You are on page 1of 20

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ

የቴክኖሎጂ ምርምር ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬት

የፋሽን ዲዛይን እና አልባሳት ቴክኖሎጂን የመስራትና የማሸጋገር


ሂደት መመሪያ

ጥቅምት 2015 ዓ.ም

ርዕስ ገ


1. መግቢያ.................................................................................................................................................3
1.1. መነሻ ሀሳብ.....................................................................................................................................4
1.2. የመመሪያው አስፈላጊነት.................................................................................................................5
1.3. የመመሪያው ጥቅል ዓላማ................................................................................................................5
1.3.1. ዝርዝር ዓላማ.........................................................................................................................5
1.4. የወሰን ደረጃ...................................................................................................................................6
1.5. ትርጓሜ.........................................................................................................................................6
1.6. አጠቃላይ የፋሽን ዲዛይን እና የፋሽን ሾው ፅንሰ ሀሳብ..........................................................................7
1.6.1. ፋሽን ሾው..............................................................................................................................7
1.6.2. ፋሽን ዲዛይን..........................................................................................................................8
1.7. የፋሽን ዲዛይን እና የፋሽን እይታ አመጣጥና አጀማመር........................................................................9
1.8. የፋሽን አልባሳትን የመስራትና የማሸጋገር ምንነት................................................................................9
1.9. የፋሽን አልባሳትን ሰርቶ ለዕይታ የማቅረብ ዓላማ................................................................................9
1.9.1. ዋና አላማ.............................................................................................................................10
1.9.2. ዝርዝር ዓላማዎች.................................................................................................................10
1.10. የአዋጭነት ትንተና ማከናወን......................................................................................................10
1.10.1. ኢኮኖሚክ አዋጭነት..............................................................................................................11
1.10.2. ቴክኒካል አዋጪነት................................................................................................................12
1.10.3. ማህበራዊ አዋጭነት..............................................................................................................12
ክፍል ሁለት.................................................................................................................................................13
2. የፋሽን አልባሳትን ለእይታ ማቅረብና ማሸጋገር..................................................................................13
2.1. የአብዢዎችን አቅምና ክፍተት መለየት............................................................................................14
2.2. አብዢዎችን ማብቃት...................................................................................................................14
2.3. ፋይዳ ዳሰሳ (Impact Assessment).................................................................................................14
ክፍል ሶስት...................................................................................................................................................16
3. የፋሽን ዲዛይን የቴክኖሎጂ ሽግግር አስፈጻሚ አካላት ተግባር እና ኃላፊነት..................................................16
3.1. የቴ/ሙ/ስ/ቴ/ልማት ቢሮ አካላት ተግባር እና ኃላፊነት.....................................................................16
3.2. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ተግባራትና ሃላፊነት........................................................16
3.3. የአሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት...................................................................................................17
አባሪ 1: - የናሙና መፈተሺያ ቼክሊስት............................................................................................................19
ለውድድር የሚቀርቡ የፋሽን ሾው ውጤቶች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነጥቦች..............................................21
የፋሽን ሾው ዝግጅት በሚደረግበትና በሚቀርብበት ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላት........................................22
የፋሽን ሾው ውድድር አደረጃጀት.............................................................................................................22
ማጠቃለያ....................................................................................................................................................22

2
1. መግቢያ

ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት በተከታታይ ያስመዘገበችውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል ልማታዊ

አስተሳሰብን በህብረተሰቡ ውስጥ በማስረፅና አምራች ዜጋን በመፍጠር የሙያ ተነሳሽነትን ማሳደግ

አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

3
ቀጣይነት ባለው መልኩ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ማምጣት የሚቻለው የልማት ፕሮግራሞች መሪ

መስሪያቤቶችን ውጤታማነት እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ሲሆን ለዚህም በኢኮኖሚ

የበለፀጉ ሀገራት ሳይንሳዊ ትንታኔ እና ሰፋፊ ጥናትና ምርምርን በማካሄድ የሰሩትን ምርቶች በተለያየ

መንገድ በማስተዋወቅና በመጠቀም የውጭ ምርትን መተካት (Import substitution) የሚያስችል

ፖሊሲ/ስትራቴጂ ተቀይሶ ትግበራ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በከተማችን ያለውን የስራ አጥነት ችግር

በመቅረፍ ገበያው በሚፈጥራቸው የስራ ዕድሎች የከተማው ነዋሪ ህብረተሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን በአዲስ

አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ በገበያው ፍላጎት መሰረት ስልጠና
በመስጠትና ብቁ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ የሆኑ ሰልጣኞችን በተለያዩ ዘርፎች እያፈለቀ ይገኛል፡፡

በመሆኑም በየአመቱ የሚዘጋጀዉ የቴ/ሙ/ ሳምንት ላይ በኮሌጆች እና ፖሊ/ቴ/ኮሌጆች በሚዘጋጀዉ


የፋሽን ሾዉ ዉድድር በማድረግ በዘርፉ ላይ ያሉ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞችና በኮሌጁ ማህበረሰብ የተሰሩ
ስራዎችን ለእይታ በማቅረብ በኮሌጆች መካከል ጤናማ የውድድር ስሜት በመፍጠር ይከናወናል፡፡ ይህንኑ
ድጋፍ አጠናክሮ ለማስቀጠል ማሰልጠኛ ተቋማት የሰሯቸውን የፈሽን ስራ ውጤቶች እና አልባሳት በየዓመቱ
በሚከበረው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ላይ በማቅረብ ተቋማት እርስ በዕርስ ልምድ የሚለዋወጡበት ከመሆኑም ባሻገር
ክፍቶታቸውን ለይተው በቀጣይ የማስተካከያ ስራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል፡፡ የተመረጡ አልባሳትና ዲዛይኖች

በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ተደራጅቶ በየዘርፎቹ በሚካሄድ ልማት ውስጥ ለተሳተፉ

ዜጎች/አንቀሳቃሾች በማቅረብ በስራ ገበያው በምርት ጥራት፤ በዋጋና በአቅርቦት ተወዳዳሪነታቸውን

እንዲያሳድጉ በማድረግና በማምረት ሂደት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮችን ለመፍታት ድጋፍ በማድረግ ወደ


ማስ ፕሮዳክሽን በመቀየር ከውጭ የሚገባን ምርት ለማስቀረት እንዲቻል ይህ ማስፈፀሚያ ማኑዋል
ተዘጋጅቷል፡፡

1.1. መነሻ ሀሳብ

በኢንዱስትሪ የበለጸጉ ሀገራት ከእድገታቸው ቁልፍ ሚስጥሮች ውስጥ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ
እንዱስትሪውን ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት መጠቀም መቻላቸው መሆኑ ከእድገት ታሪካቸው
መረዳት ይቻላል፡፡

በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሀገራት የሰሯቸውን የፋሽን ዲዛይ ውጤቶችን በጨርቃ ጨርቅና በቆዳ ዘርፍ
ለተሰማሩ የጥቃቅንና አነስተኛ እና በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር
ተወዳዳሪነትና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የውጭ ምርትን መተካት (Import substitution) የሚያስችል
የቴክኖሎጂ አቅም በመገንባት ለቀጣይ ምዕራፍ መሠረት በመጣል የማሻሻል እና አዳዲስ የመፍጠር ሥራን

4
በማጠናከር በተከታታይነት ፈጣን የኢኮኖሚ ዕደገት ማስመዝገብ ይቻላል፡፡ ስለሆነም ይህንን ሀገራዊ
ፖሊሲና ስትራቴጂ ተግባራዊ ማድረግ የሚቻለው ምርጡን የፋሽን ቴክኖሎጂ በመስራት ከውጭ የሚገቡ
አልባሳትን መተካት ከተቻለ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡

1.2. የመመሪያው አስፈላጊነት

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፈ የተለያዩ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ውጤቶችን በመስራት ፋሽን
ሾው የማቅረብ፣ የማላመድ እና የማሸጋገር ስራን ወጥ በማድረግ ከልማት ፕሮግራሞቻችን ፍላጎት
የሚነሳ የመሃበረሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ አልባሳትን ለማቅረብ የሚያስችል ሂደቶችን በመከተል
የሚፈለገውን ምርት ሰርቶ ለሚፈለገው ዘርፍ ለማቅረብና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ያሉብንን ችግሮች
አስወግደን ወጥ በሆነ መልኩ የዘርፉ ስራዎች እንዲሰሩ፤ እንዲወዳደሩ እና የተመረጡት ምርቶች
የማሸጋገር ትግበራ ሂደት እንዲኖር ማስቻል ነው።

1.3. የመመሪያው ጥቅል ዓላማ

ከትኩረት ዘርፎች በመነሳት ምርጥ አልባሳትን እና የቆዳ ውጤቶችን በመስራት በዘላቂነት ተወዳዳሪነትን
የሚያረጋግጥ ውጤታማ የፋሽን ሾው የውድድር ስርዓት እንዲኖር ማስቻል ነው፡፡

1.3.1. ዝርዝር ዓላማ


1. በፋሽን ሾው ዘርፍ አመርቂ ውጤት ማምጣት የሚቻልበትን መንገድ ከማሳለጥ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ፣
ማህበራዊ እና ባህላዊ እሴቶችን የጠበቀ አልባሳትን የማሸጋገር ስርዓት እንዲፈጠር ማስቻል፣
2. ለአልባሳት ሽግግር አብይ ሚና የሚጫወቱትን የሂደቱ አብይ ተግባራትን ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣
3. በኮሌጆቻችን እንዲሁም በጥ/አ/ እና በማኑፋክቸሪነግ ዘርፍ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተረፐራይዞች
ላይ የፋሽን ዲዛይን የማዘጋጀት፤ፓተርን የማውጣት እና በመስፋት አዋጭ የሆኑትን ማሸጋገር ላይ
የተሻለ ግልጽነትን ለመፍጠር፣
4. ፋሽን ሾን ለመስራት እና ለማቅረብ መከተል ያለብን አካሄድና ስልቶችን ለማስጨበጥ፣
5. የዲዛይኑ መነሻ ሃሳብ የመሃበረሰቡን የአለባበስ ፍላጎት ከመለየት ጀምሮ በመስራት እስከ ማሸጋገር
ድረስ ያለውን ሂደት ወጥነት እንዲኖረው ለማስቻል፡፡
6. የሰልጣኞችን ተሳትፎ በመጨመር የክህሎት ክፍተታቸው እንዲያጎለብቱ በማድረግ ብቁ ሆነው
እንዲወጡ ማስቻል

5
1.4. የወሰን ደረጃ
ይህ የፋሽን ሾው ውድድር ማስፈጸሚያ ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ ሙያ ትምህርት
እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና በስሩ ባሉ ኮሌጆች አደረጃጀት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

1.5. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጥ ካልሆነ በስተቀር በዚህ ማንዋል ውስጥ፡-

1. “ፋሽን ሾው’’ ማለት አዲስ የተነደፉ (የተሰሩ) አልባሳት ስብስብ ለተመልካች የሚቀርብበት ሂደት
ማለት ነው፡፡

2. “መነሻ ሃሳብ (inspiration)’’ ማለት አንድን ልብስ አልያም ዲዛይን ከመሰራቱ በፊት የማሰብና
የመነሳሳት ሂደት (መነሻ ነጥብ) ነው፡፡

3. “ዕውቀት” ማለት የልብስ ዲዛይኑን-ፓተርኑን እና የአመራረት ስርዓቱን (ኦፕሬሽናል ማኑዋል) ሙሉ


በሙሉ መገንዘብን እና ቴክኒካል መረጃዎችን በማከል የተገኘውን ምርት ከመስራት አልፎ ለፋሽን
ሾው ማቅረብ እና ማላመድ የሚያስችል ማለት ነው፤

4. “ባለድርሻ አካላት” ማለት የአልባሳቱን መነሻ ሃሳብ ከማምጣት አንስቶ ምርቱ ሙሉ በሙሉ ተሰርቶ
እስኪያልቅ እና የተመረጡትን አልባሳት እስከ ማሸጋገር ድረስ ባለው ሂደት ውስጥ በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ መንገድ ተሳታፊ የሚሆኑ ሰልጣኞች፣ አሰልጣኞች እና አጠቃላይ ባለድርሻ አካላት ማለት
ነው፤

5. “አብዢዎች” በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ


ኢንተርፕራይዞች ሊሸጋገሩ ከተመረጡት አልባሳትና የቆዳ ውጤቶች ላይ ስልጠና በመውሰድ
አልባሳትንና የቆዳ ውጤቶች በብዛትና በጥራት የሚያመርቱ/የሚያባዙ ኢንተርፕራይዞች ማለት ነው፤

6. “ጥራት” ማለት በአጭሩ የደንበኛን ፍላጎት ማሟላት ማለት ነው፡፡ ተጠቃሚው ባወጣው መስፈርት አልያም
በአገር ወይም በዓለም አቀፍ ደረጃ ባወጣው መስፈርት (Standard) መሠረት ምርቱ/አገልግሎቱ የሚፈለገውን
ጥራት (በክብደት፣ በቀለም፣ በርዝመት፣ በገፅታ፣ በጥንካሬ፣ በውጤታማነትና ከጊዜ አንጻር) ፍላጎትን ማሟላት
ማለት ነው፡፡

