You are on page 1of 10

የተሽከርካሪ ብልሽት መከላከል ና አነስተኛ ጥገና ማከናወን

በተሽከርካሪው ላይ የከባድ ብልሽት መንስኤ ለሊሆን የሚችሉ ቀላለል ብሌሽቶች አሽከርካሪው በራሱ አቅም መጠገን
የሚችል ከሆነ በወቅቱ በመጠገን፣ ከአቅሙ በላይ የሆነ የተሽከርካሪ ብልሽቶች ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ የከፋ
ብልሽት ከመድረሱ በፊት የጥገና አገሌግሎት እንዱያገኙ ማድረግ አለበት፡፡

ለባትሪ መሙያ ክፍል መደረግ ያለበት ጥገና

በአሽከርካሪዎች አቅም ለባትሪና ለባትሪ መሙያ ክፍልች የሚደረጉ የአነስተኛ ጥገናዎች መካከል የሚከተለት
ይገኙበታል፡፡

ለባትሪና ለባትሪ መሙያ ክፍሎች ጥገና የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች፡- ባትሪ፣ ፉውዝ፣ የተለያዩ መፍዎች፣ ፒንሳ፣ የቺንጋ
መወጠሪያና የመሳሰለት ሲሆኑ እነዚህን መሳሪያዎች በአግባቡ በመጠቀም መለስተኛ ጥገና ማድረግ ይቻላል።

 የዱናሞ ቺንጋ ከመጠን በላይ የላላ ከሆነ ተገቢውን መፌቻ በመጠቀም በአግባቡ እንዱወጠር ማድረግ ነገር ግን
የተሰነጠቀ፣ የተላጠ ወይም በጣም የሰፊ ከሆነ መቀየር
 የባትሪ ውሃ ቶል ቶል የሚጨርስ ከሆነ የሬጉላተር መበላሸት ሊሆን ስለሚችች ባለሙያ እንዱያየው ማረረግ
 የባትሪ ተርሚናልች ላልተው ቢገኙ በመፍታት ማጽዳትና በመፌቻ መልሶ ማጥበቅ
 ባትሪው በተቀመጠበት ቦታ ንቅናቄ ካለው አስፈሊጊውን መፌቻ በመጠቀም ማጥበቅ
 ባትሪው ሞተር ለማስነሳት አቅም ካጣ ፈቶ በማውረዴ ለባለሙያ ማሳየት ወ.ዘ.ተ.

ለሞተር ማስነሻ ክፍሎች የሚደረግ ቀላል ጥገና

ለሞተር ማስነሻ ክፍሎች የሚከተለትን ቀላል ጥገናዎች በአሽከርካሪዎች ማካሄድ ተገቢ ነው።

 የተቃጠለ ፊውዝ ካለ በተመሳሳይ አምፒየር ያለው ፊውዝ መቀየር


 በሞተር ማስነሻ ቁሌፌ ሞተር ለማስነሳት ስንሞክር ሞተሩ አልነሳም ካለ በስታርተር ሞተር ዙሪያ ያለትን
ገመዶች ማጠባበቅ

የመብራት ክፌልች ጥገና

መብራቶች መስራታቸውን ሲያቋርጡ የምንጠቀምባቸው እቃዎች አምፖሎች ፊውዝ፣ የእጅ ባትሪ፣ የተለያየ መጠን
ያላቸው መፍቻዎች፣ ፑዠፒንሳ፣ ካቻቢቴ /ፊሊፕስና ጠፍጣጣ/ እና የኤላክትሪክ ገመድች ሲሆኑ በእነዚህ መሳሪያዎች
የሚከተለትን ጥገና ማዴረግ ይቻላል፡፡

 የተበጠሰ የኤሌክትሪክ ገመድ አጥብቆ ማሰር ወይም መቀየር


 የተቃጠለ አምፖል ካለ በተመሳሳይ መተካት
 የተቃጠለ ፊውዝ ከተገኘ ተመሳሳይ አምፒር ባለው ውውዝ መቀየር
 የመብራት ማቀፉያዎች ከላሉ በትክክለኛ መንገድ ማጥበቅ
 የተላጡ የኤላክትሪክ ገመዶች ካጋጠሙ በፔላስተር መጠቅል
 ጡሩንባ በትክክል ድምጽ የማያወጣ ከሆነ ፈቶ ቆሻሻውን ማጽዳት ወይም በሌላመተካት ወ.ዘ.ተ.

ለነዳጅ አስተላላፊ ክሎችች መደረግ ያለበት ጥገና


የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች ሲጠገኑ የምንገለገልባቸው መሳሪያዎች የሚከተለት ናቸው፡-

 የተለያየ መጠን ያላቸው መፍቻዎች


 የነዲጅ ማጣሪያ
 የአየር ማጣሪያ
 ንጹህ ነዳጅ እና
 ንፁህ ጨርቅ የመሳሰለት ሲሆኑ

በናፍጣ ሞተር ላይ አየር በነዳጅ መስመር ውስጥ በመግባት የነዲጅ ግፊት /ፕሬዠር/ እንዲንስ በማድረግ ለሞተር
አለመነሳት ምክንያት ከሆነ ወይም ሞተር ከተነሳ በኋላ የኃይሌ መቆራረጥ የሚያጋጥም ከሆነ የሚከተለትን ተግባራት
በቅደም ተከተል በማከናወን ችግሩን መፍታት ይቻላል።

