You are on page 1of 9

የደረቅ ጭነት አጫጫን እና አወራረድ ስልት

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ አሽከርካሪዎች ጭነቶች ከቦታ ወደ ቦታ በሚጓጓዙበት ወቅት ስዠለጭነቱ ዓይነትና ስለ ጉዞው በቂ መረጃ ሊኖራቸው
ይገባል። በጉዞ ላይ በአሽከርካሪው፣ በተሽከርካሪው፣ በጭነቱ እና እንዱሁም በሰው ላይ አደጋ እንዳይደርስ ኃላፊነት እንዳለባቸው በቅድሚያ ማወቅ
አለባቸው፡፡

መረጃ አያያዝ

አንድ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ አሽከርካሪ ስምሪት በተሰጠው ጊዜ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን የሚገልፅ ተገቢ መረጃ በአግባቡ መያዝ
ይኖርበታል፡፡ መረጃ ለመያዝ በትንራንስፖርት ድርጅት የተዘጋጁ ፎርሞች ወይም ቅፆች መኖር አለባቸው፡፡ ለምሳሌ

መረጃ አያያዝና ሪፖርት የማድረግ ዘዴ/ቅፅ


1. ቀን…………………………………………………………………………… ..
2. የትራንስፖርት ድርጅት ስም………………………………………………….
3. መነሻ ቦታ………………………………………………………………… ...
4. መድረሻ ቦታ……………………………………………………………… ..
5. የጭነት አይነት……………………………………………………………… ..
6. መነሻ ሰዓት………………………………………………………………… ...
7. መድረሻ ሰአት……………………………………………………………… ..
8. የጭነት አይነት……………………………………………………………… ..
9. አጠቃላይ ርቀት በኪ.ሜትር…………………………………………………………… ..
10. የተቀዳው የነዳጅ መጠን………………………………………………………
11. የተበላሸ የተሽከርካሪ አካል ………………………………………………….
ሀ/ የተስተካከለ ለ. ያልተስተካከለ
………………………….. …………………….
………………………… ……………………….
12. መረጃ ቦታ ለመድረስ ከዘገየ ምክንያት………………………….....………………………………….
………………………………………………………………..……………………………………………
13. የትራፊክ አደጋ ካጋጠመ የአደጋው አይነት እና ምክንያት
………………………………………………………………………………………………..
……………………………………………………………………………………..
………………………………………………………..
14. የተወሰደ መፍትሔ………………………………………………….
15. አጠቃላይ የጉዞ እይታ/አተያየት----------------------------------------------------------------------------
16. የተሽከርካሪው የሠሌዳ ቁጥር……………………………………….
17. የአሽከርካሪው ሙሉ ስም…………………………………………..
ፊርማ……………………………………..
ደረቅ ጭነት ዓይነት እና ባህሪያት

አደገኛ ጭነቶች

አደገኛ ጭነት ማለት በተሽከርካሪ ወይም በሰው የሚጓጓዝ ሆኖ የታመቀ ጋዝ፣ አሲድ፣ ቅባት ነክ ንጠረ ነገር፣ ተቀጣጣይ ንጥረ ነገርና
የመሳሰለት ለጤና፣ ለደህንነትና ለንብረት አደገኛ የሆኑ ነገሮችን የሚያካትቱ ሆኖ የሚከተሉት ባህሪያት ይኖራቸል፡፡

 የሚፈነዱ አርጏዠጎን፣ ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ፣ አሞኒያ፣ ሄልየምያም፣ በብረት ሲሉንደር ውስጥ ታምቀው የሚጓጓዙ ንጥረ
ነገሮችን ወዘተ ያጠቃልላል፡፡
 ተቀጣጣይ ንጥረ ነገሮች ወይም ጋዝ ከ 230C /730F/ በታች በሆነ ሙቀት መቀጣጠል የሚችሉ የኬሚካሎች ውህደት ወይም
ድብልቅ ሲሆኑ ክብሪቶች፣ ፊውዞች፣ ናፌዠፍጣ፣ የላይተር ጋዝ፣ የባትሪ አሲድ ወዘተ የሚያጠቃልል ነው፡፡
 መርዛማ፡- በጣም ጥቂት መጠን ያለው ንጥረ ነገር በሰው ወይም በልላ አካል ላይ ጉዳት የሚያስከትል ማንኛውም ንጥረ ነገር
ሲሆን እንደ ተባይ ማጥፊያ፣ የአረም መዴዠድሀኒት ወዘተ. የሚቀጣጠል ይሆናል፡፡
 አሲዴ ወይም ዝገት ነክ ንጥረ ነገሮችን የሃይድሮጅን ውህድ ያለበት ፈሳሽ ኬሚካል ሆኖ የአሲድነት ልኬቱ ከሰባት ፒኤች
(PH) ያነሰ ማናቸውም ንጥረ ነገር እንደ ኃይዴሮክልሪክ አሲድ፣ የባትሪ አሲድ ወዘተ. የሚያካትት ነው፡፡

አደገኛ ለሆኑት የጭነት ዓይነቶች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ

አደገኛ ዕቃዎች ሲጫኑና ሲወርዱ እንዱሁም በጉዞ ወቅት የሚከተለትን ጥንቃቄዎች ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡

