You are on page 1of 26

ማውጫ

መግቢያ ....................................................................................................................................... 3
ክፍሌ አንዴ ................................................................................................................................ 4
አጠቃሊይ ሁኔታ......................................................................................................................... 4
1.1 ዓሊማ ............................................................................................................................... 4
1.2 ከሥሌጠናው የሚጠበቅ ውጤት .................................................................................... 4
1.3 የሥሌጠናው ወሰን ......................................................................................................... 5
የማሰልጠኛ ሰነድ ሽፋን ....................................................................................................... 5
1.4 የስሌጠናው ተሳታፊዎች ................................................................................................ 5
ሥሌጠናው መሠረታዊ እንዯመሆኑ ሇግብር ከፋዩ እና በግብር ከፋዩ ዴርጅት ሇሚሰሩ
በዴርጅቱ ሠራተኝነታቸው የተረጋገጠሊቸው ባሇሙያዎች ይሰጣሌ፡፡ .................................. 5
1.5 ስሌጠናው የሚወስዯው ጊዜ ........................................................................................... 5
1.6 ትርጓሜ ........................................................................................................................... 5
ክፍሌ ሁሇት ............................................................................................................................... 6
2.1 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነት ....................................................................... 6
2.2 ሠንጠረዥ“ሀ” ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ሊይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መጣኔዎች .................. 7
2.3 በአይነት የሚገኙ ጥቅሞች ሊይ ግብር ስሇማስከፈሌ ..................................................... 8
2.4 እንዯ ዓይነት ጥቅሞች የማይቆጠሩ ............................................................................... 8
2.5 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የታክስ ስላት ............................................................................ 9
2.5.1 ጉርሻ/ ቦነስ እና የአመት ፍቃዴ ሊይ የሚከፈሌ ታክስን በተመሇከተ.................... 9
2.5.2 በውለ መሰረት ሰራተኛ ሲሰናበት የሚከፈሌ ክፍያ ወይም ሰቨራንስ ................. 10
2.5.3 የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላት ................................................................................... 11
ክፍሌ ሶስት .............................................................................................................................. 12
3.1 በሠንጠረዥ "ሠ" ያሇገዯብና በገዯብ ከገቢ ግብር ነፃ የተዯረጉ ገቢዎች ...................... 12
3.2 ከመቀጠር ገቢ ጋር የተያያዙ ላልች ዴንጋጌዎች ....................................................... 18
ክፍሌ አራት ............................................................................................................................. 18
4.1 የወጪ መጋራት ........................................................................................................... 18
4.2 የወጪ ዴርሻ ................................................................................................................ 19
4.3 የወጪ መጋራት ውሌና አፈፃፀም ............................................................................... 19
4.4 ተጠቃሚው ክፍያውን በገንዘብ ሇመክፈሌ ያለ አማራቾች፡- ...................................... 21
4.5 የእፎይታ ጊዜ ............................................................................................................... 22
4.6 ማበረታቻ ...................................................................................................................... 22
4.7 የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥ እና ስሇቀጣይ ስሌጠና ሥርዓት.................................... 22
4.8 የወሇዴ አከፋፈሌና መጣኔ............................................................................................ 22

1
4.9 የአሠሪዎች ግዳታ ........................................................................................................ 24
ማጠቃሇያ.................................................................................................................................. 25
ማጣቀሻዎች .............................................................................................................................. 26

2
መግቢያ

ማንኛውም ገቢ የሚያገኝ ሰው ከሚያገኘው ገቢ ሊይ ግብር የመክፈሌ ግዳታ እንዲሇበት


በተዯነገገው መሰረት ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ አሁን ካሇው፣ ካሇፈው ወይም ወዯ ፊት
ከሚመጣው የቅጥር ውሌ ጋር በተያያዘ የሚያገኘው ዯመወዝ /ምንዲ፣ አበሌ፣ ጉርሻ፣
ኮሚሽን፣ የመሌካም ሥራ አፈፃፀም፣ ማበረታቻ፣ ስጦታ፣ ወይም ላሊ የአገሌግልት ዋጋ
ክፍያ፣ ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲሇቅ ወይም ስራን እንዱሇቅ ሇማግባባት
የሚከፈሌ ገንዘብ ወይም የስራ ውሌ በመቋረጡ ምክንያት በፈቃዯኝነት፣ በስምምነት፣
በዲኝነት ውሳኔ መሠረት በጥሬ ገንዘብ (በዓይነት) የተቀበሇው ማንኛውም የገንዘብ መጠን
ከታክስ ነጻ ከተዯረገው ውጭ፣ እንዯ ገቢ ተቆጥሮ ታክስ የሚሰሊበት ይሆናሌ፡፡
እንዱሁም የከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚዎች መንግስት ሇትምህርትና ሇላልች
አገሌግልቶች የሚያወጣውን ወጪ በመጋራት ሇከፍተኛ ትምህርት ከሚወጣው ወጪ
አንጻር መንግሥትን መርዲት በመሆኑ በተፈጸመው ውሌ መሰረት የወጪ መጋራት
በገንዘብና በአገሌግልት የሚከፈሌ ይሆናሌ ፡፡

በዚሁ መሠረት ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ፣ ከታክስ ነጻ የሆኑ ገቢዎችና በወጪ መጋራት ሊይ
ግብር ከፋዮች ግዳታቸውን አውቀው ታክስ በፈቃዯኝነት መክፈሌ እንዱችለ አስቻይ
ሁኔታን ይፈጥራሌ፡፡ በመሆኑም የታክስ ጉዲዮች ትምህርት ዲይሬክቶሬት በሚኒስቴር
መስሪያ ቤቱ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ከሚገኙ የታክስ ትምህርት እና መረጃ አቅርቦት
የሥራ ሂዯት /ቡዴን ጋር በመቀናጀት የታክስ አስተዲዯሩን ይበሌጥ ቀሌጣፋ፣ ውጤታማ
እና ተገማችነት ያሇው ሇማዴረግ ይህን ሞጁሌ አዘጋጅቷሌ፡፡

3
ክፍሌአንዴ

አጠቃሊይ ሁኔታ
1.1 ዓሊማ
በዚህ ሞጁሌ የሚሠሇጥኑ ሠሌጣኞች በሥሌጠናው መጨረሻ:-
በሥሌጠና ሞጁለ ሊይ በመወያየት ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና ተያያዥ ጉዲዮችን በገቢ
ግብር አዋጅ 979/2008፤ በዯንብ ቁ.410/2009፤መመሪያ ቁጥር 1/2011፣ በወጪ መጋራት
ዯንብ ቁጥር 154/2000 እና በወጪ መጋራት መመሪያ 2/2009 አውቀው የታክስ
ግዳታቸውን እንዱወጡ ማስቻሌ፡፡
የሞጁለ ዝርዝር ዓሊማ፤
በሞጁለ ሥሌጠና ሂዯት ሠሌጣኞች:-
 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነት ይገሌጻለ፤
 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ታክስ የሚከፈሌበት መጣኔ በመሇየት መጣኔዎቹን
ይዘረዝራለ፤
 ከመቀጠር የሚገኝ የአይነት ጥቅሞችን በመሇየት ይዘረዝራለ፤
 ከመቀጠር የሚገኙ ገቢ ከታክስ ነፃ የተዯረጉ እና በገዯብ ነፃ የተዯረጉትን ገቢዎችን
ይሇያለ፤
 የወጪ መጋራት አከፋፈሌ ሥርዓት ያስረዲለ፡፡
 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት ምንነት በመረዲት መብትና
ግዳታቸውን ይሇያለ፤

1.2ከሥሌጠናው የሚጠበቅ ውጤት


ከዚህ ሥልጠና በኋላ ሠልጣኞች፡-
ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ አጠቃላይ ዕውቀት ይኖራቸዋል፤

ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ የታክስ አዋጁ፣ ደንብ እና መመሪያዎቹ ላይ ግንዛቤ


እንዲፈጠር በማድረግ የሚመሇከታቸው ሁለ የሚጠበቅባቸውን ግዴታና ኃላፊነት
ተረድተው ግዴታቸውንና ኃላፊነታቸውን በቀላለ መወጣት ይችላለ፤
የወጪ መጋራት አዋጅ፣ ደንብ እና መመሪያ በመረዳት የሚመሇከታቸው ሁለ
ግዴታቸውን እንዲወጡ ያስችላቸዋል፡፡

4
1.3 የሥሌጠናው ወሰን

የማሰልጠኛ ሰነድ ሽፋን


በገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 የሠንጠረዥ "ሀ" እና "ሠ"፤ በደንብ ቁጥር 410 (በዓይነት
የሚገኙ ገቢዎች) ላይ እና መመሪያ ቁጥር1/2011፤ሌሎች ተያያዥ መመሪያዎች
እንዲሁም በወጪ መጋራት አዋጅ፤ ደንብ እና መመሪያ ያካተተ ይሆናል፡፡

