You are on page 1of 14

1.

ሞተር ሳይክል በመጠኑ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ የትራፊክ መጨናነቅ ባለበት ቦታ ላይ ለማሽከርከር እንደ
ሌሎች ተሸከርካሪዎች ብዙ የማሽከርከር ብቃትን አይጠይቅም?
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
2. የማሽከርካር ህጎችን መሠረት ያደረገ ሙያዊ ብቃትን በማሻሻል ሞተር ሳይክልን የሚያሽከረክር አሽከርካሪ
ነው፡፡
ሀ/ ለተሸከርካሪ የሚያስብ ሐ/ ለራሱ ደህንነት የሚያስብ
ለ/ ለህዝብ ደህንነት የሚያስብ መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
3. ለንብረት እና ለህዝብ ደህንነት የሚያስብ አሽከርካሪ የማሽከርከሪያ ህጎችን በማክበር ያሽከረክራል፡፡
ሀ/አውነት ለ/ ሀሰት
4. ለራሱ፣ ለሞተር ሳይክሉና ለእግረኛው ደህንነት በማሰብ ንቃትና ርህራሄ በተሞላበት ሁኔታ ማሽከርከር
ከአንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
5. ከሚከተሉት ውስጥ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሀላፊነት ያልሆነው የቱ ነው?
ሀ/ የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎቹን ማዘጋጀት
ለ/ የደህንነት መሣሪያዎቹን ማዘጋጀት
ሐ/ “ሀ” እና “ለ” መልስ ናቸው
መ/ መልስ የለም
6. የአደጋ መከላከያ እና የደህንነት መሳሪያዎች መለየትና አጠቃቀማቸውን ማወቅ የአንድ የሞተር ሳይክል
አሽከርካሪ ሃላፊነት አይደለም፡፡
ሀ/ አውነት ለ/ ሀሰት
7. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የመ/ቤቱን የአሰራር ሁኔታዎች እና ደንቦች ማወቅ ነው
ሀ/ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው
ለ/ ሃላፊነቱ መ/ መልሱ የለም
8. የአንድ ድርጅት የተሸከርካሪ የስራ መመሪያ /ማንዋል/ መተርጎምና ስለአፈፃፀሙ ተግባራዊነት የመከታተል
ሀላፊነት የማን ነው?
ሀ/ የአሽከርካሪው ሐ/ የረዳቱ
ለ/ የባለንብረቱ መ/ መልስ የለም
9. የሞተር ሳይክል የፍሬን ሁኔታ መፈተሸ ያለበት መቼ ነው?
ሀ/ በጉዞ ወቅት ሐ/ ከጉዞ በኋላ
ለ/ ከጉዞ በፊት መ/ መልስ የለም
10. የማንኛውም ተሸከርካሪ ፍሬን ያለበትን ሁኔታ ማረጋገጥ ከጎዞ በፊት ቢሆን ሊደርስ የሚችለውን አደጋ መጠን
ይቀንሳል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

ሞተር ሳይክል Page 1


11. አሽከርካሪው ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የተሸከርካሪው ፍሬን ከተለመደ ሁኔታ ውጪ ከሆነ ማድረግ ያለበት የቱ
ነው፡፡
ሀ/ ለሚመለከተው አካል ወዲያው ማስወቅ
ለ/ መጠገን የሚቻል ከሆነ መጠገን
ሐ/ መፍቴሄው እስኪገኝ ድረስ ተሸከርካሪውን ማቆም
መ/ ሁሉም መልስ ነው
12. የሞተር ሳይክል መሪ አገልግሎት የሆነው የቱ ነው፡፡
ሀ/ ፍጥነት ለመጨመር እና ለመቀነስ
ለ/ የሞተር ሳይክሉን አቅጣጫ መቆጣጠር
ሐ/ የአሽከርካሪው መደገፊያ መሆን
መ/ መልሱ አልተሰጠም
13. የሞተር ሳይክል መሪ የትኛውን የሞተር ሳይክል የእግር እንቅስቃሴ ይቆጣጠራል
ሀ/ የፊት ሐ/ ሀ እና ለ
ለ/ የኋላ መ/ መልስ የለም
14. የሞተር ሳይክል የፊት እግር እንቅስቃሴ የምንቆጣጠርበት በመሪው አማካኝ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
15. የሞተር ሳይክል ፍጥነት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ
ሀ/ ማርሽ መለዋወጥ ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ነው
ለ/ ነዳጅ መስጠትና መከልከል መ/ መልስ የለም
16. የሞተር ሳይክል ፍጥንት ለመቀነስ ከሚከተለው ውስጥ የትኛው ይጠቅማል?
ሀ/ ፍሬን ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ነው
ለ/ ማርሽ መ/ መልስ የለም
17. የሞተር ሳይክል ፍሬን ጥቅም የሆነው የቱ ነው?
ሀ/ ፍጥነት መቀነስ ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ነው
ለ/ የሞተር ሳይክሉን ሚዛን መጠበቅ መ/ መልስ የለም
18. የሞተር ሳይክልን ፍጥነት በቀላሉ ለመቀነስም ሆነ ለመጨመር የተስተካከለ ፍሪስዮን መኖር ከፍተኛ ድረሻ
አለው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
19. አንድ ሞተር ሳይክልን ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ለማዞር የሞተር ሳይክል መሪ ድርሻ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
20. አንድ ሞተር ሳይክልን አሽከርካሪ በሞተር ሳይክል ላይ የሰውነት አቀማመጥ በሚገባ ማወቅ
ሀ/ ሞተር ሳይክሉን ተቆጣጥሮ ለማሽከርከር ይረዳዋል
ለ/ በራሱ ላይ አደጋ እንዳይደርስ ይረዳዋል
ሐ/ በሞተር ሳይክሉ ላይ አደጋ እንዳይደረስ ለመከላከል ይረዳዋል

