Professional Documents
Culture Documents
Dhaabbata Leenjii Konkolaachistootaa Gaaddisaa
Dhaabbata Leenjii Konkolaachistootaa Gaaddisaa
የጠጡበት ቦታ ማደር
የሀገራችን የፍጥነት ወሰን ገደብ በተሸከርካሪ አይነት (ክብደት) በመንገድ ሁኔታ የተከፈለ ነው፡፡
በተሸከርካሪ መሀል ሊኖር የሚገባ ርቀት
በሰዓት 40-50km/h የ 3 መኪኖች እርዝማኔ ወይም 20 ሜትር
በሰዓት 50-60km/h የ 4 መኪኖች እርዝማኔ ወይም 25 ሜትር
በሰዓት 70-80km/h የ 5 መኪኖ
ች እርዝማኔ ወይም 30 ሜትር
በሰዓት 90-100km/h የ 6 መኪኖች እርዝማኔ ወይም 36 ሜትር
የሰኮንዶች ህግ
የ 3-ሰከንድ ህግ፡- አንድን ተሸከርካሪ በመካከለኛ ፍጥነት ስንከተል መኖር ያለበት ክፍተት ነው(የመከተያ
ርቀት)
ከፊት ለማየት የሚከልል ነገር ካለ ከ 3 ሰከንድ ወደ 4 ሰከንድ ከፍ አድርግ
የ 4-ሰከንድ ህግና ከዚያ በላይ፡- በአንሸራታች መንገድ ላይ፣ ሞተር ሳይክል የምንከተል ከሆነ፣ ከኋላ ያለ
አሽከርካሪ ሊያልፍህ ሲፈልግ፣ የጠጡና የተምታቱ አሽከርካሪ ሲገጥምህ፣ በትክክል ለማየት የሚያስቸግር ቦታ
ሲሆን ፣ በከፍተኛ ፍጥነት ማሽከርከር የሚቻልባቸው መንገዶ ላይ፣ ከኋላ የሚከተልህ ተሸከርካሪ
ሲያጋጥምህ፣ ተሳቢ ሲኖርህ ወይም ከባድ ጭነት ከጫንክ፣ አውቶቡስ ወይም አደገኛ እቃዎችን የጫነ
ተሸከርካሪ ከፊት ለፊትህ ካለ፡፡
/የትራንስፖርት ህግና ደንቦች/
- በከተማ ክልል ውስጥ ከ 6 ሰዓት በላይ ማቆም ክልክል ነው፡፡
- ከከተማ ክልል ውጭ ከ 48 ሰዓት በላይ ማቆም ክልክል ነው፡፡
- ከባድ ካሚዮን(ከባድ መኪና) ከሆነ በማንኛውም መንገድ ላይ ከ 2 ሰዓት በላይ ማቆም ክልክል ነው፡፡
1. የኤሌትሪክ ክፍሎች
2.1 እሳት የማቀጣጠል ዘዴ
2.2 ሞተር የማስነሳት ዘዴ
2.3 ባትሪ የመሙላት ዘዴ
2.4 የተለያዩ የመብራት ክፍሎች
2.2 ሞተር የማስነሳት ዘዴ
ባትሪ፡- ኬሚካል ሀይል ወደ ኤሌክትሪካል ሀይል የሚለወጥ ሲሆን በውስጡ ሊድፐር ኦክሳይድና
ስፖንጅሊድ የሚባሉ ንጥረ ነገሮችና 65 የባትሪ ውሃን 35 ሰልፈሪክ አሲድን የሚይዝ ክፍል
ነው፡፡የሞተር ማስነሻ ቁልፍ፡- ከባትሪ ወደ ተለያዩ ክፍሎች ኤሌክትሪክ የሚያስተላልፍና
የሚያቋርጥ ነው፡፡
ስታርተር ሞተር/ሞተሪኖ/፡- ከባትሪ የተቀበለውን የኤሌክትሪክ ሀይል ወደ ሜካኒካል ሀይል በመለወጥ
ሞተርን ለማስነሳት የሚያገለግል ክፍል ነው፡፡
2.3 ባትሪ የመሙላት ዘዴ
ጄኔሬተር/ዲናሞ/፡- ሜካኒካል ሀይል ወደ ኤሌክትሪካል ሀይል በመለወጥ ባትሪን ቻርጅ ያደርጋል እንዲሁም ሞተር
በሚሰራበት ወቅት ሀይልን ይሰጠናል፡፡
ሬጉሌተር፡ ጀኔሬተር ከሚፈልገው በላይ የኤሌክሪክ ሀይል አመንጭቶ ወደ ተለያዩ ክፍሎች እንዳያስተላልፍ
የሚቆጣጠር ክፍል ነው፡፡
2.4 የተለያዩ የመብራት ክፍሎች
