You are on page 1of 11

የተሳፋሪ አያያዝ መልካም የስራ ግንኙነት

የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት በዋነኝነት የሚሠጠው አገልግሎት ህዝብ ማጓጓዣ ነው፡፡ መንገደኞች ከቦታ ወደ ቦታ
የሚንቀሳቀሱት ለስራ ለማህበራዊ ጉዳዮች ለጉብኝት እና ለትምህርት አገልግሎት ሲሆን ጉዞው በቡድን
ወይም በግል ሌሆን ይችላል፡፡ የተጠቃሚዎችን አይነት በባህሪያቸው ወይም በስራ ፍላጎታቸው የተለያዩ ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች የጉዞና የመንገደኞችን አይነት በሚገባ ማወቅ አለባቸው፡፡

የጉዞ አይነቶች የሚባሉት

1. ረዥም ጉዞ፦ የሚባለው ከክልል ክልል እና ከሀገር ሀገር የሚደረግ ጉዞ ማለት ነው፡፡
2. መካከለኛ ጉዞ፦ የሚባለው ከከተማ ከተማ ወይም ከዞንዞን የሚደረግ ጉዞ ማለት ነው፡፡
3. አጭር ጉዞ፦ የሚባለው ከወረዳ ወረዳ የሚደረግ ጉዞ ማለት ነው፡፡
4. የከተማ ውስጥ ጉዞ፦ከቤት ወደ ስራ ወይም ከት/ቤት ወደ ቤት…ወዘተ በአንድ ከተማ ውስጥ
የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ማለት ነው፡፡
5. በትልቅ ድርጅት ግቢ ውስጥ የሚደረግ ጉዞ፦ የሚባለው የአንድ ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ ወይም
የቆዳ ስፋት ሰፊ በሆነ ጊዜ ሰራተኛውን ከማደሪያው ቦታ ወደ ዋናስራ ቦታው ወይም ከቢሮ ወደ
ማደሪያ የሚከናወንበት ቦታ ለማድረስና ለመመለስ የሚደረግ ጉዞ ማለት ነው፡፡

የጉዞ ዕቅድ

ጥሩ የጉዞ ዕቅድ የሚባለው

 የመነሻና መድረሻ ሰዓትን ያካተተ መሆን አለበት

 የተሳፋሪውን ምቾትና ጤና የሚጐዳና በአጠቃላይ የተሳፋሪውን ደህንነት የሚጠበቅበትን መንገድ
መርጦ የያዘ መሆን አለበት
 የተሳፋሪን ፍላጎት መሰረት ያደረገ፤ መንገደኛውንም ሆነ ሌሎችን ለትራፊክ አደጋ የማያጋልጥና
አጭር ጉዞ የሚያደርግበትን መስመር የያዘ መሆን አለበት፡፡
 ተሳፋሪን ሲያሳፍርም ሆነ ሲወርድ መንገደኛውን ወይም ሌሎችን ለአደጋ የማያጋልጥ የመቆሚያ
ስፍራ የተመረጠ መሆን አለበት፡፡
 ለስርቆት የማያጋልጥ ቦታዎችንና ሌሎችንም ማካተት ይኖርበታል፡፡
 በአጠቃላይ ዕቅድ የከተማውን ካርታ መሰረት ያደረገ ሊሆን ይገባል፡፡
 ስለሆነም አንድ አሽከርካሪ የጉዞ ዕቅዱን ሲያወጣ መነሳት ያለባቸው፡፡
 ከመነሻ እስከ መድረሻ ያለውን ርቀት በኪሎ ሜትር
 በመሃል የሚገኙ ከተሞችና ታሪካዊ ስፍራዎች
 የሚፈለጉ እርዳታዎች እንዴትና ከማን እንደሚገኙ
 የመንገደኞችን የማሳፈሪያ ቦታና ሰዓት/ለተማሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ የአውቶብስ አሽከርካሪ
የማረፊያ ቦታና ሰዓትን ለወላጅ ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡
 የመንገደኞችን እቃ የመጫኛ ሰዓት
 የተሸከርካሪው የመነሻ ሰዓት
 የቁርስ፤ የምሳና የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሁም የነዳጅ ቦታ
 የመድረሻ ቦታና ሰዓት
 የመነሻ ቀን፤ ቦታና ሰዓት

