You are on page 1of 14

ማውጫ

1. መግቢያ ............................................................................................................................................ 2
ክፍል አንድ.............................................................................................................................................. 3
አጠቃላይ ድንጋጌዎች................................................................................................................................ 3
2. አውጭው ባለሥልጣን .................................................................................................................... 3
3. አጭር ርዕስ................................................................................................................................... 3
4. ትርጓሜ ........................................................................................................................................ 3
5. የመመሪያው ዓላማ......................................................................................................................... 6
6. የመመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን ..................................................................................................... 6
7. የመመረያው አስፈላጊነት................................................................................................................. 6
ክፍል ሁለት ................................................................................................................................................ 6
8. ለአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እና ለደንብ አልባሳት የሚውሉ የጨርቅና የጫማ ዓይነቶችና መጠናቸው፡፡ ............................ 6
8.1. የጨርቅ ዓይነቶች......................................................................................................................... 6
8.2. የጫማ ዓይነቶች .......................................................................................................................... 6
ሰንጠረዥ 1 ................................................................................................................................................. 7
9. ለአደጋ መከላከያ እና ለደንብ አልባሳት የሚያስፈልግ የጨርቅ መጠን ................................................................... 7
ክፍል ሶስት ................................................................................................................................................. 8
10. የንፅህና ቁሳቁሶች አፈቃቀድ......................................................................................................... 8
1. የስራ ሁኔታቸው ለከፍተኛ የጤና ጠንቅ ለሚያጋልጣቸው ............................................................. 8
2. የስራ ሁኔታቸው በተነፃፃሪ ተጋላጭ ............................................................................................. 8
3. ሌሎች ሰራተኞች ........................................................................................................................ 8
ክፍል አራት ............................................................................................................................................. 9
የሥራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች................................................................................... 9
11. የሥራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች አሰጣጥ ........................................................ 9
12. የሥራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች የሚሰጥበት ቅድመ-ሁኔታ ፡- ......................... 9
13. ነበሥራ መደቦች ላይ የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች ፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል
ልብስ እንዲሰጥ ስለማስፈቀድ ፡- ............................................................................................................. 9
ክፍል አምስት ........................................................................................................................................ 10
የተለያዩ ክፍሎች ሥልጣንና ኃላፊነት ...................................................................................................... 10
14. ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ፡-............................................................................................... 10
15. መሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ፡- ..................................................................................... 10

0
16. የብቃት እና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ፡- .................................................................. 10
17. የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ኃላፊነት ................................................................................... 10
18. የተጠቃሚ ሠራተኞች ተወካይ ኃላፊነት ፡- ................................................................................. 11
19. የተጠቃሚው ሠራተኛ ኃላፊነትና ግዴታ ፡- ................................................................................ 11
20. መመሪያውን ስለማሻሻል............................................................................................................ 11
21. ስለተሻሩ መመሪያዎች .............................................................................................................. 12
22. መመሪው የሚፀናበት ጊዜ ......................................................................................................... 12

1
1. መግቢያ
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ዓ.ም አንቀጽ 52-60 በተደነገገው መመሪያው
መሠረት መስሪያ ቤቶች የሥራ ቦታ ደህንነትና ጤንነት መጠበቂያ መሣሪያዎችና ቁሳቁሶችን ለሠራተኞች
እንዲያቀርቡና ስለአጠቃቀማቸው መመሪያ እንዲሰጡ መደንገጉ ይታወቃል፡፡

የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎችን መነሻ በማድረግ በእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት እና በስሩ በተደራጁ ማዕከላት
ውስጥ ለሚገኙ ሰራተኞች የሥራ ልብስ ፣ የደንብ ልብስ እና የግል ንፅህና መጠበቂያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች
አሰጣጥ እና አጠቃቀም መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ሠራተኛው ሥራውን
በሚያከናውንበት ወቅት እንደሥራው ፀባይና ክብደት የሠራተኛ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅና መለያ ሆኖ
እንዲያገለግል የሚሰጠው የደንብ ልብስ ፣ የሥራ ልብስ እና የግል ንፅህና መጠበቂያ መሣሪያዎች የሠራተኞችን
ጤንነትና ደህንነት ከማስጠበቅ ባሻገር ሠራተኛው በስራው ላይ በራስ መተማመንና የሥራ ተነሳሽነት
እንዲፈጥር ያደርጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ይህ የደንብ ልብስ እና የስራ አልባሳት አሰጣጥ እና አጠቃቀም መመሪያ ከኢንስቲትዩቱ እና
በስሩ ከተደራጁ መዕከላት የሥራ ፀባይ አኳያ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