1.4 የስሌጠናው ተሳታፊዎች

ሥሌጠናው መሠረታዊ እንዯመሆኑ ሇግብር ከፋዩ እና በግብር ከፋዩ ዴርጅት ሇሚሰሩ


በዴርጅቱ ሠራተኝነታቸው የተረጋገጠሊቸው ባሇሙያዎች ይሰጣሌ፡፡

1.5 ስሌጠናው የሚወስዯው ጊዜ


ይህን ሰነዴ ሇማሠሌጠን ዘጠኝ ሰዓት ያስፈሌገዋሌ፡፡

1.6 ትርጓሜ
ዯመወዝ፡- ማሇት በአንዴ የስራ ዯረጃ ሊይ የተመዯቡ ሰራተኞች ሇሚሰጡት
አገሌግልት በቀጣሪው የሚከፈሌ ክፍያ ሲሆን አበሌንና ጥቅማ ጥቅሞችን
አይጨምርም ፡፡
የውል አበሌ፡- ማሇት ሇአንዴ ተቀጣሪ የትራንስፖርት፣ ሇስራው ቦታ እና ሇስራው
ሁኔታ አስቸጋሪነት የሚከፈሌ፣ ከመዯበኛው ሥራው ቦታ ርቆ (25 ኪ.ሜ.) ሲሄዴ
ሇመኝታ ፣ሇምግብና ሇመጠጥ እና ተዛማጅ ወጪ የሚከፈሌ አበሌ ነው
ቀጣሪ ማሇት፡- ተቀጣሪን የቀጠረ ወይም ሇተቀጣሪው ዯመወዝ የሚከፍሌ ሰው ነው፡፡
ተቀጣሪ ማሇት፡- በላሊ ሰው /በቀጣሪው/ መሪነትና ቁጥጥር ስር ሆኖ አገሌግልት
ሇመስጠት፡- በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት የተቀጠረ ግሇሰብ፣ የዴርጅት ዲይሬክተር፣
ወይም በዴርጅቱ አመራር ውስጥ ኃሊፊነት የተሰጠውን ላሊ ሰው እንዱሁም ተሿሚንና
የህዝብ ተመራጭን ጨምሮ የመንግስት ስራ ኃሊፊን ያጠቃሌሊሌ፡፡
“አሠሪ” ማሇት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመራቂን ቀጥሮ የሚያሰራ ማንኛውም
የመንግስት መስሪያ ቤት፣ የግሌ ወይም መንግስታዊ ያሌሆነ ተቋም ወይም ዓሇም
አቀፍ ወይም አህጉር አቀፍ ዴርጅት ሲሆን በሙያው በግለ ስራ የተሰማራ ሰውን
ይጨምራሌ፡፡
“ተጠቃሚ” ማሇት ማንኛውም በመንግስት ተቋም ሇመማርና የሚፈሇግበትን ወጪ
ሇመክፈሌ ከተቋሙ ጋር ዉሇታ ገብቶ የከፍተኛ ትምህርት ወይም ስሌጠና
የሚከታተሌ ተማሪ ነው

5
“ወጪ መጋራት” ማሇት የከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚና መንግስት ሇትምህርትና
ሇላልች አገሌግልቶች የሚያወጣውን ወጪ የሚጋሩበት ስርዓት ነው፡፡

ክፍሌ ሁሇት
ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ

2.1 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነት፤


ሠራተኛው ካሇፈው፣ አሁን ካሇው ወይም ወዯ ፊት ከሚመጣው የቅጥር ውሌ ጋር
በተያያዘ የሚያገኘው ዯመወዝ /ምንዲ፣ አበሌ፣ ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመሌካም ሥራ አፈፃፀም
ማበረታቻ ስጦታ ወይም ላሊ የአገሌግልት ዋጋ ክፍያ፣ ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም
ከስራ ሲሇቅ ወይም ስራን እንዱሇቅ ሇማግባባት የሚከፈሌ ገንዘብ ወይም የስራ ውሌ
በመቋረጡ ምክንያት በፈቃዯኝነት፣ በስምምነት፣ በዲኝነት ውሳኔ መሠረት በጥሬ ገንዘብ
(በዓይነት) የተቀበሇው ማንኛውም የገንዘብ መጠን ከታክስ ነጻ ከተዯረገው ውጭ፣ እንዯ ገቢ
ተቆጥሮ ታክስ የሚሰሊበት ይሆናሌ::
አንዴ ተቀጣሪ ከመቀጠር የሚያገኘው ገቢ በኢትዮጵያ የመነጨ ነው የሚባሇው ፤-
 ክፍያው የሚፈፀምበት ስፍራ ግምት ውስጥ ሳይገባ ኢትዮጵያ ውስጥ
ከሚከናወነው የቅጥር አገሌግልት የተገኘ ገቢ ወይም
 የቅጥር አገሌግልቱ የትም ቢከናወን በኢትዮጵያ ፌዯራሊዊ ዱሞክራሲያዊ
ሪፐብሉክ መንግስት ስም ክፍያው ሇተቀጣሪው ከተፈፀመ ነው፡፡
ተቀጣሪው ከመቀጠር በሚያገኘው ገቢ የሚገኘው ገቢ ሇማግኘት የሚያወጣው
ማንኛውም ወጪ በተቀናሽ ሉያዝሇት አይችሌም፡፡

ሙከራ አንዴ
ሰሌጣኞች ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ አይነትና ምንነትን ይገሇጹ?

6
2.2 ሠንጠረዥ “ሀ” ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ሊይ ተፈጻሚ የሚሆኑ መጣኔዎች
ተቁ በየወሩ ከመቀጠር ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ሊይ የተቀናሽመጠን
የሚገኝ ገቢ በብር ተፈፃሚ የሚሆን ምጣኔ

1 0-600 0% 0.00
2 601-1,650 10% 600 * 10/100 = 60
3 1651-3,200 15% 1,650 * 5/100+60 = 142.5
4 3,201-5250 20% 3,200 * 5/100+142.5 = 302.50
5 5,251-7800 25% 5,250 * 5/100+302.50 = 565
6 7,801-10,900 30% 7,800 * 5/100+565 = 955
7 ከ10,900 በሊይ 35% 10,900 * 5/100+955 = 1500

የዯመወዝ ገቢ የታክስ ስላት


ምሳሌ1፡-ድ/ር አበበ በXYZ ካምፓኒ ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን በወር 10,500 ብር
ይከፈሊቸዋሌ፡፡ ድ/ር አበበ ሇመንግስት ምን ያህሌ ግብር ይከፍሊለ?
መሌስ፡-
የድ/ር አበበ ዯመወዝ በሠንጠረዥ “ሀ” መሰረት ከ7,801 እስከ 10,900 ባሇው መካከሌ
ይገኛሌ፡፡ ስሇዚህ
ግብር = የወር ዯመወዝ x የማስከፈያ መጣኔ - ተቀናሽ
ግብር = 10,500 x 30% - 955.00
አጠቃሊይ ዯመወዝ - ተቀናሽ ግብር ግብር = 2,195.00
ላልች ወጪዎችን ሳይጨምር ተከፋይ ዯመወዝ = 10,500 - 2195 = 8,305.00
ማንኛውም ቀጣሪ ተቀጣሪው መክፈሌ የሚኖርበትን ግብር ከተቀጣሪው ገቢ ሊይ
ሳይቀንስ ራሱ ሇተቀጣሪው በሙለ ወይም በከፊሌ የከፈሇሇት እንዯሆነ፣ በቀጣሪው
የተከፈሇው የግብር መጠን ተቀጣሪው ከመቀጠር ከሚያገኘው ግብር በሚከፈሌበት
የገንዘብ መጠን ሊይ ተዯምሮ ግብሩ ይሰሊሌ፡፡

ሙከራ ሁሇት
ሠሌጣኞች ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ታክስ የሚከፈሌበት መጣኔ በመሇየት

መጣኔዎቹን ይዘርዝሩ?

7
2.3 በአይነት የሚገኙ ጥቅሞች ሊይ ግብር ስሇማስከፈሌ
የገቢ ግብር ዯንብ (410/2009) በዓይነት ሇተቀጣሪው የሚሰጥ ጥቅማ ጥቅም ዋጋና
ግብር የሚሰሊበትን ሁኔታ፡-
 ከዕዲ ነጻ የመዯረግ፤(ቀሪ የተዯረገ የዕዲ መጠን)
 የቤተሰብ አገሌግልት ሠራተኞች፤ (የቤት ሰራተኛ፣ ምግብ አብሳይ፣ ሹፌር፣
አትክሌተኛ)፣ የመኖሪያ ቤት፤
 የቅናሽ ወሇዴ ብዴር፤ (ከገበያው የማበዯሪያ ወሇዴ ምጣኔ የሚያንስ)
 የምግብ ወይም መጠጥ አገሌግልት፤
 የግሌ ወጪዎች፤ (ሇተቀጣሪው የግሌ ወጪ ጥቅም የሚያስገኝ፣ የተከፈሇ
ክፍያ…)
 የንብረት ወይም አገሌግልቶች፤(የንብረቱን /አገሌግልቱን እንዯ መዯበኛ
የሚያቀርብ ከሆነ የዋጋውን 75% ወይም በላሊ ሁኔታ የንብረቱን
/አገሌግልቱን መሸጫ ዋጋ፣
 የአየር ቲኬት ከሆነ ሇኢኮኖሚ ዯረጃ በሚከፈሇው ዋጋ
 የሠራተኞች የአክሲዮን ዏቅዴ፤(ባሇ አክስዮን የመሆን መብት /ምርጫ…)
 የተሽከርካሪ፤(ተሽከርካሪውን ሇማግኘት የወጣ ወጪ ወይም ኪራይ (ሀ)*5%/12)
 ላሊ የዓይነት ጥቅም፡፡

2.4 እንዯ ዓይነት ጥቅሞች የማይቆጠሩ


በሠንጠረዥ “ሠ” ከገቢ ግብር ነጻ የሆኑ ገቢዎች መሠረት ከግብር ነጻ የተዯረገ
ጥቅም፤

ቀጣሪ ተመሳሳይ ጥቅም የሚያቀርብበትን ዴግግሞሽ ከግምት ውስጥ በማስገባት


ዋጋው አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ማስሊቱ ምክንያታዊ ያሌሆነ እና ሇአስተዲዯር
የማያመች ጥቅም፤
በቀጣሪው ወይም በቀጣሪው ስም በሚተዲዯር የሠራተኞች ምግብ ቤት፣ ካፊቴሪያ
ወይም የመመገቢያ ክፍሌ ያሇምንም ሌዩነት ሇመዯበኛ ሠራተኞች ጥቅም ብቻ ተብል
የሚቀርብ የምግብና የመጠጥ አገሌግልት ዴጎማ፤
የሥራ አመራር አካሌ ሊሌሆነ ተቀጣሪ በሩቅ ሥፍራ የሚቀርብ የማረፊያ ወይም
የመኖሪያ ቤት አገሌግልት፤
ተቀጣሪው እንዱጠቀምበት በቀጣሪው የሚቀርብ ተንቀሳቃሽ ስሌክ፤