ለተሳፋሪዎች የሚደረግ ጥንቃቄ

መንገደኞች ወደ ሚፈልጉበት ቦታ በሚጓጓዙበት ወቅት ደህንነታቸውን መጠበቅና ብቃት ያለው አገልግሎት

እንዲያገኙ ማድረግ ከአንድ የአውቶብስ አሽከርካሪ የሚጠበቅ ቁልፍ የሆነ ስራ ሃላፊነት ነው፡፡

 አሽከርካሪዎች ተሳፋሪን ሲያሳፍሩና ሲያወርዱ ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ

 በጉዞ እቅድ ላይ በወጣው ሰዐትና ቦታ ላይ መድረስ፡፡
 አሽከርካሪው ተሸከርካሪውን ሙሉ በሙሉ በትክክለኛ አቋቋም ማቆም፡፡
 ተሸከርካሪው ከተተፈቀደለት የመጫን አቅም/መጠን ወይም ብዛት በላይ መጫን የለበትም፡፡
 በወጣው ዕቅድ መሰረት መንገደኞችን ለማሳፈር /ለመጫን በቅድሚያ መናኸሪያ ፌርማታ በማቆሚያ
ቦታ ቁጥር ላይ ተሸከርካሪን ለጉዞ አዘጋጅቶ ማቆም፡፡
 አረጋዊያንን፤ አካል ጉዳተኞች፤ ነፍሰ ጡሮችንና ህፃናት የያዙትን ቅድሚያ መስጠተት/ማስቀመጥ እና
በተሸከርካሪው መሀል ባሉ ወንበሮች አካባቢ እንዲቀመጡ ማድረግ፡፡
 ተሸከርካሪው እየተንቀሳቀሰ ማሳፈርም ሆነ ማውለድ ክልክል ነው፡፡
 ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ በመቆሚያ ቦታ ቆሞ በር እስኪከፈት ድረስ መንገደኞች ከመቀመጫ
ቦታቸው ላይ መነሳት እንደሌለባቸው ማሳወቅ፡፡
 ለምሳ ወይም ለመናፈስ መንገደኞች ወርደው ሲመለሱ ብዛታቸውን መቁጠር ይገባል፡፡ ምክንያቱም
የቀረ መንገደኛ ካለ ለመለየት ወይም ለማወቅ ስለሚረዳ፡፡

ተማሪዎችን በማጓጓዝ ወቅት የሚደረግ ጥንቃቄ

 ተማሪዎች ከት/ቤት ከመለቀቃቸው በፊት በማቆሚያው ስፍራ ተሸከርካሪውን ማቆም፡፡

 አሽከርካሪው ከተሸከርካሪው በሚወርድበት ጊዜ የሞተር ማስነሻና ማጥፊያ ቁልፍ ማንሳት አለበት፡፡
 አሽከርካሪው በትምህርት ቤት መግቢያና መውጫ በር ላይ በመሆን ተማሪዎች በሚሳፈሩበት ወቅት
የአገባባቸውን ሆኔታ ሂደት መቆጣጠርና ማስተካከል ይኖርበታል፡፡
 እድሜአቸው ከ 12 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት የተለያየ እንክብካቤ ማድረግ
 ተሽከርካሪን ከማንቀሳቀስ በፊት የተማሪዎች የመማሪያ መሳሪያዎችና የቀሩ ተማሪዎች ማየትና
መፈተሽ፡፡
 ተማሪዎችን ለማውረድ በተፈቀደው ቦ እና ለአደጋ በማያጋልጥ ቦታ ማውረድ እንዲሁም መንገዱን
የሚያቋርጥ ተማሪ ካለ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲያቋርጥ ማድረግ ህፃናት ከሆኑ ለተረካቢው ሰው
ወይም ወላጅ ማስረከብ ያስፈልጋል፡፡
ሀገር ጎብኚን (ቱሪስት) የሚያጓጉዝ አሽከርካሪ ማድረግ ያለበት

