You are on page 1of 14

የማሽከርከር ስልት አንድ

ተሽከርካሪን ለእንቅስቃሴ (ለጉዞ) ዝግጁ ማድረግ

 ከጉዞ በፊት ተሽከርካሪን ስንፈትሽ ዉስጣዊ ፍተሻና ዉጫዊ ፍተሻ ብለን እንከፋፍለዋለን፡፡ጠቅለል
ሲደረግ ግን
 B፡- የተሽከርካሪን ባትሪ መፈተሽ
 L፡- የተለያዩ የመብራት ክፍሎችን መፈተሽ
 O፡- የተለያዩ የዘይት አይነቶችን መፈተሽ
 W፡- የራዲያተር ዉሃ መፈተሽ
 A፡- የጎማ ንፋስ እና የፍሬን ሲስተም ንፋስ መፈተሽ
 F፡- የነዳጅ ክፍሎችን መፈተሽ

1. የተሽከርካሪ ባትሪን ለመፈተሽ ማድረግ ያለብን ክንዉን


 ባትሪ በዉስጡ፡- - 35 ሳልፈሪክ አሲድ
- 65 የባትሪ ዉሃ /ዲስትልድ ዋተር/
- ስፖንጅ ሊድ እና ሊድ ፐር ኦክሳይድ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡
- ባትሪ የኬሚካል ሀይልን ወደ ኤሌክትሪክ ሀይል ይቀይራል፡፡
 ባትሪ ላይ ሁለት አይነት ተርሚናሎች (የባትሪ ጀሮዎች) ይገኛሉ፡፡
1. ፖዘቲቭ ተርሚናል (+) = ወፍራም ነዉ ፡፡
2. ነጌቲቭ ተርሚናል (-) = ቀጭን ነዉ፡፡
 የባትሪ ነጌቲቭ ተርሚናል ከተሽከርካሪዉ አካል ጋር ይታሰራል (ግራዉንድ ይደረጋል)፡፡
 በተሽከርካሪ የምንጠቀማቸዉ ሁለት የተለያዩ ባትሪዎች አሉ፡፡

- ሲልድ (የታሸገ ባትሪ)= አሲድ እና ዉሃ የማይጨመርበት ባትሪ

- አን ሲልድ (ያልታሸገ ባትሪ)= አሲድና ዉሃ ጨምረን የምንጠቀምበት ባትሪ

 ባትሪ ሲፈታ፡- 1. ነጌቲቭ (-) 2. ፖዘቲቭ (+)

 ባትሪ ሲታሰር፡- 1. ፖዘቲቭ (+) 2. ነጌቲቭ (-) መሆን አለበት፡፡

 አሽከርካሪዎች ሞተር ከማስነሳታቸዉ በፊት፡-


 የባትሪ ተርሚናሎች በትክክል መታሰራቸዉን
 ባትሪዉ ከተሽከርካሪዉ አካል ጋር በትክክል መታሰሩን
 የባትሪዉ አሲድና ዉሃ አለመጉደሉን
 የባትሪ ከዳን ቀዳዳዎች በቆሻሻ አለመደፈናቸዉን
 ባትሪዉ በከመዳሪ ጎማ አለመሸፈኑን ማረጋገጥ
 የባትሪዉ ዉሃ ከጎደለ የተጣራ ዉሃ እስከ ምልክቱ ድረስ መሙላት
 አሲድና ዉሃ ሲዘጋጅ፡- - ከመቀላቀያ ዕቃዉ መጀመሪያ ማድረግ ያለብን ዉሃ ነዉ
-ቀጥሎ ከዉሃዉ ላይ አሲድ መጨመር አለብን
 የባትሪ ተርሚናሎች ላይ ቆሻሻ ካለ በቤኪንግ ሶዳ ማፅዳት /በዎየር ቡርሽ/
 ባትሪን ስንፈትሽና ስናፀዳ አሲዱ እንዳይጎዳን ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡

2. የተለያዩ የተሽከርካሪ የመብራት ክፍሎችን መፈተሽ


 በተሸከርካሪ ላይ የሚገኙ የመብራት ክፍሎች የምንላቸዉ፡-
1. የግንባር መብራት፡- - አጭር እና ረዥም ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡

2. የፍሬን መብራት /ስቶፕ ላይት/፡ - ከኋላ በኩል የሚገኝ ቀይ ደማቅ አሽከርካሪዉ .


ፍሬን ሲይዝ የሚበራ መብራት ነዉ፡፡

3. የፍሬቻ መብራት፡- -የግራ ፍሬቻ እና የቀኝ ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡

1. የግራ ፍሬቻ ጥቅሞች 2. የቀኝ ፍሬቻ ጥቅሞች


. 1. ተሽከርካሪን ለመቅደም 1. ተሽከርካሪን ለማስቀደም

2. ከቆሙበት 2. ለመቆም

3. ወደ ግራ ለመታጠፍ 3. ወደ ቀኝ ለመታጠፍ

4. በስተግራ ዞሮ ለመመለስ 4. ከግራ ወደቀኝ ረድፍ ለመቀየር

5. ከቀኝ ወደ ግራ ረድፍ ለመቀየር

4. የኋላ ማርሽ መብራት፡- - ከኋላ በኩል የሚገኝ ነጭ ከለር ያለዉ R /የኋላ ማርሽ/ ስናስገባ የሚበራ
መብራት ነዉ፡፡

5. የሀዛርድ /አደጋ/ መብራት፡- ተሽከርካሪ ሲበላሽ ወይም አደጋ ሲገጥመን የምናበራዉ የመብራት
አይነት ነዉ፡፡

6. የጭጋግ መብራት፡- በዘመናዊ ተሽከርካሪ ላይ የሚገኝ በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የምናበራዉ መብራት
ነዉ፡፡