2
ክፍል አንድ

አጠቃላይ ድንጋጌዎች

1. አውጭው ባለሥልጣን
የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

2. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች፣ የደንብና የፕሮቶኮል አልባሳት አሰጣጥና አጠቃቀም መመሪያ
ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

3. ትርጓሜ
የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ፣
1. እንስቲትዩት፡- ማለት የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ማለት ነው፡፡
2. የመንግሥት ሠራተኛ፡- ማለት በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010
በኢኒስቲትዩቱ ወይም በስሩ በተደራጁ መዕከላት በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፡፡
3. ግዜያዊ ሰራተኛ፡- ማለት በኢንስቲትዩቱ ወይም በስሩ በተደራጁ መዕከላት ውስጥ የዘላቂነት ባህሪ በሌለው
ወይም ሁኔታዎች ስያስገድዱ በቋሚ የስራ መደብ ላይ በግዜያዊነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፡፡
4. የሥራ አካባቢ፡- ማለት ሠራተኞች የሚሰሩበት የሥራ ቦታ ወይም አካባቢ ማለት ነው፡፡
5. የሥራ ላይ አልባሳት፡- ማለት ሠራተኛው ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ እንደ ሥራው ፀባይ/ባህሪ
ለሠራተኛው ጤንነትና ደህንነት መጠበቂያነት የሚያገለግል እንዲሁም ተገልጋዩ በቀላሉ ለይቶ
እንዲያውቀው ለሰራተኛው መለያ ሆኖ የሚያገለግል የደንብ ልብስ እና የሥራ ልብስ ማለት ነው፡፡
6. የሥራ አካባቢ ጤንነት እና ደህንነት፡- ማለት በሥራ ምክንያት ከሚመጡ በሽታዎች ፣ ጉዳቶች እና
በሥራ ምክንያት ከሚከሰቱ አካላዊ ፣ ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ተጽዕኖዎች ነጻ መሆን ማለት ነው፡፡
7. በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳት፡- ማለት በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ወይም በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ
ወይም ጉዳት ማለት ነው፡፡
8. የሥራ ላይ የጤና ጠንቆች፡- ማለት በሥራ ላይ የሚገኙ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሥራ ምክንያት
የሚመጡ በሽታዎች ወይም ለጉዳት የሚዳርጉ በንክኪ ፣ በትንፋሽ ወይም በሌሎች አጋላጭ መንገዶች
ሳቢያ የህመም ወይም የአካል ጉዳት የሚያደርሱ ወይም የሥራ አካባቢን የሚበክሉ ንጥረ ነገሮች ፣ ቁሶች
፣ መሣሪያዎች ወይም ስነ-ህይወታዊ ተውሳኮች ናቸው፡፡
9. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎችና ቁሳቁሶች፡- ማለት ሠራተኛው ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ከጤና
ጠንቆችና አደጋዎች ራሱን ለመከላከል የሚለበሱ ፣ የሚደረጉ ፣ የሚታሰሩ ፣ የሚጠለቁ ወይም
በጆሮዎች የሚሸጎጡ የሥራ መሣሪያዎች ወይም የሥራ ልብሶች ናቸው፡፡
10. የሥራ መሣሪያ፡- ማለት ሠራተኛው ሥራውን በወል ወይም በግል ለማከናወን እንዲጠቀምበት የሚሰጥና
ሥራውን ሲጨርስ በሥራ ቦታ የሚቀመጥ ልዩ ልዩ የሥራ መሣሪያ ወይም ዕቃ ማለት ነው፡፡

