You are on page 1of 20

P.O.

Box 1047 Addis Ababa Ethiopia


www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

በዋና የቴሌብር ወኪል

እና

በቴሌብር ወኪል መካከል የተደረገ

የቴሌብር ወኪልነት ስምምነት


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

ይህ ስምምነት እ.ኤ.አ በ ወር/ቀን/ ዓ.ም በ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በኢትዮጵያ በሚገኝ ደንብን ተከትሎ

በተቋቋመና በፌደራል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ህግ በሚተዳደረው ኢትዮ ቴሌኮም ተብሎ

በሚጠራ፤ ዋና መ/ቤቱ በአዲስ አበባ፣ ቸርቸል ጎዳና የሆነና ቢሮዎቹ በአራዳ ክ/ከ ወረዳ 01/02 በሚገኙ

እና ከዚህ በኃላ ፟ኢትዮ ቴሌኮም ፟ ተበሎ በሚጠቀሰው ተቋም

እና

…………………………………….. ተብሎ በሚጠራ፤ በ………….. ከተማ ውስጥ በሚገኘ፤ በፌደራል

ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኢትዮጵያ ህግ በሚተዳደረው፤መ/ቤቱ በ……………ከተማ ፤በ…………ክፍለ

ከተማ፤……በቤት ቁጥር …….በፓ.ሳ. ቁ…………እና በስልክ ቁጥር…ተጠቃሽ ከሆነ እና (ከዚህ በኃላ ፟ ዋና

ወኪል ፟ ተበሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር የተደረገ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም እና ዋና ወኪል ከዚህ በኃላ በአንድነት አካሎች በተናጠል ደግሞ ወይም አካል እየተባሉ

ይጠቀሳሉ፤

እነሆ የተጠቀሱት አካሎች እንደሚከተለው ተስማምተዋል፡፡


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

ስምምነቶች እና ሁኔታዎች

ቃላትና ትርጉሞቻቸው
ለዚህ ውል አላማ የሚከተሉት ቃላትና ምህፃረ ቃላት በዚህ ውል የተሰጣቸውን ትርጉም ይሰጣሉ:

አካውንት፡ ማለት ማናቸውም በኢትዮ ቴሌኮም የሚንቀሳቀስ እና የሚመራ ባለቤቱ ደንበኛ የሆነ ሂሳብ ነው፡፡

ቴሌብር፡ ማለት ደንበኛ ሞባይል ስልኩን በቀላሉ ተጠቅሞ ገቢ እንዲፈጽም፣እንዲቀበል፣ገንዘብ እንዲያዛውር እና


ወጪ እንዲያደርግ የሚያስችል የሞባይል መኒ ነው፡፡

ዋና ወኪል : ማለት በስሩ የሚገኙ ቅርንጫፎች አገልግሎቶች እና ወኪሎች ጋር ስለ ኢትዮ ቴሌኮም ቆሞ ውል


እየተዋዋለ እና እያስተዳደረ ለኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት አጠቃላይ የሆነ ስምምነት(ውል)

ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የፈጸመ ህጋዊ ሠው ነው፡፡

ወኪል ፡- ማለት በወኪሎች መመሪያ አጠቃቀም እና በሌሎች አግባብነት ባላቸው ህጎች በተደነገገው መሠረት በዋና
ወኪል ስር የውክልና ሥራ አገልግሎት ለመስጠት ከ ዋና ወኪል ጋር ውል የተዋዋለ ህጋዊ ሠው ነው፡፡

ገቢ ገንዘብ: ማለት የቴሌብር ደንበኛ ጥሬ ገንዘብን በኤሌትሪካዊ ዋጋ የሚቀይርበት ሂደት ነው፡፡ ገንዘብ ግብይት
ዘወትር የተጠቃሚው የኤሌክትሪክ አካውንት ባላንስን ውጤት የሚየሳድግ ነው፡፡

ወጪ ገንዘብ: ማለት የቴሌብር ደንበኛ ኤሌትሪካዊ ዋጋን ወደ ጥሬ ገንዘብ የሚቀይርበት ሂደት ሲሆን ግብይቶችም
የተጠቃሚን ኤሌክትሪካዊ ገንዘብ የሚቀንስ ውጤት የሚያመጡ ናቸው፡፡

ኤሌክትሪካዊ ገንዘብ፡ ማለት በሚያዘጋጀው ሠው ጠያቂነት የሚቀርብ የሚከተሉት ባህሪያት ያሉት ነዋይ ነክ
ዋጋ ነው ፡፡ በተጨማሪም (i) የኢትዮጵያ ብር ተቀብሎ የሚሰጥ፣ (ii) ከአዘጋጁም ወጭ በሆኑ በሌሎች ሠዎችም

በመገባበያነት ተቀባይነት ያለው (iii) በኢትዮጵያ ብር ከሚሰጡ ሌሎች ኤሌክትሪካዊ ገንዘቦች ጋር እኩል ዋጋ ያለው

(iv) በኤሌክትሪካዊ መሳሪያ የሚቀመጥ ዋጋ ነው፡፡

ኤሌክትሪካዊ መሳሪያ: ማለት ኮምፒውተርን ፣ ታብሌትን፣ ፖይንት ኦፍ ሴልን ፣አውቶሜትድ ቴለር ማሽንን፣
ቴሌቭዥንን፣ (ሞባይል ኔትወርክን እና ወይም ኢንተርኔትን ጨምሮ) ሞባይል ስልክን፣ ቺፕን፣ ቅድመ ክፍያ ካርድን፣
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

ክሬዲት ካርድን ፣ ዴቢት ካርድን ፣ የታሸገ ዋጋ የያዘ ምርትን/መሳሪያን እና ሌሎችም ኤሌክትሪካዊ ገንዘብ

የሚከናወንባቸው እና ተዛማጅ የሆኑ ነዋይ ነክ ምርቶች እና አገልግሎቶችን ያካትታል፡፡

ቅርንጫፍ: ማለት በዋና ወኪል እና ወይም በወኪሎቹ ወይም በኢትዮ ቴሌኮም የመሸጫ ቦታ የሚቋቋም የቴሌብር
መስሪያ ቦታ ነው፡፡

ሠው: ማለት ተፈጥሮአዊ ወይም ህጋዊ ሠው ማለት ነው፡፡

ገንዘብ ማሸሽን የሚከላከሉ ደንቦችና መመሪያዎች፡-ማለት በወንጀል ስራ አማካኝነት ገቢ የመፍጠር ሁኔታን


ለማቆም የተቀረፁ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሚመነጩ የመመሪያዎች፣የህጎች ወይም የደምቦች ስብስብ ነው፡፡