7. የሰሌዳ መብራት፡- በምሽት ወቅት የተሽከርካሪዉ ሰሌዳ በጉልህ እንዲታይ የሚበራ መብራት ነዉ፡፡

8. የጋቢና መብራት (ለአሽከርካሪዎች)፡- አሽከርካሪዎች በምሽት ወቅት በጉዞ ላይ እያሉ ይህን


መብራት ማብራት የለባቸዉም፡፡

9. የዉስጥ መብራት (ለተሳፋሪዎች)

10. የፓርኪንግ (የማቆሚያ) መብራት ፡- ከፊት ነጣ ነጣ ያለ ከኋላ ቀይ ደብዘዝ ያለ ተሽከርካሪን


በምሽት መንገድ ላይ ስናቆም የሚበራ መብራት ነዉ፡፡

 አሽከርካሪዎች ከጉዞ በፊት ሁሉም የመብራት ክፍሎች መብራታቸዉን ማረጋገጥ አለብን


. 3.የተለያዩ የዘይት አየነቶችን መፈተሽ
 በተሽከርካሪዉ ላይ የምንጠቀምባቸዉ ዘይቶች ፡-
1. የፍሬን እና የፍሪሲዮን ዘይት= /የታሸገ /DOT3 OR DOT4/
2. የመሪ ዘይት =10 ቁጥር
3. የሞተር ዘይት = 40 /30/ ቁጥር
4. የካቢዮ ዘይት = 90 ቁጥር
5. የዲፈረንሻል ዘይት ናቸዉ፡፡ = 140 ቁጥር
 የፍሬን እና የፍሪሲዮን ዘይት መፈተሽ
የፍሬን እና የፍሪሲዮን ዘይት መፈተሽ
 ፍሬን ፡- የእጅ ፍሬን እና የእግር ፍሬን ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡
 የእጅ ፍሬን መስራቱን ለማረጋገጥ ፡-
 የእጅ ፍሬን አንድ ተሽከርካሪ ከቆመ በኋላ ለአጭር ወይም ለረዥም ጊዜ ከቆመበት
እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ይጠቅማል፡፡
 ተሽከርካሪዉን ዳገት /ቁልቁለት/ ቦታ በመዉሰድ
 ማርሹን ዜሮ /N/ ላይ ማድረግ
 የእጅ ፍሬን በአግባቡ መሳብ
 የእግር ፍሬንን መልቀቅ
 ከተንሸራተተ የእጅ ፍሬን እንደማይሰራ መረዳት አለብን
 ማርሽ እና ታኮ ተጠቅመን የእጅ ፍሬን መስራቱን ማረጋገጥ አንችልም
 የእግር ፍሬን መስራቱን ለማረጋገጥ፡-
 በዘይት የሚሰራ የእግር ፍሬን አብዛኛዉን ጊዜ በቤት አዉቶሞቢል ላይ ይገኛል፡፡
 የእግር ፍሬን በጉዞ ላይ ያለን ተሽከርካሪ ፍጥነት ለመቀነስ እና ሙሉ በሙሉ ለማቆም
ያገለግላል፡፡
 የፍሬን ዘይት በቋቱ ዉስጥ በሌብሉ መሰረት መኖሩን ማረጋገጥ
 የፍሬን ዘይት ቱቦዎች ዘይት ወደ ዉጭ የሚያፈሱ መሆናቸዉን ማረጋገጥ
 የፍሬን ፔዳል ከ 1 እስከ 2 ጊዜ ያዝ ለቀቅ በማድረግ ፍሬን መስራቱን ማረጋገጥ
 ፍሬኑ የማይሰራ ከሆነ ወዲያዉኑ ለባለሙያ ማሳየት አለብን
 የፍሬን ፔዳሉን ስንጠቀም የማያንሸራትት እና በስር በኩል ፍሬን እንዳይዝ የሚያደርግ ነገር
አለመኖሩን ማረጋገጥ
 የመሪ ዘይት መፈተሽና መሙላት

