You are on page 1of 27

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሠራተኞች የክፍያና ጥቅማ ጥቅም መመሪያ፣

"ረቂቅ"

ሐምሌ 2015 ዓ/ም

i
ማውጫ
ማውጫ.............................................................................................................................................ii
ክፍል አንድ..........................................................................................................................................1
1. መግቢያ......................................................................................................................................1
2. አጭር ርዕስ.................................................................................................................................1
3. ትርጉም......................................................................................................................................1
ክፍል ሁለት.........................................................................................................................................3
2. የመመሪያው ዓላማ......................................................................................................................3
2.1. የመመሪያው አስፈላጊነት፤........................................................................................................3
2.2. የጥቅማ ጥቅም ክፍያ አወሳሰን፤.................................................................................................3
ክፍል ሦስት........................................................................................................................................4
3. የትርፍ ሰዓት ሥራ ስለመሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች.....................................................................4
3.1. እንደ ትርፍ ሰዓት የማይቆጠሩ ሥራዎች..............................................................................4
3.2. የትርፍ ሰዓት ሥራ የክፍያ ሂሣብ ስሌት እና አከፋፈል.............................................................5
3.3. የሾፊሮች ትርፍ ሰዓት ሥራ አበል አከፋፍል...........................................................................5
3.4. የመስክ አበል.........................................................................................................................5
3.5. በኮሚቴነት ለሚከናወን ሥራ የሚፈፀም አበል አወሳሰን፤.......................................................6
3.6. ልዩ ልዩ አበሎች አወሳሰን፤..................................................................................................6
3.7. የወተት አበል አወሳሰን፤......................................................................................................6
3.8. የጓዝ ማንሻ አበል፤................................................................................................................7
ክፍል አራት.........................................................................................................................................8
4. ደመወዝ..................................................................................................................................8
4.1. ዓመታዊ የደሞዝ ጭማሪ.......................................................................................................8
4.2. የምርታማነት ቦነስ /ጉርሻ......................................................................................................8
4.3. ሽልማት..................................................................................................................................9
4.4. የቤት አበል /House Allowance/...........................................................................................9
4.5. የኃላፊነት አበል...................................................................................................................10

ii
ክፍል አምስት....................................................................................................................................11
5. የሞባይል ካርድ ክፍያ እና የኢንተርኔት ወጪ አወሳሰን.................................................................11
5.1. የስልክ አጠቃቀም................................................................................................................11
5.1.1. የመደበኛ ስልክ አጠቃቀም............................................................................................11
5.1.2. ተንቀሳቃሽ ስልክ አጠቃቀም.........................................................................................11
5.2. የገመድ አልባ ኢንተርኔት (በራውተር) አጠቃቀም...................................................................11
5.3. መንጃ ፈቃድ በሚመለከት፡..................................................................................................12
5.4. የትራንስፖርት ስምሪትና አጠቃቀም.....................................................................................12
5.5. የቀን ውሎ አበል አወሳሰን፤...................................................................................................13
5.6. ማሽከርከር የማይችሉ በፑል ሰርቪስ የሚጠቀሙ መካከለኛ አመራሮች፡-................................13
5.7. ትምህርትና ስልጠና.............................................................................................................14
5.8. የመስተንግዶ አጠቃቀም......................................................................................................14
5.9. የህክምና ወጪ አወሳሰን፤.....................................................................................................14
ክፍል ስድስት....................................................................................................................................15
6. የማበረታቻ ስርአት አወሳሰን፤..................................................................................................15
6.1. የሠራተኛው ማበረታቻ እና ዕውቅና አሰጣጥ ስርአት አወሳሰን፤ መስፈርት................................15
6.2. የመመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን..............................................................................................16
ክፍል ሰባት........................................................................................................................................17
7. የባለስልጣኔ ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ..........................................................17
7.1. የባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች የባህሪ አፈጻጸም መለኪያ.......................................................18
7.2. የባለስልጣን መ/ቤቱ መካከለኛ አመራር የባህሪ አፈጻጸም መለኪያ............................................19
7.3. የባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች የአፈጻጽም መገምገሚያ.......................................................20

iii
ክፍል አንድ

1. መግቢያ
ይህ የክፍያና ጥቅማ ጥቅም ዋና ዓላማ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እና የመክፈል አቅም ጋር በተገናዘበ መልኩ በተሻለ

ሁኔታ ከማረጋገጥ ባሻገር እያንዳንዱ ሠራተኛ የግል የመፈፀም አቅሙን በራሱ ጥረት ጭምር እንዲጠናክር

እና የተሻለ አገልግሎት በጥራትና በቅልጥፍና እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

በመሆኑም ሠራተኛው የተሻሻለ የክፍያ፣ የጥቅማ ጥቅምና ማስተግበሪያ መመሪያ ማዘጋጀትና ተግባራዊ

ማድረግ አስፈልጓል፡፡

2. አጭር ርዕስ
ይህ መመሪያ " የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሠራተኞች የክፍያና ጥቅማ ጥቅም መመሪያ
" ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

3. ትርጉም
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1. “አዋጅ” ማለት የፌዴራል የመንግስት መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 ማለት ነው፤

2. “መመሪያ” ማለት የባለስልጣን መ/ቤቱ መሠረት አድርጎ የወጣውን የክፍያና ጥቅማ ጥቅም መመሪያ

የሚያስችል ስርአት ለመዘርጋት የተዘጋጀ መመሪያ ሰነድ ነው፤

3. “ክፍያ” ማለት አንድ ሠራተኛ በተቀጠረበት መሥሪያ ቤት ውስጥ ለሚሰጠው አገልግሎት በደመወዝ፣

በትርፍ ሰዓት፣ በማበረታቻ፣ በአበልና በጥቅማ ጥቅም ወይም በሌላ መልክ የሚፈጸም ክፍያ ነው፤

4. “ደመወዝ” ማለት በአንድ የሥራ ደረጃ ለተመደቡ ሥራዎች የተወሰነ መነሻ ክፍያ ወይም የእርከን

ክፍያ ነዉ፤

5. “አበል” ማለት፤ ሥራን ለማከናወን ከደመወዝ በተጨማሪ የሚያስፈልግ ክፍያ ሲሆን፤ የትርፍ ሰዓት

ክፍያንና ልዩ ልዩ አበሎችን የሚያካትት ነው፤

6. "የቀን ውሎ አበል" ማለት አንድ ሠራተኛ ከመደበኛ የሥራ ቦታው ወደ ሌላ ከተማ ለሥራ ሲጓዝ

የሚከፈል የቁርስ፣ የምሳ፣ የዕራት እና የመኝታ ወጪን የሚሸፍን ክፍያ ነው፤

7. "የአየር ፀባይ አበል" ማለት የመንግስት ሠራተኞች የአየር ፀባዩን ለመቋቋም እንዲረዳቸው በወር

ደመወዛቸው እና ውሎ አበል ላይ የሚከፈል የገንዘብ ክፍያ ነው፤

1
8. "የትርፍ ሰዓት ክፍያ" ማለት የመንግስት ሠራተኛው በአዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 35

በተደነገገው መሠረት በሁኔታዎች አስገዳጅነት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ ለሚሠራ ሠራተኛ