ካሽ ፍሎት፡ ማለት አስፈላጊ ለሆነው የውክልና አገልግሎት ለመስጫ በወኪሉ የሚያዝ ኤሌክትሪካዊ ገንዘብ

ማለት ነው፡፡

የቴሌብር ደንበኛ: ማለት የቴሌብር ሂሳብ ያለው ወይም ቴሌብር አገልግሎት የሚጠቀም ሠው ነው፡፡

ደንበኛህን እወቅ(ደእ)፡-ማለት መመሪያዎች እና አሰራሮችን ጨምሮ የመዋዕለ ነዋይ ተቋም ወይም የክፍያ ማዘዣ

አመንጭ ሊፈጽማቸው የሚገቡ ተጠቃሚን እና ከገንዘብ ነክ እንቅስቃሴዎች በስተጀርባ ያለውን ጉጉት የመለየት

የብርቱ ጥንቃቄ እርምጃ ስብስቦች ናቸው፡፡

የግብይት ደብተር ፡-ማለት ወኪሉ በመደብሩ ያከናወናቸው የግብይቶች፣ የፅሁፍ ሪከርዶች ወይም የተሳካ ግብይት

ሲፈፀም በእያንዳንዱ ደንበኛ መፈረም ያለባቸው ሰነዶች ናቸው፡፡


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

አንቀፅ 1
ምደባ
1.1 ዋና ወኪሉ አሁን ላይ ወኪልን ለመሾም(ለመመደብ) የተስማማ ሲሆን ስልጣን የተሰጠው የቴሌብር

አንቀሳቃሽም በዚህ ስምምነት ለተጠቀሰው ወቅት ግብይቶችን ለማከናውን ወኪል ሆኖ

መመደቡን አሁን ላይ ወዶ ተቀብሏል፡፡

1.2 ወኪሉ በብሄራዊ ባንክ የሚሰራባቸው ገንዘብ ማሸሽን የመከላከል እና የመግታት(ገማመመ)የሆኑ

ግዴታዎችን ጨምሮ በየጊዜው በሃገሪቱ ከሚኖሩ የሚሰራባቸው ህጎችን፣ደንቦችን ፣አዎጆችን እና ህጋዊ

ግዴታዎችን ሁሉ ያከብራል፡፡

አንቀጽ 2
የወኪሉ መብቶች እና ግዴታዎች
2.1 ወኪሉ ከቴሌብር ጋር የተገናኘ አገልግሎቶችን ማለትም የቴሌብር አካውንት ለደምበኞች የመክፈት፣

ሂሳብ ከመክፈት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሰነዶችን የመቀበል፣ገንዘብ ገቢ እና ወጪ የማድረግ

