You are on page 1of 26

የተሸከርካሪ ቴክኒክ ብቃት

አፈታተሽ
አንድ ተሸከርካሪ ከ5 መሰረታዊ
ክፍሎች የተዋቀረ ነው፡፡
•1. ሞተር
•2.የተሸከርካሪ የኤሌክትሪክ
ክፍሎች
•3. ሀይል አስፈላላፊ ክፍሎች
•4. ቻሲስ እና
•5. የተሸከርካሪ አካል(ቦዲ)
ፍተሻ ሁለት አይነት ነው፡፡
• ሀ. ውጫዊ ፍተሻ እና
• ለ. ውስጣዊ ፍተሻ ናቸው፡፡
የፍተሻ ዓላማ
•የሞት
•ከባድ የአካል ጉዳት
•የንብረት ውድመት
•በብልሽት ምክኒያት ጉዞው እንዳይስተጎጎል
•አላስፈላጊ ገንዘብን ፣ የጊዜ እና የጉልበት ወጪን ለመቆጠብ
•በቴክኒክ ብልሽት ምክኒያት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ
ለመከላከል
•በአስቸጋሪ ሁኔታ እና ቦታ በብልሽት ምክኒያት ተሽከርካሪው
እንዳይቆም ለመከላከል፡፡
•ውጫዊ ፍተሻ፡- ማለት ከተሽከርካሪው ወርደን
በማየትና በመዳሰስ የምናከናውናቸው ነገሮች
ናቸው፡፡
እነሱም፡- ፍሳሽ አለመኖሩን ማየት
-መብራቶችን
-የዝናብ መጥረጊያ
-የዘይት ዓይነቶችን
-ውሃ
-ነዳጅ
-ጎማ
-ወ.ዘ.ተ.
2. ውስጣዊ ፍተሻ ፡- ማለት ተሸከርካሪው
ውስጥ ገብተን የምናደርገው ፍተሻ ነው፡፡
እነሱም፡- ደሽ ቦርድ
-መሪ
-ፍሬን ፍሪሲወን ነዳጅ መስጫ ፔዳል
-ወዘተ
1. ለሞተር መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
•የሞተር ዘይት በቂ ዘይት መኖሩን ፣ ንፁህ እና
ውፍረቱን
•ራዲያተር ውሃ በቂ መኖሩን
•ሞተር እንደተነሳ ዳጅ እየሰጡ ያለማሞቅ
•ተሸከርካሪው በጉዞ ላይ እያለ የሞተሩና የሙቀት
መጠን በጌጁ ላይ መከታተል፡፡
•ለረጅም ጊዜ ሲሰራ የቆየን ሞተር 3-5 ደቂቃ ሚኒሞ
ማሰራት
•የሞተሩን የሰርቪስ ጊዜ ማኑዋሉ በሚያዘው መሰረት
መጠበቅ
1.1. የሞተር ሃይል አጋዥ ክፍሎች
•1. የነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች
•2. የማቀዝቀዣ ክፍሎች
•3. የማለስለሻ ክፍሎች
•4. የአሳት አቀጣጣይ ክፍሎች
ናቸው፡፡
1. ለቤንዚን እና ለናፍጣ ሞተር ነዳጅ አስተላላፊ ክፍሎች
መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
 የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋን ውስጥ እንደ ሞተሩ አይነት
ትክክለኛውን ነዳጅ መጠቀም
የነዳጅ ጋኑን በራሱ ክዳን መክደን እና በጨርቅና በላስቲክ
በመሳሰሉት አለመክደን፡፡
በማጠራቀሚያ ጋን ውስት ያለውን የነዳጅ መጠን ለማወቅ
በእንጨት ፣በፕላስቲክ ቱቦ በመሳሰሉት ለማየት አለመሞከር
የነዳጁ ጌጅ መስራቱን በትክክል ማወቅ፣
የነዳጅ መተላለፊያ ቱቦዋች ነዳጅ ወደ ውጭ የማይፈሱ
መሆናቸውን ዘወትር ማየት
ሞተር ሰርቪስ በሚደረግለት ጊዜ የነዳጅ ማጣሪያ መቀየር
ወይም ፀድተው እንዲገጠሙ ማድረግ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