የሚፈፀም ክፍያ ነው፤

9. "የጓዝ ማንሻ አበል" ማለት አንድ የመንግስት ሠራተኛ ቀድሞ ይሠራበት ከነበረው ከተማ በዝውውር

ምክንያት ወደ ሌላ ከተማ ሲዘዋወር ጓዝ ለማጓጓዝ የሚፈፀም ክፍያ ነው፤

10. "የወተት አበል" ማለት አንድ የመንግስት ሠራተኛ በሚሠራበት ከተማ ውስጥ ከመሥሪያ ቤቱ ውጪ

ሥራ የሚያዘዋውረው በመሆኑ ምክንያት ለሚያደርገው እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን የትራንስፖርት

ወጪ እንዲሸፈንለት የሚወሰን ክፍያ ነው፤

11. "የቤት አበል" ማለት በቋሚ መመሪያ የተፈቀዱ፤ ከተቋማት ጥያቄ ለሲቪል ሰርቪስ ሲቀርብ እየተጠኑ

በኮሚሽኑ ወይም በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የሚፈቀዱ እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች

በተሰጣቸው ውክልና መሠረት አጥንተው የሚፈቅዷቸው ክፍያ ነው፤

12. "የኃላፊነት አበል" ማለት በመንግስት መሥሪያ ቤቶች በየደረጃው የሚገኙት የሥራ ኃላፊዎች

የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት በተጠያቂነትና በተነሳሽነት ማከናወን እንዲችሉ የሚወሰን የክፍያ

ስርዓት ነው፤

13. “ማበረታቻ” ማለት ከሥራ አፈጻጸም ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ሲሆን በሥራ አፈጻጸማቸው ተቋሙ

የሚያስቀምጠውን ውጤት ለሚያስመዘግቡ ወይም የራሳቸውን ፈጠራ በመጠቀም አዲስ ውጤት

ለሚያስመዘግቡ ሠራተኞች የሚሰጥ የክፍያ ዓይነት ነው፤

2
ክፍል ሁለት

2. የመመሪያው ዓላማ
ከፍተኛ እውቀትና ችሎታ ያላቸውን ባለሙያዎች ለመሳብ፣ ለማቆየትና እንዲሁም ሌሎች

ሠራተኞችን ለማትጋት ብሎም የሥራ ውጤታቸውን ለማሻሻል የሚያስችል የደመወዝ ስኬል፤ ጥቅማ

ጥቅምና ልዩ ልዩ የአከፋፈል ሥርዓት እንዲኖር ማድረግ ነው፤

2.1. የመመሪያው አስፈላጊነት፤


 በባለስልጣን መ/ቤት ውስጥ ሊኖሩ የሚገባቸውን የክፍያና ጥቅማ ጥቅም ሥርዓት ለማሳካት፤

 የሠራተኛው ክፍያ ከሥራ አፈጻጸም ላይ የሚመሰረት መሆኑን ለማስገንዘብ፣

 የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጥና ለህዝብ ተደራሻ


ለማድረግ፣

2.2. የጥቅማ ጥቅም ክፍያ አወሳሰን፤

ጥቅማ ጥቅም ክፍያ ማለት በቋሚ መመሪያ የተፈቀዱ፤ ከተቋማት ጥያቄ በጠቅላይ ሚኒስትር

ጽ/ቤት ወይም ስልጣን በአለው አካል የሚፈቀዱ እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በተሰጣቸው

ውክልና መሠረት አጥንተው የሚፈቅዷቸው ሲሆኑ እንደ የተቋማት የሥራ ባህሪ እና እንደ ደረጃ

መሠረት በማድረግ ወጥነት ባለው መልኩ እና ተቀራራቢነት ባለው ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ

የሚያስችል ስርአት ለመዘርጋት የሚቻልበትን አሠራር ከዚህ በታች እንደሚከተለው ቀርቦል፣

3
ክፍል ሦስት

3. የትርፍ ሰዓት ሥራ ስለመሚፈቀድባቸው ሁኔታዎች


የመንግስት ሠራተኛው በአዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 35 በተደነገገው መሠረት በሁኔታዎች

አስገዳጅነት ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ ለሚሠራ ሠራተኛ የሚፈፀም ክፍያ ሲሆን፡-

1. ማንኛው የስራ ክፍል ሥራው ከላስገደደ በቀር በዕቅዱ መሠረት በመደበኛ በመደበኛ የሥራ ሰዓት

ሥራዎች መጠናቀቅ ይኖርባቸዎል፡፡

2. በማንያው የትርፍ ሰዓት ተግባራዊ የሚደረገው የበላይ ኃላፊ እውቅና በጀት መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ

ነው፡፡

3. በተራ ቁጥር 1 በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት ማንኛውም የስራ ክፍል ትርፍ የሥራ ሰዓት ከዚህ

በታች ያሉት ዝርዝር ተግባራት ሲኖሩ ብቻ ነው፡፡

 በድንገት የተከሰተ ልዬ ሁኔታ ሲኖር እና በመ/ቤቱ ላይ አደጋ ያስከትላል ተብሎ ሲታሰብ፣

 የመ/ቤቱ የበላይ ሀላፊ ለአቅሙ በላይ የሆነ ልዩ ሁኔታ ገጥሞት ሠራተኞችን ለማሰራት ሲፈልግ፣

 ከጊዜ ገደብ ጋር በተያያዘ በመደበኛ የሥራ ጊዜ ሊጠናቀቅ የማይችል አስቸኮይ ሥራ ሲያጋጥም፣

 በሥራ ብዛት ምክንያት የሰው ሃይል ባለመመጣጠናቸው የተነሳ በጊዜ ተገድቦ መጠናቀቅ ጣለበትን

ሥራ ለማጠናቀቅ፣

 በስራ ክፍሉ የስራ ባህሪ ምክንያት የሚፈጠሩ አስገዳጁ ሥራዎችን ለማከናወን፣

 ሊቋረጥ የማይችል ተከታታይ ሥራ የሚሰሩ ሠራተኞችን ከሥራ ከቀሩ ለመተካት፣ እንዲሁም

የመ/ቤቱ የበላይ ሃላፊ የሚሰጡ ሥራዎች ያካትታል፣

3.1. እንደ ትርፍ ሰዓት የማይቆጠሩ ሥራዎች


 የመስክ ሥራ በውሎ አበል የሚሸፈን በመስክ ሥራ ምክንያት የባከነ ሰዓትን ለማካከስ ትርፍ ሥራ

ማከናወን፣

 ማንኛው የምርምር ሥራ በመደበኛ ሰዓት የሚከናወን በመሆኑ፣

 ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ የሚሰጥ ሥልጠና፣

 አግባብ ባለው የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ሳይፈቀድ የሚከናወን ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ

የሚከናወን ሥራ፣ሹፊሮች በማንኛው ጊዜ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ያላባቸው ሲሆን በየወሩ

ከመደበኛ ደመወዝ ጋር በቁርጥ አበል የሚከፈላቸው የትርፍ ሰዓት ማካካሻን ታሳቢ አድርጎ

በመሆኑ፣

4
 በሥራ ባህሪያቸው ምክንያት በሌሊት፣በሳምንት የእርፍት ቀን ወይም በባዓላት ቀን በመደበኛ

የሽፍት ፕሮግራም የተከናወኑ ሥራዎችናቸው፡፡

3.2. የትርፍ ሰዓት ሥራ የክፍያ ሂሣብ ስሌት


አንድ የመንግስት ሰራተኛ የሚያገኘው ደመወዝ ለ 30 ቀናት ሲካፈል በአንድ ቀን የሚያገኘው

ደመወዝ፣በቀን የሚያገኘው ደመወዝ ደግሞ ለ 8 ሰዓት ሲካፈል በአንድ ሰዓት የሚከፈለው

ደመወዝ ይሰጣል፡፡በዚህም መሠረት አንድ የትርፍ ሰዓት ሥራ የሚሠራ ሰራተኛ ቢያንስ

ከመደበኛ ደመወዙ በተጨማሪ

 ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4፡00 የሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ለመደበኛ ሥራ በሰዓት

