You are on page 1of 2

ክ/ከተማ ------------------------------------ ቦሌ ከ/ክተማ

ወረዳ ------------------------------------ 17

ቀበሌ ------------------------------------- 24

ጥናቱ የሚያካትታቸው ቤቶች ---------የፍሳሽ መስመራቸው ከቤት ቁጥር 1282 እሰከ ቤት ቁጥር 1411

የሚደርስ (ባጠቃላይ 68 መኖሪያ ቤቶች)

መግቢያ
ከላይ የተጠቀሱት ከቤት ቁጥር 1282 ጀምሮ እስከ ቤት ቁጥር 1411 ያሉ የኮርፖሬሽናችን ይዞታ የሆኑ ቤቶች የፍሳሽ
መስመር ቀድሞ ተገናኝቶባት የነበረው የፍሳሽ ማጠራቀሚያ ሴፕቲክ ታነከር በማለያየት ከቤቶቹ አቅራቢያ በሆነው
በኮርፖሬሽኑ ይዞታ ስር በሚገኘው ባዶ መሬት ላይ ሌላ አዲስ ሴፕቲክ ታንከር መገንባት አስፈላጊ ሆኗል፡፡

ነባራዊ ሁኔታ
ከላይ የተገለጹት መኖሪያ ቤቶች የፍሳሽ መስመር አሁን ባለው እና ቤቶቹ ካሉበት የመሬት አቀማመትጥ የተነሳ
ያጋጠማቸው ችግር የሌለ ቢሆንም ከነሱ የሚመኘጨው የፍሳሽ ቆሻሻ ከበታች ላሉ ቤቶች ከፍተኛ ጫና የሚፈጥር
ከመሆኑም በላይ ሁለት ሴፕቲክ ታንከሮች ከአገልግሎት ብዛት በመፍረሳቸው እና አገልግሎት መስጠት ከማይችሉበት
ደረጃ በመድረሳቸው ምክንያት ለነዚህ ለተጠቀሱት 68 ለሚደርሱ ቤቶች ሌላ አዲስ የሚያመነጩትን ፍሳሽ ቆሻሻ
ሊይዝ የሚችል እና በተወሰነ ወቅት ሲሞላ በጋራ ፍሳሹን የሚያስነሱት ሴፕቲክ ታንከር መገንባት አስፈላጊ ሆኗል፡፡
በዚህ ስራ ላይ የተካተቱ መኖሪያ ቤቶች ዝረዝር (የቤት ቁጥር)
1. ከቤት ቁጥር 1282 እስከ ቤት ቁጥር 1291 የ 10 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ
2. ከቤት ቁጥር 1304 እስከ ቤት ቁጥር 1313 የ 10 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ
3. ከቤት ቁጥር 1332 እስከ ቤት ቁጥር 1399 የ 8 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ
4. ከቤት ቁጥር 1340 እስከ ቤት ቁጥር 1347 የ 8 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ
5. ከቤት ቁጥር 1364 እስከ ቤት ቁጥር 1371 የ 8 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ
6. ከቤት ቁጥር 1372 እስከ ቤት ቁጥር 1379 የ 8 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ
7. ከቤት ቁጥር 1396 እስከ ቤት ቁጥር 1403 የ 8 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ
8. ከቤት ቁጥር 1404 እስከ ቤት ቁጥር 1411 የ 8 ቤቶች ፍሳሽ ቆሻሻ

በአጠቃላይ ከ 68 ቤቶች ለሚመነጭ ከፍተኛ የፍሳሽ ቆሻሻ አዲስ ሴፕቲክ ታንከሮች የሚገነባ ይሆናል፡፡

የቀረቡ ምፍትሄዎች
መፍትሄዎቹን በሁለት ከፍለን ማለትም የአጭር ግዜና እና ዘላቂ መፍትሄ ብለን ከፋፍለን እናያለን፡፡
1. የአጭር ግዜ መፍትሄ ከላይ እንደተገለጸው በዚህ ደብዳቤ ላይ የተጠቀሱት ቤቶች ካሉበት መሬት አቀማመት
የተነሳ በዚህ ወቅት የገጠማቸው ግልጽ ችግር ባይኖርም ከቤቶቹ የሚመነጭ የፍሳሽ ቆሻሻ ከመንገድ በታች ባሉ
ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ፍጥሯል በዚህም መሰረት እንደጊዚያዊ መፍትሄ በአካባቢው ባለው የኮርፖሬሽኑ ዞታ
በሆነው መሬት ላይ የቤቶቹን ብዛት ያገናዘበ ሴፕቲክ ታንከር መገንባት፡፡
2. ዘላቂ መፍትሄ፡- ከጊዜያዊው መፍትሄ ጎን ለጎን ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር
የአካባቢውን ቤቶች የፍሳሽ መስመር ለአካባቢው በቅርበት ከሚገኝ የከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር
ማገናኘት፡፡ የዚህንም ጉዳይ ተፈጻሚነት ባለው አሰራር መሰረት የቅ/ጽቤታችን በሃላፊነት ክትትል ማድረግ
ይኖርበታል፡፡