6
1.6. አጠቃላይ የፋሽን ዲዛይን እና የፋሽን ሾው ፅንሰ ሀሳብ

1.6.1. ፋሽን ሾው

የተለያዩ መዝገበ ቃላት ፋሽን ሾን በተለያዩ አስተሳሰቦች የተረጎሙት ቢሆንም በቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ
መሠረት ፋሽን ሾው ማለት አንድ የፋሽን ዲዛይነር የሰራቸውን የመጪው የአልባሳት እና የተለያዩ
ስራዎቻቸውን ለተመልካች እይታ የሚያቀርቡበት ሂደት/ትዕይንት ነው፡፡
የፋሽን ትርዒቶች የሚዘጋጁት ማህበረሰቡ ከግዜው ጋር ምን ዓይነት አልባሳትን መልበስ እንዳለባቸው
ሐሳቦችን ለማካፈል ነው።

የፋሽን ትርዒቶች አብዛኛውን ጊዜ የሚጎርፉት የፋሽን ጋዜጠኞች፣ ፎቶግራፍ አንሺዎችና ሌሎች ፋሽን
አፍቃሪዎች ናቸው። ብዙ ግለሰቦች በፋሽን ትርዒቶች ላይ አዳዲስ የፋሽን ዲዛይኖችን ለመታደም
ይመጣሉ። የፋሽን ትርዒቶች አብዛኛውን ጊዜ ለሕዝብ ግንዛቤን በመፍጠር እና ትላልቅ የንግድ
ባለቤቶች አዳዲስ የንድፍ ሃሳቦችን የሚያዩበት ቦታ ነው።

1.6.2. ፋሽን ዲዛይን

የፋሽን ዲዛይን/ንድፍን፣ የልብስ አሰራርን እና የተፈጥሮ ውበትን ለልብስ እና ለተጨማሪ መገልገያዎቹ


የመተግበር ጥበብ ነው። የአልባሳት ዲዛይን በባህል፣ በሃይማኖት እና በተለያዩ ተጽዕኖ የተነሳ ከሀገር ሀገር፣
ከቦታ ቦታ እና በጊዜ ሊለያይ ይችላል፡፡ ፋሽን ዲዛይነር ልብሶችን፣ ሱሪዎችን፣ እና ቀሚሶችን እንዲሁም እንደ
ጫማ እና የእጅ ቦርሳ ያሉ አክሰሰሪዎችን ለአምራቾች ብሎም ለመሀበረሰቡ ይፈጥራሉ።

ፋሽን ዲዛይነሮች ጨርቆቻቸውን እና እንደ ቀለበት፣ የእጅ አምባሮች፣ የአንገት ሀብል እና የጆሮ ጌጦች ያሉ
እቃዎችን በመጠቀም ንድፎችን በተለያየ መንገድ ይሰራሉ። ልብስ በገበያ ላይ ለማውጣት በሚያስፈልገው
ጊዜ ዲዛይነሮች በሸማቾች ፍላጎቶች ላይ ለውጦችን አስቀድመው መረዳት ይኖርባቸዋል። ፋሽን ዲዛይነሮች
ለግል ልብሶች መልክን የመፍጠር፣ ቅርፅን፣ ቀለምን፣ ጨርቅን እና ሌሎችንም የመሥራት ኃላፊነት
አለባቸው።

ፋሽን ዲዛይነሮች ውበት ያላቸው ልብሶችን ለመንደፍ ይሞክራሉ፡፡ ልብስ ማን ሊለብስ እንደሚችል እና
የሚለብስበትን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በተለያዩ ቁሳቁሶች፣ ቀለሞች፣ ፓተርን እና ስታይል ውስጥ
ይሰራሉ። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ ለዕለታዊ የሚለበሱ ልብሶች በተለመደው ዘይቤዎች በተገደቡ ክልሎች

7
ውስጥ የሚወድቁ ቢሆኑም ያልተለመዱ ልብሶችን እንደ የምሽት ልብስ ወይም የፓርቲ ልብሶችንና ሌሎችን
ዲዛይን ያደርጋሉ። አንዳንድ ልብሶች በግለሰብ ደረጃ ይዘጋጃሉ ልክ እንደ “haute couture” ይህ የልብስ አይነት
በጣም ውድና ቅንጡ ከመሆኑ የተነሳ አንዳንድ ሃብታም ግለሰቦች የሚለብሱት የልብስ አይነት ነው፡፡ ዛሬ ላይ
አብዛኛው አልባሳት የሚነደፉት ለጅምላ ገበያ ነው፣ በተለይም ተራ እና ዕለታዊ ልብሶች ለመልበስ የሚሰሩ
ሲሆን “ፈጣን ፋሽን” በመባል ይታወቃሉ።

1.7. የፋሽን ዲዛይን እና የፋሽን እይታ አመጣጥና አጀማመር

የፋሽን ንድፍ የጀመረው በ 19 ኛው መቶ ክ/ዘመን እንደሆነ ተደርጎ ይታሰባል ። የፋሽን ኢንዱስትሪ 'የፀሐይ
መጥለቅ ኢንዱስትሪ' ተብሎ ይጠራ ነበር, እና በጣም በበለጸጉ ሀገሮች ውስጥ የወደፊት ተስፋ እንደሌለው
ተደርጎ ይታሰብ ነበር. ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ አስተሳሰብ ጠፍቶ ‘በመሮጫ መንገድ ላይ ፀሐይ
አትጠልቅም’ ሲሉ ሰይመውታል። የቀድሞው ድራፐር በፓሪስ ውስጥ የልብስ ንድፍ (ፋሽን ቤት) ከማቋቋሙ
በፊት የልብስ ንድፍና የፍጥረት ሥራ የሚከናወነው በአብዛኛው ስማቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ሲሆኑ በንጉሣዊ
ቤተ መንግሰቶች ውስጥ የሚለበሱት አልባሳት ከፍተኛውን የፋሽንነት ቦታ ይይዛሉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ
ሁሉም የአልባሳት ርዕሶች እንደ አልባሳት ዲዛይን በምሁራን ቢጠኑም ከ 1858 በኋላ የተፈጠሩ አልባሳት ብቻ
እንደ ፋሽን ዲዛይን ይቆጠራሉ።