3
11. የግል ንፅህና መጠበቂያ፡- ማለት ሠራተኛው ሥራውን በሚያከናውንበት ጊዜ እንደሥራው ፀባይ/ባህሪ
ሥራውን በወል ወይም በግል ሲያከናውን ለንፅህና መጠበቂያነት እንዲውል የሚሠጥ የልብስ ሳሙና ፣ የእጅ
ሳሙና ፣ ኦሞ እና ሶፍት ማለት ነው፡፡
12. ኮት፣ ሱሪ ወይም ጉርድ ቀሚስ ፡- ማለት ሱፍ ነክ ከሆነ ጨርቅ የሚሰፋ ቀለሙና ዓይነቱ ተመሳሳይ
የሆነ ልብስ ነው፡፡
13. የፕሮቶኮል ልብስ፡- ማለት ከሱፍ ነክ ጨርቅ ተሰፍቶ የተዘጋጀ ጥራቱን የጠበቀ ሙሉ ልብስ የሆነ ለአንድ
ተመሳሳይ የስራ መደብ ቀለሙ አንድ ዓይነትና ለፕሮቶኮል ሠራተኞች ከበላይ ኃላፊ ጋር ለሚንቀሳቀሱ
ሾፌሮችና አጃቢዎች የሚሰጥ ማለት ነው፡፡
14. ክራቫት፡- ማለት ከኮትና ሱሪ ወይም ኮትና ጉርድ ቀሚስ ጋር ተመሳሳይ ከሆነ ጨርቅ የሚሰራ አንገት
ላይ የሚታሰር ልብስ ነው፡፡
15. ሸሚዝ፡- ማለት ቀለሙና ዓይነቱ ተማሳሳይ የሆነ ለሸሚዝ አገልግሎት የተዘጋጀ ልብስ ነው፡፡
16. ሙሉ የሥራ ቱታ፡- ማለት ጥራቱን የጠበቀ ከጨርቅ ወይም ከቲዩል ጨርቅ የሚዘጋጅ ሆኖ ሠራተኞች
ስራቸውን በሚያከናውበት ወቅት ከጤና ጠንቅ ፣ ከአቧራ እና ከብናኝ እንዲሁም የልብስን መቆሸሽ
የሚከላከል በልብስ ላይ ተደርቦ የሚለበስ ለአንድ የስራ መደብ ቀለሙ አንድ ዓይነት የሆነ የስራ ልብስ
ነው፡፡
17. አጭር የቆዳ ጫማ፡- ማለት ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ሆኖ ቁመቱ ከቁርጭምጭሚት የማያልፍ
በቀላሉ ተንቀሳቅሶ ስራን ለማከናወን የሚረዳ በአገር ውስጥ ከቆዳ የተመረተ የሴት ወይም የወንድ ጫማ
ማለት ነው፡፡
18. ቡትስ ቆዳ ጫማ፡- ማለት ዚፕ ወይም ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ሆኖ ቁመቱ ቁርጭምጭሚት
የሚሸፍን በቀላሉ ተንቀሳቅሶ ስራን ለማከናወን የሚረዳ በአገር ውስጥ ከቆዳ የተመረተ የሴት ወይም
የወንድ ጫማ ማለት ነው፡፡
19. አፍንጫው ላይ ብረት ያለው ጫማ (ሴፍቲ ሹዝ)፡- ቁመቱ አጭር ፣ አጭር ቡትስ ወይም ረጅም ቡትስ
ሆኖ ከከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚወድቁ የተለያዩ ክብደት ካላቸው ነገሮች እንዲሁም እሾህና ጋሬጣን
ከመሳሰሉት ነገሮች ለመከላከል የሚያስችል የቆዳ ወይም የፕላስቲክ ጫማ ነው፡፡
20. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ የጨርቅ ማስክ:- ማለት ብናኝ ባለበት አካባቢ ብናኙን ለመከለከል ደረጃውን
በጠበቀ መልኩ ከጨርቅ ወይም ከጥጥ መሰል ነገር የተዘጋጀና በአፍና አፍንጫ ላይ የሚታሰር የመሸፈኛ
ጨርቅ ማለት ነው፡፡
21. ጓንት:- ማለት እጅን ከተለያዩ ባዕድ ነገሮች አካላትን ለመከላከል የሚረዳና ከፕላስቲክ ፣ ከቆዳ ወይም
ከክር የተሰራ የእጅ መሸፈኛ መሣሪያ ማለት ነው፡፡
22. ¾ኛ ጋዎን:- ማለት ከፖሊስተር ካኪ 6000 ጨርቅ የተሰራ በልብስ ላይ ተደርቦ የሚለበስ እና ቆሻሻ
ወይም አቧራ የሚከላከል ቀለሙና ዓይነቱ እንደ ስራ መደቡ የሚለያይ ልብስ ማለት ነው፡፡

