You are on page 1of 5

የተሸከርካሪ ማንዋል አይነቶች፣አጠቃቀም እና አያያዝ

የተሸከርካሪ ማንዋል ስንል በአጠቃላይ ስለተሸከርካራው መግለጫ የሚሰጡ ሲሆን ስለተሸከርካሪው አጠቃላይ ይዘት፣ የአነዳድ
ስርዓት፣የጥገና ቀን፣በዳሽ ቦርድ አካባቢ የሚነበቡ ምልክቶችን እና የመሳሰሉትን የሚያሰረዳ መመሪያ፡፡
የማንዋል አይነቶች
1. ኦፕሬቲግ ማንዋል- ይህ የማንዋል ዓይነት በተሸከርካሪ ውስጥ ያሉትን መሳሪያዎች እና ክፍሎችን አጠቃቀም እንድንረዳ
የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ- ዳሽ ቦርድ ላይ ያሉ ጠቋሚ ምልክቶችን፣ የበር አከፋፈትና አዘጋግ፣ ወንበር ማስተካከል፣
ሞተር ማስነሻ ቁልፍን፣ የማርሽ አጠቃቀምን ያካትታል፡፡
2. ሰርቪስ/የጥገና ማንዋል- ይህ የማንዋል ዓይነት ተሸከርካሪዎች /ማሽኖች የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በአግባቡ
እንዲከናወኑ ለማድረግ የእንክብካቤ ስራ የምናከናውንበት ሁኔታን ይገልፃል፡፡ በተጨማሪም በምን ያህል ጊዜ የተለያዩ
ክፍሎች መስተካከልና መለወጥ እንዳለባቸው፣የሰርቪስ የሚደረጉ ክፍሎችን በማመልከት የተሸከርካራውን የሰርቪስ
ጊዜ ለመጠበቅ እና ድንገተኛ ብልሽት ለመጠገን ይረዳል፡፡
3. ሜንቴናንስ ማንዋል- ይህ የማንዋል ዓይነት በአገልግሎት የተጎዳውን ተሸከርካሪ ክፍሎች ወደ ነበሩበት ለመመለስ
የክፍሎቹን አፈታት/አስተሳሰሩን፣ የመሳሪያዎች ቦታ አቀማመጥን እንድናውቅ ያስችላል፡፡
4. ስፔሲፊኬሽን ማንዋል- የተሸከርካሪን ዓይነት፣ የሞተር ጉልበት፣ የምት ዘመን፣ የመጫን አቅም፣ ሞዴል፣ ቀለም እና
የመሳሰሉትን ይገልፃል፡፡

 ማንዋሉ ላይ ያሉትን መመሪያዎች፣መረጃዎች፣ ቅደም ተከተሎች በሚገባ መመረዳት መተግበር አለብን፡፡

የማንዋል አጠቃቀም ማንዋልን በአግባቡ መጠቀም እና ማስቀመጥ


በሀገራችን የማንዋል አጠቃቀም እና አያያዝ ደካማነት በስፋት የስተዋላል፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው በመረዳ
ልንጠቀምባቸው ይገባል፡፡ ማንዋሎችን ስንጠቀም

 እጆቻችንን በንፅህና መያዝ/በጓንት መጠቀም


 ማንዋሎችን በንህፅና ቦታ ማስቀመጥ
 ግልፅ እና በቀላሉ ማግኘት የምንችልበት ቦታ ማስቀመጥ
 ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የታደሰ/የተሻሻለ ማንዋል መያዝ
በማሽከርከር ላይ ተፅእኖ የሚያደርጉ የተፈጥሮ ህጎች
በማሽከርከር ላይተፅዕኖ የሚያደርጉ የተፈጥሮ ህጎች የሚባሉት