2. የማቀዝቀዣ ክፍል መደረግ ያሉበት ጥንቃቄ
•እንደየተሽከርካሪው ሞዴልና ዓይነት በራዲያተር ውስጥ ወይም በኤክስፓንሽን
ታንከር ውስጥ በቂ ውሃ መኖሩን ዘወትር ማየት፡፡
•ራዲያተሩ ወደ ውጭ ውሃ የማያፈስ መሆኑን ዘወትር ማየት፡፡
•የራዲያተርን ክዳን በትክክል መክደን፣ በየተወሰነ ጊዜ በውስጡ ያለው እስፕሪንግ
ያለመላሸቁና ጎሚኒው ያልተበላ መሆኑን መፈተሽ፡፡
•ወሳጅና መላሽ ሆዝ ላይ ያሉ ክለምፖች ጠብቀው መታሰራቸውን ማየትና
ውሃ ወደ ውጭ የማያፈሱ መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡
•ውሃ ፓምፑን ሚያንቀሳቅሰው ቺንጋ; ቤልት/ ያለመላላቱንና ያለ መጥበቁን
አዘውትሮ ማየት፡፡
•ቬንትሌተር ያልተሸፈፈና ያልተሰነጠቀ መሆኑን ዘወትር ማየት፡፡
•በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ ቬንትሌተር ከሆነ ሞተሩን አስነስቶ የሚሰራ
መሆኑን በማየት ማረጋገጥ
•የአየር ማስገቢያ አንገቶች በቆሻሻና በተለያዩ ነገሮች ያልተደፈኑ
መሆናቸውን ማየት፡፡
•ፊንሶች በቆሻሻ (በዘይትና በሌሎች) ነገሮች ያልተደፈኑ መሆናቸውን ማየትና
ማጽዳት
3.ለማለስለሻ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
•ዘወትር ሞተሩን ከማስነሳት በፊት በቂ፣ ንፁህና
ተገቢ ውፍረቱን የጠበቀ ዘይት መኖሩን በዲፕስቲክ
አማካኝነት ማየት
•የሞተር ዘይት ፍሳሽ መኖር ያለመኖሩን በየጊዜው
ማየት፡
•የሞተር ሰርቪስ በተደረገ ጊዜ የሞተር ዘይት
ፊልትሮ /ማጣሪያ/ መለወጥ ወይም አጽድቶ
መግጠሙን ማረጋገጥ፡፡
•ሞተር ሲነሳና በጉዞ የሞተሩን የዘይት ግፊት
ማመልከቻ ጌጅ መከታተል
4. ለእሳት አቀጣጣይ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
•ሞተር ከማስነሳት በፊት የባትሪ ውሃን የማየት ልምድን ማዳበር
•ባትሪ በቦታው ላይ በትክክል፣ በጥንቃቄ ሳይጠብቅና ሳይላላ መታሰሩን
ዘወትር ማየት
•የባትሪ ተርሚናሎች ሰልፌት /ሻጋታ/ እንዳይዙ በተወሰነ ጊዜ
ተርሚናሎቹን በማይጎዳ ነገር ማጽዳት፡፡
•የባትሪ ተርሚናሎችን በምልክት፣ በጽሑፍ፣ በመጠናቸው በመለየት
ባትሪ በተሸከርካሪ ላይ ሲገጠምና ሲፈታ ቅደም ተከተሉን መጠበቅ
ማለትም ባትሪ ሲገጠም መጀመሪያ ፖዘቲቩን ማሰር ሲፈታ ደግሞ
ኔጋቲቩን የማስቀደም ልምድ ማዳበር
•የባትሪ ተርሚናሎችን በራሳቸው መሸፈኛ መሸፈን በጎማ ውስጥ
ላስቲክ/ከመነዳሪ/ ሙሉ ለሙሉ የመሸፈን ልምን ማስቀረት፡፡
2. በተሸከርካሪ ላይ የኤሌክትሪክ ክፍሎች
የሚባሉት የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ. የሞተር ማስነሳት ክፍል
ለ. ባትሪን የመሙላት ክፍል
ሐ. መብራትና ሌሎች ተጨማሪ ክፍሎች
መ. እሳት አቀጣጣይ ክፍል ናቸው፡፡
•የእያንዳንዱን ባትሪ ሴል ክዳን መከደኑንና የማስተንፈሻ
ቀዳዳዎች በቆሻሻ ያለመደፈናቸውን ማየትና ማጽዳት