 የነዳጅ /ናፌጣ/ የእጅ ፓምፕንን ደጋግሞ በመግፋት ሲጠነክር ተጭኖ መያዝ


 የአየር ማስተንፈሻ ቫልቩን በመፍታት ከአየር ጋር የተቀላቀለ ነዳጅ ወደ ውጪ እንፈስ ማድረግ
 የማስተንፈሻ ቫልቩን መልሶ ማሰርና አሁንም በመደጋገም ሙሉ ነዳጅ ብቻ እስኪወጣ ድረስ ተግባሩን ማከናወን
 የእጅ ፓምፕ ግፊት እየጠነከረ ከመጣ አጥብቆ ማሰርና አካባቢውን በጨርቅ ማጽዳት
 ሞተሩን ማስነሳት
 ሞተሩ ካልተነሳ ከላይ የተጠቀሱትን ሂደቶች እንደገና መሞከር

የነዳጅ ፊልትሮን መቀየር

 ትክክለኛ መሳሪያ በመጠቀም የነዳጅ ፊልትሮውን መፍታት


 የቆሻሻ ፊልትሮውን በንጹህ ነዳጅ ደጋግሞ ማጠብ
 በጣም የቆሸሸ ከሆነ በሌላ አዲስ መተካካት
 እንደ አፈታቱ ቅጀም ተከተል መሰረት መልሶ መግጠም
 አካባቢውን በጨርቅ ማጽዳት
 በነዲጅ ጋን ውስጥ በቂ ነዳጅ መኖሩን ማረጋገጥ

የአየር ማጣሪያ መቀየር

የአየር ማጣሪያ በአቧራ /በቆሻሻ/ ሊደፈን ስለሚችልና በዚህ ምክንያት የሞተሩን ጉልበት ስለሚቀንስ ዘወትር ሞተር
በማጥፋት ማጽዳት እና የቆሻሻው መጠን ከፌተኛ ከሆነ እና የሰፋ ከሆነ በሌላ ተመሳሳይ አዲስ የአየር ማጣሪያ ማንዋለ
በሚያዘው መሠረት መቀየር ያስፈጋል።

የማቀዝቀዣ ክፍሎችች በአሽከርካሪው ሊደረግ የሚገባ ጥገና

በማቀዝቀዣ ክፍሎች አገልግሎት ላይ የሚያስፈልጉ የጥገና እቃዎች ቴርሞስታት፣ የራዲያተር ውሃ፣ ቺንጊያ ፣
የራዴያተር ማጠቢያ ፍላሸር እንዱሁም ፒንሳ ና መፌቻዎች የመሳሰለ ናቸው፡፡

 በራዴያተር ውስጥ ያለውን ውሃ የራዴያተር ክዳን ሞተር ከመነሳቱ በፉት በመፍታት የተጣራ ንጹህ ውሃ
በትክክለኛ መጠን ላይ መጨመርና ውሃ ከሞላ በኋላ ሞተር ማስነሳት
 ቺንጋ እስከ መጨረሻ ድረስ ተወጥሮ ከሠፊዠፋ የውሃ ፒዠፓምፕ ና ቬንቲለተር በሚገባ ለማዞር
ስለማይችልና ለሞተር መሞቅ ምክንያት ስለሚሆን መቀየርና በጣም ሳይጠብቅ ወይም ሳይላላ
እንዱዠዲወጠር ማዴረግ
 ቴርሞስታት ተዘግቶ በመቅረቱ ምክንያት የሞተር ሙቀት የሚጨምር ከሆነ ፈትቶ ማፅዳትና በፈላ ውሃ
ውስጥ በመጨመር በትክክለኛዉ የሙቀት መጠን መክፇዠፈቱንና መዝጋቱን ማረጋገጥ፡፡ በአግባቡ የማይሰራ
ከሆነ በተመሳሳይ ሙቀት የሚከፈትና የሚዘጋ ትክክለኛ የሆነ ሌላ አዱስ ቴርሞስታት መቀየር

ማሳሰቢያ ቴርሞስታት ሲበላሽ በሌላ አዱስ በመተካት መቀየር እንጂ አውጥቶ መጣል ለሞተር ክፍሎች ጉዳት
የሚያስከትል ስለሆነ በአዲስ መተካት ይኖርብናል። ቴርሞስታት አውጥቶ መጣል የሞተር የስራ ሙቀት ቶል እንዳይደርስ
በተለያዩ የማሽከርከር ሁኔታዎች ሊይ የሞተር የስራ ሙቀት ከሚገባው በታች ሊያደርገው ይችላል።

የቆሻሻ የራዱያተር ውሃ በሚቀየርበት ወቅት የሚከናውኑ ተግባራት

 ውሃው በሚፈስበት ቦታ ላይ ተሽከርካሪውን በማቆም መቀበያ እቃ ማዘጋጀት


 በሞተር/ በራዴያተር የታችኛው ክፍል በሚገኝ ማፍሰሻ ብሎን በመፍታት ሙሉ በሙሉ ማፍሰስ
 በራዴያተር ክዳን በኩል ንጹህ ውሃ በመጨመር ከውስጥ የቀረውን ቆሻሻ ተጠራርጎ እስኪወጣ ድረስ ሞተሩን
በሚኒሞ እያሰሩ እንዲፈስ ማድረግ
 ቆሻሻ ውሃው ሲያልቅ ወይም ንጹህ ውሃ በማፍሰሻዉ በኩል መታየት ሲጀምር ማፍሰሻ ብሎኑን መዝጋት
እስኪሞላ ድረስ መጠበቅና የዝገት መከሊከያ ኬሚካሌ በመጨመር የራዴያተር ክዳኑን መዝጋት
 የራዴያተር የፊት ለፊተት ክፍል በቆሻሻና በተለያዩ ነፍሳት ሊደፈንን ወይም ፉዠፊንሶቹ ሲጨፈለቁቁ ወይም
ሲጣመሙ ለሞተር መሞቅ ምክንያት ስለሚሆኑ ቆሻሻውን ማጽዳትና ወደ ትክክለኛ ቦታቸው በመመለስ
ማስተካከል።

