ መጨነቅ፣ አለመረጋጋት ለማሽከርከር ሃይልና ፍላቶት ማጣት፡፡
በስራናቸው ስህተቶች ምክንያት እራስን ዝቅ አድርጎ ማየትና ለራስ ክብር መንፈግ፡፡
2. ጥንቃቄ /ደህንነት/
ስሜታዊ ደህንነት
ራስን ማዘጋጀትና ሚዛናዊነት /እኩልነት/
ሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች ሊሰሩ የሚችሉትን ስህተት በማሰብ መጠንቀቅ
ለሌሎች መንገድ ተጠቃሚዎች ላለማስተጓጎል መዘጋጀት
ስሜታዊ ደህንነት ጉድለት
የሞገደኝነት ስሜትና በአጋጣሚዎች የመጠቀም ፍላጎት
ለሌሎች አሽከርካሪዎች አስገዳጅ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንዲገቡ መፈለግ
ሌሎች አሽከርካሪዎችን ለመቅደም ራስን በውድድር ስሜት ውስጥ ማስገባት
አዕምሮአዊ ደህንነት
ሚዛናዊ መለያ ባህሪ
ነገሮችን (ሁኔታዎችን) ከሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎች አንጻር መመልከት
ለሌሎች አውራጎዳና ተጠቃሚዎች ሃሳብን ባህሪ ሚዛናዊና የሆነ ገለጻ መስጠት
አዕምሮአዊ ደህንነት ጉድለት
ሚዛናዊነት የጎለው መለያ ባህሪያት
የራስን የማስከርከር ጥፋት ወደ ሌሎ አሽከርካሪዎች ላይ ለማሳበብ መሞከር ለሰራነው ጥፋት መከላከያ የሚሆንና
አሳማኝ የሚመስል ምክንያቶችን ለራስ ማቅረብ
ክህሎታዊ ደህንነት
ትህትና የተሞላበት መገብባትና የመረጋጋት ስሜት
ፈታኝ ስሜትን ጎጂ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መረጋጋትና ግፊትን መቋቋም
በመንገድ ተጠቃሚዎች ላይ ጸያፍ የሆነ ቃላትን ከመጠቀም መቆጠብ
ክህሎዊ ደህንነት ጉድለት
ትህትና የጎደለው ምልልስ እና የተጋነነ አፀፋ መመለስ
ሌላው አሽከርካሪ ለሚያሳየው አግባብነት ለሌለው ባህሪ የተጋነነ አጸፋ መስጠት
መንገድ ተጠቃሚዎችን በቃል ወይም በምልክት መሳደብ
3. ብቃት
ስሜታዊ ብቃት
ደንብ ማክበር እና ልበ ሙሉነት
ለትራፊክ እንቅስቃሴ ደንብና ስርዓት ራስን ማስገዛት
ከጎንና ከፊት ለፊት ያለን መኪና በጣም ተጠግቶ ማሽከርከር
ሰፋ ያለ ቦታ በመውሰድ መኪና ማዞር
ለትራፊክ ህግ ተገዥ ያለመሆን የመሳሰሉት ናቸው፡፡
አልኮል መጠጥ የተመረዘ አሽከርካሪ ሲያጋጥመን ማድረግ ያለብን ክንዋኔዎች
ተሸከርካሪውን አለመጠጋት
ለፖሊስ ማሳወቅ
ከምሽቱ 4፡00-8፡00 ሰዓት በሚያሽከረክሩበት ወቅት ከወትሮ የተለየ ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
አልኮል መጠጥ በጠጡ ወቅት ያለማሽከርከር፡- መጠጥ ሊጠጡ ካሰቡ
በህዝብ ትራንስፖርት መጠቀም
ያልጠጣ አሽከርካሪ እንዲያሽከረክር ማድረግ
ሌላ አሽከርካሪ ደውሎ መጥራት
መጠጡን ቤት ማስመጣት
የጠጡበት ቦታ ማደር
7. ኮኒክቲንግ ሮድ(ቤላ) ፒስተን እና ክራንክ ሻፍትን የሚያገናኝ ፒስተን አናት ላይ የተፈጠረውን ሀይል
ለክራንክ ሻፍት የሚያስተላልፍ ነው፡፡
1. የኤሌትሪክ ክፍሎች
2.1 እሳት የማቀጣጠል ዘዴ
2.2 ሞተር የማስነሳት ዘዴ
2.3 ባትሪ የመሙላት ዘዴ
2.4 የተለያዩ የመብራት ክፍሎች
2.2 ሞተር የማስነሳት ዘዴ
ባትሪ፡- ኬሚካል ሀይል ወደ ኤሌክትሪካል ሀይል የሚለወጥ ሲሆን በውስጡ ሊድፐር ኦክሳይድና