የሚከፈለው ደመወዝ በ 1.25 ተባዝቶ ነው፣

 በሥረ ቀኖች ከቀኑ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡00 ሰዓት የሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ በሰዓት

የሚከፈለው ደመወዝ በ 1.5 ተባዝቶ ነው፣

 በህዝብ በዓላት ቀናት የሚሠራ የትርፍ ሰዓት ሥራ ሰዓት የሚከፈል ደመወዝ በ 2.50

ተባዝቶ አበሉ ይከፈለዋል፡፡

3.3. የሾፊሮች ትርፍ ሰዓት ሥራ አበል አከፋፍል


ሾፊሮች ከሥራ ባህሪያቸው አንፃር የትርፍ ሰዓት ክፍያ በልዩ ሁኔታ የሚያስፈልጋቸው

ሲሆን እንደሚከተው ይሆናል፣

 የመ/ቤቱ የበላይ ሃለፊዎች የዋና ዳይሬክተር እና ም/ዋና ዳይሬክተር ብረ 2000(ሁለት

ሺህ ብር) ሲሆን የፑል አገልግሎት የሚሰጡ ሾፊሮች ብር 150 በቁርጥ የሚከፈላቸው

ይሆናል፡፡

 ጥበቃና ፅዳቶች የትርፍ ሰዓት ክፍያ አይካተቱም፣

 ማንኛውም የትርፍ ሰዓት እስከ 2፡00 ሰዓት የተከናወነ ሥራ እንደ ትርፍ ሰዓት

አይቆጠርም፡፡

3.4. የመስክ አበል


 የዋና ዳይሬክተር፣ም/ዋና ዳይሬክተሮች በፋይናንስ ህግ መሠረት እየተከፈለ ባለዉ ላይ
በተጨማሪ 15‰ ከዉስጥ ገቢ ይከፈላቸዋል፡፡
 የአልጋ ክፍያ እስከ 5000 ብር በሚያቀርቡት ደረሰኝ መሠረት ይከፈላቸዋል፡፡
 መካከለኛ አመራሮች (ዳይሬክተሮች) በፋይናንስ ህግ መሠረት እየተከፈለ ባለዉ ላይ
በተጨማሪ 15‰ ከዉስጥ ገቢ ይከፈላቸዋል፡፡

5
 መካከለኛ አመራሮች (ዳይሬክተሮች) የአልጋ ክፍያ እስከ 2000 ብር በሚያቀርቡት
ደረሰኝ መሠረት ይከፈላቸዋል፡፡
 የቡድን መሪዎች በፋይናንስ ህግ መሠረት እየተከፈለ ባለዉ ላይ በተጨማሪ 10 ‰
ከዉስጥ ገቢ ይከፈላቸዋል፡፡
 ከቡድን መሪዎችበታችያሉ ሰራተኞች የአልጋ ክፍያ እስከ 1000 ብር በሚያቀርቡት
ደረሰኝ መሠረት ይከፈላቸዋል፡፡

3.5. በኮሚቴነት ለሚከናወን ሥራ የሚፈፀም አበል አወሳሰን፤


የመ/ቤቱ በሥራ ኃላፊነትም ሆነ በባለሙያነት ተመድበው የሚሠሩ ሠራተኞች ከመደበኛ ሥራቸው

በተጨማሪ በተለያዬ የኮሚቴ ሥራ ተመድበው እንዲሠሩ የሚደረግ በመሆኑ እና የኮሚቴ ሥራውን

ለመቀበልም የማይፈቅዱ ሲሆን ቢቀበሉም በውጤታማነት ለማከናወን የማይችሉ ሲሆን

ሠራተኞች በፈቃደኛነት መቀበል እንዲችሉ እና በውጤታማት ማከናወን እንዲችሉ አበል

ይኖረዎል፤

ከዚህ በላይ የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ አበል ሊፈቀድላቸው የሚገባው የግዥ አጽዳቂ ኮሚቴ፣

የግዥ ናሙና መራጭ ኮሚቴ፣ የዲሲፒሊን ኮሚቴ፣ የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ እና ሌሎች ኮሚቴዎች

ሲሆኑ በመደበኛ የአበል አከፋፈል ሥራዓት መክፍል ስለማይቻል የምሳ፣የቁርስ፣እና የሻይ ቡና

አበል የገበያውን ሁኔታ በአገናዘበ መልኩ ሊሆን ይገበዋል የመ/ቤቱ የበላይ ሃለፊ ሲፈቅድ

ተፈፃሚ የሚሆን ሲሆን መ/ቤቱ የምሳ፣የቁርስ፣እና የሻይ ቡና የሚያቀርብ ከሆነ አበል

አይከፈልም በተጨማሪም ኮሚቴው በሥራ ምክንያት ከመ/ቤቱ ውጭ ሥራዎችን የሚያከናውን

ከሆነ በመደበኛ የአበል አከፋፍል የሚስተናገድ ይሆናል፡፡

3.6. ልዩ ልዩ አበሎች አወሳሰን፤


ልዩ ልዩ አበሎች ለሠራተኞች የሥራ ባህርያቸውን መሠረት በማድረግ የሚወስን የወተት አበል፣

ሠራተኞች የሥራ ዝውውር በማድረጋቸው ምክንያት ለጓዝ ማንሻ የሚፈፀም፣ የትራንስፖርት

አበል፣ የመዘዋወሪያ አበል በመወሰን የሚፈፀም ክፍያ ሲሆን፡-

3.7. የወተት አበል አወሳሰን፤


የወተት አበል የመንግስት ሠራተኞች የተመደቡበት የሥራ መደብ ቦታና የሥራ ጸባይ ከግምት

ውስጥ በማስገባት በየመንግስት መሥሪያ ቤቱ እየተጠናና በኮሚሽኑ ፍቃድ ሲያገኝ ክፍያው

የሚፈጸም ሲሆን፣

6
 እንደ የሥራ ሁኔታ የወተት አበል የሚገባቸውን የሥራ መደቦች በጥናት ተለይተው በበላይ ሃለፊ

ሲፀድቅ ተግባራዊ ይሆናል፣

 በጥናት የተለዩት የሥራ መደቦች በጤና ላይ ጉዳት ማስከተል አለማስከተላቸውን ከሚመለከተው

የጤና ባለሙያ ተረጋግጠው ሲቀርቡ ተጠቃሚ ይሆናሉ፣

3.8. የጓዝ ማንሻ አበል፤


አንድ የመንግስት ሠራተኛ ቀድሞ ይሠራበት ከነበረው ከተማ በዝውውር ምክንያት ወደ ሌላ ከተማ

ሲዘዋወር ጓዝ ለማጓጓዝ የሚከፈል አበል ሲሆን ወጥነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል

እንደ ገበያው ሁኔታ በሚመለከተው ክፍል ተረጋግጦ በበላይ ሃላፊ ሲፀድቅ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