 መሪ ከተሽከርካሪ ከፊት ጎማ ጋር በመያያዝ ተሽከርካሪን ወደ ፈለግንበት አቅጣጫ ለመምራት


ያስችላል፡፡
 የመሪ ዘይት ቋቱን በመክፈት መጠኑን ማየት
 የመሪ ዘይት መጠኑ ከቀነሰ መሪ ለመጠቀም ያስቸግራል
 የመሪ ዘይት ስንፈትሽም ሆነ ስንሞላ መሪዉ መሀል በመሀል መሆን አለበት
 መሪ ወደ ግራ /ወደ ቀኝ/ ከተያዘ የዘይት መጠኑ በትክክል በማወቅ ያስቸግራል
 የመሪ ዘይት ቱቦዎችን እና የመሪ ችንጋዎችንም መፈተሽ አለብን
 የሞተር ዘይትን ለመፈተሽ ማድረግ ያለብን ክንዉን
 ተሽከርካሪዉ የቆመበት ቦታ ቀጥ ያለ መሆኑን ማረጋገጥ
 በስር በኩል ዝቅ በማለት ፍሳሽ መኖር እና ስለአመሩን ማረጋገጥ
 እስትራሾ /ንፁህ ጨርቅ/ ማዘጋጀትና ኮፈኑን በአግባቡ መክፈት
 ዲፕስቲክ /ሊቬሎን/ ማዉጣትና ከላዩ ላይ ያለዉን ዘይት በመጥርግ ወደ ነበረበት እስከ
መጨረሻዉ ማስገባት
 ዲፕስቲኩን በድጋሜ ማዉጣትና ቀጥ አድርጎ በመያዝ መጠኑን በእይታ መለየት
 መወፈሩን&መቅጠኑን&እንዲሁም መቆሸሹን በጣታችን በመንካት መለየት
 ከቀጠነ&ከወፈር&ከቆሸሸ መቀየር አለበት
 ንፁህ ዘይት ኑሮት ከቀነሰ የተወሰነ ዘይት መጨመር
 በመጨርሻም ዲፕስቲኩን ማስገባትና ኮፈን መዝጋት አለብን
 የሞተር ዘይት እንደ ተሽከርካሪዉ የመንገድ፣ የአየር እንዲሁም የስራ ሁኔታ ይቀይራል
 በማኑዋሉ መሰረት ግን በየ 5000 ኪ.ሜትር ይቀየራል
 የሞተር ዘይትን መጠን ለማወቅ የምንጠቀምበት መሳሪያ ዲፕስቲክ /ሊቬሎ/ ይባላል
 በሞተር ዉስጥ ያለ ዘይት በክፍሎች በትክክል መዘዋወሩን የምናዉቀዉ ዳሽ ቦርድ ላይ ባለ
የዘይት ግፊት አመልካች ጌጅ ነዉ
 የካቦዮ እና የዲፈረንሻል ዘይት መፈተሽ
 የካቢዮ እና የዲፈረንሻል ዘይት አለመፍሰሱን ዝቅ ብሎ ማረጋገጥ
 ዘይቱ ካለቀ የካቢዮ ጥርስን እና የዲፈረንሻል ጥርስ ስለሚሰበር መጠንቀቅ አለብን
4.የራዲያተር ዉሃ መሙላት እና የክዳን ቫልቮችን መፈተሽ
 የራዲያተር ክዳኑን በእጃችን ጫን በማድረግ መክፈት
 በራዲያተር ዉስጥ ያለን የዉሃ መጠን እና ንፅህና ማየት
 የራዲያተር ዉሃ ወደ ዉጭ አለመፍሰሱን በሚገባ መመልከት
 በራዲያተር እና በኤክስፓንሽን ታንከር /ሪዘርቬየር/ ዉስጥ የሚከተሉት ኬሚካሎች መጨመራቸዉን
ማረጋገጥ
1. ፀረዝገት /አንቲ ረሰት/ = የዝገት መከላከያ
2. ፀረ በረዶ /አንቲ አይስ/ = የበረዶነት መለኪያ
 በራዲያተር ክዳን ላይ የሚገኙ ስፕሪንጎች /ቫልቮች/ መስራታቸዉን በጣታችን ጫን ለቀቅ በማድረግ
ማረጋገጥ
1. ፕሬዥር እስሪንግ /ቫልቭ/ 2. ሳክሽን /ቫኪዮም/ ቫልቭ
 በሪዘርቩ ዉስጥ ዉሃ በሌብሉ ልክ መኖሩን ማረጋገጥ
 በራዲያተር ዉስጥ ያለዉ ዉሃ ከቀነሰ ሞተሩ በሚኒሞ እየሰራ ዉሃ መጨመር
 ዉሃ ፈፅሞ ከሌለዉ ሞተር ሳይነሳ ራዲያተር መሙላትና ሞተር በማስነሳት በሚኒሞ እየሰራ ዉሃ
መጨመር አለበት
 የዉሃ ፓንፕ ችንጋ ከላላ ወይም በጣም ከተወጠረ ዉሃ መቅዘፍ ስለማይችል ሞተር ከመነሳቱ በፊት
ችንጋዉን በጣታችን ያዝ ለቀቅ በማድረግ ማረጋገጥ አለብን
 የቤልት ወይም ችንጋ በትክክል አለመወጠር፡-
- የዉሃ ፓምፕ
- ጀኔሬተር /ዲናሞ/
- ፉን /ቬንቲሌተር/
- የመሪ ዘይት /ፓምፕ/ በአግባቡ እንዳይሰራ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