ስፖንጅሊድ የሚባሉ ንጥረ ነገሮችና 65 የባትሪ ውሃን 35 ሰልፈሪክ አሲድን የሚይዝ ክፍል
ነው፡፡የሞተር ማስነሻ ቁልፍ፡- ከባትሪ ወደ ተለያዩ ክፍሎች ኤሌክትሪክ የሚያስተላልፍና
የሚያቋርጥ ነው፡፡
ስታርተር ሞተር/ሞተሪኖ/፡- ከባትሪ የተቀበለውን የኤሌክትሪክ ሀይል ወደ ሜካኒካል ሀይል በመለወጥ
ሞተርን ለማስነሳት የሚያገለግል ክፍል ነው፡፡
2.3 ባትሪ የመሙላት ዘዴ
ጄኔሬተር/ዲናሞ/፡- ሜካኒካል ሀይል ወደ ኤሌክትሪካል ሀይል በመለወጥ ባትሪን ቻርጅ ያደርጋል እንዲሁም ሞተር
በሚሰራበት ወቅት ሀይልን ይሰጠናል፡፡
ሬጉሌተር፡ ጀኔሬተር ከሚፈልገው በላይ የኤሌክሪክ ሀይል አመንጭቶ ወደ ተለያዩ ክፍሎች እንዳያስተላልፍ
የሚቆጣጠር ክፍል ነው፡፡
አነስተኛ ጥገና ማለት አሸከርካሪዎችስለሚያሽከረክሩት ተሸከርካሪ መጠነኛ የጥገና እውቀት ኖራቸው ቀላል
ብልሽት ሲያጋጥማቸው በመጠገን ተሽከርካሪ ወደከፋ ወጪ መቀነስ ነው፤፤በተጨማሪ ጥገና በወቅቱ
በአሽከርካሪ አቅም በማከናወን ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ነው፡፡
በአሽከርካሪ የሚከናወን አነስተኛ ጥገና ሂደት
ተሽከርካሪን ማፅዳት፡- አንድን ተሸከርካሪ በንፅህና መያዝ በቆሻሻ ምክንያት በተሸከርካሪው ክፍሎች ላይ ሊደርስ
የሚችለውን ብልሽት ከመከላከሉም በላይ በጥገና ወቅት የተሰነጠቁ፤ የተሰበሩ ክፍሎችን በግልፅ በማወቅ የጥገና
አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡
የሥራ ላይ ደህንነት ጥያቄ፡-አንድ የጥገና ባለሙያ የተሸከርካሪ ጥገና ሲያከናውን የሚከተሉትን የስራ ላይ
ጥንቃቄ መሳሪያዎች መጠቀሙን ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡ ከነዚህም ውስጥ የስራ ቱታ ፤ የስራ ጫማ፤
ጓነት እና የራስ ቆብ ፤ የአይን መከላከያ መነፀር የመሳሰሉትን የስራ ላይ ደህንነት መጠበቂያ እቃዎች በአግባቡ
በስራ ጊዜ መጠቀም ይገባል፡፡
ተሸከርካሪ በሚፀዳበት ጊዜ የሚወሰድ ቅደመ ጥንቃቄ
ተሸከርካሪው የሚታጠብበትን ስፍራ መለየት
ተሸከርካሪውን በማጠቢያ ጉድጓድ ላይ በትክክል ማቆም
እንዳይንሸራተት ከእጅ ፍሬን በተጨማሪ ታኮ ማድረግ
በሮችና መስታዎቶች መዘጋታቸውን ማረጋገጥ
ያገለገሉ ዘይቶችን አወጋገድ ሂደት
የሚወገደውን ዘይት መለየት
የመቀበያ እቃ ማዘጋጀት
አስፈላጊውን የስራ ልብስ መጠቀም
ለስራው የሚያስፈልጉ መፍቻዎችን ማዘጋጀት
ለነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥገና
የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች ሲጠገኑ የምንገለገልባቸው መሳሪያዎች የሚከተሉት ናቸው
የተለያየ መጠን ያላቸው መፍቻዎች
የነዳጅ ማጣሪያ፤ የአየር ማጣሪያ፤ ንፁህ ነዳጅ
ለማቀዝቀዣ ክፍሎች ሊደረግ የሚገባ ጥገና፡-ለማቀዝቀዣ ክፍሎች የሚያስፈልጉ የጥገና እቃዎች ቴርሞስታት፤
ራዲያተር ውሀ፤ ችንጋ፤ ቬንትሌተር፤ የራዲያተር ማጠቢያ ፍላሸር እንዲሁም ፒንሳ፤ ጠፍጣፋ ካቻቢቴ፤