•የሞተር ማስነሻ ቁልፍ “ON” የሚለው ላይ አድርጎ ለረጅም
ጊዜ አለመቆየት፡፡
•ኢግኒሽን ኮይል ላይ፣ ዲስትሪቢዩተር ካፕ ላይና እስፓርክ
ፕላግ ላይ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል የሚሸከሙ ሽቦዎች/
ገመዶች/ በትክክል መሰካታቸውንና እሳት ወደ ውጭ
የማይሰርቁ መሆናቸውን በማየት ማረጋገጥ
•ዲስትሪቢዩተር በትክክል መገጠሙንና አለመሰንጠቁን
በማየት ማረጋገጥ
•በስፓርክ ፕላግ ማሰሪያ ላይ ዘይት ያልፈሰሰ መሆኑን ማየትና
ማረጋገጥ ነው፡፡
ሀ. ለሞተር ማስነሻ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
•ሞተርን ወዲያው ወዲያው ለማስነሳት አለመሞከር
•ሞተር አልነሳ ብሎ ሲያስቸግር ከ10 ሰከንድ ቆይታ በኋላ
ለማስነሳት መሞከር
•ሞተር ለማስነሳት የሞተር ቁልፉን “start”የሚለው ቦታ ላይ
ይዘህ ከ5 ሰከንድ በላይ አለመቆየት
•ሞተርን በራሱ ቁልፍ ማስነሳት
•ሞተር ከተነሳ በኋላ ሞተር ማስነሻ ቁልፉን ይዞ አለመቆየት
•ሞተርን ለማስነሳት ቁልፍ ከፍቶ ለረጅም ጊዜ አለመቆየት
ናቸው፡፡
ለ. ለባትሪ መሙያ ክፍሎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
•ጀነኔተር የኤሌክትሪክ ሃይል በትክክል ማመንጨቱንና
ያለማመንጨቱን ዳሽ ቦርድ ላይ ምልክቱን በማየት መከታተል
•የጀነሬተር ቺንጋ ከመጠን በላይ አለመጥበቁንና ያለመላላቱን
ሞተር ባልተነሳበት ሁኔታ በአውራ ጣት ጫን ጫን በማድረግ
መፈተሸ
•ባትሪ ቶሎቶሎ የሚጨርስ ከሆነ የሬጉሌተር መበላሸት ሊሆን
ስለሚችል በባለሙያ ማስፈጸሸ
•ባትሪ ከሚገባው በላይ እየተሞላ መሆን ያለሞኑን ማየት
ባትሪ ማፍላት ያለማፍላቱን ማረጋገጥ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
ሐ.ለመብራቶችና ለሌሎች የኤሌክትሪክ ክፍሎች መደረግ
ያለበት ጥንቃቄ
•የአሽከርካሪው እንቅስቃሴ ከመጀመሩ በፊት ሁል ጊዜ ሁሉም
መብራቶች በትክክል መስራታቸውን ማየት፣
•ሞተሩ በማይሰራበት ሁኔታ መብራት አብርቶ፣ ሬድዮ /ቴፕ/
ከፍቶ ለረጅም ጊዜ መቆየት ለባትሪ መድከም ምክንያት
ስለሚሆን መጠንቀቅ
•የኤሌክትሪክ ሃይል የሚስተላልፉ ፊውዞች ትክክኛ
መጠናቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ማየት
•አምፖሎች ሲቃጠሉ ለባለሙያ ማሳየት የመሳሰሉት ናቸው፡፡
በፓናል ቦርድ ላይ ለሚገኙ ጠቋሚ መሳሪያዎች መደረግ
ያለበት ጥንቃቄ
•ጠቋሚ መሳሪያዎቹ በትክክል መሰራተቻውን መከታተል
•ጠቋሚ መሳሪያዎቹ ሲበላሹ በወቅቱ ለባለሙያ ማሳየት
ናቸው
የአሸከርካሪ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች የሚባሉት፡-
•የሞተር ማስነሻ ቁልፍ፣
•የነዳጅ መስጫ ፔዳል፣
•ማርሽ፣
•ፍሬን
•ፍሪሲዮን፣
•መሪ፣
ለአሸከርካሪ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