፣በመክፈያ ቦታ ግብይቶችን የማከናወን ፣ የባላንስ ጥያቄዎቸን እና ሌሎቸ ማናቸውም በየጊዜው

በኢትዮ ቴሌኮም ከሚፈጠሩ ክንውኖች ጋር የተሳሰሩ ተግባራትን ብቻ የሚሠራ ይሆናል፡፡

2.2 ወኪል አዲስ የቴሌብር አገልግሎት ደንበኞችን ለመመዝገብ የተቻለውን ጥረት ሁሉ ያደርጋል፡፡

2.3 ወኪል በተቻለው ሁሉ የምዝገባ ሂደትን እና የቴሌብር ሂሳብ አሰራር መነሻን አስመልክቶ አመልካቾች

አስፈላጊውን ዕውቀት እንዲጨብጡ ይጥራል፡፡

2.4 ወኪሉ በቴሌበር ምዝገባ ወቅት በደንበኞች የተሞሉ የመመዝገቢያ ቅጾችን ያስቀምጣል፡፡ ይጠብቃል፡፡

2.5 ወኪሉ በቴሌብር ሂሳቡ በቂ ባላንስ እንዲሁም ለገቢ እና ወጪ ግብይት የሚሆን በቂ ጥሬ ገንዘብ

ይይዛል፡፡

2.6 ገንዘብ ወጪ ግብይት ሲያከናውን ወኪሉ ማናቸውም የጥሬ ገንዘብ ክፍያዎች የሚፈጸሙት፡

2.6.1 በካሽ ፍሎቱ በቂ ገንዘብ ያለ ከሆነ ብቻ እንደሆነ

2.6.2 ገንዘብ ተከፋዩ/ዯ የሞባይል ስልክ ባለቤት መሆናቸውን ከማረጋገጫ መልዕክቱ የመታወቂያ

ዝርዝር ጋር አመሳክሮ/ራ ሲያምን /ስታምን ብቻ ነው፡፡


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

2.6.3 ግብይት በተከናወነበት መደብር ግብይቱን ለማከናወን የቴሌብር ፍሎቱ በቂ ባልሆነ ጊዜ ወኪሉ

ግብይቱን ለመፈጸም ፈቃደኛ መሆን የለበትም፡፡ በመሆኑም በወለሉ የሚገኘውን ዋና ወኪል

ወይም ኢትዮ ቴሌኮምን መገናኘት የኖርበታል/ባታል፡፡

2.6.4 ወኪል የተጠቃሚ ግብይቶችን የሚፈጽመው አስቀድመው በተፈጸሙ ወይም በግብይቱ ወቅት

በተመቻቹ የቴሌብር ሂሳቦች ብቻ ነው፡፡

2.7 በዋና ወኪል ለወኪል የተሰጡ የኢትዮ ቴሌኮም መሳሪያዎች ሁሉ የኢትዮ ቴሌኮም ንብረቶች እንደሆኑ

ይቀጥላሉ ይህ ውል ሲያበቃም ተመላሽ የደረጋሉ፡፡

2.8 ወኪሉ በዚህ ስምምነት የተሰጠውን መብት ለሌሎች አሳልፎ የመስጠት አንዳችም መብት የለውም፡፡

2.9 ያለ 30 ቀናት ለዋና ወኪል የተጻፈ የቅድሚያ ማሳወቂያ ወኪል የሥራ ቦታውን አይቀይርም ወይም

አያዛውርም እንዲሁም የውክልና ሥራውን አይዘጋም፡፡

2.10 ወኪሉ በየጊዜው ዋና ወኪሉ የሚሰጠውን ቴሌብርን የተመለከቱ ትዕዛዞችን እና ወይም መመሪያዎችን

ይፈጽማል፡፡

2.11 ወኪሉ ኢትዮ ቴሌኮም ያስቀመጣቸውን የግዛት ወሰኖች ያከብራል፡፡

2.12 ግዴታውን በውጤታማ እና በብቁ ሁኔታ ለመፈጸም ወኪሉ በዚህ ውል አባሪ 3 የተደነገገውን

መስፈርት ያሟላል፡፡ የጠብቃል፡፡

2.13 የደንበኞችን ቅሬታ ለመቀበያ ወኪሉ የብቻው የሆነ ደንበኛ ማስተናገጃ ቀጥታ የስልክ መስመር (toll

free 894) ሊኖረው ይገባል፡፡

2.14 ወኪል ተገቢ እና ትክክለኛ የደንበኛ አያያዝ ሊያሰፍን ይገባል፡፡

2.15 ወኪሉ ሁሉም የደንበኞች ቅሬታዎች በወኪል ደረጃ እና በወቅቱ መፍትሄ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል፡፡

2.16 ወኪሉ የቴሌብር አገልግሎት መስጠት ያለበት በአንድ ጊዜ በአንድ ዋና ወኪል ስር ብቻ ሆኖ ነው፡፡ .

2.17 ያለ አጥጋቢ ምክንያት እና ከቀድሞ ዋና ወኪል መልቀቂያ ሳይዝ ወደሌላ ዋና ወኪል ላለመሄድ

በተቻለው ሁሉ ይጸናል፡፡

2.18 ወኪሉ የሚከተሉትን መረጃዎች ንጹህ እና ግልጥ በሆነ የተቋሙ ቦታ ለደንበኞቹ እይታ ያስቀምጣል፡፡

2.18.1 የውክልና ስርተፍኬቱን

2.18.2 ወኪሉ የሚያቀርባቸው የውክልና አገልግሎት ዝርዝሮችን

2.18.3 የኢትዮ ቴሌኮም ሥም እና ሎጎውን


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

2.18.4 የኤሌክትሪክ ሲስተም የማይሰራ ከሆነ ግብይት የማይከናወን መሆኑን የሚገልጽ ጽሁፍ

2.18.5 ለያንዳንዱ አገልግሎት በደንበኞች ለገንዘብ ተቋሙ የሚከፈሉ ክፍያዎችን ዝርዝር

ማሳያ

2.18.6 ወኪሉ የሥራውን ዘገባ የሚያቀርብበት የቴሌኮም፣ የዋና ወኪሉ ቅርፍጫፍ ወይም ንዑስ

ቅርንጫፍ ሥም፣ቴሌፎን እና የሥራ ቦታ

2.19 የውክልና ሥራ አገልግሎቱን በተመለከተ ወኪሉ ውስጣዊ አሰራሩን ፣ ሰነዶቹን ፣ዘገባዎቹን ፣መዝገቦቹን

ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ሙሉ እና ወቅታዊ ፍተሻ ፈቃደኝነቱን ያሳያል አስፈላጊ እንደሆነ ያመነበትን

ስልጣን ይቀዳጃል፡፡

2.20 ወኪሉ የሚቀጥራቸው ሰራተኞች የኢትዮ ቴሌኮም ወይም የዋና ወኪሉ ሰራተኞችእነደሆኑ

አንደማይቆጠር ይገነዘባል፡፡ በመሆኑም የነዚህ ሠራተኞች መብቶቸ እና ግዴታዎች በኢትዮ ቴሌኮም፣

በዋና ወኪል እና በወኪል መካከል ስምምነት የሚደረስበት የሆናል፡፡

2.21 ወኪሉ ከቴሌብር የተገናኘ ሥራውን ቢየንስ በተለመደው የሥራ ሰዓት ማለትም ከጥዋቱ 2 ሰዓት እስከ

ቀኑ 11፡30 ሰዓት የሚያከናውን ይሆናል

አንቀጽ 3
የሂሳብ ዓይነቶች እና ጣሪያዎች

3.1 ወኪሉ የራሱ የሆነ እና ከተጠቃሚዎች ግብይት ጋር በተገናኘ የገንዘበ መጠን ገደብ የማያደርግ

ኤሌክትሮኒክ አካውነት ተግባራዊ እንደሚያደርግ ይፋ የደርጋል፡፡

3.2 ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቸን ሂሳብ ደረጃ መሠረት በማድረግ ከፍተኛውን የአካውንት ባላንስ፣ የዕለቱን

ጠቅላላ የግብይት ጣሪያ፣ እና በደንበኞች የተከናወነ ጠቅላላ ወርሃዊ የግብይት ጣሪያ ይወስናል፡፡.

በመሆኑም፤

3.2.1 ደረጃ 1 ሂሳቦች የ 5᎖000(አምስት ሺህ) የኢትዮጵያ ብር ከፍተኛ ባላንስ ፤የ1᎖000 (አንድ ሺህ ብር)

የየዕለት ጠቅላላ የግብይት ጣሪያ፣ እና የ10᎖000(አስር ሺህ ብር) ጠቅላላ ወርሃዊ የግብይት ጣሪያ

የሚኖራቸው ይሆናል፡፡
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

3.2.2 ደረጃ 2 ሂሳቦች የ 20᎖000(ሓያ ሺህ) የኢትዮጵያ ብር ከፍተኛ ባላንስ ፤የ5᎖000 (አምስት ሺህ ብር)

የየዕለት ጠቅላላ የግብይት ጣሪያ፣ እና የ40᎖000(አርባ ሺህ ብር)ጠቅላላ ወርሃዊ የግብይት ጣሪያ

የሚኖራቸው ይሆናል፡፡

3.2.3 ደረጃ 3 ሂሳቦች የ 30᎖000(ሠላሳ ሺህ ) የኢትዮጵያ ብር ከፍተኛ ባላንስ ፤የ8᎖000 (ስምንት ሺህ ብር)