 የእያንዳዱ የጉዞ ዝርዝር በወጣው ዕቅድ መሰረት ተግባራዊ ማድረግ፡፡

 አብዛኛውን ጉዞ ከአንድ ቀን በላይ ስለሚወስድ የመንገዱና የአየሩ ፀባይ ባህሪ ስለሚለያይ ወይም
ስለሚቀያየር የሚከተሉትን ነገሮች በቅድሚያ ማዘጋጀት አለበት፡፡
 በቂ የሆነ ገንዘብና ነዳጅ መያዝ
 እንደ ጉብኝት አስፈላጊነት የተለያዩ እሽግ ምግቦችና ማብሰያ ዕቃዎች መያዝ፡፡
 ድንኳንና ልብሶችን መያዝ
 የተሟላ የተሸከርካሪ መጠገኛ መሳሪያዎችና በቀላሉ ሊበላሹና ሊጠገኑ የሚችሉ የተለያዩ ዕቃዎችን
መያዝ
 የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ መስጫ መያዝ
 እንዲሁም የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያ የመሳሰሉትን መያዝ ናቸው፡፡
 ጎብኚዎቹ በሚሰጡት ቀጠሮ መሰረት በትክክለኛው ቦታና ሰዓት አስቀድሞ በመድረስ በቦታው
መድረሻችንን ማሳወቅ፡፡
 የጎብኚዎች እቃን በመቀበል በአግባብ መጫንና ደህንነቱ እንዲጠበቅ ማድረግ፡፡
 ህፃናትና ነፍሰጡር የሆኑ ጎብኚዎች ከፊት መቀመጫ ወንበር ላይ አለማስቀመጥ፡፡
 የማስጎብኘት ስራ ከጎብኚዎች ጋር ለመግባባትና የሚፈለጉ ነገሮችን ወይም ሀሳቦች ለመግለፅ
እንዲቻል የተለያዩ አለም አቀፍ ቋንቋዎችን በሚገባ ማወቅ ለአሽከርካሪዎች አስፈላጊ ነው፡፡
 ጎብኚዎችን ይዞ የሚንቀሳቀስ አሽከርካሪ በሚገባ ካርታ የማንበብና የመረዳት ችሎታ ሊኖረው ይገባል
እንዲሁም የሚሄድባቸውን አካባቢዎች ሁኔታ ማወቅ አለበት፡፡

የተሳፋሪ የእቃ አጫጫን ሁኔታ

 እቃዎች የ 25 ኪግ በታች ከሆኑ እንዳማያስከፍሉ ማወቅ

 እንዳመጣጣቸው ሚዛን መመዘንና በታሪፍ ማስከፈል
 እቃው ወይ ሻንጣው ላይ ታግ ማድረግ
 እንደተሳፋሪው አውራረድ ቅደም ተከተል እቃውን መጫን
የተሳፋሪ እቃ በሚጫንበት ጊዜ የሚደረግ ጥንቃቄ

 በአንድ ላይ መጫን የሌለባቸው እቃዎች ማወቅና መለየት

 የእቃውን አያያዝና አቀማመጥ ማወቅ፡
 እቃዎች የሚቀመጡበትን ተገቢ ቦታ መለየት /ከኃላ ፣ፖርቶ መጋላ…)
 የተሳፋሪውን እቃ ከስርቆት ነፃ ሁኖ መጫኑንን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
በአንድ ላይ መጫን የሌለባቸው እቃዎች ማወቅና መለየት
የተወሰኑ ዕቃዎች በባህሪያቸውና በመጠናቸው እርስ በእርስ በሚቀመጡበት ወቅት ሊበካከሉ ሊሰባበሩ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ዕቃዎች በሚጫኑትበት ወቅት የዕቃዎችን ዓይነት በሚገባ አውቆና ለይቶ መጫን አስፈላጊ
ነው፡፡ አንድ ላይ የማይጫኑ ዕቃዎች፡-

 ጋዝና እህል ምግብ ነክ የሆነ፤ልብሶች፤ ሸቀጣ ሸቀጦች…….