5.የተሽከርካሪን የጎማ ነፋስ መፈተሽ


 ተሽከርካሪን ከማሽከርከራችን በፊት የጎማ ነፋስ በትክክል መኖሩን ማረጋገጥ አለብን
 ያልጫነ ተሽከርካሪ ከሆነ የጎማዉን የነፋስ መጠን ለመገመት ያዳግታል
 በብረት ጎማ /ሌባ ጎማ/ መታመታ በማድረግ በድምፁ መለየት
 ወፍራም ድምፅ ካለዉ ነፋሱ እንደቀነሰ መገመት
 ቀጭን ድምፅካለዉ ነፋሱ በቂ እንደሆነ መገመት
 ትክክለኛዉን የነፋስ መጠን ማወቅ የምንችለዉ ግን በጎማ ንፋስ መለኪያ ጌጅ በማስለካት ነዉ
 የጎማዉን አቀማመጥ እና ጥርሱ አለመበላቱን ማረጋገጥ
 የጎማ ማሰሪያ /የኮለኔቲ ብሎኖች/ ጠብቀው መታሰራቸውን ማረጋገጥ
 የጎማ ነፋስ በጣም ከተሞላ የጎማዉ መሃል ቶሎ ያልቃል
 የጎማ ነፋስ በጣም ከቀነሰ፡-
- የጎማ ዳር እና ዳር ቶሎ ያልቃል
- መሪ ወደ ቀነሰበት አቅጣጫ ይጎትታል
- ሞተሩ ከመጠን በላይ ይሞቃል
- የተሽከርካሪ ፍጥነት ይቀንሳል
6. የነዳጅ ክፍሎችን መፈተሽ
 በሳልቫቲዮ ዉስጥ በቂ ነዳጅ መኖሩን በዳሽ ቦርድ ጌጅ አማካኝነት ማረጋገጥ
 ሳልቫቲዮ በአግባቡ መከደኑን ማረጋገጥ
 የሚያፈስ /የሚያንጠባጥብ/ የነዳጅ ክፍል አለመኖሩን ማረጋገጥ
 በተሽከርካሪ ላይ የሚገኙ ፔዳሎችን መፈተሽ ፡-
 በተሽከርካሪ ላይ ሶስት አይነት ፔዳሎች ይገኛሉ፡፡
1. የነዳጅ መስጫ ፔዳል /A/ ፡- ሰጥቶ የማይቀር መሆኑን ማረጋገጥ
2. የፍሬን ፔዳል /B/፡- የማያንሸራትት እና በአግባቡ የሚሰራ መሆኑን ማረጋገጥ
3. የፍሪሲዮን ፔዳል /C/፡- በጣም ያልጠበቀ እና ያላላ ምቾት ያለዉ መሆኑን ማረጋገጥ
 በተሽከርካሪ ላይ የሚገኙ መስታዉቶችን መፈተሽ እና ማፅዳት
 በተሽከርካሪ ላይ የሚገኙ መስታዉቶች ፡-
 የግንባር መስታዉት
 የጎን መመልከቻ መስታዉት /ስፖኪዮ/
 የዉስጥ /የኋላ/ መመልከቻ ስፖኪዮ ናቸዉ
 በአጠቃላይ እነዚህን መስታዉቶችና የተሽከርካሪ ክፍሎችን በሚገባ በማፅዳት ተሽከርካሪዉን ለጉዞ
ማዘጋጀት አለብን
 ለድንገተኛ ጥገና /ደህንነት/ የሚያገለግሉ መስሪያዎች በተሽከርካሪያችን ዉስጥ ማስቀመጥ
አለብን እነሱም፡-
 እስኳርት /ተቀያሪ/ ጎማ
 የጎማ ብሎን መፍቻ
 ክሪክ እና የክሪክ ማንሻ
 የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ
 የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና መስጫ ሳጥን
 ፒንሳ /ፕላየር/
 ካቻሲቲ /እስክሪዉ ድራይቨር/
 የካንዴላ መፍቻ
 አንፀባራቂ ባለ ሶስት ማዕዘን ምልክት ወ.ዘ.ተ
 እራስን ለጉዞ ዝግጁ ማድረግ
 አሽከርካሪዎች እራሳቸዉን ለጉዞ ሲያዘጋጁ የሚከተሉትን ተግባራት ማከናወን አለባቸዉ
1. እራስን ከአልኮል መጠጥ፣ ከከባድ መድሀኒቶች፣ ከድብርት ነገሮች ነፃ መሆናቸዉን ማረጋገጥ
2. የተሽከርካሪ በርን በዉስጥ ባለዉ መዝጊያ በመዝጋት መቆለፋችን ማረጋገጥ
3. መሪ እና ፔዳሎችን በመቆጣጠር በሚያስችል ሁኔታ ወንበር ማስተካከል
4. አካባቢዉ በደንብ ለማየት በሚያስችል ሁኔታ የጎን እና የዉስጥ ስፖኪዮ ማስተካከል
5. የደህንነት ቀበቶዉን በደንብ ሉክ አድርጎ ማሰር
 ተሽከርካሪን ተቆጣጥሮ ማሽከርከር
 የተሽከርካሪ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች የሚባሉት፡-

1. የሞተር ማስነሻና ማጥፊያ ቁልፍ 4. የፍሪሲዮን ፔዳል እና የማርሽ መለዋወጫ

2. መሪ 5. የነዳጅ መስጫ ፔዳል ናቸው፡፡

3. ፍሬን

የማሽከርከር ስልት ሁለት


የተሽከርካሪ ኢንጅን /ሞተር/ ማስነሳትና ማጥፋት

1. ኢንጅን /ሞተር/ ለማስነሳት ማድረግ ያለብን ክንዉን


 ተሸከርካሪው በእጅ ፍሬን መቆሙን ማረጋገጥ
 ፍሪሲዮን በማፈን ማርሹ ዜሮ /N/ ላይ ማድረግ
 አዉቶማቲክ ማርሽ የተገጠመለት ተሽከርካሪ ከሆነ P/N ላይ ማድረግ
 የማስነሻ ቁልፍን ኳድሮ ላይ በአግባቡ መሰካት
 የሞተር ማስነሻና ማጥፊያ ቁልፍ አራት ደረጃዎች አሉት

1. LOCK /OFF/ 3. ON

2. ACC 4. START

 ቁልፉን ከ LOCK /OFF/ ወደ ON መጠምዘዝ


 የቤንዚን ሞተር ከሆነ ቾክ ቫልቩን በመሳብ ቁልፉን ወደ start መተምዘዝ
 የናፍጣ ሞተር ከሆነ ዳሽ ቦርድ ላይ የካዴሊቲ ምልክት በርቶ ሲጠፋ ቁልፉን ወደ start መጠምዘዝ
 ሞተር ስናስነሳ ቁልፉን start ላይ ከ 30 ሴኮንድ በላይ ይዘን መቆየት የለብንም
 በ 30 ሴኮንድ ዉስጥ ካልተነሳ ወደ ON በመመለስ 10 ሴኮንድ መጠበቅና በድጋሚ ወደ start
መጠምዘዝ
 ሞተር አልነሳ ካለ ቁልፍ ከመደብደብ እና በግፊት ከማስነሳት ይልቅ ለባለሙያ ማሳየት የመከራል
 ሞተር ከተነሳ በኋላ ቁልፍን ወደ start መጠምዘዝ ሞተሪኖ እንዲቃጠልና ፒኒዮን ጊሮች
እንዲሰበሩ ምክንያት ይሆናል
 በጣም በቅዝቃዜ ወቅት ሞተሩ እስኪነሳ ነዳጅ ደገፍ ማድረግ አለብን
 ሞተር መነሳቱን ስናረጋግጥ ነዳጅ እየሰጡ ማሞቅ ተገቢ ስላልሆነ ነዳጁን ወዲያዉኑ መልቀቅ
አለብን
 እንደተሽከርካሪዉ አይነትና ሁኔታ የሞተር ዘይት በክፍሎች እስኪሰራጭ ድረስ ቢያንስ ከ 10
እስከ 15 ደቂቃ በሚኒሞ ማሰራት አለብን
2. ኢንጅን /ሞተር/ ለማጥፋት ማድረግ ያለብን ክንዉን
 የምንቆምበትን ስፍራ መለየት
 በጉዞ ላይ እያለን ፍጥነትን በአንዴ ሳይሆን ደረጃ በደረጃ መቀነስ
 ሙሉ በሙሉ ፍሪሲዮን በማፈን በእግር ፍሬን መቆም
 ማርሹን ዜሮ /N/ ማድረግና የእጅ ፍሬን መያዝ
 ፍሪሲዮን እና የእግር ፍሬንን መልቀቅ
 እንደሞተሩ የሙቀት ደረጃ የዳሽ ቦርዱን ጌጅ በማየት በሚኒሞ ማሰራት አለብን
 የሞተር ማስነሻ ቁልፍን ከ ON ወደ LOCK /OFF/ መጠምዘዝ