1. የመሬት ስበት
የመሬት ስበት ሁሉንም ነገሮች ወደ መሬት መሀል የሚስብ የተፈጥሮ ሀይል ነው፡፡ ይህ የተፈጥሮ ሀይል በማሽከርከር ላይ
ተፅዕኖ የሚያደርገው ተሽከርካሪ ዳገት ሲወጣና ቁልቁለት ሲወርዱ፣ እንዲሁም በተሽከርካሪው በጉዞ ፍጥነት ላይ ሲሆን፣
በማሽከርከር ሂደት ላይ የሚሰጠው ጥቅም ጎማ መሬት ቆንጥጦ እንዲይዝ ያደርጋል፡፡ ስለዚህ የመሬት ስበት ተሽከርካሪ
ዳገት ሲወጣ ፍጥነት ይቀንሳል፤ ቁልቁለት ሲወርድ ደግሞ የተሽከርካሪው ፍጥነት ይጨምራል፡፡ በዚህም አሽከርካሪዎች
ቁልቁለት ሲወርዱ ፍጥነትን ለመቆጣጠር ከባድ ማርሽን መጠቀምና ፍሬን በትንሹ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

የመሬት ስበት በአነዳድ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ለምሳሌ

 ዳገት ስንቀጣ የመሬት ስበት ይቀንሳል፡፡ በዚህም ተሸከርካሪ ወደ ላይ ለመውጣት በመቸገር ወደ ኃላ


ሊመለስና ከቁጥጥር ውጪ ሊሆን ይችላል፡፡
 ቁልቁለት ስንወርድ የመሬት ስበት ይጨምራል፡፡ በዚህም የተሸከርካሪ ግፊት ይጨምራል እና አሽከርካሪው
ተሸከርካሪውን ሚዛን ለመጠበቅ ይቸግራል

2. የኢነርሺያ ህግ
ይህ ህግ የሚለው ሌላ ተጨማሪ ኃይል እስካልመጣ ድረስ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ ነገሮች እንቅስቃሴያቸውን መቀጠል
ይፈልጋሉ፤ የቆሙ ነገሮች ደግሞ እንደቆሙ መቆየት ይፈልጋሉ ፡፡ ስለዚህ ኢነርሺያ በማሽከርከር ላይ የሚያደርሰውን
ተፅዕኖ ለመከላከል የሚከተሉት መፍትሄ ይሆናሉ፡፡ እነሱም፡- ፍሬን በመያዝ ፣ የደህንነት ቀበቶ መጠቀም እና ድንገተኛ
አነሳስን ማስወገድ

3. ፖተንሺያል ኃይል
ይህ ነገሮች ባሉበት ቦታ ሁሉ ወይም ቅርፅ ምክንያት የሚኖራቸው የተጠራቀመ ኃይል ነው፡፡ በዚህም በማሽከርከር ላይ
ያለው ተፅዕኖ በዳገት ላይ የቆመ ተሽከርካሪ ወደ ቁልቁለት ለመሽከርከር በመሬት ስበት ምክንያት የተጠራቀመ ኋይል
ይኖረዋል፡፡

4. ኬኔቲክ ኃይል
ይህ ሀይል በእንቅስቃሴ ላይ ያለ ነገር የሚኖረው ኃይል ነው፡፡

 የተሽከርካሪ ፍጥነት በጨመረ ቁጥር የኬኔቲክ ኃይል ይጨምራል፤


 የተሽከርካሪ ክብደት በጨመረ ቁጥር የኬኔቲክ ኃይል ይጨምራል፡፡
 ተሽከርካሪ ከዳገት ወደ ታች መውረድ ሲጀምር የፖተንሺያል ኃይል ወደ ኬኔቲክ ኃይል ይቀየራል፡፡
 በሜዳ ላይ የሚንቀሳቀስ ተሸከርካሪ ፖቴንሻል ኃይል የለውም ኬኔቲክ ኃይል አለው

5. ሞመንተም
ይህ ሁለት ያልተመጣጠኑ ኃይሎች በአንድ ነገር ላይ በተቃራኒ አቅጣጫ ግፊታቸውን ሲያሳርፉ የሚንቀሳቀሰው ነገር
የያዘው ኃይል ነው፡፡
 የተሽከርካሪ ፍጥነት በጨመረ ቁጥር ሞመንተሙ ይጨምራል፤
 ሞመንተም ሲጨምር የማቆሚያ ርቀት ይጨምራል፡፡ በዚህም ኢነርሺያን ለመቆጣጠር ይከብዳል፣
አቅጣጫን ለመቀየር ያስቸግራል፤ ከመንገድ ስፋት ብዙ ይወስዳል፡፡
 የተሸከርካሪ ፍጥነትና ክብደት ሲጨምር ተሸከርካሪ በፍሬን ለመቆጣጠር ያስቸግራል፡፡ በዚህም
ሞመንተም ይጨምራል፡፡
 በግጭት ጊዜ ሞመንተም ወደ ሙቀት በመቀየር ሰዎችንና ንብረትን ይጎዳል
6. ሰበቃ
ይህ አንድ ነገር ከሌላ ነገር ጋር ሲነካካ የሚፈጠር ኃይል ነው፡፡ በዚህም ሰበቃ በተለያየ ምክንያት ሊፈጠር ይችላል፡፡
 በመንገድና በጎማ መካከል
 በፍሬን ሲስተም ውስጥ(በፍሬን ሸራና ታምቡር)
 በሞተር ክፍሎች ውስጥ
 በሀይል አስተላላፊ ክፍሎች ውስጥ(በፍሪሲዮን፣በካምቢዮና ዲፈረንሺያል) ተጠቃሽ ነው