 በርበሬና ስኳር/ ጨውና ቆርቆሮ /ጨውና ስኳር/ ፈሳሽ ነገሮች/ ንስሳትና ምግብ፤ ልብሶች፤
ሸቀጣሸቀጦች…ወዘተ ሲሆኑ እንደ ሁኔታው ድርጅቶች እዚህን ስራዎች በሌላ ሊያሰሩ ይችላሉ፡፡

የተሳፋሪ እቃ አወራረድ

 እንደ አጫጫኑ ቅደም ተከተል ማውረድ

 እቃዎችን በአግባቡ ማውረድ ማስረከብ፣ጊዜን፣ጭቅጭን፣ እቃ መጥፋትን ይከላከላል።

የክትትል ቅድመ ደረጃዎች

የክትትል ቅድመ ደረጃ ስንል በትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ ያሉ አካላት ሊኖራቸው ስለሚገባ የሥራ ኃላፊነት
ስለሚጠበቅ አሠራር ማለታችን ነው፡፡
1. አሽከርካሪዎች
2. ረዳቶች
3. ባለንብረቶች /ሱፐርቫይዘር/
የአሽከርካሪዎች የሥራ ኃላፊነት
 የጉዞ በፊትና በኃላ ፍተሻና ዝግጅት ማድረግ
 የተሳፋሪዎችንና እቃዎቻቸውን መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ
 ተሽከርካሪን መጠበቅ
 በተሳፋሪዎች የምሳና የእረፍት ሰዓት ማሳወቅ
 ተሳፋሪ ሲሳፈርና ሲወርድ ጥንቃቄ የተሞላበት ሁኔታ መሆኑንን ማረጋገጥ፣
 ለተሳፋሪዎች መረጃ መስጠት
 የተሳፋሪን ደህንነትና ምቾት መጠበቅ
 ተሳፋሪ ሥርአት አክብሮ እንዲጓዝ መመሪያ መስጠት
የረዳቶች የስራ ሀላፊነት
 ለተሳፋሪ የጉዞ ፕሐላን ማስተላለፍ
 ለተሳፋሪዎች መረጃ መስጠት
 የተሳፋሪ ብዛት መቁጠር
 ተሳፋሪን በማሰባሰብ ወደ ተሽከርካሪ እንዲገቡ ማድረግ
 የተሳፋሪን ደህንነት መጠበቅ መንከባከብ
የባለንብረቱ ወይም የሱፐር ቫይዘሩ ኃላፊነት
 መመሪያና ደንቦችን ማወጣት
 ስለአገልግሎት አሠጣጡ
 የሠራተኞች ቅጥር
 ሠራተኛው አፈፃፀም
 የዲስኘሊን እርምጃ አወሳሰድ
 ብቃት ያለው አሽከርካሪ መቅጠር
 ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ግባቶችን በበቂ ሁኔታ ማቅረቡ
 የሚጓዝበትን መንገድ ባህሪያት አካባቢውን የአየር ሁኔታ፣ የፀጥታ ሁኔታ፣ ከሚከተለው አካል
ማጣራት
 አደጋ በሚያናገጥምበት ጊዜ መረጃ የሚያስተላልፍባቸው አካላት ሥምና አድራሻ መዝግቦ
መያዝ፣ ፖሊስ ጣቢያ ፣ ቀይመስቀል
 ከተሳፋሪዎች የተለየ የጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች ቅድሚያ ማወቅ
 የሌሎች መሠል ማህበራትን፣ ድርጅቶችና ግለሠቦች ሥምና አድራሻ መያዝ
 የሚሄዱባቸውን ቦታዎች የማህበረሠብ ባህል ወግ እንዲሁም እምነታቸውን ጠንቅቆ ማወቅ፣
መረዳት እና የተሽከርካሪውን የቴክኒክ ብቃትና የተየረጉ ጥገናዎችን ጠንቅቆ ማወቅ