4
23. ካፖርት፡- ማለት ከሱፍ ፣ ከጥጥ ወይም ከጥጥ ሴንቴቲክ የተሰራ ሙቀት እንዲሰጥ ገበር ያለው በተለይ
ለለሊት ብርድ መከላከያ የሚያገለግል ለአንድ ተመሳሳይ የስራ መደብ ቀለሙ አንድ ዓይነት የሆነ ልብስ
ነው፡፡
24. የዝናብ ልብስ:- ማለት ከሴንቴቲክ የተሰራ ዝናብ የማያስገባ ቀለሙና ዓይነቱ ተመሳሳይ የሆነ የዝናብ
ልብስ ማለት ነው፡፡
25. የበረዶ ቤት ቅዝቃዜ መከላከያ ቱታ:- ማለት ወፍራም ቅዝቃዜ እንዲከላከል ተደርጎ ከሸራ ወይም
ከናይለን ውስጥ ጥጥ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ ፊት የሚሸፍን ኮፍያ ያለው በአገር ውስጥ ገበያ ሊገኝ
የሚችል ነው፡፡
26. የላስቲክ ቡትስ ጫማ:- ማለት ስሪቱ ከፕላስቲክ ሆኖ ውስጡ ገበር ያለውና በክረምትና ጭቃ ባለበት ጊዜ
የሚደረግ ጫማ ማለት ነው፡፡
27. የውስጥ ልብስ:- ማለት ሙሉ በሙሉ ጨርቅ ሆኖ ከውስጥ የሚለበስ ልብስ ነው፡፡
28. ሽርጥ፡- ማለት ከጨርቅ ወይም ከቲዩል ጨርቅ የተሰራ ሆኖ በስራ ላይ ቆሻሻ ወይም አቧራ ለመከላከል
የሚለበስ ለአንድ ተመሳሳይ የስራ መደብ ቀለሙ አንድ ዓይነት የሆነ ልብስ ነው፡
29. የላስቲክ ሽርጥ፡- ማለት ቀለሙ እንደተፈለገው ሆኖ ከላስቲክ የተሰራና ከአደገኛ ፈሳሽ ኬሚካሎች
ለመከላከልና የልብስን መቆሸሽ ለመከላከል ከላይ የሚለበስ ማለት ነው፡፡
30. ሄልሜት፡- ማለት ከጠንካራ ማይካ የተሰራና ጭንቅላትን ከጉዳት ለመከላከል በጭንቅላት የሚጠለቅ ነው፡፡
31. ቆብ (ፊልድ ኬፕ)፡- ማለት የራስ ቅልን የሚሸፍን ፀሀይን ለመከላከል የሚረዳ የራስ ቆብ ነው፡፡
32. ክብ ነጭ ቆብ፡- የራስ ቅልን የሚሸፍን ተሰፍቶ የተዘጋጀ የፅጉር ብናኞችን ከምግብና ምግብ ነክ ነገሮች
ለመከላከል የሚያገለግል፡፡
33. የቆዳ ጃኬት፡- ማለት ከቆዳ የተሰራ ሆኖ በማንኛውም የአየር ንብረት የሚለበስ ማለት ነው፡፡
34. የዓይን ጎግል፡- ማለት ዓይንን ከኬሚካል ንክኪ እና ከጨረር ለመከላከል የሚያገለግል የመነጽር ዓይነት
ነው፡፡
35. ፍራሽ፡- ማለት ከስፖንጅ የተዘጋጀ ለአንድ ሰው የሚሆን በሌሊት ሽፍት ስራ ወቅት ለማረፍ የሚያገለግል
መሣሪያ ነው፡፡
36. ዣንጥላ፡- ማለት ትልቅ ሆኖ በዝናብ ወቅት ዝናብን ለመከላከል የሚያገለግል መሣሪያ ነው፡፡
37. ብርድ ልብስ፡- ማለት በአገር ውስጥ የተመረተ ጥራቱን የጠበቀ ብርድን ለመከላከል የሚረዳ ልብስ ነው፡፡
38. አንሶላ፡- ማለት በሀገር ዉስጥ የተሰራና ከብርድ ልብስ ስር የሚለበስና ለፍራሽ መሸፈኛ የሚያገለግል
ልብስ ነዉ፡፡
39. ቀበቶ፡- ማለት በሀገር ውስጥ ከቆዳ የተሰራ ሱሪን ወገብ ላይ ለማሰር የሚረዳ ነው፡፡
40. ካልሲ፡- ማለት በእግር ላይ የሚጠለቅ ጫማ በላዩ ላይ የሚደረግበት ከጨርቅ የተዘጋጀ ልብስ ነው፡፡
41. ክብ ቆብ፡- ማለት ላስቲክ ያለው በስራ ወቅት የፀጉር ንፅህናን እና ደህንነትን ለመጠበቅ የሚለበስ ቆብ
ነው፡፡
42. ትራስ፡- ማለት በሃገር ውስጥ ከእስፖንጅ የተመረተ ጥራቱን የጠበቀ እራስን ለማሳረፍ የሚያገለግል ነው፡፡

5
4. የመመሪያው ዓላማ

የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የፕሩቶኮል እና የደንብ ልብስ የሚያስፈልገውን የሥራ መደብ በመለየት እና
ለተፈቀደላቸው ሠራተኞች በመስጠት በስራ ላይ ከሚደርስ ጉዳት ለመከላከል እንዲሁም ለተገልጋዮች ምቹ ሁኔታ
ለመፍጠር ነው፡፡

5. የመመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን

የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የፕሩቶኮል እና የደንብ ልብስ መጠቀም በሚያስፈልጋቸው የሥራ መደቦች
ላይ ተመድበው በእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ወይም በስሩ በተደራጁ መዕከላት ውስጥ ለሚሰሩ ሠራተኞች ብቻ
ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