የተለያዩ አይነት ያላቸው መፍቻዎች የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የመሪ ክፍሎች ጥገና፡-ለመሪ ክፍሎች ጥገና አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎች የመሪ ዘይት፤ ችንጋ ፤ ግሪስ ፤ንፁህ
ጨርቅ እንዲሁም የተለያየ መጠን ያላቸው መፍቻዎች ናቸው፡፡
የፍሬን ክፍሎች ጥገና
የተሸከርካሪ ማነዋሎች በአይነት በሚሰጡት አገልግሎት የተለያዩ ሲሆኑ በአብዛኛው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
አገልግሎት ይሰጣል፡፡
የተሸከርካሪ ክፍሎች ልኬትን ለማወቅ ይረዳሉ
ለተሸከርካሪ ክፍሎች ማድረግ የሚገባን ጥንቃቄ ያስረዳል
የተሸከርካሪ ክፍሎች የሰርቪስ ጊዜ ያሳውቃሉ
ባለንብረቶች ስተሸከርካሪያቸው አይነት ፤ መጠንና ደረጃ እንዲያውቁ
ተገቢ የሆኑ ማንዋሎችን መለየት
የማንዋል አይነት
የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል፡- የተሸከርካሪውን የተለያዩ ክፍሎችን የሚገልፅ ሲሆን የተሸከርካሪዎችን ምርት
ቁጥር፤ ሞዴል፤ የሞተር ቁጥር፤ የተመረተበት ዓ.ም ፤ የሻንሲ ቁጥር፤ የአክስል ክብደት መጠን፤ ጠቅላላ ነጠላ
ክብደት ወ.ዘ.ተ የሚያብራራ የማናዋል አይነት ነው፡፡
የጥገና ማንዋል፡-ተሸካርካሪው ብልሽት ሲያጋጥመውና እንዴት ተደርጎ መጠገን እንዳለበት የሚገልፅ ማንዋል
ነው፡፡
የመለዋወጫ እቃ ማንዋል፡-የእቃው አይነትና የመለያ ቁጥርና አጠቃላይ የእቃው መግለጫ የሚገኝበት
የማንዋል አይነት ነው፡፡
ማንዋል አጠቃቀም፡- የማንዋል መረጃዎችንና ልኬቶችን መጠቀም ተሸከርካሪ ሲፈተሽ፤ሲጠገን ሰርቢስ ሲደረግ
በማንዋል ውስጥ የተቀመጡትን መረጃዎች በትክክለኛ መንገድ ተጠቅሞ ስራ ማከናዎን የተሸከርካሪ እድሜ
ከማራዘም በተጨማሪ ገንዘብ ወጪ ይቀንሳል
በማንዋል ውስጥ የሚገኙ ምልክቶችን መለየት
መለኪያዎችን መለየት
ማንዋል ውስጥ ያሉትን አማራጭ መረጃዎችን መጠቀም
መረጃዎችን ልኬቶችን መተርጎም
የስራላይ ደህንነት እና የአደገኛ አደጋ ምላሽ
ንቁ ቀልጣፋ መሆን
የስራ ላይ ደህንነት ጥንቃቄ ስርአቶች
የግል የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች ፤የእጅ ጎንት ፤ካፖትር ፤ጭንቅላት መከላከያ
የጥንቃቄ መሳሪያወች
የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ ሳጥን የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ፤ታኮ የመገናና መሳሪያዎች
የጉዞ መረጃዎችን ማሰባሰብ እና እቅድ ማዘጋጀት
አንድ አሽከርካሪ መረጃን በአግባቡ የመጠቀም፤ የመያዝና የማስተላለፍ ችሎታውን በማዳበር ተሸከርካሪውን
ተሳፋሪውንና የጭነቱን ደህንነት በመጠበቅ አንፃር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መረጃዎችን በመፈለግ
በመያዝና መባስተላለፍ ከፍተኛ ትኩረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡
አሽከርካሪዎች መረጃን ለማሰባሰብና ለማስተላለፍ የማስታወሻበድተር፤ ሬዲዩ፤ ሞባይል፤ ቪዲዩ ካሜራ እና
ፎቶግራፍ ካሜራ መሳሰሉትን መጠቀም ይችላሊ፡፡