እርጥብ አየር ማጣሪያ፡- ይህ የአየር ማጣሪያ በውስጡ ከሽቦ የተሰራ ወንፊት የሚመስል ነገር ሲኖረው
አብዛኛውን ጊዜ የሞተር ዘይት የሚጠቀም ነው፡፡
የኤሌክትሪክ መስመሮች አፈታተሸ
በኤሌክትሪክ ክፍሎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ብልሽት ለመከላከል በተሸከርካሪ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና
የመብራት ክፍሎች ላይ ፍተሻ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
የባትሪ ጫፎች፡-በየጊዜው ማፅዳት እና በጣም አለመጥበቃቸውን አለመላላታቸውን በማየት በአግባቡ ንፅህናውን
መጠበቅ እና ማሰር ያስፈልጋል፡፡
የመብራት ክፍሎች፡- መብራቶች ሙሉ ለሙሉ መስራታቸውን ማረጋገጥ፤ የኤሌክትሪክ ገመዶች
አለመላላታቸውን መፈተሸ፡፡
የሞተር ማስነሻ ክፍሎች፡- የሞተር ማስነሻ ክፍሎች ላይ የሚገኙ ኤሌክትሪክ መስመሮች መላጥ
አለመላጣቸውን፤መላላት አለመላላታቸውን፤ ሙቀት ያለው ክፍል አለመጠጋታቸውን መፈተሸ ያስፈልጋል፡፡
ፊውዝ ቦርድ፡-ኤሌክትሪክ ክፍሎች ላይ ሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል በተመጣጣኝ አምፒር መጠን ባላቸወቅ
ፊውዞች እንዲገናኙ ማድረግ ነው፡፡ ፊውዝ ቦርዱ በትክክለኛ ቦታ መቀመጡንና በውስጡ የሚገኙ ፊውዞች
ከቦታቸው አለመልቀቃቸውነብ ፍተሸ ማድረግ፡፡
ባ.መ.ዘ.ው.ን.ነ. /BLOWAF/ ምርመራ
አሽከርካሪው ፍተሸ በሚያደርግበት ወቅት ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ዋና ዋናዎቹ
ባ(B)- ባትሪ
መ(L)- መብራት
ዘ(O)- ዘይት
ው(W)- ውሀ
ን(A)- ንፋስ
ነ(F)- ነዳጅ
የፍሬን ብቃት አፈታተሸ
የፍሬን ንፋስ አለለመጉደሉን
የፍሬን ዘይት አለምጉደሉን
የፍሬን ሸራ አለማለቁን
የተሸከርካሪ መሪ ብቃት አፈታተሸ
በቂ የመሪ ዘይት መኖሩን ማረጋገጥ
ዘይት የሚያፈስ መስመር አለመኖሩን ማረጋገጥ
የመሪ እንቅስቃሴ አለመጠንከከሩን መፈተሸ
የሀይል አስተላላፊ ክፍሎች አፈታተሸ
የፍሪሲዬን ፔዳል እንቅስቃሴን መፈተሸ
ማርስ በቀላሉ የሚገባና የሚወጣ መሆኑን ማየት
በቂ የፍሪሲዩን ዘይት መኖሩን ማየት
ለተሸካሚ ክክፍሎች አፈታተሸ
ባሌስትራ አለመሰበሩ
የመሪ ክፍሎች ጥገና፡-ለመሪ ክፍሎች ጥገና አገልግሎት የሚዉሉ እቃዎች የመሪ ዘይት፤ ችንጋ ፤ ግሪስ ፤ንፁህ
ጨርቅ እንዲሁም የተለያየ መጠን ያላቸው መፍቻዎች ናቸው፡፡
የፍሬን ክፍሎች ጥገና
የፍሬን ክፍሎችን ለመጠገን የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ግብአቶች፡-የፍሬን ዘይት፤ የፍሬን ሸ ራ፤ የተለያዩ