 ሲጫኑ የተሽከርካሪው የእጅ ፍሬን መያዝና እንዲይንሸራተት ከፉዠፊትና ከኃላ ታኮ ማድረግ


 እቃው ከመጫኑ ወይም ከመውረዱ በፊት የተሽከርካሪ ሞተር ማጥፋት
 የእሳት ማጥፉያ መሳሪያ መኖሩን አስቀድሞ ማረጋገጥ
 ብዙ አደገኛ ነገሮች ለሙቀት ከተጋለጡ የአደገኛነታቸው ሃይል ስለሚጨምር ከሙቀት ምንጭ ራቅ ባለ ቦታ ሊዠላይ መጫን
 እየተጫነ እያለ የፈሳሽ ምልክት መኖር እና አለመኖሩን በእይታ ማረጋገጥ
 በጉዞ ጊዜ እንዲይንቀሳቀሱ በደንብ መደገፍ
 በአካባቢው ማጨስ ክልክል መሆኑን የሚገልፅ መኖር
 በአካባቢው እሳት እና እሳትን የሚያስነሱ ቁሳቁስ አለመኖሩን ማረጋገጥ
 ጭነቱን ሊጎዱ የሚችሌዠሉ ማንኛውም ሹል ወይም ስለታማ ነገር በጭነቱ አካባቢ መኖር የለበትም
 የጭነቱን ሁኔታ የሚገልጽ በተሽከርካሪውና በዕቃው ላይ መለጠፍ አለበት
 ጭነቱ ሲጫንም ሆነ ሲወርድ በጥንቃቄ ማረፍ አለበት
 መጠናቸው ከተፈቀደው በታች የሆነ በተለይም ፈሳሽ ንጥረ ነገሮችን አለማጓጓዝ
 ከምግብና ምግብ ነክ ጭነቶች ጋር አደገኛ ዕቃዎች መጫን የለባቸውም
 እሳትና ውሃ መቋቋም በሚችል መሸፈኛ ካልተሸፈነ በስተቀር በአደገኛ ዕቃዎች መካከል ምንም ዓይነት ሌላ ጭነት ሊኖር
አይገባም
 ለማጓጓዝ ልዩ ፈቃዴ የሚያስፈልጋቸው አደገኛ ጭነቶች አሽከርካሪዎች አስቀድሞ ፈቃዴ ማግኘት ይኖርባቸዋል።

ጥቅል (ጅምላ) ጭነቶች

ጥቅል ወይም ጅምላ ጭነት የሚባለ ያልታሸጉ ሆኖ በብዛት የሚጓጓዙ የጭነት አይነቶች የሚያጠቃልል ነው፡፡ ለአብነትም ከደረቅ ጭነት
እንደ ከሰሌ፣ ጥራጥሬ፣ የዘር ማዲዠዳበሪያ፣ ከፈሳሽ ዘይት፣ ቅባት ወዘተ ከጋዝ ዓይነት ኦክስጅን፣ ናይትሮጅን ወዘተ ያጠቃልላል፡፡
እነዚህን ጭነቶች የሚያጓጉዙ አሽከርካሪዎች ስለነዚህ ጭነት ዓይነቶች ባህሪያት በቂ እውቀት ሉዠሊኖራቸው ይገባል፡፡ ጥቅል ጭነቶች
ያልታሸጉ ከመሆናቸውና በመጠንም ከፍተኛ ከመሆናቸው የተነሳ በጉዞ ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተደረገላቸው በቀላሉ ለአደጋ
ሊያጋልጡ ይችላሉ፡ አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩና በጉዞ ወቅት የተጫኑት ጭነቶች ያለበትን ሁኔታ መከታተልና መስተካከል ያለበት
ነገር ካለ በወቅቱ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

የታሸጉ እና በኮንቴነር የተቀመጡ ጭነቶች


በኮንቴነር የተቀመጡ ጭነቶች አብዛኛውን ጊዜ በባቡር ወይም በመርከብ የሚጓጓዙ ቢሆንም ከወደብ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍልች
በመኪና ሊጓጓዙ ይችላሉ፡፡ እነዚህ በኮንቴነር የሚጫኑ ጭነቶች ኮንቴይነሩ የራሱ መሣሪያ ካብ ወይም ልዩ የሆነ መቆለፊያ ክፍል
ስላላቸው በጉዞ ወቅት እንዲይወድቁ በትክክል መታሰራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡ ፡ ስለሆነም ማንኛውም አሽከርካሪ እነዚህን የጭነት
ዓይነቶች በሚያጓጎዝበት ወቅት ጉዞ ከመጀመሩና በጉዞ ወቅት የመንሸራተት ወይም የመላላት ምልክት የሚታይበት ከሆነ ተሽከርካሪውን
አቁሞ የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ ነገር ግን ከአሽከርካሪው አቅም በላይ ሆኖ ከታየው ተሽከርካሪውን ባለበት ቦታ አቁሞ
ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ አለበት፡፡