የመሪ ክፍሎች ጥገና

ለመሪ ክፌልች ጥገና አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች የመሪ ዘይት፣ ቺንጋ፣ ግሪስ፣ ንፁህ ጨርቅ እና እንዱሁም የተለያዩ
መጠንና ዓይነት ያላቸው መፍቻዎች ናቸው። የሚያፈስ የመሪ ዘይት ቱቦ ካለ አካባቢውን በመጀመሪያ ማጽዳትና ፈሳሹ
የትቦታ እንደሆነ በመለየት የላላ ከሆነ እንዱጠብቅ ማዴረግ የተቀደደ ከሆነ ዘይቱን በእቃ በመቀበል ትክክለኛው
መለዋወጫ በመጠቀም መቀየር።

በሞተር ኃይሌ የተደገፈ በዘይት የሚሰራ መሪ ቱቦ ሲቀየር በመስመሩ ውስጥ አየር ስለሚገባ በሚከተለው ቅደመ ተከተል
መሰረት አየሩን ከመሪ መስመር ማስወጣት ይኖርብናሌ፡፡

 በመጀመሪያ ሁለቱንም የፉት ጎማ በክሪክ ማንሳት


 ሞተር ከመነሳቱ በፉት የመሪ ዘይት ቋት ወስጥ መጨመር
 ሞተር ማስነሳትና በመሪ መዘውር አማካኝነት ወደ ግራና ቀኝ በተደጋጋሚ ማዞር
 ተሽከርካሪው የንፋስ ማውጫ ካለው በመፍታት አየር እንዲወጣ ማድረግ ተሽከርካሪው የንፊስ ማውጫ
ከሌለውበዘይት መያዣ ቋት በኩል እንዱወጣ ማዴረግ
 ተጨማሪ የመሪ ዘይት በመጨመር መሪ መዘውር እኩልና ቀላል እስኪሆን ድረስ ከላይ የተገለፀውን ተግባር
ማከናወን
 በመጨረሻም ትክክለኛው የመሪ አጠቃቀም ላይ ሲደርስ ሂደቱን ማቆምና የፊት ጎማ ቀጥ በማዴረግ ክሪኩን
ማውረድ
 የዘይት መጠኑ በተገቢ ቦታ ላይ እስኪደርስ ድረስ ተጨማሪ ዘይት መሙላትና ክዳኑን በትክክል መዝጋት

የጪስ ማውጫ ክፍሎች ጥገና

አለግባብ የሆነ የሞተር ጭስ ፌሳሽ ለሞተር ጉልበት መቀነስ ምክንያት ከመሆኑም በተጨማሪ ለድምጽና ለአየር ብክለት
መንስኤ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል።

የጪስ ማውጫ ክፌልችን ለመጠገን የሚያገግልሉ ዋና ዋና መሣሪያዎች የጪስ ማውጫ ጋስኬት፣ የተለያየ መጠን
ያላቸው መፌዠፍቻዎች፣ ንፁህ ጨርቅ ሲሆኑ የሚከተለትን ጥገናዎች ለማከናወን ያገግላሉ።

 የጪስ ማውጫ የላላና የተቀደደ ከሆነ በተገቢ መፌዠፍቻ ማጥበቅ ጠብቆ ጭስ የሚያስወጣ ከሆነ ለአካባቢ
ብክለት መንስኤ ስለሚሆን በመፌታት በአዱስ መቀየር
 ጭስ በጋስኬት መበሊት ምክንያት የሚወጣ ከሆነ መጀመሪያ ዙሪያውን በማጥበቅ ሞተር አስነስቶ ፍሳሹን
ማየት፣ የጭስ ፌዠፈሳሹ ካልቆመ በተመሳሳይና ትክክለኛ በሆነ መለዋወጫ በአዲስ መተካት
 የጭስ ማውጫ ቱቦዎች የሚያፈሱ ከሆነ ቱቦቹን በመፍታት ማስበየድ ነገር ግን በብየዳ የጭስ ፈሳሹን ማቆም
ካልተቻለ በአዲስ ቱቦ መቀየር።

የፍሬን ክፍልች ጥገና

የፍሬን ክፍሎችን ለመጠገን የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ግብዓቶች፡- የፍሬን ዘይት፣ የፍሬን ሸራ፣ የተለያዩ መፍቻዎች፣
ቲንሳ፣ መዶሻ፣ ስፔሲ ሜትር፣ ኦሞና ንፁህ ጨርቅ የመሳሰለት ናቸው፡፡

በዘይት የሚሠራ ፍሬን ጥገና

የሚያፈሱ ቱቦዎች ሲያጋጥሙ በመጀመሪያ በተገቢው መፍቻ ማጥበቅ በድጋሚ የሚያፈስ ከሆነ በመፍቻ በመፍታት
በሌላ አዲስ መለዋወጫ መቀየርና አጥብቆ በቦታው ማሰር