7
ክፍል አራት

4. ደመወዝ በተመከተ

ደመወዝ በአንድ የሥራ ደረጃ ለተመደቡ ሥራዎች የተወሰነ መነሻ ክፍያ ወይም የእርከን ክፍያ ሲሆን፤

በጥናት ላይ ተመሥርቶ ይዘጋጃል፡፡ የደመወዝ ሥርዓት የሚዘረጋው የሥራ ገበያ ሁኔታን (አቅርቦትንና

ፍላጎትን)፣ የመክፈል አቅምን፣ የኑሮ ሁኔታን፣ የመንግሥት ሕጎችና የመሳሰሉትን ግምት ውስጥ

በማስገባት ነው፡፡ በመሆኑም ሠራተኛውን ብቃት ያላቸው ሠራተኞችን ከገበያ ለመሳብ፣ በሥራ ላይ

ያሉትንም በማበረታታት በሥራ ላይ ለማቆየት፣ በገበያው ተወዳዳሪ ሆኖ ብቃትና ፍላጎት ያላቸውን

ሠራተኞች መሳብ የማያስችል፤ ፍትሃዊ ያልሆነና ከፊል ያህሉ የመንግሥት ሠራተኛ ከድህነት ወለል

በታች እንዲኖሩ የሚያደርግ በመሆኑ የመንግሥት የመክፈል አቅምን ከግምት ውስጥ ያስገባ የተሻሻለ

የደመወዝ ስኬል በማጥናት ለመንግሥት እንዲቀርብ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡

4.1. ዓመታዊ የደሞዝ ጭማሪ


 ባለስልጣን መ/ቤቱ የሰራተኞች ምርታማነትን እንዲሁም የምርት ብዛት እና ጥራት
ብሎም አመታዊ የተሰበሰበውን ገንዘብ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ሰራተኞች
ዓመታዊ የደሞዝ ጭማሪ ያደርጋል፡፡
 ድርጅቱ በዚሁ ስምምነት መሰረት በበጀት አመቱ መጨረሻ ከሰበሰበው ብር ተፈፃሚ
የሚሆን ግብር፣ ለመንግስት የሚከፈል እና ህጋዊ መጠባበቂያ ገንዘብ ከቀነሰ በኋላ
አመታዊ የደሞዝ ጭማሪ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ዝርዝር ሁኔታው በፋይናንስ በኩል
ይዘጋጃል፣
 እስከ ብር 1,000 እስከ 4000 ደሞዝ የሚያገኙ ሰራተኞች 8 ከመቶ ጭማሪ
 ወርሃዊ ደሞዛቸው ከብር 4,000 በላይ እና እስከ ብር 12,000 ለሚያገኙ ሰራተኞች 7
ከመቶ ጭማሪ እና
 ከብር 12,000 በላይ ለሚያገኙ ሰራተኞች 6 ከመቶ ጭማሪ ይሆናል፡፡

4.2. የምርታማነት ቦነስ /ጉርሻ


 የባለስልጣኑ መ/ቤት በስራው ውጤታማ ከሆነና የሥራ አፈፃፀም ውጤቱን
በሚመለከተው ክፍል ከተረጋገጠ የደመወዙ ከአንድ ወር እስከ ሦስት ወር በጉርሻ መልኩ
የሚከፍል ይሆናል፡፡
 የጉርሻ/ማበረታቻ እና የክፍያ ሁኔታ ብቁነት መስፈርትን በተመለከተ ከታች በተቀመጠው
መመዘና መሥፈርት መሰረት ይሆናል፡፡
8
4.3. ሽልማት
አንድ ሰራተኛ ምርጥ ውጤትን ለማሳካት (ለምሳሌ ስርቆትን መከልከል፣ ብክነትን መቀነስ እና
ወጭን በመቆጠብ ምርታማነትን ለማሻሻል በስራ አፈፃፀሙ ላይ ውጤታማነት ማሳየት እና ፈጠራ
ሃሳቦችን ማፍለቅ ብሎም አዲስ ተፈፃሚ የስራ ቴክኒክ እና ሃሳብ መፍጠር) የመሳሰሉትን
የሚያስችሉ ከመጠን በላይ ያለፈ ጥረት ማድረጉን ወይም ይህንን ስርዓት መፍጠሩ በድርጅቱ
በሚረጋገጥበት ጊዜ ላቀረበው ሃሳብ እውቅና ለመስጠት ያህል መ/ቤቱ የተለየ ሽልማት ለሰራተኛው
ሊሰጥ ይችላል፡፡ አፈፃፀም ዝርዝሩም በመ/ቤቱ ይዘጋጃል፡፡

4.4. የቤት አበል /House Allowance/


በመንግስት መሥሪያ ቤቶች በየደረጃው የሚገኙት ኃላፊዎችና ሠራተኞች የተሰጣቸውን ኃላፊነት

በአግባቡና በወቅቱ እንዲወጡ ለማስቻል የወቅቱን የቤት ኪራይ ወጪ ንብረት በተወሰነ መልኩ ለማገዝ

የሚከፈል የጥቅማ ጥቅም አይነት ሲሆን የአበል አከፋፈል ስርዓቱ የሚከተሉት መስፈርቶች ይኖሩታል፣

 በአገሪቱ ያለውን የመንግስትና የግል የቤት ኪራይ ዋጋን ግምት ውስጥ ያስገባ አማካይ የዋጋ ተመን

ጥናት መሠረት ያደረገ ይሆናል፤

 የክልል እና የከተማ አስተዳደሮች ለመንግስት ሠራተኞቻቸው የሚከፍሉትን የቤት ኪራይ አበል መረጃ

መሰረት ያደረገ፤

 መንግሥታዊ የሆኑ የልማት ድርጅቶችና ተቋማት የሠራተኞች ጥቅማ ጥቅምና ሌሎች ክፍያዎችን

መሰረት በአደረገ መልኩ፤

 የመንግስት ሠራተኞችን የደመወዝ መጠን መነሻ በማድረግ ከወቅቱ የኑሮ ሁኔታ ጋር የተገናዘበ

መሆኑን ይሆናል፤

 ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ትንተና በመሥራት የቤት ኪራይ አበል መነሻ ጥናት በወጥነት

ለመተግበር የሚያስችል በአማራጭ በማዘጋጀት ይህ የአበል ክፍያ ተቀምጧል፣

ስለሆነም የአንደ ሥራተኛ የደመወዙ ¾ ይከፈለዋል ስለሆነም የአንድ ሰራተኛ ደመወዝ 10,000(አስራ

ሺህ ብር ) የቤት አበሉ 3,330 (ሦስት ሺህ ሦስት መቶ ሰላሳ ብር) ይሆናል ማለት ነው

 የመንግስ ሹመኞች ጥቅማ ጥቅም መሠረት ይሆናል፣

4.5. የኃላፊነት አበል

በመንግስት መሥሪያ ቤቶች በየደረጃው የሚገኙት የሥራ ኃላፊዎች የተሰጣቸውን የሥራ ኃላፊነት
በተጠያቂነትና በተነሳሽነት ማከናወን እንዲችሉ የሚወሰን የክፍያ ስርዓት ሲሆን፤

የሚከተሉት መስፈርት ሊያሞላ ይገባዎል፣

9
 በተቋማት ውስጥ እንደ የሥራ ፀባያቸው የተለዩ እና የኃላፊነት አበል ክፍያ መጠን የተወሰነላቸውን

የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች የሥራ ሁኔታ እና ውስብስብነት የሥራ ባህሪ ያለ ሲሆን፤