እንስሳትን ስለማጓጓዝ

አንደ አሽከርካሪ እንስሳትን እንዲያጓጉዝ የስምሪት ትዕዛዝ ሲደርሰው የሚከተለት ነገሮች መሟላታቸውን ማረጋገጥ አለበት፡፡

 እንስሳትን ለመጫንና ለማውረዴ የሚያመች የተዘጋጀ ቦታ መኖሩን


 ከመነሻ እስከ መጨረሻ የሚያገለግል ለእንስሳት በቂ የሆነ የውሃና የምግብ ዝግጅት መኖሩን ማረጋገጥ
 እንስሳቱ የተጫኑበት የተሽከርካሪው አካል እንዳያንሸራትት የተጎዘጎዘ ሣር መኖሩን ማረጋገጥ
 ተሽከርካሪው መጫን ከሚችለው እንስሳት መጠን በላይ አለመጫኑን ማረጋገጥ ወዘተ. ሲሆን እነዚህ የተጠቀሱት
ነገሮች ከተሟለ በኋላ የትራንስፕርት ድርጅት ወይም ባለሀብት ወይም ተሽከርካሪን የሚያንቀሳቅሰው አሽከርካሪ
እንስሳት ለማጓጓዝ ተግባር ብቻ የሚውል ከሆነ የተሽከርካሪውን የቴክኒክ አቋም መፈተሽ በቂ ይሆናል፡፡ ነገር ግን በለየ
ምክንያት በደረቅ ጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንዲያጓጉዝ ከተፈለገ እንስሳቱን ከመውደቅ የሚከላክል ጊዜያዊ አጥር
በተሽከርካሪው አካል ላይ ማሰራት ያስስፈልጋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጉዞ ወቅት በተጫኑት እንስሳት ላይ ጉዳት
እንዳይደርስ በተፈቀደ ፌዠፍጥነት ማሽከርከር አለበት፡፡
ከልክ (ከመጠን) በሊይ የሆነ ጭነት ስለመጫን

ከልክ በላይ የሆኑ ግዙፍ የጭነት አይነቶችን ለማጓጓዝ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋሌ፡፡ በተለይም ጠመዝማዛና አጭር መታጠፊያ የሚበዛበት መንገድ ላይ
ጭነቶቹ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ሊንሸራተቱ ስለሚችሉ ፌጥነትን በመቀነስና ጥንቃቄ በተሟላ መልኩ ማሽከርከር ያስፈልጋል፡፡ ርዝመቱ፣ ስፊዠፋቱ፣
ከፍታውና ክብደቱ ከልክ በላይ የሆነውን ጭነት ለማጓጓዝ ሌዩ የመጓጓዣ ፈቃዴ መኖር እንዳለበት አሽከርካሪዎቹ ማወቅ የሚገባቸው ሲሆን
የማጓጓዝ ሂደቱም ሁሌጊዜ በሰዓት የተወሰነ መሆን አለበት፡፡ ጭነቱ ከመጠን በላይ መሆኑን የሚገልፅ ምልክት ማለትም ብሌዠሌጭ ብልጭ የሚል
መብራት ወይም የሚውለበለብ ባንዱዠዲራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዴ ጭነቶች ደግሞ በፖሊስ ታጅቦ ወይም ከፊት ለፊት እየተጓዙ
ምልክት የሚሰጥ ተሽከርካሪ የሚያስፈልግበት ጊዜ መኖሩን ግምት ውስጥ በማስገባት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ያስፈልጋል፡፡

ልዩ ምክት የሚያስስፈልጋቸው ጭነቶች

አንደ የደረቅ ጭነት አሽከርካሪ ከቦታ ወደ ቦታ ስለሚያጓጉዘው የጭነት አይነት ማወቅ አለበት፡፡ አንዳንዴ የጭነት አይነቶች ላይ ሊደርስ ከሚችለውና
ጭነቱ ሊያርርስ ከሚችለው አደጋ ለመከላከል ጭነቱ በካርቶንና በኮንቴነር ሊታሸጉ የሚችሉበት ሁኔታ ያለ ሲሆን ጭነቶችን በቀላሉ ለይተው
በመረዳት ሊደረግላቸው የሚገባውን ጥንቃቄ ለመውሰዴ የጭነቱን ምንነት የሚገልፅ ዕቃው በታሸገበት ካርቶን ላይ ልዩ ምልክት እንዲለጠፍ
ይደረጋል፡፡ ለአብነትም ሁሌጊዜ በካርቶን ላይ የሚታዩ ምስልችና ትርጉማቸው ቀጥሎሎ ቀርቧል፡፡

የጭነት አቀማመጥ ቀስቱ ወዲሇበት አቅጣጫ መሆን አሇበት

ጭነቱ በቀላሉ የሚሰበር ነው

ጭነቱ በዝናብ የሚበሊሽ ነው


ጭነቱ ላይ ተደራቢ ጭነት መኖር እንደሌለበት

አሽከርካሪዎች ከቦታ ወደ ቦታ የሚያጓጉዙትን ጭነቶች በተለይም የታሸጉ ጭነቶችን የሚገልፅ ምልክት መኖሩንና ትርጉማቸውን በደንብ
ተረድተው ለጭነቱ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው፡፡

የማውረጃ እና የመጫኛ መሳሪያ የሚያስፈልጉ ጭነቶች


በሰው ጉሌበት ለመጫንም ሆነ ለማውረዴ ከባድ የሆኑ የጭነት ዓይነቶች በክሬን፣ ፎርክ ሊፍት እና በመሳሰሉት መሳሪያዎች በመጠቀም
ጭነቱን መጫን ወይም ማውረድ ያስፈልጋል። ነገር ግን እነዚህን መሣሪያዎች በምንጠቀምበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ ካልተደረገ
በንብረትና በሰው ላይ ያልተጠበቀ አደጋ ሊደርስ ስለሚችል አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