ማጠቃለያ፡-
 ከጽቤታችን የሚጠበቅ
 ከላይ ለተገለጹት ስራዎች የሚያስፈልገውን ዲዛይን ፣ሰራ ዝርዝር እና የበጀት ግምት እና የስራ እቅድ
አዘጋጅቶ ማቅረብ
1
 በመጸዳጃ ፍሳሽ መስመር ስራ ላይ ከላይ በዝርዝር የተገለጹት የኮርፖሬሽናችን ቤት ነዋሪዎች ተሳታፊ
እንዲሆኑ ማስተባበር፡፡
 ከወረዳ 05 ጋር በመሆን የመንገድ ፍሳሽ ማስወገጃ መስመር እና ሴፕቲክ ታነክ ግንባታ ስራ ላይ
በወጪ መጋራት አሰራር ላይ የወረዳ 05 አስተዳደር እና የአካባቢው ነዋሪ ተሳተፊ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
 በዘላቂነት የአካባቢው አጠቃላይ የፍሳሽ ችግር ሊፈታ የሚችለው የየቤቶቹን ፍሳሽ መስመር
ከከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ጋር እንዲገናኝ ክፍተኛ ትኩረት በመስጠት መስራት፡፡
 ከወረዳ 05 አስተዳደር የሚጠበቀው
 ሴፕቲክ ታንከሮቹ ሊሰሩበት የታቀደው የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቦታ በአሁኑ ሰአት ለፕላስቲክ
ቆሻሻ ማከማቻነት የሚጠቀሙትን ወገኖች በወረዳ 05 አስተዳደር በኩል እንዲነሱ፡፡
 የቅ/ ጽቤታችንን ጥረት በበጎ በመረዳት በራስ አቅምም ሆነ ነዋሪው ህብረተሰብን በማስተባበር
የመፍትሄው አካል መሆን፡፡
 በመጸዳጃ ፍሳሽ መስመር ስራ ላይ የሚመለከታቸው ካላይ የተጠቀሱት ነዋሪዎች በወጪ መጋራቱ
አነዲሳተፉ ማስተባበር
 የመንገድ ፍሳሽ ማስወገጃ መስመር (ቱቦ) ስራን በተመለከተ የወረዳ 05 አስተዳደር እና የአካባቢው
ነዋሪ የሚስፈልገውን በጀት በተመለከተ ተገቢውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ማስተባበር፡፡
 የተከራይ ደንበኞቻችን ድርሻ ፡-
 አሁን በቅ/ጽቤታችን የታቀደው በዋናነት ደንበኞቻችንን በተገቢው ለማገልገል እና አካባቢያቸውንም
የበለጠ ለመኖሪያነት ምቹ ለማድረግ ከመሆኑ እንጻር ከማንም በላይ በሃላፊነት በመነሳት ሌሎች
የአካባቢዎቻቸው መሰል ተከራየች እንደሚያደርጉት ለስራው የሚያስፈልገውን በጀት በማዋጣት
መደገፍ ይኖርባቸውል፡፡
 ተያያዥ መረጃዎች
-በዝርዝረ የተገለጹት ቤቶች ጂ.አይ.ኤስ ማፕ እና ከማንሆል እስከ ነባሩ ሴፕቲክ ታንክ ያለው ማፕ
-ለስራው የሚያስፈልግ የስራ ዝርዝር እና ዲዛይን
የስራ ዝርዝሩየሚጠቃልላቸው ስራዎች፡-

 የሳይት ክሊሪንግ ስራዎች


 ሶስት ባለ 10x5 ኤፕቲክ ታንከሮች መገንባት
 የማንሆል ስራዎች
 የባለ 40 c.m ቱቦ ቀበራ

You might also like