8
በቀጣሪው በቀረበ የተንቀሳቃሽ ስሌክ የተዯረገን ጥሪ ጨምሮ ቀጣሪ ሇተቀጣሪ
የሚሸፍነው የተንቀሳቃሽ ስሌክ ጥሪዎች ወጪ፤
በዩኒቨርሲቲ፣ በኮላጅ ወይም በጎሌማሶች ትምህርት በሚሰጥ ላሊ ተቋም የሚሰጥ
ትምህርት መከታተሌ እንዱችሌ ቀጣሪ ሇተቀጣሪ የሚፈጽመው የትምህርት ወይም
ሥሌጠና ክፍያ፤
ሇተቀጣሪ ጥቅም የሚቀርብ የዯህንነት ጥበቃ አገሌግልት፤

ሆቴልች፣ ሬስቶራንቶች እና የምግብ አገሌግልት የሚያቀርቡ ላልች ተቋሞች


ሇተቀጣሪዎቻቸው የሚያቀርቡት የምግብና መጠጥ አገሌግልት፤
ሇተቀጣሪዎች የሚቀርብ የዯንብ ሌብስ እና የሥራ መገሌገያ ፡፡
በማንኛውም ሁኔታ በዓይነት ጥቅሞች ሊይ የሚከፈሇው ጠቅሊሊ ግብር ተቀጣሪው
በወሩ ከሚያገኘው የዯመወዝ ገቢ አስር በመቶ (10%) መብሇጥ የሇበትም፡፡

ሙከራ ሶስት
ሠሌጣኞች ከመቀጠር የሚገኝ የአይነት ጥቅሞችን በመሇየት ይዘርዝሩ?

2.5 ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ የታክስ ስላት


2.5.1 ጉርሻ /ቦነስ እና የአመት ፍቃዴ ሊይ የሚከፈሌ ታክስን በተመሇከተ
ጉርሻ /ቦነስ/፤የዓመት ፈቃዴ እና የመሳሰለት ክፍያዎች የ12 ወራት ጥቅም ስሇሆኑ
ተጠቃሇው ከተዯመሩ በኋሊ ሇ12 ተካፍሇው የተገኘው ውጤት መዯበኛ ዯመወዝ ሊይ
ከተዯመረ በኋሊ የሥራ ግብሩ እንዱሰሊ እና የተገኘው የሥራ ግብር ክፍያ ቀዯም ሲሌ በወር
ዯመወዙ የከፈሇው ግብር ተቀንሶ የእያንዲንደ 12 ወር የግብር ሌዩነት በመዯመር የሚሰሊ
ይሆናሌ፡፡
የጉርሻ /ቦነስ ታክስ አከፋፈሌ፡-
ምሳላ፡-2 አቶ አየሇ በXYZ ካምፓኒ የዴርጅቱ ሲኒየር አካውንታት ሆነው ተቀጥረዋሌ ፡፡
ዴርጅቱ በወር 12,300 ብር ዯመወዝ የሚከፍሊቸው ሲሆን በ2012 ዓ.ም ባሳዩት ውጤታማ
የስራ አፈጻጸም የወር ዯሞዛቸውን በዓመቱ መጨረሻ በቦነስ መሌክ ቢከፍሊቸው አቶ አየሇ
ካገኙት ቦነስ ሊይ መክፈሌ የሚጠበቅባቸው የስራ ግብር ስንት ነው?

9
መሌስ
1. 12,300/12=1,025 +12,300 =13,325.00
2. 13,325*35/100-1500 = 3,163.75
3. 12,300*35/100-1500 = 2,805
4. 3,163.75-2,805 = 358.75
5. 358.75*12= 4,305 ብር የመጨረሻ የቦነስ ተከፋይ የስራ ግብር ይሆናሌ፡፡
የአመት ፍቃዴ በገንዘብ ተቀይሮ ሲሰጥ ስሇሚከፈሌ የስራ ግብር
የአመት ፍቃዴን በተመሇከተ አንዴ ዓመት ያገሇገሇ የግሌ ዴርጅት ሰራተኛ 16 ቀን የዓመት
ፍቃዴ የሚሰጠው ሲሆን ከአንዴ ዓመት በሊይ ያገሇገሇ ሠራተኛ በየሁሇት ዓመቱ አንዴ
የሥራ ቀን እየታከሇበት የዓመት እረፍት ፈቃዴ ያገኛሌ፡፡
ምሳላ፡-3 አቶ አበበ በXYZ ካምፓኒ በዴርጅቱ ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆኑ በዴርጅቱ 28
ዓመት ያገሇገለ ሲሆን 10,500 ብር ዯመወዝ ይከፈሊቸዋሌ፡፡ አቶ አበበ በ2011 ዓ.ም
ያሌተጠቀሙት 30 ቀናት የአመት ፍቃዴ በገንዘብ ተቀይሮ እንዱሰጣቸው በጠየቁት መሰረት
በመጨረሻው ዓመት ሂሳቡ ተሰሌቶ ተሰጣቸው፤
1. የአመት ፍቃዲቸው በገንዘብ ተቀይሮ ከተሰጣቸው ገንዘብ ሊይ ምን ያህሌ የስራ ግብር
ይከፍሊለ?
መሌስ፡-
1. 10,500/12 = 875
2. 875+10,500 =11,375.00
3. 11,375.00*35/100 -1500 = 2,481.25
4. 10,500*30/100-955 = 2,195
5. 2,481.25-2,195 = 286.25
6. 286.25*12 = 3,435.00 ብር ተከፋይ የስራ ግብር ይሆናሌ፡፡

2.5.2 በውለ መሰረት ሰራተኛ ሲሰናበት የሚከፈሌ ክፍያ ወይም ሰቨራንስ


በውለ መሰረት ሰራተኛ ሲሰናበት የሚከፈሌ ክፍያ ወይም ሰቨራንስ ከፍያው የሚፈጸመው
ሰራተኛው ሲሰናበት የሚያገኘውን የወር ዯመወዝ መሰረት በማዴረግ ይሆናሌ፡፡ በዚህም
መሰረት ሰራተኛው ሲሰናበት የመጀመሪያ ዯመወዙን ሙለ በሙለ የሚከፈሇው ሲሆን
ቀጥል ያለት የአገሌግልት አመታት የዯመወዙን 1/3ኛ የሚከፈሌ ይሆናሌ፡፡
ምሳላ፡-4 ድ/ር ከበዯ በYZ ካምፓኒ የዴርጅቱ ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ በዴርጅቱ በነበራቸው
ቆይታ በወር 30,500 ብር ይከፈሊቸው ነበር ድ/ር ከበዯ በውሊቸው መሰረት 8 አመት
ሰርተው ዴርጅቱ ከስራ አሰናበታቸው፡፡

10
1. ተሰናባቹ ግሇሰብ ከስራ ሲሰናበቱ ስንት ብር ሉከፈሊቸው ይገባሌ?
2. ከሚከፈሊቸው የስንብት ክፍያ ሊይ ስንት ብር ሇገቢ ባሇስሌጣኑ የስራ ግብር መክፈሌ
ይኖርባቸዋሌ?
መሌስ፡-
1. ሰራተኛ ሲሰናበት ሇመጀመሪያ የወር ዯመወዙን መቶ ፐርሰንት ይከፈሇዋሌ
2. ቀጥል ሊለት አገሌግልቶችየዯመወዙን 1/3ኛ የሚከፈሌ ይሆናሌ
3. በዚህም መሰረት 30,500 ብር የወር ዯመወዝ ሇመጀመሪያው ዓመት መቶ
ፐርሰንት የሚከፈሇው ሲሆን በቀሩት ዓመታት የወር ዯመወዙ በ1/3ኛ እና በቀሩት
አመታት ይባዛሌ፡፡ በዚህም መሰረት
4. 30,500 ሇመጀመሪያው አመት መቶ ፐርሰንት
5. 30,500*1/3*7አመት = 71,166.67
6. 30,500+71,166.67 = 101,666.67
7. 101,666.67/30,500 = የ3.33 ወር ዯመወዝ ይከፈሇዋሌ፡፡
8. 30,500*35/100-1500 = 9,175*3=27,525
9. 30,500*0.33 =10,065.00
10. 10,065*30/100-955= 2,064.50
11. 27,525+2,064.50= 29,589.50 የመጨረሻው የስንብት ክፍያ የስራ ግብር
ይሆናሌ::

2.5.3 የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላት


ተቁ የትርፍ ሰዓት የተሰራበት ሠዓት /ቀን/ የክፍያ ሁኔታ
1 ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በመዯበኛ ሰዓት ክፍያው በ1.5 ተባዝቶ ይከፈሊሌ
2 ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት በመዯበኛ ሰዓት ክፍያው በ1.75 ተባዝቶ ይከፈሊሌ
3 በሳምንት የዕረፍት ቀን የተሰራ የትርፍ በመዯበኛ ሰዓት ክፍያው በ2 ተባዝቶ ይከፈሊሌ
ሰዓት
4 በበዓሊት ቀናት የተሰራ የትርፍ ሰዓት በመዯበኛ ሰዓት ክፍያው በ2.5 ተባዝቶ ይከፈሊሌ

በወሩ ውስጥ ሰራተኛው ያገኘውን የትርፍ ሰዓት ክፍያ በወሩ ከሚያገኘው ዯሞወዝ ሊይ
በመዯመር ጠቅሊሊ በተገኘው ገቢ ሊይ በሰንጠረዥ “ሀ” መሰረት ግብር ይከፈሌበታሌ፡፡
ምሳላ፡-5 በወር15,000 ብር ዯሞወዝ የሚከፈሇው ባሇሙያ በሳምንት የዕረፍት ቀን የትርፍ
ሰዓት በወር ውስጥ 20 ሰዓት ቢሰራ