 መሳሪያው ጭነቱን ለማውረዴ ወይም ለመጫን ብቃት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ


 የመሳሪያው ኦፔሬተር ስለመሳሪያውም ሆነ ስለጭነቱ አጫጫን ሁኔታ በቂ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል
 ጭነቱን ለማንሳት የሚያገለግለ እንደ ካቦ፣ ገመድና ሰንሰለት የመሳሰለትን ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ
 ጭነቱን ለመጫንም ሆነ ለማውረዴ የሚያስችል ሰፊና አመቺ ቦታ መኖሩን ማየት
 ጭነቱ በሚጫንበትም ሆነ በሚወርድበት ወቅት ሰዎች ከአካባቢው እንዱርቁ ማድረግ
 የመሳሪያው ኦፔሬተር ጭነቱን ከመጫኑና ከማውረድ በፊት ጭነቱ በመሳሪያው በትክክሌ መያዙን በቅድሚያ ማረጋገጥ

ቅድመ ጭነት ምርመራ እና ሰነዶችን ማሟላት

በደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ላይ የሚጫነውን ጭነት አስቀድሞ መመርመር በአንደ ሀገር ህግ መሰረት ለየተሽከርካሪው የሚፈቀድ
አጠቃላይ የጭነት ከፍታ፣ ስፋትና ርዝመትን በጠበቀ መልኩ ጭነቱ የተጫነ መሆኑን ለማረጋገጥ ይረዳል፡፡ ይህም እንደየ ተሽከረካሪው
ዓይነት ተሽከርካሪው ከነጭነቱ የሚኖረውን አጠቃላይ የጎን ስፋት፣ ከመሬት ወደ ላይ እስከ ጭነቱ የሚኖረውን ከፍታና አጠቃላይ ከፍትና
ከኋላ ያለው የጭነቱ ርዝመት በተፈቀደው ከፍታ፣ ስፋትና ርዝመት መሰረት መሆኑን ማረጋገጥ የአሽከርካሪው ኃላፉነት ስለሆነ የደረቅ
ጭነት ተሽከርካሪን የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በሚጓዙበት የመንገድ ስፋት፣ የመሿለኪያ ድልድይ ከፍታና ኩርባ መንገዳችን ባገናዘበ
መልኩ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

የጭነት ክብደት እና መጠን ማገናዘብ

አንድ ተሽከርካሪ መጫን ያለበትን የጭነት ክብደትና መጠን በአንድ ሀገር ህጋዊ ስልጣን ባለው አካሌ ወይም መ/ቤት አማካኝነት
የተሽከርካሪውን ክብደት ለመወሰን ታሳቢ የሚያደርጉ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ተሽከርካሪው ምን ያህል ጭነት መጫን
እንደሚችል የሚሰጥ ፈቃድ ሲሆን ይህም የተሽከርካሪውን የመጫን ሁኔታ የሚያመለክት ነው፡፡ አንድ የጭነት ተሽከርካሪ የሚጭነውን
ጭነት አስቀዴዠድሞ ማወቅ የሚከተለውን ጥቅም ይኖረዋሌ፡፡

 የተሽከርካሪውን ደህንነት ይጠብቃል


 የመንገዶችና የድልድዮችን ደህንነት ይጠብቃል
 ከአቅም በላይ በመጫኑ የሚያስከትለውን የትራፉክ አዯጋ ይቀንሳሌ
 ከሚዛን ተቆጣጣሪ ሠራተኞች ጋር ከሚደረገው አላስፈላጊ ጭቅጭቅና የጊዜ መባከን ያስቀራል
ከመጠን በሊዘላይ በመጫኑ ምክንያት በንብረትና በሰው ላይ ሊደስ የሚችለውን አደጋ ይቀንሳል..ስለሆነም አሽከርካሪዎች ጭነት ሲጭኑ
እንደተገኘ መጫን ሳይሆን ህግን መሰረት ባደረገ መልኩና የያዙት ተሽከርካሪ የመጫን አቅሙን ግምት ውስጥ በማስገባት በመጫን ከመጠን
በላይ በሆነ ክብደት ምክንያት በንብረት፣ በሰውና በመንገዶች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት የመከላከል ኃላፊነት እንዳለባቸው
አስቀዴዠድሞ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
የጭነት አቅጣጫ ቅደም ተከተል እና አደራደር