ሞተር ሳይክል Page 2


መ/ ሁሉም
21. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተሩን ከማሽከርከሩ በፊት በሞተሩ ላይ ትክክለኛ የሰውነት አቀማመጥ
አስቀድሞ ማወቅ አለበት፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
22. ጭንቅላትን /ራስን/ ከፍ አድርጎ ሞተር ሳይክል ላይ የመዉጣት ልምድ
ሀ/ ትክክለኛ የሰውነት አቀማመጥ ነዉ
ለ/ ትክክለኛ ሞተር ሳይክል ላይ የአወጣጥ ስርአት ነዉ
ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው
መ/ መልስ የለም
23. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተር ሳይክል ላይ በሚወጣበት ወቅት እጃቹን መሪ ላይ ተጠቅሞ ለመዞር
በሚያስችል ሁኔታ መሆን አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
24. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተር ሳይክል ላይ ሲቀመጥ
ሀ/ እጆቹን በትንሹ ጎበጥ ማድረግ አለበት
ለ/ ከመሪው በቂ ርቅት ላይ ሆኖ መቀመጥ አለበት
ሐ/ የእጆቹ መታጠፍ መሪ ላይ ያሉ መሳሪያዎችን ለመቆጣጠር የሚያስች መሆን አለበት
መ/ ሁሉም
25. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተሩን በሚያሽከርክርበት ወቅት እጆቹን 1800 ወደ ፊት ቀጥ አድርጎ የማሽከርከር
ልምድ ማዳበር አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
26. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተሩን በቅርብ ሆኖ ለመቆጣጠር ወደ መሪ በደንብ መቅረብ አለበት፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
27. ትክክለኛ የእጁ ጓንት ተጠቅሞ ሞተር ሳይክል ማሽከርካር ለምን ይጠቅማል
ሀ/ በድንገተኛ ሁኔታ ነዳጁን በአግባብ እንዲሰጥ
ለ/ እጁን እንዳይወላውል
ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው
መ/ መልስ የለም
28. ትክክለኛ የእጁ ጓንት መጠቀም በድንገተኛ ሁኔታ ወቅት ነዳጅ በአግባቡ ለመስጣት ይጠቀማል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
29. የእግር ጉልበትን ከነዳጅ መያዣ ጋን አንፃር አድርጎ ሞተር ሳይክልን ማሽከርከር ለምን ይጠቅማል፡፡
ሀ/ በሚታጠፍበት ወቅት ሚዛን ለመጠበቅ
ለ/ ቀጥ ብሎ ወደፊት በሚሽከረክርበት ወቅት ሚዛን ለመጠበቅ
ሐ/ የሞተሩን ፍጥነት ለመቆጣጠር
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