ተሽከርካሪን ከቆመበት እንቅስቃሴ ወይም ጉዞ ማስጀመር


 ጉዞ ለማስጀመር ማድረግ ያለብን፡-
1. አካባቢዉን እና የትራፊክ እንቅስቃሴዉን በሚገባ ማየት
2. ማርሽ መጠቀም
 የማርሽ አጠቃቀማችን የተሽከርካሪዉን ፡-
1. ቦታዉን
2. የጫነዉን ጭነቱን
3. ጉልበቱን ያገናዘበ መሆን አለበት፡፡
 ተሽከርካሪን ከቆመበት ጉዞ ለማስጀመር የምንጠቀመዉ ማርሽ
- በዳገት፡- ጫነም አልጫነም በ 1 ኛ ማርሽ እንነሳለን
- በቁልቁለት፡- ጫነም አልጫነም በ 2 ኛ ማርሽ እንነሳለን
- በሜዳ፡- ከጫነ በ 1 ኛ ማርሽ ካልጫነ በ 2 ኛ ማርሽ እንነሳለን
 ተሽከርካሪን በምናሽከረክርበት ወቅት የምንጠቀመዉ ማርሽ
- በዳገት እና ቁልቁለት መንገድ ላይ መጠቀም ያለብን ከባድ ማርሽ ነዉ
- በሜዳ ላይ ስናሽከረክር ቀላል ማርሽ መጠቀም አለብን
 ተሽከርካሪን መንገድ ላይ ስናቆም የምንጠቀመዉ ማርሽ
- በዳገት ላይ = 1 ኛ ማርሽ
- በቁልቁለት ላይ = R/የኋላ/ ማርሽ
- በሜዳ ላይ = 1 ኛ /R/ ማርሽ ነዉ፡፡
 ከባድ ማርሽ የሚባሉት ለተሽከርካሪዉ ጉልበት የሚያስገኙ ነገር ግን ፍጥነት
የሌላቸዉ ማርሾች ናቸዉ፡፡ (1 ኛ፣ 2 ኛ እና R)
 ቀላል ማረሽ የሚባሉት ለተሸከርካሪዉ ፍጥነት የሚሰጡ ነገርግን ጉልበት የሌላቸዉ
ማርሾች ናቸዉ (3 ኛ&4 ኛ እና 5 ኛ)

ማርሽ የመጨመር ቅደም ተከተል


 ፍሪሲዮኑን እስከ መጨረሻዉ ማፈን
 የማርሽ ዘንጉን ወደ አንድ አቅጣጫ ማስገባት
 ፍሪሲዮን ሳይፈጥን ሳይዘገይ መልቀቅ
 ነዳጅ በትንሹ መስጠት እና የሞተሩን ድምጥ ማዳመጥ
 ትንሽ እንደተጓዙ ነዳጁ በመልቀቅ ፍሪሲዮን አፍኖ ሁለተኛ ማርሽ ማስገባት
 በዚህ መሰረት እስከ መጨረሻዉ ማርሽ እንጠቀማለን

ማርሽ የመቀነስ ቅደም ተከተል


 ነዳጁን ሙሉ በሙሉ በመልቀቅ
 ተሽከርካሪዉ በእግር ፍሬን ማብረድ
 ፍሪሲዮን በማፈን ከ 4 ኛ ወደ 3 ኛ /3 ኛ ወደ 2 ኛ/ እንደ አስፈላጊዘቱመቀነስ
 ፍሪሲዮኑን በስርአት መልቀቅ
 ማርሽ ስንጨምርም ሆነ ስንቀንስ በቅደም ተከተል መሆን አለበት

3.ፍሬቻን መጠቀም

 ማንኛዉም አሽከርካሪ ጉዞ ለመጀመር ቀድሞ ፍሬቻ ማሳየት አለበት፡፡


 ፍሬቻዉ የማይሰራ ከሆነ ተገቢ የሆነ የእጅ ምልክት ማሳየት አለበት፡፡

ባላንስ መስራት
 ግማሽ ፍሪሲዮን እና የነዳጅ ፔንዳል አመጣጥኖ ተሸከርካሪዉን ወደ ፊት ወይም ወደ ኋላ
እንዳይንሸራተት ለተወሰነ ጊዜ ማቆም ባላንስ ይባላል፡፡

 የዳገት ባላንስ ለመስራት ማድርግ ያለብን

 ፍሪሲዮን ፍሬን በመጠቀም ተሸከርካሪዉን ሙሉ በሙሉ ማቆም


 1 ኛ ማርሽ መጠቀም
 ግማሽ ፍሪሲዮን በመልቀቅ የተሸከርካሪዉን ድምፅ መስማት
 የእግር ፍሪንን በመልቀቅ ነዳጅ ድጋፍ ማድርግ
 የእጅ ፍሪንን ከተያዘ መልቀቅ
 ፍሪንሲዮንና ነዳጅን በማመጣጠን ተሸከርካሪዉ ወደ ፊት/ ወደ ኋላ እንዳይሽራተት
ማድረግ አለብን

