You are on page 1of 5

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ

ማኑዋል
/ ቤት የቅሬታ አፈታት ስርአት ዝርጋታ የተዘጋጀ

የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ

1.ዘነበ ካሳ

2.ዘቢባ አሊ

3.ወይንሸት

ነሃሴ 2012

መግቢያ

 ቅሬታ ማለት ጥቅም ባለዉ ወይም ጥቅም በሌለዉ ነገሮች ላይ ሁለት ሰዉ እና ከዚህ በላይ የሆኑ ሰዎች

ግጭት በቂ በቀል እና አለመግባባት መፍጠር ማለት ነዉ፡፡የቅሬታ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ቢኖሩ ሰዎች

ለጋራ ጥቅም ሲባል የሚፈጠሩ ክስተት ሊሆን ይችላል፡፡

 ቅሬታ በተፈጥሮ ሊከሰት የሚችል ጉዳይ ነዉ /conflict is nature/ ስለሆነም ሰዉ ሰራሽ /Artifcal conflict /

በተለይዩ ግዜ በአበዛኛዉ እንደሚከሰት እዉን ነዉ፡፡

ራዕይ /vision/
 በወረዳ 13 አስተዳር አንድም የመንግስት ሰራተኛ ቅሬታ ፈጣሪ ሳይሆን ቅሬታ ፈች አካል ሆኖ እንዲገኝ

ማድረግ ነዉ፡፡

ተልዕኮ /Mission/

 በወረዳ 13 አስተዳር የተፈጠሩ ቅሬታዎች በአግባቡ በሰአትና በትክክለኛ ሂደት መፍታት ነዉ፡፡

ዕሴቶች /values/

 በወረዳዉ የሚፈጠሩ ቅሬታዎች በአብላጫ ቁጥር መቀነሱ

 በታማኝነት፣በፍትሃዊነት በትክክለኛ ሂደት ቅሬታዉን መፍታት

 ቅሬታ በፈጠሩ ሰራኞች ሁሉም አሸናፊ መሆን /win-win/ በሚችሉ መንገድ መፍታ፡፡

 በሴክተሩ የሚፈጠሩ ቅሬታዎች በየደረጃዉ እንዲፈቱ መጣር፡፡

1. የቅሬታ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ጉዳዬች

ለቅሬታ መነሻ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ቢኖሩ በየሴክተር ጽ/ቤቶች የሚከተሉት ጉዳዮች ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ

ይገመታል፡፡

ሀ/ የሰራኞች ጥቅማ ጥቅም በትክክል ሳይሰጣቸዉ ከቀረ

ለ/ ለሰራተኞች እኩል ኃላፊነት ሳይሰጣቸዉ ከቀረ

ሐ/ የአንድ ሴክተር ጽ/ቤት ሰራተኞችን በእኩል ዓይን /ሂደት/ሳይታዩ ከቀረ

መ/ ሰራተኞችን የማበላለጥ ሁኔታዎች በኃላፊ በኩል ሲከሰት

ሠ/ በከፊልም ሆነ በአብላጫ የሰራተኞችን ሁኔታ በትክክል ሳናይ ከቀረን

ረ/ ሰራተኞች የሚሰጧቸዉን ተልዕኮ በአግባቡ ሳይከናወኑ ከቀረ

ሰ/ የሰራተኞች የክህሎት ችግር ሳይቀረፍ ሲቀር

ሸ/ የአንዳንድ ሴክተር ጽ/ቤቶች ሰራተኞች በስራቸዉ መጠን ሳይመዘኑ ሲቀሩ ወ.ዘ.ተ


የተነሱ ቅሬታዎች ለመቀነስ መወሰድ ያለባቸዉ ጉዳዮች

 እንደሚታወቀዉ እሬታ ለምን ይነሳል ብሎ ማሰብ ሳይሆን የተከሰቱትን ቅሬታዎች በሰአቱ በቦታዉ በትክክለኛ

አካል /3R/መፍታት መቻል አለበት

 ከላይ በፁሁፍ ኩሀ-ሸ ያሉት ጉዳዮች በጥንቃቄና የመፍትሄ ሁኔታ ታክሎበት ከተሰራ ሊነሱ የሚችሉትን

ቅሬታዎች በአብዛኛዉ መቀነስ ይቻላ ተብሎ ይገመታል

በሴክተር ጽ/ቤቶች የሚነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተ

በወረዳዉ አስተዳደር ሴክተር ጽ/ቤቶች የተለያዩ ቅሬታዎች ሊከሰቱ ይችላሉ ተብሎ ይገመታል ስለሆነም የተከሰቱት

ቅሬታዎች በህጉና በደን መሰረት እንዲፈቱ በሴክተር ጽ/ቤቶቹ የቅሬታ ኮሚቴ እንደተቋቋመ ይታወቃል ፡፡ በዚህም

መሰረት ቅሬታዎቹ ሊፈቱ ይገባል፡፡

በሴክተር ጽ/ቤቶቹ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች ኃላፊነት

 በወረዳዉ ሴክተር ጽ/ቤት ቅሬታዎች ሊፈቱ ይችላሉ ተብሎ ሃላፊነት የተሰጣቸዉ ኮሚቴዎች የሚከተሉትን

ስራዎች ማከናወን ይተበቅባቸዋል፡፡

ሀ/ ቅሬታን በሚመለከት ሊሰሩ የሚችሉ ስራዎችን ማቀድና ማዘጋጀት

ለ/ የተዘጋጀዉን እቅድና የድርጊት መርሃ ግቡን በማካተት በጊዜ መፍታትና መገምገም ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሐ/ በኮሚቴዉ የተሰሩ ስራዎች በየወሩ መጨረሻ ለአቅም ግንባታ ጽ/ቤት ሪፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

መ/ በኮሚቴዉ አቅም እና ሃላፊነት በላይ ለሆኑ ጉዳዮች በሴክተር ጽ/ቤት ኃላፊ በወቅቱ ማቅረብ

ይጠበቅባቸዋል፡፡

ረ/ በጽ/ቤቱ ዉስጥ ለተከሰቱት ቅሬታዎች ያለምንም መዘገየት በፍጥነት መቅረፍ ይጠበቅባቸዋል


ሰ/ ሁሉም የቅሬታ አፈታት ስርአት በመጠቀም ሊፈቱት ይገባቸዋል፡፡/doe process of law /i.e

ADR.Arbtration mediation litigation necessary

የሴክተር ጽ/ቤት ኃላፊዎች

 መንግስት በሰጣቸዉ ኃላፊነት በትክክል በፍጥነት በታማኝነት በቅንነት የሴክተሩን ሁኔታዎች በበላይነት

በመከታተል ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል፡፡

 ከሴክተር ጽ/ቤት ኃላፊ በላይ የሆኑ ጉዳዮች ለዲስፒሊን ኮሚቴ ሊቀርብ ይገባል፡፡

የሰራተኞች መብትና ግዴታዎች

ቅሬታ ያጋጠማቸዉ ሰራተኛ ጉዳዩን በሴክተር ጽ/ቤቶች ለተቋቋመዉ ኮሚቴ ሳያቀርብ ለሌላ አካል ማቅረብ የወረዳዉን

የቅሬታ አፈታት ስርአቱን መቃወም መሆኑን አዉቆ በየደረጃዉ ሂደቱን በመከታተል የእርምት ሂደቶችን መከታተል

ይጠበቅበታል፡፡

የወረዳዉ አስተዳር የዲስፒሊን ኮሚቴ

 በወረዳዉ የተቋቋሙ የዲስፖሊን ኮሚቴ እየሰራ ባለዉ ሁኔታ መቀጠል ይጠበቅበታል

 ለኮሚቴዉ የተሰጠዉን ኃላፊነት እንደ ከዚህ በፊት አጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅበታል፡፡

 ኮሚቴዉ የቀረበዉን ቅሬታ በየደረጃዉ ሂደቱን ጠብቀዉ ኮሚቴዉ ጋ መድረሱን መከታል ይኖርባቸዋል፡፡

ማጠቃለያ ፡ -

በአንድ ሐገር ዉስጥ ቅሬታን ከነ አካቴዉ ማጥፋት የሚቻል ተግባር ሳይሆን በሀገሪቷ ዉስጥ የሚቀርብ ቅሬታዎችን ግን

መቀነስ እንደሚቻል በመገንዘብ በየደረጃዉ ያሉ የቅሬታ ኮሚቴዎች ስራቸዉን መወጣት አስፈላጊ ነዉ፡፡

ሰዉ ካራሱ ጋር ሰዉ ከተፈጥሮ ጋር እና ሰዉ ከሌላ ሰዉ ጋ እንዲጋጭ የተፈጥሮ ክስተት ቢሆንም በየቀኑ ከራሱም

ከተፈጥሮም እና ከሌላም ሰዉ ጋ ግጭት መፍጠር የዘለለ ትክክለኛ አቋም አለመሆኑን በመረዳት በራሳችን ተነሳሽነት

ቅሬታን ሊቀነስ ይገባል፡፡

You might also like