6. የመመረያው አስፈላጊነት

1. በፌደራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ከአንቀፅ 52-60 በተደነገገው መሠረት የአደጋ
መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች አፈቃቀድና አፈፃፀም ተግባራዊ ለማድረግ
2. የኢኒስቲትዩቱን ተጨባጭ ሁኔታ ያማከለ መመሪያ ለማዘጋጀት
3. የሠራተኞች የሥራ ተነሳሽነትን በመጨመር የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብና ለተገልጋዮች ምቹ ሁኔታ
ለመፍጠር መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡

ክፍል ሁለት

7. ለአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እና ለደንብ አልባሳት የሚውሉ የጨርቅና የጫማ ዓይነቶችና መጠናቸው፡፡

1. የጨርቅ ዓይነቶች

1. ፖሊስተር ካኪ 6000 ጨርቅ ፡- ለ3/4 ጋወን የሚውል


2. ካኪ ቲዩል፡- ለስራ ቱታ እና ለሽርጥ የሚውል
3. ሱፍ ወይም ከጥጥ ወይም የጥጥና ሴንቴቲክ ድብልቅ ከሆነ ጥሬ ዕቃ የተሰራ ጨርቅ፡- ለብርድ መከላከያ
የሱፍ ካፖርት የሚሆን
4. ከሴንቴቲክ የተሰራ ዝናብ የማያስገባ ጨርቅ፡- ለዝናብ ልብስ
5. ለሙሉ ልብስ የተዘጋጀ ሱፍ ነክ ጨርቅ፡- ለኮት፣ ሱሪና ጉርድ ቀሚስ

2. የጫማ ዓይነቶች

6
1. ማሰሪያ ያለው ወይም የለለው ቁመቱ ከቁርጭምጭሚት የማያልፍ ከቆዳ የተሰራ አጭር ጫማ
2. ዚፕ ወይም ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ሆኖ ቁርጭምጭሚት የሚሸፍን ከቆዳ የተሰራ ቡትስ ጫማ
3. ማሰሪያ ያለው ወይም የሌለው ቁርጭምጭሚትን የሚሸፍን ከፒላስቲክ የተሰራ ቡትስ ጫማ

ሰንጠረዥ 1

9. ለአደጋ መከላከያ እና ለደንብ አልባሳት የሚያስፈልግ የጨርቅ መጠን


ተ.ቁ የልብሱ ዓይነት መጠን በሜትር
1 ኮትና ሱሪ 3.50 ሜትር
2 ኮትና ጉርድ ቀሚስ 3.00 ሜትር
3 ¾ ጋዋን 2.50 ሜትር
4 ቱታ 3.15 ሜትር
5 ሽርጥ 2.00 ሜትር
6 ፍራሽ 90 ሴንቲ ሜትር ስፋት
7 አንሶላ 1.50 X 1.90 ሜትር
8 ብርድ ልብስ 1.80 ሜትር ስፋት ያለዉ
9 ውስጥ ልብስ 2.15 ሜትር
10 ፍልድ ኬፕ/ቆብ/ 0.25 ሜትር
11 ክራቫት 0.30 ሜትር

7
ክፍል ሶስት

10. የንፅህና ቁሳቁሶች አፈቃቀድ

1. የስራ ሁኔታቸው ለከፍተኛ የጤና ጠንቅ ለሚያጋልጣቸው

የቢሮና የላብራቶሪ ፅዳት ሰራተኞች፣ሁለገብ ጥገና ሰራተኞች፣የጉልበት ሰራተኞች፣ የእንሲሳት


ተንከባካቢ፣የወተት አላቢ፣ የዝርያ እንሲሳት ቴክኒሺያን፣እንሲሳት ሃኪም፣ረዳት እንሲሳት ሃኪም፣ እንሲሳት
ጤና ላብራቶሪ ቴክኒሽያን፣ ላብራቶሪ አቴንዳንት፣ የአባለዘር ምርት መሳሪያ አደራጅ ቴክኒሺያን፣የአባለዘር
ላብራቶሪ ቴክኒሺያንና ተክኖሎጂስት፣የወተት ምርት (አቀናባሪ)፣ የመኖ ልማት ዝግጅት ቅንብር ሰራተኛ እና
የመኖ ማቀነባበሪያ ፕላንት ኦፕሬተር፣አውቶ/አግሮ መካኒክ፣ቅባትና ነደጅ አዳይ፣ጎሚስታ፣ አትክልተኛ፣ አዳቃይ
ቴክኒሽያን፣የእንስሳት ተንከባካቢ ሰራተኞች አስተባባሪ፣ የትራክተር፣ የወተት ማለብያ ማሽን/፣የልዩ ተሸከርካሪ
ረዳት፣ የሆኑ የኢንስቲትዩቱ ወይም በስሩ የተደራጁ ማዕከላት ሰራተኞች የሚከተለው የፅዳት ቁሳቁሶች
ተፈቅዶላቸዋል፡፡