11
1. የትርፍ ሰዓት ክፍያው ስንት ነው?
2. የሚከፈሌ የስራ ግብር ስንት ይሆናሌ

የስላቱ ቀመር

የቀን ዯመወዝ = የወር ዯመወዝ/ሇ30ቀን


በሰአት የሚከፈሇው ክፍያ= የቀን ዯመወዝ/ በቀን ውስጥ ሇሚሰራው ሰዓት
የቀን ዯመወዝ = 15,000/30 = 500
በሰዓት የሚከፈሇው ክፍያ = 500/8 = 62.5
የታክሱ ስላት፡-
በትርፍ የሰራው የሰዓት ብዛትx በሰዓት የሚያገኘው ክፍያ x መጣኔ=
20 X62.5 X 2 = 2,500
15,000 + 2,500 = 17,500
17,500 x 35% -1,500 = 4,625.00 ግብር ይከፍሊሌ

ክፍሌ ሶስት

3.1 በሠንጠረዥ "ሠ" ያሇገዯብ እና በገዯብ ከገቢ ግብር ነፃ የተዯረጉ ገቢዎች


3.1.1 ያሇገዯብ ከገቢ ግብር ነፃ የተዯረጉ ገቢዎች
ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ሇሠራተኛው ህክምና አገሌግልት የከፈሇሇት
ገንዘብ፤
የመንግሥት የሌማት ዴርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርዴ አባሌ
ወይም ፀሏፊ እንዱሁም የፌዯራሌና የክሌሌ መንግሥታት ወይም የከተማ
አስተዲዯሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡዴኖች አባሌ ወይም ፀሏፊ በመሆን
የሚከፈሌ አበሌ፤
ሇሠራተኛው ጥቅም ተብል ከተቀጣሪው የወር ዯመወዝ 15% (አሥራ አምስት
በመቶ) ባሌበሇጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም
የፕሮቪዯንት ፈንዴ፤
በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ እና በግሌ ዴርጅት ሠራተኞች የጡረታ
አዋጅ ከግብር ነፃ የተዯረገ የጡረታ ገቢ፤
የኢትዮጵያ የፌዯራሌ፣ የክሌሌ ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ባንክ ከመዯበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፤

12
በዓሇም ዏቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን፤
በኢትዮጵያ ፌዯራሊዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብሉክ መንግሥት በተዯረገ ስምምነት
መሠረት ማናቸውም ገቢ ከግብር ነፃ የሚሆነው፡- ስምምነቱ የተዯረገው
ሇመንግሥት የገንዘብ፣ የቴክኒክ፣ ሰብአዊ ወይም አስተዲዯራዊ እርዲታ ሇማቅረብ
የሆነ እንዯሆነ እና ከግብር ነፃ ማዴረግ የሚያስችሇውን አንቀጽ በሚመሇከት
ሚኒስትሩ መስማማቱን በጽሁፍ ሲገሌጽ
በማንኛውም መስክ ሇሊቀ የሥራ ክንውን የሚሰጥ ሽሌማት፤
 አንዴን ቴክኖልጅ ሇማሻሻሌ፣ አዱስ የፈጠራ ስራ በመስራት ወይም ወጪን
ሇመቀነስ የሚያስችሌ የአሰራር ስርዓት ስራ ሊይ በማዋሌ የሚሰጥ ሽሌማት
 በአሇም አቀፍ ዯረጃ በሚዯረግ ውዴዴር አገርን ወክል ወይም በሀገር አቀፍ
ዯረጃ በህግ በተቋቋመ ዴርጅት በሚዯረግ ማንኛውም ውዴዴር የሚሰጥ
ሽሌማት
 በፌዯራሌ፣ በክሌሌ፣ በአዱስ አበባ እና በዴሬዯዋ ከተማ አስተዲዯር መንግስት
የሊቀ የስራ ክንውን ሊስመዘገበ ማንኛውም ግሇሰብ ወይም ዴርጅት የሚሰጥ
ሽሌማት ሲሆን ሽሌማቱ ከገቢ ግብር ነጻ ሉሆን የሚችሇው ከፈጠራ ስራው
ጋር ግንኙነት ያሇው የመንግስት አካሌ ሇፈጠራ ስራው እውቅና የተሰጠው
ወይም የፈጠራ መብት ሲኖረው ነው ፡፡
በተቀባዩ ሊይ በዯረሰ ጉዲት ወይም በላሊ ሰው ሞት ምክንያት የሚከፈሌ ካሳ፤
ስጦታው የመቀጠር፣ የኪራይ ወይም የንግዴ ሥራ ገቢ ካሌሆነ በስተቀር በስጦታ
ወይም በውርስ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሀብት፤
በትምህርት ተቋም ውስጥ ትምህርትን በነፃ ሇመከታተሌ የሚፈፀም ክፍያ፤
ሇቀሇብ ወይም ሇህፃናት ዴጋፍ የሚሰጡ ክፍያዎች፤
ዴርጅቱ ከተቋቋመበት ዓሊማ ጋር የማይገናኝ የንግዴ ሥራ ገቢን ሳይጨምር
ሇትርፍ ያሌተቋቋመ ዴርጅት የሚያገኘው ገቢ፤
ገንዘብ በሚቆጠርበት ጊዜ ሇሚዯርሰው ጉዴሇት ማካካሻ በሚሆን መጠን ብቻ
ቀጣሪው ሇተቀጣሪው የሚከፍሇው እና ሇዚሁ ዓሊማ መዋለ የተረጋገጠ የጥሬ
ገንዘብ ማካካሻ ክፍያ፤
በኢትዮጵያ ፀንቶ በሚሰራበት ሕግ መሠረት በተሇይ ከገቢ ግብር ነፃ የተዯረገ ገቢ፤
ሇመኖሪያ ቤት ሠራተኞች የሚከፈሌ ዯመወዝ፤
በነዲጅ ሥራ ሊይ የተሰማራ ሥራ ተቋራጭ ሇንዐስ ሥራ ተቋራጮች የሚፈፅመው
ክፍያ፡፡

13
ሇኢኮኖሚ፣ ሇአስተዲዯራዊ ወይም ሇማህበራዊ ምክንያቶች አንዴን ገቢ ከገቢ ግብር
ነፃ ሉያዯርግ እንዯሚችሌ ባመሇከተው መሠረት የሚከተለት ገቢዎች ከገቢ ግብር
ነፃ ናቸው፤
 በወጪ ንግዴ ሥራ ሊይ የተሠማሩ ባሇሀብቶች ሇእውቀት ሽግግር ከውጭ
ሀገር ሇሚያስመጧቸው ባሇሙያዎች ከአምስት ዓመት ሊሌበሇጠ ጊዜ
የሚከፈሊቸው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ፤

 በማንኛውም የአስራ ሁሇት ወራት ጊዜ ውስጥ ሇአንዴ ቀጣሪ ሳያቋርጥም ሆነ


በተዯጋጋሚ ከሠሊሳ ቀናት ሊሌበሇጠ ጊዜ ያገሇገሇ ማንኛውም ባሇሙያ ያሌሆነ
ተቀጣሪ የሚያገኘው ገቢ፤ ሆኖም በአስራ ሁሇት ወራት ጊዜ ውስጥ አንዴ
ሰው በተዯጋጋሚ ሇአንዴ ቀጣሪ የሰጠው አገሌግልት ሲዯመር ከአንዴ ወር
የሚበሌጥ ከሆነ ተቀጣሪው የሚከፍሇው ግብር የሚታሰበው በመጨረሻው
ቅጥር ባገኘው ገቢ ሊይ ብቻ ይሆናሌ፡፡
 “ባሇሙያ ያሌሆነ ተቀጣሪ” ማሇት መዯበኛ የሙያ ሥሌጠና ያሌወሰዯ ሌዩ
ሙያ በሚጠይቁ ማሽኖችና መሣሪያዎች የማይጠቀም በአንዴ ዓመት ጊዜ
ውስጥ በጠቅሊሊው ከ30 ቀናት ሇማይበሌጥ ጊዜ የተቀጠረ ግሇሰብ ነው፡፡

 ከግብር ነጻ የተዯረገው አሠሪው ሠራተኛው ሲታመም ሇሠራተኛው ህክምና


አገሌግልት የከፈሇሇት ገንዘብ በሠራተኞች የጤና መዴን አቅዴ መሠረት
አሠሪው ሇሠራተኞች ጥቅም የሚከፍሇውን አረቦን ይጨምራሌ፡፡
 ሇኮንስትራሽን ማሽነሪ ኦፕሬተሮች የሚከፈሇው ውል አበሌ ከ25 ኪ.ሜ. ባነሰ ወይም
በበሇጠ ርቀት ቢሆንም የተከፈሇው የውል አበሌ ከግብር ነፃ ይሆናሌ፤
 የመንግስት መስሪያ ቤት ሇተሿሚዎች እና ሇተቀጣሪዎች ከመዯበኛ የስራ ቦታቸው
ውጭ ከ25 ኪ.ሜ. በሊይ ርቀው በመሄዴ ሇሚያከናውኑት ሥራ የሚከፈሌ የቀን
ውል አበሌ ሙለ በሙለ ከግብር ነፃ ነው

3.1.2 በገዯብ ከገቢ ግብር ነፃ የተዯረጉ ገቢዎች

የትራንስፖርት አበሌ:-

በሥራ ውሌ መሠረት ሥራውን ከቦታ ወዯ ቦታ በመዘዋወር የሚያከናውን ተቀጣሪ


ሇአንዴ ወር ጉዞ የሚከፈሇው የትራንስፖርት ወይም የነዲጅ አበሌ ከገቢ ግብር ነፃ
የሚዯረገው ከጠቅሊሊ የወር ዯሞዙ ከ1/4ኛ ባሌበሇጠ ብቻ ሲሆን የዯመወዙ 1/4ኛ
ከብር 2,200 በሊይ ከሆነ ታክስ ይከፈሌበታሌ፡፡

14
አንዴ ተቀጣሪ ከመኖሪያ ቤቱ ወዯ ሥራ እንዱሁም ከሥራ ቦታው ወዯ መኖሪያ ቤቱ
ሇመሄዴ የነዲጅ ወጪ ወይም በጥሬ ገንዘብ የሚከፈሇው የትራንስፖርት አበሌ 600
ብር ብቻ ነው፤
አንዴ ተቀጣሪ ሥራውን ሇማከናወን ከመዯበኛው የሥራ ቦታ ከሚገኝበት ውጪ
ሲንቀሳቀስ ሇትራንስፖርት ወጪ ከግብር ነፃ የሚሆነው በስራ ሊይ ባሇው
የትራንስፖርት (የአየር፣ የውሃ እና የየብስ) ዋጋ ሉበሌጥ አይችሌም፡፡