መፍቻዎች ፤ ፒንሳ፤ እስክሩ ድራይቨር፤ መዶሻ ፤ ስፔሲ ሜትር፤ ኦሞና ንፁህ ጨርቅ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የማለስለሻ ክፍል ጥገና፡-በመጀመሪያ ጊዜ ዘይት የሚቀየርበት ቦታ በማዘጋጀት ለስራ የሚያስፈልጉ አልባሳት፤
ቱታ ፤ ጓንት፤ ጫማ ፤የፊልትሮና የዘይት ማፍሰሻ መፍቻዎች ነጭ ጋዝ፤ ንፁህ ጨርቅ የዘይት ማጠራቀሚያ
እቃ እንዲሁም ደረጃውን የጠበቀ የሞተር ዘይትና የዘይት ፊልትሮ በአግባቡ ማዘጋጀት
የሀይል አስተላላፊ ጥገና፡- እነዚህ ክፈሎች በሚጠገንበት ወቅት የፍሪሲሆን ዘይት፤ የጥርስ ዘይት፤የዘይት
መጨመሪያ እና መቀቢያ ፤ግሪስ ንፁህ ጨርቅ የሚያስፈልጉ ሲሆን እነዚህን እቃዎች በአግባቡ እና በንፅህና
ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል፡፡
የማንዋል አይነቶች፤ አጠቃቀም እና አጠያያዝ
የተሸከርካሪ ማነዋሎች በአይነት በሚሰጡት አገልግሎት የተለያዩ ሲሆኑ በአብዛኛው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
አገልግሎት ይሰጣል፡፡
የተሸከርካሪ ክፍሎች ልኬትን ለማወቅ ይረዳሉ
ለተሸከርካሪ ክፍሎች ማድረግ የሚገባን ጥንቃቄ ያስረዳል
የተሸከርካሪ ክፍሎች የሰርቪስ ጊዜ ያሳውቃሉ
ባለንብረቶች ስተሸከርካሪያቸው አይነት ፤ መጠንና ደረጃ እንዲያውቁ
ተገቢ የሆኑ ማንዋሎችን መለየት
የማንዋል አይነት
የአምራች ድርጅት ልኬት ማንዋል፡- የተሸከርካሪውን የተለያዩ ክፍሎችን የሚገልፅ ሲሆን የተሸከርካሪዎችን ምርት
ቁጥር፤ ሞዴል፤ የሞተር ቁጥር፤ የተመረተበት ዓ.ም ፤ የሻንሲ ቁጥር፤ የአክስል ክብደት መጠን፤ ጠቅላላ ነጠላ
ክብደት ወ.ዘ.ተ የሚያብራራ የማናዋል አይነት ነው፡፡
የጥገና ማንዋል፡-ተሸካርካሪው ብልሽት ሲያጋጥመውና እንዴት ተደርጎ መጠገን እንዳለበት የሚገልፅ ማንዋል
ነው፡፡
የመለዋወጫ እቃ ማንዋል፡-የእቃው አይነትና የመለያ ቁጥርና አጠቃላይ የእቃው መግለጫ የሚገኝበት
የማንዋል አይነት ነው፡፡
አደጋ ሊፈጥሩ ጠሚችሉ ሁኔታውችን መቀነስ ፤በቂ እረፈት ማድረግ ፤በተሸከርካሪውስጠ ሙቀት
እንዳይኖር አየር ማቀዥቀዣ መጠቀም ፤የአነዳድ ብቃት ማሻሻል ፤ህግና ስርአትን መከተል፡፡
አደጋ ጋር ተያያዥነት ያለቸው መፍትሄዎች
ለአደጋ መንስኤ ሊሆነኑ የሚችሉ ነገሮችን አስቀድሞ መለየት
የተሸከርካሪ ቲክኒክ ብቃት ማረጋገሀጥ
ንቁ ቀልጣፋ መሆን
የስራ ላይ ደህንነት ጥንቃቄ ስርአቶች
የግል የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች ፤የእጅ ጎንት ፤ካፖትር ፤ጭንቅላት መከላከያ
የጥንቃቄ መሳሪያወች
የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ ሳጥን የእሳት ማጥፊያ መሳሪያዎች ፤ታኮ የመገናና መሳሪያዎች
የጉዞ መረጃዎችን ማሰባሰብ እና እቅድ ማዘጋጀት
አንድ አሽከርካሪ መረጃን በአግባቡ የመጠቀም፤ የመያዝና የማስተላለፍ ችሎታውን በማዳበር ተሸከርካሪውን