ብዙ ንድፍ አውጪ ቤቶች ለልብስ ንድፍ ወይም ቀለም መስጠት የጀመሩት ከዚህ ግዜ ጀምሮ ነበር። የልብስ
ንድፎቹም ለደንበኞች መታየት ጀመረ፤ ይህም በሥራ ክፍሉ ውስጥ ናሙና ልብስ ከማዘጋጀት ይልቅ በጣም
ርካሽ ነበር። ደንበኛው ንድፉን የሚወደው ከሆነ እንዲሰራለት ያዛል፤ በዚህም ምክንያት ልብሱ ለቤቱ ገንዘብ
ያስገኛል ። በመሆኑም ንድፍ አውጪዎች የተጠናቀቁ ልብሶችን በሞዴሎች ላይ ለደንበኞች ከማቅረብ ይልቅ
የልብስ ንድፍ አውጥተው የማዘጋጀት ልማድ ተጀመረ።

1.8. የፋሽን አልባሳትን የመስራትና የማሸጋገር ምንነት


ውጤት ተኮር የትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ የአገራችን የፋሽን ቴክኖሎጂ አቅም ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት

የአለም አቀፍ የፋሽን ስራን መሰረት በማድረግ እና የሃገራችንን በግሉ እና በመንግስት ስር ካሉ ትምህርት

ተቋማት ላይ ተሞክሮ በመቀመር ተፈላጊና ተገቢ የሆኑ የፋሽን ዲዛይኖችን በመለየት አዋጭነታቸው

የተረጋገጡትን በመምረጥ ለማሸጋገር የተነደፈ ሃሳብ ነው፡፡

1.9. የፋሽን አልባሳትን ሰርቶ ለዕይታ የማቅረብ ዓላማ


8
1.9.1. ዋና አላማ

ዋና ዓላማ በማሰልጠኛ ኮሌጆች የተሰሩ የአልባሳት እና የተለያዩ የዲዛይን ውጤቶች ለቴ/ሙ ሳምንት የፋሽን

ሾው ዝግጅት ላይ በማቅረብ ኮሌጆች በዘርፉ የደረሱበትን ደረጃ በማሳየት የሙያው ተፈላጊነትንና

ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ እና ማበረታታት እንዲሁም ለቀጣይ በአሰልጣኙ እና በሰልጣኙ ዘንድ የውድድር

ተነሳሽነት መንፈስ ለመፍጠርና አቅምን ለማሳደግ ነው፡፡

1.9.2. ዝርዝር ዓላማዎች

1. ህብረተሰቡ ስለ አልባሳት ዲዛይንና ስለ ፈሽን ሾው ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ፣


2. አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች በዘርፉ ያለውን ክህሎት የላቀ ደረጃ ላይ በማድረስ ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ
ዕድገት የተሻለ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል፣
3. የውድድሩን ሂደት ግልፀኝነት አሳታፊ በማድረግ በየደረጃው ጤናማ የሆነ የውድድር ስሜት
ለመፍጠር፣
4. ዘርፉን በክህሎት ለማሳደግ በተሻለ ሁኔታ የተንቀሳቀሰ እና የተሻለ ተሞክሮ ያቀረበን ኮሌጅ በየደረጃው ለማበረታታት
5. የአልባሳት እና የተለያዩ ምርቶች ዲዛይኖችን በመስራት ለቴ/ሙ ሳምንት የፋሽን ሾው ዝግጅት ላይ በማቅረብ
በኮሌጆች መካከል ዘርፉን የሚያሳድግ የውድድር መንፈስ ለመፍጠር
6. አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች በአልባሳት እና የተለያዩ ምርቶች ዲዛይን ዙሪያ እውቅና እንዲያገኙና ተነሳሽነታቸው
እንዲጨምር ለማድረግ፣
7. አዋጭ የሆኑ የአልባሳት ዲዛይን ወጥ በሆነ መልኩ በየደረጃው በመለየት ጥራት ያላቸውን
በመለየት ወደ ገበያው ለማስገባትና ዕውቅና ለመስጠት፣

1.10. የአዋጭነት ትንተና ማከናወን

ምርጥ የፋሽን አልባሳት ዲዛይን የምንላቸው ለመስራት የሚመረጡ ነገር ግን አዋጭነታቸው ከታች
በተቀመጡት ግልጽ መስፈርቶች በዝርዝር ተለክተው እና ተለይተው ሲያልፉና ሰፋ ያሉ ችግሮችን የመፍታት
ሚና የሚጫወቱ ናቸው፡፡ እነዚህ የአዋጭነት ትንተና ማከናወኛ መስፈርቶች በሶስት መሰረታዊ ዋና ዋና
ነጥቦች ኢኮኖሚያዊ፣ቴክኒካል እና ማህበራዊ አዋጪነት በማለት ይከፈላሉ፡፡

እያንዳንዱ የአዋጭነት ትንተና መስፈርት ስር ከተዘረዘሩት ነጥቦች አንጻር የፋሽን ቴክኖሎጂ ዲዛይን
አዋጭነት ተንትኖ መረጋገጥ የሚኖርበት ሲሆን ከሁለት በላይ አንድ አይነት ዲዛይን ሲኖርም ይህንኑ መስፈርት
ክብደት በመስጠት መገምገምና መምረጥ የሚያስችል ይሆናል፡፡

9
1.10.1. ኢኮኖሚክ አዋጭነት

የፋሽን ኢንዱስትሪው ለሃገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መፋጠን ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳለው
ይታወቃል። ይህም የሀገራችንን ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጠቅመው በተፈጠረው የሥራ እድልና በሚያስገኘው
የገንዘብ መጠን ነው። በቴክኒክና ሙያ ያለው የፋሽን እንቅስቃሴ መሰራት በነበረበት ያክል የተሰራበት
ባይሆንም ከግዜ ወደግዜ ግን የተሻለ ተስፋ ይታይበታል። አንዳንድ ስራዎች አሁንም መሻሻል ያስፈልጋቸዋል ።
በሌላ አነጋገር በፋሽን ስራዎች ውስጥ የሚለበሱ(የሚመረቱ) ፋሽንና የማይለበሱ ፋሽን ያሉ የአልባሳት ርዕሰ
ጉዳዮችን ማወቅ አስፈላጊ የሆነው ለዚህም ነው።