አንዴ የውጭ አገር ዜጋ ስራውን ሇማከናወን ወዯ ኢትዮጵያ ሲመጣና የውሌ


ዘመኑን ጨርሶ ከሀገር ሲወጣ የሚከፈሇው የትራንስፖርት ወጪ ከገቢ ግብር ነፃ
ሉሆን የሚችሇው በተፈጸመው የቅጥር ውሌ መሰረት እና የአየር፣ የውሃ እና የየብስ
ትራንስፖርት አገሌግልት ዋጋ ታሪፍ መሰረት ሆኖ ከግብር ነፃ የሚሆነው ሇግሌ
መገሌገያ ዕቃዎች የሚከፈሇው የጭነት ሂሳብ ከ300 ኪል ግራም ሉበሌጥ አይችሌም
የስራ ቦታ አስቸጋሪነት የሚከፈሌ አበሌ ፡

የሥራ ቦታ አስቸጋሪነት ከፍተኛ ሙቀት ወይም ሇኑሮ አስቸጋሪ በመሆኑ ወይም


በላሊ ተመሳሳይ ምክንያት በተቀጣሪው ሉዯርስ የሚችሇውን ጉዲት ከግምት ውስጥ
በማስገባት ሇሚዯርስ ጉዲት የሚከፈሌ አበሌ ሲሆን ፡-
 በሥራው ቦታ አስቸጋሪነት ምክንያት የሚከፈሌ አበሌ ከግብር ነፃ የሚዯረገው
የሲቪሌ ሰርቪስ ኮሚሽን ባወጣው መመሪያ መሠረት (አንዯኛ ዯረጃ ቆሊ ከሆነ
ከዯመወዙ 40%፣ ሁሇተኛ ዯረጃ 30% እና ሶስተኛ ዯረጃ 20%) የሚከፈሌ
ነው፡፡
 በሲቪሌ ሰርቪስ ኮሚሽን የማይተዲዯሩ መ/ቤቶች እና የግሌ ዴርጅቶች ተቀጣሪ
ወይም ሹመኛ ጨምሮ በተመሳሳይ ተፈፃሚ ይሆናሌ፡፡

የስራ ሁኔታ አስቸጋሪነት የሚከፈሌ አበሌ፡-

የሥራው ሁኔታ ሇጨረር፣ ሇበሽታ፣ ሇኬሚካሌ፣ ወዘተ በጤና ዯህንነት ሊይ ጉዲት ማካካሻ
የሚከፈሌ፤-
 በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ሇሠራተኛው የሚከፈሌ አበሌ፤
(ዝቅተኛው 25%፣ ሇመካከሇኛ 40%፣ ሇከፍተኛ 60%)፤ ሲሆን የጉዲት ዯረጃውን
መሇካት የማይቻሌ ከሆነ ከተቀጣሪው የወር ዯመወዝ ከ25% (ሃያ በአምስት
መቶ) ባሌበሇጠ መጠን ከገቢ ግብር ነፃ ይዯረጋሌ፡፡
 በስራ ሁኔታ አስቸጋሪነት ምክንያት ሇሰራተኛ የሚከፈሌ አበሌ የስራው ሁኔታ
ስሇሚያዯርሰው ችግር ከሚመሇከተው አካሌ ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታሌ፡፡

15
የውል አበሌ፡-

አንዴ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ሥራ ሇማከናወን መበዯኛ የሥራ ቦታ ከሚገኝበት


ከተማ ውጪ ከ25 ኪ.ሜ. በሊይ ርቆ ሲሄዴ ሇመኝታ፣ ምግብ እና መጠጥ እና
ተዛማጅ ወጪ የሚከፈሌ ነው፤

ሇማንኛውም ዴርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም ምክትሌ ሥራ አስኪያጅ


የሚከፈሇው የውል አበሌ ከግብር ነፃ የሚዯረገው 1000 ብር ወይም የዯሞዙ
5% ከሁሇቱ ከፍተኛ ባሌበሇጠ ብቻ ሲሆን የአሌጋ አበሌ በዯረሰኝ የሚወራረዴሇት
ከሆነ ሇቁርስ፣ ሇምሳ፣ ሇእራት እና ሇመሳሰለት የሚሰጠው የውል አበሌ ከግብር
ነፃ የሚዯረገው ከብር 600 ወይም የዯሞዙ 3% ከሁሇቱ ከፍተኛ ባሌበሇጠ ብቻ
ነው፡፡
አንዴ ተቀጣሪ የሚከፈሇው የቀን ውል አበሌ ከገቢ ግብር ነፃ የሚዯረገው ከብር
500 ወይም ከዯሞዙ 4% ካሌበሇጠ ብቻ ነው፡፡
አንዴ ተቀጣሪ የአሌጋ አበሌ በዯረሰኝ የሚወራረዴሇት ከሆነ ከግብር ነፃ ሲሆን፤
ሇቁርስ፣ ሇምሳ፣ ሇእራትና ሇመሳሰለት 300 ብር ወይም ከዯሞዙ 2.5% ሆኖ
ከሁሇቱ ከፍተኛ ባሌበሇጠ ብቻ ነው፡፡
የማንኛውም ዴርጅት ሥራ አስኪያጅ ወይም ም/ሥራ አስኪያጅ ከዴርጅቱ ስራ
ጋር በተገናኘ ወዯ ውጭ ሇሚያዯርገው ጉዞ የሚከፈሇው የውል አበሌ ሇላልች
ሰራተኞች /ተቀጣሪዎች በወሰነው ሌክ ሊይ 20 በመቶ ተጨምሮበት ነው፤
አንዴ ተቀጣሪ የተቀጠረበትን ስራ ሇማከናወን ወዯ ውጭ አገር ሇሚዯረገው ጉዞ
የሚከፈሇው የውል አበሌ ከገቢ ግበር ነፃ የሚሆነው መንግስት ከተሿሚዎች
ውጪ ሇላልች ተቀጣሪዎች በወሰነው የውል አበሌ ሌክ ባሌበሇጠ ብቻ ይሆናሌ
ምሳላ አንዴ

ወ/ሮ አሌማዝ የYXZ ጨርቃ ጨርቅ እንጂነሪንግ ኩባንያ ምክትሌ ስራ አስኪያጅ ሆነው
የሚሰሩ ሲሆን በወር 50 ሺህ ብር ዯመወዝ ይከፈሊቸዋሌ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የቤት አበሌ
በወር 5ሺህ ብር፣ የስሌክ ጥሪ ወጪ 200፣ የትራንስፖርት መጓጓዣና መዘዋወሪያ አበሌ
7,500 ብር ፣ ከቤት ወዯ ሥራና ከሥራ ወዯ ቤት 1,000 ብር እና ሇመስክ ስራ ሇ10 ቀናት
ሇተንቀሳቀሱበት የውል አበሌ ተከፍሎቸዋሌ፡፡

ጥያቄ አንዴ፡- ታክስ የሚከፈሌባቸው ገቢዎች የትኞቹ ናቸው?

ጥያቄ ሁሇት፡- ታክስ የማይከፈሌባቸው ገቢዎች የትኞቹ ናቸው?

ጥያቄ ሦስት፡- ታክሱ ስንት ነው?

16
ጥያቄ አራት፡- የተከፈሊቸው ውል አበሌ ምን ያህሌ ነው?

ጥያቄ አምስት፡- ከታክስ በኋሊ የተገኘ ገቢ ስንት ነው?

መሌስ 1፡- ታክስ የሚከፈሌባቸው ገቢዎች

የትራንስፖርት መጓጓዣና መዘዋወሪያ አበሌ 50,000 x1/4= 12,500 ሲሆን የዯሞዙ ¼


ከ2200 መብሇጥ ስሇላሇበት 7500 -2200 =5,300 ይሆናሌ ማሇት ነው

ከቤት ወዯ ሥራና ከሥራ ወዯ ቤት 1000-600 = 400

በጠቅሊሇው ታክስ የሚከፈሌበት ገቢ=50,000 +5,000+5,300+400 =60,700

መሌስ 2፡- ታክስ የማይከፈሌባቸው ገቢዎች 200+2,200+600 =3,000


መሌስ 3፡- የሚከፈሇው ታክስ መጠን= 60,700 x35/100 - 1500 =19,745

መሌስ 4፡- ሇስራ አስኪያጅ ወይም ሇምክትሌ ስራ አስኪያጅ የሚከፈሇው የቀን ውል አበሌ
ከገቢ ግብር ነፃ የሚዯረገው 1,000.00 ብር ወይም ከዯመወዙ 5% ሆኖ ከሁሇቱ ከፍተኛ
ከሆነው ባሌበሇጠ ብቻ ይሆናሌ፡፡