የጉዞ መድረሻ፡- አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የጉዞውን ር 4 ቀትና መዳረሻ ማወቅ ጠቀሜታዎች
ይኖሩታል፡፡እነዚህም የጉዞ እቅድ በትክክል ለማዘጋጀት፤ ተሸከርካሪ ለጉዞ ላማዘጋጀት፤ የቁርስና የምሳ ቦታዎችና
ለማዘጋጀት
የመንገድ ላይ አገልግሎቶች፡- አንድ አሽከርካሪ በጉዞ ወቅት ለራሱ፤ ለተሳፋሪውና ለተሸከርካሪው የሚያስፈልጉ
የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶች ስለሚኖሩ ጉዞውን ሲያቅድ እነዚህን የአገልግሎት ዘርፎች ሊያገኝ በሚችልበት
መልኩ ቢሆን ይመረጣል፡፡ የነዳጅ ማደያዎች፤ ሆቴሎች፤ የስልክ አገልግሎት መስጫ፤ የፖሊስ ስልክ አድራሻ፤
የአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራዎች የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የመንገድ ሁኔታ መረጃ፡-በሀገራችን ያሉ የመንገድ አይነቶች እንደ አካባቢው መልክአ ምድርና የአየር ንብረት
ሁኔታ በተለያየ መልክ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ጉዞው የሚካሄድበትን መንገድ አደገኛ ቁልቁለትና ዳገት፤
ጠመዝማዛ ፤ ጠባብ ድልድይ፤ መሻለኪያ መሆኑን ለይቶ ማወቅ የተለያዩ የማሽከርከር ስልቶችን እንዲተገብር
ይረዳል፡፡
የመንገድ ደረጃ፡- አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ ወይም ከማቀዱ በፊት ስለመንገዱ ሁኔታ አስቀድሞ መረጃ
በመሰብሰብና ተገቢውን የጉዞ ዝግጅት በማድረግ ጉዞውን የተሳካ እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡
ከስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰነዶች
አሽከርካሪው ስለሚያጓጉዘው የጭነት ሁኔታ የሚገልፅ ስሆን ለምሳሌ፡-ለጭነቱ የተሰጠ የይለፍ /መውጫ/ ፤ፍተሸ
የማያስፈልገው መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ፤ የጭነት አይነት መግለጫየመሳሰሉትን መረጃዎች የሚያካትቱ
ናቸው፡፡
የድርጅቱ የስራ መመሪያዎች
አሰሪ ድርጅት እንደየ ስራ ባህሪያቸው አይነት ተግባራቸውን ለማከናወን የተለያዩ ህጎች ደንቦችና አሰራሮች
የሚነኖራቸው አሽከርካሪዎች የድርጅታቸውን ህግና ደንብ አክብረው የመሙላት ግዴታ አለባቸው፡፡
የጉዞ መረጃዎችን አያያዝ /ሪፖርት መሙያ ቅፅ
የጉዞ መረጃዎች ማለት የጉዞውን ሁኔታ በአጠቃላይ የሚገልፅ መረጃዎች ሲሆኑ ከሌሎች አካላት የተገኙትንም
መረጃዎች ያካትታል፡፡
በጉዞ መስመር ላይ ስለሚገኙ ማህበረሰቦች እና የጉዞ መስመር ደህንነት ሁኔታ መረዳት
መልካም ግንኑነትን ለመፍጠር ቋንቋ፤ ባህልና የፀጥታ ሁኔታ አሽከርካሪው በጉዞ ላይ ስለሚያጋጥሙት
ማህበረሰቦች ማንነት በሚገባ መገንዘብ እንዲሁም አሽከርካሪው በሚጓዝበት መንገድና በአካባቢው የሚገኘውን
የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ መረጃ በማሰባሰብ ጥንቃቄ የተሞላበት ጉዞ እንዲሆን ጥረት ማድረግ አለበት፡፡
የማሽከርከር ስልት