የአገልግሎት ክፍያ
የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪ በሰጠው አገልግሎት መጠን ልክ የአገልግሎት ክፍያ የማስከፈልና የመቀበል
መብት እንዳለው ሁሉ መንገደኞችም በሚከፍሉት ክፍያ ጥሩና አስተማማኝ አገልግሎት ማግኘት አለባቸው፡፡
የአገልግሎት ክፍያ እንደ ስምምነት በኮንትራት ለአንድ ጊዜ ጉዞ ወይም በመደበኛ ለአንድ ጊዜ፤ ሳምንታዊ፤
ወርሀዊ ጉዞ….ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ አሽከርካሪው አገልግሎት መስጠትና የአገልግሎት ክፍያውን ሲቀበል
ለመንገደኛው ደረሰኘ መስጠት አለበት፡፡
የከተማ አውቶብስ ትኬት አገልግሎት
 የአገልግሎት ትኬት መሰጠት ያለበት ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ክፍያ ከተከናወነ በኃላ ነው፡፡
 ትኬቱ የሚያገለግለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
 አንድ ሰው ትኬቱን ከተጠቀመ በኃላ ወደ ሌላ ሰው ትኬቱ ቢተላለፍ አገልግሎት አይሰጥም፡፡
የአገልግሎት ክፍያ ሊያስመልስ የሚችሉ ጉዳዮች
መንገደኛው የግል ጉዳይ አጋጥሞት ተሸከርካሪው ከመንቀሳቀሱ በፊት እንዲመለስለት ወይም አገልግሎት
የማይፈልግ መሆኑን ሲያሳውቅ፡፡ ተሸከርካሪው ተበላሽቶ ሲቆምና የጥገና ጊዜ ለረጅም ሰዓት የሚፈጅ
ከሆነ…ወዘተ ናቸው፡፡
የግጭት ማስወገጃ ስልቶች
ግጭት ምንድን ነው? በማንኛውም የሥራ አካባቢ በሰው ልጆች መካከል ግጭት ሊከሠት ይችላል፡፡
በትራንስፖርት ዘርፍ ግጭት ሊከሠት የሚችለው
1. የአካባቢ እውቀትን አለመጠቀም
2. ጠቃሚ መረጃን አለማሠባሠብ
3. ተሽከርካሪውን በአግባቡ አለመጠቀም
በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ
ባለንብረትና በአሽከርካሪው፣ በጫኝና አውራጅ እና ስምሪት ሠራተኞች መካከል ግጭት ሊፈጠር ይችላል
በተለይ በባለንብረት በአሽከርካሪ እና በረዳት መካከል የተፈጠረ ግጭት ካልተወሰደ በተሽከርካሪው ጤንነት ላይ
ከፍተኛ ችግር ሊፈጠር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
ግጭትን በማስወገድ
 ቸር መሆን
 መቻቻል
 ፈፃሚነት
 የጋራ ተጠቃሚነት
በስራ አካባቢ ሊኖር የሚገባ ባህሪ
 መልካም ግንኙነት ተጠያቂነትና ግልጽነት
 ቅንነትና ታማኝነትቀና አለካትና ሙያዊ ስነ ምግርን መወጣት
 አገልግሎት ሠጥቶ ማጐልበት ከክርክር ወደ ምክክር