ስሇዚህ 50,000x5%=2,500 የቀን ውል አበሌ 1000 ሳይሆን 2,500 ነው ምክንያም


ከሁሇት አንደ የበሇጠውን ስሇሚሌየ10 ቀናት የሥራ ቆይታ x 2,500 = 25,000 የውል
አበሌ ያገኛለ ማሇት ነው፡፡

ጠቅሊሊ ገቢ = 50,000+5,000+200+7,500+1,000+25,000= 88,700.00

መሌስ 5፡- ከታክስ በኋሊ ያሇው ገቢ =88,700-19,745 = 68,955

ሇተቀጣሪ በነፃ ሇሚቀርብ ምግብና መጠጥ


 በማዕዴን ማውጣትና ፍሇጋ፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በግብርና እና ሆርቲካሌቸር
ስራ ሊይ ሇተሰማሩ በአንዴ ወር ሇዯመወዝ በሚያወጣው ከአጠቃሊይ ዯመወዝ
ወጪ 30% ሳይበሌጥ እና
 ሆቴልች፣ በሬስቶራንቶች ወይም በላልች የምግብ አገሌግልት ስራ ሊይ ሇተሰማሩ
በአንዴ ወር ሇዯመወዝ በሚያወጣው ከአጠቃሊይ ዯመወዝ ወጪ 20% ሳይበሌጥ)
 ሇተቀጣሪዎች የሚቀርብ የዯንብ ሌብስ እና የሥራ መገሌገያ፡፡
 በዓይነት ጥቅሞች ሊይ የሚከፈሇው ጠቅሊሊ ግብር በማንኛውም ሁኔታ ተቀጣሪው
በወሩ ከሚያገኘው የዯመወዝ ገቢ 10% (አስር በመቶ) አይበሌጥም፡፡
በውጭ ሀገር ከመቀጠር የሚገኘ ገቢ
ግብርን ቀንሰው የማስቀረት ግዳታ ከላሇባቸው ቀጣሪ ዴርጅቶች ወይም ኢንባሲዎች
የሚሰራ ሰው ራሱ ግብሩን ቀንሶ ማስቀረት /መክፈሌ አሇበት፤

17
በኢትዮጵያ ነዋሪ የሆነ ተቀጣሪ በውጭ አገር በመቀጠር ገቢ ያገኘ እንዯሆነና ግብር
የከፈሇበት ከሆነ ግብር ማካካሻ ያገኛሌ፤

3.2 ከመቀጠር ገቢ ጋር የተያያዙ ላልች ዴንጋጌዎች


ማንኛውም ቀጣሪ ሇተቀጣሪው ከሚከፍሇው ዯመወዝ ሊይ ሥራ ግብሩ ቀንሶ
ማስቀረትና መክፈሌ አሇበት፤

ተቀጣሪው ከአንዴ በሊይ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ካሇው እና በአንዯኛው ቀጣሪ


ይኼው ከታወቀ በጠቅሊሊው ገቢ ሊይ ተመስርቶ ግብሩን ቀንሶ በማስቀረት
መክፈሌ አሇበት፤
ከመቀጠር ከሚገኝ ገቢ ሊይ የሚከፈሌ ግብር በቀጣሪው ተቀናሽ መዯረግ ካሇባቸው
ላልች ግዳታዎች ቅዴሚያ አሇው፤
ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ በአንዴ ሠንጠረዥ ውስጥ ከሚወዴቁ ከተሇያዩ የገቢ
ምንጮች ገቢ ያገኝ እንዯሆነ ሁለም ገቢዎች ተጣምረው በዚያው ሠንጠረዥ ሥር
የዓመቱን ግብር ይከፍሊሌ፡፡

ሙከራ አራት
ሠሌጣኞች ከመቀጠር ከሚገኙ ገቢ ሊይ ከታክስ ነፃ የተዯረጉ እና በገዯብ
ከታክስ ነፃ የተዯረጉትን ይዘርዝሩ?

ክፍሌ አራት
4.1 የወጪ መጋራት
ማንኛውም በመንግስታዊ ተቋም የከፍተኛ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ምሩቅ ተማሪ ወጪን
በመጋራት መርህ ሊይ የተመሰረተ የትምህርት፣ ስሌጠና እና አገሌግልት ክፍያ መፈጸም
ይኖርበታሌ ፡፡
ክፍያው የሚፈጸመው ከምረቃ በኋሊ ከሚገኝ የዯሞወዝ ገቢ ወይም ላሊ ገቢ ሊይ ተከፋይ
በሚሆን ግብር ይሆናሌ ፡፡ (የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 351/1995 አንቀጽ56)

ከ1996 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወዯ መንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት


በገቡ አዱስ ተማሪዎች ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ እንዱሁም የሁሇተኛ ዓመትና ከዚያ በሊይ በሆኑ
ነባር ተማሪዎች ሊይ ከነበሩበት ዓመት ጀምሮ ተፈጻሚ የሆነ ነው ፡፡

18
4.2 የወጪ ዴርሻ
መንግስት ሇምግብና ሇመኝታ የሚያወጣውን ወጪ ሙለ በሙለ እና ሇትምህርት
ከሚወጣው ውጪ ሇመነሻ 15% ያሊነሰ ተሰሌቶ ተጠቀሚዎች ይጋራለ፡፡
ተጠቃሚው ሉጋራቸው የማይገቡ ወጪዎች ፣
በትምህርት፣ በምርምር ወይም በሰባቲካሌ እረፍት ያለ መምህራንን ሇመተካት
የሚቀጠሩ የትርፍ ጊዜ መምህራን ዯመወዝ
የህክምና ባሇሙያዎች የፕሪ-ክሉኒካሌና የክሉኒካሌ አበሌ
ሇመስተንግድ፣ ሇፕሊንት፣ ሇማሽነሪ እና ሇመሳሪያ ግዢ፣ እዴሳትና ጥገና ፣ሇሀገር
ውስጥ ሇስሌጠና፣ ሇተሽከርካሪ ሇላልች እንዯተሽከርካሪ ሊለ መጓጓዣዎች መግዣ፣
ሇሕንፃ ፣ሇቁሳቁስ እና ሇተገጣጣሚዎች መግዣ ላልች ክፍያዎች እንዱሁም
በቀጥታ በተቋሙ ገቢ በማስገኘት ዓሊማ ሊይ የተሰማሩ ክፍልች ሰራተኞች ዯመወዝ
ተጠቃሚው እንዱጋራቸው አይጠበቅም፡፡

4.3 የወጪ መጋራት ውሌና አፈፃፀም


ማንኛውም በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርት እንዱከታተሌ
የተመዯበ ተጠቃሚ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በቅዴሚያ በየትኛው የክፍያ
ዓይነት ወጪ እንዯሚጋራ ከተቋሙ ጋር ውሌ ይፈጽማለ ፡፡
ውሌ የሚፈፀመው፣ በጤናና በትምህርት ሙያ ሇሚሰሇጥኑና ሇሚሰማሩ
ተጠቃሚዎች መንግስት በሚመዴባቸው ማንኛውም ቦታ በአገሌግልት ግዳታቸውን
እንዱወጡ
የወጪ መጋራትን በአገሌግልት እንዱወጡ ሇተፈቀዯሊቸው ባሇሙያዎች
ሇሰሇጠኑበት ጊዜ እኩሌ የአገሌግልት ጊዜ በመስጠት ይኖርባቸዋሌ ፡፡
እያንዲንደ እስከ ምርቃ ወይም እስካቋረጡበት ጊዜ ዴረስ የሚፈሇግበትን የወጪ
መጋራት ሂሳብ እና ጠቅሊሊ ሇትምህርቱ የወጣውን ወጪ ተቋማት ሇኢትዮጵያ
ገቢዎች ሚኒስቴር በየትምህርት ዘመኑ ከምረቃ በኋሊ በሁሇት ወር ጊዜ ውስጥ
በቋሚነት ማሳወቅ አሇባቸው፡፡
አስቀዴሞ የከፈሇ ተማሪ ትምህርቱን ካቋረጠ እስካቋረጠበት ጊዜ ዴረስ ያሇው ወጪ
ታስቦ ቀሪው ተመሊሽ ይሆንሇታሌ፡፡
በማንኛውም የትምህርት ሙያ የሚሰሇጥን ባሇሙያ ትምህርቱን ሳያጠናቅቅ
በማንኛውም ምክንያት ቢያቋርጥ እስካቋረጠበት ጊዜ ዴረስ የተጠቀመውን ወጪ
መክፈሌ ይኖርበታሌ፡፡ ሆኖም ትምህርቱን ያቋረጠው በሀገራዊ ጥሪዎችና
ተሌዕኮዎች ከሆነ ክፍያው መሰረዝ ይኖርበታሌ፡፡

19
በትምህርት ሙያ የሰሇጠነ ተጠቃሚ በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ማንኛውም
የመንግስት ትምህርት ቤት፣ ቴክኒክና ሙያ ማስሌጠኛ ፣የመምህራን ማስሌጠኛ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላልች የመንግስት ማስሌጠኛ ኢንስቲትዩት ተመዴቦ
አገሌግልት የመስጠት ግዳታ ያሇበት ሲሆን ምዯባ ካሊገኘም ሇሚመሇከተው አካሌ
በወቅቱ በማሳወቅ መረጃ በመያዝ እና በማቅረብ የወጪ መጋራቱን በገንዘብ
እንዱወጣ ይዯረጋሌ፡፡
በጤና ሙያ የሰሇጠነ ተጠቃሚ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የአዱስ አበባና ዴሬዲዋ
ከተማ አስተዲዯር /የክሌሌ ጤና ቢሮ በሚመዴበው ማንኛውም በሀገሪቱ ውስጥ
በሚገኝ የመንግስት የጤና ተቋማት አገሌግልት የመስጠት ግዳታ ሲኖርበት ምዯባ
ካሊገኘ ከጤና ጥበቃ ሚ/ር ፣ ከአዱስ አበባና ዴሬዲዋ ከተማ አስተዲዯር ከክሌሌ ጤና
ቢሮ ማስረጃ መያዝ ይኖርበታሌ፡፡ በሚያቀርበው መረጃ መነሻነት የውጪ መጋራት
ክፍያ ግዳታውን በገንዘብ እንዱወጣ ይዯረጋሌ፡፡
በአገሌግልት ግዳታውን ሇመወጣት ውሌ የፈፀመ ተጠቃሚ እንዯተመረቀ ምዯባ
በወቅቱ አሇማግኘቱን ከሚመሇከተዉ አካሌ ማሇትም ትምህርትን በሚመሇከት እንዯ
አግባብነቱ ከክሌሌ ትም/ቢሮ ወይም ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን መረጃ
ማቅረብ የማይችሌ የትምህርት ባሇሙያ እና ጤናን በሚመሇከት ከጤና ጥበቃ
ሚኒስቴር ከአዱስ አበባና ዴሬዲዋ ከተማ አስተዲዯር ከክሌሌ ጤና ቢሮ መረጃ
ማቅረብ የማይችሌ የጤና ባሇሙያ በመንግስት ተቋም በራሱ ተቀጥሮ ቢሰራ
ግዳታውን በአገሌግልት እንዯተወጣ አይቆጠርም፡፡ ግዳታውን በገንዘብ ከነመቀጫው
እንዱወጣ ይዯረጋሌ፡፡ ሆኖም ምዯባ አሇማግኘቱን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሌ
የትምህርት ባሇሙያ በመንግስት ትምህርት ቤቶችና ተቋማት በመምህርነት ሙያ
እንዱሁም ጤናን በሚመሇከት በመንግስት ጤና ተቋማት ተቀጥሮ የስራ የጤና
ባሇሙያ ግዳታውን በአገሌግልት እንዯተወጣ ይቆጠራሌ፡፡
የወጪ መጋራቱን ከገንዘብ በተሇየ መሌኩ በአገሌግልት እንዱወጣ የሚፈሇግ
ማንኛውም ተጠቃሚ ግዳታውን በአገሌግልት መወጣት ይኖርበታሌ፡፡
መንግስት በመዯበው ቦታ አገሌግልት መስጠት ያሌቻሇ ተጠቃሚ በውለ ሊይ
የተገሇፀውን /የትምህርት 15%፣ የምግብ እና የመኝታ ሙለ በሙለ ወጪ እና
የዚህን ወጪ 50% ቅጣት ጨምሮ ይከፈሊሌ፡፡ ሇተወሰነ ጊዜ አገሌግልት ሰጥቶ
ያቋረጠ ተጠቃሚ ያገሇገሇበት ዘመን ታስቦ ቀሪውን ክፍያ ከነቅጣቱ እንዱከፍሌ
ይዯረጋሌ ፡፡ ተጠቃሚው ቀዯም ሲሌ በላሊ መስክ ተሰማርቶ በገንዘብ መክፈሌ