የቴክኒክና ሙያ የፋሽን ስራዎች ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖ ለመረዳት በንግድ ውስጥ የኋላ ታሪክ ማግኘት
ሳያስፈልግ በዘርፉ አለም የደረሰበትን በመመልከት የማህበረሰቡንና የሃገሪቱን የኢኮኖሚ አቅም ከግምት
በማስገባት ስራዎችን ማስኬዱ ተገቢ ነው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቴክኒክና ሙያ ስር ያለው የፋሽን ውጤቶች በጥቅሉ ሲታዩ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውና
ገበያው ላይ ቢገቡ ለሃገር ኢኮኖሚ እድገት ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ናቸው። ከዚህም ባሻገር ሥራና
ኢኮኖሚ እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚሄዱ ሲሆን የፋሽን ኢንዱስትሪውም ትልቅ ጠቀሜታ አለው። ኢኮኖሚያዊ
አዋጭነታቸው የተረጋገጡት የፋሽን አልባሳትን በቴክኒክና ሙያ በኩል ለኢንተርፕራይዞች ሲሸጋገሩ ሀብት
እንዲያፈሩ ከማስቻልም ባሻገር ተጨማሪ የስራ እድል መፍጠሩ አይቀሬ ነው ከዚህም ጎን ለጎን የሀገሪቱን
የኢኮኖሚ እድገት ወደ ተሻለ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል።

በዋናነት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ነጥቦች፡-

 የተለየው የፋሽን ዲዛይን በዲዛይኑና በአሰራሩ ከበፊቱ በምን እንደሚለይ ማስቀመጥ እና በአነስተኛ ዋጋ
በሀገር ውስጥ መሰራት እና ማላመድ መቻሉን መፈተሽ፣
 የጥሬ እቃ አቅርቦት በአነስተኛ ዋጋ በሀገራችን ለመስራት የሚቻልበትን መንገድ መቃኘት፣
 የተመረጠው የፋሽን ዲዛይን ብዙ የሰው ሃይል አሰማርቶ የስራ እድልን መፍጠር የሚስችል መሆኑን፣
 አገራዊ ሃብትን በላቀ ደረጃ ለመጠቀም የሚያስችል መሆኑን መቃኘት፣
 የምርት ጥራትና ምርታማነትን መጨመሩን ማረጋገጥ፣
 የህብረተሰቡና የደንበኞች የመግዛት አቅምን ያገናዘበ መሆኑን ማረጋገጥ፣

10
1.10.2. ቴክኒካል አዋጪነት
 የተለየውን የፋሽን ዲዛይን መሰራት ስለመቻሉ እያንዳንዱን ክፍሎች በጥልቀት መረዳትና መተንተን
መቻሉን ማረጋገጥ፣
 የተለየው የፋሽን ዲዛይን በዲዛይኑ ከበፊቱ/ከውጭ ከሚገባው በምን እንደሚለይ ማስቀመጥ እና ሀገር
ውስጥ መሰራት እና ማላመድ መቻሉን መፈተሽ
 ቴክኒካዊ የሆኑ ሲስተሞችን በዘርፉ እውቀት እና ክህሎት በተካኑ ሰዎች መገምገም እና የአሰራር
ዘዴያቸውንና ሊያመጡ የሚችሉትን ለውጥ መዳሰስ፤
 ከዚህ ቀደም የገቡ አልባሳትን በመዳሰስ የሚሰራው በአሰራር ዘይቤውና በጥራቱ የተሻለ መሆኑን
ማረጋገጥ።
 የሚመረጠው የፋሽን ዲዛይን ውጤት የሚጨበጥ ወይም ብቁ እምርታን የሚያመጣ ከሆነ እና
በተለይ ዲዛይኑን በአግባቡ የያዘ ቢሆን ተመራጭ ያደርጋዋል።
 የሚመረጠው የፋሽን ዲዛይን የሚያስፈልጉትን ማንኛውንም ጥሬ ዕቃዎች፣ እና አክስሰሪዎች
በበቂና በቀላሉ የሚገኙ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
 የተለየውን የፋሽን ዲዛይን ለማምረት አቅም(እውቀትና ክህሎት)መኖሩን ማረጋገጥ፣

1.10.3. ማህበራዊ አዋጭነት

 የሚመረጠው የፋሽን ዲዛይን የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽል ስለ መሆኑ


 የስራ ዕድል በመፍጠር ላይ ያለው አስተዋፅኦ

 አካባቢያዊ የህብረተሰቡን ባህላዊ እሴትን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ፣


 አካባቢና ህብረተሰቡ ላይ ከሚያመጡት ተፅዕኖ አንፃር ተገቢ የሆነ መረጃ መያዛቸውን በግልፅ መቀመጥ
ይኖርባቸዋል፡፡

11
ክፍል ሁለት

2. የፋሽን አልባሳትን ለእይታ ማቅረብና ማሸጋገር


አንድ የፋሽን ውጤት ተለይቶ ንድፍ ተዘጋጅቶለት ከተሰራና ለፋሽን መድረክ ከቀረበ በኋላ ወደ ማሸጋገር ስራ
ይገባል፡፡ ከዲዛይን አንስቶ አባዝቶ ወደ ገበያ ለማሸጋገር በመጀመሪያ አብዢዎችን የመለየትና እነሱን
የማብቃት ስራ ሊሠራና ከዛም አልፎ ዲዛይኑን ከገበያ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፡፡

2.1. የአብዢዎችን አቅምና ክፍተት መለየት

አንድ የፋሽን ዲዛይን ተሠርቶ ለፋሽን ሾው ቀርቦና ፍተሻውን ካለፈ በኋላ የማሸጋገር ስራ ይሰራል፡፡ ፋሽን
ዲዛይኑን ለማባዛት መጀመሪያ አብዢን መለየት ያስፈልጋል፡፡ አብዢዎችን ስንለይ ልንመለከታቸው ከሚገቡን
ነገሮች መካከል ዋንኛው የአብዢዎቹን አቅም ማወቅ ነው፡፡ የአብዢዎችን አቅም ስንልይ ሰው ሀይል ብዛት
እንዲሁም እውቀትና ክህሎት፣ የማምረቻ ቴክኖሎጂ፣ የገንዘብ አቅምን ከግምት ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
በሀገራችን እንደ ቴክኒክና ሙያ በሽግግር ሂደት ውስጥ የማብዛቱን ስራ ሊሠሩ የሚችሉት የጥቃቅንና አነስተኛ
እና በማኑፋክቸሪንግ (በጨርቃ ጨርቅ፣ በፋሽን ዲዛይን፣በቆዳና በጋርመንት) ዘርፍ አነስተኛና መካከለኛ
ኢንተርፕራዞች ናቸው፡፡ ከኢንተርፕራይዞቹ መካከል የተለየውን የዲዛይን ውጤት ለማብዛት አቅሙ ያላቸውን
መርጦ የማባዛት ስራውን እንዲሰሩ ማድረግ ነው፡፡