ሞተር ሳይክል Page 3


30. የሞተር ሳይክል አሽከረካሪ ሞተር ሳይክሉን በሚያዞርበት ወቅት የእግሩ የጉልበት አቀማመጥ በነዳጅ ጋን
አንፃር ማድርግ ሚዛኑን እንዲጠብቅ ይረዳዋል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
31. ሚዛን ጠብቆ ለማሽከርከር እንዲያስችል አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ እግሮቹን ማስቀመጥ ያለበት
ትክክለኛ የእግር ማስቀመጫ ቦታ ላይ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
32. በሞተር ሳይክል ላይ እግርን በትክክለኛ ቦታ ላይ ማስቀመጥ ለምን ይጠቅማል፡፡
ሀ/ አደጋ እንዳያጋጥም
ለ/ ሞተር ሳይክልን በቀላሉ ለመቆጣጠር እንዲያስችል
ሐ/ እግሮቹን በፍጥነት ለመጠቀም እንዲያስችል
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
33. በጉዞ ወቅት የሞተር ሳይክል ማቆሚያ ማስደገፊያ መሬት እንዳይነካ ጥንቃቄ መደረግ አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
34. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ በሞተር ሳይክል ላይ በሚሆንበት ወቅት እግሮቹ በመቆጣጠሪያ መሳሪያ
አጠገብ መሆን አለባቸው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
35. ሚዛንን ጠብቆ ማሽከርከር እንዲቻል እና የአሽከርካሪው እግር አደጋ እንዳይደረስበት ለመከላከል የሞተር
ሳይክሉ አሽከርካሪ እግር በትክክለኛ ቦታ መኖር ከፍተኛ ድርሽ አለው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
36. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ በከፍተኛ ፍጥነት ላይ እያለ ለመታጠፍ ወይም ለማዞር ቢያስብ ያለምንም
ችግር ሊፈፅም ይችላል
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
37. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ለመታጠፍ ወይም ለማዞር ያሰበበት ቦታ ሲደርስ ማስታወል ካለበት መካከል
የማይካተት የቱ ነው?
ሀ/ ፍጥነትን መቀነስ ሐ/ ወዴት ማዘንበል እንዳለበት
ለ/ የሞተር ድምፅ ማዳመጥ መ/ ሁሉም መልሰ ነው
38. ለማዞር ወይም ለመታጠፍ የተቃረበ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የሞተሩን ፍጥነት ለመቀነስ ትክክለኛው
የሆነዉ የቱ ነው
ሀ/ የነዳጅ መጠን መቀነስ ሐ/ የእግር ፍሬን መያዝ
ለ/ የእጅ ፍሬን መያዝ መ/ ሁሉም ትክክል ነው
39. በኩርባ መንገድ ላይ የነዳጅ መጠን በመቀነስ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሁለቱንም የሞተር ሳይክል ፍሬኖች
ተጠቅሞ መታጠፍ ትክክለኛ አካሄድ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
40. በኩረባ መንገድ ላይ አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ከመታጠፍ በፊት እይታውን ማስፋት አለበት፡፡

ሞተር ሳይክል Page 4


ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
41. ከሚከተሉት ውስጥ አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ በሚታጠፍበት ወቅት ማድረግ ካለበት መካከል
የማይመደበ የቱ ነው
ሀ/ እያታውን ማስፋት ሐ/ ፍጥነት መጨመር
ለ/ የሞተሩን ድምፅ ማዳመጥ መ/ መልስ የለም
42. በማሽከርከር ወቅት በኩረባ መንገድ ላይ ለማዞር /ለመታጠፍ/ ሞተር ሳይክሉን ዘንበል ማድረግ አስፈላጊ
ነዉ፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
43. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ በሚታጠፍበት ወቅት ሞተር ሳይክሉን ማዘንበል ያለበት ወዴት አቅጣጫ
ነዉ
ሀ/ ወደ ሚታጠፍበት አቅጣጫ በተመሳሳይ ሐ/ ማዘንበል የለበትም
ለ/ ከሚታጠፍበት አቅጣጫ በተቃራኒ ማዘንበል መ/ መልስ የለም
44. ሞተር ሳይክልን ወደ አንድ አቅጣጫ ለማዘንበል የሚያስችለው እንዴት ነው
ሀ/ ወደ ምታዞርበት አቅጣጫ ያለው መሪ ላይ ክብደት ማሳረፍ
ለ/ ወደ ምታዞርበት አቅጣጫ በተቃራኒው ያለው መሪ ላይ ክብደት ማሳረፍ
ሐ/ በሁለቱም በኩል ያለው መሪ ላይ ተመሳሳይ ክብደት ማሳረፍ
መ/ መልስ የለም
45. ሞተር ሳይክል ስናሽከረክር ትክክለኛዉ የአዟዟር ሁኔታ የሆነዉ የቱ ነዉ
ሀ/ መሪውን ቀጥ በማድረግ መዞር
ለ/ መሪውን ወደ ምንዞርበት አቅጣጫ ማዘንበል
ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው
መ/ መልሱ የለም
46. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የማዞር ሂደቱን ወደ መጨረሱ አካባቢ ሲቃረብ ነዳጅ መስጠትና የሞተሩን ድምፅ
ማዳመጥ አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
47. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ትክክለኛውን የሞተር ሳይክል ላይ አቀማመጥን በመተግበር እራሱን
ከአደጋ መከላከል ይችላል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
48. ትክክለኛውን የሞተር ሳይክል ላይ አቀማመጥ ተከትሎ በማሽከርከር ሞተር ሳይክሉ በቀላሉ ለመቆጣጠር
ይቻላል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
49. ወደ ምትዞርበት አቅጣጫ ባለው የሞተር ሳይክል የመሪ እጅታ ላይ ክብደት ማስፈር ሞተር ሳይክሉ ወደ
ተመሳሳይ እንዲያዘንበል ይረዳዋል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