 ያሉ የሥራ ኃላፊነት ቦታዎች ውሳኔ የመስጠት እና የተጠያቂነት የሚያስከትሉ ስለመሆናቸው፣

የሥራ ክፍል ኃ ላፊዎች ሥራቸውን በሃላፊነት መወጣት እንዲችሉ

 በቁርጥ ክፍያ ዋና ዳይሬክተር 7000 (ሰባት ሺህ ብር) ም/ዋና ዳይሬክተር 6000(ስድስት ሺህ ብር)

ለሥራ ክፍል ሃላፊ 3000 (ሦስት ሺህ ብር) ይሆናል

ክፍል አምስት

5. የሞባይል ካርድ ክፍያ እና የኢንተርኔት ወጪ አወሳሰን


የመ/ቤቱ በኃላፊነት የሥራ መደቦች ላይ ተመድበው የሚሰሩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ከቢሮ

ለተለያዩ ሥራዎች ስለሚንቀሳቀሱና ሥራቸው ዘወትር ከተቋም የበላይ ኃላፊዎችና ከተለያዩ አካላት ጋር

ግንኙነት ማድረግ የሚጠይቅ በመሆኑ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ወጪና በዕረፍት ቀናትም የሚደረጉ የሥራ

ግንኙነቶችን ለማሳለጥ የሚፈከፈል የአበል አይነት ሲሆን፡-

10
5.1. የስልክ አጠቃቀም

5.1.1. የመደበኛ ስልክ አጠቃቀም


ለመንግስት ስራ አገልግሎት የሚውል የመደበኛ ስልክ ለዳይሬክተሮች፣ ለጽ/ቤት ኃላፊዎች እና

ለአማካሪዎች የሚኖራቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ የስራ ኃላፊና ባለሙያ የተመደበው ወርሃዊ

የመደበኛ/የቀጥታ የስልክ ጣሪያ 400 ብር ነው፡፡ የስልክ አጠቃቀሙ ከተቀመጠው የገንዘብ ጣሪያ

በላይ ሆኖ በቂ ማብራሪያ ሊቀርብለት ካልቻለ እና ያቀረበው ምክንያት አጥጋቢ (በቂ) ሆኖ

ካልተገኘ በእላፊ ጥቅም ላይ የዋለውን ከተጠቃሚው ወይም ተጠቃሚዎች ደመወዝ ተቀንሶ

ተመላሽ ይደረጋል፡፡ ዓለም አቀፍ የስልክ ግንኙነቶች ሊደረጉ የሚችሉት በበላይ አመራሩ

እውቅና ብቻ ነው፡፡

5.1.2. ተንቀሳቃሽ ስልክ አጠቃቀም


 የዋና ዳይሬክተር፣ም/ዋና ዳይሬክተሮች ለቢሮ መደበኛ ስልክ በየወሩ ብር 1‚000 ፣ለሞባይል

ብር 1‚500 ይከፈላቸዋል፡፡

 ለመካከለኛ አመራሮች ለቢሮ መደበኛ ስልክ በየወሩ ብር 800፣ ለሞባይል ብር 1‚000


ይከፈላቸዋል፡፡
 ለቡድን መሪዎች ለሞባይል በየወሩ ብር 300 ይከፈላቸዋል፡፡

 ለሥምሪት ሠራተኞች ለሞባይል በየወሩ ብር 250 ይከፈላቸዋል፡፡

5.2. የገመድ አልባ ኢንተርኔት (በራውተር) አጠቃቀም


 በመ/ቤታችን ባለው የብሮድባንድና ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ሁሉም ሰራተኛ

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

 ለመካከለኛ አመራሩና የስራ ጫና ላለባቸው ክፍሎች ገመድ አልባ ኢንተርኒት(ራውተር)

ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

 ለኢንተርኔት (CDMA/EVDO) ለሚጠቀሙት ጥቅል የኢንተርኔት ፓኬጅ የሚከፈል መሆኑ

 ለዋና ዳይሬክተር፣ም/ዋና ዳይሬክተሮች 4G በወር እስከ ብር 800.00 (ስምንት መቶ)

እንዲጠቀሙ ይደረጋል፡፡

 ለዳይሬክተሮች 4G በወር እስከ ብር 600.00 (ስድስት መቶ) እንዲጠቀሙ ይደረጋል፡፡

 በዚህ የዉስጥ መመሪያ ከተፈቀደላቸው የገንዘብ ጣሪያ በላይ የተጠቀሙ ኃላፊዎች በወሩ

መጨረሻ የመጣውን የክፍያ ልዩነት ከወር ደመወዛቸው ላይ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡

5.3. መንጃ ፈቃድ በሚመለከት፡-

11
መንጃ ፈቃድ ለሌላቸው መካከለኛ አመራሮች ማሽከርከር ለማይችሉ አመራሮች በመስሪያ ቤቱ

ድጋፍ መንጃ ፍቃድ እንዲያወጡ ይደረጋል፣ሆኖም መንጃ ፈቃድ የሚያወጣ አመራር ማስረጃ

የሚያቀርብ ሲሆን ከሁለት ጊዜ የወደቀ አመራር ወጭውን በራሱ ይሸፍናል፡፡

5.4. የትራንስፖርት ስምሪትና አጠቃቀም


በባለስልጣን መ/ቤቱ ዳይሬከተሮች አንስቶ እሰከ ፈፃሚ ባለሙያዎች ያለው የተሽከርካሪ ስምሪት

ስራን መሰረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል፡፡ በሌላ አገላለፅ ለመካከለኛ አመራሩም ሰርቪስ የሚሰጠው

በጥቅማ ጥቅም ታሳቢ ሆኖ ሳይሆን አመራሩ ከስራ ሰዓት በተጨማሪ አምሽቶና ከስራ ቀን ውጭ

ገብቶ የመስራት ተጨማሪ ኮሚትመንት ያለበት መሆኑን ታሳቢ ተደርጎ ነው፡፡

የሚያሽከረክሩ መካከለኛ አመራሮች በኃላፊነት መኪና የመ/ቤቱ መ/ቤቱ መኪና ካለው

ይሰጣል፤ሆኖም የነዳጅ አጠቃቅም የባለስልጣን መ/ቤቱ የትራንስፖርት ስምሪት ክፍል

በሚመለከታቸው አካላት ኖርማላይዚሽን በማሰራት በወር በሳምት በቀን የሚያስፈልጋቸውን የነዳጅ

ፍጆታውም መጠን ለመ/ቤቱ ሃላፊ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል ሲወሰነም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ሆኖም

መ/ቤቱ የመኪና እጥረት ከገጠመው በፑል ሰርቪስ ተሸከርካሪ እንዲመደብ ያደርጋል ፡፡የፕሮቶኮል

ሠራተኞች የፑል ሰርቪስ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሆናሉ፡፡ እንደሁኔታ የሰራተኛው የሰርቪስ አገልግሎት