የየዕለት ጠቅላላ የግብይት ጣሪያ፣ እና የ60᎖000(ስልሳ ሺህ ብር)ጠቅላላ ወርሃዊ የግብይት ጣሪያ

የሚኖራቸው ይሆናል፡፡

አንቀጽ 4
የዋና ወኪሉ መብት እና ግዴታዎች

ዋና ወኪሉ:
4.1 ለቴሌብር አገልግሎት አቅርቦት ታሳቢ ወኪሎችን የመለምላል፡፡

4.2 በአባሪ 3 እንደተዘረዘረው በኢትዮ ቴሌኮም በተቀመጠው መመዘኛ መሠረት እጩ ወኪሎቸን

ይመርጣል፡፡ ዝርዝሩንም ለማመሳከሪያ እና ለማረጋገጫ እንዲሆን ለኢትዮ ቴሌኮም ይልካል፡፡

4.3 በስሩ ለሚገኙ የቴሌብር ወኪሎች ተገቢ ስልጠና እና ድጋፍ የሰጣል፡፡

4.4 በተመለመሉ የወኪል መቀመጫዎች /መደብሮች ጥሬ ገንዘብ እና ኤሌክትሮኒክ መኒ (ፍሎት አስተዳደር)

መኖሩን፣ መከናወኑን ያረጋግጣል፡፡

4.5 በወለላቸው ቆይታን ለማረጋገጥ ከወኪሎች ጋር ግንኙነትን ያዳብራል ያጠነክራል፡፡

4.6 በወለላቸው የሚገኙ ወኪሎችን ለመቆጣጠር፣ እና ለማስተባበር የሚያስችል ብልሀት ያበጃል፡፡

4.7 የቴሌብር አገልግሎት ሥራ ትውውቅ እና የወኪል መደብሮች መስህብ በቴሌኮም የመስህብ መመሪያ

መፈጸሙን ያረጋግጣል፡፡

4.8 ይህንን ውል ተግባራዊ ከማያደርግ ወይም ሌላ ማናቸውም በኢትዮ ቴሌኮም እና በብሄራዊ ባንክ

የተቀመጡ ሁኔታዎችን ከማይፈጽም ወኪል ጋር ግንኑነት ያቋርጣል፡፡

4.9 በኢትዮ የሚሰራጩ የምርት እና የሥራ መመሪያዎች እንዲሁም ሰርቶ ማሳያዎች በወኪሎች በትክክል

መተግበራቸውን ያረጋግጣል፡፡

4.10 የራስን ደንበኛ ማንነት ማወቅ የተመለከተውን(ደዕ)መስፈርት ጨምሮ የደንበኛ አገልግሎት፣ ገንዘብ

ማሸሽ የመከላከል(ገማመ) እና ሽብር መደገፍን የመግታት (ሽመመ)፣ የደንበኞች መረጃን ሚስጥራዊነት፣


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

የገንዘብ ደህንነትን፣ መዝገብ ኣያያዝ እና የመዋዕለ ነዋይ ትምህርት በተመለከተ ለወኪሎች በቂ እውቀት

ያስጨብጣል፡፡

4.11 ከኢትዮ ቴሌኮም ከሚያገኘው የማስታወቂያ ቁሳቁሶች ለቴሌብር ማስተዋወቂያ እና ማሻሻጫ በበቂ

መጠን ይሰጣል፡፡

4.12 በኢትዮ ቴሌኮም በተቀመጠው መስፈርት እና ጊዜ መሰረት የወኪሎቹን ተጨባጭ የክንውን ግምገማ

በተከታታይ ያደርጋል፡፡

4.13 ወኪሎች የአፈጻጸም ዕቅድ እያሳኩ ፣ ደንበኛ በተገቢ እየያዙ እና ጥሰቶችን እያስወገዱ መሆናቸውን

ያረጋግጣል፡፡

4.14 በስሩ በሚገኙ ወኪሎች መካከል ተቀባይነት የሌለው አድሎ ማስወገድ፡፡

4.15 ቴሌብርን በማስተዋወቅ እና አገልግሎቱን በመስጠት የኢትዮ ቴሌኮምን መልካም ስም እና በጎ ገጽታ

ማስጠበቅ እና ማትረፍ፡፡

አንቀጽ 5
ደንበኛን ለይቶ የማወቅ መመሪያ

5.1 ወኪሉ በምዝገባ ወቅት ተገቢ የትኩረት መመዘኛዎች መሟላታቸውን እና የቴሌብር ደንበኞች ደንበኛህን

እወቅ (ደዕ) መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ በኢትዮ ቴሌኮም የተቀመረ ደንበኛን የማወቅ መረጃ

የደንበኞች ሂሳቦች ደረጃን ተገን በማድረግ ማዘጋጀት/መውሰድ እንደሚቻልም ወኪሉ ያረጋግጣል፡፡

5.1.1 ለደረጃ 1ሂሳቦች ስም፣ የልደት ቀን፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ የደንበኛው የቅርብ

ፎተግራፍ ከመቅረቡ በተጨማሪ አስቀድሞ የኢትዮ ቴሌብር ሂሳብ ባለው ሰው የሚስተዋወቅ

ይሆናል፡፡.

5.1.2 ለደረጃ 2ሂሳቦች ስም፣ የልደት ቀን፣ የመኖሪያ አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ የደንበኛው የቅርብ

ፎተግራፍ እና የደንበኛው የመታወቂያ ካርድ ከመቅረቡ በተጨማሪ በሲስተም ሊታቀፍ

ይችላል፡፡.

5.1.3 ለደረጃ 3ሂሳቦች ስም፣ የልደት ቀን፣ የመኖሪያ/ የስራ አድራሻ፣ የስልክ ቁጥር፣ የሂሳብ ባለቤቱ

ፎተግራፍ እና የደንበኛው የመታወቂያ ካርድ ከመቅረቡ በተጨማሪ ለግለስብ /ለተቋም

አመቺ ሆኖ እነደመገኘቱ በሲስተም ሊታቀፍ ይችላል፡፡.