ተሳፋሪውንና የጭነቱን ደህንነት በመጠበቅ አንፃር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ መረጃዎችን በመፈለግ
በመያዝና መባስተላለፍ ከፍተኛ ትኩረት ማድረግ ይኖርበታል፡፡
አሽከርካሪዎች መረጃን ለማሰባሰብና ለማስተላለፍ የማስታወሻበድተር፤ ሬዲዩ፤ ሞባይል፤ ቪዲዩ ካሜራ እና
ፎቶግራፍ ካሜራ መሳሰሉትን መጠቀም ይችላሊ፡፡
የጉዞ መድረሻ፡- አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ በፊት የጉዞውን ር 4 ቀትና መዳረሻ ማወቅ ጠቀሜታዎች
ይኖሩታል፡፡እነዚህም የጉዞ እቅድ በትክክል ለማዘጋጀት፤ ተሸከርካሪ ለጉዞ ላማዘጋጀት፤ የቁርስና የምሳ ቦታዎችና
ለማዘጋጀት
የመንገድ ላይ አገልግሎቶች፡- አንድ አሽከርካሪ በጉዞ ወቅት ለራሱ፤ ለተሳፋሪውና ለተሸከርካሪው የሚያስፈልጉ
የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶች ስለሚኖሩ ጉዞውን ሲያቅድ እነዚህን የአገልግሎት ዘርፎች ሊያገኝ በሚችልበት
መልኩ ቢሆን ይመረጣል፡፡ የነዳጅ ማደያዎች፤ ሆቴሎች፤ የስልክ አገልግሎት መስጫ፤ የፖሊስ ስልክ አድራሻ፤
የአውቶቡስ ማቆሚያ ስፍራዎች የመሳሰሉት ናቸው፡፡
የመንገድ ሁኔታ መረጃ፡-በሀገራችን ያሉ የመንገድ አይነቶች እንደ አካባቢው መልክአ ምድርና የአየር ንብረት
ሁኔታ በተለያየ መልክ ሊሰሩ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ጉዞው የሚካሄድበትን መንገድ አደገኛ ቁልቁለትና ዳገት፤
ጠመዝማዛ ፤ ጠባብ ድልድይ፤ መሻለኪያ መሆኑን ለይቶ ማወቅ የተለያዩ የማሽከርከር ስልቶችን እንዲተገብር
ይረዳል፡፡
የመንገድ ደረጃ፡- አንድ አሽከርካሪ ጉዞ ከመጀመሩ ወይም ከማቀዱ በፊት ስለመንገዱ ሁኔታ አስቀድሞ መረጃ
በመሰብሰብና ተገቢውን የጉዞ ዝግጅት በማድረግ ጉዞውን የተሳካ እንዲሆን ማድረግ አለበት፡፡
ከስራ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰነዶች
አሽከርካሪው ስለሚያጓጉዘው የጭነት ሁኔታ የሚገልፅ ስሆን ለምሳሌ፡-ለጭነቱ የተሰጠ የይለፍ /መውጫ/ ፤ፍተሸ
የማያስፈልገው መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ፤ የጭነት አይነት መግለጫየመሳሰሉትን መረጃዎች የሚያካትቱ
ናቸው፡፡
የጉዞ መረጃዎች ማለት የጉዞውን ሁኔታ በአጠቃላይ የሚገልፅ መረጃዎች ሲሆኑ ከሌሎች አካላት የተገኙትንም
መረጃዎች ያካትታል፡፡
በጉዞ መስመር ላይ ስለሚገኙ ማህበረሰቦች እና የጉዞ መስመር ደህንነት ሁኔታ መረዳት
መልካም ግንኑነትን ለመፍጠር ቋንቋ፤ ባህልና የፀጥታ ሁኔታ አሽከርካሪው በጉዞ ላይ ስለሚያጋጥሙት
ማህበረሰቦች ማንነት በሚገባ መገንዘብ እንዲሁም አሽከርካሪው በሚጓዝበት መንገድና በአካባቢው የሚገኘውን
የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ መረጃ በማሰባሰብ ጥንቃቄ የተሞላበት ጉዞ እንዲሆን ጥረት ማድረግ አለበት፡፡