ሞተር ሳይክል Page 5


50. የሞተር ሳይክል መሪ በትንሹ ቀጥ ማድረግ የሞተር ሳይክል የማዞር ሂደቱ ለማጠናቀቅ ሲቃረብ መውሰድ
ከሚገባው እርምጃዎች አንዱ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
51. ፍጥነት መቀነስ እና ሞተር ሳይክሉን ወዴት ማዘንበል እንዳለበት ማወቅ ሞተር ሳይክል ከማዞር በፊት
ከሚወሰድ እርምጃዎች መካከል ይመደባል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
52. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተሩን በቀላሉ ለመቆጣጠርም ሆነ በእግሮቹ ላይ አደጋ እንዳይደርስ
ለመከላከል እግሮቹን ማኖር ያለበት የት ነው
ሀ/ ትክክለኛ የእግር ማስቀመጫ ቦታ
ለ/ በነዳጅ ጎን ላይ
ሐ/ ምቾት ሊሰጠው የሚችል ቦታ ላይ
መ/ ሁሉም መልስ ነው
53. እግሮቹን በቀላሉ መጠቀም እንዲችል አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ እግሮቹን ማስቀመጥ ያለበት
ትክክለኛ የእግር ማስቀመጫ ቦታ ብቻ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

54. ሞተር ሳይክል በማሽከርከር ወቅት በድንገተኛ ሁኔታ ጊዜ ነዳጅ ያለ አግባብ በብዛት እንዲይሰጥ ለመቆጣጠር
ትክክለኛ የእጅ ጎንት መጠቀም እንደ መፍትሄ ይቆጠራል
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
55. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የእጅ እጥፋት መሪ ላይ ያሉ መሳሪያዎች ለመለየት የሚያስችል መሆን አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
56. ከሚከተሉት ውስጥ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የእግር አቀማመጥ መርሆ ያልሆነው የቱ ነው
ሀ/ እግሮቹን በትክክል የእግር ማስቀመጫ ላይ ማስቀመጥ
ለ/ እጅን ሻካራ በሆነ የመሪ እጀታ ላይ መያዝ
ሐ/ የእግር ጉልበትን በነዳጅ መያዛ ጋን አንፃር ማድርግ
መ/ መልስ የለም
57. አሽከርካሪ ሻካራ በሆነ የመሪ እጀታ ላይ መያዝ የሞተር ሳይክል የአሽከርካሪ የእጅ አቀማመጥ መርህ ውስጥ
አንዱ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
58. የሞተር ሳይክል መሪ ፍጥነት ለመቀነስ እና ለመጨመር የሚረዳ የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
59. የሞተር ሳይክል ዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ መሳሪዎች አሽከርካሪው መየት ያለበት መቼ ነው
ሀ/ ከጉዞ በፊት ሐ/ ከጉዞ በኃላ
ለ/ በጉዞ ወቅት መ/ ሁሉም መልስ ናቸው

ሞተር ሳይክል Page 6


60. በሞተር ሳይክል ዳሽ ቦርድ ላይ የሚገኙ ጠቋሚ መሳሪያዎች ጥቅማቸው እና ትርጉማቸውን ማወቅ የሞተር
ሳይክል አሽከርካሪ ግዴታ አይደለም
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
61. ከጉዞ በኃላ በዳሽ ቦርድ ላይ የሚገኙ ጠቋሚ መሳሪያዎች ማየት ብዙም አስፈላጊ አይደለም
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
62. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተሩን ከማሽከርከሩ በፊት (ከጉዞ በፊት) መፈፀም ያለበት
ሀ/ ፕሮግራም ማውጣት ሐ/ የመሬቱን መልካአ ምድር አቀማመጥ መወቅ
ለ/ የአየር ሁኔታ ማወቅ መ/ ሁሉም መልስ ነው
63. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ አስቀድሞ የመሬት መልካ ምድራዊ አቀማመጥ እና የአየር ሁኔታ ማወቅ ለምን
ይጠቅማል
ሀ/ ጉዞውን ያፈጥናል ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው
ለ/ አደጋን ይቀንሳል መ/ መልስ የለም
64. ከጉዞ በፊት ስለ ጉዞ እቅድ (ፕሮግራም) ማውጣት የአንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የብቃት መገለጫ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
65. አሽከርካሪው እራሱን ለጉዞ ማመቻቸት ማለት ምን ማለት ነው
ሀ/ የጉዞ ፕሮግራም ማውጣት
ለ/ የአካባቢውን ሁኔታ አስቀድሞ መተንበይ
ሐ/ የአየር ሁኔታ አመቺነት መረዳት
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
66. እንደ ሌሎቹ አሽከርካሪዎች የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የጉዞ ፕሮግራም ማውጣት አይጠበቅበትም
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
67. የተቃና ጉዞ እንዲኖር እና አደጋን ከመከላከል አንፃር አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ከጉዞ በፊት የጉዞ
ፕሮግራም ሊኖረው ይገባል
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
68. የጉዞ ፕሮግራም ማውጣትና ስለ ሚሄዱበት አከባቢ ማወቅ የአንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ግዴታ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
69. የሞተር ሳይክል ፍሬን በየትኛው የሞተር ሳይክል እግር ላይ ይገኛል?
ሀ/ በፊት እግር ሐ/ “ሀ” እና “ለ”
ለ/ በኋላ እግር መ/ መልስ የለም
70. በኋላ እግር ላይ ያለው የሞተር ሳይክል ፍሬን በአገልግሎት ብቃቱ በፊት እግር ላይ ካለው ይለያል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
71. በጉዞ ወቅት የሞተር ሳይክል ፍጥነት ለመቀነስ ሁለቱንም ፍሬን በአንድ ጊዜ መጠቀም ለአደጋ ያጋልጣል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