በተሽከርካሪ ላይ የሚጫን ጭነት በሁለም የተሽከርካሪ አክስሎች ላይ እኩሌ እንዳሰራጭ ካልተደረገ በጉዞ ወቅት በተሽከርካሪው መሪና
ተሸካሚ እንዱሁም የፍሬን ክፍሎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከማሳደር በላይ በእነዚህ የተሽከርካሪ ክፍሎች ሊዠላይ በሚፈጠር ጫና የተነሳ
ተሽከርካሪውን ለአደጋ የማጋለጥ እድለ የሰፊ ነው፡፡ ስለሆነም በተሽከርካሪ ላይ የሚጫንን ዕቃ በሁለም አክስሎች ላይ እኩል በሚያርፍበት
መልኩ ማሰራጨትና ጭነቱ ሲጫን ከታች ከመጫኛ ወለሉ አንስቶ ወደ ላይ ወደ መሀል አስተካክሎ መጫን ሊከሰት የሚችለውን አደጋ
ለመከሊከል ከመርዳቱም በላይ አስተማማኝ ጉዞ ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡ የተለያየ ባህሪ መጠንና ክብደት ያላቸው ጭነቶች
በአንዴ ተሽከርካሪ አንድ ላይ መጫን የማይፈቀድ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች የሚጫንበት አጋጣሚ የሚኖር ከሆነ እንዴት እና በምን
አሽከርካሪዎች አስቀድሞ የሚጭኑትን የጭነት ባህሪ ክብደት እና መጠን ለይቶ በማወቅ እንደጭነቱ ባህሪ ጥንቃቄ በተሟላ መልኩ ተገቢ
ቦታ ላይ መጫን አለባቸው፡፡ለምሳላ አንደ የጭነት ዓይነት ውስጥ ብረት፣ ዘይት፣ ጨው፣ ፓስታ ወዘተ. ቢኖር አሽከርካሪዎች መጀመሪያ
ብረት፣ ቀጥል ዘይትን፣ ጨው፣ ፓስታ ከታች ወደ ላይ በቅደም ተከተል እየደረደሩ መጫን አለባቸው፡፡

የጭነት ክብደትን ማመጣጠን


አሽከርካሪዎች ጭነት በሚያገኙበት ጊዜ በተሽከርካሪ ላይ እንዴት ጭነው ማጓጓዝ እንደሚገባቸው አስቀድሞ መደረግ ያለበትን ቅደም
ተከተል ማወቅና ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ጭነቶች በዓይነት፣ በመጠን፣ በክብደትና በባህሪያቸው የተለያዩ በመሆናቸው ግንዛቤ ውስጥ
በማስገባት የተሽከርካሪ የመጫን አቅምና ቦታ እንዳለው በቅድሚያ በቂ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በመሆኑም አሽከርካሪዎች ጭነትን
በተሽከርካሪ ላይ ሲጭኑ የሚከተለትን ሁኔታዎች መከተል አለባቸው፡፡

 ጭነቱ የሚጓጓዝበት የመንገድ ሁኔታ ማወቅ


 የተሽከርካሪ የመጫን አቅምና የቴክኒክ አቋም መፈተሽ
 ጭነቱ በቀላሉ የሚበላሽና የሚሰበር መሆኑንና አለመሆኑን ማረጋገጥ
 ለስራ የሚያስፈልጉ የደህንነት መሳሪያዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ
 ጭነቱ ያለበትን ስፍራ በማወቅ የመንገድ ሁኔታውን ማመቻቸት
 ጭነቱ በሚጫንበት ወቅት ተሽከርካሪውን አስተካክሎ ደልዳላ ቦታ ላይ ማቆም
 ጭነቶች የተለያየ መጠን፣ ዓይነትና ክብደት ያላቸው ከሆነ የአቅጣጫቸውን ቅደም ተከተል መለየት
 ጭነቱ ከመሬት የሚያነሰ የመሳሪያ ዓይነት ወይም የሰው ጉልበት መሁኑን ለይቶ ማወቅ
 ጭነቱ በተሽከርካሪ አካላ ላይ ቀስ በቀስ እንዲያርፍ በማድረግ ማደላደል
 ከተጫነ በኃላ እንዳይነቃነቅ በማድረግ ማሰርና ከፀሀይ ወይም ከዝናብ ለመከላከል በሸራ መሸፈን
ጭነት ለመጫን ወይም ለማራገፍ ተሽከርካሪን ማዘጋጀት

ቦታውን መቃኘት - ጭነት በሚወርድበት ወይም በሚራገፍበት ጊዜ አሽከርካሪዎች የደንበኛ መጋዘን ያለበትን ሁኔታ ማጥናት ይኖርባቸዋል፡፡ እቃው
የሚራገፍበት ወይም የሚጫንበት መጋዘን አስተማማኝ መግቢያና መውጫ መንገድ መኖሩን፣ ተሽከርካሪውን ለማንቀሳቀስ በቂ ስፍራ መኖሩን፣
የሚወርደውን ጭነት መጋዘኑ የሚበቃው መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ አሽከርካሪዎች ጭነት ከመጫናቸው ወይም ከማራገፋቸው በፊት
በቅዴዠድሚያ ሊያከናውኑት የሚገባ ተግባር ጭነቱ የሚጫንበትን ወይም የሚራገፍበትን ቦታ በመቃኘት የቦታውን ምቹነት ቀጥሎ በተቀመጠው
ነጥቦች አንፃር በማከናወን ያለአግባብ ሊጠፋ የሚችለውን ጊዜ እና ጉሌበት በእጅጉ ሊቆጥብ ይችላል፡፡

የከፍታ ውንነነት፡- ተሽከርካሪውን ከነጭነቱ የሚያስወጣ ወይም የሚራገፍበት ቦታ ተሽከርካሪውን ከነጭነቱ ሊያስገባ የሚችል ከፍታ እንዲሁው
ማረጋገጥ፣

የመሬቱ ምቹነት፡- ቦታው የተደለደለና ተሽከርካሪው ከነጭነቱ በሚያርፍበት ጊዜ ሳይናድ ወይም ሳይሰምጥና ልላያልተፈለገ ችግር ሳያስከትል
መሸከም የሚችል ስለመሆኑ ማረጋገጥ