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

5.2 በምዝገባ ሂደት ወቅት ወኪል የደንበኛን መታወቂያ ስካን አድርጎ ወደ ቴሌብር ሲስተሙ ይጭናል፡፡

5.3 ወኪሉ የሚከተሉትን የታደሱ የግል ለቴሌብር የሚሆኑ የደበምኝነት መታወቂያዎችን የመቀበል

መብት አለው፡፡

6.3.1የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ

5.3.2 የታደሰ ፓስፖርት

5.3.3 የታደሰ የታክስ ከፋይነት መታወቂያ

5.3.4 የታደሰ የመንጃ ፍቃድ

5.3.5 የታደሰ የተማሪ መታወቂያ

5.3.6 የታደሰ የሥራ መታወቂያ

5.4 ወኪሎች በቀረበላቸው መታወቂያ መረጃ ካልረኩ ግብይቱን ላለመፈጸም ወይም ደንበኝነቱን

ላለመቀበል ይችላሉ፡፡

5.5 ወኪሉ መታወቂያ ዋና ቅጅ እንደሆነ፣ የሚነበብ መሆኑን፣ ጠቅላላ መረጃ የሚሰጥ እና የደንበኞች
መታወቂያ ጊዜው ያላበቃ መሆኑንም ያረጋግጣል፡፡

አንቀጽ 6
ክልከላዎች

ወኪል እነዚህን ክልከላዎች ማድረግ የለበትም:

6.1 ለራሱ ከተሰጠ መልክዓ ምድር ከባቢ ውጪ የውክልና ንግድ አገልግሎት መስጠት

6.2 የሲስተም ወይም የኔትወርክ መቋረጥ ባጋጠመ ጊዜ አገልግሎት መስጠት

6.3 ለተጠቃሚዎች የዓየር (ኤሌክትሮኒክ ) አድቫይስ አለመስጠት

6.4 የዓየር ላይ ደረሰኝ ወይምአድቫይስ(ኤሌክትሮኒክ ) መስጠት ሳይቻል ግብይት መከወን

6.5 ማናቸውም አገልግሎት ነክ ክፍያዎችን ከደንበኞች በቀጥታ የመቀበል(ማስከፈል)፡፡

6.6 በሌላ ወኪሉ መከተል ባለበት የተጻፈ ህግ ከተፈቀደው በስተቀር መደበኛ ሂሳቦች የመክፈት፣ ብድር

የመስጠት፣ ሂሳብ ለመክፈት ወይም ብድር ወይም ሌላ አቅርቦት ለመስጠት ዓላማ የሚያግዙ

ማናቸውንም የምዘና ድርጊት መፈጸም፡፡

6.7 በቼክ ገቢ የማድረግ እና ቼክን በጥሬ ገንዘብ የመቀየር፡፡

6.8 በውጪ ምንዛሪ መገበያየት፡፡


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

6.9 በኢትዮ ቴሌኮም ከተሰጡት የተለየ ሌሎች የተለያዩ ግዴታዎች እና ሁኔታዎችን መጫን፡፡

6.10 ከውክልና ውል በተጻራሪ ወይም ልክ በላይ መተግበር፡፡

6.11 በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የተከለከሉ ሌሎች ተግባራትን መፈጸም፡፡

6.12 የበለጠ ኮሚሽን ለማግኘት ገቢዎችን መከፋፈል፡፡

6.13 ለደንበኞች ከሚገባቸው ያነሰ ገንዘብ መስጠት፡፡

6.14 የደንበኛን ጥቃቅን ቀሪ ሂሳቦች ያለስምምነታቸው ወጪ ማድረግ፡፡

6.15 የማይገባ ኮሚሽን ለማግኘት የሀሰት ምዝገባዎችን መፈጸም፡፡

6.16 በደንብ ያልተሞሉና ያተፈረሙ ሠነዶችን መመዝገብ እና ለምዝገባ የደንበኞችን መታወቂያ

አለመጠየቅ፡፡

6.17 የደንበኛ መረጃ በስህተት ማስገባት

6.18 ደንበኛን የተገኘውን ክፍያ ማስከፈል

6.19 የደንበኛን ገንዘብ ወደግል ሂሳብ ማዛወር

6.20 የተደጋገመ የደንበኛ ምዝገባ ማድረግ

6.21 ሲስተም ውስጥ ያለ የደንበኛ መረጃን ማየት

አንቀጽ 7
ክፍያዎች እና ድርሻዎች/ኮሚሽኖች

7.1 ወኪሉ አባሪ 2 ላይ በተጠቀሰው የኢትዮ ቴሌኮም የኮሚሽን አወቃቀር እና በዚህ ስምምነት መሰረት

ኮሚሽን/ድርሻ/ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

7.2 ኢትዮ ቴሌኮም ለዋና-ወኪል እና ወኪሎች በየጊዜው የሚከፈለውን ኮሚሽን ብቻውን የመለውጥ ወይም
የማስተካከል መብት ይኖረዋል፡፡ በኢትዮ ቴሌኮም የተደረገውም ለውጥ ለዋና-ወኪሉ ከተገለጸ ዕለት ጀምሮ

የሚፀና ይሆናል ፡፡ ዋና ወኪልም ይህንኑ ወዲያውኑ ለወኪሎች ያሳውቃል

አንቀጽ 8
መዝገብ መያዝ እና ዘገባ መላክ
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

8.1 ወኪሉ ከሚሰጠው የቴሌብር አገልግሎት ጋር በተገናኘ ተገቢ ምዝገባ ያከናውናል፡፡ እንዲሁም

የእያንዳንዱን ደንበኛ ግብይት ዝርዝሮች/ሎግ ቡክ/ ለሚመለከተው ዋና ወኪል ወይም ለኢትዮ ቴሌኮም

ወዲያውኑ መላኩን የረጋግጣል፡፡

8.2 በወኪሉ የተከናወኑ ግብይቶች ሁሉ ይመረመራሉ እንዲሁም ለኢትዮ ቴሌኮም ደህንነት በሚቀጥለው

የሥራ ቀን መጨረሻ በኢትዮ ቴሌኮም መዝገብ ላይ ይሰፍራሉ፡፡

አንቀጽ 9
ፍተሻ እና ምርመራ

9.1 ኢትዮ ቴሌኮም በዋና-ወኪል እና በወኪሎች የስራ ቦታ የመገኘት እና መደብሮቻቸውን ፣ የዚህ ውል

ተግባራዊነት ከሚሸፍናቸው ግብይቶች ጋር የተያያዙ መዝገቦችን እና ተዛማጅ ሠነዶችን በስራ ሰአት

የመፈተሽ መብት አለው፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ከዚህም በተጨማሪ ማናቸውንም ከውሉ ግዴታዎች ጋር