ያቀርባል፡፡

5.5. የቀን ውሎ አበል አወሳሰን፤


የውሎ አበል አንድ ሠራተኛ ከመደበኛ የሥራ ቦታው ወደ ሌላ ከተማ ለሥራ ሲጓዝ የሚከፈል የቁርስ፣

የምሳ፣ የዕራት እና የመኝታ ወጪን የሚሸፍን ክፍያ የመንግሥት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል
አፈፃጸም መመሪያ ቁጥር 3/2012 መሠረት ሁለት እጥፍ ይሆናል፣
 የውሎ አበል ለመ/ቤቱ የስራ ጉዳይ ከመኖሪያ ቤታቸው ውጭ ለሚላኩ ሰራተኞች
ምግባቸውን፣ መዝናኛ፣ ትራንስር እና ሌሎች ተመሳሳይ አስፈላጊ ወጭዎች ለመሸፈን
የሚሰጥ ነው፡፡
 የውሎ አበሉን በቅድሚያ የሚወስድ ይሆናል በመስክ ሥራ ላይ ቅድመ ክፍያ ማስተካከያ
ወይም ክፍያን ለማረጋገጥ የስራ ቀናቱ በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ አማካኝነት ሊራዘም
ይችላል፡፡
 ማንኛውም የመ/ቤቱ ሰራተኛ ከመደበኛ የሥራ ቦታ ውጭ ወደ ሌላ ሥራ ቦታ ለሥራ ጉዳይ

ከመላኩ በፊት የቀን ውሎ አበል መጠየቂያ፣መክፈያና መፍቀጃ ቅፆች ለጉዳዩ አግባብ ባለው

ሠራተኛ ወይም የሥራ ኃላፊ እንዲሞላ ያደርጋል ስለትክክለኛነቱ በፊርማው ያረጋግጣል፣


12
5.6. ማሽከርከር የማይችሉ በፑል ሰርቪስ የሚጠቀሙ መካከለኛ አመራሮች፡-
መ/ቤታች በፑል አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች ነዳጅ አጠቃቀም በሚሰጣቸው ስምሪት

መሰረት ኪሎ ሜትርን ታሳቢ በማድረግ እንደሚሞሉ ይደረጋል፡፡ የቆዩና ያረጁ መኪናዎች የነዳጅ

ፍጆታቸው ከፍተኛ በመሆኑ መኪናዎቱ የሚጓዙበትን ኪሎ ሜትር በማስጠናት የነዳጅ

አጠቃቅማቸውን በማይት ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

መ/ቤቱ ስራ አገልግሎት ስምሪት ተሰጧቸው ለሚሰሩ ተሽከርካሪዎች የተጓዙትን ኪሎ ሜትር

በስምሪት ክፍል በሚያዘጋጀው ፎርም እይተመዘገበ ለወሩ የተፈቀደው ነዳጅ ሲያልቅ ተጨማሪ ነዳጅ

እንዲሞላላቸው ይደረጋል፡፡

ነገር ግን ከከተማ ውጭ ፊልድ ለሚሄዱ ተሸከርካሪዎች ነዳጅ የሚሞላው መኪናው በአንድ ሌትር

ስንት ኪሎሜትር እንደሚሄድ ታሰቢ በማድረግ በተዘጋጀ የአሰራር ስርዓት መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡

በተጨማሪም ዳሬክተሮች የያዙትን መኪና ሰርቪስ ከተጠቀሙ በኋላ ባለስልጣን መ/ቤቱ ለከተማ

ውጭ ለተጨማሪ ስራ ሲታዘዝ ተሸከርካሪው በመውጫ እየታዘዘ የሄደበትን ኪሎ ሜትር

እየተመዘገበ ለወር የተፈቀደው ነዳጅ ሲያልቅ በፒቲካሽ ተጠይቆ ግዥ ይፈፀማል፡፡

5.7. ትምህርትና ስልጠና


ስለሆነም መመሪያው ከመጽደቁ በፊት በትምህርትና ስልጠና በዝቅተኛ ደረጃ ያሉ ሰራተኞችን

(ማለትም የትምህርት ዝግጅታቸው ከዲፕሎማ በታች ያሉ) እንዲያሻሽሉ ድጋፍ ይደረጋል፡፡ሆኖም

በመ/ቤቱ ውስጥ ተቀጥረው አንድ ዓመት ማገልገል ይገለገሉ እና በትምህርት እና ስልጣና

መሰረት ውል መፈፀሚ የሚችል መሆን አለበት፡፡

5.8. የመስተንግዶ አጠቃቀም


ባለስልጣን መ/ቤቱ የመስተንግዶ አጠቃቀም የሠራተኞች መገልገያ ካፌ ሲሆን ለሰራተኞች የቁርስ፣

ምሳ እና ሻይ ቡና እንዲሁም በስብሰባ ወቅት ውሀ፣ ሻይና ቡና ለተሰብሳቢ ተመጣጣኝ ዋጋ

በማቅረብ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ለመከካከለኛ አመራሩ እንግዶች ሲመጡ እና ለተሰብሰባዎች

መስተንግዶ ያቀርባል፡፡

13
5.9. የህክምና ወጪ አወሳሰን፤

የህክምና አበል የመንግስት ሠራተኛው ከተጣለበት ኃላፊነት አኳያ በየደረጃው የሚገኙት ኃላፊዎች፤

ባለሙያዎችና ሠራተኞች ተግባራቸውን በአግባቡና በኃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል አሁን ካለው

የህክምና ወጪ ንረት በተወሰነ መልኩ ለማገዝ እንዲቻል በጥናት ላይ ተመሥርቶ የሚወሰን የጥቅማ

ጥቅም ስርአት ሲሆን፡-

 የሠራተኛውን የነፍስ ወከፍ ገቢ፣ ከፍሎ የመታከም አቅም፣ የኑሮ ሁኔታን፣ከግምት ውስጥ በማስገባት

በመንግሰት እና በግል ሆስፒታል ከትንሽ እስከ ትልቅ ያለውን የህክምና ወጪ በተገቢው መንገድ

መረጃዎች በማቅረብ የህክምና ወጭውን 50‰ ሲሆን በህክምና ወጭ የሚሸፈኑ የቤተሰብ አካለት

የመ/ቤቱ ባልደረባ የትዳር አጋር እና 18 ዓመት ያልሞላቸው ልጆች ብቻ ይሆሆናሉ፡፡ማንኛውም


ሰራተኛ በመስክ ሥራ ላይ እያለ ህመም ቢገጥመው በአካባቢው በሚገኝ ማንኛውም የቅርብ
ሆስፒታል ህክምና ካገኘ በኋላ የህክምና ወረቀት ማቅረብ ያለበት ሲሆን ምስክር ወረቁ
ተቀባይነት ካገኘ የህክምና ወጭ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

ክፍል ስድስት

6. የማበረታቻ ስርአት አወሳሰን፤


የማበረታቻ ክፍያ ከሥራ አፈጻጸም ጋር በቀጥታ የሚያያዝ ሲሆን ተቋማት የተሰጣቸውን ተግባርና

ኃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚከናወን የክትትልና ግምገማ ስርአት ውጤታማ