•የኤሌክትሪክ ገመዶችን በመቀጣጠል ለማስነሳትና ለማጥፋት አለመሞከር፣
•የነዳጅ መስጫ ፔዳል እንዳያዳልጥ ፕላስቲክ ጎምኒ ፔዳል ላይ መጠቀም፣
•የነዳጅ መስጫ ፔዳሉን እስፕሪንግ ዉጥረት ማየትና እስፕሪንግ እንዳይወልቅና
ነዳጅ ሰጥቶ እንዳይቀር መጠንቀቅ፣
•ማርሽ በአግባቡና በቅደም ተከተል መጨመርና መቀነስ፣
•ማርሽ መለወጥ ባስፈለገ ጊዜ የፍሪሲዮን ፔዳል በአግባቡ መጠቀም፣መርገጥ
•የፍሪሲዮን ፔዳልን በተገቢዉ ጊዜና ቦታ ላይ መጠቀም፣
•እግርን በፍሪሲዮን ፔዳል ላይ አድርጎ ያለማሽከርከር፣
•የመሪ ክፍሎችን በንጽህና መያዝ፣መገናኛ ቦታዎችን ላይ በቂ ግሪስ ማድረግ፣
•በማንዋል የሚሰራ መሪ ላይ የመሪ ጥርስ ሳጥን ዉስጥ በተወሰነ ጊዜ ዘይት
እየተመለከቱ መጨመር
•የፊት እግር አቀማመጥ ትክክል መሆኑን ማየትና የላሉ ክፍሎች ካሉ ማጣበቅ፣
•የጎማ ንፋስና የጎማ ጥርስ አስተላለቅ ተመሳሳይ ያለመሆን በመሪ ላይ
ተፅእኖ ስለሚኖረዉ ዘወትር ማየትና ጎማን የማዟዟር ልማድ ማዳበር፣
•ለተሸከርካሪዉ ካልተፈቀደለት ጭነት በላይ አለመጫንና ጭነትን
አስተካክሎ መጫን፣
•አደገኛ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር መሪን በድንገት አለማዞር፣
•በዘይት በሚሰሩ መሪ ላይ በቂ ዘይት በዘይት መያዣ ቋት ዉስጥ
መኖሩን ማየት፣
•የዘይት መተላለፊያ ቱቦዎች ዘይት ወደዉጭ የማያፈሱ መሆናቸዉን
መመልከት፣
•የመሪ ዘይት ፓምፕ ቺንጋ ያለመበጠሱን፣ያለመጥበቁና ያለመላላቱን
ማየት፣
•በወጣ ገባ መንገድ ላይ በፍጥነት ያለማሽከርከር፣
•የተሸካሚና ፍሬን ክፍሎች መበላሽት በመሪ ላይ ተፅዕኖ
ስለሚኖረዉ በወቅቱ ማስተካከል ናቸዉ፡፡
•ለተሸከርካሪዉ ካልተፈቀደለት ጭነት በላይ አለመጫንና ጭነትን
አስተካክሎ መጫን፣
•አደገኛ ሁኔታ ካላጋጠመ በስተቀር መሪን በድንገት አለማዞር፣
•በዘይት በሚሰሩ መሪ ላይ በቂ ዘይት በዘይት መያዣ ቋት ዉስጥ
መኖሩን ማየት፣
•የዘይት መተላለፊያ ቱቦዎች ዜት ወደዉጭ የማያፈሱ መሆናቸዉን
መመልከት፣
•የመሪ ዘይት ፓምፕ ቺንጋ ያለመበጠሱን፣ያለመጥበቁና ያለመላላቱን
ማየት፣
•በወጣ ገባ መንገድ ላይ በፍጥነት ያለማሽከርከር፣
•የጎማ ንፋስና የጎማ ጥርስ አስተላለቅ ተመሳሳይ ያለመሆን በመሪ ላይ
ተፅእኖ ስለሚኖረዉ ዘወትር ማየትና ጎማን የማዟዟር ልማድ ማዳበር፣
•የተሸካሚና ፍሬን ክፍሎች መበላሽት በመሪ ላይ ተፅዕኖ
ስለሚኖረዉ በወቅቱ ማስተካከል ናቸዉ
የፍሬን ፔዳል ተረግጦ ለተሸከርካሪ በተፈለገዉ ቦታ ላይ
የማይቆምባቸዉ ምክንያቶች
•የፍሬን ዘይት በቋት ዉስጥ ያለመኖር፣
•የፍሬን ዘይት የሚያፈስ ቦታ መኖር
•በፍሬን ዘይት መተላለፊያ መስመር ዉስጥ አየር ሲገባ፣
•በማስተር ሲሊንደርና በጎማ ሲሊንደር ዉስጥ ያሉ
ሲሎች/ጎሚኒዎች/መላሸቅ ፣
•የፍሬን ዘይት መስመር መፍንዳት፣
•የፍሬን ሸራ መበላት/ማለቅ/፣
•በፍሬን ሸራ ላይ ዘይት ሲፈስ፣
•የፍሬን ድሪም/ዲስክ /መበላት የመሳሰሉት ናቸዉ