ሰበቃ በተሽከርካሪ ላይ የሚከሰተው በሞተር ውስጥ በኃይል አስተላላፊ ክፍሎች ውስጥ በፍሬን ውስጥ እና በመንገድና
ጎማ መሀከል

7. ሴንተሪፉጋል ኃይል
ይህ ኃይል አንድ ነገር በሌላ ነገር ዙሪያ ሲሽከረከር ወደ ውጭ የሚጎትት ኃይል ነው፡፡ በዚህም ተሽከርካሪ ኩርባ በፍጥነት
በሚዞርበት ጊዜ ከመንገድ ውጪ እንዲወጣ የሚጎትት ኃይል ነው፡፡ ይህን ለመቆጣጠር በጎማና በመንገድ መሀከል ያለውን
የመቆንጠጥ ኃይል በመጠቀም በመሪ ማዞር ነው፡፡ በዚህም የሴንትሪፉጋል ኃይል ኩርባ በምናዞርበት ጊዜ ተሽከርካሪን
ከመንገድ ውጪ እየጎተተ ችግር እንዳይፈጥር ለማድረግ የምንቆጣጠርባቸው መንገዶች የሚከተለት ናቸው፤
 ከማዞሪያው ከመድረሳችን በፊት ፍጥነት መቀነስ
 ፍሬን በትንሹና በጥንቃቄ መያዝ
 ከባድ ማርሽ መጠቀምና ፍጥነት መቀነስ
 ሰፋ አድርጎ ኩርባን መዞር ናቸው
 ከልክ በላይ ጭነትን አለመጫን
የሰከንደች ህግ

ርቀትን ጠብቆ የማሽከርከር ዋነኛ መፍትሔ የሶስት ሰከንድ ህግ ይባላል፤ የሶስት ሰከንድ(3) ህግ ማለት ተሸከርካሪ በሶስት
ሰከንድ የሚሄደው ርቀት ማለት ነው፤ በመንገድ ላይ ስናሽከረክር ከፊታችን ካለው ተሽከርካሪ ምን ያህል ርቀት ላይ
እንዳለን ለማወቅ የሶስት ሰከንድ ህግ የላቀ ጠቀሜታ አለው፡፡ ይህንንም ለማወቅ የሚከተለውን ድርጊት መተግበር
ያስፈልጋል፤ ከፊት ያለው ተሸከርካሪ ያለበትን ቦታ ምልክት መያዝና አንድ ሺ አንድ፣ አንድ ሺ ሁለት፣ አንድ ሺ ሶስት
በማለት በመቁጠር ይሆናል፡፡

 የመንገዱን ሁኔታ/መንገዱ አንሸራታች፣ቁልቁለት፣ ጠመዝማዛማ ከሆነ


 የተለያየ የአየር ሁኔታ ካጋጠመን/ ዝናባማ፣ ጭጋጋማ፣ አቧራ ለእይታ የሚያስቸግር ከሆነ
 ሞተር ሳይል የምንከተል ከሆነ
 እግኛ የሚበዛበት አካባቢ ከሆነ
 ከኃላ ያለ ተሸከርካሪ ሊያልፍህ ሲፈልግ
 ጭነት ከጫንን
 አደገኛ ጭነት የጫኑ አሽከርካሪዎች ሲኖሩ እና የመሳሰሉት የሚያጋጥም ከሆነ ፍጥነትህን በመቀነስ ቢያንስ ከ 4
ሰከንድ ወደ 6 ሰከንድ ክፍ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

You might also like