የሆኑ ተቋማት እየተለዩ ዕውቅና የሚሰጥበት እና የተቋሙ ተልዕኮ ከማሳካት አኳያ የተለዩ የትኩረት

መስኮች፣ ግቦችና ዒላማዎችንና ወይም የአፈጻጸም ደረጃዎችን እንዲሁም ቁልፍ የውጤት

አመልካቾችን በመውሰድ በአፈጻጸማቸው ውጤታማ የሆኑ አንዲሁም የራሳቸውን ፈጠራ በመጠቀም

አዲስ ውጤት ለሚስመዘግቡ ሠራተኞች በክፍያ ወይም በአይነት ወይም ዕውቅና በመስጠት የሚፈፀም

ይሆናል፡፡

6.1. የሠራተኛው ማበረታቻ እና ዕውቅና አሰጣጥ ስርአት አወሳሰን፤ መስፈርት


@ በውጤት ላይ የተመሰረተ የሥራ አመራር ሥርአት ለመዘርጋት የሚያስችል ዕቅድና ለአሰራር ስርአት

ዝርጋታው የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ መሰረት የተመዘነ ሲሆን፣

@ የተቋማት ተገልጋዮች በአገልግሎት አሠጣጥ ላይ ስለ ተቋሙ የሚሰጡትን አስተያዬት የተሰጠ

ውጤት፤

14
@ የተቋማት ዕቅድ የሀገሪቱን የትኩረት መስኮች፣ ግቦችና ዒላማዎችንና ወይም የአፈጻጸም

ደረጃዎችን እንዲሁም ቁልፍ የውጤት አመልካቾችን እና ዋና ዋና ተግባራትን ያስቀመጠ መሆኑን

ማረጋገጥ የሚያስችል ቼክ ሊስት በማስቀመጥ፣ የውጤት መገምገሚያ ስርአት መኖሩን ማረጋገጥ፤

@ እንደ መ/ቤቱ ከተቀመጡ ግቦች ጋር የተናበቡ የተቋም ዕቅድ በጥራት፣ ሊመዘንና ሊለካ በሚችል

መልኩ መሆኑን ማረጋገጥ፤

@ ከታች በተቀመጡት የውጤት መግለጫ መሠረት ሰራተኛ ከተወዳደሩ ሰራተኞች መካከል አብላጫ

ያመጠው ማበረታቻ እና ዕውቅና አሰጣጥ ስርአት ተመረጭ ይሆናል፡፡

6.2. የመመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን


ይህ መመሪያ በበለስልጣን መ/ቤቱ በቋሚነት እና በኩትራት ተቀጥረው በሚሰሩ ሰራተኞች ላይ

ተፈፃሚ ይሆናል ከአንድ አመት በላይ ትምህርት እና ስልጠና ለሚሂዱ ሰራተኞችን አይመለከትም

15
ክፍል ሰባት
የሥራ አፈጻጽም ቅፅ

ቅጽ-1

7. የባለስልጣኔ ሠራተኞች የሥራ አፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ

የሠራተኛው ስም

የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ

የሥራ ክፍል

የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጊዜ ከ እስከ

በግለሰብ የተሰጠ ነጥብ 25% በቡድን የተሰጠ ነጥብ 37.5% በቡድን ኃላፊ የተሰጠ ነጥብ 37.5%

(የተግባራትና ባህሪ አፈጻጸም) ድምር (የተግባራትናባህሪ አፈጻጸም አማካይ)

የሶስቱ ገምጋሚዎች አማካይ ውጤት 100%

የሥራ አፈጻጸም ግምገማውን የመራው ኃላፊ አስተያየት

ፊርማ ቀን

የፈጻሚው አስተያየት

16
ፊርማ ቀን

ከቅርብ ኃላፊው ቀጥሎ ያለው ኃላፊ አስተያየት

ፊርማ ቀን

ቅጽ-2

7.1. የባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች የባህሪ አፈጻጸም መለኪያ


የሠራተኛው ስም የሥራ መደብ መጠሪያ ደረጃ

ለመገለጫው የአፈጻጸም ደረጃ

ተ.ቁ የባህሪ መገለጫዎች የተሰጠ አስተያየት


5 4 3 2 1
ክብደት
1 ፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና 25%

ተግባርን ለማስወገድ የሚያሳየው

ጥረትና ዝንባሌ
2 ብቃት ለማሳደግ የሚያደርገው ጥረት 20%
3 ለተገልጋዩ የሚሰጠው ክብርና 15%

በማገልገሉ የሚሰማው ኩራት


4 ሌሎችን ለመደገፍና ለማብቃት 15%

የሚያደርገው ጥረት
5 አሠራሩን ለማሻሻልና በኢኮቴ 15%

ለማስደገፍ የሚያደርገው ጥረትና

17
ዝንባሌ
6 የአፈጻጸም ግብረ መልስ በወቅቱን 10%

በአገባቡ የመስጠትና መቀበል ዝንባሌ


የተጠቃለለ ውጤት 100%

ከ 40%

5 የላቀ አፈጻጸም፣ 4 ከፍተኛ አፈጻጸም 3 መካከለኛ 2 ዝቅተኛ 1 በጣም ዝቅተኛ

ማሳሰቢያ፡- የእያንዳንዱን ባህሪ ምዘና ነጥብ ሲሰጥ ለእያንዳንዱ የተሰጠው ክብደት ለአምስት ተካፍሎ

የተገኘው ውጤት በየአፈጻጸም ደረጃው በተሰጠ ነጥብ ተባዝቶ ይቀመጣል፡፡ በየባህሪ መገለጫው

የተቀመጡ ውጤቶች ተዳምረው በመጨረሻ ከመቶ ይቀመጣል፡፡

ቅጽ-3

7.2. የባለስልጣን መ/ቤቱ መካከለኛ አመራር የባህሪ አፈጻጸም መለኪያ


የሠራተኛው ስም የሥራ መደብ መጠሪያ ደረጃ

ለመገለጫው የአፈጻጸም ደረጃ

ተ.ቁ የባህሪ መገለጫዎች የተሰጠ አስተያየት


5 4 3 2 1
ክብደት
1 ፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና 25%

ተግባር ለማስወገድ የሚያደርገው

ጥረት
2 የአመራር ብቃት ለማሳደግ 20%

የሚያደርገው ጥረት
3 ለተገልጋዩ የሚሰጠው ክብርና 15%

በማገልገሉ የሚሰማው ኩራት ሌሎችን

ለማብቃት ለማበረታታት ያለው

ዝንባሌ
4 ከቡድን አባላት ጋር ተግባብቶ 15%

18
የመሥራት ዝንባሌና የቡድን

ውጤታማነትንን ለማሳደግ የሚያደርግ

ጥረት
5 በኢኮቴ ለማስደገፍ የሚያደርገው 15%

ጥረትና ዝንባሌ፣ የሂደቱን አፈጻጸም

ለማሻሻልና አሠራሩን
6 የአፈጻጸም ግብረ መልስ በወቅቱን 10%

በአገባቡ የመስጠትና መቀበል ዝንባሌ


የተጠቃለለ ውጤት 100%

ከ 40%

5 የላቀ አፈጻጸም፣ 4 ከፍተኛ አፈጻጸም 3 መካከለኛ 2 ዝቅተኛ 1 በጣም ዝቅተኛ

ማሳሰቢያ፡- የእያንዳንዱን ባህሪ ምዘና ነጥብ ሲሰጥ ለእያንዳንዱ የተሰጠው ክብደት ለአምስት ተካፍሎ

የተገኘው ውጤት በየአፈጻጸም ደረጃው በተሰጠ ነጥብ ተባዝቶ ይቀመጣል፡፡ በየባህሪ መገለጫው

የተቀመጡ ውጤቶች ተዳምረው በመጨረሻ ከመቶ ይቀመጣል፡፡

ቅጽ-4

7.3. የባለስልጣን መ/ቤቱ ሠራተኞች የአፈጻጽም መገምገሚያ


(የተግባራት ውጤት መገምገሚያ ከ 60% የሚወሰድ)