የተሳፋሪ አያያዝ መልካም የስራ ግንኙነት

የህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት በዋነኝነት የሚሠጠው አገልግሎት ህዝብ ማጓጓዣ ነው፡፡ መንገደኞች ከቦታ ወደ ቦታ
የሚንቀሳቀሱት ለስራ ለማህበራዊ ጉዳዮች ለጉብኝት እና ለትምህርት አገልግሎት ሲሆን ጉዞው በቡድን
ወይም በግል ሌሆን ይችላል፡፡ የተጠቃሚዎችን አይነት በባህሪያቸው ወይም በስራ ፍላጎታቸው የተለያዩ ሊሆኑ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች የጉዞና የመንገደኞችን አይነት በሚገባ ማወቅ አለባቸው፡፡

1. የጉዞ አይነቶች የሚባሉት

ሀ. አጭር ጉዞ ለ. መካከለኛ ጉዞ ሐ. ረዥም ጉዞ መ. ሁሉም

2. ------- የሚባለው ከክልል ክልል እና ከሀገር ሀገር የሚደረግ ጉዞ ማለት ነው፡፡

ሀ. አጭር ጉዞ ለ. መካከለኛ ጉዞ ሐ. ረዥም ጉዞ መ. የከተማ ውስጥ ጉዞ
4. ---------- የሚባለው ከወረዳ ወረዳ የሚደረግ ጉዞ ማለት ነው፡፡
ሀ. አጭር ጉዞ ለ. መካከለኛ ጉዞ ሐ. ረዥም ጉዞ መ. በጣም ረጅም
5. ------- የሚባለው ከከተማ ከተማ ወይም ከዞንዞን የሚደረግ ጉዞ ማለት ነው፡፡
ሀ. አጭር ጉዞ ለ. መካከለኛ ጉዞ ሐ. ረዥም ጉዞ መ. በጣም ረጅም
6. --------- ከቤት ወደ ስራ ወይም ከት/ቤት ወደ ቤት…ወዘተ በአንድ ከተማ ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም
እንቅስቃሴ ማለት ነው፡፡
ሀ. አጭር ጉዞ ለ. መካከለኛ ጉዞ ሐ. ረዥም ጉዞ መ. የከተማ ውስጥ ጉዞ
7. የጥሩ የጉዞ ዕቅድ የተሳፋሪን ፍላጎት መሰረት ያደረገ፤ መንገደኛውንም ሆነ ሌሎችን ለትራፊክ አደጋ
የማያጋልጥና አጭር ጉዞ የሚያደርግበትን መስመር የያዘ መሆን አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
8. ተሳፋሪን ሲያሳፍርም ሆነ ሲወርድ መንገደኛውን ወይም ሌሎችን ለአደጋ የማያጋልጥ የመቆሚያ ስፍራ
የተመረጠ መሆን አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
9. ከሚከተሉት አንዱ የጥሩ የጉዞ ዕቅድ ውስጥ አይካተትም
ሀ. ከመነሻ እስከ መድረሻ ያለውን ርቀት በኪሎ ሜትር
ለ. በመሃል የሚገኙ ከተሞችና ታሪካዊ ስፍራዎች
ሐ. የሚፈለጉ እርዳታዎች እንዴትና ከማን እንደሚገኙ
መ. የመንገደኞችን የማሳፈሪያ ቦታና ሰዓት አለማወቅ፡
10. አሸከርካሪ ተማሪዎች ከት/ቤት ከመለቀቃቸው በፊት በማቆሚያው ስፍራ ተሸከርካሪውን ማቆም አለበት

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

11. የእያንዳዱ የጉዞ ዝርዝር በወጣው ዕቅድ መሰረት ተግባራዊ ማድረግ አለበት፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
12. ህፃናትና ነፍሰጡር የሆኑ ጎብኚዎች ከፊት መቀመጫ ወንበር ላይ መቀመጥ አለባቸው፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
13.
14. የማስጎብኘት ስራ ከጎብኚዎች ጋር ለመግባባትና የሚፈለጉ ነገሮችን ወይም ሀሳቦች ለመግለፅ እንዲቻል
የተለያዩ አለም አቀፍ ቋንቋዎችን በሚገባ ማወቅ ለአሽከርካሪዎች አስፈላጊ ነው፡፡
15. ጎብኚዎችን ይዞ የሚንቀሳቀስ አሽከርካሪ በሚገባ ካርታ የማንበብና የመረዳት ችሎታ ሊኖረው ይገባል
እንዲሁም የሚሄድባቸውን አካባቢዎች ሁኔታ ማወቅ አለበት፡፡

የተሳፋሪ የእቃ አጫጫን ሁኔታ

 እቃዎች የ 25 ኪግ በታች ከሆኑ እንዳማያስከፍሉ ማወቅ

 እንዳመጣጣቸው ሚዛን መመዘንና በታሪፍ ማስከፈል
 እቃው ወይ ሻንጣው ላይ ታግ ማድረግ
 እንደተሳፋሪው አውራረድ ቅደም ተከተል እቃውን መጫን
የተሳፋሪ እቃ በሚጫንበት ጊዜ የሚደረግ ጥንቃቄ