የተገናኘ መረጃ፣ዘገባ፣እና ሰነድ ከዋና ወኪል እና ወኪሎች የመጠየቅና የማግኘት መብት

ይኖረዋል፡፡ውል ተቀባዮች የኢትዮ ቴሌኮም ጥያቄዎችን የመፈፀምና የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡


9.2 ዋና ወኪልም በወኪሎች የሥራ ቦታ በሥራ ሰዓት የመገኘት እና ሰነዳቸውን የመፈተሸ ሆነ የመመርመር

ተመሳሳይ መብት ይኖረዋል፡፡

አንቀጽ 10
መስህብ መፍጠር ፣የማስታወቂያ ቁሳቁሶች እና የአዕምሮ ሀብቶች

10.1 ኢትዮ ቴሌኮም ለዋና ወኪሉ ፤ ዋና ወኪሉ ደግሞ መልሶ ለወኪሎች የመስህብ እና የማስታወቂያ

ቁሳቁሶችን የሚሰጡ ሲሆን ነገር ግን እነዚህ ቁሳቁሶች ሁልጊዜም የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት ናቸው፡፡

ተጠየቀው ወይም ውሉ ሲያበቃ የሚመለሱ የሆናል፡፡

10.2 ወኪሉ እነዚህን የመስህብ እና የማስታወቂያ ቁሳቁሶችን በሁለቱ ወገኖች በተደረሰው ስምምነት

መሰረት የሚተክል ይሆናል፡፡

10.3 ወኪሉ ማናቸውም የተጨበጠ፣ የተሰጋ ወይም የተጠረጠረ ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የንግድ ስሞች እና

የንግድ ምልክትን የማስመሰል ወይም ሌሎች የኢትዮ ቴሌኮም የሆኑ የአዕምሮ ንብረቶች ላልተገባ

ጥቅም የዋሉበትን ሁኔታ ካወቀ ወዲያውኑ ያሳውቃል፡፡


P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

አንቀጽ 11
የአደጋ ስጋት ቅነሳ

11.1 የዋና-ወኪሉ ወይም የሰራተኞቹ ማናቸውም የስራ መሳሪያ በሚጠፋ ወይም በሚሰረቅበት ጊዜ

ኢትዮ ቴሌኮም መሳሪያው ሁነኛ ጥቅም ላይ እንዳይውል /እንዲገታ ለማስቻል እንዲህ ያለው የንብረት

መጥፋት ወይም ስርቆት ውዲያውኑ ለኢትዮ ቴሌኮም ዘገባ መላክ አለበት፡፡

11.2 ዋና ወኪሉ ራሱን ለመከላከል ሲል ከቴሌብር አገልግሎት መሳሪያው ጋር ጥቅም ላይ የሚውሉትን

ሁሉን የግል መለያዎች እና የደህንነት ቁጥሮች በሚስጥር ይይዛል እንዲሁም በማንም እንዳይታወቅ

ያደርጋል፡፡

11.3 ወኪሉ ማናቸውንም የተጠረጠሩ ወይም የተረጋገጡ የማጭበርበር ጉዳዮች፣ ብርቱ የደህንነት

ጥሰቶች፣ ማናቸውም ቀላል ያልሆኑ የአገልግሎት መገታቶች ወይም ሌሎች ዓብይ ጉዳዮች ሲገኝ

ወዲያውኑ ለዋና ወኪሉ የዘግባል፡፡

አንቀጽ 12
ማሻሻያዎች
12.1 የሁለቱን ወገኖቸ ፈቃድ በሚገልጽ በተጻፈ ስምምነት በቀር ማናቸውም የውሉ ድንጋጌዎች

አይሻሻሉም፣ አይቀየሩም ደግሞም/ ወይም አይተዉም፡፡

አንቀጽ 13
አስገዳጅ ሁኔታ
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

13.1 ያስገዳጅ ሁኔታ መኖር እና ያለመኖር አግባብነት ባለው የኢትዮጵያ ህግ ይወሰናል፡፡ የአስገዳጅ ሁኔታ

መኖር ከ3 ወር በላይ ቢቀጥል እያንዳንዱ ተዋዋይ ወገን በቅድሚያ ማሳወቂያ ይህንን ውል የማቋረጥ

መብት ይኖረዋል፡፡

13.2 መፈጸም አለመቻል የተከሰተው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ከሆነ መፈጸም ያልቻለው ወገን ተጠያቂ

አይሆንም፡፡

አንቀጽ 14
ድንበር የመጣስ ቅጣት

14.1 ወኪሎች በወለላቸው የድንበር ጥሰት ወይም ማናቸውም ገበያውን የሚረብሹ ጥፋቶች የፈጸሙ

አንደሆነ ዋናው ወኪል ከማስጠንቀቂያ ማስታወሻ አንስቶ ያለ ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ውል እስከማቆም

የሚደርስ እርምጃ ለመውሰድ መብት አለው፡፡

14.2 የድንበር ጥሰት ፈጻሚው ወኪል ጥሰቱን የፈጸመው/ችው በዋና ወኪሉ ወይም በኢትዮ ቴሌኮም

ግምት በግዴለሽነት ከሆነ ዋና ወኪሉ በራሱ ውሳኔ ይህንን ውል ለማቆም መብት አለው፡፡

አንቀጽ 15
የውል መቋረጥ
15.1 ከተዋዋይ ወገኖች ማናቸውም በዚህ ውል የገባውን ግዴታ ወይም ሁኔታ ቢጥስ ሌላኛው ወገን ለዚህ

ውል የ 30 ቀናት ቅድሚያ የጽሁፍ ማሳወቂያ ውል ለጣሰው ወገን በመስጠት የህንን ውል ለማቋረጥ

መብት አለው ፡፡ ውል የጣሰው ወገን ጥሰቱን በወቅቱ ሙሉ በሙሉ በማረም ሌላኛውን ወገን ካላረካ

በስተቀር፡፡

15.2 ወኪሉ ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ቢከሰት ዋና ወኪል ብቻውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እና ለወኪሉ