በረዥም የአገሌግሎት ጊዜ ምክንያት የፍሬን ሸራ እየተበላ ሲሄዴ ከድራም /ከፍሬን ታምቡር/ ጋር የነበረው ክፍተት
እየጨመረ ሲመጣ ለፍሬን ብቃት ማነስ አንደ ምክንያት ስለሚሆን አሽከርካሪው ይሄንን ብልሽት ለመጠገን
የሚከተለውን ተግባር ማከናወን ይኖርበታል።

 በመጀመሪያ ተገቢውን ቦታ በመምረጥ ተሽከርካሪውን ማቆም


 ታኮ ማድረግ ከዚያ ኋላ ማርሽ በማስገባት የእጅ ፍሬን መልቀቅ
 ተገቢው የስራ ደህንነት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ይዞ ከስር መግባት
 የፌሬን ሸራው ያለበትን ደረጃ በኢንስፓክሽን ሆል (ቀዳዳ) ማየት
 የፌሬን ሸራው የተበላ ከሆነ በማስተካከያ ቀዳዳ ትክክለኛና ተገቢ የሆነ ስፔሲ ሜትር በመጠቀም ወደ
ሚጠበቅበት አቅጣጫ በማዞር በማንዋል በተቀመጠው መሰረርት መሠረት በፌሬን ሸራና በድራም መሀከል
ያለው ክፍተት ማጥበብ
 ተሽከርካሪውን የትራፊክ መጨናነቅ በሌለበት በፌዠፍጥነትና በዝግታ በማንቀሳቀስ የፍሬን ብቃቱን መፈተሽ
ማሳሰቢያ፦ የተሽከርካሪ የፍሬን ብቃት ፍተሻ በሚያስፈልግበት ጊዜ የትራፉዠፊክ መጨናነቅ በሌለበት መንገዴዠድ
በአጭርና ሜዳማ ቦታ ከተፈተሸ በኋላ ቀስ በቀስ በፌጥነትና በተለያየ የመንገድ ሁኔታ ላይ ሊፈተተሽ ይገባል።

ፍሬን ይዞ ሲቀር የሚደረግ አነስተኛ ጥገና

 ተሽከርካሪውን በተገቢው ሁኔታ ማቆም


 ታኮ ማድረግ ከዚያ ማርሽ አስገብቶ የእጅ ፍሬን መሌቀቅ
 ፍሬኑ በዘይት የሚሰራ ከሆነ በተገቢው መፌዠፍቻ የዘይት ማስተንፈሻ ጡቱን በመፍታት ጥቂት ዘይት
ማስወጣት ወይም የፌዠፍሬን ሬጅስትሮውን መቀነስ
 የፌሬን ሸራው ከፌዠፍሬን ታምቡር መቀቁንና ክፌዠፍተት መኖሩን ማረጋገጥ
 ተሽከርካሪውን በማንቀሳቀስ መፌትሄ ያላመጣ ከሆነ ተሽከርካሪውን አቁሞ ባለሙያን ማማከር

የተሽከርካሪ ፍሬን ሰርቪስ ማድረጊያ ሂደት

የፌሬን ሸራ እያለቀ በሚሄድበት ጊዜ ለፍሬን ብቃት መቀነስ ምክንያት በመሆኑ አሽከርካሪዎች የሚከተለውን ቅደም
ተከተል በመጠቀም የፍሬን ክፍል ሰርቪስ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

 ተሽከርካሪውን በትክክለኛ ቦታ ላይ ማቆም


 ሁለንም የጎማ ቡለኖች በትንሹ ማላላት
 በክሪክ የተሽከርካሪውን ጎማ በማንሳት ሙለ በሙለ መፍታት
 የተሽከርካሪውን እግሮች በስታንድ ላይ እንዲቆሙ ማድረግ
 የእጅ ፌሬን መለቀቁን በማረጋገጥ የፍሬን ሬጅስትሮ ዜሮ በማድረግ ታምቡሩን ማውጣት
 የፍሬን መላሽ ስፔሪንግ በማስለቀቅ የፍሬንን ጫማው ማስለቀቅ
 ክፍሎችን በነጭ ጋዝ ወይም በውሃና ደዠዱቄት ሳሙና ማጠብ
 የፍሬን ጫማው ተጠግኖ ከመጣ በኋላ መልሶ በጥንቃቄ መግጠም
 የፍሬን ድራም /ታምቡር/ በቀላሉ መግባት ካልቻለ የፍሬን ሬጅስትሮ ማድረጊያውን በመተርተር እንደገና
ማስገባት
 ማንዋለ በሚያዘው መሠረት ስፓሲ ሜትር በመጠቀም ሁለንም የፍሬን ሸራዎች ማስተካከል
 በቅደም ተከተለ መሠረት እግሮቹ በክሪክ እያነሱ ጎማዎችን መግጠም
 ተሽከርካሪውን ከትራፊክ እንቅስቃሴ ነፃ በሆነ ቦታ ላይ የፌሬን ብቃቱን መፈተሽ

በፍተሻ ጊዜ የፌሬን ብቃት አነስተኛ ወይም የፌሬን ድራሙ ከፌዠፍተኛ ሙቀት ካስከተለ ፍሬኑን እንደገና በማንዋለ
መሠረት ክፍተቱን ማስተካከል፡፡