 በአንድ ላይ መጫን የሌለባቸው እቃዎች ማወቅና መለየት

 የእቃውን አያያዝና አቀማመጥ ማወቅ፡
 እቃዎች የሚቀመጡበትን ተገቢ ቦታ መለየት /ከኃላ ፣ፖርቶ መጋላ…)
 የተሳፋሪውን እቃ ከስርቆት ነፃ ሁኖ መጫኑንን ማረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
በአንድ ላይ መጫን የሌለባቸው እቃዎች ማወቅና መለየት

የተወሰኑ ዕቃዎች በባህሪያቸውና በመጠናቸው እርስ በእርስ በሚቀመጡበት ወቅት ሊበካከሉ ሊሰባበሩ
ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ዕቃዎች በሚጫኑትበት ወቅት የዕቃዎችን ዓይነት በሚገባ አውቆና ለይቶ መጫን አስፈላጊ
ነው፡፡ አንድ ላይ የማይጫኑ ዕቃዎች፡-

 ጋዝና እህል ምግብ ነክ የሆነ፤ልብሶች፤ ሸቀጣ ሸቀጦች…….

 በርበሬና ስኳር/ ጨውና ቆርቆሮ /ጨውና ስኳር/ ፈሳሽ ነገሮች/ ንስሳትና ምግብ፤ ልብሶች፤
ሸቀጣሸቀጦች…ወዘተ ሲሆኑ እንደ ሁኔታው ድርጅቶች እዚህን ስራዎች በሌላ ሊያሰሩ ይችላሉ፡፡