የሠራተኛው ስም የሥራ መደብ መጠሪያ ደረጃ

የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ጊዜ ከ እስከ

አፈጻጸም የተግባራት አፈጻጸም


ለመለኪያ
ተ.ቁ የአፈጻጸም ግብ ተኮር ተግባራት ከ 100% ድምር
የተሰጠ የተሰጠ ነጥብ
የሚኖረው
ነጥብ 5 4 3 2 1
ክብደት
1 ጥራት
መጠን

19
ጊዜ
2 ጥራት
መጠን
ጊዜ
3 ጥራት
መጠን
ጊዜ
4 ጥራት
መጠን
ጊዜ
የሠራተኛው ስም የቡድን አባላት/ የቅርብ ኃላፊ ስም ፊርማ

ፊርማ

20
1
yÆH¶Y BÝT mlkþÃãC
KBdT mlkþÃ yxfÉ{M mr© MNu
R (Comptencies)
{r kþ‰Y sBúbþnT xmlµkTÂ 25%  bxmlµkTM btGÆRM bkþ‰Y  kþ‰Y sBúbþnTN ymdgû wYM
tGÆRN l¥SwgD y¸ÃdRgW _rT sBúbþnT xzù¶T WS_ ymÝwM xZ¥¸ÃN y¸Ãú† L† L
xlmWdqÜ# ኪራይ ሰብሳቢነትን mr©ãC #
የመታገሉ አዝማሚያ፣  y ፀ r kþ‰Y sBúbþnT wYM yk
 የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን sBúbþnT DRgþT mr©#
ለማድረቅ የወጡ ስትራቴጂዎችን
የመፈጸም ብቃት፣
BÝtÜN l¥údG y¸ÃdRgW _rT 20% BÝtÜN l¥údG ያቀረበው ዕቅድና  ÃqrÆcW ‰SN ¥BqEà PéjKè
አፈጻጸም ንጽጽር xGÆBnT#
 kl¤lÖC lm¥R ÃlW QNnT\
 tGƉêE ÃdrUcW ‰SN y¥B
PéjKèC xfÚ[M#
ltgLU† y¸s ጠው ክብርና በማገልገሉ 15% SlxgLGlÖT xsÈ«ù btgLU† wYM bo  kWu wYM kWS_ tgLUY y¸sb
የሚሰማው ኩራት ‰ ÆLdrïcÜ y¸s_ GBr mLS mr© §Y Ymsr¬L\

l¤lÖCN lmdgFÂ l¥BÝT 15%  ll¤lÖC DUF ለመስጠት ያቀረበው  DUF ysÈcW GlsïC SltsÈcW D
y¸ÃdRgW _rT# ዕቅድና አፈጻጸም ንጽጽር# ‰T bmr© xSdGfW y¸ÃqRbùT
 yDUû W«¤¬¥nT# xStÃyT\
 ÃbÝcWÂ ydgÍcW GlsïC B²T #
x¿‰„N l¥ššL y¸ÃdRgW _rT 15%  x¿‰RN l¥ššL ÃqrÆcW ¦úïC  xfÉ{ÑN kgþz¤#_‰T m«N
yxþNæR»>N ÷Ñnþk¤>N wYM PéjKèC# XNÄþššL ÃqrbWN ¦úB tG
t½KñlÖ ጂ N የመጠቀም ZNÆl¤  b¥ššÃ £dtÜ ÃlW túTæ# Sl¥Drgù\
 xs‰„N bxþ÷t½ lmdgF ÃdrgW
ÃSgßW ውጤት #
yxfÚ[M GBr mLS bwQtÜ 10 % bxfÉ{M GMg¥ wQT ÃlW túTæ፣  £îCN xãN¬êE bçn xGÆB S
bxGÆbù የመስጠትና መቀበል ዝንባሌ  l‰sù t=Æ ጭ £S b¥QrB# ytmzgbù mr©ãC #
 ll¤lÖC t=Æ ጭ £S b¥QrB#  tgbþ yçnù £îCN tqBlÖ kmtGb„
ytmzgbù mr©ãC #

የአፈጻጸም የባሕሪ አፈፃፀም ደረጃ መግለጫ


ደረጃ
4 የላቀ የአፈጻጸም ደረጃ ሲሆን ከ 95 – 100% ባለው የአፈጻጸም ውጤት ክፍል ውስጥ ይወድቃል፣ በእዚህ ደረጃ
ውጤት ያለው ግለሰብ በአርአያነት የሚጠቀስ አፈጻጸም ያለው ነው፤ በእዚህ ደረጃ የሚወድቅ ፈጻሚ ሞዴል ፈ
ምርጥ አሠራርና አፈጻጸም ሌሎች ሊማሩበት የሚገባ ነው፤ በእዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ ፈጻሚ የባህሪ መገለጫዎቹ
/system/ የተሸጋገሩና ሌሎች አፈጻጸማቸውን ለማሻሻል ሊማሩባቸው የሚገቡ ናቸው፤ በእዚህ ደረጃ አፈ
ሠራተኞች የባህሪ አፈጻጸማቸው ከውጤት አፈጻጸማቸው ጋር ጠንካራ ትስስር ያለው ነው፡፡

3 ከፍተኛ የአፈጻጸም ደረጃ ሲሆን ከ 80 – 94% ባለው የአፈጻጸም ውጤት ክፍል ይወድቃል፤ አፈጻጸሙ ከዚህም
1
ሆኖ ከመካከለኛ አፈጻጸም ከፍ ያለ አፈጻጸም ነው፤ ከፍተኛ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚወድቅ አፈጻጸም ሞዴል
ባይሆንም ከተለመደው መካከለኛ አፈጻጸም ወደ ላይ ከፍ ያለ ነው፡፡ ከአፈጻጸሙ መካከለኛና ዝቅተኛ የአፈ
ሠራተኞች ሊማሩበት ይችላሉ፡፡ የባህሪ አፈጻጸሙ ከውጤት አፈጻጸሙ ጋር ሊሻሻል የሚችል ግን ጠንካራ ትስስር ያ

2 ይህ ደረጃ መካከለኛ የአፈጻጸም ደረጃ ነው፤ከ 60 – 79 % ያለ አፈጻጸም ምርጥ ተብሎ ልምድ የሚቀስምበት
የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚገኝ ሠራተኛ አፈጻጸሙን ሊማሩበት ይችላሉ፤ አፈጻጸሙ የመካከለኛ የአፈጻጸም ባህሪ
መደቡ ላይ ለመቆየትና ከአፈጻጸም ደረጃው ጋር የሚመጣጠን ሽልማትና የእርከን ጭማሪ የሚያስገኝ ነው፡
አፈጻጸም ብዙ መሻሻል የሚገባው ሲሆን አስፈላጊው ማሻሻያ ካልተደረገበት ወደ ዝቅተኛ አፈጻጸም ደረጃ የመ
በእዚህ ደረጃ ያለ አፈጻጸም በርካታ ሊሻሻሉ የሚገባቸው የባህሪና የውጤት አፈጻጸም ጉድለቶች የሚታዩበት ነው

1 ይህ የአፈጻጸም ደረጃ ዝቅተኛ ሲሆን ከ 50 – 59 % የሆነ አፈጻጸምን ያሳያል ፣ በመሆኑ በቀጣዩ ስድስት ወር ለሠ
ልዩ ድጋፍና ምክር የአፈጻጸም ደረጃው እንዲሻሻል ጥረት ይደረጋል ፡፡ በእዚህ ደረጃ አፈጻጸሙ የሚወድቅ ሠራ
እድል ያለው ነው፡፡

2
i

You might also like