ሰፉ ቦታ፡- ተሽከርካሪው ጭነቱን እንደጫነ ገብቶና ጭነቱን አራግፍ ያለምንም ችግር ዞሮ ለመውጣት እንዱሁም ወደ ፊትና ወደ ኋላ ማንቀሳቀስ
የሚያስችል ሰፊ ቦታ እንዳለው ማረጋገጥ፣
እሳት የማያስከትል መሆኑን፡- በተለያየ ምክንያት ጭነቱ በሚጫንበት ወይም በሚራገፍበት ጊዜ እሳት እንዲፈጠር ሊያደርጉ የሚችሉ ተቀጣጣይ
ነገሮች በአካባቢው ላይ አለመኖራቸውን አስቀድሞ ማረጋገጥ ይገባል፡፡

ተገቢ የማስረከቢያ ሰነድችና ስርዓትን መከተሌ

አንድ አሽከርካሪ የጫነውን ጭነት የደንበኛ ማራገፊያ ቦታ አድርሶ የማራገፍ ሂደት እንተጠናቀቀ ጭነቱን በዓይነት፣ በመለያ ቁጥር፣
በመጠን ወዘተ. እንደየጭነቱ አይነት በመለየት፣ በመቁጠር እና በመቆጣጠር ተገቢ የጭነት ማሰረከቢያ ሰነድ ወይም ፎርማት በመጠቀም
የጫነውን ጭነት ለደንበኛው ማስረከብ አለበት፡፡ ጭነት በሚጫንበት፣ በጉዞ እንዱሁም በሚራገፍበት ወቅት በተለያየ ምክንያት ብልሽት
ወይም ጉዲዠዳት ሊያጋጥም ስለሚችል አሽከርካሪዎች ጉዳት ወይም ብልሽት የደረሰባቸውን ጭነቶች ብዛታቸውን በመለያ ቁጥራቸው
ወይም በስማቸው ከነጉዳት መጠናቸው በመለየት መመዝገብና ማስረከብ ከደንበኛ ጋር ሊኖር የሚችለውን አለመተማመን የሚያስወግድ
በመሆኑ አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ መውሰድ አለባቸው፡፡ የማስረከቢያ ሰነድ በፍርማቱ መሰረት ተሞሌቶ እንዯተጠናቀቀ
የአሽከርካሪው እና የዯንበኛው ፉርማ በሰነደ ሊይ መኖሩ በሁሇቱም ወገን መካከሌዠል የመተማመን ደረጃ የሚጨምር ከመሆኑም በላይ
ሰነደን ህጋዊ የሚያደርግ ስለሆነ ሁለቱም ወገኖች ፊማቸውን በሰነደ ላይ ማኖር አለባቸው፡፡

ድንገተኛ አደጋ መከላከያ እና የጥንቃቄ ስርዓቶች

በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ውስጥ ጭነት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሲጓጓዝ ተገቢውን ጥንቃቄ ካልተደረገ የመበላሻት
እና አደጋ የማስከተል እድል የሰፊ ነው፡ ፡ ስለሆነም በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ አሽከርካሪዎች ጭነትን በመጫን፣ በማጓጓዝና በማራገፍ
ወቅት ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃዎችና ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን የመከላከል ስልት ሊተገበሩ ይገባል፡፡

በጭነት ወቅት መወሰዴ ያሇበት ጥንቃቄ

 የተሽከርካሪውን ሞተር ማጥፊትና የእጅ ፍሬኑን በአግባቡ መያዙን ማረጋገጥ እና ታኮ ማድረግ


 በአካባቢው የእሳት ምንጭ ሊሆን የሚችሉ ነገር አለመኖሩን ማረጋገጥ
 ጭነቱ በደንብ የታሸገና በአግባቡ የተከደነ መሆኑን ማረጋገጥ
 ጭነቱ አደገኛ ጭነት ከሆነ ስለ አደገኛነቱ የሚገልጽ መግለጫ በግልጽ ቦታ ላይ መለጠፈን ማረጋገጥ
 የሚጫነው ጭነት ለተሽከርካሪው ከተፈቀደው የጭነት መጠን በላይ አለመሆኑን አስቀድሞ ማረጋገጥ
 ጭነቱ አደገኛ ጭነት ከሆነ በጭነቱ ዙሪያ ፈሳሽ አለመኖሩን ማረጋገጥ
 ጭነቱ በምንና እንዴት እንደሚጫን መረዳትና በዚያ መሰረት በጥንቃቄ እንዲጭን ማድረግ
 ጭነቱ ሳይንከባለል ወይም ሳይጋጭ በጥንቃቄ መጫን
 አደገኛ ጭነት ከሆነ ከሙቀት አካባቢ አርቆ መጫን
 ጭነቱ ሲጫን በስርዓቱ መደርደርር ና ክፍተት ሳይፈጠር አጠጋግቶ መጫን
 የጭነቱን ዓይነት መለየትና በአንድ ላይ የማይጫኑ ጭነቶችን አራርቆ መጫን ወይም አንደ ከተጫነ በኋላ ሸፍኖ ሌላውን ደግሞ በላይ
መጫን
 የተሽከርካሪውን የቴክኒክ ሁኔታ ማረጋገጥ
 ጭነቱ ሲጫን በመቆጣጠር እንዲጫን የተፈቀደው መሆኑን በመረከቢያ ቅጹ ሊይ አረጋግጦ መረከብና መፈረም
 በተሽከርካሪው ውስጥ ለጭነቱና ለተሽከርካሪው የእሳት ማጥፉያ መኖሩን አስቀድሞ ማረጋገጥ
 ጭነቱ ሲጫን ከበድ ያለንና በቀላሉ የማይሰበሩትን ከስር አድርጎ ቀለል ያለንና በቀላሉ የሚበላሹ ወይም የሚሰበሩትን ጭነቶች ከሊዠላይ
መጫን
 ጭነቱ ሲጫን በመጫኛ ቦታው ላይ በአግባቡ መቀመጡንና ጭነቱን በሁለም ጎማዎች እኩል መሰራጨቱን ማረጋገጥ
 የተጫነው ጭነት በፀሀይ እና በዝናብ እንዳይጠቃ እንዱሁም ጭነቱ ከተሽከርካሪው ላይ እንዲይወድቅ በሸራ መሸፈንና ማሰር