 የልብስ ሳሙና ባለ 250 ግራም፣ የገላ ሳሙና ባለ 150 ግራም እና ኦሞ ባለ 200 ግራም በወር 4
(አራት) እና ሶፈት በወር 2

2. የስራ ሁኔታቸው በተነፃፃሪ ተጋላጭ

የጥበቃ ሰራተኞች፣ የጥበቃ ሽፍት ሃላፊ፣ የፅዳት ሰራተኞች ተቆጣጣሪ፣ ሾፌር እና ሾፌር መካኒክ፣
ኦፕሬተሮች/ፈሳሽ ናይትሮጂን፣ ጀነረተር፣የውሃ ፓንፕ፣ የከባድ መኪና ሾፌር ረዳት፣ ተላላኪ፣ ፎቶኮፒ
ሰራተኞች፣ የኮምፒ ጥገና ሰራተኛ፣ የእንስሳት መኖ ልማት እና ዝግጅት ፎርማን፣ ሪከርድና ማሃደር ሰራተኛ፣
የምግብ ዝግጅት ሰራተኛ፣ የልምድ አስተናጋጅ፣ እንጀራ ጋጋሪ፣ አናፅ፣ ግምበኛ፣ ኤሌክትሪሺያን፣ ሒሳብ ሰነድ
ያዥ፣ የእቃ ግምጃ ቤት ሓላፊ፣ የንብረት ምዝገባና ቁጥጥር ሠራተኛ፣ የእቃ ግምጃ ቤት ሠራተኛ፣ የእንስሳት
ግበዓት ምርት ስርጭት ሰራተኛ እና የንብረት ስራ አመራር ባለሙያ፣ የሪኮርድና ማኀደር ኃላፊ፣ የሰው ኃበት
መረጃ ሰረተኛ የሆኑ የኢንስቲትዩቱ ወይም በስሩ የተደራጁ ማዕከላት ሰራተኞች የሚከተለው የፅዳት ቁሳቁሶች
ተፈቅዶላቸዋል፡፡

 የልብስ ሳሙና ባለ 250 ግራም፣ የገላ ሳሙና ባለ 150 ግራም እና ኦሞ ባለ 200 ግራም በወር 2 እና
ሶፍት በወር 2 (ሁለት)

3. ሌሎች ሰራተኞች
ከላይ በንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 ስር ከተዘረዘሩት ውጭ የሆኑ የኢንስቲትዩቱ ወይም በስሩ የተደራጁ ማዕከላት
ሰራተኞች የሚከተለው የፅዳት ቁሳቁሶች ተፈቅዶላቸዋል፡፡

 የልብስ ሳሙና ባለ 250 ግራም፣ የገላ ሳሙና ባለ 150 ግራም፣ ኦሞ ባለ 200 ግራም እና ሶፍት በወር
1(አንድ)
4. የኤየር ፍረሽነር በእያንዳንዱ የስራ ክፍል አንዳንድ በማስቀመጥ ጥቅም ላይ የሚውል እና ሲያልቅ
የሚተካ ይሆናል፡፡

8
ክፍል አራት

የሥራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች አሰጣጥ


11. የሥራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች አሰጣጥ

1. እንደሥራው ባህሪ የስራ ላይ አልባሳት የተፈቀደላቸው ሠራተኞች የሚሰጠው የስራ ልብስ ቀለም
በበጀት ዓመቱ ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡ ይህም ማለት ልብሱ በአግባቡ ለታለመለት ስራ ላይ
መዋሉን ለመቆጣጠር እንዲረዳ ታስቦ ነው፡፡
2. በአንድ በጀት ዓመት ያልተሰጠ የስራ ልብስ ወይም የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ለሚቀጥለው
በጀት ዓመት አይተላለፍም፡፡
3. የበጀት ዓመቱ የስራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች በመጀመሪያው በስድስት ወር
ይሰጣቸዋል፡፡

12. የሥራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች የሚሰጥበት ቅድመ-ሁኔታ

1. ማንኛውም ሠራተኛ የስራ ላይ አልባሳትና የአደጋ መከላከያ መሣሪያ የተፈቀደለት የስራ መደብ ላይ
ከአንድ ወር በላይ በቋሚነት ሆነ በጊዜያዊነት ሲመደብ ለስራ መደቡ የተፈቀደውን የስራ ልብስና
የአደጋ መከላከያ መሣሪያ ያገኛል፡፡
2. ከላይ በንዑስ አንቀፅ (1) የተገለፀውን እንደተቀበሉ ወዲያውኑ ስራ የሚያቋርጡ ሠራተኞች
የወሰዷቸውን ስራ ላይ አልባሳት እና የአደጋ መከላከያ መሣሪያች እንዲመልሱ ይደረጋል፡፡