የማለስለሻ ክፍሎች ጥገና

 በመጀመሪያ የሞተር ዘይት የሚቀየርበት ቦታ በማዘጋጀት ለሥራ የሚያስፈልጉ አልባሳት፣ ቱታ፣ ጓንት፣ ጫማ፣
የፊልትሮና የዘይት ማፍሰሻ መፍቻዎች ነጭ ጋዝ፣ ንፁሔ ጨርቅ የዘይት ማጠራቀሚያ እቃ እንዱሁም
ደረጃውን የጠበቀ የሞተር ዘይትና የዘይት ፉልትሮ በአግባቡ ማዘጋጀት
 የተሽከርካሪው ሞተር እየሰራ ከነበረበት ወደ ተዘጋጀለት ቦታ በማቆም ትክክሇዠለኛውን መፌዠፍቻ
በመጠቀም የዘይት ማፌሰሻውን ብሎን በመፍታት ዘይቱን በተዘጋጀው ማጠራቀሚያ እቃ ላይ ማፌዠፍሰስ፣
ሞተር በወቅቱ ያልሠራ ከሆነ ከ 10-15 ደቂቃ ያህል በሚኒሞ ማሠራትና ከሊይ የተገለፀውን ተግባር ማከናወን
 ትክክለኛውን የፊሌትሮ መፌቻ በመጠቀም የዘይት ፊሌትሮ መፍታት
 የሞተር ዘይቱ በሙለ ተንጠፍጥፍ ማለቁ ከተረጋገጠ በኋላ የማፍሰሻ ቡሎኑን አድዴቶ መልሶ መግጠም
ደረጃውን የጠበቀ ንጹህና በቂ የሞተር ዘይት መጨመር
 የተጨመረው ዘይት ትክክለኛ መጠን ላይ መሆኑን በዲፒስቲክ (ሌቤሎ) በማየት ማረጋገጥ
 አካባቢውንና እራሱን በማጽዳት ሞተሩን ማስነሳትና በዳሽ ቦርድ ላይ ያለውን የዘይት ግፉት መቆጣጠሪያ ጌጅ
ግፉት መኖሩን ወይም የማስጠንቀቂያ መብራት መጥፋቱን ማረጋገጥ
 በመጨረሻም ሞተሩን አጥፌቶ ለተወሰነ ጊዜ በማቆየት በድጋሚ ዲፒስቲኩን አውጥቶ ጠርጎ መልሶ
እስከመጨረሻ በማስገባት መጠኑን ማየትና ካነሰ መጠኑ እስኪስተካከል ድረስ የሞተር ዘይት መጨመር

የኃይል አስተላላፊ ክፍሎች ጥገና

የኃይል አስተላላፉ ክፍሎች በሚጠገኑበት ወቅት የፌሪሲዮን ዘይት፣ የጥርሳ ጥርስ ዘይይ፣ የዘይት መጨመሪያና መቀበያ፣
የተለያዩ መፍቻዎች፣ ግሪስ እና ንፁህ ጨርቅ የሚያስስፈጉ ሲሆን እነዚህን እቃዎች በአግባቡ እና በንፁህና ጥቅም ሊይ
ማዋሌ ያስፈልጋል

የፍሪሲዮን አነስተኛ ጥገና

በሜካኒካል የሚሰራ የፍሪሲዮን ፓዳል በጣም የሰፋና የላላ እንቅስቃሴ ሲኖረው ኃይል ለማስተላፍ እና ለማቋረጥ
ስለማይችል ተገቢ ስራውን ለማከናወን ስለሚያስቸግር የመገናኛ ካቦ /ገመድ/ እንዱሁም የዘንግ መርዘምና ማጠር
ስለሚሆን ተገቢ መፍቻ በመጠቀም፡-

 የረዘመ ከሆነ እላዩላይ ባለው ማስተካከያ ዘንግ በቂ/ነፃ የሆነ እንቅስቃሴ እስከሚኖር ድረስ ማሳጠር
 የመገናኛ ቦታዎች የላለ ከሆነ በቂ እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው በማዴረግ ማጥበቅ፣
 በመታጠፊያና በመገጣጠሚያ ቦታዎች ላይ የመድረቅ ሁኔታ ካለ ማለስለሻ በማዶረግ ችግሩን ማስወገድ
 የፌሪሲዮን ፓዳል ካቦ ወይም ዘንግ የተሰበረ፣ የተበጠሰ ወይም፣ የወለቀ ከሆነ ፈትቶ ለባለሙያ ማሳየትና
ማስጠገን ካልተቻለ ተመሳሳይ እና አዲስ መግጠም

በዘይት የሚሰራ የፌፍሲዮን ፓዳል እንቅስቃሴው የሰፋ ወይም የጠበበ ሆኖ ሲገኝ የፍሪሲዮን ፔዳል ዘንግ መጣመም፣
መስፋት እና የጥርሱ መበላት ሊሆን ስለሚችል በማጠባበቅ ለማስተካከል ጥረት ማድረግ በዚህ ጥገና ለማስተካከል
ካልተቻለ በባለሙያ በተመሳሳይ እቃ እንዲለወጥ ማድረግ።

 የፍሪሲዮን ዘይት ቱቦዎች ፍሳሽ ሲያጋጥም የመላላትና የመቀደድ ችግር ሊሆን ስለሚችል አካባቢውን በማጽዳት
የሚፈስበትን ቦታ በመለየት፡- የላላ ከሆነ ለማጥበቅ መሞከር ፣ የሚያፈሰው ቱቦ ብረት ነክ ከሆነ ማስበየድ፣
የሊስቲክ ከሆነ በተመሳሳይ አዲስ በመቀየር፣ በዘይት ቋት ውስጥ በቂ የፌሪሲዮን ዘይት መጨመር