20
የጀመረ ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ብቻ መንግስት በሚመዴበው ቦታ በአገሌግልት
እንዱወጣ ይዯረጋሌ፡፡
በማንኛውም የትምህርት መስክ ተመርቀው በመንግሰት ትምህርት ቤቶች ፣
በቴክኒክና ሙያ ማስሌጠኛ በመምህራን ማስሌጠኛ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣
በላልች የመንግስት የማስሌጠኛ ኢኒስቲትዩት በመምህርነት ሙያ ወይም
በመንግስት የትምህርት እና ጤና ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት በኃሊፊነትና
በፈጻሚ ሰራተኛነት እንዱሁም በሀገር መከሊከያ ሰራዊት፣ በፌዯራሌ በአዱስ አበባና
ዴሬዲዋ ከተማ አስተዲዯር፣ በክሌሌ እና ማረሚያ ቤቶች ፖሉስ ሰራዊት አባሌ
የሆኑ ብቻ በምዯባም ይሁን በቅጥር በማገሌገሌ ሊይ ያለ የወጪ መጋራቱ
በአገሌግልት ሉያዝሊቸው ይችሊሌ፡፡ ሆኖም ግን በከፊሌ አገሌግልት ሰጥተው
ካቋረጡ ቀሪውን የወጪ መጋራት ግዳታቸውን ከነመቀጫው ገንዘብ በመክፍሌ
እንዱወጡ ይዯረጋሌ፡፡
በሀገር መከሊከያ ሰራዊት ፣በፌዯራሌ፣ በአዱስ አበባና ዴሬዲዋ ከተማ አስተዲዯር ፣
በክሌሌ እና ማረሚያ ቤቶች በፖሉስ ሰራዊት አባሌነት ብቻ አገሌግልት የሰጡ
የወጪ መጋራት ተጠቃሚዎች አገሌግልት ከሰጡበት ተቋም በሚያቀርቡት ማስረጃ
መሰረት በገቢዎች ሚኒስቴር ከዕዲ ነጻ ስሇመሆናቸው ከባሇስሌጣኑ ማስረጃ
በማቅረብ የትምህርት ማስረጃቸውን ከተማሩበት የትምህርት ተቋም ማግኘት
ይችሊለ፡፡
ማንኛውም የትምህርት መስክ ተመርቀው በምዯባም ይሁን በቅጥር በመምህርነት
ወይም በጤና ዘርፍ ተመርቀው የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ተቋማት በመስራት
ሊይ እያለ መንግስት ሇስራ ፈሌጓቸው በሹመት የተመዯቡ ስሇመሆናቸው ማረጋገጫ
በማቅረብ ሹመት ከማግኘታቸው በፊት የሰሩበት ጊዜ በአገሌግልት ታስቦ ቀሪውን
ግዳታ ያሇቅጣት በገንዘብ እንዱወጡ ይዯረጋሌ፡፡

4.4 ተጠቃሚው ክፍያውን በገንዘብ ሇመክፈሌ ያለ አማራጮች፡-


 ትምህርቱን ጨርሶ ወይም አቋርጦ ከቆየ ከአንዴ አመት የእፎይታ ጊዜ በኋሊ
በግብር መሌክ ከዯመወዙ ወይም ከገቢው ሊይ ቢያንስ ከመቶ አስር /10%/
ተቀናሽ እየተዯረገ ሉከፍሌ ይችሊሌ፡፡
 ተጠቃሚው ትምህርት በሚከታተሌበት በእያንዲደ አመት የሚፈሌግበት ክፍያ
በቅዴሚያ ወይም
 ተጠቃሚው እንዯተመረቀ ወይም ትምህርቱን እንዲቋረጠ በእፎይታ ጊዜው
ውስጥ ክፍያውን በሙለ በአንዴ ጊዜ ሉከፍሌ ይችሊሌ ፡፡

21
4.5 የእፎይታ ጊዜ
ተጠቃሚው ከተመረቀበት ወይም ትምህርቱን ካቋረጠበት ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ሥራ
ቢይዝም ባይዝም ክፍያ ሇመጀመር የአንዴ ዓመት የእፎይታ ጊዜ ይኖረዋሌ ፡፡ በዚህ ጊዜ
ውስጥ ሥራ ካሌሠራና ገቢ ካሊገኘ ከሁሇተኛው ዓመት መጀመሪያ ቀን ጀምሮ ሇስዴስት
ወራት ብቻ የእፎይታ ጊዜ ይሰጣሌ ፡፡

4.6 ማበረታቻ
ጠቅሊሊ የወጪ መጋራት በቅዴሚያ ሇሚከፍሌ ተጠቃሚ 10%
በየሴሚስተሩ ወይም በየዓመቱ ቅዴሚያ ሇሚከፍሌ 5%
ከምረቃ በኋሊ በእፎይታ ጊዜ እስከ አንዴ ዓመት ሇሚከፍሌ 3% ተቀናሽ
ይዯረግሇታሌ ፡፡

4.7 የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥ እና ስሇቀጣይ ስሌጠና ሥርዓት


የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት በአገሌግልት እንዱከፈለ የሚጠበቅባቸው
ተጠቃሚዎች የሚፈሇግባቸውን የወጪ መጋራት ግዳታ እስኪወጡ ወይም በገንዘብ
ግዳታ የገቡ ተጠቃሚዎች ክፍያ እስኪያጠናቅቁ ወይም ሇክፍያው የባንክ ዋስትና
እስኪያቀርቡ ጊዜያዊም ሆነ ዋናውን የትምህርት ማስረጃና ትራንስክርቢት /ኦፊሻሌን
ጨምሮ/ የትምህርት ማስረጃ አይሰጥም ፡፡
ማንኛውም የመንግስት ሆነ የግሌ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሙያው አገሌግልት
የመስጠት ግዳታ ያሇበትን ተመራቂ አገሌግልት መስጠቱን እንዱሁም ገንዘብ
ሇመክፈሌ ግዳታ የገባ ክፍያውን ሳያጠናቅቅ ሇቀጣይ ከፍተኛ ትምህርት መቀበሌ
የሇበትም ፡፡

4.8 የወሇዴ አከፋፈሌና መጣኔ


ተጠቃሚው የሚከፍሇው የወጪ መጋራት ክፍያ ወሇዴ የሚታሰብበት ሲሆን ወሇደ
መታሰብ የሚጀምረው ከእፎይታ ጊዜ በኋሊ ነው፡፡ የወሇደ መጠንም ተጠቃሚው ከተቋሙ
ጋር በፈረመባቸው የትምህርት ዘመናት የተቀማጭ ገንዘብ አማካይ የወሇዴ መጣኔ
ይሆናሌ፡፡
ሇምሳላ:-
ተጠቃሚው የፈጀበት የትምህርት ጊዜ አራት አመት ሆኖ የተቀማጭ ገንዘብ የወሇዴ መጣኔ
የሁሇት አመት 3% ቢሆን የቀረው ሁሇት አመት ዯግሞ 4% ቢሆን ክፍያው የሚታሰብበት
የወሇዴ መጣኔ፡-

22
2(3) + 2(4) = 14 = 3.5 ይሆናሌ፡፡
4 4
ተጠቃው የፈጀበት የትምህርት ጊዜ አምስት አመት ሆኖ የተቀማጭ ገንዘብ የወሇዴ ምጣኔ
የሁሇቱ አመት 4 ቢሆን የሦስቱ አመት ዯግሞ 5 ቢሆን ክፍያው የሚታሰብበት የወሇዴ
ምጣኔ ፡-
2(4) + 3(5) = 23 = 4.6 ይሆናሌ፡፡
5 5
 የወሇደ ስላት እና አከፋፈሌ የማንኛውም የባንክ ብዴር ወሇዴ በሚታሰብበትና
በሚከፈሌበት ዓይነት ዋናው እዲና ወሇደ ተሇይቶ መሰሊት፣ መከፈሌና መሰብሰብ
አሇበት ፡፡

ዕዲን ሇመክፈሌ ዋስ ሰሇማቅረብ


ተጠቃሚው የወጪ መጋራት ክፍያ ዕዲውን ከፍል ሳይጨርስ ከኢትዮጵያ ውጭ የሚሄዴ
ከሆነ ወይም ዋናውን /ኦርጅናሌ/ የትምህርት ማስረጃውን ከጠየቀ፡-
 ዕዲውን በአንዴ ጊዜ ሙለ በሙለ ከፍል ማጠናቀቅ ይኖርበታሌ