በጉዞ ወቅት መወሰድ ያለበት ጥንቃቄ

1. አሽከርካሪው ጭነት መጨኑን ተገንዝቦ በተፈቀደ የፌጥነት ገደብ ጥንቃቄ በተሞላ ሁኔታማሽከርከር
2. ነዳጅ ለመሙላት ካልሆነ በስተቀር ከመኖሪያ ቤት፣ ከድልድይ፣ እሳት ካለበት እና ሰው ከተሰበሰበበት አካባቢ ተሽከርካሪውን
አርቆ ማቆም
3. ተቀጣጣይ ጭነትን የጫነ ተሽከርካሪ በመንገድ ላይ ሲቆም ከተሽከርካሪው ከፊትና ከኃላ ባለሶስት ማዕዘን አንጸባራቂ ምልክት
ማስቀመጥ
4. መንገዱ የተጫነውን ጭነት ለመጓጓዝ የተፈቀደ መሆኑን ማረጋገጥ
5. በጉዞ ወቅት በየሁለት ሰዓቱ ልዩነት የተሽከርካሪውን ጎማ እና የጭነቱን ሁኔታ መፈተሽ
6. በጭነቱ ላይ ተገቢውን የማስጠንቀቂያ ምልክት ማሳየት
7. አደገኛ ጭነት በጫነ ተሽከርካሪ አቅራቢያ በ 25 ጫማ ክልል ውስጥ ሲጋራ አለማጨስ

ጭነት በሚራገፌበት ወቅት መወሰድ ያለበት ጥንቃቄ

 ተሽከርካሪውን በጥንቃቄ ወደ ማራገፊያያ ቦታ ማስጠጋት


 ጭነቱ የሚራገፍበት ቦታ ለማራፍ ምቹ መሆኑንና በሚራገፍበት ወቅት ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮች በአካባቢው አለመኖራቸውን ማረጋገጥ
 የተሽከርካሪውን ሞተር ማጥፋትና የእጅ ፍሬን ይዞ ታኮ ማድረግ
 ጭነቱን የተሸፈነበትን ሸራ በመፍታት ጭነቱን በጥንቃቄ እንደአጫጫኑ ቅደም ተከተልና የአጫጫን ስርዓት መሰረት በጥንቃቄ ማውረድ
 ጭነቱን በተዘጋጀለት ቦታ ላይ በአግባቡ ማስቀመጥ
 ጭነቱ ተራግፍ ሲያልቅ በተሽከርካሪው የመጫኛ ክፍል ላይ ፈሳሽ ካለ ማጽዳት
 ጭነቱን ቆጥሮ ለተረካቢ ክፍል በማሰረከብ ማረጋገጫ መቀበል
 ተሽከርካሪውን ለቀጣይ ስራ ዝግጁ እንዲሆን የተበላሹ ወይም የሚጠገኑ ክፍሎች ካለ መፈተሽና ለሚመለከተው አካል ሪፕርት ማድረግ

1. የደረቅ ጭነት ማመላለሻ አሽከርካሪዎች ጭነቶች ከቦታ ወደ ቦታ በሚጓጓዙበት ወቅት ለጭነቱ ዓይነትና ስለ ጉዞው በቂ መረጃ ሊኖራቸው
ይገባል።
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
2. አንድ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ አሽከርካሪ ስምሪት በተሰጠው ጊዜ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴውን የሚገልፅ ተገቢ መረጃ በአግባቡ መያዝ
አይጠበቅብኝም፡፡
ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
3. አደገኛ ጭነት ማለት በተሽከርካሪ ወይም በሰው የሚጓጓዝ ሆኖ የታመቀ ጋዝ፣ አሲድ፣ ቅባት ነክ ንጠረ ነገር፣ ተቀጣጣይ ንጥረ ነገርና
የመሳሰለት ለጤና፣ ለደህንነትና ለንብረት አደገኛ የሆኑ ነገሮችን ያካትታል፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
4. ተቀጣጣይ ንጥረ ነገሮች ወይም ጋዝ ከ 230C /730F/ በታች በሆነ ሙቀት መቀጣጠል የሚችሉ የኬሚካሎች ውህደት ወይም ድብልቅ
ሲሆኑ ክብሪቶች፣ ፊውዞች፣ ናፌዠፍጣ፣ የላይተር ጋዝ፣ የባትሪ አሲድ ወዘተ የሚያጠቃልል ነው፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