የተሳፋሪ እቃ አወራረድ

 እንደ አጫጫኑ ቅደም ተከተል ማውረድ

 እቃዎችን በአግባቡ ማውረድ ማስረከብ፣ጊዜን፣ጭቅጭን፣ እቃ መጥፋትን ይከላከላል።

የክትትል ቅድመ ደረጃዎች

የክትትል ቅድመ ደረጃ ስንል በትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ ያሉ አካላት ሊኖራቸው ስለሚገባ የሥራ ኃላፊነት
ስለሚጠበቅ አሠራር ማለታችን ነው፡፡
16. አሽከርካሪዎች
17. ረዳቶች
18. ባለንብረቶች /ሱፐርቫይዘር/
የአሽከርካሪዎች የሥራ ኃላፊነት
 የጉዞ በፊትና በኃላ ፍተሻና ዝግጅት ማድረግ
 የተሳፋሪዎችንና እቃዎቻቸውን መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ
 ተሽከርካሪን መጠበቅ
 በተሳፋሪዎች የምሳና የእረፍት ሰዓት ማሳወቅ
 ተሳፋሪ ሲሳፈርና ሲወርድ ጥንቃቄ የተሞላበት ሁኔታ መሆኑንን ማረጋገጥ፣
 ለተሳፋሪዎች መረጃ መስጠት
 የተሳፋሪን ደህንነትና ምቾት መጠበቅ
 ተሳፋሪ ሥርአት አክብሮ እንዲጓዝ መመሪያ መስጠት
የረዳቶች የስራ ሀላፊነት
 ለተሳፋሪ የጉዞ ፕሐላን ማስተላለፍ
 ለተሳፋሪዎች መረጃ መስጠት
 የተሳፋሪ ብዛት መቁጠር
 ተሳፋሪን በማሰባሰብ ወደ ተሽከርካሪ እንዲገቡ ማድረግ
 የተሳፋሪን ደህንነት መጠበቅ መንከባከብ
የባለንብረቱ ወይም የሱፐር ቫይዘሩ ኃላፊነት
 መመሪያና ደንቦችን ማወጣት
 ስለአገልግሎት አሠጣጡ
 የሠራተኞች ቅጥር
 ሠራተኛው አፈፃፀም
 የዲስኘሊን እርምጃ አወሳሰድ
 ብቃት ያለው አሽከርካሪ መቅጠር
 ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑ ግባቶችን በበቂ ሁኔታ ማቅረቡ
 የሚጓዝበትን መንገድ ባህሪያት አካባቢውን የአየር ሁኔታ፣ የፀጥታ ሁኔታ፣ ከሚከተለው አካል
ማጣራት
 አደጋ በሚያናገጥምበት ጊዜ መረጃ የሚያስተላልፍባቸው አካላት ሥምና አድራሻ መዝግቦ
መያዝ፣ ፖሊስ ጣቢያ ፣ ቀይመስቀል
 ከተሳፋሪዎች የተለየ የጤና ችግር ያለባቸውን ሰዎች ቅድሚያ ማወቅ
 የሌሎች መሠል ማህበራትን፣ ድርጅቶችና ግለሠቦች ሥምና አድራሻ መያዝ
 የሚሄዱባቸውን ቦታዎች የማህበረሠብ ባህል ወግ እንዲሁም እምነታቸውን ጠንቅቆ ማወቅ፣
መረዳት እና የተሽከርካሪውን የቴክኒክ ብቃትና የተየረጉ ጥገናዎችን ጠንቅቆ ማወቅ
የአገልግሎት ክፍያ
የህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪ በሰጠው አገልግሎት መጠን ልክ የአገልግሎት ክፍያ የማስከፈልና የመቀበል
መብት እንዳለው ሁሉ መንገደኞችም በሚከፍሉት ክፍያ ጥሩና አስተማማኝ አገልግሎት ማግኘት አለባቸው፡፡
የአገልግሎት ክፍያ እንደ ስምምነት በኮንትራት ለአንድ ጊዜ ጉዞ ወይም በመደበኛ ለአንድ ጊዜ፤ ሳምንታዊ፤
ወርሀዊ ጉዞ….ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ አሽከርካሪው አገልግሎት መስጠትና የአገልግሎት ክፍያውን ሲቀበል
ለመንገደኛው ደረሰኘ መስጠት አለበት፡፡
የከተማ አውቶብስ ትኬት አገልግሎት
 የአገልግሎት ትኬት መሰጠት ያለበት ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ክፍያ ከተከናወነ በኃላ ነው፡፡
 ትኬቱ የሚያገለግለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
 አንድ ሰው ትኬቱን ከተጠቀመ በኃላ ወደ ሌላ ሰው ትኬቱ ቢተላለፍ አገልግሎት አይሰጥም፡፡
የአገልግሎት ክፍያ ሊያስመልስ የሚችሉ ጉዳዮች
መንገደኛው የግል ጉዳይ አጋጥሞት ተሸከርካሪው ከመንቀሳቀሱ በፊት እንዲመለስለት ወይም አገልግሎት
የማይፈልግ መሆኑን ሲያሳውቅ፡፡ ተሸከርካሪው ተበላሽቶ ሲቆምና የጥገና ጊዜ ለረጅም ሰዓት የሚፈጅ
ከሆነ…ወዘተ ናቸው፡፡
የግጭት ማስወገጃ ስልቶች
ግጭት ምንድን ነው? በማንኛውም የሥራ አካባቢ በሰው ልጆች መካከል ግጭት ሊከሠት ይችላል፡፡
በትራንስፖርት ዘርፍ ግጭት ሊከሠት የሚችለው
4. የአካባቢ እውቀትን አለመጠቀም
5. ጠቃሚ መረጃን አለማሠባሠብ
6. ተሽከርካሪውን በአግባቡ አለመጠቀም
በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ
ባለንብረትና በአሽከርካሪው፣ በጫኝና አውራጅ እና ስምሪት ሠራተኞች መካከል ግጭት ሊፈጠር ይችላል
በተለይ በባለንብረት በአሽከርካሪ እና በረዳት መካከል የተፈጠረ ግጭት ካልተወሰደ በተሽከርካሪው ጤንነት ላይ
ከፍተኛ ችግር ሊፈጠር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል፡፡
ግጭትን በማስወገድ
 ቸር መሆን
 መቻቻል
 ፈፃሚነት
 የጋራ ተጠቃሚነት
በስራ አካባቢ ሊኖር የሚገባ ባህሪ
 መልካም ግንኙነት ተጠያቂነትና ግልጽነት
 ቅንነትና ታማኝነትቀና አለካትና ሙያዊ ስነ ምግርን መወጣት
 አገልግሎት ሠጥቶ ማጐልበት ከክርክር ወደ ምክክር

You might also like