12
2.2. አብዢዎችን ማብቃት
በዘርፉ ላይ ያሉትን አብዢዎች ከተለዩ በኋላ ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየትና ክፍተቱን የሚሞላ
ስልጠና አዘጋጅቶ በመስጠት ማብቃት አስፈላጊ ነው፡፡ አብዢዎችን የማብቃት ስራ ሊሠራ የሚችለው
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ሲሆን እነዚህን አብዢዎች በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት
የተደራጁ ነባርና አዲስ ኢንተተርፕራይዞችን በማብቃት እንዲያባዙ ይደረጋል፡፡ የሚሸጋገረውን ዲዛይን
በሚፈለገው ጊዜ ውስጥ ጥራቱንና ብዛቱን ጠብቆ ለማምረት እንዲያስችል የሚያስፈልገውን እውቀትና
ክህሎት የያዘ የሙያ ስብጥር ያላቸው አንቀሳቃሾችን መምረጥና ማብቃት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መልኩ ዲዛይኑ
ከተሸጋገረ በኋላ በአራቱ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት የድጋፍ ማዕቀፎች መሰረት ድጋፉን በመስጠት
ቀጣይነት ባለው መልኩ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በመስራት ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
ይሄም ኢንተርፕራይዙን በስራ ፈጠራ ክህሎት በማብቃት ምርቱን በተለያየ መንገድ በማስተዋወቅ ቀጣይነት
ባለው መልኩ አምርተው እንዲጠቀሙና ቋሚ ደንበኞች እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

2.3. ፋይዳ ዳሰሳ (Impact Assessment)


ፋይዳ ዳሰሳ በፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂው ሽግግር የመጣን ለውጥና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጡን የምናከናውንበት
ስልት ነው፡፡ይኽውም አንድ በኮሌጅ ማህበረሰብ የተሰራ እና አዋጭነቱ የተረጋገጠ የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ በቀጥታ
ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች በማሸጋገር ተባዝቶ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በማቅረብ የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂው
በኢንተርፕራይዙና በማህበረሰቡ ኑሮና ዕድገት ላይ ምርት ጥራት፣ ብዛት፣ ምርታማነት፣ ገበያ ላይ ያመጣውን ለውጥ፣ የውጪ
ምርትን ማስቀረት ማስቻሉና ብሎም ሀገሪቱ ታወጣው የነበረውን የውጭ ምንዛሪ ማስቀረት ማስቻሉን በዳሰሳ ኦዲት
ማረጋገጥ ካልተቻለ በስራው ወደፊት ለመቀጠል አዳጋች ነው፡፡ በየማሰልጠኛ ተቋማቱ ያሉ አሰልጣኞችም ሆኑ የሠልጣኞች
ሕይወት፣ የሥራ ባህሪና እንዲሁም በተቋማትና አብረዋቸው በሚሰሩት ጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት ላይ የፈጠረውም
አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ተጽዕኖ በትክክል ተቀምሮ ሊቀመጥ ይገባል፡፡ ይህም ለወደፊት የአሠራር ሂደት ማስተካከያም ሆነ
ማሻሻያ በሚደረግበት ጊዜ በተጨባጭ እንደ ማስረጃነት ይጠቅማል፡፡ የፋይዳ ዳሰሳው በቴክኖሎጂ ኦዲት ቡድን የሚከናወን
ሲሆን እንደ አጠቃላይ በዚህ የዳሰሳ ኦዲት ግኝት በቀጣይ የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂው ላይ ለሚደረገው ለውጥ እንደ
ግብዓት ያገለግላል፡፡

13
ክፍል ሶስት

3. የፋሽን ዲዛይን የቴክኖሎጂ ሽግግር አስፈጻሚ አካላት ተግባር እና ኃላፊነት


3.1. የቴ/ሙ/ስ/ቴ/ልማት ቢሮ አካላት ተግባር እና ኃላፊነት

የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኖሎጂ ምርምር፣ ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬት


የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡፡

1. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂውን ለመስራት የሚመደቡ ሙያተኞችና ኃላፊዎች ዘርፉ የሚጠይቀውን ብቃት
(በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት) ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
2. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂን ለመስራት የሚደራጀው የስራ ክፍል ግልፅ የአሰራር ስርዓት የተዘረጋለት
መሆኑን ማረጋገጥ፤
3. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂን ለሚሰሩ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች የአፈጻጸም ማንዋልና ሌሎች አስፈላጊ
ሰነዶች እና ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፤
4. ለፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ ስራ ውጤታማነት ትኩረት በመስጠት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
5. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂን መስራት እና ማሸጋገር ሥራዎች ላይ መደገፍ፣ መከታተል፣ መገምገምና
ግብረመልስ መስጠት፣
6. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂን በመስራትና በማሸጋገር ኢንተርፕራይዞች ሃብት እንዲያፈሩ ላደረጉት
አሰልጣኞች እውቅና ይሰጣል፣
7. የተሸጋገሩት ቴክኖሎጂዎች በተጠቃሚዎቸና ህብረተሰቡ ላይ ያመጡትን ለውጦች ከሌሎች አካላት ጋር
በመሆን የፋይዳ ዳሰሳ ያደርጋል፣
8. በኮሌጆች ተሰርተው ለሚሸጋገሩ ቴክኖሎጂዎች ወጥ በሆነ የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ ስራ መለኪያ
መስፈርቶች መሰረት የፋሽን ሾው ፕሮግራም ላይና በማሸጋገር ሂደቱ ላይ የሚፈጠሩ ቅሬታዎችን
ይፈታል፡፡

14
3.2. የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች ተግባራትና ሃላፊነት

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሚከተሉት በፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ ሽግግርና ስራ ሂደት ላይ
የሚከተሉት ተግባራት ያከናውናል፡፡

1. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂውን ለመስራት የሚመደቡ ሙያተኞችና ኃላፊዎች ዘርፉ የሚጠይቀውን ብቃት
(በዕውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት) ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤
2. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂን ለመስራት የሚደራጀው የስራ ክፍል ግልፅ የአሰራር ስርዓት የተዘረጋለት
መሆኑን ማረጋገጥ፤
3. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂን ለሚሰሩ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች የአፈጻጸም ማንዋልና ሌሎች አስፈላጊ
ሰነዶች እና ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፤
4. ለፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ ስራ ውጤታማነት ትኩረት በመስጠት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
5. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂውን ለመስራት የሚያስፈልጉ ወጭዎች ላይ አግባብነታቸውን በማረጋገጥ
አስፈላጊውን በጀት በመመደብና ተፈላጊውን ግብዓት ማሟላት፣
6. ቴክኖሎጂን መስራት እና ማሸጋገር ሥራዎችን መደገፍ፣ መከታተል፣ መገምገምና ግብረመልስ መስጠት፣
7. በአሰልጣኞችና በሰልጣኞች ለመቀዳት የሚቀርቡ የፋሽን ዲዛይኖቹ ተመርጠውና ተለይተው የቀረቡ
መሆናቸውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፣
8. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂን በመስራትና በማሸጋገር ኢንተርፕራይዞች ሃብት እንዲያፈሩ ላደረጉት
አሰልጣኞች እውቅና ይሰጣል፣
9. የተሸጋገሩት የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂዎች በተጠቃሚዎቸና ህብረተሰቡ ላይ ያመጡትን ለውጦች
ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን የፋይዳ ዳሰሳ ያደርጋል፣
10. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ለሚመለከተው አካላት ሪፖርት ያቀርባል፤