ሞተር ሳይክል Page 7


72. በፊት እግር ላይ ያለው የሞተር ሳይክል ፍሬን ሞተሩ በቆመበት ቦታ ለረጅም ወይም ለአጭር ጊዜ እንዲቆም
ማድረግ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
73. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሞተር ሳይክሉን ተቆጣጥሮ ለማሽከርከር እንዲያስችል ስለ ፍሬን አጠቃቀም
አስቀድሞ ማወቅ አለበት፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
74. ከሞተር ሳይክል ፍሬን መካከል የበለጠ ሃይል ያለው በየትኛው እግር ላይ ያለው ነው፡፡
ሀ/ በፊተኛው እግር ለይ ያለ ሐ/ ሁለቱም ከኩል ሃይል አላቸው
ለ/ በኃላ እግር ላይ ያለ መ/ መልስ የለም
75. ሞተር ሳይክል ለማቆም ከሚጠቅመው ሃይል ውስጥ 3/4ኛ የሚሆን ሃይል ያለው በየትኛው የሞተር ሳይክል
እግር ላይ ነው፡፡
ሀ/ በፊተኛው ሐ/ “ሀ” እና “ለ” መልስ ናቸው
ለ/ በኋላ እግር ላይ መ/ መልስ የለም
76. የኋላኛው የሞተር ሳይክል ፍሬን ከፊተኛው የበለጠ ሃይል አለው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
77. 1/4ኛው ፍሬን የመያዝ ሃይል ያለው የሞተር ሳይክል ፍሬን በየትኛው እግር ላይ ያለው ነው፡፡
ሀ/ በኃለኛው ሐ/ “ሀ” እና “ለ” መልስ ናቸው
ለ/ በፊተኛው መ/ መልስ የለም

78. በፊተኛው የሞተር ሳይክል እግር ላይ ያለው የሞተር ሳይክል የፍሬን ሃይል ምን ያህል ነው፡፡
ሀ/1/4 ሐ/ 4/3
ለ/ 3/4 መ/ መልስ የለም
79. በፊተኛው የሞተር ሳይክል እግር ላይ ያለው ፍሬን ሃይል በፐርሰንት ምን ያህል ነው፡፡
ሀ/ 75 ሐ/50
ለ/ 25 መ/ 90
80. በሁለቱ የሞተር ሳይክል እግር ላይ ያለው የፍሬን ሃይል ተመሳሳይ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
81. የትኛው የሞተር ሳይክል ፍሬን ነው በአግባብ አሽከርካሪው ሲጠቀምበት ፍሬንኑ አስተማማኝ የሚያደረገው
ሀ/ በፊት እግር ላይ ያለው ሐ/ “ሀ” እና “ለ” መልስ ናቸው
ለ/ በኋላ እግር ላይ ያለው መ/ መልስ የለም
82. የኋላ የሞተር ሳይክል እግር ፍሬን ብቻ በአግባብ እና በትክክል መጠቀም ፍሬኑን አስተማማኝ ያደርጋል
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
83. 75 በመቶ የሚሆነው የሞተር ሳይክል እግር ፍሬን በፊተኛው የሞተር ሳይክል እግር ላይ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

