Professional Documents
Culture Documents
4/27/2022
ኢ-ታክስ
ኢ-ፔይመንት
ኢ-ፋይሊንግ
ኢ-ታክስ
ኢ-መረጃ
ኢ-ክሊራንስ
ኢ-ታክስ የሚያጠቃልላቸው አገልግሎት አይነቶች በሚከተሉት
መልክ ቀርቧል፡፡
ኢ-ፋይሊንግ ፡- ግብርን የመላክ/የማሳወቅ አሰራር ስርዓት ነው፡፡
ኢ-ፔይመንት፡- ከየትኛውም ቦታ ሆኖ የኢንተርኔት አገልግሎት በመጠቀም ወደ ተቋሙ ድህረገጽ
በመግባት ቀደም ሲል በኢ-ፋይሊንግ በላከው መረጃ ክፍያውን የሚከፍልበት ሲሰተም ነው
ኢ-ክሊራንስ ፡-ግብር ከፋዩ ድርጅት የሚንስቴር መ/ቤት ድረ-ገጽ በመጠቀም የታክስ ምላሽ
ክሊራንስ ለመጠየቅ የሚያስችለው ከመሆኑም በላይ በወቅቱ ግብሩን የከፈለ እና ምንም አይነት
የታክስ ክፍያ የሌለው ግብር ከፋይ በቀላል መንገድ የዓመታዊ ንግድ ፈቃድ ማደሻም ሆነ ሌሎች
ክሊራንሶች በኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት የሚችልበት የአሰራር ስርዓት ነው፡፡
የታክስ ነክ መረጃ አገልግሎት ኢ-ታክስን ተጠቅሞ አንድ ግብር ከፋይ ድርጅት መጠየቅ
የሚፈልጋቸውን ታክስ ነክ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በቀላሉ ማግኘት የሚያስችለው ሲሆን
ግብር ከፋዮች የስርዓቱ ተጠቃሚ እየሆኑ በሄዱ ቁጥር ከሚንስቴር መ/ቤቱ ጋር ያላቸው የስራ
ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድግ እና የሚያቀራርብ በመሆኑ ከፍተኛ ጠቀሜታያለው የአሰራር
ስርዓት ነው
ኤሌክትሮንክስ የታክስ ስርዓት
በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 82
ገቢ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት
በታክስ ህጉ መሰረት ለመመዝገብ ወይም የታክስ መለያ ቁጥር ለማግኘት ማመልከቻዎች
ለማቅረብ
በታክስ ህጉ መሰረት ታክስ ማሳወቂያ ሆነ ሌላ ሰነድ ለማቅረብ
በታክስ ህጉ መሰረት ታክስ ወይም ሌላ ክፍያዎችን ለመፈፀም
በታክስ ህጉ መሰረት የታክስ ተመላሽ ክፍያን ለመፈፀም
ገቢ ሰብሳቢውን የሚያስተላልፈውን ማንኛውም ሰነድ ለመላክ
መከናወን የሚኖርበትን ወይም እንዲከናወኑ የተፈቀደ ሌላ ድርጊት ወይም ነገር ለማከናወን
ኢ-ታክስ መመዝገብ ያለበት ግብር ከፋይ ማን ነው?
የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ያለበት ማንኛውም ታክስ ነክ ክፍያዎች የሚከፍል እና
የሚያስታውቅ ግብር ከፋይ በሙሉ
ኢ-ታክስ ለመጠቀም ምን ያስፈልጋል?
Specification ያሟላ የኢ-ታክስ መጠቀሚያ ኮምፒውተር
Processer Speed 3.2 GHZ ፍጥነቱ256 KBS እና ከዚያም በላይ የሆነ ብሮድባንድ
ኢንተርኔት(EVDO)
Adobe Reader 9 ወይም ከዚህ በላይ፣
የኢንተርኔት መጠቀሚያ ኘሮግራም(Internet Browser) በቅርብ ጊዜ የመጣ መሆን ይኖርበታል፡፡
ለምሣሌ፡- Internet Explorer 7ወይም የተሻለ
Mozilla:-Fire Fox ወይም በላይ
በድርጅቱ የሚገኙ የሥራ ግብር የሚከፍሉ ሠራተኞች በሙሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስመዝገብ
ይጠበቅባቸዋል፡፡
በኤሌክትሮኒክስ ታክስ አከፋፈልን ባለመከተል የሚጣል ቅጣት
ለግብር ከፋዩ
• Time savings. ... ጊዜን ይቆጥባል
• Expenses control. ... ወጪዎቻችን በሙሉ ኤሌክትሮኒካሊ ስለሚኖር የደረሰኝ መጥፋት እና ሌሎች ነገሮችን መቆጣጠር
እንችላለን
• Reduced risk of money lost. ...