3.3. የአሰልጣኞች ተግባርና ኃላፊነት

የቴ/ሙ/ት/ስ/ተቋማት አሰልጣኞች የማሰልጠን ስራዎቻቸው እንደተጠበቁ ሆነው የፋሽን ዲዛይን


ቴክኖሎጂውን ሰርቶ በማቅረብ ሂደት ላይ በጉልህ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ አካሄድ ከፋሽን አልባሳት
ውጤታማነትና ከአቅም መገነባባት አንጻር ክፍተት እየተስተዋለበት ይገኛል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ደረጃ ላይ
የሚገኙ አሰልጣኞች የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ ላይ በጋራ እየተጋገዙ በመስራትና ተፈላጊውን የፋሽን
ዲዛይንና የአልባሳት ጥራት ማምጣት እንዲሁም እውቀትና ክህሎትን በመለዋወጥ አቅማቸውን መገንባት
ይኖርባቸዋል፡፡

15
1. በሥራው ላይ ከሚሳተፉ አካሎች ጋር በመሆን የፋሽን ዲዛይኖች ችግሮቻቸውንና ክፍተታቸውን መለየት፣
2. የተቋሙ የመስሪያ ቦታ/ወርክሾፕ ስራዎችን ለማከናወን ደረጃውን የጠበቀና በቂ ግብዓቶች ያሟላ
መሆኑንና የሌሉትን ሚመለከተው አካል እነዲያሟላ ይጠይቃል
3. የፋሽን ዲዛኖችን ለመስራትና ለማሸጋገር በክህሎት፣ በእውቀትና በአመለካከት ራሱን ማዘጋጀት እና
እንዲሁም ከስራ ክፍሉ ባልደረቦች ጋር በቡድን ለማከናወን ራሱን ማዘጋጀት፤
4. የፋሽን ዲዛኖችን ለመስራት በወጣው የአሰራር ማኑዋል፣ የአፈጻጸም መመሪያና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች
ላይ ተገቢውን ግንዛቤ መያዝ፣
5. የፋሽን ዲዛኖችን የማሸጋገር ስራ ውጤታማ እንዲሆን ትኩረት በመስጠት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
6. ለተመረጠው የፋሽን ቴክኖሎጂ ንድፍ ፓተርን ዲዛይን፣ የአመራረት ሂደት፣ የአሰራር ማኑዋልና
የሚያስፈልጉ ጥሬ እቃዎችን ዝርዝር) የያዘ ሰነድ ማዘጋጀት፣
7. የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂውን ለመስራት የሚያስፈልጉ ወጭዎች አዘጋጅቶ ማቅረብ፤
8. በተዘጋጀው ንድፍ መሠረት ደረጃውን የጠበቀ ናሙና ማዘጋጀትና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
መወያየት፣
9. በተመረጡ ዲዛይኖች ላይ ወደፊት አምርተው ለሚያስተላልፉ አብዢ ኢንተርፕራይዞችን
ስለአሠራሩ/ስለአመራረቱ ስልጠና በመስጠት ማብቃት፣
10. ተሰርቶ ለተሸጋጋገረው የፋሽን አልባስ/ዲዛይን ቴክኖሎጂ ውጤታማነት ትኩረት ሰጥቶ ለጥ/አ እና
በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩት ኢንተርፕራይዞች ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤

አባሪ 1: - የናሙና መፈተሺያ ቼክሊስት

አንድን ኮሌጅ ተወዳዳሪ የሚያደርግ ምርጥ የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ ናሙናው ከተመረተ በኃላ የናሙና
ፍተሻ እንደሚያስፈልግ ከላይ ተገልጸዋል፡፡ ፍተሻው የፋሽን ውጤቱ ሙሉ በሙሉ በጥራት መሰራቱን
ለማረጋገጥ ያገለግላል፡፡ በፍተሻው ወቅት መሟላት ያለባቸው ነገሮች፡-

16
የናሙና ምርት እና ፍተሻ የሚያስፈልገው የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ የምርት ቴክኖሎጂ መሆን ስለሚገባው
ሙሉ በሙሉ መሰራቱን ለማረጋገጥ በነዚህ ነጥቦች መመዘን ያስፈልጋል፡፡

 የዘርፉን/ጥ/አ/ኢ/ተወዳደሪነት የሚያሳድግ የፋሽን ዲዛይን የቴክኖሎጂ ፍላጎት መለየት


 ምርጡን የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ መምረጥ
 የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂውን ሙሉ ዶክመንት ማዘጋጃት
 የናሙና ምርት ማረጋገጫ (fitting test) ፍተሻ ማከናወን

የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ የመስራት ሂደት መለኪያ(FRAMEWORK)

በዚህ የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ የመስራት ሂደት መለኪያ መስፈርት (Framework) ውስጥ አሰፈላጊ የሆኑ
ዝርዝር መለኪያዎች ቀርበዋል፡፡ ነገር ግን በአገልግሎት ዘርፍ ላይ ለሚሰሩ የፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂዎች በዋናነት
የሚያሰፈልገው የአሠራር ሥርዓትን በማቀላጠፍ ወይም በማዘመን የአገልግሎት መስጫ ወይም ማግኛ ጊዜን በማሳጠር
እንዲሁም የአገልግሎት መስጫ ወጪን በመቀነስ ለተገልጋዩ እርካታን መፍጠር ስለሆነ በሰንጠረዥ-1 በተቀመጠው የምርት
ስራ መለኪያ መስፈርት (framework) ዝርዝር መሰረት በመለካትና ሂደቱን በመፈተሽ የሚያሰፈልጉ የጥራት ማረጋገጫ
ደረጃዎችን በማየት የአሰራር ሂደቱን መለካት ይቻላል፡፡
በአጠቃላይ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የፋሽን ሾው ስራ ሂደት ማዕቀፎች/መስፈርቶች በመከተል ሙሉ ወጥነት ያለውና
ጥራቱን የጠበቀ አልባሳት/ምርቶችን ለመስራት ያስችላል፡፡ በፋሽን ሾው ስራ ሂደቱም አስፈላጊ መረጃዎች መያዝ
ይኖርባቸዋል፡፡
መስፈርቶቹን መሰረት በማድረግ ለሚሰሩት አልባሳት ወጥነት ያለው ሙሉ ሰነድ በማዘጋጀትና ስለሚሰሩት አልባሳት
ጥቅም፣ምንነት፣የጥራትና በሀገር ውስጥ ባሉ ባለሙያዎች የመስራት አቅሙንና ሌሎች ጠቃሚና አሰፈላጊ መረጃዎችን
ማሰቀመጥ ያስፈልጋል፡፡