ሞተር ሳይክል Page 8


84. ሁል ጊዜ ሁለቱንም የሞተር ሳይክል ፍሬኖች መጠቀም ልምድ ማድረግ ድንገተኛ አደጋ ሲያጋጥም ለማምለጥ
ይጠቅማል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
85. በጉዞ ወቅት ሞተር ወደ ላይ የመዝለል ወይም የመነሳት ባህርይ የሚያሳየው ምን ሲሆን ነው
ሀ/ የፊት ፍሬን በደንብ አጥብቆ ሲያዝ ሐ/ ሁለቱም ፍሬን እኩል ሲያዝ
ለ/ የኋላ ፍሬን በደንብ አጥብቆ ሲያዝ መ/ መልስ የለም
86. የፊት እግር በደንብ አጥብቆ ሲያዝ ሞተር ሳይክል ወደ ላይ የመነሳት ወይም የመዝለል ባህርይ ያሳያል
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
87. በፍጥነት ላይ በመታጠፍ ወይም በመዞር ጊዜ የአሽከርካሪው የፍሬን አያያዝ በጣም ከፍ ያለ ከሆነ ሞተር
ሳይክሉ
ሀ/ ወደ አንድ ጐን ይንሸራተታል ሐ/ ወደ ኋላ ይሄዳል
ለ/ በአንድ ጊዜ ይቆማል መ/ መልስ የለም
88. ሞተር ሳይክሉ ወደ አንድ አቅጣጫ መንሽራተት ሲጀምር አሽከርካሪው መውሰድ ያለበት እርምጃ የቱ ነዉ
ሀ/ የሞተር የፊት እግር በትክክል መቆጣጠር
ለ/ የሞተር ሳይክሉ የኃላ እግር በደንብ መቆጣጠር
ሐ/ “ሀ” እና “ለ” መልስ ናቸው
መ/ መልስ የለም
89. የሞተር ሳይክሉን ፍሬን አያያዝ በጣም ከፍ ያለ ከሆነ ሞተሩ ወደ አንድ አቅጣጫ የመንሸራረት እድሉ ከፍ
ያለ ይሆናል
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
90. የሞተር ሳይክሉን ወደ አንድ አቅጣጫ የመንሸራተት ባህርይ ሲያሳይ አሽከርካሪው የሞተሩን የፊት እግር
በትክክል መቆጣጠር አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
91. በአንዳንድ ሞተር ሳይክል ላይ አሽከርካሪው የኋላ እግር ብቻ ፍሬን እንዲይዝ ቢፈልግ የፊት እግር
የሚይዝበት ሁኔታ አለ
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
92. በሞተር ሳይክሉ የፍሬን ሲስተሙ ሁለቱንም ፍሬኖች አንድ ላይ እንዲሰሩ የሚደረግበት ሁኔታ አለ
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
93. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የፍሬን አሰራርን ለማወቅ የአሽከርካሪዎችን ማንዋል በደንብ ማወቅ
ይጠበቅበታል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
94. ከሚከተሉት ውስጥ በሞተር ሳይክል ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ ሊቀንስ የሚችለው የቱ ነው
ሀ/ የሞተር ሳይክል የአሽከርካሪዎች መመሪያን ጠንቅቆ ማወቅ
ለ/ የሞተር ሳይክሉን መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች በደንብ ማወቅ

ሞተር ሳይክል Page 9


ሐ/ ከጉዞ በፊት ሁል ጊዜ ሞተር ሳይክሉን መፈተሸ
መ/ ሁሉም መልስ ነው
95. በሞተር ሳይክል ላይ የተለያዩ ቅጥያዎችን መጨመር ሞተር ሳይክሉ ለአደጋ ምክንያት እንዲሆን ያደርጋል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
96. የሞተር ሳይክል የአሽከርካሪዎች መመሪያ አለማወቅ ሞተር ሳይክል በማሽከርከር ወቅት የሚመጣ ችግር
የለውም፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
97. የሞተር ሳይክል የመቆጣጠሪያ መሳሪያዎች ከሚባሉት መካከል ያልሆነው የቱ ነው
ሀ/ፍሬን ሐ/ ነዳጅ መስጫ
ለ/ መሪ መ/ ሞተር
98. በጉዞ ወቅት አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ በግልፅ ለሌሎች እንዲታይ ከሚረዱት መካከል
የሚካተተው የትኛው ነው?
ሀ/ ትክክለኛ የሞተር ሳይክል አለባበስ መጠቀም
ለ/ በምሽት የግንባር መብራት መጠቀም
ሐ/ ትክክለኛውን ረድፍ ይዞ ሲያሽከረክር
መ/ ሁሉም መልስ ነው
99. ትክክለኛ የሞተር ሳይክል አለባበስ መልበስ ሊደርስ የሚችለውን የትራፊክ አደጋ ይቀንሳል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
100. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ለማድረግ ያሰበውን ለሌሎች ማሳወቅ የሚችለውን ትክክለኛ
ምልክት በመጠቀም ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

101. ሞተር ሳይክልን ለጉዞ ዝግጁ ለማድረግ ከሚከተሉት ተግባራት መካከል ያልሆነው የቱ ነው
ሀ/ የጎማዎችን ሁኔታ መፈተሸ ሐ/ መስታዎትን ማፅዳት
ለ/ የሞተር ዘይት ሁኔታ ማየት መ/ መልስ የለም
102. የፍሬን እና የፍሬቻ መብራት መስራታቸውን እና አለ መስራታቸው ሁል ጊዜ ከጎዞ በፊት ማረጋገጥ
ሞተር ሳይክልን ለጎዞ ዝግጁ ማድረግ ነው
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
103. ሞተር ሳይክልን ለጉዞ ዝግጁ ለማድረግ ከሚከናወኑት ተግባራት መካከል የሚመደበው የቱ ነው
ሀ/ የፍሬቻ መፈተሸ ሐ/ የፍሬን ሁኔታ መፈተሸ
ለ/ የፍሬን መብራት ሁኔታ ማየት መ/ ሁሉም መልስ ነው
104. ትክክለኛ የሞተር ሳይክል አለባበስ መጠቀም አደጋ ከመከላከል በተጨማሪ ለሞተር ሳይክል አሽከርካሪ
ምን ጥቅም ይሰጣል፡፡
ሀ/ ምቾት ሐ/ ቆሻሻን ይከላከላል

