You are on page 1of 5

የማሽከርከር ስልት/ዘዴ

የማሽከርከር ስልት/ዘዴ አሽከርካሪዎች ተሸከርካሪያቸውን ስለመፈተሽ፣ ካቆሙበት አስነስተው በሚጓዙበት

ወቅት ጠመዝማዛማ፣ በጠባብና አደገኛ መንገዶች/ሁኔታዎች ሲገጥመን ማድረግ የሚገባንን ቅደም ተከተል

በአግባቡ ለማወቅ የሚያስችልና የማሽከርከር ክህሎታችንን ወይም ግንዛቤያችንን የሚጨምር ሲሆን

በተጨማሪም በእንቅስቃሴ ወቅት መከበር ያለባቸው የመንገድ ስነ-ስርዓት ህጎችን አክብሮ ስለማሽከርከር

የሚሰጥ ስልጠና ነው፡፡

ተሸከርካሪን ለጉዞ ዝግጁ ማድረግ

 የተሸከርካሪን አካል ማፅዳና ዝግጁ ማድረግ

 የተሸከርካሪን ዘይቶችንና ማቀዝቀዣ ውሃ መፈ t ሽና መሙላት

 ክላክስ መፈተሸ

 ነዳጅ መስጫ፣ፍሪሲዮንና ፍሬን መስራታቸውን መፈተሸ

 ፍሬቻ መብራት መስራቱን ማየት

 የጎማ ንፋስና ጥርስ ማየት እና ማሰተካከል

 ባትሪ መፈተሸና ውሃ መሙላት

 የግንባር እና የኃላ መብቶችን መስራታቸውን ማረጋገጥ

 የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎችን መኖሩንና መስራቱን ማረጋገጥ

 ተቀያሪ ጎማ/ስኮርት መያዛችንን ማረጋገጥ

 የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ መያዛችንንና መሟላቱን ማረጋገጥ

 መፍቻዎችና አንፀባራቂ ባለሶስት መዓዘን ምልክት መያዛችንን ማረጋገጥ


 ራሳችንን ከአልኮል መጠጥና መድሃኒቶች ንፁህ ማድረግ

 በር በአግባቡ መዝጋት

 ወንበር ማስተካከል

 የደህንነት ቀበቶ ማሰር

 የጎንና የኃላ መመልከቻ መስታወቶችን ማስተካከል

አሽከርካሪዎች ማወቅ የሚገባቸው

 የነዳጅ መጠንና የኢንጅን ዘይት አለካክ እና አሞላልን ማወቅ እና መተግበር

 የተሸከርካሪውን ውስጣዊ ክፍሎችን መፈተሸ እና መስተካከል

 የሞተር ሀይል አጋዥ ክፍሎችን መፈተሽ

 መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችንና ዳሽ ቦርድ ላይ የሚገኙት ጠቋሚ መሳሪያዎችን በአግባቡ

መስራታቸውን መፈተሸ ያስፈልጋል፡፡

 መኪና ውስጥ ከተገባ በኃላ የመኪናውን ወንበር ማስተካከል፣ቀበቶ ማሰር፣ ቅደም ተከተሉን

ተከትለን ሞተር ማስነሳት (ለረጅም ሰዓት ከቆመ ከ 5-15 ደቂቃ መኪናው ሞተር እሰስኪሞቅ

መጠበቅ ይገባል

 ከመነሳት በፊት አካባቢን መቃኘት

 ፍሬቻ መብራት በማሳየት መነሳት (ቅድሚያ መስጠት ካለብን መስጠት ያስፈልጋል)

 በጉዞ ላይ እያለን ማሽከርከር ስርዓቱ በሚፈቅደው ሁኔታ ማሽከርከር፣የመቆጣጠሪያ

መሳሪያዎችን በአግባቡ መጠቀም

 ስፖኪዮ በአግባቡ መጠቀም


 ፍሬቻን በአግባቡ መጠቀም

 ረድፍ አያያዝ በትክክል መጠቀም

 የመንገድና የትራፊክ ህግና ስርዓትን ማክበር

 ፍጥነትን ጠብቆ ማሽከርከር

 የተሸከርካሪውን ሞተር ስለሚጎዳ እና ከባድ የነዳጅ ፍጆታ ስለሚኖረው ከባድ ማርሽ ለረጅም

ኪ.ሜ አለመጠቀም

የሽከርካሪን ፍጥነት ለመቀነስ እና ለማቆም መተግበር ያለበት

 የነዳጅ ፔዳል መልቀቅ ፍጥነት በመቀነስ አካባቢያችንን በመቃኘት፣ምልክቶችን በማየት ለማቆም

የተከለከለ መሆኑን/አለመሆኑን መመልከት

 የቀኝ ፍሬቻ በማሳየት መሪ ወደቀኝ በመያዝ በዝግታ ወደ ምንቆምበት ስፍራ መጓዝ

 ሙሉ በሙሉ ተሸከርካሪው ከቆመ በኃላ ማርሽ ዜሮ በማድረግ የፍሪስዮን ፔዳልን መልቀቅ

 የእጅ ፍሬን በመያዝ የእግር ፍሬን ፔዳል መልቀቅ

 ለረጅም ሰዓት ሲሰራ የነበረ ሞተር ከሆነ ለተወሰነ ደቂቃ ወይም የሞተሩ ሙቀት ዝቅ እስኪል

ድረስ መጠበቅ

 ሞተር ማጥፋት፣እጅ ፍሬን መያዝ፣ የሲት ቤል መፍታት መስኮት መዘጋጋት እና የመሳሰሉትን

ጥንቃቄዎች በማድረግ መውረድ

 እንደ መልካምድሩ አቀማመጥ እና እንዳስፈላጊነቱ የጎማ ታኮ ማድረግ


በአደገኛ ሁኔታ ማሽከርከር

በሚያሽከረክሩበት ጊዜ ከታች በዝርዝር የተቀመጡ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ ጥንቃቄና ተገቢውን