የጊርቦክስ /ካምብዮ/ ጥገና


የጊርቦክስ ተሸካሚ ወይም ስፖርቶ ቡሽንግ /ቢኮላ/ ሲሰበር ወይም ሲበላ ማርሽ በተገቢ ሁኔታ ያለመግባት እንዱሁም
በተሽከርካሪው እንቅስቃሴ ወቅት አላስፈጊ ንቅናቄ ስለሚያስከትል ከዚህ በሚከተለው መልኩ ጥገናውን ማካሄድ
ያስፈልጋል።

 ተሽከርካሪውን በተገቢው ቦታ ላይ በጥንቃቄ ታኮ በማዴረግ ማቆም


 አስፈላጊ የስራ ሌብስና መሳሪያዎችን ማዘጋጀት
 ጊርቦክስን ትክክለኛ ቦታው ላይ እስኪደርስ በክሪክ መጀገፍ
 የላላና የተበላ ወይም የተሰበሩ ክፍሎችችን አንድ በአንድ እየፈቱ የሚጠብቅ ከሆነ ማጥበቅ የተበለና የተሰበሩ
ከሆነ ማስሞላት ወይም ማስበየድ

በዚህ ሁኔታ ጥገናው ከተካሄደ በኋላ መልሶ በቅደም ተከተል መግጠምና ክሪኩን ቀስ በቀስ ማውረድ፡፡ ከላይ በተጠቀሰው
መሠረት ሊጠገኑ የማይችሉ ክፍሎች ካጋጠሙን ተመሳሳይ በሆነ ዕቃ መቀየር ይኖርበታል። በሰርቪስ አገሌግሎት ወቅት
የጊርቦክስ ዘይት መቀየር ሲያስፈልግ ከዚህ በታች ባለው ቅደም ተከተል ይሆናል።

 በቂና ደረጃውን የጠበቀ በማንዋለ መሰረት የጊርቦክስ ዘይት ማዘጋጀት


 ተገቢውን መፍቻና የዘይት መቀበያ ዕቃ አዘጋጅቶ የዘይቱን ማፍሰሻ በመፍታት ዘይቱን ማፍሰስ
 ዘይቱ ሙለ በሙለ ተንጠፍጥፍ እስኪያልቅ ድረስ በመጠበቅ የዘይቱን ማፍሰሻ ብሎን መልሶ ማጥበቅ
 የዘይት መጨመሪያ ክዳን በመፍታት አዲስ ዘይት በፓምፕ አማካኝነት ወይም በመያዣ ዕቃ በጥንቃቄና በንፅህና
መጨመር
 የተዘጋጀውን ፊልትሮ ጋስኬት ወይም ጎሚኒ በትክክለኛ ቦታው ላይ በማሳረፍ እንዲገጠም ማድረግ
 ማንዋለ በሚያዘው መሰረት ትክክለኛ የዘይት መጠን መሞላቱን ማረጋገጥና ክዳኑን አጥበቆ ማሰር

የዲፈረንሻል ጥገና

በዲፈረንሺያል ላይ የዘይት ፈሳሽ ብልሽት በቡለኖች መላላት፣ በጋስኬት መቀደድ፣ በጎሚኒ መበላት ወይም፣ በፈረንሻል
ሃውሲንግ መሰንጠቅ ምክንያት ያያጋጥም ስለሚችል በመጀመሪያ ዙሪያውን ማጽዳት በመቀጠልም የላሉ ቡለኖች ካሉ
በማጽዳትና ተመልሶ በቀላሉ እንይላላ የሚያደርጉ ነገሮችን በመጠቀም መልሶ ማሰር ብልሽቱ በአሽከርካሪው አቅም
ከከናውን ካልተቻለ ለባለሙያ በማሳየት ትክክለኛ ጥገና እንዲያገኝ ክትትል ማድረግ።

የአክስል መለስተኛ ጥገና

በአክስል ዙሪያ የሚገኙ ቡለኖች መላላት ወይም መሰበር ምክንያት ዘይት ወይም ግሪስ ወደ ውጪ የሚያፈስ ከሆነ
እንደተሽከርካሪው አሰራር የአሽከርካሪውን አቅምና ችልታ ግምት ውስጥ በማስገባት የላላውን በማጥበቅ የተሰበረውን
በመቀየርና በመግጠም ብልሽቱን ማስወገድ ያስፈልጋል።

ለተሽከርካሪ ጎማ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

 የተሽከርካሪ የፉት ጎማ ላይ ቀጭን ጥርሶች መግጠምና ትንሽ ጥርሱ የተበላ ከሆነ ወዱያውኑ በአዱስ ጎማ
መቀየር
 የጎማ ንፊስ ሲያንስ ወይም ሲበዛ ለጎማዎች እኩል አለመበላት ምክንያት ስለሚሆን የግፉዠፊት መቆጣጠሪያ
መሳሪያ በመጠቀም እኩል የአየር ግፊት እንዲኖራቸው አድርጎ ማስተካከል
 የጎማ ብልኖች ሲታሰሩ ግራና ቀኝ ቀስ በቀስ እያመጣጠኑ በማንዋለ መሰረት ማጥበቅ፣ የሚያዳልጡ፣ የተሰበሩ
የጎማ ቡለኖች ካለ በክሪክ በማንሳት መፍታትና መቀየር ያስፈልጋል
 በአንዴ እግር ላይ በአንድነት በሚገጠሙ ጎማዎች መካከል ድንጋይ ወይም ሌላ ባዕድ ነገር ከገባ በሌባ ጎማ
በመጠቀም ማስወጣት
 በተለያዩ ምክንያቶች የተሽከርካሪ ጎማዎች እኩል ስለማይበሉ አዟዙሮ በመግጠም አገልግሎቱ እንዲጨምር
ማዴረግ
 የመሪ መገጣጠሚያ ክፍሎች መበላት ወይም መጣመም ለፊትት ጎማ እኩል አለመበላት ምክንያት ከሆነ፣
የላላውን በማጥበቅ እና የተጣመመውን በማቃናት ቀላል ጥገና ማድረግ የሚቻል ሲሆን ከአቅም በላይ ሲሆን
ለባለሙያ ችግሩን ማሳወቅ ይገባል።