ሞተር ሳይክል Page 10


ለ/ ሙቀት መ/ ሁሉም መልስ ነው
105. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ትክክለኛ የስራ ልብስ አለባበስ መጠቀም በግጭት ጊዜ ከአደጋ
ሊከላከል ይችላል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
106. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የሚለብሱት ልብስ ሙሉ ለሙሉ ሰውነታቸውን የሚሽፍን ሳይሆን ሌሎች
አሽከርካሪዎች ምልክት ሊሰጥ በሚችል መልኩ መሆን አለበት፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
107. ከቆዳና ከሴንቴቲክ የተሰሩ ልብሶች አብዛኛውን ጊዜ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች እንዳይለብሱት
ይመከራል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

108. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የደንብ ልብስ መሆን ያለበት


ሀ/ ሰውነት ላይ በደንብ የሚጠብቅ እና ሙቀት ሊሰጥ የሚችል
ለ/ በአካል ላይ በቀላሉ የሚንቀሳቀስ
ሐ/ ለንፋስ ማስገቢያ ትርፍ ነገር ያላቸውና የሚውለበለቡ
መ/ ሁሉም መልስ ነው
109. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ትክክለኛ አለባበስ ተጠቅሞል የሚባለው
ሀ/ ትክክለኛ የራስ ቆብ ሲያደርግ ነው
ለ/ የፊትና የአይን መከላከያ ሲጠቀም ነው
ሐ/ የአደጋ መከላከያ ልብስ ሲጠቀም ነው
መ/ ሁሉም መልስ ነው
110. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ በአደጋ ምክንያት በጭንቅላትና በአንገት አከባቢ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት
ሊቀንስ የሚችለው
ሀ/ ትክክለኛ የራስ ቆብ መጠቀም
ለ/ የፊትና የአይን መከላከያ መጠቀም
ሐ/ ከቆዳ የተሰራ ጃኬት መጠቀም
መ/ መልስ የለም
111. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የራስ ቆብ በማሽከርከር ወቅት መጠቀሙ ለምን ይጠቅማል
ሀ/ በጭንቅላት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ይከላከላል
ለ/ በአንገት አካባቢ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ይቀንሳል
ሐ/ ሀ እና ለ መልስ ናቸው
መ/ መልሱ የለም
112. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የራስ ቆብ መጠቀም ያለባቸው በረጅም ጎዞ እና
በፍጥነት የሚያሽከረክሩ ከሆነ ብቻ ነው፡፡

ሞተር ሳይክል Page 11


ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
113. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የራስ ቆብ በመጠቀማቸው ምክንያት የጎን እይታቸው ይቀንሳል
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

114. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የራስ ቆብ መጠቀም ያለባቸው መቼ ነው


ሀ/ ረጅም ጎዞ በሚያሽከረከሩበት ጊዜ
ለ/ በፍጥነት በሚያሽከረከሩበት ጊዜ
ሐ/ በማሽከርከር ወቅት ሁል ጊዜ
መ/ መልሱ የለም
115. ስንት አይነት የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የራስ ቆብ ይገኛል
ሀ/ ሁለት ሐ/ አራት
ለ/ ሦስት መ/ አንድ
116. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የራስ ቆብ ዓይነት የሆነዉ የቱ ነዉ
ሀ/ ½ ፊትና ጭንቅላት የሚሸፍን
ለ/ ¾ ፊትና ጭንቅላት የሚሸፍን
ሐ/ ሙሉ በሙሉ ፊትና ጭንቅላት የሚሸፍን
መ/ “ለ” እና “ሐ” መልስ ነው
117. የፊትና የአይን መከላከያ ጥቅም ያልሆነው የቱ ነው
ሀ/ ንፋስ መከላከል
ለ/ በራሪ ነፍሳትን መከላከል
ሐ/ በጭንቅላት ላይ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ መከላከላል
መ/ ሁሉም መልስ ነው
118. የሞተር ሳይክል የፊትና የዓይን መከላከያ መሳሪያዎች ከፕላስቲክ የተሰሩ ቢሆኑ ይመረጣል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
119. የሞተር ሳይክል የፊት መስታወት ሊያካትት የሚገባዉ መከላከያ መሳሪያ የትኛዉ ነዉ
ሀ/ የፊት መከላከያ ሐ/ የጭንቅላት መከላከያ
ለ/ የዓይን መከላከያ መ/ ከ ሐ በስተቀር ሁሉም መልስ ነው
120. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የጭንቅላት መከላከያ በሞተር ሳይክል የፊት መስታወትን ሊተካ ይችላል፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
121. የሞተር ሳይክል የፊት መከላከያ መሳሪያዎች ሊኖራቸው የሚገባ ባህሪያት የሆነው የቱ ነው
ሀ/ በቀላሉ የማይበሱ ሐ/ በግልፅ የሚያሳዩ
ለ/ ከጭረት ነፃ የሆኑ መ/ ሁሉም ትክክል ነው