ውሳኔ በመወሰን አደጋን ተከታትለን ማሽከርከር አለብን

 በተለያዩ የአየር ንብቶች/ሁኔታዎች ማለትም በከባድ ዝናብ፣ ጭጋጋማ፣ ደመናማ፣ ንፋሳማና

በረዶ በሚዘንብበት ጊዜ ማሽከርከር እና መሰል የአየር ሁኔታችን በማወቅና መረጃ በመያዝ በቂ

ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

 የመንገድ ደረጃው ማለትም ኮሮኮንች፣ ጥርጊያ፣ በአቧራማ፣ አሸዋማ፣የሚፈናጠሩ ጠጠሮች

ያሉበት፣ የሚያዳልጥ መንገድ ላይ ማሽከርከር እና መሰል የመንገድ አይነቶችን በማወቅና መረጃ

በመያዝ በቂ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

 በተለያዩ መልካምድራዊ ሁኔታ ማለትም ዳገት፣ ቁልቁለት፣ ጠመዝማዛማ፣ የሚያንሸራትት፣ ወጣ

ገባ፣ አደገኛ ከርቭ/ኩርባ ላይ ማሽከርከር እና መሰል የአየር ሁኔታችን በማወቅና መረጃ በመያዝ

በቂ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

 አካባቢ በሚበክል ጢስ ያለን ተሸከርካሪ ተከትለን ማሽከርከር

 በምሽት ማሽከርከር

 ውና ወይም ጎርፍ የሚተኛባቸው መንገዶች

 ፍጥነትን ተቆጣጥሮ በማሽከርከር አደጋን መከላከል….የመሳሰሉት ናቸው፡

በማሽከርከር ወቅት መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

 አደገኛ መንገዶች ሲያጋጥሙ ከፍጥነት ወሰን በላይ አለማሽከርከር/ፍጥነት መቀነስ፣ተሸከርካሪን

መፈተና ፍሬን አያያዝ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ


 አደገኛ የአየር ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ፍጥነትን መቀነስ፣ አደገኛውን የአየር ሁኔታ ቆሞ ማሳለፍ፣

ተገቢውን መብራት/ፓርኪንግ፣ሃዛርድ፣አጭርና የግንባር መብራት መጠቀም፣ የራስን ረድፍ መያዝና

በዝግታ አካባቢውን በመቃኘት ማሽከርከር፣ አስተማማኝ የመኪና ጎማ መጠቀም

 አደገኛ መልካምድራዊ ሁኔታ/አቀማመጥ ሲያጋጥም የፍጥነት ወሰንን ማክበር፣ ተሸከርካሪን በማቆም

መፈተሸ፣ መኪናውን ማቆም እና የመኪና ታኮ መጠቀም፣ተሽከርካሪን ለመቅደም አለመሞከር፣ ረድፍ

ጠብቆ ማሽከርከር፣ርቀትን ጠብቆ ማሽከርከር

 የእንቅልፍ፣የህመምና ድካም ስሜት ማሰወገድ፣የራስን ቅልጥፍና እና ንቃትን መፈተሸ

 የትራፊክ ሁኔታን መቆጣጠር

 አስቸጋሪ ጠመዝማዛ ቁልቁለት መንገድ ላይ የቱሩንባ ድምጽ ማሰማት

 መሪ አጥብቆ መያዝ እና ወደ አንድ አቅጣጫ አለመጨረስ

 የፊት ጎማ ሲቆልፍ እና ተሸከርካሪው ወደ አንድ አቅጣጫ ሲንሽራተት መሪ ወደ ተንሸራተተበት

መያዝና ተመጣጣኝ ነዳጅ መስጠት

 ተሸከርካሪን መቅደም ከፈለግን ለመቅደም የሚከለክል ምልክት ወይም የተከለከለ ስፍራ እንዳልሆነ

በማረጋገጥ ተገቢውን ምልክት ለሌሎች ተሸከርካሪዎች በማሳየት መቅደም ይቻላል፡፡ በሀገራችን ህግ

መሰረት መቅደም የሚቻለው በግራ በኩል መሆኑን ማወቅ፡፡ በተጨማሪም በሶስተኝነት በመደረብ

መቅደም የተከለከለ መሆኑን ማወቅ፡፡

 ጠባብ ድልድይ አካባቢ ከፊት ለፊት ለሚመጣው ቅድሚያ መስጠት


 በምሽት ወቅት ማሽከርከር በሶስት(3) እጥፍ ለአደጋ ስለሚያጋልጥ ግዴታ እስካልሆነ ድረስ ማሽከርከር
አይመከርም፡፡
 ከ 4 ሰዓት በላይ አለማሽከርከር
 የተሸከርካሪ አጭር የግንባር መብራት 50 ሜትር ድረስ ረጅም መብራት ደግሞ 100 ሜትር ድረስ ማሳየት

You might also like