የማሽከርከር ስልት
1. ታኮ ለተሳቢ ማድረግ
2. የኤሌክትሪክ የንፋስ መስመር ማለቀቅ
3. ማገናኛ ፒን ማላቀቅ
4. ተሸከርካሪውን በአነስተኛ ፍጥነት ወዳፊት ማንቀሳቀስ
5. ማገናኛ ፒንወደ ቦታው መመለስ
6. ግማሽ ጭነት የጫነ ተሳቢ የመገልበጥ አደጋ እነዳይደርስበት ቅድሚያ ጭነቱን ማራገፍ፡፡
ለህዝብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች የተዘጋጀ
የህዝብ ማማለላሻ አውቶብስ አሽከርካሪዎች በየእለቱ ብዙ ተሳፋሪዎችን ከቦታ ወደ ቦታ የማጓጓዝ ስራዎችን
ያከናውናል፡፡ይህ የማጓጓዝ አገልግሎት የሚሰጠው የከተማና የሀገር አ ቋራጭ ሲሆን ከከተማ ወደ ሌላ ከተማ፤
ከክልል ወደ ክልል….. ወ.ዘ.ተ ሊሆን ይችላል፡፡
በመሆኑም ማንኛውም የህዘብ ማመላለሻ አውቶብስ ተጠቃሚ ህብረተሰብ በቀጥታ የሚገናኘው ከአውቶብስ
አሽከርካሪ ጋር ነው፡፡ ምንም እንኳን ስራው በተፈጥሮ ተደጋጋሚና አሰልቺ ቢሆንም አሽከርካሪው ሙያዊ ስነ
ምግባር በተሞላበት መንገድ የደንበኛውን ፍላጎት ምቾት ጠብቆ እራሱንም ሆነ ተጋዡን ብሎም ማህበረሰቡን
በአግባቡ ማስተናገድ ይገባል፡፡
1.የመንገደኞች የጉዞ አላማ
መንገደኞች ከቦታ ወደ ቦታ የሚነቀሳቀሱ ለስራ፤ ለማህበራዊ ጉዳዮች ለጉብኝትና ለሰትምህርት አገልግሎት
ሲሆን ጉዞው በቡድን ወይም በግል ሊሆን ይችላል፡፡ የተጠቃሚዎቹ አይነት በባህሪያቸው ወይም በስራ
ፍላጎታቸው የተለያዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የአውቶብስ አሽከርካሪዎች የጉዞና የመንገደኞች አይነት በሚገባ
ማወቅ አለባቸው፡፡
የጉዞ አይነቶች የሚባሉት
ረጅም ጉዞ
መካከለኛ ጉዞ
አጭር ጉዞ
የከተማ ውስጥ ጉዞ
በትልቅ ድርጅት ወስጥ የሚደረግ ጉዞና ሌሎች ናቸው፡፡
2.ለተሳፋሪዎች የሚደረግ ጥንቃቄ
2.1.አሽከርካሪዎች ተሳፋሪን ሲያሳፍሩና ሲያወርዱ ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄ
በጉዞ እቅድ ላይ በወጣው ሰአትና ቦታ ላይ መድረስ፡፡
አሽከርካሪው ተሸከርካሪውን ሙሉ በሙሉ በትክክለኛው አቋቋም ማቆም፡፡
ተሸከርካሪው ከተፈቀደለት የመጫን መጠን ወይም ብዛት በላይ መጫን የለበት፡፡
በወጣው እቅድ መሰረት መንገደኞችን ለማሳፈር በቅድሚያ መናኸሪያ ፌርማታ በማቆሚያ ቦታ ቁጥር
ላይ ተሸከርካሪን ለጉዞ አዘጋጅቶ ማቅም፡፡
አካል ጉዳተኞችን ፤ አረጋዊያንን ፤ ነፋስ ጡሮችንና ህፃናትን የያዙትን ማስቀመጥ ያለበት በፊትና በኋላ
ጎማ መሀል ውስጥ ባሉት ወንበሮች ላይ ቢሆን ይመረጣል፡፡
ተሸከርካሪው እየተንቀሳቀሰ ማሳፈርም ሆነ ማውረድ ክልክል ነው፡፡
መንገደኞች ለማውረድ በተፈቀደ ቦታ ወይም ለአደጋ በማያጋልጥ ቦታ ማውረደወይኖርበታል፡፡
ተሸከርካሪው ሙሉ በሙሉ በማቆምያ ቦታ ቆሞ በር እስኪከፈት ድረስ መንገደኞች ከመቀመጫ