በጎማ ላይ የሚደረጉ አነስተኛ ጥገናዎች

የጎማ ክፍሎች ሲጠገኑ ከሚያስፈልጉ መሣሪያዎች ውስጥ ክሪክ፣ የክሪክ ማንሻ፣ ጎማ፣ የጎማ መፍቻ፣ ከለመንዳሪ፣
የንፊስ ኮምፕሬስር፣ የተለያየዠዩ መጠን ያላቸው መፍቻዎች፣ እስክሩ ድራይቨር /ፍሊፒሲና ፍላት/፣ ውሃ፣ ንፁህ ጨርቅ
ሲሆኑ እነዚህን እቃዎች በጥንቃቄ እንደአስፈላጊነታቸው መጠቀም ተገቢ ነው።

 የጎማ ንፋስ ከመጠን በታች መሆን የጎማ ጥርስ ቶል እንዲያልቅ ከማድረጉም በላይ ንፋስ ባነሰበት በኩል መሪ
እንዲጎተትና ተሽከርካሪው ለአደጋ እንዲጋለጥ ስለሚያደርግ ወደ ጎማ ሠራተኛ በመውሰድ በማንዋለ መሰረት
ትክክለኛ ግፉት ላይ እስኪሆን ድረስ ንፋስ ማስሞላት ወይንም የተሽከርካሪው ፍሬን በአየር የሚሰራ ከሆነ
የመስመር ማስረዘሚያ ቱቦ /ኮንፊያጆ/ በመጠቀም በግፊት መቆጣጠሪያ መሳሪያ በመታገዝ በቂ አየር እንዲሞላ
ማድረግ፡፡ ንፋስ ተሞልቶ አየር የሚያስወጣ ከሆነ የተቀደደ ቦታ ሊኖር ስለሚችች መቀየርና ዘ የተነፈሰውን
ጎማ እንዲጠገን ማድረግ
 የጎማ ማሰሪያ ኮልኔት /ቡለኖች/ የጎደለ፣ የላላ፣ እና የተበላሹ ከሆኑ በማጥበቅ ወይም በመቀየር በትክክለኛ
መጠን እኩል እንዲጠብቁ ማድረግ የስፈልጋል።

የተሽከርካሪ ጎማ የመቀየር ሂደት

 ተሽከርካሪውን ቀጥ ያለ ቦታ ላይ አስተካክሎ ማቆም


 የእጅ ፌሬን መያዙን፣ ማርሽ መግባቱን /ከባዴ ማርሽ/ ማረጋገጥና ከሚቀየረው ጎማ በተቃራኒ ያለው ጎማ ላይ
ከፊትና ከኋላ ታኮ ማድረግ
 ክሪኩን ሻንሲው ስር ትክክለኛ እና የማይንሸራተት ቦታ ላይ አስተካክሎ ማስያዝ
 ትክክሇኛ የሆነ የጎማ ብልን የቁጥር መጠን ያለው መፌዠፍቻ መጠቀም በጎማ መፍቻ የጎማውን ቡለች ተራ
በተራ በመስቀለኛ አቅጠጫ ማላላት
 ሁለም ቡለኖች እንደላሉ ክሪኩን ማንሳትና ጎማው ሙሉ ለሙሉ ከመሬቱ እንደተላቀቀ ማቆም
 የላሉትን ቡለኖች ተራ በተራ ማውለቅና ንፁህ ቦታ ላይ ማስቀመጥ
 ሁለም ቡለኖች እንጀወለቁ ጎማውን ከፍ አድርጎ ወደ ወጪ ማውጣት፡፡ በዚህ ጊዜ የብልኖቹ ቀዳዳ
በሚወጣበት ጊዜ የቡለኑን ጥርስ እንዳይጎዳ መጠንቀቅ፡፡
 ተቀያሪውን ጎማማ ከፍ አድርጎ ማስገባትና ብልኖቹን ተራ በተራ በእጅ ማስጠጋትና ማሰር
 በመስቀለኛ ቅርፅ ቡለኖኖቹን ቀስ ብሎ በመፍቻው ማስጠጋት
 ክሪኩን ትንሽ ዝቅ አድርጎ ጎማው መሬት እንዲነካ ማድረግ
 መፌቻውን በመጠቀም በቶርኩ መሠረት በደንብ ማጥበቅ
 ክሪኩን ሙለ ለሙለ ማውረድና ታኮውን ከጎማው ስር አንስቶ ጉዞ መጀመር