13. ለሥራ መደቦች የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች ፣ የደንብ ልብስ እና


የፕሮቶኮል ልብስ እንዲሰጥ ስለማስፈቀድ

1. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች ፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ ባልተወሰነለት


የሥራ መደብ ላይ የሚመደቡ ሠራተኞች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአዲስ መልክ በማስፈቀድ ወይም
የተፈቀደውን ማሻሻል ሲያስፈልግ የሥራ አካባቢ ጤንነትና ደህንነት ባለሙያ አጥንቶ ለብቃትና
የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ያቀርባል፡፡
2. ጥናቱ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ የበላይ አመራሩ ውሳኔ ሰጥቶበት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

9
ክፍል አምስት

የተለያዩ ክፍሎች ሥልጣንና ኃላፊነት

14. ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ

1. ይህ መመሪያ ፀድቆ ተግባራዊ እንዲሆን ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣


ቁሳቁሶች፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ ለተጠቃሚ ሠራተኞች አንዱን በበጀት ዓመቱ
መጀመሪያና የቀረዉን ደግሞ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ላይ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፡፡
2. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች እና የደንብ ልብስ ግዥ በተመለከተ ከመስሪያ ቤቱ የስራ
ክፍሎች፣ የሥራ አካባቢ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ባለሙያ እና የተጠቃሚ ሠራተኞች ተወካይ
ያካተተ ኮሚቴ ያደራጃል፣ የኮሚቴውን አስተያየት ይቀበላል፣ ውሳኔ የሚያስፈልገው ሆኖ ስገኝ
ለኢንስቲትዩቱ የበላይ አመራር አስተያየቱን ለውሳኔ ያቀርባል፡፡

15. መሰረታዊ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ

1. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ የሚያስፈልጋቸውን


የክፍሉን ሠራተኞች እና የሥራ መደብ ቁጥር በመለየት የግዥ ጥያቄ ያቀርባል ፣
2. በአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች እና የደንብ ልብስ አሰጣጥ እና አጠቃቀም እንዲሁም
የግዥ ሂደት ላይ እንዲሳተፉ ከጥበቃ ፣ ከፅዳት ፣ ከሹፌር ባለሙያዎች የተውጣጡ ተወካዮችን
ይመርጣል፡፡
3. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች ፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ ወቅቱንና
ጊዜውን ጠብቆ ለተጠቃሚዎች የማሰራጨት ኃላፊነት አለበት፡፡

16. የብቃት እና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ

1. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ


የሚያስፈልጋቸው ለክፍሉ ሠራተኞች እና የሥራ መደብ ቁጥር በመለየት የግዥ ጥያቄ
ያቀርባል፡፡
2. ለአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ ምንነትና
አጠቃቀም አስመልክቶ ሠራተኞችን በማወያየት ግንዛቤ ያስጨብጣል፡፡
3. የወቅቱን ሁኔታ እያጠና በመመሪያው ላይ የማሻሻያ ጥናት ያቀርባል፡፡
4. ሠራተኞች የተሰጣቸውን የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎችና ቁሳቁሶች እና የደንብ ልብስ ለብሰው
ስራ ላይ መገኘታቸውን ይከታተላል፣ ጥቅም ላይ የማያውሉ ሠራተኞችን በመለየት የዲሲፕሊን
እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡

17. የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ኃላፊነት

1. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ


የሚያስፈልጋቸው የክፍሉን ሠራተኞች እና የሥራ መደብ ቁጥር በመለየት የግዥ ጥያቄ
ያቀርባሉ፡፡
2. የደንብ ልብስ፣ የሥራ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ባልተፈቀደላቸው መደቦች የሥራ
ፀባይ የሚገባው ሆኖ ሲገኝ መደቡ የሚገኝበት የሥራ ክፍል የበጀት ዓመት ከመጀመሩ በፊት
የብቃት እና ሰው ኃብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ ጥያቄ ያቀርባል፡፡

10
3. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ ተጠቃሚ የሆኑ
የስራ ክፍሉ ሰራተኞችን መጠቀማቸውን መከታተልና መቆጣጠር አለበት፡፡ ጥቅም ላይ
የማያውሉ ሠራተኞችን በመለየት የዲሲፕሊን እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፡፡