ሳየሳውቅ ይህንን ኮንትራት ሊያቋርጥ ይችላል፡፡

15.2.1ወኪሉ ዋነኛ የንግድ ሥራውን ካቆመ፡፡

15.2.2 ማጭበርበር ፣ እምነት ማጉደል ወይም ገንዘብ ነክ ስህተት ባለበት የወንጀል ድርጊት ጥፋተኛ

ሆኖ ከተገኘ፡፡
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

15.2.3 ኪሳራ የገጠመው ሲሆን እና በኢትዮ ቴሌኮም አስተያየት ወኪሉ የደረሰበት ኪሳራ

የገንዘብ አቅም ተደማጭነቱን በቀጣይ 3 ወራት መመለስ እንደማይቻል ከታመነ፡፡

15.2.4 የወኪሉ ውክልና በፍርድ ቤት ወይም በሌላ ሲሻር ወይም ሲሰረዝ ፡፡

15.2.5 ወይም በአዕምሮ ህመም ምክንያት አቅም ቢያጣ፡፡ (ተፈጥሮአዊን ሠው በተመለከተ)

15.2.6 ያለ ኢትዮ ቴሌኮም የተጻፈ የቅድሚያ ስምምነት የሥራ ቦታውን ሲቀይር ወይም ሲዘጋ ፡፡

15.2.7 በዚህ ኮንትራት አንቀጽ 6 የተጠቀሱትን ማናቸውንም ክልከላዎችን ከፈጸመ፡፡

15.2.8 ገንዘብ ማሸሽና ሽብር መደገፍን የመከላከል እና የመግታት አዋጅ ቁጥር 780/2013 እና

የፈቃድ እና የክፍያ ማዘዣሠነዶች ማሰራጫ መመሪያ ቁጥር ONPS/01/2020ን እና ተያያዥ

አዋጅ እና መመሪያዎቸን አለመፈጸም፡፡

15.3 ኢትዮ ቴሌኮም ስልጣኑን ተግባሩን እና ኃላፊነቱን በሚወጣበት አኳዃን በማንኛውም ጊዜ የዚህን

ውል መቆም ሊያዝ/ሊጠይቅ ይችላል፡፡

15.4 የትኛውም ወገን በራሱ አነሳሽነት የ3 ወር የጽሁፍ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ለሌላኛው ወገን

በመስጠት የህንን ኮንትራት ለማቆም ይችላል፡፡

15.5 ኮንትራቱ ሲቋረጥ ፡

15.5.1 ለውክልና ቢዝነስ አገልግሎት ማሳለጫነት ሲያገለግሉ የነበሩ ሎጎዎች እና የማስታወቂያ

ቁሳቁሶች ሁሉ ከቀድሞ ወኪል የሥራ ቦታዎች ይነሳሉ፡፡

15.5.2 ወኪሉ በንዑስ አንቀጽ 15.2 በተሰናከለበት ሁኔታ በውክልና ቢዝነስ አገልግሎት

እንደማይቀጥል ዋና ወኪሉ ያረጋግጣል፡፡

15.5.2 ወኪሉ ከእንግዲህ ራሱን የኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር አገልግሎት ሰጭ እንደሆነ መቁጠር

አይችልም፡፡ እንዲያውም የቴሌብር አገልግሎት መስጠቱን ወዲየውኑ ያቆማል፡፡

15.5.3 ወኪሉ ከዚህ በኋላ መሳሪያውን፣ የንግድ ስሞችን እና የንግድ ምልክቶችን መጠቀም

ያቆማል፡፡

15.6 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ስልጣኑን ተግባሩን እና ኃላፊነቱን በሚወጣበት አኳዃን በማንኛውም ጊዜ

የዚህን ውል መቆም ሊያዝ/ሊጠይቅ ይችላል፡፡

አንቀጽ 16
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

ሚስጠር መጠበቅ

16.1 እንዳንዱ ወገን ከሌላው ወገን የተቀበለውንና በዚህ ስምምነት ክንውን አግባብ የሚያገኘውን

መረጃዎች ሁሉ ሚስጥራዊ አድርጎ እንደሚጠብቅ ግዴታ ገብቷል፡፡

16.2 ወኪሉ ከደንበኞች፣ ከኢትዮ ቴሌኮም ወይም ከሌሎች ምንጮች ከዚህ ውል ድንጋጌ ጋር በተያያዘ

የሚሰበስበው መረጃ እና ዳታ ሁሉ የኢትዮ ቴሌኮም እንደሆነ ተገንዝቧል፡፡

አንቀጽ 17
ውዝግብ አፈታት

17.1 ከዚህ ውል በመነጨ ወይም በተዛመደ የተከሰተ ውዝግብ በተዋዋይ ወገኖች ሰላማዊ ድርድር ይፈታል፡፡

ተዋዋይ ወገኖች ከስምምነት መድረስ ካልቻሉ ሁለቱም ወገኖች ጉዳያቸውን ስልጣኑ ለሚፈቅድለት የፌደራል

ችሎት ለማቅረብ ተስማምተዋል፡፡

አንቀጽ 18
ውሉ የሚጸናበት ጊዜ እና የውል እደሳ

18.1 ይህ ስምምነት በዛሬው ቀን እ.ኤ.አ በ…………...የተፈረመ ሲሆን በኢትዮ ቴሌኮም እና በዋና ወኪ

ል ለተፈረመው የዋና ውክልና የሽፋን ወቅት ሁሉ የጸና ይሆናል፡፡


18.2 ይህ ውል ካልተቋረጠ በስተቀር በኢትዮ ቴሌኮም እና በዋና ወኪሉ የተፈጸመው የዋና ውክልና ውል እንደታደሰ

ወዲያውኑ እንደታደሰ ይቆጠራል፡፡

18.3 በኢትዮ ቴሌኮም እና በዋና ወኪሉ የተፈጸመው የዋና ውክልና ውል በማናቸውም ምክንያት ቢቋረጥ ወኪል

በኢትዮ ቴሌኮም ውሳኔ ያቋረጠውን ዋና ወኪል ተክቶ ከሚገባው ካዲሱ ዋና ወኪል ጋር ውል

ይፈጽማል፡፡ ዋና ወኪሉ አስካልተተካበት ጊዜ ድረስ ኢትዮ ቴሌኮም ለወኪሉ የቴሌብር አገልግሎት


እንዲያከናውን የሚያመቻች ይሆናል፡፡
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

አንቀጽ 19
ማሳሰቢያዎች
19.1 ከዚህ ውል የሚመነጩ ማሳሰቢያዎች ሁሉ በኢሜል፣በፋክስ ወይም በፅሁፍ ደብዳቤ ተዘጋጅተው

ማመልከቻው ላይ በተጠቀሱ አድራሻዎች ይላካሉ፡፡

ስለ ዋና ወኪል የተወኩሉና ስለ ወኪል የተወከሉና

ቀርበው የፈረሙ ቀርበው የፈረሙ

ስም …………... ስም …………………

የስራ ደረጃ መጠሪያ ……………. የስራ ደረጃ መጠሪያ ……………

ፊርማ …………………. ፊርማ ……………...

