You are on page 1of 2

ክ/ከተማ--------------ቦሌ ከ/ክተማ

ወረዳ------------------17
ቀበሌ------------------25
የቤት ቁጥር-------- ከ 3451 --- 3454
(ልዩ ስሙ ገርጂ ምክር ቤት)

ነባራዊ ችግር---- ከሽንት ቤት ጋር የተገናኘ ከፍተኛ ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡በአካባቢው በተሰሩ አዳዲስ ግንባታዎች
ምክንያት የፍሳሽ መስመራቸው በመቋረጡ የተፈጠረ ነው፡፡

መግቢያ ፦ ከላይ የተገለጸውን ችግር በቦታው ከባለሞያዎች ጋር ሆነን ተመልክተናል ፡፡ በዚሁ መሰረት መፍትሄዎች
እንደሚከተለው አዘጋጅተን አቅርበናል፡፡ የአራቱን ቤቶች ችግር ለመፍታት ሁለት አማራጭ የተቀመጠ ሲሆን ይህ
አማራጭ በአካባቢው ለሚገኙ ለምናስተዳድራቸው ቤቶች ሁሉ እንደመፍትሄ ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡

የቀረቡ ምፍትሄዎች፥- መፍትሄዎቹን በሁለት ከፍለን ማለትም የአጭር ግዜና እና ዘላቂ መፍትሄ ብለን ከፋፍለን
እናያለን፡፡
1. የአጭር ግዜ (ጊዜያዊ መፍትሄ)፡- ቤቶቹ ካለባቸው አሳሳቢ ችግር አንጻር ነዋሪዎቹን በማስተባበር በፍጥነት
መተግበር ያለበት ስራ ይሆናል፡፡ይህም ከቦታው አቀማመት እና ካለው ሰፋ ያለ ቦታ እንጻር በቤት ቁጥር 3154
ግቢ ውስጥ ሴፕቲክ ታንክ በማዘጋጀት ቀሪውን ሶስት ቤቶች ማለትም 3451, 3452, 3453 በባለ 300 ሴ.ሜ
ፒቪሲ ቱቦ ፍሳሻቸው ከሲፕቲክ ታንከሩ ጋር እንዲገናኝ በማድረግ መስራት ይቻላል፡፡ አጠቃቀሙን እና ፍሳሽ
መኪና ተጠቅሞ ቆሻሻውን የማስወገድ ስራውን ነዋሪዎች በመተባብረ በራሳቸው ማሰራት እንደሚኖርባቸው
የማስገንዘብ እና በሰነድ በተደገፈ መልኩ አፈራርሞ መረጃ መያዝ አስፈላጊ የሆናል፡፡
2. ዘላቂ መፍትሄ፡- ከጊዜያዊው መፍትሄ ጎን ለጎን ከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በመነጋገር
የአካባቢውን ቤቶች የፍሳሽ መስመር ለአካባቢው በቅርበት የሚገኝ የከተማው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ካለ
እንዲገናኝ የማድረግ ስራ መስራት ይቻላል፡፡
ሆኖም ባለን መረጃ መሰረት በአካባቢው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ያሌለ በመሆኑ የመጀመሪያው አማራጭን
ትኩርት ሰቶ በመያዝ ወደስራ እንዲገባ እጠይቃለሁ፡፡

ማጠቃለያ፡- በዚህ በተጠቀሰውውም ሆነ በተመሳሳይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ጉዳዩ የቀረበበት ጊዜ ስረዎችን


በተገቢው ፍጥነት እና ጥራት ለመስራት ወሳኝ ከመሆኑ አንጻር በተለ ይ ተከራዮችን በወጪ መጋራቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ
እንዲያደርጉ በማነሳሳት ነገ ዛሬ ሳይባል ወደስራ መግባት አስፈላጊ ይሆናል፡፡

 ከጽቤታችን የሚጠበቅ
 ነዋሪዎች በቅ/ጽ/ቤታችን ችግሩን ለመፍታት የተጀመረውን እንቅስቃሴ እንዲደግፉ የማሳወቅ ስራ
አስቀድመን መጀመር፡፡
 በአንደኛ አማራጭ የተቀመጠውን መፍትሄ ወደስራ ለማስገባት ለስራው የሚያስፈልገውን የስራ
ግምት በክፍላችን ቶሎ እንዲዘጋጅ ማድረግ፡፡
 በተዘጋጀው ግምት መሰረት የቅ/ጽቤታችንን ድርሻ በመውሰድ ነዋሪዎቹም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ
እንዲወጡ የማስገንዘብ ስራ በስፋት መስራት፡፡
 ከግንባታ ቦሃላ የሴፕቲክ ታንክ አጠቃቀምን በተመለከተ ነዋሪዎች እኩል ግዴታ እንዳለባቸው
እንዲያውቁ እና ይህም በሰነድ እንዲሰፍር ማድረግ፡፡
 የተከራይ ደንበኞቻችን ድርሻ ፡-
 ቅ/3 ጽ/ቤት ያለውን ችግር ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ በተለይ ከነሱ የሚጠበቀውን
የወጪ መጋራት ሂደት መደገፍ፡፡
 ስራው ከተጠናቀቀ ቦሃላ የሴፕቲክ ታንከሩን አጠቃቀም እና አያያዝ በተመለከተ እኩል ግዴታ
እንዳለባቸው መረዳት ህንንም በሰነድ እንዲሰፍር ማድረግ፡፡

You might also like