18. የተጠቃሚ ሠራተኞች ተወካይ ኃላፊነት

1. የተጠቃሚ ሠራተኞች ተወካይ ለናሙና የተመረጡትን በማየትና በመገምገም የአደጋ መከላከያ


መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች እና የደንብ ልብስ ጥራቱን የመለየት እና የመከታተል ኃላፊነት አለበት፡፡
2. የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎች ፣ ቁሳቁሶች ከሻጭ በሚደረገው ርክክብ ላይ እና ወደ ዕቃ ግምጃ
ቤት በሚደረገው ገቢ የማድረግ ሂደት ላይ የተጠቃሚ ሠራተኞች ተወካይ በታዛቢነት ይኖራል፤
ከቀረበው ናሙና ጋር በማነፃፀር ሪፖርት ለግዢና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ያቀርባል፡፡

19. የተጠቃሚው ሠራተኛ ኃላፊነትና ግዴታ

በፌዴራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀፅ 52-60 ላይ የተደነገገው


እንደተጠበቀው ሆኖ ተጠቃሚው ሠራተኛ ፡-
1. ጤንነትንና ደህንነትን ለመጠበቅ የወጡ መመሪያዎችን የማክበር ፣
2. የተሰጡት የአደጋ መከላከያ መሣሪያዎችን፣ ቁሳቁሶች፣ የደንብ ልብስ እና የፕሮቶኮል ልብስ በአግባቡ
ለብሶ በስራ ገበታው ላይ መገኘት አለበት፡፡
3. ለሥራ የተሰጠውን የአደጋ መከላከያ መሣሪያ እና ቁሳቁስ ባለመጠቀም ለሚደርስበት ጉዳት
ኢኒስቲትዩቱ ተጠያቂ አይደለም፡፡
4. የተሰጠውን የደንብ ወይም የፕሮቶኮል ልብስ ለሌላ አሳልፎ የሰጠ ፣ የሸጠ ወይም ከዚህ መመሪያ
ውጪ ሲጠቀም የተገኘ እንዲሁም የተሰጠውን የደንብ ወይም የፕሮቶኮል ልብስ ያልተጠቀመ ሠራተኛ
በዲሲፕሊን ግድፈት ይጠየቃል፡፡
5. አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን ሲገምት ለሚመለከተው የቅርብ ኃላፊ ወዲያኑ
የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡

20. ሌሎች ድንጋጌዎች


1. ጉርድ ቀሚስ የተፈቀደላቸው ሴቶች ሱሪ ማሰፋት ከፈለጉ የክፍላቸው የግዢ ፍላጎት ተሰብስቦ
ለግዢ ፋይናንስ ከመተላለፉ በፊት ለስራ ክፍላቸው ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሱሪ የሚያሰፉ
ከሆነ የውስጥ ልብስ የሚቀነስባቸው ይሆናል፡፡
2. በስራ ቦታ የሚያገለግሉ የአደጋ መከላከያ መሳሪያዎች እንዳስፈላጊነቱ አስገዳጅ ሆኖ ስገኝ ግዢው
የሚፈፀም ይሆናል፡፡
3. በንዑስ አንቀፅ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የስራ መደቡ የተፈቀደ ሆኖ በሰው ኃይል እጥረት
ወይም በግበዓት አለመሟላት ወይም በሌሎች ምከኒያቶች ወደ ተግባር ላልገባ የስራ መደብ ወይም
ክፍል ወይም በአካል ካሉት እና በመመሪያው ከተፈቀደላቸው ሰራተኞች ቁትር በላይ ግዢ ጠይቆ
ያስፈፀመ የስራ ኃላፊ ለባከነው የመንግስት ኃብትና ንብረት ተጠያቂ የሆናል፡፡
4. በምርምር ዘርፍ የሚመደቡ ለተመራማሪዎች የተፈቀዱ የደንብ ልብስና የስራ ቦታ መሳሪያዎች
በዘርፉ ለተመደቡ መሪ ስራ አስፈፃሚዎችና ዴስክ ኃለፊዎች ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

21. መመሪያውን ስለማሻሻል

መመሪያው ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ የብቃትና የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ


አስፈፃሚ አጥንቶ ለኢንስቲትዩቱ የበላይ አመራር አቅርቦ በማስወሰን መመሪያው እንዲሻሻል ሊያደረግ
ይችላል፡፡
11
22. ስለተሻሩ መመሪያዎች

ከአሁን በፊት የነበሩ የደንብ ልብስ ፣ የሥራ ልብስ እና የንጽህና መጠበቂያ መሣሪዎች አፈቃቀድና
አሰጣጥ መመሪያ እና በዘልማድ የነበሩ አሰራሮች በዚህ መመሪያ ተሽረዋል፡፡

23. መመሪው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ በኢንስቲትዩቱ ማናጅመንት ታይቶ በበላይ ኃላፊ ፀድቆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

ዶ/ር አስራት ጤራ

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር

12
13

You might also like