ቀን ................. ቀን …………………
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

አባሪዎች

አባሪ1
Agent Log Book for Cash In & Cash Out
ወኪል ተቀማጭ እና ወጪ ገንዘብ የሚመዘግብበት መዝገብ

Agent’s Name/ __________________________________ Branch/ ______________________________________


የወኪሉ ሥም፡ ቅርንጫፍ

Agent’s Operator Name/ ________________________ Agent’s Operator ID/ _________________________


የወኪሉ ኦፕሬተር ስም የወኪሉ ኦፕሬተር መለያ ቁ.

Despoited Withdraw
Amt./ተቀማ Amt /ወጪ
S/N Account Holder Name/የአካውንቱ ባለቤት Account Type/ Mobile Number/ ጭ የሆነው የሆነው Date/ Signature/
ተ.ቁ ስም የአካውንቱ አይነት የሞባይል ቁጥር መጠን መጠን ቀን ፊርማ
1
2
3
4
5
6
7
8
9
10
11
12
13
14
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

አባሪ 2/Annex 2

ክፍያዎች እና ኮሚሽኖች/FEES AND COMMISSIONS

የግብይት መጠንን መሠረት ያደረገ የወኪል ጉርሻ/

Transaction Based Agent commission:


የግብይትወሰን/Transaction የወኪልጉርሻ/ Agent Commission
Ranges
በወኪልየተዛወረ/Transfer ኢትዮ
Min. via agent ቢል(የመክፈያ
Max/ከፍተኛ ገቢ/Deposit ወ/ጪWithdrawal
/ዝቅተኛ ቦታ)/Ethio
Bill (OTC)
1 50 1 1 1
51 100 1 2 2 3
101 300 2 3 3
301 500 3 5 5
501 1000 4 6 7
1001 3000 6 8 9
4
3001 5000 8 10 11
5001 8000 10 12 15
አገልግሎት መሠረት ያደረገ የወኪል ጉርሻ/ Service based Agent Commission:
ደንበኛ ምዝገባ ▪ ወኪል ለተሳካ እያንዳንዱ የደረጃ 2 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የደንበኞች ምዝገባ 15 ብር ያገኛል፡፡
Customer An agent shall get 15 Birr for new successful customer registration (Level 2 and
Registration
Above)
▪ ጉርሻው ደንበኛ የመጀመሪያውን ግብይት ሲየደርግ ይለቀቃል፡፡ Commission will be released when

the customer makes first transaction: ማለትም፤ i.e.

✓ ወኪል ማናቸውም መጠን ያለው መነሻ ተቀማጭ ሲሰበስብ/ while Agent collects Initial
Deposit of any amount.
✓ ወኪል የዓየር ሰዓትመልሶ የመሙላት፣ ከፍያ መጠየቂያ የመክፈል፣ P2P ማዛወር እና የመሳሰሉትን

ግብይቶች እያንዳንዱን ደንበኛ በምዝገባ ወቅት በራሱ ማከናወን እንዲቸል ሲያስተምሩ/ while
Agent educate customers to deposit upon registration so that they can do self-
service transactions like airtime recharge, bill payment, P2P transfer, etc.
✓ ወኪል አስቀድሞ በሌላ ወኪል ስር የተመዘገበ ደንበኛን ወይም አስፈላጊውን KYC አሟልቶ ራሱን

ያስመዘገበ ደንበኛን መዝግቦ ካልተገኘ /An agent shall not register a customer registered
under another agent or self-registered fulfilling the required KYC.
P.O. Box 1047 Addis Ababa Ethiopia
www.ethiotelecom.et tel.: +251 (0) 115 505 678
fax: +251 (0) 115 515 777

የዓየር ሰዓት • ወኪል በያንዳንዱ የዓየር ሰዓት ሙሌት 9% ጉርሻ ያገኛል፡፡/Agent will get 9% commission for
መሙላት/Air each Top up
time Top up
(OTC)

/Annuity ▪ ወኪሎች በወለሎቻቸው በራሳቸው ተገልጋይ ከሆኑ ግብይቶች ከተገኘ የገቢ እና የኮሚሽን ድምር
5% የገኛሉ፡፡ /Agents will get 5% of the revenue and commission saved from self-
service transactions made by customers under their hierarchy.

ኣባሪ3 /Annex 3
የቴሌብር ወኪል ለመሆን የሚያስፈልጉ/ telebirr AGENT ENGAGEMENT
REQUIREMENTS

መመዘኛ/Criteria ዝርዝር/Description ከተማ/ ገጠር/


Urban Rural
የታደሰ የንግድ ፈቃድ/Renewed Business
√ √
license
የሚሟላ የታክስ ከፋይነት መለያ/Taxpayer’s
ሠነድ/Documentation Identification Certificate √
(እንዳስፈላጊነቱ/Where applicable)
የባንክ ሂሳብ መረጃ/Bank account Information
√ √
(እንዳስፈላጊነቱ/Where applicable)
ማሕበር የመመስረቻ ማስታወሻ እና
ጽሁፍ/Memorandum & Article of Association √
(እንዳስፈላጊነቱ/Where applicable)
ስማርት ስልክ/Smart Phone ፣ ታብሌትወይምሌላ
መስሪያ መሣሪያ/Work √
ስልክ/ Tablet or , any phone
Tool
የብቻ የሆነ ኢ-ሜይል እና ሞባይል/Dedicated √ √
Email & Mobile
መገኛ ቦታ/Point of Presence √ √
ተለይቶ በታወቀ የግዛት ሽፋን ሊገኝ የሚችል
ቅርንጫፍ(መደብር)(መገ
ኛ ቦታ)/Outlet ቦታ/Accessible Location Within Defined √ √
Territory
መስህብ መትከያ ቦታ/Space for Branding √ √
ጥሬ ገንዘብ ጥሬ ገንዘብ/Cash 5,000 2,000
እናኤሌክትሪካዊ ገንዘብ/
ኤሌክትሪካዊ ገንዘብ/E-Float 5,000 3,000
Cash & e-Float

You might also like