You are on page 1of 2

Atkena Trading PLC – Nisir Rental Technologies

+251 995 77 77 77/ +251 929 82 33 39


Addis Ababa, Ethiopia

የኤጀንት ውል

ውል ሰጪ፦ አትከና ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (የንግድ ስም - ንስር ሬንታል ቴክኖሎጂ) ከዚህ በኋላ አሰሪ
ተብሎ የሚጠራ፤

የንግድ ሥራ ፈቃድ ቁጥር፦ BL/AA/14/673/4202193/2015 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፦ 0081738648

ውል ተቀባይ፦ ___________________________________________________ ከዚህ በኋላ ኤጀንት ተብሎ የሚጠራ፤

የንግድ ሥራ ፈቃድ ቁጥር፦ _______________________________________ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፦ ________________________

አድራሻ፦ አዲስ አበባ ክፍለ ከተማ፦ ____________________ ወረዳ፦ __________ የቤት ቁጥር፦ _______________

ስልክ ቁጥር፦ ___________________________________________________

1. የውሉ ይዘት

ይህ ውል፤ አሰሪ ተብሎ በሚጠራው መስሪያ ቤት፤ የስራ ቦታው አዲስ አበባ እና ኤጀንት ተብሎ በሚጠራው ግለሰብ መካከል
የሚደረግ የውል ስምምነት ሲሆን፤ ኤጀንቱ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ስራ ላይ ለተሰማሩ አሽከርካሪዎች
የድርጅቱን የመኪና ኪራይ እና የሜትር ታክሲ አገልግሎት በማስተዋወቅ አሽከርካሪዎች የድርጅቱን መተግበሪያ አውርደው
እንዲመዘገቡ ለማድረግ፤ አሰሪው ደግሞ በዚህ ውል መሠረት የተቀመጠውን ኮሚሽን አስቦ ለመክፈል የተገባ ስምምነት
ነው።

2. የኤጀንት መብትና ግዴታ

2.1. ኤጀንቱ በስሩ ሌሎች ሰራተኞችን በራሱ ቀጥሮ የማሰራት መብት ያለው ሲሆን፤ ኤጀንቱ በሁለት ሳምንት
ቢያንስ 2000 (ሁለት ሺ) አሽከርካሪዎች የድርጅቱን መተግበሪያ አውርደው እንዲመዘገቡና የድርጅቱን ሎጎ መኪናቸው ላይ
እንዲለጥፉ የማድረግ ግዴታ አለበት፤ ዉል ሰጪ ባስቀመጠው ፎርም ላይ የኣሽከርካሪዉም ሆነ የተሽከርካሪው
መረጃዎች ባግባቡ መሞላት ይኖርበታል።በሁለት ሳምንት የተቀመጠውን ኮታ ወይም ቁጥር ማሟላት የማይችል ኤጀንት
ከአሰሪው ጋር የሚኖረው ውል የሚቋረጥ ይሆናል።

2.2. ኤጀንቱ ስላከናወነው ስራ በየጊዜው ለአሰሪው ወይም እሱ ለሚወክለው ኃላፊ ሪፖርት የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን
በዚህ ውል መሠረት ሰራተኛው የሚሰበስበው ማንኛውም መረጃ፣ ምስል፣ የሥራ ሪፖርት እንዲሁም አስተያየት የአሰሪው
ንብረቶችና መብት ይሆናል።

3. የኮሚሽን ሁኔታ

3.1. አሰሪው በዚህ ውል መሰረት ኤጀንቱ በመዘገባቸው አሽከርካሪዎች ልክ በእያንዳንዱ አሽከርካሪ 60 (ስልሳ) የኢትዮጵያ ብር
እንዲሁም ከተቀመጠላቸው ኮታ በላይ ለሚያመጡት ለተጨማሪዎቹ አሽከርካሪዎች ብቻ 70 (ሰባ) የኢትዮጵያ ብር በማሰብ
በየ 15 (አስራ አምስት) ቀኑ የሚከፍል ሲሆን ተገቢዉን የመንግስት የስራ ግብር ተቆራጭ የሚያደርግ ይሆናል።
Atkena Trading PLC – Nisir Rental Technologies
+251 995 77 77 77/ +251 929 82 33 39
Addis Ababa, Ethiopia

3.2. የኮሚሽን ወይም የማበረታቻ ጥቅማጥቅሞች የሚከፈሉት ውል ሰጪው በሚያቀርበው ፖሊሲ መሰረት ሲሆን ውል ሰጪው
የኮሚሽን ክፍያ ፖሊሲን የማሻሻል መብት አለው።

3.3. በዚህ ውል አንቀጽ 2.1 ላይ በተቀመጠው መሰረት የተጠቀሰዉን ታርጌት በሁለት ሳምንት ዉስጥ ካልተሟላ ዉል ሰጪ ምንም
ኣይነት ክፍያ የማይፈፅም ይሆናል።

4. የውሉ ጊዜ

የውሉ ዘመን ለሁለት ወር ጊዜ ከ ___________________________________ እስከ ______________________________ ለሁለቱም ወገን የሚፀና


ሲሆን በሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች የጽሁፍ ስምምነት ውሉ ሊታደስ ይችላል።

5. ውሉን ስለማቋረጥ

5.1. በዚህ ውል አንቀጽ 2.1 ላይ በተቀመጠው መሰረት ለሁለት ሳምንት የተቀመጠውን ኮታ ወይም ቁጥር ማሟላት የማይችል
ከሆነ እንዲሁም በዚህ ውል ውስጥም ሆነ በውስጥ መመሪያዎች የሚሰጡ ተግባራትን ማከናወን ካልቻለ ወይም በማንኛውንም
ጊዜ ሥራውን እና የተሰጠውን ኃላፊነት የጣሰ ከሆነ አሰሪው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውል ሊያቋርጥ ይችላል።

እኛ ተዋዋይ አካላት በነፃ ፈቃዳችን የውሉ ስምምነት የሚያስከትልብንን ግዴታዎች፤ አውቀንና ተረድተን ውል መግባታችንን
በፊርማችን እናረጋግጣለን።

ውል ሰጪ ውል ተቀባይ

ስም _________________________________________________ ስም _________________________________________________

ፊርማ _______________________________________________ ፊርማ _______________________________________________

ቀን __________________________________________________ ቀን __________________________________________________

You might also like