የተሸከርካሪ ጎማን የማቀያየር

የተሸከርካሪ ጎማን ቀጣይነት ባለው ሁኔታ ማቀያየር የተሸከርካሪ ጎማ የመከላከሌ ጥገና አካሌ ሆኖ ከፊት እስከ ኋላ
እንዱሁም ከጎን እስከ ጎን ያለውን የጎማዎችን የመበላት ፍጥነት ተመሳሳይነት እንዱኖረው ያደርጋሌ፡፡ የተሽከርካሪ
ጎማዎችን ማቀያየር የተሸከርካሪ ባለቤት ማንዋል በሚያዘው መሰረት የሚለያይ ቢሆንም በየ 3000 እስከ 5000 ማይል
ምንም እንኳዋን በጎማዎቹ ላይ ምንም አይነት የመበላት ምልክት ባይታይም ተግባራዊ ቢደረግ ይመከራል፡፡ አብዛኛውን
ጊዜ የተሽከርካሪ የሞተር ዘይት በሚቀየርበት ወቅት የጎማዎችን የማቀያየር ተግባር ማከናወን ተመራጭነት ያለው
ተግባር ነው፡፡

ዝናብ መጥረጊያ የማስተካከልና የመቀየር ሂደት

የዝናብ መጥረጊያው በትክክል የማይሰራ ከሆነ ወይም ከቦታው ሊይ ጨርሶ የሌለ ከሆነ ወይም ሁለም የዝናብ
መጥረጊያዎች እኩል የማይጠርጉ ከሆነ ወይም እንደ በሚጠርግበት ጊዜ ላስቲኩ ተበልቶ መስታወቱን የሚጭር ከሆነ
በመቀየር ወይም በማስተካከል ችግሩን ማስወገድ ይቻላል፡፡

 በመስታወት ላይ ውሃ በመጨመር ችግር ያለበትን የዝናብ መጥረጊያ መለየት


 የዝናብ መጥረጊያውን ከጥርስ ላይ በማላቀቅ በትክክል ከሚሰራው ጋር እኩል አርጎ መልሶ መግጠምና
በሚፈለገው መልኩ እየሠራ መሆኑን ማረጋገጥ
 ትክክሌ ከሆነ ማሰርና ማጥበቅ ያልተስተካከሐ እንደሆነ ጥርሱን እያዟዟሩ በመግጠም ትክክል እስኪሆን ድረስ
ደጋግሞ መሞከር
 የነበረዉ የዝናብ መጥረጊያው ላስቲክ ከቦታው ላይ የላላ ወይንም የተበላና የተሸራረፈ ከሆነ በአዲስ መቀየር፡፡

የተቃጠለ ፊውዝ እና አምፖሎች የመቀየር ሂደት

በኤላክትሪክ ሃይል የሚሠሩ የተሽከርካሪ ክፍሎችች ሲበላሹ ቀጥሎ በተዘረዘረው ቅደም ተከተሌ መሠረት መቀየር
አለባቸው፡፡

 የተቃጠለውን የኤላክትሪክ ክፍል ከመቀየሩ በፊት የሞተር ቁልፍ ማጥፋት


 የተቃጠለ ክፍል ከመቀየሩ በፊት ለሥራ አመቺ እንዲሆን ሌሎች ክፍሎች መፍታት
 የተቃጠለ አምፖል ቀስ ብሎ ማላቀቅና ማውጣት
 በአምፖሉ ላይ ባለው የሃይል መጠን ልላ አዲስ አምፖል ቦታው ላይ አስተካክሎ መግጠም
 የተቀየረው አምፖል በደንብ መስራቱን አብርቶ ማረጋገጥና የሚሠራ ከሆነ ሽፋኑን መልሶ መግጠም
 የተቃጠለ ፊውዝ ካለ በቴስት ላይት በማረጋገጥ በተመሳሳይ አምፒር መቀየር
የተሸከርካሪን ብልሽት መመዝገብና ሪፕርት የማድረግ

በጉዞ ወቅት ያልታሰበ ብልሽት በተሽከርካሪ አካል ላይ ቢከሰት አሽከርካሪው የደረሰውን የብልሽት አይነት መዝግቦ
የሚይዝበት የብልሽት መመዝገቢያና ሪፕርት የማድረጊያ ቅፅ ሊኖረው ይገባል። ይህ ቅፅ በውስጡ ብዙ ዝርዝር ጉዳዮችን
የሚያካትት ሲሆን ጠቃሚነቱ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

 አሽከርካሪው በእንቅስቃሴ ወቅት የሚያጋጥመውን የተሽከርካሪ አካሌ ብሌሽት በጥንቃቄ ለመመዝገብና


ለመያዝ ይረዳዋል።
 አሽከርካሪው የረረሰውን ብሌሽት ለሚመላከተው አካል /ጥገና ክፍል/ በዝርዝር ለማቅረብ ይረዳዋል
 ጥገናው እንዳለቀ አሽከርካሪው ባቀረበው ሪፕርት መሠረት ጥገናውን ለመከታተል ይረዳል

በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለፀው የተሽከርካሪ ብሽሽት መመዝገቢያና ሪፖርት ማድረጊያ ቅፅ አሽከርካሪዎች እንደ
አብነት ሉጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

የድርጅቱ ሥም...................................

የተሽከርካሪ የሠላዲ (የጎን) ቁጥር...........................

የተሽከርካሪው የተጓዘው ኪሎ ሜትር..............................

ተ.ቁ የተሽከርካሪ የተበላሸ ክፍል የብልሽት አይነት የአሽከርካሪው አስተያይት

የአሽከርካሪው ሥም............................... ፉርማ .................... ቀን..................

You might also like