ቦታቸው ላይመነሳት እንደሌለባቸው ማሳወቅ፡፡
ለምሳ ወይም ለመናፈስ መንገደኞች ወርደው ሲመለሱብዛታቸውን መቁጠር ይገባል፡፡ ምክንያቱም የቀረ
መንገደኛ ካለ ለማየት ወይም ለማወቅ ስለሚያስችል፡፡
መንገደኞች ለማሳፈረም ሆነ ወርደው መንገድ ለማቋረጥ በሚፈልጉበት ጊዜ አሽከርካሪው
የመንገድ ግራ እና ቀኝ በመመልከት መንገዱ ነጻ መሆኑን አረጋግጦ ወይም ቅድሚያ እንዲሰጣቸው
በማድረግ መንገዱን እንዲያቋርጡ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
2.2 ተማሪዎችን በማጓጓዝ ወቅት የሚደረግ ጥንቃቄ
ተማሪዎች ከት/ቤት ከመለቀቃቸው በፊት በማቆምያው ስፈራ ተሸከርካሪ ማቀም፡፡
አሽከርካራ ከተሸከርካሪው በሚወርድበት ጊዜ የሞተር ማስነሻ ማጥፊያ ቁልፍ ማንሳት አለበት
አሽከርካሪው በትምህርት ቤት መውጫና መግቢያ በር ላይ በመሆን ተማሪዎች በሚሳፈሩበት ወቅት
የአገባባቸውን ሁኔታ ሂደት መቆጣጠር ማስተካከል ይኖርባቸዋል፡፡
እድሜአቸው ከ 12 አመት በታች ለሆኑ ህጻናት የተለየ እንክብካቤ ማድረግ፡፡
ተሸከርካሪ ከማንቀሳቀስ በፊት የተማሪዎችን የመማሪያ መሳሪያዎችንናየቀሩ ተማሪዎችን ማየትና
መፈተሸ፡፡
የአገልግሎት ክፍያ እንደ ስምምነት በኮንትራት ለአንድ ጊዜ ጉዞ ወይም በመደበኛ ለአንድ ጊዜ ፤ ሳምንታዊ
፤ ወርሀዊ….ወ.ዘ.ተ ሊሆን ይችላል፡፡ አሽከርካሪው አገልግሎት መስጠትና የአግልግሎት ክፍያውን ሲቀበል
ለመንገደኛው ደረሰኝ መስጠት አለበት፡፡
የከተማ አውቶብስ ትኬት አገልግሎት
የአገልግሎት ትኬት መስጠት ያለበት ጉዞ ከመጀመሩ በፊት ክፍያ ከተከናወነ በኋላ ነው፡፡
ትኬት የሚያገለግለው ለአንድ ጊዜ ብቻ ነው፡
አንደ ሰው ትኬቱን ከተጠቀመ በኋላ ወደ ሌላ ሰው ትኬቱ ቢተላለፍ አገልግሎት አይሰጥም፡፡
ሀገር አቋራጭና አስጎብኝ አውቶቢስ ትኬት አገልግሎት
የሀገር አቋራጭና የአስጎብኝ የአገልግሎት ክፍያ ለሚከፍሉ መንገደኞች ለአንድ ጉዞ ወይም ደርሶ መልስ ጉዞ
ሊሆን ይችላል፡፡ በክፍያ ደረሰኝ ላይ የተሸከርካሪው ሰሌዳ ቁጥር የጎን፤ መስመር ፤ የክፍያ ስም ወ.ዘ.ተ
መሟላት ይኖርበታል፡፡
የአገልግሎት ክፍያ ሊያስመስል የሚችሉ ጉዳዩች
መንገደኛው የግል ጉዳይ አጋጥሞት ተሸከርካሪው ከመንቀሳቀሱ በፊት እንዲመልሱለት ወይ አገልግሎት
የማይፈልግ መሆኑን ሲያሳውቅ
ተሸከርካሪው ተበላሽቶ ሲቆምና የጥገና ጊዜ ለረጅም ሰአት የሚፈጅ ከሆነ ወ.ዘ.ተ ናቸው
5.የአውቶቢስ ውስጥ ማስታወቂያ
የህዘብ ማመላለሻ አሽከርካሪዎቸ የሚከተሉትን ማስታወቂያዎች በአውቶቢስ ውስጥ መለጠፍ አለባቸው፤
የተሳፋሪዎን ብዛት፤ የተሳፋሪዎችን መብትና ግዴታ፤ የባለንብረት አድራሻና ስልክ በሚታይ ቦታ ላይ በግልፅ ፅፎ
መለጠፍ አለበት፡፡ እንዲሁም የሀሳብ መስጫ ሳጥን ለተሳፋሪዎች በሚታያቸው የተሸከርካሪ ከፍ ያለ ቦታ ላይ
ማድረደግ አስፈላጊ ነው፡፡