5. አሲዴ ወይም ዝገት ነክ ንጥረ ነገሮችን የሃይድሮጅን ውህድ ያለበት ፈሳሽ ኬሚካል ሆኖ የአሲድነት ልኬቱ ከሰባት ፒኤች (PH) ያነሰ
ማናቸውም ንጥረ ነገር እንደ ኃይዴሮክልሪክ አሲድ፣ የባትሪ አሲድ ወዘተ. የሚያካትት ነው፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

6. አደገኛ ዕቃዎች ሲጫኑና ሲወርዱ እንዱሁም በጉዞ ወቅት የሚከተለትን ጥንቃቄዎች ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡

ሀ. ሲጫኑ የተሽከርካሪው የእጅ ፍሬን መያዝና እንዲይንሸራተት ከፉዠፊትና ከኃላ ታኮ ማድረግ


ለ. እቃው ከመጫኑ ወይም ከመውረዱ በፊት የተሽከርካሪ ሞተር ማጥፋት
ሐ. የእሳት ማጥፉያ መሳሪያ መኖሩን አስቀድሞ ማረጋገጥ
መ. ሁሉም መልስ ናቸው

7. ከሚከተሉት አንደ አሽከርካሪ እንስሳትን እንዲያጓጉዝ የስምሪት ትዕዛዝ ሲደርሰው የሚከተለት አንዱ ማሟላት አይጠበቅበትም፡፡

ሀ. እንስሳትን ለመጫንና ለማውረዴ የሚያመች የተዘጋጀ ቦታ መኖሩን ማረጋገጥ


ለ. ከመነሻ እስከ መጨረሻ የሚያገለግል ለእንስሳት በቂ የሆነ የውሃና የምግብ ዝግጅት መኖሩን ማረጋገጥ
ሐ. እንስሳቱ የተጫኑበት የተሽከርካሪው አካል እንዳያንሸራትት የተጎዘጎዘ ሣር መኖሩን ማረጋገጥ
መ. ተሽከርካሪው መጫን ከሚችለው እንስሳት መጠን በላይ መጫኑን ማረጋገጥ
8. ከልክ በላይ የሆኑ ግዙፍ የጭነት አይነቶችን ለማጓጓዝ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋሌ፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
9. በጠመዝማዛ መታጠፊያ የሚበዛበት መንገድ ላይ ጭነቶቹ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ሊንሸራተቱ ስለሚችሉ ፍጥነትን መጨመር ያስፈልጋል፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
10. የማውረጃ እና የመጫኛ መሳሪያ የሚያስፈልጉ ጭነቶች

ሀ. ጭነቱን ለማንሳት የሚያገለግለ እንደ ካቦ፣ ገመድና ሰንሰለት የመሳሰለትን ትክክለኛነታቸውን ማረጋገጥ
ለ. ጭነቱን ለመጫንም ሆነ ለማውረዴ የሚያስችል ሰፊና አመቺ ቦታ መኖሩን ማየት
ሐ. ጭነቱ በሚጫንበትም ሆነ በሚወርድበት ወቅት ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ማድረግ
መ. ሁሉም መልስ ነው

11. የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪን የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎች በሚጓዙበት የመንገድ ስፋት፣ የመሿለኪያ ድልድይ ከፍታና ኩርባ
መንገዳችን ባገናዘበ መልኩ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
12. አንድ የጭነት ተሽከርካሪ የሚጭነውን ጭነት አስቀድሞ ማወቅ

ሀ. የተሽከርካሪውን ደህንነት ይጠብቃል


ለ. የመንገዶችና የድልድዮችን ደህንነት ይጠብቃል
ሐ. ከአቅም በላይ በመጫኑ የሚያስከትለውን የትራፉክ አደጋ ይቀንሳል
መ. ሁሉም መልስ ናቸው

13. አንደ ጭነት ዓይነት ማለትም ብረት፣ ዘይት፣ ጨው፣ ፓስታ ወዘተ. ቢኖር አሽከርካሪዎች መጀመሪያ ብረት፣ ቀጥል ዘይትን፣
ጨው፣ ፓስታ ከታች ወደ ላይ በቅደም ተከተል እየደረደሩ መጫን አለባቸው፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት
14. አደገኛ ጭነት በጫነ ተሽከርካሪ አቅራቢያ በ------- ጫማ ክልል ውስጥ ሲጋራ አለማጨስ
ሀ. 23 ለ. 24 ሐ. 25 መ. 26

15. ጭነት በሚራገፌበት ወቅት መወሰድ ያለበት ጥንቃቄ ውስጥ አይካተትም

ሀ. ጭነቱን በተዘጋጀለት ቦታ ላይ በአግባቡ ማስቀመጥ


ለ. ጭነቱ ተራግፍ ሲያልቅ በተሽከርካሪው የመጫኛ ክፍል ላይ ፈሳሽ ካለ ማጽዳት
ሐ. ጭነቱን ቆጥሮ ለተረካቢ ክፍል አለማሰረከብ
መ. የተሽከርካሪውን ሞተር ማጥፋትና የእጅ ፍሬን ይዞ ታኮ ማድረግ
16. ጭነቱ የሚራገፍበት ቦታ ለማራፍ ምቹ መሆኑንና በሚራገፍበት ወቅት ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮች በአካባቢው አለመኖራቸውን
ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡

ሀ. እውነት ለ. ሀሰት

You might also like