ሰንጠረዥ-1 በፋሽን ዲዛይን ቴክኖሎጂ የመስራት ሂደት ውስጥ (FRAMEWORK) የሚታዩ ነጥቦች

ተ.ቁ መመዘኛ መስፈርት


1 ከማህበራዊ ጠቀሜታ  የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽል ስለ መሆኑ

አንፃር  የስራ ዕድል በመፍጠር ላይ ያለው አስተዋፅኦ

2 ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ  ከውጭ የሚገቡ አልባሳት/ምርት መተካት የሚችል መሆን Being able to

አንፃር/ In terms of replace imported clothing

17
economic benefits  የውጭ ገበያ ዉስጥ መግባት የሚችል አልባሳት/ምርት መሆኑ/export
standerd/Being able to replace imported clothing

 ከውጭ ከሚገባው ተመሳሳይ ምርት በዋጋ ያነሰ መሆኑ


 የደንበኞች/ዜጎችን የመግዛት አቅምን ያገናዘበ መሆኑ
3 ከፋሽን ቴክኖሎጂ አንፃር  አዲስ ፈጠራ አልያም መነሻ ሀሳቡ (inspire) ላይ ፈጠራ (creativity)
የታከለበት ስለመሆኑ
 አሰራር ሰነድ (ፓተርን፣ ዝርዝር ንድፈ ሀሳብ፣ የጥሬ ዕቃ ዝርዝርና ልኬት)
የያዘ መሆኑ
 ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች ተሸጋግሮ ሀብት ማፍራት ማስቻሉን
ማረጋገጫ ሠነድ መቅረቡ
4 የስራ ተነሳሽነት  ጥሩ የስራ ተነሳሽነት በግሩፑ ላይ መታየት

 ስራዎች ላይ አቅም ያላቸውን በመለየት ክፍፍል ስለመደረጉ

5 ተሳታፊ  ሰልጣኝ
 አሰልጣኝ
 የኮሌጅ ማህበረሰብ
6 የቲም ስራ  ስራዎችን ተቀናጅቶና ተናቦ በጋራ የመስራት

7 ጥሬ እቃና የጥሬ እቃዎች  የጨርቁ አይነት ተስማሚ ስለመሆኑ


ዝርዝር  የክር ከለር ከጨርቁ ጋር የሚጣጣም ስለመሆኑ

 አስፈላጊ የአክስሰሪ አይነት ስለመጠቀሱ(Accessory type)

8 የንድፍ ዲዛይን ከልኬት ጋር(  የንድፍ ዲዛይን ከልኬት ጋር በደንምብ ስለመገለፁ


Detail Pattern Design
 ጨርቁን ለመቁረጥ የሚያግዘን መስመር(Grain line)
with dimension)

9 የአገጣጠም/የአሰፋፍ
ጥራት(Joining quality)  የአገጣጠም ጥራት ለእያንዳንዱ ክፍል

 የስፌት ጥራት

18
 በስፌት መካከል ያለው ርቀት በትክክል ስለመሰራቱ (SPI)

 እያንዳንዱ ልኬት ተጠብቆ ስለመሰፋቱ

10 አጨራረስ  ትርፍና የተንዘላዘለሉ ክሮች ስለመቀምቀማቸው (Trimming quality)

 ያለቀው ምርት ስለመተኮሱ (Ironing quality)

ማስታወሻ፡-

ለውድድር የሚቀርቡ የፋሽን ሾው ውጤቶች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነጥቦች

ለውድድር የሚቀርቡ የፋሽን ሾው ውጤቶች የሚከተሉትን ሁኔታዎች ያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡-

1. ለፋሽን ሾው የሚቀርቡ አልባሳት የተሟላ ዶክመንት (ዲዛይን ቴክባክ፣ፓተርን)ሊኖራቸው ይገባል


2. ዲዛይኑ የተነሳበት መነሻ ሃሳብ የማህበረሰቡን የአለባበስ ስርኣት የጠበቀ ሆኖ የተሻለ ፈጠራ
የታከለበት መሆን
3. ከሃይማኖት ጋር በተገናኘ (ግጭት ቀስቃሽ) አልባሳትን አለመጠቀም
4. የሚቀርቡት አልባሳት ከባህል ያላፈነገጡ መሆን (sensitive) የሆኑ የሰውነት ክፍሎችን የማያሳይ
መሆን ይኖርበታ

የፋሽን ሾው ዝግጅት በሚደረግበትና በሚቀርብበት ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላት


1. በኮሌጅ የሚሰለጥኑ ሰልጣኞች፣
2. በኮሌጅ የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች፣
3. በኮሌጅ የሚገኙ አጠቃላይ ማህበረሰብ ብቻ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

የፋሽን ሾው ውድድር አደረጃጀት


የፋሽን ሾው ውድድር ሂደትና አደረጃጀት እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

 በኮሌጅ ደረጃ
 በፖሊ-ቴክኒክ ደረጃ አደረጃጀት ይኖረዋል፡፡

19
ማስታወሻ፡-

የአሸናፎዎች አሸናፊ ውድድር ዙር በሚካሄድበት ግዜ ኮሌጆችን ለማበረታታት ሲባል በሚያገኙት ውጤት ላይ የ


‹01› ነጥብ ጭማሪ ይደረግላቸዋል፡፡

ማጠቃለያ
ይህ መመሪያ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ተግባርን በአዲስ አበባ ደረጃ ወጥነት ባለው ሁኔታ የመፈጸም ክፍተትን

እንደሚሞላ ይታመናል፡፡ ሆኖም ግን በትግበራ ላይ የግልጸኝነትና የአጠቃቀም ችግሮች ሊያጋጥሙ የሚችሉ

በመሆናቸው ውድድሮችን የሚመሩ አካላት የራሳቸውን መፍትሄ እያስቀመጡ ውድድሮቹን ከፍጻሜ ማድረስ

የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ወይንም ለአፈጻጸም ተጨማሪ ማብራሪያዎች

ቢያስፈልጉ ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኖሎጂ

ምርምር ኢኖቬሽንና ሽግግር ዳይሬክቶሬትን ድጋፍ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡

20

You might also like