 የቁልቁለት ባላንስ ለመስራት ማድርግ ያለብን


 ፍሪሲዮንና ፍሪን በመጠቀም መሉ በሙሉ ማቆም

 የኋላ /R/ ማርሽ መጠቀም

 ግማሽ ፍሪሲዮን በመልቀቅ የተሸከርካሪዉን ድምፅ ማዳመጥ

 የእግር ፍሬን በመልቀቅ ነዳጅ ድጋፍ ማድርግ

 የእጅ ፍሬንን ከተያዘ መልቀቅ

 ተሸከርካሪዉ ወደፊት/ወደ ኋላ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ አለብን

የመሪ አጠቃቀም
 መሪ ከተሽከርካሪ ከፊት ጎማ ጋር በመገናኘት ተሽከርካሪዉን ወደ ፈለግንበት አቅጣጫ
ለመምራት የሚያስችል የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ነዉ፡፡
 የመሪ አቀማመጥ ችሎታን ለማዳበር የመሪ አያያዝ በዋናነት ይከፈላል
1. በቀጥታ መንገድ የመሪ አያያዝ (መሪ እስትሬት)
2. ግማሽ ወደ ቀኝ የመሪ አያያዝ
3. ሙሉ ወደ ቀኝ የመሪ አያያዝ
4. ግማሽ ወደ ግራ የመሪ አያያዝ
5. ሙሉ ወደ ግራ የመሪ አያያዝ ናቸዉ፡፡

በቀጥታ መንገድ ወደ ፊት ስናሽከረክር የመሪ አጠቃቀም


 መሪዉን በሁለት እጃችን መሀልለመሀል መያዝ
 ክርናችንን ከሰዉነታችን ማስደገፍ
 የያዙትን መስመር ሳይለቁ ተሽከርካሪዉን ተቆጣጥሮ ማሽከርከር

በቀጥታ መንገድ በስፖኪዮ ወደ ኋላ የመሪ አጠቃቀም


 ይህ የመሪ አጠቃቀም በቀጥታ መንገድ ወደ ፊት ከማሽከርከር ጋር ተመሳሳይ ነዉ፡፡

በቀጥታ መንገድ ያለ ስፖኪዮ ወደ ኋላ የመሪ አጠቃቀም


 45 ዲግሪ ከወገብ በላይ ሰዉነታችንን ዘና በማለት ማዞር
 የመሪዉን የላይኛዉን ጫፍ በግራ /በቀኝ/ እጃችን መያዝ
 የግራ ወይም የቀኝ እጃችንን ከመቀመጫ ወንበር ላይ ማስደገፍ
 የተሽከርካሪዉ አካል የመጨረሻ ጠርዝ መሄድ ካሰብንበት መስመር ጋር ማገናኘት
 ከመስመሩ ላይወጡ ተሽከርካሪዉን በአግባቡ ተቆጣጥሮ ማሽከርከር