ሞተር ሳይክል Page 12


122. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የፊት መከላከያ መሳሪያዎች የዓይን መነፅር ለማድረግ የሚያስችሉ ሆኖ
መሰራት አለባቸው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
123. ከሚከተሉት ውስጥ የሞተር ሳይክል የፊት መከላከያ መሳሪያዎች ባህሪያት የሆነው የቱ ነው
ሀ/ አየር የሚያስገቡ መሆን አለባቸው
ለ/ የዓይን መነፅር ለማድረግ የሚያስችሉ ሆኖ መሰራት አለባቸው
ሐ/ በደንብ የሚታሰሩ መሆን አለባቸው
መ/ ሁሉም መልስ ናቸው
124. ከሚከተሉት ውስጥ የአደጋ መከላከያ መሳሪያ የሆነው የቱ ነው
ሀ/ የእጅ ጓንት ሐ/ የራስ ቆብ
ለ/ ጫማ መ/ ሁሉም መልስ ነው
125. የአደጋ መከላከያ ጫማዎች
ሀ/ መጠናቸው ከፍ ያለ መሆን አለባቸው
ለ/ ሶላቸው የማያንሽራትትና ጠንከራ መሆን አለበት
ሐ/ ተረከዛቸው መሬት የማይነካ መሆን አለበት
መ/ ሁሉም መልስ ነው
126. በወጣ ገባ መንገድ ላይ የሚያሽከረክር የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሶሉ አጭር የሆነ ጫማ ማድረግ
አለበት
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
127. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች የጫማ መጠናቸው ከፍ ያሉ፣ የአሽከርካሪውን ቁርጭምጭሚት
የሚሸፍኑና ክብደት መሸከም የሚችሉ መሆን አለባቸዉ፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

128. የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ የእጅ ጓንት እንደ ጨርቅ ቀለል ካሉ ነገሮች ቢሰራ በአደጋ ወቅት አደጋን
ከመቀነስ አንፃር ከፍተኛ ድርሻ አላቸዉ
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
129. አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ በቀዝቃዛ የአየር ንብረት ውስጥ ለረጅም ሰዐት እንዲያሽከርክር
አይመከረም
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
130. የሞተር ሳይክል የደህንነት ልብስ ጥቅም የአሽከርካሪውን ሰዉነት ከቅዝቃዜ መጠበቅ ብቻ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት
131. የእጅ ጓንት የማይጠቀም አሽከርካሪ በቀዝቃዛ የአየር ንብረት ውስጥ ሞተር ሳይክል የመቆጣጠር ዕድሉ
ዝቅተኛ ነው፡፡
ሀ/ እውነት ለ/ ሀሰት

ሞተር ሳይክል Page 13


132. አደጋን ከመከላከል አንፃር አንድ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪ ሁልጊዜ በሚያሽከርክርበት ወቅት
መርሳት የሌለበት የቱን ነው፡፡
ሀ/ የእጅ ጓንት ሐ/ የጭንቅላት መከላከያ
ለ/ የአይን መከላከያ መ/ ሁሉም
133. የሞተር ሳይክል ከማሽከርከር በፊት ማንኛውም አሽከርካሪ ሞተረኛ ትራፊኩን ማስፈቀድ ይኖርበታል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
134. የሞተረኛ ልብስ አደጋ በሚደርስ ጊዜ አሽከርካሪውን ከአደጋ ለመጠበቅ ይረዳዋል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
135. ሞተር ሳይክል ለማሽከርከር ማንኛውንም ዓይነት ልብስ መልበስ ይፈቀዳል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
136. ሞተር ሳይክል ከማሽከርከራችን በፊት የራስ መከላከያ ሄልሜት ማድረግ ጠቀሜታው የጐላ ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

137. በሞተር ሳይክል እያሽከረከርን ረጅም ጉዞ ከመጓዛችን በፊት አስቀድመን የሞተር በስክሌትን ፀባይ
ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
138. የብስክሌት ቆብን ለሞተር ሳይክል መጠቀም ይፈቀዳል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
139. የሞተረኛ አልባሳት ከሐርና ከቆዳ መሰራት አለባቸው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
140. የአደጋ መከላከያ ልብስ የሞተር ብስክሌቱን መሪ በጥሩ ሁኔታ ለመያዝና በግጭት ጊዜ ከአደጋ ለመከላከል
ይጠቅማል፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
141. በተሽከርካሪም ሆነ በሞተር ብስክሌት ላይ ከፊት መገጠም ያለበት ጐማ ጥርስ ተመራጭ የሚሆነው
ቢሆን ነው፡፡
ሀ. አዲስ ሐ. መካከለኛ
ለ. ያለቀ መ. መልሱ አልተሰጠም
142. ሞተር ሳይክል በፍጥነት ላይ እያለ ለማቆም ብንፈልግ የፊት እግር ፍሬኑን በድንገት መያዝ
ይመረጣል፡፡
ሀ እውት ለ. ሀሰት
143. በሞተር ሳይክል ማሽከርከር ሂደት ወቅት ከሞተረኛው የሚጠበቀው አስተዋይና ንቁ መሆን ነው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

ሞተር ሳይክል Page 14

You might also like