• አደጋን ይቀንሳል/የገንዘብ መጥፋትና እና ግብርን ያለማሳወቅ ሁኔታን መከታተል እና መቆጣጠር ይቻላል
Username: xxx
Password:1-6@Tp
Step 3፡-E-tax service የሚለውን ክሊክ እናደርጋለን
ሁለተኛውን ዩዘርኔም እና ፓስወርድ ማስገባት
E-tax production
Username: xxxxxxxxx
Password: xxxxxxxxx
Taxpayer service ግብር ከፋዩ የሚያሳውቃቸው የታክስ አይነቶች በሙሉ የምናገኝበት ክፍል ይሆናል ፡፡ እዚህ
ክፍል ላይ ከዚህ በፊት ክሊራንስ የጠየቅነው ዝርዝር እና ክሊራንስ መጠየቂያ ክፍል ያለንን ሪቨንድ/ተመላሽ
ተመልክተን ተመላሽ የምንጠይቅበት ክፍል እና በተጨማሪም አካውንታችን ወይም በምናሳውቀው ግብር ላይ ምን
ያህል እዳ ይኑረን ተመላሽ መመልከት በተጨማሪም ግብራችንን ማሳወቂያ ክፍል አለው ፡፡
እነዚህ ከላይ የምንመለከተው የግብሮች አይነት አንድ ግብር ከፋይ ከዚህ ቀደም እያሳወቀ ያለውን የግብር አይነት
ብቻ ይዞ የሚገኝ ይሆናል ፡፡
የኢ-ታክስ ተጠቃሚ ግብር ከፋይ ግብሩን እንዴት በኢ-ታክስ ማሳወቅ ይችላል ፡፡
ግብር ከፋዩ በሶስት አይነት ግብሩን በሲስተም ማሳወቅ ይችላል
1.የኢ-ታክስ ሲስተም የማሳወቂያውን ዲክለሬሽን/ፎርማት በመክፈት እና እላዩ ላይ በመሙላት ማሳወቅ ይችላል ፡፡ለምሳሌ
ቫት እና ንግድ ትርፍ value add tax(vat)ከሚለው አጠገብ ያለውን የመደመር ምልክት ስንከፍተው ፊት ለፊት የአምስት
ወሮችን ያሳየናል ወደላይ እና ወደታች በማድረግ የምንፈልገው ወር ላይ ፋይል ናው /file now/ የሚለውን እንከፍታልን ፡፡
*
በኢ-ታክስ ሲስተም * ሊዘለል እና ሳይሞላ ሊታለፍ ማይችል ምልክት ነው ስለዚህ ሁል ጊዜ ምልክቱን ባየንበት ቦታ መዝለል አንችልም
የምናሳውቀው ዜሮ እንኳን ቢሆን ምልክት ያለበት ቦታ ላይ ዜሮን መፃፍ አለብን ፡፡
ሁሉንም መሙላት ያለብንን ግብር ከሞላን በሃላ ወደቀጣዩ ክፍል እንዲሄድልን /continue step 2 / የሚለውን እንነካለን
ዲክለሬሽን ፓርቱን ኮንፎርም እምናደርግበት ቦክስ ይመጣል
ቲክ እናደርጋለን እና ሰሚት /submit/እንላለን
ሰሚት ስንለው እርግጠኛ ነህ ይህን ግብር ለማሳወቅ / Are you sure
you want to submit the declaration?የሚል ይመጣል
አዎ/yes/እንላለን፡፡
ሰሚት ስናደርገው/ግብራችንን ካሳወቅን በሃላ ከፈለግን ፕሪንት እንድናደርግ እዚህ
ጋር ክፈት ወይም ክሊክ እናደርጋለን Your declaration's submission
number is 1404310003
If you wish to print a copy of your submitted tax declaration,
click here
ያሳወቅነውን ፕሪንት እንድናደርግ ፕሪንት የምትል እና የፕሪንት
ምስል ያለበት ይከፈታል ክሊክ እናደርጋለን/እንከፍታለን/
ፕሪንት ስንለው የዚህ አይነት ምስል ይመጣልናል የግብር ከፋዩ ሙሉ መረጃ የያዘ እና ዶክሜንት ቁጥር ያለው ይመጣል ፕሪንት
አድርገን ለክፍያ እንመጣለን፡፡
2.በኢ-ታክስ ሲስተም ተጠቃሚ ግብር ከፋይ በየወሩ የሚያሳውቀው ግብር አንድ አይነት ከሆነ እና
መረጃው የማይለያይ ከሆነ በየወሩ ያለፈውን በዚሁ ሲስተም የተጠቀመውን በመጥራት እና መረጃውን
ወደሚፈልግበት ወር ማስገባት የሚችልበት ዘዴን መጠቀም ይችላል