በጠመዝማዛ መንገድ የመሪ አጠቃቀም


 መሪን በሁለት እጃችን መሀል ለመሀል በመያዝ መሪዉ በመቀባበል መጠምዘዝ
 መሪዉን በአንድ እጅ ሳይለቁ በሌላኛዉ እጅ እየተቀባበሉ ማሽከርከር
 የመንገዱን ጠርዝ ከተሽከርካሪዉ አካል ጠርዝ ጋር በበቂ ርቀት ማየትና መገንዘብ
 መሪዉን ወደ ነበረበት አቅጣጫ በሚመለስበት ወቅት መሪን በዉስጥ በኩል መያዝ እጅ
ሊያሰብር ስለሚችል በዉስጥ አለመያዝ
 በከርቭ መንገድ ላይ ከመጠን በላይ ነዳጅ መስጠት መሪን ለመቆጣጠር ስለሚያስቸግር
ጥንቃቄ ማድረግ አለብን
 በጠመዝማዛ መንገድ ወደ ፊት ማሽከርከርና በጠመዝማዛ መንገድ በስፖኪዮ ወደ ኋላ
ከማሽከርከር ጋር ተመሳሳይነት አለዉ፡፡
 የመሪ አጠቃቀም ወደ ፊት ወደ ግራ እና ወደ ኋላ ወደ ግራ ተመሳሳይ ነዉ
 የመሪ አጠቃቀም ወደ ፊት ወደ ቀኝ እና ወደ ኋላ ወደ ቀኝ ተመሳሳይ ነዉ፡፡
ርቀትን ጠብቆ ስለማሽከርከር
 በጣም ተጠጋግቶ ማሽከርከር ለትራፊክ አደጋ መከሰት ምክንያት ነዉ
 ከኋላ እና ከፊት ግጭት እንዲበዛ ስለሚያደርግ ነዉ
 ስለሆነም አሽከርካሪዎች በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ማስተዋል ያለባቸዉ፡-
- ፍጥነታቸዉን
- የተንቀሳቃሹን ብዛት
- የመንገዱን አጠቃላይ ሁኔታ
- የአካባቢዉ አየር በርቀት የማሳየት ሁኔታ፡- ጭጋግ፣ ዝናብ፣ አቧራ ወዘተ
- የአሽከርካሪዉን የቴክኒክ አቋም
- የራስን ንቃትና ቅልጥፍና እንዲሁም አደጋን ፈጥኖ የመከላከል ችሎታ
- ከፊት ያለ አሽከርካሪ ምልክት ሳያሳይ በድንገት ቢቆምና አቅጣጫ ቢለወጥ
በቂ ርቀት መኖሩን
- ቢያንስ በሰዓት 10km/h የምትጓዝ ከሆነ 6 ሜትር ርቀት ወይም በመካከላችን አንድ
አዉቶሞቢል ገብቶ በመዉጣት የሚያስችል ጊዜ መኖሩን ማረጋገጥ
ተሽከርካሪን የመቅደምና የማስቀደም ስርዓት
1. ከፊት ያለን ተሽከርካሪን ለመቅደም ማድረግ ያለብን ክንዉን
 ቦታዉ ለመቅደም ያልተከለከለ መሆኑን ማረጋገጥ
 ተሽከርካሪን መቅደም የሚቻለዉ በግራ በኩል መሆኑን መረዳት
 በተቃራኒ አቅጣጫ ሌላ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ማረጋገጥ
 3 ኛ ተደራቢ ሁኖ መቅደም ክልክል መሆኑን መገንዘብ
 በስፖኪዮ ከኋላ ያለዉን ትእይንት መቆጣጠር
 በመጠኑ ወደ ግራ ወጣ በማለት ከፊት ማየት
 ከፊትያለን አሽከርካሪ በመብራት /በክልክል/ ማስጠንቀቅ
 ለሌሎች አሽከርካሪዎች ተገቢ ምልክት ማሳየት
 በድጋሚ በስፖኪዮ አካባቢዉን መመልከት
 ወደ ግራ የመሪ እርምጃ በመዉሰድ ፍጥነትን በመጨመር መቅደም አለብን ተሽከርካሪን
ከቀደምን በኋላ ተመልሰን ረድፍ ለመያዝ
 የቀደምነዉን ተሽከርካሪ የግንባር መብራት በስፖኪዮ መመልከት
 የቀይ ፍሬቻ ማብራት
 የቀኝ መሪ እርምጃ በመዉሰድ ረድፍን መያዝ
 ፍሬቻ ማጥፋት
2. ተሽከርካሪን ለማስቀደም ማድረግ ያለብን ክንዉን
 በፍጥነት እየመጣ ያለ እና ምልክት ያላየን ተሽከርካሪ መኖሩን ማረጋገጥ
 በቀኝ በኩል ሌላ ተሽከርካሪ አለመኖሩን ማረጋገጥ
 የሚቀድመን ተሽከርካሪ ከፊት ለአደጋ የማይጋለጥ መሆኑን ማረጋገጥ
 ፍቃደኛ መሆናችንን የቀኝ ፍሬቻ በማብራት የቀኝ ረድፋችንንመያዝ
 የሚቀድመን ተሽከርካሪ ረድፍን እንዲይዝ ፍጥነታችንን መቀነስ
ከፊት ለፊት የሚመጣን ተሽከርካሪ ለማሳለፍ
 የቀኝ ረድፍን በመያዝ በግራ በኩል በቂ ቦታ እንዲኖር ማድረግ
 ጠባብ መንገድ ከሆነ ሁሌም ቢሆን ቆሞ ቅድሚያ መስጠትን ማዳበር አለብን
 ሁለት ተሽከርካሪዎች ዳገትና ቁልቁለት መንገድ ላይ ቢገናኙ ዳገት የሚወጣዉ
ቅድሚያ ይኖረዋል
 ህዝብ የጫነ ተሽከርካሪ ከሆነ ከዳገትም ሆነ ከቁልቁለት ቅድሚያ ይኖራቸዋል
 በመጋቢ መንገድ ላይና በዋና መንገድ ላይ ሁለት ተሽከርካሪዎች ቢገናኙ በዋና መንገድ
ያለ ተሽከርካሪ ቅድሚያ ይኖረዋል

ረድፍ አያያዝና ተከታትሎ ማሽከርከር


 አካባቢዉ በሚገባ በስፖኪዮ መቆጣጠር
 ከመንገድ መሀል ሳይወጡ ተቆጣጥሮ ማሽከርከር
 መሪ እና ፍሬንን በቀላሉ ለመቆጣጠርእንዲያመች ተሽከርካሪዉን
- እንደ መንገዱ ሁኔታ
- እንደትራፊኩ ሁኔታ
- እንደ አየሩ ሁኔታ ማሽከርከር አለብን፡፡
 ቅብጥብጥ እና ክልፍልፍ የአነዳድ ባህሪን ማስወገድ
 እየተሽሎኮለኩ መቅደም፣ ከጎን የደራ ወሬ ማዉራት አደጋ ስለሚያስከትል ጥንቃቄ
ማድረግ

ተሽከርካሪን ስትከተል፣ ስታስከትል፣ እንዲሁም ጎንለጎን ስታሽከረክር


 መሪን መወላወልን
 በድንገት ፍሬን መያዝን
 በድንገት ፍጥነት መጨመርን
 በድንገት ፍጥነት መቀነስን
 የፍክክር አነዳድን ማስወገድ አለብን
 የፍጥነት ወሰንን ማክበር አለብን
 የ 3 ሰከንድ ህግን ጠብቆ ማሽከርከር አለብን
 የ 3 ሰከንድ ህግ ማለት አንድ ተሽከርካሪ ምልክት ሳያሳይ፡- -በድንገት ቢቆም
- በድንገት ቢታጠፍ
- በድንገት ረድፍ ቢቀይር
- በፊት ካለ ተሽከርካሪ ጋር ቢጋጭ እርማጃ ለመዉሰድ በቂ ጊዜና ቦታ
ለማግኝት ይጠቅማል ፡፡
ከኋላ በሌለ ተሽከርካሪ ላለመጋጨት ማድረግ ያለብን ክንዉን
 የፍሬን መብራት /stop light/ መብራቱን ማረጋገጥ
 የኋላ መስታዉቶችን ንፅህና መጠበቅ
 ፍጥነትን በአንዴ ሳይሆን ደረጃ በደረጃ መቀነስ
 ከኋላ በጣም የተጠጋ ተሽከርካሪ ካለ እንዲያልፍ እድል መስጠት
 ከመቆም፣ ከመታጠፍ፣ ረድፍ ከመቀየር በፊት በተገቢዉ ጊዜ እና ርቀት በገቢ
ምልክት ማሳየት
 አንድ አሽከርካሪ ፍጥነቱን መቀነስ ቢፈልግ በዋናነት ማድረግ ያለበት
 የነዳጅ መስጫ ፔዳሉን መልቀቅ
 የእግር ፍሬን ማቀዝቀዝ
 ከባድ ማርሽ መጠቀም አለብን