በኢንጂን ብሬክ አጠቃቀም ላይ መደረግ ያለበት
ጥንቃቄ
•ኤንጅን ብሬክ ይዞ አለመቆት
•ኤንጅን ብሬክ በቁልቁለታማና ቀጥ ያለ መንገድ ላይ
በፍጥነት ስታሽከረክር ለአጭር ጊዜ ብቻ መጠቀም፣
•ኤንጅን ብሬክ የሞተር ፍጥነት አመልካች ጌጅ ቀይ
ላይ እያለ ያለመጠቀም፣
•ኤንጅን ብሬክ ማርሽ ዜሮ ላይ እያለ ያለመጠቀም፣
•ኤንጅን ብሬክ እየተጠቀምክ ነዳጅ አለመስጠት
ናቸዉ፤፤
3. ለሀይል አስተላላፊ ክፍሎች መደረግ ለበት ጥንቃቄ
•ማርሽ ማስገባት ወይም መለወጥ ባስፈለገ ጊዜ የፍሪሲዮን ፔዳል በደንብ
መርገጥ፣
•ፍሪሲዮን መንጭቆ ሞተርን በግፊ ያለማስነሳት፣
•ማርሽ ከገባ በኋላ ፍሪሲዮን በመመንጨቅ እግርን ከፍሪሲዮን ፔዳል ላ
አለማንሳት፣
•ፍሪሲዮን ፔዳል ላይ እግርን አስደግፎ አለማሽከርከር
•ፍሪሲዮን ፔዳል ሲረገጥ በጣም ያለመጥበቁን ወይም በጣም ለመላላቱን
በየጊዜዉ መፈተሸ
•የላሉ ፍሪሲዮን ክፍሎችን ማጥበቅ፣
•ለካምቢዮና ለዴፈረንሻል Yራሳቸዉ የሆነ
•ዩኒቨርሳል ጆይንቶች በቂ ግሬስ እንዲኖራቸዉ ማድረግና ያለመላላታቸዉ
በየጊዜዉ ማየት /መፈተሸ/
•ከመጠን በላይ ጭነት ያለመጫን፣
•በወጣገባ ገባ መንገዶች ላ በፍጥነት ያለማሽከርከር፣
•የዴፈረንሻል ጥርሶች እንዳይጎዱ ጠመዝማዛ መንገዶች ላ ፍጥነትን ቀንሶ
ማሽከርክር የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ለተሸካሚ ክፍሎች መደረግ ያለበት
ጥንቃቄ
1. ተሽከርካሪ ሊጭን ከሚችለዉ ጭነት በላይ
ያለመጫን፣
2. የሚቻን ጭነትን ማደላደል ማለትም ሁሉም
ክፍሎች እኩል ጭነት እንዲያገኙ ማድረግ
3.በወጣ ገባና በኮረኮንች መንገዶች ላይ በፍጥነት
አለማሽከርከር፣
4. የተሸካሚ ክፍሎች ማፅዳትና በቂ መለስለሻ
እንዲያገኙ ማድረግ፣
ለተሽከርካሪ አካል መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
•ጉዞ ከመጀመሩ በፊት በሮች በትክክል የተዘጉ መሆናቸዉን ማረጋገጥ
•ተሸከርካሪዉ ቆሞ ሲያድር አየር ወደ ተሸከርካሪዉ አካል መግባት እነዲችል
መስታወቶችን በትንሹ ክፍት ማድረግ
•ተሸከርካሪውን በተወሰነ ጊዜ ማፅዳት የመሳሰለት ናቸዉ፡፡

ለጎማ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ


•የጎማ ንፋስ ከመጠን በታች መሆን የጎማን ዳርና ዳር ቶሎ እንዲያልቅ
ከማድረጉም ባሻገር ንፋስ ባነሰበት በኩል መሪ እንዲጎትት ያደርጋል፡፡
•የጎማ ንፋስ መጠን ሲበዛ የጎማ መካከለኛዉ ቦታ ቶሎ እንዲያልቅ ያደርጋል፡፡
•የጎማ ንፋስ አሞላል ማንወሉ በሚያዘዉ መሰረት ከመሆኑም በተጨማሪ ቦታ
የአየር ፀባይ ጋር መሙላት ያስፈልጋል፡፡
•ንፋስ ባነሰዉ/በጎደለበት/ጎማ ማሽከርከር ባለሽቦ ጎማዎችን እንዲጣመሙ
ያደርጋል
•ጎማ በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲያልቅና እድሜዉ እንዲጨምር ጎማን የማዟዟር
ልምድ ማዳበር ይገባል፡፡
ተፈፀመ

You might also like