 ዕዲውን በአንዴ ጊዜ ሙለ በሙለ ከፍል ማጠናቀቅ ካሌቻሇ በእግሩ ተተክቶ


እዲውን ከነወሇደ በየወሩ የሚከፍሌሇት የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታሌ

 ዕዲውን ከነወሇደ የሚከፍሌሇት የባንክ ዋስትና በማቅረብ ከ15 ዓመት ባሌበሇጠ


ዕዲውን ከፍል ማጠናቀቅ አሇበት፡፡

የወጪ መጋራት ስላት


ሇማስሊት መሠረት የሚዯረግባቸው ነገሮች
I. የተመረቀበት ዘመን፣
II. በምረቃ ወቅት የነበረው የባንክ ቁጠባ መጣኔ፣
III. የእፎይታ ጊዜ፡፡

ምሳላ:- 2005 ዓ.ም ሰኔ 30 የተመረቀ ተማሪ አጠቃሊይ 20 ሺህ ብር የወጪ መጋራት


ብር ቢኖርበት ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም ሊይ ሙለ ክፍያ ሇመክፈሌ ቢፈሌግ አጠቃሊይ
ክፍያው ስንት ይሆናሌ?
I. የተመረቀበት ዘመን =ሰኔ 30/2005 ዓ.ም
II. በምረቃ ወቅት የነበረው የባንክ ቁጠባ ምጣኔ = 4% ቢሆን (ግምታዊ)
III. የእፎይታ ጊዜ 1 ዓመት (2006) ይሆንና ከ2007 ጀምሮ ታክሱ የሚሰሊ ይሆናሌ፡፡

23
ወሇዴ = ታክስ X ወር X የባንክ ቁጠባ መጣኔ
12
20,000*78*0.04
12
ወሇዴ= 5,200.00
ጠቅሊሊ ክፍያ= ታክስ  ወሇዴ
ጠቅሊሊ ክፍያ = 20,000 5,200
ጠቅሊሊ ክፍያ= 25, 200.00

4.9 የአሠሪዎች ግዳታ


ማንኛው አሰሪ፡-
የቀጠራቸውን ተጠቃሚዎች ዝርዝር ሇባሇሥሌጣኑ ወይም ሇሚመወክሇው
የማስታወቅ
በገንዘብ ሇመክፈሌ ግዳታ ከገቡ ተጠቃሚዎች የሚፈሇግባቸውን እዲ የሚያሳይ
ማስረጃ ከተጠቃሚዎቹ በመቀበሌና ስሇ ትክክሇኛነቱ ከባሇሥሌጣኑ በማረጋገጥ
በየወሩ ከጥቅሌ ዯመወዛቸው ቢያንስ 10% እየቀነሰ ከእያንዲንደ ወር መጨረሻ
አንስቶ ባለት ሰሊሳ ቀናት ውስጥ ሇባሇሥሌጣኑ ወይም ሇሚወክሇው የመክፈሌ
ተጠቃሚዎች ከተቋሙ የተሰጣቸውንና የሚፈሇግባቸውን እዲ የሚያሳየውን ማስረጃ
ሇመስጠት ፍቃዯኛ ካሌሆኑ የጥቅሌ ዯመወዛቸው አንዴ ሶስተኛ እየቀነሰ ሇባሇስሌጣኑ
ወይም ሇሚወክሇው ገቢ የማዴረግ ፣
ገንዘብ በመክፈሌም ሆነ አገሌግልት በመስጠት እዲቸውን ከፍሇው ያጠናቀቁ
ተጠቃሚዎችን ዝርዝር ክፍያው በተጠናቀቀበት ወር ሇባሇሥሌጣኑ ወይም
ሇሚወክሇው የማሳወቅ
አገሌግልት በመስጠት እንዯሚከፍለ ተገሌጾ የተመዯቡሇትን ተጠቃሚዎች ተገቢውን
ክትትሌ በማዴረግ ማሰራትና አገሌግልት ካቋረጡ ሙለ ሇሙለ ማቋረጣቸውን
በማረጋገጥ ወዱያውኑ ሇባሇሥሌጣኑ ሇትምህርት ሚኒስቴር ሇመዯባቸው ሚኒስቴር
መስሪያ ቤት የማሳወቅ ግዳታ አሇበት ፡፡

የክትትሌና ቁጥጥር ተግባር


ባሇስሌጣኑ ወይም የወከሇው ገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት
ተጠቃሚዎችን ቀጥሮ የሚያሰራ የመንግት ሆነ የግሌ አሰሪ በዯንቡ የተሰጠውን
ኃሊፊነት በአግባቡ እየተወጣ ስሇመሆኑ የቅጥር እና የክፍያ ሰነድችን በመመርመር
በማጣራትና በመከታተሌ

24
እንዯ አስፈሊጊነቱም የወጪ መጋራት ክፍያው አሰባሰብ በተገቢው ሁኔታ እንዱፈፀም
ሇአሠሪው አስፈሊጊውን የምክርና ቴክኒክ ዴጋፍ በመስጠት
አሠሪው ወይም በግለ የሚሠራ ተጠቃሚ ከገቢ ሊይ ተቀናሽ በማዴረግ ክፍያውን
ሳይፈጽሙ ከቀሩ እና ግብር የመክፈሌ ግዳታውን ካሌተወጣ ሚኒስቴር መ/ቤቱ
የክፍያ ውሳኔ ማስታወቂያ አዘጋጅቶ ሇአሰሪው ወይም ሇተጠቃሚው እንዱዯርስ
ማዴረግ
አሰሪውም ሆነ ተጠቃሚው የተጣሇባቸውን ኃሊፊነት ካሌተወጡ ከገቢ ሊይ ተቀንሶ
ሇባሇስሌጣኑ ገቢ ባሌተዯረገው ገንዘብ መጠን ፤ ወሇዴ እና አስተዲዯራዊ መቀጫ
ጭምር ተጠያቂ እንዯሚሆኑ በመግሇጽ ክትትሌና ቁጥጥር ማዴረግ አሇበት ፡፡

ተመሊሽ ጥያቄ አቀራረብና አፈጻጸም


የወጪ መጋራት ክፍያ አስቀዴሞ የከፈሇ ተጠቃሚ ትምህርቱን በማቋረጡ ምክንያት
ያሌተጠቀመበት ገንዘብ እንዱሁም መክፈሌ ከሚገባው በሊይ የወጪ መጋራት ክፍያ
የፈጸመ ተጠቃሚ በስህተት በብሌጫ የከፈሇው ገንዘብ ተመሊሽ እንዱዯረግሇት
አስፈሊጊ ከሆኑ ማስረጃዎች ጋር ክፍያው ሇተፈጸመበት የባሇስሌጣኑ ቅ/ጽ/ቤት
(ውክሌና ሇተሰጠው ገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት የከፈሇ የስርዓቱ ተጠቃሚ በአቅራቢያው
ሇሚገኝ የባሇስሌጣኑ ቅ/ጽ/ቤት) ጥያቄውን ማቅረብ ይችሊሌ ፡፡

ሙከራ አምስት
ሰሌጣኞች የወጪ መጋራት አከፋፈሌ ሥርዓት ያስረደ?

ሙከራ ስዴስት
ሠሌጣኞች ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ እና የወጪ መጋራት ምንነት
በመረዲት መብትና ግዳታዎችን ይዘርዝሩ

ማጠቃሇያ
ግብር የአንዴ ሀገር መንግስት ዋነኛና አስተማማኝ የገቢ ምንጭ በመሆኑ ከመቀጠር ከሚገኝ
ገቢ (ሠንጠረዥ "ሀ") ከቅጥር ውሌ ጋር በተያያዘ የሚያገኘው ዯመወዝ /ምንዲ፣ አበሌ፣
ጉርሻ፣ ኮሚሽን፣ የመሌካም ሥራ አፈፃፀም ማበረታቻ ስጦታ ወይም ላሊ የአገሌግልት ዋጋ
ክፍያ፣ ተቀጣሪው ከስራ ሲቀነስ ወይም ከስራ ሲሇቅ ወይም ስራን እንዱሇቅ ሇማግባባት
የሚከፈሌ ገንዘብ ወይም የስራ ውሌ በመቋረጡ ምክንያት በፈቃዯኝነት፣ በስምምነት፣
በዲኝነት ውሳኔ መሠረት በጥሬ ገንዘብ (በዓይነት) የተቀበሇው ማንኛውም የገንዘብ መጠን

25
ከታክስ ነጻ ከተዯረገው ውጭ፣ እንዯ ገቢ ተቆጥሮ ታክስ የሚሰሊበት በመሆኑና የከፍተኛ
ትምህርት የወጪ መጋራትም መንግስት ሇትምህርትና ሇላልች አገሌግልቶች ያወጣውን
ወጪ መጋራት በመሆኑ ታክሱን የመሰብሰብ ኃሊፊነት የተጣሇባቸው አካሊት ታክሱን
በተቀመጠው ህግ መሰረት ሇግብር ሰብሳቢው መ/ቤት በወቅቱ ገቢ እንዱያዯርጉ እና ወጥነት
ያሇው አሰራር ሥርዓት እንዱኖር ሇማስቻሌ ነው ፡፡

ማጣቀሻዎች
በዚህስሌጠናርዕስየተጠቀምናቸውማጠቀሻአዋጆች ፤ዯምቦች እና መመሪያዎች

1. የፌዯራሌየገቢግብርአዋጅቁጥር 979/2008

2. የታክስአስተዲዯርአዋጅቁጥር 983/2008

3. ከገቢ ግብርነፃ የተዯረጉ ገቢዎችአፈፃፀምመመሪያቁጥር 1/2011

4. የወጪ መጋራት ዯንብ 154/2000

5. የወጪ መጋራት መመሪያ ቁጥር2/2009

6. የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ 351/1995

26

You might also like