ተሽከርካሪን ስለ ማቆም

 አሽከርካሪዎች አደጋ ሊገጥማቸዉ ሲል እግራቸዉን ከነዳጅ መስጫ ፔዳል ወደ ፍሬን ፔዳል


ለመዉሰድ የሚፈጅባቸዉ ጊዜ 1/0.75/3⋰ 4/ ሴኮንድ ነው፡፡
 አደጋ የመከላከል እርምጃ ለመዉሰድ ትኩረት ማድረግ የሚገባን፡-
 የፍሬን ጥራትና ብቃት
 የጎማ መሬት የመቆጣጠር አቅም
 የተሽከርካሪዉ ክብደትና ጭነት
 የአየሩ ሁኔታ ወዘተ
 የአሽከርካሪዎች አስተሳሰብ ይዘት መለዋወጥ አደጋን ፈጥኖ የመከላከል ችሎታቸዉን ይቀንሰዋል
 ለአሽከርካሪዎች የአስተሳሰብ ይዘት መለዋወጥ መንስኤ የሚሆኑ ነገሮች
 የአልኮል መጠጥ
 መታከት፣ መድከምና መወራጨት
 የተቃጠለ የነዳጅ ጭስ
 አደንዛዥ እፆች
 አነስተኛ የማየት ችሎታ ወ.ዘ.ተ ናቸዉ
 ማንኛዉም አሽከርካሪ ተሽከርካሪን በሚያቆምበት ጊዜ፡-
 የሌለዉን እንቅስቃሴ በሚከለክል /በሚያሰናክል/ ሁኔታ ማቆም የለበትም
 ሌሎች ተላላፊዎች መንገዱንና የመንገድ ምልክቶችን ማየት በማይችሉበት ሁኔታ
ማቆም የለበትም
 ድንገተኛ አደጋ ለመከላከል ካልሆነ በስተቀር በሀይልና በድንገት የእግር ፍሬን መያዝ
የለበትም
 በሀይልና በድገት የእግር ፍሬን መያዝ የሚያስከትለዉ ችግር
- አሽከርካሪ ከመሪ ጋር እንዲጋጭ
- ተሳፋሪዎች ከወንበር ጋር እንዲጋጩ
- የተጫነ ዕቃ እንዲወድቅ
- የተሽከርካሪዉ የቴክኒክ አቋም እንዲበላሽ
- የተሽከርካሪ ጎማ እንዲሸራተር ምክንያት ይሆናል
 ካልታሰበ እና ካጋጣሚ አደጋ ራስን ለመከላከል ትኩረት መስጠት የሚያስፈልጋቸዉ፡-
 ከፊት ሌላ ተሽከርካሪ ሲኖር
 ህፃናት በሚበዙበት ቦታ ስታሽከረክር
 አመች ባልሆነ መንገድ ስታሽከረክር
 በመገናኛና በማቋረጫ መንገዶች ስታሽከረክር
 በማታዉቀዉና በለመድከዉ መንገድ ስታሽከረክር
 በባቡር ሀዲድ ማቋረጫ ስታሽከረክር
 በምሽት፣ በጭጋግ፣ በሀይለኛ ዝናብ እና በአደራማ ሁኔታ ስታሽከረክር
 ተሽከርካሪ በብልሽት ምክንያት መንገድ ላይ ሲቆም ማድረግ ያለበት
 በ 50 ሜትር ርቀት ከፊትና ከኋላ አንፀባራቂ ሶስት ማዕዘን ምልክት ማስቀመጥ
 የሀዛርድ (የአደጋ) መብራት ማብራት
 በምሽት ከሆነ የፓርኪግ መብራት ማብራት
 ነገር ግን ተሽከርካሪዉ ተበላሽቶ የቆመዉ በሚከተሉት ቦታዎች ከሆነ በሌላ ተሽከርካሪ
ተጎትቶ መነሳት አለበት
- በትራፊክ መብራት 50 ሜትር ክልል
- በትራፊክ አደባባይ ዙሪያ
- በእግረኛ ማቋረጫ መንገድ ላይ
- በመንገዱ በግራ በኩል
- በመስቀለኛ መንገድና በባቡር ሀዲድ ማቋረጫ አካባቢ
ተሽከርካሪን ለረጅም ጊዜ አቁሞ ስለመሄድ
1. ሜዳ ላይ የምናቆም ከሆነ ማድረግ ያለብን
 የእጅ ፍሬን መያዝ
 1 ኛ /የኋላ/ ማርሽ መጠቀም
 ከኋላ ጎማ ከኋላ /ከፊት/ ታኮ ማድረግ
 ጎማዉን ወደ መንገድ ጠርዝ ማዞር
2. ዳገት ላይ የምናቆም ከሆነ
 የእጅ ፍሬን መያዝ
 1 ኛ ማርሽ መጠቀም
 ከኋላ ጎማ ከኋላ ታኮ ማድረግ
 ጎማዉን ወደ መንገድ ጠርዝ ማዞር
3. ቁልቁለት ላይ የምናቆም ከሆነ
 የእጅ ፍሬን መያዝ
 R /የኋላ ማርሽ/ መጠቀም
 ከኋላ ጎማ ከፊት ታኮ ማድረግ
 ጎማዉን ወደ መንገድ ጠርዝ ማዞር

You might also like